Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

“በኢህአዴግ ስር ሁኖ እየተሰቃየ የሚገኘው የኢትዮጵያ ህዝብ ወደደም ጠላም ይህ ስርዓት እስከቀጠለ ድረስ መስዋእትነት መክፈሉ አይቀርም ”–ትህዴን

Next: Hiber Radio: የሕወሃት መሪዎች የስልጣን ሽኩቻ ወደ ሀይል ግጭት ሊያመራ ነው መባሉ ፣ መድረክ አገዛዙ በግብዣ ጋጋታ የህዝብ ንብረት ማባከን አቁሞ በድርቅ ለተጎዱት እንዲደርስ ጠየቀ ፣የአሜሪካና የአውሮፓ የህዝብ እንደራሴዎች አቶ አንዳርጋቸው በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቁ፣ ጀርመናዊው የፓርላማ አባል ሁለት ሐበሻ ስደተኞችን ስላስጠጉ የግድያ ዛቻ ደረሰባቸው፣ በእስራኤል ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ በልዩ የሆድ በሽታ መጠቃታቸው፣ ቃለ መጠይቅ ኦባማን በጉብኝታቸው ልትገል በሚል የፈጠራ ክስ ከተከሰሰው ጋዜጠኛ ሀብታሙ ምናለ ፣ከአረና የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አምዶም ገ/ስላሴ ጋር ቃለ መጠይቅ እና ሎሎችም
$
0
0

arbegnoch ginbot 7
መስዋእትነት አይቀሬ ነው ታሪክ ሰርቶ ማለፍ ግን ክብር ነው!!

የትህዴን ርዕሠ አንቀጽ

በአሁኑ ግዜ በአገራችን ህዝብን የሚወክልና በህዝብ የተመረጠ መንግስት ሳይኖረን ይህንን እድል ለመፍጠር አጋጣሚውን ያገኙ ቡድኖች ሆኑ ግለሰቦች ከህዝብ ፍላጎት እና ከሃገር ጥቅም ይልቅ የግል ጥቅማቸውን‘ና የባእዳኖችን ፍላጎት በማስቀደም ያገኙትን የተለያዩ አጋጣሚዎች በመጠቀም የህዝብን ስልጣን እየነጠቁ ለህዝብ እና ለሃገር የቆሙትን እየገፉ እና እየገደሉ በጉልበት መንግስት ነን በማለት እስካሁን ስልጣን ላይ ይገኛሉ።

የኢህአዴግ አመራሮች ህዝብን የማገልገል ስራ ሳይሆን የየራሳቸውን ጥቅም በማስጠበቅ እና ስልጣን ላይ ወጥተው የህዝብን ሃብት ለግል ጥቅማቸው እያዋሉ፤ ህዝብን እንዳሻቸው እየጨቆኑ፤ እያንገላቱና እየጨፈጨፉ ባጠቃላይ ለትውልድ የሚተርፍ መጥፎ ታሪክና የማይረሳ የጥፋት አሻራ ጥለው እያለፉ መሆናቸው ግልፅ ነው።

የደርግ ስርዓት በህዝብ ልጆች መስዋእትነትና የአካል-መጉደል ከተደመሰሰ በኃላ ስልጣን የሙጥኝ ያለው ፀረ ህዝብ የኢህአዴግ ስርዓት ፋሺስታዊው የደርግ ስርዓት ለሃገር እና ለህዝብ የቆሙትን ንፁኃን ዜጎች በመጨፍጨፍ እንደሚታወቀው ሁሉ አሁን በአገዛዝ ላይ ያለው የኢህአዴግ ስርዓትም በፖለቲካ አመለካከታቸውና ደስ አላሰኙኝም በሚል ንጽሁሃን ዜጎች በድብቅና በግልፅ ብመጥፋት የራሱ የሆነ ጸረ ህዝብ እና ጸረ ሃገር የሆኑ መለያዎች አሉት።

የኢህአዴግ ስርዓት ካለፉት ጨቋኝ ስርዓቶች ለየት የሚያደርጉት በርካታ እኩይ ባህሪያቶች እዳሉት ግልጽ ነው። ስርአቱ የሚታወቅበት መቼም ሊለወጥ እና ሊሻሻል የማይችል አያሌ ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ ህዝብ አጀንዳዎች እንዳሉ ሆነው በተጨማሪም አለቆቹ በባእዳን የተነገረውን ትእዛዝ ለማስከበር ሲሉ ለባእዳኖች ባለመገዛቱ የሚታወቀውን የኢትዮጵያ ህዝብ ለመበቀል፤ኢትዮጵያን ለመበታተን’ና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የተዘጋጀውን የተሳሳተ ታሪክ ይዞ በተለይም ለስርዓቱ አልገዛም ባለው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ቂም ይዞ ለመበቀል ከፍተኛ በጀት እና የሰው ሃይል መድቦ ለጥፋት መነሳቱ የስርዓቱ ባህሪ ነው።

እንደሚታወቀው በመሳሪያ ጋጋታ እና በአፋኝ ህግ ብዛት ሃሳቡን እና ተቃውሞውን እንዳይገልጽ የተከለከለው የኢትዮጵያ ህዝብ ለስርዓቱ ያለውን እምቢተኝነት እና ተቃውሞ ባገኘው አጋጣሚ እየገለጸና ከዛም አልፎ የስርዓቱ አስመሳይ የምርጫ ሂደት ላይ ባለመሳተፍና ባለመምረጥ በስርዓቱ ላይ ያለውን ተቃውሞ ገልጿል። በመሆኑም የኢህአዴ ስርዓት በሚቀጥሉት 5 ዓመታት በስልጣን መቆየቱ የቂሙን ደረጃ የት ያደርሰዋል? ስልጣኑንስ የሚጠቀመው እውነት ሃገር እና ህዝብን ለመጥቀም ነው? ወይስ የተነሳለትን ኢትዮጵያን ህዝቧን የመበታተን ዘመቻውን አጠናክሮ ለማስቀጠል?

ለማኛውም! አጥፊ እና ጠፊ አብረው መኖር እንደማይችሉ ሁሉ መቼም ቢሆን ህዝብ ከኢህአዴግ ስርዓት ጎን ሊቆም አይችልምና ህዝቡ ለኢህአዴግ ባለመምረጡና ከህወሓት-ኢህአዴግ ጎን ባለመቆሙ ምክንያት የተለመደ የኢህአዴግ ቂም በቀል እርምጃ በእጥፍ መቀበሉ አይቀሬ ነው፤ ወያኔ በስልጣን እስካለ ድረስ በህዝቡ ላይ የሚደርሰው የጥፋት ዘመቻ፤ እስራት፤ ድብደባ፤ አፈና፤ በኑሮ ውድነት መሰቃየት፤ ከኖረበት መፈናቀሉ ሌላም ሌላም በከፋ ሁኔታ ይቀጥላል።

በኢህአዴግ ስር ሁኖ እየተሰቃየ የሚገኘው የኢትዮጵያ ህዝብ ወደደም ጠላም ይህ ስርዓት እስከቀጠለ ድረስ መስዋእትነት መክፈሉ አይቀርም ምክንያቱ የእኛ ከኢትዮጵያውያን ታሪክ አንጻር ሲታይ ለውጭ ወራሪውችም ሆነ ለውጥ ጸረ ህዝብ ስርአተወች አሜን ብሎ ተገዝቶ ኣይውቅም ስለዚህ መቼም ቢሆን አይቶ እንዳላየ መሞትን ይመርጣል ተብሎ አይገመትም።

ስለሆነም ማንኛው ኢትዮጵያዊ በሚከተለው ዓላማና በፖለቲካ አስተሳሰቡ ህይወት መክፈሉ ላይቀር እራሱን መስዋእት አድርጎ ብሄራዊ ክብሩን ለማስመለስና በሃገራችን ውስጥ እውነተኛና ያልተገደበ ዴሞክራሲ ለመገንባት፤ ለህዝብና ለሃገር ተቆርቋሪ የሆነ በህዝብ የተመረጠ መንግስት ለመመስረት በሚደረገው ትግል ላይ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ መሆን ይጠበቅበታል፣ ምክንያቱም ለማይቀረው መስዋእትነት ታሪክ ሰርቶ ማለፍ ክብርን ያጎናፅፋልና።


Hiber Radio: የሕወሃት መሪዎች የስልጣን ሽኩቻ ወደ ሀይል ግጭት ሊያመራ ነው መባሉ ፣ መድረክ አገዛዙ በግብዣ ጋጋታ የህዝብ ንብረት ማባከን አቁሞ በድርቅ ለተጎዱት እንዲደርስ ጠየቀ ፣የአሜሪካና የአውሮፓ የህዝብ እንደራሴዎች አቶ አንዳርጋቸው በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቁ፣ ጀርመናዊው የፓርላማ አባል ሁለት ሐበሻ ስደተኞችን ስላስጠጉ የግድያ ዛቻ ደረሰባቸው፣ በእስራኤል ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ በልዩ የሆድ በሽታ መጠቃታቸው፣ ቃለ መጠይቅ ኦባማን በጉብኝታቸው ልትገል በሚል የፈጠራ ክስ ከተከሰሰው ጋዜጠኛ ሀብታሙ ምናለ ፣ከአረና የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አምዶም ገ/ስላሴ ጋር ቃለ መጠይቅ እና ሎሎችም

$
0
0

Habitamu

የህብር ሬዲዮ ነሐሴ 3 ቀን 2007 ፕሮግራም

<... ...>

አምዶም ገ/ስላሴ የአረና የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ የመድረክን ልዩ አስቸኳይ ጉባኤ እና የህወሃት መሪዎችን የስልጣን ሽኩቻ አስመልክቶ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

<...> ወጣት ባንተወሰን አበበ በአርባ ምንጭ ከተማ ወንድሙ ግንኦት ሰባትን ለትግል በመቀላቀሉ ሳቢያ በደህነቶች የደረሰበትን ስቃይ ለህብር ሬዲዮ ገልጿል ( ሙሉውን ያዳምጡት)
ጋዜጠኛ ሀብታሙ ምናለ አስገራሚ ስለሆነው የተለጠፈበት ወንጀል እና የእስር ቆይታው ከሰጠን ማብራሪያ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

የሚድትራኔያን ባህርን አቋረጠው ከፈረንሳዩ የካሌስ ወደብ የደረሱ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ዛሬም ያነባሉ(ልዩ እና ወቅታዊ ዘገባ)

ለኢትዮጵያውያን ቀን በቬጋስ የበዓል አከባበር ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ሪፖርት

ከሁበር መምጣት በፊት እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎች ቃለ መጠይቅ

ሌሎችም አሉን

ዜናዎቻችን

የሕውሃት ባለስልጣናት የስልጣን ሽኩቻ ወደ ሀይል ግጭት ሊሸጋገር ይችላል ተባለ

መድረክ በልዩ ጉባዔ አገዛዙ የግብዣ ጋጋታውን ትቶ በድርቅ እየተጎዳ ላለው ህዝብ እንዲደርስ ጠየቀ

የአሜሪካ እና የአውሮፓ ሴናተሮች አቶ አንዳርጋቸው ባሰቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቁ

ጀርመናዊው የፓርላማ አባል ሁለት ወጣት አበሻ ሰደተኞችን በማሰጠለላቸው የግደያ ዛቻ ገጠማቸው

ከ700 በላይ ሰደተኞችን ከሊቢያ ወደ ጣለያን የጫነች ጀልባ አስዛኝ የሆነ አደጋ ገጠማት

እስራኤል ውስጥ በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በልዪ የሆድ እቃ ህመም እየተስቃዩ ናቸው ተባለ

የመኢአድ የውጭ ግንኙነት ሀላፊ በማዕካዊ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አለመታወቁ ተገለፀ

የኔቫዳ የትራንስፖርት ባለስልጣን ሁበርና ሊፍት ላይ ጫና ይፈጥራል የተባለ ረቂቅ ደንብ አቀረበ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

የፍርድ ቤት ውሎ

Previous: Hiber Radio: የሕወሃት መሪዎች የስልጣን ሽኩቻ ወደ ሀይል ግጭት ሊያመራ ነው መባሉ ፣ መድረክ አገዛዙ በግብዣ ጋጋታ የህዝብ ንብረት ማባከን አቁሞ በድርቅ ለተጎዱት እንዲደርስ ጠየቀ ፣የአሜሪካና የአውሮፓ የህዝብ እንደራሴዎች አቶ አንዳርጋቸው በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቁ፣ ጀርመናዊው የፓርላማ አባል ሁለት ሐበሻ ስደተኞችን ስላስጠጉ የግድያ ዛቻ ደረሰባቸው፣ በእስራኤል ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ በልዩ የሆድ በሽታ መጠቃታቸው፣ ቃለ መጠይቅ ኦባማን በጉብኝታቸው ልትገል በሚል የፈጠራ ክስ ከተከሰሰው ጋዜጠኛ ሀብታሙ ምናለ ፣ከአረና የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አምዶም ገ/ስላሴ ጋር ቃለ መጠይቅ እና ሎሎችም
$
0
0

( ለገሰ ወ/ሃና )

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ ) አመራሮች ም/ል ፕሬዝደንቱ
1 ዘመነ ምህረት
2 ጌትነት ደርሶ አባል
3 መለሠ መንገሻ የወጣቶች ድርጅት ጉዳይ ሀላፊ
ዛሬ ነሐሴ 4/2007 ዓም 4:20 ሰአት አካባቢ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል ለዛሬ ተቀጥሮ የነበረው ተከሳሾች እና ከሳሽ ያቀረቡትን መቃወሚያ መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ነበር
በዚህ መሠረት
11214278_909515852449616_49166841129975178_n
1ኛ ተከሳሽ ዘመነ ምህረት ያቀረበው የክስ መቃወሚያ ሙሉበሉ ውድቅ ተደርጏል በተለይ የተከሰሰበት አንቀፅ እንዲሻሻል ያቀረበው መቃወሚያ ፍርድ ቤቱ አንቀፁ መሻሻል የለበትም ብሏል ዘመነ የተከሰሰበት አንቀጽ ከ15 አመት እስከሞት የሚያስቀጣ መሆኑ የታወቃል
3ኛ ተከሳሽ መለሠ መንገሻ ያቀረበው መቃወሚያ በከፊል ተቀባይነት አግኝቷል በዋናነት የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር (ኢህአግ ) አባል መሆን ከአመራሮቹ ጋር በስልክ ——-መገናኘት ወዘተ የሚለው የአቃቤ ህግ ክስ
መለሠ መንገሻ ያቀረበው መቃወሚያ የኢትዮጵያ ህዝብ አረበኞች ግንባር( ኢህአግ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት ያልተፈረጀ ስለሆነ አሸባሪ ተብየ ልከሰስ አይገባኝም ያለውን ፍርድ ቤቱ ተቀብሏል
11825567_909515825782952_515505813072519969_n
ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ ላይ የቀረበው የሽብር ክስ ተሻሽሎ በህገመንግስቱ መሠረት በወንጀል ይከሰስ ሲል አቃቤ ህግ ተቃውሟል ተከሳሽ ለፍርድ ቤቱ ያቀረበው መቃወሚያ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ( ኢህአግ ) በፓርላማ በአሸባሪነት አልተፈረጀም ያለው እውነት ቢሆንም
በአሸባሪነት ከተፈረጀው ከግንቦት 7 ጋር ተዋህዷል በአሸባሪነት ነው መከሰስ ያለበት ብሏል
ፍርድ ቤቱ ግን አልተቀበለውም የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ከተከበረ በህገመንግስቱ መሠረት ክሱ ተሻሽሎ ለነሐሴ 13/2007 ዓም በተመሳሳይ ሰአት እንዲቀርብ ታዟል
ሁለተኛ ተከሳሽ ጌትነት ደርሶ ምንም አይነት ሀሳብ አልሰጠም ምክንያቱ ደግሞ ቀደም ሲል ጠበቃ አልፈልግም ክርክር አላደርግም ከዚህ ፍርድ ቤት ፍትህ ስለማላገኝ ስላለ በዛው ቀጥሏል
11846672_909515829116285_2717405600234033280_n
ዛሬስ ተከሳሾች ምን አሉ ?
ቀድሞ የመናገር እድል ያገኘው መለሰ መንገሻ ነበር
፠ በአሸባሪነት በመከሰሴ ህክምና ተከልክያለሁ
፠ ዘርን መሠረት ያደረገ ጥቃት ደርሶብኛል( አማራ በመሆኔ)
፠ ለመከላከያ ምስክርነት ወደ አራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስወሰድ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞብኛል
፠ አጄኝ አጥብቀው በካቴና አስረው አመመኝ እጄ ሊቆረጥ ነው ስላቸው ለእጅህ ይገርምሃል እንዴ ገና አንገትህን እንቆርጠዋለን ተብያለሁ ብሎ ለችሎት አቤቱታ ቢያቀርብም ዳኞች ከተመካከሩ በኇላ ” እኛ የተቀመጥነው የቀረበልንን መዝገብ መርምሮ ውሳኔ መስጠት ብቻ ነው ” የሚል መልስ ሰጥተውታል::
ዘመነ ምህረት
፠ዘመነ ፊቱን ወደ ጏደኛው መለሰ ፊቱን አዙሮ ከዚህ ፍርድ ቤት ፍትህ አንጠብቅም ለምን ትደክማለህ
፠የህግ የበላይነት በሌለበት አቤቱታ ማቅረብ ተገቢ አይደለም
፠ ወደ ዳኛ ፊቱን አዙሮ ዛሬ ወደዚህ ስመጣ በእጁ ፓሊሱን እያመለከተ ደብድቦኛል ሲል አብረውት የመጡት ታሣሪዎች ሁሉም ባንድነት አዎ መቶታል አሉ ዘመነ መታኝ ያለው ፓሊስ ይሰቅ ነበር ለመለሠ እንዳደረጉት ዳኞቹ ተማከሩ የመለሱት መልስ በጣም ያስቃል የመለሱት የመጀመሪያውን ነው ” እኛ የቀረበልንን መዝገብ መርምረን ውሳኔ መስጠት ብቻ ነው የኛ ተግባር ” አሉ
፠ ከናንተ ፍትህ አንጠብቅም እኛ ፍርድ የምንጠብቀው ከእግዚአብሔር ነው ሁላችንም በእምነታችን ወደ ፈጣሪ መጮህ አለብን በተለይ የኦርቶዶክስ አማኞች አሁን ወቅቱ የጾም ነው በርትተን መፀለይ አለብን እውነተኛ ዳኝነት የሚገኘው ከፈጣሪ ብቻ ነው በማት ሀሳቡን አጠቃሏል::
ከነ ዘመነ ምህረት በመቀጠል ቁጥራቸው 10 አካባቢ እድሜያቸው 17 እስከ 20 የሚሆን ትንንሽ ልጆች ናቸው ለአቅመ እስራት ያልደረሱ ናቸው ችሎት የቀረቡት የመጡት ከጎንደር እና ከጎጃም አካባቢ ነው ስማቸው ሲጠራ አይሰማም ነበር በዚህ ምክንያት ስማቸውን አልያዝኩም
ስለተከሰሱበት የሸብር ክስ ምንም ያልገባቸው ናቸው ከአርበኞች ግንቦት ሰባት እና ከሌሎች አሸባሪ ድርጅቶች ጋር ሽብር ለመፍጠር ስትንቀሳቀሱ ነበር የሚለውን ክስ ሲሰሙ እኛ የምትሏቸውን ስሞች እየሠማን ያለነው ከናንተ ነው እኛ አናውቃቸውም እተደበደበን ያለነው አማራ በመሆናች ነው መርማሪዎች የጠሉት አማራነታችንን ነው ብለዋል ::

