Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የቀዳማዊ ኃይለሥላሴን ልደት በማስመልከት የታተመ ልዩ ጋዜጣ –መዲና (PDF)

$
0
0

Hailesilase Birth day
ከሔኖክ ዓለማየሁ
(የዘ-ሐበሻ ዋና አዘጋጅ)

በሃገር ቤት የማሳትማት መዲና ጋዜጣና መጽሔት በ1995 በኢትዮጵያ አቆጣጠር የቀዳማዊ ኃይለሥላሴን ልደት በማስመልከት ልዩ ዕትም ጋዜጣ አዘጋጅታ ነበር:: ከጋዜጣውም በተጨማሪ ልደታቸውን በኢምፔሪያል ሆቴል አክብረን ነበር:: በዚህ 12 ገጾችን በያዘው ጋዜጣ ላይ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሕይወትን ለመዳሰስ ሞክረን ነበር:: ይህን መዲና ጋዜጣ ከ10 ዓመታት በኋላ በአሜሪካው ኮንግረስ ላይብረሪ አግኘሁት:: ዛሬ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ 123ኛ ዓመት የልደት በዓላቸው በመሆኑ ይህን ጋዜጣ በፒዲኤፍ ታነቡት ዘንድ ጋብዣለሁ::

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ


Health: ካሮትን ቀቅሎ የመብላት 5 የጤና በረከቶች

$
0
0

carrot
በሳሙኤል ዳኛቸው

ካሮት በተፈጥሮ በያዘው የቫይታሚን እና የፋየበር ክምችት ለጤናችን እጅግ ጠቃሚ መሆኑ ይነገርለታል።

ሰውነታችን ወደ ቫይታሚን ኤ የሚቀይረው ካሮቲኖይድ የተባለውን ጠቃሚ ንጥረነገርም በበቂ ሁኔታ ይዘዋል።

ፋልካሪኖል የተሰፀ እና ካንሰርን በመዋጋት አቻ የሌለው ንጥረነገርም ሌላው የካሮት የጤና ገፀ-በረከት ነው።

ታዲያ እነዚህንና ሌሎችን በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች የሚያስገኝልንን ካሮትን በምን መልኩ ብንመገበው የተሻለ ተጠቃሚ እንሆናለን? የሚለው የብዙዎቻችን ጥያቄ ነው።

1.ካንሰርን የመከላከል አቅሙ ስለሚጨምር፣

የበሰለ ካሮት ካንሰር የመከላከል አቅሙ ከጥሬው በ25 በመቶ ከፍ ያለ መሆኑን ነው ጥናቶች የሚያመለክቱት።
ጥናቶች በተጨማሪም ካሮቱ በአንድ መያዣ ውስጥ መብሰሉ አስፈላጊ ንጥረነገሮቹን በአንድ ላይ ማግኘት እንድሚያስችልን ይገልፃሉ ።

2. ጣፋጭነቱ ስለምጨምር፣

ካሮትን ጣፋጭ ጣዕም እንዲኖረው የሚያደርጉት ተፈጥሯዊ ስኳሮች የሚፈጠሩት ካሮቱ በሚበስልበት ወቅት ነው።

3 የአንቲኦክሲዳንትስ መጠን በእጅጉ ስለምጨምር፣

የበሰለ ካሮት ካልበሰለው ጋር ሲነፃፀር ጠቃሚ አንቲኦክሲዳንትስ ከ34 በመቶ በበለጠ አለው።

4.የቫይታሚን መጠኑ ስለምጨምር፣

ካሮት በሚበስልበት ወቅት የከለር፣ የቅርፅ እና የጣእም ለውጥን ብቻ ሳይሆን የሚያስከትለው፥ በውስጡ የሚፈጠሩት ውህዶች እና በውስጣቸው የሚገፀው የቫይታሚን መጠንም በተመሳሳይ ይቀየራል።

5.የካሎሪ መጠኑ ከፍተኛ በመሆኑ

የበሰለም ሆነ ያልበሰለ ካሮት የተሻለ ካሎሪን በማስገኘት ረገድ የሚታማ ባይሆንም በተመሳሳይ የበሰለው ካሮት በሁለት እጥፍ ካልበሰለው ካሮት የተሻለ ካሎሪ ሰውነታችን እንድያገኝ ያስችላል።

ምንጭ፦http://www.dailymail.co.uk/health

ዝዋይ እስር ቤት –ከፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

$
0
0

Temesgen Desalegn behindbar
ሐምሌ 17/2007

ሐምሌ 16/2007 ዓ.ም. ለአሥር ወራት በእስር ላይ የቆየውን ጋዜጠኛ፣ ተመስገን ደሳለኝን (ከኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር ዝምድና የለውም፤) ለመጠየቅ ወደዝዋይ ወህኔ ቤት ሄጄ ነበር፤ የወሕኒ ቤቱ ባለቤቶች ማረሚያ ቤት ይሉታል፤ ማረሚያ ቤት ማለት ሀሳቡን በነጻነት የሚገልጽና በሀሳቡም ከወያኔ ጋር በሎሌነት ለመተዳደር የማያመች ሲሆን የቀናውን በጉልበት የሚያጎብጡበት ማለታቸው ነው፤ ማረም ማለት ቀጥታውን ማጉበጥ ነው፤ እንዴት እንደሚያጎብጡት ላሳያችሁ፤–

1. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ እስረኞች ሰዎች በመሆናቸው ሰብአዊ ደኅንነታቸውና ክብራቸው ሁልጊዜም እንዲጠበቅላቸው ያስፈልጋል፡፡
2. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ እስረኞች ሁሉ ከመሰቃየትና ከመጉላላት በጸዳ አያያዝ እንዲጠበቁ ይደነግጋል፤
3. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ አንድ እስረኛ ዘመዶቹና ወዳጆቹ ከሚኖሩበት በጣም ርቆ አይታሰርም፤
4. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ የታመመ እስረኛ ሙሉ ህክምናና አስፈላጊውን መድኃኒት ሁሉ ማግኘት አለበት፤
5. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ እስረኞች በአእምሮና በመንፈስ የሚያድጉበት ትምህርትን የማግኘት፣ መጻሕፍትን የማግኘት መብቶች አሏቸው፤
6. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ ማንኛውም እስረኛ በእምነቱ መሠረት አምልኮቱን የመፈጸምና የሃይማኖቱን መጻሕፍት የማንበብ መብት አለው፤
7. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ ማንኛውም እስረኛ ዘመዶቹና ወዳጆቹ እንዲጎበኙት መብት አለው፤
8. እስረኞች የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰው ከወህኒ ቤት ሲወጡ ትክክለኛ የማኅበረሰቡ አባሎች ሆነው እየሠሩ ለማኅበረሰቡ እድገት ድርሻቸውን እንዲያበረክቱ ማሰናዳት ያስፈልጋል፤

በዝዋይ እንዳየነውና እንደተነገርነው የእስረኞች ሁኔታ በጣም የሚያሳዝንና ከላይ የተዘረዘሩትን የሰብአዊ መብቶች የሚጥስ ነው፤ ጤንነት ዋና ነገር ነውና በሱ እንጀምር፤ ተመስገን ደሳለኝ ወንጀል የተባለበት የፖሊቲካም ሆነ የማኅበረሰብ እምነቱን እያፍረጠረጠ በመጻፉ ነው፤ (በ1992 ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ባደረግሁት ንግግር ‹‹አትፍሩ›› ብለሃል ተብዬ ተከስሼ ነበር!) እንዲያውም ክሱን አስቂኝ የሚያደርገው መንግሥትን ነቅፈሃል የሚል መሆኑ ነው፤ ሦስት ዓመት እስራት ተፈረደበት፤ ይግባኝ ተከለከለ፤ አሁን ከታሰረ አሥር ወራት ሆኑት፤ ተመስገን በጣም ከታመመ ጥቂት ቆየ፤ አንደኛ አንዱ ጆሮው በጭራሽ አይሰማም፤ ሁለተኛ ከባድ የወገብ ሕመም ስላለበት መተኛትና መቀጥም በጭንቅ ሆኖበታል፤ ሆኖም አሳሪዎቹ ወደሀኪም ቤት ሊወስዱት ፈቃደኛ አይደሉም፤ ከዚያም በላይ መድኃኒት ከውጭ ሲመጣለት ይከለክላሉ፤ እኔም የወገብ ሕመም ስላለብኝ የወገብ ሕመሙን የሚያቀልለትን መድኃኒት ወስጄለት ነበር፤ አንድ አሥር አለቃ መድኃኒቱን አየና ከለከለ፤ መልሼ ይዤው መጣሁ፤ እንዲህ ያለውን ውሳኔ የሚያደርጉ ሁሉ ወያኔዎች ናቸው፡፡
ከተመስገን ጋር ትንሽ ጊዜ ቆይተን በዚያው በዝዋይ የታሰሩ ሌሎች ጋዜጠኞችን ለመጠየቅ መጀመሪያ ተፈቅዶልን ስለነበረ ወደዚያ ስናመራ አንድ ሹም መሳይ መጥቶ ወታደሮቹን ለብቻ ለብቻ በስም እየጠራ በመንሾካሾክ ትእዛዝ ይሰጣል፤ እየተንሾካሾከ ለአንዱ ትእዛዝ ሰጥቶ ሌሎቹን እንዳናይ ከለከለንና ተመለስን፤ ምክንያቱን ብንጠይቅ በአንድ ጊዜ መጠየቅ የሚቻለው አንድ እስረኛ ብቻ ነው ተባልን፤ ቅን መንፈስ ለጎደለውና ለሙስና ለተጋለጠ አሠራር ጥሩ ምሳሌ ነው፤ በመንሾካሾክ የሚሰጠውም ትእዛዝ ዓላማው ያው ይመስላል፤ ወያኔ በሰዎች ላይ እንዲህ ያለ ጭካኔ ማሳየት የሚፈልገው ለምንድን ነው?
በዝዋይ እስር ቤት ትምህርትም እንደመድኃኒት የተጠላ ነገር ነው፤ ለተመስገንም ሆነ ለሌሎች መጻሕፍት አይገቡላቸውም፤ ለምን? ብዬ ስጠይቅ አንዱ ጠባቂ ‹‹ለእውቀት የሚሆን መጽሐፍ ይገባል፤›› አለኝ፤ የእውቀትን ፍቺ ለመጠየቅ ስሞክር ቶሎ ግራ መጋባቱን አየሁና ተውሁት፤ እሱም እንዳያውቅ ስለሚፈልጉ፣ አለቆቹ የእውቀትን ፍቺ ጠበብና ቀለል አድርገው አስተምረውታል፤ ሎሌ ትእዛዝን በሹክሹክታ እየተቀበለ ማስፈጸም እንጂ፣ እውቀት አያስፈልገውም፤ እዚህ ላይ ምናልባት በደርግ ጊዜ በእስር ቤቶች የነበረውን የትምህርት መስፋፋት ማንሣት ይጠቅም ይሆናል፤ በደርግ ዘመን ብዙ የተማሩ ሰዎች ታስረው ስለነበረ እረስበርሳቸው እየተማማሩ አንዳንድ ሰዎች ጀርመንኛና ፈረንሳይና ቋንቋዎች፣ ግእዝና ታሪክ እየተማሩ ወጥተዋል፤ በተለይ በሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ወህኒ ቤቶች አንደኛ ሲወጡ እንደነበረ አስታውሳለሁ፤ ዛሬ በወህኒ ቤቶች ትምህርት ክልክል ነው፤ በቃሊቲ ሁለት የትምህርት ሙከራዎች ከሽፈውብናል፤ አንድ ጊዜ ኦሮምኛ ለመማር የፈለግን ሰዎች ተሰባስበን ተከልክለናል፤ ሕግ ለመማርም ጀምረን ታግደናል፤ እንዲሁም ጂምናስቲክ በቡድን መሥራት ክልክል ነበር፤ ማናቸውም እውቀት አደገኛ ነው! ታዲያ ማረሚያ ቤት የሚሉት ማንን ለማታለል ነው? ማረሚያ ቤት እንዲሆን በመጀመሪያ አሳሪዎቹ መታረም አለባቸው!
እንደተመስገን ደሳለኝ፣ እንደአብርሃ ደስታ፣ እንደእስክንድር ነጋ፣ ከዞን ዘጠኝም በፈቃዱ ኃይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አቤል ወበላ፣ አጥናፉ ብርሃኔ ገና አልተለቀቁም፤ በተጨማሪም ከእስልምና በኩል የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባሎች ዛሬም እንደታሰሩ ነው፤ የመፍትሔ አፈላላጊዎችን ማሰር ነገሩም ግራ ነው፡፡
በመጨረሻም መነሣት ያለበት አንድ አደገኛ አዝማሚያ አለ፤ ፖሊስ የሚባለው ፍርድ ቤት ከሚባለው ጋር ያለው ግንኙነት ሕግ የሚባለውን ከጨዋታ ውጭ አድርጎታል፤ ፍርድ ቤት የሚባለው እስረኛ እንዲፈታ ፖሊስ የሚባለውን ሲያዝ እንደማይፈጸም በተደጋጋሚ ታየ፤ ይህ የመጨረሻው የውድቀት ምልክትይመስለኛል፤ቆም ብሎ ማሰብና አስፈላጊውን የለውጥ እርምጃ መውሰድ የሚያስፈልገው አሁን ነው፡፡

በወሊሶ ባጃጅ ተገጭቶ ፖሊስ ጣቢያ ክሊኒክ አጠገብ ጉዳት የደረሰበት ወገን የሚረዳው አጥቶ ለ40 ደቂቃዎች ደም ፈሰሰው (ይናገራል ፎቶ)

$
0
0

እኔም ዘ-ሐበሻ ነኝ በሚል ከኢትዮጵያ የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ፎቶዎችን እና ቭዲዮዎችን ይልካሉ:: አንድ የዘ-ሐበሻ ወዳጅ ከወሊሶ ያደረሰን መረጃ የሚከተለው ነው::
“ከዚህ ቀጥሎ የምልክላችሁ ፎቶ ከወሊሶ ከተማ የተላከ ነው ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ሰው ባጃጅ አደጋ አድርሶበት ተስውሮ ነው ።
በጣም የሚያሳዝነው የአካባቢው ፖሊሶች ቅድሚያ የሰጡት ባለባጃጁን መያዝ ሲሆን ይህን ምስኪን ሰው ደሙ እየፈሰሰ ማንም ሊረዳው ኣልደፈረም:: 10 ሜትር እርቀት ላይ የዞኑ ፖሊስ ፅ/ቤት የሚገኝ ሲሆን በግቢው ውስጥ ክሊኒክ ይገኛል ። ሆኖም ቢያንስ 40 ደቂቃ ይህ ሰው ደሙ እየፈሰሰ ያለምንም እርዳታ ቆይቷል ።
3 ፖሊሶች ይህን እያዩ ነበር::
ይህ አሜሪካ ወይም ሌላ ሃገር ቢሆን ምን ይደረግ ነበር? ሰው ክብር ነው ቅድሚያ ለሰው ህይወት?”
weliso 2

weliso 3

የተደበቀው የህወሓት ማንነት ከደደቢት እስከ ቤተ መንግስት –ክፍል አንድ

$
0
0

tigrai
ታላቋንና ገናናዋን ምድር ኢትዮጰያ ሲያስተዳድር እና ሲመራ ለሺህዎች ዓመታት የዘለቀው የዘውድ ስረዓት ህልፈቱን ዓይቶ ግብዓተ መሬቱ ተፈፅሞ 225ኛው ንጉሰ ነስት ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ከዙፋናቸው ወርደው ደርግ በትረ ስልጣኑን ጨብጦ የአገሪቱ ፖለቲካዊ መፃኢ ሁኔታ በአምባገነናዊና ዴሞክራሲያዊ መንታ መንገድ ላይ ቆሞ ወደ የትኛው አቅጣጫ እንደ ሚሄድ ሳይታወቅ ከአያቶቻቸው ክህደትን እየተማሩ ያደጉት አባቶቻቸው አገርና ወግናቸውን ለነጭ ሸጠው የሚያገኙትን እና አያቶቻቸው ገላቸውን ለጣሊያን ቸርችረው የሚለቅሙትን ሶልዲ እየበሉ ያደጉ የባንዳ ልጆች በህዝብ ላይ ጭምር በቀል አርገዘው ደደቢት በርሃ በመውረድ ሸፈቱ፡፡
አረጋዊ በርሄ፣ ስዮም መስፍን፣ ግደይ ዘርዓፅዮን፣ ዘርኡ /አጋአዚ/ ገሰሰ፣ አስፍሀ ሀጎስ በጥር ወር 1967ዓ.ም ደደቢት በርሃ ወርደው ከዚያም ወደ ሳህል በርሃ በማቅናት ከኤርትራ ህዝብ ነፃነት ግንባር ወታደራዊ ስልጠና በመውስድ እንዲሁም ገንዘብ፣ ትጥቅ እና ስንቅ በመመፅወት ድርጅት ለማቋቋም እውቀትና ልምድም ጨምሮ በመዋስ ህወሓትን መሰረቱ፡፡ ከእነዚህም የህወሓት መስራች በአንፃራዊነት ከአረጋዊ በርሄ በስተቀር ሁሉም በወታደራዊ እና በፖለቲካዊ የእውቀት ደርጃቸው ትምህርታቸውን ያላጠናቀቁ እዚህ ግቡ የማይባሉ ነበሩ፡፡
meles
በመሆኑም ህወሓት ገና ከጅምሩ መስረቱ የተናጋ በመሆኑ ውሎ አድሮም ልምድ ያላቸውን ሊያገኝ ወይም ሊያፈራ ባለመቻሉ ለ17 ዓመታት በኤርትራ ህዝብ ነፃነት ግንባር ጀርባ ታዝሎ አዲስ አበባ ምኒሊክ ቤተ መንግስት ሊገባ ችሏል፡፡ የእውቀት፣ የልምድ እና የአስተሳስብ ድህነቱም ዛሬ በእጅጉ ፅንቶበት ይገኛል፡፡
ነገር ግን ህወሓት ዛሬ በገዥነት ዙፋን ላይ ሆኖ በኤርትራ መንግስት የሚደገፉ የነፃነት ሀይሎችን “የሻዕቢያ ተላላኪዎች” እያለ አፉን ሞልቶ ሲናገር ይደመጣል ፡፡
“ብሔረ ትግራይ በጨቋኝዋ የአማራ ብሄር የሚደርስባት ተህጽኖ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎላ እና እየተባባሰ በመሄዱ የብሄረ አማራ ሶሻሊስቶች፣ ትምክተኞችና አድር ባዩች ሆነው ስለሚገኙ የትግራይ ህዝብ ለርጅም ዘመን ሰብዓዊና ፖለቲካዊ መብቱ ተነፍጎ ሲጠላና ሲናቅ እንዲሁም አድሎ ሲፈጸምበት በመቆየቱ ይህም በደል ጭቋኝዋ የአማራ ብሄር ሆነ ብላ እንደ መንግስት መመሪያዋ አድርጋ ስትስራበት ቆይታለች፡፡

ጭቋኝዋ የአማራ ብሄር የምታደርገው የኢኮኖሚያዊ ብዝበዛና ፖለቲካዊ ጭቆና ታክሎበት ከዚህም በላይ የሚያኮራው የህዝባችን ታሪክ፣ ባህልና ቋንቋ እንዲዳከምና እንዲጠፋ በማድረጓ የሦስት ሺህ ዓመታት ታሪክና ባህላችን መመኪያቸውና መፎከሪያቸው ሆኖ ስለሚገኝ ይህ የታሪክ ስርቆት በአንድ በኩል የአማራው ብሄር መፎከሪያ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ሰፊው የትግራይ ህዝብ ታሪክ እንደሌለው በመቆጠሩ ምክኒያት ብሔረ ትግራይ ይህን የትጥቅ ትግል አርነት መንገድ መርጣለች፡፡ በመሆኑም ጨቋኝዋ የአማራ ብሄር ጭቆናዋን እስካላቆመች ድርስ ህብርተሰባዊ እረፍት አታገኝም…”

በማለት ህወሓቶች ከአንድ ዓመት በኋላ በየካቲት 1968 ዓ.ም ባወጡት የፖለቲካ ሰነዳቸው በርሃ ወርደው ነፍጥ ያነሱባቸውን ምክኒያቶች ይዘርዝራሉ፡፡
በ1968 ዓ.ም ባቀርቡት የፖለቲካ ሰነዳቸው ዓላማቸው ቁልጭ ባለ መንገድ በገፅ 18 ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡፡
“የትግራይ ህዝብ ብሄራዊ ትግል ፀረ አማራ ብሄራዊ ጭቆና ነው፡፡ ስለዚህም የአብዮታዊ ትግል አላማ ከባላባታዊ ስርዓትና ከኢምፔረያሊዝም ነፃ የሆነ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ማቋቋም ይሆናል፡፡”

ህወሓቶች በዚህ በ1968 ዓ.ም ባወጡት የፖለቲካ ሰነዳቸው መግቢያ ላይ የትግራይ ህዝብ ሀቀኛ ወኪል እንደሆኑ ይገልፁና የትግራይን መሬት ወሰን በተመለከተ እንዲህ ነበር የፃፉት፡፡
“የትግራይ መሬት በድቡብ ኤሊውሃ በሰሜን መረብ ሲያካልሉት በምዕራብ በኩል ደግሞ ወልቃይትና ፅለምትን ያጠቃልላል፡፡”
ስለሆነም ህወሓት ከጎንደር እና ከወሎ መሬት ቆርሶ ወደ ትግራይ ለምን እንደወሰደ ሲጠየቅ በህገ መንግስቱና በፊድራሊዝም አስተዳደር አወቃቀር መሰረት እንደሆነ የሚገልፀው ፈፅሞ ከእውነት የራቀ ነው፡፡ ሙሉ በሙሉ ያሳካው የበረሃ ህልሙን ነው ማለት ነው፡፡

ህወሓቶች ዝጎ በተሰነጣጠቀው የታሪክ መነፅራቸው ትግራይን ተመልክተው እንዲህ በለው ፃፉ፡፡

“ትግራይ አክሱም እስከ ወደቀችበት ጊዜ ድርስ የአክሱም መንግስት እየተባለች ትጠራ ነበር፡፡ አክሱም ከወደቀች በኋላ እራሷን በማስተዳደር ለብዙ ጊዜ ብትኖርም ቅሉ አልፎ፣ አልፎ በአካባቢዋ ለነበሩ መንግስታት ግብር መክፈሏ አልቀርም፡፡ በአፄ ዮሃንስ ዘመነ መንግስት ኃይሏ በርትቶ በአካባቢዋ የነበሩትን ነገስታት በቁጥጥሯ ስር አውላ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ አፄ ዮሃንስ ከሞቱ በኋላ በዳግማዊ ምኒልክ አማካኝነት ትግራይ በማዕከላዊ ግዛት ስር ወደቀች፡፡”

ህወሓቶች ቆይተው ደግሞ ስልጣን ላይ እንደወጡ “ኢትዮጵያ የ100 ዓመት ታሪክ ነው ያላት” ሲሉ በድፍርት ተናገሩ፡፡ ህወሓቶች የአያቶቻቸውን የሀገር ክህደት ሳት ዳር ጨዋታ እየሰሙ ያደጉ ባንዳ የባንዳ ልጆች የታሪክ አተላዎች በመሆናቸው፤ ማንነታቸው ግራ ቢያጋባቸው፤ የማንነት ጥግ ፍለጋ ሲሯሯጡ ብናያቸው፤ በልካቸው ያልተሰፋ የማንነት ሱሪ አጥልቀው ሲሮጡ እየወለቀባቸው መለመላቸውን ብንመለከታቸው፤ ታሪክን ክደው ሊያስክዱን ሲሞክሩ ብንሰማቸው የሚያስደንቅ አይደለም፡፡
ህወሓት ምድረ ደናቁርት በዘር ነጋሪት ከየቦታው ተጠራርተው በረሃ በመውረድ የነጭ አምላኪ ባንዳዎች የክህደት ማህበር በመሆኑ የፖለቲካ ዓላማና ፕሮግራሙ ሌኒን እንዳለው፣ ማርክስ እንደተናገረው፣ ስታሊን እንደፃፈው… በሚሉ ሀሳቦች ብቻ የታጨቀ ነው፡፡
ህወሓቶች ሽፋናቸውን በእጆቻቸው ከዳበሷቸው ነገር ግን ካልገለጧቸው ከእነዚያ ቀያይ መፅሀፍት የቅዠት ባሀር ውስጥ ገብቶ በመስጠም የጠፋውን ማንነታቸውን ዛሬም ድረስ ፈልገው ሊያገኙት አልተቻላቸውም በእርግጥም አያቶቻቸው በሶልዲ የቀየሩትን ማንነታቸውን ሊፈልጉት አልሞከሩም፡፡ ሙሉ በሙሉ ረስተውታልና፡፡ ማንነታቸውን ፍሪዳ ጥለው ቅርጫ እያደረጉ ያደጉት የህወሓት አባላት…

