Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ሁላችንም ፍራንክፈርት ደረስንና የኮቴ አስከፈሉን

0
0


fankfurt

ምሥጢረ ኃይለ ሥላሴ – ዙሪክ/ስዊዘርላንድ

በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የባሕልና የስፖርት ፌደሬሽን  አስተባባሪነት ለ13ኛ ጊዜ ያዘጋጀው የእግር ኳስ ውድድር እ.አ.አ. ከሐምሌ 15-18 በፍራንክፈርት ከተማ ተካሂዷል።  በ1ኛ ዲቪዚዮን 18 ቡድኖች፣ በ2ተኛ ዲቪዚዮን  12 ቡድኖች ተመድበው፣ በወጣቶችም ከ7-10 እና ከ11-14 ዕድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ወጣቶች መካከል በተደረገ ፉክክር አሸናፊዎቹ የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ተቀብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1ኛ ዲቪዚዮን እንደ አምናው ኢትዮ ኖርዌ ከኢት  ሎንዶን ገጥመው  ባልተጠበቀ ሁኔታ ሎንዶን በፍፁም ቅጣት ምት አሸንፎ ድጋሚ ዋንጫውን አንስቷል። ከሁለተኛ ዲቪዚዮን ከአዲስ አበባ የመጣው የአበበ ቢቂላ ቡድንና የጣልያኑ ኢትዮ ኢሚይልያ ተጋጥመው ኢሚይልያ  አሸንፎ ዋንጫ አግኝቷል። በወጣቶች  ከ7-10 በፍጹም ቅጣት ምት 5 ለ4 ፣ ጀርመን ኢትዮ ስዊስን ሲያሸንፍ ከ11-14 ኢትዮ ዙሪክ ኢትዮ ስዊስን 4-1 አሸንፎ ባለዋንጫ ሆኗል። የፌደሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ዮሐንስ የወጣቶቹ ውድድር እንዲሳካ ከፍተኛ ጥረት አድርጓል። ለወጣቶቹ አሸናፊዎች ሽልማቶቹ ተመልካች በበዛብት በሚኖርበት ጊዜ  ከትልልቆቹ ጋር፣ አለመሆኑ ምክንያቱ ግልጽ አልሆነም። ቢሆን ኖሮ ለወጣቶቹ ከፍ ያለ የሞራል እገዛ ይሆን ነበር።

ዘንድሮ በዳኝነት በኩል መልካም መሻሻል ታይቷል ቢባልም ሠዐት ያስከብራሉ ተብለው አደራ የተጣለባቸው ዳኞች በዚያ ጠራራ ፀሐይ ተጨዋቾቹን ሜዳ ላይ እያንቃንቁ በአንድ ወቅት ሊመገቡ ሄደዋል ሲባል በሌላ በኩል ያሉበት አልታወቀም ተብሎ ሲፈለጉ እንደነበረ እንዲህ በቶሎ አይረሳም። ጥላ በረድ እስኪል ተጠልለው ነው ያሉ ባይታጡም ቢያማክሩን ተጨዋቹቹም ሆነ ተመልካቹ መላ ይፈልግ ነበርና መጠነኛ ቅሬታና ማጉረመረመም እንደነበረ መጥቀሱ  አስፈላጊ ይመስለኛል። በነገራችን ላይ የቅዳሜው የቴዲ አፍሮ ኮንሰርትም ይጀመራል ከተባለው 4 ሰዓት ከ30 ያህል ዘግይቶ መጀመሩጊዜና አዘጋጂዎቹ እንዳልተጣጣሙ ያመላክታል። እንዲያው የሚመለከታቸው ወገኖች መሻሻል ይኖርባቸዋል ከሚለው ዝርዝር ውስጥ እንዲያስገቡትና  ለወደፊቱ ቢታረም አይከፋም ተብሎ እንጂ ስንቱ ጉድለት ተዘርዝሮ ያልቃል?

ከ11-14  የዕድሜ ክልል ውስጥ ተሳትፎና የዋንጫውን የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮ ስዊስን 4 ለ1 ያሸነፈው የኢትዮ ዙሪክ ታዳጊዎች ቡድን፤

ይኽ ፌደሬሽን የተጣመመውን እያቃና እንዲሄድ ሲያስተካክል አበጀህ እያልን ሲወላገድና መስመሩን ሲለቅ እየጠቆምን መቆየታችን በተለይ የፌደሬሽኑ የሥራ አስፈጻሚ አካላት በሚገባ ይገነዘቡታል የሚል እምነት አለኝ። በዚህ ረገድ ቅንጅት ስዊዘርላንድ ፓልቶክ ክፍል ከፌደሬሽኑ ሰዎችና ከተመልካችም ሆነ የቡድን መሪዎች አስተያየቶችን እያሰባሰበ ይኽ ፌደሬሽን ስህተቶችን እያረመ ከስፖርትና ኢትዮጵያዊነት ውጪ ያሉትን ነገሮች ሁሉ ሳይደበላላቅ በስፖርቱ፤ ከተቻለም ባሕልን ማስተዋወቁና ማስጠበቁ ላይ እንዲተኮር አሳስበናል። በዓመት አንድ ጊዜ ለተወሰኑ ቀናት ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የሚገናኙበት፣ በተለይ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገሮች ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ሕፃናትና ወጣቶች ሲገናኙ የሚፈጥረውን ሰሜት ስንመለከት በፌደሬሽኑ መጎልበት ሁላችንም ተጠቃሚዎች መሆናችን ግልጽ ነው። ግን ለመሆኑ ፌደሬሽኑ አድጓል፤ቀጭጯል ወይንስ ባለህበት ሂድ ነው? ማደግ ማለትስ ምንድነው? እንዴትስ ይለካል? እስቲ በስሱ እንፈትሸው፤  አንድ ልጅ ከተወለደ በሁዋላ  በየዓመቱ የሚያሳያቸው ለውጦች ከኣቅፍ ወደ ዳዴ ማለት ከዚያም እየተውተረተሩ መራመድና እራሱን ችሎ እስከ መሮጥ መድረሱ ከጤናማ እድገት ጋር የሚመጡ የእድገት መለኪያዎች ሲሆኑ በአዕሞሮ ማደግም እንዲሁ ጊዜውን ጠብቆ ሲመጣ በ13 ዓመት ዕድሜው ምን ያህል አድጓል?ይኽ ፌደሬሽን  የዛሬ 13 ዓመት ሲመሠረት የተወለዱ ልጆች እዚህ ፍራንከፈርቱ ውድድር ላይ ከ11-14 ዕድሜ ክልል ውስጥ ተካተው ተጫውተዋል፤ ትልቅ እድገት፣ ትልቅ ለውጥ ነው። እንግዲህ የፌደሬሽኑን እድገት እንዲህ ስንለካው ጤናማ እድገት አሳይቷል? በሀላፊነት ላይ የተቀመጡትስ አብረው  ማደግ ችለዋል? ዛሬ በበዐሉ ላይ የሚገኘው ሕዝብ ብዛት በአውሮፓ ነዋሪ ከሆነው ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ቁጥር ጋር ሲነጻጸር በውን  አድጓል? ሕዝቡ እርስ በርሱ ተጠራርቶና ተገባብዞ ስለተገናኘ ፌደሬሽኑ ያመጣው እድገት ነው ማለት ይቻላልን? እስቲ የፍራንክፈርቱን ዝግጅት ጠለቅ ብለን እንየው። ምንም እንኳን የፌደርሽኑ ስም እንደሚጠቁመው የ“ስፖርት እና የባሕል“ ቢባልም ከእግር ኳስ ሌላ ምንም አይነት የስፖርት እንቅስቃሴ አልታየም። ሩጫ የተባለውን አላየንም፣ የሴቶች የመረብ ኳስ (ቮሊ ቦል) አልነበረም። ከወትሮው ለየት ያለ እንቅስቃሴ ነበር ከተባለም ከአርብ ጀምሮ በሁለቱ ዋና ዋና መግቢያዎች ላይ የመግቢያ ዋጋ እናስከፍላለን ብለው የፌደሬሽኑ ተወካዮች ክፈል አልከፍልም የሚል ግብ ግብ እንደ ስፖርት እንቅስቃሴ ካልተቆጠረ በስተቀር ማለቴ ነው።

ይኸ ዓመታዊ ዝግጅት በተለያዩ አባል ቡድኖች ባሉባቸው የአውሮፓ ከተማዎች ውስጥ ሲዘጋጅ በአብዛኛው ቡድኖቻቸውን ተከትለው አለበለዝያም ወዳጅ ዘመድ፣ አንዳንድ ጊዜ በድምጽ (በይበልጥ የፓልቶክ ታዳሚዎች) የሚያውቁትን በአካል ለማግኘት የሚመጣው እንደሚበልጥ ያስታውቃል። እስካሁን በነበሩት ዝግጅቶች ሁሉ ማለት ይቻላል  በአውሮፓ ቀበሌዎች ካሉት ቁጥር ስፍር ከሌላቸው የስፖርት ማዕከላት ውስጥ ደረጃቸውን የመጠኑ ሜዳዎች ተመርጠው ውድድሮችን አስተናግደዋል። ደረጃቸውን የመጠኑ ሲባል፤ በቂ ማለትም ቢያንስ ሦስት ሳር ወይም ሰው ሠራሽ ሳር ለበስ ሜዳዎች፣ተጨማሪ የመለማመጃ ሜዳዎች፣ ቢያንስ ለዋና ዋና ጨዋታዎች የተዘጋጀ ባለ መቀመጫ (ስታድዮም መሰል ሜዳ/ትሪቡን፤ መብራትና ውሃ፣ በቂ የመጸዳጃ ቤቶች ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ) የ13ኛው በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የባሕልና የስፖርት የኳስ ውድድር አሸናፊ የሆነው ኢትዮ  ሎንዶን ቡድን

ከሁለተኛ ዲቪዚዮን ኢትዮ አበበ ቢቂላን አሸንፎ የዋንጫ ባለቤት የሆነውና ወደ 1ኛ ዲቪዚዮን የተዘዋወረው የጣልያኑ ኤሚልያ ቡድን

ፍራንከፈርት ከዚህ ለየት በጣም ለየት ያለ ነበር።ለዚህም ምክንያቱ አዘጋጂዎቹ የኢትዮ-አዲስ ፍራንክፈርት ቡድን ሰዎች በመጀመርያ ይዘነዋል ብለው በምስል የተደገፈ|“ማስረጃ“ ከላኩና በቡድን ተወካዮች ካስጎበኙ በሁዋላ ቦታው ስለተከለከለ ተለዋጭ ተብሎ የተያዘ መሆኑን በይፋም ባይሆን ሲነገር ሰማን። ከሚታጎል ተብሎ የተያዘ ነው ማለት ነው።ይሁን እንጂ ከዚህ የተሻለ በፍራንክፈርትና አካባቢዋ አልተገኘም ለማለት በጣም ይከብዳል።የብዙዎቹ ግምት የተሻለ ለማግኘት የበለጠ መከፈል ስለሚኖር የቁጠባ ሥራ ተሠርቷል ነው።  ዋናው ሜዳ (ቁጥር 1) የተባለው የተንጣለለና  ፊት ለፊት የሚገኝ ላሉት ሁለት!! ሽንት ቤቶች ቅርበት ይኑረው እንጂ መቀመጫ የሌለው በፍጹም ጨዋታ ለመመልከትም የማይመች ሲሆን ከሌሎች ሁለቱ ግን የተሻለው ነው ማለት ይቻላል። ሁለተኛው ሜዳ ወደ  ሗላ ሸጎጥ ያለ ሆኖ የተሰመሩት መስመሮች ሁሉ ተረጋግጠው ለመለማመጃ እንጂ ለመጫወቻ የተዘጋጀም አይመስል። ሦስተኛው ሜዳ ሀገራችን „አሸዋ ሜዳ“ የምንለው እዚህ አውሮፓ በዝናብ ወራት ቡድናት ለመሟሟቅያ የሚጠቀሙበት አሸዋ ለበስ ሜዳ እንጂ ለመጫወቻ የተዘጋጀ አይደለም። እዚያ ላይ ወድቆ ሳይገሸላለጥ የተነሳ የለም በብዙ መልክ የተቻላቸውንና አቅማቸው የፈቀደውን ሁሉ ሳይታክቱ ሲያደርጉ የነበሩትን አስተናጋጆች እጀ ሰባራ ካደረጉት አንዱ የሜዳዎቹ ጥራት ዝቅተኝነት መሁኑ መነገር ይኖርበታልና በዚህ በኩል አልተሳካም። በዚህ ላይ ፌደሬሽኑ የመግቢያ ማስከፈል ሲጀምር ለምኑ? የሚለው ጥያቄና የሜዳዎቹ ጥራት የለሽነት ጎልቶ ታዬ እንዲያም ክፍያው „የኮቴ“ ነው ያሉ ጥቂቶች አይደሉም።

ምግብና መጠጥ በተመጣጣኝ ዋጋ ቀርቧል። የሚያስመስግን ዝግጅት ነው። ቅሬታ የፈጠረውና ብዙ ሰዎችን ሲያስመርር የሰማነው ነገር ቢኖር የመጠጡና የምግቡ ቦታ ተራርቆ ትኬቱ ደግሞ የሚሸጠው ሌላ ቦታ መሆኑ በተለይም የጎብኝዎቹ ቁጥር እየጨመረ ሲመጣ  ሰልፉ ረጅም ጊዜ የወሰደና አሰልቺ መሆኑ ነው። ከላይ እንደተጠቀሰው ሁለት መጸዳጃ ክፍሎች ለ ብዙ ሽህ ሰዎች እንዴት ተደርጎ ተፈቀደ? ብዙዎቹን ከምር አበሳጭቷል። የትኬት ሽያጭ! ሰልፉን ፈርቶ በርከት አድርጎ የገዛ በዕለቱ  ሙሉ በሙሉ ካልተጠቀመበት ይቀልጣል ማለትም ይከስራል። ብዙ ጭቅጭቅም ተፈጥሯል።

ለምን? አዘጋጅዎቹ አላስፈላጊ ውዝግብ ውስጥ ሲዘፈቁ  አይተናል።በዚህ ላይ የመግቢያ ዋጋ ፌደሬሽኑ በመጠየቁ ብዙዎቹን አበሳጭቷል፣አነታርኳል። መቀመጫ አንኳን ሳይዘጋጅ ለምንድነው የመግቢያ እንድንከፍል የተጠየቅነው? ያሉ ጥቂት አልነበሩም። እምቢ ብለው አምባጓሮ የፈጠሩም ነበሩ። ክፍያ ለምን? ምን ተደረገና? ብዙ ብዙ ተጠይቋል፤ አሁን ዝም ብለን ከከፈልን ፌደሬሽኑ በቋሚነት ኪራይ ሰብሳቢ ሊሆን ነው  እያሉ ስጋታቸውን የገለፁ አያሌ ሰዎች አጋጥሞናል።

ይህ በዚህ እንዳለ ከአሁን ጀምሮ ፌደረሽኑ እራሱ እያዘጋጀ ገንዘቡም ለፌደረሽኑ በፌደረሽኑ የሚወሰንና ዝግጅቱን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር መወሰኑን ሰማን። እንዴት? ቢያንስ እስከ አሁን ድረስ  ለማዘጋጀት እድሉ ያልገጠማችው ክለቦች እንዲያዘጋጁ አይፈቀድላቸውም? ፌደሬሽኑስ ከአገር አገር ተዟዙሮ የማዘገጀቱ አቅሙ አለው? በቅርብ ሰለማውቀውና እስካሁን የማዘጋጀት እድሉ ስላልገጠመው ስለ ኢትዮ ዙሪክ  ትንሽ ማለት ፈልግኩ። ከሁለት ዓመታት በፊት (2013) ውድድሩ በኢትዮ ስዊስ አዘግጅነት ስዊዘርላንድ /ኒዮን በተዘጋጀበት ወቅት ሁሉም ነገር ጣራ የነካ ውድነት የታየበት በመሆኑ ሕዝብ ተማሯልና ስዊዘርላንድ ቢዘጋጅ ሰዉ አይመጣም የሚሉ አሉ። እውነት ነው በተጋነነ መልኩ ውድ ነበር። ያ ውድነት  ከስግብግብነት የመነጨ አንጂ  በምግብም ሆነ በሆቴል በኩል ከዚያን ጊዜው ቢያንስ እስከ 50% በቀነስ ሁኔታ ማዘጋጀት እንደሚቻል በባለሙያዎች የተደረጉት ጥናቶች ያረጋግጣሉ። ኢትዮ ዙሪክ  የሚያዘጋጅ ከሆነና የመግቢያ ፌደሬሽኑ ማስከፈል ቢፈልግ እንኳን ለኮቴ ሳይሆን ለምን እንደሚከፍል ከፋዩ እራሱ ያውቀዋል። ከፋዮች ለሚከፍሉት የሚመጥን አገልግሎት ያገኛሉ። አሁን እንደሚሰማው፤ ፌደሬሽኑ በራሱ ላዘጋጅ ካለ፣ የሚዘጋጅበትን ሀገርና አካባቢ ኮሚኒቲ ሳያሳትፍ ምን አይነት ዝግጅት ሊሆን ይችላል? በዚህ ጉዳይ ላይ በስፋትና በጥልቀት  መወያየት የሚያስፈልግ ይመስለኛል።

 

ከምድቡ 3ኛ ወጥቶ ከውድድሩ ቀደም ብሎ የተሰናበተው ኢትዮ ዙሪክ   ቡድን፤

ከእግር ኳሱ ይልቅ  በሊቢያ አይሲስ ለታረዱት ሰማአታት ቤተ ሰቦች ገንዘብ አሰባስቦ ኤርትራም ጭምር የሚገኙትን በማግኘት  ባደረገው እርዳታ  ታዋቂነትን  አግኝቷል።


ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ –ከቴዎድሮስ ሓይሌ

0
0

“…… ይህ ጦርነት ወደን ሳይሆን ተገደን የገባንበት በመሆኑ ገደልን እያልን የምንፎክርበት አይደለም ፤ በዚያም በኩል ያሉት የኛው ወንድሞች ናቸውና ፤ ምርጫችን ይህ መሆኑ ቢያሳዝንም መብታችንን ለማስከበር ያለው አማራጭ ይህ በመሆኑ ነው ……..’’

