Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የቀድሞዋ የአባይ ጸሐዬ ሚስት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር /ሞንጆሪኖ/

$
0
0

አቶ መለስ ዜናዊ በሕይወት በነበሩበት ዘመን የካሳንቺሱን መንግስት ከመቀሌ አምጥተው የደባለቋት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር /ሞንጆሪኖ/ በንትርክ ላይ ባለው የሕወሓት ጉባኤ ላይ ነጥረው ወጥተዋል:: ዛሬ ወይም ነገ የሕዝብ ድምጽ ይሰጥበታል በሚባለው በዚሁ ጉባኤ ላይ አቶ መለስ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አድርጎ ያመጣት ሞንጆሪኖ ለትልቅ ቦታ ታጭታለች እየተባለ ነው:: ለመሆኑ ይህች ሴት ማናት?

ኤርሚያስ ለገሰ የመለስ ትርፉቶች በሚለው መጽሐፉ ላይ እንዲህ ጽፏት ነበር:: ተጨማሪ መረጃዎች እስኪመጡ መልካም ንባብ::

fetelework

የሞንጆሪኖ ለቅሶ…

በሰፈሩት ቁና ሆነና ነገሩ የሕወሓት መሰንጠቅ የሞንጆሪኖን ፍጹማዊ አገዛዝ እንዲያከትም አደረገው:: በ እርግጥ የተስፈማሪያምን ያህል ውግዝ ከማርዮስ አልደረሰባትም:: ከአቶ መለስ ተግሳጽ ውጭ::

አቶ መለስ እንዲህ አላት:-

“ሞንጆሪኖ አዲስ አበባን የለውጥ ማዕበል ውስጥ አስገብተሽ ታስተካክያለሽ ብለን ነበር የላክንሽ:: አንቺ ግን የድርጅቱን አደራ በልተሽ ከጀርባ ስታደራጂ ከረምሽ:: ኸረ ለመሆኑ ምን ጎድሎብሽ ነው? እነስዬን ስታውቂያቸው ቀርተሽ ነው; አብረሽ ድርጅቱ ላይ ገመድ ልታጠልቂ የነበረው?”

ሞንጆሪኖ ተንሰቅስቃ አለቀሰች:: ስጋ ስው አትን ጠርታ ሁለተኛ እንደማይለመዳት ቃል ገባች:: እግሩ ላይ ተደፍታ ይቅርታ ጠየቀች:: ከነተወልደ ጋር እንዲኤት እንደተመሳጠረች ዘከዘከች:: የህቡዕ እንስቃሴው ከስድስት ወር በፊት በአዲሳባ መጀመሩን አስረዳች:: በአዲስ አበባ ያሉት የዞን ሊቀመናብርት ትልቁ ሥራቸው መሆኑን ገለጸች:: ካድሬዎቹ አባዝተው ስለበተኑት ወረቀት ዘከዘከች:: አመናት::

ፊቱን ወደ እሷ አነሳ… ራራላት::

እንደቀድሞ ባሏ አባይ ጸሐዬ የምህረቱ ተቋዳሽ አደረጋት:: የዘመናዊ ዕውቀት ማነስ የፈጠረው ችግር ሊሆን እንደሚችል በመግለጽ የቀለም ትምህርት እንድትማር ፈረንጅ ሃገር ሰደዳት:: ትምህርቷን አጠናቃ እንደመጣች ጓዟን ጠቅልላ መቀሌ ገባች:: የትግራይን ካቤኔ ተቀላቀለች:: ለአቶ መለስ ያላትን ታማኝነቷን በተግባር አሳየች:: እሱም ካሳውን በቁሙ ተቀበለ:: በዚህ ሳይወሰን በሕወሓት ሁለተኛ ትውልድ ውስጥ እንድትታቀፍ የመጀመሪያው ምርጫ አደረጋት::

(ሞንጆሪኖ ፈትለወርቅ ሆናለች:: የአዲሷ ፈትለ ወጣትነት የድሮዋ ሞንጆሪኖ ነው:: አፍታም ሳይቆይ የሕወሓት ድርጅታዊ ጉባኤ በመቀሌ ተካሄደ:: ፈትለወርቅ የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነች::

(የመለስ ትርፉቶች መጽሐፍ ገጽ 56 – 57)

***


መሪዎቻችን እውነት ተናግረው አያውቁም! ለውጥ እንፈልጋለን! –ተስፋዬ ነጋ

$
0
0

ነሐሴ  2007

Woyaneበኢትዮጵያ ተከሰተ ስለተባለው ረሃብ በማህበራዊ ሚዲያና በኢንተርኔት ላይ በስፋት ሲዘገብ ቆይቷል። አብዛኞቹ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን (ቢቢሲ፣ ዘጋርዲያን፣ አልጀዚራ፣ ኒውስ 24) በኢትዮጵያ ውስጥ በዝናብ እጥረት ሳቢያ በተከሰተ ድርቅ የተጎጂዎች ቁጥር 4.5 ሚሊዮን እንደደረሰ፣ እነዚሁን በረሃብ የተጎዱ ወገኖች ለመመገብ ለምግብና ለእህል ግዢ ተጨማሪ ከ320 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግ ሲዘግቡ ከርመዋል።

ለዝናብ እጥረት መንስኤውም የኤል ኒኖ የአየር መዛባት እንደሆነ በእነኚህ የመገናኛ ብዙሃን ተነግሯል፣ እየተነገረም ይገኛል። ችግሩ የከፋ እንደሆነና የዝናብ እጥረቱ አዝርዕትን ከማቅጨጭ አልፎ አድርቋል። በእነዚሁ ዝናብ-አጠር የኢትዮጵያ አካባቢዎች ነዋሪዎች ለተለያዩ በሽታዎች ተዳርገዋል፣ በምግብ ንጥረነገር ማነስ የተጎዱ  ህፃናትና አዋቂዎች እንዳሉ የመስክ ጥናቶች ይፋ አድርገዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጀት ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ ዘንድሮ ምዕራብ አርሲን ጨምሮ ትርፍ አምራች የሆኑ የኦሮሚያ አካባቢዎችም ጭምር የምግብ እርዳታ ይፈልጋሉ። የውሃና የግጦሽ መመንመን ተከትሎ የአርብቶ/ አርሶ አደሮችን ከብቶች ቁጥር በሞት ምክንያት በእጅጉ እንዲቀንሱ አድርጓል፣ በመሆኑም አስቸኳይ አልሚ ምግብ በዚህ አመት ከሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች ከእጥፍ በላይ [ከየካቲት 2007 (49%) እስከ ግንቦት 2007 (97%)] አድጓል። በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ጊዜያዊ ሃላፊ “የበልግ ዝናብ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሜትሮሎጂ ድርጀት ከተነበየው በተቃራኒው ለአጭር ብቻ ነው የዘነበው” ብለዋል።

ወደ ኢትዮጵያ መንግስት ስንመጣ ደግሞ የተመጣጠነ እድገት በአገሪቷ ያለ ይመስል፣ “ኢኮኖሚያችን በ 11% አድጓል፣ ድህነት ታሪክ ሆኗል፣ በቀን ሶስት ጊዜ ለመብላት በቅተናል” የሚሉ መሰረት የሌላቸው አሉባልታዎችን በፊስቡክ ካድሬዎች ሲያናፍስ የቆየ ቢሆንም እውነት ተደብቃ አትቀርምና ይኸው የድርቁ መከሰት ሰሞኑን ገሃድ ሆኖ ወጥቷል። ሕወሃት/ ኢህአዴግ ድርቅ መኖሩን ሲያስተባብል ለረጅም ወራት የቆየ ቢሆንም በቅርቡ በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች ድርቅ መኖሩን ያጋለጠ አንድ መረጃ ወጥቷል። አንድ ግለሰብ ከአዲስ አበባ አፋር ሰመራ በሚወስደው መንገድ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ በድርቁ የሞቱ የቤት እንስሳትን  ቪድዮ ቀርጾ በፊስቡክ በመልቀቁ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እየተነጋገሩበት ይገኛሉ። መረጃው የህወሃት ኢህአዴግን ውሸት ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነበር። ከዚያ በኋላም ድርቅ የለም እያለ ሲክድ የቆየው የህወሃት ወያኔ መንግስትም ይህንን አውነታ እያቅማማም ቢሆን ወደማመኑ ደረጃ ደርሷል።

ከዚህ ጋር ተይይዞ በቅርቡ የምግብ እጥረት ይኖራል በሚል ግምት አለም አቀፍ ሚዲያዎች በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ መግለጫዎችን እያወጡ ነበር። የኢትዮጵያ መንግስትም አንዴ “ድርቅ በኢትዮጵያ የለም” ሲል ሌላ ጊዜ “በ አንዳንድ አካባቢዎች ድርቅ አለ ረሃብ ግን የለም” የሚል ውሃ የማይቋጥር አሰልቺ መከራከሪያ በተደጋጋሚ አቅርቧል። ችግሮች መኖራቸውን አምኖ እርምጃ አለመውሰድ የህወሃት ኢህአዴግ ባህርይ ይህ ነው። ኢህአዴግ ማለት ችግሮቹ አፍጥጠው በገሃድ እየታዩ ሽምጥጥ አድርጎ መካድን የተካነ ቡድን ነው።

ከዚህ ሁሉ “አለ!፣ የለም!” ንትርክ ድርቁ መከሰቱን በአለም አቀፍ ሚዲያና በማህበራዊ ድህረገጾች ከተነገረም በኋላም ቢሆን ኢህአዴግ “ድርቁና ረሃቡ ከአቅሜ በላይ አይደለም” የሚል አዲስ የመከራከሪያ ስልት ይዞ ብቅ ብሏል። ህወሃት/ ኢህአዴግ በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ “ከቁጥጥራችን ውጭ አይደለም የውጭ አርዳታም አያስፈልገንም” የሚል ሰንካላ መከላከያ በማቅረብ አንባቢውን፣ ተመልካቹንና፣ አድማጩን ለማደናገር ሞክሯል። መቼም ይህች አገርና ህዝቦቿ እውነት የማይናገሩና ለችግሮቿ መፍትሄ የማይሰጡ ጨካኝ መሪዎችን በተለያዩ ጊዜያት አስተናግዳለች። ኢትዮጵያ አርሶአደሮች በዝናብ እጥረት የተነሳ አዝመራ ሲበላሽባቸውና ሲራቡ፣ የአርብቶአደሮች የቀንድና የቁም ከብቶቹ በድርቁ  ምክንያት ሲያልቁ፣ አይዟችሁ ብሎ ድጋፍ የሚሰጥ ሳይሆን፣ ምንም አዲስ ነገር እንዳልተፈጠረ አድርጎ በማሰብ ለህዝቡ አገልግሎት ከማበርከት ይልቅ ለግል ጥቅምና ዝና የሚጨነቁ የኢህአዴግ ባለስልጣናት እንደአሸን የፈሉባት አገር ሆናለች። በቅርቡ በተከሰተው ድርቅና ረሃብ አቶ ሬድዋን ሁሴን እና አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ሁነኛ ተዋናዮች ሆነው መድረኩን ተቆጣጥረውት ነበር።

ከድርቅ ጋር በተያያዘ የጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት አቶ ሬድዋን ሁሴን “የከብቶች መሞት የተከሰተው ባለቤቶቹ ለከብቶቻቸው በጊዜው ውሃ ስላላጠጧቸው ነው” የሚል አላጋጭ መልስ ለመገናኛ ብዙሃን በመስጠት በድርቁ በተጠቃው ህዝብ ላይ ተሳልቀዋል። ይህ ንግግራቸው የህወሃት ኢህአዴግ ባለስልጣናት የአስተሳሰብ ደረጃቸው ምን ያክል የዘቀጠ እንደሆነ ያሳየ ክስተት ነው። አቶ ሬድዋን የባዮሎጂ መምህር ናቸው። እናም የአርብቶ አደሩን የከብት አያያዝና አረባብ ባህል በደምብ የተረዱ አልመሰለኝም። እንዲያውም ለእርሳቸው የአርብቶ አደር ህይወት እጅግ ውስብስብ መሆኑን የተረዱት አይመስልም። አርብቶ አደር  የቁምና የቀንድ ከብቶች እንዲሁም በግና ፍየሎችን ለረጅም ዘመናት [ያለሳይንሳዊ ድጋፍ] ሲያረባ የኖረ ህዝብ ነው። አቶ ሬድዋን ያልተረዱት ጉዳይ የአሁኑ የቤት እንስሳት በጅምላ መሞት ውሃ ማጠጣት ወይም አለማጠጣት ጋር የተያያዘ አለመሆኑን ነው። እኛ እስከምናውቀው ድረስ አርብቶ አደሩ ሆነ አርሶ አደሩ ከራሱ አስበልጦ ለቤት እንስሳት እንክብካቤ የደርጋል። የቤት እንስሳት ለአርሶ አደሮችና ለአርብቶ አደሮች ህይወት ናቸው። የእኛ ህዝብ ከህይወቱ ጋር የተቆራኙ እንስሳትን አይደለም በቸልተኝነት ውሃ ባለማጠጣት እንዲሞቱ ማድረግ ይቅርና፣ አርዶ ለመብላት እንኳን በጣም የሚቸገር ህዝብ ነው። ለዚያም ነው እንስሳቱ እየሞቱ ምንም ምርጫ ስለሌለው ዝም ብሎ እያየ ያለው። አቶ ሬድዋን ደግሞ ያልመለሱት ጥያቄ ቸልተኛ ሆነው ውሃ ሳያጠጡ የቀሩት ስንት አርሶ/አርብቶ አደሮች ናቸው? የሚለው ነው። እዉነት ሁሉም አርብቶአደር ውሃ ባለበት አካባቢ እንስሳቱን አልወሰደም? ውሃ አላጠጣም? ወይስ አቶ ሬድዋን የተለመደ ህወሃታዊ አነጋገር ማንጸባረቃቸው ነው? የጊዜ ጉዳይ ነው። ይህ ሃላፊነት የጎደለው አነጋገር የኋላ ኋላ አቶ ሬድዋንን ዋጋ ያስከፍላቸዋል።

በተመሳሳይ  ሁኔታ ባለፈው ሳምንት አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ አምባሳደሮችንንና ዳያስፖራ ኢትዮጵያውያንን ሰብስበው ባናገሩበት ወቅት ድርቁን በጣም አቅልለው አይተውታል። የእርሳቸው ንግግር ሃላፊነት የጎደለው ነው። እሳቸው ህወሃት ባዘጋጀላቸው አልጋ እየተኙ የቤተመንግስት ምግብ እየበሉ በቀን አንድ ጊዜ እንኳን መብላት ያልቻለን አርሶ/አርብቶ አደርን ችግር ለማጣጣል መሞከራቸው ትዝብት ላይ ጥሏቸዋል። እሳቸው አንድ ቀን እራት ሳይበሉ ቢያድሩ ረሃብ ምን ያክል የሚያንገበግብ መሆኑን የሚያውቁት አይመስለኝም። ይባስ ብለውም አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ አለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች ድርቁን ራሳችን መቋቋም እንችል እንደሆነ ዳር ላይ ሆነው እያዩን ነው የሚል አሁንም ሃላፊነት የጎደለው ንግግር ሲናገሩ በተሌቪዥን አየኋቸው። ባይዋሹ ጥሩ ነበር፣ ውሸት አንድ አገር እመራለሁ ከሚል ጠቅላይ ሚኒስትር አይጠበቅም። እናም ጉዳዩ እርሳቸው እንዳሉት ሳይሆን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወደ 320 ሚሊዮን በላይ የሚጠጋ ገንዘብ ከእርዳታ ለጋሽ አገሮች እየፈለገ እንደሆነ በተደጋጋሚ ገልጿል። የአቶ ሃይለማሪያም መንግስት መደበ የተባለው ገንዘብ ግን 33 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው። ታዲያ ተቆርቋሪው ማነው? እኔ እስከሚገባኝ ለኢትዮጵያ ህዝብ ተቆርቋሪና ደራሽ የውጭ የእርዳታ ድርጅቶችና መንግስታት እንጂ ድርቁንና ረሃቡን የደበቁትና የካዱት ሃይለማሪያም እና እሳቸው የሚመሩት መንግስት አይደለም። ታየኝ እኮ በ 33 ሚሊዮን ዶላር ድርቁንና ረሃቡን ሲከላከሉ!

አቶ ሃይለማሪያ እንደዋሹን የድርቁና ረሃብ ጉዳይ በቀላሉ የሚታይ ሳይሆን በምግብ እጥረት የሚሰቃየው ሰው ቁጥር በ 55% በመጨመር ከ2.9 ሚሊዮን አሻቅቦ ወደ 4.5 ሚልዮን ከመድረሱም ባሻገር የእርዳታ ፈላጊው ቁጥር እስከ ሚያዚያ 2008 አሁን ካለው አህዝ ቢጨምር እንጂ እንደማይቀንስ መገለጹ ነው። አቶ ሃይለማሪያ በንግግራቸው ወቅት ትዝብት ላይ የጣላቸው ሌላው ነገር፣ ዕርዳታ ለጋሽ ድርጅቶችና አገራት እንደ ኢህአዴግ ሃላፊነት የጎደላቸው አድርገው መናገራቸው ነው። ለዘመናት በምግብ እጥረት የሚሰቃየውን ህዝብ ሃላፊነት ወስደው ህይወቱን እያተረፉት ያሉትን ለጋሽ ድርጀቶች በምን ሂሳብ ነው ህወሃት/ ኢህአዴግን አምነው “ትወጡት እንደሆነ ዳር ላይ እናያለን” የሚሉት? እርዳታ ድርጅቶቹ በሰብአዊ ድርጊታቸው ከወያኔ ጋር ማወዳደር የሚቻል አይሆንም። ምዕራብያውያን ህወሃት በሰው ህይወት ላይ የሚሰራውን ድራማ አብረው አይተውኑም። አቶ ሃይለማሪያም ይህንን ንግግር ሲናገሩ  “በምዕራብያውያን መንግስታት ተዓማኒነት አለን” ለማለት የተናገሯት ቀልድ እንደሆነች ይገባናል። አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ይህንን ሲናገሩ በእውነት ለጋሽ ድርጅቶች አማርኛ አይሰሙም ብለው አስበው ይሆን? ከሰሙኝ ይታዘቡኝ ይሆናል አይሉም? የ 320 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ በተመለከተ የ ዩኒሴፍ ተወካይና ጊዜያዊ ሃላፊ ሚስ ሜሊሶፕ  “ለጋሽ ድርጅቶች ቸር መሆን አለባቸው፣ የተፈጠረውን ቀውስ በእነሱ በተለመደ ድጋፍ እንሸፍናለን” በማለት ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል። ይህም ኢህአዴግ ኖረ አልኖረ ምዕራብያውያን አገሮች በድርቁ ለተጎዳው ኢትዮጵያዊ ሰብአዊ ዕርዳታ መስጠታቸውን ለአፍታም ቢሆን የማያቋርጡ አጋር መሆናቸውን ያሳዩበት ቃል ኪዳን ነው። ምዕራብያውያን ዕርዳታ ለጋሽ ድርጅቶችና አገራት ኢህአዴግን ሳይጠይቁ የራሳቸውን መርሃግብር አውጥተው በድርቅ የተጎዱ ተረጂዎችን ወደፊትም ይታደጓቸዋል። አቶ ሃይለማሪያም ያላወቁት ግን 100% በህዝብ ድምፅ ተመረጥኩ ያለው ኢህአዴግ ድርቅና ረሃብን ከመመከት አኳያ ምንም ተጨባጭ ሚና አለመጫወቱን ነው።

አቶ ሃይለማሪያም ሌላ የተጣረሰ መረጃ የወያኔ አምባሳደሮችና እና ዳያስፖራ ኢትዮጵያውያንን በሰበሰቡበት ወቅት ተናግረዋል። እሳቸው እንዳሉት በአሁኑ ሰዓት በምግብ እጥረት የተነሳ ለከፋ ሁኔታ ተዳርገው በማቆያ ጣቢያ እንዲመገቡ የተደረጉ ህጻናት የሉም ብለዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጀት ያወጣው መረጃ ደግሞ እሳቸው ካሉት በተቃራኒው ነው። እንደ ተመድ (UN) መረጃ ከሆነ በምግብ የተጎዱ የህጻናት ቁጥር በቅርቡ በ 14.4 ፐርሰንት በማደግ 302,605 ደርሷል። ታዲያ ለአቶ ሃይለማሪያም በምግብ የተጎዱ ህጻናት እነማን ናቸው የሚለውን ጥያቄ ሳይመልሱ ፌዝ በመሰለ ንግግራቸው አምባሳደሮችን ሸኘተዋቸዋል። አቶ ሃይለማሪያ ደሳለኝ በምግብ እጥረት መጎዳት ማለት ምን ማለት ነው የሚለውን እንኳን ሳያገናዝቡ የህወሃት ኢህአዴግ የውሸት ቅርሻት ተፍተውብናል። 14 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በተራቡበት አገር ምንም አዲስ ነገር እንዳልተከሰተ በማውራት የህወሃት ባለስልጣናትን ስኬት ብቻ መዘርዘራቸው  ትዝብት ውስጥ ጥሏቸዋል። ከንግግራቸው የተረዳነው ሃይለማሪያም በራሳቸው የሚያስቡ ሳይሆኑ ከመጋረጃ ጀርባ በተቀመጡ መሪዎቻቸው በሩቅ መቆጣጠሪያ (ረሞት ኮንትሮል) የሚንቀሳቀሱ ግለሰብ ናቸው።

እኔን እያሳሰበኝ ያለው የወደፊቱ የአገራችን ሁኔታ ነው። መቼ ነው ሃላፊነት የሚወስድ መንግስት የሚኖረን? የረሃቡ ጉዳይ እስከመቼ ይሆን በመንግስት ባለስልጣናት በዝምታ የሚታለፈው? ህዝባችን ሲራብ ለምን ዝም ይባላል? ድርቅ ሲከሰት የህወሃት ኢህአዴግ ባለስልጣናት ትዝብት ላይ የሚጥል ነገር ለምን በአደባባይ ይናገራሉ? መንግስት ለኢትዮጵያ ህዝብና ለአገር ውስጥ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ችግሩ ሲከሰት ለምን ይፋ አያደርግም? በአገራችን የሚከሰቱ ተፈጥሯዊ፣ ማህበራዊና፣ ፖለቲካዊ ችግሮች የምንሰማው ከምዕራባውያን አገራት ወይም የአለም አቀፍ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ባለስልጣናት ነው። ታዲያ የእኛ አለቆች ምንድነው የሚሰሩት? ምንስ እያደረጉ ነው ያሉት? ተመረጥን ያሉት አገርንና ወገንን ለመጥቀም መስሎኝ? በችግር ጊዜ ጥሪ ሊያሰሙ መስሎኝ? እነዚህንና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች የሚመልስልኝ ሁነኛ ሰው አጣሁ። ምን አልባትም እንደተለመደው የውጭ አገር ባለስልጣናት መልሱን አንድ ቀን ሊመልሱልኝ ይችሉ ይሆናል።

ከላይ እንደተገለጸው አሁን ያሉት የህወሃት/ ኢህአዴግ አምባገነኖች ለራሳቸው ስልጣንና ክብር ካልሆነ በስተቀር ለኢትዮጵያ ህዝብ ምንም ደንታ የሌላቸው ናቸው። ኢትዮጵያም የልመና እና እርዳታ ተምሳሌት ሆና እንድትቀጥል ህዝቡን ማስተባበር ያልቻሉ ራስ ወዳዶች ናቸው። እኛም እነዚህን ሃፍረተቢስ ዋሾዎችን መሪዎቻችን ናቸው ብለን ዝም ብለን መቀመጣችን ይገርማል። እስካሁን የሰሩት ጥፋት እንዳለ ሆኖ፣ ለእነዚህ ሰዎች በአንድነት ውሸት በቃችሁ ልንላቸው ይገልባል። ስልጣን ላይ በምርጫ [እነሱ እንደሚሉት] ይሁን በጉልበት [አለም እንደሚያውቀው] የተቀመጡት ህዝብን ሊያገለግሉት እንጂ ሊያፌዙበት አይደለም። በመሆኑም እነዚህ ግለሰቦች ማፌዝ አቁመው የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው። ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ግን ወገኖቻችንን በረሃብና በድርቅ አስጨርሰን ዝም የምንልበት ምክንያት አይታየኝም።

 

አቶ ማሙሸት አማረ ለውሳኔ ተቀጠሩ

$
0
0

‹‹ምስክርነቱ የሀሰትና የተጠና ነው!›› ጠበቃው

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

mamushetአይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም መንግስት ከጠራው ሰልፍ አንድ ቀን ቀድሞ ከለቅሶ ቤት ወደ ቤተ መንግስት ለተደረገውና ለዋናው (ለሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም) ሰልፍ አነሳስቷል በሚል ክስ የተመሰረተበት አቶ ማሙሸት አማረ ዛሬ ነሃሴ 20/2007 ዓ.ም አራዳ ምድብ ችሎት ቀርቦ ለነሃሴ 22/2007 ዓ.ም ለውሳኔ ተቀጠሯል፡፡ አቶ ማሙሸት አማረ ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም በተካሄደው ሰልፍ ላይ ሁከትና ብጥብጥ ፈጥሯል በሚል ተከሶ የነበር ቢሆንም በወቅቱ ከምርጫ ቦርድ ጋር በነበረው ክርክር ሰልፉ ላይ አለመገኘቱን የሚያጋግጥ መረጃ በማቅረቡ በነፃ እንዲለቀቅ ተወስኖ ነበር፡፡ ነገር ግን ክሱ ወደማነሳሳት ተቀይሮ እስር ቤት እንዲቆይ ተደርጓል፡፡

አቶ ማሙሸት በአዲሱ ክስ የአቃቤ ህግን ምስክሮች ለመስማት ከ5 ጊዜ በላይ ፍርድ ቤት እንደተመላለሰ የተገለፀ ሲሆን በተለይ አንዱ ምስክር በፖሊስ ተይዞ እንዲመጣ ቢጠየቅም ፖሊስ ሳያስፈፅም ቀርቷል፡፡ ከአራቱ ምስክሮች መካከል ሶስቱ ዛሬ የመሰከሩ ሲሆን ‹‹አቶ ማሙሸት አማረ 300 ብር ከፍሎ ሰልፍ እንድንወጣ አድርጎናል›› ሲሉ መስክረዋል፡፡

ይሁንና ምስክሮቹ ከማሙሸት ጋር በተገናኙበት ወቅት እንዲሁም ገንዘቡ ሲሰጣቸው፣ ሰልፉ ያለፈባቸውን ቦታዎችና ስለ ሌሎችም ጉዳዮች ሲጠየቁ ‹‹አላስታውሰውም›› ከማለት ባለፈ ዝርዝር የምስክርነት ቃል ሳይሰጡ ቀርተዋል፡፡ ከምስክሮቹ መካከል ሁለቱ አቶ ማሙሸትን ያስያዙ ደህንነቶች መሆናቸውን አቶ ማሙሸትና ጠበቃው በችሎቱ የገለፁ ሲሆን ምስክሮቹ በበኩላቸው ስራቸውን ሲጠየቁ ‹‹የግል›› እያሉ ከመመለስ ውጭ የመንግስት ስራ እንደማይሰሩ ተናግረዋል፡፡ ሆኖም የመንግስት ሰራተኛ መሆናቸውን የሚያሳይ መታወቂያ ሲጠየቁ ሊያሳዩ አልቻሉም፡፡ ከሶስቱ ምስክሮች መካከል አንደኛው ስራውን ሲጠየቅ ‹‹የግል›› ብሎ የነበር ቢሆንም በመስቀለኛ ጥያቄ የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ጥቃቅንና አነስተኛ አመራር መሆኑን አምኗል፡፡