ህወሓቶች በድርጅታቸው የፖለቲካ ፕሮግራም እገሌ እንዳለው እያሉ የሚፅፉት በማህፀን እያሉ የተጣባቸው ክህደት አመላቸው ስለሆነ ብቻ ሳይሆን ከማንነታቸው ጋር ሙልጭ ብሎ አብሮ ስለጠፋ የራሳቸው የሆነ ሀሳብ ስለሌላቸው ጭምር ነው፡፡ ከአሸዋ ላይ ተዘርተው የበቀሉ በመሆናቸው በራሳቸው መቆምና መተማመን ስለማይችሉ የሰናፍጭ ቅንጣት ያክል ሀሳብ እንኳ ቢኖራቸው ትክክል መሆናቸውን የሚያረጋግጡልን እገሌ ብሎታል በሚል ብቻና ብቻ ነው፡፡
በገፅ 8 ሰፍሮ የሚገኘው ፅሁፍ የህወሓቶችን ጭንቅላት እርቃን መቅረት በግልፅ ያሳየናል፡፡
arkebe
“ሌኒን የመገንጠልን አስፈላጊነት ሲገልፅ የህብረተሰብ መደብ መከፋፈልን ለማጥፋት የተጨቋኙ መደብ አምባገነንነት እንደሚያስፈልግ ሁሉ የማይቀረው የብሄሮች መዋሀድ ሊገኝ የሚችለው መሸጋገሪያ በሆነው የብሄሮች ነፃነት መብት፤ ማለት የብሄሮች መገንጠል መብት ሙሉ በሙሉ ሲኖር ብቻ ነው፡፡ እንግዲያውስ በዚህ መልክ የአማራ ብሄር በትግራይ ህዝብ ላይ የምታደርገውን ተፅዕኖ እንመልከት…” እያለ ይቀጥላል፡፡

ህወሓቶች በኤርትራ ህዝብ ነፃነት ግንባር ጀርባ በአንቀልባ ታዝለው ከደደቢት እስከ ቤተ መንግስት ባደረጉት ጉዞ መካከል በስብዕናም በግንዛቤም ከእነሱ የሚሻሉትን የትግል ጓዶቻቸውን ቅርጥፍ አድርገው እየበሉ ስንቅ በማድረግ ነው፡፡ ለአብነት ከሐረር ጦር አካዳሚ ተመርቀው በ1968ዓ.ም ትግሉን የተቀላቀሉት 5 የትግራይ ልጆች በወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ዕውቀታቸው ስለሚበልጧቸው አደገኛ በሆነ ቦታ ላይ ለግዳጅ አሰማርተው አስጨርሰዋቸዋል፡፡

ህወሓት ከኤርትራ ሕዝብ ነፃነት ግንባር አንቀልባ ወርዶ ራሱን ችሎ ተዋግቶ ያሸነፈበት በማስረጃ ተደግፎ ሊጠቀስ የሚችል አንድም ጦር ሜዳ የለም፡፡
ህወሓት በትግራይ ምድር ውስጥ ሰፍሮ የነበረውን 604ኛ ኮር በ1981 ዓ.ም ደመሰስኩ ሲል አይኑን በጨው አጥቦ የትግራይን ህዝብ ዋሽቶታል፡፡ ነገር ግን 604ኛ ኮር በውጊያ ተደምስሶ ሳይሆን ህወሓት ትግራይን ለመቆጣጠር የቻለው በበላይ የደርግ ባለስልጣናት የተሳሳተ ትዕዛዝ 604ኛ ኮር ወደ ጎንደር እንዲያፈገፍግ በመታዘዙነው፡፡
ደርግ በፈፀመው ጭፍጨፋ ህዝባዊ መሰረቱን በማጣቱና በ1981 ግንቦት 8 በኃያላን መንግስታት አነሳሽነትና ድጋፍ የተሞከረውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ 27 ጀነራሎች በመሞታቸው ጦሩ ያለመሪ ዕርቃኑን በመቅረቱ በራሱ ተዳክሞ ሲፈርስ ህወሓት እንደ ኢህአፓና ኢዴዩ ያሉ ብረት ያነሱ ድርጅቶችን ደምስሶ በወቅቱ የነበረው የታጠቀ ኃይል እሱ ብቻ በመሆኑ በለስ ቀንቶት አጋጣሚውን በመጠቀም ስልጣን ላይ ሊወጣ ችሏል፡፡

ግንቦት 20 በመጣ ቁጥር ለኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነት ሞቼ፣ ደምቸ፣ ተቆርጨ ፣ተፈልጨ፣ ጅኒጃንካ የሚለን ህወሓት ከተመሰረተበት ከ1967 እስከ 1981 ዓም አንድም ቀን ስለ ኢትዮጵያ ነፃነት አስቦም አልሞም አያውቅም፡፡በጦርነት ተሰው የሚላቸው ታጋዮቹም በየበርሀው እንደቅጠል ረግፈው የቀሩት እሱ እመሰርታታለሁ ብሎ ይመኛት ለነበረው ታላቋ ፅዮናዊት ትግራይ ነው፡፡

ሴተኛ አዳሪው ቡድን ህወሓት ከኤርትራ ህዝብ ነፃነት ግንባር አንቀልባ ውስጥ እንዳለ ምዕራባዊያን በዘረጉለት ሰፊ ጃንጥላ ጀንበሯን ተከልሎ አዲስ አበባ ለመግባት ውሳኔ ያሳለፈው በ1981 ዓ.ም ነበር፡፡ በመሆኑም የፖሊት ቢሮ አባል የሆኑት መለስ ዜናዊ፣ ስብሀት ነጋ፣ ስዩ አብርሀ፣ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሀዬ፣ ገብሩ አስራ፣ አለም ሰገድ ገ/አምላክ፣ አውዓሎም ወልዱ፣ አረጋሽ አዳነ፣ አርከበ ዕቁባይ፣ ፃድቃን ገ/ተንሳይ፣ አበበ ተ/ሐይማኖት እና ክንፈ ገ/መድን የኢትዮጵያን ህዝብ በመከፋፈል በትንሹ ለ100 ዓመታት የሚገዙበትን የደንቆሮዎች ዕቅድ ቀየሱ፡፡

የጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ትንታኔ በፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአስመራ ጉዞ ላይ (ከሕብር ራድዮ ጋር) –ያድምጡት

$
0
0

ከላስቬጋስ ኔቫዳ የምትሰራጨው ህብር ራድዮ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ወደ አስመራ የመጓዛቸው ሰበር ዜና እንደተሰማ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌናን በራድዮኑ ጋብዞ ትንታኔውን ተቀብሎታል:: ይህን ትንታኔ ይዘነዋል – ያድምጡት::

Birhanu Nega

አርበኞች ግንቦት 7 ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጠ “ሕወሓት እራሱ የሽብር ጥቃት አድርሶ በኛ ላይ ሊያላክክ ስለሆነ ሕዝብ ሆይ ተጠንቀቅ”

$
0
0

* እያንዳንዱ ዜጋ የህወሓትን እኩይ ሴራ ተገንዝቦ ራሱን፣ ቤተሰቡንና አካባቢውን ከጥቃት እንዲጠብቅ
* ዘረኛውና ፋሽስቱ የህወሓት አገዛዝ፣ በሕዝባዊ ኃይሎች ላይ ሊወስድ ያሰበው እርምጃ ተቀባይነት እንዲያገኝለት የሽብር ተግባር ፈጽሞ በአርበኞች ግንቦት 7 ላይ ለማላከክ ወስኗል
* በህወሓት የተደገሰልንን የሽብር ጥቃት ማምከን ይኖርብናል

ዘረኛውና ፋሽስቱ የህወሓት አገዛዝ፣ በሕዝባዊ ኃይሎች ላይ ሊወስድ ያሰበው እርምጃ ተቀባይነት እንዲያገኝለት የሽብር ተግባር ፈጽሞ በአርበኞች ግንቦት 7 ላይ ለማላከክ ወስኗል። እንዲህ ዓይነቱ እኩይ ተግባር ህወሓት ስልጣን ከመያዙ በፊትም በኋላም ሲያደርገው የነበረ መሆኑ የሚታወቅ ነው። ህወሓት እንዲህ ዓይነቱ ኢሰብዓዊና ዘግናኝ ተግባር ለመፈፀም የሚያስችሉ እኩይ ስለልቦና እና ልምድ አለው።
ginbot 7
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ በቅርቡ የጀመረው የነፃነት ትግል የፈጠረበት መደናገጥ ለመሸፈንና ንቅናቄውን በኢትዮጵያ ሕዝብና በዓለም ዓቀፍ ማኅበረሰብ ለማስወገዝ ያግዘኛል ብሎ ያመነበት ይህን ዘግናኝ ሴራ ከሳምንት በፊት ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁቱን አጠናቆ የነበረ ቢሆንም በወቅቱ የነፃ ሚዲያ አባላት ደርሰውበት ለሕዝብ ይፋ በማድረጋቸው እንዲዘገይ ተደርጎ ነበር። አሁን በደረሰን መረጃ ደግሞ ሴራው ከበፊቱ በባሰ እና ይበልጥ አውዳሚ በሆነ መጠን ተግባራዊ ለማድረግ የህወሓት “ስውር” መንግሥት ወስኗል። በዚህም ምክንያት ይህ የማስጠንቀቂያ መግለጫ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ በማያሻማ ሁኔታ እንዲገነዘብ የምንፈልገው ሀቅ የሚከተለው ነው። አርበኞች ግንቦት 7 በደረሰው መረጃ መሠረት ህወሓት በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ ወስኗል። የእቅዱ ዓላማ ዘግናኝ እርምጃ በንፁሃን ዜጎችና ሕፃናት ላይ በማድረስ “የሽብር ጥቃቶች ሰለባ” ነኝ በማለት የኢትዮጵያ እና የዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብ አዘኔታ ማግኘት ነው። የዩ. ኤስ. አሜሪካ ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያን የሚጎበኙ መሆኑ ደግሞ ይህንን እቅድ ተግባራዊ የማድረግ ጉጉቱ እንዲጨምር አድርጓል። ስለሆነም ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያ በህወሓት የሽብር አደጋ ውስጥ ነች። የቦሌ ዓለም ዓቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ እና ወደዚያ የሚያደርሰው መንገድ፣ የአፍሪቃ ኅብረት ጽ/ቤት እና የአሜሪካ ኤምባሲ ህወሓት በሽብር ጥቃት ዒላማነት ከመዘገባቸው ውስጥ ቀዳሚዎቹ ናቸው።

አርበኞች ግንቦት 7 በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚቃጡ የሽብር ጥቃቶችን መቃወም ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ተባብሮ ያመክናል። ይህ በህወሓት የተደገሰልንን የሽብር ጥቃት ማምከን ይኖርብናል። እኩይ እቅድን አስቀድሞ አውቆ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ አንድ ዓይነተኛ የሽብር መከላከያ ዘዴ ነው። በዚህ ረገድ በአገዛዙ ውስጥ ያላችሁ የሕዝብ ወገኖች ባለውለታዎች ናችሁ።

የእያንዳንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሕይወት መለኪያ በሌለው መጠን ውድና ክቡር ነው። በዚህም ምክንያት እያንዳንዱ ዜጋ የህወሓትን እኩይ ሴራ ተገንዝቦ ራሱን፣ ቤተሰቡንና አካባቢውን ከጥቃት እንዲጠብቅ አርበኞች ግንቦት 7 በጥብቅ ያሳስባል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

የጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ ሽራፊ ይቅርታ –ትንታ! (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 24.07.2015 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

ጤና ይስጥልኝ ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ እንዴት – ሰነበትክ? ደህና ነህ ወይ? ይቅርታ መጠዬቅ ለመኖራችን – ዓምድ ነው። የምድር ብቻም ሳይሆን ወይንም የገሃዱ ዓለም ብቻ ሳይሆን የመንፈሳዊው አለምም መርኽ ነው። እርግጥ ብዙም አይደፈረም። እራስን ዝቅ ማድረግን – ስለሚያጎላ። ይቅርታ – ንሥኃ ነው። ንሥኃ ደግሞ መንጨቧረቅን ሳይሆን ደህና አድርጎ ውስጥን መታጠብን – ይጠይቃል። ዬይፍቱን ብልህ ልብ ለማግኘት። ለማንኛውም ይቅርታ – በገኃዱ ዓለም ሲታይ ፈሊጡ ለማን? ለምን? መቼ? እንዴት? ወዴት? ዬት? የሚሉትን የሥነ – ጥያቄን ውስጠ አካል የማብራራት አቅም ሊኖረው – ይገባል። በተለይ ይቅርታው አደባባይ መዋል ካሰኘው። ከዚህ አንፃር ጅምሩ መልካም በመሆኑ – መከበርም እንዳለበት ሆኖ፤ ነገር ግን ተሸብልሎ የቀረበው ይቅርታ ተብራርቶ መቅረብ አለበት – ቁስለኛን ሆነ ጉዳተኛ የሆኑ ዬተደበደቡ የሥነ – ልቦና መንፈሶችን ለመፈወስ በቂ የሚጥን ወይንም የሚክስ አቅም ሊኖረው – ይገባዋል። እርግጥ ደጅ ጥናቱ በወያኔ ሃርነት ትግራይ ዬዘውድ ዘመን የተከሰስክበትና የሞት ፍርድ ያሰጠኽህን ዓብይ በኽረ ጉዳይ ተለዋጭ መስመር ስለ አሰገኘ በአመክሮ ሊያሰርዝ ይችል – ይሆናል። ይህም ያው – ተከድኖ። ገዢዎቻችን ምድር ስለሆኑ በውስጠ ወይራው ዘያቸው ተሸብልሎ ይተከዝበት – ይሆናል። ያው ጠርዝ ለጠርዝ ሲሄዱ ማደር ነውና … እነቶኔው።

የሆኖ ሆኖ ወንድም ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ – ትናንት የቅንጅትን መንፈስ በቀጣይነት ይዞ የተነሳውን ዬአንድነትን ፓርቲ ከብሄራዊ መሪው ጀምሮ እንኩት – አደረገክ፤ ዛሬ ያ ብሄራዊ ፓርቲ በዘመንተኛው የወያኔ ሃርነት ትግሬ ትዕቢት መፍረሱን ስታረጋግጥ ደግሞ ለሰላማዊ ትግል አርበኛ ሆነህ ተገኘኽ – ሌላውን የተስፋ ቅኝት ደግሞ ለመናድ – ታጥቀኽ ተሰለፍክ፤ ህፈረት የሚባል ነገር አለ። ችግርህ ኃላፊነትን በትከክል ለይቶ የማወቅ፤ ተጠያቂነት በድርሻ የመውሰድ ችግር በጉልህ ያለብህ ይመስለኛል፤ የሆነ ሆኖ በመንተፍረቱ ዛኒዛነውን ቆሞ ኤሎሄ የሚለው ይቅርታህ እንዲህ ይፈተሻል – አጀንዳዬ አንተው ነህና አብረን እላለሁ …. በትሁት መንፈስ።

የተሸበለለው የጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ ሽራፊ ይቅርታትንታ፤

ተረፍ ብላ፣ ጠብ እንዳትል፣ በመቁንን፣ ተቀንጥባ – የረባ ወይንም የመጋኛ ሀገረ ሰብዕዊ መዳህኒት ይመስል በአውራጣት ጫፍ ተለክታ፤ ወቅታዊ ዒላማዋን እንድትመታ የተሰላቸው ይቅርታ እንኳንስ በራህብ የተቦረቦረውን አንጀቴን ጎሮሮዬንም ረጠብ – አላደረገችውም። ይሄውና ወንድምአለም አለሁልህ ራህቡ እያገላበጠኝ  …. የጥማቱ ወላፈንም – እዬላጠኝ፤ ወሳፈቴም  እዬተጯጯኽ ነው፤ ምን አልባትም ስካይፒ በሚሉት አንተኑ ፍለጋ ሌልኛ ስደትም አሰኘን – ይላሉ፤ … ሸብረክ የምትል ብናኝ ተጨማሪ ሽራፊ ይቅርታ ብትገኝ ብለው ምሰና ጀምረዋል – በወልዮሽ።

  • እኔ እንደማስበው አንተ በኤርትራ በኩል የትጥቅ ትግልን ታራመድ በነበርክበት ጊዜ ደጋፊዎች – ይኖሩኃል። ሃሳቡን ደግፈው የተንቀሳቀሱ ዛሬ የማይነሱ ሰማዕታትም በሞት – አልፈዋል፤ ጦርነት የካርታ ጨዋታ – አይደለም። ሲያስፈልግህ መንገድ ነው ብለህ አወጅክ፤ እንዲህ ሲያሻኽም ደግሞ ትክክል አይደለም ብለህ ዘመቻ – ጀመርክ። ስለዚህ የነፍስ ጥፋት፣ የትውልድ እልቂት፣ የታሪክ ብክነት የጀግንነት ውሎና ውሉ እንዲህ ከፍተህ እንደምትጠጣው ዬቧንቧ ውሃ፤ ከጠጣህ በኋላ የምትዘጋው፤ ሲጠማህ ደግሞ የምትከፈትው ሊሆን – አይገባም። ለዛን ጊዜ መርሁን ተከትሎ ለፈሰሰው ደም ተጠያቂነትህን በውል አልዳሰሰም – ይቅርታኽ። ሰውን የትኛው ገብያ ይሆን ሸመት አድርገህ – የምትገዛው? ወይንስ የትኛው ፋብሪካ ላይ ይሆን የሰው ልጅን አምርተህ – የምታወጣው? ወይንስ ሰው ጣጣውን የጨረሰ ሆኖ ጎልምሶ መወለድ ይችላልን /ready made/ ዓይነት? ታሪክ ሠርተው ታሪክ አልባ ያደረካቸው ጀግና አርበኛ ወገኖቻችንስ ጉዳይ ከቶ በምን ይከተት ብለህ ታስባለህ? አንተ ዘመትኩ ለምትለን ዘመቻ ጊዜ፣ ገንዘብ፣ ጉልበት፣ ህይወት፣ ትዳር፣ ቤተሰብ፣ ወጣትነት፣ ኑሮ፣ መከራን ተቀብሎበታል ያ ያዬሕው ጀግና እና መከረኛ። የአንተው ላፒስ ደግሞ እንዲህ ባንኖ ሰርዟቸዋል …. ታሳዝናለህ?! ይህ የአርበኞች መሥራችነት ያልተገባ ክብርም በሚመለከት ግራ ነገር ነው ለእኔ፤ እነ ጀግና አበጀ በለው እኮ ደርግ እያለ በተደራጀ የሽምቅ ውጊያ ጥበብ በቋሚ ሙሉ ኃይል ሲያንቀሳቅሱት ነበር – በባዕታቸው፤ …. በትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር የጎንደር መሬት ተከለለ ሲባል ጎንደር ወሰናቸን ማን ደፍሮት ብለው ቀደም ብለው ረቂቅ መስዋዕትነት – አያሌዎች ከፍለውበታል። አረበኞቹ ጎንደር ላይ ከወያኔ ሃርነት ትግራይ /ከታላቋ ትግራይ – ቅዠት/ ጋር በነበረው ዬ18 ቀኑ ጦርነትም ሙሉ ተሳትፎ – ነበራቸው። ያን ጊዜ የመንግሥት ሠራዊት በሙሉ ቀደም ብሎ ወደ ማህል አገር – ስለተሸኘ። ከዛ በኋላ የሀገሬው ተሳትፎ ኮማንድ ፖስቱ ወደ ላይ አርምጭሆ – ተዛወረ። ስለዚህ ስሌቱ በቀደመ መልኩ በተደራጀው ላይ – ተሰለስን ወይንም ተዘለልን፣ ከዛ ደግሞ እንዳሻን ሆንበት  …. ቢባል ያስኬዳል ….
  • የኢትዮጵውያን ሌላው የተመክሮ ማሳ እንደሚያመለክተው በአንድ ወቅት የተነሳን ሃሳብ ያልደገፉ ወገኖች ምን ያህል በጫና ብዛት ድካማቸው፣ ልፋታቸው፣ አቅማቸው ቅስሙ ተሰብሮ በቋሳ ሆነ በቁርሾ አዝማችነት ከጨዋታ ውጭ እንደሚሆኑ – ይታወቃል። አብሶ ሴቶች ተመልሰው ብቅ – አይሉም። ሴቶችን አልባ ምንም ዓላማ ከዕሳቤ ደረጃ – እንደማይደርስም ልምድ ዘለቅ ተመክሮኽ ግልጽ ሆነህ ከቀረብከው ሊነግርኽ እንደሚችል አስባለሁ፤ ለነገሩ አንተና ሴቶች?! እም! – በቀነ ቀጠሮ፤ ከዚህም ሌላም በተፈጥሯቸው ቁጥብ የሆኑ ተብዕቶችም ብቅ ሲሉ ገጀሞ ከጠበቃቸው ሰብሰብ ብለው „የወንድ ልጅ ዕንባው በሆዱ“ እንዳለው የቅኔው ልዑል ብላቴ ጌታ ሎርዬት ጸጋዬ ገ/መድህን ዋጥ አድርገው የሀገራቸው ግፍና መከራ እያቃጠላቸው – እያንገበገባቸው – እዬተርመጠመጡ – ያለፉ፤ የታመሙ – የተገለሉ ሊኖሩ – ይችላሉ፤ በይቅርታህ መንፈስ ውስጥ ቦታቸው የት ላይ ሊሆን እንደሚችል አላውቅም – ምን አልባት ጠፍጥፈኸው ወይ አጣጥፈኸው አልፈኸው ሊሆን ይችላል? ልክ እንደ ታጣፊ አልጋ – አሁንም – ታሳዝናለህ?
  • የአንተን ሃሳብ የደግፉ ግን አንተን በተመክሮ – በልምድ – በዕውቀት በእጥፍ የሚበልጡትንም ቢሆኑ ኢጎህ ምን ያህል ከትክቶ አፈር ድሜ አስግጦ ቀብራቸውን በማወጅ በተጨማሪ አቅም ላይ አንተ ተረማምደህ አንቱታን ስታገኝ፤ ዬዬቤቱ ኮከብ ስትሆን፤ እነሱ ደግሞ እንዲፈልሱ መሆናቸው በማናቸውም ህዝባዊ እንቅስቃሴ ያዬሁት አምክንዮ ነውና በዚህ ዘርፍም ይቅርታህ ድቡልቡል ሆኖ ነው ያገኘሁት ….. ታሳዝናለህ?
  • ሙያህ ጋዜጠኝነት ነው። የሄድከው መረጃዎችን ለታሪክ በሚያመች መልኩ ማቀናበር ብቻ ሳይሆን ዓላማው ከእውነት ጋር ያለውን ተዛምዶ በማብራራት በዓይን ምስክርነትህ ሠራዊቱ የበቃ ደጋፊ እንዲያገኝ የአድቦኬት ተግባር ለመከወን – ይመስለኛል። ነገር ግን ፎቶህን ስመለከተው ህልምህ ሆነ ራዕይህ እንዲሁም ፍላጎትህ ሌላ ጉዳይ ነበር ልበል ይሆን? ህ!  የሥልጣን መንበር አራት ኪሎ ላይ – የከነዳ … እንዲህና እንዲያ ….  ወዲያና ወዲህ … ውዝውዝ —

http://ecadforum.com/2015/07/11/when-the-going-gets-tough-observing-shady-reporting-or-wishes/

ለዚህም ነው ዋናውን የሄድክበት ክቡር ሙያ ገፋ አድርገህ፤ የስደት ሽግግር መንግሥት ኤርትራ ላይ ለመመሥረት እንደ ነበር ከራስህ ከአንደበትህ ከወጣው ቃለ ምልልስ መረዳት ብቻ ሳይሆን፤ ዛሬ በፕሬስ ነፃነት ሥም የስደት ሽግግር መንግሥት ለማቋቋም ከተቻለም በቁልፍነት ለመቀመጥ፤ እንዲህ ሙያዊ ታማኝነት … ክህደት ሲገጥመው በምን ሂሳብ ቢወራረድ ካሳ ይገኝለት ይሆን? አኔ አላውቅም —

ያን ወደህ ፈቅደህ ዬሞት ፍርድ ያሰጠህን፣ በአንፃሩም ዬብዙኃኑ የክብር አክሊል የለገሰህን የጋዜጠኝነት ሙያህን፤ የህዝብ ፍቅር ተንበርክከኽ የዛቅበትን ተወዳጁን ኪዳን የሳተ ተግባር ስትከውን፤ ቢያንስ ያን የክብር ሰንደቅ የሆነውን የጋዜጠኝነት ሙያውን ይቅርታ በመጠዬቅ እረገድም በኩል በንሥኃኽ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ወይንም ጓዳ ያዬሁት ብጣቂ ነገር የለም። ወደ ሌላ የፍላጎት አቅጣጫ መሄድ ወይንም ሽግግር ማድረግ ሙሉ መብትህ ቢሆንም፤ በሽፋንነት የተጠቀምክበትን ሙያንም በመቅድምነት ምህረት ልትጠይቀው ይገባል ባይ ነኝ። እንደ ሰው ሊታዘብህ ወይንም ሊሂስህ ባይችልም ግን ዬሥነ ምግብሩ ችሎት ህሊናህ ነውና በርከክ ብለኽ ይቅርታ ልትጠይቀው – ይገባል። ሁለቱንም ይዤ እዬሄዳለሁ ካልክም ጊዜ የሚፈታው ይሆናል። ከዚህ ጋር አያይዤ በትህትና ልጠቁምልህ የምፈልገው ቁምነገር፤ ጋዜጠኛ የመራው የህዝብ እንቅስቃሴ ለግብ በቅቶ አይቼ አለማወቄ – ነው። ጋዜጠኛ በብሄራዊ ሙሴነት ለወንበር መትጋት እንደ ዜጋ መብት ቢሆንም፤ ግን የሙያው ተፈጥሮ ከዚህ መስመር በእጅጉ በጣም የራቀ፤ ሥነ ምግባሩ ባለድንበር መሆኑን ነው እኔ – የምረዳው። በጋዜጠኝነት ህይወት ውስጥም በብራናው ሆነ በብዕሩ እንዲሁም በልሳኑ፤ በተጨማሪም በዛ ቅናዊ የታማኝነት መንፈሱ ውስጥ የወንበር አጀንዳ  የተነነ ስለሆነ፤ በዚህ መስመር ሄደው ለድል የበቁ ካሉ ከአንተ ለመማር – ዝግጁ ነኝ። እንደ አንተ በአጥቢያነት ያዬሁት ስሌለ ለእኔ በግል የተለዬ – ሁኖብኛል። ጥምር ፍላጎት – በዝንቅ መንገድ። ያስኬድ ይሆን? ይህን አንተ – ታውቀዋለህ። የሆነ ሆኖ በስንት ፍዳና መከራ በረጅም የስቃይ ጉዞ የተደራጀውን የአርበኝነት አቅም በመስበር እረገድ …. የትናቱ ላይበቃ፤ ዛሬም በክቡሩ ሙያ ሥር ተመሳሳይ ወለምታ ሲደመጥ እጅግ – ያማል። ፈቅደህ ለሰጠኸው ድካምና መስዋዕትነት – ፈቅደህ ውሉን ፈታኸው …. ሸፈትክበትም። መ – ስ – ዋ – ዕ – ት – ነ – ት – ህ -ም ተሸብሽቦ የምር አለቀሰ = አነባ!