Birhanu Negaይህን ከላይ የሰፈረውን መልካምና ትሁት አባባል ሰሞኑን የተናገሩት የግንቦት ሰባናትና የአርበኞች ግንባር ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ወደ ወሳኙ ትግል በርሃ ከመውረዳቸው አስቀድሞ ነበር። ‘’ የዘመድ ቄስ እየፈታ ያለቅሳል’’ አበው እንዲሉ እኝህ የኢኮኖሚክስ ሊቅና የነጻነት ትግል መሪ ሳንወድ ተገደን ገባንበት ባሉት ትግል ፈቅደውም ሆነ ተገደው የወያኔ ወታድር ሆነው ለሚሰውት ኢትዮጽያውያን ያላችውን ሃዘንና ቁጭት የገለጹበት ቋንቋ በብዙዎች ዘንድ ክብርና አድናቆትን አትርፎላቸዋል።

ጀግና ይልሃል እንዲህ ነው በትዕቢት ሳይሆን በትህትና ፤ በፉከራ ሳይሆን በትንተና ፤ በጥላቻ ሳይሆን በወገናዊነት ፤ ሳንጃ ወድሮ ጥይቱን ታጥቆ ለሚፋለመው ወገን ያለውን ፍቅርና ሃዘኔታ የሚገልጽ በጎና አስተዋይ መሪ በመሆን ዶ/ር ብርሃኑ ያሳይው አቀራረብ በታሪክ የሚጠቀስ ነው። ከዚህም በላይ እኝህ ታላቅ ምሁር ህዝባችንን ያስደመሙት ፤ በዚህ ከራሴ በላይ ላሳር በሚባልበት ፤ ራስ ወዳድነት መለያችን በሆነበት ፤ ስግብግብነትና ምንቸገረኝነት በተንሰራፋበት ዘመን ፤ ሃብታም ሲሆኑ እንደ ድሃ ፤ በነጻነት ቢኖሩም እንደ ተጨቋኝ ፤ በምቾት ቢኖሩም እንደ ጎስቛላ ፤ ፌሽታ ደስታ ሁካታና ዳንኪራ ባለበት መኖር እየቻሉ ፤ ረሃብና ጥም ፤ ሞትና ዋይታ እባብና ጊንጥ ወዳለበት ወደከፋው በርሃ ያስውረዳቸው ፤ ሕሊና የሚባለው የሰውነት እዳ ፤ ነጻነት የሚባል ቅዱስ መንፈስ ፤ ሃገር የምትባል መልካም ርስት ፤ ሕዝብ የሚባል ታላቅ ቤተሰብ ፤ የወደቀበትን የግፍ አገዛዝ ለማስወገድ ለውሳኙ ትግል ጠቅለው ወደ ትግሉ ግንባር በማቅናታችው ከፍተኛ እክብሮት ከመቸራቸውም በላይ ለትግሉ መነቃቃትን ፈጥረዋል።

ዶ/ር ብርሃኑ የሃገር ፍቅርና ህዝባዊነት ግድ ያለው ዜጋ በመሆኑ ያኔ ባፍላነት እድሜው የተማሪውን እንቅስቃሴ ተከትሎ ወደ በርሃ በመውረድ የከፈለው የዜግነት ግዴታ ይበቃል ሳይል ባለፉት 40 አመታት ውስጥ ያልተቋረጠ ተሳትፎና ትግል ያካሄደ ከራሱ በላይ ለሌሎች የሚያስብ መልካም ዜጋ በመሆኑ ይህው ዛሬም የምቾት ኑሮውን ትቶ ስለ ሃገርና ወገን ሲል ለመስዋእትነት ተሰልፋል ። ይህ ሰው የፖለቲካ ትግሉን እንደገና ከመቀላቀሉ በፊት ያኔ ገና ወያኔ ስልጣን እንደያዘች ከመሪዎቿ ጋር በነበረው ትውውቅ የፖለቲካና የኢኮኖሚክስ ምክር በመለገስ ለስርአቱ መሻሻል እንዲያደርጉ በማገዝ ያደረገው ጥረት ምንም ውጤት ሊያስገኝ ካለመቻሉም በላይ የዚህን ሃገር ወዳድ ምሁር እንቅስቃሴ በቅጡ ባለመረዳት በግዜው እኔን ጨምሮ በተቃውሞው ጎራና በነጻ ሚድያው የተሰለፍነው ፤ በአድርባይ ምሁርነትና ፤ በጥገኛ ከበርቴነት ቁም ስቅሉን በትችትና ከዛም በዘለለ መደዴ ቃላት እንወቅሰው የነበረውን ሁሉ በመቋቋም በትግዕስትና በስክነት ቆይቶ ያ በታሪካችን የሚዘከረውን የዲሞክራሲና የነጻነት ማዕበል ካንቀሳቀሱት የቅንጅትና የሕብረት ጎምቱ ፖለቲከኞች አንዱና መሪ ተዋናይ በመሆን በተለይ ለሕዝብ በቀጥታ ይተላለፍ በነበረው የቴሌቭዥን ስርጭት የወያኔን ሹማምንት ድንቁርና በማስረጃና በትንተና እያጋለጠ ዶ/ር ብርሃኑ ያሳየው ምሁራዊና ሕዝባዊነት ታሪክ ይማይዘነጋው ሃቅ ነው።

ዶ/ር ብርሃኑ በሰላማዊ መንገድ በምርጫ ስርዐት ሕዝብ የስልጣን ባለቤት ይሆናል ከሚል እምነት በመንሳት በዲሞክራሲያዊ ሂደት ለውጥ ሊያመጣ ከጓዶቹ ጋር ያደረገው ትግል ፤ በቀማኛውና በሕገ አራዊቱ የዳቢሎስ የግብር ልጅ የሆኑት ወያኔዎች ሠብአዊነት የራቃችው የሠላምን መንገድ የዘነጉ ፤ በድንቁርና ተውጠው እሳቤያቸውን ሁሉ ባነገቱት ጠመንጃ ባደረጉ ወንበዴዎች የዶ/ብርሃኑ የሰላም ጉዞ ጨንግፎ ፤ ለሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ትግል የተደርገው ጥረት የማታ ማታ ውጤቱ ለብዙዎች ሞት ለሺዎች እስርና ስደት ከማትረፉም በላይ ለማያቋርጥ ጥቃትና በደል የሚዳርግ ማህብራዊ መገለልንና በማስፈን የማያላውስ የጭቆና አገዛዙን በማስፈኑ ፤ ትዕቢት ያደነደናቸውን ሃገር ሻጮችና ጠባብ ዘራፊ ዘረኞች ለማስወገድ ግድ ያላውን የምርጫዎች ሁሉ መጨረሻ ፤ ከመፍትሄዎች ሁሉ መዳረሻ የሆነውን የብረት ትግል ሊያስተባብር ሊታገልና ሊያታግል እነሆ የሞቀ ቪላውን የምቾት ኑሮውን ትቶ ድንጋይ ትራሱ ዳዋ ልብሱ ኮቾሮ ጉርሱ አድርጎ በጡረታ እድሜው ለሃገርና ለወገን ሲል ወስኖ በርሃ ወርዷል ፤

የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ወደ በርሃ መውረድ በዕርግጥ ሕሊና ላለው ለዚህ ትውልድ ሃፍረት ነው ፤ በችግር እሳት የሚገረፈው በሃገር አልባነት የሚሠደደው ፤ ሰርቶ የመኖር ነግዶ ማትረፍ ያልቻለው ፤ ባለግዜዎች ላቆሙት የዘር ጣዖት ካልሰገደ እንድባይተዋር ለሚታይው ፤ የባርነት መርግ የግፍ አገዛዝ የተጫነው ዘረኞች በጎጥ ተጠራርተው በሚከብሩብት ፤ ደናቁርት የስልጣንና የጥቅም ምንጮችን በተቆጣጠሩበት መኖር አይደለም ተስፋ ማድረግ እንኳ በማይቻልበት ሃገር እየኖረ ያለው ይህ ትውልድ ፤ ለመብት ለነጻነቱ ዋጋ መክፈል እያለበት ፀጥ ያለው ፤ እየሞተ የሚፈራውን እየተራበ የሚስቀውን ፤ እየዘፈነ የሚሰደደውን ፤ ከዚህ አስከፊ ሰው በላ አገዛዝ ለመላቀቅ ወኔ ያጠረውን ፤ ይህ የኔ ትውልድ ፤ ለመታደግ ብርሃኑ የወሰድው እርምጃ የሚያኮራ ቢሆንም ፤ እኛ የዚህ ትውልድ አባላት የዚህን ምሁርና ባለጸጋ ፤ ምንም ሳያጣ የእኛን ችግር ችግሩ አድርጎ ከጨካኞች መዳፍ ሊያላቅቀን በተምሳሌትነት ሁሉን ትቶ በርሃ የወረደውን መሪ ፈለግ በመከተል ን ለመብታችን ለመፋለም እንነሳ ዘንድ ለራሳችን ቃል መግባት ይኖርብናል።

ይህ ትውልድ ከዶ/ር ብርሃኑ ከቶስ ምን ይማራል? ይህ ሰው ታላቅ ምሁርና ባለጸጋ ሲሆን ለሃገርና ፤ ለዚህ ትውልድ ሲል ሃብት ፤ንብረቱን ፤ማዕረግ ፤ ክብሩን ፤የደመቀ የአሜሪካ ቅንጡ ኑሮውን ፤ ልጆችና ሚስቱን ፤ ብቻ ሁሉን ትቶ በርሃ ወረደ ። ይህ ትውልድ በሃገሩ ለመኖር መብት ነጻነትና የስራ እድል አጥቶ በሊብያ እንደክብት እንዲታረድ ፤ በደቡብ አፍሪካ እንደቆሻሻ እንዲቃጠል ፤ በሳውዲና በየመን እንደውሻ ተቆጥሮ እንዲገላታ ሃገር አሳጥቶ ያሰደደው አዋርዶ ያዋረድው የሸጠና የለወጠው ፤ በሃገሩም ተምሮ ድንጋይ አንጣፊ አንገት በመድፋቱ ፈሪ ተደርጎ ከሃገሩ ሃብት የበይ ተመልካች በመሆን የቀንና የሌት ህልሙ ነገ ምን በልቼ እውል ይሆን በሚል ተለውጦ ኑሮ ዳግት ሆኖብህ በዘር ሚዛን ከስራው እድል እየተገፋህ እነታሪኬ ባጭሩ በዘርና በፖለቲካ ታማኝነት ሁሉን ማድረግ ሲችሉ፤ በብርሃን ፍጥነት እነ እንቶኔ ኢንቨስተር ሆነው ቤትህን በላይህ እያፈረሱ ከከተማ ሲያባርሩህ ከቀበሌ እስከ ቤተመንግስት የአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ሹማምንት በታማኝነት እየተሾሙብህ ሰርቶ የመኖር ነግዶ የማትረፍ መብትህ በነዚህ ወራሪ የወያኔ አፓርታይድ ጉጅሌዎች ጫማ ተደፍጥጦ እስከመቼ ትኖራለህ!

ወያኔዎችን ወደ ኋላ ሄደህ ታሪካቸውን ብታጣራ ካንተ ያልተሻሉ ለመማርና ለመስልጠን የማይመቹ የአቦጊዳ ሽፍቶች ፤ የባንዳ ልጆችና ቁሳዊና መንፈሳዊ ድሆች ከገላቸው እድፍ ከጎፈሬያቸው ተባይ ውጭ እንኳን አንተን እያስራቡ እነሱ ጮማ ሊቆርጡ ደረቅ ጋቤጣ እንኳ ብርቃቸው የነበረች ቁጭራወች ዛሬ ሃገርህን ወረው ከእናትህ መዐድ በእኩልነት እንዳትቋደስ እጅህን እያሳጠሩ ኑሮህን የመከራ ያደረጕትን የቀን ጅቦች ልትፋለም በምትችለውና ባለህ አቅም ሁሉ እንድትንቀሳቀስ ታሪክ ሃይማኖት ሰው የመሆን ሞራል ግድ ይሉሃል። ወጣቱ ሆይ ዶ/ር ብርሃኑን የመሰል ሊቅና በሳል መሪ እግዚያብሄር አድሎህ ይህን የፋሽስት የሌባና የዘረኛ መንጋ በግዜ ለማስወገድ ካልተነሳህ ተስፋ የሌለህ በመሆኑ በሞራል በወኔና በቆራጥነት ክብርህን ልታስመልስ በቀለም ይሁን በፍራፍሬ አብዮት ፤ በሰላም ይሁን በአመጽ ፤ በጓንዴ ይሁን በጎራዴ ፤ በኤርትራ ይሁን በኡጋዴ ፤ በድግምት ይሁን በቃልቻ ፤ ብቻ በምትችለውና በማንኛውም መንገድ የትግሬ ነጻ አውጭ (ሕወሃት) በሚባለው ወሮበላ የሌባና የባዕዳን ቅጥረኛ ስብስብ ላይ ክንድህን ታነሳ ዘንድ ግዜውና ሁኔታው ግድ ይሉሃል።

ይህ ደግሞ ይቻላል!

ተችሏልም! መቻልም አለበት!!

የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ተገልብጦ 21 ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ * 39 ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

0
0

tigray
(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች የሚደርሱ የመኪና አደጋዎች ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ ነው:: በዚህ ዓመት እንኳ በዘሐበሻ ላይ በርከት ያሉ የመኪና አደጋዎችንና ካስከተለው የሰው ሕይወት መጥፋት ጋር ዘግበናል:: ከሃገር ቤት የመጣ ዜና እንደሚያስረዳው ትናንት በትግራይ ክልል የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ተገልብጦ 21 ሰዎች ሕይወታቸው መጥፋቱን ነው::

በትግራይ ክልል በክልተአውላዕሎ ወረዳ ነጋሽ በተባለ ቀበሌ አደጋው የደረሰው ከአክሱም ወደ አዲስ አበባ 63 መንገደኞች አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ኮድ 3 የሰሌዳ ቁጥሩ 51672 ኢትዮጵያ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ነጋሽ በተባለ ቀበሌ አቅጣጫ ስቶ 300 ሜትር ጥልቀት ባለው ገደል በመግባቱ ነው ሲል የአካባቢው ፖሊስ ገልጿል::

በዚህ አሰቃቂ የመኪና አደጋ 39 ሰዎች በከባድ የቆሰሉ ሲሆን ሶስት ሰዎች ብቻ ናቸው ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ሲል ፖሊስ አስታውቋል::

Health: ከባለቤትህ ጋር ስምምነት ፈጥረህ ለመኖር የምትችልባቸው 7 ዘዴዎች

0
0

‹‹ከባለቤቴ ጋር ስምምነት መፍጠር ተሳነኝ 

እባካችሁ አንድ በሉኝ››

ዕድሜዬ ሰላሳዎቹ መጨረሻ አካባቢ ሲሆን ባለቤቴም በዚሁ ክልል አጋማሽ ላይ ናት፡፡ ለአስር ዓመት ያህል በትዳር ህይወት አሳልፈናል፡፡ ደስ የሚሉ ሁለት ህፃናት ያሉን ሲሆን ሁለታችንም ዲግሪና ቤተሰባችንን ሊያስተዳድር የሚችል በቂ ገቢ እናገኛለን፡፡ ችግሬ ከባለቤቴ ጋር በነገሮች አለመስማማት ነው፡፡ ከሰዎች ጋር ተግባቢና ተጫዋች ስሆን ኧረ ለሌላው ችግርም አማካሪ ነኝ፡፡ ሚስቴ እኔ የማደርገው በብዛት አይጥማትም፣ የሆነ ነገር ገዝቼላት ስመጣ እንኳ አመሰግናለሁ በማለት ፈንታ ማሽሟጠጥና ማጣጣል ነው የሚቀናት፡፡ ይቅርታ የሚባል ነገር ፈፅሞ አልፈጠረባትም፡፡ ስህተቷን በጩኸትና ለቅሶ ለመሸፈን ትሞክራለች፡፡ ቤቴን ለማሻሻል ብዙ ነገሮችን ሞከርኩ፣ ከእኔም ችግር እንዳለ ለመፈተሽ ጣርኩ፡፡ አልሆነም፡፡ በዕውነት እንዳሰብኩት እየሆነም አይደለም፤ ደካከምኩኝ፡፡ ወደ ቤተክርስቲያን እንኳ አብረን እየሄድን ግማሽ መንገድ ሳንጓዝ መጨቃጨቅ እንጀምራለን፡፡ ትዳራችን በሰላምና በፍቅር መዝለቅ ይችል ዘንድ ምን ማድረግ እንደሚገባን ለሌላም ስለሚጠቅም ምክራችሁን ብትለግሱን፡፡