ከምስክሮቹ መካከል ሁለቱ የመኢአድ ደጋፊዎች መሆናቸውን ሲጠቅሱ አንደኛው አቶ ማሙሸት ባቀረቡበት የመስቀለኛ ጥያቄ ከምርጫ በኋላ የወጣቶች ሊግና የኢህአዴግ አባል መሆኑን አምኗል፡፡ የኢህአዴግ አባል ሆኖም ቢሆን መኢአድን እንደሚደግፍም ገልጾአል፡፡ ዳኛው ‹‹በሁለት ወር ውስጥ እንዴት ብለህ የወጣቶች ሊግ አባል መሆን ቻልክ?›› ሲሉት መልስ ሳይሰጥ አልፎታል፡፡

የአቶ ማሙሸት አማረ ጠበቃ ሶስቱም ምስክሮች አብዛኛዎቹን ጉዳዮች እንደማያስታውሱ በመግለፃቸው የተጠና የምስክርነት ቃል መሆኑን ለችሎቱ አስረድተዋል፡፡ በተጨማሪም ከ7 አመት በላይ አዲስ አበባ ውስጥ ኖረው መስቀል አደባባይን ጨምሮ ሰልፉ አመራባቸው የተባሉትን ቦታዎች አናውቃቸውም ማለታቸው፣ መተዳደሪያ ስራቸውን መደበቃቸውና መታወቂያ ለማሳየትም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ምስክርነቱ የሀሰት እንደሆነ ስለሚያረጋግጥ ደንበኛቸው በነፃ እንዲለቀቁ ጠይቀዋል፡፡

“እኛ ውጪ ሆነን ተጨንቀናል፤ እነርሱ ውስጥ ሆነው ያልቀላፋሉ!” –ተክሌ በቀለ

$
0
0

የህወሓት ደጋፊ አለ የተባለዉ

tekeleየፓርቲዎች ጉባኤ በኢትዮጵያቸን አስጨናቂ እየሆነ መጥቷል፡፡በተቃዉሞ ጎራዉም በገዢ ፓርቲዎችም ዉስጥ ማለት ነዉ፡፡በተቃዉሞዉም እጁ ስላለበት ተረጋግቶ ጉባኤ ማካሄድ አልተቻላቸዉም(አንዳንዶቹ በተፈጥሮኣቸዉ ያዉ ቢሆኑም)፡፡በገዥዉ ፓርቲ አባልና አጋር ፓርቲዎች መካከል ፉክክሩ ድብቅ ነዉ፡፡ጸረ ዲሞክራሲያዊና በጥቅም ላይ የተመሰረተ ነዉ፡፡ይህ የታፈነ ዉድድር የት ቦታ እንደሚበጠስና የአሸናፊና ተሸናፊ ወገን እንደሚፈጥር አይታወቅም፡፡ፍጻሜዉ ግን ይህ ሃቅ ይመስለኛል፡፡ የኢህኣዴግ አባል ፓርቲዎች ወደላይም ወደ ጎንም ማደግ አይችሉም፡፡ካደጉ ዉድቀት ይከተላል፡፡እድገታቸዉ ቀድሞዉኑ የተወሰነባቸዉ ናቸዉ፡፡ታድያ እዚህ ከተደረሰ መጪዉን ማሰብ ነዉ፡፡ማእበሉም ይበሉት ናዳዉ ሲነሳ የሚጠርገዉን በዋንኝነት ቢለይም ቅድሚያ የሚጎዳዉ ግን የአሁኑን ጎጅዎችን ነዉ፡፡ታሪክ እያሳየን ያለፈዉ ይህንን ነዉ፡፡በዚህ ማእበልና ናዳ የሚጠቀም ያለ አይመስለኝም፡፡በበኩላችን የሚጠቅመዉን ልናሳይ ባቅማችን ስንቀሳቀስ መንገዱን ዘግተዉ በደል ላይ በደል ጨምረዉ ቀብረዉም ቁመዉብናል፡፡


የብአዴንና ኦህዴድ ከፍተኛ የአመራር አባላት ጭምር እንወክለዋለን ስለሚሉት ሀዝብና ምድር የሚያቀርቡት እሮሮ የታመቀ በደል እንዳለ ያመኑ መሆኑን ይጠቁመናል፡፡ጉዳየ ተከድኖ ይብሰል አይነት ነዉና በሂደት እናየዋለን፡፡ድሮ ድሮ ህወኃት ለሁሉም የሚያለብሳቸዉ የረዕዮተ አለም ልባስ ነበረዉ፡፡ልባሱን አዉልቆ ከጣለዉ ሰንብቷል፡፡በኣንዳድንድ ልምድና ቀለም ቀመስ አመራር አባላቱ ለምኞት የሚሆን የተለጋገበ ርእዮት አለም ያላቸዉ ለማስመሰል ለአባሉና ህዝቡ በማይሰርጽበት ሁኔታ በሚድያዎቻቸዉ ሲግቱት ታዝበናል፡፡ኣባሉ ወድያዉ ይተፋወል፤ህዝቡ መስሚያ የለዉም፡፡መርህም የለም፤ለነገሩ ድሮም አልነበረም፡፡ተገፍተን ወጥተን ነበር ያሉትም የሚተካ አጥተዉ፤ተኩን ባዮችም ጠፍተዉ ወደ እርካቡ መጥተዋል፡፡ምንም አዲስ ነገር የለም!


“እኛ ውጪ ሆነን ተጨንቀናል፤ እነርሱ ውስጥ ሆነው ያልቀላፋሉ!” የህወሓት ደጋፊ የሆነ ሰዉ ተናገረዉ የተባለዉ ነዉ(የዋህ መሆኑ እንጂ የሚያንቀላፉትና ፖለቲካዉን የሚጫወቱት፤እዚያ አምሽተዉም ቤታቸዉ ገብተዉ የማይተኙትን ማየት ነበረበት)፡፡ዉስጡን ስለሚያዉቅ የጨነቀዉ አባል ነዉ፡፡ከቲፎዞነት ተነስቶ ለጥቅሙ ተጨንቆ ከማለት ይልቅ እንደ አባልና ዜጋ ጉዳዩ አሳስቦት ነዉ ብሎ ማሰብ ይሻላል፡፡ግን ይህ አባልና ሌሎች የህወሓት/ኢህኣዴግ ደጋፊዎች ደም የተገበረበትን ትግል ዲሞክራሲን በመግደል እንደተባበሩ በቅዲሚያ ሊረዱት ይገባል፡፡አገሪቱ የጋራ እንደመሆንዋ ተጸጽቶም ቀናዉን መንገድ መያዝ እንደህዝብ ለቀጣዩ ጉዞኣችን ይጠቅማል የሚል እምነት አለኝ፡፡እናንተ የለዉጥ ሃይሎች ሆይ ለዉጥን ፓርቲ እንደማይገድበዉ ልተረዱ ይገባል፡፡ከፓርቲ በላይ ሃገርና ህዝብ ነዉ፡፡ለዉጥ ፈላጊ የድርጅቱ አባላት ለዉጡ እንዳማራችሁ እንደቀረ ብናስተዉልም፤ለዉድቀታችሁ ተጠያቅዎች ግን ራሳችሁ መሆናችሁን ልትክዱት አይገባም፡፡ የህዝብ ድምጽን ደፍጥጦ በስልጣን ለመኖር ላሰበዉ ድርጅታቸችሁ በጭካኔ ሙሉ ድጋፍ ሰጥታችኃል፤በኛ በኩል የምንጠየቅበት ካለ የድርሻችንን ለመዉሰድ ዝግጁ ነን!የህዝባችንን መስዋእትነት አክብረን፤ህገ ምንግስቱን ተቀብለን ልናድግ ስንጥር ባለበሌለ አቅማችሁ ደፍጥታችሁን እዚህ ደርሳችኋል፤መልካም ጉዞ!!!!!!

 

Health: ስኬታማ ትዳር እንዴት ይፈጠራል?

$
0
0

የዘመናችን አባባል ሆኖ ነው መሰልኝ «ባል ጠፋ፣ ሚስት የታል?» የሚሉ ሃሳቦች ሲሰነዘሩ እንሰማለን። እውነት ባልም ሚስትም ጠፍተው ነው? ሰው ትዳርን ሽሽት የጀመረው ወይስ ሌላ ምክንያት አለ ? ስል ሁሌ ራሴን እጠይቃለሁ። ምላሽ ባላገኝለትም። ለራሴ የማቀርበውን ጥያቄ የብዙዎች በመሆኑ ለምን የባለሙያ ምላሽ አይሰጥበትም በማለት ማፈላለግ ጀመርኩ። ተሳካልኝና የጋብቻና የቤተሰብ አማካሪውን አቶ ይመስገን ሞላን አገኘሁ። የእርሳቸውን አጠቃላይ ማብራሪያ ከማስቀደሜ በፊት በትዳር ውስጥ ያሉና ትዳርን በሩቁ የሚፈሩ ግለሰቦችን አስተያየት ለማስቀደም ወደድኩ።

marraige
መጀመሪያ ያናገርኩት ወጣት ዮሐንስ አለማየሁ ይባላል። የመጀመሪያ ድግሪ ምሩቅ ሲሆን፤ በአንድ የመንግሥት መስሪያ ቤት ተቀጣሪ ነው። ይህ ወጣት ወደ ትዳር ለመግባት የሚስት መጥፋት ብቻ አይደለም ማነቆው ይላል። በእርሱ ሃሳብ ትዳርን ለመጀመር ሦስት ነገሮች ያሰጉታል። አንደኛውና ዋንኛው እርሱ «ነፃነቴ» የሚለውን እንደ ልብ መውጣት መግባት፣ ያለ ሃሳብ ለራስ ብቻ መኖርን ወደ ትዳር ሲገባ እንደሚያጣው ማሰቡ ነው። ብቻውን በሚኖርበት ወቅት ከሚያደርጋቸው ነገሮች መታቀቡ ነፃነትን እንደመሸጥ ነው የሚቆጥረው። ሁለተኛው ደግሞ ለማግባት የሚያስባት ሴት ባህሪ «ቢቀየርብኝስ» የሚል ስጋት ስላሳደረበት ነው። ሦስተኛው ምክንያቱ የትዳር በር ላይ ቆሞ ሲመለከት ቤተሰብ የማስተዳደር አቅም ላይ ስጋት ይይዘዋል። ከአንድ ሁለት ከሁለትም ሦስት በሚሆንበት የትዳር ሂደት ውስጥ የተሻለ ገቢ የማይኖር ከሆነ «እንዴት ይገፋል?» የሚለው ዮሐንስ «ምን አለኝ» እያለ የብቸኝነት ኑሮውን በመግፋት ላይ መሆኑን ነው ያጫወተኝ።
ሌላዋ ወጣት ትንሳኤ ተስፋዝጊ «ባል ጠፋ» ከሚሉት ወገን ናት። ይቺ ወጣት ሴትነት ወደ ማዕድቤት በሆነበት የሃገራችን ወንዶች አመለካከት ለበለጠ ኃላፊነትና የሥራ ጫና መታጨት አልፈልግም የሚል አመለካከት አላት። በነፃነት እንደልቧ ወጥታ ከምትገባበት የቤተሰብ ኑሮ ወጥታ የራሷን ቤት መመሥረት ከባድ ኃላፊነት ሆኖ ነው የሚሰማት። «ትዳርን ሳስብ ይህን ኃላፊነት መሸከም እችላለሁ ብዬ ማሰብ ስለሚከብደኝ እፈራለሁ» የምትለው ትንሳኤ ከዚህም ሌላ ስጋት አላት።
«የሀገራችን ወንዶች መበለጥንና የሴት የበላይነትን መቀበል አይፈልጉም» ትላለች። እርሷ ደግሞ የማስትሬት ድግሪ ደረጃን የያዘች በመሆኗ የምትፈልገውን ዓይነት ባል ማግኘት ጭንቅ ሆኖባታል። «የተሻለ ደረጃ ላይ ያለው በጉራ እየተወጠረ የበታች የሆነው ደግሞ የራስ መተማመን መንፈስ እያጣ ባል የሚሆን ሰው ጠፍቶኛል።» ትላለች።
ትዳርን ሲያስቡት ከሚፈሩት ወጣቶች አስተያየት ከሰበሰብኩ በኋላ አዲስ ተጋቢዎችን ምን ገጠማችሁ? አልኳቸው። መጀመሪያው አካባቢ ለምን ሁሉም ሰው አያገባም የሚያሰኝ ጣፋጭና አስደሳች የፍቅር ጊዜ እንደነበረ የምትናገረው ወይዘሮ በእምነት ታዬ ናት። «ያ ጣፋጩ የፍቅር ጊዜ ተጠናቆ እውነተኛ ማንነት ሲገለጥ ከባዱ ፈተና ይጀምራል። አዲሷ ሙሽሪት ከሁሉ ነገር በላይ አሰልቺ የሆነባት የማያቋርጥና የእርሷን ኃላፊነት ብቻ የሚጠብቀው የቤት ወስጥ ሥራ ነው» በማለት ነው የምትገልጸው።
«ወላጆቼ ጋር እያለሁ እኔ ስፈልግ ብቻ ነበር በቤት ውስጥ ሥራ ተሳታፊ የምሆነው። በትዳር ውስጥ ያለውን የሥራ ጫና መቋቋም እቅቶኛል» የምትለው ወይዘሮ በእምነት በቤት ውስጥ ኃላፊነት በመጠመዷ ቀደም ሲል ለራሷ ብቻ የምትሰጠውን ጊዜ እንኳን ልታገኝ አለመቻሏን ትናገራልች፡፡
ሌላው የመጀመሪያ ችግር የሆነባት ተነጋግሮ መግባባት ያለመቻል ጉዳይ ነበር። «በፊት አንቺ እንዳልሽ ሲል የማውቀው የትዳር አጋሬ በእያንዳንዱ ነገር ተፅዕኖ ለማድረግና የእርሱን ንግግር ብቻ እንዳዳምጥ መፈለጉ ጭራሽ የማላውቀውን ሰው ነው እንዴ ያገባሁት? እንድል አድርጎኛል» ትላለች። ያምሆኖ ከተጋቡ 10 ወራትን ያስቆጠሩት እነ በእምነት ግንኙነታቸው ከዕለት ወደ ዕለት እየተሻሻለ መሄዱን አልደበቀችም። ትዳርም ቀድማ የፈራቻቸው የችግሮች ጥርቅም ሳይሆን በራሱ ከባድ ችግሮችን ተጋፍጦ የመቆየት ሂደት መሆኑን ነው የተማረችበት።
ትዳር የሁለት የተለያዩ ሰዎች ውህደት ውስጥ የሚፈጠር ጭንቀት ነው የሚለው ደግሞ አቶ ገመቺስ ጉደታ ነው። ዘወትር ግጭት፣ ጭቅጭቅ፣ ዝንት ዓለም ያለመግባባት ያለበት የሚመስለውን ትዳር በመተሳሰብ የተሻለ ማድረግ ይቻላል ባይ ነው።
አቶ ገመቺስ እያንዳንዱ በገንዘብ በኩል የሚመጡ ኃላፊነቶች ጫንቃው ላይ የወደቁ እስኪመስለው ድረስ በከባድ ውጥረት እራሱን ሲያስጨነቅ የቆየባቸውን ያለፉትን ጊዜዎች ሲያስብ ይቆጫል። «እንዲህ እንደአሁኑ በፕሮግራም መመራት እየተቻለ ምን ነበር ያስጨነቀኝ» ሲል ራሱን ታዝቧል።
በትዳር ውስጥ ያሉና ትዳርን በሩቁ የሚፈሩ ግለሰቦች የሰጡኝን አስተያየት ይዤ ወደ ሥነልቦና ባለሙያው አቶ ይመስገን ሞላ አመራሁ። የእርሳቸው ሙያዊ ማብራሪያ ለሁላችንም ምላሽ ይሰጣልና እንደሚከተለው አቀረብኩት።
ስኬታማ ትዳር የሚባለው ብለው ይጀምራሉ ባለሞያው «ስኬታም ትዳር የሚባለው ሁሉም እንዳለበት ቦታ ሲሆን ነው። ይህ ማለት ደግሞ ባልም እንደባል፣ ሚስትም እንደ ሚስት፣ ልጅም እንደ ልጅ ሲሆኑ ነው የቤተሰቡን ግንኙነት ጤናማ የሚያደርገው። የትዳር ሕይወትም መልካም ድምዳሜ ሲኖረው ስኬታማ ይባላል። ሁሉም መድረስ የሚገባው ላይ ሲደርስ ነው ስኬት ተብሎ የሚጠራው።
ከጋብቻ በፊት አንድ ግለሰብ በሁሉም አቅጣጫ እራሱን መሳደግ አለበት። ማለትም በገንዘብ በአዕምሮና በሌሎች መልኩ ማለት ነው። በየአቅጣጫው ራሱን የገነባ ሰው ሌላ ትክክለኛ ሰው ለማግኘት አይከብደውም። ይህ ከሆነ ደግሞ ከሁለት በትክክለኛ ሰዎች የተስተካከለ ትዳር ይመሠርታሉ። ለራሱ ክብር ያለውና ሙሉ ለሙሉ ትክክለኛ እንደሆነ የሚያምን ሰው ትክክለኛ ያልሆነ ሰው አያገባም እራሱንም በደንብ ስለሚያከብር ለማያከብረውና ዋጋውን ለሚያወርድበት ሰው ራሱን አሳልፎ አይሰጥም።
አንድ ሰው ማግባት ያለበት ዕድሜ ላይ ሲደርስ ለዕድሜው የሚመጥን አመለካከት ያለው ሰው ይሆናል ማለት ነው። ዋንኛው የትዳር መሠረት ባህሪ ሲሆን፤ ማንም ሰው ያለበትን መጥፎ ባህሪ ለማስተካከል ዓመታት አይወስድበትም። ጋብቻም ከመታሰቡ በፊት አለብኝ ብሎ የሚያምናቸውን ባህሪያት ማስወገድ የግድ ይላል።
የጋብቻ መጀመሪያ አካባቢ ሁለት የግል ሕይወትና የግል ማንንት ያላቸው ሰዎች እንጋባ ብለው ሲጀምሩ ከሁለት የተለያዩ ማንነቶች የመጡት ሁለቱ ሰዎች በተለይ እንደተጋቡ ሰሞን የጫጉላ ወቅት ትዳር ደስታ ብቻ ነው የሚሆነው።
በሁለተኛው ደረጃ ከትንሽ ቆይታ በኋላ ነገሮች እንደተገመቱት አይሆንም። ይሆናል የተባለው ሁሉ ሳይሆንና የተገመተው ሲቀር ግጭቱ ከውስጥ ይጀምራል። እነዚህ ግጭቶች ግን ችግር ሳይሆኑ ሂደቶች ናቸው። ብዙ ሰዎች እነዚያን ሂደቶች በአግባቡ ማስሄድ ባለመቻላቸው ወደ ችግርነት ይቀየራሉ።
ሁለት የተለያዩ ሰዎች ሃያ ምናምን ዓመት በተለያየ ቤት፣ በተለያየ ኑሮ ፣በተለያየ ፍላጎት ፣ በተለያየ ባህል በተለያየ እውቀት አድገው አብረን እንኑር ሲሉ እንዲያውም የሚገርመው ባይጣሉ ነበር። መጣላታቸው ሁለቱም ራሳቸውን እየገለጹ ውስጣቸውን እያሳዩ ወደመተዋወቅ የሚያደርጉት ሂደት ነውና ይሚጠበቅ ነው።
ይህን ችግር ለመፍታት ግን እንዴት መግባባት እንደሚችሉ ማወቅ የግድ ነው። አንድ ሰው ምን እንደሚናገር ሳይሆን እንዴት እንደሚናገር ማወቅ አለበት። በየቀኑ በመጨቃጨቅ ወደቤት መግባት አስጠላኝ እስከሚባልበት ድረስ ማደግ የለበትም። ጭቅጭቅ የሚከሰተው አንድ ሰው የራሱን እምነት ማስረዳት ብቻ ስለሚፈልግ ነው። ይህ ሲሆን ደግሞ የትዳር አጋሬ ምን ሊል እየፈለገ ነው ብሎ ማዳመጥ እጀግ በጣም ተገቢ ነው። ለዚህም ነው መልስ ለመስጠት ከመቸኮል ይልቅ መደማመጥ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው የሚሆነው።
በጣም የሚገርመው በማይጠቅሙና በማይገቡ ነገሮች ሰዎች መጨቃጨቃቸው ነው። ለምሳሌ አንድ ሰው ዕቃ ግዛ ተብሎ ረስቶቢገባ ለምን እንደረሳ መጠየቅና ማወቅ ተገቢ ነው። መርሳቱን ምክንያት አድርገው የሚፈጠሩ ምልልሶች ናቸው ጭቅጭቅ የሚሆኑት። የማይገቡና የማያስፈልጉ ባዶ ንዝንዞችን መተው የግድ ነው። ተግባቦት ማለት የሌላ ሰው ሃሳብና ሰሜትን መረዳት ነው፡፡ ያንን ለማድረግ አዳማጭ መሆን አስፈላጊ ነው። ስህተቶችን ለማረምና ለመረዳዳት ዕድል ይሰጣል።
ጋብቻ የጋራ ሕይወት ስለሆነ የየጋራ ኃላፊነትን ለመወጣት ማሰብ ችግሮችን የቀለለ እንዲሆን ያደርገዋል። ሁሉም ሰው የየራሱ ደርሻ አለው። የየራስ ኃላፊነቶችን በመወጣት ደረጃ ግንኙነት ሲደረግ መተጋገዝ ይሆናል። አንዱ የሌላውን ኃላፊነት ደርቦ መያዘ የነገን ግንኙነት አሰልቺ እንዲሆን ያደርገዋል። ይህ ደግሞ አደገኛ ነው።
ልጆች ከተወለዱ በኋላም ባልና ሚስቶች ራሳቸውን በብዙ ነገር ማዘጋጀት አለባቸው። ካልሆነ ግን የቤተሰቡ ቁጥር እየጨመረ ሲመጣ የፍላጎትና የገቢ አለመመጣጠን ሲመጣ የሚያጋጩ ነገሮችም አብረው መፈጠራቸው አይቀርም። ለስኬታም ትዳር ባል እንደመሪ ሆኖ ሙሉ ለሙሉ የቤተሰብ ኃላፊነትን የሚወጣ ሲሆን፤ ሚስት እንደ ሽንፈት መቁጠር የለባትም። ሚስትም መሪዋን በማገዝ ሃሳብ በመካፈል መደገፍና ቤተሰቧን ማቆም ትችላለችና፡፡
ስኬታማ ትዳር ለመመሥረት መነጋገር፣ መደማመጥ፣ መከባበርና የሚከሰቱ ችግሮችን እንደ አመጣጣቸው መቀበል ያስፈልጋል። ይህን ለማድረግ የተዘጋጁ ተጋቢዎች የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ሁሉ በቀላሉ ለመፍታት አይቸገሩም። ውይይታቸው ወይም ንግግራቸው ወደ ጭቅጭቅ አያመራም። አንዳንድ ግለሰቦች ከውጪ ሆነው በሚፈጥሩት ጭንቀት ብቻ ትዳርን ጭራቅ አድርገው መሳላቸው ተገቢ አይሆንም። በመሆኑም በቅድሚያ በትዳር ለመጣመር ከማሰባቸው በፊት ራሳቸውን ለትዳር ዝግጁ ማድረግ ይገባቸዋል። ያኔ የተሳካ ትዳር ይሆንላቸዋል።

ጸሐፊ አስመረት ብስራት

አቶ ዓባይ ወልዱ የሕወሓት ሊቀመንበር ሆነው ይቀጥላሉ

$
0
0

abay-wolduከነሐሴ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ በመቀሌ የሰማዕታት አዳራሽ ሲካሄድ የከረመው 12ኛው የሕወሓት ጉባዔ አቶ ዓባይ ወልዱ ሊቀመንበር ሆነው እንዲቀጥሉ በድጋሚ መረጣቸው፡፡ ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ከሁለቱ ሊቀ መናብርት በተጨማሪ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ አቶ በየነ ምክሩ፣ ወ/ሮ አዜብ መስፍን፣ አቶ ዓለም ገብረ ዋህድ፣ አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ ዶ/ር አዲስ ዓለም ባሌማና ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሔር (ሞንጀሪኖ) የሕወሓት ሥራ አስፈጻሚ (ፖሊት ቢሮ) አባላት ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ሕወሓት ከነባር የፖሊስ ቢሮ አባላት መካከል አቶ ዓባይ ፀሐዬ፣ አቶ አባዲ ዘሞ፣ አቶ ቴድሮስ ሐጎስና አቶ ፀጋይ በረኼ በመተካካት ሸኝቷል፡፡ ወ/ሮ ሮማን ገብረ ሥላሴ፣ አቶ ተወልደ ብርሃን በርኼና አቶ ተክለወይኒ አሰፋ በፈቃዳቸው ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ለቀዋል፡፡

ለማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት 50 አባላት ታጭተው 45 አባላት የተመረጡ ሲሆን፣ የአቶ ዓባይ ወልዱ ባለቤት ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነ ማርያምና የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ክንደያ ገብረ ሕይወት ሳይመረጡ ከቀሩት አምስት አባላት መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ከሁለት ዓመት ተኩል በፊት በተካሄደው 11ኛው የሕወሓት ጉባዔ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ሆነው ከተመረጡት ውስጥ አቶ ቴዎድሮስ ሐጎስ፣ ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነ ማርያምና አቶ ገብረ መስቀል ታረቀ ሳይቀጥሉ ቀርተዋል፡፡ አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ ዶ/ር አዲስ ዓለም ባሌማና ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሔር አዳዲስ አባላት ሆነው ገብተዋል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

  አቶ መለስ ድጋሚ ሞቱ! –አበበ ቶላ ፈሳ

$
0
0

meles zenawi funeral

አቶ መለስ በመጨረሻ ሰሞናቸው ስለ ድርጅታቸው ኢህአዴግ አጥብቀው ሲያራምዱት የነበረው መተካካት! ወይም አንዳንዴ ሲሉት እንደነበረው ”ዱላ ቅብብል” ነበር። (እርግጥ ነው እኛ ዱላ የምትቀባበሉት ማንን ለመግረፍ ነው ስንል አሽሟጠን እንደነበር አይዘነጋንም) ነገር ግን አሁን አቶ መለስ ሞተዋል እና ዱላ ቅብብሉን ለተተኪዎች ሰጥተዋል ከንግዲህ በቃቸው የተባሉ አንጋፋ እና ገፋፋ ባለስልጣኖች ሁሉ ወደ ፊት ሊመጡ Delete ከተደረጉበት Recycle Bin ዳግም ተመልሰው Desktop ላይ ጉብ ብለዋል። ”ዱርዬ” እንዳልባል ፈርቼ እንጂ በበርጫ ቋንቋ ተገርበዋል ከተቃሙበት ተነስተዋል ብላቸውም በደንብ ይገልጸዋል።

እና በደፈናው፤ ህውሃትቲትም ሆነች ኢህአዴግዬ የአቶ መለስ ራዕይ እያለች ደጋግማ ብትቀውጠውም የሰውዬው ራዕይም ክቡርነትም ታላቅነትም ያለው በተወሰኑ ሰዎች ጭንቅላት እና በባለቤታቸው ወይዘሮ አዜብ ውስጥ ብቻ ነውን… እያለን እየጠረጠርን ያ. ሁ. ነ. ያ.