ሴቶችና ዬጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ – ህቅታ፤

ይህን ጹሑፍ ስጽፍ ከልቤ እያዘንኩብህ እንደሆነ ልገልጽልህ – እሻለሁ። የመጀመሪያዋ ሴት የብሄራዊ ፓርቲ መሪ ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ ዬአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ሊቀመንበር። https://en.wikipedia.org/wiki/Birtukan_Mideksa

በዘመኑ – ይህ አቅም፤ ይህ ብልህነት፤ ህግን የመተርጎም ቅንነት ሆነ ብቃትን ያሰጋው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ድርጅት ብቻ አልነበረም። በስውርም በግልጽም በነፃነት ትግሉ አካል አባል ቤተኛ ነኝ የሚለው እንደ ነበር – እረዳለሁ፤ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ አንተ ነበርክ። አንድ ጋዜጠኛ በአደባባይ የሴቶችን የእኩልነት አቅም ሲሰብር በመላ ዓለም የጋዜጠኛ ታሪክ አንተ የመጀመሪያው – ትምሰለኛለህ። ኢትዮጵያ ከረንት አፊርስ ዲስከሽን ፎረም /ተቋም/ በነበረህ ቆይታ እሷ በግፍ ለሁለተኛ ጊዜ ታስራ፣ ሃልዬ እያለቀሰች፣ አዛውንት እናት እንግልት ላይ ሆነው የሰጠኸወውን ቃለ ምልልስ – ታሰተውሰዋለህን?! „የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም።“  እ.አ.አ ግንቦት 22 – 2009 ያን ጊዜ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከዳኛ ብረቱካን ይብልጣሉ! ብርቱካን ምን አላት?¡ ቦንብ የላትም! ፕሬዚዳንቱ ግን ቦንብ አላቸው !“ብለህን ነበር – በኩራት። በዕለቱ በነበረህ የከረነት ቆይታ በክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ ዙሪያ የቀረበውን ጥያቄ ሁሉ እንዴት ትረገጥው እንደ ነበር፤ እራሱ ዬቶንህ ምቱ በንቀት ታንቡር ቲፍ ብሎ ሞልቶ ነበር – ያዳመጥነው። እሰበው – ከልብህ ሆነህ። ያን ጊዜ በትንታጉ የከረንት ወጣት አድሚን በዱዱዬ መሪነት ሆ! ብለን ተነስተን በጥያቄ ስናጣድፍህ አባጨልክ – ቀለድክ – ተሳለቅክ። ዬቅንጅት መንፈስ ቀጣይነት የታጠቀውን ዬአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ብሄራዊ ፓርቲን አቅመ ቢስ አድርገህ – አቃለልከው፤ ተስፋውንም – ተረማመድክበት፤ ምን ያህል ግዙፍና አስፈሪ አቅም እንደነበረ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ዒላማ ሆኖ ይኸው – ፈረሰልህ። ያን ጊዜ በጸጋዬ ድህረ ገጽና በራዲዮ ፕሮግራሙ ሰፊ ሽፋን ተሰጥቶት – ነበር። እርግጥ አንተ ባለ ዙፋን ስለነበርክ፤ ዘለፋህን ከሃቁ ጋር ለማነፃፀር ደረጃውም ወቅቱንም ያልጠበቀ ቢሆንም „የነጠረው ወርቅ የቅዱስ መንፈስ ጥበቃ አይለዬውም“ የሚል አንድ መጣጥፍ ጽፌ ነበር።

እንደ እኔ እርር ያሉ በርካታ ወገኖቼ በአደራሻችን አዎንታዊ አስተያዬታቸውን ሰጥተውን ነበር። ያን ጊዜ የጸጋዬ ድህረ ገጽ እጅግ ተወዳጅና ተፈቃሬ፤ በጽኑ አቋሙ የተከበረ፣ ታታሪ ድህረ ገጽ ስለነበር ታዳሚዎቹ በዕውነቱ ዙሪያ እንደ ከተሙ – እርግጠኛ ነኝ። የትናቷ ሥርጉተ ዛሬም በቆመችበት መሥመር ላይ ዝንፍ ሳትል ዕውነትን ከብክባ ተስፋዋን – ትጠብቃለች።

አዬህ ወንድሜ … ያ አቅም በእንጭጩ አንተንና አንተን የመሰሉ የውስጥ አርበኞች ባይጠቀጥኩት ኖሮ፤ ዛሬ ያለው ሁኔታ መልኩ ቀለማም በሆነ ነበር። ሴቶች የትንግርት እምቤቶች ናቸው። ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ ንጹህ መንፈስ የነበራት፤ የጸዳች፤ ወጣቱን – ሴቱን – ትውልዱን ሙሁሩን በአግባቡ በብሄራዊ ደረጃ ልትወክልና በጎ ተጽዕኖ ማሳደር የምትችል የምንም ዓይነት ሥነ ምግባር ብክለት ያልነበረባት፤ ተጨማሪ አማራጭ መንገዳችን – ነበረች። ከሊቅ አስከ ደቂቅ ፍቅርን እንደ ፏፏቴ የሰጣት – በአጭር ጊዜ በምልዕቱ ቅዱስ መንፈስ የታቀፈች ዕንቁ ነበረች። በአጋጣሚው ቀስተደመናን እና አንድነት ፓርቲን ከልብ – አመሰግናለሁ። ዛሬ ተውሎ የሚታደርበት መከረኛው ልዩ መክሊት ትምራኝ ብሎ ፈቅዶ – ነበር፤ ለቅንጅት ምሥረታ ውክልናውንም ደስ ብሎት ነበር በሐሤት – የፈቀደው። ምክንያቱም ሌላው ያለው እሱ ዘንድም እንዳለ ጠንቅቆ – ያውቃልና። እንዲያውም ባብላጫ –

ለእኔ ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ እንደ ገናናዋ  María Eva “Evita” Duarte Perón ማሪያ ኢቫ ኤቪታ ዱአርቴ ፔሮ ሁሉ የመንፈሷን ብስለትና ብሩኽነት በፍጹም ተስፋ እጠብቀው – ነበር። እንደ ኢቪታ ፔሩ በአማርኛ /ህይዋን ፔሩ/ ገና ከጅምሩ ብርቴም ብርቱ ተደመጭነት ነበራት – ሁሉንም ነበረችና። ኢትዮጵያ ሀገራችን ሥልጡን አዕምሮ፤ የቀደመ ብልህነት ያላቸው ቀንዲል ሴቶችን አላጣችም ነበር። ግን በዬት ታልፎ?! ጋሬጣ – በጋሬጣ —–

ለመሆኑ ኢቫ ፔሩ ማን ናት? በጥቂቱ

ኢቫ የድሃ ሴቶች አናት፣ የስሜን አሜሪካ የሴቶችን እኩልነት በትግሏ በተግባር ያስከበረች የሚሊዮኖች ዘላለማዊ አባባ ናት። ኢቫ ዓለምን – አወሮፓን በፍቅር የገዛች፣ ለጀርመኖች የልብ ደም ሥር በመሆን፤ ለእንግሊዞች የጥበብ እናት በመሆን ከአብነት በላይ አብነት ነበረች። ዬኢቫ ፎቶዋ ቤቴ ውስጥም በክብር አለ። ኢቫ ፔሩ የተወለደችው በሀገረ አርጀንቲና ግንቦት 7 ቀን 1919 በሎስ ቶዶለስ  Los Toldos በሚባል ከተማ ነበር። ኢቫ ከትዳር ውጪ የተወለደች በመሆኑ በወላጅ አባቷ የተገባ ክብካቤ ያላገኘች፤ እናቷም ከጋብቻ ውጪ ስለወለደች በማህበረሰቡ የተገፋች – ነበረች። ኢቫ ከእናቷ ጋር ስታድግ እጅግ በዝቅተኛ ኑሮ ነበር። ኢቫ የልጅነት ጊዜዋን በት/ቤት የቴያትር ክበብ፣ የሥነ ጥበብ ሀሁ ፊደል የቆጠረች ሲሆን፤ በረዳት በደጋፊ እጦት በታዳጊ ወጣትነት ዕድሜዋ ተገዳ ወደ ከተማ – መሄዷ፤ የገባችበት ዬሥራ መስክ የሴቶችን ኑሮ በጥልቀት በጽሞና እንድታይ – አድርጓታል። ህይወቱን ሆና አይታዋለችና። በወጣትነቷ በትናንሽ ሙቢዎች፣ የራዲዮን ድራማዎች ስትሳተፍ ቆይታ በኋላም Radio Belgrano ራዲዮ ቤልግራኖ ሁለገብ ፕሮግራም ጀምራ በዚህ ዙሪያ መስራት እንደ ቀጠለች በአንድ ዬሰብዕዊነት ዝግጅት ከባለቤቷ ከፕሬዚዳንት ፔሩ ጋር – ተዋወቀች፤ ኢቫ አጋጣሚው ረድቷት የአርጀንቲና ቀዳማይ እምቤት – ሆነች። በድርጊት የነፃነት ጥመኛው የቼጎቢራም አምሳያው – ሆነች። ቀዳማይ እመቤት ኢቫ ፔሩ በአብዛኛው የሥራ ቀናት እሰከ 20 ሰዓት ትሠራ እንደነበር ዝክረ ታሪኳ  ይናገራል፤

ድንቋ – ዕድሉን አልተኛችበትም ወይንም እንጎልቻ እንዲዘፍነበት – አለደረገችውም። ቀዳማይ እመቤት ኢቫ ፔሩ በመጀመሪያው ረድፍ ተግባሯ የሴተኛ አዳሪ ሴቶችን እውቅና – አሰጠች። ድርጅት መሰረተች፤ ሴቶች በማንኛውም መስክ እኩል ድርሻና ክብር እንዲኖራቸው በህገ መንግሥት በአንቀጽ ውስጥ እንዲረቀቅ አስደረገች፤ ነባሩ ህገ መንግሥት እንዲሻሻል – አስቻለች – አጸደቀች። ኢቫ በመጨረሻ ለም/ፕ ተወዳደረች። ሚሊዮኖች ደገፏት። ግን በነበረባት የካንሰር በሽታ ምክንያት በወጣትነቷ – በሥጋ አረፈች። በዕለተ ሞቷ በመላ አርንጀንቲ ትናንሽ ሱቆች ሳይቀር አበባ ማግኘት አይቻልም ነበር። መንገዱ በሙሉ በአበባ እና በዕንባ ዝንብ ራሰ። ሃዘኑ ለመላ ላቲን አሜሪካ መራርና ድንገተኛ ነበር። ግን እንሆ ዛሬ አርጀንቲና ውስጥ ወንዶች ሲወዳደሩ ሚስቱ ማን ናት ይባላል? ገና እኛ አብላጫዎች ያልደረስንበት፣ ያለንካነው ረቂቅ ሥርነቀል የፆታ እኩልነት አብዬት አርጀንቲናዎች በኢቫ ፔሩ አማካኝነት ከዚህ ዘመን ጀምሮ በተግባር እውን አደረጉት። ዛሬ አውሮፓ እንኳን ሲመጡ የአርጀንቲና ሴቶች በራስ የመተማመናቸው ጥንካሬ፤ ዬድፍረታቸው አቅም ፏፏቴ ከተምሳሌይቱ ሁለገብ እናታቸው ከኢቫ – ይቀዳል። እንዲያውም በአውሮፓ የሴቶች እኩልነት ከመንፈስ ጥንካሬ አንፃር ዬአርንጀንቲና ሴቶችን – አያረካቸውም። በአዲሱ የእኩልነት የለውጥ ሂደት ተጠቃሚ የሆኑት አርጀንቲናውያን ብቻም – አይደሉም። ጠቅላላ የላቲን አሜሪካ መንግሥታዊ የሥልጣን ተዋረድ፤ የተቀባይነት አድማስ ቢጠሩት ዛሬ – አይሰማም። በረቂቅ ቅዱስ መንፈስ አጋዥነት ተጨባጭ ለውጥ – አስገኘች። በብዙ የላቲን አሜሪካ ሀገሮች በሀገር መሪነትና በቁልፍ ቦታዎች ሴቶች ከላቀ ደረጃ የደረሱት በኢቫ አብዮት ነው። ኢቫ በትውና – በሙዚቃ – በፖለቲካ መሪነት – በሰብዕዊ መብት ተሟጋችነት – በሚስትነት – በፖለቲካ አማካሪነት – በራዲዮ ጋዜጠኝነት –  በፓርቲ አደራጅነት – በዳናስና በንግግር ጥበብ ሁሉንም የሰጣት የዘመን ኮከብ ነበረች። ቀለማም ምዕራፍ! የቀዳማይ እመቤት ኢቫ ፔሩ አንዱ ነጠላ የትውና ዜማ „don’t cry for me argentina“  የዓለምን ውቅያኖስ ጨምሮ የሚክል መጠነ ሰፊ ተደመጭነትና የዓለም የታሪክ መጽሐፍ መሆን ችሏል፤ ቀዳማይ እመቤት ክብርት ኢቫ ፔሩ የሀገሪቱን ታላቅ ብሄራዊ ሽልማትም – ወስዳለች። /In June of 1952 she was awarded the title “Spiritual Leader of the Nation“ ሞት ቀደማት እንጂ የኖቬል ሽልማቱም ሂደት ላይ ነበር።

ቀዳማይ እመቤት ኢቫ ፔሩ  /Democratic Union alliance/ ይህን ፓርቲ በመደገፍ ለትዳሯ ማገር በመሆን የመጀመሪያዋ የአርጀንቲ ቀዳማይ እምቤትነቷን ለቀይ ስጋጃ ምንጣፍ ዕይታ አላወለችውም – ነበር። ትዳሯን በመደገፍ ቀጥተኛ ተዋናይ በመሆን የላቀውን ደረጃ መውሰድ – ችላለች። ትዳሯ በነበረው የምርጫ ውድድር አሸናፊነትም የመሠረት አስኳል – ነበረች። ድንቋ ክብርት ኢቫ ፔሩ ለጡረተኞች፣ ለሴቶች ትርጉም ላለው እኩልነት፣ ለሠራተኞች አብሶ ለድሃ ወገኖቿ መብትና ርትህ እንዲሁም አርነት፤ በተጨማሪም ፋውንዴሽን በመመስረት ብቻ ሳትወሰን፤ ለነጡት የህግ ጥብቃ እንዲኖር በህገመንግሥት ደረጃ የለወጥ ሐዋርያ በመሆን ድርጊት ላይ እንዲውል – አስደርጋለች። በዛ ቀላማም የንግግር ጥበቧ የዓለምን ህዝብ በፍቅር – አስጊጣለች፤ ዕድሜዋ አጭር ቢሆንም የዕድሜዋን ሦስት ዕጥፍ ያህል ዓለምን በአዲስ ዘመን ለመለወጥ አቅምን – ገንብታ፣ አስተምራ – በቋሚ ተግባር – ተቋም /Century/ ሆና አልፋለች፤ ኢቫ በምክትል ፕሬዚደንትነት ስተወዳደር ደጋፊዎቿ ሚሊዮኖች ነበሩ። ነገር ግን በምርጫው ውድድር ዋዜማ ላይ /July 26, 1952 at 8:37 in the evening. She was 33 years old/  አለፈች። ዓለም በእሷ ዙሪያ የምርምርና የጥናት ተግባሩ እንደቀጠለ ሲሆን ጀርመኖች ደግሞ የላቀውን ድርሻ በመውሰድ ይህንን ክብር አጎናጽፈዋታል።

/Evita im Berliner Theater des Westenshttps://de.wikipedia.org/wiki/Evita_(Musical)#/media/File:Berlin_Theater_des_Westens_Sep_2002.jpg/

እናንተ ደግሞ የኢትዮጵያ ሴቶች አቅም ብቅ ሲል በቀንበጡ ቅንጥስ ብሎ ተሰብሮ – በለጋው አፍሮ እንዲቀር – በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ትተጋላችሁ፤ ስለ ቀዳማይ እምቤት ኢቫ ፔሩ ያነሳሁትም በመሠረታዊ በምክንያት ነው። እንደ ሚዲያ ሰውነትህ ልታበረታታ – ልትረዳ – ልታግዝ ሲጋባ፤ ኃላፊነቱን – በእጅጉ ተላለፍከው። ዕድሉን አግኝታ ቢሆን እንዲያ ብጣቂ እራፊ ሳትደርብላት ያጣጣልካትና ያብጠለጠልካት የእኛዋ ዕንቁ ብርቴ ትሆነው ነበር። ይህን የመሰለ ተስፋ ነበር ተቀጭቶ – ተቀብሮ – የቀረው። መቃብሩን ከማሱት ጋር በመንፈስ ሃዲድነት ተገናኝተህ እምሽክ – አደረከው። አንዲት ዘለላ ግድፈት ምን ያህል ተፈጥሮን እንደሚንድ – ተመልከተው። የአዲስ ዘመን ተስፋንም – እንደሚደረምስ፤ እርግጥ ነው የኢትዮጵያ ሴቶች የፈለገ ጠንካራ ቢሆኑ፤ ከጎናቸው ብረት መዝጊያ የሚሆን ሰው ከሌላቸው አቅማቸው አድዬ አበባ ነው፤ ፈንደቅ ብሎ – ክሰም። ብርቴም ከአንተ ጀምሮ እንደዛ እርብርብ ባይደረግባት ኖሮ ////  ኖሮ ወይንም ብረት መዝጊያ አቅም አጋር የትዳርም ይሁን የሥጋም ቢኖራት ኖሮ ዘመነ ጣይቱ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላ አፍሪካ በሆነ – በነበረ።

እና አቶ ወንድም ይህንስ ስለምን ትዘለዋለኽ? የሴቶችን አቅም እንኩት ያደረገው፣ ድቅቅ ያደረገው ትዕቢትህን ለማስተንፈስስ ይቅርታው ምነው በጎሬጥ – አዬው?! ያ ደም የሚተፋ ያመረቀዘው በደል እኮ አይረሳም? እንዲያውም ዒላማህ አቅምን ማደን ነውና – ያገረሻል። ከዛችን ዕለት ጀምሮ እኔ ከድህረ ገጽህ ትውር ብዬ – አላውቅም። አካል ተቆርሶ የትም ተጥሎ እንዴት ዝምድና ይኖረን?  ቀድሞ ነገር ከዚህ መሠረታዊ የእኩልነት መርህ ንድፍ አንፃር አንተኑ ለመተርጎም እንደ ነፃ ጋዜጠኛ ሆነ እንደ ሰብዕዊ መብት ተሟጋችም ለማዬትም እኔን – ይቸግረኛል፤ ስለምን? በፋሽስት እግር ብረት ለነበረች ብሄራዊ ዬፓርቲ መሪ ለትውልዱ የመጀመሪያ ቀንድ ደንዳና አንጀትኽ በክብርህ ላይ ጥቁር ቀን አውጇል እና – ፍቀት። ከዚህም በኋላ ቀልብህ ሌላ ሴት ጀግና ላይ – አረፈ። እኮ – ለምን ፈለግኸው? ሆድህ –  ያውቀዋል። አዬህ ገፈፍከው ክብርህን እራስህ፤ — እናትህን —– እህትህን —– ሚስትህን –  ዘለህ፣ ንቀህ ህይወት የለም፤ ኖሮም አያውቅም፤ ቢኖርም ብቻውን ነው የሚያወጋ  ወይንም የሚዋጋ የገደል ማሚቶ ነው የሚሆነው። ለነገሩ ዛሬ ላይ ሆኜ ሳዬው የሥልጣን ህልመኛ ስለሆንክ፤ ያ የሴቶች ደማቅ – ጉልበታም – ጉልህ አቅም አስፈርቶኽ መሆኑን ትናንት ብቻ ሳይሆን ዛሬ ፏ ፍንትው ብሎ  – ታዬኝ። ዘወርከው አቅጣጫውንም – አስቀዬርከው፤ ስለዚህ የአሁኑ ሽርፍራፊ ይቅርታኽ ለሌላ ተልዕኮ፤ ሌሎችን ደግሞ ቡጢህን ያልቀመሱትን እንደ ቀደመው በጎመራህ አስገብተኽ ለማንደድ ስለሆነ የሚቀበልህ ሊኖር አይገባም ባይ ነኝ። የኢትዮጵያ ሴቶች ሰብዕና ቢያንስ በአቅማችን ላይ ንቀት – ስርዘት ያለውን መንፈስ ሊጸዬፈው ይገባል ባይም ነኝ። „ድምፃችን ይሰማ!“

ወንድሜ – ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ እራስህን – አጥራው፤ ፍላጎትህንም አጽዳው – ባራኪና ካሰኛውም ዘፍዘፍ አድርግና ግድፈቱን አስለቅቀው – የኢጎኽን። ለአንተ ኢጎ ሲባል ዬሚሊዮኖች ክፍለ አካል የሆነው አቅም ሊረገጥ – አይገባም። ሊጠቀጠቅም – አይገባም። አንተ ሴት የመራችህ ዕለት ታንቀህ – ትሞታለኽ። የሚገርመኝ ሳይኖራቸው ሌትና ቀን ዬቡቃያ አቅም አድጎ እንዳይታይ ሲታገሉ የሚታዩ ዱዳ መንፈሶችን – አያለሁ። በዚህ ምክንያትም አካባቢውንም መላጣ አድርገውታል – አንተ ግን ያለኽ – አለኽ – ከበቂ በላይ መሆኑን አለማወቅህ ነው እዬሄድክ ካልሆነ ህልም ከርቸሌ – የምትቀረቀርው። ያንተን ያህል ዬሌላቸው ደግሞ በሥነ ምግባራቸው – ምራቁን በዋጠ የሰከነ ሥርአታቸው፤ በስልጡን ስልታቸው – በቋሚ የዕንባ አጋርነታቸውና በጽናታቸው በልጠውኽ – ይገኛሉ። ከልብህ ሆነህ –  ከህሊናህ ጋር ብትምክር ልትመራቸው ልታስዳድራቸው የምትችላቸው በርካታ ቦዶ ክፍት የሆኑ የሥራ መስኮች – ነበሩልህ። ቀዳዳችን ብዙ ነው። እንዛ ክፍት ቦታዎች ካለህ ብቁ አቅም ጋር ቢገናኙ በእውነት የነፃነት ፍላጎታችን አትራፊ በሆነ ነበር። እኛ ያለን ጥቂት አቅም ነው። እሱን ደግሞ አትፋለመው – ወያኔ ሃርነት ትግራይን ያህል እያመዘመዘ ደም የሚያወረዛ ተቀናቃኝ አስቀምጦ – ያሳዝናል። ምጥና ማጥ። ሌላው ማጥማጃ መሳሪያህም ብቅ ከሚሉ ቀንዲል ሴቶች ዞር – ይበል፤ እንዲሁም  በአርነት ትግል የውስጥ አስተዳደሩን በሚመለከትም በነፃነት የመምራት ኃላፊነት፤ በጣልቃ ገብነት የምትፈጥረው መልክ ጥፉ የመንፈስ ህውከትንም – አስታግሰው። „ድማፃችን ይሰማ!“

የቤት ምርጫ – ብንታ፤

ትክክለኛ ጋዜጠኛ ቤቱን – ያውቃል። ቤቱ የክብሩ ማማ መሆን – አለበት። በዕብነበረድ በተለበጠ ፈንጣጣማ ዓውድ እንዲሁም የብሄራዊ ክብራችን ግርማ ሞገሱ ሥርዓተ ቀበር በሚፈጸምበት ቦታ ዕዝነ ህሊናህ – እንደ ፕሬስ ሰውነትህ  – ይቅደም። በጠላት ወረዳ አንድ የነፃነት ትግል ጋዜጠኛ እንደ ቤቱ ሊዘናከትበት – ወይንም የእኔ ብሎ ሊወላዳበት – አይገባም። መሬቱን አፈሩን ጥርኙን በቀማው ጀሌ ቤት ላይ ሆኖ እሱነቱን ዘርግፎ – ሆድ ዕቃውን – ጨጓራውን ተጫዎቱበት ማለትም – አይገባውም። አቅሙን ለጠላቱ መሸለምም – አይገባውም። ካለቤቱ የተገኘ ጋዜጠኛ ቢያንስ የጠላትን መንፈስ – ዘርፎ፤ የወገንን አቅም መገንባት ሲገባው እራሱም ተዘርፎ በምርኮኛ አባልነት ሲደመር ማዬት የዛገ ብረት ነው ለእኔ – ለሥርጉተ። ጋዜጠኛ የላቀ የመንፈስ ብቃት ረቂቅ – ሥህን ነው። ተመክሮው ሲታከል ደግሞ ሊቅና ዓራት ዓይናማ – ያደርገዋል። የመንፈስ ቅኔ፤ የቃል ጣዝማ በመሆኑ አፍንጫው ረጅም ጆሮው ትልቅ ናቸው። ያዬሁትና የሰማሁት ግን ያጠረ – የተጣበቀ – ብነት የተጠናወተው ጉድ ነው። ቢያንስ ለራስ ሰብዕና እና ታሪክ እንዴት ባዕድ ይሆናል – አንድ ጋዜጠኛ? ? ? ?! ያደፈው ተመሳሳይ መፈለጉን እንዴት ማስተዋል ይሳነዋል አንድ ሥልጡን ጋዜጠኛ?! – ተመክሮው ቢያንስ ለምን እንደተፈለገ በዛ ባዕዳዊ ቦታ መፈልፈል እንዴት – ያቅተዋል አንድ የሚደያ ፍጡር? ሰሞኑን የተከበሩ ዶር ታደሰ ብሩ የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር አካል ያደረጉት ቃለ ምልልስ – ነበር። ያ ቃለ ምልልስ ዓይናማ ዳንቴል በውሃ አርሶ እርጥቡን መሬት ላይ ቢጥሉት ትቢያ ተሸክሞ – ይነሳል። ዶር. ታደስ ብሩ ለቃለ ምልልሱ ጥያቄ የሰጡት መልስ የተቆለፈ – ዬጠላትን ጎራ የአውጫጪኝ ትዕይንትን የማረከ ሲሆን – ትቢያ አቅሞ፤ ሃቅን ግን መንበሩ ላይ ያዋለ ጉልላት ነበር ማለት ይቻላል – ለነፃነት ትግላችን። ወሸኔ! የባሻ ዒላማ እንደ አዳመጥከው ድሆ ፍግም ብሎ አፈር ግጦ እንዲቀር – አደረጉት። „ልብ ያለው ሸብ“ ይላል ጎንደሬ …..