SONY DSC

SONY DSC


መልስ፡- መቼም ስለትዳር ብዙውን ጊዜ ብናወጋ በቀላሉ የምንጨርሰው አይመስለኝም፡፡ በተለያዩ አምዳችን ላይ አንስተናል፤ በሰዎች ላይም የሚያደርሰውን ተፅዕኖ በመረዳት ብዙ መንፈሳዊና አለማዊ ፀሐፍትም በየፊናቸው አውግተዋል፡፡ አሁንም ቢሆን በየትኛው የትምህርት እርከን ላይ እንደምንመድበው ባይገባንም ትዳር በህይወት ዘመናችን በርካታ ጉዳዮችን የምንማርበት መድረክ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ በዕውነት ልክ እንደሌላው ስርዓተ ትምህርት ተቀርፆለት ባለትዳሮች በዘመናቸው የሚማሩበት ዕድል ቢኖር ተመሳሳይ ችግሮች ገነው ባልተፈጠሩ፤ ቢፈጠሩ እንኳ በቀላሉ መፍትሄ ባገኙ ነበር፡፡ በቅድመ ጋብቻ ወቅት የነበረውን ለስላሳ ባህሪና ሁሌ የሚናፈቅ መረዋ ድምፅ በድህረ ጋብቻ ጊዜ ሊጎረብጥና ጆሮ ሊያሳምም ይችላል፡፡

በትዳር ህይወት ውስጥ የሚገኙ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ መቼም የአምላክ በረከቱ የትየለሌ ነው፡፡ ‹መባረክ› በገንዘብና ቁሳዊ ነገር ብቻ መስሎን ከመንገድ ወጣ ማለት ጀመርን እንጂ አሰጣጡ በተለያየ መንገድ ነው፡፡ ላንዳንዶቻችን ብዙዎች እንደምናስበው በንብረት፣ ለሌላኛው በሰው፣ ለሌላው ደግሞ በዕውቀት፣ ለሌሎቻችን በመንፈስ ፍሬዎች (ፍቅር፣ ሰላም፣ ደስታ፣ ትዕግስት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ እምነት፣ የዋህነትና ራስን መግዛት) ይባርከናል፡፡ በእርግጥ ብዙዎች ያለንን አናውቅም፤ ያወቅነውም ቢሆን ያለንን በአግባቡ አልተጠቀምንም፣ ለመጠቀምም ፈቃደኞች ያልሆንን ብዙ አለን፡፡ ያልገባን ነገር ምን መሰላችሁ ያለን የሚበዛልን የያዝነውን በመደበቅና ያለጥቅም ቁጭ እንዲል በማድረግ ሳይሆን እያወጣን ለሌላው እያካፈልን ስራ ላይ ስናውለው ነው፡፡

ሌላው ከፅሑፍህ የምንረዳው ከሰዎች ጋር በጣም ተግባቢ መሆንህን ነው፡፡ ስለዚህ ነገር በእውነት ደስ ብሎናል፡፡ እያንዳንዱ ግለሰብ ሊኖው ከሚገባ ቁልፍ ማህበራዊ ክህሎት ውስጥ አንዱ ከሌሎች ጋር ተግባብቶ መኖር ነው፡፡ አየህ እንደነገርከን ከሰው ጋር መልካም ግንኙነት ሲኖርህ የተለያዩ ሀሳባችን መካፈል ያስችልሃል፡፡ ሰዎችን ከጭንቀታቸው እረፍት እንዲያገኙ ስታደርግ፤ ውስጥህ ያለውን ዕምቅ አቅምና ክህሎት በማውጣት ለሌሎች መፍትሄ መሆን ስትጀምር በእርግጥ ደስ ይላል፡፡ ታዲያ አንተም በዚህ ሂደት ውስጥ ብዙ የምትማራቸው ነገሮች እንዳሉ እውን ነው፡፡ ከሌሎች ሰዎች ትማራለህ፤ ከራስህም ድርጊትና ተሞክሮ እንዲሁም በህይወትህ ከሚገጥሙህ መነሳትና መውደቅ ትማራለህ፡፡ ይህን ወደፊት አጠናክረህ ልትገፋበት የሚገባ መልካም ባህሪና ትልቅ ችሎታም ነው፡፡

አምላክህ እግዚአብሔር በሰጠህም ልጆች በመደሰትህ መልካም ነገር ነው፡፡ በህይወታችን ብዙ የምናማርራቸው ነገሮች እንዳሉን ሁሉ ለቁጥር የሚታክቱ ደስ የሚሉና ስለነዛም ነገር ልናመሰግንባቸው የሚገቡ ስጦታዎች አሉን፡፡ አንዳንዴ ስራ ውለህ ደክመህ፣ ቤትህ ውስጥም ከባለቤትህ ጋር በገጠመህ ጊዜያዊ ችግር ተመስጠህ ሳለህ ልጆችህ በደስታ ሲቦርቁ ስታይ ጭንቀትህን ያስረሱሃል፡፡ ከነበርክበትም ጊዜያዊ ቻናል ያወጡህና ወደ ኤፍ.ኤም… ያስገቡሃል፡፡ ልጆችህን ስታስብ ዛሬንና ነገን የተሻለ ነገር እንድትሰራ ያደርግሃል፤ ያበረቱሃልም፡፡ እንግዲህ ወንድማችን በህይወት ብዙ ተግዳሮቶች ቢኖሩም፣ በቀላሉም አሁን እንደምንላቸው ቶሎ እውን ባይሆኑም መልካም፤ ብሩህና ጥሩ የሆነውን ነገር ባሰብክ ቁጥር መልካምና የተሻለ ነገር ትሰራለህ የሚል እምነት አለን፡፡ መልካም አስብ፣ መልካም ነገር ስራ፣ መልካምም ነገር ይከናወንልሃል፡፡

ወደ ዋናው ቁም ነገሩ ስንመጣ ጥያቄህ ላንተ ብቻ ሳይሆን ለበርካታ ጥንዶችና ባለትዳሮች እንቆቅልሽ የሆነ ነገር ይመስለናል፡፡ በትዳርም ሆነ ማንኛውም ግንኙነት አልጋ በአልጋ የሆነ ምንም ነገር እንደሌለ እናምናለን፡፡ እንዲኖርም የምንጠብቅ ከሆነ የዋህነት ነው፡፡ ነገር ግን በህይወት የሚገጥሙንን ክስተቶች በአግባቡና አዎንታዊ በሆነ መንገድ ለመመለስ ከሞከርን ትዳራችንን ወደ ፈለግነው አቅጣጫ ልናመጣው እንችላለን፡፡ መሰረታዊ ከሆነው የስሜት ፍላጎቶች (የማፍቀርና የመፈቀር፣ ለራስ ያለን መልካም እይታ፣ ራስን የመቻል…ወዘተ) ባሻገር አንዳቸው የሌላኛውን ፍላጎት ማወቃቸው ለትዳራቸው መጠናከርና መሻሻል ወሳኝ የሆኑ ነገሮች ናቸው፡፡

ስለዚህ ጉዳይ በአንድ ወቅት አንዱ ወዳጃችን ሚስቶች ከባሎች ምን ይፈልጋሉ? ባሎችስ ከሚስቶቻቸው ምን ይሻሉ? የሚል ፅሑፍ የላከልንን መነሻ በማድረግና ሌሎችን መፅሐፍት በማጣቀስ የሚከተሉትን ምክሮች ተግባራዊ ብታደርጉ ትዳራችሁን አሁን ካለበት ወደተሻለ ደረጃ ታደርሳላችሁ ብለን እነሆ ብለናል፡፡ አሰጣጣችንም ለአያያዝ ስለሚያመች በአግባቡ በመያዝ በህይወታችሁ እንድትለማመዱ መሞከር የእናንተው ባለጉዳዮቹ ድርሻ ነው፡፡ ለአሁኑ እስቲ ከሚስቶች ፍላጎት እንጀምር፡፡

1. ሁልጊዜ እወድሻለሁ በላት

መቼም ስታገባት ተገደብ እንዳልሆነ ይገባናል፡፡ ወደህና ፈቅደህ ከሆነ ደግሞ ያገባሃት ልብህ ውስጥ ያለውን በማውጣት እወድሻለሁ በላት፡፡ ይህን ማለት እኮ ወጪ የለውም፡፡ ብላት ሌላ ነገር ይሰማት ይሆናል፣ ወይም ይህ ክብሬ ይቀንስብኛል አትበል፡፡ ከአምላክህ ቀጥሎ ክብርህ እርሷ ናት፤ ለርሷም አንተው ነህ፡፡ እዚህ ላይ ታዲያ በል ስላልንህ ብቻ ሳይሆን በእርግጥም ስለምትወዳት ነው ማለት የሚገባህ፡፡ መፅሐፉስ ከተደበቀ ፍቅር ግልፅ ዘለፋ ይሻላል… ሲል አላነበብክምን? አየህ እህቶች ሁሌም ቢሆን መወደዳቸውን በንግግርና በድርጊት እንድታረጋግጥላቸው ይፈልጋሉ፡፡ በእርግጥ የሚከብደው በውስጥህ የሌለውን ፍቅር ለማለት ስትሞክር ነው፡፡ ያ ማታለል ነው፣ በራስ ላይ የከፋ የስነልቦና ችግር መፍጠር ነው፡፡ ገባህ የምንልህ?

2. መረዳትና ይቅር መባልን (Understand and forgiveness)

ከሚስቶችም ሆነ ከሌሎች ሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት አንዳችን ሌሎች የሚሉትን ነገር መረዳት መቻላችን ወሳኝ ነገር ነው፡፡ የሚናገሩትንና የሚያደርጉትን ካልተረዳን፣ በነርሱም ቦታ ሆነን ካልተመለከትን አተረጓጎማችንም የተሳሳተ ነው የሚሆነው፡፡ ማንም ሰው ፍፁም ስላልሆነ ባለቤትህም ጥፋት ልትሰራ ትችላለች፡፡ ችግሯን በመረዳት ይቅርታ ለማድረግ ወደኋላ ማለት አይገባህም፡፡ እርሷ እንዳልፈጠረባት ብትነግረንም አንተ ግን ሁሌም ቢሆን ይቅር ከማለትና ከመረዳት መቦዘን የለብህም፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ እርሷን ይቅርታ ማድረግን፣ ትዕግስትን፣ ቻይነትን፣ ታስተምራለህ፡፡

መማር ዩኒቨርሲቲ ገብቶ በመመረቅ ብቻ ነው ለማለት አንደፍርም፣ ይልቁኑ አብረውን ከሚውሉ ሰዎችም መለወጥ እንዳለ እንረዳለን፡፡ ስለዚህ የምንልህ ነገር ከገባህ መልካም ግንኙነት መዝለቅ የሚችለው ይቅር በመባባል ነው፡፡ የምድሩ ብቻ ሳይሆን የሰማዩም የሚቀናው ይቅር ከልብ ስንባባል ነው፡፡ ቂም አርግዞ ብዙ መንገድ መጓዝ አይቻልም፡፡ ጊዜው ሳይደርስ ይጨናገፍና ለችግር ይዳርገናል፡፡

3. በቂ ጊዜ ማግኘትን 

ብዙዎች ሆዳችንን ለማሸነፍ አሊያም ዝናን ለማቅረብ ስንል አብዛኛውን ጊዜያችንን በስራ ማሳለፋችን አይቀርም፡፡ መድከማችን ለበጎ ቢሆንም የትዳር ህይወታችንን ግን እንዲጎዳ መፍቀድ የለብንም፡፡ ችግራችን በስራ ደክመን ጀርባችንን ከፍራሽ ላይ ለመጣል ስንጣደፍ የትዳር ህይወታችንንም አብረን እናጋድማለን፡፡ በድካም ያተረፍነውን በሽታ ስንተካከም ወንድማን እህት ሆነን እንከርማለን፡፡ የምንልህ፣ ከገባህ ሚስቶች በቂ የሆነ ጊዜ ከባሎች ማግኘትን ይሻሉና የምትወያይበት፣ አብረኻት የምትዝናናበት፣ ዕቅድህን ነጻና ግልፅ በሆነ መንገድ የምታዋይበት ጊዜ በሚገባ ስጣት፡፡ እግዚአብሔርን ባትፈራ ጥላህ ጊዜ ወደሚሰጣት ቦታ በሄደች ነበር፡፡ ነገር ግን እምነቷ ልቧን እንዳተሸፍት ስለሚከለክላት ስሜቷን ብቻ በማራቅና በመነጫነጭ ዕድሜዋን እንድትገፋ ያደርጋታል፡፡ ስሊሊህ ከዚህ አንጻርም ያላችሁበትን ሁኔታ ማጤን አግባብ ነው እንላለን፡፡

4. ከእምቢታ ይልቅ እሺ መባልን

ብዙውን ጊዜ ባለቤትህም ሆነች ልጃችሁ በሚጠይቁህ ነገር ላይ አይሆንም/እምቢታን ካስለመድካቸው አንተን መሸሻቸው እውን ነው፡፡ ምክንያቱም ሌላም ጊዜ መጠየቅ ቢፈልጉ እንኳ እሺ አይለንም የሚል ግምት ስለሚኖራቸው የጨለመ አመለካከትን ያዳብራሉ፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ሳይሆን በፊት በነበሩ ክስተቶች ላይ ይመረኮዛሉ፡፡ የጠየቁህ አይሆንም ከማለትህ በፊት ደግመህ ለማሰብ ሞክር፡፡ ይህን ስንልህ ሁሉንም ነገር እሺ በላቸው እያልን እንዳልሆነ ይታወቅልን፡፡ በእርግጥም ማለት ከተገባህ ለምን እንዳልካቸውና ለሁላችሁም ጥቅም እንደሆነ ግለፅላቸው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ለምትጠይቀው ነገር አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት ግንኙነታችሁን በቀላሉ ሲለወጥ ማየት ትችላለህ፡፡… እሺ ይበልጣል ከሺ… ሲባል አልሰማህም? አየህ ሰዎች እሺ በመባል ከጭንቀት ያርፋሉ፤ የተለያየ መላምቶችን እያሰቡ አዕምሮአቸውን በመጥፎ ነገር ከመሙላት ይተርፋሉ፡፡

5. መደመጥን

ማድመጥ ግንኙነትን ሊያሻሽሉ ከሚችሉ ነገሮች ውስጥ አንዱ እንደሆነ በተለያዩ አምዶቻችን ላይ ያነሳን ይመስለናል፡፡ በንግግራችን ወቅት ሀሳባችንን ሳንከፋፍል ትኩረት ልንሰጥ ይገባል፡፡ ማንኛውም ሰው ሚስቶችንም ጨምሮ ከሚያናግሯቸውና አብረዋቸው ካሉ ግለሰቦች መደመጥን ይሻሉ፡፡ ሚስት ከልቡ እየሰማኝ ነው ብላ የተናገረችውን ቁም ነገር ባለቤቷ እንዳልሰማ ብታውቅ ምንኛ ሊያማትና ባለቤቷ አብሯት እንዳልነበር ስትረዳ እንደሚሰማት መገመት ትችላላችሁ፡፡ ይህ ደግሞ ለርሷ ቦታ እንደማንሰጣት ሊሰማት ይችላል፡፡ በሌላ አነጋገር የምታመጪው ሀሳብ፣ ወሬ የትም የሚገባ አይደለም ነው፡፡ ስለዚህ ጉዳቱ ከማየሉ በፊት በደንብ አድምጣት፣ እየተከታተልካት ለመሆኑም የምልክት ቋንቋ አሳያት፣ ከዛም ባለፈ ያለችውን በትክክል ለመረዳት ደግመህ በሌላ ቋንቋ ንገራት፡፡ ስለዚህ የምንልህ ከጆሮ በዘለለ ባለቤትህን ከልብህ ልታዳምጣት ይገባል ነው፡፡

6. ፍቅርና ርህራሄን

ሌላው ጋብቻን ከሚያጠናክሩትና ውጤታማ ከሚያደርጉ ጉዳዮች መካከል አንዳችን ለሌላኛው የምናሳየው ፍቅርና ርህራሄ ነው፡፡ በንግግራችን ወቅት እባክሽን፣ አመሰግናለሁ ቢቻል ደግሞ ለብቻ የምንጠራባቸው ስም ቢኖረን ጥሩ ነው እንላለን፡፡ ሰዎች በኛ ውስጥ ትልቅ ስፍራ እንዳላቸው የሚገነዘቡት በምንለውና በምናደርገው ላይ በመመርኮዝ ነው፡፡ ችግሩ አንዳንድ ጥንዶች ከተጋቡ በኋላ ይህን ነገር ይዘነጋሉ፡፡ አንዳንዴ ተሳስተው እንኳ ጉንጭ፣ ከንፈር አሊያም ግንባር ላይ ያልተጠበቁ/ድንገተኛ አሳሳም አድርገው አያውቁም፡፡

