Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ፓስተር ተከስተ ሕጋዊ ሚስቴን በማማገጥ ትዳሬን እንዳልነበረ አድርጎታል የሚለው የአቶ መላኩ የሺዳኛ “ፍትህ በቤተክርስቲያን ጠፋ”አለ

$
0
0

Pastor Tekeste
ፓስተር ተከስተ ሕጋዊ ሚስቴን በማማገጥ ትዳሬን እንዳልነበረ አድርጎታል የሚለው የአቶ መላኩ የሺዳኛ “ፍትህ በቤተክርስቲያን ጠፋ” ሲል ያቀረበው ደብዳቤ

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

↧

↧

ጋዜጠኛ ሠይፉ ፋንታሁን እሁድ ሊሞሸር ነው * የሠርጉን ወጪ ሺህ አላሙዲ ችለዋል

$
0
0

Seifu Fantahun

(ዘ-ሐበሻ)ጋዜጠኛና ኮሜዲያን ሠይፉ ፋንታሁን እሁድ ጷግሜ 1 ቀን 2007 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ሊሞሸር ነው፡፡ የሰይፉ ሚዜዎች ድምፃዊ ታደለ ሮባ፤ አርቲስት ሚኪ(ባለታክሲው ፊልም ላይ የሚሰራው)፤ ጋዜጠኛ ታደለ አሰፋና ሌሎች ሁለት ጓደኞቹ መሆናቸውን ለመረዳት ችለናል፡፡

የሰርጉን ወጪ ሙሉ በሙሉ የሚሸፍኑት ሼህ መሐመድ አል አሙዲ ናቸው፡፡ በዚህ መሰረት ባለፈው ሳምንት ሠይፉ ከአርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ ጋር ወደ ዱባይ አምርቶ ለሰርጉ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ሸማምቶ ተመልሷል፡፡ በሼህ መሐመድ አል አሙዲ የተሰጣቸውን የ165 ሺ ድርሃም በመያዝ ወደዱባይ ያቀኑት ሰይፉና ሰራዊት የሚዜዎችን ልብስና ጫማ ጨምሮ በርካታ ሻንጣ ቁሳቁሶች ገዝተው እንደተመለሱ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልፀውልናል፡፡

↧

የዓባይ ፀሀዬ የመጨረሻው የጭንቀት ንግግር “ካሁን በኋላ መልካም አስተዳደር ካላመጣን በከባድ አደጋ ነው የምንወድቀው”

$
0
0

abay Tsehaye

ከአሰገደ ገብረሥላሴ

ዓባይ ፀሃየ ለሀ ወ ሓ ት ኢ ህ ኣ ደ ግ በሊቀመንበር በድርጅት ሃላፊነት እጅግ ብዙ ኣጃቢና የህወሓት ሎሌ ፓርቲዎች ፈጥረዋል:: በመንግስት መዋቅር በፈደራል ጉዳዮች በስኳር ኢንዱስትሪዎች በጠቅላይ ምኒስቴር አማካሪነት ሰርተዋል:: 40 ዓመት ሙሉ በስልጣን በነበሩበት ቡዙ ስራዎች ፈፅመዋል:: በተለይ በሀወሓት ኢህአደግ ስርኣት ውስጥ ዘርፈብዙ የመልካም ዓስተዳደር የፍትህ የሰብኣዊ ዲሞክራሲ መብቶች መጠበቅ ተጥሰዋል:: በ5 ዙር ሃገራዊ ምርጫ ብዙ ተወዳዳሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች ኣባሎቻቸው ታስረዋል ተገድለዋል:: ካገር ውጭ ተሰደዋል:: ፕሬሶች ተዘግተዋል:: እጅግ በዙ ጋዜጦኞች ታስረዋል ተገርፈዋል ወደውጭ ፈልሰዋል:: በየተሰደዱበት ሞተዋል::

ህወሓት ትላንትና ለደርግ ፋሽሽት እያለ ሲኮንን የነበረ ህወሓት ልክእንደደርግ ንጹሃን ዜጎችም ገድሏል:: የሥቃይ ምርመራ ፈጽሟል:: ይህ ተግባር በጋምቤላ በሁሉ የኦሮሞ ክፍለሃገራት በደቡብ ብሄረሰብ በኦጋዴን በትግራይ በጎንደር በጎጃም በኣዲስአበባ ወ ዘ ተ ተፈፅሟል:: የእምነት ነፃነት ተጥሶ ከሁሉም ኣማኒያነ መሪዎቸነ ተራ አማኒያን በወህኒ ቤት ታጉረዋል:: የሞቱም ኣሉ በመላው የሃገራችን ህዝቦች በትግላቸው ፋሽሽት ደርግ ኣስወግደው ከህወሓት ይጠብቁት የነበረ ሰላም ፍትሕ ነጻነት የህግ የበላይነት ልማትና ፀጥታ መረጋጋት ሁሉም አይነት መብቶች ነበር ግን አልሆነም ውሀ ዘግነው ቀሩ::

በኣንፃሩ ኣባይ ፀሀየና ጓዶቻቸው ኣይናቸውን በጨው ታጥበው ይህችን ሃገር ወደወታደራዊ አገዛዝ ኣስገቧት;:
በኢህአደግ 10ኛ ጉበኤ ሃይለማርያም ደሳለኝ ተዘጋጅቶ አንብበው ተበሎ የተሠጣቸው ሪፖርት ካነበቡ በኋላ አባይ ፀሃየ አስታያየት ሲሰጥ ያረጋገጠልን ቢኖር “ህዝባችን እሥካሁን ድረስ ነገ ከነገወድያ ይሻሻላሉ እያለ ተሸክሞን መጥተዋል በሁሉም መንገድ ፈትኖናል:: ለዚሁ ማሳያ በዘንደሮ ምርጫ ህዝብ እንዳልመረጠን አሳዩቶናል” ብለዋል::
በመጨረሻ አባይ ጸሃየ የተናዘዘው እንዲህ ይላል በአሁኑ ጊዜ ለህዝባችን መልካም አስተዳደር የማረጋገጥ ጉዳይ የሞትና የሽረት ጉዳይ ነው; በመልካም አስተዳደር ስርነቀል ለወጥ ካላመጣን በከባድ አደጋ ነው የምንወድቀው ብለዋል:: ዋዋ አባይ ፀሃየ የትሊያደሩ ነው?

የአባይ ፀሃየ ነገር ግን የሚገርመው ያ 17 ዓመት ሙሉ ታግሎ ተሸክሞ ወደ ሙቅ ወንበር የሰቀላቸው ኋላም 24 ዓመት ሙሉ እየቀጠቀጡት የመጡት ፍትሕ ዲሞክራሲ ልማት ኣጥቶ ወደ ኣረብ ና ኣፍሪካ አውሮፓ የተበታተነው ቀይ ባህር መዲትራንያን ህንድውቅያኖስ ባህር የበላው ወጣት እህት ወንድም ና በትግራይ ያለው ስር የሰደደ ማህበራዊ ችግር ሊታየው አልቻለም ስለሆነም የአባይ ፀሃየ በአሟሻሹ በ11 ኛ ው ሰኣት ኑዛዜ የጭንቀት ነው::

↧

በባህር ዳርቻ ደፋ ብሎ የተገኘው ሶርያዊ ብላቴና

$
0
0

nebyu
የማለዳ ወግ … ለጥቅም አንጅ ለሰብዕና ያልቆመው ፖለቲካ ድምር ውጤት !
=================================
* በባህር ዳርቻ ደፋ ብሎ የተገኘው ሶርያዊ ብላቴና
* “KiyiyaVuranInsanlik”

በቱርክኛ “KiyiyaVuranInsanlik” በተጻፈ አጭር ቃላት የዚህ ልብን ሰባሪ ሶርያዊ ህጻን የተናኘው ከትናንት መለዳ ጀምሮ ነበር ፣ ከስዕሉ ጋር በቱርክኛ የተያያዘውን ይህን ጽሁፍ ወደ እንግሊዝኛ ቀይሬ ተዛማጅ ትርጉም ሰጠሁት ፣ ” ሰብዕና በባህር ዳርቻ ሲረክስ ፣ ሲታጠብ “ በሚል ፣ ይህ አጭር ቃላት በቱርክኛ የተሰታጨው ወደ አረንግሊዝኛ የተቀየረውኛ ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ ለመተርጎም የሞከርኩት ሁሉም ተደምሮ የተሰራጨውም ሶርያዊ ብላና የሰብዕናን ዳራ አልገልጽልህ አለኝ ! መግለጫ ቃላት የማጣቴ የውስጥ የተጎዳ ስሜቴን ስላላረካው መሆኑን ግን የገባኝ ቆይቶ ነበር …
የዚህ ህጻንና ደፋ ብሎ መቅረትን ሳስበው ብዙ ክፉ ደግ በውስጤ ተመላለሰ ፣ በሜዲትራንያን በተሰረጎደው መርከብና አለያም ጀልባ የተጫኑት የተፈናቃይ አረቦችና አፍሪካውያን በጨቋኝ መሪዎቻቸውና በአለም አቀፉ ፖለቲካ የተከላ ሰብዕና ዘልቆ ሰውነቴን አስቆጣው !… ለጥቅም አንጅ ለሰብዕና ያልቆመው ፖለቲካ ድምር ውጤት ብየ መጻፊን አቆምኩት …

በቱርክ የባህር ዳርቻ በግንባሩ ደፋ ብሎ የቀረው ወላጆችስ የት ገቡ ? ይህ አንድ ፍሬ ልጅ ከእጃቸው አንዴት አመለጣቸው ? ነው ወይስ ሁሉም ሲሰጥሙ ተለያዩ ? ቴሌታቢስ ፣ ባርኒስ እያለች አላስነብብ አላስጸደፍ ያለችኝን ማህሌት ልጀን እያየሁ በጥልቅ የሀዘን ስሜት አሰላሰልኩት … ብዙ አሰቃቂ ምስሎችን አይቻለሁ ፣ ይህኛው ደግሞ አንጀት ይበላል ! በስዕሉ ላይ የተጻፈው ሁሉም በዘመናችን የደረስንበትን አሳፋሪ የሰብዕና መርከስ ቅሌት በትክክል አልገልጽልህ አለኝ ። ደግሜ ደጋግሜ አንብቤው አልገባህ አለኝ ! ብላቴናውን ከወደቀበት ያነሳውን ፖሊስ የተከፋ ፣ ተስፋ የቆረጠ አሳዛኝ ስሜትን ነበር ፣ የበሁለት እጆቹ የብላቴናውን ሬሳ አቅፎ ሲወስደው የሚያሳየው ን ተንቀሳቃሸረ የቪዲዮ ምስል እያየሁ ክችም ብያለሁ ፣ የፖሊሱ መከፋት ከወደቀው ህጻን ምስል እኩል አመመኝ …ቱርክኛው “KiyiyaVuranInsanlik” ይላል ” ሰብዕና ረክሶ ክቡሩ የሰው ልጅ ረክሶ በባህር ውሃ ታጥቦ ሲጣል ” ብየ ራሴው አሻሽየ ልተረጉም ብሞክርም አሁንም ስዕሉን የሚገልጽልኝ ቃላት አጥቻለሁ … ይህ ሁሉ መከራ ለጥቅም አንጅ ለሰብዕና ያልቆመው ፖለቲካ ድምር ውጤት ነው! ስል ተነፈስኩት …

23 ስደተኞች በሁለት ትናንሽ ጀልባዎች ከአንካሪላር Akyarlar ጠረፍ ተጭነው ወደ ቡርዱም Bodrum የቱርክ ባህረ ሰላጤ ሲያመሩ አደጋ አጋጠማቸው …ከተጫኑት 23 ሶርያውያን ስደተኞች መካከል አምስት ህጻናትና አንዲት አዋቂ ሴት ሞተው መገኘታቸው ተረጋግጧል ፣ ሰባት ያህል ተርፈዋል ። ሁለት ያህልም ተጨማሪም ተገኝተዋል ። የቱርክ ባህር ኃይል አባላት ብዙዎች ያሉበት ፣ የገቡበት አለመታወቁንና የመገኘት ተስፋ እንደሌላቸው ተናግረዋል !

በህይዎት የሌለ አንድ ቀይ ቲ ሸርትና ሰማያዊ ሱሪ የለበሰ ህጻን በቱርክ ታዋቂ ከሆኑት የቱሪስት መዳረሻ ቡርዱም Bodrum የባህር ዳርቻ ፊቱ ባህር ማዕበል ዘወትር በሚያጥበው አሽዋ ፊቱን ደፍቶ እስከ ወዲያኛው አንቀላፍቷል ! ይህ ማሙየ ሀገራቸው በጦርነት ታምሳ ወደ ቱርክ ከተሰደዱትና ቀን ከከፋባቸው ፣ ብቻውን ውሃ በልቶት የቀረ ያንዱና ያንዷ ልጅ ነው … በያዝነው ዓመት ብቻ የቀይ ባህሩ ሳይጨመር በሜዲትራንያን ባህር ብቻ 2,500 ያህል ስደተኞችም ህይዎት ተቀጥፏል … ጭቆናና ግፍ ቀጥሎ አለም ዝምታን መርጧልና ሰብዕና ረክሷል ፣ ባህሩ ደግሞ አፉን ከፈወቶ ይጠብቀናል … በአፍሪካና የአረብ አንባገነን መሪዎች ያልረጋ ፖለቲካ እየታመሱ ያሉ ዜጎችን አልጠገበም … በልቶ ፣ አጥፍቶ እንደማሙየ ከባህር ሆዱ አውጥቶ ለአውሬ ምግብነት ይጥለናል: (አነሆ ዘመን ስለመክፋቱ አለም ምስሉን እየተቀባበለ ክንፈሩን ይመጣል ፣ ለጥቅም አንጅ ለሰብዕና ያልቆመው ፖለቲካ ድምር ውጤት ስደት ለመሆኑ ገዥዎቻችን ጨምሮ የአለም ኃያላን መንግስታት በሚያውቁት እውነት ሰብዕና ረክሷል !
አቤቱ የዚህን ብላቴና የተገፊዎችን ነፍስ ማር !
ነቢዩ ሲራክ
ነሀሴ 28 ቀን 2007 ዓም

↧

በእስር ላይ የሚገኙ ሦስት የሰማያዊ አባላት በዓለም ላይ ከተመረጡ 20 የፖለቲካ እስረኞች መካከል ተካተቱ

$
0
0

• ሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎች የአንድ ወር ዘመቻ ያደርጉላቸዋል

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

በአሜሪካ መንግስት ኦፊሳላዊ ድረ ገጽ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ አስተባባሪነት በዓለም ላይ ለተመረጡ 20 ሴት የፖለቲካ እስረኞች ለአንድ ወር የሚቆይ ዘመቻና ማስታወሻ ሊደረግላቸው ነው፡፡ ከ20ዎቹ ሴት የፖለቲካ እስረኞች መካከል ሦስቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፣ ሁሉም የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ናቸው፡፡

