Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ታገሉ! ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ /ከዝዋይ እስር ቤት/

$
0
0

ከኤልያስ ገብሩ

ስለሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ፍርድም 

ሀሳቡን ሰንዝሯል
———-
ቦሌ አካባቢ ብርዱ ጠንከር ያለ ነበር፡፡ ከቦሌ ብራስ ወደሚሊኒየም አዳራሽ በሚወስደው ቀጭን መንገድ ላይ ወንዱም ሴቱም በፍጥነት ይራመዳል፡፡ ከታክሲ በሁለቱም አቅጣጫዎች የወረዱ ሰዎች ወደመደበኛ ሥራቸው ለመግባት ብሎም የግል ጉዳያቸውን ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ ነበር – ከትናንት በስትያ ሰኞ (ነሐሴ 04 ቀን 2007 ዓ.ም) ጥዋት 1፡45 ሰዓት፡፡
እኔ እና ወዳጄ አቤል ዓለማየሁ ወደከአዲስ አበባ 160 ኪሎ ሜትር ርቀት ወደሚገኘው ዝዋይ እስር ቤት አምርተን ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬን እና ተመስገን ደሳለኝን ለመጠየቅ በዚህ ቀን ቀጠሮ ይዘን ነበር፡፡ አቤል ከቀጠሯችን 20 ደቂቃ ዘግይቶ፣ ቦሌ ጫፍ ደረሰና ወደቃሊቲ መናሃሪያ ሁለት ታክሲዎችን በመጠቀም ደረስን፡፡ ወደዝዋይ የሚጭኑ ሚኒባስ ታክሲዎች እና ‹‹አባዱላ/ዶልፊን›› የሚል መጠሪያ የተቸራቸው የህዝብ ማመላለሻ መኪኖች ቢኖሩም በተለምዶ ‹‹ቅጥቅጥ›› የሚባለውን መካከለኛ አውቶቡስ ምርጫችን አደረግን – የትራፊክ አደጋን በመስጋት፡፡

Temesgen Desalegn behindbar
የተሳፈርንበት አውቶቡስ፣ ከቃሊቲ ትንሽ ወጣ ካለ በኋላ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ በእስር ላይ የሚገኙትን የግንቦት 7 ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ “ልማቱን አሳዩኝ” ሲለን ከከተማ ወጣ እያደረግን የምነሳየው… [እውነት ግን፣ በከባድ እስር ላይ መሆናቸው የሚገመተው አቶ አንዳርጋቸው ‹ልማቱን አሳዩኝ› ይሏቸዋልን?!]›› ሲሉ ለቪኦኤዋ ጋዜጠኛ ትዝታ በላቸው የገለጹትን፣ የአዲስ አበባ አዳማ አዲሱ የፍጥነት መንገድ (Express way)ን ተቀላቀለ፡፡ በዚህ መንገድ ሁለታችንም ሄደን አናውቅም ነበር፡፡ ሆኖም እስከዛሬ ካየኋቸው የመኪና መንገዶች በደረጃው ከፍ ያለ ይመስላል፡፡ [በሀገራችን አምረው የተሰሩ የመኪና መንገዶች በጥቂት ዓመታት ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ የመቦርቦር፣ የመፈረካከስ፣ ውሃ የማቆር ችግሮች ገጥሟቸው እንዲሁም ከመንገዱ ዳር እና ዳር የሚገኙ የብረት አጥሮች ተሰርቀው፣ ተገጭተው፣ ተጨረማምተው፣ ተነቃቅለው … አደጋ ሲያደርሱና የተለመደ የሬንጅ የመለጠፍ ሥራ ሲሰራላቸው በገሃድ የምናየው ሀቅ መሆኑን ማስታወስ ግን የግድ ይላል] ይሄኛው መንገድ ከጠቀስኳቸውና ካልጠቀስኳቸው ችግሮች ምን ያህለ ነጻ ነው? ለሚለው ትክክለኛ መስክርነት መስጠት ያለበት ለእውነት የቆመ የዘርፉ ባለሙያ ቢሆንም በኢህአዴግ ‹ልማት› ላይ የጥራት መተማመኛ ማግኘት እጅግ ከባድ መሆኑን ግን አምናለሁ፡፡ አስፋልቱ ለፍጥነት አመቺ መሆኑን ግን በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡
በሶስት ሰዓታት ጉዞ ዝዋይ በመድረስ ምሳ ከበላን በኋላ ወደእስር ቤቱ የፈረስ ጋሪ መጠቀም ግዴታችን ነበር፡፡ አቧራማው አስቸጋሪ መንገድ፣ ከፊሉ ደቃቅ አሸዋ መልበስ ጀምሯል፡፡ የእስር ቤቱ የማስፋፊያ ግንባታ ሥራ፣ በፊት ውብሸትን ለመየጠቅ ስመጣ ከማውቀው ተፋጥኗል፡፡ አንዱ የሥርዓቱ “የልማት ውጤት” እስረኛ ማብዛት አይደለ ታዲያ?!
ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ላይ የምንጠይቀውን እስረኛ በማስመዝገብ ተፈትሸን ገባን፡፡ ሁለት እስረኛ በአንዴ መጠየቅ ስለማንችል እኔ ተመስገን ጋር፣ አቤል ደግሞ ውብሸትን ለመጠየቅ ተስማምተን ነበር፡፡ አቤል ውብሸትን ከጠየቀ በኋላ እንደምንም ብሎ ተመስገንን ለመጠየቅ ጥረት እንደሚያደርግ ግን ቀድሞ ነገረኝ፡፡
ተመስገን እና ውብሸት የታሰሩበት ዞን ስለሚለያይ እኔ እና አቤል ሌላ የውስጥ ፍተሻ ካደረግን በኋላ መለያየታችን ግድ ነበር፡፡ የእስር ቤቱ ፖሊሶች የሚኖሩበትን ጉስቁልና ያጠቃቸው፣ መኖሪያ ቤቶችን አልፌ መጠየቂያው ጋር ደርሼ የታሳሪው ስም ያለባትንና በፖሊሶች የምትጻፈዋን ቁራጭ ወረቀት እስረኛን ለሚጠራው ፖሊስ ሰጠሁትና በአጣና እንጨት ርብራብ በተሰራው መጠየቂያው አግዳሚ ላይ ተቀመጥኩ፡፡ ከቅርብ ርቀት የፖሊሶች ማማ ይታያል፡፡ መሳሪያ የታጠቁ ፖሊሶች ማማው ላይና ከማማው ሥር በዛ ብለው ተቀምጠው ያወጋሉ፡፡ አብዛኞቹ ፖሊሶች ከላይ የለበሷት እና “Federal prison” የሚል የታተመባት አረንጓዴ ዩኒፎርምም በፀሃይ ብዛት ነጣ ወደማለት ደርሳለች፡፡ አንዱ ፖሊስ መጣና ከእኔ በትንሽ ሜትር ራቅ ብሎ ተቀመጠ፡፡ ‹‹አዳማጭ ነው›› አልኩ በልቤ፡፡ ወደፊት ለፊቴ ወደሚታየኝ የእስር ቤት ግቢ አማተርኩ፡፡ ለእይታ የሚጋብዝ አንዳች ነገር አጣሁ፡፡ የተበታተኑ ዛፎች፣ ቅርጽ አልባ ሳሮች፣ አስታዋሽ ያጡ አረሞች፣ ግድግዳ እና ጣራቸው በቆርቆሮ የተሰሩ የእስረኛ መኖሪያዎች፣ …ብቻ ጭርታ እና ድብታ የወረረው የግዞት መንደር ይመስላል፡፡
ከአንደኛው የእስረኛ ቆርቆሮ ቤት ጣሪያ ላይ ሁለት ተለቅ ተለቅ ያሉ ሙቀት ማቀዝቀዣዎች ይሽከረከራሉ፡፡ ወደፖሊሱ ዞሬ ‹‹ለሙቀት ነው?›› አልኩት ወደ ጣራው በመጠቀም፡፡ ‹‹አዎ፣ ወባ አደገኛ ነው›› አለኝ፡፡ ‹‹እስረኞች ሲታመሙ እንዴት ይሆናሉ?›› ስል ጥያቄ ሰነዘርኩ፡፡ ‹‹ያው እዚሁ ይታከማሉ›› አለኝ ድምጹን ቀሰስ አድርጎ፡፡ የእኔም ሆነ የእሱ ልብ፣ በማረሚያ ቤቱ (በእነሱ አጠራር) በቂ ህክምና እንደማይሰጥ ግን ያውቃል ብዬ አሰብኩ፡፡ ቀጭኑ ፖሊስ፣ ‹‹ለወባ ህመም ምግብ ወሳኝ ነው›› አለኝ አስከትሎ፡፡ ‹‹በቂ ምግብ የለም ማለት ነው?›› ስል ድጋሚ ጠየኩት፡፡ ‹‹በፊት በፊት አቀራረቡ ዝም ብሎ ነበር፤ ሙያ ባሌላቸው ሴቶች ነበር የሚሰራው፡፡ አሁን ግን ለውጥ አለ›› አለኝ፡፡ ‹‹ምን አይነት ለውጥ? ጥቂትም ቢሆን ታስሬ፣ ለእስረኞች የሚቀርበውን በጣም ደረጃውን ያልጠበቀ ምግብ አይቻለሁ›› አልኩት፡፡ ‹‹በፊት ጥቁር ጤፍ ነበር የሚቀርበው፤ አሁን የነጭ ጤፍ እንጀራ ነው የሚበሉት፤ እስረኞች ችግር የለባቸውም፤ ባለሙያ ሴቶችም ናቸው የተቀጠሩት …›› ‹‹(ውስጤ አላመነምና) ለእስረኛ የነጭ ጤፍ እንጀራ እያቀረባችሁ ነው?!›› …‹‹አዎ›› ብሎ ሊያብራራልኝ እያለ ከታች ከርቀት ‹‹አረንጓዴ ኮፊያ፣ ቲ-ሸርትና ስካርፍ ያደረገ ሰው አየሁ፡፡ ትኩረቴን ከፖሊሱ አዙሬ ቁልቁል ተመለከትኩ – ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ነበር፡፡ ተሜም፣ ረጋ ብሎ በራስ በመተማመን መንፈስ ወደመጠየቂያው ሥፍራ ቀረብ ብሎ ጠያቂውን ለማወቅ ጥረት አደረገ፡፡ ሳየው አንዳች የሀዘን ስሜት ውስጤ ገባ፡፡ ቆሜ ጠበኩት፡፡ ፈገግ እያለ መጣና ተጨባብጠን አራት አምስቴ ያህል ተቃቀፍን፡፡ ‹‹በዚህ በጸሐይ ለምን መጣህ?›› ሲል ጠየቀኝ፡፡ ከአቤል ጋር መምጣታችንን፣ እሱ ውብሸትን ሊጠይቀው መሄዱን ነገር ግን ከቂሊንጦ በኋላ እስከአሁን ዝዋይ ድረስ መጥቼ ባለመጠየቄ የጸጸት ስሜት ውስጤ እንዳለ ገለጽኩለት፡፡ ‹‹መንገዱ ረዥም ነው፣ ባትመጡም እረዳለሁ›› ካለ በኋላ፤ ‹‹ምን አዲስ ነገር አለ?›› በማለት ፊት ለፊት በእንጨት አጥር ተከልለን በመቀመጥ ጨዋታችንን ቀጠልን፡፡
‹‹አሁን ምን እየሰራችሁ ነው?››፣ ‹‹ክስህስ እንዴት ሆነ?››፣ ‹‹አዲስ ጋዜጣ ለማቋቋም ለምን ጥረት አታደርጉም?›› ከተመስገን በተከታታይ የተነሱ ጥያቄዎች ነበሩ፡፡ አጠር አጠር አድርጌ መለስኩለት፡፡ የጋዜጣ /የመጽሔት ህትመትን ድጋሚ መጀመር የግድ አስፈላጊ መሆኑን ግን ተመስገን አጽንኦት የሰጠበት ጉዳይ ነበር፡፡ …ስለተወሰኑ ጋዜጠኞችና የዞን 9 ጦማሪያን ከእስር መፈታት፣ ስለኦባማ የአዲስ አበባ ጎብኝት፣ በቂሊንጦ ዞን አንድ ከእነአብበከር አህመድ፣ ጦማሪ አቤል ዋበላና ዘላለም ክብርት ጋር ስለነበረው ቆይታ፣ እሱ ወደዝዋይ ከወረደ በኋላ እኔም በዚያ ዞን ገብቼ በነበረበት ጊዜ እነአቡበከር፣ አቤልና ዘላለም እሱን በተመለከተ ስለነገሩኝ ነገሮች ሳቅ እያልን አወጋን፡፡
ሰፊ ውይይት ያደረግነው በሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ በቅርቡ ከ7 እስከ 22 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ፍርድን በተመለከተ ነበር፡፡ ‹‹እኛ ከሙያ ጋር በተያያዘ ነው የታሰርነው፡፡ ታስረንም እንወጣለን፡፡ ከባዱ የሙስሊሞቹ እስር ነው፡፡ ኢህአዴግ እውነተኛ ሰላም ከፈለገ እነአቡበከርን በነጻ መፍታት አለበት፡፡ እኔ የእነሱ መከላከያ ምስክር ሆኜ ምስክርነቴን ሰጥቻለሁ፡፡ በወቅቱ ዘንግቼው ያልተናገርኩት አንድ ነገር ነበር፤ አሁን ሳስበው ትንሽ ይቆጨኛል – በተናገርኩ ብዬ፡፡ ያኔ (በምስክርነት ጊዜ)፣ ‹የኮሚቴዎቹ እንቅስቃሴ ሰላማዊ ነበር ወይስ አልነበረም?› የሚለው ጥያቄ በራሱ መነሳት አልነበረበትም፡፡ እንቅስቃሴያቸው፣ ሰላማዊ ባይሆን ኖሮ እንዴት ሶስት ዓመት ሙሉ በክስ ሂደት ይቀጥላል?! ሰላማዊ ስለሆኑ እኮ ነው፣ ባለፉት ሶስት ዓመታት ምንም ያልተፈጠረው፡፡ እስኪ በእነሱ አንድ የተሰበረ መስታወት አለ?! ቅንጣት የወደመ ንብረት አለ?! የማንንስ ሕይወት አጠፉ?! በእነሱ የተፈጠረ አንድም ነገር የለም፡፡ ጥያቄያቸው ኃይማኖታዊ እንጂ ፖለቲካዊ አይደለም፡፡ ፖለቲካዊ ቢሆን ኖሮ ትግሉ አቅጣጫውን ይቀይር ነበር፡፡ ‹የመጅሊስ አመራሮችን ካለመንግሥት ጣልቃ ገብነት እንምረጥ!› ነው አንዱ ሰላማዊ ጥያቄያቸው፡፡ ያው ምስክር ስትሆን ከዚህም ከዚያ ጥያቄ ሲነሳ ስለምትዘናጋ መመስከር ያሰብከውን ነው ቅድሚያ የምትሰጠው እንጂ አሁን የምልህን ያኔ ብገልጸው በጣም ደስ ይለኝ ነበር …›› በማለት በኢትዮጵያ ውስጥ ከታሪክ አኳያ፣ በሁለቱ ትልልቅ ሃይማኖት ተከታዮች መካከል ስለነበረው ግንኙነት በዝርዝር የራሱን ምልከታ እና ሀሳብ ደጋግሞ አወጋኝ፡፡ ኃይማኖታዊ መቻቻል ነበር ወይስ አልነበረም? የሁለቱም እምነት ተከታዮች ጉርብትና ነበራቸው ወይስ አልነበረባቸውም በሚሉት አንኳር ጉዳዮችም የራሱን አቋም አንጸባረቀልኝ፡፡
ኡስታዝ አቡበከር አሕመድን አስመልክቶም አንድ ጥሩ ምሳሌም አንስቶልኝ ነበር ተመስገን፡፡
‹‹አሁን ባለሁበት ዞን፣ በአንድ የወንጀል ክስ ግብረ-አበር ተብለው አምስት ዓመት የተፈረደባቸው አንድ ቄስ አሉ፡፡ እኚህ ቄስ ለጠበቃ የሚከፍሉት አጥተው የጠበቃ ክፍያ የፈጸመላቸው አቡበከር እንደሆነ ነግረውኛል››
እኔም ፣ በህዳር ወር ቂሊንጦ ዞን አንድ በነበርኩበት ጊዜ ከዚህ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ነገር፣ ስለአቡበከር ሰምቼ ነበር፡፡ ታሪኩ እንዲህ ነው፡- አንዱ እነአቡበከር ይገኙ በነበረበት ዞን 1 8ኛ ቤት ውስጥ የቀጠሮ እስረኛ ነበር፡፡ ዋስትና ይጠየቅና በዚህ ክፍል ውስጥ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ አንድ የናጠጡ ሀብታም (ልጃቸው 22 አካባቢ እጅግ ዘመናዊ ሆቴል አለው) ጋር ጠጋ ብሎ ለዋስትና የሚሆን ብር ተጨንቆ በአክብሮት ይጠይቃቸዋል፡፡ እሳቸውም ‹‹እኔም እንደአንተው እስረኛ እኮ ነኝ!›› በማለት ይመልሱለታል፤፡፡ ልጁም ያዝናል፡፡ ይህ ጉዳይ አቡበከር ጆሮ ይገባና ለልጁ የሚስፈልገውን የዋስትና ብር ከፍሎ ልጁን ከእስር እንዲወጣ አድርጎታል፡፡ እንግዲህ፣ ከሁለቱ እውነተኛ ምሳሌዎች በመነሳት፣ አቡበከር ለወገኖቹ ሃይማኖትን መሰረት ሳያደርግ፣ በሰብዓዊነት ደግ መሆኑን እንማራለን፡፡
ከተመስገን ጋር በነበረን ሰፋ ባለ የጨዋታ ጊዜ፣ ከጎኔ የነበረው ፖሊስ በተመስጦ ቢያዳምጥም፣ አንዴም አላቋረጠንም ነበር፡፡ …ስለ 100% ቱ የዘንድሮ ምርጫ ፍጻሜ፣ በሰሞኑ በአፋር ክልል ስለደረሰው የድርቅ አደጋ፣ በአይ ኤስ አሸባሪ ቡድን ስለተቀሉና ስለተገደሉት ኢትዮጵያኖች፣ ድርጊቱን በማውገዝ በመስቀል አደባባይ በተጠራው ሰልፍ ላይ ስለተፈጠረው ረብሻ፣ ጉዳትና እስር ተመስገን የራሱን አተያይ በስሜት ተውጦ የግሉን ሀሳብ አብራራልኝ፡፡ በተጨማሪም፣ አይ ኤስ ያንን ድርጊት፣ ያንን ጊዜ መርጦ አደረገ ያለበትን የራሱን የተለየ (ከማንም ያላደመጥኩትን፣ ተጽፎም ያላነበብኩትን) ሀሳብ አጋራኝ፡፡ የተለየ ሃሳብ በመሆኑም ‹‹አሃ!›› ብያለሁ፡፡
ከተመስገን በጣም የገረመኝ፣ የማስታወስ ችሎታው ነበር፡፡ በጥቅምት ወር፣ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ‹‹ጥፋተኛ›› በተባለበት ማግስት ጥዋት አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ልጠይወቅ ሄጄ በማያመች ሁኔታ ውስጥ ሆነን አብዮትን አስመልክቶ የተለዋወጥናቸውን ሃሳቦችን፣ እንዲሁም ከአቤል ጋር ቂሊንጦ ስንጠይቀው ያነሳናቸውን ሀሳቦች ድጋሚ በማስታወስ በዚህ ቀን ለተነሱት ርዕሰ ጉዳዮች የውይይት ማጠናከሪያ ሀሳብ ሲያደርጋቸው አስተውያለሁ፡፡
ለተመስገን አሁን ስለሚገኝበት ዞን ሁኔታ ጥያቄ አቀረብኩለት፡፡ ቀደም ሲል ከእነውብሸት ጋር አብሮ እንደነበረ ጠቅሶ፣ ‹‹የኢትዮጵያ ገመና›› በሚል ርዕስ በእስር ቤት ውስጥ ስላወቀው ነገር ሁለት ተከታታይ ጽሑፎችን ካወጣ በኋላ ወደዚህ ዞን መዘዋወሩን ይገልጻል፡፡ አሁን ባለበት ክፍል 80 የሚሆኑ እስረኞች አብረውት አሉ፡፡ ብዙዎቹ ከደቡብ ክልል የመጡ ናቸው፡፡ ከእሱ ጋር አንድም የፖለቲካ እስረኛም ሆነ ጋዜጠኛ አብሮት የለም፡፡ [አቶ በቀለ ገርባ ከወራቶች በፊት የ3 ዓመት ከ7 ወር የእስር ጊዜያቸውን አጠናቅቀው ከዝዋይ እስር ቤት በተፈቱ ማግስት ተመስገን ከባድ ወደሆነው ወደዚህ ዞን መሸጋገሩን ነግረውኝ ነበር] አሁን ባለበት ዞንም ከእሱ ጋር እስረኞች እንዳያወሩ እና እንዲያገልሉት በዘዴ ተደርጓል፡፡ ከእሱ ጋር በቅርበት ሆነው የሚያወሩ ካሉ፣ እንደትልቅ ተስፋ በሚጠብቁት አመክሯቸው ላይ እንደመፍረድ ይቆጠራል እንደተመስገን አባባል፡፡ ‹‹በዚህ ጉዳይ ማናቸውም ላይ አልፈርድም፤ ከእኔ ጋር አውርተው የአመክሮ ጊዜያቸውን እንዲያጡ አልሻም፡፡ ግን እንዲህ ያደረጉት ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች ቢሆኑ ኖሮ ይሰማኝ ነበር፡፡›› ሲል ያለበትን ከባድ ሁኔታ ያስረዳል፡፡
‹‹ማንበብ፣ ማጸፍስ ትችላለህ?›› ሌላኛው ጥያቄዬ ነበር፡፡ ‹‹መጽሐፍ አይገባም ተልክሏል፤ ያነበብኳቸው ጥቂት ልብወለድ መጽሐፍቶች አሉ፡፡ መጻፍ ትንሽ ጀምሬ በእስረኞች በኩል ተጠቁሞ የጻፍኩት ተወሰደ፡፡ ሁለት ሶስቴ ለመጻፍ ሞክሬ ነበር፡፡ ግን ተመሳሳይ እርምጃ በመወሰዱ ተውኩት፡፡›› ይላል ተመስገን፡፡ ‹‹ቀኑን እንዴት ነው የምታልፈው?›› የሚለው የመጨረሻ ጥያቄዬ ነበር፡፡ ‹‹ሁለት የማውቃቸው የአዲስ አበባ ልጆች አሉ፤ ጫናውን ችለው ያናግሩኛል፡፡ ከእነሱ ጋር ቼዝ እጫወታለሁ፡፡ የእግር ኳስ ፕሮግራም የሚተላለፍባቸው ቻናሎች ቢኖሩም መገለሉን አስበውና ደስ ስለማይለኝ ወደክፍሌ እገባለሁ›› የሚለው የተመስገን መልስ ነበር፡፡
ተመስገን አቤልን ከርቀት አይቶት ‹‹ያ አቤል ነው አይደለ?›› አለኝ፡፡ ዞሬ አየሁት፣ አቤል ውብሸትን ጠይቆት ከርቀት ወደመውጪያው በር እየሄደ ነበር፡፡ ‹‹ግን እንዴት አስገቧችሁ?፤ ይመልሱ ነበር እኮ›› አለኝ፡፡ አቤልም ተመስገንን ተመስገንም አቤልን ማግኘት ፈልገው ነበር፡፡ ብዙም ሳይቆይ አቤል አንዱን ፖሊስ እንደምንም አናግሮ ተመስገንን ሊጠይቅ መጣ፡፡ ተቃቅፈው ተሳሳሙ፡፡ የሶስትዮሽ ጨዋታችንን ለግማሽ ሰዓት ያህል አደራነው፡፡ ተመስገን ከታሰረ በኋላ የግራ ጆሮው እንደማይሰማለት እና ወገቡም ሕክምና በማጣቱ አሁንም ድረስ እንደሚያመው አልሸሸገንም – ‹‹እዚህ ያለው መድኃኒት ፓናዶል ብቻ ነው›› በማለት፡፡ አያይዞም ‹‹ሰው መጥቶ ሲጠይቅህ ደስ ይላል፤ ጥሩ እንቅልፍ ትተኛለህ፤ግን የመንገዱን ርቀት ሳስበው ሰው ባይመጣ እላለሁ›› አለን በድጋሚ፡፡
የእስረኛ መጠየቂያ ጊዜ መጠናቀቁን ፖሊሶች ነገሩንና ተቃቅፎ መለያት ግድ ሆነ፡፡ ‹‹አይዞህ የምትባል አይደለህምና ሰላም ሁን›› አልኩት፡፡ ‹‹ምን መልዕክት አለህ?›› ስል የመጨረሻ ጥያቄዬን ሰነዘርኩለት፡፡ ተመስገንም ‹‹ታገሉ!›› ሲል መለሰና በመጣበት መንገድ ቻው ብሎን እርምጃውን ቀጠለ፡፡ ሲሄድ አራት እና አምስት ጊዜ ያህል ዞረን አየነው፡፡ ስለገኘነው ደስ ቢለንም በሳሮች መካከል ባለው መንገድ ወደታሰረበት ክፍል ሲያመራ ማየት ዳግመኛ የመረበሽ እና የማዘን ስሜት በውስጤ ፈጥሮብኝ ነበር፡፡ ስሜቱ በጣም የሚገባው በቦታው ላይ ሲገኙ ነው!
ተመስገን፣ ያመነበትን ሀሳብ በድፍረት ስለጻፈ ነበር በኢ-ፍትሃዊነት ሶስት ዓመት እስር የተፈረደበት፡፡ ሰው መታሰሩ ሳያንስ፤ ከቤተሰቡ፣ ከወዳጁ፣ ከዘመዱ፣ ከጓዳኞቹ እርቆ እንዲታሰር ማድረግ ሌላ ቅጣት ነው! ሰው መታሰሩ ሳያንስ፣ ህክምና መከልከሉ፣ በሌሎች እስረኞች እንዲገለል መደረጉ፣ መጽሐፍ ማንበብ እና የግል ማስታወሻዎቹን እንዳይጽፍ መከልከሉ ይሄም ሌላ ቅጣት ነው! ሰው ግን በስንቱ ይቀጣል?! እንዲህም ሆኖ፣ ትናንት የምናውቀው ጋዜጠኛ ተመስገን፣ አሁንም ድረስ ያ ያመነበትን የመናገር ድፍረቱ፣ መንፈሳዊ ብርታትና ጥንካሬው አብሮት አለ!!! አካል ቢታሰር ህሊና መቼም አይታሰር!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!


የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች በእያንዳንዳቸው የ15 ሺህ ብር ዋስ ተጠየቀባቸው

$
0
0

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
ከምርጫው ማግስት ከአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በፖሊስ ተይዘው የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እያንዳንዳቸው 15 ሺህ ብር ዋስ ተጠየቀባቸው፡፡ አመራሮቹ ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ አራት ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ፖሊስ በሽብርተኝነት ወንጀል እንደጠረጠራቸው ሲገልጽ ቆይቷል፡፡ ፖሊስ ‹‹ለግንቦት 7 አባላትን እየመለመሉ ይልካሉ፡፡ ኤርትራ ድረስ ሄደው ስልጠና ወስደዋል፡፡›› የሚል ክስ አቅርቦባቸው የነበር ቢሆንም ለክሱ ምንም አይነት ማስረጃ ሳያቀርብ ቀርቷል፡፡ አመራሮቹ በበኩላቸው የታሰሩት በሰላማዊ ትግል ጠንካራ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ በመሆናቸው፣ በተለይም በምርጫው ወቅት ፓርቲያቸውን በማስተዋወቅና ህዝብን በማደራጀት ጠንካራ ስራ በመስራታቸው ገዥው ፓርቲ የወሰደባቸው በቀል መሆኑን ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡ ከመታሰራቸው በፊት የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች ከፖለቲካው እንዲርቁ ሲያስጠነቅቁዋቸው እንደቆዩም አስታውቀዋል፡፡
ፖሊስ ላቀረበው ክስ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ዛሬ ነሃሴ 6/2007 ዓ.ም ከምርጫው ማግስት እየታደኑ ከታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች መካከል 8ቱ እያንዳንዳቸው የ15 ሺህ ብር ዋስ አቅርበው እንዲፈቱ ወስኗል፡፡ ከምርጫው በኋላ ታስረው በዛሬው ዕለት እያንዳንዳቸው 15 ሺህ ብር ዋስ ከፍለው እንዲወጡ የተጠየቀባቸው፡-
1. ልዑልሰገድ እምባቆም
2. ፋንታሁን ብዙአየሁ
3. መንግስቴ ታዴ
4. አበረ ሙሉ
5. አዳነ አለሙ
6. ሞላ የኑስ
7. ስማቸው ምንይችል
8. አበባው አያሌው ናቸው፡፡
ዛሬ ፍርድ ቤቱ በ15 ሺህ ብር ከፍለው ይውጡ ካላቸው በተጨማሪ በአማራና በደቡብ ክልል በርካታ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ታስረው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተለይም ከተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ታድነው ከተያዙ በኋላ ባህርዳር ከተማ ውስጥ ታስረው የሚገኙት የፓርቲው አመራሮችና አባላት ከፍተኛ ድብደባ እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

አለቃዎ ሳይሆን ቅን ህሊናዎ የሚያዝዎትን በመፈፀም መልካም ዜጋ ይሁኑ!- አርበኞች ግንቦት 7 

$
0
0

መልካም ዜጋ ማለት ምን ማለት ነው?

ginbot 7ይህን ጥያቄ ለመመለስ በርካታ መጻሕፍት መፃፍ ይቻላል፤ መሠረተ ሀሳቡን ግን በጥቂት ዓረፍተ ነገሮች ማቅረብ ይቻላል።

መልካም ዜጋ ኢፍትሃዊ ተግባር ሲፈፀም “እኔ ምናገባኝ?” አይልም። መልካም ዜጋ “ያባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ”፤ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶም አይብቀል”፤ “እያለህ ካልሆነ ከሌለህ የለህም” እና በርካታ መሰል ምሳሌዎችን አይሰማም። መልካም ዜጋ በማናቸውም ሁኔታ ውስጥ ቢሆን ከነፃና ቅን ህሊናው ጋር ታርቆ ይኖራል።

የህወሓት አገዛዝ፣ መልካም ዜጋ ማለት የመንግሥት ሥልጣን የያዘን ማንኛውም አካል ማክበርና በታማኝነት ማገልገል ተደርጎ እንዲተረጎምለት ይሻል። ፍትህ የሚያዛባ መንግሥትን መቃወም የመልካም ዜጋ አቢይ ተግባር መሆኑ የዘመናችን ወጣት እንዳይገነዘብ ያደርጋል። በተለይ ባለሙያዎች የሚያገለግሉትን አገዛዝ ባህርይ እግምት ውስጥ ሳያስገቡ የተቀጠሩበትን ሥርዓት በታማኝነት ማገልገል የዜግነት ግዴታቸው አድርገው እንዲወስዱት ይወተውታል።

ኦስካር ግሮኒንግ ( Oskar Groening)የዘጠና አራት ዓመት ሽማግሌ ጀርመናዊ ነው። በጀርመን የሂትለር አገዛዝ ወቅት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ንፁሃን የተፈጁበት አሽዊትስ ካምፕ ውስጥ የሂሳብና ጽህፈት ሠራተኛ ነበር። ኦስካር ግሮኒንግ አንድም ሰው አልገደለም፤ አንድም ሰው አልገረፈም። እሱ ሂሳብ ነው የሠራው። ሆኖም በደል ሲፈፀም አይቶ “ምናገባኝ” ብሎ አልፏልና ከብዙ ዓመታት በኋላ ተከሶ በቅርቡ የ4 ዓመታት እስር ተፈርዶበት በሁለት እግሮቹ መቆም በማይችልበት በ 94 ዓመቱ በእርጅናውና በመጦሪያው ዘመን ቤተሰቦቹና ጓደኞቹ ፊት ተዋርዶ እስር ቤት ወርዷል።

በአንፃሩ ኦስካር ሽንድለር (Oskar Schindler) በጀርመን ናዚ ወቅት ሂትለር ይመራው የነበረው የናዚ ፓርቲ አባልና ሰላይ ነበር። ሆኖም ግን የሥርዓቱን ኢሰብዓዊነት ሲረዳ እዚያው የናዚ ፓርቲ ውስጥ ሆኖ አለቆቹ ያዘዙትን ሳይሆን ቅን ህሊናው ያዘዘውን በምስጢር መሥራት ጀመረ፤ በዚህም የ 1200 ሰዎችን ሕይወት ታደገ። ከጦርነቱ በኋላ ኦስካር ተከብሮ የኖረ በርካታ የክብር ስሞችና ሽልማቶች የተሰጠው በመልካም አርዓያነቱ የሚጠቀስ ሰው ሆነ።

በአገራችንም በአምስት ዓመታቱ የፋሽስት ወረራ ወቅት ስመ ጥር የውስጥ አርበኞች ነበሩ። ከነፃነት በኋላ ባንዶች እንኳን በውስጥ አርበኝነት ለመጠራት ያደርጉት የነበረውን እሽቅድድም ልብ በሉ።

በህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴግ፣ ደህዴግ እንዲሁም አብዴፓ፣ ቤጉህዴፓ፣ ጋህአዴን፣ ሀብሊና ኢሶዴፓ ያላችሁ ወገኞች ኦስካር ግሮኒንግን ወይንስ ኦስካር ሽንድለርን መምሰል ትፈልጋላችሁ? በህወሓት ፋሽስታዊ አገዛዝ የጦርና የፓሊስ ሠራዊት ውስጥ ያላችሁ ወገኖቻችን ነገ የምትዋረዱበትን ሥራ መሥራት ነው የሚበጃችሁ ወይስ ዛሬ ከህሊናችሁ ጋር ታርቃችሁ እየኖራችሁ ነገ ደግሞ ልጆቻችሁና የልጅ ልጆቻችሁ የሚኮሩበትን ተግባር መፈፀም ትፈልጋላችሁ? በአገዛዙ የስለላ ድርጅቶች ውስጥ ያላችሁ ወገኖች ስማችሁን በመልካም ማስጠራት አትሹምን?

ልቦና ያላችሁ ወገኖቻችን ሆይ! መልካም ዜግነት ሎሌነት አይደለም። መልካም ዜግነት ለቅን ህሊና ታማኝ መሆን ነው። መልካም ዜግነት ሲመች በገሀድ፤ ሳይመች በምስጢር ኢፍትሃዊነትን መዋጋት ነው።

አርበኞች ግንቦት 7 የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ በማናቸውም መንገድ በአገዛዙ የፓለቲካ፣ የጦርና የፓሊስ ተቋማት፤ በስለላም ይሁን በሌላ የሲቪል ሙያ የተሰማራችሁ ወገኖቻችን የታዘዛችሁትን ሳይሆን ቅን ህሊናችሁ የሚጠይቃችሁን በመሥራት ኢፍትሃዊ፣ ፋሽስታዊና ዘረኛ የሆነውን የህወሓት አገዛዝን እንድታዳክሙ ጥሪ ያቀርብላችኋል። በአገዛዙ ውስጥ ሆናችሁ እያለም የምትሠሩት ለሀገርና ለትውልድ የሚጠቅም በርካታ ሥራ አለ። የአገዛዙን ምስጢራዊ ሰነዶች ለአርበኞች ግንቦት 7 እንዲደርስ ማድረግ፤ አሊያም በማኅበራዊ ሚዲያዎች (ለምሳሌ ፌስ ቡክና ቱተር) ማሰራጨት ትልቅ ዋጋ ያለ ሥራ ነው። የህወሓት ፀረ-አገር እና ፀረ-ሕዝብ ፕሮጀክቶችን ማሰናከል ሌላ ትልቅ ሥራ ነው። በነፃነት ታጋዮች ላይ የሚደረጉ ዱለታዎችን ማክሸፍ ሕይወት አድን ሥራ ነው። ድርጅቶቹ ውስጥ ሆኖ ድርጅቶቹን ማዳከም የመልካም ዜግነት ግዴታ መወጣት ነው።

በሥርዓቱ ውስጥ ሆነው ኢፍትሃዊነትን ለማጋለጥ እና ሥርዓቱን ለማዳከም ለሚጥሩ ወገኞች አርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ ክብር አለው፤ ደህንነታቸው እንዲጠበቅም የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል። ፀረ ኢትዮጵያ እና ፀረ ሰው የሆነውን የህወሓትን ሥርዓት ለመጣል እና በምትኩ ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲ፣ እኩልነትና የሀገር አንድነት የተረጋገጠባት ኢትዮጵያን ለማጽናት ከሥርዓቱ ውስጥም ውጭም የሚደረገውን ትግል እናፋፍም።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

የወለደችውን የ1 ወር ህጻን ልጅ ገደለች የተባለች ኢትዮጵያዊት በዱባይ ተያዘች

$
0
0

girum
ግሩም ተ/ሀይማኖት
የተባበሩት አረብ ኤምሬት.. ሻርጃ ውስጥ የወለደችውን የአንድ ወር ህጻን ገድላ በኮርኒስና ኮንክሪት ውስጥ የደበቀችው ኢትዮጵያዊት መያዟን ካሊጅ ታይምስ ዘገበ። ጨካኝ…ባላት ኢትዮጵያዊት ላይ Mother kills love child and stuffs body in box በሚል ርዕስ ካልጅ ታይምስ ዘግባውን አቅርቧል።
የኤማሬት ቤተሰቦች ጋር የምትሰራው ገዳይ..የገዳይ ፍቅረኛና ሌላ ሴትም በሻርጃ ፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት ትናንት ማክሰኞ ነው። (ሌሊት በመሆኑ የጻፍኩት ከትላንትና ወዲያ ማክሰኞ ብል ይቀላል)
ፖሊስ በስጠው መግለጫ ይፋ እንዳደረገው ከሆነ ዝም ብሎ ሳይሆን በቁጥጥር ስር ያዋላቸው በዲ ኤን ኤ ምርመራ ትክክለኛ እናት መሆኗን አረጋግጦ ነው።

የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የመጨረሻ መጽሃፍ –መጽሃፍ ቅዱሱን ተነጠቀ!!

$
0
0

eskinder2

(ዳዊት ከበደ ወየሳ እንደዘገበው)

ሃሳቡን በጽሁፍ ስላቀረበ “አሸባሪ” ተብሎ 18 አመት የተፈረደበት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፤ በእስር ቤት ውስጥ በከፍተኛ ጫና እየደረሰበት መሆኑ ተገለጸ። ምንም ነገር ማንበብም ሆነ መጻፍ ተከልክሏል። በአንድ ለሊት እስከሶስት ግዜ ክፍሉ እየመጡ፤ ከእንቅልፉ በመቀስቀስ ፍተሻ ያደርጉበታል። ይህ ሁሉ የሚደረገው ደግሞ ከህግ እና ህገ መንግስቱ ተጻራሪ በሆነ መንገድ ነው።

ለምሳሌ – በህገ መንግስቱ አንቀጽ 21 ላይ፤ “የህግ እስረኛ መብት ሊጠበቅ ይገባል።” ይላል። አንድ ታሳሪ ሰብአዊ ክብሩም መጠበቅ እንዳለበት ይዘረዝራል። ይህ ብቻ አይደለም። በዚሁ አንቀጽ ቁጥር 2 ላይ “ማንኛውም እስረኛ ከሚቀርበው ሰው ጋር መገናኘት ይችላል” ይልና መብቱን በዝርዝር ሲገለጽ- ከትዳር ጓደኛው፣ ከቅርብ ዘመዶች፣ ጓደኞች ከሃይማኖት አማካሪው፣ ከሃኪሙ እና ከህግ አማካሪው ጋር የመገናኘት መብት እንዳለው ብቻ ሳይሆን፤ ስለጾም እና ጸሎት ለመማከር ቢፈልግ የሃይማኖት አባት ማነጋገር እንደሚችል ተደንግጓል።

በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ ግን ራሳቸውን ከህገ መንግስቱ በላይ ያደረጉ የወህኒ ቤቱ አዛዦች ሰብአዊ መብቱን የሚጋፉ ድርጊቶች በተደጋጋሚ ሲፈጽሙበት ቆይተዋል። ይህም በጨለማ ቤት ውስጥ ከማሰር ጀምሮ ቤተሰብ እና ጓደኞቹ እንዳይጠይቁት እስከማድረግ ድረስ ይዘልቃል። በተለይም ከቅርብ ግዜ ወዲህ ገብረወልድ የተባለ ደህንነት በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ ተመድቦበት፤ በቁም እንዲሰቃይ እያደረገው ነው። በቀን እና በለሊት በማንኛውም ግዜ ጋዜጠኛ እስክንድር ወደታሰረበት ክፍል በመግባት ያዋክበዋል፤ የሚጠቀምበትንም ቁሳቁስ ይወስድበታል።

ለምሳሌ – እስረኞች እዚያው ከሚሰሩትና ገዝተው ከሚጠቀሙባቸው ቁሳቁሶች መካከል እዚያው ግቢ ውስጥ የሚሰራው መቀመጫ አንዱ ነው። ይህን መቀመጫ ከጋዜጠኛ እስክንድር ክፍል ውስጥ ወስደውበታል። እንዲህ ያለ ተራ ተግባር ነው እየተፈጸመ ያለው። ከእስር ቤት አካባቢ የደረሰን መረጃ እንደሚያስረዳው፤ መቀመጫ ወንበሩን ከጋዜጠኛው ላይ ከወሰዱበት በኋላ፤ በእስር ክፍሉ ውስጥ የሚገኘውን ባልዲ ገልብጦ፤ እንደወንበር ይጠቀምበታል። “ይህን ዘገባ ሲመለከቱ ደግሞ፤ ይህቺኑ ባልዲ ሊወስዱበት ይችላሉ” ብለውናል ዘገባውን ያደረሱልን ግለሰቦች።

ይህን እንደምሳሌ ገለጽን እንጂ፤ በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ ከዚህ በላይ የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲደርስበት ነበር፤ አሁንም እየደረሰበት ነው። በአሁኑ ወቅት ምንም አይነት መጽሃፍ ወይም ወረቀት እንዲኖረው አይፈቀድለትም። ባለፈው ሳምንት ክፍሉን የበረበረው ገብረወልድ ሲያስጠነቅቀው፤ “እስክሪብቶ እንኳን ይዘህ እንዳይህ አልፈልግም።” ሲል ነበር የዛተበት። ሌላው ቀርቶ እስክንድር ያነበው የነበረውን የመጨረሻ መጽሃፍ – መጽሃፍ ቅዱሱን ጭር ወስደውበታል። ይህን መጽሃፍ ቅዱስ በእስር ላይ በነበረበት ወቅት ባለቤቱ ሰርካለም ፋሲል የሰጠችው ነበር። ከምንም ነገር በላይ ግን ከአምላኩ ጋር የሚገናኝበት፤ በጸሎት ግዜ የማይለየውን መጽሃፍ ቅዱስ የወሰዱበት የጋዜጠኛውን ቅስም ጭምር ለመስበር ቢሆንም፤ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ግን አሁንም በመንፈሰ ጠንካራነት ከሚታወቁት እስረኞች መካከል አንዱ ነው።

ኢትዮጵያ በህገ መንግስቷ ላይ እንደተገለጸው ከሆነ የአለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶችን ትቀበላለች። ሆኖም በጋዜጠኛ እስክንድር ላይ የሚደርሰው ግፍ ግን የሰው ልጅ ሊሸከመው የሚከብድ ነው። ትላንት ለሌሎች ኢትዮጵያውያን መብት መከበር ይቆረቆር እና ይጽፍ የነበረው ጋዜጠኛ ህክምና ጭምር ተከልክሎ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። ይቅርታ ጠይቆ እንዲወጣ ተጠይቆ ፈቃደኛ ባለመሆኑጥርስ ተነክሶበታል። እንደኢትዮጵያ አለም አቀፉን የሰብአዊ መብት አያያዝ የፈረሙ አገሮች የእስረኞችን ሰብአዊ ክብር ይጠብቃሉ። እስረኞች እንደየሃይማኖታቸው መጽሃፍ ቅዱስም ሆነ ቅዱስ ቁርአን እንዳያነቡም ሆነ እንዳይኖራቸው አይከለከሉም፤ በኢትዮጵያ ግን እየሆነ ያለው ከዚህ በተቃራኒ ነው። (በዚህ አጋጣሚ የቤተ ክርስቲያን ሰዎች – የጋዜጠኛው መጽሃፍ ቅዱስ እንዲመለስለት ጠቅላይ ሚንስትሩን እንዲጠይቁ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን)

በአሁኑ ወቅት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በታሰረበት ክፍል ውስጥ፤ እሱን ጨምሮ አምስት እስረኞች አሉ። ከነሱም ውስጥ “መንግስትን በሃይል ወይም በመፈንቅለ መንግስት ለመገልበጥ ሙከራ አድርጋችኋል” ተብለው ሞት የተፈረደባቸው ጌታቸው ብርሌ እና መላኩ ተፈራ፤ ከመኢዴፓ ክንፈሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ) እና በከፍተኛ ሙስና የታሰረው የጉምሩኩ ገብረዋህድ አብረው ነው የታሰሩት።

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከታሰረ በኋላ፤ ሃብት እና ንብረቱን – ገንዘብ እና ቤቱን ሳይቀር መንግስት አግዶበታል። የወላጆቹን ንብረት እንዳይሰበብ ሆኗል። በሚሊዮን ይቆጠር የነበረውን እና እናቱ በባንክ አካውንታቸው ያስቀመጡት ገንዘብ ከፍርድ ቤት እግድ ውጪ እንዳይንቀሳቀስ ተደርጓል። እናቱ በህይወት በነበሩበት ወቅት፤ ክሊንካቸውን እንዲዘጉ ከተደረጉ በኋላ ንብረታቸውን አዘርፍታል። አራት ኪሎ የሚገኘው ቤታቸው ተወስዶባቸው ሆቴል ውስጥ ነበር የሚኖሩት። በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ፤ የእስር ብቻ ሳይሆን የግል መኖሪያ ቤቱ እና ንብረቱ ጭምር እግድ ወጥቶበታል። ይሄ ሁሉ ሆኖ ግን ከሁለት አመት በፊት፤ የመጨረሻ ውሳኔ ሲሰጠው፤ “እኛ ሁላችን እናልፋለን። ልጄ ናፍቆት እክንድር አድጎ፤ አንድ ቀን ንብረታችንን ያስመልሰዋል።” የሚል ምላሽ ለፍርድ ቤቱ መስጠቱ ይታወሳል።

ከዚህ በታች ያወጣነው ለፍርድ ቤቱ የተጠየቀው የእግድ ደብዳቤ ነው። በደብዳቤው ላይ እንደተገለጸው፤ 1ኛ ንፋስ ስልክ ላፍቶ የሚገኘው G+2 መኖሪያ ቤት፤ ከእናቱ በውርስ ያገኘው የካ ወረዳ የሚገኘው ትልቅ ቪላ ቤት እንዲሁም ልጁን ናፍቆት እስክንድርን ትምህርት ቤት ያመላልሱበት የነበረው አቶዝ መኪና በባለቤቱ በወ/ሮ ሰርካለም ተመዝግቦ እንደሚገኝ ደብዳቤው ገልጾ፤ በመንግስት እንዲወረስ ጥያቄ ቀርቧል።

በደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ በወረዳው አመራር ላይ በተወረወረው ቦምብ 2 ልጆች ሞቱ * አመራሩና ባለቤታቸው ቆስለዋል

$
0
0

news
የደህሚት ድምጽ እንዘገበው በደቡብ ወሎ ዞን፤ ቦረና ወረዳ ውስጥ ሓምሌ 4/2007 ዓ/ም ወደ ወረዳው አመራሩ በተወረወረው ቦምብ ምክንያት 2 ልጆች መገደላቸው ተገለፀ።

በአማራ ክልል፤ ደቡብ ወሎ ዞን፤ ቦረና ወረዳ ውስጥ ሓምሌ 4/2007 ዓ/ም ከሌሊቱ 5 ሰዓት ላይ በወረዳው አመራር በአቶ መሓመድ ረሽድ ላይ በተወረወረው ቦምብ 2 ልጆች መሞታቸውና ራሱና ባለቤቱም ጭምር ክፉኛ በመቁሰላቸው ምክንያት ደሴ ሆስፒታል እያተካሙ መሆናቸውና እስካሁን ድረስም ድርጊቱ የፈፀመው አካል እንዳልተያዘ ለማወቅ ተችሏል።

በአሁኑ ግዜ በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች የስርዓቱ ባለስልጣናት በህዝቡ ላይ በሚያደርሱት ከፍተኛ ችግር ምክንያት ህዝቡ በአስተዳድሪዎቹ ላይ የበቀል እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ይታወቃል።

አለምነህ ዋሴ ለምን ከራድዮ ፋና ከዜና መጽሔት መሪነት እንደተነሳ ይናገራል (የሚደመጥ)

$
0
0

አለምነህ ዋሴ ለምን ከራድዮ ፋና ከዜና መጽሔት መሪነት እንደተነሳ ይናገራል (የሚደመጥ)

Alemeneh

Health: የድድ ህመምና መፍትሔዎቹ

$
0
0

Dede Tirs

ማለዳ ወደ ሥራ ለመምጣት በገባሁበት ታክሲ ውስጥ ነው ከፊቴ የተቀመጡት ሁለት ጓደኛሞች የሚነጋገሩት ነገር ጆሮዬ ውስጥ የገባው። «ጥርሶቼ ደህና ሆነው ድዴን ያመኛል ስፍቀው በጣም ይደማል ምን ይሻለኛል?» ትላለች የመጀመሪያዋ «በሎሚ እሺው ይተውሻል ጥርስሽ ደህና ከሆነ ችግር የለውም» የሚል መልስ ሰጠቻት አብራት ያለች የዕደሜ አቻዋ። የእነርሱን ወሬ ተወት አድርጌ ወደ ራሴ ሃሳብ ገባሁ። «እውነት የድድ ህመም በቀላል የምናየው ነው ወይስ ከባድ በሽታ?» ስል አሰብኩ። የዚህን ጥያቄ መልስ ለማግኘት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥርስ ህክምና ማዕከል ውስጥ የማስተማርና የህክምና አገልግሎት የሚሰጡትን ዶክተር ባንቺአምላክ ደምሴ ለማግኘት ቀጠሮ ያዝኩ።

ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር ባንቺአምላክ የፊትና የአገጭ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስትና መምህርት ናቸው። ስለተነሳሁበት ጉዳይ ሙያዊ ማብራሪያ ሰጥተውኛልና ላካፍላችሁ ወደድኩ። ለቃለምልሱ ፈቃደኛ ስለሆኑና እውቀታቸውን ስላካፈሉን  ምስጋናዬ በቅድሚያ ይድረሳቸው።

– የድድ ህመም ምንድንነውመንስኤውስ?