7. የቤት ውስጥ የልጆች አስተዳደግ ኃላፊነትን መጋራት

ሌላው በጣም ሚስቶች የሚሹትና ባሎች ሊረዷቸው ከሚፈልጓቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ የቤት ውስጥ ኃላፊነትን መጋራት ላይ ነው፡፡ ሁለታችሁም ሰራተኞች እንደመሆናችሁ ቤት ስትገቡ ይደክማችኋል፡፡ ይህን ከግምት በማስገባት በቤት ውስጥ የስራ ክፍፍል ታደርጋላችሁን? ልጆችንስ በመንከባከብ በኩል ኃላፊነት በሚሰማው መንገድ ትተጋገዛላችሁን? ይህን ካላደረግን ሚስቶች ሊማረሩ፣ ወደፊት ልጅ ሁሉ ሲባል ላይስቡ ይችላሉ፡፡ ሁሉም የጋራ ፍሬዎቻችሁ እንደመሆናቸው በጋራ ልትንከባከቧቸው የግድ ይላል፡፡ እቤት ውስጥ የሚሰሩ ማናቸውንም ነገሮች እርሷ እስክትልህ ድረስ መጠበቅ የለብህም፡፡ ለዚህ ደግሞ ፍትሃዊ የሆነ የስራ ክፍፍልን ማድረግ ይጠይቃል፡፡

እንግዲህ የሰው ልጅ ፍላጎት እንዲሁ በቀላሉ የሚገታ ባይሆንም አቅምህ በፈቀደ መጠን ከላይ የጠቀስናቸውን ምክሮች ተግባራዊ ብታደርግ፣ ጋብቻን የሚያፀናው አምላክም ሲፈርስ ማየት ስለማይሻ ይረዳሃል የሚል እምነት አለን፡፡ ሌላው ልታስታውስ የሚገባው… ባሎች ሚስቶቻቸውን እንደገዛ ስጋቸው መውደድ ይገባቸዋል፡፡ ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል፡፡ የገዛ ስጋውን የሚጠላ ማንም የለም፤ ይመግበዋል፤ ይንከባከበዋል፤ ክርስቶስም ለቤተክርስቲያን ያደረገው ልክ እንደዚሁ ነው… የሚለውን ነው፡፡

ከላይ የዘረዘርናቸውን ነጥቦች ሚስቶችም ተግባራዊ ልታደርጉት ይገባል፡፡ ምክንያቱም ጎጂ የሚፀናው በሁለታችንም ጥረትና በእግዚአብሔር እርዳታ ነው፡፡ ከዚህ በመቀጠል ደግሞ ባሎችስ ከትዳራቸው/ሚስቶቻቸው ምን ይሻሉ? የሚለውን አጠር ባለ አገላለፅ ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡

– ባሎች ያላቸውን ችሎታና ክህሎት ሚስቶቻቸው እንዲያምኗቸው ይፈልጋሉ፡፡ ይህን ደግሞ እንዲያውቁት በተለያየ መንገድ ግለፁላቸው፡፡ ላከናወኑትም ተግባር በተለያየ መንገድ አበረታቷቸው፡፡ ጀርባ መታ፣ ሳም፣ ባሌ እኮ ባትሆን… የመሳሰሉትን ነገር ማንሳት ተገቢ ይመስለናል፡፡

– ተጨባጭ የሆነ መረጃ ሳታዩ ባላችሁን አትጠርጥሩ፡፡ በሚያደርጉት ነገር እመኗቸው፤ የሞሳድና የሲ.አይ.ኤ ስራ ከመስራትም ይልቅ ልክ እንደዚህ አይነት ምክር የምታገኙበትን ተቋም መጎብኘት መልካም ነው እንላለን፡፡

– ባሎቻችሁን አንዳንዴ በማይፈልጉት አካሄድ ለመለወጥ አትሞክሩ፡፡ በቀላሉ መለወጥ የምትችሉት መጀመሪያ ራሳችሁን ነው፡፡ ባሎቻችሁ ላይ ስህተታችሁን ለመሸፈን አልቅሶ ማታለልና መቆጣት የሚፈጥረው ዘላቂና የተሻለ ነገር የለም፡፡

– ፍቅር የማይለውጠው ነገር የለምና ፍቅራችሁን ሳትሰስቱ ለግሷቸው፡፡ ያለ እናንተ ማን አላቸው ብላችሁ? ይህንንም በተለያየ መንገድ ማለትም በፅሑፍ፣ በመሳም፣ በማቀፍ፣ የተለያዩ ነገሮችን በመስጠት ግለጡላቸው፡፡

– ባሎች መከበርን ይሻሉና ተገቢው ክብር ስጧቸው፡፡ በሚያመጡት አሳብና ምክር ላይ አሉታዊ አስተያየት ለመስጠት አትቸኩሉ፡፡

ለዛሬ ይህንን ካልን የሚበቃ መሰለን፡፡ ጤና ይስጠን እንጂ ወደፊት በዚህ ርዕስ ላይ በሰፊው እናወጋለን የሚል እምነት አለን፡፡ ከሁሉ በላይ ደግሞ አምላካችሁ በትዳራችሁ ላይ ጣልቃ እንዲገባ ጋበዙት፡፡ እርሱ የሌለበት ነገር በሙሉ ከንቱ ነው፡፡ ቸር እንሰንብት፡፡

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አቤቱታ ነገ ውሳኔ ያገኛል

0
0

temesgen
ነገ ሐምሌ 22/2007ዓም ከሰዓት 8:00 ሰዓት 6 ኪሎ በሚገኘው ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የሰበር ሰሚ አቤቱታ ውሳኔ ይገኛል።

ከታሪኩ ደሳለኝ

ተመሰገን አንዱን ጋዜጣ ሲዘጉበት በሌላ መንገድ እየመጣ አዱን በር ሲዘጉ ሌላ እየሰበረ ዱላና እንግልታቸውም ማባበያና ማስፈራሪያቸውን ንቁ ወደ ፍርሀት ፊቱን ሳያዞር ለሀገሬ ስል እሰከ ቀራኔዮ ነዉ ጉዞዬ እንደለ አለ። ገና ከሱ የተጀመረ ዕለት ተመስገን ለፍርድ ቤቱ ይህን መናገሩ ይታወቃል። እዚህ ፍርድ ቤት ሰቆም በሀገሬ ሰማይ ስር ፍትህ እንደሌለ አጥቼው አይደለም፣ ነፃ እወጣለሁ ብይ አሰቢም አልመጣሁም፣ ወሳኔው የናተ ደኞች እንዳልሆነ የፖለቲካ ውሳኔ እንደሆነና ከክሱ በፊት እንደተፈረደብኝም አውቃለሁ ታውቃላችሁ፣ አዚህ የተከሳሽ ሳጥን ውስጥ ስቆም ፍርዱ የህዝብና የታሪክ ነው ብዬ ነው። የተከሰስኩባቸው ፁሁፎቼ የማምንባቸው ሀሳቦቼ ናቸው። ወድጄ ፈቅጄ የፃፍኳቸው ናቸው፣ ዛሬም ነገም ደግሚ የምፅፋቸው ናቸው። ለሀገሬ ይበጃታ ብዬ የማምነውን ነገር ሁሉ ከማድረግ ከእምነቴ ላንድ አፍታ እንኳን ወደ ኃላ እንደማልል እንድታውቁ እፈልጋለሁ። የምታደርጉት ነገር ሁሉ አያስቆመኝም፣ መሆን ያለብኝን ሁሉ ለሀገሬ ስል እሆናለው፣ጉዞዬ እስከ ቀራኒዮ ድረስ ነው። ማለቱን እናስታውሳልን ያስታውሳሉ። ተመስገን የተናገርከውን በመሆን ግንባርህንም ቃልህንም ባለማጠፍህ በበርሃ ውስጥ አስረውህ ትገኛለህ። ለገጠመህ የጀርባና የጆሮ ህመም ህክምና እንዳታገኝ አድርገውሀል። ያለ ፍርሀት የመንከውን በመፅፍህ ወንጀል ብለው ያእሰሩበትን ሂደት እንኳን እንዳትከታተል አደርገውሀል። ቢሆንም ግን በእምነትህ ፀንተህ በዙዎችን አፍርተህ ሀሳብ እንደማይታሰር አሳይተህነሀል አሳይተሀቸዋል። ለሀገሬ ስል ነው ያልካት ሀገርህም አረሳችህም አትረስክምም።

Sport: ሰርጂዮራሞስ ወደ ኦልድትራፎርድ?

0
0

ማንችስተር ዩናይትድ በ2009 ፕሪ ሲዝን ፖርቹጋላዊው ኢንተርናሽናል ክርስቲያኖ ሮናልዶን ከሪያል ማድሪድ ከሸጠ ወዲህ በሁለቱ የዓለማችን ታላላቅ ክለቦች መካከል በግዙፍነቱ አቻ የማይገኝለት የዝውውር ውል ሊፈርም ተቃርቧል፡፡ ውሉ የሚያመለክታቸው ተጨዋቾች የስፔን ኢንተርናሽናሎቹ ዳቪድ ዳሂኦና ሰርጂዮ ራምስ ናቸው፡፡ ሪያል ማድሪድ ከወዲሁ ዳሂአን ለማንችስተር ዩናይትድ ለመግዛት ያቀደ መሆኑ ይታወቃል፡፡

Sergio Ramos Wallpapers (2)አሁን ደግሞ የማንቸስተር ዩናይትድ ኃላፊዎች ከዳሂአ የዝውውር ውል ስፔናዊው የተከላካይ መስመር ተጨዋች የዳሂአ የዝውውር አካል ሆኖ በልዋጩ ወደ ክለቡ የሚመጣበት ሃሳብን አቅርቧል፡፡ ሪያል ማድሪድ በ2005 ከሲቪያ ያስፈረመው ዋጋ 65 ሚሊዮን ዩሮስ ቢሆንም በሁለቱ የዓለማችን ሀብታም ክለቦች መካከል በሚደረገው ስምምነት ግን ይህ ዋጋው ዳቪድ ዳሂአን ከኦልድትራፎርድ ወደ ሳንቲያጎ በርናባ የሚሸኝ በመሆኑ የማውረድ ጥረት ይደረግበታል፡፡

የ29 ዓመቱ ስፔናዊ ተከላካይ ከወዲሁም ባለፈው ሲዝን መጠናቀቅ በኋላ የሪያል ማድሪዱ ፕሬዝዳንት ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ ጣሊያናዊው አሰልጣኝ ካርሎ አንቼሎቲ ከሥራቸው በሸኙበት ተግባራቸው ቅር እንዳሰኘው መናገሩ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ባሻገር የክለቡ ኃላፊዎች የገቡለት ቃልን በማክበር የኮንትራት ማራዘሚያ ውል ሳይፈቅዱለት መቅረታቸው አስገራሚ ሆኖበታል፡፡

ከዚህ በፊት ሪያል ማድሪድ ለራምስ የገባለት ቃል የዓመት ደመወዙን ወደ 10 ሚሊዮን ዩሮስ ከፍ የሚያደርግበት የኮንትራት ማራዘሚያ ውል ይፈቅዱለታል የሚል ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት ከሪያል ማድሪድ ጋር ያለው እስከ ጁን 2017 ድረስ የሚዘልቀው የኮንትራት ውሉ ግን በዓት የሚያስገኝለት 6 ሚሊዮን ዩሮስ ነው፡፡ ከመሀል ተከላካይ ሚና ባሻገር በሁሉም የተከላካይ መስመር ቦታዎች ላይ ለመሰለፍ የሚችልበት ሁለገብ ብቃትን የተላበሰውን የራምስን ቅሬታን ይበልጥ ያባባሰው ባለፉት 12 ወራት ውስጥ የሌሎቹ የሪያል ማድሪድ ተጨዋቾች ኮንትራት ውል ሲታደስ የእሱ ግን ችላ ተብሎ መዝለቁ ነው፡፡

በተለይም በክለቡ ደጋፊዎች የተጣለው ዌልሳዊው ኢንተርናሽናል ጋሬዝ ቤል የዓት ደመወዙን ከ9 ሚሊየን ዩሮስ ወደ 10 ሚሊየን ዩሮስ ከፍ ያደረገለት የኮንትራት ማራዘሚያ የዛሬ ዓመት ተፈቅዶለታል፡፡ በሌሎች ታላላቅ ክለቦች የሚገኙ የመሃል ተከላካይ ሚና ባለቤቶች ዓመታዊ ደመወዝም ከራምስ በላይ ነው፡፡ በተለይ ብራዚላዊያኖቹ ቲያጎ ሲልቫና ዳቪድ ዳሂአ በፒኤስጂ የሚፈላቸው ዓመታዊ ደመወዝ 12 ሚሊየንና 11 ሚሊየን ዩሮስ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ጆን ቴሪና ዤራርድ ፒኬን የመሳሰሉት የመሀል ተከላካይ ሚና ባለቤቶችም ከራምስ በላይ የደመወዝ ክፍያን በማግኘት ላይ ናቸው፡፡ በዚህ መልኩ ራምስ ለድፍን 10 ዓመታት የዘለቀበት ሪያል ማድሪድን የመልቀቅ ሃሳብን መያዙን ከግንዛቤ በማስገባትም ለባርሴሎና ፕሬዝዳንትነት ምርጫ እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት ጆርዲ ማጅ ራምስና ከሪያል ማድሪድ የመግዛት እቅድን ይዘዋል፡፡

ሆኖም ግን የ20 ዓመቱ ስፔናዊ ኢንተርናሽናል ከዚህ በፊት በሰጣቸው መግለጫዎች ሪያል ማድሪድን ለመልቀቅ የሚገደድ ከሆነ የመጀመሪያው ምርጫው ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በማምራት መጫወት እንደሚሆን መናገሩ የተለመደ ነው፡፡ ለበርካታ ወራቶች ስማቸው ከማንቸስተር ዩናይትድ ዝውውር ጋር በስፋት ሲያያዝ የዘለቀው የሪያል ማድሪድ ተጨዋቾች ጋሬዝ ቤልና ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ቢሆንም አሁን ግን ሆላንዳዊው አሰልጣኝ ሉዊ ቫንሃል ዳቬድ ዳሂአን በሪያል ማድሪድ የሚነጠቁ ከሆነ አጠቃላዩ የቡድኑ የተከላካይ መስመር እንደሚጎዳ ከግንዛቤ በማስገባት ራምስን ማግኘትን የመጀመሪያው ምርጫቸው አድርገውታል፡፡ በሪያል ማድሪድ ፕሬዝዳንት ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ እስካሁን ድረስ የራምስን ኮንትራትን የማራዘም ምንም አይነት ፍላጎት የሌላቸው መሆኑም ስፔናዊው የተከላካይ መስመር ተጨዋች ኦልድትራፎርድ የመድረሱ ተስፋን የበለጠ እያሰፋው የመጣ ጉዳይ ሆኗል፡፡

ከ2009 እስከ 2013 ድረስ ለአትሌቲኮ ማድሪድ የተሰለፈው ዳቪድ ዳሂም ማንቸስተር ዩናይትድን በመልቀቅ ወደ ሪያል ማድሪድ የማምራቱ ተስፋ ሰፊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በርካታዎቹ የእንግሊዝ ጋዜጦች ሰሞኑን ባቀረቡት ዘገባ ዳሂኦ ለማንቸስተር ዩናይትድ አንዳንድ ተጨዋቾች ወደ ማድሪድ ከተማ ተመልሶ ለመጫወት መወሰኑን እንደነገራቸው ጠቁመዋል፡፡ ዳሂአ ከማንቸስተር ዩናይትድ የቀረበለት 200 ሺ ፓውንድ የሳምንት ደመወዝን የሚያገኝበት የኮንትራት ማራዘሚያ ጥሪን ከወዲሁ ያልተቀበለው መሆኑ ይታወቃል፡፡
የስፔን ብሔራዊ ቡድን ጓደኛው ሁዋን ማታ በጉዳዩ ዙሪያ በትናንትናው ዕለት በሰጠው መግለጫው የ2014-15 ሲዝን የክለባቸው ኮከብ ተጨዋች ሆኖ የተመረጠው ዳሂአ ለተጨማሪ ዓመታት በማንቸስተር ዩናይትድ እንዲቆይ ከፍተኛ ጉጉትን ማሳደሩን አረጋግጦ የዳሂኦ ፍላጎት ግን ወደ ሪያል ማድሪድ ማምራት ከሆነ ውሳኔውን ልናከብርለት ይገባል ብሏል፡፡

ማታ በመቀጠልም በሰነዘረው አስተያየት ‹‹በርካታ ጉዳይ በዳሂአ ጉዳይ ላይ በተደጋጋሚ ጥያቄን ያቀርቡልኛል፡፡ የእኔ የቅርብ ጓደኛ እንደመሆኑ ከክለባችን እንዲለይ በጭራሽ አልመኝም፡፡ በአሁኑ ወቅት በዓለም ፉትቦል እጅግ ወሳኙ ግብ ጠባቂ በመሆኑም እኔ በግሌ በማንቸስተር ዩናይድ ለተጨማሪ ዓመታት እንዲቆይ ያለኝ ፍላጎት እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ሆኖም ግን ውሳኔው ከዚህ የተለየ ከሆነ በሄደበት መልካም ነገሮች እንዲገጥሙት በመመኘት ከመሸኘት በስተቀር ሌላ አማራጭ ሊኖረን አይችልም›› ብሏል፡፡
የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሉዊ ቫንሃል የሪያል ማድሪድ ተከላካይ ሰርጂዮ ራምስን የዳሂአ ዝውውር አካል አድርገው ለማግኘት እቅዳቸው ባሻገር የ24 ዓመቱ ስፔናዊ ግብ ጠባቂን ለመተካት የሚችልላቸው አስተማማኝ ብቃት ያለው ግብ ጠባቂ የመግዛት ሃሳብ አላቸው፡፡ ለዚህ ተግባራዊነት የቅድሚያ ሙሉ ትኩረታቸው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ቁጥር አንድ የሆነው ሁጎ ሎሪስን ከቶተንሃም ሆትስበርስ መግዛት ነው፡፡ ሆኖም ግን የቶተንሃም ኃላፊዎች በሁጎ ሎሪስ ላይ ያወጡት 35 ሚሊዮን ፓውንድ ዋጋ ለቫንሃል የሚዋጥላቸው አልሆነም፡፡

በኢስላም ማህፀንን ማከራየትና መከራየት እንዴት ይታያል?