Nigist
ከዛሬ 20 አመት በፊት ሴቶችን ለማብቃት፣ የጾታ እኩልነትን ለማስፈን እና የልጃ ገረዶችን ሰብዓዊ መብት ለማስጠበቅ የቤጂንግ መርሃ ጉዞ ተቀምጦ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በእነዚህ 20 አመታት ልክ ከዓለም ሀገራት በፖለቲካ እስረኝነታቸው የተመረጡ 20 ሴት እስረኞችን ለማሰብ የሚደረገው ዘመቻ መነሻው ይህ መርሃ ጉዞ ነው፡፡
በዚህ መሰረት ከኢትዮጵያ ብሌን መስፍን፣ ንግስት ወንዲፍራው እና ሜሮን አለማየሁ የተካተቱ ሲሆን ከቻይና እንዲሁ ሦስት ሴት የፖለቲካ እስረኞች ተመርጠው ይታወሳሉ፡፡ ከብዙ ሴት የፖለቲካ እስረኞች መካከል እነዚህ ጥቂቶች መሆናቸውን የጠቀሰው ድረ ገጹ በመስከረም ወር ‹‹ሴቶችን አብቋቸው፣ አትሰሯቸው!›› በሚል መርህ ዘመቻው ይደረጋል፡፡ በዚህም መንግስታት ሴቶችን በፖለቲካ አመለካከታቸው ማሰር አቁመው ማብቃት ላይ እንዲያተኩሩ መልዕክት ይተላለፍበታል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ዘመቻው ለታሳሪ ቤተሰቦችና ለራሳቸው ለታሳሪዎች ብቻቸውን እንዳልሆኑና እንዳልተዘነጉ ለማሳየት ታስቦ እንደሚካሄድ ለማወቅ ተችሏል፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ የሰጡት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣ በኢትዮጵያ ሦስት ሴት የፖለቲካ እስረኞች በዚህ ደረጃ መጠቀሳቸው በሀገራችን ያለውን ስርዓት ዓለም እንደተረዳውና ኢትዮጵያ በመጥፎ እንድትነሳ እያደረጋት መሆኑን ያሳያል ብለዋል፡፡
ዘመቻው እንዲደረግላቸው ከተመረጡት መካከል ከኢትዮጵያና ቻይና ሶስት ሶስት፣ ከቬትናም፣ አዘርባጃንና በርማ ሁለት ሁለት እንዲሁም ከኢራን፣ ግብፅ፣ ኤርትራ፣ ኡዝቤኪስታን፣ ቬንዞዌላ፣ ሶሪያ፣ ሩሲያ/ዩክሬንና ሰሜን ኮሪያ አንድ አንድ ሴት የህሊና እስረኞች ናቸው፡፡

ዘመቻው ‪#‎FreeThe20‬ በሚል መለያ (ሀሽታግ) ይደረጋል፡፡
http://www.humanrights.gov/freethe20/

↧
↧

Health: ስኬታማ ትዳር እንዴት ይፈጠራል?

$
0
0

የዘመናችን አባባል ሆኖ ነው መሰልኝ «ባል ጠፋ፣ ሚስት የታል?» የሚሉ ሃሳቦች ሲሰነዘሩ እንሰማለን። እውነት ባልም ሚስትም ጠፍተው ነው? ሰው ትዳርን ሽሽት የጀመረው ወይስ ሌላ ምክንያት አለ ? ስል ሁሌ ራሴን እጠይቃለሁ። ምላሽ ባላገኝለትም። ለራሴ የማቀርበውን ጥያቄ የብዙዎች በመሆኑ ለምን የባለሙያ ምላሽ አይሰጥበትም በማለት ማፈላለግ ጀመርኩ። ተሳካልኝና የጋብቻና የቤተሰብ አማካሪውን አቶ ይመስገን ሞላን አገኘሁ። የእርሳቸውን አጠቃላይ ማብራሪያ ከማስቀደሜ በፊት በትዳር ውስጥ ያሉና ትዳርን በሩቁ የሚፈሩ ግለሰቦችን አስተያየት ለማስቀደም ወደድኩ። 

መጀመሪያ ያናገርኩት ወጣት ዮሐንስ አለማየሁ ይባላል። የመጀመሪያ ድግሪ ምሩቅ ሲሆን፤ በአንድ የመንግሥት መስሪያ ቤት ተቀጣሪ ነው። ይህ ወጣት ወደ ትዳር ለመግባት የሚስት መጥፋት ብቻ አይደለም ማነቆው ይላል። በእርሱ ሃሳብ ትዳርን ለመጀመር ሦስት ነገሮች ያሰጉታል። አንደኛውና ዋንኛው እርሱ «ነፃነቴ» የሚለውን እንደ ልብ መውጣት መግባት፣ ያለ ሃሳብ ለራስ ብቻ መኖርን ወደ ትዳር ሲገባ እንደሚያጣው ማሰቡ ነው። ብቻውን በሚኖርበት ወቅት ከሚያደርጋቸው ነገሮች መታቀቡ ነፃነትን እንደመሸጥ ነው የሚቆጥረው። ሁለተኛው ደግሞ ለማግባት የሚያስባት ሴት ባህሪ «ቢቀየርብኝስ» የሚል ስጋት ስላሳደረበት ነው። ሦስተኛው ምክንያቱ የትዳር በር ላይ ቆሞ ሲመለከት ቤተሰብ የማስተዳደር አቅም ላይ ስጋት ይይዘዋል። ከአንድ ሁለት ከሁለትም ሦስት በሚሆንበት የትዳር ሂደት ውስጥ የተሻለ ገቢ የማይኖር ከሆነ «እንዴት ይገፋል?» የሚለው ዮሐንስ «ምን አለኝ» እያለ የብቸኝነት ኑሮውን በመግፋት ላይ መሆኑን ነው ያጫወተኝ። 

marraige

ሌላዋ ወጣት ትንሳኤ ተስፋዝጊ «ባል ጠፋ» ከሚሉት ወገን ናት። ይቺ ወጣት ሴትነት ወደ ማዕድቤት በሆነበት የሃገራችን ወንዶች አመለካከት ለበለጠ ኃላፊነትና የሥራ ጫና መታጨት አልፈልግም የሚል አመለካከት አላት። በነፃነት እንደልቧ ወጥታ ከምትገባበት የቤተሰብ ኑሮ ወጥታ የራሷን ቤት መመሥረት ከባድ ኃላፊነት ሆኖ ነው የሚሰማት። «ትዳርን ሳስብ ይህን ኃላፊነት መሸከም እችላለሁ ብዬ ማሰብ ስለሚከብደኝ እፈራለሁ» የምትለው ትንሳኤ ከዚህም ሌላ ስጋት አላት።

«የሀገራችን ወንዶች መበለጥንና የሴት የበላይነትን መቀበል አይፈልጉም» ትላለች። እርሷ ደግሞ የማስትሬት ድግሪ ደረጃን የያዘች በመሆኗ የምትፈልገውን ዓይነት ባል ማግኘት ጭንቅ ሆኖባታል። «የተሻለ ደረጃ ላይ ያለው በጉራ እየተወጠረ የበታች የሆነው ደግሞ የራስ መተማመን መንፈስ እያጣ ባል የሚሆን ሰው ጠፍቶኛል።» ትላለች። 

ትዳርን ሲያስቡት ከሚፈሩት ወጣቶች አስተያየት ከሰበሰብኩ በኋላ አዲስ ተጋቢዎችን ምን ገጠማችሁ? አልኳቸው። መጀመሪያው አካባቢ ለምን ሁሉም ሰው አያገባም የሚያሰኝ ጣፋጭና አስደሳች የፍቅር ጊዜ እንደነበረ የምትናገረው ወይዘሮ በእምነት ታዬ ናት። «ያ ጣፋጩ የፍቅር ጊዜ ተጠናቆ እውነተኛ ማንነት ሲገለጥ ከባዱ ፈተና ይጀምራል። አዲሷ ሙሽሪት ከሁሉ ነገር በላይ አሰልቺ የሆነባት የማያቋርጥና የእርሷን ኃላፊነት ብቻ የሚጠብቀው የቤት ወስጥ ሥራ ነው» በማለት ነው የምትገልጸው።

«ወላጆቼ ጋር እያለሁ እኔ ስፈልግ ብቻ ነበር በቤት ውስጥ ሥራ ተሳታፊ የምሆነው። በትዳር ውስጥ ያለውን የሥራ ጫና መቋቋም እቅቶኛል» የምትለው ወይዘሮ በእምነት በቤት ውስጥ ኃላፊነት በመጠመዷ ቀደም ሲል ለራሷ ብቻ የምትሰጠውን ጊዜ እንኳን ልታገኝ አለመቻሏን ትናገራልች፡፡

ሌላው የመጀመሪያ ችግር የሆነባት ተነጋግሮ መግባባት ያለመቻል ጉዳይ ነበር። «በፊት አንቺ እንዳልሽ ሲል የማውቀው የትዳር አጋሬ በእያንዳንዱ ነገር ተፅዕኖ ለማድረግና የእርሱን ንግግር ብቻ እንዳዳምጥ መፈለጉ ጭራሽ የማላውቀውን ሰው ነው እንዴ ያገባሁት? እንድል አድርጎኛል» ትላለች። ያምሆኖ ከተጋቡ 10 ወራትን ያስቆጠሩት እነ በእምነት ግንኙነታቸው ከዕለት ወደ ዕለት እየተሻሻለ መሄዱን አልደበቀችም። ትዳርም ቀድማ የፈራቻቸው የችግሮች ጥርቅም ሳይሆን በራሱ ከባድ ችግሮችን ተጋፍጦ የመቆየት ሂደት መሆኑን ነው የተማረችበት።

ትዳር የሁለት የተለያዩ ሰዎች ውህደት ውስጥ የሚፈጠር ጭንቀት ነው የሚለው ደግሞ አቶ ገመቺስ ጉደታ ነው። ዘወትር ግጭት፣ ጭቅጭቅ፣ ዝንት ዓለም ያለመግባባት ያለበት የሚመስለውን ትዳር በመተሳሰብ የተሻለ ማድረግ ይቻላል ባይ ነው።

አቶ ገመቺስ እያንዳንዱ በገንዘብ በኩል የሚመጡ ኃላፊነቶች ጫንቃው ላይ የወደቁ እስኪመስለው ድረስ በከባድ ውጥረት እራሱን ሲያስጨነቅ የቆየባቸውን ያለፉትን ጊዜዎች ሲያስብ ይቆጫል። «እንዲህ እንደአሁኑ በፕሮግራም መመራት እየተቻለ ምን ነበር ያስጨነቀኝ» ሲል ራሱን ታዝቧል።

በትዳር ውስጥ ያሉና ትዳርን በሩቁ የሚፈሩ ግለሰቦች የሰጡኝን አስተያየት ይዤ ወደ ሥነልቦና ባለሙያው አቶ ይመስገን ሞላ አመራሁ። የእርሳቸው ሙያዊ ማብራሪያ ለሁላችንም ምላሽ ይሰጣልና እንደሚከተለው አቀረብኩት።

ስኬታማ ትዳር የሚባለው ብለው ይጀምራሉ ባለሞያው «ስኬታም ትዳር የሚባለው ሁሉም እንዳለበት ቦታ ሲሆን ነው። ይህ ማለት ደግሞ ባልም እንደባል፣ ሚስትም እንደ ሚስት፣ ልጅም እንደ ልጅ ሲሆኑ ነው የቤተሰቡን ግንኙነት ጤናማ የሚያደርገው። የትዳር ሕይወትም መልካም ድምዳሜ ሲኖረው ስኬታማ ይባላል። ሁሉም መድረስ የሚገባው ላይ ሲደርስ ነው ስኬት ተብሎ የሚጠራው። 

ከጋብቻ በፊት አንድ ግለሰብ በሁሉም አቅጣጫ እራሱን መሳደግ አለበት። ማለትም በገንዘብ በአዕምሮና በሌሎች መልኩ ማለት ነው። በየአቅጣጫው ራሱን የገነባ ሰው ሌላ ትክክለኛ ሰው ለማግኘት አይከብደውም። ይህ ከሆነ ደግሞ ከሁለት በትክክለኛ ሰዎች የተስተካከለ ትዳር ይመሠርታሉ። ለራሱ ክብር ያለውና ሙሉ ለሙሉ ትክክለኛ እንደሆነ የሚያምን ሰው ትክክለኛ ያልሆነ ሰው አያገባም እራሱንም በደንብ ስለሚያከብር ለማያከብረውና ዋጋውን ለሚያወርድበት ሰው ራሱን አሳልፎ አይሰጥም።

አንድ ሰው ማግባት ያለበት ዕድሜ ላይ ሲደርስ ለዕድሜው የሚመጥን አመለካከት ያለው ሰው ይሆናል ማለት ነው። ዋንኛው የትዳር መሠረት ባህሪ ሲሆን፤ ማንም ሰው ያለበትን መጥፎ ባህሪ ለማስተካከል ዓመታት አይወስድበትም። ጋብቻም ከመታሰቡ በፊት አለብኝ ብሎ የሚያምናቸውን ባህሪያት ማስወገድ የግድ ይላል።

የጋብቻ መጀመሪያ አካባቢ ሁለት የግል ሕይወትና የግል ማንንት ያላቸው ሰዎች እንጋባ ብለው ሲጀምሩ ከሁለት የተለያዩ ማንነቶች የመጡት ሁለቱ ሰዎች በተለይ እንደተጋቡ ሰሞን የጫጉላ ወቅት ትዳር ደስታ ብቻ ነው የሚሆነው። 

በሁለተኛው ደረጃ ከትንሽ ቆይታ በኋላ ነገሮች እንደተገመቱት አይሆንም። ይሆናል የተባለው ሁሉ ሳይሆንና የተገመተው ሲቀር ግጭቱ ከውስጥ ይጀምራል። እነዚህ ግጭቶች ግን ችግር ሳይሆኑ ሂደቶች ናቸው። ብዙ ሰዎች እነዚያን ሂደቶች በአግባቡ ማስሄድ ባለመቻላቸው ወደ ችግርነት ይቀየራሉ። 

