Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ብዙአየሁ ደምሴ በፍራንክፈርት ኢትዮጵያውያኑን ሲያዝናና አመሸ (Video)

$
0
0


የኢትዮ-አውሮፓ የ እግር ኳስ እና የባህል ፌስቲቫል ዘንድሮ በፍራንክፈርት ከተማ በደመቀ ስነስርዓት ተደርጓል:: በዚህ በዓል ላይ ከታዩት ደማቅ ፕሮግራሞች መካከል ደግሞ የድምፃዊ ብዙአየሁ ደምሴ የሙዚቃ ኮንሰርት ነው:: ደማቅ ሆኖ ባለፈው በዚህ ኮንሰርት ላይ የነበረውን የብዙአየሁ እንቅስቃሴ ለማየት እዚህ ይጫኑ::

ብዙአየሁ ደምሴ በፍራንክፈርት ኢትዮጵያውያኑን ሲያዝናና አመሸ (Video)


ውጊያው በጎንደር አካባቢ ልዩ ወረዳዎች ቀጥሏል * አርበኞች ግንቦት 7 የሱር ኮንስትራክሽንን ንብረት አወደምኩ አለ

$
0
0
(Photo File)

(Photo File)

የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት ጋዜጣዊ መግለጫ:-

የአርበኞች ግንቦት 7 ጀግና የነፃነት ፋኖዎች በኢትዮጵያ መሬት ላይ በህዝቡ ጉያ ውስጥ ሆነው በወልቃይት የጀመሩትን ወታደራዊ ጥቃት አሁንም አጠናክረው በመቀጠል የህወሓትን አገዛዝ እያሽመደመዱት ነው፡፡

ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ የተባለውን በቁሙ ደርቆ የበሰበሰ ዛፍ ከስሩ ገዝግዞ ለመቁረጥ የተጀመረው ትግል ሰሞኑን በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ልዩ ልዩ አካባቢዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ከወታደራዊ ጥቅምና ደህንነት አንፃር ስማቸውን ለመግለፅ
በማይቻልባቸው የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ልዩ ልዩ አካባቢዎች ላይ በሚንቀሳቀሰው የህወሓት ፀረ-ሽምቅና ሚሊሻ ኃይል ላይ ደፈጣ በመጣል ደምስሰውታል፡፡

በአዘዞ እና ጠዳ ከተሞች መካከል ከሚገኘው መገጭ ወንዝ አጠገብ በግንባታ ስራ ላይ የነበረው የሱር ኮንስትራክሽን የድንጋይ መፍጫ ማሽነሪዎች እና ሌሎችን የግንባታ ቁሳቁሶች በአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች ሙሉ በሙሉ በመውደሙ ስራውን አቁሞ እንዲሸሽ ተገዷል፡፡

ሱር ኮንስትራክሽን የህወሓቶች የግል ንብረት የሆነው ኤፈርት በስሩ ካሉት ከ60 በላይ የንግድ ኩባንያዎች አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ሱር ኮንስትራክሽን ውድመት በደረሰበት አካባቢ የግንባታ ስራውን በብቸኝነት የያዘው እንደተለመደው ያልምንም ጨረታ ነው፡፡

በተያያዘ ዜና ከዚያው ጎንደር ዙሪያ ወረዳ ውስጥ የሚኖር አቶ ጎሸ ሽባባው የተባለ ገበሬ ለአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች ስንቅ አቀብለሃል በሚል በህወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ውሎ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሞበታል፡፡ አቶ ጎሸ ሽባባው አሁን በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ማክሰኝት እስር ቤት ውስጥ ይገኛል፡፡
በላይ አርማጭሆ አንገረባ ቀበሌ የአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች እና የህወሓት ጸረ-ሽምቅ ኃይል ለአንድ ሰዓት የዘለቀ ጦርነት አድርገዋል፡፡ ጦርነቱም የተካሄደው ሀምሌ 11 2007 ዓ.ም ሲሆን በአካባቢው ለአሰሳ ሲንቀሳቀስ የነበረውን የህወሓት ፀረ-ሽምቅ ኃይል በውስጥ አርበኞች የተከፈተበትን ድንገተኛ የደፈጣ ጥቃት መቋቋም ስላልቻለ አንድ ሰዓት ከፈጀ የተኩስ ልውውጥ በኋላ ለጊዜው ቁጥራቸው በትክክል ያልታወቁ በርካታ አባላቱ ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል፡፡

የሱዳን መከላከያ ኃይል የኢትዮጵያን ወሰን ጥሶ ገብቶ ከሆር ሁመር ገበሬዎች ጋር መታኮሱ ታውቋል፡፡

በተደረገው የተኩስ ልውውጥ 2 ገበሬዎች ለሞት ተዳርገዋል፡፡ በአካባቢው ሰፍሮ የሚገኘው ህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊት የሱዳን መከላከያ ኃይል ድንበር ሰብሮ ገብቶ በገሬው ህዝብ ላይ የጦር ጥቃት ሲያደርስ እየተመለከተ እንዳላየ በዝምታ አልፎታል፡፡

የነአብርሃ ደስታ ክስ መከላከያ ውድቅ ተደረገ • ለነሀሴ 14/2007 ዓ.ም ለብይን ተቀጥረዋል

$
0
0

Abrha-Desta-Yeshiwas-Assefa-Daneil-Shibeshi-Habtamu-Ayalew
የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች መቃወሚያ ውድቅ ተደረገ
• ለነሀሴ 14/2007 ዓ.ም ለብይን ተቀጥረዋል

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

በእነ ዘላለም ወርቃገኘው የክስ መዝገብ ከ1-6ኛ እንዲሁም የ9ኛ ተከሳሾች ጠበቃ የሆኑት ተማም አባቡልጉ በደንበኞቻቸው ላይ በቀረበባቸው የክስ ማስረጃ ላይ ያቀረቡት ባለ 10 ገፅ መቃወሚያ በፍርድ ቤቱ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ ተደርጓል፡፡ ጠበቃው ተከሳሾቹ ሀምሌ 1/2006 ዓ.ም ተይዘው ከሶስት ወር በኋላ ጥቅምት 7/2006 ዓ.ም ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት ተገኘ የተባለ መረጃ ከአቃቤ ህግ ማስረጃዎች ማስረጃ ዝርዝርነት እንዲወጣ፣ ተከሳሾቹ ለፖሊስ መረጃ የሰጡበት መንገድና ፖሊስ የሰነድ ማስረጃዎችን የያዘበትን መንገድም አቃቤ ህግ ህጋዊ መሆኑን ስላላረጋገጠ በደንበኞቼ ላይ በማስረጃነት እንዳይያዝ ሲሉ መቀወወሚያ አቅርበው ነበር፡፡

ከተከሳሾቹ መካከል በዛሬው ችሎት አንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ ‹‹መቃወሚያው የቀረበው ከተከሳሾች እጅ ተገኙ የተባሉት ማስረጃዎች በህጋዊ መንገድ የተገኙ ስለመሆናቸው አቃቤ ህግ በማስረጃ ስላላረጋገጠ ነው›› ሲል ፍርድ ቤቱ መቃወሚያውን እንዲቀበለው ጠይቋል፡፡ ሆኖም ዛሬ ሀምሌ 14/2007 ዓ.ም በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት መቃወሚያውን ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጎታል፡፡ በሌላ በኩል ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ በነፃ ይሰናበቱ ወይንም ይከራከሩ የሚለውን ለመወሰን ለብይን ለነሀሴ 14/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ ከ1-6ኛ እንዲሁም 9ኛ ተከሳሾች ጠበቃ የሆኑት ተማም አባቡልጉ ከጥብቅና በመታገዳቸው ምክንያት ሰባቱም ተከሳሾች በዛሬው ችሎት ያለ ጠበቃ ቀርበዋል፡፡ በዚህ መዝገብ ተከሰው አቶ ተማም መቃወሚያ ካቀረቡላቸው መካከል አቶ የሸዋስ አሰፋ፣ አቶ አብርሃ ደስታ፣ አቶ ሀብታሙ አያሌውና አቶ ዳንኤል ሺበሽ ይገኙበታል፡፡

Sport: ‹‹አርሰናል ከህይወቴ ጋር ተቆራኝቷል›› –ካዞርላ

$
0
0

Arsenal's Santi Cazorla reacts after scoring against Aston Villa, during their English Premier League soccer match, at the Emirates Stadium, in London, Saturday, Feb. 23, 2013. (AP Photo/Bogdan Maran)

Arsenal’s Santi Cazorla reacts after scoring against Aston Villa, during their English Premier League soccer match, at the Emirates Stadium, in London, Saturday, Feb. 23, 2013. (AP Photo/Bogdan Maran)


አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር ብቃታቸውን ያስመሰከሩ እና በቴክኒክ ተሰጧቸው ጎልተው የወጡ የላ ሊጋ ተጨዋቾችን ለማስፈረም ያላቸው ብልሃት አስገራሚ ነው፡፡ ግለሰቡ በተደጋጋሚ ይህንን ፈፅመዋል፡፡ ማንም ሳያውቃቸው እርሳቸው እነኚህን ተጨዋቾችን ለማስፈረም አይቸገሩም፡፡

ቬንገር ባለፉት ሶስት የዝውውር ጊዜያቶች በዚህ አይነት መልኩ ተጨዋቾችን አስፈርመዋል፡፡ በ2013 አርሰናል የአማካይ ክፍሉን ማጠናከር ነበረበት፡፡ ቬንገር በተረጋጋ ስሜት ውስጥ ሆነው በመጨረሻም በሪያል ማድሪድ የተገፋውን ሜሱት ኦዚልን አስፈርመዋል፡፡ በወቅቱ የሊቨርፑሉን አጥቂ ሉዊስ ሱዋሬዝን ለማስፈረም ፍላጎት የነበራቸው ቢሆንም ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡ ኡራጓዊውን አጥቂ ማግኘት የተሳናቸው ፈረንሳዊው አሰልጣኝ በመጨረሻም ሳይጠበቁ 42.5 ሚሊዮን ፓውንድ ከፍለው ጀርመናዊውን አማካይ የግላቸው አድርገውታል፣ ይህ ክፍያ ለአርሰናል በተጨዋቾች የዝውውር ሪከርድ ታሪክ ቀዳሚውን ቦታ ይወስዳል፡፡

ቬንገር በሌሎች ክለቦች የዝውውር ረድፍ ውስጥ ያልገቡ ተጨዋቾችን ማስፈረማቸውን ቀጥለዋል፡፡ ከብራዚሉ የዓለም ዋንጫ መልስ ባርሴሎና ሱዋሬዝን ሊያስፈርም በአጥቂ መስመሩ ከሚገኙ ተጨዋቾች መሀከል አንዱን መልቀቅ ነበረበት፡፡ ሊዮኔል ሜሲ የባርሴሎና ምልክት በመሆኑ ይህንን ማሰብ አይቻልም፡፡ ኔይማር ወደ ባርሴሎና ካመራ የተቆጠሩት የወራት ጊዜ ብቻ መሆናቸው እንዲሁም የወጣበት ከፍተኛ ክፍያ ይህንን እንድናስብ የሚያስችል አይመስልም፡፡ ስለዚህ የባርሴሎና አመራሮች የነበራቸው አማራጭ አሌክሲስ ሳንቼዝን ማሰናበት ነበር፡፡

ሳንቼዝን ለማስፈረም ሊቨርፑል ከፍ ያለ ፍላጎት ነበረው፡፡ አሰልጣኝ ብሬንዳን ሮጀርስ ከሱዋሬዝ ዝውውር ያገኙትን 75 ሚሊዮን ፓውንድ ተጠቅመው ቺሊያዊውን ለማስፈረም ከፍ ያለ ፍላጎት ቢያሳዩትም ቬንገር የተጨዋቾቹን ፍላጎት ተጠቅመው በመጨረሻም ግን ኢምሬትስ አምጥተውታል፡፡ በወቅቱ ለዝውውሩ የወጣበት ክፍያ ከኦዚል ያነሰ ቢሆንም በክለቡ ታሪክ ከውድ ተጨዋቾች ተርታ የሚቀመጥ ነው፡፡ 35 ሚሊን ፓውንድ የወጣበት አጭሩ አጥቂ ከአርሰናል የአንድ ዓመት ቆይታው አስደናቂ ጊዜያትን አሳልፏል፡፡ የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫ ያነሳው ሳንቼዝ በ52 ጨዋታዎች 25 ጎሎችን አስቆጥሯል፡፡ በፕሪሚየር ሊጉ ያስቆጠራቸው ሊጉ ተሳታፊ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን የአርሰናል ተጨዋቾች በተመሳሳይ ወቅት ምርጥ ብቃታቸውን አውጥተው ቢጠቀሙም ቬንገር ግን ካዞርላን ያስቀድማሉ፣ ሁለገቡ ተጨዋች ሜዳውን አካልሎ የሚጫወትበት መንገድ በጣም ይገርማል፣ በአማካይ ተከላካይ ላይ ከፍራንሷ ኮክለ ፊት ተጫውቷል፣ ተደራቢ አጥቂ እና በሁለቱም መስመሮ ተጫውቷል፡፡
ቬንገርም በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ያሳየውን ብቃት በጣም በጥንቃቄ እና በጥልቀት ተመልክተው ‹‹ሳንቲ ካዞርላ ከውድድር ዓመቱ ጅማሮ አንስቶ እስከመጨረሻው ድረስ ድንቅ ብቃቱን አሳይቷል›› ብለው መስክረውለታል፡፡

ቬንገር ሌሎች ተጨዋቾች በግል ያሳዩትን ብቃት አጥተውት አይደለም፡፡ ካዞርላን በቀዳሚነት ሲያስቀምጡ ምክንያታቸው ተጫዋቹ በዙሪያው የሚገኙ ተጨዋቾች ያላቸውን ብቃት አውጥተው እንዲጠቀሙ ባበረከተው አስተዋፅኦ ነው፡፡

የአርሰናል አማካይ ክፍል እስትንፋስ ኮክለ ቢሆንም ከእርሱ ጎን ተሰልፎ የማጥቃቱን እንቅስቃሴ የሚያስጀምረው እና በመጨረሻዎቹ 30 ሜትሮች ላይ የጨዋታውን እንቅስቃሴ የሚያፈጥነው ካዞርላ ነው፡፡ ትልልቅ ቡድኖች ሚዛናዊነትን የሚጠብቁት በዚህ አይነት መልኩ ነው፡፡ ከሶስት ዓመት በፊት አርሰናልን ሲቀላቀል በቅንጦት መልክ ያልታየው ካዞርላ በአሁኑ ሰዓት የአርሰናል መሪ ሆኗል፡፡

