Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የአዲግራት ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ሃላፊ ሆኖ ሲሰራ የነበረው አፅብሃ ወልደገብርኤል ተገደለ

$
0
0

Zehabesha News
በትግራይ ወረዳዎች ተመድበው የሚሰሩ አስተዳደሮች ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች እየተገደሉ እንደሚገኙ ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ያገኘነው መረጃ አመለከተ ሲል የትህዴን ድምጽ ዘግቧል:: በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የአዲግራት ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ሃላፊ ሆኖ ሲሰራ የነበረው አፅብሃ ወልደገብርኤል የተባለው ለሆዱ ያደረ የህወሓት ኢህአዴግ ካድሬ ነሃሴ 12 /2007 ዓ/ም ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ቤቱ ውስጥ ተገድሎ እንደተገኘ የትህዴን ድምጽ ዘገበ::

ፖሊስ ጉዳዩን ለማጣራት በሚል የተወሰነ እንቅስቃሴ ቢያደርግም ነዋሪው ህዝብ ሊተባበራቸው ባለመቻሉ ምክንያት በግለሰቡ አሟሟት ምክንያት ተሳስሮ ሰዎች ሊጠረጥሩት ሞክረው ህዝቡ ሊቀበላቸው ባለመቻሉ ምክንያት ገዳዩ ሳይታወቅ ዝምታን እንደመረጡ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።

በተመሳሳይ- በሳዕስዕ ፃዕዳ እምባ ሳዕስዕ ቀበሌ የሚኖር ህዝብ ደስታ ጎቢጥ የተባለ የቀድሞ ታጋይ ባልታወቁ ሰዎች ነሃሴ 13 2007ዓ/ም በድንጋይና በዱላ እንደተገደለ ለማወቅ ተችሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ- ተገድለዋል እየተባሉ ያሉት ሰዎች ከአካባቢው ካድሬዎች ጋር ስምምነት ያልነበራቸውና ጥቅም ያጣላቸው የኢህአዴግ አባላት ናቸው የሚል ጥርጣሬ በህዝቡ ዘንድ እንዳለ ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ አክሎ ገልጿል።


አቡነ ፊሊጶስ አረፉ

$
0
0

abune

(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ሃገር ቤት ባለው ሲኖዶስ ስር የኢሉባቦር እና ጋምቤላ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበርይት ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ማረፋቸው ተሰማ::

የዘ-ሐበሻ የቤተክህነት ምንጮች እንዳስታወቁት አቡነ ፊልጶስ የቀብራቸው ስነስርዓት ነገ ማክሰኞ ሴፕቴምበር 1 ቀን 2015 ዓ.ም ይፈጸማል::

Hiber Radio: ኢትዮጵያ በመጭው አምስት ዓመት ሳተላይት ወደ ህዋ አመጥቃለሁ ማለቷ፣ አቶ በቀለ ገርባ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ ምን እንደሚጠብቃቸው እንደማያውቁ መግለጻቸውና ሌሎችም ዜናዎች

$
0
0

የአቶ መለስ ዜናዊ ዉርስና ቅርስ

$
0
0

meles zenawiከግንቦት 1983 ዓ.ም. አንስቶ ለቀጣይ 21 ዓመታት ኢትዮጵያን የመሩት የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሦስተኛ የሙት ዓመት ታስቧል። የሙት ዓመታቸዉን ለመዘከርም የተለያዩ ዝግጅቶች መከናወናቸዉ ተሰምቷል።

የሀገር ዉስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደሚሉት የቀየሷቸዉ በተለይም የልማት እና የምጣኔ ሃብት መርሆዎችን ስልጣን ላይ የሚገኘዉ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ ተግባራዊ ለማድረግ እየሠራ ነዉ። ባለስልጣናቱም የእሳቸዉን ዉርስ እና ቅርስ ለማስቀጠል ቃል ሲገቡ ይደመጣል። ለመሆኑ አቶ መለስ በምን ይታወሳሉ? ዉርሳቸዉስ? ዝርዝሩን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Source -Deutsche Welle

8‬ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች በኢትዮጵያና ሱዳን አዋሳኝ ድንበር መሬት ላይ ኩላሊታቸውን ለመዝረፍ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተገለፀ

$
0
0

‎ስምንት‬ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች በኢትዮጵያና ሱዳን አዋሳኝ ድንበር መሬት ላይ ኩላሊታቸውን ለመዝረፍ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተገለፀ፡፡
‎የህወሓት‬ አገዛዝ ሙሉ እምነት ያላሳደረባቸውን የራሱን ሹሞች በደህንነቶቹ እያሳፈነ ወዳልታወቀ ቦታ እያጋዛቸው ነው፡፡
‎ሱዳን‬ ከኢትዮጵያ ግዛት ተጫሪ መሬቶችን ለመውሰድ ለህወሓት አገዛዝ ጥያቄ ማቅረቧን ሄራልድ ትርቢውን የተባለ የሱዳን ጋዜጣ ዘገበ፡፡
====================================================

ስምንት ኢትዮጵያዊን ወጣቶች በኢትዮጵያና ሱዳን አዋሳኝ ድንበር መሬት ላይ ኩላሊታቸውን ለመዝረፍ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተገለፀ፡፡
ስምንቱ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ወደ አገራችንና ሱዳን ድንበር መሬት የተንቀሳቀሱት የሰሊጥ አረም የጉልበት ስራ በመስራት የዕለት ጉርሳቸውን ለማሟላት ሲሆን እጅግ በጣም ዘግናኝ በሆነ አገዳደል ሁኔታ ለእንጀራ ሲሉ በግፍ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
ስምንቱ ኢትዮጵያዊያን ከተገደሉ በኋላ ሆድ ሆዳቸው ተቀዶ ኩላሊታቸው ሙልጭ ብሎ መዘረፉን አስከሬኖቹን የተመለከቱ የዓይን እማኞች ለአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገልፀዋል፡፡

Ethiosudan
ስምንቱን የጉልበት ሰራተኛ ኢትዮጵያዊያን በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል ኩላሊታቸውን አውጥተው የወሰዱት የሱዳን ዜጎች መሆናቸውን ምንጮቻችን ጨምረው አስታውቀዋል፡፡
የህወሓት አገዛዝ ሙሉ እምነት ያላሳደረባቸውን የራሱን ሹሞች በደህንነቶቹ እያሳፈነ ወዳልታወቀ ቦታ እያጋዛቸው ነው፡፡
ከትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ውጭ የሆኑ የህወሓት የሲቪልና የፀጥታ ሹሞች በድንገት እየተሰወሩ የሚገኙ ሲሆን አፈናው በመከላከያና በፖሊስ ኃይሎች ውስጥ በተለየና በተጠናከረ እንዲሁም ምስጢራዊነቱን በጠበቀ ሁኔታ መቀጠሉ እየተነገረ ነው፡፡
በመከላከያ ውስጥ በተለያዩ ዕዞች ከትግራይ ብሄር ተወላጆች ውጭ የሆኑ ወታደራዊ አዛዦች በመብራት እየተፈለጉ በመለቀም ታፍነው ወዳልታወቀ ቦታ እየተወሰዱ ነው፡፡
ለአገዛዙ ታማኝ እንዳልሆኑ የሚጠረጠሩ ከፍተኛ እና ዝቅተኛ የፖሊስ ሹሞችም እንዲሁ አፈናው በተመሳሳይ ሁኔታ በርትቶባቸዋል፡፡ ከሰሞኑ የጭልጋ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ በህወሓት ደህንነቶች ታፍኖ መወሰዱ እና አሁን የት እንደሚገኝ አድራሻው ፈፅሞ እንደማይታወቅ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ተናግረዋል፡፡
የህወሓት ዘረኛ ቡድን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እያደረሰው ከሚገኘው ከዚህ ሰዎችን አፍኖ መሰወር ዜና ጋር በተያያዘ አቶ ሙሉቀን ገብሩ የተባለ ወጣትና በባጃጅ ሹፍርና ስራ የሚተዳደር የሸዲ ነዋሪ በቅርቡ በደህንነቶች ታፍኖ ተወስዶ የደረሰበት አልታወቀም፡፡
ሱዳን ከኢትዮጵያ ግዛት ተጫሪ መሬቶችን ለመውሰድ ለህወሓት አገዛዝ ጥያቄ ማቅረቧን ሄራልድ ትርቢውን የተባለ የሱዳን ጋዜጣ ዘገበ፡፡
ሱዳን ያነሳችው የመሬት ይገባኛል ጥያቄ ከስድስት መቶ ሺህ ሄክታር በላይ “የአማራ ክልልን” መሬት ወደ ገዳሪፍና ቡሉ ናይል ግዛቶች አስገብቶ ለማጠቃለል በማለም ነው፡፡
ጥያቄው የቀረበለት ራሱን እንደመንግስት የሚቆጥረው የህወሓት አገዛዝ ጠብመንጃ ካነሱ የነፃነት ኃይሎች እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ለህልውናው ስለሚያሰጋው ከሱዳን መንግስት ጋር ግጭት ውስጥ ላለመግባት የሱዳንን መንግስት ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ለማርካት ውስጥ ለውስጥ በምስጢር እየሰራ መሆኑ ከውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
የህወሓት አገዛዝ ከዚህ ቀደም እጅግ በጣም ሰፋፊና ለምየሆኑ “የአማራ ክልል” መሬቶችን ከምስኪን ገበሬዎች ነጥቆ ለሱዳን መንግስት እጅ መንሻ መስጠቱ አይዘነጋም፡፡

 

ዜናው የተገኘው ከአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ ነው

የህወሓት አገዛዝ ታጣቂዎች ጭምብል ለብሰው በሌሊት የስርዓቱ ደጋፊ ያልሆኑ ኢትዮጵያዊያንን ቤት ሰብረው በመግባት አሰቃቂ ግድያ በመፈፀም ላይ ናቸው

$
0
0

clash

አርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ እንደዘገበው የህወሓት አገዛዝ ታጣቂዎች ማንነታቸው እዳይታወቅ ጭምብል ለብሰው በሌሊት የስርዓቱ ደጋፊ ያልሆኑ ኢትዮጵያዊያንን ቤት ሰብረው በመግባት አሰቃቂ ግድያ በመፈፀም ላይ ናቸው!

በጎንደርና አካባቢው በተለይም ደግሞ በደምቢያ ወረዳ ቆላድባ ከተማ ውስጥ የህወሓት ታጣቂ ኃይሎች ጭምብል አጥልቀው በሌሊት እየተንቀሳቀሱ የሰፈር ቤት ሰርሳሪዎችን በመምሰል የአገዛዙ ደጋፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ቤት ሰብረው በመግባት ሰዎቹን በጩቤና በጥይት በመግደል ንብረታቸውን በመዝረፍ ስራ ላይ በሰፊው ተሰማርተዋል፡፡

ራሱን በመንግስትነት የሚጠራው ህወሓት የማፊያ ቡድን በውድቅት ሌሊት የሚፈፅመው አሰቃቂ ግድያና ዘረፋ በርካታ የስርዓቱ ደጋፊ ያልሆኑ ሰላማዊ ዜጎች ሰለባ የሆኑ ሲሆን የሰ/ጎንደር ደምቢያ ወረዳ ቆላድባ ከተማ ቀበሌ 02 ነዋሪ የሆነው የሰባት ልጆች አባት አቶ አብዬ ታረቀኝ አንደኛው ነው፡፡

ከጥቂት ዓመታት በፊት የህወሓት የአየር ኃይል አዛዥ የነበረው ሜ/ጀነራል ሞላ ኃ/ማሪያም ከነበረበት የኃላፊነት ቦታው ተወግዶ በአሁኑ ጊዜ የት እንዳለ እንደማይታወቅ የመከላከያ ምንጮቻችን ገለፁ፡፡

ገና ከበርሃ ጀምሮ እነመለስ ዜናዊና ስብሃት ነጋን በአጃቢነት እያገለገለ ጥሩ ቅርርብ የነበረውና ከመከላከያ ኤታማጆር ሹሙ ሳሞራ የኑስ ጋር ዶሮና ጥሬ ሆኖ የቆየው ሞላ ኃ/ማሪያም የመለስን ሞት ተከትሎ ከአየር ኃይል አዛዥነቱ የተወገደ ሲሆን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የብላቴ ማሰልጠኛ ማዕከል አዛዥ ቀጥሎም የጦላይ የበታች ሹም ማሰልጠኛ አዛዥ ሆኖ የቆየ ሲሆን አሁን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ደግሞ በአጠቃላይ ከመከላከያ ተወግዷል፡፡ በምን ሁኔታ ላይ እደሚገኝም በውል እደማይታወቅ የመከላከያ ምንጮቻችን ጨምረው አስታውቀዋል፡፡

ለስዋዚላንዱ ንጉሥ ምስዋቲ 3ኛ የዳንስ ትርኢት ለማሳየትና ለሚስትነት ለመመረጥ ይጓዙ የነበሩ 38 ልጃገረዶች በመኪና አደጋ ሕይወታቸው አለፈ

$
0
0

swis 2 swis et swis

ጴጥሮስ አሸናፊ እንደዘገበው:-

አደጋው የደረሰው 50 ደናግላንን ጭኖ ሎዚታ ወደሚገኘው የንጉሥ ምስዋቲ ቤተመንግሥት በማምራት ላይ የነበረው አውቶቡስ ማትሳፋ አውራ ጎዳና ላይ በሚገኝ ድልድይ ከኋላው ይከተለው የነበረ ሌላ ተሽከርካሪ ባደረሰበት ከፍተኛ ግጭት ምክንያት ነው።

የሪድ ፌስቲቫል (Reed Festival) በየአመቱ የሚከናወን ታላቅ የባሕላዊ ዳንስ ትእይንት ሲሆን ንጉሥ ምስዋቲም አንዲት ልጃገረድ ለሚስትነት የሚመርጡበትም ነው።
እዚህ ላይ ግርማዊነታቸው ንጉሥ ምስዋቲ 3ኛ በየአመቱ አንዲት ልጃገረድ በይፋ እንደሚያገቡ ልብ ይሏል።

የሪድ ፌስቲቫል ከአመት ወደ አመት ከፍተኛ የቱሪስት መስህብ እየሆነ የመጣ ሲሆን ቁጥራቸው ከ80,000 በላይ የሆኑ ወጣት ሴቶች ባህላዊ የዳንስ ትእይንት ለንጉሥ ምስዋቲ የሚያቀርቡትም ነው።

በሰላሳ ስምንቱ ሴት ደናግላን ላይ በደረሰው አሳዛኝና ድንገተኛ ሞት ምክንያት ዛሬ ሰኞ ኦገስት 31 ቀን 2015 ዓ/ም መጀመር ያለበት ፌስቲቫል እንዲሰረዝ ግፊት እየተደረገ ቢሆንም እንዳንዳንድ ምንጮች መረጃ ደግሞ ከፍተኛ ወጪ የወጣበት ፣ ብዙ ማስታወቂያ የተነገረለት ፣ በርካታ ቱሪስቶች ወደ ስዋዚላንድ የተመሙበት በተጨማሪም ወጣት ደናግላን ሴቶች የንጉሥ ሚስት ለመሆን ራሳቸውን ለዉድድር የሚያቀርቡበት ፌስቲቫል ሊካሄድ ይችላል የሚል ግምታቸውን እየሰነዘሩ ነው። ይሄ ለእኔ የሞተ ተጎዳ አይነት አስተሳሰብ ነው።

የአገሪቱ ፖሊስ የሟቾች ቁጥር 13 ብቻ ነው ያለ ቢሆንም አሁን እየወጡ ያሉት የመብት ተከራካሪዎች መረጃ የሟቾች ቁጥር ወደ 65 ከፍ እንዳለ የሚያሳይ ነው።

ለሞቱት ነፍስ ይማርልን!

ቤኒሻንጉል ክልል በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ ግድያ ተፈጸመባቸው

$
0
0

Benishangul
ኢሳት ዜና (ነሐሴ 25, 2015)
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ የተቀነባበረ ጥቃት መሰንዘሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ። ባለፈው ሚያዚያ ወር መጨረሻ ተፈጸመ በተባለው በዚሁ ጥቃት፣ ከ80 በላይ ሰዎች መገደላቸውንና በአንድ ቀበሌ ውስጥ የሚገኙ አማሮች ሙሉ በሙሉ የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን ዕማኞች ለኢሳት ገልጸዋል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወንበራ ወረዳ መልካ ቀበሌ ከሶስት ወራት በፊት በተፈጸመው በዚሁ ጥቃት 84 ሰዎች መገደላቸውን የገለጹት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ግድያውም በጦር መሳሪያና በስለት ጭምር የታገዘ መሆኑን አስረድተዋል። ለቀናት አማሮች የሚደርስላቸው በማጣታቸው የተረፉት ንብረታቸውን ጥለው መሸሻቸውን ገልጸዋል።
ሚያዚያ 27 እና 28 ለሁለት ቀናት በወንበራ ወረዳ መልካ ቀበሌ ለቀጠለው ጥቃት መነሻው አንድ የአካባቢው ተወላጅ ባልታወቁ ሰዎች ተገደሎ መገኘቱ እንደሆነም ተመልክቷል።
በአማሮች ላይ በአካባቢው ባለስልጣናት ግፊትና ድጋፍ ለተቀነባበረውና ለቀጠለው ጥቃት የሚደርስ አካል በመታጣቱ፣ ሰለባዎቹ ለቀናት አደጋውን ሲጋፈጡ መቆየታቸውንም መረዳት ተችሏል።
ኢሳት ያነጋገራቸው ሁለት የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት የሟቾቹ አስከሬን የተሰበሰበው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከቀናት በኋላ ወደስፍራው ሲደርሱ ነው።
ጥቃቱን በማድረስ የተጠረጠሩ 10 ያህል ሰዎች የተያዙ ቢሆንም፣ ድርጊቱን በማቀነባበርና በመምራት ተሳታፊ የሆኑ ባለስልጣናት አለመጠየቃቸውን መረዳት ተችሏል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወንበራ ወረዳ መልካ ቀበሌ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች በአብዛኛው ሲገደሉ፣ የቀሩት በመሸሻቸው በአሁኑ ወቅት በቀበሌው አንድም የአማራ ተወላጅ እንደማይኖር ለኢሳት ምስክርነታቸውን የሰጡ ወገኖች ገልጸዋል።


ስካይ ባስ ባደረሰው ጉዳት የተወሰነበትን የካሳ ክፍያ በሰበር አሳገደ

$
0
0

new busesጥር 8 ቀን 2004 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር ሲጓዝ ዓባይ በረሃ ውስጥ በተገለበጠው አውቶቡስ ምክንያት በደረሰው የሞት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት ካሳ እንዲከፍል በሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የተላለፈበት ስካይ ባስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት በማግኘቱ ውሳኔው ታገደ፡፡

በወቅቱ በአውቶቡስ ይጓዙ ከነበሩት 48 መንገደኞች መካከል በሕይወት ከተረፉት ከስድስቱ መንገደኞች አንዱ ለአቶ አገኘሁ መኮንን የቂርቆስ ምድብ 2ኛ ፍትሕ ብሔር ችሎት ሰኔ 10 ቀን 2007 ዓ.ም. በዋለው ችሎት፣ ከ300 ሺሕ ብር በላይ እንዲከፈላቸው መወሰኑን ባለፈው ሳምንት መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ይኼንን ውሳኔ የተቃወመው የስካይ ባስ ኩባንያ ጉዳዩን ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያለ ቢሆንም፣ የከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሐምሌ 7 ቀን 2007 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ውሳኔው እንዲፀና ወስኗል፡፡

ዓባይ በረሃ ገደል ውስጥ በገባው ስካይ ባስ 43 ሰዎች አለቁ

ይኼንን ውሳኔ በመቃወም ስካይ ባስ ጉዳዩን ለፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት አቅርቧል፡፡ አቤቱታውም ሐምሌ 9 ቀን 2007 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንደሚያትተው የአመልካችን የጥፋት ኃላፊነት አስመልክቶ ከንግድ ሕግ ቁጥር 599 አንፃር በካሳ መጠን አወሳሰኑ ላይም የንግድ ሕጉንና የፍትሐ ብሔር ሕጉን መሠረት ያደረገ መሆን አለመሆኑ ለማጣራት ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ይቅረብ ሲል አዟል፡፡ መዝገቡ ተመርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ለኅዳር 30 ቀን 2008 ዓ.ም. የተቀጠረ ሲሆን፣ በሥር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ትዕዛዝ እንዲታገድ አዟል፡፡

ስካይ ባስ ትራንስፖርት ሲስተም አክሲዮን ማኅበር ለሪፖርተር በላከው መግለጫ፣ ዕግድ ከተደረገበትና ከተሸነፈበት ውጪ በአማራ ክልልና በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተመሳሳይ ጉዳይ ተከሶ ማሸነፉን ገልጿል፡፡ የተያያዙት መዝገቦችም ይህንኑ ያሳያሉ፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ከጠቅላላ ጉባኤው ሲመለሱ ተደበደቡ