ዶክተር ባንቺአምላክ፦ የድድ ህመም ሲባል የአንድ በሽታ ስም ቢመስልም የተለያየ ዓይነት የድድ ህመሞች አሉ። አንደኛው በኢንፌክሽን ምክንያት የሚመጣ ማለትም በምንበላው ምግብ የተነሳ የመቆጣት ህመም ሲሆን፤ ሌላው ደግሞ በእባጭ መልክ የሚመጣ ከጥርስ ጋር በተያያዘ ከዕጢ ወይም ከካንሰር ጋር በተያያዘ የሚመጣ የድድ ህመም ነው። ሌላው ከሰውነታችን የጤንነት ጉድለት ማለትም በቪታሚን ሲ እጥረት ምክንያት በስኳር በሽታና ሌሎች የጤና ችግሮች ሳቢያ ሊመጣ የሚችል ነው። በዋናነት በእድገት አለመስተካከል ማለትም ጥርስ እድገቱን ሳይጨርስ ውስጥ ሲቀር የሚከሰተውና በጥርስ ንፅህና ጉድለት የሚመጡት ናቸው። በተለይ ደግሞ በጥርስ ንፅሀና ጉድለት የሚከሰተው ህመም በአብዛኛው የሀገራችን ታማሚዎች ችግር ነው።

አዲስ ዘመን፦ ህመሙ የሚያመጣው ጉዳት እንዴት ይገለጻል?

ዶክተር ባንቺአምላክ፦ በጥርስ ንፅህና ጉድለት የሚመጣው በሽታ የድድ መሸሽ እና ድድ አቅም አጥቶ ጥርስ በራሱ ጊዜ እንዲወልቅ ያደርጋል፡፡ ሌላው ደግሞ እንደየ ህመሙ ዓይነት የተለያዩ ጉዳቶችን በማድረስ የነርቭ ችግር እስከማምጣት ብሎም እስከሞት የሚያደርሱ የድድ ህመሞች መገለጫዎች ናቸው።

 ይሄን ችግር ለመከላከል ምን መደረግ አለበት?

ዶክተር ባንቺአምላክ፦ የሀገራችን ዋንኛ ችግር የሆነውን በፅዳት ጉድለት የሚመጣ የጥርስ ህመም በአግባቡ በማፅዳት ብቻ መከላከል ይቻላል። ይህም ሲባል በመጀመሪያ ደረጃ በመጉመጥመጥ፣ በመፋቂያ በመፋቅ ማስወገድ ይቻላል፡፡ አንዳንዴም እየተመገብናቸው ቆጠሻሻን የሚያስወግዱ የምግብ ዓይነቶች ማለትም እንደ ሸንኮራ፣ ኮክ፣ ካሮት የመሳሰሉትን በማኘክ ማፅዳት ይቻላል። ሌላው በጥርስ ሳሙና መቦረሽ ፅዳትን ይፈጥራል። 

ሌሎቹን ዓይነት ህመሞችንስ በምን መከላከል እንችላለን?

ዶክተር ባንቺ አምላክ፦ ሌሎቹን ማለትም በተለያዩ ህመሞች ምክንያት የሚመጡትን መከላከል በጣም ከባድ ነው። ለምሳሌ ኤችአይ.ቪ ህመም ያለባቸው ሰዎች ድዳቸው የማበጥ ችግር ያመጣል፡፡ ለተለያዩ ዓይነት በሽታዎች የሚወሰዷቸው መድኃኒቶችም ድድን ሊያሳብጡ ይችላሉ። በእርግዝና ወቅት የሚመጡ የድድ ህመሞች አሉ። እነዚህን በህክምና ለማስወገድ መሞከርና በራሳቸው ጊዜ ሊተዉ የሚችሉ ከመሆናቸው በቀር ይህ ቢደረግ ይተዋል የሚባል ነገር አይኖርም።

 ድድ ራሱ አብጦ ራሱ ይጎድላል ይሄስ ህመም ነው ወይስ ሌላ የጤና ችግር?

ዶክተር ባንቺአምላክ፦ ይህ ችግር የሚመጣው «ሸሄላ» ማለትም ምግብ በጥርስ ውስጡ ተጠራቅሞ በሚጠነክርበት ጊዜ በድድ ውስጥ ስር ሰዶ ድዱ እንዲቆጣና እንዲደማ ሲያደርገው ነው፡፡ ይሄ ጥርስ እየተፀዳም ቢሆን በአጸዳድ ጉድለት ሊመጣ ይችላል፡፡ በነገራችን ላይ በጥርስ ህክምና ታሪክ እንደ ድድ ህመም ከባድና አስቸጋሪ ሁኔታ የለም። ድድን ማዳን ከባድ ነው። ጥርሱን አቃፊ አልባ ሊያደርግ የሚችል ጉዳት ያደርሳል።

 ድድ የማበጥ ችግር እንዳ ይከሰትበ ት ምን መደረግ አለበት?

ዶክተር ባንቺ አምላክ፦ ችግሩ እንዳይመጣ መንስኤውን ማቆም ዋናው መፍትሔ ነው። በበሽታ ምክንያት የሚመጣውንም የድድ ህመም በመታከም በትክክለኛ አፋፋቅ በማፅዳት የጥርስ ህመምን ማስወገድ ይኖርብናል። ንፁህ ጥርስ እንዲኖረንም ቢያነስ በቀን ሁለቴ ማለትም ጠዋት ቁርስ ከተበላ በኋላና ማታ ወደ መኝታ ከመኬዱ በፊት ጥርስ መፋቅ አለበት። ውሃ መጉመጥመጥም ለጥርስ ንፅህና ይረዳል።

ጥርስ ሲፋቅ ቢያንስ ለደቂቃ ያህል በትዕግስት መፋቅ አለበት። ይህም ከቀኝ የላይኛው የጥርስ ክፍል እየተፋቀ ወደ ግራ ከግራ ደግሞ ወደታችኛው የጥርስ ክፍል ከዚያ ደግሞ ወደቀኝ በማድረግ ውስጡንና ምላስንም በጥንቃቄና በተገቢው መንገድ ማፅዳት ያስፈልጋል።

የድድ ህክምናስ እንዴት ይካሄዳል?

ዶክተር ባንቺ፦ ህክምናው በንፅህና ጉድለት የሚመጣውን በንፅህና ከመከላከል ባሻገር ህክምናው የተጋገረ ቆሻሻ ካለ በእጥበት ማስወገድ፣ የተጎዳ ጥርስ ካለ በሙሌት ማከም ወይንም መንቀል፣ ድድ በተለያዩ መድኃኒቶች እንዲድን ማድረግና እስከ ቀዶ ህክምና የሚደርሱ የህክምና ዓይነቶች አሉት።

 የጥርስ ሳሙና መጠቀም አፍ ያሸታል የሚባለውስ ነገር ምን ያህል እውነት ነው?

ዶክተር ባንቺአምላክ፦ አዎ ብዙ ሰው አፍ ያሸታል ሲል ይደመጣል። የጥርስ ብሩሽ በመጠቀም አፍ ያሸታል የሚባለው ነገር ግን ከእውነት የራቀ ነው። እንዲያውም በተቃራኒው ለአፍ ጥሩ ጠረን በመስጠት ጥሩ ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል። ማንኛውም የጥርስ ሳሙና የማፅዳት፣ የአፍ ጠረንን የማሳመር አቅም አለው፣ ተዋስያንን የመግደል ብቃትም አለው፣ ፍሎራይድ የያዘ ስለሚሆን መጠቀሙ ምንም ጉዳት አይኖረውም። 

በአጋጣሚ አለርጂክ ኖሯቸው የድድ መቆጣትና ሌላ ችግር እንዳይገጥማቸው የሚመቻቸውን መምረጥ የተጠቃሚዎች ፈንታ ነው። አፍ ያሸታል የሚባለው ነገር የሚመጣው እኔ ሲመስለኝ ንፅህናውን ተለማምደው ሲተውት የሚከተለው የቆሻሻውን የመለየት ሂደት ሊሆን ይችላል።

የምንጠቀመውሰ የጥርስ ብሩሽ ለምን ያህል ጊዜ ያገለግላል?

ዶክተር ባንቺ አምላክ፦ በአብዛኛው የጥርስ ብሩሽ አጠቃቀም ላይ ችግሮች ይስተዋላሉ። የምንጠቀመው የጥርስ ብሩሽ የእጅ መያዣው ወደታች ብሩሹን ወደላይ በማድረግ አየር እንዲያገኝ ማድረግ ይቻላል። በየሦስት ወሩ በመቀየር ጤናው በተጠበቀ ብሩሽ ጥርስን ማፅዳት ተገቢ ነው።

የጥርስ ሳሙና በራሱ የጣፋጭነት ጣዕም ስላለው ጣፋጭነቱ ጥርስን አይጎዳም ወይ?

ዶክተር ባንቺ አምላክ፦ የጥርስ ሳሙናዎች ሲዘጋጁ ጣዕም ለማሳመር የሚደረጉ ፍሌቨሮች ካልሆኑ በስተቀር ጥርስን የሚጎዳ ምንም ነገር አይኖረውም፡፡ ይህማ ከሆነ የተነሱለትን ዓላማ ዘነጉ ማለት ነው። የጥርስ ሳሙናዎች ጥርስ የማጠንከር የአፍ ጠረንን የማሳመርና የማፅዳት አቅም ነው ያሏቸው።

በአጠቃላይ በድድ ላይ ያሉትን ህመሞች ከማከም በላይ ለሁሉም ቢያንስ በቀን ሁለቴ ማፅዳት፣ ጥርስ ስለታመመ ብቻ ሳይሆን በየጊዜው እየሄዱ የጥርሱ ህመም ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ማሳየት፣ ከመታመሙና ችግር ከመፈጠሩ በፊት መከላከል ያስችላል። 

ጸሐፊ አስመረት ብስራት


የወያኔ ገመና ሸፋኝ…የኢትዮጵያ ደመኛ ጨቋኝ…መለስ ዜናዊ ሁለት ባህሪያት።

$
0
0

Melesኦባማ ኬኒያ በመግባት ከኬኒያው ፕሬዝዳንት ጋር ባደረጉት የሁለትዮሽ ግንኙነት የኬኒያ ፕሬዝዳንት ያሳዩት በራስ መተማመን ብቃት ኬኒያዊያኑን አልፎ እኛንም ጎረቤት አገራት አኩርቶናል። ይህንን ኩራትና ደስታ ባየንበት በቀናት ልዩነት ባራክ ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ  ሲመጣ ከኩራት ይልቅ ውርደት ከክብር ይልቅ ሃፍረት ለብሰናል። የዚህ ግዜ ነው ምነው መልስ ዜናዊ በሆነ ያልኩት። መልስ ዜናዊ በውጪ አቋሙ ጥሩ ከሚባሉት ተርታ ነው። ባራክ ኦባማን መልስ ቢቀበለው ኖሮ የተሻለ አቀባበል ሊያደርግላቸው እንደሚችል እሙን ነው። የኢትዮጵያ ህዝብም መለስ ዜናዊን በውጪ አቋሙ ሳይሆን በውስጥ አቋሙ ነው ያልተቀበለው። መልስ ኢህአዴግ የሚባል መረብ ሲዘረጋ በውስጣዊ ተንኮል የተተበተበ፣ በክፋት የተሳሰረ፣ መሙስና የረካከሰ፣ በድድብና የበለጻጸገ አድርጎ  ነው። ኢህአዴግ የሚባል ድርጅት በህይወት እስካለ  ድረስ መለስ ቢመራቸው ቢያንስ ማንነታቸው  እንደዚህ በተዝረከረከ መልኩ አደባባይ ወጥቶ  ፀሃይ አይሞቅም ነበረ። መለስ ለኢህአዴግ ገመናቸው፣ ክብራቸው፣ ንጉሳቸው ነበረ። ለዚህም ነው ከፍ አድርገው የሰቀሉት። የመለስ አለመኖር እንኳን በአገር ማስተዳደር ሂደት ውስጥ ይቅርና እንግዳ በመቀበል የፈጠረውን ክፍተት ቁልጭ ብሎ የአለም ህዝብ ያየው አሳፋሪ ክንውን ነው። ኢህአዴግ ውስጥ እንደዚህ አይነት ክፍተት ሊመጣ የቻለው ከምን የተነሳ ነው? በጥቂቱ እንይ

መልስ ዜናዊ ሁለት አይነት ባህሪ አለው። ውጪአዊ እና ውስጣዊ። ውጪአዊ እና ውስጣዊ ሁለት አይነት ናቸው። የመጀመሪያው ለውጪ መንግስታት ወይም ህዝብ እና ለኢትዮጵያ ህዝብ ያለው አመለካከት። ሁለተኛው ደግሞ በአፋዊ ወይም ለእይታ የሚናገረው እና በውስጥ የሚያስበው ወይም የሚሰራው ክንውኖች ናቸው።

ለውጪ መንግስት ወይም ህዝብ የሚያሳየው ክብር ለየት ያለ ነው። ንግግሩም በጣም የተለሳለሰ ነው። በውጪው ማንነቱ አይተውት ጥሩ ግምት የሚሰጡት አሉ። ለዚህ ማሳያ የሚሆነው ኢትዮጵያ ኬኒያ  እና ሱዳን ሊገነቡት ላሰቡት ትልቁን የነዳጅ ማጣሪያ መሰረት ለመጣል በሄደበት ግዜ የሱዳንን እና የኬኒያ ህዝቦችን እጁን እያውለበለበ በቅርብ ሰላምታ ይሰጣቸው ነበረ ይሄንን ሰላምታ ግን ኢትዮጵያ  ውስጥ አንድም ቀን አድርጎት አያውቅም። በምረቃው ወቅት የውጪ ማንነቱ የውጪ ዜጎችን ያስደሰተ  ቢሆንም ውስጣዊ ማንነቱ ግን ኢትዮጵያዊያንን ያናደደ ነበረ። አገርን እመራለው የሚል መሪ የአገሩን ባንድራ ገልብጦ ይዞ ከአቻው አጎራባች አገር መሪዎች እኩል ተሰልፎ መታየቱ ህዝባችንን ያሳዘነ ጉዳይ ነው። ይህ ጉዳይ ያጋጣሚ ጉዳይ አይደለም ምክንያቱም አንድ የአገር መሪ በዙሪያው ብዙ አይኖች ስላሉት መለስ ሳያየው ነው ቢባል በዙሪያው ያሉት አላዩም ማለት ግን አይቻልም ይህ የሚያሳየው ለውጪ አገር ያለው ክብር እና ቅርበት ምን ያህል እንደሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ ያለውን ጥላቻ እና ንቀት ምን እንደሚመስል ያንጸባረቀበት ነው። በተለይ እንደ መለስ አይነት ጠንቃቃ ሰው ያለ ምክንያት የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማውን ዘቅዝቆ ያዘው ለማለት አይቻልም።

ሰላም መጣ፣ ዲሞክራሲ መጣ፣ ነጻነት መጣ፣ እኩልነት መጣ፣ የሚለው ቃል የውስጥ ተንኮሎች ሊሰሩበት ሽፋን የሆነ ተግባር ላይ ያልዋለ የማስመሰያ ቃላቶች እንደሆነ የሚታወቅ ነው። ክልሎች በራሳቸው ሰው ይመሩ በሚልም ሽፋን ወደ ስልጣን የሚመጣው ባለስልጣን እንዲሁም ሌሎች በሚንስትር ደረጃ የተሰየሙት ሁሉ ሁለት ነገሮችን የሰሩ ናቸው ወይም ከሁለት አንዱ ያደረጉ ናቸው። እነርሱም ሙስና  እና የእውቀት ማነስ። ከኢህአዲግ ባለስልጣን ጥቂት የተማሩ ቢኖሩም እንኳን ሙስና ውስጥ ያልገባ  ግን ማግኘት አይቻልም። የግል ማህደራቸው የሚያሳየውም ይሄንኑ ነው። ወደዚህ የዘቀጠ ተግባር ወይም የጥፋት ስራ ባለስልጣኑ በሙሉ ወደው ነው የገቡት ወይስ ተገደው የሚለውን ለማየት ሌላ ጥናትና ትንታኔ ይፈልጋል ለአሁኑ ወደዚህ ጉዳይ ውስጥ አልገባም ነገር ግን ሁሉም ባለስልጣን የዚህ በሽታ ተጠቂ ያደረጋቸው መለስ ዜናዊ እንደሆነ ግን ይታወቃል።

የውስጥ ማንነት የሚባለውም ይሄ ነው። እንደዚህ አይነቱ መረብ በጣም ከባድ እና አጣብቂኝ ነው። ወደዚህ መረብ ውስጥ የገባ ሰው በሙሉ ወደደም ጠለም አድርግ የተባለውን ያደርጋል አታድርግ የተባለውን አያደርግም ምክንያቱም ሌላ አማራጭ ስለሌለው። ሙስና የሰራ በአገሪቱ ህግ መሰረት ከፍተኛ ቅጣት ያስቀጣል። ከአገርም ውጪ በአለም ህግ መሰረት ሙስና የሰራ እና የሰው ነፍስ ያጠፋ ወደ ሁለተኛ አገር ሄዶ መደበቅ አይችልም። የሄደበት አገር አሳልፎ ይሰጠዋል። ቢሰወር እንኳን በኢንተርፖል ታድኖ ይያዝና ይመለሳል። ባለስልጣኖች በሙሉ በተለያየ እና በድብቅ ወይም ባልተረዱት  መንገድ ወይም ልማት በሚል ሽፋን ወደሙስና እንዲገቡ ወይም ሙስናውን እንዲፈጽሙ ከተደረጉ በኋላ ድብቅ እቅዱን በግልጽ ይነገራቸዋል። ከዚህ በኋላ እንደ ባሪያ ማገልገል እንጂ የፈለጉትን ማድረግ  የማይችሉ ተደርገው ይቀረጻሉ። መለስ ከሚላቸው ውጪ ማሰብም ወይም መናገርም የማይችሉት ለዚህ ነው። መለስ በፓርላማው ውስጥ ከሳቀ የማያስቅ ቢሆን እንኳን ሁሉም ይስቃሉ ምንድነው የሚያስቃችሁ ተብለው ቢጠየቁ መለስ ስቋል እኮ ብለው የሚመልሱም አይነት የመስለኛል። ለዚህ ነው አሁን ያሉት ባለስልጣናት በሙሉ ጉዳይ አስፈጻሚ እንጂ ውሳኔ ሰጪ ያልሆኑት። በእንደዚህ ብቃት በሌላቸው እና ወሳኝ ባልሆኑ ሰዎች አገር መመራት አደገኛ ነው። ምክንያቱም የሰሩትን ስራ ከህዝብ የሚያሸሽ ወንጀል ስለሆነ ሽሽታቸውን በብቃት መወጣት ስለማይችሉ ህዝብን በመጉዳት፣ አገርን በማፍረስ፣ ስራ ውስጥ ይገባሉ። የዚህ ሁላ መሰረት ጥቂት ሰዎች እንደሆኑ ይታወቃሉ። ጥቂቱን በማጋለጥ አገርን ከሙስና የጸዳ እና ብቃት ያላቸው ዜጎች ወደ ስልጣን ማምጣቱ የሁላችንም ትግል ወሳኝ ነው። ያኔ እውነተኛ፣ አገርን ወዳድ፣ ህዝብን አክባሪ እና አስከባሪ ባለስልጣኖች ይኖሩናል።