ካዞርላን ከሌሎች ተጨዋቾች ለየት የሚያደርገው በየትኛው እግሩ እንደሚጫወት ግራ እስኪያጋባ ድረስ በሁለቱም እግሮቹ መጫወቱ ነው፡፡ ሆኖም የዚህ ምክንያት ከጉዳቱ ጋር የተያያዘ ነው፡፡

‹‹ሁልጊዜም ቢሆን እግር ኳስ እጫወት የነበረው በቀኝ እግሬ ነበር፡፡ በአንድ አጋጣሚ የቀኝ እግሬ ጉልበቴ ላይ መጠነኛ ጉዳት አስተናገድኩኝ፤ ይህ ደግሞ በግራ እግሬም እንድጫወት አስገደደኝ፣ በዚህም ይበልጥ በግራ እግሬ መጫወት ጀመርኩኝ፡፡

‹‹በግራ እግሬ ይበልጥ ውጤታማ ለመሆን ከመደበኛ ልምምድ መልስ በተደጋጋሚ ግድግዳ ላይ ኳስን እመታ ነበር፡፡ ይህንን ደጋግሜ በመፈፀም የምመታው ምት ጠንካራ ስለመሆኑ አረጋግጥ ነበር፡፡ ወጣት ተጨዋቾች ሁሉም ነገር የሚሳካው በጠንካራ ሥራ እንደሆነ መረዳት አለባቸው፡፡ ስለዚህ በመጨረሻ ተስፋ መቁረጥ የለባቸውም፡፡
‹‹እግርኳስን መጫወት ከጀመርኩበት ጊዜ አንስቶ በሁለቱም እግሮቼ መጫወት ተፈጥሯዊ ልማዴ ሆኗል፡፡ ነገር ግን በሁለቱም እግሮቼ እኩል ለመጫወት (አንዱን ከአንዱ ላለማበላለጥ) ጠንክሬ መሥራት ነበረብኝ፡፡ በመጨረሻም ይህንን ማሳካት ችያለሁኝ›› በማለት ተፈጥሯዊው እግሩ የትኛው እንደሆነ ግራ እስኪያጋባ ድረስ በሁለቱም እግሮቹ መጫወት የቻለበትን ምስጢር አስረድቷል፡፡

30 ዓመቱን የደፈነው ካዞርላ በእግርኳስ ህይወቱ አስደሳች አጋጣሚ ቢያሳልፍም አሁንም ቁርጠኝነቱ በጣም ይገርማል፡፡ አርሰናልን ከተቀላቀለ በኋላ ባለፉት ሁለት ዓመታት (2013 እና 2015) ያሳካቸው የኤፍ.ኤ.ካፕ ድሎች ቀዳሚውን ቦታ ይወስዳሉ፡፡ እነኚህ ሁለት ዋንጫዎች ለእርሱ ብቻ ሳይሆን ከ2004/05 የውድድር ዘመን በኋላ ምንም ዋንጫ ላላገኙት ቬንገርም ሆነ ደጋፊዎቹ ወሳኝ ናቸው፡፡

በስፔን ብሔራዊ ቡድን ግን ውጤታማ ጊዜያትን አሳልፏል፡፡ ለአገሩ 73 ጨዋታዎችን የፈፀመው አማካይ በ2008 እና 2012 የአውሮፓ ዋንጫ ላነሳችው ስፔን ወጣ ገባ እያለ ተጫውቷል፡፡ ስፔን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫውን ስታነሳ ግን በአንጀት ህመም ምክንያት የቡድኑ አካል አልነበረም፡፡
የሳንቲ ህልም አንድ ቦታ ላይ የሚቆም አይመስልም፡፡ ጫማውን ከመስቀሉ በፊት ተጨማሪ ድሎችን ማሳካት ይፈልጋል፡፡

‹‹የውድድር ዓመቱን የፈፀምነው አስደሳች በሆነ መልኩ ነው›› የሚል አስተያየትን የሚሰጠው የቀድሞው የማላጋ ኮከብ ‹‹በቀጣዩ ዓመት ይበልጥ ተጠናክረን መቅረብ አለብን፣ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ‹‹ስለማንሳት እና በቻምፒዮንስ ሊጉ ረጅም ርቀትን ስለመጓዝ ማሰብ አለብን›› ጠንካራ ቡድን እንዳለን ይሰማኛል፣ ተግተን መስራት ያለብን ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት ላይ ነው፡፡ ጠንካራ አዕምሮዎችን ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ያሸጋግረናል፡፡ ቼልሲ ጠንካራ ቡድን ነው፡፡ አዎን ይህ በግልፅ የሚታይ ነው፡፡ የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ሆነዋል፤ የእኛም ቡድን ቢሆን ያለጥርጥር ጠንካራ ነው፡፡ ከመጀመሪያው ጨዋታ አንስቶ ዝግጁ መሆን አለብን፡፡ በአውሮፓ ሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎናን የመሳሰሉ ክለቦች የዓለማችን ምርጥ ተጨዋቾች ይዘዋል፡፡ እኛም ብንሆን በእነርሱ ደረጃ ስለመገኘት ማሰብ አለብን›› በማለት ሁልጊዜም ቢሆን መዳረሻቸው በትልቅ ደረጃ ሊሆን እንደሚገባ ጠቁሟል፡፡

ካዞርላ ደረጃቸው የላቁ ተጨዋቾች መፈረማቸው አርሰናልን እንደሚያጠናክረው ያምናል፡፡ የሳንቼዝ እና ኦዚል ዝውውር ምን ያህል በግል ደረጃውን እንዳሻሻለው ጠንቅቆ ይረዳል፡፡ በቀጣዩ ዓመትም በተመሳሳይ ደረጃቸው የላቀ ተጨዋች እንዲመጡ ያለው ፍላጎት ከፍተኛ ነው፡፡

‹‹ስም ያላቸው ተጨዋቾች መፈረማቸው ያስደስታል፣ ሁሉም ተጨዋቾች ያላቸው ስሜት ተመሳሳይነት አለው›› ይላል ሳንቲ፡፡ ‹‹እንደ አሌክሲስ እና ሜሱት አይነት ምርጥ ተጨዋቾች ወደዚህ መምጣታቸው ብቃቴን አውጥቼ እንድጠቀምና እንዳሻሽል አግዞኛል፤ የሁለቱ ተጨዋቾች ጥምረት ቡድናችንን ይበልጥ ጠንካራ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ በዚህ ላይ የአጨዋወት ዘይቤያቸው ከቡድኑ ጋር በፍጥነት የሚዋሃድ አይነት ነው››

አርሰናል ከግብ ጠባቂ እስከ አጥቂ ድረስ ሙሉ የሆነ ቡድን ይመላል፡፡ ይበልጥ በአማካይ ስፍራ ላይ በርካታ አማራጮችን ይዟል፣ በዚህ ቦታ ላይ ከሚጫወቱ ተጨዋቾች መሀከል አንዱ የሆነው ጃክ ዊልሸር በውድድር ዓመቱ ከጉዳት ጋር እየታገለ በአርሰናል ማልያ በቂ ጨዋታዎችን ቢያከናውንም ባለፈው ዓመት መጨረሻ ተስፋ ሰጪ ነገር አሳይቷል፡፡
እንግሊዝ በቅርቡ ከሶሎቬንያ ጋር ባደረገችው ጨዋታ ላይ ያሳየው ብቃት እና ጎል ማስቆጠሩ ሁሉንም ነገር ሊነግረን ይችላል፣ ካዞርላ የቡድን ጓደኛው ከእንግሊዛውያን ተጨዋቾች በተቃራኒ በላ ሊጋው መጫወት የሚያስችል ኳሊቲ እንዳለው ጠቅሷል፡፡

‹‹ጃክ ያለጥርጥር በስፔን መጫወት የሚያስችል ኳሊቲ አለው›› ይላል ካዞርላ፡፡ ‹‹ተሰጥኦ ያለው ታላቅ ተጨዋች ነው፡፡ እርሱን የመሰለ ተጨዋች መያዛችን እድለኞች ነን፤ የእግር ኳስ ህይወቱን ወደላቀ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ከሆነ በስፔን ላ ሊጋ የመጫወት አቅም እና ብቃት እንዳለው እርግጠኛ ሆኜ መናገር እችላለሁኝ፡፡
‹‹እንግሊዛውያን ተጨዋቾች ግን ስፔን ላ ሊጋ ተጉዘው የማይጫወቱበት ምክንያት አይገባኝም፡፡ ነገሩን ሳስበው እግረማለሁኝ፤ እርግጥ ነው ከዚህ ቀደም ስቲቭ ማከማናማን፣ ዴቪድ ቤካም እና ማይክል ኦዌን በላ ሊጋው ተጫውተዋል፡፡ ሆኖም ግን ቁጥራቸው ብዙ የሚባል አይነት አይደለም›› በማለት የእንግሊዛውያን ተጨዋቾች በላ ሊጋው ያለመታየታቸው ምክንያት እንዳልገባው ያስረዳል፡፡

የላ ሊጋ ክለቦች የካዞርላን በድጋሚ ወደ ስፔን መመለስ አጥብቀው ይመኛሉ፤ በቀጣይ አማካዩን ለማግኘት ጥረት ያደርጋሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ግን አርሰናልን ለመልቀቅ የሚደፍር አይመስልም፡፡ እርሱም ቢሆን ከኢምሬትስ መልቀቅ የሚፈልግ አይነት አይደለም፡፡

‹‹ለጊዜው አርሰናል ቤቴ ነው፡፡ የምኖረው የዕለት ህይወቴን እንጂ መጪውን ዘመን አሻግሬ አልመለከትም፣ በአሁኑ ሰዓት ከአርሰናል ጋር ስኬትን እንጂ ከዚያ ተቃራኒ የሆነ ነገር ማሰብ አልፈልግም፤ አርሰናል አቅጣጫዬን የሚጠቁምልኝ መንገዴ ነው፡፡ ከምንም በላይ ከህይወቴ ጋር የተዋሃደ ጉዳይ ሆኗል›› በማለት በኢምሬትስ ቆይታው ስኬታማ መሆንን እንጂ ከክለቡ ጋር ስለመለያየት በጭራሽ እንደማያስብ ጠቁሟል፡፡

ስፔናዊውን ተጨዋቾች በፕሪሚየር ሊጉ ለረጅም ጊዜ ቆይተው ስኬታማ የሆኑበትን ጊዜ ማስታወስ አስቸጋሪ ነው፡፡ ሴስክ ፋብሪጋዝ በአርሰናል ስምንት ዓመት ቢቆይም አንድም ዋንጫ አላነሳም፤ ካዞርላ በሶስት ዓመት ቆይታው ሁለት ጊዜ የኤፍ.ኤ ካፕ ዋንጫዎችን አንስቷል፤ እንደ ፋብሪጋዝ የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ለመሆን ቀጣዩ ዓመት የምርጥ አጋጣሚ ይመስላል፡፡

አርሰናል ከ2003/04 የውድድር ዘመን በኃላ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ምን ያስፈልገዋል? ካዞርላ እንዳለው ጠንካራ አዕምሮ፣ ወጥ አቋም እና ደረጃቸው የላቁ ተጨዋቾችን ማስፈረም ይህ ብቻውን በቂ አይመስልም፣ ሻምፒዮን የሚሆኑ ቡድኖች ጠንካራ የተከላካይ መስመር አላቸው፡፡

‹‹በቀጣዩ ዓመት አስተካክለን መቅረብ ከሚገባን ግብአቶች መሀከል ቀዳሚውን ቦታ የሚወስደው የተከላካይ መስመሩ ጥንካሬ ሊሆን ይገባል›› የሚል መረጃን ሰጥቶ ‹‹ይህንን ማስተካከል ከቻልን የአጥቂ መስመራችን ጠንካራ ይሆናል፡፡ ባለፈው ዓመት በሜዳችን ሳይቀር በትንንሽ ቡድኖች ነጥብ የመጣላችን ምስጢር ይኸው የተከላካይ መስመራችን የቦታ አጠባበቅ ወሳኝነት አለው›› ይላል፡፡

የሰሜን ለንደኑ ክለብ በቀጣይ አዳዲስ ተጨዋቾችን የሚያስፈርም ከሆነ ፔትር ቼክ እና የፖርቶው አጥቂ ጃክሰን ማርቲኔዝ በአማራጭነት ይቀርባሉ፡፡ ኮሎምቢያዊው አጥቂ ለዝውውር 25 ሚሊዮን ፓውንድ ተጠይቆበታል፡፡ የቼክ ዝውውር ደግሞ ውስብስብነት በዝቶበታል፡፡

‹‹ይህ ፈታኝ ውሳኔ ነው፡፡ አርሰን ቬንገር ውሳኔውን እንደሚያሳልፍ ይሰማኛል፣ የእርሱ ውሳኔ ለቡድኑ የላቀ ጠቀሜታ አለው፣ የትኛውም ተጨዋች ቢመጣ ወሳኙ ነገር የቡድኑን ደረጃ የሚያጎለብት መሆን አለበት፡፡ በየትኛው ቦታ ተጨዋቾች እንዲመጡ ብትጠይቁኝ ቅድሚያ የምሰጠው በአጥቂ ቦታ ላይ የሚጫወት መሆን አለበት፡፡ እዚያ ቦታ ላይ ተጫውቶ ቡድኑን ውጤታማ የሚያደርግ ቢሆን ደስ ይለኛል›› ይላል፡፡

የተከላካይ መስመሩ ግን አሁንም ትኩረት ይሻዋል በመሀከል ተከላካይነት ቦታ ላይ አስተማማኝ ሊባል የሚችለው ሎሮ ኮሲዬልኒ ነው፣ ፔር ሜርትሳከር ዕድሜው ገፍቷል፡፡ ከጉዳት ጋር በተያያዘ በእርሱ ላይ እርግጠና መሆን አይቻልም፡፡ ማቲዮ ዴቡቼም ለጉዳት ቅርብ ተጨዋች ሆኗል፡፡ በክረምቱ ከሳውዝአምፕተን አርሰናልን የተቀላቀለው ካሉም ቼምበርስ የመሀል ተከላካይ ሆኖ መጫወት ቢችልም በውጤታማነቱ ላይ እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡

የካርል ጄንኪንሰን ቆይታ አስተማማኝ የሚባል አይነት አይደለም፡፡ እንግሊዛዊውን ተከላካይ በውሰት ለመውሰድ ዌስትሃም ዩናይትድ እና ሳውዛመውተን ጥያቄ ቢያቀርቡም አርሰናል ያቀረበውን የ15 ሚሊዮን ፓውንድ ሂሳብ ሳይቀበሉ ቀርተዋል፡፡ ምናልባት የቀድሞው የቻርልተን አትሌቲክ ተከላካይ በቀጣይ ወደ ሰንደርላንድ ሊያመራ ይችላል፡፡
እንደ ካዞርላ እምነት ጠንካራ አዕምሮ፣ ወጥ የሆነ አቋምና ደረጃቸው የላቁ ተጨዋቾች ማስፈረም እና ጠንካራ የተከላካይ መስመር መገንባት በቀጣዩ ሲዝን አርሰናልን ለፕሪሚየር ሊጉ ስኬት አብቅቶ ለቻምፒዮንስ ሊግ ተፎካካሪነት ያበቃዋል፡፡
ሳንቲ ካርላን እንወቅ
ሙሉ ስም፡- ሳንቲያጎ ካዞርላ ጎንዛሌዝ
የትውልድ ዘመን፡- ዲሴምበር 13/1984
ዕድሜ፡- 30
የትውልድ ቦታ፡- ሊያኔራ (ስፔን)
ቁመት፡- 1.68 ሜትር
ቦታ፡- የመስመር አማካይ (የአማካይ አጥቂ)
ክለብ፡- አርሰናል
የማልያ ቁጥር፡- 19

Health: እንዴት አንድ ሰው ለሁሉም የጉበት ቫይረስ ፖዘቲቭ ሊሆን ይችላል?