$
0
0

ነገረ ኢትዮጵያ 118

‹‹የደበደበኝና የዘረፈኝ ሰው ተለቆ እኔ ታስሬያለሁ›› አቶ ጌትነት በሱፍቃድ

በወላይታ ዞን ቦሎቶሶሬ ወረዳ አረካ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የሆኑት አቶ ጌትነት በሱፍቃድ ተደብድበው ንብረቶቻቸውን መዘረፋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በምርጫው ወቅት ቅስቀሳ ላይ እያሉም በገዥው ፓርቲ ካድሬዎች ተመሳሳይ ወንጀል ተፈፅሞባቸው እንደነበር የገለፁት አቶ ጌትነት ‹‹በምርጫው ወቅት ቅስቀሳ ላይ እያለሁ በካድሬዎች ተደብድቤ ንብረቴን ተቀምቻለሁ፡፡ ሌሎች የትግል ጓደኞቼም ተመሳሳይ ወንጀል ተፈፅሞባቸዋል፡፡ ሆኖም ከፖሊስ ጣቢያ ጀምሮ እስከ ከንቲባው ፅ/ቤት ድረስ በመሄድ አቤቱታ ብናቀርብም የሚሰማን አላገኘንም፡፡›› ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በቦሎቶሶሬ ወረዳ የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ጌትነት በሱፍቃድ ከሰማያዊ ጠቅላላ ጉባኤ ተሳትፈው ከተመለሱ በኋላ ነሃሴ 20/2007 ዓ.ም በአረካ ከተማ ተመሳሳይ ወንጀል እንደተፈፀመባቸው ገልጸዋል፡፡ ደብድቦ ስልካቸውንና የአንገት ሀብላቸውን የቀማቸው ሰው እጅ ከፍንጅ ከተያዘ በኋላ ስልካቸው በፖሊስ እንደተመለሰላቸው የገለፁት አቶ ጌትነት እሳቸው ታስረው እስከ ሌሊቱ 5 ሰዓት ሲቆዩ ወንጀሉን የፈፀመው ሰው ወዲያውኑ መለቀቁን ገልጸዋል፡፡

‹‹የደበደበኝና የዘረፈኝ ሰው ተለቆ እኔ ታስሬያለሁ፡፡ የደበደበኝ ሰው ካድሬ ነው፡፡ ጭራሹን ለፖሊስ ለመክሰስ በሄድኩበት ወቅት ‹እሱም ሊከስህ ስለሆነ አንተም መክሰስ የለብህም፡፡ እንዳትካሰሱ ብለን መዝገቡን ዘግተነዋል› ብለው መልሰውኛል›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡ የአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ የትውልድ ቦታ በሆነው አረካ ከተማ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ላይ ከፍተኛ በደል እንደሚፈፀም በተደጋጋሚ የሚገለፅ ሲሆን አቶ ጌትነትም ‹‹የሚደርሰው በደል ከፍተኛ ነው፡፡ ባለፈውም ለተፈፀመብን አሁንም ለተፈፀመብኝ ወንጀል መፍትሄ አልተሰጠኝም፡፡ ለአንድ ሰው ካድሬዎች በመንጋ መጥተው ነው የሚያጠቁህ፡፡ አቤት የምትልበት አካል የለም›› ሲሉ ገልጸውልናል፡፡

የማለዳ ወግ…የባለስልጣኖቻችን ጉብኝትና የእኛ ኑሮ…. ! በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሴቶች ዳይሬክቶሬት ጀኔራል ዶር ደስታ ወ/ዮሃንስ በጅዳ ሳውዲ አረቢያ 

$
0
0
saudi ethiopia saudi
ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በምንገኝበት በሳውዲ አረቢያ በአለማችን በመንግስት ባለስልጣናት ከሚጎበኙት ቀዳሚ መሆኑ አሊ አይባልም። ከጠቅላይ ሚኒስትር ከፍተኛ ባለስልጣል ጀምሮ በሚኒስቴር ፣ በሚኒስቴር ዴታና በዳይሬክቶሬት ኃላፊነት ያሉ ከፍተኛ ሹሞቻችን እያሰለሱ ጎብኝተውናል ። ምንም እንኳን ኃላፊዎች ሲመጡ ተራው ነዋሪን ለማነጋገር ባይችሉም በአደረጃቸት የታቀፉትን የገዥው ፖርቲ አባላት ፣ ማህበራትንና ኮሚኒቲውን በተደጋጋሚ ሰብስበው አነጋግረው ያውቃሉ።  ለመንግስት አስተዳደር በታቀፉት ድርጅት በኩል ቀረቤታ ካላቸው ካደሬዎች ፣ በልማት ማህበር ተብየዎችና በኮሚኒቲው ኃላፊዎች የተሸራረፈም ቢሆን ነዋሪው ስላለበት ችግር ፣ በቆንስልና በኢንባሲ ተወካዮች ስላለው የመብት ማስጠበቅ ህጸጽ ሳይናገሩ የቀሩበት ጊዜ የለም ።

ዳሩ ግና የሚመጡት ባለስልጣናት ሁሉ ብሶት መከራው ን ሰምተው ” እርማት ይደረግበታል !” ብለው ቃል ከገቡት የሚጨበጥ ለመጥፋቱ ብዙዎችን ለነዋሪው ሳይሆን ለድርጅት ታማኝ አገልጋይ የሆኑ ካድሬዎች ሳይቀር  ተስፋ አስቆርጧቸዋል ፣ አስከፍቷቸዋል  ! እውነቱ ይህ ሆነና ሀገሪቱን ከፍተኛ የአስተዳደር ከፍ ያለ መቀመጫ ያላቸው ባለስልጣናት የህዝብና ሀገር ገንዘብ ተደርጎ የሚያደርጉት ጉብኝት ” ባለስልጣናቱ የሚመጡት በስራ ስም  ለገብያ ነው! ” ወደ ሚል መደምደሚያ እንዳደረሳቸው ” መረጃው በእኔና ባንተ ይቅር! ” ያሉኝ አንዳንዴ ከፖለቲካው ሰብዕናው እያጠቃቸው አሾልከው መረጃ የሚያቀብሉኝ ከፍተኛ የኢህአዴግ ድርጅት ኃላፊዎች ሹክ ብለውኛል …

ከወራት በፊት ወደ ጅዳ መጥተው በአካል ያገኘኋቸ ው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሴቶች ዳይሬክቶሬት ዶር ደስታ ወ/ዮሃንስ ጋር ባረፉበት ሆቴል ተገኝቸ ብዙ በማህበራዊ ህይዎቱ ዙሪያ ስለሚታዩ የመብት ጥሰትና ተዛማጅ ጉዳዮችን ከነመረጃ ማስረጃው አቀብያቸውም ነበር ።  በተለይ በተለይ  ካረፉበት ሆቴል የአንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ካለው የዶር ፈቂ ሆስፒታል ስለተኛው ስለ ብላቴናው መሀመድን እና በቤተሰቡ ላይ ያረፈውን የመከራ ቀንበርና በብሪማን እስር ቤት ለወራት በታሰርኩበት አጋጣሚ በአካል ያየሁትን ወንድም የከፋ በደል በተጨባጭ ማስረጃ አጫውቻቸው በጥልቅ አዝነውና እንባ ተራጭተናል …

በወቅቱ እጅጉን የከፋው በደል  የከብትና ግመል እረኛ ሳለ ” ከብት አጥፍተሃል ” ተብሎ የታሰረው ” እረኛ “ወንድም በህግ ከለላ በእስር ላይ እያለ በአንድ አዕምሮ እስረኛ የባለቤቱን ነፍስ አጥፍቶ በታሰረ ያገር በደረሰበት ድብደባ አካሉን የረገፈው ጎልማሳ አሳዛኝ ህይዎት አሻውቻቸዋለሁ። ይህ ወንድም  ፍትህ ርትዕ ማግኘቱ ቀርቶ በቂ ህክምና ሳይደረግለት በግፍ ከሳውዲ መሸኘቱን አግባነት የሌለው ስራ መሆኑን ለዶር ደስታ ከፎቶ ማስረጃ ው አሳይቻቸዋለሁ አብረን ተላቅሰናል ። ጉዳዩ እንዲጣራ  ያደርጉ ዘንድ ያ ግፉኡ ወንድም የረባ ህክምና ሳያገኝ ለምን ተሸኘ ?  አካሉ ረግፎ ሀገር እንዲገባ ከጅዳ ቆንስላ የመጓጓዣ ሰነድ ሊሴ ፖሴ ማን ሰጠው  ? መጓጓዣ ከመሰጠቱ በፊት  በህግ ከለላ ያለ ሰው ህግ በአስከባ ሪዎች እንዝህላልነት በደል ሲደርስ በት ለተፈጸመበት ወንጀል ተጠያቂዎች ለምን ለፍርድ እንዲቀርቡ  አልተደረገም ? ቁስሉ ሳይሽር አዋክቦ ለመሸኘት ተፈለገ ?  ለምን ተበዳይ ለተበደለው ካሳ አግኝቶ ይሂድ ተብሎ  አልተጠየቀም  ? ለሚለው ጥያቄ መልስ እንደ ሚያስፈልገው ከዶር ደስታ ወ/ ዮሃንስ ጋር ተስማምተን ፣ ባለስልጣኗ ይህንን ለማጣራት ቃል ገብተውልኝ ተለያየን ። ያ ከሆነ ቀናት ሳምንታትን ፣ ሳምንታት ወራትን እየወለዱ  ጊዜው ነጉዶ ዛሬ ላይ ስንደርስ  ” አዲስ አበባ የገባውን ወንድም እከታተላለሁ ፣ በመንግስት ሆስፒታል እንዲታከም አደርጋለሁ ፣ ጉዳዩን አጣርቸ ተጠያቂዎችን አጣራለሁ! ” ብለው ቃል ከገቡልኝ እመቤት  ከዶር ደስታ ጠብ የሚል መልስ  አላገኝ አልኩ ..  ያ የፈረደበት ምስኪን መከረኛ ” እረኛ ” ወንድምም  ህክምና ሳያገኝ ከነቁስሉ ተሸኝቷልና የድሃ ቤተሰቦቹ ሸክም ሆኖ ቀረ ፣ የዶር ደስታ ቃል እንደ ሀምሌ ጉም በኖ ጠፋ  … ” ቄሱም ዝም ፣ መጽሐፉም ዝም! ” እንዲሉ ዶር ደስታ  ቃል የገቡትን ሳይፈጽሙ እነሆ ግራ ያጋባ ለሁለተኛ ጊዜ የጅዳ ጉብኝታቸውን ከዋውነው ትናንት ሰኞ ለማክሰኞ አጥቢያ ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል ! የባለስልጣኗ ጉብኝት ምን ይመስል ነበር ?  ካላችሁ ደግሞ ወደዚያው እናቅና …

የዶር ደስታ የንጉስ ፋአድ ሆስፒታል ጉብኝት …
=============================
በአዲሷ የሴቶች ሊቀ መንበር ወሮ ሙሉካ ሁሴን አጋፋሪነት በንጉስ ፉአድ ሆስፒታል የተኙትንና ሶስት ታህል ታማሚዎች የጎበኙት ዶር ደስታ  ምንም እንኳን የጉብኝታቸው መቋጫ ውሉ ባይገባኝም ሶስት ታማሚዎችን መጎብኘታቸውን በቦታው ከነበሩት ሰምቻለሁ ።  በንጉስ ፉአድን ሆስፒታል ከተጎብኙት  ታማሚዎች መካከል ባንድ ወቅት የጅዳ ቆንስል ከአፍንጫው ስር ለአመታት በሰመመን ውስጥ ስላለችው እህት ይጎብኝ ብየ መረጃ በማቀበሌ እኔና የመረጃ አቀባየ በቆንስሉ አንድ ዲፕሎማት የተወረፍንባት ማንነቷ ሳይታወቅ በንጉስ ፉአድ ለአመታት የተኛችው እህት ትገኝበታለች። ግራ ቢገባኝ ዶር ደስታ  የዚህች እህት ማንነትና ይታወቅና  ቤተሰቦቿ ይፈለጉ ዘንድ ትዕዛዝ በሉት መመሪያ አለመስጠታቸውን ስሰማ አዝኛለሁ  ! የሴቶች ዳይሬክቶሬት ከሆስፒታሉ ኃላፊዎችም ሆነ ከውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ጋር ግንኙነት ፈጥረው የጎበኟቸው እህቶች ህክምናቸው ይሻሻል ስለማለታቸውም ሆነ አድራሻቸው የማይታወቀውን ለማጣራት ስላደረጉት ጥረትም ውጤት አልተነገረምና ፣  አልሰማሁም … ታላቋ ባለስልጣን መጎብኘታቸውን ብቻ ሰምተናል  !
ክፍል አንድ በዚህ አከተመ …

የቀጣይ ወጎች ቅምሻ …
================
በዶር ደስታ ክፍል 2 …ዳሰሳየ
ሀሙሱ ፣ ሰኞ ፣ የሽሜሲ እስር ጉብኝት ውይይት  …
===============================
በሳውዲ መንግስት በኩል ” ህገ ወጥ”  ተብለው በሌሊት ቤት ሰበራና አፈሳ የታሰሩ ዜጎች የሚገኙበትን የሽሜሲ እስር ቤት ዶር ደስታ ሀሙስ ታሳሪዎችን ፣ ሰኞ የሳውዲውን ባለስልጣን   ጎብኝተዋል …ህጋዊ መኖሪያ ፍቃድ እያላቸው ያለ አግባብ ለተያዙት ”  መብታችን ተጥሶ  ወደ ሀገር ለመግባት ፎርም አንሞላም!” ያሉትን በርካታ ኢትዮጵየ ያን እንዳገኙና እንዳወያዩዋቸው የጨነቀ የጠበባቸው ሁሌም እያለቀሱ ብሶት ምሬታቸውን የሚነግሩኝ ታሳሪዎች ያቀበሉኝ መረጃ ያስረዳል …

በዶር ደስታ ክፍል 3 4  … ዳሰሳየ
እያልኩ  በማቀርበው ዳሰሳየ የሴቶች ዳይሬክቶሬት ዶር ደስታ የሴቶች ስብሰባን ይሆናል… ለቅምሻ ስቀጥል :)
=================================
የሴቶች ዳይሬክቶሬት ዶር ደስታ ጉብኝት አስመልክቶ ጉብኝቱን ስዳስስ ይህም አይቀር ላንሳው ብየ እንጅ ውይይት ምክክሩ የረባ እንዳልነበር ተነግሮኛል። ዲፕሎማቶች በሞሉበት የሴቶች ስብሰባ የሟች ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሶስተኛ ሙት አመት በሻማ ማብራት ታስቧል ። ከዚህ ቀደም አዳራሹን የሚያደምቁት የድርጅት ማህበር አባላት ፣ የጅዳ ቆንስል ” ነጭ በሬ”  ሴቶች ወይዛዝርት በዚህ የሴቶች ስብሰባ አልተሳተፉም።  በጣት የሚቆጠሩ እህቶች በታደሙበት የቀዘቀዘ ውይይት ተደርጎም የብዙሃኑ ነዋሪ እህቶች ብሶት በስብሰባ ውይይቱ አልተንጸባረቀም  …
****************
እልና በሴቶች ስብሰባ ስላልተወሳው በርካታ የሴቶች ጉዳይ ብላቴናው መሀመድ በባለስልጣኗ እንዳይጎበኝ ግፊት አለመደረጉን  አነሳለሁ …
****************
..ቢረሳ ቢረሳ መዲና ለሁለት አመታት ያለ ጠያቂ በአንድ ሆስፒታል ተጥላ ያለችውን እህት ጉዳይ እንኳ ማንሳት ለምን አልተቻለም?  ከአሰሪያቸው ተፈናቅለው ፣ ተባረውና ተጥለው በመጠለያው ስለሚገኙ እህቶች  ፣ በኩንትራት መጥተው ስለሚሰቃዩ ፣ ስላበዱ ፣ ስለተደፈሩ መናገር አለመቻሉ ፣ በዘገየው ፖስፖርት መኖሪያ ፈቃዳቸው ስለወደቀባቸው ሴቶች እና ሌላም ሌላም መወያየት  መረጃ ጠፍቶ ሳይሆን” ያገባኛል !” ባይ ለነፍሱ ያደረ ደፋር ጠፍቶ በስብሰባው ጥልቅ ውይይት ሳይደረግበት ተዘሏል  ! ….

የሴቶች ዋና ዳይሬክቶሬት በተገኙበት ስብሰባ የመሀመድን ጉዳይ ለምን ማንሳትና መወያየት እንዳልቻሉ አልገባኝም ! ” ነግ በኔ !”  ነውና ቢያንስ ማህበሩ የመሀመድን እናት በቤት ኪራይ ፣ በትራንስፖርት በመሳሰሉት  እንደግፍ ብሎ መም ከር ያልቻለበት ምክንያት ምን እንደሆነ የሚያውቁት እነሱ ብቻ ናቸው !

 ዶር ደስታ ወ/ዮሃንስ በጅዳ የሽሜሲ እስር  ቤት ጉብኝትና ውይይት !
=============================
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ዶር ደስታ ወ/ዮሃንስ ጅዳ ለሁለተኛ ጊዜ ሲጎበኙ አውቃለሁ። አምና ተገናኝተን በሆነውና ከሰሞኑም ለቀናት ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ተከታታይ መረጃ ማቅረብ ጀምሬያለሁ ።  በክፍል አንድ ዳሰሳየ ዶር ደስታ በጅዳ ንጉስ ፉአድ ሆስፒታል ያደረጉትን ጉብኝት ማነሳሳቴ አይዘነጋም ። ዛሬ ደግሞ በርካታ ኢትዮጵያውያን ታስረው በሚገኙበት ከመካ የቅርብ ርቀት በሚገኘው የሽሜሲ እስር ቤት ታዳሪዎችን ስለጎበኙበትና ከሳውዲ ኃላፊዎች ጋር ስለተቀመጡበት ውይይት ከፍል ሁለት ዳሰሳየን እንዲህ እቀጥላለሁ! የፈቀዳችሁ ተከተሉኝ …

በሽሜሲ እስር ቤት ዶር ደስታ  ከታሳሪዎች ጋር ..
==============================
በሳውዲ መንግስት በኩል ” ህገ ወጥ”  ተብለው በሌሊት ቤት ሰበራና አፈሳ የታሰሩ ዜጎች የሚገኙበትን የሽሜሲ እስር ቤትን ጅዳን ለቀናት የጎበኙት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዶር ደስታ ወ/ዮሃንስ ሀሙስ  ፣ ነሀሴ 14 ቀን 2007 ዓም  ጎብኝተዋል።  በዚሁ ጉብኝት  ”  መብታችን ተጥሶ  ወደ ሀገር ለመግባት ፎርም አንሞላም!” በሚል ከእስር ቤት ወደ ሀገር ለመሄድ ፈቃደኛነት ያላሳዩ  ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ እያላቸው ያለ አግባብ የተያዙትን ፣  ከአሰሪያቸው ጋር ተጣልተው ጉዳያቸው በፍ/ቤት ተይዞ እያለ “ህጋዊ አይደላችሁም!” ተብለው የታሰሩትን  ፣ ሌሊት ቤት እየተሰበረ እርቃናቸውን የተያዙትን ፣ በሌሊት አሰሳ ፍተሻው ከነ ልጆቻቸው የተጋዙ አባዎራዎችን ፣ ሁሉንም ባይሆን በመቶዎች የሚቆጠሩትን ዶር ደስታ በጉብኝታቸው በአካል አግኝተው የተበደልን ተገፋን ሮሮ ፣ አቤቱታ ምሬታቸውን አድምጠዋል ፣ ታሳሪዎች በተለይም ወደ ሀገር ይሸኙ እንኳ ቢባል በሳውዲ ለአመታት ሲኖሩ ያፈሩትን ሀብት ንብረት ፣ የሰሩበትን የላብ ዋጋ በአሰሪ አረቦች የተቀሙትና የበተኑትን ሀብት ንብረት እንዲመለስላቸውም ሆነ እንዲሰበስቡባ ወደ ሀገር እንዲልኩ ያደርጉ ዘንድ ባለስልጣኗን ሲማጸኑ ” በዋስትና እንኳ እንድንፈታ መንገድ ይፈልጉልን ” እንዳሏቸው ታሳሪዎች አጫውተውኛል ። ጨነቀ የጠበባቸው ሁሌም እያለቀሱ ብሶት ምሬታቸውን አሾልከው በሚያገኟት አጋጣሚ በስልክ የሚነግሩኝ እኒሁ ታሳሪዎች ከዶር ደስታ ጋር ሲወያዩ ዶሯ  በውይይቱ በሰሙት መረጃ ማዘን መቆጨታቸውን ጠቁመውኛል .. .