በምዕራብ ጎጃም የብአዴን አባላት አርበኞች ግንቦት 7 ውስጣችን ሰርጎ ገብቷል በሚል እርስበርስ እየተወነጃጀሉ መሆኑ ተሰማ * ክፍፍሉንም አባብሶታል

$
0
0

Zehabesha News
በምዕራብ ጎጃም የብአዴን አመራሮች መካከል መከፋፈል ተፈጠረ

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ እንደዘገበው የምዕራብ ጎጃም የብአዴን አመራርና አባላት ከሀምሌ 29 እስከ ነሀሴ 1 2007 ዓ.ም ባካሄዱት ስብሰባ ላይ ነው መከፋፈሉ ሊከስት የቻለው፡፡ የምዕራብ ጎጃም የብአዴን የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ሀብታሙ፣ የዞኑ ምክትል ከንቲባ አስፋው ገበየሁና የወረዳው የብአዴን ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አላምር ተሻለ የተባሉ የህወሓት አገልጋይ የመሩት በዱላ ቀረሽ ስድድብ፣ እርስበርስ መወነጃጀልና የተደበቀ ገመናን በመነስነስ ታጅቦ ለሦስት ቀናት የዘለቀው ስብሰባ ከመነሻው በዋናነት ለውይይት ያቀረባቸው አርበኞች ግንቦት 7 ባወጀው ጦርነት ላይ ተመስርቶ በሽበርተኝነት ላይ የሚያጠነጥን አንድ ሃሳብና የብአዴንን 35ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አከባበርን የሚመለከት ሌላ ተጨማሪ እርዕስ ያነገበ ሁለት አብይ አጀንዳዎች ነበሩ፡፡

ነገር ግን ስብሰባው የታቀደለትን አቅጣጫ ስቶ ፈር በመልቀቅ አባላትና የበታች የብአዴን አመራሮች ከአንድ ላይ በማበር በበላይ አመራሮቻቸው ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲያነሱ የበላይ አመራሮች ደግሞ በፌደራል መንግስቱ በሚገኙ የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች ላይ ጣታቸውን ቀስረዋል፡፡

በመሆኑም የህወሓት ጉዳይ አስፈፃሚ የሆነው ብአዴን ከሦስት ጎራ የመሰነጣጠቅ እጣ ገጥሞት ከፍተኛ አደጋ ተደቅኖበት ይገኛል፡፡

የብአዴን አባላትና የበታች አመራሮች የበላይ አመራሮቻቸውን “የህወሓት አሽከሮች በመሆናችሁ ለክልሉ ብሎም ለአገራችን ምንም አይነት አዎንታዊ ሚና አከናውናችሁ ለውጥ ልታመጡ አልቻላችሁም፡፡” በማለት ልክ ልካቸውን ነግረው እርቃናቸውን ሲያስቀሯቸው የበላይ አመራሮች ደግሞ በበኩላቸው “ችግሩ የኛ አይደለም የአሳ ግማቱ ከአናቱ እንዲሉ ብልሽቱ ያለው ከላይ ከአለቆቻችን ነው፤ የፌደራሉ የብአዴን አመራር በህወሓት አንገቱን ታንቆ ተይዟል፡፡” በማለት የብአዴንን ቁንጮዎች በአደባባይ አበሻቅጠዋቸዋል፡፡
የምዕራብ ጎጃም የብአዴን ዝቅተኛ አመራሮችና አባላት “በአገሪቱ ብሎም በክልሉ እስካሁን ምንም አይነት እድገት አልተመዘገበም፤ ዘወትር የምታቀርቡት ሪፖርት ነጭ ውሸት ነው፤ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተከናወነ የሚገኘው የልማት እንቅስቃሴ አንድ ክልል ላይ ብቻ ያተኮረ ነው፤ ልክ እንደ ትግራይ ሁሉ ዳያስፖራው ክልሉን እንዲያለማ እድል አልተሰጠውም በሩ ክርችም ብሎ ተዘግቷል…” የሚሉ ሃሳቦችን አጠናክረው አንስተዋል፡፡

አስፋው ገበየሁ፣ አማረ የተባሉና ሌሎች የምዕራብ ጎጃም የብአዴን አመራሮች በስርቆት ከፍተኛ ሀብት ማፍራታቸው በስብሰባው ላይ ተጋልጧል፡፡

በተጨማሪም የምዕራብ ጎጃም የብአዴን አመራሮችና አባላት በውስጣቸው የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት እንደተሰገሰጉ በማመን እርስበርስ ወደ መፈራረጅ በመሄዳቸው ሹጉጣቸውን ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠው በዓይነ ቁራኛ እየተያዩ ስብሰባውን ያጠናቀቁ መሆናቸውን ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡

በዳንሻ ከተማ ለህዝቡ ሊከፋፈል በመጋዘን የተከማቸ ከ30 ሺህ ሊትር በላይ የምግብ ዘይት የደረሰበት በመጥፋቱ በአካባቢው ከፍተኛ የሆነ እጥረት መከሰቱ ታወቀ፡፡
የምግብ ዘይቱን ለዳንሻና አካባቢው ህዝብ እንዲያከፋፍሉ የተረከቡት ክብሮምና ተክላይ የተባሉት ግለሰቦች ሲሆኑ ከ30 ሺህ ሊትር በላይ የሆነውን የምግብ ዘይት ተዘረፈብን ሲሉ ህብረተሰቡን ለከፋ ችግር ዳርገውት ይገኛሉ፡፡

“ሰላማዊ ትግል ለማይገባዉ አምባገነን በሚገባዉ ቋንቋ እናናግረዋለን!!”–ድምጻችን ይሰማ ደቡብ አፍሪካ (ደ.ይ.ድ.አ)

$
0
0

south africa

በትናንትናዉ እለት ሰኞ 10/08/2015 በደቡብ አፍሪካ የሚገኘዉ የሰላማዊ ትግል ተምሳሌት ድምጻችን ይሰማ ታላቅ ስብሰባ አደርገ። እንደሚታወቀዉ በቅርቡ አንባገነኑ ወያኔ ሚሊዮኖች በወከሏቸዉ የንጹሃን የህዝበ ሙስሊም ኮሚቴዎች ላይ ታሪክ ይቅር የማይለዉ ኢ_ፍትሐዊ ፍርድ በመፍረዱ ምክንያት የደቡብ አሪካዉ ድምጻችን ይሰማ ኮሚቴ በጠራዉ የዉይይት መድረክ ላይ የተገኙ ሙስሊም ኢትዮጵያዊን ወገኖች ቁጣቸዉን ገለጹ።
በእለቱ የተከበሩ የህዝበ ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ወገኖች ተወካዮችና የሐይማኖት ሊቆች፣ሼሆች፣ ኡስታዞች፣ የተገኙ ሲሆን ሼህ መሐመድ አሚን፣ ኡስታዝ ኡስማን አህመድ፣ የየእለቱ መክፈክቻ ንግግሩ ሹሞች ነበሩ።
” ሰላማዊ ትግል የሚነገርዉ ሰላም ለሚገባዉ እንጂ እንደ ወያኔ ላለ አምባገነን አይደለም ይህ አካሄዳችን ፈጽሞ በወያኔ ታጥቦ ተወስዷል በመሆኑም ሰላማዊ ትግል ማለት ነጭ ወረቀት ብቻ ማዉለብለብ አይደለም ” ኢስላም ሰላም ነዉ ” ነገር ግን ይህ ለሚገባዉ ብቻ ነዉ ለማይገባዉ ግን የምንሄደዉ መንገድ ሁሉ ለኛ ሰላም ነዉ! በሚል ታሪካዊ ንግግር የተከፈዉ ስብሰባ በቁጭትና በምሬት የተካሔደ ነበር።

በኦሮምኛ ቋንቋና በአማርኛ ቋንቋ በድንቅ ሁኔታ የተካሄደዉ የትናንቱን የድምጻችን ይሰማ ስብሰባ ላይ በኦሮምኛ ቋንቋ ስነ ግጥም የቀረበ ሲሆን በቅጽል ስሙ ( ፀረ ወያኔ ) በመባል የሚታወቀዉ ገጣሚ አብዱራህማን ቦንከሬ ሙስሊም ወንድሞቻችን በወህኒ ተከርችመዉ መሬት ለመቀራመት ወደ ሐገር ቤት የነጎዱ በሙስሊሙ ስም የሚንቀሳቀሱ የዲን ጠላቶች የወያኔ ዲያስፖራዎችን በቅንፍ ዉስጥ ያስገባ ስነ ግጥም ያቀረበ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ በተለያዩ የህዝበ ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በደቡብ አፍሪካ በሚያደርጉት ዝግጅት ላይ የተለያዩ ጽሁፎችን ይዞ የሚቀርበዉ የጆሐንስበርጉ ጀማል ዲያስፖራ ላሜ ቦራ በሚል እርእስ ከበድ ያለ ምልእክት አስተላልፏል።

በእለቱ የተካሄደዉ ስብሰባ በፍቅር ያስተናገዱት ሼህ ይስሐቅ ሙስሊም ማለት ከግርግዳ ጀርባ ብርሐን የሚመለከት ህዝብ ነዉ ወደ ብርሐንኑም እኛዉ እራሳችን እንሄዳለን ሲሉ ሰምና ወርቅ ያዘለ ንግግር ሲያስቀምጡ ኡስታዝ ፈይሰልም አስተምሮት ያለዉ ድንቅ ንግግር ከማድረጋቸዉም ባሻገር ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ አይወክለንም ሙስሊም ካልሆኑ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ጋር ሊያጋጬን የማይጭረዉ የማይንደዉ ሐረካት እንዳለ እናዉቃለን እኛ የጋራ ጤላታችን ወያኔ ነዉ የሚሉ ታላላቅ ንግግሮችም የእለቱን ታሪካዊነት ሲያጎሉት ። በስተመጨረሻ አጠቃላይ ዉይይቱ ወደ መላዉ ሕዝብ የገባ ሲሆን የዉይይት መድረኩ በድምጻችን ይሰማ ደቡብ አፍሪካ አወያዮች የተመራ ነበር በመሆኑም፡…..

1. ኡስታዝ ሸምሱ
2. ጋዜጤኛ አብዱራህሚን
3. ከድምጻችን ይሰማ ኮሚቴዎች ጋር ታስሮ የነበረዉና በዋስ ከወጣ ወዲህ በስደት ደቡብ አፍሪካ የሚገኘዉ በሌለበት የ 15 አመት ፍርደኛዉ አሊ መኪ፡ ሲሆኑ ዉይይቱን የከፈተዉ ጋዜጠኛ አብዱራህሚን ለትዉስታ ያህል የፍርደኛ ንጹሐን ሙስሊም ወኪሎችን የፍርድ ቤ/ት ዉሎ ባስታወሰ መልኩ የማነቃቂያ ንግግሮች በማድረግ ሐሳብ የመስጤቱ እድል ወደ ህዝቡ ከሆነ ህዝቡ ከደቡብ አፍሪካ ከተለያዩ ስፍራዎች የተገኘዉ በቁጭት የተሞላዉ ህዝበ ሙስሊም እጥዮጵያዊያን ወገኖች ” ጉዞዉ ወደ ትግል ብቻ ነዉ ” የሚል ሐሳብ መሆኑን በጥቅል ያሳየ ሲሆን በሼህ ሸምሱም የተመራዉ የመፈክር ስእነ ስርአት (ለዲናችን እስከመጨረሻዉ ለመስራት ዝግጁ ነን ገንዘብም ሆነ ህይወት ለመስጠት ዝግጁ ነን በወያኔ አያሸብረንም!!! ) የሚል የህብረት መፈክር ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ጉድሽ ወያኔ

በአዳማ ገልማ አባገዳ አዳራሽ የኦሮሞ ዲያስፖራ አባላት የመንግስት ባለስልጣናትን በጥያቄ አጨናነቁ

$
0
0

Opdo
(ራዲዮ ዳንዲ ሃቃ ማክሰኞ ሐምሌ 5/ 2007) ስብሰባው ከአርባ ሰባት ሃገራት የተሰባሰቡ የኦሮሞ የዲያስፖራ አባላትን የአርባ ሰባቱ ሃገሮች ዲፕሎማቶች በተገኙበት ተካሂዷል ።

መንግስት የኦሮሞ ዲያስፖራ ሳምንት ብሎ የሰየመውን ሳምንት በማስመልከት: ከመላው አለም ያሰባሰባቸውን የኦሮሚያ ዲያስፖራ አባላት: በሚሊኒየም አዳራሽ ጠቅላይ ሚስትሩ በተገኙበት ደማቅ የአቀባበል ስነ ስርዓት ካደረገላቸውና : ለሶስት ቀናት ያክል ሃገሪቷን ካስጎበኛቸው በኃላ : በአዳማ ገልማ አባገዳ አዳራሽ በመሰብሰብ : የተለመደ ፕሮፓጋንዳውን ለመንዛት ቢሞክርም: ከኦሮሚያ የዲያስፖራ አባላት ፍፁም ያልጠበቀው :የጥያቄ ውርጅብኝ ዘንቦበታል ።
ስብስባውን የመሩት አቶ አባዱላ ገመዳ አቶ ሙክታር ኸድር እና ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ሲሆኑ : ከኦሮሞ ዲያስፖራ አባላት የተነሱት ጥያቄዎች በአራት ነገሮች ላይ ያጠነጠኑ እንደነበሩና እነሱ :–

1)የሙስሊሙ ህብረተሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴን የፍርድ ሂደት በተመለከተ
2) የጋዜጠኞችን መታሰር ጉዳይ በተመለከተ
3) የኦሮሞ ተማሪዎችና ወጣቶች መታሰርን በተመለከተና
4) የመሬት ማስተር ፕላኑንና በተመለከተና በማስተር ፕላን ሰበብ ህዝብ ላይ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ እንደነበር ምንጮቻችን አያይዘው ገልፀዋል።
በተለይም የሙስሊሙ ህብረተሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ጉዳይ ከዲያስፖራው አባላት ሲነሳ : የተሳታፊዎቹ ስሜት ፍፁም ልዩ እንደነበርና: እያንዳንዱ እነሱን በሚመለከት የሚነሳ ጥያቄ በተነሳ ቁጥር : ከኃላው ከፍተኛ ጭብጨባ ይከተለው እንደነበር ምንጮቻችን ገልፀዋል ። በእለቱ ኮሚቴዎችን በተመለከተ ጥያቄ ካነሱት መካከል ከሳውዝ አፍሪካ የመጣው ወንድም እኔ እዚህ የመጣሁት መሬት ፈልጌ አይደለም : አባቴ ብዙ መሬት አለው ። ተጨማሪ መሬት ካስፈለገኝም ገንዘቤን አውጥቼ ከናንተው እገዛለው ። የመጣሁት አንድ ጥያቄ ለመጠየቅ ነው። ያሰራቿቸውን ኮሞቴዎቻችን ትፈታላችሁ አትፈቱም ? አቶ ሙክታር ከድር ና ፣አቶ አባዱላ ገመዳ ሁለታችሁን ነው የምጠይቀው ። ይህንን ጥያቄ መልሱልኝ ። መሬት ብሰጡኝ እንኳን አልቀበልም ። ለምን ፈረዳችሁባቸው ? ጥያቄውን የጠየቅነው እኛ ነን ። ህዝብ እየሰማ ትፈታላችሁ አትፈቱም ? ነው የምንላችሁ: እምቢ አንፈታም ካላችሁ : መሳሪያ ገዝተን በናንተ ላይ ነው የምንነሳው : ይህ የምትቀመጡበት ወንበር ነገ አይኖርም ። የህዝቡ ነው ልትነሱ ትችላላችሁ በማለት ቆምጠጥ ያለ ንግግር ማድረጉን: አንድ የባሌ ተወላጅ የሆነ ወጣት ደግሞ ሀይለስላሴ ይህችን ሀገር ፈጣሪ ለኔ አደራ ሰጥቶኛል : እያለ ስብስባ ላይ ሲያወራ : በስብሰባው ላይ ተሳታፊ የነበሩት ሀጂ አደም ሳዶ የተባሉ ሙስሊም : ፈጣሪ ይህችን ሃገር ለአንተ አደራ ሲሰጥህ : ባሌን ረስቷታል ወይ አሉት : እኔ ደግሞ እናንተን እላችኋለው ። እናንተ የህዝቡን መብት እናስጠብቃለን ስትሉ የሙስሊሙን መብት ከመሃል ረሳችሁት ወይ ? እነዚህ ሙስሊም ወንድሞቼ የጠየቁት ጥያቄ መልስ የማያገኝ ከሆነ : ልማት የሚባል ነገር የለም። ነገሩም ዛሬ ቁጭ ብለን እየተሳሳቅን እንደምናወራው አይነት ወሬ አይሆንም ።
ከአሜሪካ ሜኒሶታ የመጡ ሽማግሌም : እኛ ትንሿ ኦሮሚያ ብለን የጠራናት ከተማ ሜኒሶታ ላይ ገንብተናል። ወደዳችሁም ጠላችሁም ስለችግራችን እዛ እንወያያለን ። እኛ ወደ ሌላ መጥፎ ነገር ሳንገባ ጥያቄውን መልሱ ኮሚቴዎችን ፍቱ ። ኮሚቴዎቹ ላይ የፈረደባቸው የመንገድ ዱርዬ ከሆነ እንደ መንግስት የማስተካከል ግዴታ አለባችሁ : አስተካክሉ : ለዚህም ነው ሀገር አቋርጠን የመጣነው : የምታስካክሉ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ ሳይመሸ አስተካክሉ : እኔ እንደሆነ ነፍሴ በራሷ ሠዐት አጀሏ እየደረሰ ነው። ምንም የምፈራው ነገር የለም። እዚህ ምላሳችሁን ለማጣፈጥ የምትሞክሩ ስትወጡ ምላሳችሁ ሌላ ነው እኔ ግን እዚህ ም እዚያም አንድ ነኝ : በማለት ድንቅ ንግግር አድርገዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የኦሮሚያ ወጣቶች ላይ መንግስት በተለያየ ወቅት :በተለያየ ምክንያት :የወሰዳቸውን እርምጃዎች በተመለከተ፣ መንግስት በጋዜጠኞች ላይ እያደረሰ ያለውን እስራትና ማሳደድ በተመለከተ ፣ የመሬትንና ማሰተር ፕላኑን በተመለከተ : ጥያቄዎች ለባለስልጣኑ የቀረቡላቸው ሲሆን : ከባለስልጣኑ የተሰጠው መልስ: እንደተለመደው አለባብሶ የማለፍ ዘዴ መሆኑንና : የመሬትን የኮንዲኒየም ቤትን በተመለከተ ግን : እንደማንኛውም ዜጋ አስፈላጊውን ምዝገባና ፎርማሊቲ ካሟሉ ብቻ : ሊያገኙ እንደሚችሉ እንደተገለፀላቸው ምንጮቻችን አያይዘው ዘግበዋል ።
በእለቱ የኦሮሞ ዲያሰፖራ አባላት እንደ ሙስሊምነታቸውና :እንደ ኦሮሞነታቸው: በቂና የሚያኮራ ስራ እንደሰሩ ምንጮቻችን አያይዘው ገልፀዋል።
ስብሰባው ለሁለተኛ ቀን የቀጠለ ሲሆን: በእለቱ በመጀመሪያው ቀን ስብስባ ላይ ድንቅ: ንግግር ያደረጉት የሜኒሶታው ሽማግሌ አባት : ንግግር ለማድረግ (ጥያቄ ለመጠየቅ) እጃቸውን በተደጋጋሚ ቢያወጡም በመጀመሪያው ቀን ስብሰባ ላይ :ያደረጉትን ምርጥ ንግግር : ያልወደዱላቸው ባለስልጣናት: እድል ስለከለከሏቸው ተበሳጭተው : ብድግ ብለው በመነሳት : ከሰብሳቢዎች አንዱ የሆነውን አብዱልዐዚዝ የተባለውን ባለስልጣን “Shame on you ” Shame on you ” በማለት የሰራውን ተገቢ ያልሆነ ስራ ፊት ለፊት ተቃውመውታል ።
መንግስት መላውን ኢትዮዺያዊ የዲያስፖራ አባላት ለዲያስፖራ ሳምንት በማለት ስብሰባ እንደጠራ የሚታወቅ ሲሆን በሰብሰባው የሚሳተፋ ተሳታፊዎች : ከኦሮሞ የዲያስፖራ አባላት ትምህርት በመውሰድ ድምፃቸውን በተገቢው መንገድ እንዲያሰሙ ምንጮቻችን አጥብቀው አደራ ብለዋል ።