$
0
0

Print

እንደሚታወቀው የጉበት በሽታን ሊያስከትሉ የሚችሉ የተለያዩ ምክንያቶች ያሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ቫይረሶች በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ጉበትን ከሚያጠቁ ዋና ዋና ቫይረሶች ደግሞ ዋነኛው ‹‹ሂፖታይተስ›› በመባል የሚታወቁት አምስት አይነት ቫይረሶች ሲሆኑ ከእነዚህም አንዱ ‹‹Hepatitis B virus›› የተባለው ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ ‹‹Hepatitis C virus›› የተባለው እና በጠያቂያችን ላይ የተገኙት ናቸው፡፡ እነዚህ ቫይረሶች ለጉበት በሽታ በተለይም በታዳጊ አገራት ዋና መንስኤ ናቸው፡፡ የሚያስከትሉት በሽታም አጣዳፊ ወይም ስር የሰደደ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁንና ምንም አይነት በሽታ ሳያስከትልም ወይም ከአጣዳፊ በሽታም ካገገሙ በኋላ በተወሰኑ ታማሚዎች ላይ ምንም በሽታ ሳያስከትል በደም ውስጥ ሊገኙ ይችላሉ፡፡ (B እና C የተሰኙት አይነቶች)፡፡ በሌላ አገላለፅ የቫይረሱ ተሸካሚ ከቫይረሱ ጋር አብሮ ኗሪ ናቸው ማለት አይደለም፡፡ ምናልባት ለሌላ የጤና እክል ካልተዳረጉ በስተቀር በሽታው አያገረሽም ወይም ጎልቶ አይወጣም፡፡ የማገርሸቱ እድልም በጣም ትንሽ ነው፡፡ ስለሆነም ጉበትን ለጉዳትና ለተጨማሪ ኢንፌክሽ የሚዳርጉ ሁኔታዎችን በማስወገድ እና በመከላከል ማገርሸቱን መከላከል ይቻላል፡፡ ስለዚህም ጠያቂያችን ይህን ከማድረግ ባለፈ ምንም ሊያሳስቦት አይገባም፡፡ በእርግጥ እነዚህ የቫይረሱ ተሸካሚዎች በደም ንክኪ ወይም በልቅ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ወደ ሌላ ሰው ሊያስተላልፉ ስለሚችሉ መጠንቀቁ ተገቢ ነው፡፡

ጉበት በቫይረስ መጠቃቱን እንዴት ማወቅ ይቻላል?

ይህም ጠያቂያችንን ያሳሰባቸው ሌላው ጥያቄ ነው፡፡ በተለይም የላቦራቶሪ ውጤታቸው ‹‹ፖዘቲቭ›› መባሉ፡፡ እንደማንኛውም በሽታ የጉበት በሽታም መጠቃቱና መጎዳቱን ለመለየት የሚረዱ ዋና ዋናዎቹ ዘዴዎች በህመምተኛው ላይ የሚደርሱት የበሽታ ምልክቶች፣ የላቦራቶሪ ምርመራዎች፣ የአልትራሳውንድ ምርመራዎችና ሌሎችም ናቸው፡፡ ሁሉም የየራሳቸው ፋይዳ አላቸው፡፡

ከልዩ ልዩ የላቦራቶሪ ምርመራዎችም ውስጥ የቫይረሱን በደም ውስጥ መኖር የሚጠቁሙ የተለያዩ የምርመራ አይነቶች ያሉ ሲሆን በጥቅሉ ‹‹Viral Markers›› ተብለው ይጠራሉ፡፡ እነዚህም ሰውነታችን ኢንፌክሽኑን ለመቋቋም በሚያደርገው የመከላከል ሂደት ውስጥ የሚከሰቱ የቫይረሱ ‹‹አንቲጂኖች›› ወይም ‹‹አንቲቦዲዎች›› ናቸው፡፡ ከእነዚህም አንዱ በጠያቂያችን ደም ውስጥ የተገኙት እነዚህ ማርከሮች (ጠቋሚ ፕሮቲኖች) ናቸው፡፡ እነዚህም በአጣዳፊ በሽታ ወቅት ብቻ ሳይሆን ስር የሰደደ ህመም (Chronic viral Hepatitis) አሊያም በሽታው በሌለበት የተሸካሚነት ሁኔታም ሊገኙ ይችላሉ፡፡ በጠያቂያችን ላይ የበሽታ ምልክቶች ያለመኖራቸው የቫይረሱ ተሸካሚ እንጂ ታማሚ አለመሆናቸውን ስለሚያረጋግጥ ሊጨነቁ አይገባም፡፡ ጥንቃቄ ማድረጉ ብቻ በቂ ነው፡፡ ቤተሰብም መመርመሩ ከቫይረሶቹ የደም፣ የግብረ ሥጋና የወሊድ ተላላፊነት አንፃር ለጥንቃቄ ሲባል ነውና አይረበሹ፡፡

ለመሆኑ ቫይረሱ ሄፖታይተስ እና ህክምናው ምን ይመስላል? የሚለው ሌላው የአቶ መላኩ ጥያቄ ነው፡፡ አጣዳፊ የጉበት ኢንፌክሽ በሆስፒታል ውስጥ ተኝተው መታከም ካለባቸው በሽታዎች አንዱ ነው፡፡ እንዳብዛኛው የቫይረስ በሽታዎች ቫይረሱን ሙሉ ለሙሉ የሚያጠፉ ፈዋሽ መድሃኒቶች ባይኖርም በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ግን ከፍተኛ ለውጥ የሚያመጡ መድሃኒቶች ተገኝተው በጥቅም ላይ መዋል መጀመራቸው ሌላኛው አስደሳች ነገር ነው፡፡ በሽታው ተወሳስቦ ለከፋ ጉዳት ለሞት እንዳያደርስ የሚያደርጉ የተለያዩ ህክምናዎችም አሉት፡፡ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

– የበሽታው ዋነኛ መገለጫ የሆኑትን ምልክቶች ለመግታት የሚዳርጉ እገዛዎች ማለትም ትውከትን ማስቆም፣ ህመምን ማስታገስ፣  ምግብን የግሉኮስ እርዳታ መስጠት ትኩሳትን ማስታገስ እና የመሳሰሉትን ያካትታል፡፡

– የሚያባብሱ ነገሮችን ማስወገድ ማለትም አልኮል፣ አንዳንድ መርዛማ መድሃኒቶችንና የመሳሰሉትን ማስወገድ፡፡

– ውጤታማ ፀረ ቫይረስ መድሃኒቶችን መስጠት፡፡

– ሌሎች ተጓዳኝ ህመሞች ካሉ በአግባቡ ማከም፡፡

– ተገቢውን የቅርብ ክትትልና እርዳታ ማድረግ ናቸው፡፡

– አጠቃላይ ምርመራዎችን በማድረግ የተዳከመ የቫይረሱ አይነት እንዳለብንና እንደሌለብን በማረጋገጥ ቫይረሱ እርስዎ እንደጠቀሱት ያለህመም ስሜት የሚገኝም ከሆነ በበቂ ህክምና ወደ ባሰ ሁኔታ እንዳይሄድ ማድረግ ይገባል፡፡

አንባቢያን ስለዚህ ህመም ማወቅ ያለባቸው አጋላጭ ሁኔታዎች ምን ምን ናቸው?

ቫይረሶቹን ወደ ደም ውስጥ ብሎም ወደ ጉበት እንዲደርስ የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ዋነኞቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

– በእርግዝና ወይም በወሊድ ወቅት ከእናት ወደ ልጅ፣

– ልቅ የግብረ ሥጋ ግንኙነት (በተለይም ቢ ለተባለው አይነት)

– የደም ልገሳ (በተለይም ሲ ለተባለው አይነት)

– በቀዶ ህክምና መሳሪያዎች ሳቢያ እና

– በጉበት ልገሳና ዝውውር ምክንያት ናቸው፡፡

ይሁንና ቫይረሶቹ ወደ ጉበት ደረሱ ማለት የግድ በሽታውን ያስከትላሉ ማለት አይደለም፡፡ ይህ የሚሆነው አልፎ አልፎ ነው፡፡ በተለይ ጉበት ቀደም ሲል በተጠቀሱት በሽታዎች ለምሳሌ በአልኮል ሳቢያ ከተጎዳና እየተዳከመ ከሄደ የቫይረሶቹ ኢንፌክሽኖች ወደ በሽታ የመለወጣቸውን እድል ያስፋፋል፡፡

በተቻለ መጠን የጉበት ህመምን የሚያባብሱ የአልኮል መጠጥ አዘውታሪነት ካለ መቀነስ እንዲሁም የቅባት ምግብ መጠንንና ክብደት መቀነስም ያስፈልጋል፡፡ በቤተሰብዎ ውስጥም በቀላሉ ለደም ንክኪ የሚያጋልጡ ስለታም ነገሮችን በጋራ ከመጠቀም ይቆጠቡ፡፡ ደም ከመለገስም እንዲሁ፡፡ በዚህ አጋጣሚም የኤች.አይ.ቪ ምርመራ ቢያደርጉ እንደሚመከር ይረዱ፡፡ የእነዚህ ቫይረሶች መኖር ለኤች.አይ.ቪ መኖር መሰረታዊ አመላካች ባይሆንም መተላለፊያ መንገዳቸው ተመሳሳይነት ያለው በመሆኑ አብሮ የመከሰት ዕድል አላቸው፡፡ ልጆችዎንም በማስመርመር በአገራችን የሚሰጠውን የፀረ ጉበት ቫይረስ (በተለይ ለ‹‹ቢ››) ክትባት እንዲወሰዱ ያድርጓቸው፡፡ ከዚህ በተረፈ ለወደፊት የጉበት ህመም ማለትም ቫይረሱ ወደ ጉበት ህመምተኝነት የመቀየሩ ጉዳይ በጥቂቶች ላይ የሚስተዋል በመሆኑ ተጋላጭነትን የሚቀንሰው አንዱ ወሳኝ ጉዳይ ንፁህ እድልም ጭምር ነውና መልካም ዕድል

በእነ ወይንሸት ላይ የተጠየቀው ይግባኝ ውድቅ ተደረገ

$
0
0

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

weynishetመንግስት አይ.ኤስ.አይ.ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ እስር ላይ የቆዩት እነ ወይንሸት ሞላ ሰኔ 15/2007 ዓ.ም በቄራ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት እንዲፈቱ ከተፈረደላቸው በኋላ ሰኔ 22/2007 አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆባቸው ነበር፡፡ ይሁንና የልደታ ፍርድ ቤት ዛሬ ሀምሌ 14/2007 ዓ.ም በዋለው ችሎት የቄራ ፍርድ ቤት በእነ ወይንሸት ላይ የወሰነውን ውሳኔ በማፅናት አቃቤ ህግ የጠየቀውን ይግባኝ ውድቅ አድርጎታል፡፡
ወንይሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለወርቅ ከውጭ ሆነው ሲከራከሩ የቆዩ ሲሆን ‹‹የፍርድ ቤቱን ውሳኔ አልተቀበልክም›› በሚል ተጨማሪ አንድ ወር የተፈረደበት ማስተዋል ፈቃዱ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሆኖ ጉዳዩን ሲከታተል ቆይቷል፡፡ ማስተዋል ፈቃዱ የ3 ወር እስሩን የጨረሰ በመሆኑ በዛሬው ዕለት ከእስር ይለቀቃል ተብሎ ይገመታል፡፡

የፕሬዝዳንት ኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝትና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥያቄ –እስክንድር ፍሬው VOA)

$
0
0

Merera-Gudinaሰሞኑን ወደ አዲስ አበባ የሚመጡት ያሜሪካው ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ተቃዋሚዎችን የማነጋገር ፕሮግራም እንደሌላቸው ግልጽ እየሆነ መጥቷል፤ ሲሉ ጥያቄ ያቀረቡ ፓርቲዎች መሪዎች ተናገሩ።

ፕሬዘዳንቱ ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ አይቀር እኛንም ያነጋግሩን በሚል ያቀረቡት ጥያቄም ይፋ ምላሽ እንዳላገኘ እነዚሁ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች አስረድተዋል።

ፍሬ ከሌለው (ይገረም አለሙ)

$
0
0

{ህይወትን ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ ሰው ምላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኮል ከመናገር ይከልክል፣ (የጴጥሮስ መልእክት 3፣10)