ዶር ደስታ ሁሉንም ሰምተው ፣ በሆነው አዝነው ፣ በእስር ቤቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተወካይ ከሆኑት ከዶር መሀመድ ኑሪጋ ጋር በቀረበው የታሳሪዎች ብሶት ፣ ምሬትና አቤቱታ ዙሪያ ለመምከር ለሰኞ ሰኔ 17 ቀን 2007 ዓም  በቀጠሮ ተለያዩ …

በሽሜሲ እስር ቤት፣ዶር ደስታና የኃላፊው ውይይት!
===============================
የአረብ ቀጠሮ ሆነና የሰኞ ሰኔ 17 ቀን 2007 ዓም ቀጠሮ ወደ ማክሰኞ 18 ቀን 2007 ተላለፈ …ከሀሙስ እስከ ማክሰኞ ባሉት ቀናት ፍተሻ አሰሳው ጦፎ ፣  ከሌሊት ሰበራው ለመሸሸት ከሚኖርበት ፎቅ ደመ ነፍሱን በመስኮት የዘለለ የሁለት ልጆች አባወራ ከሞት ላደረሰ አደጋ መጋለጡን ሰማን …

የዶር ደስታና የሳውዲው ኃላፊ ቀጠሮ ማክሰኞ 18 ቀን 2007 ደረሰ ።  ዶር ደስታ ፣ የቆንስሉ ኃላፊዎችና የጅዳ ሴቶች ማህበር ሊቀመንበር በተገኙበት በሳውዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሽሜሲ እስር ቤት ተወካይ ከሆኑ ከዶር መሀመድ ኑጋሪ ጋር ውይይቱ  እኩለ ቀን ተጀመረ  !

ዶር ደስታ በውይይታቸው ሀሙስ ታሳሪ ኢትዮጵያውያንን ሲጎበኙ ያዳመጡትን በዜጎች የቀረበውን አቤቱታ በዝርዝር አቀረቡ። ሳውዲው ኃላፊ ዶር መሀመድ ዶር ደስታ ስላቀረቡት በሌሊት ቤት ሰበራ ፣ ማዋከብ ፣ ሀይማኖቱ በማይፈቅደው መልኩ እርቃናቸውንና የረባ ልብስ ሳይለብሱና ጫማ ሳይጫሙ የመሳሰለውን አይነት ግፍ በታሰሩ ዜጎች ላይ ተፈጽሟል ስላሉት ቅሬታ የቆንስሉ በኩል ከዚህ ቀደም ምንም አይነት ቅሬታም ሆነ አቤቱታ እንዳልቀረበና በዚህ ረገድ ከቆንስል ኃላፊዎች በኩል ክትትል መጉደሉን ሳውዲው ኃላፊ እንቀጩን ተናግረዋል።  ዶር መሀመድ በዚሁ ውይይት የመብት ገፈፋን ለመከላከል አሰሳው በጥናትና ከተለያዩ የመንግስት አካላት በተውጣጡ ኮሚቴዎች  የሚካሄድ በመሆኑ የመብት ጥሰት አለ ብለው እንደማያምኑ በመጠቆም ጉዳዩ ተፈጽሞ ከሆነ እንደሚያጣሩት ቃል ገብተዋል። በማከልም የሳውዲ መንግስት ከህገ ወጦች አስጠግተው ወይም ተጠግተው የተያዙትን መያዙ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ቆንስል መስሪያ ቤቱ ይህንን ለመተግበር ትብብር እንዲያደርግ መጠየቃቸው ተጠቁሟል ። ባለስልጣኑ ይህን ቢሉም ዶር ደስታ ከታሳሪ ኢትዮጵያውያን በኩል የቀረበላቸውን አቤቱታና ተማጽኖ በማውሳት ለአመታት ሲኖሩ ያፈሩትን ሀብት ንብረት የመሰብሰብ  ፣ የሰሩበትን የላብ ዋጋ በአሰሪ አረቦች የተቀሙትና የበተኑትን ሀብት ንብረት እንዲመለስላቸውም ሆነ እንዲሰበስቡ ዋስትና አግኝተው እንዲፈቱ እንዲደረግ ጠይቀው የነበረ ቢሆንም ጥያቄው በሳውዲው የውጭ ጉዳይ ተወካይ ለዶር መሀመድ በኩል ተቀባይነት አላገኘም።

ለአመታት ጠያቂ ያጣው የዜጎች ንብረት እንደቀልድ !
================================
በዚሁ ውይይት የተነሳው ሌላው ጉዳይ እአአ 2013 ሳውዲ በአዋጅ ህገ ወጦች ስታስወጣ “እናንተ ሂዱ ፣ እቃችሁ ይላካል! ” ተብሎ ቃል የተገባላቸውና የሰልተፈጸመው በሽዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ተነላሾች የሻንጣና የተንቀሳቃሽ ስልክ ጉዳይ ነው።

(ከአመታት በፊት ዜጎች ወደ ሀገር ሲሸኙ ጥለውት የሄዱት በመቶዎች የሚቆጠር ሻንጣና ወደ 7 ሽህ ጉዳይ እኔም በጅዳ የወገን ለወገን አስተባባሪ ኮሚቴ እያለው የማውቀው ጉዳይ ሲሆን ለአመታት እልባት በቆንስል መስሪያ ቤቱ እንዝህላልነት በሉት በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እህት ወንድሞቻችን በላባቸው ያፈሩት ንብረት ጠያቂ አጥቶ ጉዳዩ ያለባለቤት ሲንከላወስ መኖሩን አውቃለሁ)

ወደ ውይይቱ ስንመለስ ዶር መሀመድ ከላይ በጠቀስኩት ወቅት በሽሜሲ የተሸኙ ዜጎቻችን ሻንጣ ተንቀሳቃሽ ስልክ ንብረት እንዳለ አስረግጠው ፣   የጅዳ ቆንስል መ/ቤት ንብረቱን ተረክቦ ወደ ሀገር እንዲልክ ደብዳቤ ሳይቀር መጻፉን ለዶር ደስታ አስረድተዋል። በማከልም  አሁንም በሽሜሲ እስር ቤቱ ያለውን የኢትዮጵያውያን ንብረት የጅዳ ቆንስል እንዲረከባቸው ለዶር ደስታ አስረድተዋል ሲሉ በስብሰባው ዙሪያ ያገኘሁት የመረጃ ምንጭ ያስረዳል !

ከወራት በፊት የታገደው ለታሳሪዎች ሻንጣ ማቀበል ይከፈት ዘንድ በዶር ደስታ ተነስቶ የነበረ ቢሆንም ሻንጣ ማቀበሉ ስራ በውስጣዊ ችግር ምክንያት በቅርቡ እንደማይከፈት ሳውዲው ኃላፊ በማያሻማ ቋንቋ አሳውቀዋቸዋል ። …

“ዜጎቻችሁ ህግና ስርዓት ይያዙ  “የውይይቱ መቋጫ ….
==================================
በዚሁ ውይይት የሳውዲው ኃላፊ በአጽንኦት ባስተላለፉት መልዕክት  ” ዜጎቻችሁ ህግና ስርዓት ካልያዙ ፣ ከህገ ወጥ ጋር ከተገኙና ከተያዙ ታስረው ወደ ሃገራቸው መላኩ በህግና መመሪያ የወጣበት ጉዳይ ነውና ፣ ተጠናክሮ ቀጣይ እንጅ የሚቆም አይደለም! ” ሲሉ የሳውዲው ባለስልጣን ለዶር ደስታ ገልጸውላቸዋል !

በጉብኝቱ የዜጎችን ብሶት ዶር ደስታ ወ/ዮሃንስ መናገራቸው እውነት ነው ፣ ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆነና ” የታሰሩት አይፈቱም ፣ በዋስም አይወጡም ፣ ህግ ነውና ይተገበራል ፣ ቀሪውም ህገ ወጥ ያልታሰረ ዜጋችሁ በቀጣዩ ዘመቻ እንዳይታፈስ ህጋዊው ለህገ ወጦች ወጦች ሽፋን እንዳይሆን ምክሩት ፣ በዚህ ላይ ምህረት የለም  !” የሚለውን መልዕክት ብልጡ የሳውዲ ባለስልጣን ለእኛዎቹ ባለስልጣናት አስተላልፈዋል …

በጉብኝት ውይይቱ የተገኘ ውጤትና ፋይዳ ይህው ነው … ታሳሪዎች ብሶትና ሮሮ በዶር ደስታም ሆነ በጅዳ ቆንስል ሺሞቻችን መልስ አላገኘም  ! ፎርም አንሞላም ብለው በእስር ቤት የሚገኙ ሀቁን ተገንዝበው የራሳቸውን ውሳኔ ሊወስዱ ይገባል  !  …  ጠቅለል ብሎ ሲቀርብ ከታማኝ ምንጮቸ ያሰባሰብኩት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች  ጉዳይ ዳይሬክቶሬት የዶር ደስታ ወ/ዮሃንስ የሽሜሲ ውሎ ሲብራራ ከዚህ ያለፈ አይደለም …

የሴቶች ዳይሬክቶሬት ጀኔራል ዶር ደስታና በጅዳ የሴቶች ስብሰባ
==========================
እነሆ አንድ ሁለት ብየ የሴቶች ዳይሬክቶሬት ጀኔራል ዶር ደስታ ወ/ዮሃንስን ባደረጉት ሰሞነኛ የሳውዲ ጅዳ ጉብኝት አስመልክቶ ከጀመርኩት ሶስተኛ ክፍል ዳሰሳ ደርሻለሁ።  ይህም አይቀር ላንሳው ብየ እንጅ ውይይት ምክክሩ የረባ እንዳልነበር ተነግሮኛል ። ባሳለፍነው ቅዳሜ ነሀሴ 16 ቀን 2007 በጅዳ ኮሚኒቲ አዳራሽ በተካሄደው የሴቶች ስብሰባ በርከት ያሉ ወንድ የቆንስል ፣  ኮሚኒቲ ፣ ሰራተኞችና ዲፕሎማቶች ተገኝተው የሟች ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሶስተኛ ሙት አመት በሻማ ማብራት ታስቧል ። ከዚህ ቀደም አዳራሹን የሚያደምቁት የድርጅት ፣ ማህበር አባላት ፣ የጅዳ ቆንስል ” ነጭ በሬ”  ሴት ወይዛዝርት እንደቀድሞው በዚህ ስብሰባ አልተሳተፉም። የኢህአዴግ ድርጅቶችና ማህበራት ድግስ ደግሰው የማያለቅ ልደትና የተለያዩ በአላትን ሲያከብሩ ቄጠማ ነስንሰው አምባሻ ደፍተውና ቡናና አበባ ቆሎ ቆልተው የሚያቀርቡ የሚያስተባብሩት እማማ አደይ በስብሰባው የተገኙት በሽምግልናና ጉትጎታ መገኘታቸው ተጠቁሟል ። ያም ሆኖ በእነ እማማ አደይ ዘንድ ግብብ የሌላቸው በጣት የሚቆጠሩ የአዲሧ የሴቶች ሊቀመንበር የወሮ ሙሉካ ሁሴን ባልንጀሮችና ወዳጆችነ ጨምሮ ጥቂት ነባር አባላት በታደሙበት የቀዘቀዘ ስብሰባ ውይይት ተደርጎ ነበር ። መረጃውን ያቀበሉኝ ወዳጆቸ ውይይቱ የብዙሃኑ ነዋሪ እህቶች ብሶት አልተንጸባረቀም ሲሉ አንቶ ፈንቶ  በማለት የጅዳ ቆንስልን የውስጥ አሰራር የተገመገመበት እዚህ ግባ የማይባል ውይይት ነበር ሲሉ አጣጥለውታል ።

እኔ ከሁሉም ያዘንኩት ከጀዳ ቆንስል ኃላፊዎች ጋር ጥብቅ ግንኙነት መመስረት የማይታክታቸው ፣ ከዚህ ቀደም በሰብአዊ ድጋፍና በዜጎች ተቆርቋሪነታቸው ፤ጠንካራ ሰራተኝነታቸው የማውቃቸው አዲሷ የጅዳ ሴቶች ማህበር ሊቀ መንበር ወሮ ሙሉካ ሁሴን በከባቢው ሴቶች በደል ዙሪያ የጠለቀ መረጃ እያላቸው ፣ ለስብሰባው ግብአት አለማድረጋቸው ገርሞኛል ።  ብርቱና ታታሪዋ ሰርቶ አደር እህትወ/ሮ ሙሉካ  የሴቶች ዳይሬክቶሬት ጀኔራል ዶር ደስታን ከሽሜሲ እስከ የደመቁ የጀዳ ዘመናዊ አልባሳትና ቁሳቁስ ገበያዎች ሲያጋፍሩ ሲሰነብቱ በእጃቸው ያሉ መረጃዎችን ማቀበል ለምን እንዳቃታቸው ሳስበው አዝናለሁ ። ወሮ ሙሉካ የሴቶችን አስረጅ ደፋር አባል ቢያጡና ቢጠፋ ፤ ሰርክ እንደኔ መረጃ በሚለቅሙበት ሰልካቸው ያለውን አንድ ሁለት በተቃረብ ጊዜ መረጃ ስበው በስብሰባው ወቅት ማወያያ ማድረግ እንዴት እንደገደዳቸው የሚያውቀው ፈጣሪ ነው ! ቢረሳ ቢረሳ መዲና ለሁለት አመታት ገደማ ማንነቷ አልታዎቀም ተብላ ያለ ጠያቂ በአንድ ሆስፒታል ተጥላ ያለችውን እህት ጉዳይ እንኳ ማንሳት ለምን አልተቻለም ?  ከአሰሪያቸው ተፈናቅለው ፣ ከስራ ተባረውና ፣ተደፍረው ፣ ተደብድበው ፣ በፈላ ውሃ ተቃጥለውና ተጥለው ፣ በመጠለያው ሰላለፉና ስለሚገኙ እህቶች መደረግ ሰላለበትና ወደፊት መሰራት ሰላለበት ለመምከር ለምን አልተሞከረም ?  በሴቶች ስብሰባ በኮንትራት መጥተው በየቤቱ መድረሻ አጥተው ስለሚሰቃዩ ፣ ”ድረሱልን“ ስለሚሉ ደራሽ ግን ስላጡት ፤ ስላበዱ ፣ ተደፈረው አርግዘውና ወልደው አበሳ ስቅየት ስላዩትና ስለሚያዩት ፣ የድሃ ቤተሰብ ሸክም ስለሚሆኑት ምንዱባን እህቶች መናገር እንዴት አልተቻለም ? በዘገየው ፖስፖርት መኖሪያ ፈቃዳቸው የወደቀባቸው ሴቶች የሉም ?ይህ ሁሉ ተረስቶ ነው ? ወይስ ተዘሎ ?  ይህ ሁሉ የስደተኛ አበሳ ያልተዳሰሰው ለሊቀመነበሯና ለቀሩት ተሰብሳቢዎች እንግዳ ነገር ሆኖ ወይስ መረጃ ጠፍቶ  ?  ለእኔ መረጃ የመረጃ እጥረት ሳይሆን ለእውነት የቆመ ሰው ችግር እያንገላታን እንደሆነ ይሰማኛል።  ” ያገባኛል !” ባይ ተቆርቋሪ አጥተናል ፤ ለነፍሱ ያደረ ደፋር ጠፍቶ የሴቶች ጉዳይ በሴቶች ጥልቅ ውይይት ሳይደረግበት ተዘሏል ብየ ስበሰባውን እኔም በበቃኝ ልዝለለው !

ዶር ደሰታ ሹም ስንፈግ መጡ ፣ ባስፈላጊው ቦታ ሳይገኙ ቀሩ  …
===================================
የስብሰባው ተውሸክሽኮ መከዎን እና በስብሰባው ይነሳል ብየ የጠበቅኩት የብላቴናው መሀመድና የእናቱ ጉዳይ ሳይነሳ የመቅረቱ አንደምታ አንድ የቅርብ ቀን ትዝታን አስታዎሰኝ ።  ሰኔ ሲጠባ የብላቴናው መሀመድን የ9 አመት ሰቃይና አቤቱታ ይዥ እንድቀርብ እናት ሀሊማ “ የበደል ድምጼን ለአለም አሰማልኝ !” ብላ ጠይቃኝ በቪዲዮ የተደገፈ መረጃ አቀረብኩ ፣ ይህን ባቀረብኩ ማግስት የጅዳ ቆንስል አንድ ሃላፊ “ ከዚ በፊት የነበሩ የቆንስል ሃላፊዎች ባይሰሩትም ፤ አሁን ያለነው እኛ ጉዳዩን ይዘን እየተከታተልን እያለ ለምን ለነቢዩ ሲራክ መረጃ ታቀበላለች ” ከሚል ቅንነት በጎደለው እሳቤ ቅር መሰኘታቸው መረጃ ደረሰኝ ፣ ቀጠለና ባልንጀራቸው አዲሷ የሴቶች ሹም ወሮ ሙልካ ጓዶቻቸውን ይዘው ብላቴናውን መሀመድን እናት ለመጠየቅ ሄዱ፣ ችኩሏ እህት ወሮ ሙልካ የባልንጀራቸ ቅሬታ አሟቸው ብቻ ምኑንም ሳይረዱ  ” ለምን ለነቢዩ ሲራክ ቆንስል ኢንባሲ 9 ዓመት አልደገፈኝም አልሽ ? ” በማለት ብርቱዋን የብላቴላው መሀመድ እናት ሀሊማን ግራ የሚያጋባ ጥያቄ ጠይቀው ያሰራጩትን መረጃ “ተብየ” ተመልክቻለሁ ።  ታዲያ የያኔው የአዲስ ተሿሚና የሴቶች ማህበር አመራሮች ጉብኝት ከተቆርቋሪነት ስሜት የመነጨ ከነበር የሴቶች ዋና ዳይሬክቶሬት በተገኙበት ስብሰባ የመሀመድን ጉዳይ ለምን ማንሳትና መወያየት እንዳልቻሉ አልገባኝም !

” ነግ በኔ !”  ነውና ቢያንስ ማህበሩ የመሀመድን እናት በቤት ኪራይ ፣ በትራንስፖርት በመሳሰሉት  እንደግፍ ብሎ ከመምከር ያልቻሉበት ምክንያት ምን እንደሆነ የሚያውቁት እነሱ ብቻ ናቸው !  አንደበተ ርቱዕ የሆኑት የቀድሞ ወዳጀ የጅዳ ሴቶች ሊቀ መንበር ወሮ ሙሉካ ሌላው ቢቀር በየደቂቃዋ መረጃ በሚመለከቱባት በእኔው ፊስ ቡክ መረጃ መረብ ለክቡር የሴቶች ዳይሬክቶሬት ዶር ደስታ የላኩላቸውን ተከታይ አጭር መልዕክት አልተመለከቱትም አልልም ! መልዕክቴም አጭርና ግልጽ ነበር

“ይድረስ ለክቡር የሴቶች ዳይሬክቶሬት ዶር ደስታ …
ብላቴናው መሀመድን ይጎብኙ ፡ ብላቴናው መሀመድ እርስዎ ካረፉበት ሆቴል የአንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ካለው የዶር ፈቂ ሆስፒታል ተጋድሞ ይገኛል ፣ አስጎብኝዎ የሴቶች ማህበር ተብየዎችም ሆኑ የቆንስል ሰዎች ለምን ብላቴናው መሀመድን እንዲጎበኙ እንዳላደረጉ አልገባኝም …  በተለይ እንደ ልጅ እናትነትዎ የታዳጊውን አበሳ ፣ እንደ ሴትና እንደ ሴቶች ተወካይ ዳይሬክቶሬትነትዎ ሰብዕናዋን ለንዋይ ፍቅር ያልሸጠችውን እናት ሃሊማን ማግኘት በራሱ ለእርስዎ መታደል ነው … በሆስፒታል ሄደው ብላቴናው መሀመድንና የመሀመድን እናት ይጎብኙ ፣  በአልጋ ላይ ተንጋሎ ባደገው ህጻን የግፉን ልክ ፣ ከመሀመድ እናት ከሀሊማ ደግሞ ጽናትና  የእምነት ጥንካሬን ይማራሉ ! የእናት የልጅና የቤተሰቡን የ9 ዓመት የመከራ ጉዞም ይረዱታል …  ! እናም ብላቴናውን ይጎብኙት  ! …ሳውዲ ለምንም ይሁን ለምን ከመጡ አይቀር መሀመድን ጎብኝተው በነካ እጅዎ ስለበደሉ ለሳውዲ ከፍተኛ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃላፊዎች አቤት ይበሉልን  !  ለፍትህ አካላትና ለሚመለከታቸው የሳውዲ ባለስልጣናት በብላቴናው መሀመድ  አብድልአዚዝ የተፈጸመውን ተዳፍኖ የከረመ በደል ያቅርቡልን ፣ ”  ፍትህ ለመሀመድ !” ብለው ይጠይቁን ዘንድ በባንዴራው ብቻ ሳይሆን በልጆችዎ እንማጸንዎታለን ! … ” ብየ መጠቆሜን ወሮ ሙሉካ አስታውሰው በስብሰባው ላይ ጉዳዩ እንዲነሳ ባለማድረጋቸው ባለስልጣኗን ዶር ፈቂ ሆስፒታል 9 አመት ፍትህ ተነፍጎ የተኛውን ብላቴናው መሀመድና እናቱን ማስጎብኘት አልቻሉና እኔ ብቻ ሳልሆን ብዙዎች አዝነናል ።
አረቦች ብረትና “ምንቴስን” “ሲግል ነው መቀጥቀጥ !” እንዲሉ የብላቴናው መሀመድ ጉዳይ  ከሳውዲ አልፎ የአረብ ሀገራትና የአለም መነጋገሪያ እየሆነ ባለበት በዚህ ወሳኝ አጋጣሚ በጅዳ ሴቶች ስብሰባ ላይ ዶር ደስታ ከሳውዲ ባለስልጣናትና የፍትህ አካላት ጋር ተገናኝተው እንዲመክሩ አለመጠየቁና ግፊት አለመደረጉ አዙሮ ላየው የሴቶች ማህበር ወዴት ነህ ? ያስብላል…
በደፈናው ዶር ደሰታ ሹም ስንፈግ መጡ ፣ ባስፈላጊው ቦታ ሳይገኙ ቀሩ  … በላቴናው መሀመድንና በርቱዋን እናት ላይ ግን ጨከኑ…

ማጠቃለያ …
=========
ከዚህ በላይ ለመጠቃቀስ እንደሞከርኩት በሴቶች ማህበር ስብሰባ አንኳር አንኳር የአካባቢያችን ሴቶች ጥያቄ የሆነው የኮንትራት ሰራተኞች አበሳ ጨምሮ የብላቴናው መሀመድን እና የእናቱን ጉዳይ በጥልቅ ውይይት እንዲደረግበት አልተደረገም ።  ዛሬም “ ስብሰባው የእውነት ፡ የሴቶች ማህበር ከተገፉ ሴቶች ወኪል ነው!” እንድንል በተጨባጭ ያየነው እውነት የለምና በሴቶች ማህበር ስም የሚሰራው ሁሉ ያሳስበናል! ትናንትናም ሆነ ዛሬ የምናውቀው የማንቀበለው እውነት አለ ፡ እሱም ስም ይዘው በተደራጁ ማህበራት ብዛት ችግራችን አይፈታም ፡ ችግራችን የሚገፈተው ፡ የሚገፋው ድፍን አንድ አመት ሙሉ እየተቀያየሩ እየሄዱ በሚመለሱት ጉምቱ ባለስልጣናት ሳይሆን በእኛ በችግር ቀማሽ ስደተኞች ትብብር መሆኑን ልብ ይሏል !
ቸር ያሰማን  !