የኦባም አቀባበል ግዜ የታየውን የተዝረከረከ የውስጥ ማንነታቸው ሚንስትሮችም ሆኑ የወያኔ ካድሬዎች ወይም ደጋፊዎች መለስ ቢኖር ኖሮ  ብለው የተቆጩበት ብሎም በጥልቅ ያሰቡበት ሰዓት ነበረ። ምክንያቱም ገመናቸው በሙሉ የተሸፈነው በአንድ ሰው ነበረና። ወያኔ ውስጥ ትልቅ ችግር የፈጠረው የድርጅቱ ድብቅ አላማ እና የድርጅቱ የአቀራረጽ ሁኔታ ነው። ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘበት ሰዓት ጀምሮ  አብሮ ታግለው የመጡትን አሉ የተባሉ ታጋዮችን ኃየሎም አርኣያን ጨምሮ ሰላሳ ስድስት ሺ (36.000)ንጽኋን ታጋዮችን በተቀረጸው ህግ ያልተስማሙ ስለነበሩ በቀጭን ትእዛዝ እንዲገደሉ ተደርጓል። በአሁኑ ሰአት ያሉት ባለስልጣን በሙሉ ሊወጡ በማይችሉበት መረብ ተተብትበው ተቀርጸው የተቀመጡ እና የእውቀት ብስለትም ሆነ በራስ መተማመን የጎደላቸው ናቸው። አሁን ላለው የእርስ በእርስ ያለመተማመን በወስጣቸው መንገስ፣ እርስ በራሳቸው መጠላለፍ፣ በውስጣቸው መደማመጥ መጥፋቱ፣ መሪና ተመሪ ማን እንደሆነ አለማወቃቸው፣ እርስ በራሳቸው አለመተማመን  በማህከላቸው መንገስ፣ በማይቀረፍ መልኩ በወያኔ ውስጥ ሊኖር የቻለው ድርጅቱ ሲቀረጽ ሰዎችን ጥያቄ እንዳያነሱ እና ተሸማቀው እንዲኖሩ የሚያደርግ አሳሪ ህግ ተሰርቶለት ስለሆነ ነው። ወደ ስልጣን ወንበር ሲመጡ ታስረው እንደመግባት ማለት ነው። አሳሪውም ደግሞ አንድ ሰው ነው። መለስ ዜናዊ ያሰረውን የጥልፍልፎሽ የሞት ቋጠሮ መፍታት የሚችሉበት አቅሙ ስለሌላቸው እርስ በራሳቸው የጎንዮሽ እየተያዩ  ከሞትንም አብረን እንሙት ከኖርንም አብረን እንኑር በሚል ህሳቤ ያለብቃታቸው አገር እያተራመሱ እነሱም እየተተራመሱ ይገኛሉ። በአሁኑ ሰዓት የኢህአዴግን ባለስልጣን እያስጨነቀ እና እያተራመሰ  ያለው ሁኔታ ስርዓቱ አብቅቶለት ስለመውደቁ አይደለም የውድቀታቸው ቀን እንደሚመጣ ጠንቅቀው ያውቁታል። ኢህአዴግ የተያያዘው መፍጨርጨር የሰሩት ከፍተኛ ወንጀሎች በዝርዝር ስለሚቀርብባቸው ይህ እንዳይገለጽባቸው ስልጣን ላይ መቆየታቸው ብቸኛው አማራጫቸው ስለሆነ ነው። ከዚህ የተነሳ  እርስ ባራሳቸው እየተተራመሱ አገርን እያተራመሱ ያለ ሙያቸው እና ያለ አቅማቸው ትላልቅ ቦታዎችን ይዘው የህልውናቸው ጉዳይ በመሆኑ የመጨረሻ አቅማቸውን እየተጠቀሙ ያሉት። የኢትዮጵያ ህዝብ በተለያየ  አቅጣጫ ስርዓቱን የሚከዱ በዝተዋል። ከመለስ ሞት በፊት ስርዓቱን የሚከዱ አንድ ወይም ሁለት ሰው ነበረ። ከመለስ ሞታ  በኃላ በብዛት ሆነው ስርዓቱን መክዳት ተጀመረ  ሌላው ቀርቶ ተዋጊ ሄሊኮፕተር ጭምር ይዘው እስከመሰወር ተደርሷል። ከጥቂት ግዜ በኋላ ደግሞ ሙሉ ወለጋ ስርዓቱን ከዱ፣ ሙሉ ጎጃም ስርዓቱን ከዱ፣ ሙሉ ጎንደር ስርዓቱን ከዱ፣ ሙሉ ጅማ ስርዓቱን ከዱ፣ ሙሉ ሸዋ፣ሐረር፣ሐዋሳ …. ለወያኔ  አልገዛም በማለት ወያኔዎችን ከሞተው ስርዓታቸው ጋር ከውስጣቸው በማስወጣት እራሳቸውን ነጻ አድርገዋል የሚለው ግዜ  ይመጣል። ይሄ እንደሚመጣ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ከፍተኛ ጭንቅ ላይ ናቸው። በዚህ ሰዓትና ግዜ  ከወያኔ የሚተላለፈውን ሃሳብ ማንም መስማት አይገባውም። ከህዝቡ ነጥቃችሁት የበላችሁትን፡ ከናተ ተነጥቆ ለህዝቡ የሚደርስበት ስራ እየተሰራ ነው። ህዝቡን አደህይታቹ እራሳችሁን በሃብት ወንበር ላይ የተቀመጣችሁ የወያኔ ተላላኪዎች ህዝቡን ወደተሻለ ሃብት እና ወደ ሚፈልገው ሰላም ለመመለስ በኢትዮጵያ ልጆች እየተሰራ  ነው። ግዜው ሳይረፍድ ተፀፅቶ የተመለሰ ማንም ባለስልጣን ቢሆን ንስሃውን የማይቀበል ማንም ኢትዮጵያዊ የለም። ህዝባችን ይቅርታ አድራጊ ነውና ። ከነበደል መሞት ግን ሁለተኛ ሞት ነው።

ከተማ ዋቅጅራ

08.09.2015

Email- waqjirak@yahoo.com

 

ፍርድ ቤቱ ለሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የሰጠው ዋስትና በፖሊስ ታገደ

$
0
0

ነገረ ኢትዮጵያ

11855873_752610074864653_9011892683978376437_nከምርጫው ማግስት ከአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በፖሊስ ተይዘው ነሃሴ 6/2007 ዓ.ም እያንዳንዳቸው በ15 ሺህ ብር ዋስ እንዲወጡ ተጠይቀው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ዋስትናቸው በአቃቤ ህግና በፖሊስ መታገዱን የፓርቲው የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተባባሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ፖሊስ በአመራሮቹ ላይ ላቀረበው ክስ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ነሃሴ 6/2007 ዓ.ም ከምርጫው ማግስት እየታደኑ የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ጨምሮ 8 የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን እያንዳንዳቸው የ15 ሺህ ብር ዋስ አቅርበው እንዲፈቱ የወሰነ ሲሆን ሁለቱ ወዲያውኑ ወጥተዋል፡፡ ይሁንና የዋስትናው ገንዘብ እስኪሞላላቸው እስር ቤት የቆዩት 6ቱ አመራሮች ትናንት ነሃሴ 7/2007 ዓ.ም የክልሉ አቃቤ ህግና ፖሊስ ለማረሚያ ቤቱ ባቀረቡት ጥያቄ ዋስትናቸው መታገዱ ታውቋል፡፡ አመራሮቹና አባላቱ ዋስትናቸው የታገደው ገንዘቡን ካስያዙ በኋላ መሆኑም ታውቋል፡፡ እንዲከፍሉ የተጠየቁትን ገንዘብ ካስያዙ በኋላ ዋስትና የተከለከሉት አመራሮች፡-

1. ልዑልሰገድ እምባቆም
2. ፋንታሁን ብዙአየሁ
3. መንግስቴ ታዴ
4. አዳነ አለሙ
5. ስማቸው ምንይችል
6. አበባው አያሌው ናቸው

አንዳርጋቸውና ጓዶቹ –ከአንተነህ መርዕድ

$
0
0

andargachew Tisgeአምና ሰኔ 2006 ዓ ም አንዳርጋቸው ጽጌ በትራንዚት ላይ እያለ ከየመን በወያኔ መታፈኑ ሲነገር ሃዘንና ንዴት ያልተሰማው አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም። ወያኔ ኤርትራ ውስጥ እንዳለ ሊገድለው ያደረገውን ሙከራ ኢሳት በተከታታይ ስላቀረበው ምን ያህል አዳጋ ውስጥ እንዳለ ለሁሉም ግልፅ ነበር። የአንዳርጋቸው መያዝ ከታለመው ግብ  በተፃራሪ አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ከዳር ዳር በቁጣ በማንቀሳቀሱ አፋኞቹ አምባገነኖች ከጠበቁት ውጭ ራሳቸውን ችግር ውስጥ ነው ያገኙት። መታፈኑ ለአስርት ዓመታት አፍዝዞ የያዘን ፍርሃትንና ክፍፍልን ሰባብሮ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በጋራ እንዲቆም ከማድረጉም በላይ አንዳርጋቸው የደላ ኑሮውን ትቶ በረሃ ለበረሃ የተንከራተተለት፣ በርሃብና በበሽታ የተንገላታለት፣ ከጓዶቹ ጋር ለኢትዮጵያውያን ነፃነት ይበጃል ብሎ የደከመለት ግንቦት ሰባት በብዙ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ እንዲገባና የማይነጥፍ ድጋፍ ባልተጠበቀ ፍጥነት እንዲያገኝ ሲያደርግ የወያኔንና የመሰሎችን ጎራ ናዳ ልኮባቸዋል። በተለይም በክፍፍልና በፍርሃት ተሸብቦ የነበረው ውጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ከወትሮው በተለዬ ዘላቂ ለሆነ ትግል ራሱን ማዘጋጀቱን በተለያዩ እንቅስቃሴዎቹ እያሳየ ሲሆን አገር ውስጥ በሰላማዊ ትግል ይሳተፉ የነበሩ በርካታ ወጣቶች ቁጭ ብሎ ከመታሰር በርሃ እያቆራረጡ ወደትግሉ መቀላቀላቸውና ሌላውም ህዝብ መነሳሳትን ማሳየቱን ወያኔዎችም ሊደብቁት አልተቻላቸውም።

አንዳርጋቸው የህይወት ተልዕኮውን በሚገባ ተወጥቷል። የግንቦት ሰባትን መሰረት ጥሏል። ከሌሎች ጋር ተባብሮ የመስራትን በር ከፍቷል። ከሁሉም በላይ የአንድ መሪ ሥራና ተልዕኮ አርዐያ መሆን ነውና በድፍረት በትግሉ ወላፈን ውስጥ ራሱን ማግዶ በማሳየቱ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን አነቃንቋል። ጠላቶቹም ሳይቀሩ ሊያከብሩት ያስገደደ ድርጊት ሆኗል። ዛሬ ወያኔ መጨበጫ አጥቶ እንደሚጨነቅ ሰሞኑን ቴዎድሮስ አድሃኖምን ማዳመጡ ብቻ በቂ ነው።  አንዳርጋቸው በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ወያኔን የሚያውቅ ሁሉ ይረዳዋል። አንዳርጋቸው ችቦውን ለኩሶ ለተከታዩ ትውልድ አስተላልፏል። አንዳርጋቸው ከአሁን በኋላ መንፈስ ነው። ለጠላቶቹ የማይጨበጥ በጠባብ የወያኔ ጉላግ የማይታፈን የፅናት፣ የነፃነት መንፈስ። ጥላቻቸውንና ዘረኝነታቸውን ለመወጣትበጨለማ በሚያሰቃዩት አንዳርጋቸው ስም የሚታተም መጽሃፍ ሆነ ሌላ ቲያትር ዋጋ የለውም። ሚሊዮን አንዳርጋቸዎች ተንደርድረው በመግባት እሱን መስለውና እሱን አክለው ትግሉን ተቀላቅለዋል።

በዘንድሮው ሃምሌ ደግሞ ልክ በዓመቱ ትግሉን አምዘግዝጎ እጥፍ ድርብ በሚያሳድግ ሁኔታ በፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ወደ በረሃ መግባት ተደገመ። ትግሉ ይቀዘቅዛል ሲሉት ሞቀ፣ ይደክማል ሲሉት ጠነከረ፣ ይለሰልሳል ሲሉት ደደረ። የአንዳርጋቸው ስቃይ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ያንገበገበ ቢሆንም የትግል ጓዶቹ የግንቦት ሰባት አመራሮች የገቡበትን እልህና ቁጭት ሃያልነት የሰሞኑ ድርጊታቸው ጉልህ ምስክር ሆኗል። ነዓምን ዘለቀ፣ ኤፍሬም ማዴቦና ሌሎችም አመራሮች እየተንደረደሩ መሬት ወርደዋል።(ምናለ ለዛሬ ብቻ የምወደውን ሄኖክ የሺጥላን መሆን በቻልሁ) ገጣሚ ባለመሆኔ ስሜቴን መግለፅ አልቻልሁምና ድሮ ከጎህ መፅሄት ካነበብሁት ለዚህ ሰሞን የሚመጥነውን ስንኝ መንፈሱን ብቻ እንዲህ ልበል

ጓድ እኮ ጓዱ ቢሞት

በትግል ሜዳ ላይ ቢቀጠፍበት

እዬዬ አይልም፣ አያለቅስም

ቁጭ ብሎ አያላዝንም

ይወርዳል፣ ይንደረደራል እንጂ በምትኩ ሺ ሊለቅም።

አዎ! ብርሃኑ፣ ነዓምን፣ ኤፍሬምና ሌሎችም ያደረጉት ይህንኑ ነው። ጓዳቸው ሲታሰርና ሲንገላታ ተቀምጠው ከንፈር አልመጠጡም፣ አላለቀሱም። ይልቅስ የጀመረውን ትግል መልካም ፍፃሜ ላይ ለማድረስ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ህይወታቸውን ረክዘው መሬት ላይ ወርደዋል። የፋሲል የኔዓልምን አባባል ልዋስና “ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የመስዋዕቱን ጣርያ ከፍ አድርጎ ሰቀለው” የሚለውን በሚገባ እስማማበታለሁ። ፈረንጆች እንደሚሉት “he shattered the ceiling” የመስዋዕትነቱን ጣርያ ሰበረው እንደማለት ነው።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ በዚህ ድርጊቱ ትግሉን ከፍተኛ ደረጃ ከማድረሱም በላይ ጣምራ ተቀናቃኞቹን ማለትም ወያኔንና በተቃውሞ ጎራ ራሳቸውን መድበው ከእንቅፋትነት ውጭ ምንም የማይፈይዱ ከንቱዎችን ድንክ ነው ያደረጋቸው። ፀጥ ረጭ ነው ያሰኛቸው። እደገና ግጥም ፍለጋ ልባዝን። ጀግኖች አባቶቻችን አድዋ ላይ ጠላትን ድባቅ ሲመቱ ወገንን አላስጠጋ ያለውን የጣልያን መድፍ በወገን መድፍ አፉን የዘጋውን አባተ ቧ ያለውን እንዲህ ነበር ያሞገሱት።

አባተ ቧ ያለው ነገረኛ አዋሻኪ ሰው

ይህንን መድፍ ከዚያ መድፍ አቆራረጠው።

የብርሃኑ ወደ ትግል ሜዳ መግባት የዚያን መድፍ ያህል ጠላቱን ፀጥ ሲያደርገው የነፃነት ናፋቂ ኢትዮጵያውያንን ተስፋና ተነሳሽነት የትየለሌ ወደ ላይ ተኩሶታል። በአንዳርጋቸው መያዝ የተፈጠረው መነሳሳት በብርሃኑ ፋኖነት ወደ ሁሉን አቀፍ የድርጊት ትግል ተቀይሯል። በወያኔ ሚድያ፣በዌብሳይቶች፣ በፓልቶኮች፣ በባንኮኒ ዙርያ ለስርዓቱ ደጋፊዎችና አስመሳይ ተቃዋሚዎች ሳምባ ውስጥ ለጊዜውም ቢሆን አየር ጠፍቷል።

የትግሉ ሂደት (ፓራዳይሙ) ተቀይሯል። ወያኔ አንድ ነገር ባደረገ ቁጥር (አልሞትሁም ብዬ አልዋሽም ነው ያሉት) በስድት ወር መግለጫ በማውጣት አለሁ የሚለው ፖለቲካ ከሃያ ዓመት በላይ ኖረንበት አልፈየደምና አሁን ማብቃት አለበት። ሳምንት ሙሉ ሲለፋ ከርሞ ዲያስፖራው የሚያርፍባትን የሰንበት ሰዓቱንና ገንዘቡን ላልተጨበጠ ተረታ ተረት ማለቭ ሊያቆም ይገባል። የሚገደለው፣ የሚታሰረው፣ የሚደበደበው፣ የሚሰደደው ኢትዮጵያዊ ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። የስደት መንግስትና ካቢኔ ማቋቋምም እቃቃ ጨዋታ ነው። አንድም መሬት ወርዶ መታገል ያለዚያም መሬት ላይ ያሉትን በሰላማዊ ሆነ በትጥቅ ትግል የሚፋለሙትን መርዳት እንጂ እዚህ በነፃው ዓለም ቁጭ ብሎ መስዋዕት እየከፈሉ ባሉት ላይ አቃቂር ማውጣት ሆነ በስማቸው መነገድ ጊዜው እያለፈበት ሄዷል።

የአብዛኛው ቅን ኢትዮጵያዊ ተግባርም የመከራውን ቀን ለማሳጠር ተግባራዊ ትግል በማድረግ ላይ ያሉትን አይዟችሁ ማለትና መደገፍ፣ ሲሳሳቱም በምክር ማስተካከልና ማጠናከር ነው። በስሜቱ በሚጫወቱና ሲጫወቱ በኖሩት ደጋግሞ መታለል አያስፈልግም። ድርጊታቸውን ሳይሆን ስምና አጀንዳቸውን ከጊዜው ጋር እየቀያየሩ ብቅ የሚሉትንም “እስቲ በተግባር እንያችሁና እንደግፋችሁ” ሊል ያስፈልጋል። በሰላማዊ ትግሉ ግንባራቸውን ሳያጥፉ ወህኒና ማእከላዊ የሚማቅቁ ጀግኖችንና ቤተሰቦቻቸውን መደገፍ አንዱ የትግል ግንባር ስለሆነ መታሰብና መከወን ያለበት ጉዳይ ነው። መከራውን የሚያሳጥረው ፕሮፌሰር ብርሃኑ እንዳለው እየተሰበሰቡ ማውገዝና መማማል ሳይሆን የተግባር እንቅስቃሴ  ማድረግ ነው ። ትንንሿን የግል አቅማችንን ሳንንቃት ከሌሎች ጋር በማዳበል ጠጠሩ ሁሉ ወደ አንድ አቅጣጫ ማለትን የወያኔን የጨለማ አገዛዝ ለማስወገድ ወደሚደረግ የትግል አቅጣጫ መወርወር እንጀምር።

አንድ ህይወታቸውን ለአገር በሰጡት ወገኖች ላይ የሚሰነዘረውን ማንኛውንም አይነት የጎንዮሽ ደባ ማጋለጥና እረፉ ማለት የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ ነን። ጊዜው ሰከን ብለን እየተደጋገፍን ወደ አንድ አገራዊ አቅጣጫ ለመሄድ የምንንቀሳቀስበት እንጂ እየተጠላለፍን ስንድህ የምንኖርበት አይደለም።

እግዜብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!

 

 

 

የተደበቀው የህወሓት ማንነት ከደደቢት እስከ ቤተ መንግስት (ክፍል ሦስት) –የሌ/ጀነራል ፃድቃን እና የሌ/ጀነራል አበበ ድብቅ ገመና

$
0
0

ሌተናል ጀነራል ፃድቃን ገ/ተንሳይ

ፃድቃን ገ/ተንሳይ ኤርትራዊ ከሆኑት ወላጆቹ ስራየ አውራጃ ሰገነይቱ ተወልዶ አድጎ ልክ እንደ ሳሞራ የኑስ ወደ ትግራይ የመጣው በስደት ነው፡፡
ከወላጆቹ ጋር ከኤርትራ ተሰዶ ማይጨው የመጣው በ1955 ዓ.ም ነበር፡፡ ወደ ደደቢት በረሀ አምርቶ ህወሓትን የተቀላቀለው የ12ኛ ክፍል ትምህርቱን በማቋረጥ ከመቀሌ ኮብልሎ ነው፡፡
Interview with Lt. General Tsadkan Gebretensae – SBS Amharic
ፃድቃን ገ/ተንሳይ ከእነ ሳሞራና ሌሎች የህወሓት ድኩማን ጀነራሎች በወታደራዊ ዕውቀቱ የተሻለ እንደሆነ ይወራለት እንጂ ማንነቱ በትክክል ሲፈተሽ በደደቢት በረሀ ከወሰዱት እዚህ ግቢ የማትባል የአንድ ወር ወታደራዊ ትምህርት በስተቀር ምንም አይነት እውቀት የሌለው፣ በውጊያም እንደ መለስ ዜናዊና ሳሞራ የኑስ እልምያለ ፈሪ እና በየትኛውም ጦርነት ላይ ተዋግቶም ሆነ አዋግቶ የማያውቅ እንደሆነ እሱን በቅርበት የሚያውቁት ሀቁን ይመሰክራሉ፡፡
አነሩ መለስ ዜናዊ ድመቶችን በዙሪያው ሰብስቦ ነብር መስሎ ለመታየት ለ21 ዓመታት ሲፍጨረጨር እንደታየው ሁሉ ወጠጤው ፃድቃን ገ/ተንሳይም በግልገሎች መካከል ቆሞ ሰንጋ መስሎ ለመታየት ሞክሯል፡፡

በ1971 ዓ.ም ዓብይ ወዲ እና ዓዲ ኮኾብ እንዲሁም በተጨማሪ በ1973 ዓ.ም ሀውዜን ላይ በተደረጉት ውጊያ መሰል መጠነኛ መቆራቆሶች ፃድቃንን ከድንጋይ ስር ተደብቆ በፍርሀት ሲርበተበት በአይኖቹ በብረቱ እደተመለከተው የቀድሞው የህወሓት ነባር ታጋይ ገ/መድህን አርአያ ይናገራል፡፡

በመሆኑም ሦስት ጊዜ በተደጋጋሚ ፈርቶ ከጦር ሜዳ የሸሸው ፃድቃን ገ/ተንሳይ ለአምስት ወራት መታሰሩን ከህወሓት ዶሴ ላይ ሰፍሮ የሚገኘው የኋላ ታሪኩ ያስረዳል፡፡ ነገር ግን ከመለስ ዜናዊና ከስብሀት ነጋ ጋር ባለው የጠበቀ ወዳጅነትና ቅርርብ የእስር ጊዜውን ካጠናቀቀ በኋላ በለስ ቀንቷቸው መላ አገሪቱን እስከ ተቆጣጠሩበት 1983 ዓ.ም ድረስ በኮሚሰርነት ተመድቦ ቆይቷል፡፡ ቢሆንም ዳር ቆሞ ሲመለከት ኖረ እንጂ አንድም ጊዜ ተሳስቶ ጦርነት አልመራም፡፡

ፃድቃን ገ/ተንሳይ ከበረሀ ጀምሮ ፈፅሞ በማይግባባውና እጅግ በጣም ይጠላው በነበረው ሀየሎም አርአያ ግድያ ከመለስ ዜናዊ፣ ስብሀት ነጋ እና አርከበ ዑቁባይ በተጨማሪ እጁ እዳለበት መቶ በመቶ የተረጋገጠ ሀቅ ነው፡፡

ፃድቃን ገ/ተንሳይ ከኤርትራ ጋር በተደረገው ውጊያ እሱ ባወጣው መቶ በመቶ የተሳሳተ የጦር ስልት ምክኒያት በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ የደሀው የኢትዮጵያ ህዝብ ልጆች ፆረና ላይ ያለአግባብ በከንቱ ረግፈው ቀርተዋል፡፡ ሬሳቸው እንኳን የሚለቅመው ጠፍቶ በፆረና ተራሮች ላይ ተዘርተው አፅማቸው ተልከስክሶ አሁንም ይገኛል፡፡ መሀይሙ ጀነራል ፃድቃን የቀየሰው የጦር ንድፍ መቶ በመቶ ሲበለሻሽና ከፍተኛ እልቂት ሲደርስ ከሱ በታች ያሉ ሌሎች ጀነራሎችን አስከትሎ ከአከባቢው ሸሽቷል፡፡
ፃድቃን ገ/ተንሳይ በጡረታ ስም ከሰራዊቱ ይገለል እንጂ በስልጣን ዘመኑ በዘረፋ ያካበተው ከፍተኛ ሀብት ሳያንሰው ኤታማጆር ሹም በነበረበት ጊዜ ያገኘው የነበረው ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ሳይሸራረፍ ሙሉ በሙሉ ተከብሮለት በእጅጉ በተንደላቀቀ ህይወት ውስጥ ይገኛል፡፡