ይገረም አለሙ

ሰሞኑን ሁለት ነገሮች ጎን ለጎን እየተሰሙ ነው፡፡ አንደኛው ኢትዮጵያን ከወያኔ የግፍ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት ሁሉን አቀፍ ትግል ማድረግ ግድ ነው ያሉና ለዚሁ እየተዘጋጁ እንደሆነ ሲገልጹ የቆዩት ኃይሎች ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መሸጋገራቸውን ከማወጅ አልፈው ሊቀመንበሩ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ ትግሉ ወደተጀመረበት አካባቢ መሄዳቸው ሲሆን ሁለተኛው በተለያየ መንገድ ይህን ትግል የሚቃወሙ ድምጾች ናቸው፡፡ የወያኔን አገዛዝ እንታገላለን በሚሉ መካከል እንዲህ አይነት የነጻነት ትግልን ለማደናቀፍ ያለመ ልዩነት መታየቱ አሳዛኝ ነው፡፡

በቅዱሱ መጽኃፍ ጢሞቲዎስ 2፣2፣20 {በትልቅም ቤት የእንጨትና የሸክላ ዕቃ ደግሞ አለ እንጂ የወርቅና የብር ዕቃ ብቻ አይደለም፡፡እኩሌቶቹም ለክብር እኩሌቶቹም ለውርደት ይሆናሉ፡፡እንግዲህ ማንም ራሱን ከእነዚህ ቢያነጻ ለክብርም የሚሆን የተቀደሰም ለጌታውም የሚጠቅም ለበጎ ስራ የተዘጋጀ ዕቃ ይሆናል፡፡} ተብሎ እንደተጻፈው እንዲህ ወሳኝ ቀን ሲመጣ መፈተኛው ተግባር ሲሆን በአንድ ጎራ የተሰለፉት ወርቅና ብሩ እንጨትና ሸክለው ግልጽ ብለው ይታያሉ፣ይለያሉ ይታወቃሉ፡፡

ሁሉም እንደ አቅሙ በአንድ ሀገር ልጅነቱ ተግባብቶና እንደ እውቀት ዝንባሌው፣እንደ ሙያና ችሎታው ተሰልፎ ሲሆን ተባብሮ ካልሆነም ተከባብሮ ቢጓዝ ለሀገርም ለሕዝብም የሚጠቅም በጎ ተግባር መከወን ይቻል ነበር፡፡ የወያኔ አገዛዝ ዘመንም እንዲህ ባረዘመ ነበር፡፡ መነጋገሩ ከሌለ መግባባቱ ከጠፋ እንዲህ ስታዩኝ ሸክላ ወይንም እንጨት ብመስላችሁም እኔ ወርቅ ነኝ ብሎ መኮፈስና ያልሆኑትን ለመሆን መዳከር ካለ፣ መልካም ቀኖችን ማየት የሚቻል አይሆንም፡፡ ማንነታችንን አውቀን አቅማችንን ተረድተን የምንችለውንና የሚገባንን እየሰራን ለበጎ ምግባር የተዘጋጀን እንሁን ሲባል ደግሞ የለም ወርቅ ባልሆንም ወርቅ ነህ ብላችሁ ካልተቀበላችሁኝ አይሞከርም ከተባለ በታሪካችን ተደጋግሞ እንደታየው እነዚህ ሰዎች የሚማሩም የሚመከሩም አይደሉምና {ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ ርኩሱንም አትንኩ} (ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2፣6፣17) ተብሎ እንደተጻፈው  የሚበጀው መለየቱ ነው፡፡

ነገር ግን መለየቱ  ብቻውን ለክብር አያበቃም፣ በዮሐንስ መልእክት (1፣3፣17) {እንግዲህ እናንተ ወዳጆች ሆይ ይህን አስቀድማችሁ ስለምታውቁ በአመጸኞች ስህተት ተስባችሁ ከራሳችሁ ጽናት አንዳትወድቁ ተጠንቀቁ}፡ ተብሎ እንደተጻፈው በመሰሪዎቹ ሴራ ተጠልፎ ሳይወድቁ፣ በስብከታቸው ተስቦ መንገድ ሳይስቱ፣ ለመለየት ምክንያት የሆነውን ዓላማ ከዳር ለማድረስ በቁርጠኝነት መሰለፍ ነው የሚያስከብረው፡፡

ዛሬ በተለይ የነጻነት ትግሉ ወደ ተግባር ተሸጋገረ ከተባለበት እለት አንስቶ የምንሰማቸው ነገሮች ሁሉ ከመልካም እሳቤ የመነጩና ለበጎ ተብሎ የሚቀርቡ ቢሆኑ ኖሮ ከሁለትና ሶስት አመት ጀምሮ በሰማናቸውና ዛሬ የመለያያ ሳይሆን የመስማሚያ፣የመነታረኪያ ሳይሆን የመፍትሄ ሀሳቦች በሆኑ ነበር፡፡ ነገር ግን በታላቁ መጽሀፍ 1ኛ ጢሞቲዎስ 1፣5-7፣{የትዕዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹህ ልብና ከበጎ ህሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው፡፡ ከእነዚህም አንዳንዶቹ ስተው የሚሉትን ወይንም እነርሱ አስረግጠው የሚናገሩትን ሳያስተውሉ የህግ አስተማሪዎች ሊሆኑ እየወደዱ ወደ ክፉ ንግግር ፈቀቅ ብለዋል፣} ተብሎ እንደተገለጸው ሆነና  ንጹህ ልብ፣ በጎ ህሊና፣ እምነትና ፍቅር የሚባሉ ነገሮች ጠፍተው ለጥፋት የተነሳሳ ልብና ተንኮል ያረገዘ ህሊና በመግነኑ በአንድ ወይንም በሌላ መልኩ ድጋፍ መስጠት በሚገባበት ሰአት የነጻነት ትግሉን ለማደናቀፍ ያለሙ ድምጾች እዚህም እዛም ይሰማሉ፡፡፡

በማቲዎስ ወንጌል 23፣3-8 {ከባድና አስቸጋሪ ሸክም ተብትበው በሰው ትከሻ ይጭናሉ፣ እነርሱ ግን በጣታቸው እንኳን ሊነኩት አይወዱም ለሰውም እንዲታዩ ሥራቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡ ስለዚህ አሸንክታባቸውን ያሰፋሉ፣ዘርፉንም ያስረዝማሉ፣ በምሳም የከበሬታ ሥፍራ በምኩራብም የከበሬታ ወንበር በገበያም ሠላምታና መምህር ሆይ መምህር ሆይ ተብለው መጠራትን ይወዳሉ} እንደተባለው እነርሱ አስበው ያልተሳካላቸውን፣ሞክረው ያልሆነላቸውን፣ወይንም ሊነኩት ያልደፈሩትን ሊሄዱበት ያልመረጡትን ወዘተ ሌላው ሲጀምረው ለማሳካትም ስንዝር ሲራመድ የሆነ ያልሆነ ሰበብ ደርድረው አፍራሽ ጩኸታቸውን ያሰማሉ፡፡ ትግለው ውጤት ለማሳየት ከመጣር ራሳቸውን  በመካብ በየመድረኩና በየመገናኛ ብዙኃኑ ክቡር እየተባሉ ያለስራቸው መሞገስን፣ ወርቅ ሳይሆኑ ወርቅ መባልን ይሻሉ፡፡

ስለሆነም {እንግዲህ ማንም ራሱን ከእነዚህ ቢያነጻ ለክብርም የሚሆን የተቀደሰም ለጌታውም የሚጠቅም ለበጎ ስራ የተዘጋጀ ዕቃ ይሆናል፡፡} ተብሎ በሁለተኛይቱ የሐዋሪያው ጳውሎስ መልእክት ወደ ጢሞቲዎስ ሰዎች ምእራፍ 2 ቁጥር 20 ላይ እንደተጻፈው ከእነዚህ ሰዎች ጋር ንትርክና አንካ ሰላንትያ ማብዛት ሳያስፈልግ መለየትና ራስን አንጽቶ በሚቻለውና በሚመርጠው መንገድ የድርሻን ማበርከት ነው የነጻነቱን ቀን ሊያፋጥን የሚችለው፡፡

መጽሀፍ ቅዱስ {ህይወትን ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ ሰው ምላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኮል ከመናገር ይከልክል፣ ከክፉ ፈቀቅ ይበል፣መልካምንም ያድርግ ሰላምን ይሻ ይከተለውም፡} ይላል፡፡ (የጴጥሮስ መልእክት 3፣10) ኢትዮጵያ ከወያኔ አገዛዝ የምትላቀቅበትን ቀን ማየት እንደሚፈልጉ የሚነጋሩ ሰዎች ዛሬ የሚናገሩት ክፉ ነገርና የሚሰሩት ተንኮል እውነት ያችን መልካም ቀን ለማየት የሚናፍቁ ናቸውን የሚል ጣያቄ የሚያስነሳ ነው፡፡

{ፍሬ ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ ይልቁን ግለጡት እንጂ፣ እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት መናገር እንኳን ነውር ነውና ሁሉ ግን በብርሀን ነውና } ( ኤፌሶን 5፣11-13) ተብሎ እንደተጻፈው የተለያየ ሰበብ እየተጠቀሰ የነጻነት ትግሉን ለማደናቀፍ የሚደረገውን ስውር ሴራ  አለመተባበር ብቻ ሳይሆን በግልጽ እንዲታወቅ ከጓዳ ወደ አደባባይ ከጨለማ ወደ ብርሀን እንዲወጣ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ {ረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞርን በገበያም ሰላምታን፣ በምኩራብም የከበሬታን ወንበር፣ በግብርም የከበሬታን ስፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠበቁ} ( የማርቆስ ወንጌል 12፣38/39) በማለት እየሱስ እንዳስተማረው ከእንዲህ አይነት ሰዎች መለየትም መጠበቅም ያስፈልጋል፡፡ታላቁ መጽሀፍም ይላል፡ {ቅንአትና አድመኝነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ሥራ ሁሉ አሉና ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽህት ናት፡፡ በኋላም ታራቂ፣ ገር፣ እሺ ባይ፣ ምህረትና በጎ ፍሬ የሞላባት ጥርጣሬና ግብዝነት የሌለባት ናት ፡፡ የጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉት ሰዎች በሰላም ይዞራል፡፡} ያዕቆብ 3፣16-18)      አንድየ የማሪያም ልጅ ለክፉዎች ልብ፣ ለበጎዎች ጽናት፣ ለእናት ኢትዮጵያ ነጻነት፣ለኢትዮጵያዉያን ፍቅር ይስጥ….አሜን…

Comment


(ሰበር ዜና) 6 የኦሮሞ ነፃነት ግንባሮች በቅንጅት አንድ ላይ ሊመጡ ነው * 4ቱ ተዋህደዋል

$
0
0

OLF Army
(ዘ-ሐበሻ) አርበኞች ግንቦት 7 በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የሕወሓትን ሰራዊት የማጥቃቱ ዜና በተጧጧፈበት ወቅት የኦሮሞ ነፃነት ግንባርም በሐረር የሕወሓት የጦር ሰፈር ላይ በከፈተው ጥቃት 28 የሕወሓት ወታደሮችን መግደሉን ትናንት ድርጅቱ መግለጹን ዘ-ሐበሻ ማስነበቧ ይታወሳል:: ዛሬ በደረሰን ሰበር ዜና 6 የተለያዩ ኦሮሞ ነፃነት ግንባር ስም የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ወደ አንድ ላይ በመቀናጀት ለለውጥ መዘጋጀታቸውን ነው::

ለዘ-ሐበሻ የደረሰው ሰበር መረጃ እንደሚያመለክተው
1ኛ. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (በቦንሳ ሰባ የሚመራው)
2ኛ. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (በዶ/ር ኑሮ ደደፎ የሚመራው)
3ኛ. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጊዜያዊ አባሎች (በአቶ ድሪባ ወርዶፋ የሚመራው)
4ኛ. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ታጋዮች ቡድን (በአብደታ ሹኬ የሚመራው) ከጁን 27 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአንድ ላይ በመወሃድ በጋራ መስራት ጀምረዋል:: በቅርብ ቀናት ውስጥም የጀነራል ከማል ገልቹ እና በዳዑድ ኢብሳ የሚመሩት ኦነጎች ወደዚሁ ጥምረት እንደሚያመሩና በቅንጅት ትግሉን ለማጧጧፍ መዘጋጀታቸውን ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ተናግረዋል::

ጁን 27 2015 የተዋሃዱት አራቱ በኦሮሞ ነፃነት ግንባር ስም የሚንቀሳቀሱት ድርጅቶች በአንድ አመራር ስር የሆኑ ሲሆን በጀነራል ከማል ገልቹም ሆነ በኦቦ ዳውድ ኢብሳ የሚመሩት ኦነጎች ይጠቃለላሉ ተብሎ ይጠበቃል::

ትግሉ እጅግ በጣም እየተቀጣጠለ በመጣበት በዚህ ወሳኝ ወቅት ላይ የተከፋፈሉና ትግሉን ወደ ኋላ የሚጎትቱ የኦነግ አመራር አባላት ላይ በውስጥም ሆነ በውጭ ከፍተኛ የሆነ ጫና እያጋጠማቸው መሆኑን ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች ይጠቁማሉ::

በ6ቱ በኦነግ ስም በሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች መካከል የሚደረገው ውህደትና ጥምረት በወቅቱ መራራ ትግል ላይ ከፍተኛ የሆነ ለውጥ ያመጣል ተብሎ በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እና በየጫካው የሚገኙ ብረት አንስተው በሚታገሉ ወገኖች ዘንድ ተስፋ ተጥሎበታል::

በ15ኛው ዙር ሊዝ ጨረታ በመርካቶ ለቀረቡ ቦታዎች ከፍተኛ ዋጋ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል

$
0
0

–ላፍቶ አካባቢ ለጨረታ የቀረቡ ቦታዎች መሰረዛቸው እያነጋገረ ነው

merkato-addis-ababa-copyረቡዕ ሐምሌ 15 ቀን 2007 ዓ.ም. በሚከፈተው 15ኛው ሊዝ ጨረታ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መርካቶ አካባቢ የቀረቡት አራት ቦታዎች ከፍተኛ የመጫረቻ ዋጋ ይቀርብላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በዚሁ ጨረታ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ላፍቶ ሞል ፊት ለፊት የሚገኙ ሁለት ቦታዎች በመጨረሻ ሰዓት መሰረዛቸው እያነጋገረ ነው፡፡

በ11ኛው ሊዝ ጨረታ መርካቶ አካባቢ ቀርቦ ለነበረው 449 ካሬ ሜትር ቦታ በካሬ ሜትር 305 ሺሕ ብር መቅረቡ ይታወሳል፡፡ ለዚህ መሬት በከተማው ታሪክ ክብረ ወሰን የሆነውን የመጫረቻ ዋጋ ያቀረበው ዝዋይ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ያቀረበው ገንዘብ ከፍተኛ መነጋሪያ ሆኖ ስለነበር፣ ወደ ኋላ በማፈግፈግ በተሰጠው ጊዜ ውል ሳይዋዋል ቀርቷል፡፡