ነቢዩ ሲራክ
ነሃሴ 2015 ዓም

የመሐል ሀገር ሰው መልዕክት ለትግራይ ሰው! (በፍቃዱ ኃይሉ)

$
0
0

በፍቃዱ ኃይሉ
ትግራይ የኢትዮጵያ ገናና ታሪክ መሬቷ ላይ የተጻፈባት ክልል ናት፡፡ ብዙዎች ‹‹የኢትዮጵያ ራስ ናት›› የሚሉት ለዚህ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ታሪክ ወደኋላ 3000 ዓመት የሚያደርሰው የአክሱም ስልጣኔ አሻራውን ትቶ የሄደው በትግራይ ክልል፣ አክሱም ከተማ ነው፡፡ ከአረቦች ተቀድቷል የሚባለውን የንግስተ ሳባ ታሪክ ‹‹ክብረ ነገስት›› በሚባለው መጽሐፍ ተርጉመው ለዚህ ትውልድ ያኖሩልን የትግራይ ሊቃውንት ናቸው፡፡
ሌላው ቀርቶ ህብረ-ብሄራዊ ቅርስ የሆነንን የሳባ ፊደል ለመላው ኢትዮጵያዊ ያወረሱት የትግራይ ሊቃውንት ናቸው፡፡ ከኢትዮጵያዊነት ቀለሞች አንዱ የሆነው ያሬዳዊው ዜማ የተቀዳው ከትግራይ ምድር ነው፡፡ እነዚህና ሌሎች ያልጠቀስኳቸው እውነታዎች ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚኮራባቸው ናቸው፡፡
ኢትዮጵያዊነት በትግራይና በሌሎችም ህዝቦች አኩሪ ታሪክ፣ ባህልና ስርዓት ተገምዶ የተፈጠረ ማንነት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ነገሥታት በመጡና በሄዱ ቁጥር ለራሳቸው ጥቅም አንዱን ወገን ከጎናቸው በማሰለፍ ሌላውን ወገን ያጠቁ ነበር፡፡ የአሁኑ የሀገራችን ገዢዎችም፣ ይህንን ስልት እየተጠቀሙ በስጋና መንፈስ የተገነባውን ህብረታችንን ሊያፈርሱብን ከጫፍ ደርሰዋል፡፡ የዚህ ጽሁፍ ዓላማ ለዚህ እኩይ ተግባር ትግራዋዮች ተባባሪ እንዳይሆኑ መጠየቅ ነው፡፡
እንደሚታወቀው አምባገነኑን ደርግ ለመጣል በተደረገው ትግል የትግራይ ህዝብ የከፈለው መስዋዕትነት ቀላል አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ደርግን ተክቶ ስልጣን የያዘው ሕወሓት ቃል የገባውን ዴሞክራሲ እና ነጻነት ማምጣት ከብዶታል፡፡ እንዲያውም መልሶ ከደርግ ያልተናነሰ አምባገነን ሊሆን ተቃርቧል፡፡ ይህ አልበቃ ብሎት በትግራይ ህዝብ ስም የጥቂት ግለሰቦችን ጥቅም እያካበተ ነው፡፡ በዚህም የከፋፍለህ ግዛ ስልቱ በትግራይ ህዝብ እና በሌሎቻችን መካከል የቅራኔ ግንብ እየገነባ ነው፡፡
እኔ የመሐል ሀገር ሰው ነኝ፡፡ የመሐል ሀገር ሰው በሕወሓት ከፋፍለህ ግዛ ስልት ምን ያክል እንደተሸወደ አይቻለሁ፡፡ እኔም የችግሩ ሰለባ ነኝ፡፡ የመሐል ሀገር ሰው ትግራዋይ ሁሉ የሕወሓት አባል ይመስለዋል ቢባል የተጋነነ ውሸት አይደለም፡፡ የፖለቲካ ቅሬታ ያለው የመሐል ሀገር ሰው ትግራዋዮች ፊት ችግሩን አያወራም፡፡ ሁሉም አንድ ናቸው ብሎ ይፈራል፡፡ ታዲያ በዚህ የመሐል ሀገር ሰው ሊወቀስ አይገባም፡፡ ምክንያቱም የሕወሓት ፖሮፖጋንዳ ሰለባ አድርጎታል፡፡ ሕወሓት ራሱን የትግራይ ሕዝብ ወኪል አስመስሎ ያቀርባል፡፡ በደል እና ጭቆና የበዛበት የመሐል ሀገር ሕዝብ፣ ሕወሓት የጨቆነው የትግራይ ህዝብ የጨቆነው ይመስለዋል፡፡
በዚህ ጉዳይ ከብዙ የትግራይ ልጆች ጋር ካወራሁ በኋላ ሌላ ነገር ተገለጸልኝ፡፡ ለካስ ትንሽ የማይባሉ የትግራይ ልጆቹ የመሐል ሀገር ሰው ይጠላናል ብለው ያስባሉ፡፡ የመሐል ሀገር ሰው በሕወሓት እና በትግራይ ሕዝብ መሐል ያለውን ልዩነት መረዳት ባለመቻሉ፣ የትግራይ ሰው በፍራቻ ከሕወሓት ሌላ አማራጭ እንዳይዝ አድርጎታል፡፡ ሕወሓት የጨቋኞች ቡድን ነው፡፡ አንድ ጨቋኝ ቡድን ደግሞ እየመረጠ አይበድልም፡፡ ለስልጣኑ እና ለጥቅሙ ያልተመቸውን ሁሉ ይበድላል፡፡ ስለዚህ የህወሓት ጨቋኝነት ለትግራይ ሕዝብም የሚቀር አይደለም፡፡ እኔ (የመሐል ሀገር ሰው) የትግራይ ህዝብ ከህወሓት የተባበረ የሚመስለኝ በስርዓቱ ተጠቃሚ ስለሆነ ይመስለኝ ነበር፡፡ ተሳስቻለሁ፡፡ ለካስ የእኛ ጥርጣሬ የፈጠረው ፍራቻ ነው፡፡
ከትግራይ ልጆች ጋር በግልጽ ስንነጋገር የተረዳሁት ይህንን ነው፡፡ የትግራይ ሰዎች ሕወሓትን የሚመርጡ የሚመስሉት ሌላ የሚያምኑት ባለማግኘታቸው ነው፡፡ እርግጥ ነው፣ ጭቆናም ሆነ ነጻነት ለአንዱ ተሰጥቶ ለሌላው የሚነፈግ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ሁላችንም በህብረት የምንኖርባት ሀገር እስከሆነች ድረስ፣ የትግራይ ህዝብ ነጻ ወጥቶ ሌላው ሳይወጣ አይቀርም፡፡ ሌላው እየተጨቆነ ከሆነ ደግሞ የትግራይም ህዝብ እየተጨቆነ ነው ማለት ነው፡፡ እንደተረዳሁት ግን፣ ይህንን ሐቅ የሕወሓት ፕሮፖጋንዳ ሸፍኖታል፡፡
ልክ የመሐል ሀገር ሰዎች የትግራይ ሰዎችን ሁሉ በሕወሓት አባልነትና ደጋፊነት እንደሚጠረጥሯቸውና እንደሚፈሯቸው ሁሉ፣ የትግራይ ሰዎችም የመሐል ሀገር ሰዎች ከህወሓት ጋር ቀይጠው ያጠቁናል ብለው ይጠረጥራሉ፤ ወይም ይፈራሉ፡፡ ይህ በመካከላችን ትልቅ የፍርሃት ግድግዳ ፈጥሯል፡፡ ግድግዳውን በመተማመን ማፍረስ ደግሞ የእኔና የእናንተ ኃላፊነት ነው፡፡
ጋዜጠኛ ዮናስ በላይ ሽፍቶቹ፣ ወያኔዎች እና የትግራይ ህዝብ የተለያዩ ናቸው ይላል፡፡ ወያኔዎቹ የነጻነት ታጋዮች ናቸው፡፡ ሽፍቶቹ ደግሞ በነጻነት ታጋዮቹ ስም የሚነግዱት የአሁኖቹ ጨቋኞች (ሕወሓቶች) ናቸው፡፡ ዮናስ በላይ የትግራይ ህዝብ የሽፍቶቹ ተባባሪ እንዳልሆነ የጻፈውን ከልቤ ተቀብየዋለሁ፡፡ የትግራይ ህዝብ የሽፍቶቹ ተባባሪ ካልሆነ አሁን ብዙዎቻችን እያደረግን ያለነውን የነጻነትና የዴሞክራሲ ጥረት (ትግል) ይቀላቀላል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በእርግጥም ብዙ ትግራዋይ የነጻነት ታጋዮች ዛሬም አሉ፡፡ ነገር ግን ትግላቸው ከመሐል፣ ከምዕራብ፣ ከምስራቅና ደቡብ ሀገር ሰዎች ጋር መቀናጀት አልቻለም፡፡
እዚህ ጋር ከብዙ በእስር ከሚሰቃዩ የትግራይ ልጆች መሀከል አብርሃ ደስታን መጥቀስ ይኖርብኛል፡፡ አብርሃ የትም ቦታ የሚደረግ ጭቆና ይሰማኛል ብሎ የሚታገል ታጋይ፣ ምሁርና ምክንያታዊ የሐውዜን ልጅ ነው፡፡ አብርሃ ከማንም በላይ በትግራይ እና በመሐል ሀገር ሰው መካከል ያለውን አለመተማመን የሰበረ ሰው ነው፡፡ አብርሃ በኃይለኛ ብዕሩ ሕወሓትን ሲተች የተመለከቱ የመሐል ሀገር ሰዎች ‹‹ለካስ ትግራዋዮችም ህወሓትን ይቃወማሉ›› አስብሏቸዋል፡፡ ይህንን ሰው ግን ለነጻነት ታግያለሁ የሚለው ሕወሓት በመቃወሙ አስሮታል፡፡ አሁን በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጠያቂ ተከልክሎ፣ በጥብቅ ክትትል እንደወንጀለኛ ታስሯል፡፡ በትግራይ ልጆች መስዋዕትነት ስልጣን ላይ የወጣው ሕወሓት በስልጣኑ ከመጡበት ለትግራይ ልጆችም እንደማይመለስ አብርሃ ደስታ ማሳያ ነው፡፡
ሕወሓት በትግራይ ስም እየነገደ ነው፡፡ የትግራይ ሕዝብ በህወሓት ስም መልካም ገጽታው እየጎደፈ ነው፡፡ ይህ ግን መቀጠል የሌለበት ታሪክ ነው፡፡ የትግራይ ህዝብ፣ በተለይ የትግራይ ወጣቶች ይህንን ታሪክ ከሌላው ሕዝብ ጎን ቆመው ማስቆም አለባቸው፡፡ የትግራይ ህዝብ ለጭቆና እምቢ ባይነት ሕወሓት በሚል ስም ራሳቸውን ለሚጠሩት ሽፍቶችም መዋል አለበት፡፡ ኑ! እምቢ አልጨቆንም እንበል፡፡

የዑም ኩልሡም ሙዚየም እና የጥላሁን ገሠሠ አልባሳት ዕጣ

$
0
0

Tilahun Legend
ከዘከሪያ መሀመድ

ጥላሁን ገሠሠ በሕይወቱ ሳለ ያደንቃቸው ከነበሩ ታላላቅ ድምጻውያን መካከል፣ የዓረቡ ዓለም ድምጻውያን ንግሥት የምትሰኘው ዑም ኩልሡም አንዷ ነበረች፡፡

ዑም ኩልሡም እ.አ.አ. ሜይ 4, 1904 ገደማ ግብፅ ውስጥ ቱማይ አል-ዘሃይራህ በሚባል አውራጃ ተወልዳ፣ ፌብሯሪ 3፣ 1975 ከዚህ ዓለም ተለይታለች፡፡ ሥርዓተ ቀብሯም ከአንድ ሚሊዮን የማያንስ ሕዝብ በተገኘበት ካይሮ ውስጥ ተፈጽሟል፡፡ እ.አ.አ. በ2001 የግብጽ መንግሥት ለዑም ኩልሱም ‹‹ከውከብ አል-ሸርቅ›› (“የንጋት ኮከብ” ማለት ይመስለኛል) እየተባለ የሚጠራ በተለይ ዑም ኩልሱምን የሚዘክር ሙዚየም ያቋቋመላት ሲኾን፣ በዛማሊክ ሐውልት ቆሞላታል፡፡ የዑም ኩልሱም አልባሳት፣ እንዲሁም በኋለኛ ዕድሜዋ መድረክ ላይ ሳይቀር ታደርገው የነበረው መነጽሯን ጨምሮ በርካታ የግል መጠቀሚያዎቿ በስሟ በተሰየመው ሙዚየም በቋሚነት ለዕይታ በቅተዋል፡፡ …

እንደ ጥላሁን ሁሉ፣ ዑም ኩልሡም ለግማሽ ምዕተ ዓመት ያህል የዐረቡን ዓለም በዜማዎቿ እየመሰጠች ኖራለች፤ ዛሬም በተመስጦ ትደመጣለች [ከነምስሏ በመድረክ ላይ ስትዘፍን ማየት የፈለገ፣ “ሩታና ክላሲክ” ጣቢያ ላይ ያገኛታል፡፡] ዑም ኩልሡም በዓረቡ ዓለም እጅግ ተወዳጅ የነበረችውን ያህል፣ አድናቂዋ ጥላሁን ገሠሠ በእኛ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት ነበረው፡፡ በሀገራችን ዘመናዊ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ በግንባር ቀደምነት የሚጠቀሰው ጥላሁን ገሠሠ፣ አንድ ቀን በአዲስ አበባ ከተማ ኃውልት እንደሚቆምለት ተስፋ ማድረግ እንችላለን፡፡ አልባሳቶቹ እና አንዳንድ የግል መጠቀሚያዎቹ በስሙ በሚሰየም ሙዝየም የመቀመጣቸው ነገር ግን ያጠራጥራል፡፡ ይህን የሚያስብለን ሰሞኑን የተወሰኑ የጥላሁን አልባሳት ለመቄዶንያ የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማኅበር መሰጠታቸውን መስማታችን ነው፡፡

የጥላሁን አልባሳት ለመቄዶንያ የተለገሱት ለምን ዓላማ እንዲውሉ ታልሞ እንደሆነ አላወቅሁም፡፡ እንደኔ እንደኔ፣ የመቄዶንያ መሥራች የታላቁ ድምጻዊ አልባሳት ትልቅ ታሪካዊ ዋጋ ያላቸው መሆኑን በመገንዘብ፣ ለበጎ አድራጎት ተቋማቸው ቋሚ ገቢ ሊያስገኝ በሚያስችል መልኩ ቢጠቀሙበት መልካም ነው፡፡ የአዲስ አበባ መስተዳድር በሰጣቸው ሰፊ መሬት ላይ ለሚገነቡት ግዙፍ የአዕምሮ ህሙማን መንከባከቢያ ማዕከል ግንባታ የሚውል ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የሚያስፈልጋቸው የድርጅቱ መሥራች የጥላሁንን አልባሳት ለጎብኝዎች በሚመች መልኩ በማስቀመጥ፣ ለጥላሁን ገሠሠ ሙዝየም መሠረት የሚጥሉበትን አንድ ርምጃ ቢራመዱ ጥሩ ይመስለኛል፡፡ እርሳቸው አንድ ርምጃ ሲራመዱ፣ ሙዝየሙን ለማጠናከር ሕዝብ የየድርሻውን አስተዋጽኦ ማድረግ ይጀምራል፡፡ ማን ያውቃል የተቀሩት የጥላሁን ገሠሠ አልባሳትም ወደ ‹‹መቄዶንያ የጥላሁን ገሠሠ ሙዝየም›› ይመጡ ይሆናል፡፡

ለማንኛውም፣ በአዲስ አበባ ‹‹የጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሙዝየም›› ተቋቁሞ እስክናይ ድረስ፣ ካይሮ የሚገኘውን የዑም ኩልሡም ሙዝየም ከፊል ገጽታ በፎቶግራፍ እንጎብኝ፡፡ …
tilahun

Tilahun 2

Tilahun 4

Tilahun 5

tilahun 6

መቻቻል (ከፍቅሬቶሎሳ፥ ፕሮፌሰር ኦፍ ሁማኒቲስ)

$
0
0
(ፍቅሬ ቶሎሳ፥ ፒ ኤች ዲ – የሁማኒቲስ ፕሮፌሰር)

(ፍቅሬ ቶሎሳ፥ ፒ ኤች ዲ – የሁማኒቲስ ፕሮፌሰር)

ውድ አንባብያን ሆይ፥ እኛ ኢትዮጵያውያን በትንሽሁም እንኩዋን ቢሆን መቻቻል ስለሌለን ወዳጅን ከጠላት መለየት እያቃተን ራሳችንን ብዙ ጎድተናል። የአገራችን ዕጣ ብሩህ ይሆን ዘንድ ለአንድ አላማ የቆምን ሰዎች ሁሉ እንድንቻቻል ግድ ይላል። አልዛ በጥፋት ላይ ጥፋት ይጨምራል። ይህን ገጥም የደረስኩት የዛሬ 32 ዐመት ቢሆንም አሁንም ወቅታዊ ነው። ወደፊትም ይሆናል።

[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

ለ3ኛ ጊዜ በመንግስት ቤቱ የፈረሰበት ወጣት ራሱን አጠፋ

$
0
0

‹‹የሳምንት አራስ ጎዳና ላይ ወድቃለች››

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

imagesበወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ መርካቶ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ጎላ መንደር ‹‹ህገ ወጥ የቤት ግንባታ›› በሚል በመንግስት ለሶስተኛ ጊዜ ቤቱ የፈረሰበት ወጣት ታምራት ታንቱ ባሳ ራሱን ማጥፋቱን ምንጮች ከሶዶ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ወጣት ታምራት ታንቱ ባሳ በዚህ መንደር ረዘም ላለ ጊዜ እንደኖረ የገለፁት ምንጮች ለሶስተኛ ጊዜ ‹‹ህገ ወጥ ግንባታ ነው›› ብለው እንዳፈረሱበት አቶ ታደመ ፈቃዱ የተባሉ የሶዶ ነዋሪ ለነገረ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

በተደጋጋሚ ቤቱ በመንግስት የፈረሰበት ታምራት ታንቱ ‹‹በዚህ ሁኔታ እንዴት ብዬ እኖራለሁ?›› ብሎ ራሱን ያጠፋው ነሃሴ 24/2007 ዓ.ም ሲሆን በትናንትናው ዕለት የቀብር ስነ ስርዓቱ እንደተፈፀመም አቶ አበራ የተባሉ የከተማው ነዋሪ ገልጸውልናል፡፡

በሶዶ ከተማ ህገ ወጥ ናቸው ተብለው ከ500 በላይ ቤቶች መፍረሳቸውን የገለፁት የአካባቢው ነዋሪዎቹ አብዛኛዎቹ ከአምስት አመት እስከ ዘጠኝ አመት በአካባቢው ኖረውበታል ብለዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ነዋሪዎች ለከፋ ችግር እንደተጋለጡ የተነገረ ሲሆን ሚሚ ባቴ የተባለች የሳምንት አራስም ቤቷ ስለፈረሰባት ጎዳና ላይ ወድቃለች ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ትናንት ነሃሴ 25/2007 ዓ.ም ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ አምስት ሰዓት በሶዶ ከተማ ቅዳሜ ገበያ በሚባለው የገበያ ማዕከል ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ በርካታ የንግድ ቤቶች መውደማቸውን የሶዶ ከተማ ነዋሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡


14ኛው የኢትዮጵያ ቀን በዓል ክብረ በዓል በዳላስ ቴክሳስ – (ፍላየር)

$
0
0

በየዓመቱ በዳላስ ቴክሳስ የሚከበረው የኢትዮጵያውያን ቀን ዘንድሮም ሴፕቴምበር 5 እና 6 2015 ዓ.ም ይካሄዳል:: በዚህ በዓል ላይ በክብር እንግድነት አርቲስት ደበበ እሸቱ; ዓለምጸሃይ ወዳጆና ሌሎችም የሚገኙ ሲሆን ሕዝቡን ለማዝናናትም ክበበው ገዳ; መስከረም በቀለ; ት ዕግስት ንጋቱ ይገኛሉ:: በሌላ በኩልም የዚህ ትልቅ በዓል አካል አርቲስት ብርሃኑ ተዘራ ነው:: ፍላየሩን ይመልከቱ::
dallas ethiopia

2000 East Spring Creek Parkway, Plano TX 76076
Date: September 5 and 6, 2015 (Saturday & Sunday)
For more information visit the website:
http://maaecdallas.org/ethiopian-day-2015/
Telephone: 214-321-9992
Entrance: $20.00
The entrance for children under 13 years old is free.