0
0

 

ዳኢ መንሱር ሁሴን ስለ ማህፀን ማከራየት ከኢስላም አስተምህሮ አንፃር እንደሚከተለው አብራርተውልናል፡፡

ምስጋና ለአሏህ (ሱ.ወ) የተገባ ነው፡፡ ሶላትና ሰላም በአሏህ መልዕክተኛ በሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ይስፈን፡፡

ወደ ዋናው ርዕሳችን ከመግባታችን በፊት እንደ ኢስላም አስተምህሮ የሰው ልጆች የተፈጠሩባቸውን አራት መንገዶች እንመልከት፡፡

የመጀመሪያው መነሻችን የሆኑት የአባታችን አደም (ዐ.ሰ) አፈጣጠር ሲሆን፣ እርሳቸውም ያለ እናትና አባት በአሏኅ ችሎታና ጥበብ ከአፈር መፈጠራቸው ነው፡፡ በመቀጠልም እናታችን ህዋ ደግሞ ያለ ሴት ከአባታችን አደም ጎን ተፈጠሩ፡፡ በሶስተኛ የምናገኘው የነቢዩሏህ ዒሳ (ዐ.ሰ) ከእናት ብቻ ያለ አባት በአሏህ (ሱ.ወ) የ‹‹ሁን›› ቃል የተወለዱበት ተአምራዊ አፈጣጠር ነው፡፡ በመጨረሻ የምናገኘው ብዙሃኑ የአደም ልጆች ከእናትና አባት የተወለድን የምንራባበት መንገድ ነው፡፡
pregnancy-facts04
የሰው ልጆች ምድር ላይ የተገኘንባቸውን መንገዶች ካየን፣ በርዕሳችን ስላነሳነው ልጅ ምናልባትም ከሶስት ወላጆች እንዲገኝ ‹‹ሰለጠንኩ›› የምትለው ዓለም ስላመቻቸችው፣ ‹‹የማህፀን ኪራይ›› ኢስላም የሚለውን ትንሽ እንበላችሁ፡፡

እንደሚታወቀው ይህ ጉዳይ፣ በቀደሙት ጊዜያቶች የማይታወቅና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተጀምሮ ዓለም ላይ እየተስፋፋ ያለ ነገር ነው፡፡ ከዚህ በፊት ስላልነበረ ቀደምት የኢስላም ምሁራን በጉዳዩ ላይ የተናገሩት ነገር የለም፡፡ በተጨማሪም ታዋቂ የሙስሊሙ ማህበረሰብ መሪዎች (የመዝሃብ ባለቤቶች) የነበሩ፣ ይህን ጉዳይ በኢስላም መፈቀዱን ወይም አለመፈቀዱን የዘገቡትም የተናገሩትም ነገር የለም፡፡

እዚህ ላይ ልብ ልንል የሚገባን ነገር ቢኖር፣ የሙስሊሙ የመዝሃብ መሪዎች ከቁርአን እና ከሐዲስ (የነብዩ ሙሐሙድ አስተምህሮ) ባገኙት ትንተና ሰጥተዋል፡፡ ይህ አይነቱ ትንታኔ ደግሞ ከቁርአን እና ከሐዲስ ቀጥሎ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ቦታ አለው፡፡ ሕይወቱንም እዚያ ላይ ባገኘው ሕግ ነው የሚመራው፡፡

ለዚህም ነው ከላይ በጉዳዩ ላይ ከነርሱ የተገኘ ማብራሪያ አለ? ወይስ የለም የሚለውን ለማስቀመጥ የሞከርነው፡፡ እነሱ የሰጡት ትንታኔ የለም ማለት ግን ኢስላም ስለዚህ ጉዳይ የሚሰጠው ብያኔ የለም ማለት አይደለም፡፡ አሏህ (ሱ.ወ) ከቁርአኑ ላይ እንዲህ ብሏል፡-

‹‹በመጽሐፉ (በቁርአን) ውስጥ ምንም (ስለምንም) ነገር (ሳንገልፅ) አልተውንም›› (አል አንአም 38) በሌላ ምዕራፍ ላይም፣ ‹‹ዕውቀቱ ከሌላችሁ የዕውቀት ባለቤቶችን ጠይቁ›› (አል አንቢያእ 7)

ይህ ማለት፣ የትኛውም አዲስ ነገር ቢፈጠር የሚፈጠረው ነገር ጠቅለል ብሎ በተቀመጠው የአሏኅ (ሱ.ወ) ቃል (ቁርአን) እና የመልዕክተኛው ንግግር (ሐዲስ) ሕግ ስር በጊዜው በሚኖሩ ምሁሮች ጥልቅ እይታ እና ግንዛቤ በሚኖሩ ምሁሮች ጥልቅ እይታ እና ግንዛቤ መሰረት ተገቢ የሆነ ትንተና እና ብያኔ ይሰጥበታል፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው፣ ይህ ጉዳይ መጤ ከመሆኑም ጋር አንዳንድ ሰዎች ስለ ጉዳዩ ሰፊ ጥናት ሳያደርጉ፣ በደፈናው ችግር እንደሌለውና ለሰዎች ጥሩ የሕይወት መቀጠያ ዘዴ አድርገው ይገልፁታል፡፡ ነገር ግን ይህ አመለካከት እንደማያዋጣና ጉዳዩን ትኩረት ሰጥተን ልናየው እንደሚገባ በዚህ ጽሑፍ ለመጠቆም እንሞክራለን፡፡

ማህፀንን ስለማከራየትም ሆነ መከራየት አሁን ላይ ያሉ ሙስሊም ምሁራ የሰጡትን ትንታኔ እና ብያኔ ከማየታችን በፊት አላህ (ሱ.ወ) ስለ ሀፍረተ ገላችን ምን እንደተናገረ አጠር ባለ መልኩ እንመልከት፡፡

አንደኛ፡- ‹‹(አማኞች) እነዚያ ብልቶቻቸውን (ከሐራም) የሚጠብቁት…›› (አል ሙእሚኑን፤ 5-6)

ከአንቀፁ እንደምንረዳው፣ አላህ (ሱ.ወ) አንድ ወንድ በሸሪዓዊ መንገድ ከተፈቀደችለት ሴት ውጭ የሚያደርገውን የግብረ ሥጋ ግንኙነት እርም አድርጓል፡፡

ሁለተኛ፡- አሏህ (ሱ.ወ) የሰውን ልጆች ዘራቸውን እና ልጆቻቸውን እንዲጠብቁ አደራ ብሏል፡፡

ሀፍረተ ገላችንን እና ክብራችንን እንዴት መጠበቅ እንዳለብን በአጭሩ ይህን ካልን፣ ወደ ዋናው ርዕሰ ገዳይ ስንገባ ማህፀን ማከራየት ካለምንም የሐሳብ ልዩነት በኢስላም ክልክል (ሐራም) ነው ይሉናል- ሙስሊም በኢስላም ክልክል (ሐራም) ነው ይሉናል- ሙስሊም ምሁራኑ፡፡ ለዚህም የሚከተሉትን ምክንያቶች ያቀርባሉ፡፡

1. የሚወለደው ልጅ የእናት፣ የአባት ብሎም የዘር እውቅናን ሙሉ በሙሉ ይህ ነው ለማለት ብዥታ ውስጥ ይከተላል፡፡ ይህ ብዥታ በኪራይዋ እናት እና በዋናዋ እናት መካከል ወደ ፀብ ይወስዳል፡፡ የሚወለደው ልጅ ከሁለቱ እናቶች የአንዷ እንደሆነ እርግጠኛ ብንሆንም፣ በእርግጠኝነት የዚህች ነው ብሎ መወሰን ግን አንችልም፡፡ ከሳይንሱም ጋር ተያይዞ በዘርፉ ሰፊ ጥናት ያደረጉት ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮች ስለ ችግሩ ብዙ የሚሉት ስላለ ያንን ፈልጎ መረዳት ከእኛ የሚጠበቅ ይሆናል፡፡ ስለዚህ እንደ ኢስላም ህብረተሰቡ ይህን እንዲርቀው ይመከራል፡፡

2. ይህን ጉዳይ ከወንዱ ፍትወት እንዲሁም ከሴቷ እንቁላል ለመውሰድ ሂደቱ የእሷንም የሱንም ሀፍረተ ገላ ማየት ይጠይቃል፡፡ በተጨማሪም የኪራይዋ እናት ሀፍረተ ገላን ማየት ግድ ይላል፡፡ ይህ ደግሞ ከላይ ከተጠቀሰው የኢስላም አስተምህሮ ጋር ይጋጫል፡፡ የሌላን ወገን ሀፍረተ ገላን ማየት ክልክል ስለሆነ (ባል የሚስትን ሚስት የባልን ሐፍረተ ገላ ማየት ሲቀር)

ይህን በተመለከተ አሏህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- ‹‹ለአማኝ ወንዶች እይታቸውን እንዲቆጣጠሩና ብልቶቻቸውንም እንዲጠብቁ ንገራቸው›› (አን ኑር 30)

ይህም አንዱ የሌላውን ሀፍረተ ገላ አይመልከት፡፡ ለዚያም እይታውን ወደ ታች ይመልስ፣ የራሱንም ሀፍረተ ገላ ይሸፍን ማለት ነው፡፡ ከፊል ሙስሊም ምሑራን በጣም ለከፋ ችግር ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ፣ (ሴት ከሆነች አባቷ፣ ባሏ፣ ለአቅመ አዳም የደረሰ ወንድሟ ወይም ልጇ ባሉበት) መታየት እንደሚቻል ብይን ይሰጣሉ፡፡

ይህ አይነቱ ጥንቃቄ ያስፈለገውም፣ ሰይጣን የሰው ልጆች ከአምላካቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት በማቋረጥ የራሱ ግብረ አበሮች እንዳያደርጋቸው በማሰብ ነው፡፡ ተቃራኒ ፆታዎች ከተፈጥሮ መሳሳቡ ጋር የሰይጣን ጉትጎታ ሲጨምር፣ ህገ ወጥ የሆኑ መነካካትና መተያየት ወደ ዝሙት እንዳያመራቸው ነው፡፡

3. የማህፀን ኪራይ የምዕራቡ ዓለም ‹‹ስልጣኔ›› የፈጠረው ግኝት ነው፡፡ በተለይ ከሃይማኖት ህግጋት አንፃር ስልጣኔቸው ደግሞ በከፊል ሰይጣኔ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ኢስላም ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ጋር ሰፊ ግንኙነት ቢኖረውም ሰዎች ከተፈጠሩለት አሏህን የማምለክና ለትዕዛዙ እጅ የመስጠት አላማ ጋር የሚያጋጭን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውጤት አያስተናግድም፡፡

ጠቅለል ባለ መልኩ፣ በስልጣኔ ስም ሁሉንም መከተል ሳይሆን ጥሩና መጥፎ ጎጂና ጠቃሚውን ለይተን ልንጠቀምበት እንደሚገባ ኢስላም ያስተምራል፡፡

ኢስላም እንደ እምነት፣ ለስነ ምግባርና ባህሪ በጥቅሉ ለመልካም ማህበራዊ እሴቶች ትልቅ ዋጋ ይሰጣል፡፡ በተቃራኒው ምዕራቡ ዓለም ደግሞ ለዚህ ጉዳይ ትኩረት ሲሰጥ አይታይም ይላሉ ምሁራኑ፡፡ ስለ ማህፀን ኪራይ ክልክልነት ለማስረዳት ከተነሱት ምክንያቶች፣ ማህበረሰባዊ ቀውሶችን ስለሚያስከትል ሸሪዓዊ (ኢስላማዊ ሕግ) መነሻ የለውም የሚል ነው፡፡ ይልቁንም ማህፀን የሴቷ ሀፍረተ ገላ ስለሆነ ለሕጋዊ ባሏ እንጂ ህጋዊ ባሏ ያልሆነ ወንድ ፍትወት ተቀብላ ልታሳድግበት አይፈቀድላትም፤ ሸሪዓ አምርሮ ይቃወመዋል፡፡

እንደ ኢስላም አንድ ወንድ ያላገባትን ሴት ባይተዋር ለሆነ እርግዝና የመጠቀም መብት የለውም፡፡ በሌላ አገላለፅ አንዲት ሴት ማህፀኗን ላላገባት ወንድ ስታከራይ ሀፍረተ ገላዋን በጋብቻ ላልተሳሰራት ወንድ እየፈቀደች ነው፡፡ እርሷም ለእርሱ እርሱም ለእርሷ ስለማይፈቀዱ ሙሉ ዝሙት ይሆናል ባይባልም ተግባሩ ግን ሙሉ በሙሉ ሐራም ነው፡፡

የእርሱን ፍትወት በእርሷ ውስጥ እንዲያሳድግ ከማድረጉም በላይ፣ ፅንሱ የሚመገበውና የሚያድገው በማህፀን ውስጥ ስለሆነ በጎም ሆነ መጥፎ ተፅዕኖ የሚያርፍበት ከኪራይዋ እናቱ ነው፡፡ ስለሆነም ይህቺ ሴት የጎጂ ልማዶች (መቃም፣ ማጨስ፣ አልኮል መጠጣት ወዘተ…) ተጠቂ ብትሆን ፅንሱ ከጅምሩ ገና ለአደጋ ተጋላጭ ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ ሂደት ላይ ጽንሱን የሚከታተለው ዶክተር፣ ፅንሱ ላይ የአካል ጉዳት ይታያልና የወሊድ ጊዜሽ ከመድረሱ በፊት በቀዶ ጥገና ወጥቶ ጽንሱ መታከም አለበት ቢላት ፈቃደኛ ትሆናለች? የእኔ ለማትለው የሰው ልጅ ትክክለኛዋ እናቱ ብትሆን፣ ልታደርገው የምትችለውን የራሷን ሕይወት ቤዛ የማድረግ ጥያቄ ትቀበላለች?

እዚህ ላይ ሌላ ሳንጠቅስ የማናልፈው ሐሳብ ቢኖር፣ በሕጋዊ ባልና ሚስቶች መካከል በተፈጠረ አንዳች ውስጣዊ ችግር ምክንያት፣ ሚስቲቱ መፀነስ ካልቻለች በሕክምና ድጋፍ የባሏን ፍትወትና የራሷን እንቁላል ውጭ ላይ አሳድጎ ፅንሱን ወደ ራሷ ማህፀን አስገብተው ቢወልዱ የራሳቸው እስከሆነ ድረስ ችግር እንደሌለው ሙስሊም ምሑራን ይገልፃሉ፡፡

4. በእርግዝና ወቅት ያልተጠበቁ እንደ ስኳር፣ የደም ግፊት ያሉ ከባባድ ህመሞች የሚገጥሟቸው ሴቶች አሉ፡፡ እነኚህ በሽታዎች በአፋጣኝ ህክምና ካላገኙ የነፍሰ ጡሯን ህይወት ሊቀጥፉ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ፅንሱን ለመጠበቅ (ለማዳን) ቀዶ ህክምና (ኦፕራሲዮን) የግድ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁን ኃላፊነትስ የሚወጣው ማን ነው? ይህቺው የኪራይ እናት ወይስ የእንቁላሏ ባለቤት?

ከዚህ ሂደት ጋር ተያይዘው የተለያዩ እንግዳ ነገሮችም ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ እነዚህን የባህል፣ የስነ ልቦና እና ሌሎች ማህበራዊ ቀውሶች እንዴት ነው የምንፈታቸው? ኃላፊነቱን ለየትኛይቱ እናት እንስጣት?