ሁለት የተለያዩ ሰዎች ሃያ ምናምን ዓመት በተለያየ ቤት፣ በተለያየ ኑሮ ፣በተለያየ ፍላጎት ፣ በተለያየ ባህል በተለያየ እውቀት አድገው አብረን እንኑር ሲሉ እንዲያውም የሚገርመው ባይጣሉ ነበር። መጣላታቸው ሁለቱም ራሳቸውን እየገለጹ ውስጣቸውን እያሳዩ ወደመተዋወቅ የሚያደርጉት ሂደት ነውና ይሚጠበቅ ነው።

ይህን ችግር ለመፍታት ግን እንዴት መግባባት እንደሚችሉ ማወቅ የግድ ነው። አንድ ሰው ምን እንደሚናገር ሳይሆን እንዴት እንደሚናገር ማወቅ አለበት። በየቀኑ በመጨቃጨቅ ወደቤት መግባት አስጠላኝ እስከሚባልበት ድረስ ማደግ የለበትም። ጭቅጭቅ የሚከሰተው አንድ ሰው የራሱን እምነት ማስረዳት ብቻ ስለሚፈልግ ነው። ይህ ሲሆን ደግሞ የትዳር አጋሬ ምን ሊል እየፈለገ ነው ብሎ ማዳመጥ እጀግ በጣም ተገቢ ነው። ለዚህም ነው መልስ ለመስጠት ከመቸኮል ይልቅ መደማመጥ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው የሚሆነው።

በጣም የሚገርመው በማይጠቅሙና በማይገቡ ነገሮች ሰዎች መጨቃጨቃቸው ነው። ለምሳሌ አንድ ሰው ዕቃ ግዛ ተብሎ ረስቶቢገባ ለምን እንደረሳ መጠየቅና ማወቅ ተገቢ ነው። መርሳቱን ምክንያት አድርገው የሚፈጠሩ ምልልሶች ናቸው ጭቅጭቅ የሚሆኑት። የማይገቡና የማያስፈልጉ ባዶ ንዝንዞችን መተው የግድ ነው። ተግባቦት ማለት የሌላ ሰው ሃሳብና ሰሜትን መረዳት ነው፡፡ ያንን ለማድረግ አዳማጭ መሆን አስፈላጊ ነው። ስህተቶችን ለማረምና ለመረዳዳት ዕድል ይሰጣል።

ጋብቻ የጋራ ሕይወት ስለሆነ የየጋራ ኃላፊነትን ለመወጣት ማሰብ ችግሮችን የቀለለ እንዲሆን ያደርገዋል። ሁሉም ሰው የየራሱ ደርሻ አለው። የየራስ ኃላፊነቶችን በመወጣት ደረጃ ግንኙነት ሲደረግ መተጋገዝ ይሆናል። አንዱ የሌላውን ኃላፊነት ደርቦ መያዘ የነገን ግንኙነት አሰልቺ እንዲሆን ያደርገዋል። ይህ ደግሞ አደገኛ ነው። 

ልጆች ከተወለዱ በኋላም ባልና ሚስቶች ራሳቸውን በብዙ ነገር ማዘጋጀት አለባቸው። ካልሆነ ግን የቤተሰቡ ቁጥር እየጨመረ ሲመጣ የፍላጎትና የገቢ አለመመጣጠን ሲመጣ የሚያጋጩ ነገሮችም አብረው መፈጠራቸው አይቀርም። ለስኬታም ትዳር ባል እንደመሪ ሆኖ ሙሉ ለሙሉ የቤተሰብ ኃላፊነትን የሚወጣ ሲሆን፤ ሚስት እንደ ሽንፈት መቁጠር የለባትም። ሚስትም መሪዋን በማገዝ ሃሳብ በመካፈል መደገፍና ቤተሰቧን ማቆም ትችላለችና፡፡ 

ስኬታማ ትዳር ለመመሥረት መነጋገር፣ መደማመጥ፣ መከባበርና የሚከሰቱ ችግሮችን እንደ አመጣጣቸው መቀበል ያስፈልጋል። ይህን ለማድረግ የተዘጋጁ ተጋቢዎች የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ሁሉ በቀላሉ ለመፍታት አይቸገሩም። ውይይታቸው ወይም ንግግራቸው ወደ ጭቅጭቅ አያመራም። አንዳንድ ግለሰቦች ከውጪ ሆነው በሚፈጥሩት ጭንቀት ብቻ ትዳርን ጭራቅ አድርገው መሳላቸው ተገቢ አይሆንም። በመሆኑም በቅድሚያ በትዳር ለመጣመር ከማሰባቸው በፊት ራሳቸውን ለትዳር ዝግጁ ማድረግ ይገባቸዋል። ያኔ የተሳካ ትዳር ይሆንላቸዋል።

ጸሐፊ አስመረት ብስራት 

↧

የእንግሊዝ ቪዛ የተከለከሉት ፕሮፌስር መስፍን ወ/ማርያም አሜሪካ ገቡ

$
0
0

Mesfin Woldemariam

(ዘ-ሐበሻ) ወደ እንግሊዝ ሃገር የሚያስኬዳቸውን ቪዛ ተከልክለው ወደዚያው ሊያደርጉት የነበረው ጉዞ የተስተጓጎለባቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ፕሮፌሰር መስፍን ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ መግባታቸውን በስፍራው የሚገኙ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አስታወቁ::

በቅርቡ ‘አዳፍኔ’ የተሰኘ ‘አወዛጋቢ’ መጽሐፍ ለንባብ ያበቁት እኚሁ ፕሮፌሰር ዛሬ ዋሽንግተን ዱሉስ ኤርፖርት ሲደርሱ ወዳጆቻቸው ሞቅ ያለ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አስታውቀዋል::

ፕሮፌሰር መስፍን በአሜሪካ ቆይታቸው አዲሱ መጽሓፋቸውን በዋሽንግተን ዲሲ በሸራተን ፔንታጎን ሲቲ እሁድ ሴፕቴምበር 13, 2015 ዓ.ም ከ2 ሰዓት ጀምሮ ያስመርቃሉ:: በዚህም ወቅት የሕዝብ ጋር ወቅታዊ ውይይት እንደሚያደርጉ አዘጋጆቹ ለዘ-ሐበሻ ከላኩት ፍላየር (በራሪ ወረቀት) መረዳት ተችሏል::

ፕሮፌሰር መስፍን እንግሊዝ ሃገር በተለያዩ ጊዜያት ቢመላለሱም ዘንድሮ ቪዛ መከልከላቸው ብዙዎችን አነጋግሩዋል። የእንግሊዝ መንግስት ቪዛ የከለከለበት ምክንያት በዚያው ሊቀሩ ይችላሉ በሚል ነው።

↧

የተደበቀው የህወሓት ማንነት ከደደቢት እስከ ቤተ መንግስት – (ክፍል 5) ነብሰጡር ሴቶችና አዛውንቶች ሳይቀሩ በስለት ታርደዋል

$
0
0

meles zenawi funeral
==============================================
“…ሰፊው የትግራይ ህዝብ ስራ አጥቶ በሴተኛ አዳሪነትና ስደት ብቻ ሳይሆን በርሃብ፣ በድንቁርና እና በሽታ እየተሰቃየ በመኖሩ ምክኒያት ጠብመንጃ አንስተን በርሃ ለመውረድ ቻልን…”
ብሎን ነበር ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ያኔ በሽፍትነት ዘመኑ በ1968 ዓ.ም ባሳታመው የፖለቲካ ፕረሮግራሙ ከወደ ደደቢት፡፡
ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ይህን ካለ ከ40 ዓመታት በኋላ ዛሬም ረሃብ፣ በሽታ፣ ስራ አጥነት፣ ሴተኛ አዳሪነት፣ ድንቁርና እና ስደት አለ፡፡ እንዴውም ያን እሱ የተቸውን ዘመን በመሚያስመግን ሁኔታ፡፡ ታግየለታለሁ የሚለውን ትግራይን ጨምሮ መላው የኢትዮጵያ ወጣት በየቀኑ በግፍ ይሰደዳል፡፡
ስደትን አስቆማለሁ ብሎ ጠብመንጃ ያነሳው ህወሓት በስልጣን ዘመኑ ለዕልፍ አዕላፍ ኢትዮጵያዊያን ተሰዶ በባህር በዱር በገደልና በበርሃ ማለቅ ዋነኛ ምክኒያት ሆነ፡፡
ድህነትን ከአገራችን ምድር አጠፋለሁ ብሎ ታጥቆ የተነሳው ህወሓት ኢትዮጵያን ከኒጀር ቀጥላ የዓለም ሁለተኛዋ መናጢ ደሃ አገር ሆና በውርደት መዝገብ ስሟ እዲሰፍር አድርጎ ገናና ታሪኳን ሙልጭ አድርጎ ከምድረ ገፅ አጠፋው፡፡
ኮሌጅ የበጠሱ ወጣቶች የህወሓት ትምህርት ሜኒስቴር የሰጣቸው ክርታስ እንጀራ ሊያስቆርሳቸው ባለመቻሉ ረጅም የስደት ጅረት በመፍጠር ልክ እንደወንዞቻችን የተፈጥሮ ሀብታችንን ተሸክመው ያለማቋረጥ ወደ ውጭ መፍሰሳቸውን ቀጥለዋል፡፡ የመን ውስጥ ብቻ 800 ሺህ ወጣቶች እንደሚገኙ ዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት /I.O.M/ ያወጣው ሪፖርት ያረጋግጣል፡፡
“ተስፋ ብቻ ያዘሉ ፍሬ ቢስ ባዶ አዎጆችና መግለጫዎች በየጊዜው ይለፈፋሉ፡፡ እነዚህ ከእውነት የራቁ መግለጫዎችና ጽሁፎች በመገናኛ መስመሮች በጭቁን ህዝብና በአገር ስም ይታወጃሉ፤ የዓዋጆች ዓላማ የህዝቡን አስተሳሰብ ለማደናገርና ወታደራዊ ደርግ በስልጣን ለመቆየት ያለው ፍላጎት እደዚሁም ቡድናዊ ጥቅም ለመጠበቅ ሆን ተብሎ የሚደረግ የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ነው…” በሽፍትነት ዘመኑ ይህን ይፅፍ የነበረው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ በለስ ቀንቶት ከደደቢት ምኒልክ ቤተ መንግስት ከገባ በኋላ “የላም አለኝ በሰማይ” አሰልቺ ዲስኩሩን ውሽንፍር ከጠባቡ የአዕምሮው አድማስ ወደ ሰፊዋ ምድር እያወረደና የመኖር አድባር ተራሮችን በሃሰት መባርቅት እያረሰ የፈጠራቸው በተስፋ ውሃ የተሞሉ ኩሬዎች ግማት ህዝብ አፍንጫና አፍን በእጆቹ ሸፍኖ ሽሽትን እንዲመርጥ ጋበዘው፡፡ ህዝቡን ከመደናገር ጉድጓድ እግሮቹን አውጥቶ ለቡድናቸው ጥቅም ብቻ የቆሙ ስልጣናቸውን ለማራዘም ከሚያደርጉት የማወናበድ ድርጊት ሊያባንነው የተነሳው ህወሓት የኢትዮጵያን ህዝብ የባሰውን ወደ መደናገር ሸለቆ በመወርወር ከሸለቆው አፋፍ ላይ የሚገኝ የስልጣን ጉብታ ላይ ተኮፍሶ ወደታች አዘቅዝቆ እያየ በመገልፈጥ ለ24 ዓመታት በመከራው አላገጠበት፡፡
የሚሊየነር ቡድኖችን ፈጥሮ ሚሊዮኖችን የበይ ተመልካች አደረጋቸው፤ ጫት አቅራቢ፣ መጠጥ ቸርቻሪ ሆኖ የወጣቶችን አዕምሮ በማደንዘዝ ሃሳባቸውን አኮላሽቶ በአጭር በማስቀረት በቁማቸው እንዲያንቀላፉ አደረጋቸው፡፡
“ጊዜው ያለፈበት የኢኮኖሚ ስርዓት ባስከተለው ብዝበዛ ምክንያት በህብረተሰቡ ውስጥ ያሉት መሰረታዊ ችግሮች ድንቁርና፣ በሽታ፣ ድህነትና ርሃብ የመሳሰሉ እንደዚሁም መደቦችና የመደብ ብዝበዛ ለማጥፋት ህወሓት የማያቆርጥ ትግል ታደርጋለች…” ሲል በፖለቲካ ፕሮግራሙ ላይ የፃፈው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ራሱን በበዝባዦች መደብ ላይ አስቀምጦ ብቸኛው በዝባዥ ሆኖ በወፍ ዘራሽነት በኢትዮጵያ ጥቁር አፈር ላይ በመብቀል ልክ እንደ ባህር ዛፍ ስሩን አስረዝሞ የሌሎች ተክሎችን ምግብና ውሃ እየተሻማ አጠውልጎ በቁማቸው አደረቃቸው፡፡ ኢትዮጵያችን የድንቁርና፣ በሽታ፣ ድህነት፣ ርሃብና ስደት አሜኬላ ከባህር ዛፍ እግር ስር በቅለው የተንሰራፉባት ምድር ሆነች፡፡ በተጨማሪም ህወሓት የፖለቲካ እሳት መንዶውን ባንድ እጁ የማህበራዊ ሾተሉን በሌላኛው ዕጁ አንስቶ በህዝቡ ገላ ላይ እያሳረፈ 40 በመግረፍ አገራችንን የባሰውኑ ምድራዊ ሲኦል አደረጋት፡፡ በዚህ የተነሳ ዜጎች ሲኦልን ሽሽት ግን ወደ ሌላኛው ይሻላል ብለው ወደ ገመቱት ሲኦል መጓዛቸውን ያለምንም ፋታ ተያያዙት፡፡ በህወሓት ኃጢያት ተኮንነው ገኀነም በመግባት ትልቅ ዋጋ በመክፈል ላይ ናቸው፡፡
ትናንትና በስለት አንገት አንገታቸውን የታረዱት ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች በግፍ የፈሰሰ ደም ከሊቢያ ምድር ላይ ሳይደርቅ ዛሬ ደግሞ ሱዳን ላይ በርካታ ወጣቶች በአሰቃቂ ሁኔታ እየተገደሉ ኩላሊታቸው በመውጣት ላይ ነው፡፡
እልቂቱ፣ ግፍና መከራው፣ መሰደድና መፈናቀሉ፣ ፍዳና ሰቆቃው፣ በስለት መታረዱና በጥይት መጨፍጨፍ፣ ውርደትና ክብር ማጣቱ… በሰው አገር ብቻ ሳይሆን በገዛ አገራችንም በባሰ ሁኔታ መፈፀሙ የእኛን የኢትዮጵያዊያንን ችግር እጥፍ ድርብ ያደርገዋል፡፡ ወጣቶች ከመከራ ላይ የመከራ ካባ ደራርበው እንዲለብሱ ከሰቆቃ ላይ ሌላ የሰቆቃ ሸማ እዲጎናፀፉ ያደርጋቸዋል፡፡
ሳዑዲ አረቢያ ላይ የደረሰው መፈናቀል በኢትዮጵያችን ምድር ላይም በህወሓት ተከስቷል፡፡ ኢትዮጵያዊያን በቋንቋቸው ዘራችሁ ሌላ ነው ተብለው ከቤንች ማጅ ዞን ጉራ ፋርዳ ወረዳ ከሌሎችም በርካታ አካባቢዎች ቤት ንብረታቸውን እየተነጠቁ በተደጋጋሚ ተባረዋል፡፡
በቅርቡ በሊቢያ ውስጥ በአይሲስ የተፈፀመው የ30 ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በስለት መታረድና በጥይት መጨፍጨፍ፤ አርባ ጉጉ በደኖ ላይ ዘራችሁ ሌላ ነው ተብለው ዕልፍ አዕላፍ ኢትዮጵያዊያን ገና ነብስ ያላወቁ ህፃናት፣ ነብሰጡር ሴቶችና አዛውንቶች ሳይቀሩ በስለት ታርደዋል፤ ህወሓት በሳለው ጎራዴ አካላቸው ልክ እንደ ዶሮ ተበልቷል፡፡
ጋምቤላ ውስጥ አኙዋኮች ብቻ እየታደኑ በህወሓት ሰራዊት መትረየስና ክላሽን ኮቭ ተጨፍጭፈዋል፡፡
በ1997 ዓ.ም ድምፃችን ተዘረፈ ብለው ለተቃውሞ ሰልፍ አደባባይ የወጡ ወጣቶች ከትምህርት ቤት የሚመለሱ ህፃናትን ጨምሮ በአልሞ ተኳሽ ግንባር ግባራቸውን ተመትተው ሰቅጣጩ አስከሬናቸው በየጎዳናው ተልከስክሷል፡፡