ሌተናል ጀነራል አበበ ተ/ኃይማኖት ወይንም ጆቤ

መቀሌ የተወለደው አበበ ተ/ኃይማኖት ህወሓትን የተቀላቀለው በ1968 ዓ.ም ሲሆን ልክ እንደማናቸውም የህወሓት ጀነራሎች የአንድ ወር ወታደራዊ ስልጠና ከወሰደ በኃላ የሐለዋ ወያኔ ባዶ ስድስት ወይንም የትግራይ ጓንታናሞ ኃላፊ ሆኖ በቀጥታ ቡምበት ላይ ተመደበ፡፡
የታጋዮች ቀራኒዮ የነበረውና ዕልፍ ዓዕላፍ ንፁሀንን ህይወት ቅርጥፍ አድርጎ የበላው ያ አደገኛ ወህኒ ከቡምበት ተነስቶ ወደ አጽርጋት ሱር ከተዛወረበት 1969 ዓ.ም እስከ 1974 ዓ.ም ኃላፊው አበበ ተ/ኃይማኖት ነበር፡፡
abebe tekelehaimanot
ብስራት አማረ፣ ታደሰ መሰረት፣ ተስፋዬ መረሳ፣ ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል፣ ተስፋዬ አፅብሃ፣ ዘአማኑኤል ለገሰ፣ አበበ ዘሚካኤል፣ ዘርዓይ ይህደጎ፣ ሐሰን ሽፋ እና ክንፈ ገ/መድህን በዋነኝነት ከአበበ ተ/ኃይማኖት በተጨማሪ ሐለዋ ወያኔ ወይንም ባዶ ስድስት በተባለው አደገኛ ወህኒ ውስጥ በየጊዜው በሚታሰሩ ታጋዮች ላይ ሰቆቃና አሰቃቂ ግድያ ሲፈፅሙ የኖሩ ናቸው፡፡

አበበ ተ/ኃይማኖትና ሌሎችም ሰቆቃና አሰቃቂ ግድያ ፈፃሚ የህወሓት ታጋዮች ተጠሪነታቸው ለመለስ ዜናዊ፣ ስብሀት ነጋ እና አባይ ፀሐዬ ነበር፡፡
አበበ ተ/ኃይማኖት ወይንም ጆቤ የሐለዋ ወያኔ-ባዶ ስድስት ወህኒ ቤት ኃላፊ ሆኖ በሰራባቸው ዓመታት ውስጥ በግፍ በታሰሩ ንፁሀን ታጋዮች ላይ እንዲፈፀሙ ካደረጋቸው በርካታ የማሰቃያ ወይም የ”ቶርቸር” ድርጊቶች መካከል ሴቶችንም ጭምር ርቃን ገላቸውን ከግንድ ጋር በማሰር ለረጅም ጊዜ ፀሀይና ብርድ እንዲፈራረቅባቸው ማድረግ፣ ገልብጦ የእግር መዳፍን መግረፍ፣ ከ16 ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝን አሽዋ ከወንዶች ብልታቸው ላይ ከሴቶች ደግሞ ጡታቸው ላይ ማሰር፣ በፈላ ውሀ መቀቀል፣ በጋለ ብረት መቀመጫን ማቃጠል፣ ጭንቅላትን ወደታች ዘቅዝቆ ማንጠልጠል፣ ባዶ እግርን በሾህ ላይ እንዲራመዱ ማድረግና ከፍተኛ ክብደት ያለው ብረት ወይንም ድንጋይ አሸክሞ ለረጅም ጊዜ ማቆም ዋና ዋና ዎቹ ናቸው፡፡

እነኚህ የማሰቃያ ወይንም “ቶርቸር” አይነቶች ዛሬም በየእስር ቤቱ በስራ ላይ እተተገበሩ ይገኛሉ፡፡ ማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ የህወሓት ደህንነቶች ሴቶችን በወር አበባቸው ሳይቀር ልብሶቻቸውን አስወልቀው ዕርቃናቸውን አቁመው በሀፍረተ ስጋቸው እየተሳለቁ የሚመረምሯቸው መሆኑ በቅርቡ የተረጋገጠ ሀቅ ነው፡፡
አበበ ተ/ኃይማኖት በሱር የሐለዋ ወያኔ ወይም ባዶ ስድስት ኃላፊ በነበረበት ወቅት የወልቃይት ህዝብ በገፍ እየታፈሰ እንዲረሸንና በጅምላ እዲቀበር በማድረግ ዘር ማጥፋት ፈፅሟል፡፡

አበበ ተ/ኃይማኖት ከአደገኛው እስር ቤት ኃላፊነቱ በ10 ሺህዎች በሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ሰቆቃና ጭፍጨፋ ከመፈፀምና የገበሬውን ሰራዊት ማርኪሲዝምና ሌኒንዝም ርዕዮተ ዓለም ከማስተማር በዘለለ ለአንድ ጊዜ እንኳን ውጊያ ላይ አልተሳተፈም ፡፡ ልክ እንደ ሳሞራ እና ፃድቃን እሱም ለጀነራልነት የበቃው ለእነ መለስ ዜናዊና ስብሀት ነጋ ባለው ታማኝነትና አጎብዳጅነት ብቻ ነው፡፡

አገራችንን ረግጠው በኃይል ለመግዛት ከቻሉ በኋላም እንኳን ሊኮፈስባት በገንዘብ የገዛት የህግ ባችለር ዲግሪው ከሙያው ጋር የማትገናኝ በመሆኗ እሱንም እንደሌሎቹ የበረሃ ጓዶቹ የህወሓት ጀነራሎች የጦር ማሃይምነት ድቅድቅ ጨለማ ውጦት ቀርቷል፡፡

አበበ ተ/ኃይማኖት ወይም ጆቤ ልክ እንደ ሳሞራ የኑስ የወጣለት ሴሰኛ በመሆኑ የበረሃ ጓዶቹን ሚስቶች ሳይቀር በማባለግ ይታወቃል፡፡ የአየር ኃይል አዛዥ በነበረበት ወቅት አየር ኃይል ጠ/መምሪያ ቢሮ የምትሰራውን የሜ/ጀነራል መሃሪ ዘውዴን ባለቤት በማባለጉ “ባለቤቴን ማባለጉ አልበቃ ብሎ ባልሽን ወደ አንዱ ጦርነት ስለምልከው እና ስለሚሞት ልጅ ውለጅልኝ እያለ ባለቤቴን ቁምስቅሏን እያሳያት ነው፤” ሲል መሀሪ ዘውዴ ክንፈ ገ/መድህን በተገደለበት የህወሓት ከፍተኛ መኮንኖች ስብሰባ ላይ ከሶታል፡፡ ከእሱ በኋላ የአየር ኃይል አዛዥ የሆነውን ሜጀር ጀነራል ሞላ ኃ/ማሪያምን ሚስቱን ቢሰጠው የጀነራልነት ማዕረግ ትከሻው ላይ እንደሚያስርለት ነግሮት ሞላም በጉዳዩ ተስማምቶ የሁለት ልጆቹን እናት ለአበበ ተክለ ኃይማኖት በማከራየት ከኮሎኔልነት ጀነራል በመሆን ህልሙን አሳክቷል፡፡ በመጨረሻም የሞላ ኃ/ማሪያም ትዳር በአበበ ተ/ኃይማኖት ምክንያት ሊፈርስ ችሏል፡፡

አበበ ተ/ኃይማኖት የአየር ኃይል አዛዥ በነበረበት ወቅት አየር ኃይል የቁልቁለት ጉዞ በሸርተቴ የተጓዘ ሲሆን የራሽያን ጀነራሎች በአማካሪነት ስም አምጥቶ ቀዳዳውን ለመሸፈን ተፍጨርጭሯል፡፡

ብ/ጀነራል ተጫኔ መስፍንንም ከእስር ቤት አውጥቶ አማካሪው አድርጎታል፡፡

ከሴሰኝነት በተጨማሪ የህወሓት ዋነኛ መለያዎች የሆኑት ዘረኝነትና ሌብነት አበበ ተ/ኃይማኖት ላይም በጉልህ ይታዩ ነበር፡፡ በመሆኑም አየር ኃይሉን አንድ አይነት ቋንቋ በሚናገሩ የአንድ አካባቢ ሰዎች ሞልቶታል፤ እስኪበቃውም መዝብሮታል፤ አስመዝብሮታል፡፡

አበበ ተ/ኃይማኖት በአንድ ወቅት በአሉዌት ሄሊኮፕተር ተሳፍሮ ወደ ጋምቤላ ሲሄድ ካላበረርኩ ብሎ አብራሪውን በማስቸገሩ አብራሪው ቦታውን ለቆለት ተቀብሎ አሉዌት ሄሊኮፕተሯን ልክ እንደ እምቧይ ከምድር አፍርጧታል፡፡ በተጨማሪም አበበ ተ/ኃይማኖት ሲጋራ፣ ዊስኪ እና ሴት ለማስመጣት በየከተማው ሄሊኮፕተር ይልክ ነበር፡፡
አበበ ተ/ኃይማኖት ምንም እንኳን ዛሬ በስጋ ከህወሓት የተነጠለ ቢመስልም በመንፈስ ግን ጨርሶ አልተለየም፡፡ በ1993 ዓ.ም የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ከሁለት ሲሰነጠቁ በአንጃነት ተፈርጀው የተባረሩት የቀድሞ ታጋዮች እንዲመለሱ ተወስኖ ጥሪ ሲደረግላቸው አበበ ተ/ኃይማኖትንም አካተውት ወደ ባንዳዎች ስብስብ ለመመለስ እና በባንዳነቱ ለመቀጠል ስምምነቱን ገልጿል፡፡

የምድር ኃይሉ እና የአየር ኃይሉ ቁንጮ የነበሩት ሁለቱ የህወሓት ጀነራሎች አበበ ተ/ኃይማኖት እና ፃድቃን ገ/ተንሳይ ከመከላከያ ሰራዊቱ ሲወገዱ በህወሓት መንደር አንዳች ለውጥ አለመታየቱ የሰዎቹን ሚናየለሽ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ የጀነራልነትን ማዕረግ ለበሱት እንጂ ከጀነራልነቱ ማዕረግ ጋር የሚመጣጠን ወታደራዊ ዕውቀት የሌላቸው ቦታ ብቻ የያዙ ባዶ ዕቃዎች መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡

ግንቦት 8 ቀን 1981 ዓ.ም ተሞክሮ በከሸፈው መፈንቅለ መንግስት ተሳታፊ የነበሩት ጀነራሎች መረሸን ግን ከአንድ ዓመት በኋላ ደርግን ለውድቀት ዳርጎታል፡፡

የአፋር መስተዳደር አዲስ ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳደር ሾመ

$
0
0

afar

አኩ ኢብን ከአፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው:

በኢህኣደግ ሰርዓት እረጂም ዓመታት በክልል መሪነት በማገልገል ሪከርድ የሰበረው ብቼኛ ኣገልጋይ ኣቶ እስማዒል ዓሊ ሲሮ ባለፈው ምረጫ ለፈደራል ፐርላማ መወዳደራቸውን ተከትሎ ዛሬ ኣዲስ መሪ ተሾሟል።
ዛሬ የተሾሙት ኣቶ ኣዋል ዓርባ ዑንዴ ከምርጫው ቀደም ብሎ ከግብሪና እና ገጠር ልማት ቢሮ ወደ ምክትል ረዕሰ መስተዳደር በማምጣት የተሾሙ ሲሆን ኣሁን ደግሞ ከዛሬ ጀምሮ የክልሉ ጊዜያዊ ፕረዝዳንት ሆኖው ይቆያሉ ተብሏል።
በኣሁኑ ወቅት በኣጣቃላይ በኢህዴግ መሪዎች ዉስጥ ያለውን ኣለመግባባትን ተከትሎ የኣፋር ክልል ካድረዎች ዉስጥም ክፍተኛ የሆነ ኣለመግባባት ኢየታየ ነው።
በነግራችን ላይ የኣፋር ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ( ኣብደፓ) በነገው ዕለት ጣቅላላ ጉባኤ ያድርጋል ትብሎ ይጠበቃል።
በዚህ በነገው ሰብሰባ የክልሉ ምክትል ፕርዝድንት፣ የክልሉ ምክሪቤት ኣፌጉባኤ እና የፓርቲ ኃላፊ ይምረጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ወትርዉም ብሆን የኣፋር ክልል መሪ የሚመረጠው በህወሃት ጣልቃ ገብነት ሲሆን ኣሁን በጊዜዊነት የተሾሙት ኣዋል ዓርባ በክልል መሪነት ይቀጥሉ ኣይቀጥሉ ኣይታወቂም።
ኢህአዴግ ህወሀት ባለፉት ሁለት ኣስርት ዓመታት የብሔር ብሔርሰቦችን መብት ኣክብሬያለሁ በሚል ሽፋን በኣፋር ህዝብ ላይ ያደርሰው በደሎች ኢንኳን ጉልቻ መቀያየርን ቀርቶ እራሱ ኢህአደግ ብቀየሪም ታሪክ ይቅር የማይለው የመግደል፣የማፋናቀል፣የማሰር እና በሃብታቸው እንዳይጠቀሙ በማድረግ የፈጸመው በድሎች በኣፋር ክልል የህወሀት ተቃዋሚዎች እንዲበረከቱ ምክንያት ሆነዋል።
በኣሁኑ ወቅት በኣፋር ክልል ወጣቶች ብዙ የትደራረበ ጥላጫ ለኢህአደግ መንግንስት እንዳላቸው በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየግለጹ ሲሆን ለምሳሌ ያህል መንግስት በክልሉ ህዝብን በማፋናቀል እየሰራ ያለው ልማት ተብዮው በኣፋር ኣርብቶ ኣደሮች ህይዎት ላይ ያስከተለው ችግር ቀላል ኣይደለም።
እይዉነት ለመናገር የኣፋር ህዝብ ካሁን በፊት ባልፉት ሰርዓቶች በዚህ ሁኔታ ኣልራበም።
በተለይ በምስራቅ የክልሉ ኣክባቢ በኣዋሽ ወንዝ ዳር ይኖሩ የነበሩ ኣርብቶ ኣደሮች ተፈናቅለው መሬታቸው በሙሉ ለመንግስት የስኳር እርሻ ተከለዋል።
የዚህ ዉጤት እነሆ ዛሬ በህዝብ ላይ ክፊተኛ ረሃብ አስከትሎ የኣለም ኣቀፍ ሚዲያዎች መንጋገሪያ ሆኖ ይገኛል።
በኣፋር ክልል እየሞቱ ያሉት ከብቶች ብቻ ኣይደለም፣ ሰዎቹም እየሞቱ ነው።
ኢስካሁን ባለኝ መረጃ መሰረት በዱብቴ ወረዳ ፣ ዳትባሃሪ ኣከባቢ በራሃብ ና በጥም እንዲሁም የቆሸሸ ዉሃ ጠጥተው
የስምንት ህጻናት ህይዎት ኣልፈዋል።
በሚሌ፣ በኦንዳ ፎኦ አከባቢም ከብቶቻቸው ያለቁባቸው ነወሪዎች እራሳቸው ያጠፉ እንዳሉ ሰሚቼያለሁ።
ሌላው ድግሞ በሰሜን የክልሉ ኣከባቢ ከዳሎል ኢስከ ማጋሌ ወረዳ ያለው የትግራይ መሬት ነው በማለት ነዋሪዎችን በማጋጨት ብዙ ኣፋሮች በወያኔ ሚልሻዎች ተገድልዋል።
በባራህሌ ወረዳ የሚገኘው ኣሞሌ ጨው ለኣንድት የትግራይ ሃብታም ካልሰጠሁ በማለት የባራህሌ ወረዳ ኣፋሮችና ወያኔ ከተፋጠጡ ወራት ተቆጥረዋል።
በዳሉል ወረዳ ኣብዛኛው መሬት በዋያኔ ተጠቃሚነት ለውጭ ኣገር ድሪጅቶች የተሰጠ ሲሆን የቀረው መሬትም በቅርብ ለፖጣሽ ኣምራቶች ተሰጥቶ ህዝብ ገና ካሁን በኋላ ልፈናቀል መሆኑን የኣፋር ክልል የወያኔ ኣገልጋይ ተሰናባቹ እስማዕል አሊ ሲሮ ባለፈው ሳምንት በኢቢሲ በሰጡት መግለጫ የገለጹ ሲሆን ኣሁን በኣዲሱ በዳሉል ወረዳ ለፖጣሽ የተሰጠው መሬት ስፋቱ ከሶስት መቶ ሲልሳ ኣምስት በላይ ስከዌር ኪሎ ሚትር መሆኑን በካምፓኒው ዲህረ ገጽ ኣምቢበውለሁ።
ሌላውና ቀዳሚው የኣፋር ክልል የጨው ሃብት ባለበት የሆነችው ኣፍደራ ሲትሆን በኣፍደራ የጨው መሬት የለለው የወያኔ ባለስልጣን፣የወያኔ ጀነራል የለም።
ኢንዲሁም ባለፈው ሳምንት በኣስመራ ታስረዋል የተባለው የኤረትራ የጻጥታ ሀላፊ ( ሚነስተር ) በኣፍደራ የጨው መሬት ኣላቸው፣ የቀድሞው የትግራይ ክልል መሪ ኣቶ ፀጋይ በርሄን ጨምሮ ኢያንዳንዳቸው የህወሀት መሪዎች በኣፍደራ የጨው መሬት ኣላቸው።
ሌላው ዶቢ ዓስቦ ( የዶቢ ጨው ሲሆን ዶቢ የሚባለው በኣፋር ክልል ኢትዮጲያ ከጀቡቲ በሚያዋስን ቦታ ላይ የሚገኝ የጨው መሬት ነው።
ይህ መሬት ሙሉ በሙሉ የኣንድ ባለሃብት ሆኖ ይሚገኝ ሲሆን እርሱ ማሀመድ ሁመድ ይባላል።
በኣፋሮች ዶቢ ዓስማሀማድ በሚል ቅጽል ሲሙ ሲታወቅ በህወሀት የተለመደው ልማታዊ ባለሃብት የሚል ማዓረግ ተስጦታል።
ለነገሩ ልማታዊ ባለሃብት ማለት የወያኔ ደጋፊ የሆነ ባለሃብት ማለት ኣይደል ?
ትርጉሙ በተዘዋዋሪም ብሆን ይህ ብሆን ነው እንጂ ልማታዊማ ብሆን ሲንት ህዝብ በራሃብ ኢና በዉሃ ጥም እየሞተ እያየ እንዳላየ የሚያልፍ ሃብታም ልማታዊ ባለሃብት ሲባል ምን ትለውለህ ?
የብሔር ብሔረሰቦች መብት ኣስክብረናል በሚል ሽፋን የብሔር ብሔርስቦችን ባህሎች፣ሃይሞኖቶች፣ሃብቶችና ክርሶች እያጠፋና እዘረፈ ያለው ህወሀት በኣፋር ክልል ያለው እውነታ ግን ዜሮ ዜሮ ነው።
ለምሳሌ፦ በየኣጋጣሚው ባህላዊ ጨፈራ በተለቭዥን ከማሳየት የዘለለ የተከበረ መብት የለም ።
ኣራት ነጥብ

ይህ ግጥም የጻፈው ገጣሚ ስሙን እንዳይገለጽ የጠየቀን ሲሆን የኣሊጋራብ ጥቁር ነቢር በሚለው ቅጺል ስሙ ትጠቅመናል።

ጥቅት ሆዳሞች።።።።

ጥቅት ሆዳሞች ህዝብን ስያታልሉ
በሰመ ልማት ኪሳቸው እየሞሉ
አገር አደገች ብለው ድረቅ ብለው ይውሻሉ
እባካቹሁ ሰዎች አንድ ነገር በሉ
አፋር አፋር የኢትዮጲያ አይን የኢትዮጲያ ክብር
የሰው ዘር መገኛ ታሪካዊ ምድር
ሉሲ እኮ አለች የቅርብ ጊዜ ምስክር
ተፅፎ አይልቂም ስንት ብየ ሊዘርዝር
ከዳሉል ጀምሮ፣ ባራሕሌ፣ ኮናባ፣
ኤረብቲ ፣ማጋሌ፣ አበኣላ፣ ስትገባ
ክርስ መሬቶቹዋ በማዕድን ተውባ
አገሬ ተሰቃየች በድህነት ተረባ
ጨው፣ ፖጣሹ፣ ወርቅ፣ የተከበረ ድንጋይ፣
በውስጧ ተቀበረው የሄ ሁሉ ስቃይ
የት ያለ እድገት ነው በአይን የማይታይ
እነ ሲሮ የሚጮሁት የወያነ አገልጋይ
ዞን አራት ካሉዋን፣ ያሎ፣ ቴሩ
የማዕድን ሀብታችን ተጠንው በመረመሩ
ማእቀብ ተደርጎበት እንዳይቆፈሩ
የአብዴፓ መሪዎች ለሆዳቸው ያደሩ
አንዱ የሄ ነው ከድብቅ አጀንዳቸው፣ ከሚስጥሩ
ዞን አምስትም እንደዚሁ፣ ዞን ሶስት ጋቢ ራሱ፣
ዞን አንድም እደዚሁ አውሲ ራሱ፣
ህዝብን እያጋጩ እርስ በርሱ
አገር እንዳይለማ በህብረት እንዳይርሱ
በላሌ፣ በሰዳዓ፣በሆራ፣በኬኬ እየዘለሉ ማጫወት
በቴልቪዢን መስኮት ደጋግሞ ማሳየት
በዚሁ ከሆነ የተጠበቀው መብት
ዶሮን ሊያታልሏት በማጫኛ አሰረዋት
ቋንቋችን ባህላችን ከትንጥ የቆየ ነው
ህጋችን ደንባችን የአፋር ማድዓ ነው
አዲስ ነገር የለም አሁን ያገኘነው
አዲስ ነገር ቢኖር የቀኝ አገዛዝ ነው
የህዝብ ጥያቄ አንድና አንድ ብቻ ነው
ፊተጥ፣ ዴሞክራሲ፣ሰፍኖ በልማት ማደግ ነው
መሪያችን ስሆን እኛ የመረጥነው
በቋንቋቸው፣ በስማቸው አፋሮች
በእጅ አዙር የሌላ አገልጋዮች
አቅም የሌላቸው ድንቆሮ መሀይሞች
ህዝበባችን አጠፉት የአብዴፓ መሪዎች
ሐጂ ሱዩም፣ አንበጣ እስማዕል ሲሮ
ሌላ መሪ አላቸው በድብቅ በሰተጓሮ
ተትእዛዝ የሚያስተላሊፍ አጀንዳው ዘርዝሮ
ገብረፂዮን ወያኔ ከፈደራል ቢሮ
የተማረ አልወጣም ከዚህ ሁሉ ወጣት
ወራሽ ሰለታጣ ነው እንዴ፧ ሲሮን የሚያምኑት
ህዝባችን እያየ አይናቸው የጨፈኑት
ዝም ብለን አናይም እየጠፋ አገራችን
አኩ ኢብን አፋር ብቅ አለ ከጎናችን
በአብዴፓ መርዝ የደነዘዘ አካላችን
በቃ ተነሱ ብሎ ቀሰቀሰን ከእንቅልፋችን
አኩ ኢብን አፋር አኩ ኢብን አፋር
የመጀመሪያ ጀግና የመጀመሪያ ደፋር
በአብዴፓ የተዘጋው የነፃነት በር
ከጎኑ እንሰለፍ ይህን ህብረት ለመስበር
ገጣሚ
፨ የአሊ ጋራብ ጥቁር ነብር ፨

13/ 08 /2015
ፊትህ ለኢትዮጲያ ህዝብ
ክብር ለነፃነት ተጋዮች
ውርደት ለወያኔ

አንድ አፍታ በሸዋሮቢት እስር ቤት

$
0
0

በላይ ማናዬ

አዲስ አበባ ላምበረት አካባቢ በሚገኘው ሰሜን በር መናሃሪያ ከጓደኛዬ ጋር የጉዞ ትኬታችንን በእጃችን አስገብተን ‹‹ሸዋሮቢት! ሸዋሮቢት›› በሚል መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ (በተለምዶ ቅጥቅጥ የሚባል መኪና) ውስጥ ገብተን ቦታችንን ይዘናል፡፡ ለጉዟችን ሻንጣ አልያም ከበድ ያለ ሸክም አልያዝንም፡፡ ሸዋሮቢት ለመሄድ ካለምኩ ረዘም ያለ ጊዜ ቢያልፈኝም ለመተግበር ዛሬን (ነሃሴ 7/2007 ዓ.ም) መጠበቅ ነበረብኝ፡፡ ወደ ሸዋሮቢት የምሄደው እዚያ ርቀው የተወሰዱ የህሊና እስረኛ ወንድሞቼን ለመጠየቅ ነው፡፡ ጓደኛየም ሆነ እኔ ሸዋሮቢት የሚገኘውን የፌደራል ማረሚያ ቤት አናውቀውም፡፡ ስለሆነም የሚያውቁ ሰዎችን መማተራችን አልቀረም፡፡
shwa
የጉዞ መኪናችን ገና መናሃሪያውን ሳይለቅ ከተቀመጥንበት ወንበር ኋላ ያለ ወንበር ላይ የተቀመጡ አንዲት እናት ደጋግመው የድካም ትንፋሽ ሲተነፍሱ በመስማቴ ዞር አልኩ፡፡ አፍንጫየን ትኩስ የቤት ዳቦ ሽታ ስቦ አስቀረው፡፡ እኒህ እናት እንደኛው ሸዋሮቢት የታሰረ ሰው ሊጠይቁ እየሄዱ መሆናቸውን ተገነዘብኩ፡፡ የድካም ትንፋሻቸውን እንደገና ሲተነፍሱ ሰማሁ፤ የመማረርና የመሰላቸት ትንፋሽ! እኒህ እናት እኔና ጓደኛየ ለመጀመሪያ ጊዜ የምንሄድበትን የሸዋሮቢት እስር ቤት ስንቴ ተመላልሰውበት ይሆን ስል ራሴን ጠየቅሁኝ፡፡

የአንድ ሰው መታሰር (በተለይ በግፍ ለሚታሰሩ) ምን ማለት እንደሆነ ከታሳሪው በላይ በዙሪያው ያሉት ቤተሰቦቹና ወዳጆቹ ሊገነዘቡት እንደሚችሉ ግልጽ ነው፡፡ እኒህ በጉዞ ላይ ያገኘኋቸውን እናት ስመለከት ከታሳሪው የበለጠ ለእናትየዋ ሀዘንና ርህራሄ ተሰምቶኛል፡፡ ከአዲስ አበባ 250 ኪሎ ሜትር ያህል ርቀትን ትራንስፖርት ከፍለው፣ ስንቅ አዘጋጅተውና ተሸክመው እስረኛውን መጎብኘት ምንኛ ከባድ ሸክም ነው!?