Health: ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ 5 የስኳር ሕመም ምልክቶች

$
0
0

suger
(በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም)
የስኳር ሕመምን በተመለከተ በተለያዩ የጤና ምክር መስጫ ፕሮግራሞች ላይ ሰፋ ያለ ግንዛቤ የማስጨበቻ ሥራዎች እየተሰሩ ናቸው፡፡
ከዚህ በታች ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የሕመሙን ጠቋሚ ምልክቶች እንግራችኋለሁ፡፡ ስለስኳር ሕመም በዝርዝር በቅርቡ የሚያስገባችሁ ይሆናል፡፡
1) ከተለመደው ጊዜ በተለይ ውሃ መጠማትና በተደጋጋሚ የውኃ ሽንት መምጣት፡፡
የስኳር ሕመም ለኩላሊት ችግር በማጋለጥ ቀዳሚ ደረጃን የሚይዝ ሲሁን በደምውስጥ የሚገኝ የስኳር መጠን መጨመር የኩላሊት ሥራ ያዛባል፡፡
2) የድካም ስሜት መሰማት
የስኳር ሕመም ከፍተኛ የድካም ስሜትን ያስከትላል፡፡ የሰውንት ክብደት መጨመር በራሱ ለስኳር ሕመም ከማጋለጥ ባለፈ የድካም ስሜት እንዲበረታ ያደርጋል፡፡
3) የዓይን ችግር
ማናኛውም ዓይነት የዓይን ችግር የስኳር ሕመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል ጊዜ ሳይሰጡ ወደ ሕክምና ቦታ በመሄድ ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
የስኳር ሕመምተኞች ለግላውኮማ የመጋለጥ ዕድላቸው ስለሚጨምርና በካታራክት (በዓይን ሞራ) ሊጠቁ ስለሚችሉ የዓይን ሕመም ከተሰማ ወደ ሕክምና ቦታ መሄድ ይመከራል፡፡
4) የእግር መደንዘዝ
የስኳር ሕመም የነርቭ ጉዳትን ያስከትላል፡፡ ይህም ጉዳት በአብዛኛው የሚከሰተው በእጃችንና በእግራችን ላይ ባሉ ነርቮች ላይ ነው፡፡ በነርቭ ወይንም በደም ሥር ላይ የሚደርስ ጉዳት የእግር መደንዘዝ ቀጥሎም የሕመም ስሜትን ያስከትላል፡፡ ሕመሙ በጊዜ ብዛት እየባሰ የሚሄድ ሲሆን መጠጥ እና ሲጋር ማጨስ ሕመሙን ያባብሰዋል፡፡
5) የቆዳ ላይ ኢንፌክሽንና በቶሎ የማይድን ቁስለት
የስኳር ሕመም ቆዳችንን ጨምሮ ማንኛውንም የሰውነት ክፍላችንን ሊጎዳ ይችላል እንዲያውም የስኳር ሕመም ያለበት ሰው በቀላሉ በባክቴሪያ እና በፈንገስ የሚመጣ ለቆዳ ላይ ኢንፌክሽን ያጋልጣል እነዚህም ኢንፌክሽኖች ቁስለትን ያስከትላሉ በቶሎ ሊድኑም አይችሉም፡፡
ጤና ይስጥልኝ

ለኢትዮጵያዊውስ ማን አለው?

$
0
0

በያሬድ ታዬ መኮንን፤ ቶሮንቶ

ቶሮንቶ ከመጣሁ ሶስተኛ ሳምንቴን ያዝኩኝ፡፡ ቀኑን ሙሉ፤ ከሰሜን ደቡብ፤ ከምስራቅ ምእራብ ሳካልለው ውዬ፤ መጀመሪያ በጓደኛዬ ቤት፤ አሁን ደግሞ መንግስት በሰጠኝ፤ በቶሮንቶ፤ ኦንቴርዮ ጎዳና ላይ በሚገኘውና እኔና ሌላ አንድ ሰው በምንጋራው ክፍል ጣሪያ ስር ሆኜ፤ ወደጣሪያው አንጋጥጬ፤ የኢትዮጵያና የካናዳ ህይወቴን፤ እንዲሁም ነጻነቴን ማሰላሰል ይዣለሁ፡፡ ነጻነት እንዴት ይጥማል፡፡ ድህነት አንድ ነገር ነው፡፡ መራብም አንድ ነገር ነው፡፡ ሰው ግን ነጻነቱንና ክብሩን እንዴት ባገሩ ይነፈጋል፡፡ እነሆ በማያውቁን፤ በማላውቃቸው፤ በሰው አገር የተሰጠኝን ክብርና እንክብካቤ እያጣጣምኩ ሳለሁ፤ የሩቅ ጓደኛዬ የነገረኝ ታሪክ ትዝ አለኝ፡፡  ይህ የሩቅ ጓደኛዬ አውነተኛ ታሪክ ነው ብሎ ያጫወተኝን፤ እኔም የተቀበልኩትን ገጠመኝ ላጫውታችሁ፡፡

federalእውነት መሆኑን እንዴት ተቀበልከው፤ ያላችሁኝ እንደሆነ ኢትዮጵያ ሃገሬ ውስጥ እንኳን ይሄ ይቅርና፤ ወያኔ “ተቃዋሚዎችም መርጠውኛል”  ብሎን ተቀብለነው የለም እንዴ? መቼ ነው ያለው፤ ለምትሉኝ ደግሞ አሁን ባሳለፍነው ምርጫ 2007፤ በአይኔ ያየሁት፤ ምናልባትም ብዙዎቻችሁ በሶሻል ሜዲያ ያነበባችሁ፤ እና ያሰገረማችሁ የምርጫ ውጤት እንደሚያሳየው፤ በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች፤ ከ1000 መራጮች መካከል ኢህአዴግ፤ 1000 ከ1000 ተብሎ በምርጫው ጣቢያ ሲለጠፍ፤ አስቡት እንግዲህ፤ ይህ 1000 መራጭ የተቃዋሚ ተመራጭ ተወዳዳሪዎችን ጨምሮ መሆኑን፡፡ እንግዲህ ይህንንም አምነን “አሜን” ብለን ተቀብለን የለም ወይ? እንግዲህ የጓደኛዬንም የህይወት ገጠመኝ አምኜዋለሁ፡፡

የወያኔን ጉድ እስቲ ይሁን ብለን እንለፈውና ወደዋናው ታሪክ እንመለስ፡፡ በነገራችን ላይ ስም መጥቀስ ስላላስፈለገኝ፤ ጓደኛዬ እያልኩ በመተረኬ፤ ቅር አይበላችሁ፡፡ ያው እንደምታውቁት ጊዜው አስቸጋሪ ስለሆነ ስም ባይጠቀስ ይሻላል ብዬ ነው፡፡

ይህ ጓደኛዬ እና አንድ የስራ ባልደረባው ከስራ በኋላ መሸትሸት ሲል ለመዝናናት፤ 22 አካባቢ ወደሚገኙት የመዝናኛ ቤቶች ጎራ ይላሉ፡፡ ከአንዱ ቤት ወደ ሌላኛው በመቀያየር ሲዝናኑ ይቆዩና፤ አትላስ አካባቢ ወደሚገኝ አንድ ታዋቂ የጭፈራ ቤት (በተለምዶ ክለብ) ይገባሉ፡፡ በክለቡ ውስጥ የተለያዩ ሰዎች የነበሩ ሲሆን፤ ከእነዚህም መሀከል ከወደምስራቅ አካባቢ የመጡም (በግምት ቻይናውያን ይመስሉታል) ነበሩበት፡፡ ሙዚቃው ቀጠለ፤ ጨዋታውም ደራ፡፡ መቼስ በዳንስ ውዝዋዜ መሀል መነካካት አይጠፋም፤ የጓደኛዬ ጓደኛ ከአንዱ ቻይናዊ ጋር ይነካካል፡፡ ከዚያም ይቅርታ ጠይቆ ጨዋታውን ይቀጥላል፡፡ ቻይናዊው ጉዳዩን በቀላሉ አልተመለከተውም፡፡ “ሳታውቅ ሳይሆን እንደው ነገር ስትፈልገኝ ነው” በማለት እምቧ ከረዮውን አቀለጠው፡፡ ሰዎች ነገሩን ለማረጋጋት ቢሞክሩም፤ አጅሬ ቻይና ካልደበደብኩት ብሎ ሰፈሩን ቀውጢ አደረገው፡፡ ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ መሆን በጀመረበት ሰዓት፤ የሀገሬው ፈላጭ ቆራጭ፣ ምንም ቢያደርግ ጠያቂ የሌለው፣ ማሰር፣ መደብደብ ካሻውም መግደል መብት የተሰጠው፤ መቼስ ታውቁታላችሁ ስለማን እያወራሁ እንዳለ፤ የወያኔ አካል የሆነው፡ ፈደራል ፖሊስ መጣ፡፡ ግርግሩም ቀዝቀዝ እያለ ሁሉም በመረጋጋት ስሜት ባሉበት ሁኔታ፤ ቻይናዊው ፌዴራሉን ሲመለከት የልብልብ ተሰምቶት ኖሮ፤ እጁን ሰንዝሮ የጓደኛዬን ጓደኛ በቡጢ ቢለውስ፡፡ ያኛውስ ከማን አንሶ በእጁ በሶ አልጨበጠ መልሶ ቢቦቅሰውስ፡፡ ታዲያ ይኽኔ ነበር ግራ የሚያጋባውና ማንነትን የሚፈታተነው ጉዳይ የተከሰተው፡፡

እንዲህ ነው የሆነው፡፡ ከፌዴራል ፖሊሶቹ መሀከል ሁለቱ ተንደርድረው መሃል በመግባት አንደኛው ቻይናዊውን ወደ ጎን ሲያደርገው፤ ሌላኛው የጓደኛዬን ጓደኛ በዚያ በያዘው የሚያቃጥል ቆመጥ (መቼስ የቀመሰ ያውቃታል) ሲዠልጠው ለተመለከተ ማንኛውም ሰው፤ እጅግ በጣም አስገራሚና አሳዛኝ ነበር፡፡ ቻይናዊውም ለካስ ይኼን አውቆ ኖሯል እንደዛ የልብልብ ተሰምቶት ቦክስ የሰነዘረው፡፡ ለጓደኛዬ ጉዳዩን ዝም ብሎ መመልከት አልሆንለት ቢለው፤ ጠጋ ብሎ በልመና መልክ ለማግባባት እየሞከረ፤ “ኽረ እባካችሁ ተውት እሱ ምንም አላጠፋም” በማለት ለማስረዳት ቢሞክር፤ አንተስ የት ይቀርልሃል ብለው ያላንዳች ማመንታት የዚያች ቆመጥ ተቋዳሽ በማድረግ፤ ሦስት አራት ጊዜ ካቀመሱት በኋላ፤ ቻይናዊውን በክብር ከይቅርታ ጋር ወደ ውስጥ እንዲገባ በምልክት (ያው እንደምታውቁት ቋንቋ ችግር ነው) ይነግሩት እና ጓደኛዬን እና ጓደኛውን በያዙት ፒክ አፕ መኪና ጭነው ወደ ፖሊስ ጣቢያ፡፡

ለመዝናናት የወጡት እኚህ ኢትዮጵያውያን፤ በገዛ ሀገራቸው ክብር ተነግፏቸው፤ ለውጭ ዜጋ ጎንበስ ቀና ባለማለታቸው የመዝናኛ ጊዜያቸውን በፖሊስ ጣቢያ አሳልፈው፤ እንዲህ አይነት ነገር እንዳይለመዳቸው ከማስጠንቀቂያ ጋር በበነጋታው መለቀቃቸውን የነገረኝ፤ እጅግ በንዴት እና በቁጭት መንፈስ ነበር፡፡ እንዲህ አይነት ክስተቶች በተለያየ መንገድ ያጋጠመን ሰዎች እንኖር ይሆናል፡፡ ያላጋጠማችሁም ወደፊት ቢያጋጥማችሁ ግር አይበላችሁ፡፡ እንደው ነገርን ነገር አነሳውና ነው እንጅ፤ ከዚህም የባሰ ብዙ አይተናል ሰምተናል፡፡

ሁሌም ውስጤን የሚያንገበግበው ነገር ቢኖር፤ ቢያንስ ለሌሎች ዜጎች ሀገራችን ላይ የሚሰጣቸውን ክብር ያክል እንኳን ሰው በሀገሩ የማይሰጠው ከሆነ ለኢትዮጵያዊውስ ማን አለው? ማንስ አለሁልክ፤ አይዞህ ይለዋል?

ሁሉም ነገር ከራስ ነው የሚጀምረው የሚል እምነት አለኝ፡፡ ፍቅርም ቢሆን፣ አክብሮትም ቢሆን ለራስ ሰጥቶ ነው ወደሌላኛው የሚኬደው፡፡ እራሱን እና የራሱ የሆነውን የማያከብር፤ ሌላውን አከብራለሁ እጠብቃለሁ ቢል፤ ለእኔ እንደማስመሰል ነው የምቆጥረው፡፡ እዚህ ላይ የሌላ ሀገር ዜጎች አይከበሩ እያልኩኝ አይደለም፡፡ ነገር ግን ሰው ከሀገሩ የበለጠ ጥበቃ እና ከለላ ሊያገኝ የሚችልበት የተሻለ ቦታ የት ነው ያለው? ያደጉት እና እኛን ጥለው የሄዱት ሀገራት ከሀገራቸው አልፈው በሰው ሀገር ስለሚገኙት እያንዳንዱ ዜጎቻቸው ክትትል በማድረግ፤ ያሉበትን ሁኔታ ሰላማዊነት ሲያረጋግጡ የምንመለከተው ጉዳይ ነው፡፡ ይህን ማድረግ ካለንበት ነባራዊ ሁኔታ አንፃር አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ ሀገራችን ውስጥ ግን ለሚከሰተው ማንኛውም ጉዳይ የዜጎቹን መብት ሊያስከበር የሚችል ስራ የመስራት ግዴታ የመንግስት አንዱ ሃላፊነት ነው ብዬ አስባለሁ፡፡

ሰው ሀገር አለኝ ብሎ በሀገሩ ሰርቶ እና ተለውጦ፣ የዘር፣ የጎሳ፣ እንዲሁም የቀለም ልዩነት ሳይገጥመው መኖር ካልቻለ፤ ከመሰደድ ውጭ ምን አማራጭ ይኖረዋል? አስቡት እስቲ በሀገሩ ክብር ተነፍጎት በሰው ሀገር ተከብሮ የሚኖረውን ስትመለከቱ ምን ይሰማችኋል? እንደው ወያኔ የሀገር ትርጉም አልገባውም እንጂ ቢገባው ኖሮ ይሄንን ግጥም ያዜምልን ነበር፡-

ሀገርን ሀገር ያሰኘው
ሰው የተባለው ፍጡር  ነው!

ያሬድ ታዬ መኮንን፡ ሀምሌ/ነሀሴ፤ 2015፡ ቶሮንቶ


አዳፍኔ ፍርሃትና መክሸፍ በእኔ ዕይታ!