የህወሓት ድብቅ ሴራዎች

ህወሓት በሽፍትነት ዘመኑ 17 ዓመታት ሙሉ ሴራ ሲጎነጉን፣ ሸፍጥ ሲሰራ፣ የተንኮል ዕቅድ ሲነድፍ፣ የጠልፎ መጣል ስልት ሲያቀነባብር፣ ያለምንም ድካምና ዋጋ እንዲሁም ዕውቀት የስልጣን ኮረቻ ላይ ለመፈናጠጥ የሚያስችለውን የሀሳብ ቀመር ሲቀምርና የዘር ሂሳብ ሲያሰላ ነበር የኖረው፡፡ ህወሓት በአውደ ውጊያ ካሳለፋቸው ዓመታት ይልቅ በየዋሻውና በየሸለቆው አድፍጦ የጥፋት ሴራ ሲጠነስስ የነበረባቸው ዓመታት ይበልጣሉ፡፡
የግራ ርዕዮተ ዓለም የሚያራምዱትን ሲያገኝ የሶሻሊስትነት ካባ ደርቦ በመቅረብ የቀኝ ርዕዮተ ዓለም ከሚያራምዱት ፊት ደግሞ ማርክሲስት ሌኒንስት ካባውን ሳያወልቅ የሌበራልነት ካባ በላዩ ላይ ደርቦ በመታየት እንደ እስስት ቆዳውን በመቀያየር በመስሎ አዳሪነት ባህሪውም የሚያክለው የለም፤ ሴተኛ አዳሪው ድርጅት ህወሓት፡፡
ህወሓት በሽፍትነት ዘመኑ ከአረብ አገራት እርዳታ ለማግኘት በማለም የውጭ ጉዳይ ኃላፊ የነበረውን ስዩም መስፍንን ስሙን ቀይሮ ስዩም ሙሳ ተብሎ እንዲጠራ አድርጓል፡፡
ህወሓት ገና ስሙን ሳይቀይር ተሓህት/ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ/ ይባል በነበረበት ወቅት ግገሓት/ ግምባር ገድሊ ሓርነት ትግራይ/ ከተባለው ከእሱ በፊት ተመስርቶ በትግራይና በኤርትራ አዋሳኝ መሬቶች ላይ ይንቀሳቀስ በነበረው የታጠቀ ድርጅት ጋር ሙሉ በሙሉ ውህደት ለመፈፀም ስምምነት ላይ ደርሳል፡፡ ቀጥሎም ሁለቱ ድርጅቶች ማለትም ተሓህት-ህወሓት እና ግገሓት ውህደት ወደሚፈፅሙበት ቦታ ምስራቅ ትግራይ ዘገብላ ተብላ ወደ ምትጠራው ቦታ ሰራዊታቸውን ወስደው ካሰፈሩ በኃላ አመሻሽ ላይ የተሓህት-ህወሓት አመራሮች ቀን ሲሸርቡት የዋሉትን ሴራ ለሰራዊታቸው በጠቅላላ በምስጢር እዲተላለፍ አደረጉ፡፡ ይህም እያንዳንዱ የተሓህት-ህወሓት ታጋይ ከግገሓት ታጋይ ጋር ጥንድ ጥንድ እየሆኑ እንዲተኙና ግገሓቶች እንቅልፍ ወስዷቸው የተኩስ ትዕዛዝ እስኪተላለፍ በንቃት እዲጠባበቅ የሚል ነበር፡፡
ከዚያም እኩለ ሌሊት ላይ የግገሓት ሰራዊት በእንቅልፍ ላይ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ የተሓህት-ህወሓት ታጋዮች ከጎን ከጎናቸው ከተኙ የግገሓት ታጋዮች ላይ እንዲተኩሱ በምልክት ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ለውህደት የመጣው የግገሓት ሰራዊት ከነመሪዎቹ በእንቅልፍ ላይ እንዳለ ተጨፍጭፎ ሙሉ በሙሉ ተደመሰሰ፡፡
ምክትል ፕረዝዳንቱን ፍስሃ ደስታን ጨምሮ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ከፍተኛና ዝቅተኛ የደርግ ባለስልጣናትን ራሱ ደርግ እንዲረሽናቸው ህወሓት በ1970 ዓ.ም አንድ ሴራ ጠንስሶ ሙሉ በሙሉ ተሳክቶለታል፡፡
ህወሓት ደርግ እንዲረሽናቸው የሚፈልጋቸውን በከፍተኛና ዝቅተኛ የመንግስት አመራር የሚገኙ የትግራይ ብሄር ተወላጆችን ስም ዝርዝር በቀላሉ ሊሰበር በሚችል ኮድ በማስፈር እና ለህወሓት የሰሩትን ስራ ከጎን በመፃፍ ሐሰተኛ ደብዳቤ አዘጋጅቶ የከተማውን የህቡ እንቅስቃሴ ከሚመራው ተክሉ ሃዋዝ የተባለ ታጋይ ለሊቀመንበሩ አባይ ፀሃዬ የተላከ በማስመሰል ሶስት ታጋዮች ደብዳቤውን ይዘው ወደ አክሱም ከተማ እዲገቡ ካደረገ በኃላ ራሱ በተዘዋዋሪ መንገድ ጠቁሞ በደርግ ደህንነቶች ቁጥጥር ስር እንዲውሉ አስደርጓቸዋል፡፡
ከዚያም ከተክሉ ሃዋዝ ለአባይ ፀሐዬ እንደተላከ ተደርጎ የተዘጋጀው ደብዳቤ ከደርግ ደህንነቶች እጅ ይገባና ወደ መቀሌ ተልኮ ኮዱ ተሰብሮ ሰም ዝርዝራቸው ሰፍሮ የተገኙት በከፍተኛና ዝቅተኛ የመንግስት አመራር ውስጥ የሚገኙ ዕልፍ አዕላፍ የትግራይ ተወላጆች እየታደኑ ወደ ወህኒ ተወስደው አሰቃቂ ምርመራ ከተደረገባቸው በኋላ ያለ ኃጢያታቸው ተረሸኑ፡፡
ህወሓት ባዘጋጀው ሃሰተኛ ደብዳቤ ላይ አባሎቹ እንደሆኑ አስመስሎ ስማቸውን ከዘረዘራቸው የትግራይ ተወላጅ ከሆኑት የደርግ አመራሮች ምንም ሳይሆን የቀረው ፍሰሃ ደስታ ብቻ ነበር ፡፡
ህወሓት ከተመሰረተበት ከ1967 ዓ.ም እስከ 1977 ዓ.ም ድረስ በነበሩት 10 የሽፍትነት ዓመታት ውስጥ ከአመራሩ ውጭ ያሉ ታጋዮች ፆታዊ ግንኙነት ካደረጉ ያለምንም ምህረት ይረሸኑ ነበር፡፡ በመሆኑም ፆታዊ ግንኙነት አድርገው የተነቃባቸው የህወሓት ታጋዮች ከመረሸን ለመዳን ለደርግ እጃቸውን ይሰጡ ነበር፡፡
በፆታዊ ግንኙነት ምክንያት በየጊዜው የሚከዱ ታጋዮችን ደርግ በጥሩ ሁኔታ እደሚቀበላቸው መረጃው የደረሰው ህወሓት ይህን ተንተርሶ ሴራ ጠነሰሰ፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሴት ታጋዮችን ፆታዊ ግንኙነት አድርገው እንዲያረግዙ ቀጭንና የማያዳግም መመሪያ አወረደ፡፡
መመሪያ የተሰጣቸው በርካታ ሴት ታጋዮች ካገኙት ወንድ ታጋይ ጋር ሁሉ ልክ እንደ እንስሳ ፆታዊ ግንኙነት በማድረግ አርግዘው የህወሓትን መሪዎች ቀጭን ትዕዛዝ ተግባራዊ አደረጉ፡፡ ቀጥሎም የህወሓት መሪዎች እርጉዞቹ ታጋዮች ለደርግ እጃቸውን ሰጥተው በምስጢር እንዲሰልሉ አዘዙ፡፡
ይህ የሰውን ልጅ ከሰውነት ወደ እንስሳነት ተራ የሚያወርድ ሴራ እና ለስልጣን ሲባል በሴት ልጅ ላይ የተፈፀመው ግፍ በሴት ታጋዮች ላይ የሞራል ውድቀትና ሰቆቃ ከማስከተሉ በስተቀር ለህወሓት ከዚህ ግባ የሚባል ውጤት አላስገኘለትም፡፡
በጦር ሜዳ ተዋግቶ ከማሸነፍ ይልቅ በቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ አድፍጦ ሴራ መጎንጎን የሚቀናው ህወሓት ደርግን ከትግራይ ህዝብ ነጥሎ እሱ ሰፊ ድጋፍ የሚያገኝበትን ሌላ ሼር ደግሞ ጠነሰሰ፡፡
እሱም “የሀውዜን ጫፍጨፋ” በመባል የሚታወቀው ነው፡፡ ህወሓት በፀራራ ፀሀይ በገበያ ቀን ሰራዊቱን በሀውዜን ከተማ እንዲያልፍና ከፊሉ ደግሞ በግቢያተኛው መካከል እንዲሰራጭ በማድረግ እና በተዘዋዋሪ መንገድ ለማድረግ ደህንነት ቢሮ ጥቆማ በመስጠት ህዝቡን በአውሮፕላን ቦምብ አስጨፈጨፉት፡፡ አስቀድው ባዘጋጁት የቪድዮ ካሜራም በቀጥታ በመቅረፅ ለዓለም አሰራጭተው እንወክለዋለን በሚሉት የትግራይ ህዝብ ሞት የፖለቲካ ትርፍ አጋበሱበት፡፡
ህወሓት በበረሃ አያለ ህዝቡን ለሰራዊትነት ሲመለምል ፈቃደኛ ያልሆኑ ወጣቶችን ቀሚስ አልብሶ በአደባባይ እያዞረ በህዝቡ ፊት ያሸማቅቃቸው ነበር፡፡

↧

Health: የፀጉር መበጣጠስን ለማስቀረት 5 ቀላል ዘዴዎች

$
0
0

Young woman holding hair against white background

የፀጉር መበጣጠስን ለማስቀረት በሚል ውድ የውበት መጠበቂያና የፀጉር መንከባከቢያ ውጤቶችን ከመሸመት ይልቅ በቀላሉ የምናገኛቸውን ነገሮች እና ተፈጥሯዊ ዘዴዎችን በመጠቀም ለፀጉራችን እንክብካቤ ማድረጉ የሚመረጥ ሲሆን፥ የውበት ባለሙያዎችም ይህንኑ እንድናደርግ ነው የሚመክሩን።

በመሆኑም እነዚህን አምስት አማራጮች እንድንተገብራቸው ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ያወጣው መረጃ ይመክራል።

1.ዘይት መጠቀም፣

የወይራ ዘይት፣ የኮኮናት ዘይት አልያም ሌላ ማንኛውንም አይነት ዘይት ወስደን እናፈላዋለን፤ ከዚያም ለብ ሲል በጥንቃቄ የፀጉራችንን ስር በደንብ እያዳረስን እንቀባዋለን፤ ለአንድ ሰዓት ያህልም በሻሽ ወይም ፎጣ ጠቅልለን ካቆየን በኋላ በሻምፖ እንለቃለቀዋለን።

2. ተፈጥሯዊ ጭማቂዎች (ጂውሶችን) መጠቀም፣

አመሻሽ ላይ የነጭ፣ ቀይ ሽንኩርት አልያም የዝንጅብል ጭማቂን ወስደን በተመሳሳይ የፀጉራችን ስሩን በደንብ መቀባት፤ ከዚያም በማግስቱ ልንለቃለቀው እንችላለን።

3. የጭንቅላት ማሳጅ (መታሸት)

የፀጉራችን ስር አካባቢ ለተወሰኑ ደቂቃዎች በየቀኑ የምናደርገው የማሸት (ማሳጅ) የማድረግ ተግባር የደም ዝውውርን የሚያቀላጥፍ ሲሆን፥ የደም ዝውውር መቀላጠፍም በአንፃሩ የፀጉር ሴሎችን እድገት ያነቃቃል።

4.አረንጓዴ ሻይ መጠቀም፣

ሁለት የአረንጓዴ ሻይ ከረጢት በአንድ ኩባያ የፈላ ውሃ ላይ በመጠቀም የፀጉራችንን የስረኛው ክፍል መቀባት፣ ለአንድ ሰዓት ያህል ካቆየነው በኋላም እንደምንፈልገው ልንለቃለቀው እንችላለን።