እና አቶ መለስ መተካካት ሲሉ የፈጠሯት ነገር (አሁንም በቅንፍ በርግጥ እርሳቸውም ተቀናቃኞቻቸውን እና ተፎካካሪዎቻቸውን ገሸሽ ለማድረግ የተጠቀሙባት መላ ናት እንደሚባለም እናውቃለን…. ግን አንናገርም።) ብቻ ግን እነዚህ ሪፖርተር የጠቀሳቸው ጉምቱዎች አቶ መለስ በሌሎች ሲተኳቸው፤ ራሳቸውን ደግሞ እግዜሩ በ አቶ ሃይሌ ተክቷቸው መተካታቸውን ጠብቀው ዳግም የተመለሱ ናቸው። ጉምቱዎቹ አቶ መለስ ተመልሰው እንደማይመጡ ሲያውቁ… ሹልክ ብለው ከየከረሙበት ወደ ስልጣናቸው መጥተዋል ብንልም ይሆናል!

ቀልዱ ቀልድ ነው… ጨዋታውም ጨዋታ ነው….ምሩ ግን ኢህአዴግ ራሷ ያወጣችውን ህግ ራሷ እንኳ ለማክበር ሞራል እና አቅም ሳይኖራት እኛን አክብሩ እያለች ቁም ስቅላችንን ስታወጣው ነውር አይደለም ወይ…. ብለን እየጠየቅን፤ እግረ መንገዳችንንም መለስ ዜናዊ በሌሉበት አጓጉል ተደፍረዋል እና እነሆ መለስ ዳግም ሞቱ!!! እንላለን… (ነፍሳቸውን እንዳሻው ያድርግልን!!!)

ፖሊስ የሕወሓት ደጋፊዎቹ የማዲንጎ እና የአስቴር ኮንሰርት እንዲሳካ የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት እንዲሰረዝ ግፊት እያደረገ መሆኑ ተጋለጠ

$
0
0

teddy afro

(ዘ-ሐበሻ) ለአዲሱ ዓመት ዋዜማ በሁለት ቦታዎች ሁለት የተለያዩ ኮንሰርቶች እንደሚደረግ ተገልጾ ነበር:: ይህም አንደኛው የሕወሓት መንግስት ቀደኛ ደጋፊውና በመንግስት ኃይሎች የሚወደደው ማዲንጎ አፈወርቅ እና የሕወሓት መንግስት በሚያዘጋጃቸው ዝግጅቶች እየተገኘች ድጋፏን የምታሳየው አስቴር አወቀ በአንድ ላይ የሚሰሩት ኮንሰርት ሲሆን ሁለተኛው ቴዲ አፍሮ በላፍቶ ሞል ያደርገዋል የተባለው ኮንሰርት ነበር::

ከአዲስ አበባ ያገኘናቸው መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የመንግስት ኃይሎች የቴዲ አፍሮን ኮንሰርት ለማሠረዝ ከፍተኛ የሆነ ሥራ እየሰሩ ይገኛሉ:: ከነዚህም መካከል ፖሊስ እስካሁን ድረስ የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት እንዲካሄድ ፍቃድ አልሰጠም:: አዘጋጆቹ ለቴዲ የኮንሰርቱ አዘጋጆች ለድምፃዊው 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ቢከፍሉም ፈቃድ እስካሁን አልተሰጠም::

aster

አዘጋጆቹ ላለፉት 7 ቀናት ፖሊስ ዘንድ ሄደው ፈቃዱን ለማግኘት ቢሯሯጡም ከመመላለስ በስተቀር ምንም መፍትሄ አልተገኘም:: አሁን ባለው ሁኔታም የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ለአዲሱ ዓመት ዋዜማ የመደረጉ ነገር በጣም ጥርጣሬ ውስጥ ገብቷል::

በሌላ በኩል የሕወሓት መንግስት ቅርብ ሰዎች የሚያዘጋጁትና ማዲንጎ አፈወርቅ እና አስቴር አወቀ የሚያደርጉት ኮንሰርት ፈቃድ ማግኘቱ ታውቋል::


የተደበቀው የህወሓት ማንነት ከደደቢት እስከ ቤተ መንግስት (ክፍል 4) –የሜ/ጀነራል ሞላ ኃ/ማርያም; የጌታቸው አሰፋና ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ ገመና

$
0
0

Mola
ሜጀር ጀነራል ሞላ ኃ/ማርያም
ሞላ ኃ/ማርያም በትጥቅ ትግሉ ወቅት ልክ እንደ አበበ ተ/ኃይማኖት ሓለዋ ወያኔ ወይም ባዶ ስድስት እየተባለ በሚጠራው አደገኛ የማሰቃያ እስር ቤት ውስጥ ተመድቦ ይሰራ ነበር፡፡
ጠውቆ ከሚባል ቦታ የተቋቋመውን አደገኛ እስር ቤት እዲጠብቁ ተመርጠው ከተመደቡት 500 ታማኝ የህወሓት ታጋዮች የ250ዎቹ አዛዥ ሞላ ኃ/ማሪያም ነበር፡፡ በመሆኑም በየጊዜው ወደ አደገኛው ወህኒ የሚገቡ እልፍ አዕላፍ ታጋዮችን እሱ በሚያዘው በጥበቃ ስም በተደራጀ ገዳይ ቡድን በጥይት እያስጨፈጨፈ ለዓመታት ኖሯል፡፡ ሞላ ከሚያዘው ገዳይ ቡድን እስረኞቹን በግፍ ከማስረሸኑ ባለፈ ራሱም በሽህ የሚቆጠሩ “የአማራ ብሄር” ተወላጆችን በአንድ ላይ ሰብስቦ በማቆም መትረየስ ጠምዶ በእሩምታ ተኩስ ጨፍጭፎ በጅምላ እዲቀበሩ አድርጓል፡፡
ሞላ ኃ/ማሪያም በህወሓቶች የሽፍትነት ዘመን በእስር ቤት ሰዎችን ከመረሸንና የገዳይ ቡድኑ መሪ ከመሆን እና ስብሃት ነጋና መለስ ዜናዊን በአጃቢነት ከማገልገል የዘለለ ሚና አልነበረውም፡፡ ምንም አይነት ጦርነት ላይ አልተካፈለም ነበር፡፡ ነገር ግን በርሃ ወርዶ የባንዳውን ቡድን ህወሓትን ሲቀላቀል የትምህርት ደረጃው ከ8ኛ ክፍል በታች የነበረው ሞላ ኃ/ማሪያም የጀነራልነት ማዕረግ አግኝቶ የአየር ኃይል አዛዥ ሆነ፡፡
ከህወሓት የጦር መሀይማን ጀነራሎች አንዱ የሆነው ሞላ ከኮሎኔልነት ማዕረግ ወደ ጀነራልነት ሊያድግ የቻለው የሁለት ልጆቹን እናት ለአበበ ተ/ኃይማኖት በቅምጥነት ስጦታ በመስጠት ነው፡፡ እሱም ልክ እንደ ሳሞራ የኑስ፣ አበበ ተ/ኃይማኖትና ሌሎች የህወሓት ባለስልጣናት የወጣለት ሴሰኛ ነው፡፡
በአየር ኃይል ጠ/መምሪያ ውስጥ የሚሰሩ ባለትዳር ሴቶችን አባልጓል፡፡ ባለቤቱም ከቤት ሰራተኛው ጋር ተኝቶ መኝታ ቤታቸው ውስጥ እጅ ከፍንጅ ይዛዋለች፡፡
ሞላ ኃ/ማሪያም የአየር ኃይል አዛዥ በነበረበት ወቅት በርካታ የዘረፋ ወንጀሎችን ፈፅሟል፡፡ በአንድ ወቅት የአሜሪካ መንግስት ለአየር ኃይሉ አብራሪዎች በጠቅላላ ስልጠና ሊሰጥ ስምምነት ላይ ይደርስና የአሜሪካ አየር ኃይል አባላት የሆኑ ከፍተኛ ሙያተኞች ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ፡፡ ከዚያም አሜሪካውያኑ ለበረራ ልምምድ የሚውል ብዛት ያለው ነዳጅ እዲገዙና በደረሰኙ መሰረት እደሚያወራርዱላቸው ሞላንና ሌሎችን የአየር ኃይሉ አመራሮች የሆኑ የህወሓት ሰዎችን ይነግሯቸዋል፡፡ የአየር ኃይሉ ዋና አዛዥ የሆነው ሞላ አሜሪካዊያኑን እደምንም አሳምኖ ገንዘቡን ቅድሚያ እዲሰጡዋቸው በማድረግ ለስልጠናው የሚያስፈልገውን ነዳጅ ከዚያው ከአየር ኃይል ዴፖ በመሙላት ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ዶላር ለግሉ አድርጎታል፡፡
ሞላ ኃ/ማሪያም በ2005 ዓ.ም ለሆራ አየር ኃይል ሆስፒታል በሚሊዮኖች ዶላር ከውጭ ተገዝተው የገቡ ሙሉ የህክምና ቁሳቁሶችን ከመጋዘን አውጥቶ ሸጧል፡፡ የህክምና ቁሳቁሶቹን በሌሊት ከሆስፒታሉ መጋዘን ወጥተው በመኪና ተጭነው ሲጋዙ ተረኛ ሀኪም ሆኖ በአጋጣሚ የተመለከተውን የጉራጌ ተወላጅ የሆነውን አምሳ አለቃ ሰለሞንን ሞላ ሻለቃ ገ/ህይወት /ወዲ ራያ/ የተባለውን የአየር ኃይሉን የደህንነት ኃላፊ ልኮ አስገድሎታል፡፡
በህወሓት የሽፍትነት ዘመን የወጣለት ገዳይ፣ የአፋኝና ረሻኝ ቡድን መሪ የነበረው ሞላ ኃ/ማሪያም የአየር ኃይል አዛዥ በነበረበት ወቅት በርካታ የአየር ኃይል አባላትን በስውር እዲገደሉ አድርጓል፡፡
ለምሳሌ፡- በ2001 ዓ.ም ለግል ቪላ ቤት መገንቢያ ታስቦ ሲሚንቶ፣ ብረትና ቆርቆሮ ከአየር ኃይል ግቢ በሌሊት ተጭኖ ሲወጣ የተመለከተው ሻምበል ዓለሙ የተባለ የጥበቃ ሰራተኛ ሆን ተብሎ በመኪና ተገጭቶ እንዲገደል አድርጓል፡፡
ከሽሬ ሰለክላካ አርሶ አደርነት የአየር ኃይል አዛዥ የሆነው ሞላ ኃ/ማሪያም ሓለዋ ወያኔ /ባዶ ስድስት/ አደገኛ እስር ቤት ውስጥ በቆየባቸው ረጅም ዓመታት ውስጥ ግድያና ዘረፋን በሚገባ ተክኖታል፡፡
በአየር ኃይል ጠ/መምሪያ ግቢ መጋዘን ውስጥ ተከማችቶ የነበረ በርካታ የጦር መሳሪያ ክላሽን ኮቭና ሽጉጥ ከነመሰል ጥይቶቹ በድብቅ አውጥቶ ለሆራ አርሰዲ፣ ጨፌ፣ ዝቋላና አካባቢው ገበሬዎች ቸብችቦታል፡፡
ከባህር ማዶ ነዳጅ የመጣባቸውን በርሜሎች አሰብስቦ በጨረታ እዲሸጡ በማድረግ ገንዘቡን ከተባባሪዎች የህወሓት ሰዎች ጋር ተከፋፍሎታል፡፡
ሙልጭ ያለው ሌባ ጀነራል ሞላ ኃ/ማሪያም ከአፄ ኃይለስላሴ ጀምሮ በአየር ኃይል ግቢ ውስጥ የነበሩትን ባለ ግርማ ሞገስ ግዙፍ፣ ግዙፍ ዛፎችንም አስቆርጦ ሸጦ በልቷቸዋል፡፡
ማፍያው ጀነራል ሞላ ኃ/ማሪያም በተለያዩ ጊዜያት በተደጋጋሚ የአየር ኃይሉን ንብረቶች በሌሊት አስጭኖ በማስወጣት እየሸጠ በሌቦች ተዘረፈ አስብሏል፡፡
ለአብነት በ2002 ዓ.ም በተደጋጋሚ የተደረጉትን የኮምፒውተሮችና ሌሎች በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ከውጭ የሚገቡ ቁሳቁሶችን ዘረፋ ማስታወሱ ብቻ በቂ ምስክር ነው፡፡
በየጊዜው ከቻርተር በረራዎች /ከኪራይ/ የሚገኘውን ወፈር ያለ ገቢ ሞላ ኃ/ማርያም ወደግል የባንክ ሂሳቡ እንዲጨመር አድርጓል፡፡ ለምሳሌ ባንድ ወቅት “የናሽናል ጂኦግራፊ” አዘጋጆች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ሄሊኮፕተር በመከራየት ወደ ኤርታሌ አምርተው ነበር፡፡ ታድያ የህዝብ ንብረት ከሆነው ሄሊኮፕተር ኪራይ የተገኘውን ገቢ ሞላ ኃ/ማርያምና ሌሎች የአየር ኃይሉ ቁንጮ የሆኑት ህወሓቶች በመዝረፍ ጮማ ቆርጠውበታል ዊስኪ ተራጭተውበታል፡፡
ሞላ እና በአየር ኃይሉ ውስጥ የሚገኙ የህወሓት መኮንኖች ከራሱ ከአየር ኃይል በዘረፉት ገንዘብ የገዟቸውን መኪኖች ለአየር ኃይሉ አከራይተው ከፍተኛ ገንዘብ አጋብሰዋል፡፡ አየር ኃይሉ ለሠራተኞቹ የትራንስፖርት አግልግሎት የሚሰጡ የራሱ መኪኖች እንዳይኖሩት የተደረገው ሆን ተብሎ ለዚህ ዓላማ ነው፡፡
ሞላ ኃ/ማሪያምና ሌሎች ህወሓታዊያን የአየር ኃይሉ ሹማምንቶች ቅልብ አብራሪዎች በመባል ይታወቃሉ፡፡ ሜጀር ጀነራል ሞላ ኃይለ ማርያምንና መሐሪ ዘውዴን እጃቸውን ይዞ የበረራ ትምህርት ያስተማራቸው የቀድሞው ሰራዊት አባል መቶ አለቃ እንደገና ታደሰ ነው፡፡ ጀነራል ሞላ ኮሎኔል በነበረበት ወቅት በቀድሞው አየር ኃይል አባልና የምክትል መቶ አለቅነት ማዕረግ ባለው ዮናስ በላይ /ደቦራው/ ይመራ ነበር፡፡

Getachew asefa

ጌታቸው አሰፋ
ጌታቸው አሰፋም እንዲሁ አበበ ተ/ኃይማኖትና ሞላ ኃ/ማሪያም በህወሓት የሽፍትነት ዘመን ሐለዋ ወያኔ የተባለው ጋሃነም አለቃ ነበር፡፡ ጌታቸው አሰፋ በሓለዋ ወያኔ /ባዶ ስድስት/ አደገኛ ወህኒ ውስጥ በርካታ ኢትዮጵዊያን ላይ አያሌ ሰቆቃዎችን ፈፅሟል፡፡
ተለይተው እየታፈሱ ወደ አደገኛው ወህኒ በየጊዜው የሚገቡ “የአማራ ብሄር” ተወላጆችን አንድ ላይ ሰብስቦ ላያቸው ላይ መትረየስ በማርከፍከፍ ጨፍጭፏቸዋል፡፡
የገሀነሙ አለቃ ጌታቸው አሰፋ ሓለዋ ወያነ ባዶ ስድስት አደገኛ ወህኒ ውስጥ ቁጥር ስፍር የሌላቸውን ታሳሪዎች በፋስ ጭንቅላታቸውን ተርትሯል፣ ሙሉ አካላቸውን በፈላ ውሃ አንፍሯል፣ ብልታቸውን በጋለ ብረት አቃጥሏል፡፡
ጌታቸው አሰፋ ዛሬም በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሰቆቃ፣ አፈና እና ግድያ እየፈፀመ የሚገኘው የህወሓት ደህንነት ቢሮ ዋና ተጠሪ ነው፡፡

ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ
እንደ አብዛኞቹ የህወሓት ባለስልጣናት ትምህርቱን ከ9ኛ ክፍል ያቆመው ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ እሱም እጆቹ በንፁህ ኢትዮጵያዊያን ደም የተጨማለቁ ወንጀለኛና የለየለት ነብሰ በላ ነው፡፡
በህወሓት የሽፍትነት ዘመን በ1980 ዓ.ም ከትግራይ ውጭ ላለው የኢትዮጵያ መሬት አንዋጋም ካሉት ታጋዮች ውስጥ 36 ሺህዎቹ ሲረሸኑ ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ ከገዳዮቹ አንዱ እደሆነ ምስጢሩን የሚያውቁ የትግል ጓዶቹ ይመሰክራሉ፡፡
ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ በአሁኑ ጊዜም ከጌታቸው አሰፋ ቀጥሎ የህወሓት ደህንነት ቢሮ ሁለተኛ ሰው ሲሆን በደህንነቱ ውስጥ በስውር ተደራጅቶ የአፈና፣ ግድያና ድብደባ ተግባር የሚፈፅመው ቡድን የሚታዘዘው በእሱ ነው፡፡
ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ የ1997 ዓ.ም ምርጫ ውጤትን መጭበርበር ተከትሎ በተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ እሱ የሚያዘውን ገዳይ ቡድን ከአግአዚ ኮማንዶ ጋር አቀናጅቶ በመምራት ህፃናትና ወጣቶችን በጥይት እስጨፍጭፏል፡፡
ህወሓት እንደ ጌታቸው አሰፋና ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ አይነት ከበርሃ ጀምሮ በአረመኔነታቸው የሚታወቁ ተኩላዎችን አሰማርቶ ነው የኢትዮጵያን ህዝብ በሰቆቃ፣ አፈና፣ ግርፋትና ግድያ ረግጦ እየገዛ ለ24 ዓመታት የዘለቀው፡፡

ፍርድ ቤቱ አቶ ማሙሸት አማረ በነፃ እንዲቀለቀቅ ወሰነ 

$
0
0

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

የአራዳ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ነሃሴ 22/2007 ዓ.ም በዋለው ችሎት አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም መንግስት ከጠራው ሰልፍ አንድ ቀን ቀድሞ ከለቅሶ ቤት ወደ ቤተ መንግስት የተደረገውን ሰልፍ አደራጅቶ መርቷል እንዲሁም ለዋናው (ለሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም) ሰልፍ አነሳስቷል በሚል ክስ የተመሰረተበት አቶ ማሙሸት አማረ በነፃ እንዲለቀቅ ወስኗል፡፡

mamushetአቃቤ ህግ ነሃሴ 20/2007 ዓ.ም አቶ ማሙሸት ገንዘብ ከፍሎ ወጣቶችን ሰልፍ እንዳስወጣቸው፣ ወጣቶችን እንዳደራጀ፣ በሰላማዊ ሰልፉ ወቅትም መንግስትን የሚተቹ መፈክሮችን በመሪነት ሲያሰማ እንደነበርና ለሚያዝያ 14 ሰልፍም ሲያደራጅ እንደነበር ያስረዱልኛል ያላቸውን ሶስት የሰው ምስክሮችን ማሰማቱ ይታወሳል፡፡
ይሁንና ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግ ምስክሮች የግል ሰራተኛ እንደሆነ በምስክርነት ቃላቸው ቢሰጡም በመስቀለኛ ጥያቄ አንደኛው የመንግስት ሰራተኛ፣ ሁለተኛው የወጣቶች ሊግ ከዚህም አለፍ ሲል የኢህአዴግ አባል፣ ሶስተኛው ደግሞ የጥቃቅንና አነስተኛ ባልደረባ መሆናቸውን በማመናቸው የሰጡት ምስክርነት ትክክል አለመሆኑን ያስረዳል ብሏል፡፡ በተጨማሪም ምስክሮቹ ገዥው ፓርቲን የሚደግፉና የወጣት ሊግ አባል ሆነው ገዥው ፓርቲን የሚቃወም ግለሰብ ላይ የሰጡት ምስክርነት ገለልተኛ ነው ብሎ ለማመን ያስቸግራል ብሏል፡፡
ከዚህም ባሻገር ምስክሮቹ የገዥው ፓርቲ ደጋፊ ሆነው እያለ አቶ ማሙሸት አማረ በተደጋጋሚ ይደውልላቸው እና ይገናኙም እንደነበር የመሰከሩ ሲሆን አቶ ማሙሸት ቀንደኛ የገዥው ፓርቲ ተቃዋሚ ሆኖ እያለ ከመንግስት (ከገዥው ፓርቲ) ቀንደኛ ደጋፊዎች እንዲህ አይነት ግንኙነት ይኖረዋል ብሎ ለማመን እንደማይቻል አስረድቷል፡፡ በሌላ በኩል ከ4 አመት ጀምሮ እስከ 7 አመት አዲስ አበባ ውስጥ የኖሩት ምስክሮች ስለ ሰልፉ ባስረዱበት ወቅት ቤተ መንግስትን ጨምሮ ሰልፉ ያለፈባቸውን ቦታዎች አናውቃቸውም ማለታቸው ራሳቸውን ከመስቀለኛ ጥያቄ ለማዳን ያደረጉት እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ገልጾአል፡፡ በመሆኑም የምስክሮቹ ቃል ታማኒነት ስለሌለው አቶ ማሙሸት አማረ መከላከል ሳያስፈልገው በዛሬው ዕለት በነፃ እንዲለቀቅ ሲል ፍርድ ቤቱ ወስኗል፡፡
አቶ ማሙሸት አማረ ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም በተካሄደው ሰልፍ ላይ ሁከትና ብጥብጥ ፈጥሯል በሚል ተከሶ የነበር ቢሆንም በወቅቱ ከምርጫ ቦርድ ጋር በነበረው ክርክር ሰልፉ ላይ አለመገኘቱን የሚያጋግጥ መረጃ በማምጣቱ በነፃ እንዲለቀቅ ተወስኖ ነበር፡፡ ነገር ግን ክሱ ወደማነሳሳት ተቀይሮ እስከዛሬ እስር ቤት እንዲቆይ ተደርጓል፡፡

የማኅበረ ቅዱሳን ንዋያተ ቅድሳት ማምረቻ ክፍል ቃጠሎ ደረሰበት

$
0
0

ማህበረ ቅዱሳን በድረገጹ እንደዘገበው:-

በማኅበረ ቅዱሳን የልማት ተቋማት አስተዳደር የንዋያተ ቅድሳት ማምረቻ ክፍል ነሐሴ 18 ቀን 2007 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ቃጠሎ እንደደረሰበት የልማት ተቋማት አስተዳደር ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ ፍስሐ ገለጹ፡፡

kidusan kudsuan
መረጃው ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት እንደደረሳቸው የገለጹት አቶ ኃይሉ በማምረቻ ክፍሉ ተከስቶ የነበረውን ቃጠሎ በአካባቢው ሕዝብና በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ወረዳ የእሳት አደጋ ማጥፊያና መቆጣጠሪያ ክፍል አባላት ርብርብ ወደ ሌሎች ክፍሎች ሳይዛመት በቁጥጥር ሥር እንዲውል መደረጉን ተናግረዋል፡፡
በቃጠሎው 12 የልብስ ስፌት ማሽኖች፤ 2 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ካውያዎች፤ 1 መዘምዘሚያ ማሽን፤ 1 ቁልፍ መትከያ ማሽን፤ በዝግጅት ላይ የነበሩና ያልተጠናቀቁ፤ ለስፌት የሚያገለግሉ የግሪክ ጨርቆች፤ የካህናት፤ የዘማርያንና የሰባኪያን አልባሳት፤ ለአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተዘጋጁ አልባሳት፤ የግሪክ ጣቃ ጨርቆች፤ የማምረቻ ክፍሉ በሮች፤ መስኮቶችና ኮርኒስን ጨምሮ ሙሉ ለሙሉ ወድመዋል፡፡ ግምታቸውንም ለጊዜው ማወቅ እንዳልተቻለ ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡
በዕለቱ ቀኑን ሙሉ መብራት ጠፍቶ ስለነበር ምንም ዓይነት ሥራ አገልጋዮቹ እንዳለከናወኑ የገለጹት ዳይሬክተሩ ቃጠሎው የተከሰተው አገልጋዮቹ ከወጡ በኋላ በመሆኑ የአደጋው መንስኤ እሰካሁን አለመታወቁን ተናግረዋል፡፡ አደጋው የተከሰተበት ምክንያት ፖሊስ የቴክኒክ ምርመራ በማካሔድ ላይ ስለሚገኝ ምርመራው እንደተተናቀቀ የሚታወቅ ይሆናል ብለዋል፡፡
ወደፊት ጥንቃቄ የተሞላበት ሥራ ለማከናወን ጥረት እንደሚደረግ የገለጹት አቶ ኃይሉ ከኢንሹራንሽ ጋር በተያያዘም ወደፊት የሚሠሩ ሥራዎች እንደሚኖሩ ጠቁመዋል፡፡ በቃጠሎው ከፍተኛ ጉዳት ሳይደርስ በቁጥጥር ሥር እንዲውል ላደረጉ አካላት ለአራዳ ክፍለ ከተማ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መቆጣጠሪያ ጣቢያ፣ ለአካባቢው ምእመናንና ፖሊስ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በንዋያተ ቅዱሳት ማምረቻ ውስጥ የአልባሳት፤ የመባ /ዕጣን፤ ጧፍ፤ ዘቢብ/ ዝግጅት፤ የተማሪዎች አልባሳት፤ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውሉና በእንጨት የሚዘጋጁ ንዋያተ ቅድሳት እንዲሁም የብረታ ብረት ሥራዎች ይመረታሉ፡፡

ኤርትራ ሄደው ግንቦት 7ን ሊቀላቀሉ ነበር ተብለው በተከሰሱት ላይ ምስክርነት ተሰማ

$
0
0

birhanu tekle

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን አቋርጠው ኤርትራ የሚገኘውን ግንቦት ሰባት የተባለ በተወካዮች ም/ቤት ሽብርተኛ የተባለ ድርጅትን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ላይ የአቃቤ ህግ ምስክር ተሰማ፡፡