ጉዟችን ጠዋት ለአንድ ሰዓት ሩብ ጉዳይ ከአዲስ አበባ ተነስተን ወደ ሸዋሮቢት አድርገናል፡፡ በጉዟችን ከታዘብኩትና አሰልቺ ሆኖ ካገኘሁት ጉዳይ ዋነኛው በየጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት እንድንቆም መገደዳችን ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ተነስተን ሸዋሮቢት እስክንደርስ ስድስት ጊዜ በፖሊስ (በአብዛኛው በትራፊክ ፖሊስ) እንድንቆም ተደርገናል፤ የተጋነነ ቢመስልም ሀቁ ግን ይህን ያል ጊዜ መቆማችን ነው፡፡ አንድ ጊዜ ደግሞ ሁላችንም ከመኪና እንድንወርድ ታዝዘን ፍተሻ ተካሂዶብናል፡፡ ይሄ ሁሉ ጋጋታ ለምን እንደሆነ ግን ማንም ያወቀ የለም፡፡ ቁም ይባላል፣ ሹፌሩም የታዘዘውን ይፈጽማል፡፡ ይህን የተመለከቱ አንድ ከአጠገቤ የተቀመጡ አባት ‹‹አሁንስ ብሶባቸዋል!›› ሲሉ ሰምቼ ‹‹ከአሁን በፊት እንዲህ አልነበረም እንዴ?›› ስል ጠይቄያቸው ነበር፡፡ እሳቸው ግን ‹‹ኸረ ተወው ልጄ!›› ከማለት ውጭ ተጨማሪ ነገር መናገር አልፈለጉም፡፡

በእርግጥ ወደ ሸዋሮቢት ለመሄድ ስነሳ የራሴ የሆነ መጠነኛ የጸጥታ ስጋት ሳያድርብኝ አልቀረም፡፡ ምክንያቱም እንኳንስ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ሰሜን የሚደረግን ጉዞ ሰበብ አግኝተው ይቅርና አዲስ አበባ ላይ አንድ ወዳጄን ይዘው ‹‹ግንቦት ሰባትን ልትቀላቀል ወደ ኤርትራ ልትሄድ ስትል ነው የተያዝከው›› ብለውት ነበር፣ ሳያፍሩ! (አሁን ያ ወዳጄ ከእስር ተፈትቷል፡፡) ስለሆነም ፍተሻው ብዙም አላስገረመኝም፡፡ ከአንድ ወር በፊትም የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሆኑ አምስት የሸዋሮቢት ነዋሪዎች ‹‹ለግንቦት ሰባት አባላትን ትመለምላላችሁ›› በሚል ጥርጣሬ ተይዘው ወደ ማዕከላዊ መምጣታቸውን ሰምቼ ስለነበር ሸዋሮቢት መጓዝ እንደድሮው ሊሆን እንደማይችል ግምቱ ነበረኝ፡፡

በዚህ ሁኔታ በጠዋት ተነስተን ስድስት ሰዓት አካባቢ ሸዋሮቢት ደረስን፡፡ ከመኪናችን ስንወርድ እኒያ ከኋላየ የነበሩትን እናት ዞር ብየ አየኋቸው፡፡ የተሸከሙት ስንቅ ክብደት እንዳለው በማየቴ ተቀብያቸው ከመኪና አወረድኩላቸው፡፡ ደጋግመው የድካም ትንፋሽ ያስወጣሉ፡፡ ባጃጅ ይዘን ማረሚያ ቤቱ ጋ ደረስን፡፡ ሰዓቴን ሳይ ስድስት ሰዓት ሆኗል፡፡ ቃሊቲና ቂሊንጦ እስር ቤቶችን አስታውሸ ‹‹ከሰዓት ነው የምንገባው ማለት ነው?›› ብዬ ስጋት ገባኝ፡፡ ግን ስጋቴ ልክ አልነበረም፡፡ ሸዋሮቢት ሙሉ ቀን እስረኛን መጠየቅ ይቻላል፣ ምሳ ሰዓትን ጨምሮ፡፡ እናም በቀጥታ ወደበሩ በማምራት አስፈላጊውን ፍተሻ ካደረግን በኋላ የምንጠይቃቸውን ሰዎችና የሚገኙበትን ዞን አስመዘገብን፡፡ ሸዋሮቢት ሌላው መልካም ነገር በተለያዩ ዞኖች የሚገኙ እስረኞችን በተመሳሳይ ቀን መጠየቅ መፈቀዱ ነው፡፡ ስለሆነም በዞን አንድ እና በዞን ሦስት የሚገኙ ሦስት እስረኞችን ማለትም ናትናኤል ያለምዘውድ፣ ስንታየሁ ቸኮል እና ፋንቱ ዳኜን አስመዝግበን ገባን፡፡

መጀመሪያ የገባነው ዞን አንድ ወደሚገኘው ናትናኤል ያለምዘውድ ነበር፡፡ ናቲን አስጠርተን እስኪመጣ ትንሽ ደቂቃዎችን በትዕግስት መጠበቅ ነበረብን፡፡ ናቲ ስስ ማልያና ቁምጣ ብቻ ለብሶ ከእርቀት ሲመጣ አየነው፡፡ አለባበሱ የሸዋሮቢትን ሙቀት ያገናዘበ መሆኑ ነው፡፡ ከሁለት ወራት በኋላ ስላየሁት ደስ ብሰኝም የታሰረበትን ምክንያት ሳስብ ግን ወዲያው ስሜቴ መረበሹ አልቀረም፡፡ ናትናኤል ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም መንግስት የአይኤስ የሽብር ድርጊትን ለማውገዝ በጠራው ሰልፍ ላይ በመንግስት ላይ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞውን ስለገለጸ ከ3 ዓመት በላይ እስር የተፈረደበት የህሊና እስረኛ ነው፡፡ ሰው ወንድሙ በሽብር ቡድን ስለታረደበት በተሰማው ቁጣ ምክንያት መንግስትን ‹‹ሰደበ›› ተብሎ ይህን ያህል እስር ቅጣት ይፈረድበታል፡፡
ናትናኤል ያለምዘውድ ጋር ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ስለጤንነቱና እዚያ ስላለው አያያዙ ለደቂቃዎች አወራን፡፡ በተለይ በቅርቡ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ሸዋሮቢት ተገኝተው ከጠየቁት በኋላ በእስር ቤቱ አስተዳደር የደረሰበትን ጉዳይ ሲያወጋን የሚጠበቅ ቢሆንም እኔና ጓደኛየ መገረማችን አልቀረም፡፡ ‹‹እነ ይልቃል ከመጡ ወዲህ ቢሮ አስጠርተው‹አርፈህ ብትታሰር ይሻልሃል› ብለውኛል›› አለን ናቲ ሳቅ እያለ፡፡

ናትናኤል ጋር የነበረንን ቆይታ አሳጥረን ዞን ሦስት ወደሚገኙት ስንታየሁ ቸኮልና ፋንቱ ዳኜ ማምራት ነበረብን፡፡ በተለይ በዚያው ዕለት ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ ትራንስፖርት እንዳንቸገር በማሰብ ቆይታችንን ማሳጠር ግድ ይለን ነበር፡፡ ዞን ሦስት ልንገባ በር ላይ ስንደርስ በድጋሜ ካልሲ ማውለቅን ያካተተ ጠበቅ ያለ ፍተሻ ተደረገብን፡፡ ፍተሻውን አልፈን ስንታየሁንና ፋንቱን አስጠራን፡፡ በተመሳሳይ ከእነሱም ጋር ስለጤንነታቸው ከጠየቅን በኋላ ‹‹እንዴት ነው የሸዋሮቢት የእስር ሁኔታ?›› አልናቸው፡፡ ግራና ቀኝ ያሉ ፖሊሶች ጆሯቸው ሲቆም ይታወቀናል፡፡ ስንታየሁ ‹‹ከፍተኛ የመረጃ ጥማት አለብን፡፡ ያው በኢቲቪ ‹ቶርች› እንደረጋለን›› ብሎ ፈገግ አለ፡፡ ፋንቱ በበኩሉ እነ ይልቃል ጠይቀዋቸው ከሄዱ ወዲህ የእስር ቤቱ አስተዳዳሪዎች እንደተከፉና ልክ እንደ ናትናኤል ተጠርተው ‹‹አርፋችሁ ታሰሩ›› መባላቸውን ነገረን፡፡ በነገራችን ላይ ስንታየሁ ቸኮልና ፋንቱ ዳኜም ከሚያዝያ 14ቱ ሰልፍ ጋር በተያያዘ የተፈረደባቸው ናቸው፡፡

ከሦስቱም እስረኞች ጋር የነበረን ቆይታ በጊዜና ባለው የጸጥታ ሁኔታ ባይገደብ ብዙ ጉዳዮችን ባወጋን ነበር፡፡ አንድ ሁሉም በተመሳሳይ የነገሩን ጉዳይ ግን በድርቁ ምክንያት ያደረባቸውን ስጋት ነው፡፡ ‹‹ዝናብ የት አለ!? ሁለት ጊዜ ብቻ መሰለኝ እስካሁን የዘነበው፤ ዝናብ የለም›› ነበር ያለን ናትናኤል፡፡ ‹‹ሸዋሮቢት ዝናብ የለም…ያልታደለ ገበሬ ሊጎዳብን ነው›› በማለት ስንታየሁ በትካዜ ተውጦ ነግሮናል፡፡ እኛም በጉዟችን ወቅት አብረውን መኪና ውስጥ ከነበሩ ሰዎች የተረዳነው ይሄንኑ ነው፡፡ ከተማዋ ደረቅና ወበቃማ አየር ነው የሚነፍስባት፡፡ በእርግጥ ከሸዋሮቢት ወደ አዲስ አበባ በተጓዝን መጠን የዝናቡ ሁኔታ የተሻለ መሆኑን አይተናል፡፡ ዳሩ ግን ከሸዋሮቢት ወደ ሰሜንና ሰሜን ምስራቅ ያለው ሁኔታ አስጊ መሆኑን ነው የተገነዘብነው፡፡
የሸዋሮቢት ቆይታችን አጭር ነበር፡፡ ቢሆንም ግን የእኛ እዚያ መገኘት ለወዳጆቻችን (ለግፍ እስረኞች) ምን አይነት ስሜት እንደፈጠረ በማየታችን በጉዟችን ደስተኞች ነን፡፡ በነገራችን ላይ የሸዋሮቢት እስር ቤት ፖሊሶች አዲስ አበባ ቃሊቲና ቂሊንጦ ካሉት ጋር ሲተያዩ ብዙ ልዩነቶች እንዳሉ አስተውለናል፡፡ የሸዋሮቢቶቹ ቅንነት ይታይባቸዋል፡፡ ፍተሻ ሲያደርጉም ሆነ መረጃ ሲጠየቁ በጎነታቸው አብሮ አለ፡፡ ስራቸውን በአንጻራዊነት ሰብዓዊነት በተላበሰ ሁኔታ ሲያከናውኑ አይተናል፡፡ እናቶች የተሸከሙትን ስንቅ ተቀብሎ በመሸከም እስከ መጠየቂያው ቦታ ያደርሳሉ፡፡ ለጠያቂ ተገቢውን ክብር ይሰጣሉ፡፡ ለዚህ መልካም ስራቸው (ጨዋነታቸው) ማመስገኑም ተገቢ ነው፡፡ ዝዋይ፣ ቃሊቲና ቂሊንጦ (ሁሉም ባይሆን) የሚያመናጭቁን ፖሊሶችም ከሸዋሮቢቶቹ ቢማሩ አይጎዳቸውም፡፡

ለማነኛውም፣ የተቃውሞ ድምጽ የሚያሰሙ ዜጎችን ማሰሩ ለውጥን አያስቀርም፡፡ ስለ ነጻነት ዋጋ የሚከፍሉም ድካማቸው ከንቱ አይሆንምና ብርታቱን ይሰጣቸው ዘንድ እመኛለሁ፡፡ ወዳጆቼ! ከሸዋሮቢት ወደ አዲስ አበባ በአካል ስመለስ መንፈሴ አብሯችሁ ቀርቷል፡፡
በርቱ!!

ግዱን ለመጣል ቅርንጫፉን መመልመል –ይገረም አለሙ

$
0
0

በሀገራችን ጥበበኛ ዛፍ ቆራጮች አሉ፡፡ከርዝመቱ የውፍረቱ, ካዳገበት ቦታ ጠባብነት፣ የቅርንጫፎቹ ብዛት፣ የሚያሳፈራውን ዛፍ አንድም ጉዳት ሳያደርሱ እንዳልነበረ ያደርጉታል፡፡ ቆረጣውን ለመጀመር ዛፉ ላይ ሲወጡ ተመልክቶ እንዴት ተደርጎ ያለ ሰው ፍጻሜውን ሲያይ አጀኢብ ማለቱ አይቀርም፡፡ በስራው የተካኑት እነዚህ ባለሙያዎች በቅድሚያ ዛፉንና ዙሪያውን በደንብ ያጠናሉ፡፡ ከዛም ከአናት ይወጡና ተራ በተራ ቅርንጫፎቹን በመመልመል ግንዱን መለመላውን ያስቀሩታል፡፡ በመጨረሻም ግንዱን ለመጣል ያላቸውን ቦታ ይገምቱና ከላይ ጀምረው በመጠን በመጠን እየቆረጡ ከአሳነሱት በኋላ ከስሩ ቆርጠው ይጥሉታል፡ አንድም የቤት ጣራ ላይ ጉዳት ሳይደርስ፡፡

የፖለቲካው ትግል ሰላማዊም ይሁን ሁለገብ በዚህ ስልት መካሄድ ያለበት ይመስለኛል፡፡በቀጥታ ግንዱ ላይ አተኩሮ የሚደረግ ትግል ጉዳቱ ያመዝናል፤ግንዱ መውደቁ ላይቀር በመውደቁ በራሱ የከፋ አደጋ ያደርሳል፡፡እናም አደጋውን ለመቀንስ፤መስዋዕትነቱን ለማሳነስ ብሎም ውጤቱን አስተማማኝና ዘላቂ ለማድረግ ግንዱንና ቅርንጫፎቹን ለይቶ ማወቅ፤የቅርንጫፎቹን ብዛት ውፍረትና ርዝመት ማጤን ከዛም እቅድ አውጥቶ የአፈጻጸም ስልት ነድፎ ተግባራዊ ማድረግ ይበጃል፡፡

ወያኔ ይህን ስልት በራሱም ውስጥ በተቀዋሚዎችም ላይ በሚገባ ተጥቅሞ ውጤታማ ሆኖበታል፣ ወያኔ ብቻውን ባይሰራውም ደርግ መጨረሻ ሲወድቅ ኮረኔል መንግሥቱ ብቻቸውን ነበሩ፡፡ ከጠላትም መማር ብልህነት ነውና ጥቂቶቹን እንመልከት፡፡

1-ወያኔ ስልጣን በያዘ ሰሞን አዲስ አበባ ከተማን ያጥለቀለቀ የተባለ ሰላማዊ ሰለፍ ያካሄደ ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ህብረት የተሰኘ ፓርቲ ነበር፡፡ይቺ ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም የሚለው ወያኔ የቤት ስራውን ሰራና የፓርቲውን ሊቀመንበር አቶ ጸጋየን አሰረ፡፡ ለካንስ የአቶ ጸጋየ ቅርንጫፎች በወያኔ የቤት ስራ ተመልምለው ከግንዱ ተለያይተው ኖሮ ለምን ታሰሩ ብሎ የሚጠይቅ ይፈቱ ብሎ የሚጮህ አንድም የአመራር አባል ሳይታይ ቀረ፡፡ እንደውም እነርሱ በስልጣን ሽኩቻ ተጠመዱ፡፡ አቶ ሙላቱ ጣሰው (  በቅርብ ግዜ አንድነት ፓር ውስጥ ነበሩ) ሊቀመንበር ቢባሉም ፓርቲው ስም ብቻ ሆኖ ኖሮ በምርጫ 97 ዋዜማ አከተመ፡፡ አንድነትን በምርጫ ቦርድ የተሸለሙት አቶ ትእግስቱ አዎሉ የዛ ፓርቲ አመራር አባል የነበሩ ናቸው፡፡

2–የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት(መአህድ) ተመስርቶ በአጭር ግዜ ከተማ ከገጠር ተንቀሳቀሰ፡፡ ሳይቃጠል በቅጠል ያለው ወያኔ ፕሬዝዳንቱን ፕ/ር ዓስራት ወልደየስን በሆነ ባልሆነው ፖሊስ ጣቢያ እያመላለሰ በውስጥ ቅርንጫፎቹን የመመልመል ስራውን ሲያጠናቅቅ አንደዛ የገዘፈ ፓርቲ ፕርዝዳንትን ያለምንም ኮሽታ  ወህኒ አወረዳቸው፡፡ ከዛም ምክትል ሊቀመናብርቶቹ አንዱ ለቀቁ አንዱ ሀገር ጥለው ወጡ፣ መአህድም በቀኝ አዝማች ነቅአጥበብ እጅ ላይ ሆኖ በደህንነት ሹሙ ክንፈ የሚመራ ፓርቲ ሆኖ  አንድ ቀን ለይምሰል አንኳን አስራት ይፈቱ የሚል ሰላማዊ ሰልፍ ሳይጠራ አስራት በወህኒ ማቀው ሞቱ፡፡

3–ወያኔ ሳያስበው በድንገት የተፈጠረውና በሙጫ የተጣበቁ ናቸው የትም አይደርሱም ብሎ የናቀው ቅንጅት በምርጫ ካርድ ያደረሰበትን ሽንፈት በጠመንጃ ሀይልና በአሜሪካ ዲፕሎማሲዊ ድጋፍ ከቀለበሰ በኋላ ዳግም ሽንፈት ላለማየት የቅንጅትን መንፈስ ለማጥፋት ሲጣጣር ወ/ት ብርካን ሚደቅሳ ከእስር መልስ የቅንጅትን ቤተሰቦች አሰባስባ የቅንጅት ወረሽ ነን ብላ አንድነት የተሰኘ ፓርቲ መስርታ ብቅ አለች፡፡ ከሀገር ቤት አልፎ አውሮፓና አሜሪካ የሚኖረው የቅንጅት ደጋፊ በአንድነት ደጋፊነት ተሰለፈ፡፡ አንድነት በዚህ ከቀጠለ ምን ሊከተል እንደሚችል ግልጽ ነበርና ወያኔ በጎቹ እንዲበተኑ እረኛውን ምታ ብሂሉን ተግባራዊ ለማድረግ ግዜ አላጠፋም፡፡ብርቱካንን ከእስር የተፈታሽበትን ቅድመ ሁኔታ ጥሰሻል አስተባብይ እያሉ እያዋከቡ ጎን ለጎን ቅርንጫፎቹን የመመልመል  ስራቸውን ቀጠሉ፡፡ በመጨረሻም ይሄ ጉዳይ የሊቀመንበሯ የግል ጉዳይ ነው የፓርቲ ጉዳይ አይደለም የሚል ማረጋገጫ ከአመራሩ ሲያገኙና ብርቱካን ብቻዋን መቆሟን ሲያረጋግጡ አንደ ወንበዴ ከመንገድ ጠልፈው አሰሯት፡፡ የአንድነት አመራሮች በምርጫ 2002 ሲወዳደሩ  ለአፋቸው አንኳን በምርጫ የምንወዳደረው ሊቀመንበራን ከተፈታች ነው ለማለት ሳይደፍሩ ቀሩ፡፡

4-ሀወኃት በተሰነጠቀበት ወቅት አፈንጋጭ የተባለው ወገን ካድሬውም ታጋዩም በእጃችን ነው ብሎ ሲኩራራ ይህን የተረዱት መለስ ርምጃ ለመውሰድ በቅድምያ ግንዱን ከቅርንጫፎቹ መለየት ነበረባቸውና መቀሌ ላይ የካድሬ ስብሰባ ጠሩ፡፡ አፈንጋጭ የተባሉቱ የተደገሰላቸውን ሳያውቁ አቶ መለስ ባዘጋጁዋቸው ሰዎች በሰማእታት እየተባሉ እየተለመኑ ያንን መድረክ ረግጠው ወጡ፡፡ ይህም የአቶ መለሰን እቅድ ያሳካ ተግባር ሆነና ሲለምኑዋቸው ካድሬውና ታጋይ ተጋዳላዩ ሰማእታትን ረግጠው የሄዱ በማለት ከእነርሱ ተለየ የአቶ መለስ ደጋፊም ሆነ፡፡ እንዲህ ሆነና አቶ መለስ ሁሉንም በግላጭ ስላገኙዋቸው የሚያባርሩትን አባረሩ ሌላውንም ወደ ወህኒ አወረዱ፡፡