በአረንጓዴ ሻይ ውስጥ የምናገኘው አንቲኦክሲዳንትስ የፀጉር መነቃቀልን ይከላከላል።

በተጨማሪም የፀጉር ዕድገትን ያፋጥናል።

5. ጭንቀትን ማስወገድ፣

ለፀጉር መሳሳት እና መነቃቀል አብይ ምክንያት ተደርጎ የሚወሰደው ጭንቀት ነው።

በመሆኑም ከአላስፈላጊ ጭንቀት ራስን መከላከል እና የተመስጦ (ሜዲቴሽን) ተግባርን በማከናወን የፀጉር መነቃቀልንም ሆነ መሳሳትን መከላከል ይቻላል።

ተመስጦ በተጨማሪም የሆርሞን መመጣጠን እንዲኖር በማገዝ የፀጉር እድገት ፍጥነትን እንደሚጨምርም ነው የሚነገረው።

ምንጭ፦ timesofindia.indiatimes.com

↧
↧

ሀብታሙ አያሌው ቂሊንጦ እስር ቤት ላይ ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ ተደረገ

$
0
0

• ‹‹ችሎቱ ታሪካዊ ስህተት እየሰራ ነው›› አቶ ሀብታሙ አያሌው
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
አቶ ሀብታሙ አያሌው ነሀሴ 14/2007 ዓ.ም ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ከተከሰሰበት የሽብር ወንጀል ነጻ ነው በማለት ከእስር እንዲፈታ የሰጠው ትዕዛዝ ተከብሮ እንዲፈታ ትዕዛዝ እንዲሰጥለት ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ ተደርጓል፡፡
habtamu ayalew
ዛሬ ነሀሴ 29/2007 ዓ.ም ልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት የቀረቡት አቶ ሀብታሙ አያሌው እና መልስ እንዲሰጥ የተጠራው የቂሊንጦ እስር ቤት አስተዳደር ተወካዮች ሲሆኑ፣ የእስር ቤቱ የእስረኛ አስተዳደር ኃላፊ ሱፐር ኢንቴንደንት ጣዕመ ደምሴ አቶ ሀብታሙ አያሌውን ለምን ከእስር እንዳልለቀቁ አስረድተዋል፡፡ ኃላፊው እንደሚሉት አቶ ሀብታሙ ከቂሊንጦ እስር ቤት ያልተፈታበት ምክንያት እስር ቤቱ ከአቃቤ ህግ ይግባኝ እንደተጠየቀበት እና ይህን ተከትሎ ተያይዞ ከጠቅላይ ፍርድ ቤት የተጻፈ የእግድ ትዕዛዝ ስለደረሳቸው ነው፡፡

ሱፐር ኢንቴንደንት ጣዕመ ደምሴ እንደገለጹት የመፈቻ ደብዳቤው እና የእግድ ትዕዛዙ የደረሳቸው ነሀሴ 15/2007 ዓ.ም ሲሆን፣ አቶ ሀብታሙ ግን ከእስር መፈቻ ትዕዛዙ የተጻፈለት ከከፍተኛው ፍርድ ቤት ነጻ ናችሁ የሚል ብይን በተሰጠበት ዕለት፣ ማለትም ነሀሴ 14/2007 ዓ.ም ነበር፡፡ በመሆኑም አቶ ሀብታሙ የማስፈቻ ደብዳቤው እንደተጻፈለት ከእስር ሊለቀቅ ይገባ ነበር፡፡ በእርግጥም የማስፈቻ ደብዳቤው በ14/2007 ዓ.ም እንደተጻፈ ነገረ ኢትዮጵያ ማረጋገጥ ችላለች፡፡

በሌላ በኩል አቶ ሀብታሙ አያሌው ይግባኝ እንደተጠየቀበትና የእግድ ትዕዛዝ ለቂሊንጦ እንደተጻፈ በወቅቱ በደብዳቤ ጭምር መረጃ የጠየቀ ቢሆንም እንዳልተነገረው ለተረኛ ችሎቱ አስረድቷል፡፡ በዚህም ቤተሰቦቹ ለእንግልት፣ አቶ ሀብታሙ ደግሞ ለሞራል ጉዳት መዳረጋቸውን ተናግሯል፡፡ ቂሊንጦ እስር ቤት አስተዳደር ግን ይህን ባለመቀበል በጊዜው መረጃ መስጠቱን ይከራከራል፡፡

ተረኛ ችሎቱ የቀረበለትን አቤቱታ እና የአስተዳደሩን መልስ ከሰማ በኋላ ቂሊንጦ እስር ቤት ከጠቅላይ ፍርድ ቤት የደረሰውን ትዕዛዝ እንዳስፈጸመ በመጥቀስ ትክክለኛ ነው ሲል በይኗል፡፡ በመሆኑም አቶ ሀብታሙ አያሌው በእስር ቆይቶ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚሰጠውን ብይን እንዲጠብቅ ታዝዟል፡፡ አቶ ሀብታሙ የተረኛ ችሎቱን ብይን ከሰማ በኋላ ‹‹ይህ ችሎት ታሪካዊ ስህተት እየሰራ ነው፤ የውሳኔ ግልባጩ ይሰጠኝና የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቀው አደርጋለሁ›› ሲል ተናግሯል፡፡
አቶ ሀብታሙ አያሌው ከሌሎች አራት ተከሳሾች ጋር መስከረም 21/2008 ዓ.ም ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

↧

Sport: ዳኒዌልቤክ እስከ ፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ድረስ ለአርሰናል ግልጋሎት አይሰጥም ተባለ

$
0
0

dani
እንግሊዛዊው የ አርሰናል አጥቂ ዳኒ ዌልቤክ እስከ ፈረንጆቹ አድስ አመት ድረስ በጉዳት አገልግሎት እንደማይሰጥ ተረጋገጠ፡፡

አጥቂው በግራ ጉልበቱ ላይ ቀዶ ጥገና እንደሚያደርግ አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር ካስታወቁ በኃላ ነው ወራቶችን በጉዳት የሚያሳልፈው፡፡

በመድፈኞቹ ቤት ከዚህ በፊት ጃክ ዊልሻየር አሮን ራምሴና ቶማስ ቨርማሊን የገጠማቸውን አይነት ከፍተኛ ጉዳት እንደገጠመውም ተገልፃል፡፡

በክረምቱ የዝውውር ገበያ ላይ 10 ሚሊዮን ፓውንድ ብቻ ያወጡት አርሰን ቬንገር በስብስባቸው ውስጥ የአጥቂ ክፍል ተጨዋቾች ውስንነት መኖሩን ተከትሎ የዌልቤክ አለመኖር ተፅኖ ውስጥ ያስገባቸዋልም ተብሏል፡፡

የመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ አሰልጣኙ ከሚጠቀሙባቸው ተጨዋቾች ውስጥ ከዌልቤክ በተጨማሪ ሜሱት ኦዚልና ጃክ ዊልሻየር ጉዳት ላይ የሚገኙ ተጨዋቾች ናቸው፡፡
በፕሪሜርሊጉ ያለፈውን የውድድር አመት ከባለክብሮቹ ቸልሲዎች በ 12 ነጥብ ርቀው የጨረሱት መድፈኞቹ በአሁኑ የውድድር አመት ላይም ከ አራት የፕሪሜርሊግ ጨዋታወች ውስጥ ማሸነፍ የቻሉት በሁለቱ ብቻ ነው፡፡

የ24 አመቱ ዳኒ ዌልቤክ ከቀያይ ሰይጣኖቹ ቤት መድፈኞቹን ከተቀላቀለ በኋላ በ 34 ጨዋታወች 8 ጎሎችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል፡፡

(ደቡብ ስፖርት)

Danny Welbeck: Arsenal striker out until Christmas with knee injury

By David Ornstein
BBC Sport
Arsenal striker Danny Welbeck is expected to be out until Christmas after having a knee operation.
Welbeck, 24, who had surgery last week on the injury sustained in April, has scored eight goals in his first 34 games for the Gunners.
Arsenal, who were linked with Karim Benzema, knew the extent of the problem before the transfer window closed but did not reinforce their attack.
That means Olivier Giroud is their only recognised striker fit for selection.
Theo Walcott, Alexis Sanchez and Joel Campbell – who has not played for the Gunners since January – have experience of operating in that position, but are mainly used by Arsenal as wide players.
England international Welbeck, who joined from Manchester United in 2014, picked up the injury to his left knee after coming on as a substitute in Arsenal’s 0-0 home draw with Chelsea in late April.
“The injury to his cartilage did not respond as well as hoped and the decision was taken last week for him to undergo surgery,” said a statement.
Arsenal did explore the possibility of recruiting a new striker before Tuesday’s transfer deadline, but they ended the window with goalkeeper Petr Cech as their only signing.
They were the only club from the top five European leagues not to sign an outfield player during the summer.
That led to the Arsenal Supporters’ Trust calling for an inquiry into the club’s transfer policy.
“No-one wants Arsenal to buy players just for the sake of it, but we do want to see the money being invested to make the club stronger,” it said in a statement.
Manager Arsene Wenger said: “Am I happy with the investment I make? Yes, every time. You have to find the players to invest in.”

↧

አርበኞች ግንቦት 7 ለ1 ሰዓት የፈጀ ውጊያ ማድረጉን አስታወቀ * ገድያለሁ፣ መሳሪያም ማርኬያለሁ ብሏል

$
0
0

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ የውስጥ አርበኞች በህወሓት አገዛዝ መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት በመሰንዘር ለአንድ ሰዓት የዘለቀ ከባድ ውጊያ አድርገው ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን አስታወቀ::
Arebegnoch Ginbot 7
የአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች ህወሓት “ክልል አንድ” እያለ በሚጠራው በጎንደር-ወልቃይት ደጃች ሜዳ ወረዳ አቤራ ቀበሌ ስልኪ ዳግባ በተባለው ቦታ ነሃሴ 23 2007 ዓ.ም በህወሓት መከላከያ ኃይል ላይ ድንገተኛ የተኩስ ውርጅብኝ በመክፈት ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ወታደሮችን ገድለውና አቁስለው ድል መቀዳጀታቸውን ዘ-ሐበሻ ከአርበኞች ግንቦት 7 ራድዮ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል::

በአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞችና በህወሓት የመከላከያ ሰራዊት መካከል የተካሄደው ድንገተኛ የሆነ ከባድ ፍልሚያ እኩለ ቀን ላይ ከ6፡30 ጀምሮ እስከ 7፡30 ለአንድ ሰዓት የዘለቀ ሲሆን ምሳ በመመገብ ላይ እያለ ባልገመተው ሁኔታና ባለሰበው አሳቻ ሰዓት ድንገተኛ ተኩስ ተከፍቶበት የእሳት ዝናብ በላዩ ላይ የወረደበት የህወሓት ሰራዊት አብዛኛው ተበታትኖ ከአካባቢው የሸሸ ሲሆን የአፀፋ ተኩስ ከፍቶ ለአንድ ሰዓት ለመከላከል የሞከረው ደግሞ ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል ያለው ራድዮው የውስጥ አርበኛው ሽምቅ ተዋጊ ኃይል መትረየሶችን ጨምሮ በርካታ ክላሽን ኮቮች ከነመሰል ጥይቶቻቸው ለመማረክ ችሏል ብሏል::

የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ከሰኔ 25 2007 ዓ.ም እስከ ሀምሌ ወር መጀመሪያ በወልቃይት ቃፍታ መሲን፣ ኮርጃሙስ፤ ማይ ሰገን፣ ንኳል ሳግላ፣ በዋልና ማይ እምቧ ላይ በህወሓት መከላከያ ሰራዊት ላይ ተከታታይ ጥቃቶችን በመክፈት በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ የሆነ እልቂትና ኪሳራ በማድረስ ተደጋጋሚ ድሎችን መጎናፀፉ አይዘነጋም ሲል ራድዮኑ ሲዘግብ ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል የተሰጠ ምንም መረጃ የለም::

↧

አጥር ሰባሪው፣ ሕገ ወጥና ሁከት ጋባዡ ማን ይሆን? –

$
0
0

ዘመቻ አባ መላኩ በአትላንታ ሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አጥር ሰባሪው፣ ሕገ ወጥና ሁከት ጋባዡ ማን ይሆን? “ጩሀቴን ቀሙኝ!” ነበር ያለው አቀንቃኙ? የአትላንታ ሰዓሊተ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ጩሀቱን በመጋቢ ብሉይ አባ ኃ/ሚካኤል ተቀምቶ ስለ አጥር ሰባሪነት፣ሁከተኝትና ስርዓተ አልበኝነት መንፈሳዊ ትምህርት ሳይሆን የፖሎቲካ ካድሬ ዲስኩር ትምህርት መሰል ባለፈው እሁድ  08/30/15  በቤተመቅደስ ውስጥ ቀርቦለታል።

አጥሯን ለምን ታፈርሳለህ?

eseweመጋቤ ብሉይ አባ ኃ/ሚካኤል ከላይ በተጠቀሰው ርእሰ ትምህርት መሰል የጥላቻ ቅስቀሳ በእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ላይ ነበር ያቀረቡት። በዚህ ርእሳቸው ላይ የእስላም፣ካቶሊክ፣ፕሮቴስታንትና ተሃድሶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ እያደረሱ ነው ያሉትን አደጋ ለማቀረብ ሙከራ አድርገዋል። በተጨማሪም የመረጃ ምንጫቸውን ሳይገልጹ የአሜሪካ ኮንግረስ የኦርቶዶክስ ቤ/ክ ለግሎባላይዜሽን እንቅፋት ስለምትሆን የምትጠፋበት መንገድ እያጠና እንደሆነም ነግረውኗል።አሁንም

[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

 

 

↧
↧

የእብዶች ስብስብ –ይገርማል ታሪኩ

$
0
0

TPLFየእብዶች ስብስብ የምለው ወድጀ አይደለም:: አገርን ያህል ነገር እመራለሁ: ኢትዮጵያውያንን ያህል ታሪካዊና ኩሩ ሕዝብ አስተዳድራለሁ ብሎ ከተቀመጠ ቡድን ውስጥ ለቁምነገር የሚፈለግ: ለጠበቃነትና ለዋስነት ሊጠራ የሚችል አንድ እንኳ ለህሊናውና ለፈጣሪው ተገዥ የሆነ ፈሪሀ እግዚአብሐር የፈጠረበት ሰው ሲጠፋ ታዲያ ምን ልበል!

እንደኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1990 ዓ.ም ክረምት ካንድ ሰው ጋር ሆስፒታል ውስጥ ተገናኘን:: ሁለታችንም የምናስታምማቸው ሆስፒታል ውስጥ የተኙ ሰወች ነበሩን:: አንዳችን ያንዳችንን ጭንቀት የመረዳታችን ምክንያት ይመስለኛል ተግባብተን ለመጨዋወት ያበቃን::

ታማሚው ምንህ ነው? ህመሙ ምንድን ነው? ከሚለው ተነስተን ወደህይወትና ፖለቲካ ዝባዝንኬ ገባን:: ሲያዩት ቀናና ግልጽ ይመስላል:: ታሪኩን ቃል በቃል ባላስታውሰውም ጭብጡን በነገረኝ ልክ ላካፍላችሁ:: እንዲህ አለኝ

“የገጠር ልጅ ነኝ:: ትምህርት ቤት ገብቸ 12ኛ ክፍልን አጠናቅቄአለሁ:: ቤተሰቦቸ የኑሮው ሸክም የከበዳቸው ስለሆኑ ከትምህርት መልስ አንዳንዴም ከትምህርት ቤት እየቀረሁ በስራ አግዛቸው በተጨማሪም ያገኘሁትን የጉልበት ስራ  እየሰራሁ በማገኛት ጥቂት ገቢ ቢያንስ የት/ቤት ጣጣየን እሸፍን ነበር:: ስራ ለማግኘት ስል ይሁን ወይም ተፈጥሮየ ሆኖ እንጃ ብቻ ባህሪየ ጥሩ የሚባልና የሰው መውደድ ያደለኝ ነበርሁ:: ት/ቤት የምሄደው በአካባቢየ ያሉትን ወጣቶች ለመምሰል እንጅ የትምህርት ጥቅሙ ገብቶኝ አልነበረም:: ያም ሆኖ አንድም ጊዜ ሳልደግም 12ኛን ክፍል አጠናቀኩ::

ከ12ኛ ክፍል በላይ ሊያስቀጥል የሚችል ነጥብም ሆነ የኢኮኖሚ አቅም ስላልነበረኝ ስራ ፍለጋ ስባዝን ፖሊስ እንቀጥራለን የሚል ማስታወቂያ አየሁና ሄጀ ተመዘገብኩ:: የቅጥሩን ፎርማሊቲ አሟልተው ለፖሊስነት ከተመለመሉት ውስጥ አንዱ በመሆኔ የሰፈሬን አድባርም አምላኬንም አመሰገንሁ:: ስልጠናውን ከጨረስሁ በኋላ ከዚያው ከወረዳየ እንድሰራ ስለተመደብሁ ደስታየ ወሰን አልነበረውም:: በፍትህና በሰላም እጦት የሚሰቃየውን ወገኔን ልረዳ የምችልበት እድል ሳገኝ እንዴት አልደሰት!

ደስታየ ግን ብዙም አልቆየ:: ከበላይ የሚሰጠኝን ትእዛዝ ብቻ መፈጸም እንዳለብኝ ይነገረኝ ጀመር:: ለማነሳቸው ጥያቄወች የሚሰጡኝ መልሶች ስራየንና እራሴን እንድጠላ አደረገኝ:: ‘ለምን? እንዴት? የሚሉ ጥያቄወች ማንሳት ፖሊሳዊ ባህል አይደለም: አድርግ የተባልኸውን ብቻ ፈጽመህ መገኘት ነው የሚገባህ’ እየተባልሁ በግምገማ ተወጠርሁ:: ቤተሰቤ: ዘመዶቸ: ጎረቤቶቸና መላው የወረዳችን ህዝብ ከአይን ያውጣህ እንዳላሉኝ የፖሊስ ስራ ከጀመርሁ በኋላ ግን ያም ያም አይንህ ይጥፋ ይለኝ ያዘ::

የፖሊስነት ስራየን ‘ሀ’ ብየ መስራት በጀመርሁበት ጊዜ ህገወጥ መሳሪያ የያዙትን ሰወች ትጥቅ አስፈቱ የሚል መመሪያ መጣ:: ይህን ተከትሎ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ማስፈታት በሚል ሰበብ መሳሪያ ደብቋል ተብሎ የተጠረጠረን ሰው አስሬ እየገረፍሁ እንዳዋጣው ጫናው በረታብኝ:: አንድም እንጀራየን ብየ ሌላም የፖለቲካውን ተንኮል ባለመረዳት ተታልየ ህገወጥ መሳሪያ የታጠቁ ህገወጦች ናቸው ተብለው የተጠረጠሩትን ሰወች የደበቁትን መሳሪያ እንዲያመጡ ከሌሎች የስራ ባልደረቦቸ ጋር ተባብሬ አይሰሩ ስራ ሰራሁ::

ወገን ያለው ታሳሪ ያልደበቀውን መሳሪያ እሽ አስገባለሁ እያለ ወገኖቹ ዳር አገር ድረስ አፈላልገው መሳሪያ ገዝተው እያስረከቡ እንዲለቀቅ ሲያደረጉ ወገን ያጣና ያልቻለው ግን የሲኦልን ፍዳ በምድር ተቀበለ:: ማንም የብአዴን አባልና ደጋፊ ነኝ የሚል ሁሉ ህገወጥ መሳሪያ የያዘን እንዲጠቁም የተሰጠውን  መመሪያ ተመርኩዞ አንዳንዱ ህሊና ቢስ በትንሽ በትልቁ የተጣላውን ሰው ሳይቀር በሀሰት መሳሪያ ደብቋል በማለት እየጠቆመ ታሪክ ይቅር የማይለው በደል ተፈጸመ::

ፖሊስ ጣቢያወች የንጹሀን እንባና ደም የሚፈስባቸው የመከራ ካምፖች ሆኑ:: ወገን: ሀገር: እየተቀባበለ” እሪው” ብሎ ጮኸ:: የጩኸቱ መበርከት ስማችንን ያጎድፋል ብለው የሰጉ የብአዴን ባለስልጣኖች  አለ የተባለውን ችግር የሚያጠና ሰው ልከናል በማለት ሌላ ዙር የተንኮል ቀልድ ቀለዱ:: ከዞንና ከክልል የመጡት ሹመኞች የተሰጣቸው ተልእኮ እኛን የገና በግ ማድረግ ነበር::

በአንድ የሰንበት ቀን በየቀበሌው ያለው ህዝብ በየቤተክርስቲያኑ እንዲገኝና ተፈጠረ በተባለው ችግር ዙሪያ ውይይት ተደርጎ የማያዳግም መፍትሄ እንዲሰጥ ቅስቀሳ ተደረገ:: በእለቱ የወረዳው ፖሊስ አባላትም አብረን እንድንገኝ ትእዛዝ ደርሶን ስለነበር ሁላችንም ቀድመን ከስፍራው ተገኘን:: እኔ በተገኘሁበት የስብሰባ ቦታ የተገኘውን ህዝብ ሳይ ለቤት ጥበቃ እንኳ የቀረ ሰው ያለ አይመስልም ነበር:: የፖለቲካ ተዋናዩ የመንግስትን አቋምና ለህዝብ ያለውን ወገንተኝነት ካብራራ በኋላ ብአዴን የቆሰለበትና የሞተለት የዜጎች የዴሞክራሲና የሰብአዊ መብት መጣስ ከምንም በላይ እንደሚያሳስበው ገልጾ የደረሰባችሁን በደል አስረዱ ሲል ተሰብሳቢውን ጋበዘ:: ምን ይባላል! አንዱ በአንዱ ላይ እየተረባረበ ደረሰብን ያለውን ጉድ ይዘከዝከው ጀመር::

‘መንግስት ባለበት ሀገር እንዴት እንዲህ ያለ የውንብድና ግፍ ይፈጸምብን’ ሲሉ በስም እየጠቀሱ: በጣታቸው እየጠቆሙ እያሳዩ: ለህዝብ ተቆርቋሪ የሆነው መንግስት ሳያይና ሳይሰማ መአት አወረዱብን ያሉንን እኛን በጥርሳቸው ሊነክሱን በጥፍራቸው ሊቧጥጡን አሰፍስፈው ተነሱ:: ‘ባትደርሱልን ኖሮ አንዳችንም አንተርፍም ነበር’ ሲሉ እንባ እየተናነቃቸው ብሶታቸውን አጎረፉት::

ስብሰባው የተጠራው እኛን ለማስገምገም መሆኑን ባለማወቃችን ምንም ዝግጅት ሳናደርግ ስለመጣን እራሳችንን መከላከል የተሳነን ፍጹም ምዑታን ሆነን በጋለ ብረትምጣድ ላይ እንደተጣለ ላስቲክ ተጨራመትን:: ለመናገር አፋቸውን በደመነፍስ ያላቀቁትን ጓደኞቸን ሊናገሩት ያሰቡትን መልሰው እንዲውጡት በሀይለቃል ሲነገራቸው ስሰማ ውስጤን ድብልቅልቅ ያለ ግራ የተጋባ መንፈስ ወረረው:: ሆኖም ቃል አልወጣኝም: የምናገረው ቃል ቢኖረኝስ እንዴት አድርጌ!

ተባለ ተባለና መጨረሻ ላይ ‘ታዲያ እኒህን በህግና በህዝብ ላይ ያመጹትን ወንበዴወች ምን እናድርጋቸው ሲሉ’ ሰብሳቢው ምልአተ ህዝቡን ጠየቁ:: ማን ምን እንደሚናገር ማወቅ  አስቸጋሪ ሆነ:: ሁሉም እየጮኸ ተመጣጣኝ ነው የሚለውን ፍርድ ይሰጥ ጀመር:: ‘እድሜ ይፍታህ ይታሰሩ!  እንደገረፉን እነሱም በተራቸው 80 ይገረፉ:  ይሰቀሉ:  በጥይት ይገደሉ ——::

ቤተሰቦቸን በአይኔ ፈለኳቸው:: አባቴ አንገቱን ሰብሯል: እናቴ በድንጋጤ ጭብጥ አክላ አይኗ ፈጦ እኔን እኔን ታያለች:: ምነው ባልተወለድሁ! በመጨረሻም አስገምጋሚ ፖለቲከኛው የህዝብ ተቆርቋሪነትና ደም መላሽነት በተላበሰ መንፈስ ተሞልተው ከጩኸት ባልተናነሰ ድምጽ ‘በቃ! በቃ! ሀሳባችሁን ለግብአትነት እንጠቀምበታለን:: የተወሰደውን እርምጃ ወደፊት ትሰማላችሁ:: ማንም እንደፈለገው ህግን ተላልፎ የሰወችን የማይገሰስ መብት ሊገስ አይችልም:: ስለትብብራችሁ እናመሰግናለን: ደህና ሁኑ’  አሉና ግምገማውን አጠናቀቁ::

የተወለድሁበት ቀየ… ያሳደገኝ ህዝብ — ሁሉንም ደግሜ ላላያቸው ፊቴን ሳዞር አንዱ ከሹመኞቹ ጋር የመጣ ፖሊስ እጆቸን በሀይል ወደኋላ ጠመዘዛቸውና ካቴና አጠለቀባቸው:: ድንጋጤ: ፍርሀትና ግራ መጋባት የፈጠረብኝ ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ከእኔ ጋር የተገመገሙትን ጓደኞቸን ሁኔታ እንዳላስታውስ ጋረደኝ:: ያም ሆኖ ግን ወደዞኑ ከተማ ስንጓዝ አብረውን እንዳልነበሩ አስታውሳለሁ:: ከዞኑ ዋና ከተማ ስንደርስ ‘ከእንግዲህ በኋላ በስራህ አትቀጥልም: ወደፈለክበት መሄድ ትችላለህ’ ተብየ ካቴናው ወለቀልኝ:: የኔ ነገር በዚሁ አበቃ:: እኔም ሆንኩ ህዝቡ የማንፈለግ: አንዳችን በአንዳችን እንድንጠፋ መንገዶች የሚመቻቹልን አላስፈላጊ አረሞች ነን:: አስገምጋሚወቸ ተራው እስኪደርሳቸው ድረስ የተሰጣቸውን ስራ አከናውነው ባገኙት ሙገሳ ተደስተው ረክተው ይሆናል: እኔ ግን ያለምሁት ሳይደርስ ያሰብሁት ሳይሳካ አግዘዋለሁ ብየ ያሰብሁትን ወገኔን አሰቃይቸ ከማንም ሳልሆን ከቆሰለ ህሊና ጋር ተሳዳጅ ሆንኩ” አለኝ::

ሲናገር ጸጸት ባህር አንጀቱ ገብቶ እያንሰፈሰፈው: ንዴት ቆሽቱን እያደበነው እንደሆነ አጠቃላይ ሁኔታውን ላየ ስሜቱን ከመረዳት አልፎ ይጋባበታል:: “የመንግስት የውስጥ መመሪያ” ማለትት ምን ማለት እንደሆነ ያልተረዳ ሰው ከዚህ ድርጊት ጥቂትም ቢሆን ግንዛቤ ሊጨብጥ ይችላል ብየ አስባለሁ:: ምንም አይነት የጽሁፍ ትዕዛዝ ሳይደርስህ አንድ የሚፈለግ የጥፋት ተግባር እንድትፈጽም ትታዘዛለህ:: ስለጉዳዩ ምንነት ካወቅህ በኋላ እሽም ሆነ እምቢ ብለህ አትተርፍም:: ሚስጥር ካወቅህ በኋላ ከነሚስጥርህ ማን በሰላም ይለቅሀል:: ብቻ ከንጹህ ህሊናህ ጋር መቀበር ከፈለክ የህገወጥ ድርጊት ተባባሪ ወይም ፈጻሚ አልሆንም ብለህ የነገውን ሞት ዛሬ መቀበል ነው:: እንደታምር ሆኖ ይህ ከ18 አመት በፊት ያገኘሁት ወጣት ለወሬ ነጋሪነት ተርፎ ይህን ያጫወትኋችሁን እውነት ለመተንፈስ በቃ:: እኔም ዘግይቸም ቢሆን የዚያን ወጣት የቁም ኑዛዜ ለናንተ አደረስኩ::

የወያኔ አላማ ግልጽ ነው:: አልገባን ብሎ ወይም ፈርተን እንደሆነ እንጅ ወያኔ እንደሆነ ገና ጫካ እያለ ጀምሮ በአማራው: በኦርቶዶክስ ሀይማኖትና በኢትዮጵያዊነት ላይ ያለውን ጥላቻ በሰነድ አስፍሮ ‘በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቡራኬ በጉልበት በአማራው በተፈጠረችው የመቶ አመቷ ኢትዮጵያ የብሔሮች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት እስከመገንጠል ድረስ ተግባራዊ ለማድረግ ነው የምንታገለው’ እያለ ሁሉንም ለማጥፋት አልሞ ነው የመጣው::

ስለዚህ “እሾህን በእሾህ” ነው እንዲሉ ወያኔወች አንዱን አማራ በሌላው አማራ እያጠፉ: እነርሱ ከደሙ ንጹህ ነን እያሉ በነርሱ ምጡቅ ዐዕምሮ ተኩራርተው በሌሎች ጅልነት ተሳልቀው ቀጥለዋል:: ከአማራው አብራክ የተገኘን ነን የሚሉት የብአዴን ሰዎች እንወክለዋለን የሚሉት ሕዝብ በያለበት የጥቃት ሰለባ ሲሆን ምንም ሳይቆረቁራቸው እንዲያውም የወንጀሉ ተባባሪና ፈጻሚ ሆነው ሲገኙ ምን ይባላል! ሌሎች የኢህአዴግ አባልና አጋር ድርጅቶችስ ቢሆኑ የወያኔ ዱላ ሆነው ህዝባቸውን በሆነ ባልሆነው እየገረፉ እያቆሰሉት አይደለም! መቸ ነው ወደህሊናቸው ተመልሰው የህዝባቸውን ስቃይ ለማስቆም የሚሰሩት! ጅል ጅሉ እየተመረጠ ከስልጣን ላይ ወጥቶ የታዘዘውን እየፈጸመ እንዲቀጥል የሚደረገው የወያኔ ሴራ ሊከሽፍ የሚችለው ነፍስ ያወቀው ዜጋ አንገቱን ካቀና ብቻ ነው::

ወያኔወች እንደሆኑ “የላም አሸናፊ” ናቸው:: ፈርተው ቢሸሿቸውም እየተከታተሉ መውጋታቸውን አይተውም:: በተለያየ ሱስ የተለከፉ: በቂምና በጥላቻ የተበከሉ: የሚፈልጉትን ነገር ማድረግ በመቻላቸው ተደስተው የሚኖሩ ከራሳቸው ውጪ ለሆነ ለማንም ለምንም ግድ የሌላቸው ወፈፌወች ናቸው:: ታዲያ እኒህን ጊዜ ከስልጣን ማማ ላይ ያስቀመጣቸውን የጉዶች ስብስብ ምን ብየ ልጥራው? የእብዶች ስብስብ ብል አይገልጸው ይሆን! ወገን እንንቃ!