የህወሀት የጥላቻ መርከብ በኢትዮጵያ እየሰመጠ ነው?

$
0
0

TPLF

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

የህወሀት የጥላቻ መርከብ በፍርሀት እና በጥልቅ የጥላቻ ውቅያኖስ ውስጥ ሰምጧልን?
እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ እያለ የሚጠራው ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ገዥው ወንጀለኛ ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ በማጭበርበር እራሱን መንግስት አስመስሎ ሆኖም ግን ትክክለኛ የመንግስት ባህሪያትን በምንም ዓይነት መልኩ ሳይላበስ እስከ አሁን ድረስ በመግዛት ላይ ይገኛል፡፡
በዚህ ባለፈው ግንቦት ወር ተካሄደ በተባለው የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ይፋ በሆነ መልኩ 90 የፖለቲካ ፓርቲዎች ተመዝግበው በሚንቀሳቀሱበት የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ለዝንጀሮ/ጦጣው የይስሙላ ፓርላማ ከተያዙት 547 መቀመጫዎች ውስጥ እንደ ቀድሞው ለይስሙላ አንድ እንኳ መቀመጫ ለሌላ የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅት ሳያቃምስ 547ቱንም መቀመጫዎች መቶ በመቶ ድል አሸነፍኩ ብሎ አለሃፍረት አወጀ፡፡

ሆኖም ግን ባለፈው ሳምንት የህወሀት የይስሙላ (አሻንጉሊት) ጠቅላይ ሚኒስትር የሆነው ኃይለማርያም ደሳለኝ ሁሉንም መቀመጫዎች መቶ በመቶ እንዳሸነፈ ሳይሆን እንደተሸነፈ ቅስሙ የተሰበረ አነጋገር አድርጎ ነበር።
ኃይለማርያም እርዳታ እንዲደረግለት የመማጸን እና የመጮህ እንደምታ ያለው ስብዕናን በመከናነብ ይናገር ነበር፡፡
በእውነት ኃይለማርያም በስሜታዊነት መንፈስ ውስጥ በመዘፈቅ “መርከባችንን ልትሰምጥ ነው አድኑን” የሚል መልዕክት የሚያስተላልፍ መስሎ ታይቷል፡፡

…_ _ _… (በሞርስ ኮድ ማለት )

ኃይለማርያም ከየት እንደመጣ በማይታወቅ መልኩ የጦርነት መጥረቢያውን ከፍ አድርጎ በመያዝ በስሜታዊነት ከወዲያ ወዲህ እየተቅበዘበዘ በጎሰኝነት፣ ቡድናዊነት፣ የኃይማኖት ጽንፈኝነት፣ የጎሳ ትምክህተኝነት፣ የጎሳ ክፍፍል፣ የእራስን ባህል ከሌሎች ብሄረሰቦች አስበልጦ በማየት፣ በእብሪት እና የጠባብነት አመለካከት ስሜት ላይ በመዝመት ድንፋታውን ሲያሰማ ተስተውሏል፡፡
በአጭሩ በእራሱ ጥላሞት ላይ ገጀራ በመያዝ ጥላሞቱን ቆርጦ ለመጣል እንደሚንቀሳቀስ የለየለት እብድ መስሎ ታይቷል፡፡
የኃይለማርያም ህወሀት በጎሰኝነት፣ ቡድናዊነት፣ የኃይማኖት ጽንፈኝነት እና በሌሎች ለሩብ ምዕተ ዓመት ድረስ በፖለቲካ ፕሮግራሙ ውስጥ በማስገባት እራሱን በስልጣን እርካብ ላይ ለማቆየት ከፍተኛ ቅስቀሳ እና የፕሮፓጋንዳ ስራ እየሰራ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ኃይለማርያም በእነዚህ እኩይ ምግባሮች ማለትም በጎሰኝነት፣ በቡድናዊነት፣ በኃይማኖት ጽንፈኝነት ላይ እና በሌሎችም የሀሰት ውንጀላ ክስ እንዲያሰማ እርሱን አስቀምጠውታል፡፡

ስለጎሰኝነት፣ ቡድናዊነት እና የኃይማኖት ጽንፈኝነት ሰይጣናዊነት የኃይለማርያምን ድንፋታ ስሰማ “የቬኑሱ ነጋዴ“ በሚል ርዕስ በሸክስፒር የተጻፈው እና እንዲህ የሚለው አባባል ትዝ አለኝ፡:

“ሰይጣን ለእራሱ እኩይ ምግባር ማስፈጸሚያ ሲል ከመጽሐፍ ቅዱስ ይጠቅሳል/ሰይጣናዊ የሆነች ነብስ የቅዱስነትም ምስክርነት ትሰጣለች የሚለው አባባል ከሚስቁ የሰይጣን ጉንጮች ጋር እኩል የመሆን ያህል ነው፣ በጣም የሚስበው እና የሚያስጎመጀው የትርንጎ ፍራፍሬ መሀሉ በስብሷል ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ እናም ከለየለት ቅጥፈት በላይ ምን የሚስብ ነገር ሊኖር ይችላል!” (ጅራፍ ራሷ ገርፋ ራሷ ትጮሃለች አነደሚሉት።)

TPLF 1ኃይለማርያም ለብሄራዊ አንድነት፣ ለፍቅር፣ ለጋራ መግባባት እና ዕርቀ ሰላም ለማውረድ እንዲህ በማለት እራሱን እንደ ቅዱስ ምስክር ሰጭ አድርጎ አቀረበ። ያስቃል ያስገረማል ።

“ስለኪራይ ሰብሳቢነት [በዘይቤ አነጋገር ሙሰኞች] የተለያዩ አመለካከቶች አሉ፡፡ የመጀመሪያው ጠባብነት ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ እብሪተኝነት ነው፡፡ ሶሰተኛው የኃይማኖት ጽንፈኝነት ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች ሀገራችንን የሚበታትኑ እና የሚያጠፉ ስለመሆናቸው አምነን ከስምምነት ላይ መድረስ መቻል አለብን፡፡ እንደዚህ ያሉ የአውዳሚ ዘሮች አስተሳሰብን መዝራት መሰረቱ መምህራን ናቸው፡፡ እነዚህ አስተሳሰቦች በተማሪዎች ቀልብ ላይ ያርፋሉ፣ እናም ግጭቶች እና ጦርነቶች እንዲከሰቱ ያደርጋሉ፣ ሆኖም ግን ዘሩ የተዘራው ከላይ ከቆንጮው ነው” አለ ኃይለማርያም ።
ኃይለማርያም ስለኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት መጠበቅ፣ ስለማንነት እና ስለኃይማኖት መቻቻል የቅዱስነት ምስክርነትን መስጠት መቻል ማለት ለእራሱ እኩይ ምግባሮች ሲል ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በመጥቀስ ከሚሰብከው ፈጣጣ ሰይጣን ጋር መሳ ለመሳ ነው፡፡

ቅዱስ _ _ _ ! ድንቄም ቅዱስ!

በዓለም ላይ ከሚደረጉ ነገሮች ሁሉ በኢፍትሀዊነታቸው ምክንያት ብስጭት ይዞት ኃይለማርያም ካደረጋቸው የእዩልኝ እመኑልኝ ንግግሮች እውነታዊ ነገሮች ሁሉ ምን የቀረ ነገር አለ?
ኃይለማርያም የእዩልኝ እመኑልኝ ንግግሮች እውነታዊ ነገሮች በማለት በአፋ ላይ በማድረግ የሀሰት የቅሌት ሸፍጡን እየዘራ ያለው ለምንድነው?
ኃይለማርያም ከወያኔ ኃይለኛ ምት እና የመርከብ የአቅጣጫ መጠቆሚያ መሳሪያው/ራዳር ጠፍቶበት ከአደጋ አድኑኝ፣ ነብሴን ከመከራ ታደጓት እያለ ጠቋሚ ምልክቶችን በመጠቀም የክላዊ ጎሰኝነትን ማቆሚያ በሌለው መልኩ (እንደ 21ኛው ክፍለ ዘመን የደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ ዓይነት ባንቱስታን) የበረዶ ክምሩን በኃይል ለመምታት እና ለመደረማመስ ጥረት እያደረገ ነውን?
የኃይለማርያም የአድኑኝ ዋይታ እና ጩኸት ላለፉት ሩብ ምዕተ ዓመታት ያህል የደደቢቱ (ደደብ አላልኩም) የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የፍርኃት እና የጥላቻ መርከብ ቀስ በቀስ እየሰመጠ እና እየዘቀጠ ወደ ጥልቁ እና የመጨረሻ ወደሆነው የውቅያኖስ ክፍል በመሄዱ ምክንያት ነውን?

ኃይለማርያም የወያኔን የትዕዛዝ መስጫ የመለስ ዜናዊን መርከብ መስመጥ እየተመለከተ አድኑኝ የሚል እገዛን ለማግኘት ፈጣን የተስፋ መቁረጥ መልዕክት እያስተላለፈ ሊሆን ይችላልን? በርካታ የመርከቡ ነጅ ካፒቴኖች በደቦ ሆነው እየተተራመሱ የመለስ ዜናዊን የጥፋት መርከብ ወደ ጥልቁ እና የመጨረሻ ወደሆነው የውቅያኖሱ ክፍል እየነዱት በማስመጥ ላይ ናቸውን?
ኃይለማርያም በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ውስጣዊ የቡድን ሽኩቻ ላይ የበላይነቱን ለመቀዳጀት እንዲመቸው በማሰብ ብልህነትን በተላበሰ መልኩ ብሄራዊ አንድነት እና ኢትዮጵያዊነት በማለት ጩኸቱን ከፍ አድርጎ በማሰማት የህዝቡን ቀልብ ለመሳብ እንዲመቸው ያደረገው ጥረት ሊሆን ይችላልን?

ኃይለማርያም ሀገራዊ የአርበኝነት ስሜት ያለው በማስመሰል እና በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ውስጣዊ የቡድን ሽኩቻ ላይ ድልን ለመቀዳጀት ከፍተኛ የሆነ የህዝብ ድጋፍን ለማግኘት ሲል እያደረገው ያለ ነገር ሊሆን ይችላልን?

ኃለማርያም በወያኔ አለቆቹ አማካይነት አዲስ የተገኘ የጎሳ ስምምነት ኃይማኖት እና ስለኃይማኖት መቻቻል አዲስ ተንሳፋፊ ፊኛ ወደ ህዝብ አየር ላይ በመልቀቅ የሚሰራ እና የማይሰራ መሆኑን ለማረጋገጥ ህዝቡም ምን ዓይነት ምላሽ ሊሰጥ እንደሚችል ለማወቅ የተሰጠው የቤት ስራ እና የተነገረው ምክር ነበርን?

በእርግጠኝነት ኃይለማርያም ከወያኔ የመነጋገሪያ ነጥቦች መጽሐፍ ውስጥ በመውሰድ ነበር ንግግር እያሰማ የነበረው? (ኃይለማርያም የወያኔ የህዝብ ግንኙነት አገልጋይ ሎሌ እንደሆነ ማንም ያውቃል፡፡ እርሱ በደመወዝ ከፋይ የወያኔ አለቆቹ እንዲያደርግ ካልተነገረው በስተቀር በእራሱ ስብዕና ድፍረት ኖሮት እንደዚህ ያሉ ንግግሮችን ለማድረግ የሚችል አይሆንም፡፡)
ኃይለማርያም አመልካች ጣቱን ወደ “የጠባብነት ስሜት አራማጆች” በመቀሰር ሲጠቁም ሶስት ጣቶች አሱ ላይ አንደሚጦቁሙ ለማየት አልቻለም፡፡

ኃይለማርያም የጠባብ ስሜት፣ የጥላቻ አራማጆች እና ጦር ናፋቂዎች የሚላቸው የትኞቹን የህብረተሰብ ክፍሎች ነው?
ኃይለማርያም ኢትዮጵያን ለማጥፋት ደባ እየሸረቡ እና እየዶለቱ ያላቸውን የጠባብ ጎሰኝነት ስሜት አራማጆች እና በጥላቻ የተሞሉ ጦር ናፋቂዎች እያለ ስለተናገራቸው ሰዎች ስም ዝርዝር ምንም የተናገረው ነገር የለም፡፡

HaileMariam
ሆኖም ግን የጠባብ ጎሰኝነት አራማጆች መለያ ልዩ ባህሪያት ምንድን ናቸው?
አለመቻቻል ማለት ነውን? የጠባብነት አስተሳሰብ ማለት ነውን? በጥላቻ መሞላት ማለት ነውን? ትዕግስትየለሽነት መሆን ማለት ነውን? ድንቁርና ማለት ነውን? መንደርተኝነት ማለት ነውን? አዲስ ሀሳብ የማያመነጩ ማለት ነውን? ጠባብ ጎጠኝነት ማለት ነውን?
ይህንን ጉዳይ እንዲህ በማለት እውነታውን እንደ እምቧይ ፍርጥ በማድረግ ፊት ለፊት እንጋፈጥ፡ ምድር ተብላ በምትጠራው ፕላኔት ላይ ከወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች እና አባላት የበለጠ የጠባብ ጎጠኝነት አራማጅ ሰው ይኖራልን?
የጠባብ ጎጠኝነት አስተሳሰብ ተቃራኒው ግልጽ አስተሳሰብ ያለው እና ከጠባብነት የአስተሳሰብ ስሜት ነጻ የሆነ ማለት ነው፡፡
ግልጽ አስተሳሰብ ያለው እና ከጠባብነት ስሜት ነጻ የሆነ ሰው አዕምሮው ለአዳዲስ ሀሳቦች እና ጥያቄዎች እራሱንም/ሷንም ጨምሮ/ጨምራ ባካተተ መልኩ ክፍት ነው፡፡

ከጠባብነት ስሜት ነጻ የሆነ እና ግልጽ አስተሳሰብ ያለው ሰው ሁልጊዜ ሰዎችን ለማዳመጥ ፈቃደኛ ነው፣ እናም ግልጽ በሆነ መልኩ በተለያዩ እና ተጻራሪ በሆኑ አስተሳሰቦች ላይ በግልጽ ወይይት እና ክርክር ያደርጋል፡፡
ከጠባብነት ስሜት ነጻ የሆነ እና ግልጽ አስተሳሰብ ያለው ሰው ስህተት ሊሰራ/ልትሰራ እንደሚችል/ምትችል አምነው ይቀበላሉ፣ እናም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እራሳቸውን ለማረም ፈቃደኞች ናቸው፡፡

ከጠባብነት ነጻ የሆነ እና ግልጽ አስተሳሰብ በማራመድ ላይ ያለ ሰው ማንም የፈለገውን ቢያስብ እውነቱን ይናገራል፡፡
እንዲያው ለመሆኑ ከጠባብነት አስተሳሰብ ነጻ የሆነ እና ግልጽ አስተሳሰብን የሚያራምድ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራር ወይም ደግሞ አባል በባትሪ ተፈልጎ ይገኛልን?

ዳዮግነስ ሲኖፔ (የግሪክ ፈላስፋ እና የሳይኒክ [የፍልስፍናው መርህ ተከታዮች የሕይወት ዓላማ በክብር ለመኖር ነው የሚል ሀሳብን የሚያራምዱ]) ፍልስፍናን ከመሰረቱት ሰዎች መካከል አንዱ የነበሩት በቀን ብርሀን በከተማ ውስጥ የበራ ፋኖስ በእጃቸው በመያዝ ጉዞ ማድረግ ጀመሩ፡፡ እንደዚህ ያለ አዲስ የሆነ ነገር ለምን እያደረጉ እንዳሉ ሲጠየቁ እንዲህ የሚል መልስ ሰጡ፣ “እኔ በእርግጥ በዚህ የፋኖስ ብርሀን እውነተኛ ሰው ለማግኘት እየፈለግሁ ነው፡፡“ ዳዮግነስ በእርሳቸው የፍለጋ ጥረት መሰረት አንድም እውነተኛ ሰው ያላገኙ ሲሆን ይልቁንም በተቃራኒው ታማኝነት የሌለው አታላይ እና ክበርየለሽ መርህ አልባ የሆኑ ሰዎችን ነው ማግኘት የቻሉት፡፡