ከዚህ በመነሳት አንድ ድምዳሜ ላይ እንደርሳለን፡፡ ይኸውም ፅሱ በዚያችው በእውነተኛ እናቱ ማህፀን አሏህ (ሱ.ወ) እንደፈቀደለት ይኑር፡፡ እናቱም ጽንሱን የመጠበቅና የመንከባከብና በአሏህ ፈቃድ ጊዜው ሲደርስም የመውለድ ሰብአዊ፣ ሃይማኖታዊና ህጋዊ ግዴታ ይኖርባታል፡፡

‹‹ማህጸን መከራየት ሞግዚት እንደመቅጠር ነው›› የሚሉ አንዳንድ ወገኖች አሉ፡፡ ፍየል ወዲያ… እንዲሉ፣ ይህ ጤነኛ አዕምሮ ሊቀበለው የማይችል ሐሳብ ነው፡፡ አንድን የተወለደ ልጅ ሞግዚት ብትንከባከበው፣ ጡቷን ብታጠባውና ብታሳድገው ልጁ በኪራይ ማህፀን እንደሚያድገው ፅንስ ያለ ተፅዕኖ አይገጥመውም፡፡ ከሞግዚቷ ጋር አለመግባባት ቢፈጠር ወይም በሆነ ምክንያት ጡት ማጥባት ብትከለክለው (ብታቆም)፣ ልጁ በቀላሉ ወደ ወላጅ እናቱ ተመልሶ አስፈላጊውን እንክብካቤ ማግኘት ይችላል፡፡ ህይወቱም ያለምንም እንከን መቀጠል ትችላለች፡፡

5. የማህፀን ኪራይ፣ በትዳር ህይወት ውስጥ በባልና ሚስት መካከል ሌላ ሶስተኛ ሰው ጣልቃ እንዲገባ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡ ባል ወደ ኪራይ እናት የሚሳብበት ክፍተት ይፈጠራል፡፡ ይኸው መጤ ፍልስፍና በምዕራቡ ዓለም ውስጥ ብዙ ቀውሶችን እያመጣ ይገኛል፡፡ አንድ ክስተት እንደ አብነት ብናነሳ፡፡ እንግሊዝ ሀገር ውስጥ ዋናዋ እናት ለኪራይዋ እናት ለመክፈል የተስማማችውን 20 ሺ ፓውንድ የማህፀን ኪራይ ጊዜው ደርሶ ልጇ ከተወለደላት በኋላ አልከፍልም በማለት ጭቅጭቅ አስነስታ ነበር፡፡ የኪራይዋ እናትም ‹‹ብሩን ካላመጣሽ ልጁ የእኔ ነው፣ እውቅና አልሰጥሽ›› ብላ ክስ እንደመሰረተችባት ተሰምቷል፡፡ ይህ ወረርሽኝ በእኛ ሀገር ደረጃ ደግሞ ከዚህ የከፋ ችግሮችን ይዞ እንደማይመጣ ምን ያህል እርግጠኞች ነን?  ስለዚህ ልብ ያለው ልብ ይበል ነው ነገሩ፡፡

የወንድ ዘር (ስፐርም) ልገሳ

ስለማህፀን ኪራይ ካነሳን ዘንዳ፣ ጉዳዩ ተቀራራቢነት ስላለው የወንድ ዘር (ስፐርም) ልገሳን በተመለከተ ትንሽ ማለት ወደድን፡፡ እርስዎ እስካሁን ከሰሟቸው ልገሳዎች ‹‹የደም፣ የልብ፣ የኩላሊት፣ የዓይን ልገሳ ወዘተ…›› ባለፈ ወንዶች ፍትወታቸውን በመለገስ ላይ ናቸው፡፡ በዚህ ሂደት ደግሞ አንድ ‹‹ቸር›› የሆነ ወንድ፣ በዚህ ልገሳ ከተሰማራ ስለማንነታቸውና ስለዚህች ምድር ዕጣ ፈንታቸው የማይጨነቅላቸውን ጭራሹንም የማያውቃቸውን የትየለሌ ልጆች ሊያፈራ እንደሚችል መገመት አያዳግትም፡፡

ይህ የማስተዋል አቅሙ ላልከዳው ሰው፣ እጅግ ከባድና ዘግናኝ በመሆኑ ለመስማት እንኳን የሚከብድ ጉዳይ ነው፡፡ ኢስላም በተለይ ወንድ እንደ አባት ለልጆቹ፣ የምድራዊም ሆነ ሰማያዊ ዓለም ሁለንተናዊ ዕጣ ፈንታቸው የሚበጃቸውን የማመላከት፣ የመንከባከብና መሰል ኃላፊነቶች አስረክቦታል፡፡ ወንዱ የአባትነት ሚናውን ለማይወጣበት ይህ አይነት የዘር (ስፐርም) ልገሳ ክልክል ነው፡፡

ኦባማ ጋዜጠኞች መታሰር የለባቸውም አሉ * መሪዎች የስልጣን ጊዜያቸው ሲያልቅ መውረድ አለባቸው ሲሉ አስጠነቀቁ

0
0

obama
ከአሰግድ ታመነ

የኢትዮጵያ መንግስት በዲሞክራሲያዊ ምርጫ የመጣ ነው በማለት እጅጉን አስቀይሞን የነበረው ኦባማ ዛሬ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ልዩ ሆኖ ቀረበ።

ኦባማ “ዴሞክራሲ ማለት ፎርማል ምርጫ ማለት ብቻ አይደለም” ሲል አዳራሹ በአንድ እግሩ ቆመ ጭብጨባው ቀለጠ ፉጨቱ አስተጋባ ሁሉም በዚህች ሰበብ ምርጫ እያጭበረበሩ እዴሜ ያራዝሙ ስለነበር እውቅና ያገኙ መሰላቸው የኦባማ ንግግር ግን ባላሰቡት መንገድ ነበር የቀጠለው “ጋዜጠኞች ስራቸውን በመስራታቸው የሚታሰሩ ከሆነ ፣ ወይም መንግስት ሲቪል ሶሳይቲ ላይ በሚወስደው ጥብቅ እርምጃ ንቁ የፖለቲካ ተሳታፊዎች ዛቻ የሚደርስባቸው ከሆነ ያኔ ዴሞክራሲ ስሙ ብቻ ይኖራችኋል ነገር ግን ቁም ነገሩ እና በጣም አስፈላጊ የሆነው ፍሬ ነገር አይኖረውም” በማለት ኩም ሲያደርጋቸው እየደበራቸውም ቢሆን ጭብጨባውን አምበጫረቁት።

እኔ አምናለው ሀገራት የሰጡትን የነፃነት ሙሉ ተስፋ ከፍፃሜ ማድረስ አይችሉም የህዝባቸውን ሙሉ መብት እስካልጠበቁ ድረስ በማለት የህዝብ መብት መከበር እንዳለበት በአንክሮ አሳሰበ።

እኔ አይገባኝም ሰዎች ስልጣን ላይ ረጅም ጊዜ መቆየት ለምን እንደሚፈልጉ በተለይ ብዙ ገንዘብ ካገኙ በኃላ። የአፍሪካ መሪዎች ህገ-መንግስታቸውን ማክበር አለባቸው ፣ የስልጣን ዘመናቸው ሲያልቅ ከስልጣን መውረድ አለባቸው ስልጣን ለማራዘም ሲባል ህገ-መንግስቱን የሚቀያይሩ ከሆነ አለመረጋጋትን ይፈጥራል በማለት የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ለሶስተኛ ጊዜ ለስልጣን መወዳደራቸውን ተከትሎ የተነሳውን ረብሻ በመጥቀስ ማንም ሰው እድሜ ልኩን ፕሬዝዳንት ሆኖ መኖር አይችልም አለ።
እኔ ፕሬዝዳንት መሆኔ ለእኔ ልዩ መብት ነው ከዚህ የተሻለ ኢንተረስቲንግ ስራ አላገኝም ነገር ግን ማንም ሰው ከህግ በላይ መሆን አይችልም ፕሬዝዳንቱም ጭምር ስለዚህ ስለዚህ ለሶስተኛ ጊዜ እንድወዳደር ህጉ ስለማይፈቅድልኝ ስልጣኔን አስረክባለው። እኔ ብቻ ለሀገሬ እማስብ እና መስራት የምችል ብሎ ማሰብ ስህተት ነው በማለት የአፍሪካ መሪዎችን እስከ አፍንጫቸው ነግሯቸው ወረደ።


ኮማንደር ወልደሚካኤል ገ/እግዚአብሄር እና ካሕሳይ ነጋሽ በአርበኞች ግንቦት 7 መገደላቸውን ትህዴን አስታወቀ

0
0

clash
በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ማይ-ሰገን በተባለው አካባቢ የሚገኙትን የኢህአዴግ የሰራዊት አባላት በግንቦት 7 አርበኞች ግንባር ሰራዊት በደረሰባቸው ድንገተኛ የማጥቃት እርምጃ ምክንያት ሙትና ቁስለኛ መሆናቸውን የትህዴን መረጃ መረብ ለዘ-ሐበሻ በላከው መረጃ አመለከተ::

ባለፈው ቀናት በሑመራ አካባቢ ማይ ሰገን በተባለው ቦታ ላይ የግንቦት 7 አርበኞች ግንባር ሰራዊት በኢህአዴግ ሰራዊት ላይ ባደረሱት ድንገተኛ የማጥቃት እርምጃ ብዛት ያላቸው ታጣቂዎች ከጥቅም ውጭ ማድረጋቸውን የገለጸው መረጃው በውጊያው ከተገደሉት ታጣቂ አመራሮችም። ኮማንደር ወልደሚካኤል ገብረእዝጊአብሄር የሃይል አዛዥ የነበረ፤ ካሕሳይ ነጋሽ በባዕኸር የሚልሻ አዛዥ የነበረ፤ ለግዜው ስሙ ያልታወቀው የሻምበል ማእርግ ያለው በ24ኛ ክፍለጦር የሓይል አዛዥ የሆነውና ሌሎች የሚገኙባቸው እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል። እነዚህ የስርዓቱ ታጣቂዎች- በአካባቢው ሰላማዊ ህዝብ የተለያዩ ግፍ ሲፈፅሙ የቆዩ በመሆናቸው የተነሳ የግንቦት 7 አርበኞች ግንባር ሰራዊት በላያቸው ላይ እርምጃ መውሰዱን የተገኘው መረጃው አስረድቷል።

ቀስተደመና ቀድሞ ለተቀሰተባት፣ ለሰው ዘር መገኛ ለኢትዮጵያ! –ባራክ ኦባማ

0
0

ADF6D103-B2F3-45BA-BEC7-4DA0AC962E4A_w640_r1_sየኢትዮጵያና የአሜሪካ ሕዝቦች ምንጫቸው አንድ ስለመሆኑ ማስረጃ አለን ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለሌላ የምዕት ዓመት የሁለቱ ሃገሮች ግንኙነት፣ አንድ ለሆነው ሰብዓዊ ቤተሰብ፣ ቀስተደመና ቀድሞ ለተቀሰተባትም ምድር ለኢትዮጵያ እንዲሁም “ለጤናችን” ፅዋ አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያና የአሜሪካ ሕዝቦች ምንጫቸው አንድ ስለመሆኑ ማስረጃ አለን ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለሌላ የምዕት ዓመት የሁለቱ ሃገሮች ግንኙነት፣ አንድ ለሆነው ሰብዓዊ ቤተሰብ፣ ቀስተደመና ቀድሞ ለተቀሰተባትም ምድር ለኢትዮጵያ እንዲሁም “ለጤናችን” ፅዋ አንስተዋል፡፡

የሁለቱን ሃገሮች ወዳጅነትና ግንኙነቶች መሠረቶች የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝም “እጆቻችንን ዘርግተን እንኳን ደኅና መጣችሁ እንላለን” ብለዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Source – V O A

በረከት ስምዖን ደክመዋል

0
0
በረከት ስም ዖን እና ባለቤታቸው ወ/ሮ አሰፉ

በረከት ስም ዖን እና ባለቤታቸው ወ/ሮ አሰፉ

* በጥቂት ቀናት በ እንግሊዝ; በጀርመን እና በሳዑዲ አረቢያ ህክምና ውስጥ ነበሩ
* በልብ በሽታ የተነሳ ከመጠጥ ከብስጭት እና ከአልኮል መጠጦች እንዲርቁ ተመክረው ነበር
* ሳዑዲ አረቢያው ብግሻን ሆስፒታል በሕይወት ብዙም እንደማይቆዩ ተነግሯቸዋል
* በረከት ለወ/ሮ አሰፉ “ከዚህ በኋላ የምተርፍም አይመስለኝም” ብለዋቸዋል

 

(ዘ-ሐበሻ) ለኢትዮጵያ ውድቀት ተጠያቂ ከሆኑት ሆዳም የብአዴን መስራች አባላት ውስጥ አንዱ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን የጤና ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ:: ለአቶ በረከት ህክምናም ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ እየፈሰሰ ነው::

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን በሳዑዲ አረቢያ ሲደረግላቸው የቆየው ህክምና ምንም ሳይረዳቸው በመቅረቱ በቅርብ ቀናት ውስጥ ህመማቸው ተባብሶ ወደ እንግሊዝ ሃገር ተጉዘው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወደ እዚያው እየተላከ ሲታከሙ ቢቆይም ከህመማቸው ሊድኑ አለመቻላቸው ተገልጿል::

የ እንግሊዝ ሃገር ህክምናውም ያልረዳቸው አቶ በረከት ወደ ጀርመን ሃገር ለተሻለ ህክምና ሄደው የነበረ ቢሆንም ያም ቢሆን ውጤት አልባ እንደሆነባቸው የቅርብ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ አስታውቀዋል:: ለአቶ በረከት ስምዖን ህክምና በሳዑዲ አረቢያና በደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ወጪ እየወጣ የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ በ እንግሊዝ ሃገር እና በጀርመን ከፍተኛ ገንዘብ እየወጣ ቢታከሙም ውጤት እንደጠፋ የገለጹት ምንጮች አቶ በረከት ለባለቤታቸው ወ/ሮ አሰፉ “ካሁን በኋላ ዋጋ የለኝም:: በሕይወት የምቆይም አይመስለኝም:: ወደ ሃገሬ መልሱኝና እዚያው እንደሆንኩ ልሁን” እንዳሉ አስታውቀዋል::

በረከት ለንደን ለህክምና ሲሄዱ የተነሱት ፎቶ

በረከት ለንደን ለህክምና ሲሄዱ የተነሱት ፎቶ


በጤናቸው ከፍተኛውን ተስፋ የቆረጡት አቶ በረከት ሕይወታቸው በአስጊ ሁኔታ ላይ እንዳለ የቅርብ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::

በሌላ በኩል ጅዳ የሚገኘው ኢትዮጵያ ሃገሬ አቶ በረከት ከጀርመን ህክምና መልስ ሳዑዲ አረቢያ እንደነበሩ ዘግቧል::

እንደዘገባው ከሆነ በልብ በሽታ የሚሰቃዩት አቶ በረከት ለህክምና ጅዳ ሳውዲ አረቢያ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል ህክምናቸውን ተከታትለው ወደ ሃገር ከተመለሱ ወዲህ የጤንነታቸው ሁኔታ እንብዛም ባለመስተካከሉ አመት ባልሞላ ግዜ ውስጥ ለሁለተኛ ዙር ወደ ሳውዲ አረቢያ « ብግሻን» ሪፈራል ሆስፒታል ማቅናታቸው የታወሳል::

አቶ በረከት ስሞኦን ከብስጭት ከተለያዩ የአልኮል መጠጦችና ከአይምሮ አደንዛዥ እጽ እንዲርቁ ተመክረው ጤንነታቸው አሰተማማኝ ደረጃ እስኪ ደርስ የዶክተሮች ቅርብ ክትትል እንደሚያሻው ተነግሯቸው በቀጠሮ ቢሸኙም የቀጠሮ ግዜያቸውን አክብረው ዶክተሮቻቸው ጋር መቀረብ አለመቻላቸውን የሚገልጹ የሆስፒታሉ ምንጮች ባለስልጣኑ በህይወት መኖራቸውን ይጠራጠራሉ። ጅዳ « ብግሻን» ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ የልብ ቧንቧ ማስፋት ህክምና የተደረገላቸው የኢ.ህ.አ.ዴ.ጉ ሹም የጤነነት ሁኔታ የሚጠበቀውን ያህል ለወጥ አስይቶ እንዳል ነበር ሙያዊ ትንታኔ የሚሰጡ ምስጢራዊ የሆስፒታሉ ምንጮች በሽታው የልብ እንደ መሆኑ መጠን ባልታሰበ ግዜ ባለስልጣኑን ለሞት ሊዳርጋቸው እንደሚችል ከአቶ በረከት ጋር ለመጣ አስታማሚ ገልጸው እንደ ነበር ያስታውሳሉ። በዚህም መስረት አቶ በረከት ስሞዖን ለሶስተኛ ግዜ ልባቸውን መታየት እንዳለባቸው ተነግሮቸው ቢሰናበቱም በቀጠሮ ቀን ተገኝተው ህክምናቸውን መከታተል ባለመቻላቸው በጤናቸው ላይ ሊያደርስ የሚችለው ተጽዕኖ ከፍተኛ መሆኑን የሚያሳየው የምርመራ ውጤት በረከት ሌላ ሃገር ለህክምና ሄዶ ካልሆነ በቀር አሁን ባሉበት ሁኔታ የልብ በሽታው አደጋ ሊጥላቸው እንደሚችል ተገልጿል:: ። በአቶ በረከት ስሞን ጤንነት ዙሪያ ከጅዳ «ብግሻን» ሆስፒታል ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ጥረት እናደርጋለን ።