ብይን ዬህሊና! ለቅን ወገኖቼ –

  • ቀደም ብዬ እንዳነሳሁት ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ በኢትዮጵያ ከረንት አፊርስ ተቋም በግንቦት 22 ቀን 2009 በሰጠው ቃለ ምልልስ „ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከዳኛ ብረቱካን ይብልጣሉ! ብርቱካን ምን አላት¡ ቦንብ የላትም፤ ፕሬዚዳንቱ ግን ቦንብ አላቸው“
  • የተከበሩ ዶር ሙሉአለም አዳሙ የ2009 ዓለምአቀፍ የሴቶችን ቀን ምክንያት በማድረግ በነበረን የ24 ደቂቃ ቃለ ምልልስ ውስጥ ስለ ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ እንዲህ ነበር ያሉኝ „ … አንዳንዶቹ ወደ ኔልሰን ማንዴላ የሚያስጠጓት አሉ። በእውነት ይህ የሚገባት ጀግና ቆራጥ የፍትህ ሴት ናት። ለሴቶች መኩሪያ ተምሳሌነት ስትሆን ከዚያም አልፎ ብዙዎቻችን ዬብርቱካን ተምሳሌነት የተከተልን፤ inspire ያደረገችን፤ ወደ ትግሉ እንድንሳተፍ የሳበችን ወጣት ናት። ወደፊት ለኢትዮጵያ ብሩኽ ተስፋ ሊያመጡ ይቻላሉ ተብለው ከሚጠቀሱት በጣም ጥቂቶች ውስጥ አንዷ ናት።“
  • ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ ከእሥር ከተፈታች በኋላ ያደረገችው የመክፈቻ ንግግር በሀገረ አሜሪካ „እኛ የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲያ ፓርቲ መሪዎች የሰውን ልጅ ክብር ከምር በመውሰዳችን ይህን ክብር የሚመጠን እና የሚያረጋግጥ የዲሞክራሲያዊ ሥርአት በሀገራችን ላይ ለማዬት በመጓጓታችን፣ ለዚህ ጉጉት መሳካት ከዜጋ የሚጠበቀውን ለመስራት በመቁረጣችና እና ይህን በመተግበራችን …  “

ውድ ለሴቶች ብቃት ክብር ያላችሁ ወገኖቼ ይህን እንግዲህ በተንጣለለው የህሊና ችሎት ሚዛን ላይ አስቀምጡት። …   „የሰውን ልጅ ክብር ከምር በመውሰዳችን ….“ ይህ ኃይለ ቃልን ነው ቀዳማይ እመቤት ኢቫ ፔሩ በምድረ ላቲን አሜሪካ እውን ያደረገቸው።

የተከበራችሁ የሀገሬ ልጆች ክብሮቼ  የሀገሬን ሴቶች፤ ወንዶች ወንድሞቼም – እናቶችን፣ እህቶችን፤ የትዳር አጋራችሁን፤ አክስቶቻችሁን፤ ሴት ጓደኛችሁን ለምታከብሩ ሁሉ ይህን አቅም አንቱ ያለውን ክቡር ዶር. ሙሉአለም አዳሙን ወይንስ ያራካሰውን ጋዜጠኛ ክፍሌ የትኛው ይሆን ለመንፈሳችሁ ቅርቡ?! የትውልድ – ቅርሱስ ማን ይሁን ትላላችሁ? ለሰው ልጅ ተፈጥሮ ለዛውም ዬእናትነትን ጠረን  አስጠግታችሁ  – ዳኙት። ፍርድ ለራስ ነው …. ለዚህም ነው በአንድ ወቅት „ላቂያ“ በሚል እርእስ ውስጤ ለዶር. ሙሉአለም አዳሙ ያለውን ፍጹም የተለዬ አክብሮትና ታማኝት የገለጽኩት። በመንፈሴም አለኝ የምለው  – ጋሻዬም። የክብር – ሰዌም!

ክውና – አቶ ወንድም ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ እንዲህ ሆነልህ – እግዚአብሄርን አመሰገንኩኝ፤ በቤተ ኢትዮጵያዊነት ተቋም የሴቶችን የእኩልነት አቅም እንዲሁም የቅንጅትን መንፈስ ቀጣይነት ያወጀችን ብቁ መሪ ካራከስክበት ዕለት ጀምሮ፤ በቤትህ ትውር አለማለቴ ዛሬ ክብሬ – ሆነልኝ። የፈልግኸውን ዓይነት መልስ ብትጽፍም ይህ የመጨረሻዬ – ይሆናል። ምን አልባት ለዚያ ቢያበቃን በልዕልት ኢትዮጵያ ትምህርተ ሥነ – እኩልነት የህሊና መሰናዶ ት/ቤት ተከፍቶ በተማሪነት ትምህርቱን ወስደህ የተመረቅክ ቀን እንታረቅ – ይሆናል፤ በህይወት – ከቆዬሁ። ማን ያውቃል? ነገ አዲስ ቀለም አዲስ ቀንም ነው። ጊዜ ታሪክን ይሠራል  – ይጽፋልም።  …. በተረፈ በቦሌ ጫካ ተገኝተህ የድሉን ደወል ዬማብሰር ትልመ – ጉዞህን በሚመለከትም መልካም ዕድል እምኝልሃለሁ ከልብ – Good luck! ቧልት እንዳይመስልህ። ድንግል ትጠብቅህ። መኖር ተቋም ነውና የሰው ልጅ ሰብዕና የገበጣ ጨዋታ ባለመሆኑ መማር ትችል ዘንድ ዕድሜውን ጨምሮ ይስጥህ – አባታችን። ደህና – ሁኑልኝ።

የጹሑፌ ምንጭ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45140#sthash.lDgOQPc2.dpuf

የኔዎቹ መሸቢያ ሰንበት።

  • ማሳሰቢያ ለውዶቼ – ራዲዮ ሎራ ፕሮግራሙ የጸጋዬ ራዲዮን ጨምሮ ወደ 300 ዝግጅቶቹ በሙሉ የበጋ እረፍት ላይ ነው።

አርበኞቻችን መንገዶቻችን ናቸው!

ሴቶች ለነፃት ትግል ፍቱን ናቸው!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።


ትንታኔ:- የፕሬዝዳንት ኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት ዜና አቀባበልና ውጤት ከ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ጋር

$
0
0

አሉላ ከበደ

obamaሁለት ቀናት የቀረው የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ጉብኝት ዜና አቀባበልና የጉብኝታቸው ውጤት፤ ትንታኔው የሚያተኩርባቸው ጭብጦች ናቸው።፤

ትዝብትና ምሁራዊ ትንታኔውን የሚሰጡን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና ትምሕርት ሲያስተምሩ የቆዩትና በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትንታኔ በማቅረብ የሚታወቁት ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ናቸው።

ታፍኖ የታሰረው መምህር የት እንዳለ አልታወቀም

$
0
0

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

11745397_744508902341437_379102506433974454_nሀምሌ 1/2007 ዓ.ም ጎንደር ከተማ ውስጥ በፖሊስና ደህንነቶች ታፍኖ የታሰረው የሰማያዊ ፓርቲ አባል መምህር አለላቸው አታለለ የት እንደሚገኝ ለማወቅ እንዳልቻሉ ቤተሰቦቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ በጎንደር መምህራን ኮሌጅ የአይ ሲቲ መምህርና የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ የሆነው መምህር አለላቸው አታለለ ሀምሌ 1/2007 ዓ.ም ወደ ደብረታቦር ተወስዶ በደብረታቦር ከተማ አንደኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ እንደነበር መረጃ ደርሷቸው ታሰረ የተባለበት ቦታ ድረስ ሄደው ቢጠይቁም እንደሌለ ተነግሯቸዋል፡፡ ሌሎች እስር ቤቶች ውስጥ ቢያጠያይቁም ሊያገኙት እንዳልቻሉ ገልጸዋል፡፡

መምህር አለላቸው ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ ከቤተሰቦቹ ጋር ሳይገናኝ የቆየ ሲሆን ከሳምንት በፊት ወደ አዲስ አበባ ተወስዷል በመባላቸው አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ እስር ቤቶች ውስጥ እስከ ዛሬ ሀምሌ 18/2007 ዓ.ም ቢጠይቁም እንደሌለ ተነግሯቸዋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

$
0
0

• ‹‹የታሰርኩት የመተማ መሬት ለሱዳን መሸጡን በመናገሬ ነው›› አቶ አግባው ሰጠኝ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

political-prisoners-ethiopia2በእነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት የተከሰሱት 16 የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ዛሬ ሀምሌ 17/2007 ዓ.ም የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ አመራሮቹ ሀምሌ 1/2007 ዓ.ም በጠበቆቻቸው በኩል የክስ መቃወሚያና የዋስትና ጥያቄ አቅርበው፣ ሀምሌ 13/2007 ዓ.ም አቃቤ ህግ ለጥያቄው መቃወሚያ እንዲያሰማ ቀጠሮ ተሰጥቶት ተቃውሞ ሳያቀርብ ቀርቷል፡፡ በመሆኑም የተከሳሾቹ ጠበቃዎች ደንበኞቻቸው በሽብር ወንጀል ያልተሳተፉ በመሆናቸው በሽብር ወንጀል መከሰሳቸው ትክክል አለመሆኑን፣ ቢቻል ክሱ ተዘግቶ እንዲሰናበቱ፣ ይህ ባይሆን እንኳ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆላቸው በውጭ ሆነው እንዲከራከሩ ያቀረቡትን ጥያቄ መሰረት አድርጎ ብይን እንዲሰጥላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀው ለዛሬ ተቀጥሮ ነበር፡፡ ይሁንና ዛሬ ሀምሌ 17/2007 ዓ.ም በልደታ ፍርድ ቤት 14ኛ ምድብ ችሎት በዋለው ችሎት ፍርድ ቤቱ ‹‹በመረጃ የሚረጋገጥ ይሆናል›› በሚል ጠበቆች ያቀረቡትን መቃወሚያ ውድቅ አድርጓል፡፡

ፍርድ ቤቱ የክስ መቃወሚያውን ውድቅ ካደረገ በኋላ የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ በጠየቀው መሰረት 16ቱም አመራሮች የተከሰሱበትን ወንጀል አልፈፀምንም ሲሉ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ ከተከሳሾቹ መካከል የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አቶ አግባው ሰጠኝ ‹‹የታሰርኩት የመተማ መሬት ለሱዳን መሸጡን በመናገሬ ነው፡፡ ትናንትም መሬቱ መሸጡን ስናገር ቆይቻለሁ፡፡ ወደፊትም እናገራለሁ፡፡ የተከሰስኩት በመሬቱ ጉዳይ ነው እንጅ አሁን የተከሰስኩበትን ወንጀል ፈጽሜ አይደለም፡፡›› ሲል የእምነት ክህደት ቃሉን ሰጥቷል፡፡ ተከሳሾቹ የመኢአድ፣ የቀድሞው አንድነትና የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ናቸው፡፡
በእነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ የተከሰሱት አመራሮች፡-

1ኛ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮነን
2ኛ በላይነህ ሲሳይ
3ኛ አለባቸው ማሞ
4ኛ አወቀ ሞኝሆዴ
5ኛ ዘሪሁን በሬ
6ኛ ወርቅየ ምስጋናው
7ኛ አማረ መስፍን
8ኛ ተስፋየ ታሪኩ
9ኛ ቢሆነኝ አለነ
10ኛ ተፈሪ ፈንታሁን
11ኛ ፈረጀ ሙሉ
12ኛ አትርሳው አስቻለው
13ኛ እንግዳው ቃኘው
14ኛ አንጋው ተገኘ
15ኛ አግባው ሰጠኝ
16ኛ አባይ ዘውዱ ናቸው፡፡

በእነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ የተከሰሱት 16 የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች የአቃቤ ህግን ምስክር ለመስማት ለነሃሴ 12ና 13/2007 ዓ.ም ተቀጥረዋል፡፡ በተመሳሳይ በዛሬው ዕለት በልደታ ፍርድ ቤት የእምነት ክህደት ቃል ለመስጠት ተቀጥረው የነበሩት እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ ለሀምሌ 28/2007 ዓ.ም ተቀጥረዋል፡፡

ስለ ቀድሞ ባልንጀራዬ በጣም በሥሱ (ደረጀ ሀብተወልድ-ኢሳት)

$
0
0

በጠጠሩ ምትክ፣ በወንጭፉ ፋንታ፣
የሳዖልን ካባ፣ ያለበሱት ለታ፣
ያኔ ጊዜ ነው ዳዊት ፣ላይድን የተረታ።

ከዳዊት ከበደ(አውራምባ ታይምስ) ጋር ያለን ወዳጅነት ከሀዳር ምስረታ ዋዜማ አንስቶ እስከ ቃሊቲ ይዘልቃል። በዚህ ረዥም ጊዜ ውስጥ ክፉውንም፣ ደጉንም አሳልፈናል። (…እንዳስፈላጊነቱና እንደሁኔታው እያደር የምንጫዎተው ነገር ሊኖርም፤ላይኖርም ይችላል።)
Dawit kebede
-ከእስር ከተፈታን በኋላ እኛ ስንሰደድ ዳዊት ፈቃድ አግኝቶ አውራምባ ታይምስን ጀመረ። በነጻ የተፈቱት ሢሳይ አጌናና እስክንድር ነጋ ፈቃድ ተከልክለው በይቅርታ የተፈታው ዳዊት ፈቃድ ያገኘበትን ምክንያት የሚያውቁት እግዜርና ፈቃድ ሰጪው አካል ቢሆኑም፤ ዳዊት አውራምባን በመጀመሩ ደስተኛ ነበርኩ። ለዚህም ነበር አውራምባን ሲያቋቁም በጋዜጣው እንድሳተፍ ሲጠይቀኝ በደስታ ፈቃደኝነቴን የገለጽኩለት። ቃል በገባሁትም መሰረት ጽሁፌን እንዳያትም “ማስጠንቀቂያ እስኪደርሰው ድረስ” ባመቸኝ ጊዜ “ይድረስ ለባልንጀራዬ” በሚል ርዕስ አልፍ አልፎ ጽሁፎችን ልልክለት ሞክሬያለሁ።

-ዳዊት ለሲፒጄ ሽልማት ሲታጭ እነ ቶም ሩድስ አስተያዬት ያሰባሰቡት ከሌላ አካል ሳይሆን ከእኛው ከኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ነው።በወቅቱ ከአንዳንድ የሥራ ባልደረቦቼ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ስንነጋገር ያስተዋልኩት ነገር ፤ እኔን ጨምሮ ሁላችንም የዳዊትን መሸለም በደስታና በጥሩ ጎኑ መመልከታችንን ነው። “ሲፒጄ አንድ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛን( የሥራ ባልደረባችንን) ለዚህ ሽልማት ማብቃቱ ፤ ለኛ ለኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች የሰጠውን ክብርና አትኩሮት ያሳያል ፤ ዳዊት ተሸለመ ማለት እኛ ተሸለምን ማለት ነው” የሚል ነበር የሁላችንም መደምደሚያ።ከዚህ ውጪ አንዳንድ ሰዎች እንዳሉት፦“እንዴት ሆኖ?፣በልምድም፣ በከፈሉት መስዋዕትነትም ሆነ በሙያው ከእርሱ የሚልቁ ጋዜጠኞች እያሉ ሲፒጄ እንዴት እርሱን ይመርጣል? ምናምን..” የሚል ክርክርም ሆነ ጥያቄ በአንድኛችንም አልተነሳም። ይህንን፤ ማለትም እርሱ ለሽልማት በመታጨቱ በሁላችንም ዘንድ ጥሩ መንፈስ የማደሩን ነገር ፤በሥሱም ቢሆን ለዳዊት ሹክ ያልኩት ይመስለኛል።

– በሽልማቱ ዋዜማ ለሲ. ኤን. ኤን በሰጠው ቃለ-ምልልስ፦ “ ስደትን በፍጹም እንደማይሞክረው ብቻ ሳይሆን፤ መሥራት ተስኖን የተሰደድነውን ባልደረቦቹን “በመሰደዳችን” ሸንቆጥ ያደረገን ዳዊት ፤ በሽልማቱ ማግስት ብዙም ሳይቆይ አንድ ቀን ምሽት ላይ ድንገት መሰደዱን ነገረኝ። ከነበረን ቅርበት አኳያ አሜሪካ እንደደረሰ ምሽት ላይ መጀመሪያ የሆነውን ነገር የነገረኝ ለኔ ነበር። ደነገጥኩ፣አዘንኩም። ከሱ መሰደድ በላይ አውራምባ ታይምስ መዘጋቷ፣በጋዜጠኞቹም ላይ ድንገት የመበተን አደጋ ማንዣበቡ ይበልጥ አሳዝነኝ።”አይዞህ!በርታ! ጠንክር!!” ብዬ ላጽንናው ሞከርኩ። ለጊዜው ከነበረበት ቦታ አኳያ ከዚህ በላይ ማውራት አልቻልንም።

ይሁንና፦”ይቅርታዬን በማንሳት የቃሊቲውን ፍርድ ሊያጸኑብኝ እንደኾነ መረጃው ደርሶኝ ነው የወጣሁት።” በማለት ለመሰደዱ የሰጠኝ ምክንያት ለረዥም ጊዜ ግርታ ሳይፈጥርብኝ አልቀረም። ምክንያቱም ዳዊት ከቅንጅት መሪዎች ጋር በይቅርታ ይፈታ እንጂ እሱና ሌሎች ሦስት ጋዜጠኞች የተፈረደባቸው አራት ዓመት አካባቢ ነው። አመክሮው ሲታሰብ፤ አንድ የአራት አመት ፍርደኛ እስር ቤት የሚቆየው 32 ወራት ነው። ይህ ማለት ወደ 20 ወራት የታሰረው ዳዊት ይቅርታውን አንስተው ፍርዱን ቢያጸኑበት እንኳ ሊታሰር የሚችለው ከ12 ወራት(አንድ ዓመት) አይበልጥም ማለት ነው። እንግዲህ እሱ ያለውን አምነን ብንቀበል እንኳ “እሞታታለሁ እንጂ ስደትን ፈጽሞ አማራጭ አላደርግም” ያለው ዳዊት የተናገረው ቃል በጆሯችን ማቃጨሉን ሳያቆም ለስደት የተነሳው አንድ ዓመት ላለመታሰር ብሎ ነው ማለት ነው። ? ? ? …እናም ተሰደደ፤ ስደትንም ለመደ።
-እያደር እየለመደ ሲመጣ አውራምባ ታይምስን ከዚህ ሆኖ ስለሚቀጥልበት ከተቻለ ደግሞ አብረን መሥራት በምንችልበት ሁኔታ መነጋገራችንን ቀጠልን።

ኢሳት ላይ በቶሎ ሥራ የመጀመር ፍላጎቱ ከአንዳንድ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ለጊዜው እደግመዋለሁ ለጊዜው ሳይሳካ ቀረ። ጥቂት እንዲታገስም ተነገረው።
-ይህን ተከትሎ አውራምባን ወደማስቀጠል ሀሳቡ በማዘንበሉ ከአርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በዬነ ጀምሮ- እንደ ሚዲያ እስከ ኢሳት ድረስ በዋሽንግተን ዲሲ የአውራምባን ምስረታ በማስተዋወቅና በመቀስቀስ በተቻለ መጠን ከፍተኛ ድጋፍ አደረጉለት። በኢሳት ራዲዮና ቲቪ ላይም እንግዳ ኾኖ እየቀረበ በአንዳንድ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ አስተያዬቱን ሲገልጽም ቆዬ።
-በዚህ ሁሉ ሂደት ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ወይም ከጧቱ አንስቶ እስከመጨረሻው ድረስ ዳዊት ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች በተለዬ መልኩ ለዶክተር ብርሀኑ ፍቅር እንደነበረው ነበር የማውቀው። ዶክተር ብርሀኑም እንዲሁ ለዳዊት መልካም አመለካከት ያለው ሰው እንደኾነ ራሱ ዳዊት ያውቀዋል።
-ይህ በእንዲህ እንዳለ ዳዊት ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ በመመለሻው ዋዜማ በሚያወጣቸው ጽሁፎችና ቪዲዮዎች ድንገት ዶክተር ብርሀኑ እና ንቅናቄያቸው ግንቦት 7 ላይ መተኮስ መጀመሩ አስደነገጠኝ። ከጋዜጠኝነት ሥነ-ምግባር ባፈነገጠ ሁኔታ ዶክተር ብርሀኑ ላይ ጥቃቱን አጠናክሮ ከፈተ።ይህ የዳዊት 380 ዲግሪ የመዞር ክስተት፤ በጊዜው እኛን ብቻ ሳይሆን በቅርብም፣በሩቅም የሚያውቁትን ሁሉ ማስገረሙ ይታወቃል።

ከዚያም አልፎ አውራምባ ላይ በሚያወጣቸው ጽሁፎች ሁሉ ኢሳትን- “የግንቦት ሰባት ልሳን” ማለት ጀመረ።

ይሁንና እሱ እንዳለው ኢሳት የግንቦት ሰባት ልሳን ቢኾን ወይም ኢሳት በግንቦት ሰባት ጫና የሚሽከረከር ቢኾን ኖሮ ዳዊት እስካሁን የኢሳት ሠራተኛ ሆኖ በቀጠለ ነበር። ዳዊት ኢሳት ላይ በቶሎ እደግመዋለሁ በቶሎ ሊሠራ ያልቻለው ከግንቦት ሰባት መሪዎች ይሁኝታ በመታጣቱ እንደኾነ አድርጎ ቢያስብም፤ ይህ አስተሣሰቡ ግን የመርጋ በቃናን አገላለጽ ልዋስና መት ፐርሰንት ስህተት ነው።

አንድ ምሳሌ ልጥቀስ፦ዳዊት ኢሳት ውስጥ የመሥራት ፍላጎት እንዳለው የገለጸ ሰሞን ዶክተር ብርሀኑ ለሥራ ጉዳይ ወደ አውሮፓ መጥቶ ነበር። ዶክተር ብርሀን፣ፋሲል እና እኔ አንድ ምሽት ራት እየበላን ሳለ ዶክተር ብርሀኑ ዳዊት በኢሳት ለመሥራት መፈለጉን እንደገለጸለትና ቦታ ካለ ይቀጠር ዘንድ ለማኔጅመንቱ ግፊት እንድናደርግለት አጥብቆ ጠየቀን። በዚህም ሳያቆም የዳዊት ኢሳት ውስጥ መግባት ይኖራቸዋል ብሎ የሚያስባቸውን ጠቀሜታዎች ሰፊ ሰዓት ወስዶ በዝርዝር ነገረን።

ይሁንና ኢሳት ውስጥ ስለሚቀጠሩ ጋዜጠኞችም ሆነ ስለ ሌሎች አስተዳደራዊ ጉዳዮች የሚወስኑት ማኔጅመንቱና የኤዲቶሪያል ቦርዱ ናቸው ።ዶክተር ብርሀኑ ዳዊት በቶሎ ኢሳት ውስጥ ሥራ እንዲጀምር ፍላጎቱ ቢኾንም የሱ ድርሻ ሃሳብ ከማቅረብ የዘለለ አይደለም።እደግመዋለሁ፦በዚህ ጉዳይ ላይ ውሳኔ የሚሰጡት ማኔጅመንቱና የኤዲቶሪያል ቦርዱ በጋራ ነው።ይህን ፕሮፌሰር ብርሀኑም ያውቀዋል። ለዚህም ነበር ዶክተር ብርሁኑ ፦”እናንተ ለማኔጅመንቱ ሃሳብ ብታቀርቡ..” የሚል አስተያዬት ደጋግሞ ሢሰጥ የነበረው።