$
0
0

adafne
በአብርሃም በዕውቀት
እርግጥ ነው ፕሮፌሰርን ለመተቼት የሚመጥን ቀርቶ ሊመጥን የሚጠጋ የዕውቀት ልክ ላይኖረኝ ይችላል፡፡ ለዚያውም ከፕሮፌሰርነታቸውም በላይ ሕይወት ያስተማራቸውንና በተቃውሞ ፖለቲካው ጫፍ የወጣ ዕውቅና ያላቸውን ፕሮፌሰር ጽሑፍ መንቀፍ በፌስቡክ ዳኞች በስቅላት ሁሉ ሊያስቀጣ ይችላል፡፡ ኧረ ራሳቸውም ሊሰቅሉኝ ባይችሉም ሊያሳቅሉኝ ይችላሉ፡፡ በእርግጠኝነት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምን ለመተቼት መሞከር የሚያስከትለውን ዘለፋና ነቀፌታ በሚገባ አውቀዋለሁ፡፡ ምክንያቱም እርሳቸው ከአገራችን ፊደላውያን መካከል ቁንጮ ናቸውና፡፡ ነገር ግን ፈርቶ ከመሞት ተናግሮ መሞት ይሻላል ብዬ ትችቴን ልቀጥል መሰለኝ? በቃ እንዲያውም ቀጠልኩ፡፡
ፕሮፌሰሩ ባለፈው ግንቦት ወር አዳፍኔ ፍርሃትና መክሸፍ የሚል መጽሐፍ ለገበያ አብቅተዋል፡፡ በነገራችን ላይ ፕሮፌሰር መስፍን በፈረንጅ ቋንቋ ሶስት አራት ‹‹ጆርናል›› ጽፈው የሚኮፈሱ ምሁራንን የሚያስከነዱ ቁጥራቸው በርከት ያሉ መጻሕፍትን ለኢትዮጵያውያን በራሳቸው ቋንቋ የሚጽፉ ሰው ናቸው፡፡ በዚህ ሥራቸው በእጅጉ አመሰግናቸዋለሁ፤ አደንቃቸዋለሁ፡፡
ሌሎቹ የአገራችን ፊደላውያን ቀደም ሲል እንደገለፅኩት ጥቂት ‹‹ጆርናሎችን›› በተለያዩ ርዕሶች ላይ ከመጻፋቸው ውጭ ለዚያውም ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውጭ አንባቢም ተጠቃሚም በሌላቸው ጭብጦች ላይ በአማርኛ ቋንቋ አንዳች ነገር ሲፅፉ አይታዩም፡፡ ለዚህም ነው ምሁራን ከማለት ተቆጥቤ ፊደላውያን የምላቸው፡፡ የፊደል እንጅ የተግባር ዕውቀት ስለሌላቸው፡፡

ወደ ተነሳሁበት የፕሮፌሰር መስፍን መጽሐፍ አዳፍኔ ፍርሃትና መክሸፍ ልመለስ፡፡ መጽሐፉ ዋነኛ ትኩረቱ ከዚህ በፊት ‹‹መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ›› በሚል ያሳተሙትንና በብዙዎቹ ዘንድ የተቃውሞ አቧራ ያስነሳውን መጽሐፍ ነቀፌታዎች ለማብራራትና አንዳንድ ተችዎችንም ልክ ለማስገባት የተፃፈ ይመስላል፡፡
በመጽሐፉ ገፅ 27 ሁለተኛው አንቀፅ ላይ ‹‹መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክን ስፅፍ በኢትዮጵያዊነቴ መንፈስ ተይዤ ነው፤ ይህንን መካድ አልችልም፤ ከሰማይ እንደወረደ ሰው ሆኜ ስለኢትዮጵያ ታሪክ መጻፍ እችላለሁ የሚል ኢትዮጵያዊ ታሪክ ጸሐፊ (ወይም የታሪክ ተመራማሪ) ካለ የሚናገረውን የሚያውቅ አይመስለኝም፤ ከኢትዮጵያዊ ትውልዴ፣ ከኢትዮጵያዊ አስተዳደጌና ስሜቴ፣ ከበርበሬው መፋጄትና ከቡናው ትኩስነት ራሴን ሙሉ በሙሉ አግልዬ ስለኢትዮጵያ መናገር እችላለሁ ብዬ አልዋሽም›› የሚሉት ፕሮፌሰሩ በእኔ ዕይታ የዚህ ዘመን ታሪክ ፅሐፊዎችም እንደ ድሮ ግለ-ታሪክ ፀሐፊዎች (chroniclers) ሁሉ ገለልተኞች (objective) አይደሉም እያሉ ነው የሚል ድምዳሜ ደርሻለሁ፡፡ ስለዚህ መጽሐፉ ከስሜታዊነት አልፀዳም፤ ታሪክ አይደለም፤ ከሽፏል፡፡

በእርግጥ መጽሐፉ እርሳቸው ስለመክሸፍ የሰጡትን ትርጓሜና የክሽፈታችን ማስረጃዎች ናቸው ያሏቸውን ሀሳቦች በጥልቀት ለማብራራት ይሞክራል፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን እንደሚሉት በተለይ ዓድዋ ላይ በዓፄ ምኒልክ ዘመን ድል ያደረግነውና ዓለምን ያስደመምንበት ጣሊያን ከአርባ ዓመታት ዝግጅት በኋላ በዓፄ ኃይለስላሴ ዘመን ከ1928 ዓ.ም እስከ 1933ዓ.ም ድረስ ድል አድርጎናል፤ እኛ ግን በአርባ ዓመታት ውስጥ ከመሻሻል ይልቅ ስንበሰብስ ቆይተናል ይላሉ፡፡ እዚህ ላይ ለፕሮፌሰር ጥያቄ ላንሳ፤ ‹‹ዓድዋ ላይ ጣሊያንን ያሸነፍነው በስልጣኔና በጦር መሳሪያ በልጠነው ስለነበር ነው?›› እንደኔ አይደለም፡፡ ይህ ለፕሮፌሰር ይጠፋቸዋል ብዬ ባልጠብቅም ጳውሎስ ኞኞ ‹‹አጤ ምኒልክ›› በሚል ባሳተመው መጽሐፍ ገፅ 159 ጀምሮ እንዳስቀመጠው ኢትዮጵያውያን ወደ ዓድዋ ዘመቻ ሲሄዱ 42 መድፎች ብቻ ነበሯቸው፡፡ ይህ ቁጥር ከኢጣሊያ ዘመናዊ የተራራ መድፍ ጋር አይወዳደርም ሲልም ይገልፃል፡፡ በሰራዊት ቁጥር ደረጃ በአንፃሩ ኢትዮጵያውያን እጅግ ብዙ ነበሩ፡፡

ጳውሎስ ኞኞ በመጽሐፉ እንዳስቀመጠው የኢጣሊያ ጦር ብዛት ከ20ሺህ የማይበልጥ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ በኩል ግን ንጉሠ ነገሥቱ ዓፄ ምኒልክ የመሩት ጦር ብቻ 30ሺህ እግረኛ እና 12ሺህ ፈረሰኛ ነበረው፡፡ ራስ ሚካኤል ደግሞ ስድስት ሺህ አግረኛ እና 10ሺህ ፈረሰኛ ጦር ይዘው ዘምተዋል፡፡ በአጠቃላይ በዓድዋው ጦርነት በኢትዮጵያ በኩል 120ሺህ እግረኛ እና 28ሺህ ፈረሰኛ ጦር ተሰማርቷል፡፡ በሰው ደረጃ ሲቆጠር ዓድዋ ላይ 148ሺህ ሕዝብ ዘምቷል፡፡ በንፅፅር ሲታይ ለአንድ የኢጣልያ ወታደር ቢያንስ ሰባት ኢትዮጵያውያን ተመድበው ነበር ማለት ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ያኔ ኢጣሊያን ያሸነፍነው በቴክኖሎጂና በወታደራዊ ስልት በልጠን ነበር ወይ? ካልሆነ የኋለኛው ሽንፈታችን እንዴት ክሽፈት ሊሆን ይችላል? ከዕድለ-ቢስነት ውጭ!

ሁለተኛውን የኢጣሊያ ወረራ ስንመለከት ደግሞ አንድርዜይ ባርትኒስኪ እና ዮዓና ማንቴል-ኒየችኮ ጽፈውት አለማየሁ አበበ ወደ አማርኛ የመለሰው ‹‹የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጄመሪያው እስከ አሁኑ ዘመን›› የሚለው መጽሐፍ ላይ ከገፅ 508 ጀምሮ እንደተብራራው የኢጣልያ ጦር ብዛት ተጠባባቂውን ጨምሮ 500ሺህ ያህል ነበር፡፡ በኢትዮጵያ በኩልም በእርግጥ 600ሺህ ያህል የሰው ኃይል ለጦርነቱ ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ ኢጣሊያዎቹ በዘመናዊ የጦር መሳሪያ፣ ታንክና በበርካታ የጦር አውሮፕላኖች የሚታገዙ የነበሩ ሲሆን ኢትዮጵያውያኑ ግን ከግማሽ የማያንሱት ቆመጥ የታጠቁ ነበሩ፡፡ እንግዲህ በሁለተኛው የኢጣሊያ ወረራ ወቅት የጦር መሳሪያ ቴክኖሎጂዎችን ደረጃ ማወዳደሩን ትተን በሰው ኃይል ብቻ እንኳ ብናወዳድረው ንፅፅሩ አንድ ለአንድ ነበር ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከዓድዋው የአንድ ለሰባት ጥምርታ በጣም ያነሰ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ታዲያ በዚህ ሁኔታ መሸነፍ መክሸፍ ነው ፕሮፌሰር?
ሌላው ለፕሮፌሰሩ ማንሳት የምፈልገው ጥያቄ ከዓፄ ቴዎድሮስ ሽንፈትና ከዓፄ ዮሐንስ ጋር በተያያዘ ነው፡፡ በመጀመሪያ ግምቴን ሳስቀምጥ ፕሮፌሰር መስፍን ለዓፄ ዮሐንስ 4ኛ ያላቸው አመለካከት ግብዝነት ያለበት (stereotype) ይመስለኛል፡፡ የውጫሌ ውል እ.ኤ.አ ግንቦት 2 ቀን 1889 ቦሩ ሜዳ አጠገብ በምኒልክና በኢጣሊያ መካከል ተፈረመ፡፡ ዓፄ ምኒልክ ውሉን መፈረማቸው ስህተት መሆኑን እ.ኤ.አ መስከረም 27 ቀን 1890 የአንቀፅ 17ን የጣሊያንኛ ትርጓሜ ስህተት መሆን በመጥቀስ ለኢጣሊያ ስህተት መሆኑን በደብዳቤ ጽፈው አሳወቁ፡፡ ውሉን እንደማይቀበሉት ለአውሮፓ መንግስታት ይፋ ያደረጉት ግን አምስት ዓመታትን ዘግይተው ነበር፡፡ ከዚያ ዓፄ ምኒልክ የውጫሌ ስህተታቸውን ያረሙት ስህተቱን ከፈፀሙ ከ8 ዓመታት በኋላ አሁንም በአውሮፓውያኑ መጋቢት 01 ቀን 1896 ዓድዋ ላይ ባስመዘገቡት ድል ነበር፡፡

ነገር ግን ፕሮፌሰር መስፍን ዓፄ ዮሐንስን በመጽሐፋቸው (አዳፍኔ ፍርሃትና መክሸፍ) ገፅ 15 ላይ ሲነቅፉ ‹‹አጼ ምኒልክ በውጫሌ ውል የሠሩትን ስህተት በአድዋ ላይ አርመውታል፤ አጼ ዮሐንስ ግን ከእንግሊዞች ጋር ባደረጉት ውል የተሠራውን ስህተት ማረም አልቻሉም፡፡›› ይላሉ፡፡ አሁንም ጥያቄን ላንሳ፤ ዓፄ ዮሐንስ ከእንግሊዝ ጋር እ.ኤ.አ በሰኔ 03 ቀን 1884 ዓድዋ ላይ የተፈራረሙትን ውል ስህተት ለማረም እንደ ምኒልክ 8 ዓመት ነበራቸው ወይ? ሌላው ጥያቄ ደግሞ እንግሊዞች ቴዎድሮስን ለመውጋትና ዜጎቻቸውን ለማስፈታት ወደ መቅደላ ሲመጡ የተባበሯቸው ብቸኛ የቴዎድሮስ ጠላት ተደርገው በፕሮፌሰሩ የቀረቡት በዝብዝ ካሳ (በኋላ ዮሐንስ 4ኛ) ናቸው፡፡ ፕሮፌሰሩ ዋግሹም ጎበዜን (በኋላ ተክለ ጊዮርጊስ) ረስተዋቸው ነው? ቀደም ሲል አለማየሁ አበበ ወደ አማርኛ መልሶታል ባልኩት የኢትዮጵያ ታሪክ መጽሐፍ ገፅ 282 ላይ እንደተገለፀው እንግሊዞች ወደ መቅደላ ሲገሰግሱ ዋግሹም ጎበዜ 60ሺህ ወታደሮች በስራቸው ነበሩ፡፡ ነገር ግን በእንግሊዞች ላይ ኮሽታ አላሰሙም፤ ለዚህ ውለታቸውም የወቅቱን መዲና መቅደላን በስጦታነት አግኝተዋል፡፡ ታዲያ ፕሮፌሰሩ ስለዓፄ ዮሐንስ 4ኛ ግብዝነት የጀቦነው ጥላቻ ባይኖርባቸው ኖሮ ስለምን እንግሊዞችን የደገፉ ብቼኛ ተጠያቂ ያደርጓቸዋል?

“አዳፍኔ፣ፍርሃትና መክሸፍ›› እርስ በእርስ የሚቃረኑ ሀሳቦችም አሉበት፡፡ ለምሳሌ በመጽሐፉ ገፅ 63 የመጨረሻው አንቀፅ ላይ ‹‹ትምህርት የአዳፍኔ ፀር ነው፤ ስለዚህም አዳፍኔም የትምህርት ፀር ነው›› ይላሉ፡፡ ገፅ 68 መካከለኛው አንቀፅ ላይ ሲደርሱ ደግሞ ‹‹በአጠቃላይ አዳፍኔ ባለበት የትምህርት መሣሪያነት በመጀመሪያ ለአዳፍኔ፣ ቀጥሎም ለቤተ ሃይማኖት ነው፤›› ይላሉ፡፡ መጀመሪያ ነገር አዳፍኔ ለትምህርት፣ ትምህርትም ለአዳፍኔ ፀር ከሆኑ አንዱ ለአንዱ እንዴት መሳሪያ ሊሆን ይችላል? አንዱ ለአንዱ መሳሪያ ሊሆን የሚችለው እኮ በሁለቱ መካከል የለበጣም ቢሆን ፍቅር ሲኖር ነው?
ፕሮፌሰር መስፍን ሲቀጥሉ በገፅ 114 ላይ ‹‹ወደጥሩው ለውጥ የሚወስደውን አቅጣጫ ለመያዝ የማያስችለው ጋሬጣ አዳፍኔ ነው፤ የአዳፍኔ ዋናው ሥራ ጤንነት፣ ዕውቀት፣ ትብብር፣ ብልፅግና፣ ማኅበራዊ ጥንካሬ እንዳይፈጠሩና ሕዝቡ ወይም ሕብረተሰቡ ደካማና ተስፋ ቢስ ሆኖ በቀላሉ ለመገዛት የሚመች እንዲሆን ነው›› ይላሉ፡፡ ለእኔ በገባኝ ልክ ፕሮፌሰሩ ‹‹አዳፍኔ›› የሚሉት ስርዓተ-መንግስቱን ወይም ገዥውን አካል ይመስለኛል፡፡ አሁን ወንዝ በበራፉ ዓመቱን ሙሉ የሚያልፍበት ሰው በንፅህና ጉድለት በሚመጣ በሽታ ቢጠቃ ስለምን አዳፍኔ ተጠያቂ ይሆናል? ወንዝ ዳር እየኖረ ጳጉሜን ጠብቆ የሚታጠብ ሰው ቢኖር ንፅህናውን አለመጠበቁ የግለሰቡ ድክመት እንጅ ‹‹የአዳፍኔ›› እጅ ነው ለማለት ምክንያት የለኝም፡፡ ለብዙዎቻችን እኮ ተንኮልና መጠፋፋትን የሚያስተምሩን ወላጆቻችን ናቸው፡፡ መሪዎችም እንደኛው ሰለሆኑ ወላጆች አሏቸው፤ የወላጆቻቸው የአስተዳደግ ውጤትም ናቸው፡፡ የብዙዎቻችን ወላጆች እኮ የሚመክሩን ‹‹ከጠላትህ ሳይሆን ከወዳጅህ ተጠንቀቅ›› ብለው ነው፡፡ ፀሎታችንም ‹‹አንተ ከወዳጄ ጠብቀኝ፤ ጠላቶቼን እኔ ነቅቼ እጠብቃለሁ›› የሚል ነው፡፡

በአገራችን ያሉ የተለያዩ የፈውስ መድኃኒቶችን የሚያውቁ የባሕል ሐኪሞች በብዛት ነበሩን፡፡ ነገር ግን እነዚህ አዋቂዎች በዕድሜ በጣም ሲገፉ ለአንድ በጣም ለሚወዱት ልጅ ከሚነግሩት በቀር ለማንም ቀርቶ ለሁሉም ልጆቻቸው መድኃኒቱን አያሳዩም፡፡ ይህ ዓይነት ግላዊ የተተበተበ የምቀኝነት አባዜ ባሕል በሆነበት ህብረተሰብ ውስጥ ያደገ አዳፍኔ ያልሆነ መሪም ሆነ ስርዓት እንዴት ሊገኝ እንደሚችል ፕሮፌሰሩ የጠቆሙት ነገር የለም፡፡ በእኔ እምነት ከማኅበራዊ ችግሮቻችን ተኮትኩተው የሚያድጉ ችግሮቻችንን ፖለቲካዊ ያደረጓቸው ይመስለኛል፡፡ አዳፍኔ ሕዝብን ተስፋ ቢስ ቢያደርግ ኖሮ ስለምን በደርግ የጭፍጨፋ ዘመን ሕዝቡ ተስፋ ቆርጦ ፀጥ ረጭ ብሎ አልተገዛም፡፡ እንዲያውም ሕዝብ እንደሕዝብም ተስፋ አይቆርጥም የሚል አቋም አለኝ፤ ተስፋ መቁረጥ የሚመነጨው ከአዕምሮ ስለሆነና የወል የሆነ ሕዝባዊ አዕምሮ ስለሌለ፡፡ አዕምሮ ያለው በግለሰብ ደረጃ ነው፤ ስለዚህ ተስፋ የሚቆርጠውም ተስፋ የሚያደርገውም ግለሰብ ነው፡፡

ሌላው ፕሮፌሰር መስፍን ስለታሪካችን ሲፅፉ በገፅ 117 ላይ ‹‹ማርቲን በርናል የተባለ ሊቅ የተማርነውን ሁሉ ገለበጠው፤ የሴም ቋንቋዎች ከኢትዮጵያ ወደ ባሕር ማዶ ተሻገሩ እንጅ ከዚያ ወደዚህ አልመጡም አለ›› ይሉና ‹‹ባለፉት 27 ዓመታት ውስጥ የበርናልን ፈር ተከትሎ የኢትዮጵያን ታሪክ ተከትሎ የኢትዮጵያን ታሪክ ለመከለስ የሞከረ አንድም ባለሙያ መኖሩን አልሰማሁም፤ የታሪክ ተመራማሪ የሚባሉ ግን አሉ›› ሲሉ ይደመድማሉ፡፡ እርሳቸው እንዳሉት በርናል ጥናቱ የፈጄበት 10 ዓመት ነው፡፡ አስፈላጊና ትክክለኛ ሆኖ ካገኙት የሚያስኬድም ከመሰላቸው ስለምን እርሳቸው ሳይሞክሩት 27 ዓመታትን አሳለፉ? የታሪክ ተመራማሪ ከሚባሉት ውስጥ አርሳቸው የሉበት ይሆን ይሆን?
በነገራችን ላይ የፕሮፌሰር መስፍን አዳፍኔ የአርትኦት ችግሮችም አሉበት፡፡ መጽሐፉ በጥድፊያ የታተመ ይመስላል፡፡ በጥድፊያ አርትኦት ሳይሰራለት ለመታተሙ የሚያሳብቁ በርካታ የፊደል ግድፈቶች አሉበት፡፡ የፊደል ግድፈቶቹን እንተዋቸውና ያልተሟሉ መረጃዎችን እንኳ ለማሟላት ፕሮፌሰሩ ትዕግስት አልነበራቸውም፡፡ ለአብነት በገፅ 129 ላይ ሰንጠረጅ 2 (በሰንጠረጅ 1 ላይ የተመሠረተ) ተብሎ ዓመተ ምህረትና ክፍለ ሀገር (ጠቅላይ ግዛት) የተፃፈበት ነገር ግን ‹‹በሰንጠረጅ 1 ያለው የአርበኞች ስርጭት በመቶኛ›› ተብሎ ባዶ ሰንጠረዥ ታትሟል፡፡ መቼም ይህ ስህተት ለሕትመት ከመቻኮል ካልመነጨ በቀር አይከሰትም፡፡ ወይም ደግሞ ፕሮፌሰሩ ‹‹ከእኔ በላይ ላሳር›› ብለው ለማንም አርታኢ አላሳዩትም ማለት ነው፡፡ ምናልባት እንደርሳቸው በዓፄው ዘመን የተማሩ አርታኢዎች አጥተው ይሆን? እነማዕረጉ በዛብህ የእርሳቸው ዘመን ተማሪዎች አይሆኑ ይሆን?
ወደ መጨረሻ ማንሳት የምፈልገው ነጥብ ደግሞ ፕሮፌሰሩ ‹‹ከእኔ በላይ አዋቂ የለም›› ባይና ዘላፊ መሆናቸውን በመጽሐፉ ማንፀባረቃቸውን ነው፡፡ በመጽሐፋቸው ገፅ 73 ላይ ፕሮፌሰር ባሕሩን እንዲህ ይላሉ፡፡ ‹‹ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ አንድ አስተማሪ ያስታጠቀውን ጉዳይ ይዞ አንድ መጽሐፍ አሳትሟል፡፡›› በተለይ በ‹‹መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ›› መጽሐፍ ላይ አስተያዬት የሰነዘሩ ሰዎችማ የስድብ ናዳ ወርዶባቸዋል፤ ዳግመኛ ለሂስ ብዕራቸውን የሚያነሱም ሆነ አንደበታቸውን የሚከፍቱ አይመስልም፡፡ ብርሃኑ ደቦጭ የተባለውን ተች ‹‹እንግሊዝኛን በአማርኛ ፊደል መጻፍ የሚችል መሆኑን አወቅሁለት›› ሲሉ አጣጥለውታል፡፡ እርሳቸው ታምራት ነገራን ሲወርፉ ከገፅ 214 ጀምሮ ‹‹ፓራግራፍ›› እያሉ እንደጻፉት የሚጽፍ ለማለት ፈልገው ይመስለኛል፡፡