ማንም ቢሆን በኢትዮጵያ በአውራ መንገዶች እና በጠባብ የህዝብ እና የትራፊክ መንቀሳቀሻ መንገዶች ላይ ቢጓዝ፣ ወደ ከፍተኛው ተራራ ቢወጣ እና ሸለቆዎችን ሁሉ በሞተር በመንቀሳቀስ ቢያቋርጥ እና ፓውዛ መብራት ይዞ ቢፈልግ ከወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራር ወይም አባላት ውስጥ አንድም ነጻ አስተሳሰብ ያለው እና ግልጽ ሀሳብን የሚያራምድ ሰው በፍጹም አይገኝም፡፡ ይልቁንም በጠባብ የአስተሳሰብ ስሜት እና በጎጠኝነት በሽታ ተለክፈው የሚገኙ እምነተ ቢስ አታላዮች እና ቅሌታሞች ክብርየለሽ መርህ አልባ ስብስቦች ብቻ ናቸው የሚገኙት፡፡
በተገላቢጦሽ አሳዛኙ ነገር ኃይለማርያም አመልካች ጣቱን ስም በሌላቸው የጠባብ ስሜት አራማጆች ላይ እንደቀሰረው ሁሉ ሌሎቹ ሶስቱ ጣቶቹ ደግሞ ወደ እራሱ የሚያመለክቱ መሆናቸውን መገንዘብ ይኖርበታል፡፡
ኃይለማርያም “ግጭት የሚፈጥሩትን እና ጦርነት ናፋቂ“ እብሪተኞችን ከሷል፡፡
ለመሆኑ በኢትዮጵያ የጥላቻን እና የጦርነት ናፋቂነት እኩይ ምግባራት እንዲከሰቱ ደባ የሚሸርብ እና ጎሰኝነትን ለማስፋፋት፣ የኃይማኖት ጽንፈኝነትን፣ ቡድናዊነትን፣ ወዘተ እያስፋፋ ያለ እብሪተኛ ማን ነው?
ከዚህ አንጻር ኃይለማርያም አንድም በስም የጠቀሰው ሰው የለም፡፡
ሆኖም ግን ክብርም አለ እናም እብሪትም እንደዚሁ አለ፡፡
ኃይለማርያም እና የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አለቆቹ በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት ይገነዘቡታል ብየ አላስብም፡፡
አንድ ሰው ስለእራሱ/ሷ መልካም ነገር ሲያስብ ወይም ስታስብ፣ ወይም ደግ ነገርን ለመስራት ሲያስብ/ስታስብ በእራስ መተማመን ይፈጠራል፣ እናም ከአታላይነት፣ ከአስመሳይነት፣ በሁለት ቢላዋ ከመቁረጥ፣ ወዘተ ነጻ በመሆን ክብር ያለው የኑሮ ዘይቤ መኖር በመሞከር ትክክለኛ ክብር ያለው ኑሮ ይኖራል/ትኖራለች፡፡
እብሪተኝነት የአስመሳይነት ክብር ነው፡፡ እብሪት በእራስ ወዳድነት ማዕከልነት የሚነዳ እና እራሱን በጠብ ኣጫሪ ኃይለኝነት፣ በጥርጣሬ እና በእምነተቢስነት የሚገልጽ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ክብርን የመውደድ የእብሪተኝነት መገለጫ ነው፡፡ እብሪተኛ ሰው ሁልጊዜ የበታችነት ስሜት ስቃይ ውስጥ ገብቶ የመዳከር ስሜት ይሰማዋል፣ እንደዚሁም ደግሞ የብቃት የለሽነት እና ለእራሱ እርባና የሌለው ከንቱ ፍጡር የመሆን ስሜት ይሰማዋል፡፡
እንደገና ደግሞ ከጥሬ ሀቆች ጋር አንድ ጊዜ እስቲ እንዲህ በማለት እንጋፈጥ፡ ማንም ሰው ቢሆን በዚህች ምድር ፕላኔት ላይ ከወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራር ወይም አባላት የበለጠ ነጻ አስተሳሰብ የሌለው እና ግልጽ ሀሳብን የማያራምድ እብሪተኛ ሰው ሊኖር ይችላልን?
ለበታችነት ስሜት አስተሳሰባቸው፣ ለብቃት የለሽነታቸው እና የእራስን እርባናቢስነት ማካካሻ ለማድረግ በማሰብ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች እና የእነርሱ አገልጋይ ሎሌዎቻቸው የአካዳሚክ ክብርን ለመጎናጸፍ የመስቀል ጦርነትን በማራመድ ላይ ይገኛሉ፡፡
በርካታዎቹ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ቁንጮ አመራሮች ከዲፕሎማ መቀፍቀፊያ ወፍጮ ተቋማት ዲግሪ በመግዛት ላይ እንደሚገኙ ሀገር ያወቀው ጸሐይ የሞቀው የማይካድ እውነታ ነው፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የተጭበረበሩ ዲግሪዎችን በመግዛት ምንም ዓይነት የአካዳሚክ ብቃት ሳይኖራቸው የእምነታቸው አራማጅ የሆኑትን ታዛዥ ሎሌዎች እና መንፈሰ ደካማ ሰዎችን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ፕሮፌሰሮች እያሉ ይሾሟቸዋል፡፡ ሀገር ሲያረጅ ጃርት ያፈራል እንዲሉ!
አሁን በህይወት የሌለው እና ትንሹ አምላክ የነበረው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ቀንደኛ አድራጊ ፈጣሪ መሪ መለስ ዜናዊ ከኦፕን ዩኒቨርሲቲ በመመረቅ ዲግሪው ከቤተመንግስቱ ድረስ እንዲመጣለት ዝግጅት አድርጎ ነበር፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች እና ልሂቃን ተብዬዎች በርካታ የዲፕሎማ መቀፍቀፊያ የንግድ ወፍጮዎች አነሱ ባይኖሩ በከሰሩ ነበር።
ለዚህ አባባል ማስገንዘቢያ አንዱ ቀላሉ ነጥብ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች እና ልሂቃን እነርሱ ከሚጨቁኗቸው ከሁሉም ህዝቦች የተሻሉ፣ ማራኪዎች እና የበለጡ ጠቃሚዎች፣ አዋቂዎች እንደሆኑ አድርገው በመቁጠር ዓለም እንዲያረጋግጥላቸው ይፈልጋሉ፡፡ ሆኖም ግን እያንዳንዱ ሰው እንደሚያውቀው እነርሱ ምንም ነገር የሌላቸው እርባናየለሽ ፍጡሮች ናቸው::
የእነዚህ ደናቁርት እብሪት ስለ በፊቱ ያፍሪካ አምባገነኖች ያስታዉሰኛል፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እና አሁን በህይወት የሌለው መሪያቸው ይፋ መጠሪያው “የተከበሩ፣ የእድሜ ልክ ፕሬዚዳንት፣ ፊልድ ማርሻል አልሀጅ፣ ዶ/ር ኢዲ አሚን ዳዳ፣ የኮሙኒስት የሽምቅ ተዋጊ፣ የማሪን/ባህር ወታደር፣ የሁለም በመሬት ላይ የሚገኙ ኃይለኞች እና በውኃ ላይ ለሚገኙ ፍጡራን ሁሉ የበላይ ሀያል አለቃ እና በአፍሪካ የእንግሊዞችን ግዛት በአጠቃላይ እና በዩጋንዳ በተለይ ድል ያደረገውን እና ስም የተባለውን ሁሉ ጠቅልሎ የያዘውን“ ያንን የለየለት እብሪተኛ ኢዲ አሚንን አስታወሰኝ፡፡

መለስ ዜናዊም በተመሳሳይ መልኩ “ታላቁ መሪ፣ ታላቁ ባለራዕዩ፣ የደደቢት ታላቅ ጀግና፣ በመሬት እና በባህር ላይ ለሚገኙ ፍጡራን ለሁሉም ኃይለኞች ሁሉ የበላይ አለቃ እና በደርግ እና በኢትዮጵያ ግዛት እንዲሁም በሁሉም የጎሳ ቡድኖች ላይ ድል አድራጊነትን የተጎናጸፈ፣ ወዘተ፣ ወዘተ፣ ወዘተ…“ የሚሉ ተቀጥያ ስሞችን ጠቅልሎ ይዞ ነበር፡፡
ኃይለማርያም ስማቸው ተለይቶ ባልታወቁ መምህራን እና ፕሮፌሰሮች ላይ አመልካች ጣቱን ቀስሯል፡፡
ለመሆኑ ኃይለማርያም ስለጎሳ ክፍፍል፣ ስለኃይማኖት ጽንፈኝነት እና የጥላቻ እና የጦርነት ነጋሪት የሚጎስሙት ብሎ የወነጀሏቸው እነዚያ በስም ያልጠቀሳቸው መምህራን እና ፕሮፌሰሮች እነማን ናቸው?
ኃይለማርያም የውንጀላ ክስ የመሰረተባቸው የኢትዮጵያ መምህራን እና ፕሮፌሰሮች በጣም ውሱን የሆኑ እና የሚያስፈሩ ናቸው፡፡ ኃይለማርያም በኢትዮጵያ በጣም የተማረው የህብረተሰብ ክፍል አባላት ለሀገሪቱ የፖለቲካ እና የማህበራዊ ችግሮች ዋና ምንጮች ናቸው ይላል፡፡ እነዚህን የህብረተሰብ ከፍሎች ስብዕና ጥላሸት ይቀባል፣ የጥላቻ አራጋቢዎች ብሎ ይፈርጃቸዋል፣ በተለይም ደግሞ ወጣቶቹን፡፡

ባለፉት 24 ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ጥላቻን፣ ጎሰኝነትን፣ የኃይማኖት ጽንፈኝነትን፣ ቡድናዊነትን፣ ወዘተ ያስፋፉ በጣም ደንቆሮዎች እና እምነተ ቢሶቹ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች መሆናቸው እውነታነት የለውምን?
በጣም እየደነቀኝ ያለሁበት ሁኔታ ነው፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሌላ ጅምላ፣ ህዝባዊ ማባረርን በዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ፕሮፌሰሮች ላይ ለመተግበር ሌላ ዙር ዝግጅት እያደረገ ነውን?
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሊገመት የሚችል ሁኔታ አለው፡፡
ወያኔ በግፍ ሰለባዎቹ ላይ እርምጃ ከመውሰዱ በፊት በቅድሚያ ስም የማጠልሸት ስራ መስራት ይጀምራል፡፡
ከዚያም በኋላ የማዋረድ አስነዋሪ ድርጊቱን ይቀጥላል፣ እናም ህዝብ ግብር እየከፈለ በሚያስተዳድራቸው የመገናኛ ብዙሀን የተለመደ ስም የማጥፋት ዕኩይ ምግባሩን ይቀጥላል፡፡
በመቀጠልም እነዚህ የእርሱ የግፍ ሰለባዎች እራሳቸው ኃላፊነቱን እንዲወስዱ ያደርጋል፡፡ ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሀል እንዲሉ፡

ከዚያም በመቀጠል ገራፊ ወሮበሎቹን በማሰማራት በግፍ ሰለባዎቹ ላይ የማስፈራራት እና የማሰሸማቀቅ እኩይ ምግባራትን ይሰራል፡፡
በመቀጠልም እባብ በመስክ ላይ እንዳለች አይጥ መርዙን በመርጨት ለምግቡ እንደሚያደርሳት ሁሉ ይህ እኩይ የማፊያ ስብስብ ድርጅት በሰላማዊ ምሁራን ላይ መርዙን በመርጨት በድንገት በቁጥጥር ስር ያውል እና በሸፍጥ የታጀበ የጸረ ሽብር ክስ እንዲመሰረትባቸው ያደርጋል፡፡
ከዚያም በማጎሪያው እስር ቤት ገብተው በይስሙላው የዝንጀሮ/ጦጣ ፍርድ ቤት የተንዛዛ ቀጠሮ እየተመላለሱ ለዓመታት እንዲማቅቁ ያደርጋል፡፡
በግድግዳው ላይ የተጻፈውን ነገር መምህራን ተጠንቀቁ፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን መስመር የማትከተሉ የኢትዮጵያ መምህራን እና ፕሮፌሰሮች ለመባረር መዘጋጀት ይኖርባችኋል፣ ምክንያቱም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እናንተን ከምታስተምሩበት ቅጥር ግቢ ውስጥ መንጥሮ ለማባረር እና የእራሱን ቤት ለማጽዳት ተዘጋጅቶ መጥቷልና!
ለሌላ ዙር እስራት እና የጸ ሽብር የዱለታ የዝንጀሮ ክስ ዝግጁ ሁኑ!
እ.ኤ.አ በ1993 የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እንደዚህ ያለ ተመሳሳይ ድርጊትን ፈጽሟል፡፡ ከፋፋይ እና የጠባብ ጎሰኝነት አፈራማጅ እና ከፋፋይ የእብሪተኝነት ዕኩይ ዓላማውን የማይደግፉትን አንቱ የተባሉ ምርጥ እና ምጡቅ የዩኒቨርሲቲ መምህራንን እና ፕሮፌሰሮችን በድንቁርና እና በማንአለብኝነት ሀገሪቱ በስንት ዓመታት አስተምራ ያወጣቻቸውን አንቱ የተባሉ መምህራን በጅምላ በማባረር የሰው ሀገር ሲሳይ እንዲሆኑ አድርገዋል፡፡ ሄደውም ስለሀገራቸው ጉዳይ ጸጥ ብለው ሳይቀመጡ ከስራዎቻቸው በተጓዳኝ በሀገራቸው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲመሰረት እና ይህ ለህዝብ እና ለሀገሪቱ ዕኩይ የሆነ ስርዓት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ አፈር ድሜ በልቶ ወደ የታሪክ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቅርጫት ውስጥ እንዲጣል ለለውጥ ተግተው በመታገል ላይ ይገኛሉ፡፡

አንዳንዶቹም በዓላማቸው ጸንተው በሀገር ውስጥ የግል ስራቸውን እየሰሩ ለሀገራቸው ነጻነት እና ለህዝባቸው ልዕልና ሌት ከቀን በመታገል ላይ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ በእብሪተኝነት በደንቆሮዎች ውሳኔ ከሚያስተምሩባቸው ግቢዎች እንዲባረሩ የተደረጉት የምርጦች ሁሉ ምርጥ መምህራን እና ፕሮፌሰሮች የሚከተሉትን ያካትታል፡:

1ኛ) ፕሮፌሰር መኮንን ቢሻው
2ኛ) ፕሮፌሰር ሰለሞን ተርፋ
3ኛ) ፕሮፌሰር ስብሀት መርሴ ሀዘን
4ኛ) ፕሮፌሰር ታዬ ወልደሰማያት
5ኛ) ፕሮፌሰር ፍስኃ ዘውዴ
6ኛ) ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ
7ኛ) ፕሮፌሰር አየነው እጅጉ
8ኛ) ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ኃይሌ
9ኛ) ፕሮፌሰር መኮንን ዲልጋሳ
10ኛ) ፕሮፌሰር ታምሬ ሁዋንዳ
11ኛ) ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ
12ኛ ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ተፈራ
13ኛ) ፕሮፌሰር አድማሱ ዋሴ
14ኛ) ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ
15ኛ) ፕሮፌሰር ዳዊት ዘውዴ
16ኛ) ፕሮፌሰር አስፋው ደስታ
17ኛ) ፕሮፌሰር ታዬ መኩሪያ
18ኛ) ፕሮፌሰር አየለ ተርፈ
19ኛ) ፕሮፌሰር በፈቃዱ ደግፌ
20ኛ) ፕሮፌሰር ኃይሉ አርአያ
21ኛ) ፕሮፌሰር ታዬ አሰፋ
22ኛ) ፕሮፌሰር ወርቁ ተፈራ
23ኛ) ፕሮፌሰር ንጋቱ ተስፋዬ
24ኛ ሌክቸረር ሰለሞን ወንድወሰን
25ኛ) ሌክቸረር ኃይሉአንተን አባተ
26ኛ) ሌከቸረር ሽፈራው አጎናፍር
27ኛ) ልክቸረር መኩሪያ አሰፋ
28ኛ) ሌክቸረር ፈለቀ ደስታ
29ኛ) ሌክቸረር አክሊሉ ታደሰ
30ኛ) ሌክቸረር ብርሀኑ ባንካሸ
31ኛ) ሌክቸረር ለዓለም ብርሀኑ
32ኛ) ሌክቸረር አይናለም አሸብር
33ኛ) ሌክቸረር ፕሮፌሰር ጸሐዬ ብርሀኔ
34ኛ) ሌክቸረር ምንዳርያለው ዘውዴ
35ኛ) ሌክቸረር አየለ ታረቀኝ
36ኛ) ሌክቸረር ዘሪሁን ተሾመ
37ኛ) ሌክቸረር ፈቃደ ሸዋቀና
38ኛ) ታደሰ በዬነ
39ኛ) ተስፋዬ ሸዋዬ
40ኛ) ሰይፉ መታፈሪያ
41ኛ) ረዳት ሌክቸረር መስከረም አበበ ናቸው፡፡

እ.ኤ.አ በ2015 ከሚያስተምሩበት ግቢ እንዲባረሩ ስም ዝርዝራቸው በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ውስጥ የሰፈረው ፕሮፌሰሮች፣ መምህራን እና ሌሎች የትምህርት ባለሙያዎች እነማን ናቸው?
ይህንን እኩይ ድርጊት በጭንቀት እንጠብቃለን!
ኃይለማርያም ስለኃይማኖት ጽንፈኝነት፣ ስለጥላቻ ማራገብ እና ስለጦርነት ነጋሪት መጎሰም ብዙ ያወራል፡፡
ለመሆኑ ኃይለማርያም ስለኃይማኖት ጽንፈኝነት እየተናገረ ያለው ስለእነማን ነው?
ከጥቂት ሳምንታት በፊት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የይስሙላ የዝንጀሮ (የጦጣ) ፍርድ ቤት በ18 ወጣት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች (ሂዩማን ራይትስ ዎች፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ዩኤስሲአርአይኤፍ/USCRIF፣ የአፍሪካ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና ሌሎች በርካታ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ሰላማዊ የተቃዋሚ መሪዎች እና ወትዋቾች እያሉ የሚጠሯቸውን) ላይ የኃይማኖት ጽንፈኝነትን እና የቡድናዊነት ስሜትን በማራመድ በሚል የአሸባሪነት ክስ ከ7 እሰከ 22 ዓመታት የእስር ውሳኔ በየነ፡፡
ወጣት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የጸረ ሽብር ድርጊት ሙከራ፣ እስላማዊ መንግስት ለማቋቋም እና የአመጽ ቅስቀሳ በማካሄድ በሚል የተቀነባበረ ሽረባ እና ደባ ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የዩስሙላ የዝንጀሮ ፍርድ ቤት በአቡባከር አህመድ፣ በአህመዲን ጀቤል፣ በያሲን ኑሩ እና በከማል ሸምሱ በእያንዳንዳቸው ላይ እጃቸው ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ በሚታሰብ የ22 ዓመት እስር በይኗል፡፡

በይስሙላው የዝንጀሮ ፍርድ ቤት ሌሎች ተከላካዮች ላይ ማለትም በሙኒር ሁሴን፣ በሳቢር ይርጉ፣ በበድሩ ሁሴን፣ በመሀመድ አባተ እና በአቡበከር አለሙ በእያንዳንዳቸው ላይ እጃቸው ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ በሚታሰብ የ18 ዓመት እስራት በይኗል፡፡
እንደዚሁም ደግሞ በአህመድ ሙስጠፋ፣ በከሀሊድ ኢብራሂም፣ በሸክ መከተ ሙሄ፣ በሸክ ሰይድ ዓሊ እና በሙባረክ አደም በእያንዳንዳቸው ላይ እጃቸው ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ በሚታሰብ የ15 ዓመት እስራት ወስኗል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የይስሙላ የዝንጀሮ ፍርድ ቤት በዩሱፍ ጌታቸው፣ በኑሩ ተርኪ፣ በሙራድ ሽኩር እና በባህሩ ኡመር በእያንዳንዳቸው ላይ እጃቸው ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ በሚታሰብ የ7 ዓመት እስራት በይኗል፡፡
እሰከ አሁንም ድረስ ከትልቁ ቋጥኝ ጀርባ ተደብቀው ውድመትን ለመፍጠር የተዘጋጁ ሌሎች የኃይማኖት ጽነፈኞች አሉ ማለት ነውን?