የአዲስ አበባ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ይህንን መሬት በ15ኛው ሊዝ ጨረታ አካቶ አቅርቧል፡፡ ከዚህ መሬት በተጨማሪ በዚያው በመርካቶ ከይርጋ ኃይሌ የገበያ ማዕከል ጀርባ 222 ካሬ ሜትር ቦታ ለጨረታ ቀርቧል፡፡ ሰባተኛ አካባቢም 150 ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸው ሁለት ቦታዎች ለጨረታ ቀርበዋል፡፡ እነዚህ ቦታዎች ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚካሄድባቸው በመሆኑ፣ በርካታ ባለሀብቶች ቦታዎቹን ለመግዛት የጨረታ ሰነድ መግዛታቸው ታውቋል፡፡

እነዚህን ለመግዛት ከፍተኛ የመጫረቻ ዋጋ እንደሚቀርብ ለመሬት ሊዝ ጨረታ ቅርብ የሆኑ ምንጮች እየተናገሩ ነው፡፡ ከእነዚህ ቦታዎች በተጨማሪ ለ15ኛው ሊዝ ጨረታ ከቀረቡት ትኩረት የሳቡ ቦታዎች የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ቦታዎች ናቸው፡፡

እነዚህ ሁለት ቦታዎች ከላፍቶ ሞል ፊት ለፊት 2,100 ካሬ ሜትር እና 1,800 ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸው ቦታዎች ለጨረታ ቀርበው ነበር፡፡ በጉብኝት ወቅት እነዚህ ቦታዎች እንዳይታዩ ሲደረግ መቆየቱንና የጨረታ መክፈቻ ጊዜ ሲቃረብ ቦታዎቹ እንዲሰረዙ መደረጉ መነጋሪያ ሆኗል፡፡

ቦታው ለንግድና ኢንቨስትመንት ሥራ አመቺ በመሆናቸው የበርካቶችን ትኩረት የሳቡ ሲሆን፣ የከተማው መሬት ባንክ ቦታዎቹ ለሽያጭ መቅረብ ይችላሉ በማለት ለገበያ ቢያቀርብም፣ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ከጨረታ ዝርዝር ውስጥ ተሰርዘዋል፡፡

በ15ኛው ሊዝ ጨረታ በአቃቂ ቃሊቲ 70፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ 44፣ በአዲስ ከተማ አራትና በኮልፌ ቀራኒዮ በርካታ ቦታዎች ለጨረታ ቀርበዋል፡፡ ጨረታው ከሐምሌ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ ባህልና ቴአትር አዳራሽ ይከፈታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

የኦባማ የኢትዮጵያ ጉዞ ለጨቋኞች ጥንካሬ ሰጪ ወይስ ነጻነትን ለሚሻዉ ህዝብ መፍትሔ አምጪ? –ወቅታዊ ፕሮግራም በሳዲቅ አህመድ (Audio)

$
0
0

የኢትዮጵያዉያን አይኖች በኦባማ ቃልኪዳኖች
የኦባማ የኢትዮጵያ ጉዞ ለጨቋኞች ጥንካሬ ሰጪ ወይስ ነጻነትን ለሚሻዉ ህዝብ መፍትሔ አምጪ?

ወቅታዊ ፕሮግራም በሳዲቅ አህመድ

Sadik Ahemed Journalist

ፍርድ ቤቱ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አቶ አንዳርጋቸውን እንዲያቀርብ ቀጠሮ ሰጠ

$
0
0

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

Andargachew Tsige.jpg2አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ድረስ ለተጠቀሱት ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ የወሰነው የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በምስክርነት እንዲያቀርብ ለሀምሌ 29/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጠ፡፡

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሀምሌ 13/2007 ዓ.ም ልደታ ፍርድ ቤት ቀርበው የመከላከያ ምስክር እንዲሆኑ ፍርድ ቤቱ ወስኖ የነበር ቢሆንም ይገኙበታል ለሚባሉት ማረሚያ ቤቶች በተለይም ለቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚላከው ማዘዣ ዘግይቶ በመላኩ እንዳልደረሰለት ገልጾ ለዛሬ ሀምሌ 15/2007 ለምስክርነት እንዲቀርቡ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር፡፡ ሆኖም አቶ አንዳርጋቸው ዛሬም ሳይቀርቡ ቀርተዋል፡፡
አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ለምን እንዳላቀረበ የተጠየቀው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ማዘዣው እንደደረሰው ገልጾ ነገር ግን ማዘዣው ለቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተብሎ መፃፍ ሲገባው ለአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ተብሎ በመፃፉ አቶ አንዳርጋቸውን ማቅረብ እንዳልቻለ ገልጾአል፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ማዘዣው ለቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተብሎ ተፅፎ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሀምሌ 29/2007 ለመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡
በእነ ዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ከተከሰሱት 10 ግለሰቦች መካከል ከአቶ አንዳርጋቸው ጋር ተገናኝታችኋል የሚል ክስ የቀረበባቸውና አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በመከላከያ ምስክርነት እንዲመሰክሩላቸው የጠሩት አቶ አሸናፊ አካሉ፣ አቶ ደህናሁን ቤዛ፣ አቶ ማንዴላ ጥላሁን፣ አቶ አንሙት የኔዋስና አቶ አሰፋ ደሳለኝ ናቸው፡፡

አንዳርጋቸው በተልካሻ ምክንያት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ * እንደገና ሐምሌ 29/2007 ዓ.ም እንዲቀርቡ ታዘዘ

$
0
0

andargachew Tisge
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ድረስ ለተጠቀሱት ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ የወሰነው የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በምስክርነት እንዲያቀርብ ለሀምሌ 29/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጠ፡፡
አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሀምሌ 13/2007 ዓ.ም ልደታ ፍርድ ቤት ቀርበው የመከላከያ ምስክር እንዲሆኑ ፍርድ ቤቱ ወስኖ የነበር ቢሆንም ይገኙበታል ለሚባሉት ማረሚያ ቤቶች በተለይም ለቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚላከው ማዘዣ ዘግይቶ በመላኩ እንዳልደረሰለት ገልጾ ለዛሬ ሀምሌ 15/2007 ለምስክርነት እንዲቀርቡ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር፡፡ ሆኖም አቶ አንዳርጋቸው ዛሬም ሳይቀርቡ ቀርተዋል፡፡

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ለምን እንዳላቀረበ የተጠየቀው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ማዘዣው እንደደረሰው ገልጾ ነገር ግን ማዘዣው ለቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተብሎ መፃፍ ሲገባው ለአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ተብሎ በመፃፉ አቶ አንዳርጋቸውን ማቅረብ እንዳልቻለ ገልጾአል፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ማዘዣው ለቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተብሎ ተፅፎ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሀምሌ 29/2007 ለመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡
በእነ ዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ከተከሰሱት 10 ግለሰቦች መካከል ከአቶ አንዳርጋቸው ጋር ተገናኝታችኋል የሚል ክስ የቀረበባቸውና አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በመከላከያ ምስክርነት እንዲመሰክሩላቸው የጠሩት አቶ አሸናፊ አካሉ፣ አቶ ደህናሁን ቤዛ፣ አቶ ማንዴላ ጥላሁን፣ አቶ አንሙት የኔዋስና አቶ አሰፋ ደሳለኝ ናቸው፡፡

የመጥረቢያው እጀታዎች –ከተማ ዋቅጅራ

$
0
0

Ketemaፍቅር በምትባል አገር ውስጥ አንድ ሽፍታ ይኖራል። ሽፍታው በየግዜው እየዘረፈ እና እየገደለ አስቸገረ። ዛሬ እዚኛው መንደር ከገደለ ነገ እዛኛው መንደር ይገድላል ዛሬ እዚኛው መንደር ከዘረፈ ነገ እዛኛው መንደር ይዘርፋል። ዛሬ እዚህ መንደር እሳት ነገ እዛ መንደር እሳት  ሁሉም መንደር በየተራው የሽፍታው ጅራፍ ያላረፈበት የለም። የፍቅር ነዋሪዎችም ሽፍታው ከዛሬ ነገ ይለወጣል ሽፍታነቱንም ይተዋል ወደ ፍቅር  ኑሮ ይመለሳል በሚል ተስፋ ቢጠበቅም ይባሱኑ ሽፍታነቱ ብሶበታል። በጥባጭ ካለ ጥሩ ጠላ አይጠጣም እንደሚባለው ሁሉ ህዝቡ በፍቅር አገሩ መኖር እስከሚያስጠላው ተበጠበጠ ዛሬ እዚህ መንደር ነጋ እዛ መንደር አዘን ነው እንደ ክረምት እና በጋ አዘን ገባ አዘን መጣ መባባል ከተጀመረ በፍቅር አገር ሰነበተ። ገዳይ ካለ ሟች እንዳለ የተረዳው የፍቅር ነዋሪዎች በመሰባሰብ ተማከሩ ለሁሉም ነዋሪ መልዕክት አስተላልፈው ምክክር ያዙ። እንዲህም በሚል፡-

ሽፍታ አገራችን ከገባ ሰንብቷል ዛሬ የኛን መንደር አምሶት ገድሎ  ከሄደ ሌላ ግዜ ሌላው መንደር እንደዚሁ ያደርጋል ሃዘን ያልገባበት መንደር ችግር ያላጋጠመው አካባቢ የለም የሚያደርሰው ጉዳት እየከፋ ስለመጣ በአገራችን ሃዘን እንዳይኖር ጥፋትም እንዳይከሰት ይህንን ሽፍታ  ማጥፋት አለብን ሽፍታው እስካልጠፋ  ድረስ ሃዘናችን እየጨመረ ጉዳታችንም እየከፋ ይመጣል እንጂ ሰላም አይኖረንም በሚል ተወያዩ። የተለያዩ  ሃሳቦች መንሸራሸር ጀመሩ።

ከአንዱ መንደር የመጣው ከመሃል ተነስቶ እንዲ አለ፡- ሽፍታው መሳሪያ  ታጥቋል ብዙ ሰራዊቶችም አሉት ነካክተነው መንደራችንን በሙሉ እንዳያጠፋው አሉ።

ከሌላ መንደር የመጣው አንዱ ከመሃል ተነስቶ እንዲ አለ ፡- አሁን መቼ እየኖርን ነውና አገሬው እየተገደለ መንደራችን እየታመሰች አይደል እንዴ? እሱ የታጠቀውን መሳሪያ እኛ የማንታጠቀው ምን ስለሆነ ነው? ትሰማለህ አሉ ወደ  አስተያየት ሰጪው ዞወር ብለው ቁጣ በተሞላበት አነጋገር በታሪክም ሆነ በእውነቱ ህዝብን ተዋግቶ  ያሸነፈ  ማንም የለም! ይልቅስ ሽፍታው እየገደለን እኛ እያለቀስን ከምንኖር ገዳያችንን በህብረት ተነስተን ገድለነው በሰላም መኖር አሉ። የሁሉም ሃሳብ በሚመስል ሁሉም የአዎንታ ስሜት አሳዩ።

ከሌላው መንደር የመጣውም ተነስቶ እንዲ አለ፡-ለሽፍታው ጉልበት የሆነው እኛው የምንመግበው እኛ የምናጠጣው እኛ የምንሞተውም እኛ እሱ ምን ያድርግ የፈለገውን አንስቶ ሲወስድ ዝም የፈለገወን ገድለ ዘርፎ ሲወስድ ዝም የፈለገውን ሲያስር የፈለገውንም ሲፈታ ዝም ታዲያ  ምን ያድርግ በአገሩ ወንድ የሌለ መሰለው ወንድ እራሱ ብቻ እንደሆነ አድርጎ እየተዘዋወረ ይጨርሰን እንጂ…. እንግዲህ ባገራችን በፍቅር ለመሮር የሁሉም መንደር ሽፍታውን ላለመመገብ ውሃም ላለማጠጣት ሊገድለን ሲመጣ  ሽፍውን በመግደል ሞት ሽፍታ መንደር እንደሚገባ ማሳየት አለብን አሉ።

ከሌላ መንደር የመጣውም ሌላኛው ተነስቶ  እንዲህ አለ፡- መጥረቢያ  የተባለች አንዲት ትንሽ ብረት ዛፎቻችንን ጨፍጭፋ  ጨረሰች  ስለዚህ ለፍርድ ትቅረብልን ብለው ዛፎች ሁሉ ሰልፍ ወጡ እናም መጥረቢያ  ለፍርድ ቀረበች ዳኛውም ስለምንድን ነው ዛፎችን የምትጨፈጭፊው ብለው ጠየቋት መጥረቢያም ስትመልስ መቼ እኔ ሆንኩኝና የምጨፈጭፋቸው ከነርሱ መሃል ጠማማ እንጨት እጀታ ሆናኝ ነው እንጂ እኔ መቼ ሃይል አለኝ አለች ይባላል። ለሽፍታው ሃይል ሆነው ህዝባችንን የምናስጨርስ ከኛ መሃል እጅ የሆኑት አሉና ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ ወደ ፍቅር አገራቸው ሳይመሽባቸው እንዲቀላቀሉ እንጠይቃለን አለበለዛ  ግን ሽፍታው በሚጠፋበት ግዜ እነሱም አብረው እንደሚጠፉ ማወቅ አለባቸው ፍቅር ወደ ቤቷ እንድትመለስ ሰላም ወደ መንደራችን እንዲገባ ለሽፍታው እጀታ የሆናችሁ በሙሉ ስለእውነት፣ ስለ ሰላም፣ ስለነጻነት፣ ከህዝቡ ጎን እንድትሆኑ ጥሪያችን ነው አሉ። የዚህን ግዜ  የተሰበሰበው ህዝብ በሙሉ በጭብጨባ  አጀባቸው። ለሽፍታ  እጅ በመሆን ወገኑን የሚያስጨፈጭፍ  እና በደልን የሚያደርስ ሁሉ ቆም ብሎ  የሚያስብበት ግዜ ነው። ሽፍታው በሚያዝበት ግዜ እና በሚጠየቅበት ግዜ መቼ እኔ ሃይል ነበረኝ ከእናንተ  ውስጥ የበቀሉ ጠማማ ሰዎች እጅ ሃይል ሆነውኝ ገደልኩኝ እንጂ ብሎ እንዳይመሰክርብን የሽፍታ አገልጋይ ከመሆን ወጥተን ወደ ፍቅር አገራችን እንቀላቀል። ያኔም ገዳዩን በመግደል ሞት ባገራችን እንዳይኖር እናደርጋለን። የሞት ንጉስ እስከመጨረሻው ተገርሰስ፡ የፍቅር ንጉስ ባገራችን ንገስ ብለን ፍቅርን እናነግሳለን።