በኦባማ ጉብኝት ኢሕአዴጎች ለሁለት ተከፍለዋል –“የምርጫው 100% ውጤት የዓለም መሳቂያ አድርጎናል”የሚሉ ካድሬዎች በዝተዋል

0
0

(ዘ-ሐበሻ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያ መምጣት ጠቅሞናል በሚሉና መሳቂያ አድርጎናል በሚሉ ሃሳቦች የኢሕ አዴግ አባላት ለሁለት መከፋፈላቸውን የዘ-ሐበሻ የውስጥ ምንጮች አስታወቁ::
obama
እንደምንጮቻችን ገለጻ በኢሕ አዴግ ውስጥ የተፈጠረው ክፍፍል የፕሬዚዳንቱን መምጣት ተከትሎ የዓለም ታላላቅ ሚዲያዎች የኢትዮጵያን ዲሞክራሲና ሰብአብዊ መብት አያያዝ በከፍተኛ ሁኔታ መተቸታቸውና ኢሕ አዴግ 100% አሸንፍኩ የሚለውን ምርጫ መሳቂያ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው:: በተጨማሪም ኢሕአዴጎች ባራክ ኦባማ እንደ አርበኞች ግንቦት 7 እና ኦነግን የመሳሰሉ መሳሪያ አንስተው ድርጅቱን ለመጣል የሚንቀሳቀሱትን ድርጅቶች አሸባሪዎች እንዲልላቸው ፈልገው የነበረ ቢሆንም ፕሬዚዳንቱ እነዚህን ድርጅቶች በአሸባሪነት አለመፈረጃቸው በኢህ አዴግ አባላት ዘንድ ከፍተኛ የፖለቲካ ክስረትን አስከትሏል::

የኦባማን ወደ ኢትዮጵያ መሄድ ተከትሎ በኢሕአዴግ የይስሙላ የ100% የአሸንፌያለሁ የምርጫ ውጤት የተሳለቁት ከሱዛን ራይስ ጨምሮ የዓለም ታላላቅ ሚዲያዎች ሲሆኑ እነዚህም ሚድያዎች የኦባማን ኢትዮጵያ መሄድ ተከትሎ በምርጫው ውጤት ከመሳለቃቸው በተጨማሪ በሃገሪቱ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብት አያያዝ መዘገባቸው አንዳንድ የኢሕ አዴግ አባላት “የኦባማ መምጣት በውጭ ሚድያዎች አጋለጠን; ለተቃዋሚዎች ጥቂት ወንበር ብንሰጥ ኖሮ ከዚህ ውርደት እንተርፍ ነበር” በሚል አቋም መከፈላቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል::

ሲኤን ኤን; ዘጋርዲያን; ዩኤስ ኤ ቱደይ; ያሁ ኒውስ; ሮይተርስ; ፎክስ; ኤ ኤፍ ፒ: ኤፒ; ኤቢሲ; ኤንቢሲ; ፖለቲኮ; ቢቢሲ; ኤንፒአር; ኤቢሲ; አልጀዚራን ጨምሮ በየዓለማቱ ያሉ ትላልቅ ሚድያዎች የሕወሓት/ኢሕ አዴግን የሰብ አዊ መብት አያያዝና መሳቂያውን ምርጫ የኦባማን ጉብኝት ተከትሎ እያነሱ በሰፊው ተችተውበታል:: በዚህም የኢሕ አዴግ አባላት ደስተኛ እንዳልሆኑ ተገልጿል::

የሰማዕቱ ቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ ድምጽ

0
0

ሐምሌ 22 ቀን 1928 / ሰማዕትነት የተቀበሉበት ቀን

በሰላሌ አውራጃ ፍቼ ከተማ የተወልዱት አቡነ ጴጥሮስ ገና በለጋ እድሜአቸው ወደ ደብረ ሊባኖስ በመሄድ መንፈሳዊ ትምህርታቸውም በመከታተል ያደጉ ቅዱስ አባት ናቸው። ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ትልቅ ሰው አንዱ የሆኑት አቡነ ጴጥሮስ ላገራችን በሰሩት ስራ ሁሌም ልናስባቸው እና ልናከብራቸው  የሚገባ አባት ናቸው።

Abune Petrosጣሊያን ኢትዮጵያን ሊወር በመጡ ሰዓት ከቤተ መንግስቱ  ቀጥሎ ትልቅ ቦታ የነበራት ቤተ ክህነት ነበረች። ጣሊያንም ይህንን በቅጡ ስለተረዱ ቤተ ክህነትን ካሳመንን  ኢትዮጵያን በቀላሉ መቆጣጠር እንችላለን የሚል ግምት አድሮባቸው መልእክተኛ ወደ አቡነ ጴጥሮስ ይልካሉ። የተላኩት የአገራችን ዜጎች ቢሆኑም ነገር ግን የአገርን ክብር አሳልፎ በመስጠት ለጣሊያን አገልጋይ የሆኑ ባንዳዎች ነበሩ። የጣሊያን ቅጥረኛ በመሆን ዜጋዎችን በማስገደል በማሳደድ ስራ የተሰማሩ የአገር መረጃን አሳልፎ ለጠላት በመስጠት ለሆዳቸው ያደሩ ሆድ አደሮች ናቸው። እነዚህ ባንዳዎች አቡነ ጴጥሮስ ጋር በመቅረብ  ኢትዮጵያ በጣልያን ስር እንድትሆን እንዲስማሙ ይወተውቷቸው ጀመር የመጡት ቅጥረኛ ባንዳዎች ከጣልያኖች የተሸለሙትን ኒሻን በደረታቸው ላይ አንጠልጥለው ነበረ። አቡነ ጴጥሮስም ሁሉንም ከቃኙ በኋላ የአገር ልጅ ሆነው የአገሩን ልጅ በማስገደል እና የአገርን ክብር አሳልፈው ለጠላት በመስጠት የተሰማሩትን….. ትሰማላችሁ አሏቸው ደረታችሁ ላይ ያንጠለጠላችሁት የክብር ኒሻን ሳይሆን የወገኖቻችሁ ደም ነው። የአገርን ክብር አሳልፎ በመስጠት ወንድሞቻችሁን እና እህቶቻችሁን በማስገደል የተሸለማችሁት ኒሻን ነው። ይህንን ኒሻን አውልቁና ጣሉት ካሉዋቸው በኋላ በሉ ሂዱና ለላኳችሁ ጣልያኖች ሃይማኖትን ለሚያጠፋ ህዝቤን በባርነት ለመግዛት ለሚሻ አገሬን አሳልፌ አልሰጥም በሏቸው አሏቸው። መልክተኞቹ የሆነውን ሁሉ ለጣልያኖቹ ነገሯቸው የዚህን ግዜ እንዴት ሃሳባችንን አይቀበልም ብለው ተናደዱ በአደባባይም ሊገድሏቸው ወሰኑ። አቡነ ጴጥሮስን በመግደል ህዝቡ ደንግጦ ይገዛልናል በማለት ሊገድሏቸው ወደ አደባባይ አወጧቸው። አነጣጣሪ ተኳሾች በአስር ሜትር ርቀት ባልሞላ መሳሪያቸውን በመያዝ ተንበርክከው ወደ አቡነ ጴጥሮስ እንዲደቅኑ የጣልያኑ አዛዥ ትእዛዝ አስተላለፈ ተኳሾችም እንደታዘዙት አደረጉ ይህንን አይተው ፈርተው ሃሳባቸውን ይቀይራሉ በማለት ተኳሾችን መሳሪያውን ከአቡነ ጴጥሮስ ላይ እንዲነሳ በማዘዝ አሁን የመጨረሻ እድል እንስጦ ምን ይላሉ አሏቸው።

አቡነ ጴጥሮስም እንዲህ በማለት ተናገሩ፡- አገር አፍራሽ፡ ሃይማኖት ለዋጭ፡ ለሆነው ጠላት አገሬን አሳልፌ አልሰጥም እውነትን በሃሰት ክብሬንም በነውር አለውጥም የሸዋ ህዝብ ሆይ ስማኝ፣ የጎጋም ህዝብ ሆይ ስማኝ፣ የጅማ ህዝብ ሆይ ስማኝ፣ የወለጋ ህዝብ ሆይ ስማኝ፣ የጎንደር ህዝብ ሆይ ስማኝ፣ የሃረር ህዝብ ሆይ ስማኝ የትግራይ ህዝብ ሆይ ስማኝ ሃገርህን ለባእድ አሳልፈህ እንዳትሰጥ  ሃይማኖትህንም ለውጠህ እንዳትገኝ ይህንን ያደራ ቃሌን ስሙኝ በምድር የሰጠኋችሁን አደራ ጠብቁ ብለው በእጃቸው የያዟትን ሰዓት አየት አደረጓት። የቡነ ጴጥሮስ ቃል በእውነት የተሞላ፣ የአገር ወዳድነት ስሜት የተላበሰ፣ ስለ ህዝብ ፍቅር እስከ ሰማዕትነት የደረሰ፣ ጥቅማ ጥቅም ያለወጣቸው፣ እውነትን ተናግረው፣ እውነትን ለብሰው፣ ስለ እውነት የኖሩ፣ እውነትን ይዘው ሰማዕትነትን የተቀበሉ፣ የኢትዮጵያ ብርቅዬ አባት ናቸው።

የጣልያኑ አዛዝም ተንበርክከው ለነበሩት ታጣቂዎች እንዲገደሏቸው ትዕዛዝ አስተላለፉ ተኳሾችም ስምንቱም በመተኮስ አቡነ ጴትሮስ በአደባባይ ስለ አገር ክብር ስለ ህዝብ ፍቅር ብለው ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ/ም የሰማዕትነትን ክብር ተቀበሉ። ከዛች ሰዓት ጀምሮ  በታላቅ ቁጣ ህዝቡ ተነሳ ጣልያንንም ከኢትዮጵያ ምድር ለማጥፋት ሁሉም ህዝብ ውስጥ የጽናት ሃይልን ከአብነ ጴጥሮስ ተቀብሎ ሄዱ ጽናት አስተማሪ እውነተኛ አባት የአባቶችን ድምጽ ሰሚ እውነተኛ ህዝብ በዘመኑ ነበሩና የድሉን ብስራት ጣሊያንን ከኢትዮጵያ በማባረር የአቡነ ጴጥሮስን ቃል ተግብረዋል።

ዛሬም እንደ አቡነ ጴጥሮስ አይነት አባት በእውነት መንገድ ላይ በመቆም ስለ አገሩ፣ ስለ ህዝቡ፣ ስለ ሃይማኖቱ በክብር የቆመ የሃይማኖት አባት ያስፈልጉናል ያባቶችን ቃል ፈጻሚ ባገሩ የማይደራደር፣ በሃይማኖቱ የማይደራደር ለጠላት የማይገዛ እውነተኛ ትውልድ ያስፈልጋል። ህዝቡን ወዳጅ አገሩን የሚወድ ለእውነት የቆመ ትውልድ ያስፈልገናል።

እንግዲህ ሁላችን ወደ ልቦናችን እንመለስ ያኔ ከእውነት ጋር እንገናኛለን፣ ያኔ ስለ አገር እናስባለን ያኔ፣ ያኔ ስለ ሃይማኖት እንኖራለን፣ ያኔም አሸናፊዎች እንሆናለን።

ስለ አገር ክብር  ስለ ህዝብ ፍቅር በእውነት በመቆም የተሰውቱን ሰማዕት አቡነ ጴጥሮስን ሁላችን በክብር እናስባቸው።

ከተማ ዋቅጅራ

28.07.2015

Email waqjirak@yahoo.com

 

ኦባማ የአፍሪካን ገዢዎች እያዋዛ ደቆሳቸው! –ፕ/ሮ መስፍን ወልደ ማርያም

0
0

Obama “Moonwalking” Human Rights in Africa? – by Prof. Alemayehu G Mariam
ሐምሌ/2007

ኦባማ በአፍሪካ ኅብረት ያደረገው ንግግር ብዙ ጥያቄዎችን መልሷል፤ የኦባማ ጉብኝት ያስከተለው ጫጫታ ሁሉ መልስ አገኘ፤ የሰው ልጆች በመሀከላቸው ምንም ዓይነት የአድልዎ ልዩነት ሳይደረግባቸው በሰውነታቸው ብቻ በተፈጥሮ ያገኙትን ክብራቸውንና መገሣቸውን አስከብረው መኖር እንዳለባቸው በአጽንኦት ተናገረ፤ ዛሬ የአሜሪካኑ ፕሬዚደንት ያደረገው ንግግር ከፕሬዚደንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ጀምሮ እስከፖሊሶች፣ መርማሪዎችና አዛዦቻቸው፣ እስከጦር ኃይሉና አዛዦቻቸው፣ አስከዓቃብያነ ሕግና ዳኞች፣ እስከወህኒ ቤት ጠባቂዎችና አዛዦች በየሥልጣን ተዋረዱ ላይ ሆነው የኢትዮጵያውያንን የሰውነትና የዜግነት እኩልነት አፈራርሰው በጎሣ መሠረት ላይ ሊበታትኑት የሚሞክሩትን በኃይለኛ ቃላት ከመሬት በታች ከቶአቸዋል፤ ማሰብና ማስተዋል የጎደለው፣ ከአፍንጫ የራቀ አመለካከት የሌለበት፣ አገርን የሚያጠፋ፣ ከሰውነት ጎዳና የሚያወጣ የድንቁርና መንገድ መሆኑን ገልጧል፡፡

ኦባማ የኢትዮጵያን ገዢዎች ብቻ ሳይሆን የአፍሪካን ገዢዎች በሙሉ አላግጦባቸዋል፤ በሥልጣን ላይ ሙጭጭ በማለታቸው፣ በሙስናቸው፣ በአፈናቸው፣ ልክ ልካቸውን ሲነግራቸው እፍረታቸውን ውጠው ያጨበጭቡለት ነበር፤ የአፍሪካ ገዢዎች ሕጉን እንደፈለጉ የሚጠመዝዙትን መሳቂያ አድርጓቸዋል፤ በአዳራሹ ውስጥ የነበሩ ወጣቶች የኦባማን ንግግር በማድነቅ በጭብጨባና በጩኸት ይገልጹ ነበር፤ ለወግ ብቻ የሚደረግ ምርጫ የዴሞክራሲ መግለጫ አይሆንም አለ፤ ዴሞክራሲ ነጻና ትክክለኛ ምርጫን፣ ሀሳብን በነጻነት መግለጽን፣ በነጻነት መደራጀትንና መሰብሰብን ያካትታል፤ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድረጅቶችን ማገድና መገደብ ለዴሞክራሲ እንቅፋትና ለእድገት ጸር ነው፡፡

አገዛዞች ነጻነትን በማፈናቸው ሁለት ዋና ዋና የማኅበረሰብ ዓምዶችን ማለትም ደኅንነትንና ሰላምን ያጣሉ፤ ሰላምና ደኅንነት ሰጠፋ ማኅበረሰቡ የጉልበተኞች መጫወቻ ሆኖ ይደናበራል፤ ይህ አደገኛ ጉዞ ነው፤ መልካም አስተዳደር ከሰፈነ ሽብርተኛነት የሚበቅልበት መሬት አያገኝም፤ ሰዎች ሁሉ በሰውነታቸውና በዜግነታቸው እኩልነት ሰብአዊ መብቶቻቸው ሁሉ ከተከበሩላቸው ወደኃይል እርምጃ የሚወስደውን መንገድ የሚከተሉበት ምክንያት የለም፤ እድገት የነጻነትና የዴሞክራሲ ውጤት ነው፤ ነጻነት የሰው ልጆች ሁሉ ዓላማ ነው፡፡

ማንም ቢሆን ከሕግ በታችና ለሕግ ተገዢ መሆን አለበት፤ ሕገ መንግሥቱን ለእሱ እንደሚበጀው እያደረገ በመተርጎም በሥልጣን ላይ መቆየት አይቻልም፤ ሊፈቀድም አይገባም፤ በአጠቃላይ አባማ በአፍሪካ ኅብረት በአደረገው ንግግር የአፍሪካ ገዢዎችን ሁሉ ቁስላቸውን በአልኮል ሲያጥብላቸው እየለበለባቸው ተመልክተውታል፤ አዳምጠውታል፤ አንዳንዶቹም እያፈሩ አጨብጭበውለታል፡፡

የዚህ ንግግር የመጨረሻው ግብ ያልገባቸው የአፍሪካ ገዢዎች ክፉ ነገር ይጠብቃቸዋል፤ በሽብርተኛነት መነገድ መልኩን ሊለውጥ ነው፤ ካላወቁበት የማያውቁት ሽብር ቤታቸውን ይጠርግላቸዋል!