ዳንኤል ክብረት በፕሮፌሰር መስፍን ከገፅ 222 ጀምሮ እንደወፍጮ በተደጋጋሚ የተወቀረ ተች ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ ‹‹ያውቃል እንዲባል የሚፅፍ እንጅ አውቆ የሚጽፍ አይመስልም›› በሚል ውረፋ የጀመሩት ፕሮፌሰር ‹‹የዩኒቨርሲቲን ዓለም የማያውቁ ሰዎች ሌላ ትርጉም በመስጠት እንዳይሳሳቱ ማስጠንቀቅ ያስፈልጋል፣ በአካል ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሆነው ልባቸው ከደብተራ ተንኮል ላልፀዳም ቀናውን የእውነት መንገድ እንዲያመለክታቸው እመኛለሁ›› ሲሉም አስከተሉ፡፡ ‹‹ይህ ሰው አንብቤአለሁ ሲል በመሀይም ድፍረት ነው›› የሚል ውረፋም ተመርቆለታል፡፡ የዳንኤል ክብረት የዲቁና ማዕረግም በፕሮፌሰር መስፍን ስልጣን ተገፍፏል፡፡ ምክንያት ያሉት ደግሞ ‹‹እኔ እንደማውቀው ዲያቆን ሶስት ደረጃዎች ሲኖሩት የዲያቆኖች አለቃ ሊቀ ዲያቆናት ይባላል፤ አቶ ዳንኤል ሊቀ ዲያቆናትም አልሆነም፤ የአቶ ዳንኤል ዲያቆንነት የቱ ዘንድ እንደሚወድቅና ምን ማለትም እንደሆነ አላውቅም›› ይላሉ፡፡ ዲያቆንነት ሶስት ደረጃዎች ካሉት ዳንኤል ክብረት ሊቀ ዲያቆን ካልሆነ ቀሪዎቹን ሁለት ደረጃዎች ሊሆን እንዳማይችል ግን ፕሮፌሰር መስፍን ግልፅ አላደረጉትም፡፡ በነገራችን ላይ ዳንኤል ብቻ ሳይሆን የዳንኤል ደጋፊዎች የተባሉትም በአዳፍኔ ስድብ ተዳፍነዋል፡፡

የአንተ አሽከር፣ የአንተ ቡችላ፤
ኩፍ ኩፍ ይላል እንደጉሽ ጠላ!

የሚል ስንኝም ተቋጥሮላቸዋል፡፡ ብቻ በአዳፍኔ ብዙ የተዳፈኑ ነገሮችንም አንብቤያለሁ፡፡ ፕሮፌሰሩ እንዲህ ተሳዳቢ መሆናቸውን አላውቅም ነበር፡፡ ከደርግም ሆነ ከኢህአዴግ አባላትም ሆነ ደጋፊዎች አንድም ምሁር ሰው አለመኖሩንም ፕሮፌሰሩ በልበ-ሙሉነት ያስረዳሉ፡፡ ምሁራኑ በአዳፍኔ ተዳፍነዋል፤ አዳፍኔና ዕውቀት ተፃራሪ ናቸውና፡፡ ሁለት ትልልቅ ትምህርቶችንም በአዳፍኔ ፍርሃትና መክሸፍ ውስጥ አግኝቻለሁ፡፡ አንደኛው ኢትዮጵያ ውስጥ ሙስናን ማስቀረት ከባድ መሆኑን፤ ገፁንና ቃላቱን አንድ ባንድ ባላስታውሰውም ‹‹ኢትዮጵያውያን ፈጣሪያቸውን ጭምር በሙስና ውስጥ ለመክተት ስለት የሚሳሉ ሰዎች ናቸው›› ያሉትን የፕሮፌሰር ሀሳብ በጣም ወድጄዋለሁ፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የተራደሁት ነገር ቢኖር ሰዎችን አንድ ባንድ እያነሱ በመሳደብ መጽሐፍ ማሳተም እንደሚቻል ነው፡፡ ሶስተኛ ቁም ነገር ልጨምር ካልኩ ምሁር ለመባል ወይ በንጉሱ ዘመን መማር አሊያ በፕሮፌሰር መስፍን ጽሁፎች ላይ እንደነማዕረጉ በዛብህና ማስረሻ ማሞ የፕሮፌሰሩን ሀሳብ ደጋፊ አስተያዬት ብቻ መስጠት ያስፈልጋል፡፡ ካልሆነ የዳንኤል ክብረት፣ የኢህአዴግና የደርግ ምሁራን እጣ ፋንታ ገጥሞህ ከ8ኛ ክፍል አላለፈም ትባላለህ፡፡

በመጨረሻም በእርግጥ ይህንን በማለቴ ፕሮፌሰር መስፍን እንደ ዳንኤል ክብረት በስድብ ናዳ መቀመቅ ሊያወርዱኝ ይችላሉ፤ እንደምንም የተማርኳቸውን ሁለት ዲግሪዎችም ወደ ሁለተኛ ክፍል ሊያወርዷቸው ይችላሉ፤ ለነገሩ ከመጀመሪያውም የዚህን ዘመን ተማሪዎች ዕውቅና አልሰጡንም፤ ማን ያውቃል የአዳፍኔ ማዳፈኛ ብለው ሌላ የስድብ መጽሐፍ እንዲጽፉም መነሻ ልሆናቸው እችል ይሆናል፤ ምናልባት ፌስቡክ ላይ እንደኔ አይጣዱ እንደሆነ ደግሞ ላያነቡትና ምንም ላይቀየሙኝም ይችላሉ፡፡ የመጨረሻው ምኞቴ በሆነልኝ እንዳልል ‹‹ይኸው ፈራህ፤ ከሽፈሀል!›› ሊሉኝ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ የፈለጉትን ይበሉ፡፡

እነ ማቲያስ መኩሪያ ለነሃሴ 18 ተቀጠረባቸው

$
0
0

• አቶ ማሙሸት አማረ ለነሃሴ 20 ተቀጥሮበታል
አይ ኤስ አይ ኤስ በኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ ለመቃወም መንግስት በጠራው ሰልፍ ሰበብ የታሰሩት እነ ማቲያስ መኩሪያ ለነሃሴ 18/2007 ዓ.ም ተቀጠረባቸው፡፡ ፖሊስ በጊዜ ቀጠሮ ወቅት ‹‹የቪዲዮ ማስረጃም አለን›› በማለቱ ተከሳሾቹ ‹‹ቪዲዮው ይቅረብልን፡፡ የቪዲዮ ማስረጃው ለእኛም የመከላከያ ምስክርነት ይጠቅመናል›› ብለው ጠይቀው የነበር በመሆኑ፤ ፍርድ ቤቱ የቪዲዮ ማስረጃው መቅረብ እንዳለበትና እንደሌለበት ብይን ለመስጠጥ ለዛሬ ነሃሴ 5/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር፡፡ ይሁንና የመናገሻ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት የማይሰራ በመሆኑ ችሎቱ በአራዳ ፍርድ ቤት በተረኛ ዳኛ ታይቷል፡፡ የልደታ ፍርድ ቤትም ‹‹ጉዳዩ አልተመረመረም፡፡›› በሚል ብይን ለመስጠት ለነሃሴ 18/2007 ዓ. ቀጠሮ ሰጥተዋል፡፡

11855873_752610074864653_9011892683978376437_n
ፍርድ ቤቱ ቪዲዮው ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ሲሰጥ የዛሬው ለሶስተኛ ጊዜ ሲሆን ተከሳሾቹም እየተጉላሉ መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ ቅሬታ አቅርበዋል፡፡ አንደኛ ተከሳሽ ማቲያስ መኩሪያ ‹‹በቪዲዮው ጉዳይ ለመወሰን ለሶስተኛ ጊዜ ሲቀጠር ነው፡፡ እኛም ቤተሰቦቻችንም እየተጉላላን ነው፡፡›› ሲል ቅሬታውን አቅርቧል፡፡ በተመሳሳይ 2ኛ ተከሳሽ መሳይ ደጉሰው ‹‹ድሃ ቤተሰብ አለን፡፡ ቤተሰቦቻችን መርዳት እንዳንችል እየተጉላላን ነው፡፡›› ብሏል፡፡ በማቲያስ መኩሪያ መዝገብ የተከሰሱት 1ኛ ማቲያስ መኩሪያ፣ 2ኛ መሳይ ደጉሰው፣ 3ኛ ብሌን መስፍን፣ 4ኛ ተዋቸው ዳምጤ ሲሆኑ ከመሳይ ደጉሰው ውጭ ያሉት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ናቸው፡፡
በተመሳሳይ በአራዳ ፍርድ ቤት የአቃቤ ህግ ምስክሮችን ለመስማት ለዛሬ ተቀጥሮ የነበረው አቶ ማሙሸት አማረም ለነሃሴ 20/2007 ዓ.ም ተቀጥሮበታል፡፡ አቶ ማሙሸት የአቃቤ ህግ ምስክሮችን ለመስማት በተደጋጋሚ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ‹‹ምስክሮቹ ስላልተሟሉና ብዙ መዝገቦችም ስላሉ ምስክርነት መስማት አልቻልንም›› በሚል ምስክሮቹ ሳይሰሙ ቀርተዋል፡፡ በተጨማሪም የአንድነት አባልና የሚሊዮኖች ድምፅ ጋዜጣ አምደኛ የነበረው እስማኤል ዳውድ አራዳ ፍርድ ቤት ቀርቦ ለነሃሴ 28/2007 ዓ.ም ተቀጥሮበታል፡፡
ፍርድ ቤቱ ‹‹በክረምት ከማይሰሩ የተለያዩ ፍርድ ቤቶች መዝገቦች በመምጣታቸው ምስክር መስማት አልቻልንም፡፡ ስራ በዝቶብናል›› በሚል በበርካታ ተከሳሾች ላይ ረዘም ያለ ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን በተለይ በሰልፉ ሰበብ የታሰሩ ተከሳሾች በተለይም ሴቶች እና ቤተሰቦቻቸው የተፋጠነ ፍርድ ልናገኝ አልቻልንም በሚል ፍርድ ቤቱ ግቢ ውስጥ ሲያለቅሱ ተስተውለዋል፡፡

ምንጭ :-ነገረ ኢትዮጵያ

የፖለቲካ እስረኞች ፍትሕ ሳያገኙ በቀጥሮ እየተንገላቱ ነው

$
0
0

11705269_742488912543436_1050118275188445148_nነኅሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አይ ኤስ አይ ኤስ በኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ ለመቃወም መንግስት በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ሰበብ የታሰሩት እነ ማቲያስ መኩሪያ፣ ፖሊስ በጊዜ ቀጠሮ ወቅት ‹‹የቪዲዮ ማስረጃም አለን›› በማለቱና ተከሳሾቹ ‹‹ቪዲዮው ይቅረብልን፣ የቪዲዮ ማስረጃው ለእኛም የመከላከያ ምስክርነት ይጠቅመናል›› ብለው በመጠየቃቸው፣ ፍርድ ቤቱ የቪዲዮ ማስረጃው መቅረብ እንዳለበትና እንደሌለበት ብይን ለመስጠጥ ለዛሬ ነሃሴ 5 ቀን 2007 ዓ.ም. ቀጠሮ ቢሰጥም ፣ የመናገሻ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት የማይሰራ በመሆኑ ችሎቱ በአራዳ ፍርድ ቤት በተረኛ ዳኛ ታይቷል፡፡ የልደታ ፍርድ ቤትም ‹‹ጉዳዩ አልተመረመረም፡፡›› በሚል ብይን ለመስጠት ለነሃሴ 18 ቀን 2007 ዓ. ቀጠሮ ሰጥቷል።
ፍርድ ቤቱ ቪዲዮው ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ሲሰጥ የዛሬው ለሶስተኛ ጊዜ ሲሆን ፣ ተከሳሾቹም እየተጉላሉ መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ አቤት ብለዋል።
2ኛ ተከሳሽ መሳይ ደጉሰው ‹‹ድሃ ቤተሰብ አለን፡፡ ቤተሰቦቻችን መርዳት እንዳንችል እየተጉላላን ነው›› በማለት ችግራቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል። በዚሁ የክስ መዝገብ ማቲያስ መኩሪያ ፣ መሳይ ደጉሰው፣ ብሌን መስፍንና ተዋቸው ዳምጤ ሲገኙ ከመሳይ ደጉሰው ውጭ ያሉት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ናቸው፡፡
በተመሳሳይ በአራዳ ፍርድ ቤት የአቃቤ ህግ ምስክሮችን ለመስማት ለዛሬ ተቀጥሮ የነበረው አቶ ማሙሸት አማረም ለነሃሴ 20 ቀን 2007 ዓ.ም. ተቀጥሯል፡፡ አቶ ማሙሸት የአቃቤ ህግ ምስክሮችን ለመስማት በተደጋጋሚ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለትም ‹‹ምስክሮቹ ስላልተሟሉና ብዙ መዝገቦችም ስላሉ ምስክርነት መስማት አልቻልንም›› ተብሎአል።
የአንድነት አባልና የሚሊዮኖች ድምፅ ጋዜጣ አምደኛ የነበረው እስማኤል ዳውድ አራዳ ፍርድ ቤት ቀርቦ ለነሃሴ 28 ቀን 2007 ዓ.ም. ቀጠሮ ተሰጥቶበታል።
ፍርድ ቤቱ ‹‹በክረምት ከማይሰሩ የተለያዩ ፍርድ ቤቶች መዝገቦች በመምጣታቸው ምስክርነት መስማት አልቻልንም፡፡ ስራ በዝቶብናል›› በሚል በበርካታ ተከሳሾች ላይ ረዘም ያለ ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን ፣ በሰልፉ ሰበብ የታሰሩ ተከሳሾች ፣ በተለይም ሴቶች እና ቤተሰቦቻቸው የተፋጠነ ፍርድ ልናገኝ አልቻልንም፣ በሚል ፍርድ ቤቱ ግቢ ውስጥ ሲያለቅሱ ተስተውለዋል ሲል ነገረ – ኢትዮጵያ ዘግቧል።

Source:: Ethsat

የማለዳ ወግ…ለአሚራና ቤተሰቦቿ የጎደለው ፍትህ … !

$
0
0

የማለዳ ወግ…ለአሚራና ቤተሰቦቿ የጎደለው ፍትህ … !
==================================
* ህጻን የደፋረን የ4 ወር እስር መቅጣት ምን ይሉታል ?
* ፍርዱ ቅጣት ነው? ወይስ ማበረታታት ?
* ህግ አውጭና አስፈጻሚ አካላት ወዴት ናችሁ?
* ወላጆቿ ” ወላጅ ይፍረደን፣ህዝብና ሀገር ይፍረደን!”ይላሉ

የኢፊድሬ ህገ መንግሰት ሴቶች ልክ እንደ ወንዶች በሕገ-መንግሥቱ እኩል መብትና ጥበቃ እንዲሰጣቸው ይደነግጋል ። ትግበራውን መከታተልና ማስፈጸም ያለባቸው ህግ እውጭና አስፈጻሚ አካላት የሴቶችን መደፈር ለመከላከል የከበደ ኃላፊነት እንዳለባቸው ይህው የፈረደበት ህገ መንግስት ያስረዳል ! ዳሩ ግና አልፎ አልፎ የሚሰማ የሚታየው የነገር ጭብጥ ውጤት ህግ አውጭና የሚያወጡት ህግ ደንብና መመሪያ ከወንጀል ፈጻሚው ባልተናነሰ በህግ አስከባሪና አስፈጻሚዎች ህጉ ይጣሳል ። ህግ ተጥሶ የዜጎች ሰብአዊ መብት መዳጡ በአደባባይ እየተሰማና እየታየ ህግ አውጭ አካላት የሚወስዱት እርምት እርምጃ አያስደስትም ። የሴት ጠለፋ በተለይም በህጻናትና ታዳጊዎች ላይ የሚፈጸም አስገድዶ መድፈር ዝርዝሩ ሰፋ ያለ ይሆናል ። ዳሩ ግን የህግ እውቀት ኖሮኝ ያንን ለመተንተን ባይዳዳኝም በህግ አስከባሪዎች ፍትህ እየጎደለ በዜጎች ላይ የሚፈጸመው በደል ዘልቆ ቢያመኝ እንደ ዜጋ በጎደለው ፍትህ ተቃውሞና በቅሬታየ ዙሪያ የዜጋ ድምጼን ማሰማት ግድ ብሎኛል …

ዛሬ ዛሬ የምንሰማው ሰው በሰው ላይ ቀርቶ በእንስሳ ላይ መፈጸም የሌለበትን ርክሰት የተጠናወተው ወንጀል ጀሯችን ሆኗል ። በተለይ በአቅመ ደካማ ህጻናት ታዳጊዎችና በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ወንጀል እያደር መክፋቱ ጸሀይ የሞቀው እውነት ሆኗል። በዚህ ረገድ እየተኬደ ያለውን የከፋ ወንጀል ሳስበው ” ወደ የት እየሄድን ይሆን? ” እያልኩ ያስፈራኛል ! የአጉራ ዘለል አስገድዶ የመድፈር ወንጀለኞች መስፋፋት ፣ እያደር ውሎ አዳራችንና አብሮነታችን እንዳያጎድፈውም በአስፈሪ የታሪክ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን ! ሴሰኛ ወንጀለኛ ሽምጥ ጋልቦ እዚህ ሲደርስ ወንጀሉን በጥብቅ ተከታትሎ የማያዳግም ቅጣት አርአያነት ያለው ውሳኔ ቢሰጥ ዛሬ እዚህ ባልተደረሰ ነበር ፣ ይህ አይፈጸምምና ፣ ይህ አልተደረገምና ዛሬ ውርደትን መከናነብ ግድ ብሎናል ። የተከናነብነው ውርደት ምክንያት የሆነን ወንጀልም ሊሰሙት ከሚችሉት በላይ ሰቅጣጭና የከበደ እየሆነ ለመምጣቱ ብዙ ማሳያዎችን ማቅረብ አይገድም !

ይህን ሁሉ የምለው በአንዲት የ4 ዓመት ከ6 ወር ብላቴና ተዳጊ ላይ የተፈጸመው ወንጀልና ተመጣጣኝ ያልሆነውን የፍርድ ውሳኔ ወደምቃዎምበት የማለዳ ወጌ የመረጃ ግብአት ለመዝለቅ ነው ! እንደኔ የፍትህ መዛባት ዘልቆ ያመማችሁ ተከተሉኝና ፍርዱን ስጡ … !