ዛሬ ነሀሴ 22/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት አንደኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ ሁለተኛ ተከሳሽ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ሦስተኛ ተከሳሽ ፍቅረማርያም አስማማው እንዲሁም አራተኛ ተከሳሽ ደሴ ካህሳይ ‹‹አቃቤ ህግ በጻፈውና ለተከሳሽ በደረሰው የክስ ማመልከቻ ላይ አቃቤ ህግ የሰው ማስረጃ (ምስክር) አልጠቀሰም፤ እኛም መቃወሚያ ስናስገባም ሆነ እምነት ክህደት ቃል ስንሰጥ ይህን ግምት ውስጥ በማስገባት ነው፤ በመሆኑም የአቃቤ ህግ ምስክር ሊሰማብን አይገባም›› በሚል ተቃውሞ ቢያቀርቡም አቃቤ ህግ ለፍርድ ቤቱ ባስገባው ክስ ላይ ምስክሩን መጥቀሱን በማስረዳት ምስክሩ እንዲሰሙለት ጠይቋል፡፡

ፍርድ ቤቱ የደረሰው የክስ ማመልከቻ ላይ ምስክር እንደተመዘገበ በማረጋገጥም ብቸኛ ሆነው የቀረቡትን አንድ የአቃቤ ህግ ምስክር ሰምቷል፡፡ ምስክሩም ከ1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ተከሰሾች ጋር ሰማያዊ ፓርቲ በሰላማዊ ትግል ውስጥ ሆነው እንደሚተዋወቁ፣ የካቲት 12/2007 ዓ.ም በ1ኛ እና 2ኛ ተከሳሽ አማካኝነት ሰላማዊ ትግሉ እንዳላዋጣ በመጥቀስ ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ መጓዝ ማሰባቸውን ገልጸውለት በዚያው ቀን ማታ 3ኛ ተከሳሽን ጨምሮ ወደ ባህር ዳር እንደተጓዙ ለችሎቱ አስረድቷል፡፡

ባህር ዳር ሲደርሱ ጠዋት ላይ ግን ምስክሩ ሀሳቡን በመቀየር ወደ አዲስ አበባ መመለስ እንደሚፈልግ እንደገለጸላቸው፣ 1ኛ ተከሳሽ በበኩሉ ‹ጎንደር ላይ የምናገኘው ሰው ስላለ ቢያንስ እሱን ካገኘኸው በኋላ መመለስ ትችላለህ› እናዳለው፣ ነገር ግን ምስክሩ በሀሳቡ ባለመስማማት ወደ አዲስ አበባ መመለሱንና ሌሎቹ ሦስቱ ግን ጉዟቸውን መቀጠላቸውን አስረድቷል፡፡ ‹‹ባህር ዳር ላይ ለምን ለመመለስ ወሰንህ›› የሚል መስቀለኛ ጥያቄ ከ1ኛ ተከሳሽ የቀረበለት ምስክሩ፣ ‹‹በወቅቱ ስሜታዊ የሚያደርጉ የግል ጉዳዮች ስለነበሩብኝ በስሜታዊነት የወሰንኩት ውሳኔ በመሆኑ ነው›› ሲል ተናግሯል፡፡

ምስክሩ ‹‹ለምስክርነት ያስገደደህ አካል የለም ወይ›› ተብሎ ሲጠየቅ ‹‹የለም›› የሚል መልስ ሰጥቷል፡፡ ‹‹ግንቦት ሰባት ነጻ አውጭ ድርጅት ነው ወይስ አሸባሪ›› ተብሎ በተከሳሾች መስቀለኛ ጥያቄ ተነስቶ፣ አቃቤ ህግ ተቃውሞውን በማሰማት ‹‹ድርጅቱ በተወካዮች ም/ቤት አሸባሪ ተብሏል፡፡ ይህ የህግ ጉዳይ ነው›› በማለት ጥያቄውን ምስክሩ የመመለስ ግዴታ እንደሌለባቸው አስረድቷል፡፡ ፍርድ ቤቱም ይህን ተቃውሞ ተቀብሎ ምስክሩ ጥያቄውን እንዲያልፉት ተደርጓል፡፡ ‹‹ማዕከላዊ ታስረህ ነበር፣ ድብደባም እንደደረሰብህ በሚዲያ ሳይቀር ተዘግቧል፡፡ ልክ ነው?›› ተብሎ በመስቀለኛ ጥያቄ ሲጠየቅ ምስክሩ ‹‹ማዕከላዊ ቃል እንድሰጥ ተደርጌያለሁ፤ ግን አልታሰርኩም›› የሚል መልስ ሰጥቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ የምስክሩን ቃል ከሰማ በኋላ የአቃቤ ህግን አስተያየት የጠየቀ ሲሆን፣ አቃቤ ህግ የምስክሩ ቃልና የሰነድ ማስረጃውን መርምሮ ፍርድ ቤቱ ብይን እንዲሰጥለት ጠይቋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ብይኑን ለማሰማት ለመስከረም 5/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ :: ህወሃት ጎጠኝነትን ብትኮንን የመለስ ዜናዊ አጽም ይወቅሳታል።

$
0
0

ቢላል አበጋዝ

ዋሽግቶን ዲ ሲ

ዓርብ ፣ ኦገስት 28 ቀን 2015

tplf-rotten-apple-245x300ማን የብሄር ብሄረሰብ፤ መገንጠል ፤መገነጣጠልን አሾረው፤ ደነገገው  ? እቅድ ሀ ሲቻል ኢትዮጵያን ግጦ ለመብላት እቅድ ለ ደግሞ ትግራይ መገንጠል።ኢትዮጵያን ማፈራረስ የማንና አሁንም የሚሰራበት ዕቅድ ነው ? አንባቢን ማሰልቸት አልሻም::ዛሬ አትወጡት መቀራቅር ገባችሁ።ጀምበር እየጠለቀችባችሁ ሲሆን ዘረኝነትን “የምትኮንኑ” ሆናችሁ::ይህን ስትሉ መስማት እኮ ለኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ትልቅ ድል ነው። እያጥወለወላችሁ ካፋችሁ ወጣ። ሌሎችን ግን ለዚህ ክፋት፤ውድቀት፤ብልሽት አትውቀሱ።

የህወሃት ዋና ቃል አቀባይ ሀይለ ማርያም ደሳለኝ በቪኦአ(አሜሪካ ድምጽ) ጎጠኝነትን የሚያወግዝ መግለጫ ሰጥቷል።”ብሄራዊ መግባባት” “ዲሞክራሲያዊ ብሄርተኝነት” የተለመደው “ኪራይ ሰብሳቢ” ሁሉንም የህወሃት ንግድ ምልክቶች እየጠቀሰ የጎጠኝነት መዘዝን፤አስከፊው ህወሃት: ያመጣውን፤ የዘራውን መርዝ ኮነነ። አጃኢብ! ይላል ያገሬ ሰው።ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ። አይሰማ የለም ህወሃት ጎጠኝነትን ስታወግዝ ሰማን።ደስ የሚለው ከቱባ ዘረኞቹ ብንሰማው ነበር።በድርቅና “አማራ” ከሆኑት በሰማነው። እነሱ ግን ተላላኪ መረጡ። እንደሚቀፋቸው አልጠራጠርም።መጋረጃ ኋላ ሆኖ መዘወር ነው ዘዴአቸው።ሟቹ መለስን የሚወዳደር አፈጮሌ አላፈራችሁም። ልውጣ ቢልም አታስወጡት።እርስ በርስ የተጠላለፋችሁ መንጋ መሃይሞች።ሸር ብቻ።ኪራይ ሰብስባችሁ ወደውጭ አገር በፊት ለፊት የሞሸለቃችሁትን ስታሸሹ፤ማነው  ኪራይ ሰብሳቢው ?

ክልል፤ ዘረኝነት አደጋ ነው።ይህን መንገድ አትሂዱበት ስትባሉ “በህግ” ደንግጋችሁ እስከ መገንጠል ብላችሁ አምሳችሁ አተራምሳችሁ ዛሬ ዘረኝነትን ለመኮነን ደረሳችሁ!ግን ማነው ዘረኛው? ትምክህተኛ ያላችሁት አማራ ?ያጥላላችሁ እስር ቤት ያጎራችሁት ኦሮሞ? የጨፈጨፋችሁት አኝዋክ የገደላችሁት አፋርና የኦዴን ሶማሊ ? ያተራመሳችሁ የደቡብ ህዝብ? ማነው ዘረኛው? ትልቁንና አስገራሚው ውሸት ዋሻችሁ ዛሬ ! የተለመደው ማጭበርበር ስለሆነ ተከታዩን እንጠብቃለን።ወደ ትግራይ ያካለላችሁትን ልንመልስ ነው ልትሉን ነው? ለሱዳን የለገሳችሁትን መሬት አስመለስን ልትሉን? “ጎጠኝነትን ኮንኑ” ተብሎ የተኩላ ባህሪያችሁ ሊረሳ? አካሄዳችሁ የደፋር ነው። ህዝብ ታዝቧችሁ አብቅቷል። ጽዋው ሞልቶ ፈሷል። ያበቃ ነገር ነው። አውቃችሁ ባትሰራም ይችን ትሪክ እንስራት ብላችሁ ነው። ይህ ድርጊታችሁ ፍርሃታችሁን፤ህዝቡ ሊያስወግዳችሁ፤ከጫንቃው ሊያወርዳችሁ መነሳቱን፤ መቁረጡን አመናችሁ ማለት ነው።እብሪቱ የታል? “ልክ ማስገባት ነው” የታል? እንዴ ህወሃቶች ምን ነካችሁ?

የድሮ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ህወሃቶችን ትተን ጉዳያቸው ያገር ጉዳይ እንጂ የጎጥ አልነበረም። የዘር አልነበረም።ጭቆና ይቅር።መብት ይከበር::አርሶ አደር ላባደር አይበዝበዝ።የባእድ ተልካሻ ባህል አንፈልግም።ደቡብ አፍሪካ የነገሰው አፓርቴድ ይጥፋ።ቅርብ እሩቅም ያሉ የዴሞክራሲ ትግሎችን የመደገፍ ነበር።ዓለምን ሁሉ ያካለለ እይታ ነበር።ጎጥ አልነበረም ወጉ። ምሁርነት ባገራችን ክቡር የነበረ ጊዜ። ደጉ ዘመን:: ምሁራን ጀግኖችም ነበሩ።ህወሃቶችን ትተን።ድሮ ዩንቨርስቲ አንድ ከክፍለ አገር የመጣ ተማሪ በአራት ዓመታት ከራሱ ክፍለ አገሩ የመጡትን ብቻ ሳይሆን ከመላ ኢትዮጵያ የመጡት ጋር ተምሮ የእድሜ ልክ ጓደኛም አፍርቶ ህይወቱ የተቃና ዜጋ እንዲሆን እድል የሚያገኝበት ነበር።ዩንቨርስቲ በክልል።ስራ በክልል።ንግድ በክልል።ሁሉን አጥራችሁት ዛሬ ሰብል አማረላችሁ።እጨዱ እንጂ ! መምህራኑ ብቻ አይወቀሱም። እናንተ በመንግስት ደረጃ ላደረጋችሁት።በክልል አጥራችሁ ያደገውን ትውልድ ነው የሚያስተምሩት።መምህራኑም በእድሜ ያልጠኑ ከሆነ የስርዓታችሁ ውጤቶች ናቸው።አትላኩባቸው።ዛሩም አውልያውም እናንተው ህወሃቶች ናችሁ!

የአሁኑ ጎጠኝነትን መኮነን ለፖለቲካ ፍጆታ መሆኑን ማንም ያውቀዋል።አንዴም በህወሃቶች መሀል ክልል ዘረኝነት አከራክሮ አለያይቶ አያውቅም።እርስ በርስ “እኔ ብልጫ ያለኝ ዘረኛ ነኝ” መባባል ምባልባት አጋጭቶ ይሆናል። “እንኳ ተፈጠርናን” ማን ሊረሳ።ሰቆቃውን፤ድብደባውን እስሩን እያባሳችሁት አሁን ጎጠኝነት አሳስቧችሁ? በፍርድ ስም እያላገጣችሁ ? እረ እንዴት ? እንደሚመስለኝ ከዚህ የበለጠ የምትሸፍጡት ሸፍጥ ይህ የዛሬው አንደኛ ትእይንት ይመስለኛል። ሌሎች ውጥረት ማርገቢያዎች “ክልል ይቅር” “ተነሱ እንነሳ አሰብን እናስመልስ” “ኤርትራ እንዝመት” ሎሎች አኬል ዳማ መሰለ ድራማዎች ተጨምረው።ቱባ ወያኔዎች ባደባባይ “ኢትዮጵያ ማሪን በድለንሻል” ሊሉም ይችላሉ።ህዝብ ግን ህወሃቶች ተራ ሌብነታቸውን ለመቀጠል የሚያካሂዱት መሆኑ ያውቃል።የኦሮሞ ህዝብ ዛሬ እያየን እየሰማን::  የሀረር አማሮች  ስልጣን እደያዛችሁ፤ ከቀዬው ያፈናቀላችሁት።የአፋር፡ የኦጋዴን የአኝዋኮች ስቃይ የት ያድርስ ? በመምህራን እና ተማሪዎች ላይ ሊላከክ ? ዩንቨርስቲን ያህል የውቀት የምርምር ቀዬ እጅግ ኋላ ቀር የሆነው የዘረኝነት ኩሬ መሆኑን ታዝበው የቆጫታቸው ምሁራኑ በብሶት ቢናገሩም፤ያውም ታፍነው ስራ አልባ ሆነው ያገር ፍቅር ቢናግራቸው፤”እዲህ ያለ ዘመን ደረስን” ብለው ቢናገሩ እውነቱን አፈረጡት።ሌላ ምንም።

ህዝብ አሁን ምን ያድርግ ? የእስታሁን ትዕግስቱ፤እስበስ መቻቻሉ አምበርክኳችኋል።እንደ ውጭ ጠላት አገርን መተራችሁ፤ህዝቡን ፈተናችሁት። በአንጻሩ ህዝቡ መርዛችሁን እንዳከሸፈ ነው።የዘረኝነት መጥፋት እናንተ ሳትወገዱ የሚታሰብ አይደለም።የኔ መሰሎች ይህን ማለት ማክረር፤ጥላቻ፤ አይደለም። ሬኮርዳችሁ እንዲህ የሚፋቅ አይደለም። የከሰረ መንገድ ይዛችኋል ለተረፈች አጭር እድሜአችሁ መፍጨርጨር ነው።

ከእባብ እንቁላል እርግብ አይገኝም።ህወሃት ተጣሞ ያደገ ያረጀ ያፈጀ የተንኮል ድርጅት ነው።የተቀነባበረው የስለላ ክፍላችሁ ተግባር አንድም እንዲህ ህዝብ ያረረበትን ጉዳይ አንስታችሁ የአዞ እንባ ማፍሰስ ነው።ሌላው በአይጋ ፎረምና በሌሎች አንዳንድ ድረ ገጾች ቀስበቀስ የምታናፍሱት ብኩን ፕሮፓጋንዳ ነው።ያፈናቀላችሁትን፤መሬቱን ለውጭ ከበርቴ የሸጣችሁበትን፤ዘሩን ጠቅሳችሁ ጢቅ ብላችሁ የተፋችሁበትን ህዝብ መልሳችሁ በዘረኝነት መውቀስ እብደታችሁን አመልካች ነው።የዘረኝነት ሰንኮፉ እናንተ ስትነቀሉ ተመነገለ ማለት ነው።የለውጥ ሱናሚ ድምጹ ከሰሜን ኢትዮጵያ ተነስቷል።እንደወትሮው።አገር ወዳዱ በዓለም የተሰራጨው ኢትዮጵያዊ ለወገኑ መቆሙን ተግባራዊ እያደረገ ነው።ህወሃቶች የሽኝት ግብዣችሁ ድግሱ አልቋል።ለበስ ለበስ፤ ወጣ ወጣ ነው ሻንጣችሁን ይዛችሁ።

ኢትዮጵያ በሰላም ተከብራ በዜጎቿ ሁሉ አንድነት ለዘለዓለም ትኑር!

 

 

የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ማህበራዊ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ አለነ ማህፀንቱ ውሳኔ ሳያገኙ ቀሩ

$
0
0
Alene

አቶ አለነ ማህፀንቱ

‹‹ስብስባን በማወክ›› ወንጀል የተከሰሱት የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ማህበራዊ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ አለነ ማህፀንቱ ውሳኔ ሳያገኙ ተለዋጭ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው፤ የተከሳሹ ጠበቃ አቶ ገበየሁ ይርዳው ገለፁ፡፡

አቶ አለነ ዛሬ ነሐሴ 21 ቀን 2007 ዓ.ም አራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበረ ሲሆን፤ መዝገባቸውን እየተከታተለ የሚገኘው ተረኛ ችሎትም መዝገቡን እየተመለከተ እንዳለና ብይኑ እንዳልደረሰ ገልፆ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ አቶ ገበየሁ፣ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ እንደተቃወሙና ደምበኛቸው ብይን ለማግኘት ይህን ያህል ጊዜ መንገላታት እንደሌለባቸው እንዲሁም ዋስትናቸውን መከልከላቸው አግባብ እንዳልሆነ ለተረኛው ችሎት አስረድተዋል፡፡ ተረኛ ችሎቱ ብይኑ ስላልደረሰ ውሳኔ ላይ እንዳልደረሱ በመግለፅ ውሳኔውን ለማስተላለፍ ማለትም አቶ አለነ ‹‹ክሳቸውን ሊከላከሉ ይገባል ወይስ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ ተሰናብተዋል›› በሚለው ላይ ብይኑን ለማስተላለፍ ተለዋጭ ቀጠሮ ለመስከረም 5 ቀን 2008 ዓ.ም ሰጥቷል፡፡

አቃቤ ህግ በአቶ አለነ ማህፀንቱ ላይ ሁለት ምስክሮችን አሰምቶ ተከሳሹ ብይን ሳያገኙ፤ መዝገባቸው ከመደበኛ ችሎት ወደ ተረኛ ችሎት እንደተላለፈ ይታወቃል፡፡ አቶ አለነ መንግስት አይኤስን ለማውገዝ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ‹‹ስብሰባን አውከዋል›› የሚል ክስ ቀርቦባቸው፤ ክሳቸውን ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በመሆን ከግንቦት ወር 2007 ዓ.ም ጀምሮ እየተከታተሉ እንዳለ አይዘነጋም፡፡

ኦሮሚያን እንገነጥላለን የሚለው ጥያቄ ታላቋ ኢትዮጵያን ለመሰረተው የኦሮሞ ህዝብ ስድብ ነው

$
0
0

ማስታወሻ፡- ቀጥሎ የምታነቡትን ጽሑፍ በፍቃዱ ኃይሉ በአማርኛና በኦሮምኛ ቋንቋዎች ለአንባቢያን እንዲደርስለት ለነገረ ኢትዮጵያ የላከው ነው፡፡ ኦሮምኛውን ቀደም ብለን የለቀቅን ሲሆን አማርኛውን ደግሞ እንሆ!
Guddaa saalpaa fariddi guniddaan dhessa

በፍቃዱ ኃይሉ (ከቂሊንጦ እስር ቤት)

በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ አውሮፓውያን አፍሪካን ለመቀራመት ተሰብስበው ወሰኑ፡፡ ኃያላኑ መንግስታት የየድርሻቸውን ሲወስዱ የኢትዮጵያን አካባቢዎች ለመውረር የሞከረው የጣሊያን መንግስት ነበር፡፡ አውሮፓውያን ወራሪዎች ‹‹ዓላማችን አፍሪካውያንን ከእንቅልፋቸው ቀስቅሶ ማሰልጠን ነው›› ቢሉም እየዋሹ ነበር፡፡ ዋነኛ ዓላማቸው የአፍሪካን ሀብት ለፋብሪካዎቻቸው ጥሬ ዕቃ ማድረግ ነበር፡፡ ሆኖም እግረ መንገዳቸውን አፍሪካውያንን ሀይማኖታቸውን እያስለወጡ ከራሳቸው ጋር ያመሳስሉታል፡፡ ቋንቋ፣ ወግ እና ልማዶችን በማጥናት ዘመናዊ በሚሉት በራሳቸው ቋንቋ፣ ወግ እና ልማድ ይተኩታል፡፡ አፍሪካውያንን ማሰልጠን የሚሉት ይህንን ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ከቅኝ ግዛት በኋላ ብዙ አፍሪካውያን የራሳቸውን ቋንቋ፣ ባህል እና ስርዓት ሙሉ ለሙሉ አጥተው በአውሮፓውያን ገዥዎቻቸው ባህል እና ስርዓት እየተዳደሩ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ግን በአንጻሩ ይህንን ወረራ በኅብረት መመከት በመቻሏ ምንም እንኳን ከአውሮፓ ተጽዕኖ ባትተርፍም የተለየ (የራሷን) ባህል እና ወጎችን እንደያዘች አለች፡፡

(ጋዜጠኛ በፈቃዱ ኃይሉ)

(ጋዜጠኛ በፈቃዱ ኃይሉ)

ኢትዮጵያ የአውሮፓ ወራሪዎችን መመከት የቻለችው ህዝቦቿ በመተባበራቸው ነው፡፡ የጣልያን ሰራዊት አድዋ ላይ ድል ካደረጉት የጦር መሪዎች መካከል ባልቻ ሳፎ (በፈረስ ስማቸው አባ ነፍሶ) ሳይጠቀሱ የማይታለፉ የኦሮሞ ልጅ ናቸው፡፡ ከምንም ተነስተው የጦር ሚንስትር እስከመሆን የደረሱት ሀብተጊዎርጊስ ዲነግዴ (አባ መላ) ለዚህ ደረጃ የበቁት በአድዋ ባሳዩት ጀግንነት እና መለኝነት ነበር፡፡ እርሳቸውም የኦሮሞ ልጅ ናቸው፡፡ ጣልያን ድል ሆኖ መመለሱ ቆጭቶት ከ40 አመታት በኋላ ሲመለስም ወረራውን በመመከት ረገድ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ኦሮሞዎች ተሰልፈው ነበር፡፡ ከነዚህም መካከል የማይዘነጉት እነ ገረሱ ዱኪ እና ጃጋማ ኬሎ ይገኙበታል፡፡ ጀግናው ጃጋማ ኬሎ ፍቀረማርቆስ ደስታ በጻፈላቸው ታሪካቸው ውስጥ ‹‹ኦሮሞ የኢትዮጵያ ግንድ ነው›› ሲሉ ነግረውታል፡፡ እውነታቸውን ነው፡፡

የኦሮሞ ህዝብ በብዛት ትልቁ ኢትዮጵያዊ ብሄረሰብ ነው፡፡ የኦሮሞ ታሪክ ከተጻፈው በላይ ትልቅ ነው፡፡ የኦሮሞ ጎሳዎች ይተዳደሩበት የነበረው የገዳ ስርዓት ዴሞክራሲ ለኦሮሞ ህዝብ ባህሉ ነው ያስብላል፡፡ በኦሮሞ ባህል የሰዎች አደረጃጀት የበላይና የበታች የሚለው ብዙም ተቀባይነት የለውም፡፡ በየትኛውም የገዳ ስርዓት የስልጣን እርከን ላይ ያለን ሰው የትኛውም ተራ ሰው መተቸት እንዲችል የኦሮሞ ባህል ይፈቅድለታል፡፡ ይህ ዓይነቱ ባህል የህዝብ መሪዎች ከህዝብ ትችት እንዳያመልጡ የሚያደርግ ስለሆነ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ያስፈልገናል፡፡

የኦሮሞ ህዝብ፣ ምንም እንኳን የብዛቱን ያህል ተጠቃሚ ባይሆንም የኦሮሞ ልጆች በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የስልጣን ተቀናቃኝ ሆነው አልፈዋል፡፡ አንዳንድ ባለታሪኮች ‹ዘመነ መሳፍንት› የሚሉት የኢትዮጵያ ክፍለ ታሪክ በየጁ ኦሮሞዎች ኢትዮጵያ የተመራችበት ዘመን ነው ይላሉ፡፡ ያኔ መናገሻ የነበረችው ጎንደር ከተማ የስራ ቋንቋዋ ኦሮምኛ ሆኖ ነበር፡፡ በሌላ ጊዜ ደግሞ ንግስናውን ያገኙት የአማራ እና የትግሬ ገዢዎች ከኦሮሞ ጦረኞች ጋር ተስማምቶ ለማደር በጋብቻ መተሳሰርን መርጠዋል፡፡ ለምሳሌ ቴዎድሮስ ልባቸው እስኪጠፋ ያፈቅሯት የነበረችው ሚስታቸው የወሎው ኦሮሞ ራስ አሊ ልጅ ተዋበች ነበረች፡፡ አጤ ምኒልክ ያገቡት ‹‹የኢትዮጵያ ብርሃን›› የምትባለውን ዜደኛ የየጁ ኦሮሞ ሴት ጣይቱ ብጡልን ነበር፡፡ …ኦሮሞዎች ኢትዮጵያን በቀጥታ ባልገዙበት ዘመን በተዘዋዋሪ አዝዘውባታል፡፡

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እንዳለመታደል ሆኖ ህዝቡ ተመችቶት አልኖረም፡፡ የኦሮሞ ህዝብም የዚሁ ገፈት ቀማሽ ነበር፡፡ መሪዎች በተገላበጡ ቁጥር ለራሳቸው ሲሉ ድሃውን ገበሬ ሲያንገላቱ ኖረዋል፡፡ ነገስታቱ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ከጎናቸው ያልተሰለፈውን ሁሉ በኃይል ያጠቁ ነበር፡፡ ገበሬው ያመረተውን ቆርሶ የማካፈል ግዴታ ነበረበት፡፡ ግብር የበዛባቸው ገበሬዎች ከመማረራቸው የተነሳ የእህል ክምራቸውን የንጉስ ወታደሮች ሊወስዱባቸው ሲመጡ እህሉ ላይ እሳት ለኩሰውበት ይሸሹ ነበር፡፡ ነገስታት በመጡ፣ ነገስታት በሄዱ ቁጥር ድሃው ህዝብ እረፍት ሳያገኝ ኖሯል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ከጥቂቶቹ የስልጣን ተቀናቃኞች በስተቀር ቀሪው ያሳለፈው ታሪክ የፈተና ነበር፡፡ ሆኖም ግን ጭቆናው ዴሞክራሲያዊ (ህዝባዊ) ያልሆኑ መንግስታት ባሉበት ቦታ ሁሉ ብዙሃኑ ላይ የሚጫን ቀንበር ነው፡፡