ከተማ ዋቅጅራ

23.07.2015

Email- waqjirak@yahoo.com

ሰበር መረጃ – ከውስጥ ታጋይ አርበኞች የተላከ መረጃ

$
0
0
(Photo File)

(Photo File)

“ሰሞኑን ከተው የከረሙት የህወዓት ባለስልጣናት የተስማሙበት እና ለፓርላማ ውይይት እንዲቀርብ የደረሱበት ውሳኔ-

አገሪቷ የተቃጣባትን ጥቃት ለመከላከል እራስን የመከላከል ካውንተር ኦፌንሲቭ እርምጃ መውሰድ አለብን፥፥ ይህ እርምጃ የ አለም አቀፍ ስምምነቶችን ከግንዛቤ ያስገባ እና ወዳጅ አገሮቻችን ለምናደርገው እራስን የመከላከል እርምጃ ድጋፋቸው እንዳይለየን በ አገራችን እና ህዝባችን ሰላም ላይ ያነጣጠረ የስጋት ድባብ ማየሉን በመረጃ አስደግፈን ለ አለም የጸጥታው ምክርቤት ፥ ለኢጋድ እና መሰል ድርጅቶች እና አጋር አገሮች ደብዳቤ ሰርኩሌት በማድረግ ህጋዊነታችንን ማረጋገጥ አለብን፥፥

ይህ የምናደርገው ሁለገብ ካወንተር ኦፌንሲቭ ለ አንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ሰላማችንን እና ልማታችንን የሚያደናቅፉ የጥፋት ሃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን፥፥ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ለህዝባችን እና ለ አለም ህዝብ በተለይ ደግሞ ለ ወዳጅ አገሮች ይህ ጦርነት ወደን ሳይሆን ተገደን የምንገባበት መሆኑን ከፈተኛ የሆነ የፕሮፓጋንዳ እና የዲፕሎማሲ ስራወችን መስራት ይጠበቅብናል:: የተቃጣብን ትንኮሳ በተለይ በ አሁኑ ወቅት አገራችን በ አልሻባብ እስላማዊ አክራሪ ቡድን ላይ የተቃጣብንን ዳግም ትንኮሳ በመመከት ላይ እያለን መሆኑ የ አለም ህዝብ እንዲገነዘብልን መስራት አለብን፥፥

ይህን ወቅታዊ ችግራችንን አይተው ለመጠቀም ያሰፈሰፉ አሸባሪወችን ለመከላከል በምናደርገው ሁለገብ እራስን የመከላልከል እርምጃ በተለይ የሱዳን ህዝብና መንግስት ከጎናችን እንዲቆም ጥሪ ማቅረብ አለብን:: ደህንነት እና መከላከያ በጋራ በመሆን አስቸኳይ ካወንተር ኦፌንሲቭ ኮምፕረኽንሲቭ እቅድ መንደፍ እንዳለባቸው በማሳሰብ ይህንን የሚመራ ጊዜያዊ ቡድን ተመርጧል፥፥”


አርበኞች ግንቦት 7 አርማጭሆ ሌድሆ ማርያም ቀበሌ ባሂድባ ላይ የሕወሓት ሽምቅ ታጣቂዎችን ረፈረፍኩ አለ * የሕወሓት መንግስት የአርማጭሆ ገበሬን አርበኞች ግንቦት 7ትን ትረዳላችሁ በሚል እያሰቃየ ነው ተባለ

$
0
0

* የሕወሓት መንግስት የአርማጭሆ ገበሬን አርበኞች ግንቦት 7ትን ትረዳላችሁ በሚል እያሰቃየ ነው ተባለ
* የሱዳን መከላከያ ሀይልና ህወሓት መራሹ ጦር ድንበር ላይ ተፋጠው እንደሚገኙ ተዘገቧል
* አርማጭሆ ማሂን አቦ ተነስቶ ወደ ጦርነቱ ይጓዝ በነበረው የፌደራል ፖሊስ ስራዊት ተመታ
* ሱዳን ከአሴራ እስከ ገላባት እንዲሁም ቲሃን ጨምሮ በሺህዎች የሚቆጠር ከባድ መሳሪያ ሳይቀር የታጠቀ ጦር አስፍራለች፡፡

(Photo File)

(Photo File)

ከአርበኞች ግንቦት 7 ሕዝብ ግንኙነት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ:-

የአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች የህወሓት ፀረ ሽምቅ የተባለ ታጣቂ ሀይል ላይ አርማጭሆ ሌድሆ ማርያም ቀበሌ ባሂድባ ላይ ረፈረፉት፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞችና የህወሓት ፀረ ሽምቅ ሀይል ከባድ ወጊያ ያደረጉት ሐምሌ 13 2007 ዓ.ም ከጥዋቱ 3-4 ስዓት ሲሆን ቁጥራቸው ያልታወቀ የፀረ ሽምቅ አባላት ተግድለዋል፡፡

በተጨማሪም ሌዳሆ ላይ በጥይት እየተቀጠቀጠ የሚገኘውን የፀረ ሽምቅ ሀይል ለማገዝ ከዚያው ላይ አርማጭሆ ማሂን አቦ ተነስቶ ወደ ጦርነቱ ይጓዝ በነበረው የፌደራል ፖሊስ ስራዊት ላይ ሌሎች የውስጥ አርበኞች አድፍጠው ተኩስ በመክፈት ከፍተኛ ጉዳት በማድርስ መንገድ ላይ አስቀርተውታል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የህወሓት የታጥቁ ኃይሎች ለአርበኞች ግንቦት 7 ስንቅ ታቀብላላችሁ በሚል በአርማጭሆ ገበሬ ላይ ጭፍጨፋ እየፈፀሙ መሆናቸው ታውቋል፡፡

የሱዳን መከላከያ ሀይልና ህወሓት መራሹ ጦር ድንበር ላይ ተፋጠው እንደሚገኙ ተዘገቧል፡፡

የሱዳን መከላከያ ሀይል በተደጋጋሚ የኢትዮጰያን ድንበር ጥሶ እየገባ በገበሬው ህዝብ ላይ ጥቃት ፈፅሞ መመለሱ ቆሽታቸውን ያሳረረው ለህዝብ የሚቆርቆሩ ጥቂት የህወሓት የመከላከያና የሚሊሻ ሰራዊት አባላት ያለአለቆቻቸው ትዕዛዝ ሐምሌ 10 2007 ዓ.ም ከስድስት የሚልቁ የሱዳን ወታደሮችን ትኩስው በመግደላቸው እና የሱዳን ንብረት የሆኑ ሁለት የእርሻ መኪኖች በማቃጠላቸው ነበር ግጭቱ የተቀስቀሰው፡፡

ግጭቱን ተከትሎ ሱዳን ጦሯን ከማህል ሀገር ወደ ኢትዮጰያ በማስጠጋት ላይ ትገኛለች፡፡ ከአሴራ እስከ ገላባት እንዲሁም ቲሃን ጨምሮ በሺህዎች የሚቆጠር ከባድ መሳሪያ ሳይቀር የታጠቀ ጦር አስፍራለች፡፡

ምንም እንኳን ህወሓት ጦሩን ወደ ሱዳን ድንበር ለማስጠጋት እየሞከረ የሚገኝ ቢሆንም ለህዝብ ተቆርቁረው በራሳቸው ተነሳሽነት በሱዳን ጦር ላይ እርምጃ የወሰዱትን የመከላከያና የሚሊሻ አባላት ለይቶ ለሱዳን አሳልፎ በመስጠት ወይንም ራሱ በመረሸን ጉንብስ ተዋርዶ በተለመደው መለማመጥና የአህያ ባልነቱ ሊቀጥል እንደሚችል ከወዲሁ ይገመታል፡፡

Sport: ጋሪ ኩክ –የማንችስትር ሲቲው አዳኝ

$
0
0

Garry Cook
የማንችስተር ሲቲን እጅግ ውጤታማ ጊዜ የሚዘክር ታሪክ በሚፃፍበት ወቅት ጋሪ ኩክ ጎላ ያለ ስፍራ ይኖራቸዋል፡፡ ሮቤርቶ ማንቺኒ፣ ሰርጂዮ አጉዌሮ፣ ያያ ቱሬ እና ማኑኤል ፔሌግሪኒን የመሳሰሉ ስሞችም የትርክቱ ዋነኛ ገፀ ባህሪያት መሆናቸው አይቀርም፡፡ ደግሞም ይገባቸዋል፡፡ ነገር ግን ሁሉም ሲቲ በቅርቡ ያሳካቸው ድሎች እውን የሆኑት እንዲሁም ወደ ፊት ሊያሳካቸው እየተንደረደረ ያለው ነገሮች የሚሳኩት ኩክ ክለቡን ከኪሳራ አፋፍ መልሶ ወደ ስኬት ጉዞ እንዲጀምር እና ከእግር ኳስ ሃያላን ጎራ እንዲቀላቀል ያስቻለውን ህልም ለሼህ ማንሱር በመሸጣቸው ነው፡፡

‹‹የማንችስተር ሲቲ አዳኝ እንደሆንኩ ተደርጎ እንዲወራ አልፈልግም›› ሲሉ በኤቲሃድ ባሳለፉት በውጣ ውረድ ተሞሉ ሶስት ዓመታት ለራሳቸውም ሆነ ለክለባቸው ዝቅ ያለ አመለካከት ባለመያዛቸው የሚታወቁት ግለሰብ ይናገራሉ፡፡ ሆኖም ግን ኩክ መታወስ ያለባቸው በዚያ መልኩ ነው፡፡
በ2008 የቀድሞው የናይኪ የማርኬቲንግ ሰራተኛ ለማንችስተር ሲቲ ደጋፊዎች ቡድናቸው ከመራራ ባላንጣቸው ማንቸስተር ዩናይትድ ብቻ ሳይሆን በተቀረው ዓለም ከሚገኙ ቡድኖች ሁሉ የበላይ ይሆናል ብለው ሲናገሩ ብዙዎች አላመኗቸውም ነበር፡፡

በ2011 በስህተት የላኩት የኢሜይል መልዕክት በካንሰር ህመም እየተሰቃየች ባለችው የኔዱም ኦኑሃ እናት ላይ የሚያፌዝ ሆኖ በመገኘቱ ሲቲ የኤፍኤ ካፑን ዋንጫ ካነሳ ከአራት ወራት በኋላ ራሳቸውን ከኃላፊነት አነሱ፡፡

ከትዳራቸው ያስቀደሙትን ስራ ሲያጡም ‹‹ልባቸው ደምቶ እና ቅስማቸው ተሰብሮ›› ክለቡን እንደለቀቁም ተናግረዋል፡፡ አሁንም ድረስ ግን በኤቲሃዱ ክለብ ባለስልጣናት ዘንድ ከፍተኛ ክብር አላቸው፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው በሚቀጥለው ሳምንት በቻምፒዮንስ ሊግ ሲቲ ከባርሴሎና ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ በምቹው የዳይሬክተሮች መቀመጫ ክፍል ተገኝተው እንዲከታተሉ መጋበዛቸው ነው፡፡ በዚያ ተቀምጠውም በሜይ 2008 ታክሲን ሺናዋትራ በናይኪ የነበራቸውን ኃላፊነት በመተው የሲቲ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ እንዲሆኑ ያቀረቡላቸውን ጥያቄ የተቀበሉበትን ወቅት ወደኋላ መለስ ብለው ማስታወሳቸው አይቀርም፡፡
በትውልድ ሀገራቸው በሰብአዊ መብት ጥሰት እና ማጭበርበር የሚከሰሱት የቀድሞው የታይላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸው እና በፕሪሚየር ሊጉ ያደረጉት ኢንቨስትመንት እያሳሰባቸው መሆኑን ለመረዳት ኩክ ጊዜ አልወሰደባቸውም፡፡ ‹‹ለሺናዋትራ ለክለቡ ገዢ ከማፈላለግ ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላቸው ለማሳወቅ ወደ 10 ቀናት ወስዶብኛል፡፡ ምክሬን ባይቀበሉ ኖሮ ሲቲን የሚጠብቀው ወደ መቀመቅ መውረድ ነበር፡፡ እውነት ለመናገር እጅግ በከፋ መጥፎ እና አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ነበርን፡፡ የቆምነው በገደል አፋፍ ላይ ነበር፡፡

‹‹ችግሩን ለመቅረፍ የተጓዝንበት መንገድ ዘላቂነት አልነበረውም፡፡ ለምሳሌ አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማስፈረም የሚረዳንን ገንዘብ ለማግኘት የቴሌቪዥን ስርጭት ሽያጭ ክፍያን ከጊዜው አስቀድመን እንሰበስብ ነበር፡፡ ይህ በራሱ ምን ያህል አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደነበርን ያሳያል፡፡ ከዚህም አለፈ እና ደግሞ የተጫዋቾችን ደመወዝ ለመክፈል ክለቡን ለሺናዋትራ አሳልፈው ከሸጡት የቀድሞው ሊቀመንበር ጆን ዋርድልን ገንዘብ መበደር ጀመርን፡፡

‹‹ሲቲ እንደ ክለብ ፀንቶ እንዲቆም ወሳኙን ሚና የተጫወቱት ጆን ነበሩ፡፡ በእርሳቸው ደግነት እና ልገሳ እየተደገፈም እንኳን ሲቲ ወደ አዘቅት ሊያመራ ከጫፍ ደርሶ ነበር፡፡ በመጨረሻም ተሳካልኝ እና ናኪን ለመልቀቅ ስወስን ለክለቡ የነበረኝን ህልም ለሼክ ማንሱር እና በእርሱ ስር ለሚሰሩ ሰዎች ለመሸጥ ቻልኩ፡፡
‹‹ትክክለኛ ማዕበል ነበር፡፡ ሲቲ እጅግ በከፋ ሁኔታ ውስጥ ነበር፡፡ አቡ ዳቢ ደግሞ በዓለም ያላትን ስም ለማሳደግ በፕሪሚየር ሊጉ ኢንቨስት ማድረግ ትፈልግ ነበር፡፡ ጥሩ ግጥምጥሞሽ ሆነ›› ሲሉ ሁኔታውን መለስ ብለው ያስታውሱታል፡፡