በያዝነው ሳምንት ማህበራዊ መገናኛ ድህረ ገጾችን ቀልብ የሳበው ጉዳይ መካከል የ4 ዓመት ከ6 ወሯ ታዳጊ መደፈርን ተከትሎ የተላለፈው ዜና የብዙዎቻችን ቀልብ ስቧል ። ለዚህ መሰሉ ዜና አዲስ ባይንሆንም ብላቴናዋ መደፈሯ ሳይሰማ ባሳለፍነው ሳምንት ሀሙስ በመጨረሻ ው የፍርድ ውሳኔ ጋር ሰማን ፣ በውሳኔውም ደፋሪው የ4 ወር እስራት ቅጣት ፍርድ መሰጠቱን በአንድ ላይ ሲነገረን ማመን ከተቸገሩት መካከል አንዱ ነበርኩ። የጉዳዩን ጭብጥ ለማጣራት ባደረግኩት ሙከራ ያገኘሁት መረጃ ይዠ የዜጋ ተቃውሞ ድምጼን በማለዳ ወጌ ላሰዳ ስውተረተር በድሬ ትዩብ ስሟን በመጥቀስ በጉዳዩ ዙሪያ የቀረበ አንድ ዘገባ ለወጌ መረጃ ግብአትነት ተጠቅሜበታለሁ ። ትክክለኛ ስሟ ስለመሆኑ ግን ማረጋገጫ አላገኘሁም ። ስሟ ቢታወቅም መግለጹ አስፈላጊ ባለመሆኑ የድሬ ትዮብን ስም ተቀብየ እዘልቃለሁ ። ከዚሁ በተጨማሪ ሌላም ሌላ መረጃዎችን ለማሰባሰብና ለማጣራት ሞክሬ በእርግጥም ወንጀሉ ለመሰራቱና ፍርደ ገምድል ብይን የመሰጠቱ ሁነኛነት አረጋግጫለሁ !

የተሰራጩ መረጃዎች እንደሚስረዱት ታዳጊዋን የ4 ዓመት ከ6 ወር ተዳጊዋን አሚራ ትባላለች ። ኑሮዋም አዲስ አበባ አቃቂ ክፍለ ከተማ እንደሆነ ተጠቁሟል። ደፈረ የተባለው አስነዋሪ ወንጀል ፈጻሚ የ25 ዓመት ጎረምሳ ነው። በችርቻሮ ንግድ የሚተዳደሩት የአሚራ ቤተሰቦቿ ቤት ጎን ተከራቶ ነበር አሉ ።

ከውሳኔው አስቀድሞ ተከሳሽ አሚራን ስለመድፈሩ ክስ ቀርቦበት ፣ ጉዳዩ በፖሊስ ቀርቦና ተጣርቶ ተከሳሽ ተይዞ በፊዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአቃቂ ቃሊቲ ፍርድ ቤት ችሎት የቀረበ ሲሆን በ30 ሽህ ብር ዋስትና ተለቀቀ። ክሱን በዋስ ወጥቶ እንዲከላከል በፊዴራድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአቃቂ ቃሊቲ ፍርድ ቤት ወሰነ ። ያ ከሆነ በኋላ ባሳለፍነው ሳምንት ተከሳሽ ለብይን ቀረበ ። ፍርድ ቤቱ በፖሊስ የቀረበለትም ምርመራ ተመልክቶ በሰጠው ውሳኔ ” ተከሳሽ ድንግልናዋን ባይገስም በእጆቹ የማህጸኗ ግድግዳ የመሰንጠቅና የመላላጥ ጉዳትና ማድረሱና በማህጸኗ የመቅላት ምልክት በመታየቱ !” በሚል ማስረጃ ፍርድ ቤተ ተከሳሽን ” ሞከርክ ” በሚል ወንጀለኛ ሲል የ4 ወር እስራትን አስተላልፎበታል ። ይህው ፍርድ ቤት ገና የትምህርት ገበታ ያልቀመጠችን ታዳጊ ብላቴና አመራን የደፈረበትን የጨካኝ ድርጊት ከደፈረ ሞከረ ቀይሮ በቀረበ ማስረጃ በፍትሀ ብሔር ህግ 6264 ሀ መሰረት ውሳኔ መሰጠቱ ተነግሮናል ። አስገራሚ ፣ አስደንጋጭና አሳዛኝ የፍርድ ውሳኔ !

ክሱን አቀለለ ወደተባለው ምክንያት ስንሄድ ደግሞ ይበልጡኑ እንታመማለን … ወንጀለኛው ” የሳንባ ነቀርሳ በሽተኛና በቀጣዩ አመት ተመራቂ !” መሆኑን በቅጣት ማቅለያነት አቅርቦ በፍርድ ቤቶ ተቀባይነት ማግኘቱ አገኘ ብለውናል ። ለእኔ የክስ ማቅለያ የቀረበው ሀሳብ የተማረ የተመራመረው ” የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ” ነኝ ባይ ወንጀለኛ ነው ፣ ምንም የማታውቅን እምቦቃቅላ ታዳጊ ገላን በአሻው መንገድ አድርጎ ገፎታል ፣ ገፈፋውም የተፈጸመው በአንድ አዋቂ መሆኑ ብቻ ወንጀሉን ሊያከብድ እንጅ ሊያቀል ባልተገባ ነበር ባይ ነኝ ። ይህ ያቀረበው የክስ ማቅለያ ይልቁንም በሰነድ ተረጋግጦ ክሱን ማጠንከር ሲገባው ክሱን ማቅለያ ሆኖ መቅረቡና ከምን ወደ ምን እንደቀለለ ያልተገለጸው ማቅለያ ተቀባይነት ማግኘቱ በራሱ በምንም ሚዛን ፍትሃዊነት የለውም ! ይህን ለመናገር ሰብእናና የራስን ፍርድ መስጠት እንጅ ግዴታ ህግ ማጥናት አያስፈልገውም …

የህዝብን መብት ለማስጠበቅ የተሰየሙትን የፍትህ አካላት የሙያ ብቃት ጥያቄ ውስጥ የጣለው ይህ መሰሉ አሳዛኙ የፍትህ ውሳኔ ማህበረሰቡ በፍትህ እንዳይተማመን ከማድ ረግ ባሻገር በህግ ጥላ ስር መጠበቁን በጥርጣሬና እንዲ ያይ እንደሚያደርገው ጥርጥር የለኝም ። ከዚህም አልፎ ተርፎ በአሚራ ደፋሪ ላይ የተላለፈው ውሳኔ ሀገሬው ፍትህ አጥቶ የሚንገዋለል እንዲሆን አድርጎታል ወደሚል መደምደሚያ አድርሶኛል … የአስገድዶ መድፈር ወንጀለኞ ች ጉዳይ መስፋፋትና ገደብ ማጣት በተደጋጋሚ በመንግ ስት ላይ የሰላ ወቀሳ ይቀርባል ። በተለይም የህግ ጥበቃ ውንና ቅጣቱን ከማጠንከሩ በተጓዳኝ ተማኝነት እንጅ የሙያ ብቃት ሚዛን ሆኖ ቅጥር ስለማይፈጸም ተደጋጋሚ ችግሮች ተስተውለዋል ። የፍትህ አካላት ብዛት እንጅ ጥራት የጎደላቸው መሆኑ ከዚሁ ጋር ይጠቀሳል ። የተባለውን ወቀሳ እውነታነት እንዳለው ለመረዳት የአሚራን አይነት በደል ተሰርቶ የተሰጠውን ውሳኔ መመልከት ብቻ ማየት ከበቂ በላይ ይመስለኛል ።

በአሚራ ውሳኔ አሰጣጥ እንዳየነው ከምንም በላይ የፍትህ ስርአቱ በወንጀለኛውም ሆነ በጠበቆች የቀረበውን የተውተፈተፈ መከላከያና ቅጣት ማቅለያ መቀበላቸው ለፍትህ አካላት የደረሱበትን ደረጃ ያሳይ ከሆነ መልካም ነው ። የአሚራን ጉዳይ በግርድፉ ላየ ለተመለከተው ጥፋታቸውን በአዞ እንባ ለመሸፋፈን ከተጉ ወንጀለኞች ጎን ለገንዘብ ብለው ጥፋቱን ለማቅለል ሚሞግቱት ጠበቆች ሰብዕና ያማል ፣ የዳኞቹ ውሳኔ አሰጣጥና ውሳኔ ማቅለያ አቀባበል ደግሞ ይገርማል ፣ ይደንቃል … ! ይህ መሰል ከእውነታው ጋር የሚጋጭ የተፋለሰ ፍርድ በአደባባይ ሲሰጥ ህጉን ማስከበር ያለባቸው አቃቤ ህግ ተወካዮች የታሉ ? ፍትህ ወዴት ነህ ? ያስብላል …

በሰብዕና ላይ ወንጀል ሲሰራ በቸልተኝነት መመልከት ሊቆም ይገባል ። የሴቶችን መብት ለማስከበር ተብሎ የወጡት ሕጎች ተፈጻሚ ይሆኑ ዘንድ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አካል የሆነ የሴቶችና ሕጻናት ጉዳዮች ብሔራዊ ኮሚሽንን በ2005 ዓም መቋቋሙን ከሰማን አመታት ተቆጥረዋል ። ኮሚሽኑ በሴቶችና በሕጻናት ለሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተገን እንደሚሆን ቢጠቀስም ለአሚና የጎደለ ፍትህ ድምጹን ሲያሰማ አለመታየቱ ግር ያለው እኔን ብቻ ከሆነ መልካም ነው ፣ ግን አይመስለኝም ። ” መብቷ ይከበር ፣ ፍትህ ጎድሎባታል፣ ፍትህ ታግኝ ” የምንላት ታዳጊዋ አሚራ ያለ ፈቃዷ አይደለም ገላዋ የጸጉር መጠምጠሚያ “ሂጃቧ ” ሊነካ አይገባም ፣ ከተነካ ህግ ተጥሷል ! አሚና ድንግልናዋ አልተገሰሰም ፣ ማህጸኗ ግን ተነካክቷል ብሎ ወንጀለኛን ከአስገድዶ መድፈር ወንጀል ማራቅ ፣ ማሸሸት ፍትህን ማረጋገጥ ሳይሆን ፍትህን ማርከስ አድርጌ ነው የምቆጥረው ። ወንጀለኛው ” አስገድዶ የደፈረ ” ለመባል አሚራ በጭካኔ ተደፍራ እንደተገደለችው እንደ ሀና ኦላንጎ መሆን አልነበረባትም ! አሚራም ሀና እንደሆነችው ባትሆንም በአሚራም ማህጸን ዙሪያ ክብረ ነክ የመድፈር ሙከራ አድርጓል ። የቀረበው ማስረጃ የሚየስረዳው አርቆ አሳቢው የተማረ ጎልማሳ ምንም በማታውቀው የ4 ዓመት ከ6 ወር ታዳጊ ህጻን ላይ ወንጀል አስገድዶ መድፈር ለመሆኑ ሌላ ከበቂ በላይ ማስረጃ አለ ብየ አላምንም!

የሴቶችና ሕጻናት ጉዳዮች ብሔራዊ ኮሚሽንን ሴቶች ሥርዓተ-ፆታን መሠረት ያደረገ ጥቃት ደርሶባቸው እንዲህ ሲመለከት አብሮ ከተጎጅ ወገኖች ጎን መቆም ፣ የሕግ ጥበቃ ማቆም ፣ የህግ ጠበቃ የማቆም አቅም ከሌለው የህግ ጥሰቱን በአደባባይ ተቀውሞ ስታዳጊዋ ብላቴና ስለአሚራ ፍትህ ማግኘት ድምጹን ሊያሰማ ይገባል !

በፍርድ ገምድሉ ውሳኔ ያዘኑ ቤተሰቦች ወላጆቿ ፍትህ ጎድሎባቸው ” ወላጅ ይፍረደን፣ህዝብና ሀገር ይፍረደን!” ማለታቸው ስሰማ የእነሱም ጩኸትና አቤቱታ የእኔም ለአሚራና ቤተሰቦቿ ፍትህ ርትዕ ይከበርላቸው የሚል ጥያቄ እንዳነሳ አድርጎኛል ! ከምንም በላይ የሴት ልጅ በረከት የታደልኩ አባት እንደመሆኔ የሴት ልጅን ወሰን የሌለው ፍቅር አውቀዋለሁና ከአሚራ ቤተሰቦች ጋር ልቤ በሀዘን ተሰብሯል ፣ በጎለው ፍትህ አምርሬም አዝኛለሁ … !

ፍትህ ለህጻን አሚራና ቤተሰቦቿ ስል እጠይቃለሁ !

ነቢዩ ሲራክ
ነሀሴ 5 ቀን 2007 ዓም

ለኢትዮጵያዊውስ ማን አለው? –በያሬድ ታዬ መኮንን፤ ቶሮንቶ

$
0
0

 

Ethiopiaቶሮንቶ ከመጣሁ ሶስተኛ ሳምንቴን ያዝኩኝ፡፡ ቀኑን ሙሉ፤ ከሰሜን ደቡብ፤ ከምስራቅ ምእራብ ሳካልለው ውዬ፤ መጀመሪያ በጓደኛዬ ቤት፤ አሁን ደግሞ መንግስት በሰጠኝ፤ በቶሮንቶ፤ ኦንቴርዮ ጎዳና ላይ በሚገኘውና እኔና ሌላ አንድ ሰው በምንጋራው ክፍል ጣሪያ ስር ሆኜ፤ ወደጣሪያው አንጋጥጬ፤ የኢትዮጵያና የካናዳ ህይወቴን፤ እንዲሁም ነጻነቴን ማሰላሰል ይዣለሁ፡፡ ነጻነት እንዴት ይጥማል፡፡ ድህነት አንድ ነገር ነው፡፡ መራብም አንድ ነገር ነው፡፡ ሰው ግን ነጻነቱንና ክብሩን እንዴት ባገሩ ይነፈጋል፡፡ እነሆ በማያውቁን፤ በማላውቃቸው፤ በሰው አገር የተሰጠኝን ክብርና እንክብካቤ እያጣጣምኩ ሳለሁ፤ የሩቅ ጓደኛዬ የነገረኝ ታሪክ ትዝ አለኝ፡፡  ይህ የሩቅ ጓደኛዬ አውነተኛ ታሪክ ነው ብሎ ያጫወተኝን፤ እኔም የተቀበልኩትን ገጠመኝ ላጫውታችሁ፡፡

እውነት መሆኑን እንዴት ተቀበልከው፤ ያላችሁኝ እንደሆነ ኢትዮጵያ ሃገሬ ውስጥ እንኳን ይሄ ይቅርና፤ ወያኔ “ተቃዋሚዎችም መርጠውኛል”  ብሎን ተቀብለነው የለም እንዴ? መቼ ነው ያለው፤ ለምትሉኝ ደግሞ አሁን ባሳለፍነው ምርጫ 2007፤ በአይኔ ያየሁት፤ ምናልባትም ብዙዎቻችሁ በሶሻል ሜዲያ ያነበባችሁ፤ እና ያሰገረማችሁ የምርጫ ውጤት እንደሚያሳየው፤ በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች፤ ከ1000 መራጮች መካከል ኢህአዴግ፤ 1000 ከ1000 ተብሎ በምርጫው ጣቢያ ሲለጠፍ፤ አስቡት እንግዲህ፤ ይህ 1000 መራጭ የተቃዋሚ ተመራጭ ተወዳዳሪዎችን ጨምሮ መሆኑን፡፡ እንግዲህ ይህንንም አምነን “አሜን” ብለን ተቀብለን የለም ወይ? እንግዲህ የጓደኛዬንም የህይወት ገጠመኝ አምኜዋለሁ፡፡

የወያኔን ጉድ እስቲ ይሁን ብለን እንለፈውና ወደዋናው ታሪክ እንመለስ፡፡ በነገራችን ላይ ስም መጥቀስ ስላላስፈለገኝ፤ ጓደኛዬ እያልኩ በመተረኬ፤ ቅር አይበላችሁ፡፡ ያው እንደምታውቁት ጊዜው አስቸጋሪ ስለሆነ ስም ባይጠቀስ ይሻላል ብዬ ነው፡፡

ይህ ጓደኛዬ እና አንድ የስራ ባልደረባው ከስራ በኋላ መሸትሸት ሲል ለመዝናናት፤ 22 አካባቢ ወደሚገኙት የመዝናኛ ቤቶች ጎራ ይላሉ፡፡ ከአንዱ ቤት ወደ ሌላኛው በመቀያየር ሲዝናኑ ይቆዩና፤ አትላስ አካባቢ ወደሚገኝ አንድ ታዋቂ የጭፈራ ቤት (በተለምዶ ክለብ) ይገባሉ፡፡ በክለቡ ውስጥ የተለያዩ ሰዎች የነበሩ ሲሆን፤ ከእነዚህም መሀከል ከወደምስራቅ አካባቢ የመጡም (በግምት ቻይናውያን ይመስሉታል) ነበሩበት፡፡ ሙዚቃው ቀጠለ፤ ጨዋታውም ደራ፡፡ መቼስ በዳንስ ውዝዋዜ መሀል መነካካት አይጠፋም፤ የጓደኛዬ ጓደኛ ከአንዱ ቻይናዊ ጋር ይነካካል፡፡ ከዚያም ይቅርታ ጠይቆ ጨዋታውን ይቀጥላል፡፡ ቻይናዊው ጉዳዩን በቀላሉ አልተመለከተውም፡፡ “ሳታውቅ ሳይሆን እንደው ነገር ስትፈልገኝ ነው” በማለት እምቧ ከረዮውን አቀለጠው፡፡ ሰዎች ነገሩን ለማረጋጋት ቢሞክሩም፤ አጅሬ ቻይና ካልደበደብኩት ብሎ ሰፈሩን ቀውጢ አደረገው፡፡ ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ መሆን በጀመረበት ሰዓት፤ የሀገሬው ፈላጭ ቆራጭ፣ ምንም ቢያደርግ ጠያቂ የሌለው፣ ማሰር፣ መደብደብ ካሻውም መግደል መብት የተሰጠው፤ መቼስ ታውቁታላችሁ ስለማን እያወራሁ እንዳለ፤ የወያኔ አካል የሆነው፡ ፈደራል ፖሊስ መጣ፡፡ ግርግሩም ቀዝቀዝ እያለ ሁሉም በመረጋጋት ስሜት ባሉበት ሁኔታ፤ ቻይናዊው ፌዴራሉን ሲመለከት የልብልብ ተሰምቶት ኖሮ፤ እጁን ሰንዝሮ የጓደኛዬን ጓደኛ በቡጢ ቢለውስ፡፡ ያኛውስ ከማን አንሶ በእጁ በሶ አልጨበጠ መልሶ ቢቦቅሰውስ፡፡ ታዲያ ይኽኔ ነበር ግራ የሚያጋባውና ማንነትን የሚፈታተነው ጉዳይ የተከሰተው፡፡

እንዲህ ነው የሆነው፡፡ ከፌዴራል ፖሊሶቹ መሀከል ሁለቱ ተንደርድረው መሃል በመግባት አንደኛው ቻይናዊውን ወደ ጎን ሲያደርገው፤ ሌላኛው የጓደኛዬን ጓደኛ በዚያ በያዘው የሚያቃጥል ቆመጥ (መቼስ የቀመሰ ያውቃታል) ሲዠልጠው ለተመለከተ ማንኛውም ሰው፤ እጅግ በጣም አስገራሚና አሳዛኝ ነበር፡፡ ቻይናዊውም ለካስ ይኼን አውቆ ኖሯል እንደዛ የልብልብ ተሰምቶት ቦክስ የሰነዘረው፡፡ ለጓደኛዬ ጉዳዩን ዝም ብሎ መመልከት አልሆንለት ቢለው፤ ጠጋ ብሎ በልመና መልክ ለማግባባት እየሞከረ፤ “ኽረ እባካችሁ ተውት እሱ ምንም አላጠፋም” በማለት ለማስረዳት ቢሞክር፤ አንተስ የት ይቀርልሃል ብለው ያላንዳች ማመንታት የዚያች ቆመጥ ተቋዳሽ በማድረግ፤ ሦስት አራት ጊዜ ካቀመሱት በኋላ፤ ቻይናዊውን በክብር ከይቅርታ ጋር ወደ ውስጥ እንዲገባ በምልክት (ያው እንደምታውቁት ቋንቋ ችግር ነው) ይነግሩት እና ጓደኛዬን እና ጓደኛውን በያዙት ፒክ አፕ መኪና ጭነው ወደ ፖሊስ ጣቢያ፡፡

ለመዝናናት የወጡት እኚህ ኢትዮጵያውያን፤ በገዛ ሀገራቸው ክብር ተነግፏቸው፤ ለውጭ ዜጋ ጎንበስ ቀና ባለማለታቸው የመዝናኛ ጊዜያቸውን በፖሊስ ጣቢያ አሳልፈው፤ እንዲህ አይነት ነገር እንዳይለመዳቸው ከማስጠንቀቂያ ጋር በበነጋታው መለቀቃቸውን የነገረኝ፤ እጅግ በንዴት እና በቁጭት መንፈስ ነበር፡፡ እንዲህ አይነት ክስተቶች በተለያየ መንገድ ያጋጠመን ሰዎች እንኖር ይሆናል፡፡ ያላጋጠማችሁም ወደፊት ቢያጋጥማችሁ ግር አይበላችሁ፡፡ እንደው ነገርን ነገር አነሳውና ነው እንጅ፤ ከዚህም የባሰ ብዙ አይተናል ሰምተናል፡፡

ሁሌም ውስጤን የሚያንገበግበው ነገር ቢኖር፤ ቢያንስ ለሌሎች ዜጎች ሀገራችን ላይ የሚሰጣቸውን ክብር ያክል እንኳን ሰው በሀገሩ የማይሰጠው ከሆነ ለኢትዮጵያዊውስ ማን አለው? ማንስ አለሁልክ፤ አይዞህ ይለዋል?