በመጨረሻም የኤዲቶሪያል ቦርዱና ማኔጅመንቱ በመነጋገር ዳዊት ከኢሳት ኤዲቶሪያል ፖሊሲ ጋር በተጣጣመ መልኩ ከፈለገ በትግረኛ አለያም በአማርኛ በሳምንት አንድ ጊዜ የሚተላለፍ የራሱን ፕሮግራም እንዲያዘጋጅ ስምምነት ላይ ተደረሰ። ይህም ውሳኔ በቅርቡ ካሉት ጋዜጠኞች በአንድኛው እንዲነገረው ተወሰነ።ይሁንና ዳዊት ውሳኔውን ሳይጠብቅ ተነስቶ ወደ አሪዞና አቀና። ውሳኔውን ሳይጠብቅ ወደ አሪዞና የሄደው፦ “ለምን ቶሎ ሥራ አልጀመርኩም? ሆን ብለው ነው እያሹኝ ያሉት” ከሚል ኩርፊያ ተነስቶ እንደሆነ እጥረጥራለሁ። ምክንያቱም ዳዊትን ለረዥም ጊዜ እንደማውቀው በባህርይው ቶሎ ተናዳጅና ችኩል ነው። ሀቁ ይኼው ነው። ይህ እኔ አሳምሬ የማውቀው እውነት ነው። ምናልባት ሌላ የማላውቀው ነገር ኖሮ አሳንሸው ይሆናል እንጂ አልጨመርኩበትም።ጓደኞቼም፣ ዳዊትም ምስክሮች ናቸው።ከነሱ በላይ ደግሞ ህሊና አለ።

ዳዊት ግን ይህን እውነታ አልተቀበለውም፤ወይም አላመነውም።በቶሎ ሥራ ያልጀመረው የግንቦት ሰባት መሪዎች በተለይም ዶክተር ብርሀኑ “እንድሠራ ስላልፈለገ ነው” ብሎ ያስብ ነበር። ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ተቋማት -በሰዎች(በግለሰቦች) ከሚሽከረከሩበት ባህል ውስጥ የወጣን ከመኾናችን አንጻር ዳዊት ይህን በማሰቡ አልተደነቅኩም።ምናልባት እኔም በሱ ቦታ ብኾን እንዲህ ላስብ እችል ይሆናል። ይህ አስተሣሰቡ ግን ስህተት እንደኾነ በወቅቱ ነግሬዋለሁ።

አይገርምም? ዶክተር ብርሀኑ “እባካችሁ አስገቡት?” እያለ ይማጸናል-ዳዊት “እንዳልገባ ያደረገኝ እሱ ነው”ብሎ ያስባል።

ዶክተር ብርሀኑ ሁሌም በአንድ ባህርይው ያሳዝነኛል። ያም ባህርይው ማናቸውንም ሰው በሙሉ ልቡ ማመኑ ወይም ለጥርጣሬ ጥቂት ቦታ እንኳ አለማስቀረቱ ነው። ዳዊት እሱ ላይ አነጣጥሮ መጻፍ እስኪጀምር ድረስ ዶክተር ብርሀኑ ዳዊት ኢሳት ውሥጥ እንዲሠራ ሀሳብ ማቅረቡን አላቆመም ነበር። ያ ብቻ አይደለም፤ ዳዊት እንደ ግለሰብ በእርሱ፣ እንደ ድርጅት በሚመራው ንቅናቄ ላይ አነጣጥሮ በተደጋጋሚ መጻፉን ተከትሎ ብዙዎች “ሰላይ”የሚል ስም ሢሰጡት እሱ ግን ይህን አይቀበልም። “ዳዊት ወደ አሜሪካ ሢመጣ አገኘዋለሁ ብሎ የጠበቀውን ነገር ባለማግኘቱ ነው በእልክ ወደ ሌላ አቅጣጫ የገባው” ብሎ ነው የሚያስበው። ከዚህ ውጪ ለሚጻፍበት ነገር ብዙ ትኩረት አይሰጠውም።
-ለህይውቱ ሰግቶ የተሰደደው ዳዊት በክብር አገር ቤት ተመለሰ። በ”ስደቱ” ዋዜማ “ለስድብ የተፈጠሩ ጥንዶች” ብሎ ከጻፈባቸው፣ እንዲሁም የሱን ዋና አዘጋጅ ውብሸ ታዬን ካሣሰሩት ከነ ሚሚ ስብሀቱ ካምፕ ጋር በይፋ ተቀላቀለ።

በአውራምባ ምክንያት ከህጻን ልጁ ተለይቶ የታሰረው ውብሸት ግን እስካሁን በቂሊንጦ እየማቀቀ ይገኛል።

-ከሰሞኑ ዶክተር ብርሀኑ ነጋ ወደ ግንባር ማቅናቱ ይፋ ከሆነበት ዕለት አንስቶ ዳዊት ዕረፍት አጥቷል። “ ጩኽ! ጩኽ! ተሳደብ! ተሳደብ!” ብሎታል።ከዛሬ ነገ ንዴቱ በርዶለት ወደ ኅሊናው ይመለሳል የሚል ተስፋዬን ሁሉ ጨርሶ ገደል ከቶታል።

-ዳዊት ያሰባሰበው መረጃ አለቀ መሰል አሜሪካ በነበረበት ወቅት በዶክተር ብርሀኑ ልጆች ምርቃት ሥነ-ስርዓት ላይ በእንግድነት ተጋብዞ የተገኘበትን ቤተዘመዳዊ የግብዣ ሥነ ስርአት በቪዲዮ ቀርጾ እነሆ ገጹ ላይ ለብዶታል። “የእውነት ታጋዮች ይህን ይመስላሉን?” በማለትም ሊሳለቅ ሞክሯል። ቪዲዮው የሚያስተላልፈው መልዕክት ግን እሱ ካሰበው በተቃራኒው ነው።ቪዲዮውን ያዩ ሰዎች ሁሉ ዶክተር ብርሀኑ የአሁን ለደረሰበት ውሳኔ ይበልጥ አድናቆታቸውን ሢሰጡ ነው ያደመጥኳቸው።

ስዬ አብርሀ በአንድ ወቅት ባቀረቡልን ጽሁፍ፦ “አሁን ያሉትን የኢህአዴግ ደጋፊዎችና አባሎች አስተሣስሮ ያቆማቸው እህል ውሀ ነው” ማለታቸውን አስታውሳለሁ። ትክክል ነው። ህወሀት-ኢሃዴግን በአባልነትም ሆነ በደጋፊነት ከከበቡት መካከል ብዙዎቹ -በቃኝ በማያውቀው ሆዳቸ ተሸንፈው እንጅ በድርጅቱ ዓላማ አምነውበት እንዳልሆነ ግልጽ ነው።ለነሱ የመጨረሻ ግባቸው እየበሉና እየጠጡ መኖር ነው።እነ ዶክተር ብርሀኑ ደግሞ “ ህዝባችን በመከራ፣ ሀገራችን በጭቆና በተያዙበት ወቅት በምቾት መኖር ዕረፍት አይሰጠንም” ብለው በረሀ ወረዱ።ይህ የዶክተር ብርሀኑ ውሳኔ ለሀወሀት-ኢሃዴጎች እብደት ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም በነ ሆዶሙ አምላኮሙ እና-በነ ዶክተር ብርሀኑ መካከል ሰፊ የአስተሣሰብ ልዩነት አለ።ይህ ልዩነት በአልዓዛርና- በሀኬተኛው ባለጸጋ መካከል እንዳለው ገደል ይሰፋል ብል አጋነንክ እንደማትሉኝ ተስፋ አደርጋለሁ። አዎ!ለኮንዶሚኒየምና ለ40 በ 60 ህሊናቸውን ሸጠው በወገን ስቃይ ለሚቀልዱ ሰዎች- እነ ነዶክተር ብርሀኑ ለነጻነት ሲሉ የተደላደለ ኑሯቸውን ትተው የመከራ ጽዋን ለመጎንጨት ወደ ቀራኒዮ መጓዛቸው ፈጽሞ ሊገባቸው አይችልም። የዶክተር ብርሀኑ ውሳኔ ትልቅና ጥልቅ ትርጉም ያለው በመከራና በስቃይ ውስጥ እየማቀቀ ለሚገኘውና ከፍትህ ጎን ለቆመው ብዙሀኑ ኢትዮጵያውዊ ነው።(እቀጥላለሁ)

ትንሽ ስለ ፕ/ር ብርሀኑ –    ይገረም አለሙ

$
0
0

Birhanu Negaፕ/ር  ብርሀኑ ነጋ ሰሞኑን የተናገሩትን ስሰማ አስር አመት ወደ ኋላ ተመልሼ አንዳስብ ግድ አለኝ፡፡ ፕ/ሩ ኢትዮጵያም ሆኑ አሜሪካ ወይንም አስመራ ሰላማዊ ተጋይም ሆኑ ሁሉን አቀፍ የትግል ስልት አራማጅ እምነት አስተሳሰባቸው የማይለዋወጥ መሆኑን ለመገንዘብ ቻልኩኝ፡፡

ጊዜው 1997 መጨረሻ ወቅቱ ሕዝብ ይመርጣል ጠመንጃ ያሸንፋል ሆኖ የፖለቲካው አየር የጋመበት ቅንጅትም ወያኔም በየራሳቸው በጭንቅ ውስጥ የነበሩበት ነው፡፡ የወያኔ ጭንቀት ሥልጣኑን ላለማጣት ሲሆን የቅንጅት ጭንቀት ደግሞ ሥልጣን ወይንም ሞት የሚለው ወያኔ ወንበሩን ከሚያጣ ሀገር ቢፈርስ ሕዝብ ቢጨራረስ ደንታ የሌለው በመሆኑ ነገሮች ወደዚህ አንዳያመሩ በማሰብ ነው፡፡

በዚህ ሁኔታ ላይ ሆነው ቅንጅቶች ከመረጣቸው ሕዝብ ጋር ለመወያየት አዲስ አበባ ላይ በየሳምንቱ ቅዳሜና ዕሁድ በየወረዳዎች ስብሰባዎችን ማዘጋጀት ጀመሩ፡፡ ኢ/ር ኃይሉ ሻውል ለተወካዮች ምክር ቤት የያኔው ዶ/ር ብርሀኑ ለአዲስ አበባ ምክር ቤት ተወዳድረው በተመረጡበት ወረዳ 23 ብስራተ ገብርኤል አካባቢ በተጠራ ስብሰባ ላይ  የወረዳው ነዋሪ ባልሆንም ተገኝቻለሁ፡፡ወደ አዳራሹ የመጣ ማንም ኢትዮጵያዊ የነዋሪነት፣ የአባልነት፣ የጎሳም ሆነ የኃይማት ልዩነት ገደብ ሳይደረግበት ስብሰባውን የመሳተፍ ሙሉ መብት ነበረው፡፡

መድረክ ላይ ያሉት ሰዎች ተራ በተራ ንግግር ሲያደርጉ የዶ/ር ብርሀኑ ተራ ደረሰ፡፡ (በወቅቱ በነበራቸው ማዕረግ ነው የምጠራቸው)የዶ/ሩ ንግግር የተሰብሳቢውን ስሜት በመቆጣጠሩ አዳራሹ በጭብጨባ ተናውጧል፡ “ወያኔዎች ያለ ጸብና ቅራኔ መኖር አይችሉም፣እኛ ደግሞ አንጣላቸውም፤የሚጣሉት ሲያጡ ርስ በርሳቸው ይጣላሉ፣… እኛ በምንም መልኩ አነርሱን አንሆንም ፣እነርሱን የሆን እለት ተሸንፈናል ማለት ነው፤” አዳራሹ በጭበጨባ ቀለጠ፡፡ ዶ/ር እየተናገሩ ነው “ ዛሬ እዚህ አዳራሽ የተገኛችሁ ሁሉ ወደየቤታችሁ እንደተመላሳችሁ የተጣላችሁት የኢህአዴግ አባለል ካለ የበደላችሁ እሱ እንኳን ቢሆን እናንተ ይቅርታ እየጠየቃችሁ ታረቁ” ተቃውሞ የለም ድጋፍ ጭብጨባ ብቻ እንደውም አንዳንድ ወጣቶች በድምጽም እሺ ሲሉ ይሰማ ነበር፡፡ እኔ ግን በተመስጦ እያዳመጥኩ በሀሳብ ወደ ፊትና ወደ ኋላ እየነጎድኩ  አእምሮየ እጆቼን ለጭብጨባ ማዘዝ አልተቻለውም፡፡ የዶ/ር ብርሀኑ ንግግር ቀጥሏል፡፡

በየመድረኩ ሆነ በመገናኛ ብዙኃን ከፖለቲከኞቻችን ( በሁሉም ጎራ ካሉት) በአብዛኛው ስንሰማ የኖርነው ልክ ልካቸውን መንገር በሚል አስተሳሰብ የተቃኘ፣ የጠላትነት ስሜት የሚንጸባረቅበት እናሸንፋችኋለን ልክ እናስገባችኋለን ወዘተ በሚል ፉከራ የታጀበ የበቀል ቃና ያለው ወዘተ ንግግር  በመሆኑ ነበር የዶ/ር ብርሀኑ ንግግርና አነጋገር በተመስጦ ያነጎደኝ፡፡

የዶ/ር ብርሀኑ ንግግር የቅንጅት አመራር አባል ያውም በምርጫ አሸንፎ ተሸንፈሀል የተባለ  ፖለቲከኛ ሳይሆን ከፈጣሪ የተላከ በአንድ እጁ እየሱስ ክርስቶሰ የተሰቀለበትን የፍቅርና የነጻነት መሰቀል በሌላ እጁ ቃሉ የተጻፈበትን ቅዱስ መጽኃፍ ይዞ በፈጣሪ ስም የሚያስተምር የኃይማኖት ሰባኪ ነበር የሚመስለው፡፡ ከሀይማኖት ሰባኪም ስለ ፍቅር ስለ አንድነት ስለ ይቅር ባይነት ለመስበክ ተዘጋጅቶ የመጣ የዚህችን አለም ህይወት አሸንፎ ራሱን የሰጠ መምህር ነበር የሚመስሉት፡፡

ፖለቲካ መጠላላት በሆነበት ሀገር፤ አይደለም በአላማ ተለይቶ የሚታገልን በአመለካከት የተለየን ካላጠፉ አንቅልፍ የማይወስዳቸው በበዙበት ዘመን፤ የፖለቲካው ጨዋታ ጥሎ ማለፍ  የሰዎቹ ባህርይ ጥላቻና በቀል የሚንጸባርቅበት በሆነበት ከዚህም በላይ ስሜት ፖለቲካውን በተቆጣጠረበት በዛ ወቅት ከዶ/ር ብርሀኑ  አንደበት የተደመጠው ንግግር  ቀልብ የሚስብ ብቻ ሳይሆን ሁለንተናን የሚገዛ ነበር፡፡ እናም ፈጣሪ ይህችን ሀገር ሊታረቃት ይሆን! ከመገዳደል አዙሪት ልንወጣና የዴሞክራሲ ቀንዲል ልናይ ይሆን!ወዘተ እያልኩ ራሴን እየጠየኩ ተስፋና ጨለማ በአንድ ላይ እየታዩኘ ነበር በሀሳብ የነጎድኩት፡፡

ግና ተስፋዬ እንደ ጉም ሲበን ወራት አልተቆጠሩም፡ እኚህ ፍቅርን የሰበኩ ይቅር ባይነትን ያስተማሩ የአንድ ሀገር ልጅነት ከፖለቲካ አመለካከት ልዩነት በላይ መሆኑን በተግባር ለማሳየት የጣሩ ሰው ወንጀለኛ ተብለው ከትግል ጓዶቻቸው  ጋር ታሰሩ፡፡ ከመታሰራቸው በላይ ዘር ማጥፋት ሀገር ክህደት ህገ መንግሥታዊውን ሥርዓት በኃይል ለመጣል መሞከር ወዘተ በሚል መከሰሳቸው የሀገራችንን መጻኢ እድል ጨለማነት በበግልጽ ያሳየ ነበር፡፡

ዶ/ር ብርሀኑ በቃሊቲ ወህኒ ቤት ሆነው በጻፉት የነጻነት ጎህ ሲቀድ በተሰኘው መጽኃፋቸው የገለጹት ከላይ የገለጽኩትን እምነት አመለካከታቸውን የሚያንጸባርቅ የሰላም ደቀ መዝሙርነታቸውን የሚያሳይ ለመሆኑ ያነበበ ሁሉ የሚያረጋግጠው ይመስለኛል፡፡ ከሁለት አመት የእስር ቆይታ በኋላ አሜሪካ ሄደው ወያኔ በሰላማዊ ትግል ብቻ ስልጣን አንደማይለቅ በተግባር አረጋግጠናል፤ነጻነት ከተመኘን፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ አንባገነን አገዛዝ አንዲላቀቅ የምንፈልግ ከሆነ ትግሉ ሁሉን አቀፍ መሆን አለበት ብለው ግንቦት 7ን ሲመሰርቱም ጡንቻ ወለድ የሆኑ ቃላት አልተሰሙባቸውም፡፡ አሸባሪ ተብለው በሌሉበት ተከሰው ሞት ቢፈርድባቸውም የጥላቻና የበቀል ስሜት አልተንጸባረቀባቸውም፡፡

እነሆ ልክ ከላይ የገለጽኩትን ቃል በተናገሩ አስር አመት( በምርጫ ማግስት መሆኑም ያመሳስለዋል) የጠመንጃውን ትግል ለመምራት ወደ አስመራ ሲያመሩ፤ ..ደም መፋሰስ ውስጥ ሳንገባ የሀገራችንን ችግር ቁጭ ብለን በመነጋገር ብንፈታ እንወድ ነበር.ይህ ጦርነት ወደንና ፈቅደን ሳይሆን በወያኔ እብሪት ተገደን የገባንበት  በመሆኑ ገደልን እያልን የምንፎክርበት አይደለም፡፡ ከሁለታችንም  የሚሞተው ወገን በመሆኑ እናዝናለን፤ አሁን ቢሆን ወያኔዎች ለድርደር ፈቃደኛ ከሆኑ እኛ ጦርነት ምርጫችን አይደለም፤ወዘተ ማለታቸውን ሰማን፡፡((ቃል በቃል አልጠቀስኩ ይሆናል) ይህም ዶ/ር ብርሀኑ የሚናገሩት በወቅታዊ ትኩሳት እየተገፉ፣ምን ብናገር አድማጭ ጆሮ አገኛለሁ በሚል ስልት ሳይሆን የሚያምኑበትን ለመሆኑ ይህ በትንሹ በአስር ዓመታ ውስጥ ከነገሮች መለዋወጥ ጋር ያልተለወጠው ንግግራቸው በቂ ማረጋገጫ ይመስለኛል፡፡

በዚህ ሁሉ ሂደትና አመታት ያልተለወጠ አላማና እምነት ከዚህ በኋላ ይለወጣል ተብሎ ባይሰጋም  በእምነት ዓላማቸው እንደጸኑ ለድል እንዲበቁና በኢትዮጵያ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ከፋች እንዲሆኑ ፈጣሪ ይርዳቸው፡፡

ነጻነቴን የምንል፤ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊት ሀገር ሆና ለማየት፣ (ለእኛ ባትደርስ  ለልጆቻችን) የምንመኝ ዜጎችም በምኞትና በፍላጎት ብቻ የሚገኝ አይደለምና የዶ/ር ብርሀኑን ባታደልም በያለንበት በምንችለው ድጋፍ መስጠት ይገባናል፡፡ካልሆነም አደናቃፊ ከመሆን መቆጠብ፡፡

 

 

 

 

በሕወሓት ወታደሮች ውስጥ አለመተማመኑ ነግሷል –በጀነራል ሳሞራ የኑስ ቡድን እና በሌ/ጀነራል አብረሀ ወ/ማርያም ቡድን መካከል ያለው ልዩነት ተካሯል

$
0
0

* ህዝባዊ‬ ወያኔ ሓርነት ትግራይ በሚቆጣጠረው መከላከያ ሰራዊት ውስጥ እርስበርስ አለመተማመንና ጥርጣሬ አይሏል፡፡
‪* የህወሓት‬ አገዛዝ ከሱዳን ጋር የተፈጠረውን ወታደራዊ ግጭት የህዝቡን ትኩረት ሊያስቀይርበት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡
* የህወሓት አገልጋይ የሆኑ “የአማራ ክልል” ባለስልጣናት ወደ ወልቃይት ሄደው በአካል ህዝቡን እንዲያነጋግሩ ከህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት ቀጭን ትዕዛዝ መተላለፉ ታወቀ፡፡

አርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ ራድዮ እንደዘገበው

ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ በሚቆጣጠረው መከላከያ ሰራዊት ውስጥ እርስበርስ አለመተማመንና ጥርጣሬ አይሏል፡፡
በከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ማለትም በጀነራል ሳሞራ የኑስ ቡድን እና በሌ/ጀነራል አብረሀ ወ/ማርያም ቡድን መካከል ተፈጥሮ የቆየው ጎራ ለይቶ መሰላለፍና አንዱ ቡድን ሌላኛን ለማስወገድ የሚያደርገው ፍትጊያ በእጅጉ ከሯል፡፡
samora and azeb
በመሆኑም አለመተማመኑ ስር ሰዶ እስከ ታች ድረስ በመውረዱ በተዋጊው ሰራዊትና በአዛዦቹ፣ በአዛዦችና በአዛዦች፣ በአዛዦችና በህወሓት ባለስልጣናት፣ በተዋጊውና በተዋጊው እንዲሁም በተጨማሪ ባጠቃላይ በትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች እና በሌሎች ቋንቋዎች ተናጋሪዎች መካከል ከፍተኛ ጥርጣሬ ነግሷል፡፡

ለህወሓት ታማኝና ቅርብ ነው የሚባለው አግአዚ ኮማንዶ ጦርም ባለመተማመኑ ማዕበል ተመትቶ መሰረቱ ተናግቷል፡፡ በዋና አዛዡ መቶ አለቃ ታፈሰ እና በምክትሉ ሻለቃ ባሻ ሰለሞን ኃ/ማርያም የሚመራው አንድ ሻምበል የአግአዚ ጦር ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት ፈጥሯል በሚል ጥርጣሬ መሽጎ ከቆየበት ሁመራ አካባቢ ዲማ የተባለ ቦታ ወደ ኋላ 30 ኪ.ሜ እንዲያፈገፍግ ተደርጎ ኩሃጂ ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡፡

የህወሓት አገዛዝ ከሱዳን ጋር የተፈጠረውን ግጭት የህዝቡን ትኩረት ሊያስቀይርበት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡

የሱዳን መከላከያ ሰራዊት ድንበር ጥሶ ወደ ኢትዮጵያ የጠረፍ መንደሮችና እስከ መሀል ከተሞች ዘልቆ እየገባ በህዝብ ላይ ጭፍጨፋ እና የንብረት ውድመት በተደጋጋሚ እየፈፀመ መመለሱ ያስቆጫቸው አንዳንድ የህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊት አባላት የአዛዦቻቸውን መመሪያ በመጣስ የፈፀሙት አፀፋዊ ጥቃት ያስከተለውን ግጭት በመንተራስ የህወሓት አገዛዝ ቅጥረኛ ካድሬዎች ሱዳን በጉልበት የወሰደችብንን መሬት ልናስመልስ ስለሆነ እርዱን በማለት ህዝቡን እየሰበኩ ከተጀመረው የነፃነት ትግል ለማዘናጋት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡

በተጨማሪም ካድሬዎቹ ሱዳን እና ኤርትራ የኢትዮጵያን መሬት ወረዋል የሚል ምክንያትና የገንዘብ መደለያ በማቅረብ ከመከላከያ የወጡ የቀድሞ አባላትን እንዲመለሱ በመማፀን ላይ ናቸው፡፡

የህወሓት አገልጋይ “የአማራ ክልል” ባለስልጣናት ወደ ወልቃይት ሄደው በአካል ህዝቡን እንዲያነጋግሩ ከህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት ቀጭን ትዕዛዝ መተላለፉ ታወቀ፡፡
ከአርበኞች ግንቦት 7 ጎን በመሰለፍ ለነፃነቱ እየተዋደቀ የሚገኘው እና “ክልል ሶስት እና ክልል አንድ የሚባል አናውቅም እኛ የጎንደር በጌምድር ተወላጅ ኢትዮጵያዊያን ነን” በማለት ለህወሓት ዘርን መሰረት ያደረገ አስተዳደር አልገዛም ብሎ በአንድነት የተነሳው የወልቃይት ህዝብ በህወሓት ህልውና ላይ ከፍተኛ ስጋት በመደቀኑ ነው የአማራ ክልል የህወሓት አገልጋይ ባለስልጣናት ወደ ቦታው ሄደው ህዝቡን በአካል በማግኘት ሰብከው ሃሳቡን እንዲያስለውጡና እንዲማፀኑም ጭምር በጌቶቻቸው የታዘዙት፡፡