የኦሮሞ ህዝብ በታሪኩ ባደረጋቸው እንቅስቃሴዎች ከደቡብ ወደ ሰሜን በመስፋፋት ያልሰፈረበት የኢትዮጵያ ግዛት የለም፡፡ ከሁሉም ህዝብ ጋር ተቀላቅሏል፡፡ በአንዳንድ ቦታዎች የራሱን ባህልና ቋንቋ ሲያወርስ በሌሎች ቦታዎች ደግሞ ከተስፋፋባቸው አካባቢዎቹ የቀድሞዎችን ነዋሪዎች ባህልና ቋንቋ እንዲሁም ሀይማኖት ወርሷል፡፡ ‹‹ግማሽ ሲዳማ››፣ ‹‹ግማሽ ጉራጌ›› የሲዳማንና የጉራጌን ባህል የወረሱ ኦሮሞዎች ናቸው፡፡ የወሎ ኦሮሞዎች አማርኛ ቋንቋ እና እስልምና ሀይማኖት ወርሰዋል፡፡ ራያ እና አዘቦዎች ትግርኛ ቋንቋና ክርስትናን ወርሰዋል፡፡ … በዚህ መንገድ ኦሮሞዎች ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ተሳስረዋል፡፡ ሶሾሎጂስቱ ዶናልድ ሌቪን የኦሮሞዎች እንዲህ ከሌሎች የመዋሃድ ችሎታ ትልቋን ኢትዮጵያ ፈጥሯል ይላሉ፡፡

የኢትዮጵያ ህዝቦች አሁንም ከገዥው ጭቆና አልተላቀቁም፡፡ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ልክ እንደ ትላንቷ ኢትዮጵያ የመብት ጥያቄ ያነሱ ልጆች በኃይል ይጨፈለቃሉ፡፡ ይህንን ጭቆና ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች በየራሳቸው መንገድ እየታገሉት ነው፡፡ ይሁን እንጂ በተባበረ ክንድ መታገል ባለመቻላቸው ጭቆናው ሊቆም አልቻለም፡፡ ብዙ የኦሮሞ ልጆች መፍትሄው የኦሮሚያ መገንጠል እንደሆነ ሊያምኑ ይችላሉ፡፡ ኦነግ በቀድሞው ብርታቱ ባይኖርም መንፈሱ አለ፡፡ ብዙዎች የኦነግ መንፈስ የሚሉት ይህንን ‹‹እንገነጠላለን›› የሚለውን ጥያቄ ነው፡፡ ብዙዎች የተሰውለት፣ ብዙዎች የታሰሩለት፣ ብዙዎች የተሰደዱለት ጥያቄ ይሄው ቢሆንም እስካሁን ለውጥ አላመጣም፡፡ በእኔ እምነት ጥያቄው ለውጥ ያላመጣው በሁለት ምክንያቶች ነው፡፡ አንደኛ ትልቋን ኢትዮጵያ የመሰረተው የኢትዮጵያ ግንድ (የኦሮሞ ህዝብ) እንደቅርንጫፍ እገነጠላለሁ ማለቱ ነበር፡፡ ሁለተኛ ጠላታችን የሆነውን ጭቆና ማሸነፍ የምንችለው በመተባበር እንጂ በመለያየት ባለመሆኑ ነው፡፡

የጣልያን ወረራን ያሸነፍነው በተባበረ ክንዳችን እንጂ በተነጣጠለ ኃይል አይደለም፡፡ አሜሪካ ዓለምን የምትመራው ክፍለ ሀገሮቿ ተባብረው አንድነት ስለቆሙ ነው፡፡ አውሮፓውያን የአውሮፓ ህብረትን የመሰረቱት የአሜሪካን ኃያልነት በህብረት ለመቋቋም ነው፡፡ አፍሪካም ወደ ህብረት እየሄደች ነው፡፡ በህብረታችን ታሪካዊ ጠላታችን ጭቆናን ማሸነፍ ይቻላል፡፡ መገነጣጠል ግን ይብሱን ያደክመን ይሆናል እንጂ አይበጀንም፡፡ የኤርትራ መገንጠል ለኤርትራ ህዝብ ነጻነት አላስገኘም፡፡ የደቡብ ሱዳን መገንጠል ለደቡብ ሱዳናውያን ሰላም አላመጣላቸውም፡፡ የሶማሊያ አንድ ብሄር መሆንና አንድ ሀይማኖት መከተል ከመበጣበጥ አላዳናቸውም፡፡ መዋጋት ያለብን ጭቆናን እንጂ ህብረታችንን አይደለም፡፡

ኦሮሚያን እንገነጥላለን የሚለው ጥያቄ ታላቋ ኢትዮጵያን ለመሰረተው የኦሮሞ ህዝብ ስድብ ነው፡፡ ሽንፈት ነው፡፡ ትግሉ መሆን ያለበት ጠንካራና ነጻ ኢትዮጵያን ለማረጋገጥ ነው፡፡ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ለዚህ ዓላማ (ሌሎች ፖለቲከኞች ባይመቿቸው እንኳ) የዴሞክራሲ ባህላቸውን ተጠቅመው ሊታገሉት ይገባል እንጂ የገነቧትን ትልቋን ኢትዮጵያ ጥለው እንገነጠላለን ማለት የለባቸውም እላለሁ፡፡ የታላቅነት ምስጢሩ ህብረት እንጂ ነጠላነት አይደለም፡፡ በህብረት እናሸንፋለን!


ዝዋይ ላይ ከፍተኛ የመኪና አደጋ ደረሰ * ነዳጅ የያዘው መኪና ቃጠሎ አስከትሎ ሁለት ሰዎች ተቃጥለው ሞቱ

$
0
0

zeway zeway 1 zeway eth

(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ ከ እለት ወደ እለት እየደረሰ ያለው የመኪና አደጋ አስፈሪና በተለይም በመኪና ረዥም መንገድ መሄድን የማያስመኝ እየሆነ መጥቷል:: ዛሬ ጠዋት ላይ በዝዋይ ከተማ አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ ወደ እሳትነት ተቀይሯል::

ከአካባቢው ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ነዳጅ የያዘው የጭነት መኪና ከሕዝብ ንብረት ማመላለሻ አይሱዙ መኪና ጋር የተጋጩ ሲሆን ነዳጅ የያዘው መኪና እሳት ተነስቶበት ለሁለቱም መኪኖች መቃጠል ምክንያት ሆኗል:: እስካሁን የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደሚሉት የመኪናዎቹ አስከርካሪዎች የሁኑ 2 ሰዎች ተቃጥለው ሕይወታቸው አልፏል:: ሆኖም ግን ፖሊስ ሰፋ ያለ ማብራሪያ የሰጠው ነገር የለም::

የኤፍሬም ማዴቦ ጽሑፍ ከኤርትራ በርሃ: ከዊሃ እስከ ኦምሃጀር –አንድ ሰሞን ከአርበኞች ጋር

$
0
0

ቃል የዕምነት ዕዳ ነዉ። ከዊሃ እስከ ኦምሃጀር – አንድ ሰሞን ከአርበኞች ጋር ,-በኤፍሬም ማዴቦ

ቃል የዕምነት ዕዳ ነዉ። አዎ! ማተቡን ላጠበቀና በአምላኩ ለሚታመን በእርግጥ ቃል የዕምነት ዕዳ ነዉ። ሰዉ ነኝና እንደ ፈጣሪ ቃሌ ሁሉ እዉነት ነዉ ብዬ አለተፈጥሮዬ አላብጥም። ግን ሰዉ ብሆንም ፈጣሪዬን የምፈራ ሰዉ ነኝና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ስል ልቦናዬ እያወቀዉ እንደነ ጋሼ እንደልቡ ዉሸት ደርድሬ ለአንባቢ የማቀርብበት ምንም ምክንያት የለም። ከዚህ ቀጥሎ የማስነብባችሁ እያንዳንዱ ቃል እንደ ዳያስፖራ ተረተኞች የምተርተዉ ‘ሰዉ ሰዉ’ የማይሸተት ተረት ሳይሆን ኢትዮጵያ ድንበር ላይ በየግንባሩ የተሰለፉትንና በስልጠና ላይ የሚገኙትን የኢትዮጵያ አርበኞች ስጎበኝ በአይኔ ያየሁትንና በጆሮዬ የሰማሁትን ቃል ነዉ።
Ephrem Madeno
ቨርጂኒያ ወደሚገኘዉ “Dulles” አዉሮፕላን ማረፊያ የሄድኩት ከልጄ ጋር ነበር። ከቤቴ Dulles የግማሽ ሰዐት መንገድ ነዉ። ያቺን ግማሽ ሰዐትና አዉሮፕላን ማረፊያ ደርሼ ሻንጣዬን እስካስጭን ድረስ አይኔ እያንዳንዷን ደቂቃ ከልጄ ከቢኒያም አልተለየም። መለየቱን ስላልወደደዉ ልቤ ደንግጧል። ከወያኔ ጋር ለመፋለም በረሃ የሚጓዘዉ ኤፍሬም ከአንድ ልጁ መለየት አቃተዉ። ምነዉ ብዬ እራሴን ጠየኩት- እኔዉ መልሼ ምንም አልኩ። ልጄን አቀፍኩት፤ አሁንም ደግሜ ደጋግሜ አቀፍኩት። እምባ ፊቴን ሞላዉ። ቀና ብሎ ተመለከተኝና ሲከፋዉ ታየኝ። ሁለተኛ ዙር እምባ ፊቴን ሞላዉ። “Son I don’t want to do this, but I have to do it” አልኩ በሁለት እጄ አቅፌ እንደያዝኩት። ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ አባት ሆይ ፈቃድህ ከሆነች ይቺ ጽዋ ከኔ ትለፍ ብሎ የጸለየዉ ፀሎት ትዝ አለኝ። እኛ ሰዎች የዳንነዉ ይህ ፀሎት ባለመመለሱ መሆኑ ትዉስ ሲለኝ ልቤ በሀሳቡ ጸና። አባባ Come on . . . be strong. I promise I will be the son that you raised- you will be proud of me” አለኝ ቢኒያም በዚያ 17 አመት ሙሉ በማዉቀዉ ቆንጆ ድምጹ። የተናገራቸዉ ቃላት ዉስጤ ገብተዉ ኃይል ሲሆኑኝ ተሰማኝ። ጠነከርኩ። ተሰናብቼዉ ወደኋላ እያየሁት ወደ ዉስጥ ገባሁ። ወደ ፍተሻዉ ቦታ ስሄድ ልቤን ከፍተኛ የመለየት ኃዘን እንደ ግግር በረዶ ሲጫነዉ ተሰማኝ፤ መሸከም አቃተኝና እንደ ህፃን ልጅ እያነባሁ ፍተሻዉ መስመር ላይ ገብቼ ወረፋ ያዝኩ።

እንደፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር ረቡዕ ኦጎስት 5 ቀን ከሌሊቱ 9 ሰዐት የተሳፈርኩበት አዉሮፕላን አስመራ አለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ አይኔ ላይ ዉል ዉል እያለ ልቤን የሰቀለዉ የሚጠብቀኝ የትግል ዉጣ ዉረድ ሳይሆን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመርቄ በ22 አመቴ ስራ የጀመርኩባት ዉቧ የአስመራ ከተማ ምን ትመስል ይሆን የሚል የሀሳብ ዉጣ ዉረድ ነበር። ሆኖም አካልም መንፈስም እየከዳ ምንም ነገር ማሰብ አይቻልምና ወደ ግዜያዊ ማረፊያ ቦታዬ እንደወሰዱኝ ለሁለት ቀን ከግማሽ የተጠራቀመ እንቅልፍ ይዞኝ ጭልጥ አለ።

ረቡዕ ከቀኑ አንድ ሰዐት አካባቢ “እባክህ ተነሳና ምሳ እንብላ” የሚል የሁለት ሰዎች ድምጽ ተራ በተራ ጆሮዬ ዉስጥ ገባና እንቅልፌን ሰለበዉ. . . መነሳት ባልፈልግም በልቤ ትግሉ ተጀመረ አልኩና ከተጋደምኩበት ቀና አልኩ። ፊት ለፊቴ ቆመዉ ተነስ እያሉ የሚጨቀጭቁኝ የትግል ጓደኞቼ ነአምን ዘለቀና ብርሀኑ ነጋ ነበሩ። ምሳ ላይ ተቀምጠን እነሱ የሚያወሩት ወደ ኤርትራ በረሃዎች ሰለሚደረገዉ ጉዞ ሲሆን እኔ ደግሞ በወጣትነቴ ስለማዉቃት የአስመራ ከተማ ነበር። አስመራን ትቼ ከነሱ ጋር እንደነሱ ማሰብ ሞከርኩ . . . አሁንም አሁንም ሞከርኩና ሲያቅተኝ ተዉኩት። በተለይ ምሳ የበላንበት ካራቨል ሬስቶራንት ዉስጥ በወጣትነቴ ብዙ ትዝታዎች ነበሩኝና ጭራሽ ምግቡን ትቼ በምናብ ወደ ወጣትነቴ ሽምጥ ጋለብኩ። ባር ኡጎ፤ ባር ቱኔል፤ ባር ፀአዳ ፈርስ፤ ባር እምባባና የባቢሎን ጋጋታ እንዳለ ፊቴ ላይ እየመጡ ተደቀኑ። ቀና ስል ነአምንና ብርሀኑ . . . አትበላም እንዴ አሉኝ። ወደ ኋላ ሽምጥ ያስጋለበኝን ፈረሴን ልጓም ያዝ አደረኩና ካሁን በኋላ ወደፊት ብቻ ብዬ ከሁለቱ ጓደኞቼ ጋር በአካልም በመንፈስም ተቀላቀልኩ።
የአስመራ ከረን መንገድ ከተነጠፈ አስፋልት ዉጭ ሌላ ምንም አይቶ ለማያዉቅ ለእንደኔ አይነቱ የዳያስፖራ ‘በለስ’ ቀርቶ ደጋግሞ የተጓዘበትንም ሰዉ ልብ ይሰልባል። አስመራን ይዞ፤ አዲአቤቶንና እምባደርሆን ይዞ በአዲተከለዛን፤ በኢላበርዕድ፤ በከረንና በሀጋዝ አድርጎ አቆርደት ድረስ የሚዘልቀዉ መንገድ የአለም ተራራዎች ስብሰባ ተጠራርተዉ ወደየመጡበት ላለመመለስ ተማምለዉ የመሸጉበት ቦታ ይመስላል። አንዱን ተራራ ሽቅብ ወጥተንና ቁልቁል ወርደን እፎይ ብለን ሳንጨርስ ሌላዉ ከተፍ ይላል። በስተቀኛችን ያለዉን ተራራ አይተን ወይ ጉድ ስንል በግራችን ያለዉ ድንቄም ጉድ እያለ ያሾፍብናል። እልፍ ስንል ተራራ፤ ከዚያም ተራራ፤ተራራ፤ ተራራ ብቻ ነዉ። ፊት ለፊቴ የማያቸዉ ተራራዎች ተፈጥሮ የቆለለዉ የዲንጋይ ክምር ሳይሆን አዋቂ በዉኃ ልክ እየጠረበ የደረደረዉ ሾጣጣ ኃዉልት ይመስላሉ። አንኳን ለሰዉ ልጅ ለገደሉ ንጉስ ለዝንጀሮም አይመቹም። ባጠቃላይ የአስመራ አቆርደትን መንገድ ሲመለከቱት እንደ አጥር ከተሰለፉት ተራራዎች ባሻገር አገር ያለ አይመስልም። አላማና ጽናት ላለዉ ሰዉ ግን ከተራራዉ ወዲያ አገር ከአገርም ወዲያ ሌላ. . . ሌላ ወያኔ የቀማን አገር አለ።

አላማ የሌለዉ፤ ሆዱ ያልቆረጠ፤ ፈሪ፤ ወኔ የከዳዉና አይኑን ተራራዎቹ ላይ ብቻ ያሳረፈ ሰዉ ከአስመራ ተነስቶ በከረን በኩል አቆርደትን አቋርጦ የጀግኖቹ መንደር ሀሬና የሚደርስ አይመስለዉም። ለዚህ ነዉ ሁሉን የሚችል እግዚአብሄር አይዞህ ብሎ የላከዉ የብሉይ ኪዳኑ ነቢዩ ኤልያስ ኤልዛቤልን ፈርቶ እንደሸሸ ሁሉ የኛም ዘመን ጋዜጠኛ ነን ባዮች፤ ዘፋኞችና አርበኛ ነን ባይ የሀሰት ነቢያት ገና ከረን ሳይደርሱ ተራራዉን እየፈሩ በኤርትራ በኩል ምንም ነገር መስራት አይቻልም እያሉ እንደ ግመል ሽንት የኋሊት የሚጓዙት። ድንቄም ጋዜጠኛ! ጋዜጠኛ ታሪክ ሸራርፎ በሰጠዉ ግዜ እየኖረ ያየዉንና የሰማዉን ለትዉልድ እያስተላለፈ ለራሱ የማይኖር ልዩ ፍጡር ነዉ። የኛዎቹ “ጋዜጠኛ” ነን ባዮች ግን እራሳቸዉ ለራሳቸዉ በሰጡት ግዜ እየኖሩ የራሳቸዉን ግሳንግስ የፈጠራ ታሪክ የሚነግሩን ከህያዉ በታችና ከሙታን በላይ ባለዉ ባዶ ቦታ የሚኖሩ ባዶዎች ናቸዉ። አምላክ በምህረቱ ወደ ላይ ይሳባቸዉና ከህያዋን ጋር ይቀላቅላቸዉ።
ምድረ የወሬ ቋቶች ይግባችሁ! የኢትዮጵያ ህዝብ ዉኃ ዉኃ የሚያሰኝ የእሳት ጉድጓድ ዉስጥ ነዉ ያለዉ፤እሱ ከጉድጓዱ ባስቸኳይ መዉጣት እንጂ እንደናንተ በኤርትራ በኩል ከሆነ ይቅርብኝ ብሎ የሚጃጃልበት ግዜዉም ትዕግስቱም የለዉም። ለነገሩ እነዚህ የወሬ አርበኞች ተራራ ወጥተዉ፤ በረሃ አቋርጠዉና ወንዝ ተሻግረዉ ከወያኔ ጋር ሳንጃ ሊማዘዙ ቀርቶ የገዛ ልጆቻቸውን የልደት ኬክ ደፍረዉ በቢላዋ የማይቆርጡ የ”ዳዉን ታዉን” ቅምጦልች ናቸዉና ከነወሬያቸዉ እዚያዉ “ዳዉን ታወን” ብንተዋቸዉ የሚበጅ ይመስለኛል። አይደል?

ወሬና ስራ ለየቅል ናቸዉ፤ ለወሬ የሚያስፈልገዉ ሹል አፍ ብቻ ነዉ። ለስራ ግን አፍ፤ እጅ፤ አግር፤ አይን፤ ጆሮና የሚያስብ አዕምሮ ያስፈልጋል። ወረኛና ለስራ ያልተፈጠረ ሰዉ የተራራዉ ከፍታ እየታየዉ “በዚህ በኩል እንዴት ተደርጎ” እያለ የወሬ ቱማታዉን መደርደር ይጀምራል። የሚሰራ ሰዉ ግን ግቡ ከተራራዉ ባሻገር ከተከዜ ማዶ ነዉና ተራራዉን ሽቅብ ወጥቶና ከጠመዝማዛዉ መንገድ ጋር እኩል ተጠማዝዞ ወዳለመዉ ግብ ይጓዛል። አንባቢ ሆይ! ሠራተኛ በለኝ አትበለኝ እሱ ያንተ ጉዳይ ነዉ፤ መዳረሻዬ ከተከዜና ከመረብ ወንዞች ባሻገር መሆኑንና አላማዬም ፍትህና ነጻነት መሆኑን ግን እኔዉ እራሴ አብጠርጥሬ ልነግርህ እችላለሁ። የምወደዉን አንድ ልጄንና ጥሩ ስራዬን ደህና ሁኑ ብዬ በረሃ የገባሁት እናት አገሬ ዉስጥ ፍትህ፤ ነጻነት፤ እኩልነትና ዲሞክራሲ አብበዉ ለማየት ነዉ እንጂ የኤርትራ በረሃና ተራራ ናፍቆኝ አይደለም። የናፈቀኝ ተራራና በረሃ ቢሆን ኖሮ አሪዞናና ኮሎራዶ ይቀርቡኝ ነበር።

ዉቧን የአቆርደት ከተማና ቀዳማዊ ኃ/ሥላሤ ያሰሩትን ግዙፍ መስጊድ በስተቀኝ እያየን ወደ ባሬንቱ ስናመራ ያ ከአስመራ ጀምሮ የተከተለን የተራራ መንጋ ፀሐይ እንደገላመጠዉ በረዶ እየሟሸሸ ሄዶ ገና ሀይኮታ ሳንደርስ ሜዳ ሆኖ አረፈዉ። የበረሃዉ ሙቀት እንዳለ ቢሆንም ባሬንቱ ስንደረስ የሚነፍሰዉ ቀዝቃዛ አየር ሙቀቱን አለዝቦታል። ባሬንቱን ለቅቀን ወደ ተሰነይ ስናመራ መሬቱ ሜዳ፤ ሰማዩ ደመናማ፤ አየሩ ነፋሻማ እየሆነ ይመጣል። ትናንሽ ልጆች እዚህም እዚያም ይዘልላሉ፤ ትራክተሩ ያርሳል፤ ግረደሩ ይዳምጣል፤ እንደኔ አይነቱ ጠመዝማዛዉ መንገድ ቀልቡን የሰለበዉና ፀሐዩ ያቀለጠዉ ምስኪን ደግሞ ወላዲት አምላክ ምን በደልኩሽ እያለ ያምጣል። ባሬንቱ ያኔ እኔ ሳዉቃት የጋሽና ሰቲት አዉራጃ ዋና ከተማ ነበረች፤ ዛሬ ከሃያ ስምንት አመት በኋላ ያየኋት ባሬንቱ ግን ከፍተኛ የንግድና የእርሻ እንቅስቃሴ ይታይባታል፤ ዉብትም ስፋቷም በእጥፍ ጨምሯል ፤ደግሞም የዛሬዋ ባሬንቱ የጋሽ ባርካ ዞን ዋና ከተማ ናት።
ከባሬንቱ ወደ ተሰነይ ሲወጣ ግራና ቀኝ አዉራጎዳናዉን ይዞ ኢትዮጵያና ሱዳን ጠረፍ ድረስ የተንጣለለዉ መሬት የኤርትራ የእህል መቀነት ነዉ። አካባቢዉ ከፍተኛ የልማት እንቅስቃሴ ይታይበታል። የኤርትራን ልማትና የኤኮኖሚ እንቅስቃሴ ማየት የፈለገ ሰዉ ከአስመራና ከሌሎች ትላልቅ ከተማዎች ወጥቶ ገጠር መግባት አለበት። ግድቡ፤ እርሻዉ፤ የጤና ተቋሙና ሌላም ሌላ የመሠረተ ልማት ምልክቶች በጉልህ የሚታዩት ገጠሪቱ ኤርትራ ዉስጥ ነዉ።

ከተሰነይ ወጥተን ጥቂት እንደተጓዝን መኪናችን አስፋልቱን ለቅቃ ኮረኮንቹ መንገድ ዉስጥ ገብታ ስትንገጫገጭ ከእንቅልፌ ነቃሁና እንደመንጠራራት ብዬ . . . ደረስን እንዴ አልኩ … የመኪናችንን ሾፌር። ገና ነዉ ትንሽ ይቀራል አሉ ወደኋላ ዞር ብለዉ። እንዳዉ ለነገሩ ነዉ እንጂ ሰዉዬዉ ዬት እንሄዳለን፤ መቼ አንሄዳለን ወይም መቼ እንመለሳለን ለሚሉ ጥያቄዎች በፍጹም መልስ አይሰጡም። ወያኔ የማይሰማን ሁሉንም ነገር ሆዳችን ዉስጥ ከያዝነዉ ብቻ ነዉ የሚል ፈሊጥ አላቸዉ። ዋናዉን መንገድ ለቅቀን ኮረኮንቹን ከተያያዝነዉ በግምት ከ20 ደቂቃ በኋላ አርበኞች መንደር ቁጥር አንድ ደርስን። ዘፈኑ፤ ጭፈራዉ፤ ሆታዉና ዕልልታዉ ቀለጠ። አርበኛዉ ጠመንጃዉን እንደታቀፈ እየዘለለና እየፎከረ እንኳን ደህና መጣህልን እያለ መሪዉ ላይ ተጠቀለለ። “የወያኔ ዘረኞችና አንዳንድ ተላላዎች አንተንና ጓዶችህን ትኩስ ሀምበርገር እየበላችሁ ወጣቱን በረሃ ዉስጥ ታስጨርሳላችሁ” እያሉ አርበኛዉንና መሪዉን ለመለያየት ብዙ ጥረዋል። እናንተ ግን የሞቀ ኑሯችሁን ትታችሁ ታግላችሁ ልታታግሉን በረሃዉ ድረስ መጥታችሁ ተቀላቅላችሁናል . . . እሴይ የኢትዮጵያ አምላክ! . . . ወያኔ የተሸነፈዉ ዛሬ ነዉ እየለ አርበኛዉ በሆታና በዕልልታ ከዉስጥ የመነጨ ደስታዉን ገልጸ። ብቻ ምን አለፋችሁ ጀግኖቹን ያሉበት ቦታ ድረስ ልናይ ሄደን የጀግና አቀባበል ተደረገልን። እንደ አንድ ታጋይ ድል አፋፍ ላይ ልድረስ አልድረስ አላዉቅም፤ ማሸነፋችንን ግን አረጋገጥኩ።

የነፍስ ወከፍ ጠመንጃዉን እንዳቀፈ ሰላም ሊለኝ ሲመጣ ትኩር ብዬ አየሁት። ወጣት ነዉ፤ ጽናቱና ቁርጠኝነቱ ፊቱ ላይ ይነበባል። በፈገግታ የታጀበዉ የዋህ ፊቱ ልጅነቱን በአዋጅ ይናገራል። ዕድሜዉ ከሃያ አይበልጥም። ተቃቅፈን ሰላም ስንባባል እጅብ እጅብ ብሎ የተጎነጎነ ፀጉሩን በእጄ እያሻሸሁ “እቺን ነገር ታበድረኛለህ” አልኩት ፀጉር እየከዳዉ ያስቸገረኝን እራሴን እያሳየሁት። ችግር የለም አለኝ። “ችግር የለም” በአርበኞቹ ሠፈር የተለመደ አባባል ነዉ። የበረሃዉ ንዳድ፤ የዉኃዉ ጥማት፤ የምግብ ችግር፤ ክብደት ተሸክሞ ተራራዉን ሽቅብ መዉጣትና ባጠቃላይ ወያኔንና ዘረኛ ስርዐቱን ማስወገድ ለአርበኛዉ ችግር አይደለም። አርበኛዉ ለእንደነዚሀ አይነት ችግሮች ተዘጋጅቶ ስለመጣ እንደችግር አይመለከታቸዉም።