ሁሉም ነገር ከራስ ነው የሚጀምረው የሚል እምነት አለኝ፡፡ ፍቅርም ቢሆን፣ አክብሮትም ቢሆን ለራስ ሰጥቶ ነው ወደሌላኛው የሚኬደው፡፡ እራሱን እና የራሱ የሆነውን የማያከብር፤ ሌላውን አከብራለሁ እጠብቃለሁ ቢል፤ ለእኔ እንደማስመሰል ነው የምቆጥረው፡፡ እዚህ ላይ የሌላ ሀገር ዜጎች አይከበሩ እያልኩኝ አይደለም፡፡ ነገር ግን ሰው ከሀገሩ የበለጠ ጥበቃ እና ከለላ ሊያገኝ የሚችልበት የተሻለ ቦታ የት ነው ያለው? ያደጉት እና እኛን ጥለው የሄዱት ሀገራት ከሀገራቸው አልፈው በሰው ሀገር ስለሚገኙት እያንዳንዱ ዜጎቻቸው ክትትል በማድረግ፤ ያሉበትን ሁኔታ ሰላማዊነት ሲያረጋግጡ የምንመለከተው ጉዳይ ነው፡፡ ይህን ማድረግ ካለንበት ነባራዊ ሁኔታ አንፃር አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ ሀገራችን ውስጥ ግን ለሚከሰተው ማንኛውም ጉዳይ የዜጎቹን መብት ሊያስከበር የሚችል ስራ የመስራት ግዴታ የመንግስት አንዱ ሃላፊነት ነው ብዬ አስባለሁ፡፡

ሰው ሀገር አለኝ ብሎ በሀገሩ ሰርቶ እና ተለውጦ፣ የዘር፣ የጎሳ፣ እንዲሁም የቀለም ልዩነት ሳይገጥመው መኖር ካልቻለ፤ ከመሰደድ ውጭ ምን አማራጭ ይኖረዋል? አስቡት እስቲ በሀገሩ ክብር ተነፍጎት በሰው ሀገር ተከብሮ የሚኖረውን ስትመለከቱ ምን ይሰማችኋል? እንደው ወያኔ የሀገር ትርጉም አልገባውም እንጂ ቢገባው ኖሮ ይሄንን ግጥም ያዜምልን ነበር፡-
ሀገርን ሀገር ያሰኘው
ሰው የተባለው ፍጡር  ነው!

 

ያሬድ ታዬ መኮንን፡ ሀምሌ/ነሀሴ፤ 2015፡ ቶሮንቶ

ኢትዮጵያ ውስጥ መንግስት የመቶ ብር ኖቶችን እንደጉድ እያተማቸው ነው * መቶ ብር በዛ ኢኮኖሚ ጠነዛ

$
0
0

ethiopia-100birr
አገሪቱ ውስጥ የመቶ ብር ኖቶች መጠን

በ1999 ዓ.ም 7.7 ቢሊዮን ብር
በ2000 ዓ.ም 10 ቢሊዮን ብር
በ2001 ዓ.ም 14 ቢሊዮን ብር
በ2002 ዓ.ም 17 ቢሊዮን ብር
በ2003 ዓ.ም 23 ቢሊዮን ብር
በ2004 ዓ.ም 30 ቢሊዮን ብር
በ2005 ዓ.ም 40 ቢሊዮን ብር
በ2006 ዓ.ም 40 ቢሊዮን ብር
በ2007 ዓ.ም 53 ቢሊዮን ብር

ከሰባት ዓመት በፊት በ99 ዓ.ም፣ በአገሪቱ የነበረው ጠቅላላ የመገበያያ ገንዘብ፣ 12 ቢሊዮን ብር ነበር። ከዚያስ? ከዚያ በኋላ ያለውማ፣ “የተዋጣለት የ‘Inflation’ ታሪክ ነው” ልንለው እንችላለን – ገንዘብ እንዴት እንደሚረክስ የሚያሳይ ታሪክ። በአዲሱ ሚሊኒዬም መግቢያ ላይ፣ 15 ቢሊዮን ብር ከደረሰ በኋላ፣ በዚያው ዓመት መጨረሻ ላይ ወደ ሃያ ቢሊዮን፣ እንደገና በቀጣዩ ዓመት አጋማሽ፣ ወደ 24 ቢሊዮን ብር ተሸጋግሯል።
በቃ፤ ሦስት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ፣ በአገሪቱ ውስጥ የሚንቀሳቀሰው የገንዘብ መጠን በእጥፍ ጨምሯል። ያው፣ ገንዘብ ሲረክስ፣ የሸቀጦች ዋጋ ይጨምራል። ሚስጥር አይደለም። ማለትም… በ2000 ዓም. እና በ2001 ዓ.ም፣ በዋጋ ንረት፣ ኢትዮጵያ የአለም አንደኛ የሆነችው አለምክንያት አይደለም።
ያኔ ነው፣ መንግስት የብር ኖት ህትመቱን ረገብ ያደረገው፣ ከ2001 ዓ.ም አጋማሽ በኋላ፣ ለአንድ ዓመት ያህል፣ ብዙም አልጨመረም። ለዚህም ነው፣ የዋጋ ንረቱ (ወደኋላ ባይመለስም)፣ ቀስ በቀስ መረጋጋት የጀመረው። ግን አልዘለቀበትም። ለምን? መንግስት እንደገና፣ የብር ሕትመቱን ተያያዘዋ።
በአገሪቱ የሚንቀሳቀሰው የብር ኖቶች መጠን፣ ከ26 ቢሊዮን ብር ወደ 39 ቢሊዮን ብር የጨመረው፣ በ18 ወራት ውስጥ ነው – እስከ 2003 ዓ.ም መጨረሻ ላይ። ይሄኛው አመትም እንዲሁ፣ “በመላው አለም ከቀዳሚዎቹ ተርታ የሚጠቀስ የዋጋ ንረት”፣ በኢትዮጵያ የተከሰተበት ወቅት እንደሆነ አስታውሱ። የብር ኖቶች መጠን፣ እንዲያ በአጭር ጊዜ ውስጥ በሃምሳ በመቶ ሲጨምር፣ ገንዘብ መርከሱና የሸቀጦች ዋጋ ሽቅብ መምጠቁ የግድ ነው።
በተቃራኒው፣ የብር ህትመት ረገብ ሲል ደግሞ፣ የዋጋ ንረቱ ይረጋጋል። ከ2003 ዓ.ም የመጨረሻ ወራት በኋላ፣ ያሉትን 18 ወራት መመልከት ይቻላል። ታተመ፣ ታተመና፤ የአገሪቱ የብር ኖቶች ወደ 46 ቢሊዮን ገደማ ደረሰ – እስከ 2005 መግቢያ ማለት ነው። በዚህ ጊዜ ውስጥ የብር ኖቶች መጠን የጨመረው፣ በ17% ገደማ ነው። ቀላል አይደለም። ግን፣ እንደ በፊቱ በሃምሳ ፐርሰንት ባለመጨመሩ፣ “ትንሽ ተሽሎታል” ልንል እንችላለን። በዚህም ምክንያት፣ በ2003 ዓ.ም ከሰላሳ በመቶ በላይ እያሻቀበ የነበረው የሸቀጦች ዋጋ፣ ቀስ በቀስ እየተረጋጋ ወደ አስር በመቶ እየበረደ መጥቷል።
ከዚያስ?
ከ2005 ዓ.ም መግቢያ አንስቶ፣ እስከ 2006 አጋማሽ ድረስ ባሉት 18 ወራት፣ ምን ተፈጠረ?
የዋጋ ንረቱም ይበልጥ ተረጋጋ። የሸቀጦች ዋጋ መጨመሩኮ አልቆመም። ግን፣ አመታዊው የዋጋ ጭማሪ፣ ወደ ስድስት ወደ ሰባት በመቶ በመውረድ፣ ቀዝቀዝ ብሏል። ለምን? የብር ህትመቱ ይበልጥ ረግቧላ። የገንዘቡ መጠን፣ 51 ቢሊዮን ብር ደርሷል። ግን፣ በ18 ወራት ውስጥ፣ በአራት ተኩል ቢሊዮን ብር (በአስር በመቶ ገደማ) ነው የጨመረው። ከቀድሞው ጋር ሲነፃፀም፣ “ደህና እየተሻለው መጥቷል” ልንል እንችላለን።
በዚሁ እርጋታው አለመቀጠሉ ነው ችግሩ። በ2006 መጨረሻ ላይ፣ የብር ህትመቱ እንደገና አገረሸበት።
ሰሞኑን ብሔራዊ ባንክ ባወጣው ሪፖርት ላይ፣ ባለፈው መጋቢት 2007 ዓም፣ በአገሪቱ ውስጥ ያለው የብር ኖቶች መጠን ምን ያህል እንደሆነ ተገልጿል። 64 ቢሊዮን ብር ደርሷል፣ ይላል ሪፖርቱ።
እውነትም አገርሽቶበታል። ያው… በአንድ አመት ተኩል ጊዜ ውስጥ፣ የብር ኖቶች መጠን፣ እንዲህ በ25 በመቶ ሲጨምር፣… የሸቀጦች ዋጋ እንደ በፊቱ ተረጋግቶ ሊቀጥል አይችልም። ሰሞኑን በማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የወጣው መረጃም፣ ይህንን ያረጋግጣል።
ካለፈው መስከረምና ጥቅምት ወር ወዲህ፣ የሸቀጦች የዋጋ ንረት ያለማቋረጥ እያሻቀበ መጥቷል። እንዳትሳሳቱ። “የሸቀጦች ዋጋ ያለማቋረጥ እየጨመረ ነው” ማለቴ አይደለም። ጭማሪውንማ ለምደነዋል። መንግስት፣ የብር ህትመት ላይ በደንብ ፍሬን ለመያዝ ፈቃደኛ እስካልሆነ ድረስ፣ የሸቀጦች ዋጋ እየጨመረ መሄዱን አያቆምም። አስቸጋሪው ነገር፣… የጭማሪው ፍጥነት እየባሰበት መምጣቱ ነው። በአመት ውስጥ የሚከሰተው የዋጋ ጭማሪ፣ ከአስር በመቶ በላይ እየሆነ መምጣቱ ነው ፈተናው።
መስከረም ላይ፣ አመታዊው የዋጋ ጭማሪ ከስድስት በመቶ ብቻ እንደነበረ የሚገልፀው የስታትስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ፤ ታህሳስ ላይ ሰባት መቶ፣… የካቲት ላይ ስምንት በመቶ፣… ሚያዚያ ላይ ዘጠኝ በመቶ፣… በሰኔ ወር ደግሞ ከአስር በመቶ በላይ ሆኗል። እንደ “ቀይ መስመር” ተደርጎ የሚታሰበውን ድንበር፣ ጥሶ አለፈ ማለት ነው – ወደ “ደብል ዲጂት” ተሻግሯል።
ሐሙስ እለት የተሰራጩ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ደግሞ፣ በሐምሌ ወር አመታዊው የዋጋ ንረት፣ ብሶበት 12% ደርሷል። የአለም ባንክ እንደሚለውማ፣ የዋጋ ንረቱ ከዚህም በላይ ወደ 15 በመቶ መጠጋቱ አይቀርም ነበር – በአለም ገበያ፣ የነዳጅ ዋጋ ከአምናው ባይቀንስ ኖሮ።
በእርግጥ፣ ባለፉት አመታት እንዳየነው፣ ቅጥ ባጣ የገንዘብ ህትመት ሳቢያ “የዋጋ ንረት” በተባባሰ ቁጥር፣ ጥፋቱ የሚሳበበው በነጋዴዎችና በቢዝነስ ሰዎች ላይ ነው።
ዘንድሮም፣ መንግስት፣ ጥፋቱን በነጋዴዎች ላይ ለማሳበብ መሞከሩ አይቀርም። ነገር ግን፣ ከንቱ ሙከራ ነው። ለነገሩ፣ አብዛኛው ኢትዮጵያዊም፣ ነጋዴዎችን ለማውገዝና ለመወንጀል እጅጉን ይፈጥናል። ጨርሶ፣ መረጃዎችን በወጉ ማየትና ማገናዘብ አያ….

ምንጭ ፡፡ አዲስ አድማስ

Sport: ዋሊያዎቹ ከሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድን ጋር የወዳጅነት የጨዋታ ለማድረግ ወደ ኪጋሊ ይጓዛሉ

$
0
0

walia

በኢትዮጵያ እግር ኴስ ፌዴሬሽን የወዳጅነት ጨዋታ ጥያቄ አቅራቢነት በፈረንጆቹ August 28 የኢትዮጵያ እግርኳስ ብሔራዊ ቡድን ከሩዋንዳቸው ጋር ኢንተርናሽናል ፊፋ የወዳጅነት ጨዋታቸውን ኪጋሊ ላይ እንደሚያደርጉ ኢትዮ ኪክ ዘገበ::

የሩዋንዳ እግርኳስ ፌዴሬሽን August 29 ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ጋር ሊያደርግ የነበረው የወዳጅነተት ጨዋታ መሰረዙን ተከትሎ የኢትዮጵያን ጥያቄ ሙሉ ለሙሉ ተቀብሏል።

የኢትዮጰያ ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ አቻቸው ጋር September 5 ለሚያደርገው ጨዋታ ከወራት በፊት ዝግጅቱን ባህርዳር እያደረጉ ይገኛሉ:


የሕወሓት መንግስት ቅንጅትን ለማፍረስ የተባበሩትን አቶ አየለ ጫሚሶን እንደሸንኮራ መጦ ጣላቸው

$
0
0

chamiso ayele
የሕወሓት መንግስት በሚዲያዎቹ በኩል እንደዘገበው ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (ቅንጅት) የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የፓርቲውን ሊቀመንበር አቶ አየለ ጫሚሶንና የፓርቲውን የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ አስረስ በትረን ከአመራርና አባልነት ማስወገዱን ገልጿል:: እንደ መንግስት ሚዲያዎች ዘገባ በፓርቲው ስም የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውሳኔ በሚል ደብዳቤ የላኩ ግለሰቦች በህገወጥ ድርጊትና ወንጀል ከፓርቲው የተሰናበቱ መሆናቸውን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አየለ ጫሚሶ አሳወቁ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ ችግራቸውን በፓርቲው መተዳደሪያ ደንበ መሠረት እንዲፈቱ አሳሰበ። ይህ የምርጫ ቦርድ ተግባር በአንድነት ፓርቲ ላይ የተለመደ አካሄድ ነው ሲሉ ፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ::

የሕወሓት መንግስት ያደራጃቸው የፓርቲው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በፓርቲው ዋና ፀሐፊ፣የፅሕፈት ቤቱ ኃላፊና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በአቶ ሳሳሁልህ ከበደ ሰሞኑን ለኢህ አዴግ ሚድያዎች በላከው የውሳኔ ማሳወቂያ ደብዳቤ ሁለቱ ከፍተኛ አመራሮች ከፓርቲና ከሥልጣናቸው እንዲወገዱ የተደረገው በፓርቲው ህገ ደንብ መሠረት ከሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መካከል አንደ ሦስተኛው ስብሰባ እንዲደረግ ሲጠይቁ አስቸኳይ ስብሰባ መጥራት ስለሚቻል በዚሁ መሠረት ስብሰባው የተካሄደ መሆኑን ያስረዳል።

በፓርቲው ውስጥ ህገ ወጥ አሠራሮች የተስፋፉበት፣ውጫዊና ውስጣዊ ወንጀሎች እየተበራከቱ የመጡበት ሁኔታ መኖሩን ፣በህጋዊ ፓርቲ ሽፋን ከፓርቲው አቋም ውጪ መንቀሳቀስ የሚሉና ሌሎች ችግሮች ከታዩ በኋላ ችግሩን ከምንጩ ለማድረቅና ፓርቲውን ለማዳን ሲባል እርምጃው መወሰዱን ያትታል። የስብሰባው ቃለ ጉባኤና ውሳኔም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መላኩንም ያስረዳል።

የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዚዳንት አቶ አየለ ጫሚሶ የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውሳኔ አስመልክቶ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ «በፓርቲው ስም የውሳኔ ሃሳብ በሚል የሚያቀርቡት ግለሰቦች ህገወጥ ድርጊትና ወንጀል ፈፅመው በፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ከሰኔ 28 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ ከአመራርነትና ኃላፊነት የተባረሩ ናቸው» ቢሉም ክርክራቸው ጉንጭ አልፋ ነው የሚሉ በርካታ ናቸው::

አቶ አየለ ጫሚሶ ከሕወሓት መንግስት ጋር የነበራቸው ፍቅር ያለቀ ሲሆን እንደሸንኮራ ተመጠዋል:: እኚህ ፖለቲከኛ የቅንጅትን ትልቅ ትግል ገደል ለመክተት የተባበሩና ለጥቅም ያደሩ በመሆኑ ዛሬ እንደሸንኮራ ተመጠው ወያኔ ባዘጋጃቸው ሰዎች ቢጣሉም የሚቆረቆርላቸውም የለም የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ::