አጭር ጥያቄ ለእነ ኦባማ አጭር ማስገንዘቢያ ለእነ ወያኔ! –ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

$
0
0
ከአምሳሉ ገ/ኪዳን

ከአምሳሉ ገ/ኪዳን

አቶ ኦባማ እንደፈከሩ አደረጉት አይደል! ጥሩ አንዴ ልብ ብለው ያድምጡኝ? እኛ ኢትዮጵያዊያን በአሁኑ ጊዜ የራሳችን የሆነ ሉዓላዊ መንግሥትና ሀገር ቢኖረን እናንተም በሀገራችን የውስጥ ጉዳይ ላይ የማትገቡ ብትሆኑና ወያኔን አስታግሱልን አደብ አስገዙልን መብቶቻችንን አስጠብቁልን፤ እንቢ ካላቹህ የምታደርጉለትን ሁሉ አቀፍ ድጋፍ አቁሙ! አታርጉ! አትስጡ! አስጨረሳቹህልን! አስፈጃቹህን! እያልን ነጋ ጠባ ወደናንተ አቤቱታ የማናቀርብ ብንሆን ምንኛ መልካም በነበረ ምንኛ ደስ ባለን ነበር፡፡ ምክንያቱም እኛ ይሄንን በማለታችን ሉዓላዊነታችንን ማስደፈር እንደሆነ ስለምናስብ፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን የሉዓላዊነት የነጻነት የክብር ጉዳይ በእጅጉ ስለሚያንገበግበን ነው፡፡

ነገር ግን ምን ዋጋ አለው የሀገር ነጻነት ሉዓላዊነት ክብር የሚባል ነገር የማያውቅ የማይገባው ያለ ራሱ ጥቅም የማይታየው “ወያኔ” የሚባል የእፉኝት ልጅ መጥቶ አስደፈረን አዋረደን፡፡ ካለበት ከባድ በራስ ያለመተማመንና የአቅም ውስንነት የሚመነጭ የጥገኝነት ችግር የተነሣ በረሀ እያለ ጀምሮ እናንተንም ሆነ ሌሎቹን ምዕራባዊያን በውስጥ ጉዳያችን ዘው ብላቹህ እንድትገቡ በማድረጉ “ግንቦት 7 አሸባሪ ቡድን ነው፣ ዲሞክራሲያዊውን (መስፍነ ሕዝባዊውን) የወያኔን አገዛዝ ማንም እንዳይነካው፣ ዝንቡን እንኳን እሽ እንዳይልብን፣ በእሱ ላይ እጁን የሚያነሣ ቢኖር ጠላታችን ነው!” እያላቹህ እንደ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብነታቹህ በምንጋራቸው ጥቅሞች ላይ ጥብቅና በመቆም የኢትዮጵያ ሕዝብ የሰብአዊና ፖለቲካዊ መብቶችን ማጣቱ መገፈፉ አሳስቧቹህ እንደ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አካልነታቹህ መውሰድ ያለባቹህን እርምጃዎች አንዲትም ሳትወስዱ ከየራሳቹህና ዓለም ዓቀፍ ሕጎችና ስምምነቶች በተጻራሪ ለዚህ አንባገነናዊ አገዛዝ ጠበቃና አለኝታ ሆናቹህ አገዛዙ ሉዓላዊነታችንን እንድትጥሱ እንድትዳፈሩ አድርጎ በውስጥ ጉዳያችን እንድትገቡ እንድትፈተፍቱ በማድረጉ ነው እኛ ኢትዮጵያዊያን “እባካቹህን?” እያልን ዘወትር የምንዘበዝባቹህ የምንማጸናቹህ የምንለምናቹህ እንጅ ምንም ስለሆናቹህ አልነበረም፡፡

ከዚህ ዐውድ አንጻር አሁንም እንለምናቹሀለን እንማጸናቹሀለን እጃቹህን አንሡልን! የእኛን ጉዳይ ለእኛው ተውልን! የእናንተ እጅ ከወጣልን ነገሩ ሁሉ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በጣም ቀላል ነው፡፡ እንቢ ካላቹህና አንሰማቹህም የምትሉ ከሆነ ደግሞ ወያኔን ለሥልጣን ካበቃቹህበት ጊዜ ጀምሮ ወያኔ በሀገራችን በኢትዮጵያና በሕዝቧ ላይ ለፈጸመብን ግፍ፣ ሰቆቃ፣ ጥቃት፣ ጥሰት፣ የዘር ማጥፋትን ጨምሮ ለበርካታ የወንጀል ዓይነቶች ኃላፊነትን ውሰዱልን ወይም ተጠያቂ እንደሆናቹህ እወቁት የሚለው ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ አንገብጋቢ ጥያቄና ማሳሰቢያ፡፡

ወያኔ ሆይ! ለእነዚህ ጌቶችሽ ለሞግዚቶችሽ ከአንድ ያውም ነጻነቷን ጠብቃ ከኖረች ከሉዓላዊት ሀገር ኢትዮጵያ መንግሥት ነኝ ከሚል አይደለም ከሰፈር ኩሊዎች እንኳን ፈጽሞ በማይጠበቅ ደረጃ ወርደሽ “ሲጠሩት አቤት ሲልኩት ወዴት” ባይ አሽከርና ባሪያ ሆነሻቸው እያገለገልሻቸውም እንኳ በየዓመቱ በሚያወጧቸው የሀገራት የሰብአዊ መብት አያያዝን በሚተነትነው መግለጫቸው የፈጸምሻትን ወንጀል ሁሉ ልቅም አድርገው እየጠቀሱ ምን ያህል እንደሚያዋርዱሽ እንደሚያሸማቅቁሽ እንደሚያሳጡሽ ዓይተሻል ሰምተሸል፡፡ እነሱ ይሄንን የሚያደርጉበት ምክንያት 1. የዓለም ፖሊስ (ጸጥታ አስከባሪ) ነን ብለው እያለ ስንት ወንጀልና ጥሰት እየፈጸምሽ ምንም እንዳላደረግሽ ዝም ቢሉሽ ለነሱም ጥሩ ስለማይሆን ቢያንስ ካላወገዝንማ እንሳጣለን ከሚል ሲሆን 2ኛው ደግሞ ወንጀሎችሽን ሁሉ እየዘረዘሩ አንችን በማሸማቀቅ “ዋ! አርፈሽ ትገዥልን እንደሆነ ጸጥ ብለሽ ተገዥ አለበለዚያ ግን በዚህ ሁሉ ወንጀልሽ ተጠያቂ አድርገን እርምጃ እንወስድብሻለን መቀመቅ እናወርድሻለን!” እያሉ ለማስፈራራትና አሁን ካለሽው የበለጠ ተገዣቸው ባሪያቸው አሽከራቸው ሎሌያቸው ታማኛቸው እንድትሆኝ ለማድረግ ነው፡፡ መግለጫዎቻቸው ከእነዚህ ከሁለቱ ውጪ ምንም ዓይነት ዓላማ የለውም፡፡ ምክንያቱም ሌላው ሁሉ ቀርቶ እነሱ በሚጠቅሱት ወንጀሎችሽ ብቻ እንኳን አንቺን ተጠያቂ አድርገው ሲቀጡሽ እርምጃ ሲወስዱብሽ ታይተው ተሰምተው አይታወቁምና፡፡

እንደምናየው ዓላማቸውም የተሳካላቸው ይመስላል ምክንያቱም እንደዚያ እያሉ በየዓመቱ መግለጫዎቻቸው እንደዚያ እያሉ ሲኮንኑሽ ሲያብጠለጥሉሽ “እዚህ ድረስ ወርጀ አሽከር ባሪያ ሆኘ እናንተን እያገለገልኩ እንዴት እንዲህ ብላቹህ ታዋርዱኛላቹህ? እንዲህ እማ ከሆነ በቃኝ!” ሳትዪ ወገብሽን አስረሽ በኩሊነትሽ እየተገዛሽላቸው እያገለገልሻቸው “ሲጠሩሽ አቤት ሲልኩሽ ወዴት” በማለት ከበቀደም ትናንት ከትናንት ዛሬ የበለጠ ባሪያና አሽከር ሎሌ በመሆን ተዋርደሽ ሀገሪቱንም አዋርደሻል፡፡ ለተወሳሰበ ችግር ለጣጣም ዳርደሻል፡፡ ይሄንን እያወቅሽም እራስሽን ነጻ ልታወጭ አልቻልሽም ጨርሶም አልሞከርሽም ከነአካቴውም አታስቢምም ታስረሻልና ልትሞክሪም አትችይም፡፡ ከመጀመሪያውም በፈጸምሽብን ግፍና በደል ባሸከምሽን ውርደት የኢትዮጵያን ሕዝብ አንጀት እንደቆረጥሽ ጠንቅቀሽ ታውቂዋለሽና “ይቅርታ ምሕረት አያደርግልኝም” ብለሽ ተስፋ በመቁረጥሽ አሁንም የመጨረሻ ዋስትናሽ እነሱው እንደሆኑ ታስቢያለሽ ታምኛለሽ፡፡ ይህ ውርደትሽ በዓለማችን “መንግሥታት” ታሪክ ልዩ ሥፍራ የሚይዝልሽ ይሆናል፡፡

የዚህ ወራዳና አሳፋሪ ታሪክ መቸት ኢትዮጵያ መሆኗ ለዚህች ለነጻነቷ ለሉዓላዊነቷ ለክብሯ ለኩራቷ ያልከፈለችው የመሥዋዕትነት ዓይነት ለሌላት ሀገር ታላቅ ውርደት ሐፍረትና ስብራት ነው፡፡ ይሁንና ይሄንን የውርደት የሐፍረት ሸክም ያሸከምሽን ያከናነብሽን አንች ወይም በአንድ አናሳ ጎሳ አባላት የተገነባሽው በመሆንሽ ከውጪ ወደ ውስጥ ለሚያዩን ውርደቱ የኢትዮጵያ ሆኖ ቢታይም ከውስጥ ለሚያዩት ግን የዚህ ውርደት ሐፍረት ተሸካሚዎች ከአናሳ ጎሳነታቸው የተነሣ በራስ መተማመን የሌላቸውና በዚህም ምክንያት  ጥገኛነት የሚያጠቃቸው የወያኔ ደጋፊና አባላት የሆኑት የዚያ አናሳ ጎሳ አባላት በመሆኑ የተቀረነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወይም በሐውርት (ብሔረሰቦች) ከዚህ መሸማቀቅና ውርደት ነጻ ነንና ልናፍር ልንሸማቀቅ የሚገባ አይመስለኝም፡፡ በዚህ አጋጣሚ ለትግሬ ሕዝብ (ለትግራይ ሕዝብ ያላልኩት በትግራይ ውስጥ ከ5 በላይ የተለያዩ ጎሳዎች ያሉ በመሆናቸውና መልዕክቴ ያተኮረው ወያኔ መከታየ መሠረቴ አለኝታዬ የሚለው የትግሬ ጎሳ በመሆኑ ነው) እናም የዚህ ጎሳ ሕዝብ ይሄ ውርደት የሚያሸማቅቀው የሚያሳፍረው ከሆነ ለወያኔ ሲሰጠው የኖረውን ሙሉ ድጋፍ ቶሎ በማቆም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን በመሰለፍ ለነጻና ሉዓላዊት ኢትዮጵያ መፈጠር የበኩሉን ድርሻ እንዲያበረክት ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡

እስከ አሁን ወያኔን እንታገላለን ብለው ከተደራጁት በትግሬ ጎሳ ስም ከተደራጁት ድርጅቶች ወያኔ “ለምን የበለጠ ወያኔ ሆኖ የበለጠ ተጠቃሚ አላደረገንም” ከሚል ቅሬታ እንጅ “ወያኔ ለምን ኢትዮጵያዊ አልሆነም” የሚሉ ባለመሆናቸው ወያኔን ከድተህ እነሱን ብትቀላቀልም “ጉልቻ ቢለዋወጥ” መሆኑ ነው እንጅ የሞራል (የቅስም) እና የማንነት ተሐድሶ ማድረግህል አያመለክትም፡፡ በቅድሚያ እንደ ሕዝብ ለዚህ ወያኔ ላደረሰብህ ላከናነቡህ ውርደት የሚዳርግህን የጥገኝነትና በራስ ያለመተማመን ከባድ የሥነ ልቡና ችግር ራስህን ነጻ አድርግ፡፡ ከዚህ የሥነልቡና ችግር ነጻ ልትሆን የምትችለውም በኢትዮጵያዊነትህ በመተማመን ከኢትዮጵያ የሚበልጥብህ ምንም ዓይነት ደባል ጥቅም እንዳይኖርህ በማድረግ ነው፡፡ እንዲህ አድርገው እራሳቸውን በኢትዮጵያዊነት ጸበል መፈወስ ካልቻሉ ግን ይህ ጎሳ ከኢትዮጵያ ሕዝብ የተለየና አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ካለው ፍላጎትና ይሄንን ጥቅም ለማግኘት የሚያስችል አቅም ከማጣት ከሚመነጭ በራስ ያለመተማመንና የጥገኝነት ስሜት ችግር ዘለዓለም የጠላት መጠቀሚያ በመሆን ይህችን ሀገር ሲያምስ የሚኖር ጎሳ እንደሚሆን አጥብቄ ላስገነዝብ እወዳለሁ፡፡ የትግሬ ሕዝብ ሙሉ ለሙሉ እንዲህ ዓይነት ችግር አለበት ማለቴ አይደለም፡፡ ከሽህ አንድ ቢሆንም ኢትዮጵያዊ የሆነ አስተሳሰብ ያላቸው የሚኖሩ ይመስለኛል፡፡

ከዚህ አናሳ ጎሳ ከወጡ መሪዎች እንዲህ ዓይነቱን ውርደትና ሸክም ሀገራችንንና ሕዝባችንን ሲያከናንቡን ይህ የመጀመሪያ ጊዜ አይደለም፡፡ ከዚህ ቀደምም በዐፄ ቴዎድሮስ ወይም በሀገር ላይ ክህደት በመፈጸም ለእንግሊዝ ባንዳ ሆነው በሠሩት ውለታ በምላሹ ከእንግሊዝ በተደረገላቸው እገዛ ለንጉሥነት የበቁትና ንጉሥ ከሆኑም በኋላ ለዚህ ላበቋቸው እንግሊዞች የመታዘዝ ግዴታ እንዳለባቸው ያስቡ የነበሩት የመጀመሪያው የትግሬ ንጉሥ ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ (አንዳንዶች ትግሬ አይደሉም ኢሮብ ናቸው ይላሉ) እሳቸው እንደ መሪ አርቀው ማሰብ ባለመቻላቸው፣ ኃላፊነት የሚሰማቸውና በሳል ባለመሆናቸው፣ ከጎረቤት ሀገር ጋር ለባዕድ ሕዝብና መንግሥት አድሮ ተቀጥሮ መጣላቱ መጋጨቱ የማይሽር የቂም ቁስል እንደሚፈጥር፣ ወደፊት ሀገርን ዋጋ ሊያስከፍል ሰላም ሊያሳጣን የሚችል ጠንቅና ጠላት መትከል መሆኑን ባለመረዳት የእንግሊዝ አሽከርና ተቀጣሪ ሎሌ ሆነው እንግሊዝ የላከቻቸው ወታደሮቿ ድል ስለተመቱባትና ስላቃታት ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ጦር ልከው በደርቡሾች ወይም በመሐዲስቶች ተከበው መውጫ አጥተው ሊደመሰሱ የነበሩትን የደርቡሾችን ሀገር ወራሪዎች የግብጽና የቱርክ ወታደሮችን እንዲያድኗቸው እንዲታደጓቸው ወይም ነጻ እንዲያወጧቸውና በምጽዋ በኩል ወደ ሀገራቸው እንዲሸኟቸው ስለተባሉ ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ለእንግሊዝ ጥቅም ሲሉ በስምምነታቸው መሠረት ጦር ልከው ለነጻነታቸው እየተጋደሉ ከድል አፋፍ ደርሰው የነበሩትን መሀዲስቶችን ወይም ደርቡሾችን በመውጋት ሊቀዳጁት የነበረውን ድል ከማስጣላቸውም ባሻገር ከባድ ጉዳትም እንዲደርስባቸው በማድረጋቸው ደርቡሾች በዚህ በደረሰባቸው ግፍና በደል ቂም ቋጥረው ለበቀል በመነሣት ሀገራችንን በተደጋጋሚ በመውረር ጎንደር ድረስ ዘልቀው እየገቡ እንድትወድም ሊያደርጓት ችለዋል፡፡

የኒህ ንጉሥ ድንቁርና የዐባይን ምንጭ ጣናንና አካባቢውን የመቆጣጠርና የግብጽ ግዛት አካል የማድረግ ግብ አንግቦ እየገሰገሰ የነበረውን የግብጽና የቱርክን ጦር ደርቡሾች መግታታቸው ለኢትዮጵያ ጥቅም መሆኑን በመረዳት ደርቡሾቹን መርዳት ማገዝ ሲገባቸው ምጽዋን ማግኘት ከማንም ልንቸረው የማይገባ መብታችንና የገዛ ንብረታችን ሆኖ እያለ እንግሊዝን ባለ መብት አድርጎ በመቁጠር ምጽዋን ከእንግሊዝ እጅ ለማግኘት በመፈለግ በደነቆረና በማይሆን አደገኛ ስምምነት ምጽዋን በእጅ ለማድረግ በመፈለግ የሚያስከትለውን ጣጣ ባለማወቅ ደርቡሾቹን ወግተው ተከበው የነበሩትን ግብጾችና ቱርኮች ታድገው አድነው እንደተባሉት በምጽዋ በኩል ወደሀገራቸው ሸኟቸው፡፡ ራሳቸው ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ የሞቱትም ይሄው ስሕተት ባመጣው የበቀል ጦርነት ከደርቡሾች ጋር በተደረገ ጦርነት ነው፡፡ ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ በዚህ ስሕተታቸው ዐፄ ቴዎድሮስ ገና ዐፄ ሳይሆኑ በሽፍትነት ጊዜያቸው ከእንድሪስ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት መሥርተው ግንባር በመፍጠር የ11 ቀን ጉዞ ወደ ሱዳን ውስጥ በማድረግ የጋራ ጠላት የሆኑትን ዓረቦቹን እስከ መውጋት ድረስ ፈጥረውት መሥርተውት የነበረው የአንድነት የቃልኪዳን መሠረት ፈረሰ፡፡ መፍረስ ብቻ አይደለም ከዚያ በኋላ ቀንደኛ ጠላት ሊሆኑብንም ቻሉ፡፡

እንደ አባታቸው ሁሉም የዛሬዎቹ ልጆቻቸውም ያንን ታሪካዊ ስሕተት በሶማሊያ ላይ ለምዕራባዊያኑ ጥቅም ሲሉ በመድገም ለሀገራችንና ለሕዝቧ ጠንቅ ተክለውላታል የቂም ቁስል ፈጥረውላታል፡፡ ሶማሌዎች ይሄንን የተፈጸመባቸውን በደል መቸም እንደማይረሱትና አንድ ቀን አቅም በፈቀደላቸው በቻሉ ጊዜ እንደ ደርቡሽ ሁሉ ሀገራችንን እንደሚበቀሏት ዘወትር የሚዝቱት ዛቻ ሆኗል፡፡ የምዕራባዊያኑም ዓላማ ይህ ነው፡፡ ይህችን ሀገር ከውጭና ከውስጥ መቋጫ በሌለው የግጭትና የጦርነት አዙሪት ከትተው መውጫ በማሳጣት ደቅቃ ከስማ እንድትቀር ማድረግ፡፡ እንጅማ ወያኔ እራሱ መንግሥታዊ ሽብር መፈጸምን ዋነኛ የህልውናውና የአሥተዳደር ዘይቤው ያደረገ አገዛዝ እንደሆነ ጠንቅቀው እያወቁ “ለፀረ ሽብር ትግል ታማኝና ብቁ አጋር ነው” ብለው አምነው አይደለም አጋር አድርገውት ገብቶ እንዲወጋላቸው እያደረጉ ያሉት፡፡ ሲጀመር ምዕራባዊያን ሽብርንና ሽብርተኝነትን ማጥፋት ዓላማቸው አይደለም ማበራከት ማስፋፋት እንጅ፡፡ ለዚህም ነው ሊቢያን የጋዳፊን መንግሥት “አንባገነን ነው” ብለው የተረጋጋውንና ሰላም የነበረውን ሀገር አፈራርሰው ሀገሪቱን ለሽብርተኞች መናኸሪያ ምቹ አውድማ አድርገዋት ቃል የገቡትን የመልሶ ማቋቋሚያ ገንዘብም ሳይሰጡ መንግሥትም እንዲያቋቁሙ ሳይረዷቸው ጥለዋቸው የጠፉት፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com

 


ጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸው ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት የደረሰበትን አሰቃቂ ድርጊት

$
0
0

11755090_700274113450178_6512538590114751539_nሐምሌ 2 /2004 ለሊት ሰባት ሰዓት ማዕከላዊ የደረሰው ጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸው ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት የደረሰበትን አሰቃቂ ድርጊት አስረድቷል፡፡ በዚህ የተበሳጩት የማዕከላዊ ቢሮ ቁጥር 49 መርማሪዎች ኢንስፔክተር አለማየሁ፣ዘመድኩንና ጸጋዬ የተባሉ የሱፍን ከፍርድ ቤት መልስ ቢሯቸው ድረስ በማስመጣት ‹‹ፍርድ ቤት ሄደህ መጥሪያ ይዘህልን መጣህ አሉ ባክህ?›› ‹‹የደረሰብኝን ከመናገር ውጪ ምን አጠፋሁ?›› ባገኙት ነገር ሁሉ ወረዱበት ጾሙን ለመፍታት እየተዘጋጀ የነበረው የሱፍ ዱላውን መቋቋም ተስኖት ተዝለፍልፎ ወደቀ ፡፡
መርማሪዎቹ ቂም ቋጥረው በየቀኑ ከባድ ስፖርቶችን በማሰራት ይደበድቡት ነበር፡፡በመጨረሻም ባላነበበውና ቃሉን ባልተቀበሉት ሁኔታ መርማሪዎቹ ባዘጋጁለት የቃል መቀበያ ወረቀት ላይ እንዲፈርም አደረጉት፡፡
ኢንስፔክተር አለማየሁ –ሱሪህን አውልቅ አለኝ
የሱፍ — አላወልቅም አልኩት፡፡
መርማሪው– ለምን ?
የሱፍ — እኔ ወንድ ነኝ የወንድን ገላም ለማየት
አልናፍቅም፡፡ከፈለግክ አንተ መጥተህ አውልቀው አልኩት፡፡
እናም መሬት ላይ አስተኝተው ደበደቡኝ ።

ሐሳብን ከመግለጽ ነጻነት ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ከሚገኙ ጋዜጠኞችና ጦማርያን የተወሰኑት

$
0
0

Eskinder Nega* ሁሉም የታሰሩለት አላማ እስኪፈታ ድምጻችንን እናሰማለን
1. እስክንድር ነጋ (በህገ ወጥ መንገድ በሞያው እንዳይሰራ የታገደ በኋላም በግንቦት ሰባት አባልነትና የአረቡን አለም አይነት አብዩት በኢትዩጵያ እንዲፈጠር ታደራጃለህ ተብሎ 18 ዓመት የተፈረደበት ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ተሟጋች)
2. ውብሸት ታዬ (የቀድሞዋ አውራምባ ታይምስ ምክትል ዋና አዘጋጅ ‹‹ህዝቡ የት ገባ››በማለት በመጠየቁ 14 ዓመት የፈረደበት)
3. ተመስገን ደሳለኝ (ስርዓቱ በህትመት ውጤቶቹ ላይ የሚወስድበትን አፈና በዘዴ በመቋቋም ትውልዱን ‹‹የፈራ ይመለስ ››በማለት በማጠየቁ ሶስት ዓመት ተፈርዶበት ለወህኒ የተዳረገ ደፋር ጋዜጠኛ)
4. የሱፍ ጌታቸው(በሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ልብ ልዩ ስፍራ በሚሰጣት የሙስሊሞች ጉዳይ መጽሔት በዋና አዘጋጅነት በመስራቱ የተከሰሰ)
5.ሰለሞን ከበደ(የሙስሊሞች ጉዳይ መጽሔት ማኔጂንግ ኤዲተር ያልተነገረለት ምርጥ ጋዜጠኛ)
6.እስማኤል ዳውድ (በሚልዩኖች ድምጽ ጋዜጣ ያቀርባቸው በነበሩ ጽሁፎች ተስፋን ፈንጥቆ የነበረ ብዕረኛ)
6. ሃብታሙ ምናለ(ከአንድ እትም በላይ እድሜ እንዳይኖራት በተደረገችው ቀዳሚ ገጽና በሚልዩኖች ድምጽ ይሰራ የነበረ ስርዓቱ ኦባማ ላይ የሽብር ጥቃት ለማድረስ ከአልሻባብ ጋር ተማክረሃል በማለት አስሮታል)
7. በፍቃዱ ኃይሉ የዞን ዘጠኝ አባል ፣የዕንቁ መጽሔት ኤዲተር እንዲሁም የመጽሐፍ ደራሲ
8. አቤል ዋበላ የዞን ዘጠኝ አባል
9. አጥናፍ ብርሃኔ — የዞን ዘጠኝ አባል
10. ናትናኤል ፈለቀ –የዞን ዘጠኝ አባል
11.አብርሃ ደስታ — በማህበራዊ ድረ ገጾች በዋናነት ህወሓት በትግራይ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን በደል ያጋልጥ የነበረ