ድንኳን ዉስጥ ገብተን ቁጭ እንዳልን . . . . እዚህ አካባቢ ችግራቸሁ ምንድነዉ አልኩት። ይምጡ አለኝና ከድንኳኑ ይዞኝ ወጥቶ ገዢ መሬት ይዘዉ የመሸጉትን የተለያዩ ካምፖች አሳየኝና የእያንዳንዳቸዉን ስም ነገረኝ። ሁላችንም የመጣነዉ ከኢትዮጵያ ነዉ፤ ሁላችንም የምንታገለዉ ወያኔን ነዉ፤ ደግሞም የሁላችንም ጥያቄ ፍትህ፤ ነጻነትት፤ እኩልነትና ዲሞክራሲ ነዉ. . . .. ግን አንድ ላይ አንታገልም። እስከመቼ ነዉ የአንድ አገር አርበኞች ከአገራችን ወጥተን፤ የተለያየ ድንኳን ተክለን፤ በተናጠል የጋራ ጠላታችንን የምንዋጋዉ? እባካችሁ ገላግሉን ብሎኝ ቀና ሲል አይኑ ካይኔ ገጠመ። በአፉ ከነገረኝ በአይኑ የነገረኝ በለጠብኝ። እንዲህ አይነቱን ብስለት የተሞላዉ ንግግር የሰማሁት ከልጄ ብዙም ከማይበልጥ ኢትዮጵያዊ ወጣት መሆኑ ሲሰማኝ እራሴን ታዘብኩት፤ ኢትዮጵያዊነቴን ግን ከወደድኩት በላይ ወደድኩት። አዎ አሁንም አሁንም አትዮጵያዊነቴን ከነችግሩ ወደድኩት። ደግሞስ ዬኔ ስራ ችግር መፍታት ነዉ እንጂ የአገሬ ችግር ፊቴ ላይ በተደቀነ ቁጥር ኢትዮጵያዊነቴን ጥያቄ ዉስጥ ማስገባት አይደለም።በነገራችን ላይ በተናጠል የሚደረገዉ ትግል አያዋጣምና “እባካችሁ አንድ አድርጉን” የሚለዉ ጥያቄ የአንድ አርበኛ ጥያቄ ሳይሆን በየሄድኩበት ካምፕ፤ ግምባርና ምሽግ ዉስጥ ከአብዛኛዉ አርበኛ አፍ የሚወጣ ጥያቄ ነዉ።

ቀኝ እጄን ወጣቱ አርበኛ ግራ ትከሻ ላይ አሳረፍኩና በሌባ ጣቴ በርቀት የሚታዩትን ካምፖች እያሳየሁት… አንዱጋ መሄድ እንችላለን አልኩት። አይ ጋሼ አሁን መሽቷል አለኝ። ሰዐቱ ገና ከቀኑ 9 ሰዐት ቢሆንም ሰፈሩ የአርበኞች ስለሆነ በነሱ ህግ መተዳደር አለብኝ ብዬ እሺ አልኩት። አይዞት እናንተ አስተባብራችሁ አንድ አድርጉን እንጂ ሌላ ሌላዉ ችግር የለዉም አለኝ። እኔም እንደ ወጣቱ አርበኛ በድፍረት “ችግር የለም” ለማለት ባልደፍርም . . . አይዞህ ትብብርን በተመለከተ በቅርብ ግዜ ሁላችንንም የሚያስደስት ዜና አብረን እንሰማለን አልኩት። ፈገግ አለና እሱን ከጨረሳችሁልን ሌላዉን ለኛ ተዉት አለኝና ይዞኝ ወደ ድንኳኑ ገባ።

ሐሙስ ነኃሴ 13 ቀን ጎህ ሳይቀድ ከእንቅልፌ ተነሳሁና ትንሽ ዞር ዞር ብዬ አልጋዬ ላይ ተመልሼ መጽሐፌን ማንበብ ጀመርኩ። ሁለት ምዕራፍ ጨርሼ ሦስተኛዉን ልጀምር ስል ከሩቁ ቡና ቡና ሸተተኝ። ቀና ብዬ ስመለከት ፍረወይኒ የቆላችዉን ቡና እስከነማንከሽከሻዉ ተሸክማ ልታስሸትተኝ ስትመጣ አየኋት፤ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ቁርስ ደረሰ እንዴ ብዬ ማንከሽከሺያዉ ላይ የሚንቦገቦገዉን ጭስ በእጄ ደጋግሜ ወደ አፍንጫዬ ሳብኩት። ‘ኡወ ቁርሲ ደሪሱ’ ብላ ፍረወይኒ የተቆላዉን ቡና ይዛ ወደ መጣችበት ተመለሰች።

ከጧቱ አንድ ሰዐት ከመሆኑ በፊት ቁርስ ተበልቶ አለቀና ሁላችንም ወደየተመደብንበት መኪና እንድንገባ ተነገረን። የሚጸዳዳዉ ተጸዳድቶ ሲጋራ የሚያጤሰዉም ሲጋራዉን ለምጦ ጉዞ ተጀመረ። ዬት እንደምንሄድ ወይም ለምን እንደምንሄድ የጠየቀም የተናገረም አልነበረም። . . . ዋ! ትንፍንሽ ብትሉ የተባለ ይመስል ሁሉም አፉን ዘግቶ ወደማያዉቀዉ ቦታ ጉዞዉን ቀጠለ። አንድ ሰዐት ያክል እንደተጓዝን . . . “እነዚያ ቤቶች ይታዩሃል” የሚል ድምጽ መኪናዉ ዉስጥ የሰፈነዉን የዝምታ ጽላሎት ሰበረዉ።አዎ ይታየኛል . . . ምን የምትባል ከተማ ናት ብዬ ቀና ስል ትልቅ ወንዝ አየሁ፤ ግን ወንዙንም ከተማዉንም ስለማላዉቃቸዉ ምንም አልተሰማኝም። እንድያዉም ፀሐይ ያጋለዉን ሰዉነቴን ለማቀዝቀዝ ወደ ወንዙ እንሂድ አልኳቸዉ። “ይቅርብህ እንደቀዘቀዝክ ትቀራለህ” አለኝ ከአጃቢያችን አንዱ። ከተማዉ ኦምሀጀር፤ ወንዙ ተከዜ፤ ከወንዙ ባሻገር የሚታየዉ ከተማ ደግሞ ሁመራ መሆኑ ሲነገረኝ . . . የምን ወንዝ መዉረድ እዚያዉ ቀዝቅዤ ቀረሁ። አደራ ቦቅቧቃ እንዳትሉኝ . . . አልፈራሁም አልደነገጥኩም። በእርግጥ እንኳን እንደዚያ ቀርቤዉ ከሩቅ ከባህር ማዶም ጠልፎ ሊወስደኝ የሚፈልግ ሰላቢ የነገሰበትን ምድር ሳላዉቀዉ እንደዚያ በድንገት መቅረቤ ትንሽም ቢሆን አሳስቦኛል። ይልቅ እንደዚያ ያፈዘዘኝና ገና ወንዙ ዉስጥ ሳልገባ ያቀዘቀዘኝ እናት አገሬን ኢትዮጵያን በ25 አመት ለመጀመሪያ ግዜ ማየት መቻሌ ወይም የእናት ኢትዮጵያ ናፍቆት ነዉ። ለነገሩ አገርም ሰዉም የሚናፍቀዉ ርቀዉ ሲሄዱ ነዉ። ዬኔ ናፍቆት ግን ልዩ ጭራሽ ልዩ ነዉ። አጠገቧ ቆሜ አገሬ ናፈቀችኝ። አዎ! መግቢያዬ ቀረበ መሰለኝ ኢትዮጵያ ስቀርባት ይበልጥ ናፈቀችኝ።

በቃ አንሂድ አለ ይዞን የመጣዉ የበላይ መኮንን . . . አዎ እንሂድ እንጂ ከዚህ በላይ መቆየት ለወያኔ ካልሆነ ለሌላ ለማንም አይበጅም አሉ ሌላዉ በዕድሜ ጠና ያሉ የበላይ መኮንን። እኚህ ሰዉ የወያኔ ስም ሲነሳ ደማቸዉ ይፈላል ፤ እሳቸዉ እራሳቸዉ እንደ ዳዊት ሲደጋግሙት ግን ምንም አይሰማቸዉም። ከሰዐት በኋላ ረፋዱ ላይ ሁላችንም ወደየመኪናችን ገብተን ኦምሀጀርን ለቅቀን ወደ ጀግኖቹ አገር ወደ ሀሬና አቀናን። ሀሬና አርበኞች ግንቦት 7ን፤የጋምቤላ ህዝብ ነጻነት ንቅናቄን፤ የአማራ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄን፤ የቤንሻንጉል ህዝብ ነጻነት ድርጅትንና ደምህትን ወላድ ማህፀንዋ ዉስጥ አምቃ የያዘች እርጉዝ ምድር ናት። እርግጠኛ ነኝ በቅርቡ ትወልዳለች።

የአስመራ ምፅዋ መንገድ እንደ ጥምጥም እየተጠመጠመ እየቀናና እየጠመመ ለረጂም ሰዐት የሚዘልቅ ያዋቂንም የልጅንም ቀልብ የሚሰልብ ሰላቢ መንገድ ነዉ። እግዚኦ . . . የከረን መንገድ በስንት መልኩ! ከአስመራ ምፅዋ መሄድ ማለት ከ2500 ሜትር ተራራ ላይ ቁልቁል ወርዶ ባህር ወለል መድረስ ማለት ነዉ። ትንፋሼን ቋጥሬ በቀኜ ገደሉን በግራዬ ተራራዉን እያየሁ ለሰዐታት ቁልቁለቱን ከተያያዝኩት በኋላ የቋጠርኩትን ትንፋሽ አዉጥቼ እፎይ ማለት የጀመርኩት ማይ አጣል ስደርስ ነዉ። ከማይ አጣል በኋላ ምፅዋ ድረስ መንገዱ ሜዳ ነዉ።

ምፅዋ ልንደርስ ትንሽ ሲቀረን ሆዴን ባር ባር አለዉ። የደስታ ይሁን የሀዘን ወይም የሲቃ አላዉቅም ብቻ ልቤ ሌላ ሌላዉን ሰዉነቴን ትቶ ደረቴ ዉስጥ ብቻዉን ይዘላል። “ዉስጥ እጄን ይበላኛል” ምን ሊያሳየኝ ይሆን . . . ይል ነበር የልጅነት ጓደኛዬ። ምነዉ እኔም እንደሱ ሆኜ ዉስጥ እጄን በበላኝ . . . ልቤ ደረቴን ጥሶ የሚወጣ እሰኪመስል ድረስ ደረቴ ዉስጥ ከሚዘል። አይፎኔን አወጣሁና ግራና ቀኙን አይኔ ያረፈበትን ቦታ ሁሉ ፎቶ አነሳሁ። ቦታዉ ዶጋሌ ይባላል. . . አዎ! ዶጋሌ . . . ጀግናዉ ራስ አሉላ 500 የጣሊያን ወታደሮችን ዶጋ አመድ ያደረጉበት የድል ቦታ። ለካስ ልቤ አለምክንያት አልዘለለም! ጣሊያን ዋና ከተማ ሮም ዉስጥ የአምስት መቶዎቹ አደባባይ የሚባል ቦታ አለ (ፒያዛ ዴ ቺንኮ ቼንቶ)። እመኑኝ እኛም አገር አይቀርም! ባንዳ ባንዳዉንና ልክ ልኩ ሲነገረዉ ደንግጦ የሞተዉን ምናምንቴ ሁሉ ትተን ሞተዉ ህይወት የሆኑልንን የትናንትናና የዛሬ ጀግኖቻችንን እናስታዉሳለን።

ምፅዋ ሁለት ቀን ብቻ ነዉ ያደርኩት – ቅዳሜና እሁድን። በጦርነቱ የፈራረሱ ህንጻዎች አሁንም አልፎ አልፎ ይታያሉ፤ ያም ሆኖ ምፅዋ ዉብ ከተማ ናት፤ ደግሞም አያሌ አዳዲስ ህንጻዎች ተሰርተዉባታል። የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ጠ/መምሪያ የነበረዉ ማዕከል ግን በጦርነቱ እንደፈረሰ ነዉ፤ ያየዉም የነካዉም ያለ አይመስልም።
እሁድ ነኃሴ 16 ቀን ከምፅዋ ተነስተን 45 ደቂቃ ከነዳን በኋላ ዊሃ ደርስን። ዊሃ ሌላዉ የአርበኞች መንደር ነዉ። ዊሃ ያለዉ አርበኛ እንዴት እንደተቀበልን ለመግለጽ አማርኛ ቋንቋ እንደገና “ሀ” ብዬ መጀመር የሚኖርብኝ ይመስለኛል። በዚያ የወፍ ማረፊያ በሌለበትና በየሴኮንዱ ዉኃ ዉኃ በሚያሰኝበት ንዳድ ዉስጥ ወታደራዊ ሥልጠና መዉሰድ ቀርቶ አንድ ሜትር መራመድም እጅግ በጣም ይከብዳል። እንግዲህ ይታያችሁ የኛዎቹ ጀግኖች እንደዚህ የምድር ሲኦል በመሰለ ቦታ ነዉ ወገኖቻቸዉን ከወያኔ መንጋጋ ነፃ ለማዉጣት እልህ አስጨራሽ የሆነ ወታደራዊ ሥልጠና የሚወስዱት። እኔም የኢትዮጵያን ህዝብ ከወያኔ ዘረኞች ለማላቀቅ እንደወያኔ 17 አመት ጫካ ለጫካ መንፏቀቅ እንደሌለብን ቁልጭ ብሎ የታየኝ ዊሃ ሄጄ እነዚህን የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ስመለከት ነዉ።

ሰኞ ነኃሴ 17 ቀን በጧት ተነስተን ጉርጉሱም ሄድን። ጉርጉሱም ቀይ ባህር ዳርቻ ላይ የሚገኝ ቆንጆ የመዋኛ ቦታ ነዉ። ቁርስ አዝዘን ሳንጨርስ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ መሪ አቶ ሞላ አስገዶም ከተፍ አለ። ታጋይ ሞላ በድንገት አልነበረም የመጣዉ፤ ልክ በቀጠሮዉ ሰዐት ነበር የደረሰዉ። አብሮን ቁርስ በላና እኛ ቀይ ባህር ዉስጥ ገብተን ስንምቦጫረቅ እሱ ማይ አጣል እንገናኝ ብሎ መኪናዉን አስነስቶ ከነፈ።

ከጥዋቱ 11፡30 ሲሆን ዋናችንን ጨርሰን የምፅዋ አስመራን መንገድ ተያያዝነዉ። ከምፅዋ አስመራ ጉዞ ማለት ሽቅብ ወደሰማይ የሚደረግ ጉዞ ማለት ነዉ፤ እንደኔ አይነቱ የዋህ ሰዉ ሰማዩን ደርሶ በእጁ የሚነካ ይመስለዋል ፤ ግን ሰማዩም ሞኝ አይደለም ደረስኩብህ ሲሉት ይሸሻል። ከቀኑ 12፡30 ሲሆን ማይ አጣል ደረስንና አስፋልቱን ትተን ወደ ደምህቶች ካምፕ የሚወስደዉን የኮረኮንች መንገድ ተያያዝነዉ። ወደ ካምፑ ስንደርስ ዊሃን፤ ሄሬናን፤ አምሀጀርንና ሌሎቹንም የአርበኞች ግንቦት 7 ካምፖች ስንጎበኝ ያየነዉ ፍጹም ኢትዮጵያዊ የሆነ የእንግዳ አቀባበል ተደረገልን። በነገራችን ላይ የደምህቶችን ካምፕ ስንጎበኝ ይህ የመጀመሪያችን አይደለም። ለእግራችን ዉኋ ቀረበልንና ነጠላ ጫማ ያደረገዉ ሁሉ እግሩን በቀዝቃዛ ዉኃ አራሰዉ። ቀዝቃዛ ዉኋ ለእግር ማቅረብ በሁሉም አርበኞች ካምፕና በበረሃዉ የኤርትራ ክፍል የተለመደ ባህል ነዉ። ከቀኑ እንድ ሰዐት ሲሆን ምሳ ቀርቦ እየተበላ ቡና ይፈላ ጀመር። ረከቦቱ፤ጀበናዉ፤ ማቶቱ፤ የከሰል ምድጃዉ፤ ፈንዲሻዉና የተደረደረዉ ስኒ በቀጥታ ወደ አደኩበት ሠፈሬ ፒያሳ ወሰደኝ። አዎ! ፒያሳ… የአዲስ አበባዉ ሳይሆን የአዋሳዉ ፒያሳ።

ቡናዉ እየተጠጣ ጨዋታዉ ሞቅ ሲል ቆየት ካሉት የጥላሁን ገሠሠ ሙዚቃዎች አንዱ ከሩቅ በለሆሳስ ተሰማኝ። በዉኔ ነዉ በህልሜ ብዬ ቀና ስል ነአምን ዘለቀ ጥላሁንን ከቴፑ ጋር አብሮ ይጫወታል። በህልሜ አለመሆኔን አወቅኩት። በሞት የተለዩን ድምጻዉያን የኛዎቹም የዉጮቹም ከላይ ከሰማይ ቢጫወቱልን እርገጠኛ ነኝ ጋላክሲዉንና ናሳ “Black Hole” እያለ የሚነግረንን ዬትየለሌ ክስተት አቋርጦ ከፀሐይ ብርሐን ቀድሞ እኛጋ የሚደርሰዉ ዘመን አይሽሬዉ የጥላሁን ገሠሠ ድምፅ ብቻ ነዉ። ይህንን ስሜት የሚኮረኩር፤ ጅማት የሚወጥርና አዕምሮን ሰብስቦ በትዝታ የሚያስዋኝ ዉብ ቃና ነበር ደምህቶች ሲያሰሙን የዋሉት። ብቻ ምን ልበላችሁ. . . ወበቅ የተቀላቀለዉ የምፅዋ ንዳድ ሳይቀር ለጥላሁን ገሠሠ ሙዚቃ ቦታዉን ለቀቀ። እኛም ወታደራዊ ትዕዛዝ የተሰጠን ይመስል የሁላችንም አፍ ተዘግቶ የሚንቀሳቀሰዉ እግራችን፤ ትከሻችንና ጭንቅላታችን ብቻ ሆነ።

“አልማዝን አይቼ እልማዝን ሳያት”፤ “እንጉዳዬ ነሺ” “አመልካች ጣት” “መሳቁን ያስቃል” . . . ብቻ ምን አለፋችሁ የጥላሁን ሙዚቃ ተዥጎደጎደ። ጥላሁን ገሠሠ አስመራ ላይ የሚጠብቀንን ቀጠሮ ብቻ ሳይሆን ጭራሽ እኛነታችንን አስረሳን። ቢበዛ አንድ ሰዐት ብለን የመጣን ሰዎች ከሦስት ሰዐት በላይ ከደምህት ጓዶቻችን ጋር ቆየን። በመጨረሻ የጉዟችን መሪ “አንድ ለመንገድ” ብሎ ከተቀመጠበት ተነሳ። እሱ ሲነሳ “እንክርዳድ እንክርዳድ የተንከረደደ፤ ስንዴ መስሎ ገብቶ ስንቱን አሳበደ” የሚለዉ ዘፈን እያለቀ ነበር። ነአምን. . . ነአምን ብዬ ስጣራ . . . “One for the road” ይቀረናልኮ አለ ነአምን . . . እንሂድ የምለዉ መስሎት። ይህንን ሙዚቃ እንደ እንክርዳድ ተቀላቅሎን ለሚያሳብደን የዳያስፖራ ቱልቱላ መርጫለሁ አልኩት። ሳቅ አለና ከቴፑ ጋር መጫወቱን ቀጠለ። እርግጠኛ ነኝ ተቦርነ በየነ ወይም መሳይ መኮንን አንድ ቀን “እንክርዳድ እንክርዳድን” በኢሳት ያሰሙናል። አይደል ተቦርነ?

በመጨረሻ የኛም መሄጃ የሙዚቃዉም መገባደጃ ደረሰ። “One for the road” የተባለለት ሙዚቃ (ዘፈን) ገና ሲጀምር ሰማሁና ኢችንማ አምላክ ነዉ የመረጠልን አልኩ በልቤ። ያ በቁሙ “አጥንቴም ይከስከስ” ብሎ ያስተባበረን ጥላሁን ገሠሠ አሁንም ከላይ ከሰማይ ቤት “ቃልሽ አይለወጥ እባክሺ….ን” እያለ ቃል እንድንገባባ አደረገን። ተራ በተራ ከአርበኛ ሞላ አስገዶም ጋር እየተቃቀፍን “ቃልሽ- አይለወጥ- አባክሽን” ብለን ተለያየን። ቃል የዕምነት ዕዳ ነዉ ብዬ ነበር የጀመርኳችሁ፤ አሁንም ቃሌ ይሄዉ ነዉ። ቃላችን አይለወጥ! ቸር ይግጠመን።
ኤፍሬም ነኝ ከአርበኞች መንደር

ሥህነ –ቤዛ! ቅኝተ –ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ! –ሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

28.08.2015 /ሲወዘርላንድ –  ዙሪክ/

ምዕርፍ አራት –  ዕርገት!

 

ሳይሽ እውላለሁ ከልቤ አስቀምጬ

ሳይሽም አድራለሁ እቅፍ አንተርሼ

አወሳሳሻለሁ አድርሽኝ ለብሼ፤

አነሳሳሻለሁ ፍቅር አንተርሼ፤

እመጣልሻለሁ ግንነት ደግሼ

እንደ ወጣሁ አልቀር አይቀር እንደ መሼ!

Birhanuእንዴት ናችሁ የሐገሬ ልጆች። የዚህች የሥንኝ – ቋጠሮ ዕርእስ „አድርሽኝ“ የሚለው መሆኑን በትህትና አሳስቤ ወደ ባለፈው ምዕራፍ ሦስትን የከውንኩብትን ትንሽ ከፍ ብዬ ላውሳ  „…. እናት ሐገሩን ኢትዮጵያን ጽላቱ እንደ አደረገ – ኖረበት። መታደል ነው። ዘመን የማይሽረው፤ ድንበር ያለወሰነው የእናትና የልጅ ንጡሕ ጡታዊ ሃዲድ፤ እትብታዊ ትስስር በፍቅራዊነት ክህሎት ሲመነዘር እናት ሆዱ ያሰኘዋል። የእትብት ጥሪኝ አንዲህ ረቂቅ ግን ብቁና ብልህ አስተዳዳሪነት ነው። እራሱን በዜግነት ፕሮግራም ወይንም ማኒፌስቶ ለመምራት የቻለ ዘላቂ ተስፋችን መምራት ስለመቻሉ ምስክሩ ተግባሩ ብቻ ነው። ያዬነው ከመሆን ተነስቶ ወደ መሆን ሲሄድ ነው።“ ለጥቄ ሳጠቃልለው ደግሞ እንዲህ ብዬ ነበር „እንደ ዘመኑ ታዳሚነታችን ያዬነው ወይንም የሰማነውን ወይንም ካነበብነው ያገናዘብነው፤ እሱን የተረጎምንበትን ሆነ ወደ ውስጡ ዘልቀን መክሊቱን ያደመጥነው ነገር ምን ሌላስ ይኖረው ይሆን? ወጣቱ መማር ያለበትን፤ መከተል ያለበትን ትክክለኛ መንገድ የማሳዬትን“ አስፈላጊነት በዚህ ልፋማ ዕይታዬ ነበር  የቋጨሁት።

ዛሬ ምዕራፍ አራትን እንደ ዕርገት ወይንም የወስጥ መሰብሰቢያ ዕልፍኝ ለማድረግ ሃሳቡ አለኝ።

ምዕታት ገድላቸውን – ሲዘክሩ፤ ታሪክ ሂደቱን – ሲመሰክር፤ ትናንት አደራን አቆይቶ በጥንቃቄ – ሲያስርክብ፤ ትውፊት ትውልዱን በውርርስ ቅብብል – ሲመረምር፤ ሐገር ዕንባውን ለዘመኑ ጥቁር አንበሳ – ስትልክ፤ የልዕልታችን የምጥ ጥሪኝ ምሬት ድረሱልኝ ስያሰማ፤ የጀግንነት ቀለማም አደራ ዝክረውን – ሲቀምር፤ ሰማይም ቅዕብዕውን ሲልክ – በስምምነት ረጋ ብሎ በአንድምታ – ሰከነ።

የኔታነት፤

የኔታነት የከበረ ጸጋ ነው። የኔታነት ፈጣሪ አምላካችንም የመረጠውና በምድር በነበረበት ጊዜም የተገበረው፣ የቅዱስ መንፈስ ምርቃት የተቸረው የዕውቀቶች ሁሉ መሰላል ነው። መምህርነት ከመንፈሳዊው ዓለም ወጥተን በገሃዱ ዓለምም ቢሆን ተግባር ቀለብ የሆነ የትውልድ ቀዳሚ ብቸኛ ተጠሪ፤ የከበረ – የደመቀ – ዕድሜ ጠገብ – ልምድ ዘለቅ – ምስጉን የንጋት አጥቢያ ኮከብ ሙያ ነው። መምህርነት የወላጃዊነት ፍጹማዊ መንፈስ – የረበበት፤ የኃላፊነትን ስሜት በቅንነት ፈቅዶ የሚቀበሉበት የሙያዎች ሁሉ እጬጌ ነው። መምህርነት ጥሩ አስተዳዳሪነት፤ ጥንግ የሥነ – ልቦና መክሊት ያለው የአንድ ሐገር የብቁ ዜጋ መሠረተ – ሟተት ነው።

መምህርነት ማሕበራዊነትን በተግባር የሚያነጋግር የግንኙነት መሥመርም ነው። መምህርነት የሀገርን ችግር ከሁሉ ቀድሞ የመጋራት ብቻ ሳይሆን መፍትሄ በማመንጨት በኩልም አንቱ የሆነ ሙያ ነው። መምህርነት የመመዘን – ውጤትን በዕውነት ላይ የመገምግም – ርትህን በሁለገብ መልኩ ዓይቶ እንደ ተፈጥሮው የመተርጎም፤ዳኘት አቅም ያለው የሙያዎች ሁሉ ዓፄ ነው። አንድ ለሙያው ኃላፊነት የሚሰማው ብቁ መምህር ትውልዱን በተገባው መልኩ ለመቅረጽ መነሻው እውነትና የዕውነት ጭብጦች ብቻ ናቸው ውስጥን የሚመሩት። ተግባሩን በጊዜ ሰሌዳ የሚመራ የትልም መሃንዲስ ነው። ብልህ መምህር ሊያስተምር ብቻ ሳይሆን ከተማሪዎቹም ሊማር እንደሚችል የተሰጠው መሆኑ ተፈጥሮን ቅጥ ባለው ሁኔታ መተርጎም ከመቻሉ ሚስጢር – ይቀዳል። ስለ መምህርነት ኃላፊነት ብቃት ጠቅላላ ገጽታ ስገልጽ ሟቹን ወላጅ አባቴን መምህሩንና የቤተመጻህፍት ባለሙያ የሆነውን አበይን፤ መካር መምህርት ታላቅ አህቴን – እትዬን በመንፈሴ ውስጥ ተጠዬቁ እያልኩ ነው። በእነሱ መዋለ ህይወት ያዬኋቸው ብርቅ ብልሃቶች፤ ጥልቅ የራስ መተማመን ጥሪቶቼ ሆነው እኔን ቀጥ አድርገው ያነጹኝ በመሆናቸው ዬተጠቃሚነቴን ጭማቂ ሰብላማነትም ጭምር ነው። ስለዚህ ምስክርነቴ ከህይወት እውነተኝነት ይመነጫል። ከዚህ ጋር አንድ ትልቅ አምክንዮ ሊነሳ ይችላል። ታዲያ ጠ/ሚር ኃይለማርያም ደሳለኝስ መምህር አይደሉም ወይ ልትሉኝ ትቻላለችሁ። እውነት ለመናገር ሳይፈቀድላቸው ነው ወደ ሙያው ዘው ያሉት ብዬ አስባለሁ። ከዚህ ጸጋ ጋር መሆን አይደለም ንክኪው የላቸውም። ስለሆነም እሳቸው ህይወታቸውን የሚመሩት በጀርባቸው ነው። ምን አልባትም በጀርባ መኖርን የመረጡ የመጀመሪያው ጠ/ሚር መምህር ሳይሆኑ አይቀሩም። በጀርባው የሚኖር ሰው ሲያነብም የወረቀቱን ጀርባ ነው። ሲናገርም የፍሬ ነገሩን ቅርፊት ነው። በጀርባ ነው ኑሮን ሲያነጋግርም ያው ጀርበኛ ነው። ጀርባና ጀርባ ደግሞ ገደል ይሆናል ዕጣቸው። ስለዚህ ያን ክቡር ሙያ አንዲህ ቀንጣ ከሆኑ ተማላ ግድፈቶች ጋር ማስታመም አይገባም ባይ ነኝ። የሆነ ሆኖ ዛሬ እናት ሐገሬ ኢትዮጵያ ብቁ መምህር ብቻ ሳይሆን ከእሷ ዝቀሽ ጸጋም የበለጠ ለመማር የፈቀደ የኔታ አግኝታለች። እልልታ …..