 

ኦባማ የአፍሪካን ገዢዎች እያዋዛ ደቆሳቸው! –መስፍን ወልደ ማርያም

0
0

ሐምሌ/2007

Prof. Mesfin Woldemariam

Prof. Mesfin Woldemariam

ኦባማ በአፍሪካ ኅብረት ያደረገው ንግግር ብዙ ጥያቄዎችን መልሷል፤ የኦባማ ጉብኝት ያስከተለው ጫጫታ ሁሉ መልስ አገኘ፤ የሰው ልጆች በመሀከላቸው ምንም ዓይነት የአድልዎ ልዩነት ሳይደረግባቸው በሰውነታቸው ብቻ በተፈጥሮ ያገኙትን ክብራቸውንና መገሣቸውን አስከብረው መኖር እንዳለባቸው በአጽንኦት ተናገረ፤ ዛሬ የአሜሪካኑ ፕሬዚደንት ያደረገው ንግግር ከፕሬዚደንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ጀምሮ እስከፖሊሶች፣ መርማሪዎችና አዛዦቻቸው፣ እስከጦር ኃይሉና አዛዦቻቸው፣ አስከዓቃብያነ ሕግና ዳኞች፣ እስከወህኒ ቤት ጠባቂዎችና አዛዦች በየሥልጣን ተዋረዱ ላይ ሆነው የኢትዮጵያውያንን የሰውነትና የዜግነት እኩልነት አፈራርሰው በጎሣ መሠረት ላይ ሊበታትኑት የሚሞክሩትን በኃይለኛ ቃላት ከመሬት በታች ከቶአቸዋል፤ ማሰብና ማስተዋል የጎደለው፣ ከአፍንጫ የራቀ አመለካከት የሌለበት፣ አገርን የሚያጠፋ፣ ከሰውነት ጎዳና የሚያወጣ የድንቁርና መንገድ መሆኑን ገልጧል፡፡

ኦባማ የኢትዮጵያን ገዢዎች ብቻ ሳይሆን የአፍሪካን ገዢዎች በሙሉ አላግጦባቸዋል፤ በሥልጣን ላይ ሙጭጭ በማለታቸው፣ በሙስናቸው፣ በአፈናቸው፣ ልክ ልካቸውን ሲነግራቸው እፍረታቸውን ውጠው ያጨበጭቡለት ነበር፤ የአፍሪካ ገዢዎች ሕጉን እንደፈለጉ የሚጠመዝዙትን መሳቂያ አድርጓቸዋል፤ በአዳራሹ ውስጥ የነበሩ ወጣቶች የኦባማን ንግግር በማድነቅ በጭብጨባና በጩኸት ይገልጹ ነበር፤ ለወግ ብቻ የሚደረግ ምርጫ የዴሞክራሲ መግለጫ አይሆንም አለ፤ ዴሞክራሲ ነጻና ትክክለኛ ምርጫን፣ ሀሳብን በነጻነት መግለጽን፣ በነጻነት መደራጀትንና መሰብሰብን ያካትታል፤ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድረጅቶችን ማገድና መገደብ ለዴሞክራሲ እንቅፋትና ለእድገት ጸር ነው፡፡

አገዛዞች ነጻነትን በማፈናቸው ሁለት ዋና ዋና የማኅበረሰብ ዓምዶችን ማለትም ደኅንነትንና ሰላምን ያጣሉ፤ ሰላምና ደኅንነት ሰጠፋ ማኅበረሰቡ የጉልበተኞች መጫወቻ ሆኖ ይደናበራል፤ ይህ አደገኛ ጉዞ ነው፤ መልካም አስተዳደር ከሰፈነ ሽብርተኛነት የሚበቅልበት መሬት አያገኝም፤ ሰዎች ሁሉ በሰውነታቸውና በዜግነታቸው እኩልነት ሰብአዊ መብቶቻቸው ሁሉ ከተከበሩላቸው ወደኃይል እርምጃ የሚወስደውን መንገድ የሚከተሉበት ምክንያት የለም፤ እድገት የነጻነትና የዴሞክራሲ ውጤት ነው፤ ነጻነት የሰው ልጆች ሁሉ ዓላማ ነው፡፡

ማንም ቢሆን ከሕግ በታችና ለሕግ ተገዢ መሆን አለበት፤ ሕገ መንግሥቱን ለእሱ እንደሚበጀው እያደረገ በመተርጎም በሥልጣን ላይ መቆየት አይቻልም፤ ሊፈቀድም አይገባም፤ በአጠቃላይ አባማ በአፍሪካ ኅብረት በአደረገው ንግግር የአፍሪካ ገዢዎችን ሁሉ ቁስላቸውን በአልኮል ሲያጥብላቸው እየለበለባቸው ተመልክተውታል፤ አዳምጠውታል፤ አንዳንዶቹም እያፈሩ አጨብጭበውለታል፡፡
የዚህ ንግግር የመጨረሻው ግብ ያልገባቸው የአፍሪካ ገዢዎች ክፉ ነገር ይጠብቃቸዋል፤ በሽብርተኛነት መነገድ መልኩን ሊለውጥ ነው፤ ካላወቁበት የማያውቁት ሽብር ቤታቸውን ይጠርግላቸዋል!


የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የሰበር ወሳኔ ለመስጠት በድጋሚ ለሐምሌ 30/2007ዓም ተቀጠረ

0
0

Temesgen Desalegn behindbar
ከታሪኩ ደሳለኝ

የጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሰሚ ችሎት ለዛሬ የተመስገን ፍርድ ላይ የህግ ሰህተት አለበት የለበትም የሚለው ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል። ሆኖም ዛሬ አዲስ የተቀየሩት ደኞች የሰበር ውሳኔውን ለመወሰን የስር ፍርድ ቤቱ ለህገ መንግስት አጣሪ ኮሚሽን መቅረብ የለበትም ብሎ ብይን የሰጠበትን ሰነድ አቅርቡና ወሳኔውን ለሐምሌ 30/2007 ዓም ከሰዓት በ8:00 ሰዓት እንሰጣለን በማለት ፍርድቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥተል።

ቴዎድሮስ አድሃኖም “አንዳርጋቸው ጽጌን በመኪና እያዞርን ልማቱን እያስጎበኘነው ነው”አሉ

0
0

“ለአንዳርጋቸው ፅጌ ላፕቶፕ ገብቶለት መፅሀፍ ፅፎ ኦልሞስት ጨርሷል”
“በመኪና እየዞረ የሀገሪቱን ልማት ያያል። አዳማ ላይ ልማቱን አይቶ ተደንቋል።”

andargachew new picture
የአሜሪካ ድምጽ ራድትዮ እንደዘገበው በኢትዮጵያ እስር ቤት የሚገኙት የግንቦት ሰባት ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ በተሻለ ሁኔታ መያዛቸዉን የአገሪቱ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገለጹ።

ሚኒስትሩ ትላንት ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዩ የአማርኛዉ ቋንቋ ስርጭት ስለ ፕሬዚደንት ኦባማ ኢትዮጵያ ጉብኚት በሰጡት ቃለ ምልልስ ስለ አቶ አንዳርጋቸዉ አያያዝ ተጠይቀዉ ፣ ታሳሪዉ በመኪና ሆነዉ አገሪቱ በልማት እያደረገች ያለችዉን ግስጋሴ እንዲጎበኙ ሁሉ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

አቶ አንዳርጋቸዉ ፍርድ ፊት ለመቅረብ ፣ የህግ ጥብቅና ለማግነትና በቤተሰብ ለመጎብኘትስ ችለዋል ወይ ሲል ላቀረበላቸው ጥያቄ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ የሚከተለዉን መልሰዋል።

የእንጊግሊዝ ዜግነት ያላቸዉ የግንቦት ሰባት ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ ከአንድ ዓመት በፊት ሰኔ 2006 ዓም የመን ዉስጥ በኢትዮጽያ ጸጥታ ሃይሎች ተይዘዉ መወሰዳቸዉ ይታወሳል። ከዚያን ጊዜ ወዲህ ሁለት ጊዜ ብቻ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኤምባሳ ባለስልጣናት እንደተጎበኙ ተገልጿል። የብሪታኒያ መንግስት በቅርቡ ባወጣዉ መግለጫ የዜጋዉ የአንዳርጋቸዉ ጽጌ ጉዳይ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ባለዉ ግንኙነት አሉታዊ እንደምታ እንዳያስከትል መናገሩ አይዘነጋም።

የአሜሪካ ድምጽ ራድዮ ዘገባን ያድምጡ:-

የዞን 9 ጦማርያን በድጋሚ ለብይን ተቀጥረዋል

0
0

የዞን9 ማስታወሻ

በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ በፌደራል አቃቤ ህግ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው ከአንድ አመት በላይ እየተጓተተ ከሚገኙት አራቱ የዞን 9 ጦማርያን ለነሀሴ 13/2007 ዓ.ም ለብይን ተቀጥረዋል፡፡
zone 9 bloggers
ዛሬ ሐምሌ 22 ቀን 2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ “ፍርድ ቤት” ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት ጦማርያኑ በተከታታይ ቀጠሮ በተሰጠበትና እልባት ባላገኘው ‹ተከሳሾች መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ ይሰናበቱ ወይስ ይከላከሉ› በሚለው ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ሌላ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

መዝገቡ ለዛሬ ተቀጥሮ የነበረው የአቃቤ ህግ የደረጃ ምስክሮች ቃል ከመቅረጸ ድምጽ ተገልብጦ በጽሁፍ ከመዝገቡ ጋር መያያዙን ለመጠባበቅ ነበር፡፡ በዚህም ፍርድ ቤቱ የምስክሮቹ ቃል በጽሁፍ ተገልብጦ ከመዝገቡ ጋር መያያዙን በመግለጽ መዝገቡን መርምሮ ተከሳሾች መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ ይሰናበቱ ወይስ መከላከል ያስፈልጋቸዋል የሚለውን ለመበየን ለነሀሴ 13/2007 ቀጠሮ ይዟል፡፡

የተሰጠው የቀጠሮ ጊዜ ረዘመ በሚል ቀጠሮው አጭር እንዲሆን የተከሳሾች ጠበቃ ቢጠይቁም ፍርድ ቤቱ ‹‹ከተያያዘው የመዝገብ ብዛት አንጻር ከነሀሴ 13/2007 በፊት አይደርስልንም›› በማለት የተሰጠው ጊዜ ምክንያታዊ እንደሆነ ለማስረዳት ሞክሯል፡፡ ጠበቃው በበኩላቸው ‹‹መዝገቡ ብዙ ቢመስልም የተጠቀሰውን ያህል ጊዜ ሊወስድ አይችልም ብለን ስለምናምን አጭር ቀጠሮ ይሰጠን፤ በሌላ በኩል ክሱ ከተቋረጠላቸው ሰዎች ጋር በተያያዘ መዝገቡ እንደቀነሰ እናምናለን›› በማለት መዝገቡ ከተባለው ጊዜ በፊት ተመርምሮ ብይን ሊሰጥ ይገባል በሚል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ሆኖም ግን ፍርድ ቤቱ ከነሀሴ 15/2007 ዓ.ም በኋላ እንደማይሰየም በመግለጽ፣ ከዚያ በፊት ነሀሴ 13/2007 ዓ.ም ብይኑን ለማድረስ፣ ካልተቻለ ደግሞ እስከ 15/2007 ባሉት ሁለት ቀናት ለመጨረስ እንደሚሞክር በመግለጽ ቀጠሮውን በነሀሴ 13/2007 ዓ.ም አጽንቷል፡፡
በዛሬው ውሎ ከቂሊንጦ እስር ቤት በፍቃዱ ኃይሉ፣ አጥናፍ ብርሃኔ፣ አቤል ዋበላና ናትናኤል ፈለቀ የቀረቡ ሲሆን አሁን በክስ ላይ ከሚገኙት ውስጥ አንደኛ ተከሳሽ የሆነችው ሶልያና ሽመልስ በሌለችበት ጉዳያቸው ለአጭር ጊዜ ታይቷል፡፡

የዞን9 ማስታወሻ

የዞን9 ጦማርያንን የፍርድ ቤት ሂደት በማጓተት ያልተሰራ ወንጀልን መፍጠር አይቻልም፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ጉዳየዮን ማንጓተቱን ያቆም ዘንድ የመንግስት ስራ አስፈጻሚ አካላት በጉዳዬ ላይ ውሳኔያቸውን በአፋጣኝ እንዲሰጡልን ለመጠየቅ እንወዳለን፡፡

የባህርዳሩ ከንቲባ የሕዝብን ገንዘብ ሰርቋል ተብሎ ቢታሰርም ባለስልጣናቱ ተሯሩጠው ማስፈታታቸውን ሕዝቡ እየተቃወመ ነው

0
0

ትህዴን እንደዘገበው የህዝብና የሀገርን ሃብት ለግል ጥቅሙ አውሎታል ተብሎ ለግዜው ቢያዝም በአጭር ግዜ በመፈታቱ ምክንያት ህዝቡ እየተቃወመው እንደሚገኝ ተገለጸ።በአማራ ክልል፤ የባህርዳር ከተማ ከንቲባ የተባለው የስርዓቱ ካድሬ ለመሰረተ ልማት እንዲውል ተብሎ ከተመደበው በጀት 165 ሺ ብር ለአንዳንድ ስራ ማከናወኛ ብሎ ወጪ በማድረግ ለግል ጥቅሙ ስላዋለው ሓምሌ 5/ 2007 ዓ/ም ለተወሰነ ሰዓታት ተይዞ ሲያበቃ ያለ ምንም ማጣራት የክልሉ ባለስልጣናት ተሯሩጠው እንዲፈታ ማድረጋቸውን ተገለፀ።
kentiba
መረጃው በማከል- የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች ገንዘቡን ያጠፋፋው ባለስልጣን ህጉ በሚያዘው መሰረት በሚመለከተው ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶበትና ጉዳዩን ተጣርቶ ገንዘቡን ማስረከብ ሲገባው በባለስልጣኖች ትእዛዝ በመፈታቱ ተቃውማቸው እያሰሙ መሆናቸውና በተለይ የባለስልጣኑን ብልሹ ተግባር የሚያውቁት ሸነሺ ይመርና ቴዲ ግርማ የተባሉ ሰዎች ወንጀለኛው የፈቱት ባለስጣናት ድረስ በመሄድ የተቃውሞ ሃሳባቸው ማቅረባቸውን የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል።

ያልተጻፈ በኢትዮጵያ 19 ዓመት ያስፈርዳል (ዳዊት ሰለሞን)

0
0
11800154_10204789730123973_238976150452403969_n

ወይዘሮ ሂሩት ክፍሌ

በኢትዮጵያ የሚገኘው የፍትህ ስርዓት ራሱን እንደ ካሮት ቁልቁል ማሳደግ ከጀመረ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡በተለይ ከቅርብ አመታት ወዲህ የፍትህ ስርዓቱ ዋነኛ መገለጫ በሆኑ ፍርድ ቤቶች ዳኞች ውሳኔ የሚሰጡባቸው ጉዳዩች ‹‹ፍትህ››መሳቂያ መሳለቂያ መሆኗን በገሃድ እያሳዩን ይገኛሉ፡፡
በእነ ኤልያስ ክፍሌ የክስ መዝገብ ስሟ ሰፍሮ በ2004 በቁጥጥር ስር የዋለችው ወይዘሮ ሂሩት ክፍሌ የፍትህ ስርዓቱ ወደለየለት ውርደት ውስጥ ለመዘፈቁ የቀረበባት ክስ አይነተኛ ማሳያ ተደርጎ ሊጠቀስ ቢችልም በዚህ ዝቃጭ ክስ ከልጇ ተነጥላ 19 ዓመት የተፈረደባት መሆኑ ግን ያሳቅቃል፡፡
ከሀዋሳ የተያዘችው ሂሩት አሜሪካን አገር ከሚገኘው ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ ትዕዛዝ በመቀበል ‹‹በቃ››የሚል ጽሁፍ በማጻፍ በከተማው ውስጥ ለማሰራጨት ስትዘጋጅ ተይዛለች››የሚል ክስ ቀርቦባት ፍርድ ቤቱ ይህ ሽብር ነው በማለቱ 19 ዓመት በይኖባታል፡፡


አስገራሚው ነገር ሂሩት ላይ በምስክርነት የቀረቡ ሰዎች ‹‹በቃ››የሚል ጽሁፍ በኮምፒውተር እንዲጻፍላት ከጠየቀች በኋላ ትታዋለች››በማለት መናገራቸው ነው፡፡አስባ ትታዋለች በተባለ ሁለት ፊደል የተነሳ አቃቤ ህግ የኤልያስ ክፍሌ ተባባሪ ናቸው ካላቸው ጋዜጠኛ ርዕዩት ዓለሙ፣ውብሸት ታዬና ዘሪሁን ገ/እግዚአብሄር ጋር በአንድ የክስ መዝገብ ስሟን አስፍሯል፡፡


ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ለንባብ ባበቃው ‹‹የነጻነት ድምጾች››መጽሐፉ እርሱና ዘሪሁን ሂሩትን ለመጀመሪያ ግዜ የተዋወቋት በማዕከላዊ ግቢ ውስጥ አሻራ እንዲሰጡ በተጠሩበት ወቅት መሆኑን በማስታወስ በወቅቱም ሂሩት በመገረም ‹‹ታውቁኛላችሁ፣ኤልያስ ክፍሌ የሚባለውስ ሰው ምን አይነት ነው››በማለት እንደጠየቀቻቸው አስፍሯል፡፡


ሂሩት ክፍሌ በአስቂኙ ፍርድ ቤት የተጣለባትን የፍርድ ውሳኔ በአሁኑ ወቅት በቃሊቲ ወህኒ ቤት በማሳለፍ ላይ የምትገኝ ሲሆን ሁለቱ ስዊዲናዊያን ጋዜጠኞች የይቅርታ ጥያቄ ባቀረቡበት ወቅትም ሂሩት ምንም እንኳን ወንጀል የተፈጸመባት እርሷ ብትሆንም ፎርሙን በመሙላት አሳሪዎቿ ስህተታቸውን የሚያርሙበት ዕድል እንዲያገኙ ብታደርግም ጥያቄዋን ውድቅ በማድረግ በፍትህ ላይ በድጋሚ ተሳልቀዋል፡፡

 

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live