ኃይለማርያም የኃይማኖት ጽንፈኝነትን በሚያወግዝበት ጊዜ በቅርቡ በቁጥጥር ስር የሚውሉ ሌሎች ያሉ እና በሌላ ዙር የሙስሊም አሸባሪዎችን እንይዛለን የሚል ዘገምተኛ ማስታወቂያ እያሰማ ነውን?
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የማታለያ ዘዴ፡ “የጎሳ ፌዴራሊዝም (ክልላዊነት)”
ከ25 የአገዛዝ ዓመታት በኋላ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ዋና ችግር የጎሳ ጥላቻ እና በኃይማኖት አለመቻቻልን እንደ አብይ የአገዛዙ ስልት በመቁጠር ሲያራምዱት የቆየው ዕኩይ ምግባር በአሁኑ ወቅት በጣም እያደገ በመምጣት እራሳቸውን ከጀርባ በመሆን ሊነክሳቸው እያኮበኮበ የመገኘቱ ሁኔታ ነው፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ “የጎሳ ፌዴራሊዝም (ክልላዊነት)” ምንድን ነው?
“የጎሳ ፌዴራሊዝም” ኢትዮጵያ ወይም ደግሞ የኢትዮጵያ ታሪክ የሚባል ነገር የለም የሚል የተጠቃለለ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ዋና ፍልስፍና ነው፡፡
ኢትዮጵያ የሚለው ቃል በንድፈ ሀሳብ ደረጃ በአንድ በተወሰነ የጎሳ ቡድን አባላት አዕምሮ ውስጥ የሚገኝ ምዕናባዊ አስተሳሰብ ነው፡፡

“ኢትዮጵያ” ከአንድ ክፍለ ዘመን በፊት እውቅና አግኝታ ወደዚህ ዓለም የመጣች ሀገር ናት፡፡
“ኢትዮጵያ” የተነጣጠሉ “የብሄሮች እና ብሄረሰቦች” ስብስብ ናት፡፡
“ኢትዮጵያ” እርስ በእርሳቸው በማይደጋገፉ ህዝቦች እና ተጻራሪ የሆኑ ፍላጎቶች ያሏቸው በመሳሪያ ኃይል በግድ አንድ እንዲሆኑ ተጨፍልቀው ተይዘው ያሉ ህዝቦች ናቸው፡፡

“ኢትዮጵያውያን” በተከፋፈለ ጎሳ፣ ቋንቋ እና ኃይማኖት ካምፖች እንዲሁም በተጻራሪ ፍላጎቶች በተሻለ ሁኔታ መገዛት ይችላሉ፡፡
እንደ እነርሱ አባባል ኢትዮጵያዊ ነን ብለው የሚያስቡ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ድብቅ ዓለማቸው በሌሎች የጎሳ ቡድኖች ላይ የበላይነትን የሚያራመዱ ብሄረተኞች ናቸው፡፡

በመሰረቱ ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ትርጉም ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ውድቀት እና በመጨረሻም እንዳይነሳ ሆኖ መደምሰስ ማለት ነው፡፡

“ኢትዮጵያ” በሀሳብ፣ በታሪክ እና በሁለመናዋ መንገድ በእርግጥ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ግዛት ህልውና ማግኘት እና መጠናከር የትኛውንም ያህል ዋጋ ተከፍሎም ቢሆን መደምሰስ እና መቀበር አለባት
ስለሆነም የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በአሁኑ ጊዜ ምን ቀረው?
ደህና እንግዲህ በአሁኑ ጊዜ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የዘሩትን ማጨድያ ጊዜ ነው? (ምናልባት?!)
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለሩብ ምዕተ ዓመታት ያህል የዘራውን የጎሳ ፌዴራሊዝም ዘር ሰብል ለማጨድ በዝግጅት ላይ ነው፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የጥላቻ አዝመራ አጨዳ፣

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ስልጣኑን አንቆ በመያዝ ለመቆየት እና ቁጥጥሩን ለማጠናከር እንዲችል የጎሳ ፌዴራሊዝምን ስርዓት ቀይሷል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የጎሳ ፌዴራሊዝሙ በከፍተኛ ደረጃ አድጓል፣ ተጠናክሯል እናም በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ቀስ በቀስ የእራሱን የወያኔን ጉሮሮ ያንቃል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በግድግዳ ላይ የተጻፈውን እየተመለከተ ነው፣ መምህራንን እና ፕሮፌሰሮችን እንዲሁም ወጣቱን ትውልድ እያዳመጠ ነው፡፡ ወያኔው ማንኛውንም የሚመለከተውንም ሆነ የሚሰማውን ነገር ሁሉ አይወድም፡፡
ፒትሪም ሶሮኪን የተባሉ ሰው በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፣ “ጥላቻ ጥላቻን ይወልዳል፣ ኃይል ሌላ የኃይል አደጋን ያስከትላል፣ አስመሳይነት በአስመሳይነት ምላሽ ያገኛል፣ ጦርነት ጦርነትን ይወልዳል፣ እንደዚሁም ደግሞ ፍቅር ፍቅርን ይፈጥራል፡፡

“ ቅዱሳት መጽሐፍት እንዲህ በማለት ያስተምሩናል፣ “ሰው የዘራውን ያጭዳል፡፡“
በአሁኑ ጊዜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች ፈታኙን ወቅት የሚጋፈጡበት ጊዜ ነውን?
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እንደውዳሴ ማርያም ሲደግመው እና ሲዘምርለት የከረመውን ስለብሄሮች ክፍፍል፣ ስለጎሰኝነት፣ ስለቡድናዊነት፣ ስለኃይማኖት ጽንፈኝነት እና ስለሌሎች ስለቀሩትም ሁሉ እየመጣ ላለው ችግር ኃላፊነቱን ጠቅልሎ ለመምህራን እና ለፕሮፌሰሮች ለመስጠት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ እንደ ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ የሚጮህ ግራ ገብቶት ግራ የሚያጋባ ስርዓት!

እውነት እንናገር!

መምህራን እና ፕሮፌሰሮች ወጣቶችን በመንከስ የጥላቻን መርዝ ያሰራጫሉ ብለን ካሰብን እነዚህን መምህራን እና ፕሮፌሰሮች እንዲሆኑ የሾማቸው ማን ነው?
“የውርስ ታሪክ” እየተባለ የሚጠራውን አዲስ ፋሽን በማድረግ በዩኒቨርሲቲው ስርዓተ ትምህርት/curriculum ውስጥ እንዲካተት ያደረገው ማን ነው?
የውርስ ታሪክ መሰረት ያደረገው በአሁኑ ጊዜ ያለው የኢትዮጵያ ታሪክ ለትርጉም የሚጋብዝ፣ የግል አመለካከት የተንጸባረቀበት እና አጠቃላይ ይዘቱ ሲታይ ሚዛናዊነትን ያልጠበቀ አንድ ዓይነት የሆነ በጽሁፍ ከተገኙት ሰነዶች ብቻ ተወስዶ እንደገና የተጻፈ ሆኖ ይገኛል፡፡ ብሄራዊ ታሪካችንን እንደገና የማደራጀቱ የመጻፉ ስራ ሌላ ተለዋጭ የመረጃ ምንጭ የማግኘቱ እና የመጠቀሙ ጉዳይ ጊዜ የሚሰጠው ነገር አይደለም…
የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ስለእራሳቸው ጎሳ ቡድን እንጅ ስለሌላ ስለማንም እንዳይዘግብ ሆኖ በስርዓት ትምህርቱ ውስጥ እንዲካተት ያደረገ ማን ነው?
የማለያየት ፖሊሲን በትምህርት ቤቶች ላይ በመቅረጽ እና ተማሪዎች እያደጉ ሲሄዱ ጓደኞቻቸው ወደፊት ጠላቶቻቸው እንደሚሆኑ የሚያስቡ እንዲሆን ከተደረገ ይህንን ከፋፋይ ፖሊሲ እንዲቀረጽ እና እንዲተገበር ያደረገው ማን ነው?
የተለያዩ ብሄሮች እና ጎሳዎች የጋራ መግባቢያ የሆነውን ሀገራዊ ቋንቋቸውን ትተው ወንዝ የማያሻግር እና የጠባብነት ስሜትን ወደሚያዳብረው በብሄር ቋንቋ ብቻ እንዲማሩ ፖሊሲ የነደፈው እና እንዲተገበር ያደረገው ማን ነው?
የሚከተሉትን ክልሎች (የብሄር ቋንቋን መሰረት ያደረጉ ክልላዊ መንግስታት) ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ትግራይ፣ አፋር፣ ሶማሊ፣ ቤንሻንጉል-ጉሙዝ፣ ደቡብ ሕዝቦች፣ ጋምቤላ፣ እና ሀራሪ፣ (አዲስ አበባ/ድሬዳዋ በፌዴራል ደረጃ የሚተዳደሩ ከተሞች) የፈጠረ ማን ነው?

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሕገ መንግስቱን እንዲህ የሚለውን የመገንጠል እና የመገነጣጠል አንቀጹን አንቀጽ 39ን፡ “እያንዳንዱ ብሄር ብሄረሰብ ወይም ህዝብ የእራሱን እድል በእራሱ የመወሰን እስከመገንጠል“ የጻፈው ማን ነው? የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አንቀጽ 39ን በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሰውነት ላይ ለመጨረሻ ውድመት የቀበረው በሰዓት የተሞላ ቦምብ ወያኔ ግብዓተ መሬቱ ሲደርስ እና ወደ ታሪክ ቆሻሻ ማጠራሚያ ቅርጫት ውስጥ ሲጣል እንዲፈነዳ ታስቦ የተቀበረ ነውን?
በሀገሪቱ ውስጥ ሁሉንም የፖለቲካ ውክልናዎችን፣ የውሳኔ ሰጭነትን፣ በክልሎች የህዝብ መድረኮችን የተቆጣጠረው፣ በበላይነት የሚይዘው እና በጥቅል ሁሉንም ነገር ጨምድዶ ይዞት የሚገኘው ማን ነው?
በህዝቡ መካከል ውጥረት እና የጥላቻ መንፈስ እንዲሰራጭ የሚያደርግ እና በጎሳ ቡድኖች እና በማህበረሰቦች መካከል የትጥቅ ግጭት እንዲፈጠር፣ የኃይማኖት ጽንፈኝነት እና በኢትዮጵያ ጦረኝነት እንዲነግስ ለሚደረገው እኩይ ምግባራት ሁሉ በዋናነት ተጠያቂው ማን ነው?
ስውር በሆነ መልኩ በጎሳዎች መካከል ግጭት እንዲፈጠር በማድረግ አጋጣሚውን በመጠቀም ሁኔታውን ለማባባስ በጎሳ ግጭት እሳቱ ላይ ነዳጅ የሚያርከፈክፈው ማን ነው?
የጎሳ ፌዴራሊዝም (ወይም ደግሞ ጦጣ አየች፣ ጦጣ ሰራች ዓይነት ፌዴራሊዝም) ካስገኘው ተሞክሮ ምን የተገኘ ጥቅም እና የተመዘገበ ነገር አለ?
በጎሳ ፌዴራሊዝም ሁሉንም ጠቃሚ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ውሳኔዎችን የሚወስነው ማን ነው?
በእርግጠኝነት የጎሳ ፌዴራሊዝም እንዴት ነው እየሰራ ያለው?
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ለክልል ሎሌ መንግስታት ዴሞክራሲያዊ ማዕከልነትን በጠበቀ መልኩ ለትግበራ ይወስኑላቸዋልን?
የክልል መንግስታት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት እና የክልል ምክር ቤቶች የፌዴራሉን ውሳኔ በመያዝ ማህተም ለማሳረፍ ብቻ የተቀመጡ ታዛዥ ሎሌዎች ናቸውን?
የክልል መንግስታትን ጉዳዮች የሚቆጣጠረው ማን ነው? የክልል እና የአካባቢ መንግስታትን የገቢ እና በጀት አጠቃላይ ጉዳዮችን የሚቆጣጠረው ማን ነው?
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እራሱ ሕግ ካወጣ በኋላ ያወጣውን ሕግ በመደፍጠጥ ለምንድን ነው በክልሎች ጉዳይ ላይ ወታደራዊ ጣልቃገብነትን የሚያራምደው እና ሕጉን ጠብቀው የሚንቀሳቀሱ የክልል አመራሮችን ከስልጣን የሚያግደው?
የክልል መንግስታት በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አለቆቻቸው ከላይ ተወስኖ ከተሰጣቸው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ አጀንዳ ውጭ ሊያስቡ እና ሊሰሩ የሚችሉባቸው አሉን?
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እምነተቢስ ሁኔታ ክልሎች ቁራጭ ዳቦ ለማግኘት ሲባል በወያኔ ጠረጴዛዎች ላይ ጦርነት መግጠም አለባቸውን?
ክልላዊነት ለተጮቆኑት የጎሳ እና አናሳ ቡድኖች ወይም ደግሞ ለመገንጠል እንዲያመች በስውር ነዳጅ የሚጨምሩ ቡድኖች ቀደም ሲል ያቀርቧቸው የነበሩት ታሪካዊ ቅሬታዎች መፍትሄዎቻቸውን አግኝተዋልን?
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በኢትዮጵያ ሕዝቦች መካከል የጎሳ ማንነትን በመፍጠር፣ በጅምላ ተጠራጣሪነትን፣ ፍርሀትን እና ጥላቻን በመዝራት በህዝቦች መካከል ለዘለቄታው የጎሳ ክፍፍልን ለማቆየት እንዲመቸው የጎሳ ፌዴራሊዝምን አዋቅሯል፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኢትዮጵያን ለመጨረሻ ጊዜ ለመቅበር እና በቀብር ቦታዋ ላይ የእራሱን ሐውልት ለመገንባት የሚሉትን እንደመሳሪያ ለመጠቀም እንዲችል የጎሳ ፌዴራሊዝምን አዋቅሯል፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አድራጊ ፈጣሪ ዋና መሀንዲስ ለኢትዮጵያ በቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ እራሱ ገብቶበት ተገኝቷል፡፡

እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ ግን የጎሳ ፌዴራሊዝም የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ዋና መሳሪያ እና ሌሎች ሁሉም የጎሳ ቡድኖች ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ታማኝ ሎሌዎች ሆነው እንዲያገለግሉ የሚያስችል ስርዓትን መፍጠር ነው፡፡
ከሩብ ምዕተ ዓመት አገዛዝ በኋላ የጎሳ ፌዴራሊዝም ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ኢትዮጵያን ለመግዛት አስቸጋሪ እየሆነበት መጥቷል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የጎሳ ግንኙነቶች ከምንጊዜውም በላይ አስከፊ እየሆኑበት መጥተዋል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እራሱን እና ሌሎችን የጎሳ ቡድኖች ለማገዝ በማሰብ የጎሳ ፌዴራሊዝምን አዋቅሯል፡፡
ወሳኙ እና በመጨረሻ ሊነሳ የሚገባው ጥያቄ ሁሉም የኢትዮጵያ ጎሳዎች እና ኃይማኖቶች ቀደም ከነበሩበት የተሻለ ነጻነት፣ ከፍ ያለ የኃላፊነት ስልጣን እና በእራስ የመተማመን ስሜት በሌላ ጊዜ ከነበሩበት ይልቅ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አገዛዝ ስር አግኝተዋልን?

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ዳንስ አብቅቷል!

እንዲህ የሚባል አባባል አለ፣ “ሁሉንም ሰዎች ለጥቂት ጊዜ ማሞኘት ይቻላል፡፡ ጥቂት ሰዎችን ግን ሁልጊዜ ማሞኘት ይቻላል፡፡ ሆኖም ግን ሁሉንም ሰዎች ሁልጊዜ ለማሞኘት አይቻልም፡፡“
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከፊሉን ህዝብ ሁልጊዜ አሞኝቷል፣ ጥቂቶችን ግን ሙሉ ለሙሉ ለ25 ዓመታት ያህል ሲያታልል ቆይቷል፡፡ ሆኖም ግን አሁን ሁሉንም ለሁልጊዜ ማታለል ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ አብዛኛው ህዝብ ነቅቷል!
ስለሆነም በአሁኑ ጊዜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሳይሆን እራሱን በማሞኘት ላይ ብቻ ታጥሮ ይገኛል፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እራሱን በኢትዮጵያ በስልጣን ኮርቻ ላይ አደላድሎ ለመቀመጥ ላለፉት ሩብ ምዕተ ዓመታት በህዝቦች መካከል ለዘራው እና እየተጠናከረ ለመጣው የዘር ጥላቻ እራሱን ነጻ በማድረግ እኩይ ድርጊቱን ወደ መምህራን እና ፕሮፌሰሮች ለማላከክ ድሁር ድሁር ይላል፡፡ የእምዬን ወደ አብዬ እንዲሉ!

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በአሁኑ ጊዜ ምን እንደሚሰራ የሚያውቀው ነገር የለም፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከለኮሰው የጎሳ እሳት ነበልባል ለመዳን ሲል ሊሰማው የሚችል ማንኛውንም ሰው ካገኘ አስቸኳይ መልዕክት እንደሚልክ ምንም የሚያጠያይቅ ጉዳይ አይደለም የሚል እምነት አለኝ፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አዲስ ያገኘውን ብሄራዊነት እና አርበኝነት በህዝቡ ዘንድ ለመፈተን ኃይለማርያምን የተነፋ ፊኛ አስይዞ ወደ አየር እንዲንሳፈፍ ማድረግ የሚቻል ጉዳይ ነው፡፡ ያ የሙከራ ፊኛ እንደ ዋና ፊኛ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል የሚል እምነት አለኝ፡፡

በአሁኑ ጊዜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አለቆች ቆፍረውት በነበረው ስለኢትዮጵያ የጎሳ መቃብር በግድግዳው ላይ የተጻፈውን ማንበብ ጀምረዋል፣ እናም እራሳቸውን ለማዳን ሲሉ ስለብሄራዊ አንድነት፣ የጋራ ማንነት፣ ስለአርበኝነት፣ ወዘተ በድፍረት መናገር ጀምረዋል፡፡

የኃይለማርያምን ስሜታዊ የድንፋታ ንግግር ከሚገባው በላይ አንብቤዋለሁ ወይም ትንታኔ ሰጥቸበታለሁን? የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች ሲያልቅባቸው ሌላ ማታለያ ይዘው ይቀርባሉን? በኃይለማርያም የማጭበርበር የጥፋተኝነት ኃላፊነትን በሌሎች ላይ ለመጫን በሚደረገው እርባናቢስ ገለጻ ላይ ህዝቡ አወንታዊ ምላሽ ካለው ምናልባትም ከእርሱ ጋር መጓዝ ይችላሉን?
በግድግዳው ላይ የተጻፈው ጽሑፍ፣

የሕዝብ የውልደት ሱናሜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን አጥለቅልቆታል፡፡
በአሁኑ ጊዜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሲያራምደው የቆየው የጎሳ ፌዴራሊዝም/ክልላዊነት እሳት ነበልባል እንደገና ወደ እርሱ ዞሮ ሊለበልበው እንደሚችል እና ዶግ አመድ እንደሚያደርገው በዚህም ሳቢያ ሊከተል የሚችለውን አሉታዊ እንደምታ በግልጽ ተመልክቶታል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የማታለያ ሸፍጥ ተይዘው ያሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወጣቶች አሉ፡፡

ወጣቶቹ በጫካኝ የወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ መገዛትን አይፈልጉም፡፡ የእራሳቸውን መንግስት መመስረት ይፈልጋሉ፡፡ እነዚህ ወጣቶች ነጻነት፣ ዴሞክራሲ እና የሰብአዊ መብት ጥበቃ እንዲኖር ይፈልጋሉ፡፡
ጊዚያቸውን ይጠብቃሉ፡፡ በየዕለቱ ስሞችን ይጽፋሉ፡፡ የእራሳቸውን ጓደኞች እና ጠላቶች ለይተው አሳምረው ያውቃሉ፡፡
ከ25 ዓመታት በላይ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በኢትዮጵያ መከራ እና ስቃይን ያሰራጨ ጨቋኙ እና ሰይጣኑ በማለት የአማራን ህዝብ ጥላሸት ሲቀባ ቆይቷል፡፡ ያ ዓይነት ገለጻ ለጊዜው ሰርቷል፣ ሆኖም ግን በዘላቂነት ሊሰራ አልቻለም፡፡ አሁን የከሸፈ ጥይት ሆኗል፡፡

እንግዲህ የእርሱ አባባል እውነት ቢሆን እንኳ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ “አማራ ጨቅዋኝ መንግስት” አያለ አንደሚተርከው በአሁኑ ጊዜ ራሱ “አዲሱ አማራ” ሆኗል፡፡ እነዚህ ግፈኛ ሸፍጠኞች በሁሉም ህዝብ በከፋ መልኩ ተጠልተዋል፡፡ (ይህንን እውነታ ሸፋፍኘ ባልፈው ደስ ባለኝ ግን አልችልም ፡፡)

ይህ ሊካድ የማይችል ሀቅ ነው! ይህንን ነገር ያልኩት እኔ አይደለሁም ምክንያቱም እኔ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከሚሰራው እኩይ ምግባር በተጻራሪው የቆምኩ ሰው በመሆኔ ብቻ አይደለም።
የእኛ ታላላቆች እንዲህ ይላሉ፣ “የዛሬ ፍሬዎች የነገ አበባዎች“

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከ25 ዓመታት በፊት የዘራው ዘር በአሁኑ ጊዜ ጥላቻን ላዲስ ትውልድ ለማጨድ በስሎ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን፣ ወይም ደግሞ አመራሮችን፣ ወይም አባላቱን የግል ችግር የለኝም፡፡ እንደግለሰቦች ስለእነርሱ ምንም ዓይነት ጉዳይ የለኝም፡፡
እኔ ጉዳዬ ያለው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች በኢትዮጵያ ላይ የጎሰኝነት ጥላቻን እና የኃይማኖት ጽንፈኝነትን በማራመድ ሀገሪቱን ለማጥፋት እና ህዝቡ ተሳስሮበት የሚገኘውን ገመድ ለመበጣጣስ ከሚያደርጓቸው ሰይጣናዊ ድርጊቶች ነው ጋር ነው ጉዳዬ ያለው፡፡
ሆኖም ግን ከጎሰኝነት እና ከኃይማኖት ጽንፈኝነት ነጻ የሆነች አዲሲቱ ኢትዮጵያ ላይ ውይይት እና ክርክር እንዲደረግ ለማመቻቸት ታማኞች እና ቅን ልቦና ያላቸው ቢሆኑ ኖሮ እኔ ለእነርሱ ነበርኩ፡፡

ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዲህ በማለት አስተምረውናል፣ “ጨለማን ጨለማ አያስወግደውም፡፡ ይህንን ማድረግ የሚችለው ብርሀን ብቻ ነው፡፡ ጥላቻን ጥላቻ አያስወግደውም፡፡ ይህንን ማድረግ የሚችለው ፍቅር ብቻ ነው፡፡“

ምንም ዓይነት የፖለቲካ ስልጣን እንደማይፈልግ እና እንደሰብአዊ መብት ተሟጋችነቴ ጥላቻን በፍቅር ከማሸነፍ ጦርነት ጋር ከማንኛውም ሰው ጋር ለመወያየት እና አስተያየቴን ለማካፈል ፈቃደኛ ነኝ፡፡

ዶ/ር ኪንግ እንደዚያ ዓይነቱን ፍቅር በተቃራኒ ጾታ ላይ ሳይሆን ሰው በሰውነቱ ብቻ እራስን በተወ አኳኋን ሰውን እንደ ወንድም እና እንደ እህት ማፍቀር፣ በአጠቃላይም ማህበረሰቡን ማፍቀር ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት አምላክ ሰውን እንደሚወድ ሁሉ ሰውም አምላኩን እንደሚወድ ዓይነት ማለት ይሆናል፡፡
ጥላቻን እጠላለሁ ምክንያቱም፡

ጥላቻ በናዚ ጀርመን አገዛዝ ጊዜ ለ6 ሚሊዮን ህዝቦች እና ቁጥራቸው ላልተነገረ የክርስትና እምነት ተከታዮች እና ለሌሎች ህዝቦች ሞት ምክንያት ሆኗል፡፡
ጥላቻ ህንድ እ.ኤአ. በ1947 ነጻነቷን ከተጎናጸፈች በኋላ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህዝቦች እንዲያልቁ አድርጓል፡፡
ጥላቻ እ.ኤ.አ በ1971 በባንግላዴሽ (ምስራቅ ፓኪስታን) በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህዝቦች እንዲያልቁ አድርጓል፡፡
ጥላቻ በቢያፍራ (በምስራቅ ናይጀሪያ) ከሚሊዮን በላይ ህዝቦች እንዲያልቁ አድርጓል፡፡
ጥላቻ እ.ኤ.አ በ1972 በቡሩንዲ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ህዝቦች እንዲያልቁ አድርጓል፡፡
ጥላቻ እ.ኤ.አ ከ1985 – 79 ድረስ ባሉት ዓመታት ውስጥ ባካምቦዲያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህዝቦች እንዲገደሉ አድርጓል፡፡
ጥላቻ እ.ኤ.አ በ1994 በሩዋንዳ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎች ህይወት ህልፈት ምክንያት ሆኗል፡፡
ጥላቻ እ.ኤ.አ ከ1985 – 2015 ባሉት ዓመታት ውስጥ በደቡብ ሱዳን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህዝቦች እንዲያልቁ አድርጓል፡፡
ጥላቻ በኢትዮጵያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎች እንዲያልቁ አድርጓል፡፡
ጥላቻ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቼን እና እህቶቼን ወይም ደግሞ ማንኛውንም የሰው ልጅ ፍጡር የሆነን ሁሉ ሲገድልብኝ ማየት አልፈልግም፡፡

ኢትዮጵያውያን/ት ከታሪክ እንዲህ የሚል ትምህርት መማር አለባቸው፡ “ጥላቻ እነርሱን ከመግደሉ በፊት እነርሱ ጥላቻን ከልቦቻቸው እና ከአዕምሯቸው ውስጥ መንጥቀው በማውጣት መግደል አለባቸው!”