↧

Health: ሁልጊዜ የድካም ስሜት እንዲሰማዎ የሚያደረጉ 7 ምክንያቶች

$
0
0

always tiredReason’s you’re always tired

(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

1• አካል ብቃት እንቅስቃሴ አያደርጉም
2• በቂ ውሃን አይጠጡም
3• አይረን የሚባል ንጥረ ነገር ያላቸውን ምግቦች አያዘወትሩም
4• ቁርስዎን አይመገቡም
5• ለጤና ተስማሚ ከሆኑ ምግቦች ይልቅ ጣፋጭ እና ቅባታማ ምግቦችን ይመገባሉ
6• የሥራ ቦታዎ የተዘበራረቀ እና ያልተስተካከለ ከሆነ ነው
7 • በሥራ ምክንያት ሰለሚያመሹ በቂ እንቅልፍ አለማግኝትዎ ነው፡፡
ጤና ይስጥልኝ

• You don’t have enough exercise
• You don’t drink enough water
• You’re not consuming enough iron
• Skipping your breakfast
• Eating too much junk food
• You have a messy office
• You always stay up late

↧

Health: የእከክ ህመም ምልክቶች –ሕክምናውና ሊደረግ የሚገባው ጥንቃቄ

$
0
0

እከክ ቆዳን የሚያሳክክ በቆዳ ስር በሚቀመጡ ሳርኮፕቴስ እስኬቢስ በሚባሉ ተዋሲያን የሚከሰት የቆዳ ላይ ችግር ነዉ፡፡ ህመሙ በቤተሰብ፣ በህፃናት እንክብካቤ ማዕከል፣ ትምህርት ቤቶች፣የህመሙማን መንከባከቢያ ማዕከልና እስር ቤቶች ዉስጥ በቀላሉ በአካላዊ ንክኪ ሊተላለፍ የሚችል የህመም አይነት ነዉ፡፡
itchy skin
በቆዳዎ ላይ ሊቀቡ የሚችሉ ምድሃኒቶች በሽታዉን ሊያመጡ የሚችሉ ተዋሲያንንና እንቁላላቸዉን በቀላሉ የሚገድል ነዉ፡፡

የህመሙ ምልክቶች፡-

· የቆዳ ማሳከክ፡- ብዙዉን ጊዜ ከፍ ያለና ማታ ማታ የሚባባስ
· ቀጫጭን የሆኑ የተቦረቦሩ የቆዳ ላይ ቁስለቶች መታየት

የተቦረቦሩ ቁስለቶች በተጣጠፉ የቆዳ ክፍሎች ላይ በብዛት ይታያል፡፡ እከክ ምንም እንኳ በየትኛዉም የሰዉነት ቆዳ ላይ ቢከሰትም በተለይ በሚከተሉት የሰዉነት ክፍሎች አካባቢ በብዛት ይከሰታል፡-
· በጣቶች መካከል
· በብብት ስር
· በወገብ አካባቢ
· በዉስጠኛዉ የእጅዎ ክፍል
· በዉስጠኛዉ የክርን ክፍል
· በዉስጥ እግር
· ጡት አካባቢ
· በወንዶች ብልት አካባቢ
· በመቀመጫ አካባቢ
· በጉልበት አካባቢ ናቸዉ፡፡

ከዚህ በፊት በእከክ ተይዘዉ ከነበረ አሁን በድጋሚ ቢያዙ የህመሙ ምልክቶች በጥቂት ቀናት ዉስጥ የሚታይ ሲሆን ከዚህ በፊት በእከክ ተይዘዉ የማያዉቁ ከሆነ ግን የህመሙ ምልክቶች ለመታየት እስከ 6 ሳምንታት ሊወስድ ይችላል፡፡ ማስታወስ የሚገባዎ ነገር ቢኖር ምንም እንኳ የህመሙ ምልክት ባይታይቦትም በሽታዉን ሊያሰራጩ እንደሚችሉ ነዉ፡፡ ቅርበት ያለዉ አካላዊ ግንኙነትና ልብስን ወይም መኝታን መጋራት ለህመሙ መዛመት/መተላለፍ ዋነኛዉ መንገድ ነዉ፡፡

ሊደረግ የሚችል ህክምና

የእከክ ህክምና የበሽታዉን አምጭ ተዋሲያን ማጥፋት ሲሆን በክሬምና በሎሽን መልክ ያሉ መድሃኒቶች ሊታዘዙ ይችላሉ፡፡እከክ በቀላሉ የሚተላለፍ የቆዳ ላይ ችግር ስለሆነ ሌሎች የቤተሰብ አባላት የህመሙ ምልክቶች ባይኖራቸዉም የህክምና ባለሙያዎ መድሃኒቱን ለሁሉም የቤተሰብ አባላትዎ ሊያዝ ይችላል፡፡

እንዴት መከላከል ይቻላል?

ህመሙ ተመልሶ እንዳይዞትና ወደ ሌሎች ሰዎች እንዳይተላለፍ ሁሉንም ልብሶችዎንና አንሶላዎችን በንፅህና ማፅዳት፡፡ ይህም በሞቀ ዉሃና ሳሙና ልብሶችን፣ ፎጣዎችንና አንሶላዎችን ህክምና ከመጀመርዎ ከሶስት ቀናት በፊት የተጠቀሙባቸዉን በሙል በደንብ ካጠቡ በኃላ በሙቀት ማድረቅ፡፡ በዉሃ መታጠብ የማይችሉትን ደግሞ በፀሃይ ብርሃን ማድረቅ/ማሞቅ ናቸዉ፡፡

↧

Health: ቋቁቻ የቆዳ ችግር እንዴት ይድናል?

$
0
0

quqqucha

ቋቁቻ  በብዛት ሊከሰት የሚችል ከሰዉ ወደ ሰዉ የማይተላለፍ በፈንገስ ምክንት የሚመጣ የቆዳ ላይ ችግር ነዉ::
ፈንገሱ የቆዳ ተፈጥሮዊ መልክን በማሳጣት ትናንሽ፣ነጣ ወይም ጠቆር ያሉ መልካቸዉን የለወጡ ነገሮች በቆዳ ላይ እንዲወጡ ያደርጋል፡፡ ቐቁቻ በብዛት የሚከሰትዉ በአንገት፣ትከሻ ደረትና ጀርባ ላይ ነዉ፡፡

የህመሙ ምልክቶች

· በጀረባ፣ ደረት፣ አንገት፣ እጅ ላይ (ከክርን በላይ ከፍ ብሎ ባለዉ) የቆዳ ከለር መለወጥ

· መጠነኛ ማሳከክ
· የቆዳ መቀረፍ የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡

የህመሙ መንስኔዎች

ቋቁቻን ሊያመጡ የሚችሉ ፈንገሶች በጤናማ ቆዳ ላይ ሊገኙ ይችላሉ፡፡ ይህ ችግር በብዛት በለጋነትና በወጣትነት እድሜ ክልል ይከሰታል፡፡ ቐቁቻ ህመም የለዉም፤ ከሰዉ ወደ ሰዉ አይተላለፍም፡፡ ነገር ግን ሊያስጨንቅ ወይም የሀፍረት ስሜት እንዲሰማን ሊያደርግ ይችላል፡፡ ይህ የሚሆነም ፈንገሱ ከመጠን በላይ ሲያድግ ነዉ፡፡ ቐቁቻ እንዲመጣ የሚያደርጉ/እንዲባባስ የሚያደርጉ ነገሮች:-
· ሞቃታማና እችጥበታማ የአየር ፀባይ
· ወዛማ ቆዳ ካለዎት
· የሆርሞን መለዋወጥ
· የበሽታ መከላከል መዳከም ናቸዉ፡፡

የህክምና ባለሙያዎን መመከር የሚገባዎ መቼ

· ለቆዳዎ እያደረጉት ያለዉ ጥንቃቄ ለዉጥ ካላመጣ
· ህመሙ ከጠፋ በኃላ ተመልሶ ከመጣ
· ህመሙ ብዙ የቆዳ ክፍልን ከሸፈነ

ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች
ቋቁቻ በፈንገስ ምክንት የሚመጣ የቆዳ ችግር ስለሆነ የሚከተሉት መድሃኒቶች ሊታዘዙ ይችላሉ፡፡ የተወሰኑት መድሃኒቶች በቆዳ ላይ ሊቀቡ የሚችሉ ሲሆን ቀሪዎቹ የሚዋጡ ናቸዉ፡፡
· የፍሉኮናዞል እንክብል ወይም ፈሳሽ መድሃኒት
· ኢትራኮናዞል( እንክብል፣ካፕሲዩል ወይም ፈሳሽ)
· ኬቶኮናዞል( ክሬም፣ ጄል ወይም ሻንፖ) ናቸዉ፡፡

ምንም እንኳ ህክምናዉን በደንብ ቢከታተሉትና ህመሙ ቢሻሎትም ለሳምንታት ወይም ለወራት የቆዳዎ ቀለምዎ ሳይለወጥና እንደሻከረ ሊቀጥል ይችላል፡፡ እነዳንዴ ደግሞ ህመሙ ተመልሶ ሊመጣ ይችላል( በተለይ በሞቃታማና እርጥበታማ የአየር ፀባይ ወቅት)፡፡ ስለሆነም ኢንፌክሽኑ ተመልሶ እንዳይመጣ መድሃኒት በወር አንዴ ወይም ሁለቴ መዉሰድ ሊስፈልግ ይችላል፡፡

↧
↧

በሳይንስ ዘርፍ –የ2007 ዓ.ም. በጎ ሰው ተሸላሚ –ፕሮፌሰር አበበ በጅጋ 

$
0
0

abebe bejga

ጌጡ ተመስገን ከአዲስ አበባ አክሱም ሆቴል እንደዘገበው:-

ፕሮፌሰር አበበ በጅጋ

ፕሮፌሰር አበበ በጅጋ የዓይን ሕመም ከፍተኛ ችግር በሆነበትና በቀላል ሕክምና ሊድኑ የሚችሉ የዓይን ሕመሞች ዓይነ ሥውርነትን በሚያስከትሉበት ሀገራችን ውስጥ ይህንን ችግር ለመፍታት በግንባር ቀደምነት ከተሰለፉ ባለሞያዎች መካከል ናቸው፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕክምና(MD,)ከዚሁ ዩኒቨርሲቲ በኦፕታልሞሎጂ ስፔሻላይዝድ ያደረጉት ፕሮፌሰር አበበ በጅጋ አውስትራልያ ከሚገኘው ኒው ካስል ዩኒቨርሲቲ በክሊኒካል ኤፒዲሞሎጂና ባዮ ስታትስቲክስ ዲፕሎማ አግኝተዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የሚሠሩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነው፡፡ ይህም አገልግሎታቸው ከ30 ዓመታት በላይ ሆኖታል፡፡

ፕሮፌሰር አበበ በጅጋ ሞያቸውን በተመለከተ በማስተማር፣ጥናት በማድረግና ልዩ ልዩ ሞያዊ ተቋማትን በማገልገል ይታወቃሉ፡፡ በሞያዊ ጆርናሎች አርታዒና አማካሪ በመሆን(ከአራት በላይ ቢሆኑ የኦፕቲሞሎጂ ጆርናሎች አባልና መሪ ተሳታፊ ናቸው)፣ በልዩ ልዩ ጉባኤያት አወያይና ተወያይ በመሆን(በሞያው ዘርፍ የተደረጉ ሁለት ሀገር አቀፍ ጉባኤያትን በመሪ ተወያይነት አገልግለዋል)፣ የሕክምና ማኅበራትን በመምራትና በቦርድ አባልነት በማገልገል(ከስድስት በላይ ሞያውን የተመለከቱ ማኅበራትና ሀገር አቀፍ ኮሚቴዎች ውስጥ በቦርድ አባልነትና በኮሚቴ አባልነት ያገለግላሉ)፡፡

እስካሁን ድረስ ኦፕቲሞሎጂን የተመለከቱ ከ30 በላይ ጥናቶችን በራሳቸውና ከአጋሮቻቸው ጋር ሆነው በመሥራት ያሳተሙ ሲሆን ላበረከቱት አስተዋጽዖም ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ተቀብለዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል የኢትዮጵያ ኦፕቲሞሎጂካል ማኅበር (እኤአ በ2010) በጥናት መስክ ላበረከቱት አስተዋጽዖ የዕውቅና ሽልማት፣ እኤአ በ2012 በመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች የዓመቱ ምርጥ መምህር፣ እኤአ በ2014 የዓመቱ ምርጥ መምህር ተብለው ለስፔሻላይዜሽን በሚማሩ የክፍለ ትምህርቱ ተማሪዎች ተመርጠዋል፡፡

ዶክተር አበበ በጅጋ ከዚህ ሁሉ በላይ የሚታወቁት ዕውቀታቸውን ሳይሰስቱ ለመስጠት በሚያደርጉት ትጋትና ሕሙማኑን ለመርዳት በሚከፍሉት መሥዋዕትነት ነው፡፡ ከ1000 በላይ የሚሆኑ ሕጻናትን ከዓይነ ሥውርነት ታድገዋል፡፡ ተማሪዎቻቸው በዕውቀት ብቁ፣ በሥነ ምግባር ምስጉን፣ በሕዝብ አገልጋይነትም ታማኝ ሆነው እንዲወጡ ይፈልጋሉ፡፡ ለዚህ ደግሞ ዕውቀታቸውንም፣ ምክራቸውንም ይለግሳሉ፡፡ ተማሪዎችን በማክበር ሕዝብ የሚያከብሩ የሕክምና ባለሞያዎችን ለመፍጠር ይተጋሉ፡፡ በተደጋጋሚ በተማሪዎቻቸው ተመራጭ መምህር ያደረጋቸውም ይኼው ነው፡፡ ሕሙማኑን እስከመጨረሻው በመርዳት መፍትሔ እንዲያገኙ ይተጋሉ፡፡ ከእርሳቸው እጅ ሕክምናን ለማግኘት ዕድል ያገኙ ሁሉ ከሞያዊ ችሎታቸው ባሻገር የአባትነትና የወንድምነት ጠባያቸውን፣ ችግሩን ፈትተው የዓይን ብርሃንን ለመመለስና የዓይንን ጤንነት ለመጠበቅ የሚያደርጉትን ግብግብ ያስታውሳሉ፡፡ የሞያ አጋሮቻቸውና ተማሪዎቻቸው ‹ችግርን በመፍታት እንጂ ገንዘብን በማግኘት የማይደሰቱ› ይሏቸዋል፡፡

↧

በስነጥበብ ዘርፍ –የ2007 ዓ.ም. በጎ ሰው ተሸላሚ –ሰዓሊ ታደሰ መስፍን!