ብዙ ማሳያዎችን ማንሳት ቢቻልም ይበቃል፡፡ አሁን ወደ እኛ አንምጣ ግንዱ ግልጽ ነው ይታወቃል ህውኃት ነው፡፡ ቅርንጫፎቹ ግን ብዙ ናቸው፡፡ እና መጀመሪያ ለይቶ ማወቁና ደረጃ ማውጣቱ ዋና ስራ ነው፡፡ ከዛ ደግሞ እንደየደረጃቸው እንደ ማንነት ምንነታቸው  ከግንዱ ለመለየት የሚያስችል ስልት ማውጣትና ተግባራዊ ማድረግ ከባዱ ተግባር ይሆናል፡፡ ለአንዳንዶቹ ከግንዱ መለየት ህልውናቸውን ማጣት ሆኖ ስለሚሰማቸው እነዚህ  ፤ላይ ግዜም ጉልበትም ማባከን ላያስፈልግ ይችላል፡፡ ለምሳሌ ኢህአዴግ የሚል ጭንብል ለህውኃት ያጠለቁለት ብአዴን ኦህዴድና ደኢህዴግ ቅርንጫፎች ሲሆኑ ከግንዱ ሊለዩ የሚችሉበት ምንም አጋጣሚ አይኖርም ብሎ መደምደም ባይቻልም በተቀዋሚ ወገኖች ስራና ጥረት መለየት ይቻላል ብሎ መገመት ይቸግራል፤ስለሆነም እነሱን ለመለየትም ሳይደክሙ ከግንዱ ጋር አንድ አድርጎም ሳያዩ የተለየ ስልት መጠቀም፡፡

ሊሎች ከአጋር ድርጅቶች እስከ ስመ ተቀዋሚዎች፤በጥቅም ከተያዙት በሙስና እስከተነካኩት፤ አማራጭ በማጣት ከተጠጉት በዘረኝነት ስሜት እስከሚደግፉትከቀበሌ ሹማምት እስከ መከላከያ ሰራዊት ወዘተ ድረስ ያሉት ቅርንጫፎች የነጻነት ትግሉን አላማና ግብ ተረድተው በማወቅም ይሁን ባለማወቅ እያደረሱት ያለውን ጥፋት ተገንዝበው ቢቻል የትግሉ አጋር አንዲሆኑ ካልተቻለም የጥፋት ተባባሪነታቸውን አንዲያቆሙ ማድረግ ከተቻለ ጠቃሚ ነውና  የትግሉ አንድ አካል ተደርጎ መወሰድ ያለበት ነው፡፡

ለነጻነት የሚደረገው ትግል ወያኔን ማስወገድ የሚል ብቻ ሳይሆን ሶስት ነገሮችን ያጣመረ ቢሆን ይመረጣል፤እንደሆነም ተስፋ አለኝ፡፡ለኢትዮጵያና ለህዝቧ ጠንቅ የሆነው ወያኔ ከዚህ ልክፍቱ የሚድን አለመሆኑ ሀያ አራት አመታት በተደረጉ ጥረቶች የተረጋገጠ በመሆኑ መፍትሄው ከሥልጣን ማውረድ መሆኑ ከትናንት ዛሬ የማያከራክር ሆኗል፡፡ በመሆኑም ቀዳሚውና ዋናው ጉዳይ ይህ ሲሆን ከሥልጣን መሰናበቱ ላይቀር በአጉል  መንፈራገጥ ጉዳት አንዳያደርስ ማድረግ ደግሞ ሁለተኛው ጉዳይ ይሆናል፡፡ ሶስተኛው እንደ ቀደሙት ሁለት ለውጦች ለዴሞክራሲ የተከፈለው መስዋዕትነት ሌላ አንባገነናዊ ሥርዐት አንዳይወልድ ከድል በኋላ አስተማማኝ የዴሞክራሲ መሰረት መጣል የሚቻልበትን መንገድ ከወዲሁ ማመቻቸት ነው፡፡

ይህ ሁሉ አንዲህ እንደሚጻፈውና እንደሚነገረው ቀላል አይደለም፡፡በተለይ ደግሞ ወያኔ ሥልጣኑን ከሚያጣ ሀገር ቢፈራርስ ህዝብ ርስ በርሱ ቢጨራረስ ደንታ የሌለው ነውና የታጋዮቹን ኃላፊነት ድርብ ድርብርብ ስራቸውንም ከባድ ያደርገዋል፡፡ስለሆነም በየትኛውም መንገድ ይሁን በማንም ከምር የሚካሄድ የነጻነት ትግል ነጻነት የሚሻውን ዜጋ ሁሉ ድጋፍ ይፈልጋል፡፡ ግንዱን በቀላሉ ብዙ ጉዳት ሳያደርስ ለመጣል አንዲቻል ቅርንጫፎቹን የመመልመል ስራም ሁሉም አንደ ችሎታና ዝንባሌው በያለበት ሆኖ ሊከውነው የሚችል ተግባር ነው፡፡ ይህ ደግሞ በምንም ሁኔታ ወያኔን የሚጠቅምና የነጻነት ትግሉን የሚጎዳ ተግባር ካለመፈጸም ይጀምራል፡፡ በዚህ አስቸጋሪና ከባድ ግን አኩሪ ተግባር ላይ በግንባር ቀደምትነት የተሰለፉ ወገኖቸ የሚያካሂዱትን ትግል የሚጎዳ ተግባር መፈጸም ግን በታሪክም በትውልድም ይቅር ሊባል የማይችል ነው፡፡

ስለሆነም ወያኔ በስልጣን እንዲቆይ የሚፈልገውና የማይፈልገው ከተለየና ከታወቀ በኋላ፤የማይፈልገው ወገን ከላይ የተጠቀሱት ሶስት  ጉዳዮች ማለትም ወያኔን ከሥልጣን ማውረድ፤ሲፈራገጥ ጉዳት እንዳያደርስ ማድረግ፤ከድል በኋላ አስተማማኝ ዴሞክራሲዊ ሥርዓት መመስረት የሚያስችል መደላድል መፍጠር ላይ እየተነጋገረና እየተጋገዘ የድሉን ቀን ማሳጠር አንጂ ምክንያት እየፈጠሩ ተለያይቶ መቆም የወያኔ ቅርንጫፍ መሆን ነው፡፡

Comment

 


ሥህነ –ቤዛ! ቅኝተ –ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ! (ሥርጉተ ሥላሴ )

$
0
0

15.08.2015 /ሲወዘርላንድ –  ዙሪክ/

ምዕርፍ ሁለት ….

Birhanuእንደ መግቢያ በር – እንዴት ናችሁ የኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ? የአንድ ሃሳብ ዕድሜ ዘላቂነት ሆነ ታላቅነት መለኪያው ዬተግባሩ ሥነ -ምግባሩ ብቻ ነው። አቅጣጫ ቢሱን፤ መደምደሚያ ቢሱን፤ ማለቂያ – አልቦውን እስከ ትብትባዊ ዝክትንትሉ፤ እንዲሁም በብዙ ቋሳ የዘለበውን ችግር –  እስከ ጉስቁሉ ጥንዙል ተስፋችን፣ እንደአለ በሙሉ ፈቃደኝነት፤ ለዛውም ከነገመናው ለመሸከም መፍቀድ ብቻ ሳይሆን፤ መፍትሄ አመንጭነቱንም መሬት ያሳያዝ፤ በተጨማሪም ኃላፊነት የሚሰማውን ጥንቁቅ ብልሃትን የሰጠን፤  አቤቱታችነን በተጠያቂነት – ያዳመጠ፤ በነጠፈ ሌማት የራህብ መና ላዘጋጀልን፤ በምድረበዳ የጥማት ማርኪያ የምንጭ ውሃ ያፈለቅልን ፈጣሪ አምላካችን ልዑል እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን – አሜን!

እንዲህ ሆኖ ነበር። ያን ክፉ ዘመን ይቋቋሙ ዘንድ ቤተ – እስራኤላውያን አምላካችን ያዘጋጀላቸው የሚገዛ አለቃ አልነበረም የነብያትን መሪነት ነበር መርቆ የሰጣቸው። እኛስ በእግዚአብሄር መንበር ፊት እንደ እስራላውያን አምሳል አይደለንም? ፈጣሪ አምላክ – አያዳላም። በፈጣሪያችን ዘንድ ዕንባችን እኩልነት አለው። ከሰማዩ ችሎቱ ፊት – ለፊት ለመቆም ሙሉ ዕውቅና – አለው። በዛ የሱራፌል ዙፋን አቤቱታው ለመደመጥ ሙሉ አቅም አለው።

ያለንበትን የረረበት ዘመን ፈጣሪያችን  – ያውቃል። ጽናታችን ሊፈትን ነው። ከመከራው በስተጀርባ ትልቅ ክብር አለና። ይህ ዘመን ……  ሽምግልና የታሰረበት – ዘመን! መፍትሄ የተገነዘበት – ዘመን። ዬእርቅ ጥያቄ የተወገረበትና  የተቀጠቀጠበት ጠቀራማ ዘመን ነው። የሃይማኖት አቨው እንደ አልባሌ እቃ የተወረወሩበት – የተንዘገዘጉበት – ከትቢያ በታች የታዩበት ዘመነ፤ ዘመነ – ጉግ ማንጉግ … ዘመነ – ሲዖል፤ ዘመነ – ረመጥ —-

የኔዎቹ – ወገኖቼ። ምዕራፍ አንድ የምዕራፍ ሁለት ዋዜማ ነውና …. ማወራረስ እንዲቻል ምዕረፍ አንድን የከወንቡበት ፍሬ ነገር እንዲህ ይል ነበር።

„በማህሌት ደጋፊነት በትጋት ማዕለተ – ተሌሊት ሰዓታት የቆሙት የ24 ዓመታት ዬቅዱሳን የዕንባ ሱባኤ፣ ጻድቅ የዕንባ ዘጉባኤ፤  …. መልክ ያዘ። ዘመነ  – ሱባኤው በድል – ይሰክናል። ተግባርን የሚረታው በእኩል የተግባር ወቄት ቢሆንም ፈቃዱም ታትሞበታል።የኔዎቹ – የማከብራችሁ ዛሬም ውስጤ የሚሰማውን ላጋራችሁ ነውና፤ በተመቻችሁ ሁኔታ ትምረምሩት ዘንድ በትህታና ገልጬ …. መብቱም ፈቃዱም የውዶቼ ነውና የቤት ሥራውን ለእናንተው ለውዶቼ  – ልተዎው።

እርግጥ ነው  ቅዱሳን አባቶቼ የሐገሬ ዬአንድምታ ሊቀ ሊቃውንታት ትርጓሜውን ሆነ ሚስጢሩን መፍታት ሰማያዊ ጸጋ ባለቤቶች ናቸውና ይህን ለደጋግ አቨው ለአባቶቼ  ትቼ ፤ እኔ ሳይገባኝና ሳልመቸው ግን ውስጤ አስጨንቆ ያስገደደኝን እገልጸው ዘንድ የፈቀደልኝ ጌታ አምላኬን – አመሰግነዋለሁ፤ እኔ ትቢያዋና ደካማዋ የሥላሴ ባርያ ንባቡን ብቻ አንዲህ ልሂድበት። ሸበላ የመደማመጥ ጊዜ ተመኘሁ – ለክብሮቼ – ለጹሑፌ ታዳሚዎች።

በቃሉ።

„እግዚአብሄርም፣ ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፣ – ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው፣ ከእነርሱም ከእያንዳንዱ ከዬአባቶቻቸው ቤት አንድ አንድ በትር ከአለቆቻቸው ከዬአባቶቻቸው ቤት „አሥራ ሁለት በትሮች“ ውሰድ፤ የእያንዳንዱንም ሥም በዬበትሩ ላይ ፃፍ፤ „አንድ በትርም ለአባቶቻቸው ቤት አለቃ ይሆናልና፤“ „በሌዌ በትር“ ላይ ያሮንን ስም ፃፈ። እኔ ከእናንተ ጋር በምገናኝበት „በመገናኛ ድንኳን“ ውስጥ „በምስክሩ ፊት አኑራቸው።“ እንዲህም ይሆናል። „የመረጥኩት ሰው በትር ታቈጥቈጣለች።“ በእናንተም ላይ „የሚያጕረመርምባችሁን“ የእስራልን ልጆች „ማጕረምረም ከእኔ ዘንድ አጠፋለሁ።“ ሙሴም ለእስራል ልጆች ተናገራቸው፤ አለቆቻቸው ሁሉ አሥራ ሁለት በትሮች እያንዳንዱም አለቃ በዬአባቱ ቤት አንድ አንድ በትር ሰጡት፤ የአሮንም በትር በበትሮቻቸው መካከል ነበረች። ሙሴም በትሮቹን በእግዚአብሄር ፊት በምስክሩ ድንኳን ውስጥ አኖራቸው። እንዲህም ሆነ „በነጋው“ ሙሴም ወደ ምስክሩ ድንኳን ውስጥ ገባ። እነሆም „ለሌዊ ቤት“ የሆነች የአሮን በትር አቈጠቈጠች፤ ለመለመችም፤ አበባም አወጣች፣ የበሰለ ለወዝም አፈራች። ሙሴም በትሮችን ሁሉ ከእግዚአብሄር ፊት ወደ እስራል ልጆች አወጣቸው፤ „እነርሱም አዩ፤“ እያንዳንዱም በትሩን ወሰደ“ ኦሪት ዘኊልቍ ምዕራፍ 17 ቁጥር 1 እስከ 9

 

እንደ – ቃሉ!  

  • በመገናኛ ድንኳን“ ሥህነ – ቤዛ በባዕቱ ሆኖ የነፃነት ፍላጎቱ ስኬታማ – አልሆነም። ፈቃዱ አልነበረምና። ምልክት ግን ታይቷል፤ ምልክት ነውና። ተሰዶም በተሟላ ኑሮ መንፈሱ መጠለያ – አላገኘም። ከእሱ የቀደሙም ወገኖቹ በቦታው – ተገኝተውበታል። /ሳይንቲስቱም ሆነ ፕሮፌሰሩም/ ሳይቀሩ ግን ያ መንፈስ ባልተሰበ ሁኔታ መቋረጥ – ገጥሞታል። ፈጣሪ አምላካችን የሚጠብቀው ልዩ ማዕዶት ነበረው። የተመረጠ ዬቀን አገልግል ነበር። እንሆ ሌላ ሚስጢር እግዚአብሄር – ገለጠ። እግዚአብሄር የፈቀደለትና የመረቀለት „በድንኳኑ ቤት“ ብቻ ሆኖ ራዕዩን ማነጋገር እንዲችል – ነበር። ለዚህም እንዲህም ሆነ — ድንኳኑን እንደ አምላኩ ፈቃዱ መረጠ – ድንኳኗ ስንት ሰማያዊ ገድል የተቀዳበት የቀዩ ባህር ክፍለ አካል ጋር በተአምር – ተወዳጀ። በድንኳኑ ትንቢት – ተተከለ፤ ሊጸድቅ።  ….  የተለያዩ እትብታዊ ልጆቹ መገናኛ! ነገም ብሩኽ ነው። በቃሉ ስለቃሉ ለቃሉ – አትጠራጠሩ! መገናኛ ዘመን – መጣ። ዬስጋትን አንጥሽት ውሃውን የሚያፈሰው መዳህኒዓለም ነውና።
  • „በምስክሩ ፊት አኑራቸው።“ የኢትዮጵያ ህዝብና የኤርትራም ህዝብ ለዳኝነት የተሰጠው ክህሎት ብቃቱን – ይገልጣል፤ እነሆ ብዙዎቹ ቃሉን – ፈቀዱት ጥጋቸው አደረጉት። ወደዱት፤ አከበሩት። ከበከቡት፤ተከተሉት = በፍቅር ሞሸሩትም።
  • „የመረጥኩት ሰው በትር ታቈጥቈጣለች።“ ይሄው በዬደቂቃው የመንፈስ ለውጥ አብዬት ላይ – እንገኛለን። የብዙዎች ውስጥ ታጠበ – ንጹህ ህሊናን አበራከተ። የተመረጠችው ቅድሰት በትረ በሁሉም መስክ በዬደቂቃው ማቆጥቆጥ ጀመራለች እና … ከእኛ ይልቅ ብላቴናዎቹ ቀድመውን አዳመጡ – ከልብ ሆነው። ታቦሩ ላይ ሊያበራ! ዓለምም አዳመጠ – በማስተዋል ሆኖ፤ አደብ ግዙ! ፍለጋው የነፃነት ነው በማለት በዓለሙ መሪ አንደበት ተከፍቶ ማህተም – ታታመ። መንገዱ ዬነፃነት ቅኔ ነው ተብሎ ዕውቅና አገኘ። እግዚአብሄር ሲመርጥ መግቢያውንም መውጫውንም በር በቅድስና ከፍቶ ነውና።- … መንገዱ ዬቀና ነው ….. ተስፋ በዜማ ይዘምር … ራዕይ ማህሌት ይቁም፤ ናፍቆትም በሰዓታት ፈጣሪውን ያመስግን፤ ፍቅርም ድዋ ይያዝ …. የኔዎቹ – አትጣራጠሩ ስለክብሩ መገለጥ አመስግኑ እንጂ …
  • „አሥራ ሁለት በትሮች“ ከ80 በላይ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ቤተ ነገዶችን ያመልክታል …. ሁሉንም በእኩልነት መርምሯል አምላካችን። የመረጠውን ሥጦታ በመረጠበት አምላካዊ ሚዛኑ እንሆ – ቀብቶታል። ፈጣሪያችን ከሁሉ በላይ ንጡህ ልቦናን፤ መንፈሱ ቤተመቅደሱ ሊሆን የሚችለውን እንደ ትእዛዙ የፈቀደውን ቅን አልቆ በሰማያዊ ሥነ ጥበቡ ይመርጣልና ….. እንሆ በፈጣሪ ቃል በፈተና የነጠረው ወርቅ ያበራል – ያነጋል …. መርሁ እግዚአብሄርም ለእኔ ተውሉኝ ብሎታል። የኔ ነው ብሎታል፤ ከዬነገዶቹ አልተቆጠረም ለማዕከላዊ እርስተ መንፈሱ ብቻ የታጨ ስለሆነ። ለታላቅ ተልዕኮ – ለኢትዮጵያዊነት!
  • „የሚያጕረመርምባችሁን“ ከቃልህ በመራቃችን ብቻ ማስተዋሉን አዘገዬነው እንጂ አዎን! ነጠል ብለው ተለይተው ወጠተው ወገኖቻችን ሲያጉረመርሙ – አይተናል። እነሱም የእኛ ናቸውና ምህረትህ ጎብኝቷቸው የቃልህን ድምጽ ያደምጡ ዘንድ አንተ – ፍቀድላቸው። ለንሥኃም አብቃቸው። ዕዝነ ልቦናቸውን በምርቃት – ክፈትላቸው። እኛም የቂም በቀል ደጀን አንዳንሆን ልቦናችን አቤቱ! – ጥረግልን። የጨለመውን ሥነ -ልቦናችን አንጋልን። አቤቱ! በቃችሁም በለን።
  • „ለሌዊ ቤት“ ከቤተ ነገዶች ለእረኝነት የተመረጠው አንዱ ቤተ – መዳፍ ብቻ መሆኑን – ይሄው አዬን፤ በድረጊት ሲከበር ተመለከትን፤ ፈቃደ እግዚአብሄር ነውና አብሮነት በአኃቲነት ዕርገት አደረገ። በዚህ መሥመርም የቆሸሸ ስብዕና ያልታዬበትን ንጡህ መንፈስ ቤቱ አደረገ – ፈጣሪው ….. መረቆታልና እረኛውን፤ ስኬት መንገዱ ይሆናል፤ ለእኛ ብቻ አይደልም እንሆ አፍሪካም …. ምስብክህ …. አፍሪካኒዝምን – ያልቃል። የቆዬ ሰው ይይው። እንደተመኘነው – ይሆናል። ጧፉ ይበራል በእማዋይሽ – አፍሪካ። – ያበራል – ይመራል – ተስፋችን – ይሠራል።
  • „ ማጕረምረም ከእኔ ዘንድ አጠፋለሁ።“ ጕርምርታው ጽንስ ጎልቶ የወጣው፤- – የተነሳው በአዋጅ ተናጋሪዎች በመለከት ቤተሰቦች ላይ – ነበር። ሳሎኑም መኝታ ቤቱም ኮሪደሩም ከማህል አስከ ጠርዙ እነዛው አውታራዊ ዘርፎች ነበሩ። በአንድም በሌላም መንገድ። ህውክቱ ሰላምን ጠጥቶ ችግሩ ፍቺ አግኝቶ ካለ ይግባኝ በአሸናፊነት የሰከነውም በዕወጃው ቤተ መንበር ላይ – ነበር። ጉርምርምታውን በግነት በለው እያለ – „አዲስ ድምጽ“ ጀመረው፤ ከዛው ላይም ምህረት ወርዶ እንደ ንሥኃ አበበ እያለ ደግሞ እንሆ – አዳመጥን። ተመስገን አንተ የሰማይና የምድር ንጉሥ አልን። የጉዞውን መልካም ምኞትም ተከታዩ ቀላጤ – ብራና ላይ ተነበበ፤ አሁንም የሁሉን ጌታ አንተን – አመሰገን። ሁሉንም የምሥራች አዳመጥን – ሐሴትም አደረግን።

እንዲሁም በልዕልት ሀገራችን በኢትዮጵያ ፈቃደ እግዚአብሄር ታምሩን ይገልጥ ዘንድ ከሹክሽክታ ወጥቶ የተመረጠችው በትር ታቆጠቆጥ – ታንቆጠቁጥም ዘንድ የመጀመሪያው ጥቁር አሜሪካዊ ዬተከበሩ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን አነሳስቶ ለምክንያት በምድሯ ወስዶ በምድሯ ጥልቅ ታምሩን – ገለጠ። እኛ ግን ከፈጣሪ ገድለ ረቂቅ ምርቃት ውጪ ነበርን።  በዕወጃ  ጉባኤ በኢትዮጵያ መሬት ከሁሉ የቀደመው ጥያቄ የታወከው ጀውጃዋ መንፈስን አዝሎ ሊያዝል ፀላዬ ሰናይ ሲነሳ ከዛው ላይ በሽንፈት – ከነሸንኮፉ በዓለም አዳባይ – ከሰመ – ምኞት መቃበር ሲሰምጥ – አስተዋልንበት።

የፈጣሪ ጥበብ እንዲህ ነው። ከተወረወረ ቀስት እንድን ዘንድ ቃሉ አናገረ …. ቃሉ አሸናፊ ሆነ። ቃሉ ገዢ መሬቱን ተቆጣጠረ …. ቃሉ ነገን አናገረ …. ተመስገን!