‪#‎Free‬ all Prisoners of Conscience

ቴዎድሮስ አድሃኖም የግብረሰዶማውያንን ዣንጥላ ይዘው ኦባማን ተቀበሉ (ይናገራል ፎቶ)

Next: Hiber radio ፕ/ት ባራክ ኦባማ አዲስ አበባ ሲገቡ ቀስተ ደመና መታየቱ ነዋሪውን አነጋገረ፣ ሕዝቡ ፕሬዝዳንቱ ቶሎ በሄዱልን የሚል ምሬት ውስጥ መግባቱ ተገለጸ፣ኦባማ አዲስ አበባ ገብተውም አገዛዙ በተቃዋሚዎች ላይ የሚያደርገውን ጫና መቀጠሉ፣አርበኞች ግንቦት ሰባት የህዝብ ንብረት የማውደም ዓላማ የለኝም ማለቱ፣የዶ/ር አክሎግ ቢራራ በኦባማ አማካሪ ሲሳን ራይስ መግለጫ ላይ የተሰጠ ቃለ መጠይቅ፣የሳንባ ካንሰር፣የኦባማ ጉዞ ዳሰሳ፣ሁበር የፈጠረው ጫናና የታክሲ አሽከርካሪዎች ስጋት እና ሎሎችም
$
0
0
ታየ ምህረቱ ከቀበና
ብዙዎች “የፌስቡክ ሚኒስትር” ሲሉ የሚጠሯቸው ቴዎድሮስ አድሃኖም ዛሬ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ አውሮፕላን ማረፊያው ላይ የያዙት ዣንጥላ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው:: የፌስቡኩ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሃኖም የያዙት ዣንጥላ ተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን የሚደግፉና በዛው ውስጥ ያሉ ሰዎች የሚይዙት የቀስተደመና ባንዲራ ነው::  ብዙዎች ለምን ቴዎድሮስ ይህን ዣንጥላ እንደያዙት ግራ ገብቷቸዋል:: እየተወያዩበትም ነው::
100 percent

Hiber radio ፕ/ት ባራክ ኦባማ አዲስ አበባ ሲገቡ ቀስተ ደመና መታየቱ ነዋሪውን አነጋገረ፣ ሕዝቡ ፕሬዝዳንቱ ቶሎ በሄዱልን የሚል ምሬት ውስጥ መግባቱ ተገለጸ፣ኦባማ አዲስ አበባ ገብተውም አገዛዙ በተቃዋሚዎች ላይ የሚያደርገውን ጫና መቀጠሉ፣አርበኞች ግንቦት ሰባት የህዝብ ንብረት የማውደም ዓላማ የለኝም ማለቱ፣የዶ/ር አክሎግ ቢራራ በኦባማ አማካሪ ሲሳን ራይስ መግለጫ ላይ የተሰጠ ቃለ መጠይቅ፣የሳንባ ካንሰር፣የኦባማ ጉዞ ዳሰሳ፣ሁበር የፈጠረው ጫናና የታክሲ አሽከርካሪዎች ስጋት እና ሎሎችም

$
0
0
የህብር ሬዲዮ  ሐምሌ 19 ቀን 2007 ፕሮግራም
<…በኢትዮጵያው አገዛዝ የይስሙላ ምርጫ ላይ የፕሬዝዳንት ኦባማ አማካሪና የህወሃት ወዳጅ ሲዛን ራይስየመቶ በመቶ ምርጫው ዲሞክራሲያዊ ነው ማለታቸውና  እሳቸው እንደሳቁት እኔም ስቄያለሁ የሳቸው ሳቅና የኔሳቅ የተለያየ ነው። የመቶ በመቶ ምርጫው  እንዳሉት ሳይሆን በርካታ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ፍሪደምሀውስን ጨምሮ ምርጫው የድሮ የሶቪየትን ምርጫ ነው ፣የሰሜን ኮሪያን ምርጫ ነው የሚያስታውሰውብለዋል። አምባሳደር ሱሳን ራይስ የጎዱት የኢትዮጵያን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለአሜሪካ በኢትዮጵያ ሕዝብ በኩልየሚኖረውን አክብሮትም ጎድተውታል።ምክንያቱም  …>
 
Habitamu / አክሎግ ቢራራ በፕ/ ኦባማ የኢትዮጵአ ጉዞና የፕሬዝዳንቱ የብሔራዊ ጸጥታ አማካሪ የሆኑት ሱሳንራይስ በጉብኝቱ ላይ የሰጡትን መግለጫ በተመለከተ  ተጠይቀው ከሰጡን ሰፋ ያለ ማብራሪያየተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)
 
<…በአዲስ አበባ አራት አይነት ዩኒፎርም የለበሱ ፖሊሶች ሕዝቡን በከፍተኛ ሁኔታ እያስጨነቁት ነው ነገ(ሰኞ)ሕዝቡ በአብዛኛው በዚህ ተማሮ፣የታክሲው ወረፋ ስራ የሚሄድ አይመስለኝም/ ኦባማ እዚህም እያሉሕጋዊው የመኢአድ አመራሮች እየታደኑ እየታሰሩ ነው ግማሾቹ የደረሱበት አልታወቀም። ፕሬዝዳንቱምተቃዋሚዎችን የሚያናግሩ አይመስለኝም…>  አቶ አበበ ውቤ የህጋዊው መኢአድ የጭርቆስ ቀጠና ሀላፊ በእስርስጋት ውስጥ ሆነው ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
የፕሬዝዳንት ኦባማ የኬኒያና የኢትዮጵያ  ጉዞን ተከትሎ የተከሰቱ ተቃውሞና ድጋፎች ፣አስገራሚ ክስተቶች ሲዳሰሱ
አሜሪካ ጋር እንደምነወዳጅ ሁሉ ከአሜሪካ ጋር ልዮነቶች እንዳሉን ማወቅ አለብንየኬነያው / ኡሁሩኬኔያታ ( ልዩ ጥንቅር)
የሳምባ ካንሰርና  ሐኪም ለሞቱ ቀን የቆረጠለት ግለሰብ በስራው ቦታ ባልደረቦቹን ሊሰናበት የሄደበት አስደንጋጭ ሁኔታና የጓደኞቹ ምላሽ( ልዩ ዘገባ)
 
 
<… የቬጋስ አሽከርካሪዎች የሁበርን እየመጣሁ ነው ማለት ተከትሎ የመጣ ስጋት፣ የታክሲ ኩባንያዎቹ ተጨማሪ ታክሲ የማግኘት ሩጫና ስራው ላይ የሚያመጣው ተጽዕኖ …> (ውይይት ከታክሲ አሽከርካሪዎች ጋር)
 
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
/ ባራክ ኦባማ  አዲስ አበባ ሲገቡ ቀስተ ደመና መታየቱነዋሪውን አነጋገረ
ሕዝቡ ፕ/ት ኦባማ ከኢትዮጵያ ቶሎ የሄደው ከዚህ አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ በተገላገልን የሚል ምሬት ውስጥ መግባቱ ተገለጸ
ባራክ ኦባማ ይሄ ኢትዮጵያ እንጂ አሜሪካ ወይም ኬኒያአይደለምየኦባማን ወደ / መምጣት ከተቃወሙነዋሪዋች መካከል ያስማው ተቃውሞ
የግንቦት 7አርበኞች ግንባር ንቅናቄ የሕዝብ ንብረትየማውደም  ዓላማ የለኝም አለ
በኢትዮኤርትራ ድንበር ላይ መጠነ ሰፊ ጦርነትሊቀጣጠል እንደሚችል አንድ ምሁር አስጠነቁቁ
ኦባማ ኢትዮጵያው ገብተው የተቃዋሚ አመራሮችና አባላት በደህነቶች እየታፈኑ መወሰድ መቀጠሉን አንድ የተቃዋሚ አመራር ገለጹ
ታዋቂዋ አሜርካዊት የሲኒማ ተዋንያት እና ዳይሬክተርአንጄሊና ጆሊ ከኢትዮጵያ የወሰደቻት ልጇን ልታጣትነው
ቴኤ የኡበርና ሊፍትን ወደ ቬጋስ መምጣት በመቃወም ከ320 በላይ ታክሲ ፈቀደ
ገደብ የነበረባቸውን ታክሲዎች ገደቡን አነሳላቸው
ኡበር በኒዮርክ የገጠመውን ጠንካራ ተቃውሞ በድልመወጣቱ ተዘገበ
ሌሎችም ዜናዎች አሉ
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8  ሰዓት ህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

የኢትዮጵያውያን የአውሮፓ ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን የ13ኛው ዓመት በዓል በኢትዮ-ለንደንና በኢትዮ-ኢሚሊያ የዋንጫ ባለቤትነት ተፈጽሟል፤

Previous: Hiber radio ፕ/ት ባራክ ኦባማ አዲስ አበባ ሲገቡ ቀስተ ደመና መታየቱ ነዋሪውን አነጋገረ፣ ሕዝቡ ፕሬዝዳንቱ ቶሎ በሄዱልን የሚል ምሬት ውስጥ መግባቱ ተገለጸ፣ኦባማ አዲስ አበባ ገብተውም አገዛዙ በተቃዋሚዎች ላይ የሚያደርገውን ጫና መቀጠሉ፣አርበኞች ግንቦት ሰባት የህዝብ ንብረት የማውደም ዓላማ የለኝም ማለቱ፣የዶ/ር አክሎግ ቢራራ በኦባማ አማካሪ ሲሳን ራይስ መግለጫ ላይ የተሰጠ ቃለ መጠይቅ፣የሳንባ ካንሰር፣የኦባማ ጉዞ ዳሰሳ፣ሁበር የፈጠረው ጫናና የታክሲ አሽከርካሪዎች ስጋት እና ሎሎችም
$
0
0

 

ESCFE-20151-407x280ባለፈው ዓመት 2014 .. ኢትዮምዩኒክ ባዘጋጀው የኢትዮጵያውያን የአውሮፓ ስፖርትና ባህል 13ኛውን ዓመት በዓል የማዘጋጀት እድል የተሰጠው ለኢትዮአዲስ ፍራንክፈርት ነበር፡፡በዚህ መሰረት ኢትዮአዲስ ፍራንክፈርት 13ኛውን ዓመት የኢትዮጵያውያን የስፖርት ባህል ዝግጀት ሃላፊነት ተሰጥቶት፥ በፍራንክፈርት ከተማ ጀርመን አገር ከጁላይ 15 ቀን 2015 .. እስከ ጁላይ 18 ቀን 2015 .. ድረስ ዝግጅቱን አቀናብሮ እውን እንዲሆን አስችሏል፡፡

ለዚህም ፍራንክፈርትሬብስቶክ በሚባል ከተማ ውስጥ ሶስት የእግር ኩኣስ መጫወቻ ሜዳዎችን፥ የመጀመሪያ እርዳት ስጪ ባለሙያዎችና አንድ መኪና፥ የጀርመኖች አጨዋች ዳኞች ልብስ መለወጫ ክፍል፥ ሽንት ቤቶች ለሴቶችና ወንዶች፥ ለፌዴሬሽኑ የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባላት መቀመጫ ቢሮ፥ ለተጨዋቾች ከሞላ ጎደል የመልበሻና መታጠቢያ ክፍሎች፥ ለሽልማት አስፈላጊ የሆኑ ዋንጫዎችንና ሌሎች ሽልማቶቸን፥ መጠጥናን ምግብ አቅርቦት፥ የሙዚቃ ማጫወቻ መሳሪያና አጨዋቾች፥ ቆሻሻ የሚጣልባቸው ሰማያዊ ላስቲኮች በየቦታዎቹ፥ ቆሻሻና ክፍሎቹን የሚያፀዳ ግብረ ሃይል፥ የኢትዮጵያ ቡና በአገር ባህል አቅርቦት የሚስተናገድበት፥ የተለያዩ በሽያጭ ልክ አቅርቦት(አገራዊ ልብሶች፥ ካኔቴራዎች፥ ባርኔጣዎች፥ ወዘተ) ወዘተ የኢትዮአዲስ ፍራንክፈርት በማመቻቸት ድርሻውን ተወጥቷል፡፡

የኢትዮጵያውያን የስፓርትና ባህል ፌዴሬሽን ሊቀ መንበር አማካይነት የበዓሉን መክፈቻ ንግግር በማድረግና የበዓሉ የክብር እንግዳ የነበሩት አቶ ስዩም አባተን ለህዝቡ አስተዋወቀዋል፡፡አቶ ስዩም አባተም አጠር ያለ ንግግር አድርገው የመክፈቻው በዓሉ ተጠናቁኣል፡፡በቅድሚያ ግን የስፖርት ፕሮግራሙ ተጀምሮ ነበር፡፡

በተጨማሪም የምግብ አቅርቦት፥ የመጠጥ አቅርቦት፥ የአገር ባህል ነክ የሆኑ ነገሮችን፥ መፃህፍት የሚሸጥበት፥ የኢትዮጵያ ቡና የሚጠጣበት፥ህፃናት የሚጫወቱበትና በውሃ የሚቀዘቅዙበትን ሁኔታ በግለሰብ ወይም በግሩፐ ከሚያቀርቡ ጋር ተዋውሎ እውን ተደርገዋል፡፡

የዝግጅት ስፍራ ሙዚቃ እንደልብ ማታም ሆነ ለማጫወት የመኖሪያ አካባቢ ባለመሆኑ የተመቸ ሲሆን፥ ሶስቱ የእግር ኩኣስ ሜዳዎች ሁለቱ ሳር አንዱ አሸዋ ሜዳ ነበሩ፡፡ሁለቱ ሳር ሜዳዎች መብራት የለሽ ሲሆኑ፥ የአሸዋው ሜዳ መብራት ነበረው፡፡በተቻለ ሶስቱም መብራት ያላቸው ቢሆኑ ይመረጣል፡፡አንድ ጨዋታ በሜዳ ሁለት ቁጥር ላይ ሐሙስ ማታ የተደረገው መደረግ የሌለ ነበር፡፡የዚህ ዓይነቱ ሁኔታ ወደፊት እንዳይደገም ጥንቃቄ ደረግበት ይገባል፡፡

በስፖርት ሜዳው አካባቢ የነበረው የሙዚቃው ቅንብር የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃዎች ይዘት ብቻ ሊኖራቸው በዓሉ የኢትዮጵያውያን ባህል የሚደረግበትና ኢትዮጵያዊ ጭፈራዎች የሚታዩበት መድረክ ሊሆን ይገባል፡፡የኢትዮጵያ ሙዚቃ ያልሆኑ ሙዚቃዎች ፈጽሞ በዚህ በዓል ላይ አስፈላጊ አይደለም፡፡የፌዴሬሽኑም አንዱና ዋናው ዓላማ የኢትዮጵያን ባህል ማስተዋወቅና ማሳደግ ሊሆን እንደሚገባውና ግዴታውም እንደሆነ ነው፡፡ይህ በዓል የኢትዮጵያውያን በዓል ሲሆንም ሙዚቃውም የኢትዮጵያ ሙዚቃዎች የሚደመጡበት በዓል ሊሆን ይገባል፡፡

የሙዚቃው ድምፅ የእግር ኣሁ ሂደት እንዳያውክና የዳኞች ፊሽካ ድምፅ ለተጨዋቾቹና ለተመልካቹ እንዳይሰማና ችግር እንዳይፈጠር፥ ሙዚቃውን ጨዋታ በሚካሄድበት ወቅት ማቆሙ ተገቢ ነው፡፡ጨዋታ በማይካሄድበት ወቅት ሙዚቃውን በደንብ ማስጮኽ አስፈላጊ ከሆነ ይቻላል፡

አጨዋች ዳኞች

አብዛኛውን የእግር £ ጨዋታዎች የጀርመን የእግር £ ዳኞች ተመድበው በፊፋ የእግር £ ሕጎች መሰረት ሲዳኙ፥ የጀርመኖቹ ዳኞቹ ሙቀቱ በጣም ሃይለኛ ስለነበርና ስለደከማቸው ሁለት ሶስት ግዜ ተደብቀው እንደነበር ነው፡፡የኢትዮጵያውያን ዳኞች የመጨረሻ ጨዋታዎችንና የሕፃናትና ወጣቶች ውድድር በማጫወትና በመሃከልም ጀርመኖቹ ዳኞቹ በማገዝ የተወሰኑ ጨዋታዎች አጫውተዋል፡፡በተጨማሪ እንደ አራተኛ ዳኛ በመሆን የተጨዋቾችን መታወቂያዎች በመቆጣጠር ተንቀሳቅሰዋል፡፡

ባሁኑ ውድድር ወቅት ለጀርመኖቹ አጨዋች ዳኞች የልብስ መቀየሪያና መታጠቢያ እንዲኖራቸው ሲደረግ፥ ለኢትዮጵያውያኖቹ አጨዋች ኞች ግን አልተደረገም፡፡ይህ ለወደፊቱ ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ለሁሉም ዳኞች የጋራ የሆነ የልብስ መለወጭያና መታጠቢያ ቦታ አስፈላጊ ነው፡፡

የመጫወቻ £ ለእያንዳንዱ የአጨዋች ዳኞች ግሩፕ ቢያንስ አንድ £ ተዘጋጅቶ ሲቀርብ ተመሳሳይ መለያ ልብሶች ለለበሱ ሁለት ተጋጣሚ ቡድኖች ከላይ የሚለበሱ ሌላ ቀለም ያላቸው መለያዎች በፌዴሬሽኑ በኩል ተዝጋጅቶ እንደነበር ለመገንዘብ ችለናል፡፡ፌዴሬሽኑ ወደፊቱ የአጨዋች ዳኞች ማራገቢያ 8 ወይም 6 ቢኖረው ችግሮቹ ሰቱ መፍትሄ ለመሻት ያመቻል፡፡ሁለት አጨዋች ብቻ ከኢትዮጵያውያን ዳኞች የራሳቸውን ማራገቢያ ይዘው ስለመጡ፥ ሶስኛው ሜዳ ላይ ሌላ ጨርቅ ይዘው ሁለት ዳኞች ለማራገብ ተገደዋል፡፡ከኢትዮጵያውያን ዳኞች መሃከል ፊሽካ የሌለው ዳኛም እንደነበረ ሹክ ብለውናል፡፡በአጠቃላይ የኢትዮጵያውያን ዳኞች ለአንድ አጨዋች ዳኛ አስፈላጊ ሆኑ ትጥቆችን አሟልተው መቅረብ ግዴታቸው ሊሆን ይገባል፡፡

ኢትዮስዊዝ ከኢትዮ ኖርዌይ ቡድን ጋር ያጫወቱት ዳኛ አንድ የኢትዮስዊዝ ቡድን ተጨዋች ጨዋታው ሲያልቅ አጨዋቹ ዳኛ የሚጨብጥ መስሎ ጠጋ በማለት እንደሰደባቸ ነው፡፡እኝህ ኢትዮስዊዝ ከኢትዮ ኖርዌይ ቡድን ጋር ያጫወቱት ዳኛ ጨዋታውን የእግር £ ሕጎች በሚፈቅዱት መሰረት ለመዳኘታቸው በበኩላችን ምንም ጥርጥር የለንም፡፡የዚህ ዓይነት ጨዋነት የጎደላቸው ተጨዋቾች ግን ፌዴሬሽኑ ተገቢውን እርምጃ በመውሰድ እንዲቀጡ ድረጉ በእኛ ብኩል ተገቢ ነው እንላለን፡፡የኢትዮኖርዌይና ኢትዮስዊዝ ጨዋታ ለተመለከቱ የስፖርት አፍቃሪዎች የኢትዮኖርዌይ ቡድን በጣም በጨዋታ በልጦ በስፖርታዊ ጨዋነት ለማሸነፉ ስፖርትን በስፖርትነቱ ለተከታተልን ስፖርት አፍቃሪዎች ሁሉ ግልጽ ነበር፡፡ታዲያ ለምን አጨዋቹ ዳኛውን ምክንያት ማድረግ አስፈለገ? ይህ ሲባል የኢትስዊዝ ቡድን ሳይሆን አንድ ስፖርታዊ ጨዋነት የጎደለው ተጨዋች ብቻ ተወቃሽ መሆኑን አስምረን ማለፍ እንሻለን፡፡

የአጨዋች ዳኞችን ልብስ የቀለም ዓይነት በሚመለከት ፌዴሬሽኑ ቀደም ብሎ አጨዋች ዳኞቹን በመሰብሰብ ለአራት ቀና የሚሆኑ የተለያዩ ቀለማት ያሏቸው የአጨዋች ዳኛ ከላይ የሚለበሱ መለያዎች አዝጋጅተው እንዲመጡ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ለምሳሌ ለአራቱ ቀናት አምስት ዓይነት ቀለማት ያላቸው ከላይ የሚለበሱ የአጨዋች ዳኛ መለያ ጥቁር፥ ቢጫ፥ ሰማያዊ፥ ቀይ፥ ግራጫ ከተስማሙ ሁሉም አጨዋች ዳኞች እነዚህን ይዘው ሊመጡ ይገደዳሉ፡፡ከዚያም ለመጀመሪያው ቀን ጨዋታ ሁሉም ጥቁር፥ በሁለተኛው ቀን ሰማያዊ፥ በሶስተኛው ቀን ይ፥ በአራተኛው ቀን ቢጫ ወይም ግራጫ ይዘው እንዲመጡ አስቀድሞ ተነግሯቸው ተግባራዊ ማድረግ ይኖረባቸዋል ማለት ነው፡፡

የኢትዮጵያውያን አጨዋች ዳኞች መሃከል ሊሻሻል የሚገባቸው ገሮች ቢኖሩ፥ የሕፃናት ጨዋታዎች ሲያጫውቱ ያለዳኛ ትጥቅ ያጫወቱ እንደነበሩና ይህ መቅረት እንደሚኖርበት ነው፡፡ትክክለኛውን የአጨዋች ዳኛ ትጥቅ አድርገው እያንዳንዱን የህፃናትና ወጣቶች ጨዋታዎች ሊመሩ ይገባል፡፡ሁለት የህፃናት ቡድኖች በጣም ተመሳሳይ የሆኑ መለያ ብሰው ሲጫውቱ ታይቷል፡፡አጨዋ ዳኛ ከላይ የሚለበሱ ባለሌላ ቀለም ከፌዴሬሽኑ መቀመጫ ቢሮ በመውሰድ አንዱ ቡድን በእጣ እንዲለብስ ማድረጉ ተገቢ ሲሆን ግን አልተደረገም፡፡ይህም ወጣቶቹንም እንዲማሩ ይረዳል፡፡

የመጀመሪያው ቀን የኢትዮጵያውያን ዳኞች በረዳት ዳኝነት ያለትጥቅ አንድ ዳኛ ሜዳ ሁለት ቁጥር ላይ ሲያራግቡ እንደነበር ነው፡፡ሶስት ሌሎች ዳኞች ያለገንባሌ ሲዳኙ ሲያረግቡ የመጀመሪያው ቀን ታይቷል፡፡ ይህ ለወደፊቱ ሊደገም አይገባውም፡፡እያንዳንዱ ዳኛ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን አሟልቶ የመቅረብ ግዴታ አለበት፡፡

የሁለት ለባዶ መሸነፍ ጉዳይ

በውድድሩ ላይ የተወሰኑ ቡድኖች በተባለው ሰዓት በሜዳው ላይ ባለመገኘታቸው ምክንያት ሁለት ለባዶ ተሸናፊ እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡ለምሳሌ ኢትዮ ሽቱትጋርትና ኢትዮ አዲስ ፍራንክፈርት2 መጥቀስ ይቻላል፡፡የሚገርመው ደግሞ የኢትዮ አዲስ ፍራንክፈርት2 እንደ አዘጋጅ በተባለው ሰዓትና ቦታ ባለመገኘቱ ትንሽ ሰዉን አስገርሞታል፡፡ኢትዮ ሽቱትጋርትም ሆነ ሌሎች ቡድኖች በግዜው በቦታው ያለመገኝት ችግር የአበሻ ቀጠሮ በሚለው የደካሞች አስተሳሰብ ምክንያት አንደሆነ ተነግሮናል፡፡ይህ የአበሻ ቀጠሮ የሚለው መጥፎ ባህል ሊወገድ የሚገባው የተስቦ በሽታ ሲሆን፥ ፌዴሬሽኑ በዚህ ጉዳይ ላይ የወሰደው እርምጃ እሰየው የሚያሰኝ ነው፡፡እኛ ቀጠሮ ይከበር ያላከበረ ይቀጣ የምንል ነን፡፡

የምግብ አቅራቢ ቅሬታዎች

የምግብ አቅራቢዎቹ በአንድ አካባቢ አንድ ላይ መደረጋቸው ትክክል ቢሆንም፥ በአካባቢው የመጠጥ አቅርቦት ቢኖርም ትኬት ለመግዛት የነበረው ሁኔታ ግን በጣም ሩቅ ነበር፡፡ሁለት የትኬት መቁረጫ ማድረግ ሲቻል አለመደረጉ ለተመጋቢዎች የሚጠጣ ለማግኘት አስቸጋሪ ነበር፡፡መጠጣት ለሚፈልግና ትኬት አስቀድሞ ላልቆረጠ ሰው ምግቡ ከሚሸጥበት አካባቢ ረጅም መንገድ