ከዚያን ጊዜ ወዲህም የአቡ ዳቢ ከበርቴዎች ከ1 ቢሊዮን ፓውንድ በላይ ለማፍሰስ ወደ ውድቀት እያመራ የነበረውን ክለብ ወደ ሃያልነት እየቀየሩ ነው፡፡ ሆኖም ኩክ ለዘመናት ሲቲን ሲፈታተነው በከረመው ችግር ላይ ገንዘብ ማፍሰስ ብቻውን መፍትሄ እንደማይሆን ተረድተዋል፡፡ ከክለቡ ጋር ከፍተኛ የሆነ መንፈሳዊ ቁርኝት ያላቸውን ሰዎች ልብ እና አዕምሮ መማረክ ወሳኝ መሆኑንም ይናገራሉ፡፡

‹‹ለአቡ ዳቢ ዩናይትድ ግሩፕ ያቀረብኩት ገለፃ አሁንም ድረስ በእጄ ይገኛል፡፡ አቡ ዳቢ ዩናትድ ግሩፕ እንደ አማራጭ የያዛቸው ሌሎች ሶስት ክለቦች ነበሩ፡፡ እኛ ግን ከሁሉም ተሽለን ተገኘን፡፡ ያቀረብነው ማንቸስተር የሚለውን ስም ይዘን ነው፡፡ ያለ ሀፍረት በግልፅ የምናደርገው ሀሳባችንን ከግብ ለማድረስ የባላንጣችን ማንቸስተር ዩናይትድን ዓለም አቀፍ ተቀባይነት እንደ መሳሪያ መጠቀማችንን ነው፡፡ ሲቲ የሚለውን ወደ ፊት በታም ሃያል የሚሆን ብራንድ እና የማስፋፊያ ስራ በሚያመች 800 ሺ ካሬ ሜትር ዙሪያውን የተከበበ ስታዲየም ባለቤት እንደሆነ ተናገርኩ፡፡

‹‹መልዕክቱን ያስተላለፍኩት ማንቸስተር ሲቲ ምን ያህል እምቅ አቅም እንዳለው መረዳት ለቻሉ ብልህ እና አስተዋይ ሰዎች ነበር፡፡ ህልሜ እውን ሊሆን እንደሚችል አውቀውት ነበር፡፡
‹‹የሚገርመው ለማሳመን የተቸገርኩት በክለቡ ሲያገለግሉ የከረሙ ሰዎችን እና ብዙሃኑን የሲቲ ታማኝ ደጋፊዎች ነበር፡፡ ወደ ማንቸስተር ሲቲ ደጋፊዎች ክለብ ሄጄ ማንቸስተርን ማሸነፍ እንደምንችል እና አንድ ቀን የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ እንደምናነሳ ነገርኳቸው፡፡ አያይዤም በቋሚነት በቻምፒዮንስ ሊጉ ተወዳዳሪ እንደምንሆን አሳወቅኳቸው፡፡ ሁሉም ግን የተመለከቱኝ እንደ እብድ ነበር፡፡

‹‹በክለቡ የሚሰሩ ደጋፊዎች በፕሪሚየር ሊጉ ሊያቆየን የሚችለውን 40 ነጥቦች መሰብሰባችንን ሲያውቁ በደስታ ይፍነከነኩ ነበር፡፡ የ35 ዓመታት ውድቀትን እልባት ልናበጅለት ተገደን ነበር፡፡ የቡድኑን ባህል እና አብዛኞቹን በቡድኑ ያሉ መሰረተ ልማት እንደ አዲስ መገንባት ነበረብን፡፡

‹‹መፍትሄውን ዝግመተ ለውጥ ሳይሆን አብዮት ነበር፡፡ አንዳንድ ሰዎችን በተናገርኳቸው ነገሮች እንዳስከፋኋቸው አውቃለሁ፡፡ መሰረታችንን ላለመልቀቅ ታግለናል፡፡ ምንም እንኳን አንዳንዱ የክለቡ ታሪክ ውድቀት ቢሆንም የክለቡን ታሪክ ጠብቀን ለማቆየት ታግለናል፡፡ መጥፎዎቹን አሮጌ ዘመናት ወደ ኋላ በመተው ከዜሮ መጀመር ነበረብን፡፡
‹‹የመጣሁት ከአሜሪካዊ ባህል ነው፡፡ ናይኪን ከመሰለ ታላቅ ካምፓኒ የተገኘሁ ነኝ፡፡ በዚያ በነበርኩበት ወቅት አንዲትም ቀን አዲዳስ ስለሚሰራው ነገር ተጨንቀን አናውቅም ነበርር፡ በመሆኑም ወደ ማንቸስተር ሲቲ ስመጣ እና የምንፎካከረው ማንቸስተር ዩናይትድን እንደሆነ ሲነግረኝ ለሰከንድ እንኳን በኦልድትራፎርድ ምን እንደሚሰራ ለማሰብ አልሞከርኩም፡፡ በቀጥታ ትኩረቴን ያደረግኩት በባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ ላይ ነው፡፡ ሌሎች ሰዎች ከማንቸስተር ዩናይትድ የበለጠ ቡድን እንሆን ይሆን እንዴ ብለው ሲነጋገሩ እኔ ግን የምፈልገው ከባርሴሎና እንድንበልጥ ነበር›› በማለት ለክለቡ የተመኙትን ከፍታ አሳውቀዋል፡፡

ኩክ በአሁኑ ወቅት የአልቲሜት ፋይቲንግ ቻምፒዮንሺፕ ምክትል ፕሬዝዳንት ናቸው፡፡ የተቋሙ አላማ ቅይጥ ማርሻል አርትን በአውሮፓ፣ መካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ ማስተዋወቅ ነው፡፡ በለንደን እና ላስ ቬጋስ ቤት እና ንብረት አላቸው፡፡ በሲቲ የነበራቸው ቆይታ የማይሽር ጠባሳ ጥሎባቸው ያለፈ ቢሆንም ቤቴ ብለው የሚተሩት ማንቸስተርን ነው፡፡

‹‹በሲቲ በሰራሁት ስራ እኮራለሁ፡፡ ስሜቴ የተጎዳ ቢሆንም እንደ ፕሮፌሽናል ሁኔታውን ከገመገምነው እኔ ዕድለኛ ነኝ፡፡ 24 ሰዓቱን በሙሉ የምኖረው ለስራዬ ነበርር፡ ስበላም፣ ስተኛም የማስበው ስለ ስራዬ ነበር፡፡

‹‹ከዚህ በፊት ስህተቶችን እፈፅም ነበር፡፡ የፈፀምኩት አንድ ትልቅ ጥፋት ግን ስራዬን እንዳጣ አስገደደኝ፡፡ መልቀቂያ ያስገባሁት ክለቡን ለማዋረድ ባለመፈለጌ ነው፡፡ ነገር ግን ልቤ ደምቶ እና ቅስሜ ተሰብሮ እንደነበር መሸሸግ አልፈልግም፡፡

‹‹ቤተሰቦቼ የሚገኙት ኦሬጎን ውስጥ ፖርትላንድ በሚባል ስፍራ ከማንቸስተር ትንሽ ወጣ ብሎ ፔሻዬር ውስጥ ነው፡፡ ምክንያቱም አካባቢውን የምወደው በፍቅር ነው፡፡ የሚፀፅተኝ ነገር ቢኖርም ማንቸስተር ሲቲ ታሪክ እንዲሰራ በመጠኑም ቢሆን እገዛ አድርጌያለሁ ብዬ አስባለሁ፡፡ እኛ የፈፀምነው ነገር ዳግመኛ ይደረጋል ብዬ አላስብም›› ሲሉ በሲቲ ያሳኩት ገድል የማይረሳ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

ለማንቸስተር ሲቲ ሃያል የእግር ኳስ ክለብ ሆኖ ብቅ ማለት የያያ ቱሬ አስተዋፅኦ የገዘፈ ነው፡፡ የቀድሞው ሲቲ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ጋሪ ኩክ በ2008 ሼክ ማንሱር ሲቲን መረከባቸውን ተከትሎ በበርካታ ተጨዋቾች ላይ ገንዘብ አፍስሰዋል፡፡ በዚያው ዓመት ብራዚላዊውን ሪቢንሆ በ32 ሚሊዮን ፓውንድ ወደ ሲቲ መቀላቀል የቻሉ ሲሆን በቀጣዩ ዓመት ደግሞ ካርሎስ ቴቪዝን አስፈርመዋል፡፡ ሆኖም ግን ኩክ ከፈፀሟቸው ዝውውሮች ሁሉ ያያ ቱሬን ያገኙበት ቀዳሚው እንደሆነ ያምናሉ፡፡ አይቮሪኮስታው ባርሳን የለቀቀው በሳምንት የሚያገኘውን 200 ሺ ፓውንድ ታሳቢ አድርጎ እንዳልሆነ ኩክ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ፡፡

‹‹ያያ ቱሬ በሲቲ የለውጥ ምክንያት ሆነ፡፡ ሮቢንሆን እና ካርሎስ ቴቪዝን ያስፈረምናቸው ሌሎች ተጨዋቾችን ወደ ክለቡ ለመማረክ በማሰብ እንደሆነ የብዙሃኑ እምነት ነው፡፡ እውነት ለመናገር ሁለቱም ተጨዋቾች ሲቲን የተቀላቀሉት ለሲቲ ከሚያበረክቱት ይልቅ የሚያገኙትን ታሳቢ አድርገው ነው፡፡

‹‹ያያ ግን የተለየ ነው፡፡ እንደመጣም ይህን ክለብ ታላቅ አደርገዋለሁ ሲል ተናገረ፡፡ እንዳለውም አደረገ፡፡ እርሱን ካስፈረመን በኋላ ታላላቅ ተጨዋቾች በሙሉ ሲቲን መቀላቀል የሚችሉበት ዕድል መኖሩን መመርመር ጀመሩ፡፡ ለምሳሌ ያያን ባናስፈርም ኖሮ ዴቪድ ሲልቫ ይመጣል ብዬ አላስብም፡፡ እርሱን ካስፈረምን በኋላ ሌሎቹ ተከታትለው መጡ››
ከአምስት ዓመት በፊት ሲቲ ከኤሲ ሚላን ካካን ለማዘዋወር ሙከራ አድርጎ ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡ የቀድሞው የሲቲ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ተጫዋቹ የዓለም ሪከርድ በሆነ 100 ሚሊዮን ፓውንድ ዋጋ ወደ ኢቲሃድ ሊያደርገው የነበረው ዝውውር ሳይሳካ መቅረቱ እንደፀፀተው እንደነገራቸው ተናግረዋል፡፡ በዚያው ክረምት ብራዚላዊው ለሪያል ማድሪድ ተሽጦ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ተመልሶ በሚላን በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡

ኩክ የዝውውሩን ሂደት በተቆጣጠሩበት መንገድ ወቀሳ ተሰንዝሮባቸዋል፡፡ ነገር ግን የሚላን ባለቤት እና የጣሊያን ጠ/ሚኒስትር የሆኑት ሲልቪዮ ቤርሉስኮኒ ፖለቲካዊ ትርፍ ለማግኘት ሲሉ ዝውውሩን አገዱት እንጂ ተጫዋቹን የማዘዋወሩ ሂደቱ ተጠናቅቆ እንደነበር የሚያመላክቱ ጠንካራ ማስረጃዎች አሉ፡፡
‹‹ሚላን ተጫዋቹን ለመሸጥ ተስማምቶ እንደነበር የሚያረጋግጥ ሰነድ አሁንም ድረስ በእጄ ይገኛል፡፡ እኔ እና ካካ የሲቲን ማሊያ ይዘን ከኋላችን ደግሞ የሚላኑ ቼፍ ኤግዚኪዩቲቭ አድሪያኖ ጋሊያ ቆመው የሚያሳይ ፎቶ አለኝ፡፡ ይህን ያህል ተጉዘን ነበርር፡ ችግሩ የተፈጠረው ካካን መሸጥ ምን ያህል ደጋፊውን ሊያስከፋ እንደሚችል መጀመሪያ ላይ ከግምት ባለማስገባታቸው ነው፡፡ ከተጫዋቹ አባት ጋር ስለ ቆይታው እና ጥቅማ ጥቅሞች ለመነጋገር ባመራሁበት ወቅት የሆነ ችግር እንዳለ ተገለጠልኝ፡፡ እጅግ የተጋነኑ ጥያቄዎችን ይጠይቁ ጀመር፡፡ ያንን ማሟላት የምንችልበት ዕድል ደግሞ አልነበረም፡፡ በወቅቱ የተፈጠረው ችግር ምን እንደሆነ መጠየቄን አስታውሳለሁ፡፡
‹‹ካካ በረንዳ ላይ ቆሞ የሚላንን ማሊያ ሲያውለበልብ በቴሌቪዥን ስመለከት ከዚያ የመንቀሳቀሻ ጊዜዬ መሆኑን አወቅኩ፡፡ የማስበው ቤርሎስኮኒ አጋጣሚውን ሊጠቀሙበት እንደፈለጉ ነው፡፡ ሚስተር ቤርሎስኮኒ ልምድ ያላቸው ፖለቲከኛ ናቸው፡፡ አጋጣሚውን ከሚላን ነዋሪዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማጠንከር እና የሆነ ፖለቲካዊ ትርፍ ለማግኘት የተጠቀሙበት ይመስለኛል፡፡

‹‹ሚላን ካካን ሊሸጥልን ተስማምቶ ነበር፡፡ የደጋፊውን ተቃውሞ ሲመለከት ቃሉን አጠፈ፡፡ ከጊዜ በኋላ ካካን በሮቢንሆ ሰርግ ላይ አግኝቼው ነበር፡፡ ለሲቲ ፈርሞ ቢሆን ኖሮ ደስተኛ ይሆን እንደነበር ነግሮናል፡፡ ዳግም ልናስፈርመው የምንችልበት ዕድል መኖር አለመኖሩን ሲጠይቀኝም መርከቢቷ ትታው እንደተጓዘች ነግሬዋለሁ፡፡ በቅርቡም እጅጉን እንደሚቆጭ ነግሮኛል›› ሲሉ በሲቲ የነበራቸውን ቆይታ መለስ ብለው የቃኙበትን ሀሳብ ያጠናቅቃሉ፡፡