$
0
0

seali tades

ጌጡ ተመስገን ከአዲስ አበባ አክሱም ሆቴል እንደዘገበው:-

ሰዓሊ ታደሰ መስፍን

ሰዓሊ ታደሰ መስፍን በ1945 ዓ.ም በወልዲያ ነበር የተወለደው፡፡ ከእረኝነቱ ጀምሮ እጅና እግሩ ላይ በእንጨት በመሞንጨር ሥዕልን የጀመረው አዳጊው ምንም እንኳን ዝንባሌው ወደ ሥዕል ማጋደሉን ከልጅነቱ ቢረዳም መደበኛ ትምህርቱን ከመከታተል ወደ ኋላ አላለም፤ በዚሁ መሠረት በዕቴጌ ጣይቱ ብጡል ት/ቤት መደበኛ ትምህርቱን ጀምሮ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት ቆይታውን እንዳጠናቀቀ የ6 ዓመቱ ታዳጊ ከአጎቱ ጋር ለመኖር ወደ አዲስ አበባ መጣ፡፡ አዲስ አበባ ከመጣ በኋላም በስዊዲሽ ሚሽን ት/ቤት ገብቶ መደበኛ ትምህርቱን በማጠናቀቅ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በበዕደ ማርያም ት/ቤት አጠናቀቀ፡፡ ከመደበኛ ትምህርቱ ጎን ለጎን ግን በትምህርት ቤቱ ውስጥ ለሚዘጋጀው መጽሔት “ኢሉስትሬሽን” የውጭ ሽፋን የመሳሰሉትን ይሰራ ነበር፡፡

ሰዓሊ የመሆን ጥልቅ ፍላጎትና ችሎታ ስለነበረው 1960 ዓ.ም ሥነ ጥበብ ት/ቤት ገባ፡፡ በአዲስ አበባ ሥነ ጥበብ ት/ቤት ቆይታው ታዋቂው ሰዓሊ ገ/ክርስቶስ ደስታ ያስተማረው ሲሆን እንደነ ዲዛይነር ታደሰ ግዛውን ጨምሮ በድንቅ መምህራን መማሩን የሚናገረው ሰዓሊ ታደሰ በተማሪነቱ ከሌሎች አቻዎቹ የላቀ ሥራ በመሥራት የከፍተኛ ትምህርቱን በማዕረግ አጠናቋል፡፡

የዛሬው አንጋፋው የያኔው ወጣቱ ሰዓሊ ከተመረቀ ከአምስት ዓመት በኋላ የብሔራዊ ቴአትር “አንድ ሰዓሊ መርጣችሁ ላኩልን” በማለት ለሥነ ጥበብ ት/ቤቱ በደብዳቤ ጥያቄ አቀረበ፡፡ ሰዓሊ ገ/ክርስቶስ ደስታም በወጣቱ ችሎታ በመተማመን ሰዓሊ ታደሰን ወደ ብሔራዊ ቴአትር ላከው፡፡ በመድረክ ዲዛይን ሥራው የብዙዎችን አድናቆት የተቸረው ሲሆን በቅርበት ሥራውን የተከታተሉ ሙያተኞች “በዚያን ዘመን እሱ ይሰራቸው የነበሩት የመድረክ ዲዛይኖች ዛሬ እንኳ በዲጂታል ዘመን እንዳልተሠራ ይመሰክራሉ፡፡

ለተጨማሪ ከፍተኛ ትምሕርት ወደ ራሽያ ሀገር በማቅናት በሴንት ፒተርስበርግ ከተማ በሚገኘው ሬፒን አካዳሚ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርቱን ለመከታተል የቻለ ሲሆን በዚህ ተቋም በነበረው ቆይታ ከራሽያ ተማሪዎችም ሆነ ከሌላ ሐገር ከሄዱት ተማሪዎች እጅግ የላቀ ብቃት አሳይቷል፡፡ በዚህም ልዩ ብቃቱ በአካዳሚው ታሪክ የመጀመሪያው የውጭ አገር ዜጋ የክብር ተሸላሚ በመሆን ማስተርሱን ይዞ ወደ አገሩ ተመለሰ፡፡ በከፍተኛ ውጤት በማዕረግ ተመርቆ ሐገሩ ከተመለሰ በኋላ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ስር የሚገኘውን እና ለሀገራችን ፋና ወጊ የሆነውን የአዲስ አበባ ሥነ ጥበብ ት/ቤት ሰዓሊ ታደሰን እና ሠዓሊ እሸቱ ጥሩነህን ተቀብሎ በተቋሙ የነበረውን የኪነ ንድፍ(ድሮዊንግ) ደረጃ በጣም ከፍ ያደረጉበት ጊዜ ነበር፡፡

በደርግ ጊዜ በየጊዜው ለብሔራዊ ግዴታ በሚሉ እና በሌሎችም መነሻዎች ምንም ሳይከፈለው በነፃ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ፖስተሮችንና ሥዕሎችን በመስራት፣ የሶሻሊስት ኢትዮጵያ ዓርማን በመቅረፅ፣ ለታላቁ የሕዝብ ለሕዝብ ትዕይንት የሚሆኑ የመድረክ እና የአልባሳት ዲዛይን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በማዘጋጀት፣ እንዲሁም የሀገራችን የመገበያያ ሳንቲሞች (25 ሳንቲም እና 50 ሳንቲም) ላይ የራሱን ሙያዊ አስተዋፅዖ በማድረግ አንጋፋው አስተማሪ እና ሰዓሊ ታደሰ የሚጠበቅበትን ሀገራዊ ግዴታ ሊወጣ ችሏል፡፡

በተለያዩ ጊዜያት በመንግሥት እና በሌሎችም አካላት ሙያዊ አስተዋጽዖን ሲጠየቅ ወደ ኋላ ብሎ የማያውቀው ሰዓሊው ከደርግ መንግሥት መውደቅ በኋላም በተለያዩ የመታሰቢያ ሥራዎች ላይ ሙያዊ ተሳትፎን አድርጓል ከቅርብ ጊዜ ሥራዎቹ ውስጥም ትግራይ ላይ ያለውን የሰማዕታት ሐውልት የመጀመሪያውን ንድፍ ያጠናና የፈጠረ እንዲሁም በአማራ የሰማዕታት ሐውልት ሥራ ላይ የበዛ አስተዋፅኦ ያደረገባቸውን መጥቀሱ በቂ ይሆናል፡፡

ሰዓሊ ታደሰ መስፍን ገና በወጣትነቱ ከሥነ ጥበብ ት/ቤቱ በማዕረግ ሲያጠናቅቅ ጃንሆይ የወርቅ ሰዓት ሸልመውታል፡፡ የሥነ ጥበብ እና የመገናኛ ብዙኃን ሽልማት ላይ በምርጥ ሰዓሊነቱ መሸለሙ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ውጪ ግን ለበርካታ ዓመታት ሀገሩን ያገለገለው አንጋፋው ሰዓሊ የሚገባውን ያህል ቀርቶ ለሥራው መታሰቢያ የሚሆን እውቅናን እንኳን በተለይ ከሥነ ጥበብ ትምህርት ቤቱ አልተሰጠውም፡፡ ከተቋሙ በተቃራኒው ግን በሥነ ጥበብ ት/ቤቱ ተማሪዎቹ በተደጋጋሚ ሊሸለምና ሊመሰገን ችሏል፡፡

በአሁኑ አጠራሩ አለ የሥነ-ጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ጥሩ ጥሩ መምህራን ቢኖሩም ለተማሪዎች የምንጊዜም ምርጥ መምህራቸው በመሆን ሰዓሊ ታደለ መስፍን በእነርሱ የቃል ምስጋና ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ሽልማቶችን አግኝቷል፡፡ “ተማሪ በአንድ ድምፅ የሚወደውና የሚያደንቀው አንጋፋ ሰዓሊ ነው” በማለት የሚመሰክሩለት ተማሪዎቹ “ለመምህራቸው እና እውቁ ሰዓሊ ታደሰ መስፍን የማይገባው ሽልማት የለም” ሲሉ ይከራከራሉ፡፡ ታዋቂው ሰዓሊ መዝገቡ ተሰማ በበኩሉ “በሥነ ሥዕል እንደ ታደሰ መስፍን ለመንግሥት ሆነ ለአገሩ በሚገባ ያገለገለ ሰው የለም፡፡ እሱ እንደዚህ አድርግ ካሉት “እምቢ” የማይል ሰው ነው፡፡ በዚያ ላይ ቢያንስ እንኳን መልሳችሁ እንደዚህ አድርጉልኝ የማይል ነው፡፡” በማለት የአንጋፋውን ሰዓሊ ብቃት ይመሰክራል፡፡

አንጋፋው ሰዓሊ እሸቱ ጥሩነህ በበኩላቸው “እንደ ታደሰ መስፍን ዓይነት ሠዓሊ በዘመናት ውስጥ አንድ ሁለት ሰው ነው የሚታየው” በማለት አድናቆታቸውን ካወሱ በኋላ የታደሰ ብቃትን የሚያህል የዕውቀትና የጥበብ ሰው የሌለን በመሆኑ ከእኛም አልፎ አፍሪካን የሚያስጠራ ነው፡፡ በማለት ስለሙያተኛው ብቃት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡

↧

በስፖርት ዘርፍ –የ2007 ዓ.ም. በጎ ሰው ተሸላሚ –ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ!

$
0
0

woldemeskel

– ዶ/ር ወልደ መስቀል ኮስትሬ

ጥር 1939 ዓ ም ሰሜን ሸዋ ተጉለት እና ቡልጋ የተወለዱት ወልደ መስቀል ኮስትሬ በ2 ዙር በመጀመሪያ ከ1964 -1970 እንደገና ደግሞ ከ1974 -1982 በአጠቃላይ 14 አመታትን በወጣትነታቸው ካሳለፉባት የምስራቅ አውሮፓዋ ሀገር ሀንጋሪ በባዮሎጂ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ የዶክትሬት ዲግሪ ባለቤት ናቸው፡፡

ዶ/ር ወልደመስቀል ወደ ሀንጋሪ ለትምህርት ከማምራታቸው ከሳምንታት በፊት በ1964 በቶኪዮ ኦሎምፒክ ለሚሳተፈው የአትሌቲክስ ቡድናችን በ800 ሜ እና 1500 ሜትር ለተወዳዳሪነት ተመርጠው ነበር፡፡ ነገር ግን ትምህርት ይሻለኛል በማለት ውድድሩን በመተው ወደ ሀንጋሪ አምርተዋል፡፡ የአትሌቲክስ አሰልጣኝነትን የጀመሩት በኮተቤ ኮሌጅ አስተማሪ እያሉ በ70ዎቹ መጀመሪያ ላይ ሲሆን በ1972 የሙኒክ ኦሎምፒክ በሚሳተፈው ቡድናችን ውስጥ ዋና አሰልጣኝ ለነበሩት ንጉሴ ሮባ ምክትል አሰልጣኝ በመሆን ነበር፡፡

ዶክተር ወልደመስቀል በ1982 የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከተቀበሉ በኋላ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው በስፖርት ኮሚሽን ውስጥ በከፍተኛ ባለሙያነት ሰርተዋል፡፡ ወደ አትሌቲክስ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝነት የመጡት የአሰልጣኝ ንጉሴ ሮባን ኅልፈት ተከትሎ በ1992 ነው፡፡

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያ ለዓለም ካበረከተቻቸው ምርጥ ምርጥ አትሌቶች ጀርባ እኝህ ኮስታራ አሰልጣኝ ይገኛሉ፡፡ ከ1992 የባርሴሎና እስከ 2008 ቤጂንግ ኦሎምፒክ ለ16 ዓመታት በዘለቀው የዋና አሰልጣኝነት ዘመናቸው ኢትዮጵያ በዓለም አደባባይ ያኮሯትን የ5000 እና የ10,000 ሜትር አትሌቶች ለውጤት በማብቃት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ዶ/ር ወልደመስቀል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድንን እያሰለጠኑ በተሳተፉባቸው አምስት ኦሎምፒኮች ላይ 28 ሜዳሊያዎችን በድምሩ ለሀገራቸው አስገኝተዋል (13 ወርቅ 5የብር እና 10 የነሐስ ሜዳሊያዎችን)፡፡ በአትሌቲክሱ ዓለም ለአሰልጣኞች የሚሸለመውን የዓመቱ ምርጥ አሰልጣኝነት ሽልማትን በ2006 ዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የዓመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ብሎ ሸልሟቸዋል፡፡

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live