መሄድ ግድ ነበር፡፡ቅዳሜ ለት ግን የምግብ ሽያጮቹ እራሳቸው ድንኩኣን ውስጥ የጠርሙስ ቢራ 3€ ሲሸጡ ታይተዋል፡፡ ቢራም Ù በኩል በአጥሩ ላይ ሲገባ ለማየት ችለናል፡፡ ሀጋዊ ይሁን አይሁን ግን አናውቅም፡፡ይህ ለሚቀጥለው ዓመት ዝግጅት ትምሀርት ሆኖ ተሻሽሎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

ሌላው ባላፈው ዓመት ማለትም 2014 .. በኢትዮምዩኒክ የተዘጋጀው ዝግጅት ላይ ለኢትዮጵያውያን አጨዋጭ ዳኞች የምግብና የመጠጥ ትኬት ለፌዴሬሽ በመስጠት ፌዴሬሽኑ ደግሞ ለዳኞቹ በመስጠት ዳኞቹ የመረጡትን ምግብና መጠጥ የመጠቀም ሁኔታ ተግባራዊ ተደርጎ ነበር፡፡በአሁኑ የኢትዮአዲስ ፍራንክፈርት 2015 .. ዝግጅት ላይ ግን ለየት ባለ መልኩ ተግባራዊ ተደርÙ ል፡፡እዚህ ላይ መነገር ያለበት ፌዴሬሽኑ ትኬቶቹ እንዲሰጠውና ለዳኞቹ እንዲያድል ጠይቆ በኢትዮ አዲስ ፍራንክፈርት በኩል ፈቃደኛነት አልነበረም፡፡የሆነው የኢትዮጵያውያን ዳኞች አዋሬበሚባል ድን£ ውስጥ ብቻ ሄደው እንዲበሉ የኢትዮ አዲስ ፍራንክፈርት ወስኖ በዚሁ መሰረት ምግብ እዚያ እንዲበሉ ተደርÙ ል፡፡የሚጠጣ ውሃ ወይም ለስላሳ ከአንድ የመጠጥ መሽጫ ቦታ ዳኞች እንዲጠጡ ተወስኖ ተግባራዊ ተድርÙ ል፡፡ ይህም ብዙም አመቺ አልነበረም፡፡ምክንያቱም ዳኞቹ ትኬት ይዘው ስለማይቀር ማለት ነው፡፡ለዳኞች ውሃ ፌዴሬሽኑ ቢሮ ውስጥ በብቃት ቀርቦ ዳኞች ተጠቅመዋል፡፡

ይህ አንድ ቦታ ብቻ ዳኞች እንዲበሉ በኢትዮአዲስ ፍራንክፈርት መደረጉን አንዳንድ ዳኞች በቅሬታ መልክ አንስተውታል፡፡ቅሬታውም ለምን አንድ ቦታ ብቻ እንዲበሉ እንደተደረጉ ነው፡፡ግልጽ ለማድረግ ፌዴሬሽኑ ኢትዮአዲስ ፍራንክፈርትን ትኬት እንዲሰጠው ጠይቆ ትኬት ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ተግባራዊ የተደረገ እንደሆነ ነው፡፡በዚህም ምክንያት አንድ ጥሩ ክትፎ በመሆኑ የሚደነቀው አቅርቦት ባለቤቶች ይህን የዳኞች አንድ ቦታ ብቻ መመገብ ሰምተው ቅሬታቸውን በምሬት አሰምተዋል፡፡ትክክልም እንዳልሆነ በግልጽ ተችተዋል፡፡በዚህ ነጥብ ፌዴሬሽኑ ፈጽሞ ሊተች እንደማይገባውና ትችቱ ወደ አዘጋጁ ኢትዮ አዲስ ፍራንክፈርት ሃላፊዎች ማምራቱ ተገቢ እንደሆነ ነው፡፡ምክንያቱም ፌዴሬሽኑ ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዳኛ 8 ትኬት ለአራት ቀን ምሳና እራት የሚሆንና ለሚጠጣም ነገር እንዲሁ 8 ትኬቶች በቅድሚያ እንዲሰጠውና ፌዴሬሽኑ ለዳኞቹ ለማከፋፈል ጠይቆ አልተሳካለትም፡፡ለወደፊቱም ፌዴሬሽኑ ይህንን አቅጣጫ ተክትሎ ተግባራዊ ማድረጉ ይጠበቅበታል፡፡

የምግቡና የመጠጡ ዋጋዎች ተመጣጣኝ ነበሩ፡፡ይህም የፌዴሬሽኑ ሚና እዚህም ውስጥ ለወደፊቱም ዝምብሎ ለንግድ ብቻ ለሚመጡና ውድ ዋጋዎች በማስከፈል መክበር ለሚፈልጉት ፍሬን እንዲይዙ የሚያደርግ ሃላፊነቱን በተገቢው ሊወጣ ይገባል፡፡ዋጋው ውድ ቢሆን የተሳታፊው ህዝብ የመግዛት አቅም ያንስና የሚፈለገውም ሽያጭ ይገኝም፡፡ያሁኑ የዋጋ ተመን ጥሩ ነበር ማለት ይቻላል፡፡

የተለያዩ አማራጮች መቅረባቸውም ከሽሮ ወጥ፥ ጥብስ፥ ክትፎ፥ የፆም በያይነቱ፥ ቅቅል፥ወዘተ ለተመጋቢው ህዝብ ሲቀርብ፥ ከድን£ኖቹ ሁኣላና ፊት ተመጋቢው ተቀምጦ የሚበላበትም ቦታ ተዘጋጅቷል፡፡ ይህ መልካም ነው፡፡

የመጠጥ ትኬት ሽያጭ የሌብነት አሰራር፤

የኢትዮአዲስ ፍራንክፈርት ብዙ የሚመሰገንባቸው ነጥቦች ቢኖሩትም፥ በጣም የሚያስወቅሰውን የሌብነ ስራ በመጠጥ ትኬቶች ሽያጭ ላይ ተግባራዊ አድርÙ ል፡፡ይህም ከተራ ሌብነት ወይም ስርቆት የሚለይ አይደለም፡፡ ለምን ለሚለው? የመጠጥ ትኬት ሽያጩ ላይ በየቀኑ የተለያዩ ቀለማት ያላቸውንና ቀን የተፃፈባቸው ትኬቶችን በማዘጋጀት ለምሳሌ ዓርብ እለት አርንÙ ቀለምና BON 17.07. የተፃፈበትና ቅዳሜ ደግሞ ቀለሙ ሰማያዊ ሆኖ BON 18.07.የተፃፈበትን መጥቀሱ ጠቃሚ ነው፡፡ዓርብ እለት ማለትም 17.07.2015 ሰዎች ብዙ ትኬቶች አረንÙ ቀለም ያለውን ገዝተው ቅዳሜ እለት 18.07.2015 ለመጠቀም ቢፈልጉ መጠቀም አይችሉም፡፡ይህ የተደረገው በምስጢር መሆኑን የሚያጋልጠው ሻጮቹ ለገዢዎቹ ትኬቱ ለአንድ ቀን ብቻ እንደሚሰራ ፈጽሞ አይናገሩም ነበር፡፡ምክንያቱም በብዛት ለነገም ተነጎዲያ የሚገዙና የሚከስሩ እንዳሉ ያውቃሉና ነው፡፡ይህ የሌብነት አሰራር ለተጠቃሚው ህዝብም ሆነ ለፌዴሬሽኑም የተነገረ እንዳልሆነ ነው፡፡ለህዝቡ በድምፅ ማጉያ ከተነገረ ሁሉም ሰው የዛሬውን ብቻ ትኬት ይገዛል፡፡ በዚህ መልክ ብዙ ቅጥል ያሉ የስፖርት አፍቃሪዎች ሲንጫጩ አይተናል፡፡ የኢትዮአዲስ ከስፖርት አፍቃሪዎች ብዙ ብር ቢራ ሳይሰጥ ኪሱ አስገብቷል፡፡ ይህ ሌብነትና ዘረፋ ነው፡፡በዚህ ትኬት ዓርብ ጁላይ 17 ቀን 2015 .. ብቻ መጠጥ መግዛት እንደሚቻልበት ነበር፡፡በዚህ ትኬት ቅዳሜ ጁላይ 18 ቀን 2015 .. መጠጥ ማግኘት አንድ ሰው ቢፈልግ እንደማይችል ነው፡፡ለምን? ዓርብ እለት ትኬቱ ስለገዛውና ቅዳሜ እንዳይጠቀም ተደርጎ የተዘጋጀ የስርቆት ዘዴ በመሆኑ ነው፡፡ለምሳሌ አንድ ሰው 30 ኢሮ 15 የመጠጥ ትኬቶች ዓርብ ዕለት ቢገዛ፥ እነዚህን ትኬቶች ቅዳሜ እለት የሚጠጣ ነገር ለማግኘት ቢፈልግ መጠጥ አያገኝም፡፡ምክንያቱ ቀኑ አልፏል በማለት ነው፡፡ይህ ማለት የኢትዮአዲስ ፍራንክፈርት €30 ቢራ ሳይሰጥ ሰረቀ ማለት ነው፡፡በዚህ ድርጊት ምናልባትም ብዙ ሰዎች ብዙ ገንዘብ በመሰረቃቸው በጣም ሲናደዱ ታይተዋል፡፡ትኬት ሻጮቹም ትኬቱ ለአንድ ቀን እንደሚያገለግል ምንም ነገር ትንፍሽ እንዳላሉ ለረጅም ግዜ ተከታትለን አረጋግጠናል፡፡ ለወደፊቱ ፌዴሬሽኑም ከዚህ ዓይነቱ የሌብነት አሰራር ራሱን ነፃ አድርጎ መንቀሳቅስ ይኖርበታል ብለን እናምናለን፡፡ ለዚህ ድርጊቱ ኢትዮአዲስ ፍራንክፈርት የስፖርት ፍቃሪዎችን ይቅርታ በመጠየቅ ትኬት ላላቸው የዘረፈውን ገንዝብ ሊመልስላቸው ይገባል ባይ ነን፡፡

ሺሻና ጫት

በእፅ ሱስ የተጨማለቁ የአደንዛዥ እፅ ሺያጮች አስመልክቶ ምዩኒክ ጀርመን ዝግጅት ጋር ሲነፃፀር እጅግ በጣም ቀንሷል፡፡ይህ መልካም ሲሆን ጥቂቶች በስፖርት ሜዳው ግቢ አጥሩ ጥግ ጥግ ሆነው ሺሻ ሲያጨሱና ጫት ሲበሉ ቅዳሜ እለት ተመልክተናል፡፡ለወደፊቱ ግን ፈጽሞ ስፖርቱ ቦታ አካባቢ እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች እንዳይደርሱ በሕግ መከልከልና እምቢ ካሉም ለአካባቢው ፖሊስ አስታውቆ በፖሊስ አስፈላጊውን እርምጃ ማስወሰድ ተገቢ ነው፡፡በዚህ ስፖርት አካባቢ ብዙ ታዳጊ ህፃናትና ወጣቶች በዚህ የአልባሌ የአድንዛዥ እፅ የእሳት እራት እንዳይሆኑ ፌዴሬሽኑ ነጋዴዎቹን ያለምንም ይሉኝታ ማስወገድ ግዴታው ነው፡፡

የስፖርት ሜዳው ላይ ጭፈራ

ከቀኑ አስራ አንድ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ጀምሮ የተመልካቹ ቁጥር በየቀኑ የሚጨምርበት፥ ሙቀቱ በመጠኑም ቢሆን ቀዝቀዝ የሚልበት፥ የዲስክ ውይም ፍላሽ ሙዚቃዎች እየተለቀቁ እንግዶች በኢትዮጵያ ባህል የሚወዛወዙበት ወቅት ነበር፡፡ጭፈራው ምግቡ መጠጡ ጎን ለጎን ሆነው ሕዝቡ እየበላ እየጠጣ ቢያንስ እስከ ሌሊቱ ስድስት ሰኦኣት ድረስ የተቆየበት ሁኔታ ነበር፡፡ለዚህም በአሸዋው ሜዳ ላይ የነበረው መብራት ስለነበረ ወለል ብሎ ይታይ ነበር፡፡ይህ የሜዳ መብራት ባይኖር ኦሮ ሙዚቃውና እስክስታ ወራጆቹ ምን ይውጣቸው ነበር? ሙዚቃው ግን አንዳንድ ቀን ከኢትዮጵያዊው የባህል ሙዚቃ ወጣ ይል ነበር፡፡በዚህ የኢትዮጵያውያን የባህል በዓል ላይ በዲስክና ፍላሽ ማጫውት የሚገባው የኢትዮጵያን ሙዘቃ ብቻ ሊሆን ይገባል፡፡ በዓመት አንድ ግዜ ለሚደረገው በዓል የኢትዮጵያን የተለያዩ ሙዚቃዎችን መርጦ ማጫወቱ፥ ኢትዮጵያውያን ወጣጦች የባህላቸውን አጨዋወት ሊማሩበትና ጎልማሶች ያላቸውን የመወዛወዝ ችሎታቸውን የሚያሳዩበት መድረክ ሊሆን ይገባል፡፡ምክንያቱም በዓመት አንድ ግዜ ለኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የሚዘጋጅ የባህል ሙዚቃ በመሆኑ ነው፡፡እንዲያውም ለወደፊቱ ፌዴሬሽኑ ትናንሽ ሽልማቶችን ለወጣቶችና ለጎልማሶች ቢያዘጋጅ ብዙ ተመልካቾችን የሚስብ ይሆናል ብለን እናምናለን፡፡

ሁለት የተደነቁ ቡድኖች

በዚህ የኢትዮ አውሮፓ ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን በፍራንክፈርትጀርመን ከጁላይ 15 ቀን እስከ ጁላይ 18 ቀን 2015 በተካሄደው የእግር £ ውድድር በጥሩ አጨዋወታቸው በብዙ ሰዎች ሲደነቁ የሰማነው ከዲቪዢን A የኢትዮኖርዌይ ቡድን ሲሆን፥ ከዲቪዢን B ደግሞ ኢትዮካታንጋ ነው፡፡እነዚህ ሁለት ቡድኖች በእግር £ አጨዋወታቸው ሲደነቁ፥ በአባዛኛው በወጣቶች የታቀፉ ቡድኖች ናቸው፡፡የኢትዮካታንጋ ቡድን ጠገብን ያውቁ £ስን በደንብ መጫወት የሚችሉ፥ በወጣቶች የተገነባ ቡድን ነው፡፡ለምንስ ዲቪዢን B ውስጥ እንዳሉ ብዙ ሰው ተገርሟል፡፡ አንዳንድ ተጨዋቾች ወደግጭት የገፉበት ሁኔታ ተከስቷል፡፡ለምሳሌ ከአውስትሪያ ጋር ሲጫወቱ አንድ የውጭ አገር ዜግነት ያለው ወጣት ተጨዋች ለግጭት ሲጋበዝ እንደነበር ታይቷል፡፡ይህ የማያስፈልግና ለወደፊቱም ለቡድኑም ጠቃሚ ያልሆነ ድርጊት ነበር፡፡በተረፈ ቡድኑ £ስን ይጫወታል፡፡በርቱ ቀጥሉብት እንላቸዋለን፡፡

የኢትዮኖርዌይ ባለፈውም ዓመት ባሁኑም ውድድር በሁለተኛነት ደረጃ ያጠናቀቀ፥ £ በተቀናጀና ውጤታም በሆነ መልኩ መጫውት የሚችል ቡድን መሆኑን አስመስክሯል፡፡ከኢትዮለንደን ጋር ባደረገው የዋንጫ ውድድር በጨዋታው ወቅት ያገኘውን የፍጹም ቅጣት መት ቢያገባ አሽናፊ የመሆን እድሉ ያመዘነ ነበር፡፡ ግን አልተሳካለትም፡፡ሁለት ግዜ ሁለተኛ በመሆን ግን አንደኛ ነው፡፡በጣም የተጠና አጨዋወት ስልት ኢትዮኖርዌይ እየተጠቀመ እንደነበር ማሳበቅ ይቻላል፡፡ብዙ ጥሩ ችሎታ ያላቸው ወጣቶች ያሉበት ቡድን በመሆኑ በርቱ እንላቸዋለን፡፡

በዚህ አጋጣሚ የኢትዮለንደን ቡድን እን£ ደስ ያላችሁ እንላለን፡፡

የድምፅ ማጉያ አጠቃቀም

አንድ የፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ተወካይ የድምፅ ማጉያ ይዞ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በየግዜው በተቻለ መጠን ለመጡ እንግዶችና ስፖርተኞች ሲያቀብል እንደነበር ነው፡፡ይሄ ጥሩ ጎኑ ሲሆን፥ መረጃውን በሚያስተላልፍበት ወቅት አንዳንዴ እሱ ራሱ ያለበትን ቦታ ዬት እንደሆነ በደንብ አይገልጽም፡፡ይህ መሻሻል ያለበትና ያለበት ቦታ በቀላል ቁኣንቁኣ ለአድማጮቹ መግለጹ እሱን በቀላሉ ለማግኘት ያስችላል፡፡

ሌላው ለሚቀጥለው ግዜ ግን ሶስት የድምጽ ማጉያዎች ሊኖሩ ቢችሉና አንዱ የፌዴሬሽኑ ስራ አስኪያጆች የሚቀመጡበት ቢሮ ውስጥ፥ አንዱ ለፈዴሬሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ተወካይና አንዱ አጨዋች ዳኞች ተወካይ ቢሆን፥ ከቦታ ወደቦታ መሯሯጡናን ድካምን አላስፈላጊ የግዜ መባከንን ይቀንሳል፡፡ሶስቱም ካሉበት ሆነው የሚፈልጉትን መረጃዎች በድምፅ ማጉያው ማስተላለፍና እርስ በእርስ ያለብዙ ድካም መገናኝት ሲችሉ የሚሰሩ ስራዎችም በተቀላጠፈ ሁኔታ ሊካሄዱ ይችላሉ የሚል እምነት አለን፡፡

አበሻ ቀጠሮጠፍቶ ቀጠሮ ይከበር!

በዚህ ነጥብ ላይ አንዳንድ ቡድኖች ቀጠሮ የማክበር በሽታ ያልለቀቃቸው ቢኖሩም፥ በአብዛኛው ግነ ቡድኖች ቀጠሮ የማክበሩን ሁኔታ ተግባራዊ እንዳደረጉ ነው፡፡በፌዴሬሽኑም በኩል ይህ ቀጠሮ የማክበሩ ሁኔታ ከበፊቱ የተሻለ ቢሆንም፥ መሉ በሙሉ ተከብሯል ማለት አይቻልም፡፡ለምሳሌ የህፃናትና ወጣቶች ጨዋታው የሚጀመርበት ሰዓት ባለመከበሩ ወላጆች በጣም ሲነጫነጩ ታዝበናል፡፡መነጫነጫጨውም ተገቢ ነበር፡፡ፌዴሬሽኑ ውድድሩን ባለው ሰዓት ባለማስጀመሩ ነበር፡፡ይህ ሊሻሻል ይገባል፡፡

ሶስት እናቶች

የህጻናትና ወጣቶች እናቶች በጣም ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ ልጆቻቸውንም ሆኑ የእነርሱን ቡድን በስፖርታዊ መንፈስ በጋለ ስሜት ሲያበረታቱ ተመልክተናል፡፡ጎሽ አበጃችሁ የሚያስኝ ሲሆን፥ አንዷ እናት በሃይል በማፏጨት ቡድኗን ስታበረታታ እንደነበር ተመልክተናል፡፡

አንዳንድ ወላጆችና ቪዲዮ ቀራጮች ግን ሜዳው ላይ በመግባትና እዚ በመቆም ሕግ እየጣሱ እንደነበርና ይሄ ለልጆቹ ጥሩ ስሜት ስለማይሰጥ ልክ እንደ ትልልቆቹ የእነርሱም ጨዋታ ሊከበር ይገበዋል፡፡ስለሆነም አንዳንድ ወላጆችን የቪ ቀራጮች ለወደፊቱ ጨዋታው ሜዳ ላይ ከመግባት እንድትቆጠቡ ማሳሰብ እንሻለን፡፡

የህፃናት ጨዋታዎች የፍጹም ቅጣት ምት ሲምታም ሆነ የትልልቆቹ የፍጹም ቅጣት ምት ሲመታም ተመልካቾች ከሜዳው መውጣት ነበረባቸው፡፡ሜዳው ላይ ሊኖሩ የሚገባቸው ተጨዋቾችና ዳኞች ብቻ ነበሩ፡፡ይህ በጣም ሊወገድና ለወደፊቱ ሊሻሻል የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡

የሽልማት አሰጣጥ ስነ ስርዓት

የሽልማት አሰጣጥ ስነ ስርዓቱ ከፍ ቦታ በመሆኑ ከዚህ በፊት ከነበሩት ሁሉ የተሻለ ነበር፡፡ለተጨዋቾች የተዘጋጁ የዋንጫ ሽልማቶች፥ ለዳኞች የምስክር ወረቀት፥ ለእያንዳንዱ ቡድኖች ምስክር ወረቀት፥ወዘተ ከክብር እንግዳው ከአቶ ስዩም አባተ፥ ከፈዴሬሽኑ ሊቀ መንበርና የቴክኒክ ኮሚቴ ሃላፊ ከአቶ ዮሃንስና ከአቶ ከበደ ተሰጥተዋል፡፡በመጨረሻም የውድድሩ የአንደኛ ዲቪዚዮንና ሁለተኛ ዲቪዚዮን የዋንጫ ባለቤት ለሆኑት ኢትዮ ኤሚሊያና ለኢትዮ ለንደን የተዘጋጁት ዋንጫዎች በሽልማት መልክ ተስጥተው የሽልማቱ ስነ ስርዓት ተፈጽሟል፡፡የሽልማት ቦታው ለወደፊቱ ከፍ ያለ ልዩ ቦታ ሊዘጋጅና ተመልካቾች በተወሰነ ርቀት ላይ ሆነው ተግባራዊ የሚሆንበትን ፌዴሬሽኑ እንድሚያሳካ ተስፋ እናደርጋለን፡፡

ልዩ ልዩ

የጠፉ ህፃናትና እቃዎች

ህፃናት ጠፍተው የፌዴሬሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ተጠሪ በመምጣት እየተናገሩ ቤተሰቦቻቸው ልጆቻቸውን እንዲያገኙ ተደርጉኣል፡፡የተለያዩ እቃዎች ወድቀው አግኝተው ለፌዴሬሽኑ በመስጠት በለቤቶቻቸው መጥተው የወሰዱበት ሁኔታ ተከስቷል፡፡ይህ እጅግ የሚያስደስት ሲሆን፥ ቤተሰቦች ግን ለልጆቻችሁ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረጉ ተገቢ ነው እንላለን፡፡

የአን ደቂቃ የሕሊና ጸሎት

ፌዴሬሽኑ በሶስቱም እግር ኩኣስ ሜዳዎች ላይ ይካሄዱ የነበሩትን ጨዋታዎች ዳኞች ጨዋታውን ለአንድ ደቂቃ አቁመው በሊቢያ፥ በደቡብ አፍሪካና በተለያዩ ዓረብ አገሮች ህይወታቸውን በግፍ ላጡ ኢትዮጵያውያን የአንድ ደቂቃ የሕሊና ጸሎት አስድርÙል፡፡ይህ በጣም ሊበረታታ የሚገባና ጥሩ ድርጊት ነው፡፡

የአውሮፓው የስፖርትና ባህል ዝግጅት ጉዳይ፤

እስካሁን ድረስ በክለቦች ይዘጋጅ የነበረው አውሮፓው የስፖርትና ባህል ዝግጀት 2016 .. ጀምሮ በራሱ በፌዴሬሽኑ የሚዘጋጅ እንደሆነ መወሰኑ ነው፡፡ስለዚህ በሚቀጥለው ዓመት ማለትም 2016 .. ፌዴሬሽኑ የሚዘጋጀው የመጀመሪያው ዝግጅት ይሆናል ማለት ነው፡፡ በሽኩሽኩታ እንደተሰማው ከሆነ የሚቀጥለው ዝግጅት በሆላንድ በዴንሃግ እንደሚደረግ ነው፡፡ግን ገና እርግጠኛ መሆኑ አልታወቀም፡፡

የስፖርት ቦታውን አድራሻ ዴንሃግ ከሆነ፥ ካሁኑ የስፖርት ሜዳውን ይዞ ቢያሳውቅ ለስፖርት ቡድኖችም፥ ለደጋፊዎችም፥ ለተመልካቾችም ለዳኞችም፥ ለፌዴሬሽኑም ዝግጀት እቅድ አውጥቶ ለመዘጋጀት በጣም ጠቃሚ ይሆናል ብለን እናምናለን፡፡ለማንኛውም ሁላችንንም የዚያ ሰው ይበለን!

የሙዚቃው ዝግ ከቴዲ አፍሮ ጋር

ቀደም ብሎ ቅዳሜ እለት ማለትም ጁላይ 18 ቀን 2015 .. ምሽት ላይ የስፖርቱ ፕሮግራም ተጠናቆ በቴ አፎሮ ተዋናያነት የሚካሄደው የሙዚቃ ድግስ አይስ ስፖርትሃለ በሚባል የበረዶ ላይ መጫወቻ ስታዲዮም ውስጥ ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ለዚህም ዝግጅት መግቢያ ስፖርት ሜዳው አካባቢ €35 መግዛት ለሚፈልጉ ይሸጥ ነበር፡፡አስቀድሞ መግዛት ለማይፈልግ ግሞ €40 በዝግጀቱ ቦታ እንዲሽጥ ተደርጉኣል፡፡

ከተንሳይት በቃና

ጁላይ 26 ቀን 2015 ..

Tsedal2009@gmx.de

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live