ብሄራዊ ነፃነቱ ርቦት ቀደም ብሎ ዱር ቤቴ ያለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ የነፃነት ተስፋ አርበኛ መምህሩን ብቻ ሳይሆን ተማሪውንም ሥህነ – ቤዛን አግኝቷል። ተማሪውን ብቻ ሳይሆን አባቱንም አግኝቷል። አባቱንም ብቻ ሳይሆን ለተሳትፎው ትክክለኛ ሚዛኑን አግኝቷል። የታደለው ሠራዊት በዬደቂቃው ከምምህሩ ከሥህነ – ቤዛ በግድፈት ያልባለቀውን ውባታም ጸጋዎችን እዬተመገበ፤ እሱ ያለውን የነፃነት ፍቅርና ዬተመክሮ ዕምቅ ሃብት እያጎራረሰው እንደ አባት አደሩ እቀና ፍቅርን – በአብሮነትን መኖርን – መማር – ማስተማርን በጋራ ለመጋራት ለድል ስምረት ደስ ብሎት፤ ዘና ብሎ – ተረጋግቶ – በሰከነ አመራር ለራዕዩ እንዲተጋ አምላኩ ስለፈቀደለት ድካሙ – ጥረቱ – መስዋዕትነቱ – ህልሙ ፍሬ ዘለቅ እንደሚሆን ባለተስፋው የአርበኝነት መንፈስ ተጋሪው ዬሚሊዮኖች ፈቃድ እንዲሆን ግድ ይላል።

ዬዕውነት መሪነት።

ጊዜን አድመጦ የተነሳው ብሄራዊ ፍላጎት፣ በተረጋጋ አያያዝ ከጅምሩ እስከ ዛሬ የደረሰበት ደረጃ ድረስ ልብ ሞልቶ ሊያናግር የሚችለው መሰረታዊ ቁም ነገር ከአርበኛው ጋር የተዋህደው መንፈስ ዕብለትን የሚጸዬፍ ሰብዕና ካለው ጋር መሆኑ ሌላው የድል ዋዜማ ነው። ድል ሲታሰብ በሃሰት ዲሪቶ ተጠቅልሎ ከሆነ ነገ ቢከፍቱት ተልባ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው። በሀገራችን ብሄራዊ ታሪክ ውስጥ የውሸትን – የግነትን ግንብ የናዳው የመጀመሪያው ሚዲያ የቀድሞው የግንቦት ሰባት ራዲዮ ነበር። ራዲዮው በምሥረታ ዘመኑ ተግቼ ሳደምጠው ነበር፤ መረጃ ሲሰጥ አንድ ሰው ከሆነ „አንድ ሰው፣ ጥቂት ሰው ከሆነ ጥቂት ሰው፣ ሁለት ሰው ከሆነ ሁለት ሰው“ በማለት ለእውነት ጥብቅና ሚዲያ ሲቆም በታሪካችን የመጀመሪያው ነው ማለት እችላለሁ። ይህ ለምን ሆነ? ሚዲያው ዕውነትን ከተቀበለ፣ ስለ ዕውነት ክብር ካለው፤ ስለ ዕውነት አሸናፊነት – ስለ ውሸት ተሸናፊነት የቀደመ ህሊና ይመራው ስለ ነበር ነው። ስለዚህ ነፃነት ራህቡ የሆነው የኢትዮጵያ ብሄራዊ አርበኛ እውነት አንደ ተፍጥሮው ዘመን ሸልሞታልና ፈጣሪውን ያመስግን። ዕውነት ዋስ፣ ጠበቃ፣ ጥግ፣ ነገም ሰለሆነ በዝንፈት መረጃ ከእንግዲህ የኢትዮጵያ ነፃነት የአርበኝነት ውሎ – አይታወክም። የእውነት ሁነኛ የሆነው አርበኛ ቅንጣት ታክል ዕብለትን የሞሸረ መሸማቀቅ አንደማይገጥመው በጣም በእርግጠኝነት መግለጽ እችላለሁ – ይህ ለዚህ ዘመን ልዩ ሥጦታ ነው። ነገም ሃሰትን የጀርባ አጥንት ያደረጉ ቦንዳዎች ሁሉ ሞሽሸው – ይሞታሉ፤ ከእንግዲህ በተዛባ – በዘበጠ መረጃ መታመስ ተቀበረ። ውህደቱ የኢትዮዽያ ውስጥነት ነው።

ርትህ – ፈላጊነት፤

ፍትህን የሚወዷት የእውነት አርበኞች ብቻ ናቸው። የፍትህ እጦት የህግ የበላይነት መጠለያ ማጣት ነው፤ ዛሬ የሚሊዮኖች ዕንባ ሁሉንም የመከራ ዓይነት መፈተኛ የሆነው ሃሰት ቀን ስለ ሰጠው ነው። ለነገሩ እራሱ ህወሓት ውሸት እኮ ነው። ነገር ግን በተለያዬ ሁኔታ ሥህነ – ቤዛ በተሳተፈባቸው መስኮች ሁሉ ፍትህ ፈላጊነቱ ከውስጡ ስለመሆኑ ተመልከቻለሁ። ስለዚህ ዛሬ አደራን በተቀበለው የታሪካችን ልዩ ምዕራፍ ህግን መሠረት ያደረገ ፍትሃዊ አመራርና አስተዳደር አርበኛው ወገኔ በቅርበት ስለሚያገኝ ሁለመናውን ለውስጡ ፍላጎት ለመስገዛት የሚጎትተው አንዳችም ኢ – ህጋዊ የሆነ ነገር አለመኖሩ፤ ማግስትን ጨምሮ የሚያሳምር የውበት ማክዳ ይሆናል የሚል ሙሉ ዕምነት አለኝ። ስለዚህም ተሳፋችን መሠረቱ ጥብቅ ማገር ያለው ነው – የማይነቃነቅ።

ውይይትን መድፈር፤

ቀደም ባለው ጊዜም ከፊውዳል ሥርዓት በፊት በነበሩት ሆነ ዛሬ የዐለም አስተዳዳሪ ውይይት ነው። ንግግር በፊውዳሉ ዘመን የህዝብ ንብረትነቱን ተነጥቆ የጥቂት የመሬት ከበርቴዎች ስለነበር  „ፊውዳሊዝም የንግግር የጨላማ ዘመን“ ይባል ነበር።ለማንኛውም ውይይት ዘመናችንም የፈቀደው ሰፊ የማህበረሰብ ሙሉዑ የተሳትፎ ማሳ ነው። ማናቸውም ችግሮችን በመፍቻነት መሳሪያ የሆነው ውይይት ነው። ውይይት የሥነ – ንግግር ዘርፍ ነው። ሥነ – ንግግር ሁለት አውራ ቤተሰቦች አሉት። አንዱ ተናገሪ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አድማጭ ነው። የሁለቱ አጋፋሪ ሃዲድ ደግሞ ውይይት ነው። በዚህ ዘርፍ እኔ እንዳስተዋልኩት ከአንድ ብቁ መሪ የሚጠበቀውን ተናጋሪነት፤ አድማጭነት፤ ውይይትን የመድፈር አቅም ያለው መሪ ብሄራዊ ሠራዊታችን አግኝቷል ባይ ነኝ። አንድ ጥሩ ተናጋሪ ሠራዊቱን ለግዳጅ ለማሰማራት ብቻ ሳይሆን የሰራዊቱን አቅለግዳጅ ለማሰማራት በሰው ሃይል በተከታታይነት በማደራት እረገድም አዲስ ሃሳብን ለመቀበል አለመሸሸት ወሳኝ ስለሆነ፤ ይህ ጸጋ ያለው ሥነ – ቤዛና እና ሠራዊቱ በመደማመጥ ላይ የሰከነ የድል ባለቤትነቱ አይቀሬ ይሆናል። ህይወቱ በበሰለ ውይይት ተቀምሮ ያዪሁት ስለሆነም አርበኞቻችን ጥሩ አድማጭነት ጥሩ ተዋጊነት ብቻ ሳይሆን ጥሩ አሸናፊነትም ነውና ከልባቸው ሆነው ሙሴያቸውን ያደምጡት ዘንድ በታላቅ አክብሮት – አሳስባቸዋለሁ።

ችግርን መጋራት፤

መቼም ጦር ግንባር ላይ ትልቁ መስፈርት ይመስለኛል አንድ ሙሴ የአካሎቹን ችግር፤ መካራን በመጋራት አብይ ድርሻ አለው ፤ ለዚህ ደግሞ ሥህነ – ቤዛ ተፈጥሮባታል። ይህን የምለው ያለምክንያት – አይደለም። አዲስ አባባ በማዕካላዊ ታሥሮ በነበረበት ጊዜ የቤተ – ኦሮሞ ወንድሞቻችን ምሬታቸውን ጮክ ብለው ሲገልጹ አዳምጦ፣ ከልቦናው አስተውሎ አሳሪዎቹን እባካችሁ እንዳወያያቸው ፍቀዱልኝ በማለት ጠይቆ ነበር። የሚገርመው እሱም እስረኛ ነበር። ግን አልተፈቀደለትም። የእስረኛ ወገኖቹን ብሶት በቅርበት ለማደማጥ ችግር ላይ ሆኖ እንኳን መፍቀዱ በማናቸውም ሁኔታ ችግር ለሚገጥም ወገን ቅርብ ስለመሆኑ፣ አጽህኖታዊ መምህርነቱን ጉልበታም አንዲሆን ስለሚያደርግ በፈተናችሁ፣ በችግራችሁ፤ በውስጥ ብሶታችሁ ሁሉ አብሮ ሊሆን የሚችል መሪ ማግኝት የሰው ሥጦታ አይደለም፤ ግልጽ ሆናችሁ በመቅረብ ውስጣችሁ የሚላችሁን – ንገሩት። በመከራ ዕንባ፣ በአሳር ራህብ ሲቀልድ ዬኖረው የህወሓት ዘመን ማክተሙን የምታዩበት ብሩህ ዋዜማ ላይ እንዳለን ይሰማኛል ለእኔ፣ የአምላካችን  የሥነ ስኬት መሳሪያውን እንዲህ ረቂቅ ጸጋዎችን ለማዬት የመንፈስ ጥንካሬ አዎንታዊ ጉልበት ሲኖረው ብቻ ነው።

ዬእናት ሆዱነት – ፊርማ።

እናት ሆድነት የሚመነጨው ኢትዮጵያን ጽላት ከማድረግ ይመነጫል። ሥጦታም ነው ሰማያዊ። ሁላችንንም የእኔ ብሎ መቀበል።ይህን ብሄራዊ ስሜት ያልተቀማ፤ ሁለመናውን የእናቱን ጠረን ያጣጠመ ብቁ ዜጋ የወገኖቹን መከፋት የእኔ ብሎ የመቀበል አቅም እንዲኖረው ያደርገዋል። ለዚህም የሃቅ (fact) መጸሐፍ ጸሐፊው ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና „የቃሊቲው መንግሥት“ መጸሐፉ ላይ ሥህነ – ቤዛ  ጠያቂ ለሌላቸው አዛውንታት እዛው እስር ቤት አብሮ በቃልቲ ታሥሮ ጉዳያቸውን በባለቤትነት ተረክቦ በአገኘው አጋጣሚ ሁሉ ዋስ በመሆን፤ ስንቅ ሊያቅብላቸው የሚችል ቤተሰብ የሌላቸውን ወገኖች ዬራሱን ስንቅ በማከፈል ብቻ ሳይወሰን መጸሐፉን „የነፃነት ጎህ ሲቀድ“ ሥጦታ ከባርከተላቸው አንዱ እኒያ አዛውንት አባታችን አንዱ እንደሆኑ ነው እኔ የተረዳሁት።

በዚህ የሰብዕዊነቱን ትልቅነት ዘመነ አራዊታዊ አስተዳደር ሲያከትም „ሰብዕዊነት“ ህጋችን – መተዳደሪያችን – ኑሯችን ሊሆን እንደሚችል ምልክቱ በብሄራዊ የነፃነት ሠራዊታችን ግንባታ መሰረቱን የሚጠለው በጭካኔ ላይ ሳይሆን „ሰውን“ አልቆ በተረጎመው ልዑቅ የዓለም ህዝብ ሁለመና ቋንቋ በሆነው „ሰው“ ከሚለው አምክንዮ ስለሚነሳ ነገ ብረሃን ነው። …. ውትድርና „ዬሰው“ ዘርን የሚያጠፋ ሳይሆን „ውትድርና „ለሰው ልጆች“ ተቆርቋሪ፣ ጠባቂ ተቋም እንዲሆን መንገዱ እዬተጠረገ ነው። … ይህ ለቀጣዩ ትውልድ ቋሳ – ገደል፤ ቂም – ገደል፤ ምህረት – አምንጪ፤ ፍቅርን – ከብካቢ፤ አብሮነትን – አንጋሺ አስከዛሬ ያልተጀመረ ወፍ ያወጣው አዲሱ መንገድ ነው። ….. ልናዬው የሚናፍቀን። ….. ልንኖርበት – የምንፈቅደው። ሰውኛ ጠርን ያለው። አዲስ ህይወት። ……. አንዳችን – ለሁላችን፤ ሁላችን – ለአንዳችን፤ እንደ ተፈጥሯችን ለመኖር የሚፈቀድልን፤ ፍንድቅድቅ ያለ ያልኖርንበት ግን አስኳሉ በሚያምር ሁኔታ የተጀመረ። ከዚህ ጋር በኢትዮጵያ መሬት በአካልም በመንፈስም በቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብዕዊነት ጉባኤ /ኢሰመጉ/ የነበረው በኽረ የተባ ተሳትፎም ውስጡ ምን ያህል ለስብዕዊነት ክፍትና ግልጥ ፣ ቀና፣ ቅን እንደሆነ የሚያሳይ ንጡር ፊርማችን ነው።

የበለጸገ የተመክሮ ክህሎት አውድማ።

ተመክሮ በልምድም በሙያያም በዕድሜም የሚገኝ የብስለት ዕሴት ነው። የሰው ልጅ በትምህርት ተቋማት ብቻ አይደለም ልምድን የሚቀስመው። ይልቁንም የሰው ልጅ ለመማር ፈቃዱን ለመንፈሱ ከሰጠ ከሁሉም መልካም ነገሮች መማር ይችላል። በተለይ አንድ ሰው በተፈጥሮ የአስተዳደግ ብድለት ወይንም የማንነት ችግር ከሌለበት ከሚያሳድገው ታናሽ የአብርክና የማህጸን ልጅም እንኳን በዬሰዓቱ ት/ቤት ከቤቱ ጀምሮ አለው። የመጀመሪያዋ የህይወት ት/ቤት እናት ናት። ከዚህ ላይ ነው ሚስጢሩ ያለው። ሥህነ – ቤዛ  በአደገበት ቤተሰብ ገና ከውጥኑ በእውቀት መጎልመሱን የምታዩት ገና ት/ቤት እያለ ነበር የተማሪዎችን ውክልና ያስገኘው። ያ „ሀ“ ብሎ የቅብዕ ተመክሮው የተጠነሰሰበት ዓውደ – ማሳ ነበር። ከዚያ በኋላ በሀገር ውስጥ ሆነ በውጪ ሐገር የተሰማራባቸው የሥራ መስኮች፤ ውይይቶችን በመምራት፤ በሽምግልና ንቁ ተሳትፍ በማድረግ፤ አስታራቂነት-  በአስማሚነት ነጠላና ድርብርብ፤  ወላዊና ግላዊ የፖለቲካን ችግሮችን ሳይገፋ ልክ እንደ ወለደች እንደ እናት እጅግ አስጠግቶ ያዪባቸው ፈሊጦቹ ማግኔቶች ናቸው። ኃላፊነትን ሳይሸሽ – አጋጣሚዎችን ሁሉ ለተሳትፎ መፈቀዱ፤ የደረጀ ተመክሮውን ሁለገብና ሰብላማ እንዲሆን አድርጎታል። ይህ „ሁለገብ“ የትግል ስልት ሚስጢሩ ዝልቅ ነው። ይህ የዳበረ ልምድና በከፍተኛ ዩንቨርስቲዎች፤ በብሄራዊ ሐገራዊ የፓርቲ ምስረታ አዲስ ሃሳብ አስገኝነቱና የክንው ሂደቱ ጥሩ አዳማጭ ከሆን ምን አንዳለው፤ ምን እንደሚፈልግ፤ ምን እንደሚችል በተጨባጭ – አሳይቶናል። ዕውቅት ላይ የተመሠረ ብቃቱ፤ በተመክሮ የዳበረ ክህሎት፤ ተግባር ጠገብ በመሆኑ ለብሄራዊ የነፃነት አርበኛችን የቀና መንገድ ይሆነዋል። በአግባቡ በታነጸ፣ በተደራጀ መንፈስ ውስጥ ነገንም አሳምሮ መተመን ያስችላል። እውነት ለመናገር ውጤቱን ለመተንበይ ነብይነትን አይጠይቅም።

የሠራዊት ሥነምግባር

ሥነ – ምግባር በብዙ መልኮች የተለያዩ ገጽታዎች አሉት። እራሱን ያሸነፈ በዬትኛውም የሥነ – ምግባር ዓይነቶች ለመተዳዳር በህግጋቱ ወይንም በደንቦች ለመተዳደር ዝግጁ ነው። የውትድርና ሥነ – ምግባር ደግሞ ጠብቅ ያለ በመሆኑ በዚህ ሙያ ላልነበሩ ወገኖች ሲጀመር ከበድ ሊላቸው ይችላል። ነገር ግን ለሥነ – ቤዛ ወጣትነቱን በርሃ ላይ በኢህአፓ ጋንታ ውስጥ ተሰልፎ የሠራ በመሆኑ፤ የነበረውን ልምዱ ዘመኑ ከሚፈቅደው ከሙሉ ዕድሜ ጋር ይታደስለት እንደሆነ እንጂ አዲሱ ስላልሆነ፤ በሥነ ምግባሩ ውስጥ የኖረ ስለሆነ የልምድ ልውውጥ የሽግግር ጊዜ ሳያስፈልገው በቀጥታ ተግባር መስመር ላይ ለመግባት ይቀለዋል። ከዚህ ጋር ላስውሰው እምሻው ትልቁ ቁም ነገር ወጣት ሳለ ኤርትራመሬት ላይ  ከተሰጠው ምርጫ አንዱን መርጦ የዕውቀት ባለጸጋ እንዲሆን፤ ሌሎች ልምዶችን እንዲያካብት ወደ ሱዳን መሻገሪያ የነበረችው መሬት ስትሆን ዛሬ በጉልምስናው ደግሞ ብሄራዊ ሃላፊነቱን ይወጣ ዘንድ እጇን ዘርጋታ የተቀበለችው የተከደነ ሚስጢር የሚቀናባት መሬት መሆኗ ነው። ለሥህን – ቤዛ የኤርትራ መሬት አዲሱ አይደለም። ትናንት ነበረበት። ወደ ሱዳን ከመሄዱ በፊት ኖሮባታል። በርሃ ቀመስ አዬሯን ቀድሞ – አጣጥሞታል። ወዙም ናት። ከዛ በኋላ ነው ወደ ሱዳን ያቀናው፤ ዛሬ ደግሞ ከአሜሪካ ወደ ኤርትራ እንዲህ መንገድ ሲዘረጋ ፈጣሪ አምካላችን ምን ይሆን ያሰበው? ይንፍቀኛል ይህ ሚስጢር ተትርጉሞ ተመሳጥሮ በሥነ – ጥበቡ የማይበት።

የቤተሰብ ሃላፊነት በመቀበል መብቀል።

ቤተሰብ የማህበረሰቡ መሰረት ነው። የአንድ ማህበረሰብ መነሻ የሆነው ቤተሰባዊ አስተዳደር በሀገር ግንባታ ላይ እጅግ መሠረታዊ ጉዳይ ነው። አንድ ብቁ የቤተሰብ መሪ ሌላውንም ለመምራት መሳሪያው በማዳፉ ነው። ሥህን – ቤዛ ባለትዳርና የልጆች አባት መሆኑ፤ በሠራዊቱ ውስጥ ያሉትን ከቤተሰብ ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ጉዳዮች በፈቃደኝነት ለማስተናገድ በሩ ክፍት ነው። ሠራዊቱን እንደ ቤተሰቡ የማዬት አቅሙም እዮር ነው። ሠራዊቱ በቤተሰቡ ጉዳይ ለሚያቀርበው ጥያቄም ብቁ አድማጫቸው ይሆናል። ሁሉንም ለመጋራት ስንዱነቱ ወግ ያለው መስመር ነው። ከዚህ ጋር በምንም ሁኔታ ኑሮው ጥገኛ አይሆንም። በዘመናይ ኑሮው በኃላፊነት ቤት ውስጥ ተግባር ላይ የተገኘበት ልምዱ ሠራዊቱ በድንቅነት የሚማርባቸው ት/ቤቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ ሙሉ ዕምነት አለኝ።

ናፍቆትን መጋራት – በተመሰጦ።

ናፍቆት ብትፈልጉትም ባትፈልጉትም የማይለቅ የመንፈስ ሞጋች፤ አዛዥም ናዛዥም ሥነ – አምክንዮ ነው። የሚፍቅ ሰው ጠረኑ „ሰውኛ“ ነው። የሚናፍቅ ሰው ፍቅር ነው። የሚናፍቅ ሰው የእኛ ነው። ናፍቆት የውስጥ ነው። ስለሆነም ረቂቅ ነው። ረቂቅነቱን አብራርቶ ለመግለጥ ቢቸግርም ናፍቆት ፍቅር የያዘው ሰው እንደሚያብተከትከው መላ ቅጥ – ያሳጣል። አንዳንድ ጊዜም የህመም ስሜትን ያስከትላል ግን ህመሙ ሥም የለሽ ነው። ናፍቆት ልትሸሸው የማትችል የምትወደው ሆኖ የማታገኘው ስትሆን ግን ብስጩ የሚያድርግ ነው። ሀገሩን የሚወድ ህዝቡንም ከልቡ ውስጥ – ይወዳል። ሀገሩን የሚናፍቅ ህዝቡንም ከህሊናው – ይናፍቃል። ናፍቆቱን ለማወራረድ አጋጣሚውን ሲያገኝ ደግሞ ለእሱ የሰማይ ገነት ነው።

ሥህነ – ቤዛ የኤርትራን መሬት ሲረግጥ አቀባባል ያደረጉለትን ወገኖቹን ሲያገኝ እንዲት እቅፍ አድርጎ እንደያዛቸው ፎቶውን ደጋግማችሁ – መርምሩት። እዩት – አስተውሉት። አዳምጡት – ማህበራዊ ሚደያ ላይ ስላለ – በትህትና ። እንደዛ ጥብቅ አድርጎ፣ እንደዛ ጥግት ብሎ የሀገሩን ወዝ ሲጣጣ ተመልክተናል። ስለዚህ ራህብን የሚያውቀው የተራበው ስለሆነ፤ ናፍቆትን የሚያውቀውም የናፍቆት ጉጉተኛ ስለሆነ፤ የሠራዊታችን አባላትና አካላት ላለባቸው ብሄራዊ፣ ቤተሰባዊ፣ ወገናዊ፤ ነፃነታዊ የናፍቆት ረሃብ ቅርባቸው አንደሚሆን ያ ፎቶ አሳምሮ ለሥርጉተ – ነግሯታል። እግዚአብሄርንም አምስግናበታለች። በሁኔታው ሁሉ ተሸብሬ ቢያስለቅሰኝም ግን ሻማዬን አብርቼ እናት ሀገሬን ከነሁለመናዋ በምልሰት – ቃኝቼበታለሁ። እኔም የሀገሬን የኢትዮጵያ ትዝታ ተሳለሜበታለሁ። አብሶ የገጠሩን አርሶ አደር ናፍቆት ለእኔ ልዩ ጌጤ ነውና፤ የሐገሬን የኢትዮጵያ ገበሬዎችንም ከምንም ከማንም በላይ እወዳቸዋለሁ።

የገበሬው ኑሮ ሥነ – ደንብ የእኔነቴ ሰነድ ነውና – ዕንባዬ በተፈጥሯዊ ሁለቱ መስኮቶች እዬለቀኩኝ ናፍቆቴን አወራርጄበታለሁ። ስለዚህም የምትፈልጉትን፤ በውስጣችሁ የምታልሙትን፤ በዕውን መሬት ላይ ሆኖ ስታዩት ሐሤት ነው። ዕንባን አምላክ – ያዳምጣል። ሰጠን! እኔ በሂደቱ ሁሉ እጅግ – ተማርኬያለሁ፤ ተመስጫለሁ፤ መንፈሴ ሁሉ – ረግቶልኛል። የብሄራዊ ነፃነት ናፍቆት ምርኮኛ ነኝና። ፈተናን እረቶ የወጣ ንጥር ቀለም በቦታው ተገኜ።