ኔልሰን ማንዴል እዲህ ብለው ነበር፣ “ትምህርት ዓለምን ለመለወጥ ልንጠቀምበት የሚገባ ጠቃሚ መሳሪያ ነው፡፡“
በሌላ በኩልም እንዲህ የሚል አባባል አለ፣ “ድንቁርና አምባገነኖች በእጃቸው ይዘው የሚጠቀሙበት ጠቃሚ መሳሪያ ነው፡፡“
ዋነኛው እና ተመራጩ መንገድ እሳትን በእሳት ሳይሆን በውኃ ማጥፋት ነው፡፡

ዋነኛው እና ተመራጩ መንገድ ጥላቻን በጥላቻ ሳይሆን በፍቅር እና በእውቀት ብርሀን መዋጋት ነው፡፡
ዋናው እና ተማራጩ መንገድ ድንቁርናን በእውቀት እና በትምህርት መዋጋት ነው፡፡

ኢትዮጵያ የሩዋንዳን፣ የካምቦዲያን፣ የደቡብ ሱዳንን፣ ወይም ደግሞ እንደ ኢትዮጵያ ያለ ዕደል ያላቸው ሌሎች ሀገሮችን ዓይነት ዕድል እንዲገጥማት አልሻም፡፡

የኃይለማርያም የጩኸት እወጃ ከዚያም በላይ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ፍላጎት እና ሀሳብ ቢሆንም ጥላቻን ማቆም እና ቁስሉን የማዳን እና የእርቀ ሰላም ሂደቱን መጀመር ከሁሉም በላይ የተሻለው እና ተመራጩ መንገድ ነው፡፡ ከዚያም እኔ ሙሉ በሙሉ ከዚህ ሀሳብ ጋር ነኝ፡፡

በርካታ ሰዎች የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች በምንም ዓይነት መልኩ ጥፋታቸውን የማያምኑ እና እራሳቸውን ከሕግ በላይ ያደረጉ፣ ምንም ዓይነት ተስፋ የማይጣልባቸው እና ተስፋ የቆረጡ ስብስቦች ናቸው የሚሉ ሰዎች እንደሚኖሩ አውቃለሁ፡፡

ጠቃቀጠቋማው ጅብ ዥንጉርጉር ቆዳውን ለመለወጥ ቢፈልግም እንኳ መለወጥ አይችልም የሚል አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች አሉ፡፡
ከድንቁርና እና ከጥላቻ ጉድጓድ ውስጥ ተመንጥቀን በመውጣት ከፍተኛ የሆኑ አወንታዊ ነገሮችን ማከናወን እንችላለን ብዬ አስባለሁ፡፡

ሆኖም ግን መማር እና አዕምሯችንን መጥፎ ነገሮችን ከመፈልፈል እንዲያቆም ማድረግ አለብን፡፡
መሞከር ከቻልን ብቻ ልንማራቸው እና ከመተግበር ልናቆማቸው የሚገቡ ነገሮች፣
ልንማራቸው የሚገቡ በርካታ ነገሮች አሉ፣ እንደዚሁም ሁሉ መሞከር ከቻልን ብቻ ከመተግበር ልናቆማቸው የሚገቡ በርካታ ነገሮች አሉ፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች ከዶ/ር ሴውስ (አዎ የ“ድመት በባርኔጣ ውስጥ“ ደራሲ) መጽሐፍ ውስጥ እንዲህ የሚል ቁምነገርን መማር ይችላሉ፣ “ወደ ግራም አስብ፣ ወደ ቀኝም አስብ፡፡ እንደዚሁም ወደ ታች አስብ፣ ወደ ላይም አስብ፡፡ ኦ፣ ማሰቡን መሞከር ከቻልክ ብቻ ነው አዲስ የአሰራር ዘዴ ወይም ሀሳብ ልታገኝ የምትቸለው!“
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እራሱን ከአደጋ ለመጠበቅ እና የሙጥኝ ብሎ በያዘው ስልጣኑ ላይ ለዘላለም ለመቀጠል የሚያስባቸው ሀሳቦች አሉ፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጥላቻን ሲያራምድበት የቆየበትን መንገድ እንደገና የማየት እና ከዚህ መጥፎ ድርጊት ታቅቦ እንደገና ፍቅርን ወደ መስበኩ ሁኔታ የሚያስባቸው ሀሳቦች አሉ፡፡
ሆኖም ግን እንደ ኢትዮጵያዊነት ዋና ቁልፍ ችግር ግራ ማሰብ እና ቀኝ ማሰብ መቻል ነው፣ ወደታች ማሰብ እና ወደላይ ማሰብ መቻል ነው፡፡ ኦ፣ ማሰቡን መሞከር ከቻልን ብቻ ነው አዲስ የአሰራር ዘዴ ወይም ሀሳብ ልናገኘው የምንችለው!
ለማሰብ ደፋር ሁን!
ለማወቅ ደፋር ሁን!
ለመማር ደፋር ሁን!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ነሐሴ 26 ቀን 2007 ዓ.ም

ኮንቴይነር በተገኘ ቁጥር ‹‹ኢትዮጵያዊ ተደብቋል› ›መባል ተጀምሯል –የ10 ዓመት ታዳጊ ይገኝበታል

$
0
0

ethiopians

ከዳዊት ሰለሞን

በዛምቢያ ሴሬንጄ በተሰኘች ግዛት ፖሊስ 100 ኢትዮጵያዊያንን በመኪና ተጭነው ሲያመሩ መያዙን የአገሪቱ ዴይሊ ሜይል ጋዜጣ አስነብቧል፡፡
ስደተኞቹ ከናኮንዴ ሳይነሱ እንዳልቀሩ የጠቀሰው ፖሊስ ካኖና በተባለ የፍተሻ ኬላ በመኪናው ላይ በተደረገ ፍተሻ ሰዎቹ ተደብቀው መገኘታቸውን ጠቅሷል፡፡መኪናው በጫነው ኮንቴይነር በዛምቢያ ተወዳጅ የሆነውን ካፔንታ (የደረቀ አሳ) ሲያመላልስ የነበረ መሆኑን ጋዜጣው አውስቷል፡፡
ፖሊስ በናኮንዴ ድንበር አቋርጠው ኢትዮጵያዊያኑ ያለ ህጋዊ ፈቃድ በመግባታቸውና እነርሱን ለማዘዋወር ክፍያ የተፈጸመላቸውን ዛምቢያዊያንን እንደሚከስም ፖሊስ ነገረኝ ያለው ጋዜጣው ዘግቧል፡፡


ሎምቤ ካሙኮሺ ኮሚሽነር ናቸው ለጋዜጣው ‹‹100 ህገ ወጥ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ያሳፈረ መኪና መያዛችንን አረጋግጥላችኋለሁ፡፡ከእኛ ጋር በመስራት ላይ የሚገኘው የስደተኞች መስሪያ ቤታችን ስደተኞቹን የኢቦላ ምርመራ ያደረገላቸው ሲሆን ሌሎች ምርመራዎችንም እያደረገ ይገኛል››ብለዋል፡፡


ኮሚሽነሩ ህገ ወጥ ያሏቸውን ስደተኞች ያዘዋወሩ ያሏቸውን ሶስት የአገራቸውን ዜጎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውንም አስረድተዋል፡፡ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ከ10 -50 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን የተናገሩት ኮሚሽነሩ የሚበዙት ወጣቶች ናቸው ማለታቸውን ጋዜጣው አስፍሯል፡፡
100ዎቹ ስደተኞች በአሁኑ ወቅት በዛምቢያ ሙኮቤኮ በተባለ ወህኒ ቤት ይገኛሉ ተብሏል፡፡በቅርቡ በሞያሌ ድንበር በማቋረጥ ወደ ኬንያ የገቡ 100 ስደተኛ ኢትዮጵያዊያንን የአገሪቱ ፖሊስ ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡ስደተኞቹ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማምራት የተንቀሳቀሱ መሆናቸውም ይነገራል፡፡ከኬንያ እስከ ደቡብ አፍሪካ መዳረሻ ያሉ አገራት ኮንቴይነሮችን የጫኑ መኪኖችን በድንበር አካባቢ ሲያገኙ‹‹ኢትዮጵያዊያን ይኖራሉ››በማለት ጠንከር ያለ ፍተሻ ማድረግ መጀመራቸውን በሂደቱ የተሳተፉ ሰዎች ሲናገሩ ይደመጣል፡፡

የኢትዮጵያውያን አርቲስቶች የአሜሪካ አቀባበል አጨራረሱም እንደ አቀባበሉ ቢሆን

$
0
0

[ቴዲ ድንቅ – አትላንታ]
እንደአጀማመሩ ያስጨርስልን
ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች፣ በተለይ በአሜሪካ ኮንስርት ለማቅረብ ሲመጡ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የተጀመሩ የአቀባበል ሥነ ሥርዓቶች አሉ። አንዳንዱ እንደ አገር መሪ በሊሞ፣ ሌላው በሄሊኮፕተር፣ … ሌላው በፈረስ .. ሌላው ደግሞ እንዳቅሚቲ በ እቅፍ አበባ ተቀብሎ ፣ በራሱ መኪና ሆቴል ያደርሳል። አንዳንዱ የአሜሪካ ፖሊሶችን አነጋግሮ ወይም ተስማምቶ በሞተር ሳይክል የሚያሳጅብም አለ። ኦባማ ነው ወይስ ሌላ እስክንል ድረስ በአምስትና ስድስት ሊሞዎች መቀበልና ማጀብም አለ። አንዱ ከበፊቱ ለመብለጥ በሚደረግ ጥረት ፣ ወደፊትም ሌላ ዓይነት አቀባበል ልናይ እንችላለን

ጃኪ ጎሲን በሂሊኮፕተር

ጃኪ ጎሲን በሂሊኮፕተር

ጥሩ ነው። አርቲስትን ማክበር፣ ለአገራችን ባለሙያዎች ክብር መስጠት ደስ ይላል። እኛም አርቲስቶቻችን ሲከበሩና ደስ ሲላቸው ስናይ ደስ ይለናል እንጂ አይከፋንም። ደስታችን ዘለቄታዊ እንዲሆን ታዲያ …….

….ደስታችን ዘለቄታ ያለው እንዲሆን ታዲያ ..፣ ከዚያም በኋላ ያለው፣ እስከመጨረሻው ድረስም የሚኖረው የሙዚቃ ዝግጅት ፣ እንደ አጀማመሩ እንዲሆን፣ እንዲጨነቁለት፣ እንዲፎካከሩለት እንፈልጋለን።

ቴዎድሮስ ታደሰን በሊሞ

ቴዎድሮስ ታደሰን በሊሞ

ሰው ተስቦ እንዲመጣ ፣ ከአቀባበሉ ጀምሮ ለማሳመር ጥረት እንደሚደረግ ሁሉ፣የመጣው ሰውም ተደስቶ እንዲሄድ አብሮ ጥረት ይደረግ። ለአቀባበሉ ዕቅድና ግብ፣ ስብሰባና ውሳኔ እንደተደረገ ሁሉ፣ ለዝግጅቱ ማማር፣ ለኮንስርቱ የተዋጣለት መሆን፣ የመጣው ሰው እንዲደሰት፣ አርቲስቱ የሚጠበቅበትን ያህል በሚገባ እንዲጫወት፣ በሰአት ተጀምሮ ፣ በስአት እንዲያልቅ፣ የመጣው ሰው በጋጠወጦች እንዳይረበሽ አብሮ ዕቅድና ግብ፣ ስብስባና ውሳኔ ሊኖር ያስፈልጋል።

 

ጸጋዬ እሸቱን በሊሞ

ጸጋዬ እሸቱን በሊሞ

አርቲስቱ እና ፕሮሞተሮቹም መጨረሻ ላይ ከመጨቃጨቅ ፣ ቀድመው ዝርዝሩን ተወያይተው እንዳማረባቸው፣ እንደአቀባበሉ በሊሞና ሞተር ብስክሌት ባይሆንም፣ ቢያንስ ተቃቅፈው በሰላም ለመያየት ያብቃቸው። ፕሮሞተሮችም፣ ብዙ ጊዜ እንደሚታየው፣ ሲጀመር አብረው ሰርተውና አጀማመሩን አሳምረው፣ ካለቀ በኋላ በገንዘብም ይሁን፣ “ያንተ ጥፋት ነው፣ ያንቺ ጥፋት ነው” ተባብለው ከመጣላትም ይሰውራቸው። ለስኬት አብሮነት እንዳለ ሁሉ፣ ባይሳካምም፣ አለመሳካቱ የሁሉም እኩል ሃላፊነት ሊሆን ይገባል።

ተመስገንን በሰረገላ

ተመስገንን በሰረገላ

እናም ኮንሰርቶቻችን አቀባበል ላይ አሁን አሁን እንደሚታየው ያማረ አጨራረስም እንዲኖራቸው እንመኛለን።

የመኢአድ ሕጋዊው ፕ/ት አቶ ማሙሸት አማረ እንገድልሃለን ብለዋል እስኪገሉኝ ትግሉን እቀጥላለሁ አሉ

$
0
0

አቶ ማሙሸት አማረ ፍርድ ቤት በነጻ ከለቀቃቸው ያለ አንዳች ምክንያት ለአምስት ተጨማሪ ቀናት ታስረው ትላንት ቢፈቱም ዛሬም ባሉበት ቤት አካባቢ በፍርድ ቤት በሀሰት የቆሙባቸውን ጨምሮ ሌሎች የደህነት አባላት ክትትል እያደረጉ እንዳሉ ከመውጣታቸውም በፊት በእስር ላይ ሳሉ <<አንተን ከዚህ በሁዋላ አስረን የሚዲአ መነጋገሪያ አናደርግም አርፈህ የማትቀመጥ ከሆነ በማንኛውም ሰዓት እናስወግድሃለን>> እንዳላቸው ገልጸዋል። እስኪገሏቸው ድረስ የጀመሩትን ሰላማዊ ትግል አጠናክረው እንደሚገፉበት ለህብር ሬዲዮሶስት ወር ከሃያ ሁለት ቀን እስር በሁዋላ ከእስር ቤት እንደወጡ በሰጡት ቃለ ምልልስ ገለጹ።

mamushetከምርጫ 97 በፊትና በሁዋላ ከቅንጅት መሪዎች አንዱ ሆነው የታሰሩትን ጨምሮ ለስምንት ጊዜያት በተለያዩ እስር ቤቶች ታስረው የተንገላቱት አቶ ማሙሸት አማረ ሕጋዊው የመኢአድ ፕ/ት ሲሆኑ ምርጫ ቦርድ በሕገወጥ መንገድ ፓርቲውን ለተለጣፊው የእነ አቶ አበባው መሐሪ ቡድን ሲያስረክብ ከቢሮ ተባረው ቦርዱን ከሰው በክርክር ላይ ሳሉ ግንቦት 5 ቀን 2007 ከቤታቸው አቅራቢያ በደህነቶች ታፍነው መታሰራቸው ይታወሳል።በተደጋጋሚ በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ሲቀርቡ ከእስር ቤት እስር ቤት ሲመላለሱና ሁለቴ በነጻ አንዴ በዋስ ይፈቱ ተብለው ሳይፈቱ መቆየታቸውን በዚሁ ቃለ ምልልሳቸው አብራርተዋል።

<<በእስር ቤት ከዚህ ወጥተህ እንቅስቃሴ ብታደርግ እናስወግድሃለን ከዚህ በሁዋላ አንተን አናስርም>> የሚል ጠበቅ ያለ ማስፈራሪያ የተሰጣቸው አቶ ማሙሸት አማረ <<በማንኛውም ሰዓት ሊገድሉኝ ይችላሉ ትግሉን ግን እስከመጨረሻው አላቆምም።በጀመርኩት ሰላማዊ ትግል እቀጥላለሁ >> ብለዋል።

አገዛዙ ከግንቦት 16ቱ ምርጫ በፊት እሳቸውን ባሰረበት ወቅት በምርጫው ላይ ችግር ስለሚፈጥሩ እንዳይፈቱ ሲል ጊዜ ቀጠሮ መጠየቁን ያወሱት አቶ ማሙሸት እሳቸውም ሆነ ዛሬም ድረስ በአዲስ አበባና በክልል እየታደኑ የታሰሩ የመኢአድ አመራሮችና ጠንካራ አደራጆች ለአገዛዙ ስጋት ስለፈጠሩና መኢአድን ለማፍረስ የተደረገ እንቅስቃሴ ነው ብለዋል።

<<በሃያ አራት ዓመት ውስጥ አንድ ዳኛ የተቀነባበረውን የፈጠራ ክስና የተዘጋጁትን የሀሰት ምስክሮች በማየት ምስክርነቱን ውድቅ አድርጎ በነጻ ይፈታ ሲል አምስት ቀን ሳልፈታ ቆይቻለሁ>> ያሉት አቶ ማሙሸት ለኢትዮጵአ ሕዝብ እኩልነት ለሕግ የበላይነት የሚያደርጉትን ትግል በእንገድልሃለን በሚለው ዛቻ እንደማይተውና ሰላማዊ ትግሉን የሚከፈለውን መስዋዕትነት እየከፈሉ እንደሚቀጥሉበት ገልጸዋል። በማንኛውም ጊዜ ሊገድላቸውም ሆነ መልሰው በፈጠራ ሊያስሯቸው እንደሚችሉ ጠቅሰዋል።ዛሬም በተለያዩ እስር ቤቶች ያሉ የሕጋዊው መኢአድ አመራሮችና ጠንካራ አባላት እንዲፈቱ ጥረታቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸው እሳቸውን ጨምሮ የታሰሩት ሁሉ በአገዛዙ በኩል ሲጠየቁ የነበረው ምርጫ ቦርድ <<መኢአድ>>የሚለውን ስምና ቢሮ ያስረከባቸውን አቶ አበባው መሀሪ ጋር ለምን አብራችሁ አትሰሩም የሚል ጭምር እንደነበር ገልጸዋል።

በአገር ቤትም ሆነ በውጭ አለው ሕዝብ ትግሉ ሞቀ ቀዘቀዘ ሳይል ጠንክሮ የሚፈለገው የሕግ የበላይነትና ዲሞክራሲአዊ ለውት እስኪመጣ መደገፍ መስዋዕት የሚከፍሉትን በርቱ ማለት አለበት ብለዋል። ከአቶ ማሙሸት አማረ ሕጋዊው የመኢአድ ፕ/ት ጋር ከእስር እንደወጡ ያደረግነውን ሰፋ ያለ ቃለ መጠይቅ ሰሞኑን ይዘን እንቀርባለን።

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live