መንግስት በሕዝብ የተመረጠው ቴዲ አፍሮን በስነጥበብ ዘርፍ ለመሸለም ፍላጎት እንደሌለው በይፋ አሳየ

$
0
0

teddy afro
(ዘ-ሐበሻ) በየዓመቱ የሚካሄደና ዘንድሮም ለ3ኛ ጊዜ ነሐሴ 30 ቀን 2007 ዓም በአዲስ አበባ ካፒታል ሆቴል በሚከናወነው ‹የዓመቱ በጎ ሰው ሽልማት› በየዘርፉ የተመረጡ የመጨረሻዎቹ አምስት ዕጩዎችን መንግስት ልክ እንደምርጫው አጭበርብሮ ራሱ የሚፈልጋቸውን ሰዎች አስቀመጠ:: ካለፈው ታህሳስ ወር ጀምሮ በተሰጠው የሕዝብ ጥቆማ የዓመቱ በጎ ሰው በሚል በስነጥበብ ዘርፍ ዝነኛው ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ ምርጫን ቢያገኝም መንግስት በምርጫው እንደማጭበርበር እንደለመደው በፖለቲካዊ ውሳኔ ከ እጩዎች ዘንድ እንዳይካተት መደረጉ ተጋልጧል:: ከታኅሣሥ ወር ጀምሮ በተሰጠው የሕዝብ ጥቆማ መሠረት ታሪካቸውና ሥራቸው ተሰብስቦ፣ በበጎ ሰው ሽልማት የምርጫ ሂደት ኮሚቴ የተመረጡት 45 ዕጩዎች ናቸው ብሎ መንግስት ካስቀመጣቸው ሰዎች መካከል ሁሉም መንግስት ራሱ እንዲሸለሙልኝ እፈልጋለሁ ያላቸውን እንዳጨ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል:: ቴዲ አፍሮ በስነጥበብ የዓመቱ በጎ ሰው ዘርፍ የበርካታ ሕዝብ ድምጽን ቢያገኝም ከ እጩዎች ዝርዝር እንዲወጣ ተደርጓል::

ዘንድሮ መንግስት 9 ሰዎችን በሕዝብ ምርጫ እሸልማለሁ ቢልም ቅሉ ምርጫው ለመንግስት ፖለቲካ ቅርበት ያላቸው ሰዎችን የሚያካትት እንጂ ትክከለኛው የሕዝብ ጥቆማ እንዳልሆነ ታማኝ ምንጮች ይናጋራሉ::

ሕወሓት የሚመራው መንግስት በሕዝብ የተጠቆሙ ሰዎችን ትቶ በራሱ መንገድ ሕዝብ መረጣቸው ብሎ ያስቀመጣቸው ሰዎች ዝርዝራቸው የሚከተለው ነው፡፡

በ2007ዓም በልዩ ልዩ ዘርፎች ዕጩ የሆኑ በጎ ሰዎች

በሳይንስ ምርምር ዘርፍ ዕጩዎች
1. ፕ/ር ኢ/ር አበበ ድንቁ (አአዩ)
2. ኬሚካል መሐንዲስ ጌታሁን ሄራሞ
3. ዶክተር አበበ በጅጋ
4. ፕሮፌሰር አሥራት ኃይሉ
5. ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት (ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል)

በሥነ ጥበብ ዘርፍ ዕጩዎች
1. አቶ አለ ፈለገ ሰላም
2. እማሆይ ጽጌ ማርያም ገብሩ
3. አቶ ተስፋየ አበበ(የክብር ዶክተር)
4. ሰዓሊ ታደሰ መስፍን
5. አባተ መኩሪያ
በበጎ አድራጎት ዘርፍ ዕጩዎች
1. ወ/ሮ አበበች ጎበና
2. አቶ አስመሮም ተፈራ /ሲኒማ ራስ አካባቢ የተቸገሩትን የሚረዳ/
3. ስንታየሁ አበጀ (የወደቁትን አንሱ) እንጦጦ ማርያም አካባቢ)
4. አቶ አስፋው የምሩ /የአሠረ ሐዋርያት ት/ቤት መሥራች/ ዊንጌት አካባቢ
5. ትርሐስ መዝገበ

በቢዝነስና ሥራ ፈጠራ ዘርፍ ዕጩዎች
1. አባ ሐዊ /አቶ ገብረ ሚካኤል (በትግራይ ክልል ለአብርሃ ወአጽብሐ አካባቢ ገበሬዎች ሥራ የፈጠሩ ገበሬ)
2. ሰላም ባልትና
3. አዋሽ ባንክ
4. ካፒቴን ሰሎሞን ግዛው
5. ካልዲስ ቡና
በቅርስና ባሕል ዘርፍ ዕጩዎች
1. አቶ ዓለማየሁ ፋንታ
2. አቶ ሀብተ ሥላሴ ታፈሰ
3. አቶ ዓለሙ አጋ
4. EMML /HMML(የኢትዮጵያ የብራና መጻሕፍት ማይክሮ ፊልም ድርጅት)
5. ማኅበረ ቅዱሳን

በማኅበራዊ ጥናት ዘርፍ ዕጩዎች
1. ፕ/ር ሪቻርድ ፓንክረስት
2. ደሳለኝ ራሕመቶ
3. ዶክተር ፈቃደ አዘዘ
4. ፕሮፌሰር ሺፈራው በቀለ
5. ፕሮፌሰር በላይ ካሣ

በጋዜጠኛነት ዘርፍ ዕጩዎች
1. አቶ መዓርጉ በዛብህ
2. አቶ ያዕቆብ ወልደ ማርያም
3. አቶ ነጋሽ ገብረ ማርያም
4. ታምራት ገብረ ጊዮርጊስ(ፎርቹን ጋዜጣ)
5. ቴዎድሮስ ጸጋየ

በስፖርት ዘርፍ ዕጩዎች
1. አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው
2. መምህር ስንታየሁ እሸቱ (ከበቆጅ ብዙ አትሌቶች እንዲወጡ ያደረገ መምህር)
3. መሠረት ደፋር
4. ኢንስትራክተር ሽፈራው እሸቱ
5. ዶክተር ወ/መስቀል ኮስትሬ

መንግሥታዊ ኃላፊነትን በብቃት በመወጣት ዘርፍ ዕጩዎች
1. አቶ ግርማ ዋቄ(የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩ)
2. አቶ መኮንን ማን ያዘዋል
3. አቶ ሽመልስ አዱኛ
4. ዐማኑኤል የአእምሮ ሕክምና ሆስፒታል
5. ኢንጅነር ስመኘው በቀለ

Health: የጥቁር አዝሙድ አስደናቂ የጤና በረከቶች

$
0
0

Black cumin
በሙለታ መንገሻ

ሰዎች ጥቁር አዝሙድን ለበርካታ ዓመታት ከተለያዩ ህመሞች ለመፈወስ ይጠቀሙበታል።

ጥቁር አዝሙድ በሞቃታማ አካባቢዎች የሚበቅል ተክል ሲሆን፥ በጥንት የስልጣኔ ዘመን ግብጾች እንደ አለርጂ፣ የሰውነት መመረዝ፣ ድብርት እና በርከት ያሉ የጤና ችግሮችን ለማከም ሲጠቀሙበት እንደነበረ ይነገርለታል።

ከሞት በቀር ሁሉንም በሽታ የሚያድን ተክል እስከማለት የሚነገርለት ጥቁር አዝሙድ ከዳቦ ጋር ቀላቅሎ መጋገርም የሚመከር ሲሆን፥ ይህም የሆድ ህመም፣ የሳንባ እንዲሁም ማስመለስን ለማስቆም ይረዳልም ይባላል።

ጥቁር አዝሙድ

ጥቁር አዝሙድ የሆዳችን ተግባር እንዲስተካከል በማድረግ የምግብ መፈጨት ስርዓትን ያፋጥናል።

እንዲሁም ከመተንፈሻ አካላት ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ እንደ አስም፣ ብሮንካይት እና ሌሎች ህመሞችን ለማከም ይረዳል።

በሽታ የመከላከል አቅማችንን በመጨመር እንደ ካንሰር ባሉ ህመሞች በቀላሉ እንዳንጋለጥም ይረዳናል።

የጥቁር አዝሙድ ዘይት

የጥቁር አዝሙድ ዘይት ለጤና በጣም ጠቃሚ ከሚባሉት ውስጥ ይመደባል።

ይህም እንደ ብሮንካይት፣ አስም እና ማይግሬይን የራስ ህመምን ለማከም እንደሚረዳ ይነገርለታል።

እንዲሁም የጸጉር መነቃቀልን የሚከላከል ሲሆን፥ ክብደትን ለመጨመር ለሚፈልጉም ጠቃሚ ነው ተብሏል።

በተጨማሪም የስኳር ህመምን ለማከም፣ እና የደም ግፊትን ለመቆጣጠር የሚረዳን ሲሆን፥ ችግሩ ያለባቸው ሰዎች ቢያንስ ለተከታታይ 6 ወራት ያህል በሚመገቡት ምግብ ውስጥ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ጨምረው እንዲመገቡ ይመከራል።

የጥቁር አዝሙድ ዘይቱን በምግባችን ውስጥ በምንጨምርበት ጊዜም ምግቡን አብስለን ከጨረሰን በኋላ መጨመር ይኖርብናል።

ሌሎች በሽታዎችን ለመከላከል ይረዳን ዘንድም በቀን ለሶስት ጊዜ አንድ የሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት መጠጣት ይመከራል።

አስምን ለማከም የሚረዳን የጥቁር አዝሙድ ሽሮፕ

አንድ የሻይ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ በደንብ እንዲደቅ አድርገን መውቀጥ፣ ሁለት ፍሬ ነጭ ስንኩርት የተፈጨ፣ ሁለት የሻይ ማንኪያ ማር አንድ ላይ በመደባለቅ፤ ውህዱን ሁሌም ጠዋት ከእንቅልፋችን እንደነቃን ከምግብ በፊት መጠጣት።

ምንጭ፦ yourhealthypage.com

ኃይለማርያም ደሳለኝ በጠቅላይ ሚኒስተርነታቸው ይቀጥላሉ ተባለ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በኦህዴድ; በብ አዴን እና በሕወሓት ውስጥ በተፈጠረው የስልጣን ሽኩቻ እየታመሰ የሚገኘው የኢሕአዴግ መንግስት በመጪው መስከረም ወር በሚመሰረተው “አዲሱ” መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ቦታውን ይዘው እንዲቆዩ እንደሚያደርግ የድርጅቱ የቅርብ ሰዎች ለዘ-ሐበሻ አስታውቀዋል::
hailemariam
በአሁኑ ወቅት በሶሥቱ ትላልቅ ፓርቲዎች ውስጥ የተፈጠረው አለመተማመን ሃይለማርያም በቦታቸው እንዲቆዩ እንደኢያደርጋቸው የሚገልጹት ምንጮች በተለይም በብ አዴን እና በ ኦህዴድ ውስጥ ተገቢ የሚባል ጥያቄ የሚጠይቁ አባላትን በሙስና ለማሰር ሃሳብ እንዳለ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ተናግረዋል::

ህወሃት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድ እና ደኢህዴን በያዝነው ወር ድርጅታዊ ጉባኤያቸውን በተናጠል በማካሄድ እያንዳንዳቸው ዘጠኝ አባላት ያሏቸውን የሥራ አስፈፃሚ አባላትን የሚመርጡ ሲሆን እነዚህ አባላትም በያዝነው ወር መጨረሻ ወይንም በመስከረም ወር መግቢያ በመቀሌ ከተማ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው የኢህአዴግ ጉባዔ ላይ የግንባሩን ሊቀመናብርት ይመርጣሉ ተባሏል:: የኢሕ አዴግ ሊቀመንበርም ሃይለማርያም ደሳለኝ ሆነው እንደሚቆዩና ሆኖም ግን ሌሎች ድርጅቱን ብዙ ዓመት አገልግለዋል የተባሉ ባለስልጣናት እንደሚሸኙ ተገልጿል::

የጠቅላይ ሚኒስተርነቱን ቦታን ሕወሓቶች አሁንም የሚፈልጉት ሲሆን የራሳቸውን ሰው ለማስቀመጥ ከላይ ታች እየተሯሯጡ ይገኛሉ:: ሆኖም ግን እርስ በ እርሳቸው መግባባት ስላልቻሉ ኃይለማርያም እንዲቀጥሉ ምክንያት ይሆናል ሲሉ ምንጮቻችን አክለው ገልጸዋል::

ጥቂት ስለ አቶ መለስ…የክፋት ጭንቅላት መስራት ካቆመ 3 አመቱ = በክፋት የተጨመቁ መሃይማን ግዞት ቀጥሏል

$
0
0

(ምንሊክ ሳልሳዊ)

መለስ ዜናዊ ከጅምሩ በክፋት የሰለጠነ መሆኑ እሙን ነው:;ድርጊቶቹ ሁሉ ይመሰክራሉ::አስተዳደጉ እንኳን ብናየው ከቀሪው ኢትዮጵያዊ ላይ ከፍተኛ የሆነ የጥላቻ ተረት ተረት እየተነገረው ያደገ ሲሆን በእድገት ዘመኑ እናትና አባቱ ብሎም የቅርብ ዘመዶቹ ሲናገሩ የሚሰማው የጣሊያንን ደግነት እና የኢትዮጵያውያንን ሃጢያተኝነት በተለይ የንጉሰነገስቶችን እና የአማራን ጥላቻ ሲሰበክ ያደገ የሰላቶ አገልጋዮች የባንድ ልጅ መሆኑ ይታወቃል::እንደዚህ አይነት ግለሰብ ለኢትዮጵያ ደግ ያስባል ለኢትዮጵያውያን መልካምነትን ይመኛል ማለት ከዘበትም በላይ በድርጊት የታየ ነው::ታሪክን የኋሊዮሽ ካየን በባንዳ ቤተሰብ ውስጥ ያደጉ ሰዎች እስከዛሬ ስለሃገር እና ስለሕዝብ የማያስቡ የጀርባ ቅማሎች ሆነው እያየናቸው ነው::

11231209_1623159974621065_3459709504333964141_n

በባንዳ ቤተሰብ ውስጥ የነጮችን የበላይነት ሲሰበክ ያደገው መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያውያን ላይ ያለው ጥላቻ ካደገ በኋላ ወደ መሃል አገር በሚያየው የኢትዮጵያውያን ደግነት እና ጨዋነት እንዲሁም ፍቅር ከመማረክ ይልቅ በቅናት እና ባደገበት ጥላቻ ተመርኩዞ የበታችነት ስሜቱ ስላጠላበት ትምህርቱን ጥሎ መሰደዱም ሌላኛው ባዶነቱን ያሳያል::በረሃም ገብቶ ለኢትዮጵያውያን ያልተኛው መለስ ዜናዊ በአላማ የማይለዩትን የተማሪ ቤት አጋሮቹን የሆኑትን የኢሕአፓ አባላት በመፍጀት እና በማስፈጀት ለሞት ለእስር እና ለስደት ዳርጓቸዋል::በበረሃ ቆይታው ከፍተኛ ወንጀሎችን በመስራት ከተባባሪዎቹ ከነስብሃት ነጋ ጋር በመሆን ወደ ከፍተኛ እርከን የደረሰው ይህ ሰው እጁ ከበለሃ ጀምሮ በደም የተነከረ ለአገር ይጠቅማሉ የተባሉ በርካታ ታጋዮችን ያጠፋ ሲሆን አብዛኛዎቹ ታጋዮች ሊጠፉ የቻሉት ኢትዮጵያዊ ከሚል የሃሳብ መደርደሪያ በመነሳታችው መሆኑ አንዱ ምክንያት ሲሆን በአስተሳሰብ ልዩነት አሊያም በልጠው የተገኙትን በማስገደል እና እንዲሰደዱ በማድረግ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል::

መለስ ዜናዊ ሱዳን ላይ ተቀምጦ አንድ ጥይት ሳይተኩስ በልጅነቱ ከጓደኛው ጋር ሲደባደብ የተፈነከተውን ጠባሳ ይዞ ጥይት መቶኝ ነበር በማለት ከፍተኛ በሃሰት የተሞላ ጀግንነት እና ጀብደኝነት ሲያወራ የነበር የሃሰት ሰው ነበር::ማንበብ የሚወደው የማኪያቬሊዝም ፍልስፍና ተከታይ የሆነው መለስ ዜናዊ ከበረሃ በኋላ በሃገር ድረጃ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ ከፍተኛ ወንጀሎችን ብመላው ኢትዮጵያውያን ላይ ፈጽሟል::ትዘርዝሮ የማያልቅ የፖለቲካ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ወንጀሎችን የፈጸመው መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያውያን ካለቤተሰብ በትኗል አስገድሏል አሰድዷል አስሯል በአንድ አገር ውስጥ መሪ ነኝ ከሚል አንድ ባለስልጣን የማይጠበቅ ሁኔታ በዜጎች ላይ ከፍተኛ ታሪክ ይቅር የማይለው ከሱ በፊት የነበሩ መንግስታት ያልፈጸሙትን በገሃድ እና በሕቡእ ከባባድ ወንጀሎች ፈጽሟል::የመለስ ዜናዊ ወንጀሎች ተዘርዝረው አያልቁም::በአለም አቀፍ ደረጃ ቱጃር ከሚባሉት የአገር መሪዎች ግንባር ቀደም የነበረው መለስ ዜናዊ የሃገራችንን አንጡረ ሃብት ርሕራሄ በሌለው ሁኔታ ከነሚስቱ እና አሾክሻኪዎቹ ጋር በመሆን ዘርፏል::

የመለስ ዜናዊን ወንጀል ተንቶ ለመጻፍ እጅግ ብዙ ጊዜ ይወስዳል::በስልጣን ዘመኑ አንድ ቀን ሃገሬ ሳይል “ይህቺ ሃገር…” ምናምን እንዳለ ሕዝብን እየተሳደብ ሲያፈናቅል እና ሲያሸማቅቅ የሞተው ይህ ከይሲ የሱን ፈለግ የተከተሉ እና በክፋት የተጨመቁ ባለስልጣናት እና በነፈሰበት የሚነፍሱ አጋሮቻቸው በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ተቀምጠው እየገደሉ እያሰሩ እያሳደዱ እና እየዘረፉ በመኖር ላይ ይገኛሉ ::እነዚህ አምባገነን የማፊያ ቡድን መንግስታዊ አሸባሪዎችን ከኢትዮጵያ ምድር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት ሁላችንም በጋራ ሆነን ከትግሉ ጋር ተቀላቅለን እጅ ለእጅ በመያያዝ በሃገር ውስጥ እና በዳር አገር የተጀመረውን ትግል ዳር በማድረስ ለድል በመብቃት ነጻነታችንን እና መብታችንን ማስከበር ይጠበቅብናል::የመለስ ዜናዊን የሙት መንፈስ እና የአምባገነን የወያኔ ጉጅሌዎችን ማጥፋት የምንችለው እያንዳንዳችን ስለ ነጻነታችን በምንከፍለው መስእዋትነት እና የዜግነት ግዴታ መሆኑን አንዘንጋ::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live