ዬሃሳብ ነፃነትን – መፍቀድ።

ነፃ ማሕበረሰብ ህልማችን ነው። አዲስ ሃሳብ ለማፍለቅ የሚችሉ ወገኖች በባዕታቸው ምን ያህል እስረኛ አንደሆኑ ከልቡ ሆኖ ያዳማጠው ሙሴ በሀገሩ በኢትዮጵያ በተገኘ ጊዜ የሃሳብ ነፃነት መታሰርን በተለያዩ አንግላት ውስጥ ሆኖ ከልቡ መርምሮታል። ዬነፃነት አስፈላጊነት በሚገባ ውስጡን ዘልቆ መጎብኘት ብቻ ሳይሆን፤  ባገኘው አጋጣሚ፤ በጹሑፎቹ፤ በመመጣጥፉ በቃለምልልሱ፤ በኢህአፓም በነበረበት ጊዜ ለእስር የዳረገው ይሄው መሆኑን – ተርድቻለሁ። በተሳተፋባቸው የውይይት መድረኮች፤ ፓናል ዴስከሽኖች፤ የአወያይነት – ዕድሎች፤ ፓለቲካዊ ክርክሮች (ሙግቶች) ሁሉ ተጠዬቅን የመፍቀድ አቅሙ ውስጡን በግልጥ ማዬት አስችሎኛል። ስለሆነም ለነፃነት ሁለገብ ተፈጥሮ ሐዋርያ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ስለዚህ ለሃሳብ ነፃነት ራሱን ያሰናዳ ብቻ ሳይሆን፤ ቀዳሚ ተሟጋችነቱን ሥራ ላይ ለማዋል በቅርበት በአርበኛው ውስጥ መገኘቱ፤ ካለምንም እንቅፋት በሠራዊቱ ውስጥ ሃሳብን ያለ ተዕቅቦ ማንሸራሸር – ያስችላል። ስለዚህም የሠራዊቱ አባላት የሚሰማቸውን፤ ይጠቅማል የሚሉትን፤ ያወጣል የሚሉትን ሳይሸማቀቁ፤ ሳይሰጉ ያለምንም ገደብ የሚገልፁበት አጋጣሚው ሰፊ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፤ ይህ የመጀመሪያው ዬሃሳብ ነፃነት ት/ቤት የመሆኑ ዕድሉም ሰፊ ይሆናል ብዬ አስባለሁ። ሰው እራሱን መግለጽ ሲችል ውስጡን ማዬት ይቻላል። ውስጡን ማዬት ሲቻል ደግሞ ለመምራት ሆነ ለማስተዳደር ቀና መስመር ተገኘ ማለት ነውና፤ መክሊትና ምኞት አኃታዊ ጋብቻ ይፈጽማሉ ብዬ አስባለሁ። ይህ በራሱ የበላይነት እዬሞሸሸ፤ የበታችነትም በአዲስ መንፈስ እያቆጠቆጠ መሃል ላይ የመደማመጥ ባህል መባቻ ዕውጃ ክ/ጊዜ ይሆናል። ነገም ሳይታፈን እንደ እድገቱ እንዲበቅል ይለፍ – ይኖረዋል።

አጽህኖት

ተፈጥሮ ብዙ የምትልገሰው ነገር አላት። የሰው ልጅ ማህበራዊ አንሰሳ ነው የሚበላው ኑሮውን የሚመራው በማህበራዊ ሁነቶች ስለመሆኑ ለማገናዘብ ነው። ማህበራዊነት የወልዮሽ ገብታ ነው። የወልዮሹ ሌማት በፖለቲካ ዕሳቤ ሲዘምን በግል ኃላፊንትና በጋራ አመራር ላይ የተመሠረተ ይሆናል። በዚህ የአደረጃጃት ሂደታዊ መዋለ ጉዞ ቀደም ባለው ጊዜ ግንቦት 7ን ሳስተዋለው አጽህኖት ያለው ስልጡን አመራር አንደ ነበረው ነው። እኔ በንቅናቄው መሪ አካላት የብቃት ድልድል፤ የምርጫ ስምሪት ልዩ የሆነ የጸደቀ መንፈስ አይቸበታለሁ። ኮሽ የሚል ነገር አይደመጥም። አፈንግጦ የሚወጣ የሥነ – ምግባር ግድፈት – አይታይም። አልፎ ተርፎም የሌላውን ደንበር የጣሰ የሥነ – ምግባራ ጉዱፍ ቅንጣት የነቁጥ ያህል – አልታዬበትም። ፍጹም የተረጋጋ፤ በውስጡ ሰላም ተጠቃሚ፤ በተሰጠው ጸጋ አቅሙን የገነባ ንቅናቄ ሆነ ነበር የማዬው። እንዲያውም ከውስጤ ሆኜ ስለምከታተለው የቤተሳባዊ አቀራረብ አያያዙ አመዝኖ አይቼዋለሁ።

የችሎታው ትኩረት ብቁነት ዓላማን ለማሰካት ባለ ልዩ ብቁነት፤ አቅል ያለው – ብልህነት፤ የቁርጠኛ ሃሳብ – ቤተኝነት፤ የአውንታዊነት ጣዕምና ለዛ፤ ጊዜን የመተመን – ስልታዊነት፤ ጠንካራ – ሰራተኝነት፤ የወራት ቅደም ተከተልና ለቀድመው ልዩ አጽህኖት መስጠትን፤ ሌሎችን ለመሳብ ሆነ ለማነሳሳት እንዲሁም ለማንቀሳቀስ ያስቻለው ልዩ ተስጦዕው ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ከሁሉ በላይ ወደፊት ለማዬት ያለው አጽህኖት ዘመን አሻጋሪ  – አድርጎታል። ራሱን ሳይሸሽ ፈተናን እዬረታ ወደ ፊት መገስገሱ የድፍረቱ ልክ በእጁ ካለው ሙሉ አቅሙ የሚቀዳ ስለመሆኑ ምስክሩ ተግባሩ ነው። ራዕዩን በማካፈል ወይንም በማጋራት ረገድም ቆጥቋጣ – አይደለም። ስለሆነም ነው በፖለቲካ አመራሩ አጽህኖታዊ ብቃት ተፏካካሪነቱ ሆነ ተደማጭነቶ ነጥሮ በመውጣት ጉልበታም መሆኑ ለጠላትም ለወዳጅም የማይነቃነቅ ብረት መዝጊያ መሆኑን ያስመሰከረው። ለዚህም ነበር እኔ በግሌ በዬአጋጣሚ የሚነሱ ወጀቦችን ጥሼ በመግባት የውትድርና ወይንም የዘበኝነት ተግባር ስከውን የኖርኩት። ለእኔ የተግባሩ ሂደት ምላሽ የሚሰጠኝ የዲሞክራሲ ባህሉ በማዕካላዊ አመራሩ አድጎ የጎለመሰ ስለመሆኑ ከመነሻው ነበር የተገነዘብኩት። „የሚያድግ ጥጃ ከገመዱ። በአያያዝ ይቀደዳል በአነጋገር ይፈረዳል“ እንዲሉ። ዓላማውን በአውሮፓ ሲያስተዋውቅ የጻፍኩት መጣጥፍ  „ሽልማታችን“ ይል ነበር። ሁለተኛ ሂደቱንም „ወርቅ ያነጠረ ብረት ያቀለጠ“ የሚል እርግጠኛ የሚያደርግ እርምጃ ነበር የወሰድኩት ዛሬ ላይ ሁኜ መጣጥፎቹን ሳነብ – ይገርመኛል። ምክንያቱም ጥርት ያለው የአደረጃጃት መሰረቱ ገና ከውጥኑ ብልሃቱ ያናግር ነበር። ትርምሳዊ ወጀቦችን ኬላ የሠራላቸው በማንፌስቶ ላይ ነበር። ሁለቱንም የፁሑፎቼን ሊንኮች መጨረሻ ላይ እለጥፋቸዋለሁ። ዛሬም አጽህኖት መገብ ሂደቱ ለተስፋ እውነተኛ ጽኑ አርበኛ እንዲሆን አድርጎታል። አጽህኖታዊ ጉዞው ለራዕያችን የትውልድ ያህል አስተማማኝ ነው ማለት እችላለሁ። መሪ ያለው ፍላጎት ዛሬን ያኖራል። ነገን – ያስገኛል። ከነገ ወዲያንም ይገራል – በአጽህኖት!

እንቅልፍ አልቦሽ – ገድነት

ገድ ለመንገድ ልዩ ዕድል ነው። የነቃ መንፈስ ሲፈጠር እንቅልፍን – ይጸዬፈዋል። ተኝቶ መኖር ክፍሉ – አይደለም። የነቃ መንፈስ ተስፋ ቆራጭነት ተዋሽም አይደለም። የነቃ መንፈስ ሽንፈት መንገዱ – አይደለም። መዳፍ የሚስቀድመው መንፈስ ሁልጊዜም ትጉህ  – ታታሪና ባተሌ ነው። ተግባር ባለበት ሁሉ የተግባር ገበሬ ሰብላማ ነው። ሳተናው – ዓላማ ያለው ስለሆነ ታክቶ የሚተወው አንዳችም ነገር አይኖረውም። መጀመሪያ በበር ይጀምራል። በሩ ሲዘጋ በመስኮት። መስኮቱ ሲዘጋ በጣሪያ፤ ጣሪያው ሲዘጋ ደግሞ በምድር በታች። ሁሉንም ዓይነት ነገር በሁለገብ ይሞክራል – ራዕዩን በድል ያሰክናል። ከሥህነ – ቤዛ ያዬነው ይህን ነው። በተፈቀደለትም – ባልተፈቀደለትም፤ በተወደደለትም ባልተወደደበትም፤ ይለፍ በተሰጣውም ይለፍ በተከለከለበትም መንገድ ሳይተኛ ይልቁንም በጠንካራ መንፈስ ቀጠለ — ቀጠለ —- ቀጠለ ዕድለኛ ነው የልብ አድራሽ አጋርም አላጣም። አይዞሕ ባይም አልተነፈገም፤ ይሔው በዚህ ቀጪ የህወሓት ፋሽስታዊ ዘመን የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሆን የሰጠው እንቅልፍ አልቦሽነቱ ነው እላለሁ – እኔው። ይቻላል እንደ ገና አንደ ገና – ከተመኮረ። ከዚህ ብዙ የምንማርበት የተምሳሌት፤ የአብነት ሰብሎች አሉ። በተለይም ወጣቱ እኔም እንደሱ …. ማለትን፤ ሞዴላችሁ – ተምሳሌችሁ ገድም ነውና። መንፈሳችሁን ሳትሰስቱ ቀልቡት ለእናንተው ነው የሚታክተው ነገን ለመውለድ። ድምጹን ሩሃችሁ አድርጉት።

ዕድልን አለማሽሎክ

ብዙ ሰው ለዚህ ተጠቃሚ አይደለም። እንዲያውም ዕድሉ ካለፈ በኋላ እንኳን ዕድሉ ስለመኖሩ ማስተወስ እንኳን የማይቻልበት ብዙ ገጠመኞች አሉ። በዚህ ዘርፍ ሥህነ – ቤዛ በጣም በሠለጠነ አኳኋን ዕድሉን ሁሉ – ተጥቅሞበታል። ሁልአቀፍ ችሎታው – ሃይሉ ሆነ ብርታታቱ የተቀዳውም ከዚኽው ነው። ዝልቅ ፍላጎቱን – ዘለግ ያለ ራዕዩን ለማሳካት ታላቁ መሳሪያው የሚያገኛቸውን ዕድሎች ጥቃቅኖች ናቸው ብሎ ሳይንቅ በሚገባ ተጥቅሞባቸዋል። ግዙፎችንም ከነፈተናቸው የመሸከም አቅሙም አንቱ ነው። ይህ ፍጹም ረቂቅ የሆነ ጸጋ ለሁላችንም ተቋም ሊሆኑ የሚችል – ይመስለኛል። ስዋሰው።

ትልምና ግብ

ትልም ህልም ስለሆነ ሁሉ ሰው ሊኖረው ይችላል። ቁምነገሩ ለትልሙ ስኬት መንገድ መምረጥ፤ ሂደቱን አስቀድሞ በርቀት መተንበይ ከመቻሉ ላይ ነው። ይህን ሥህነ – ቤዛ በሚወጥናቸው አዳዲስ ትልሞች፤ በሚሳተፍባቸው አዳዲስ የተግባር ማሳዎች በጋራ የመሥራት መርህን ዕውን ለማድረግ ከማን ጋር ነው የምሥራው? የሚለውን ቀድሞ ጊዜ ወስዶ እልባት የሚሰጥ ብልህ ሰው መሆኑን እኔ በግሌ – ተገንዝቤያለሁ። ዝም ብሎ አቅሙን አያባክንም። የሁለመና የስሌት ቀመሩ ዝንጥ ያለች ሌሊኛ – ሥልጡን -ሞድኛ ናት። ማማከር ይወዳል – በጥንቁቁነት። በግል ህይወቱም ቢሆን ፈተና ያለባቸውን አቅጣጫዎች ሁሉ ደፍሮ የመጀመር አቅሙ ድጋፍ የሚያገኘው ከቤቱ ከትዳር አካሉ ጀምሮ ነው። ይህ የምርጫውን ጥራትና ብቃት አሳምሮ – ይተረጉምልናል። እሱ አብዝቶ ጊዜ በሚሰጥባቸው ማናቸውም ጉዳዮች የቤተሰቡን ጊዜ በእጅጉ ይቀናንሳል፤ ያጎሳቆላል፤ ባለፈም ጥቃትም ያደርሳል። ነገር ግን ስሌቱ የነብይነት ያህል ስለሆነ ዬስኬቱ ፍሬው ዝቀሽ ነው። ያካክሳል። ድፍረቱ አቅምን የለካ ብቻ ሳይሆን የወቅት ሥጦታዎችንም – ያብራራ ነው። ስለዚህ አሁንም ይህን የመሰለ እርምጃ ሲወስድ በግልብ አስቦ በጥድፊያ ተልሞ የከወነው አይደለም። ምክንያቱም ካለፈበት የህይወት ተመክሮው ሁሉ እራሱን የማድመጥ አቅሙ የፀሐይ ብርሃን ያህል ጉልበት አለው። እርምጃው ሳቢ፣ ሌሎችንም በቀጥታ ወደ መንገዱ – የሚያስገባ፤ ሌሎችን በፍቅር የሚነሳሳና የሚያሳትፍ ግልጽነት – ቀጥተኝነት በተጠያቂነት ያጌጠ መንገድ ተከታይ ነው። ……

መርኽ

የጋራ ሥራ ሁነኛነት መለኪያው የመርኽ ሰውነት ነው። መርኽ የሚነሳው እራስን ከመግዛት፤ እራስን ከማስተዳደር፤ እራሰን ከማቅ ነው። በሂደቱ ጉስቁል የሚያድርጉ ገጠመኞች ሊኖሩ ቢችሉም የመርኽ ሰው የመርህ ተፈጻሚት በራሱ ላይ ሲሆን አደላድሎና አስመችቶ የመቀበል አቅሙ ነው የመርኸው ሰው የሚያሰኘው። የሰው ልጅ በግል ህይወቱ ህይወቱን የሚመራበት ደንበር ሊኖረው ይገባል። ያን ደንበር ጥሶ እንዳይሄድ የሚያደርገው መርኽ አክባሪነቱ ነው። በማናቸውም ሃይማኖታዊ፤ ባህላዊ፤ ሙያዊው፤ ፖለቲካዊ ተሳትፏዊ፤ ሃላፊነታዊ፤ ወላዊ ጉዳዮች ሁሉ በአባልነት እራሱን ሲያስመዘግብ ማዕቀፉ አስተዳደሪው ውል ያሠረበት መርኽ ይሆናል። በዚህ መሥፈርት እንደ ሌሎቹ የቁም ነገር መስኮች ሁሉ መርኽ ይከበር የመጀመሪያው ቀዳሚው የሥህነ – ቤዛ የፊደል ገበታው መሆኑን በሚገባ – ተገንዝቤያለሁ። ለዚህም ነው እላፊ ሄዶ የሌላውን ድንበር ሲጥስ የማይታዬው። ይህ ሥህነ – ምግባር በኃላፊነት የሚመራቸውን ድርጀቶችም ከተመልካች ጠረባ አድኖታል።

ሌላው በመርኽ አልተገዛም ብሎ የመወቅስ አንድ ሰው እሱ በዛ መርኽ ውስጥ መሆኑን ማረጋጋጥ አለበት። አንድ ሰው መብቱ በአደባባይ ተረገጠ ብሎ የሚጮኽ ሰው ለዛውም ለረጋጮች ተራጋጭ ጥብቅና የቆመ ሰው፤ ለሌላው የሚሰጠው የሰውነት ክብርም በማዋረድ፣ በማንቋሸሽ፤ በሳቅና በስላቅ መሞሽር፤ በማጣጣል ማንቆጥቆጥ – አይኖርበትም። ለዛውም ቁጥር ሥፍር የሌላቸው አንቱ አቅም ያላቸው ደጋፊዎች ላሉት፤ የጋራ ጠላት ወያኔ ያሰረው – በሌለበት ሞት የፈረደበት፤  ያ ሰው ልኩም ደረጃውም አቅሙም ከፍ ያለ ሆኖ ፤ የበዛ ተቀባይነትና ተደማጭነት ያለው፤ ህወሓት ጠላቴ ነው ባዩ ወገኑን አውርዶ ሲጠቀጥቅ ለመርኽ ተገዥነቱን ታዛቢዎች ውስጡን እንዲለኩ፤ ስዕላቸውን እንዲያስተካክሉ ገልጦ አስርክቧል ማለት ነው። አብሶ ተምሬያለሁ በሚለው ወገን ከሆነ ግድፈቱ የሚፈጸመው የእኔ ማህይምነት በስንት ጣዕሙ ትላለች – ሥርጉትሻ። እድገት ወደ ላይ እንጂ ቁልቁል ሲሆን፣ አጋጣሚዎች ሁሉ መክነው ሲታዩ፣ ለትውልድ የውርዴት ት/ቤት ናሙና ለመሆን እራስ መፍቀድ ስለሆነ፣ ጸሎት ያስፈልገዋል። የሆነ ሆኖ የመርኽ ሰውነቱ ፍሬ አዘል ሰብል ገብ የሆነው ሥህን – ቤዛ በመርኽ ምሰሶነት የነገ የድህነት አብይ መንገድ ነው። የመርኽ ሰውነት የሚያስከብረው እራስን ብቻ ሳይሆን ሐገርንም ጭምር ነው። በግድፈቶች ልክ ሀገር ትወቃሳለች፤ በመልካም ነገሮች ልክም ሀገር ትከብራለች። ቀደም ባላው ጊዜ ሐገራችን ኢትዮጵያ ጎልታ የምትታይ ተፈሪ – ተከባሪ ሐገር ነበረች። የመርኽ ልጇቿ አንቱ አሰኝተዋታል። ዛሬም ጥሪያዋ ይኸው ነው። የሐገር ፍቅር የሚባለው መጀመሪያ ራስን በመርኽ ማስገዛት ነው። አብሶ ያልተጻፈው ህጋችን ከዩንቨርስቲ ምርቁነት በላይ – በላይ ነው። ልብ ይስጠን።

ድምዳሜ

ለእኔ ፎቶ ብዙ ነገር – ይነግረኛል። ለእኔ ጹሑፍ ብዙ – ያስተምረኛል። ለእኔ ንግግር ብዙ  – ያሳዬኛል። ሰውንም ሳገኝ ገበርዲኑን አካላዊ ቁመናውን ወይንም ቁመቱን ወይንም የዕውቀት ደረጃውን አይደለም የማዬው – ውስጡን ነው። ውስጥን ፈቅጄ ፈልጌ  ማዬቴ እራሴም የሚጎድልብኝን ነገር ለማስተካክል ነው። አለኝ የምለው ነገር ልፈትሽበት ነው። ከሁሉ በላይ ሐገራዊ በሆኑ አጋጣሚዎች እጅግ የለማ ሂደቶችን ዕድሌ ስላስተናገደ – ማነፃጸርም  – ማወዳደርም የምችልበት ውበታም የሆኑ ወቅታትን በህይወቴ አሳልፌያለሁ። አጋጣሚዎቹ ከዕድሜዬ በላይ እጥፍ ናቸው። እርግጥ ዬፈተና አጥር የበዛበት ቢሆንም ፈተናዎቼ በራሳቸው የይበቃኛል ተቋሞቼ ናቸው። ከሁሉ በላይ ተመክሮወቼ ሆነ ተፈጥሮዬ የማምንበትን ውስጤን ገልጬ የመድፈር አቅሙ አኑሮልኛል

ስለሆነም በሥህነ – ቤዛ ዙሪያ ምስጋናው ቀርቶ ድንበር ዘለል ዘለፋዎቹና አቅምን የሚፈታተኑ የጥላቻ ወጆቦች፤ የቅናት ቅንቅን „ሰው“ የሚለውን ታላቅ ፍጡር – የተዳፈሩ፤ የነፃነት ናፍቆት ቃናን – የተጋፉ፤ የተስፋዬ ተጻራሪ አቋሞች ስለነበሩ፤ ውስጤን ገልጬ ማሳዬት ግድ አለኝና እንዲህ በተከታታይ ልጽፍ – ፈልግሁኝ። እርግጥ አልፎ አልፎም የነበሩትን አውሎዎች በአጽህኖት ስገልጽ ብቆይም ራሱን አስችዬ በርዕስ መጻፉ ግን ወቅታዊ መሆኑ ብቻ ሳይሆን – እኔም አንዲት ኢትዮጵያዊ ዜጋ ነኝና የእኔ ለሆኑ ሁነኛወች ነፃነቴን መጠቀም ግድ አለኝ ።

ላለው በኽረ አምክንዮ ነገ ኢትዮጵያ ሀገራችን በነበረችበት የታመሰ ረግረጋዊ ቂም ተከል መንገድ መቀጠል የለባትም። ለዚህም ጥራትና ብቃት ያለው፤ ሌሎች ከህይወቱ ሊማሩበት የሚችሉ፤ ተተኪዎች ተምሳሌነቱን ሊጠጡት የሚችሉት፤ ሞዴል ሊሆን የቻለ ራሱን በሁለገብ በብቃት ያሰናዳ መንፈስ ልዕልት ኢትዮጵያ – ያስፈልጋታል። ስለሆነም ተግባሩ ከዛሬ ጀምሮ መሬት ይዞ መሰራት ስላለበት አምኘበት ነው የጀመርኩት። ስለሆነም የምዕራፋት እርገት በጊዜያዊነት እንጂ እንደ አስፈላጊነቱ በዚህ ወሳኝና ዓይን ጉዳይ ላይ እምመላለስበት ቀጥተኛ ሀዲዴ ስለመሆኑ መግለጽ – አውዳለሁ። የዜግነት እኩልነት መንፈስ ቡቃያ ድርድር የለም።

በዓይን ቀልድ የለም። በሰንደቅዓላማችን ዳግሚያ ተንሳኤ ድርድር – ቧልት የለም። በአብሮነታችን የእኩልነት አዲስ የዴሚክራሲ ፍላጎታችን የላሜ ቦራ ጨዋታ ሆነ አፍራሽ ትዕይንት መከርቸም ይኖርበታል። ከሁሉ በላይ ድነት የማያጣው የሰፈርተኝነት፤ የቤተ – ነገድ ነቀርሳዊ ትርትር ዕሳቤ ቀብሩ መከወን አለበት። እኛ ሁሉን አሳታፊ፤ አዲስ ብሩህ የእኩልነት ሥርዓት ናፍቆት አለብን። አሸናፊና ተሸናፊ የሌለበት የመደማመጥ ስስት አለብን። አሸናፊው ሃሳብ ተሸናፊውንም በጥሩ አያያዝ ሳያገል እኩል ተጠቃሚ የሚሆንበትን ያደገ የዴሞክራሲ ሂደት ቀልባችን ነው። ስለሆነም ሥህነ – ቤዛ አርበኛ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሆነ የከፍተኛ አርበኞች ግንቦት 7 አመራሮቹን ዓላማ የራሴ ጉዳይ ነውና ሥነ – ልቦናዊ ጥበቃውን በሚመለከት ሁልጊዜም ዘብ – እቆማለሁ። አርበኞቼ ከህይወቴ በላይ ናቸው። ናሙናነት እሳትን በመድፈር አርበኛ ነአምን ዘለቀ እና አርበኛ ኤፍሬም ማዲቦ በመሆን ጌጥ ሆኑ። ታሪክም ከበረ። ትውልድም ለሰንደቅዓላማው ባንድ ቅኔ ዜማ ዘመረ። ኑሩልን እግዚአብሄር ይስጥልን።

በመጨረሻ – መሆንን ላከበረ፣ መሆንን ለፈቀደ የኤርትራው ከፍተኛ የፖለቲካ አመራርም ከልብ በአክብሮት ምስጋናዬን አቀርባለሁ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ብሌናችን የእኛ ብቻ ሳይሆን የናንተም ሃብት ነው። አንዲሁም የአፍሪካ ቀንድም፤ ባለፈም የአኽጉራችን የሰላም፣ የመረጋጋት የፍቅር ሃዲድ ሐዋርያ ነውና በጋራ በመከባበር ከድህነት፤ ከጥላቻ፤ ከፉክክር፤ ከቁርሾ የምንላቀቅበት፤ በእኩልነት ላይ የተመሰረተ እትብታዊ ጉርብትና አውራ መንገድ ነውና ጥበቃውና ጥንቃቄውን አክሎ በኃላፊነት የኤርትራ ፕሬዚዳንታዊ ቢሮ እንዲወስድም በትሁት መንፈስ  – አሳስባለሁ። ዬኤርትራ ጉርብትና ለእኛ እንደ ኬንያ ወይንም እንደ ሱዳን አይደለም። እእ። ኤርትራ እኛ ናት። እስኪ ወግ ደርሶን መኖርን በፍቅር እንደ ገና አዎን! እንደ ገና በድርጊት አስጊጠን – እንሞሽር ….. ወህም እንበል። ተምሳሌነታዊ ጉርብትና እስኪ ጊዜ ይፈቅድለት። ለዚያ ያብቃን አዶናይ! አሜን!

ለነበረን ሽክ ያለ ዘንካታ የመደማመጥ ጊዜ አመሰግንኳችሁ። አከብርኳችሁ። ከልብ መንፈሴን ሸልምኳችሁ – ለእኔዎቹ ታዳሚዎቼ።

ዘሐበሻ ትእግስታችሁ አስተማረኝ  -ኑሩልኝ።  የልብ አድራሿ ነፃነት እንዲህ – ትጥማለች።

http://ethio.info/tsegaye/April2009/Edemta-Shelematachen.pdf

http://ethio.info/tsegaye/June2009/Tesfa-Ginbot-7-Sebesba.pdf

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል

እግዚአብሄር ይስጥልኝ

 

 

 

የሰራዊቱ አባላት “ዝምታችን አጋጣሚን እየጠበቀ ነው”አሉ –የሳዲቅ አህመድ ምርጥ ትንታኔ በድምጽ

$
0
0

የሰራዊቱ አባላት “ዝምታችን አጋጣሚን እየጠበቀ ነው” አሉ – የሳዲቅ አህመድ ምርጥ ትንታኔ በድምጽ


meles and his milltery

“ጎሳን ለይቶ የሚደረግ ጥቃትን ለማስወገድ መሰረታዊ ለውጥ ያሻል”ሲል ሸንጎ አሳሰበ

$
0
0

shengo
ጎሳን ለይቶ የሚደረግ ጥቃትን ለማስወገድ መሰረታዊ ለውጥ ያሻል

ነሀሴ 24፣ 2007 (ኦገስት 30፣ 2015)

አንድ መንግስት ልማታዊ ሊባል የሚችለው የሚመራውን ሕዝብ ከዃላ ቀርነትና ከድህነት አሮንቓ መንጥቆ ሲያወጣ፣የህዝቡን አንድነትና መልካም ግንኙነት ሲያጠናክር፣የአገርን ብሔራዊ ጥቅምና ዳር ድንበር ሲያስከብር ነው።

ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>
<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596344.js" async> </script>