ታመርህ ምንኛ ድንቅ ነው። እረኛው አምላክ ወደ ጠራው የሱባኤ ድንኳን የተጓዘው ሰሞናቱም ይሄው የታምራትህ መገለጫ ወቅታት ነበሩ፤ የዓለሙ መሪም እረኛው ደልቶት ከሚኖርበት ቦታ ተነስተው እረኛው ባዕቱን በግፍ ወደ ተቀማበት እትብቱ ከተቀበረበት ቦታ – ተገኙ። ረቂቅ ታምሩ እንዲህ ነው። የታላቋ ሐገር የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ዬኢትዮጵያዊነት ቤተሰብነታቸውን በልበ ሙሉነት – አረጋገጡ። በእምቤት ኢትዮጵያ … ትንግርት ተመሳጠረ፤ ገድል በቅኔ – ተቀዳ። …. እያንዳንዷ ቀንና ጉዞ በሚስጢር የተቃኘች የቅኔ ቤተኛ ሆነች። የሆነው ሁሉ ለምክንያት ነበር። ስለ ተከደነውን ሲሳይ ስለ ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ ዘለግ ብለን በአርምሞና በተደሞ እንድናስተውል – ሆነልን። ስለሆነም ጥበቃው የላይኛው ነውና በቅቶ ግን ተከድኖ የኖረው ቀለም የሥርዬት መንገድ እንሆ። ይቻላል በሚያስችለው አምላክ። የድህነት ትልም ነው። የፍውሰት መርኽ ነው። መርኹ ደማችን እንሆ – ሆነ።

አሁንም ሰላምንና ፍቅርን – ይሰብካል። „ግራ ቀኙ የኔ ናቸው አለ“ ለዚህ ያበቃን አምላክ ክብር ምስጋና ለእሱ ይሁን። ስጋት ያለባችሁ ወገኖቼ አቶ እገሌ፤ ጄኒራል እግሌ፤ የውቅያኖስ ያህል ብራናው በቀለም ቢለቀለቅ ከዚህ ከጸደቀው ታዕምር ጋር መቀባትን የማጉበጥ አቅም – የለውም።  ህውከት ፈጣሪ ወጀቦች ማረፊያ ብትን አፈር – የላቸውም። ይባናሉ። በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያዊነት በደጅ ጥናት ነው የሚገኘው። የሸፈተው ልብ ሁሉ የሚመለሰብት ጊዜ ነው ወደ ውበቱ። ኑ እዩ ኢትዮጵያዊነት ሲያበራ! በብርሃኑ መንገድ ሁኑበት። በውስጣችሁ በክብር ኑሩበት! አንድዬን – እመኑ! ድሉ ለተመረጠው እረኛ እሱ አዶናይ – ሰጥቶታል። ይህን ትብትብ እጅግም ውስብስብ ፈተናዎችን ለመሸከም የመከራ ዘመን ለመታደግ፤ ይህን የውርዴት ዘመን ይፍታህ ለማለት መመረጥም – ነብይነት ነው። ሐዋርያነት ነው። ሰማዕትነት ነው። ሃገሬ መከራዋ ብዙ ነው፤ ግን ቁልፍ አለኝ ብሏል – አማኑኤል። የተመረጠው ቀኑን ቀን ማድረግ የሚችለው በተሰጠው የፈጣሪ ምርቃት ብቻ ነው። አቅሙ ከሰማዬ ሰማይት ነው የሚቀዳው። ከገሃዱ ዓለም ሳይሆን ከመንፈሳዊው ቅዱስ አለም። እሱም እራሱ ሱባኤ ይያዝ – ሥጦታውን ያክብር። ፈጣሪውን ተንበርክኮ ያመስግን። መጠነ ሰፊውን ፍቅር ይሰነብትለት ዘንድ – አምላኩን – ይማጠን። ፈጣሪው መንገዱን ጠርጎለታልና …. የተሰጠውን በረከቱን አብዝቶ ይጠንቀቅለት። ከምድር ሃብታት ሁሉ እጅግ የላቀ ነውና የዕንባ መዳህኒትነት – በፍቅራዊነት (Loveism) ሲሞሸር።

  • „ለሌዊ ቤት“ ቤተ መዳፍ ተመረጠ። ይህ ቃለ ምህዳን የሆነው የቤተ – መዳፍ በትር አቈጠቈጠች፤ ለመለመችም፤ አበባም አወጣች፣ የበሰለ ለወዝም አፈራች ይላል ቃሉ።። ጥርጣሬን የሚፈውሰው የመዳህኒት ቃል ነው። ሥጋትን የሚበትነውም እሱ ቃሉ ነው። መሻሪያው ቃሉ ነው። ልሳናችን ሳይሆን ልባችን ለፈጠረው ፈጣሪ – ከሰጠነው። ቢያንስ ለመዳህኒተ – ዓለም ቃለ ወንጌል መንፈሳችን ካላሸፈትናው። እባካችሁን! በፈጣሪ ሥጦታ አትቅኑ! የድርሻችሁን የተገባችሁን በልካችሁ ሰጥቷችኋል ፈጣሪያችን። – ፈቃዱን አትተላለፉ ….. የኔዎቹ ውዶቼ።
  • „በነጋው“ ወገኖቼ አስተውለን እንዬው ይህን ቃል። በቃሉ መሃከል ጠባቂ ዘቦች አሉ። ጠበቂ ዘቦች ‚በ‘ እና ው‘ ናቸው። በመሃላቸው ያለው ኃይለ በትረ ሥም „ነጋ“ ነው። ተልዕኮውም ጉምን ገፎ – ምህረትን፣ ልዩነትን እረትቶ እርቅን፤ ጥላቻን ንዶ – ስምምነትን፤ ቂምን ሸኝቶ – ሥርዬትን፤ ጨላማን ገፎ የትውልድን ተስፋ ማብራት አዎን ሊያነጋ ….. ነው፤ ፍቅርን አውጆ ተስፋን – ሊያሰብል። በዚያ ወቅት አሸናፊው ቃሉ ብቻ ነው። ድሉ የባለቃሉ የህዝብ ልጅ ነው። „በ ሆነ ው“ አብረውት የተጓዙት ምርጦቹ ናቸው። እነሱም የተመረጡ ዮሴፎች – ናቸው። ጠባቂዎቹን ሳይቀር መርጦለታል። ሥህን – ቤዛን የእኔ ነው ብሎታልና ለአደራ ይበቁ ዘንድ በፀሎት – ይትጉ። የረገጣት መሬት ሁሉ ብሩክ ናት። የተጠጋት ትልም ለምለም ናት። የጀመራት ተከታይ ፍጻሜም አላት።
  • „ሙሴም በትሮችን ሁሉ ከእግዚአብሄር ፊት ወደ እስራል ልጆች አወጣቸው፤“ ሁሉም የተሰጠውን የተፈቀደለትን ብቻ ይከውን ነው ቃሉ የሚለው። ድርሻ አለን ሁላችንም። የድርሻችን ደንበሩን የወሰነው የሰማዩ ዳኛ አምላከችን ብቻ ነውይህ ሰው ሰራሽ – አይደለም። ምድባችን ሰማያዊ ነውና። በዬተመደብንበት አቅማችን ለጥሪያችን – እናውል።
  • „እነርሱም አዩ፤“ አዎን! አቤቱ አምላኬ ሆይ! እኔም ባሪያህ እነሆ በአንተ ፈቃድ ዓይኖቼ ከበፊቱ በበለጠ ጉልላታማና ብቁ አድማጭ ሆነው ቦግ ብለው – ተገለጡ፤ ለዐይኔ ውሃዎች ለጠረናቸው ሆነ ለጥራታቸው በድርጊት የተባን ተስፋን – ሸልምካቸው። አቤቱ ጌታዬ ሆይ! – አመስግንሃለሁ። አባ ቅንዬንም ይምራሽ ብለህ ከነ መክሊቱ ስልፈቀድክልኝ አቤቱ – ሰገድኩልህ። የኢትዮጵያዊነትን መዳኛ እግዚአብሄር ሰጥቶኛል። አምላኬንም ክብሬን ስለሰጠኝ ደግሜ – እንሆ አመስግናለሁ። ፍለሰቲትን ሆነ ተከታትዬም ፆመ ጽጌንም ሥጦታውን – አክበርበታለሁ። ለዛሬም ብቻ ሳይሆን ለወደፊትም የተመረጠው „ባለ ቅብዕ በትር“ ብቻ ነው። ከዚህ በኋላ ሌላ መዳህኒት እኔ አልጠብቅም። ሥህነ ቤዛን ዘመንና አምላኬ ሰጥተውኛል እና። ተስፋዬን ከ24 የህልም ጉዞ  በኋላ – በዕውን አግኝቻለሁ። „ጊዜ ገቢረ ለእግዚአበሄር“ እንሆ አሁን ሆነ። አዎን ሆነ። ይቻላል ሆነ። ማድረግን ሆነ። ነፃነት የራባቸው አንስት እህቶቼም በተሰጣቸው ድርሻ ብቻ – ይትጉ! ተግተውም ጥላ ከለላ ሆነው – ይርዱት! ወንድማቸውን –  ይገዙትም። አባታቸውን አለንልህ ይበሉት። አማንያን ተግተው በፀሎት አጥር ይጠብቁት ዘንድ በትህትና እኔ ሎሌያቸው ዝቅ ብዬ አሳስባለሁ። እግዚአብሄር ይመስገን። አቤቱ መዳህኒታችን የተሰደዱ መንፈሶችን ሁሉ ዬቃልህ ሚስጢር፤ የፈቃድህ ትንግረት ጉልበት አለውና – ይሰብሰብልን። አሜን!
  • „አንድ በትርም ለአባቶቻቸው ቤት አለቃ ይሆናልና፤“ ሥህነ – ቤዛ የቃለ እግዚአብሄር ሥጦታ ነው። ሁሉም ነገር እስከ ዛሬ የሆነው ለምክንያት ነበር። „ስለምን ቅንጅት ተመረጠው ህዝቡን መልሰው እንግባ አንግባ ብለው ጠዬቁ ወዘተ… ፤“ እንደ ትልቅ ወንጀል ዛሬ ድረስ እንደ አዲስ የሚነሳሱ ነገሮ አሉ ነው። የመርኽ ጉዳዮች ነበሩ። በጠጨማሪም ያ ፈቃደ እግዚብሔር ምልክቱን ለማሳየት ብቻ ያመሳጠረበት ሂደት ነበር። የቀደመውን የመንገድ ጠራጊውንም የፍላጎት እትብትንም በማስተዋል እዩት። የፍቅር ሚዛኑ – የተቀባይነት ልኩ – የፈተና ተቀባይነት አቅሙን –  በዬትኛው በትር ላይ እንደሆነ ሚስጢሩን ይገልጥበት ዘንድ የሆነ ነው። እርግጥ አይደለም ያን ጊዜ አሁንም ጥቂቶችች ሊያሰተውሉት – አልፈቀዱም። ልባቸውን – ስለቆለፉት። ክብር „ከእኔ“ ይጀምር፤ ተቀባይነትም በእኔ ይጽደቅ የሚለውን መታበይ ተሸናፊ ማድረግ – ስላልቻሉ። እሩቅ ከማሰብ፤ የማይቻልን ከመተለም በፊት ከግንባር ካለው መጀመር ብልህነት ነው። እሱም ራስን ማሸነፍ። ሁሉም ለምክንያት ነበር፤ አፍላነቱን በምልሰት ጉልምስናውን በተደሞ ሁሉ ለመልካም ነበር።
  • ሌላም ሚስጥር ተቀና። የዓለሙ መሪ በቅኔ ዘጉባኤ ቅኔውን ዘረፉልን የተከበሩ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የዚያን የቅኔው ንጉሥ የብላቴ ጌታ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ትንቢት ተቃኙት፤ ጋሼ ጸጋዬ እኮ ነብይ ነበር። ለዚህም ነው ለእኔ ህይወት አባቴ እጬጌዬ – የሆነው። የቅዱሱና የሰማዕቱ አባት የአቡነ ጴጥሮስ „ምድሪቱ ለፋሽስት አንዳትገዛ ግዝት“ ሰማዕትነት ጉባኤም በሰሞናቱ ነበር በሃምሌ 22 ቀን ነበር። አሁንም ድህነትን መሬታችን ጠይቃለች! የጸሐፊ ምስብዕከ ወርቁ „ዴርቶ ጋዳ” ራዕያዊ ጥበብ፤ የቅኔው ዕንቡጥ ዬቴዲ አፍሮ „ፍቅር ያሸንፋል” አንዲህ ቀስተ ዳመና ላይ በክብር – ሰከነ። ተባረከልን። የቀስተዳመና ፓርቲ መሥራች  መርኹ ትንቢቱን እንዲህ – አገናኛው። የመክሊት መገናኛ። የቅኔ ትንቢት መዳረሻ። “Here is the land where the first harmony in the rainbow was born. We walk on the bed rock of our planet’s first continent. Here is the root of the Genesis of Life; the human family was first planted here by the evolutionary hand of Time….We walk on the footprints of the evolutionary ancestors of Man.”

ይሄ ነው ቃሉ። በቀስተዳመናችን ሥር የፈጣሪያችን ፍላጎት ስለመሆኑ  – እናዳምጥ። አቅማችን – ፍላጎታችን – ሰብስበን ለብሄራዊ ነፃነታችን – እናውል። የሐገሬ ልጆች ስጋትን – ወርውሩት። የፈጣሪ ቃል ሁሉንም የማሸነፍ አቅም – አለው። የአምላካችን ምርቃት ሁሉንም መርታት – ይችላል። የፈርዖን ልብ በፈጣሪ ቃል አልተገራንም? ኢትዮጵያ ሁልጊዜም መንበር ናት – የዕምነት ንጥህና – ቅድስና ሀገር! ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተመረጠ ነው። ኢትዮጵያ ትልቅ ሐገር ናት። ለሁላችሁም አቅም ላላችሁ ሙሁር ሊቅ ልጆቿ – ትበቃለች። ብዙ ብዙ መጠነ ሰፊ አቅምን የሚጠይቁ ክፍት ቦታዎች አሉ። ቅንነትን እንዳ እዬብ ከታጠቃችሁ – የብሩኽ ዕውቀት ባለድርሻ ወገኖቼ።

ስንት ነገር አዬን – ሙሉ ተስፋ ሰንቀን ኢዲህቅን – አማራጩንም – ህበረቱንም – ቅንጅቱንም – አንድነቱንም – መድረኩንም – በዬቤት ቤታቸው የተደራጁትንም – /ሰማያዊውንም ገና ለጋ ወጣት ነው/ አዬን፤ አዎን! ተመለከትን። አዳመጥን። ተሳተፍን። ግን ተከፍተን – ኖርን። ግን በሃዘን ተቆራምድን ኖርን። አሁን ግን ለቀኑ ቀኑ ተክሊል – ደፋለት። ቤተ መዳፍ በክፉ ቀን ቀልጦ እንዲያበራተፈቀደ። ለሠርግ እኮ አልሄደም። ለሽርሽርም አይደለም። ለጉብኝትም አይደለም። እናስተውል ከልብ ሆነን ሞትን ወዶ ፈቅዶ እጅግ አጣብቂኝና አስጊ እርምጃን ነው የወሰደው። አዎን በሰከነ ብልህ እርምጃው አውሎ እረፍት አደረገ – በረዶውም ተግ አለ። ወጮፈውም ቢሆን በመጣበት – ተመለሰ። ነጕድጓዱም እግሬን አውጪኝ አለ። ነፋሻማና ሳቂተኛ፤ ባለ ሙሉ ልብ በቃሉ ውሎ ውሉን አዬን። ኪዳኑን በተግባር ቀለበት – አሰረ፤ ስለቃሉ ሙሉ ቃል ሆነ። እኛም – ተመስገን አለን።

ተስፋዬን ቀለብኩት

ይሁንልኝ ብዬ አምላኬን —- ለመንኩት፤

የልቤ እንዲሆን እንዲህ —  ተማጸንኩት፤

ተስፋዬ ነውና – ተስፋዬን  — ቀለብኩት

የመሆን ነውና – በውስጤ አኖርኩት

ቤዛዬ ነውና መንፈሴን – ሸለምኩት!

እርገት ይሁን አይደል – የኔዎቹ?! ለእኛ ቁርባናችን – ታቦታችን – ጸሎታችን – ስግደታችን – ሳላዳችን – የወልዮሽ የባህል ዝክረ ነገራችን – የሃይማኖት ማዕዳችን – ቤተ አምልኳችን ንግሥት ኢትዮጵያ ናት። ለነፃነት ፍላጎታችን ማደሪያ የተመረጠው ደግሞ ሥህነቤዛ ነው። እሱ የአርቅ ጉባኤን ከአድማስ ወዲህና ባሻገር መሳላል – የሥርዬት መክሊት መገናኛ መርከባችን አንባችን – ነው።

በተረፈ – በአጋጣሚው ትንሽ ነገር ልከል፤ ከመሆን በላይ ሌላ የመሆን ፍሬ ነገር መጠበቅ እራስን ማተለል መሆኑን አብክሬ መግለጽ እሻለሁ። እራሱን የሸነገለ ህውከት፤ ጦሮ ንፋስን ፈቅዶ አምላካችን ያስከፋ፤ የውስጥ ሰላምን መንጠቅም እንዳለ ይገንዘብ። ለተግባር ገበሬ፤ – እራሱን ችሎ ለግለግ ብሎ ለወጣ ዬዕውነት የቀስተዳመና ዓላማ፤ ምስክርነት – ያስፈልገዋል። አለንልህ ልጆችህ፤ አለንልህ የአብነት ተማሪዎችህ፤ አይዞኽ ማለትም በልበሙሉነት – ይገባል። እግዚአብሄር ይስጥልኝም ማለት – የተገባ ነው። ልዑል እግዚአብሄር ሚስጢሩን ገልጦ ይህን ለመሰለ ለተምሳሌነት ያበቃ አምላክ ጥንካሬውን ብርታቱን፤ ጥበቃውን ይስጥልኝ – ለአርበኞቼ! ድንግልዬ ድስስ ታድርግ፤ የጎደለውንም ትሙላ – እናት!

መሸቢያ ሰንበት – ለእኔዎቹ። ውድ ዘሃበሻ ኑሩልኝ – የመንፈስ ጥሪቶቼ። ምዕራፍ ሦስት ይቀጥላል።

ማሳሰቢያ – አባቱ የእኔ ጀግና ናትናኤልሻ እሺ –  እኔ ሎሌህ ነኝ። በጹሑፎቼ ሁሉ መልእክትህን እለጥፋለሁ። በራዲዮ ፕሮግራሜም በድምጽ መልእክትህን ሙሉውን – አስተላልፋለሁ። http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45527

ፈጣሪ አምላክ እኛን ስለሰጠን እናመስግን!

ወስብሃት ለእግዚአብሄር።

 

ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 77 (PDF)

$
0
0

ከረዢም አመታት በፊት የተጀመረው የባህርዳር ሞጣ ብቸና መንገድ አሁንም ችግር እየፈጠረ መሆኑ ተነገረ

$
0
0

Motta 2012 week1 044-ከአመታት በፊት ተጀምሮ በማዝገም ላይ ያለው የባህርዳር ሞጣ ደጀን መንገድ አሁንም በንግድ እንቅስቃሴያቸው ላይ ከፍተኛ ችግር እየፈጠረባቸው መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ በትራንስፖት ቢሮ የትራንስፖርት አገልግሎት የስምሪት ተተኪ የስራ ሂደት ውስጥ የሚገኙ ባለሙያ እንደተናገሩት መንገዱ በተደጋጋሚ በመበላሸቱ እና ለረዢም ጊዜ ባለመሰራቱ ህብረተሰቡ መቸገሩን ገልጸው፤ለመንገድ ስራ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤቶች ስራውን እንዲያጠናቅቁ በተደጋጋሚ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ቢጻፍላቸውም ስራውን ለማጠናቀቅ አልቻሉም።
ባለሙያው በተጨማሪ እንደተናገሩት የስራውን መጠናቀቅ ተከታትሎ ለማስፈጸም ሃላፊነቱን የወሰደው የፌደራል ትራንስፖርት ሚኒስቴር የህዝቡን ተደጋጋሚ ቅሬታ ሰምቶ እንዳልሰማ መሆኑ የመልካም አስተዳደር ችግር እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡
ከአዲስ አበባ በቡሬ ባህርዳር አሁን የሚያገለግለው የአስፓልት መንገድ 565 ኪሎ ሜትር ሲሆን ከአዲስ አበባ በሞጣ ባህርዳር ግን አንድ መቶ ኪሎ ሜትር የሚቀንስ በመሆኑ ነጋዴዎች የሸቀጥ ጭነታቸውን በሞጣ በኩል በመጫን በትራንስፖርት መቀነስ ምክንያት የሚኖረውን የኑሮ ውድነት በመጠኑ ለማገዝ የሚያስችል የንግድ እንቅስቃሴ ለመፍጠር የሚችሉበትን ዕድል እንዳላገኙ ነጋዴዎች ይናገራሉ፡፡
በተለይ ከደጀን ብቸና በሚወስደው መንገድ ብቸና ከተማ አካባቢ የሚገኘው የሰዋ ወንዝ ድልድይ ባለፈው የክረምቱ ወራት ወቅት መሰበሩ በርካታ ችግሮችን እንዲያሳልፉ መገደዳቸውን የሚናገሩት የብቸና ከተማ ነዋሪዎች፣ የዚህ መስመር የአስፓልት መንገድ ለምን በተያዘለት ጊዜ እንደማይጠናቀቅ ሁሌም እንደሚገረሙ ተናግረዋል፡፡
ከደጀን ፈለገ ብርሃን ያለው የመንገድ ፕሮጀክት ሳትኮን በሚባል ሃገር በቀል የመንገድ ስራ ተቋራጭ እየተከናወነ ቢገኝም የጥራቱ ጉዳይ አሳሳቢ ከመሆኑና በአካባቢው የተሰሩት ድልድዮች ከማነሳቸው የተነሳ በስራቸው ጎርፍ ማሳለፍ አቅቷቸው በላያቸው ላይ እየፈሰሰ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ያሰማሉ፡፡ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሳምሶን ወንድሙ ከሁለት አመት በፊት ባደረጉት ገለጻ ከደጀን ፈለገ ብርሃን ድረስ ያለው የመንገድ ፕሮጀክት በቶሎ እንደሚጠናቀቅ አስታውሰው፥ ከዘማ ወንዝ እስከ ባህርዳር ድረስ ያለው የመንገድ ፕሮጀክትም በ2006 ይጀመራል በማለት በነሃሴ ወር 2005 ዓ.ም ቃል ቢገቡም የመንገድ ስራው ፐሮጀክት በዚህ አመት ተጀምሮ በመጓተት ላይ መሆኑን ቅሬታ አቅራቢዎች ይናገራሉ፡፡
የሳትኮን ባለቤት አቶ ሳሙ ኤል ተኽላይ የሰራተኞችን ደመ ዎዝ ለወራት በመ ከልከልና በማ ሰቃየት፣የመ ኪ ና ክራይ በወቅቱ ባለመ ክፈልና ስራን በማጓተት በተደጋጋሚ ቢከሰሱም፣ ገዢ ው ፓ ርቲ ለሁሉም ፕሮጀክቶቻቸው ከለላ በመ ስጠት ከተጠ ያቂነት ነጻ ሲያደርጋቸው መ ቆየቱን ታዛቢዎ ች ይናገራሉ፡፡
ሳትኮን ኮንስትራክሽን በህውሃት መንግስት ታቅፈው በአዲስ አበባ በስፋት ከሚንቀሳቀሱ የህወሃት ደጋፊ የሪልስቴት ባለሃብቶች መካከል አንዱ ሲሆን፣ በርካታ የግንባታ ስራዎችን ያለ ጨረታ ይወስዳል። አምባሳደር ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ አካካየ ሪልስቴት፣ክንዴ ሃጎስ ሪልስቴት፣ ተክለብርሃን አምባዬ ሪልስቴት፣ ጊፍት ትሬዲንግ፣ ሲቲ ዋይድ ኢንጂነሪንግ፣ አሴ ትሬዲንግ፣ ስብሃቱ እና ቤተሰቡ ትሬዲንግ ከህወሃት ጋር በቅርብ የሚሰሩ የሪል ስቴት ኩባንያዎች ናቸው።

Source:: Ethsat

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ለጋንቦ ወረዳ አሁንም ውጥረቱ እንደተባባሰ የቪዲዪ ማስረጃ ደርሶናል (ቢቢኤን)

$
0
0

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ለጋንቦ ወረዳ አሁንም ውጥረቱ እንደተባባሰ የቪዲዪ ማስረጃ ደርሶናል (ቢቢኤን)

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ለጋንቦ ወረዳ አሁንም ውጥረቱ እንደተባባሰ የቪዲዪ ማስረጃ ደርሶናል (ቢቢኤን)

“አንገነጠልም –ትግላችን የኦሮሞ ሕዝብ ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ ነው”–ብ/ ጀነራል ኃይሉ ጎንፋ ከአስመራ (የሚደመጥ)

$
0
0

ከሁለት ሳምንት በፊት አራት የኦነግ ድርጅቶች ወደ አንድ መምጣታቸውን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ ይታወሳል:: ይህን ተከትሎ ከአውስትራሊያ የሚሰራጨው ሲቢኤስ ራድዮ ብ/ጄ ኃይሉ ጎንፋ፤ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር – ኦነግ (በአባ ነጋ ጃራ የሚመራው) ምክትል ሊቀ መንበር፤ ስለ ኦነግ ዳግም መሰባሰብ አንጋግሯቸዋል:: ጀነራሉ ተበታትነን ምንም አናመጣም ብለዋል:: “ኦነግ የሚለውን ስያሜ በባለቤትነት እኔ ነኝ ብሎ የሚወስደው ማን ነው?” ለሚለው ጥያቄም ምላሽ ሰጥተዋል:: ያድምጡት::

General

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live