ርዕዮት ዓለሙ ምስጋና አቀረበች

$
0
0

በእስር ቆይታዬ ወቅት ከጎኔ ለነበራችሁ ሁሉ
ርዕዮት አለሙ

የፕሬስ ነፃነትን በማፈንና የሰብአዊ መብትን በመርገጥ የሚታወቀው የኢህአዴግ መንግስት የፈፀመብኝን እስር በመቃወምና በማውገዝእንዲሁም ያለቅድመ ሁኔታ እፈታ ዘንድ በመጠየቅ ከጎኔ ለነበራችሁ በሙሉ ምስጋናዬን የማቀርበው በታላቅ ትህትናና አድናቆት ነው፡፡

ርዕዮት ዓለሙ ከእህቷ እስከዳር ዓለሙ ጋር ከ እስር ከተፈታች በኋላ

ርዕዮት ዓለሙ ከእህቷ እስከዳር ዓለሙ ጋር ከ እስር ከተፈታች በኋላ

በነዚያ የጨለማ ቀናት አብሮነታችሁ ያልተለየኝ አለምአቀፍና ሀገር አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡
ዩኔስኮ፣ አለምአቀፍ የሴቶች ሚዲያ ፋውንዴሽን፣ ሚዲያ ሌጋል ዲፈንስ ኢንሼቲቭ፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሂዩማን ራይትስዎች፣ ሲፒጄ፣ ፔን ኢንተርናሽናል፣ ዶሀ ፍሪደም ሴንተር፣ አርቲክል 19ንና ሌሎች ያልጠቀስኳችሁ በርካታ አለምአቀፍ ድርጅቶች ለጉዳዬ የሰጣችሁት ትኩረት በኢትዮጵያ ያለውን አምባገነን ስርዓት በማጋለጥ በኩል ትልቁን ድርሻ ተጫውቷልና ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርብላችኋለሁ፡፡

መፈታቴን እንደራሳቸው ጉዳይ ቆጥረው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እንደ ማርቲን ሽቢዬ፣ፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም፣ አና ጎሜዝ፣ ናኒ ጃንሰን፣ ክርስቲያን አማንፑርና ሌሎች ዘርዝሬ መጨረስ የማልችላቸው በርካታ ግለሰቦች ለጉዳዩ የነበራቸውን ጠንካራ መሰጠት አብዝቼ አደንቃለሁ፡፡

ምንም እንኳን በአስከፋ ሁኔታ ተገልዬ የቆየሁባቸውና ጤናዬ ተቃውሶ የነበረባቸው መጥፎ ጊዜያትን ያሳለፍኩ ቢሆንም ከእስር የወጣሁት ግን ሁኔታዎቹ ሞራሌን ሳይሰብሩትና ይልቁንም ለዲሞክራሲ በተለይ ደግሞ ለፕሬስ ነፃነት መከበር የምችለውን ሁሉ ለማድረግ የበለጠ ቁርጠኝነት ኖሮኝ ነው፡፡

በመሆኑም ለዲሞክራሲ ስለታገሉና ሀሳባቸውን ስለገለፁ ብቻ በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ካለምንም ጥፋታቸው ታስረው የሚሰቃዩ በጣም ብዙ አርበኞችና ጓዶች ከሀሳቤ አይለዩም ፡፡ ኢፍትሀዊነትን አምርራችሁ የምትጠሉ ኢትዮጵያዊያንም ሆናችሁ የሌላ ሀገራት ዜጎች ለነዚህ ሰዎች መፈታት ያላሳለሰ ጥረት ታደርጉ ዘንድ እጠይቃለሁ፡፡
በድጋሚ አመሰግናለሁ
ርዕዮት አለሙ

To all those who stood by me when I was in prison.
Reeyot Alemu

It is with great humility and appreciation that I convey my gratitude to all who protested and condemned my incarceration by the EPRDF Government which is known worldwide for trampling on freedom of the press and human rights, and demanded my unconditional release.

I would like to thank those international and local Medias for being with me in my darkest days.
Special thanks goes to UNSECO , IWMF, Media Legal Defense Initiative, Amnesty International, Human Rights Watch, CPJ, Pen International , Doha freedom center, Article 19 and countless organization whose championship of my incarceration helped expose the cross dictatorship prevailing in Ethiopia.

I am also very appreciative of the steadfast commitment shown by those individuals who made my release their case like Martin shibbye, Prof. Alemayehu G.mariam, Ana Gomez, Nani Jansen, Christian Amanpour and so many others.
Though the harsh conditions under which I was kept some times incommunicado, precipitated in the deterioration of my health, I came out morally unscathed and even more resolved to do everything within my power in the cause of democracy, particularly freedom of the press in my country.

My thoughts go out to my so many compatriots and compatriots and comrades who are suffering in Ethiopian jails for no reason other than expressing their views and advocating democracy. I urge all Ethiopians and all people who abhor injustice to work tirelessly for their release.
I thank you all again
Reeyot Alemu

”የምታስፈራው የታማኝ ኢትዬጲያ!” – ከኤርሚያስ ለገሰ

$
0
0

ባልጠበኩት ሁኔታ ሰሞኑን ፋታ ካጡ ግለሰቦች መደዳ ተሰልፌያለሁ። ሳይቸግረኝ ” የኢትዬጲያ አየር ሀይል” ከሚባል የታሪክ ባህር ውስጥ ገብቼ እየዳከርኩ ነው። በየቀኑ በበርሜል እየጠጣሁ እንኳን ልረካ አልቻልኩም። ርግጥም የኢትዬጲያ አየር ሀይል ከጥግ እስከ ጥግ ሊቀዘፍ የማይችል ባህር ነው። መስመጥ ያልፈለገ እንዲጀምረው አይመከርም!!…እንደ ታማኝ በየነ እንባውን ባደባባይ አፍሶ መጠነኛ ትንፋሽ መውሰድ ካልተቻለ በስተቀር።

tamagn
ስለ ኢትዬጲያ አየር ሀይል በዝርዝር ለማወቅ የገፋፉኝ ምክንያቶች በርካታ ናቸው። የመጀመሪያው አለማወቄን ማወቄ ነው። በተለይም ከታማኝ ጋር በነበረኝ ተደጋጋሚ ጉዞዎች ስለ ቀድሞው መከላከያ ሰራዊት ( ምድር ሀይል፣ አየር ሀይል፣ ባህር ሀይል…ወዘተ) ያለው ተዝቆ የማያልቅ መረጃ እራሴን እንድፈትሽ አግዞኛል። ታማኝ ስለ ኮንጐ ዘማች ኢትዬጲያውያን ገድል በመረጃ ተደግፎ ሲናገር አፍ ያስከፍታል። እነዚህ መረጃዎች ምን አልባት የአሜሪካው ኮንግረስ ላይብረሪ ይገኙ ይሆናል እንጂ፣ ኢትዬጲያ ( ያውም በታቀደ ሁኔታ ታሪክ በሚወድምበት ዘመን) ለማግኘት የሚቻሉ አይደለም። የኢትዬጲያ መከላከያ ሰራዊት ጦር መሳሪያ እስከ አፍንጫው የታጠቀውን የዚያድባሬ ጦር አሳፍሮ ለመመለስ ያደረገውን ተጋድሎ በቪዲዬና ኦዲዬ አስደግፎ ሲያቀርብ መመልከት ከእግር እስከ ጥፍር ይነዝራል። ስለ ጀነራል ፋንታ፣ ጀነራል ለገሰ፣ ኮረኔል በዛብህ ጴጥሮስ የጦር ሜዳ ጀብዱ ሲተርክ ለሰማ ሰው ” የታማኝን ኢትዬጲያ” ለመረዳት ጊዜ አይወስድበትም። 

በነገራችን ላይ ዛሬ ይህቺን አጭር ማስታወሻ በውድቅት ለሊት እንድጵፍ የገፋፋኝ ከአንድ ወዳጄ ጋር ያደረግነው ጨዋታ ነው። ለወዳጄ ሰሞኑን ስለተጠመድኩበት የቀድሞው የኢትዬጲያ አየር ሀይል ታሪክ በተመስጦ ሳጫውተው ከአፌ ተቀብሎ፣
” በል እንደ ታማኝ እንባህን እንዳትዘራ!” አለኝ።
እኔም ” እውነትን መርምሮ ማወቅ ከእንባ በላይ ያስኬዳል!” አልኩት።
ወዳጄ እንደመቀለድ እያለ፣
” የአንዳንዶች በተለይም እንደ ታማኝ ያላችሁ ሰዎች የምታስቧት ኢትዬጲያ ታስፈራለች!” አለኝ።ይህንን ቃል ከሌላም ሰው ሰምቼው ስለነበረ ብዙም አልገረመኝም። ለምላሹም ማሰብ አልጠየቀኝም። በአጭሩ፣
” እውነትህን ነው ወዳጄ በጣም ታስፈራለች ” አልኩት። ለምን እንደምታስፈራም እንዲህ በማለት በአጭሩ ነገርኩት፣

የታማኝ ኢትዬጲያ መሰረቷ ” በኢትዬጲያ አምላክ ይዣችኃለሁ እንዳትሸሹ!” የሚለው የጀነራል ፋንታ በላይ ተማጵኖ ያቆያት በመሆኑ ታስፈራለች!…የታማኝ ኢትዬጲያ በአየር ላይ እንደ ንስር አሞራ እየተገለባበጠ በአንድ ጊዜ አራት የሱማሊያ ተዋጊ አውሮፕላኖችን ከጥቅም ውጪ ያደረገው ጀነራል ለገሰ ሀገር በመሆኗ ታስፈራለች!…የታማኝ ኢትዬጲያ የአዶልፍ ፓርለሳክ እውነተኛ ታሪክ የሆነውን ” የአበሻ ጀብዱ” መጵሀፍ ውስጥ የአቢቹን ገድል የያዘች ስለሆነ ታስፈራለች!…የታማኝ ኢትዬጲያ ” የህውሀት ማኒፌስቶ” ፣ ” የኤርትራ ህዝብ ትግል ከየት ወዴት!” የሚለውን የህውሀት ውስጠ ሚስጥር ተገንዝባ ያለሞሞዳሞድ አምርራ የምትታገል በመሆኗ ታስፈራለች!!…የታማኝ ኢትዬጲያ ገዥዎች ባንዲራ ጨርቅ ነው ባሉ ማግስት በመቶሺዎችን በመስቀል አደባባይ ሰብስባ ” ባንዲራችን የአባቶቻችን ደምና አጥንት ነው! ” በማለት የምትናገር በመሆኗ ታስፈራለች!…የታማኝ ኢትዬጲያ የስልጣን እና የሀብት ክፍፍል ፍትሀዊ እንዳልሆነ በመረጃ ላይ ተደግፋ የምታጋልጥ፣ ” ይሄ ነወይ ፌደራሊዝም?” ብላ የምትጠይቅ በመሆኗ ታስፈራለች!!…ወዘተ።
( የጀነራል ለገሰ ተፈራን ቪዲዬ፣ የአበሻ ጀብዱ መጱሀፍ፣ የህውሀት ማኒፌስቶ/ ኦርጅናል/፣ ” የኤርትራ ህዝብ ትግል ከየት ወዴት” የሚለውን መጵሀፍ ራሱ ታመኝ እንዳነብ የሰጠኝ መሆኑን ከምስጋና ጋር መጥቀስ እፈልጋለሁ!”)

በአፋር ክልል በኤርትራ ድምበር አካባቢ የህወሓት መከላከያ ሰራዊት ህዝብን ከቀዬው እያፈናቀለ በስጋት እና በፍርሃት ቆሟል

$
0
0

* ምናልባት ሰሞኑን የአርበኞች ግንቦት 7 በወያኔ ስርዓት ላይ ያወጀው ጦርነት ከህዝብ ለመደበቅ ሲባል የሚወስዱት እርምጃ ይሆን?
* ሴቶችን አስገድዶ ከመድፈር ባለፈ በአፋር ህዝብ አኗኗር የተለመደ ከሆነው ከቦታ ወደ ቦታ እየተንቀሳቀሱ እንስሶቻቸውን የመመገብ ነፃነታቸው ላይ ገደብ ተጥሏል
* ቁጥራቸው 5 የሚሆኑ ሴቶች በተለያየ ርቀት ፍየሎቻቸውን እየጠበቁ በነበረ ሰአት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ድብደባ ደረሰባቸው

Photo File

Photo File

አኩ ኢብን ከአፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው

በኢትዮጵያ አፋር ክልል የዔሊ ዳዓር ወረዳ ከኤርትራ ጋር ድምር ናት። በዔሊ ዳዓር ወረዳ ቡሬ ላይ ትልቅ የመከላከያ ሰራዊት ካሞፕ ይገኛል። በዚህ ካምፕ የሚገኙ የመላከያ ሰራዊት አባላት በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ የተለያዩ ጥቃቶች እያደረሱ ቆይቷል። ለምሳሌ ሴቶችን አስገድዶ ከመድፈር ባለፈ በአፋር ህዝብ አኗኗር የተለመደ ከሆነው ከቦታ ወደ ቦታ እየተንቀሳቀሱ እንስሶቻቸውን የመመገብ ነፃነታቸው ላይ ገደብ ተጥሏል። አሁን ደግሞ ሰሞኑን ከምንጊዜም በባሰ ሁኔታ መከላከያ ሰራዊቱ ህዝብን መውጫና መግቢያ አሳጥቷል። በትናንናው ዕለት በዔሊ ዳዓር ወረዳ በዓድገኖ እና በታሙክሌ ቀበሌ አካባቢዎች ህዝብ እንደ ነፃ ነዋሪ መንቀሳቀስ እንዳልቻለ ለምንጮቻችን ተናገሯል።
«እኛ ስንኖርበት የነበረው ቀዬችን የመከላከያ ሰራዊት አዲስ ካምፕ ሆነ። እኛ ከዛ በአሰቸኳይ እንድንነሳ ተነገረን፣ እኛ የምንኖረው በግብርና ስለሆነ ለእንስሶች ውኃ በቀላሉ ማግኘት አንችልም። ለውኃ ስንጠቀምበት ወደነበረው አካባቢዎች ድርሽ እንዳንል ተከልክለናል። ሴቶቻችን ይደፈሩብናል፣ ይደበደቡብናል፣ ወጣቶች ይታሰሩብናል፣ ከብቶች እና ፍየሎች በማን አለብኝነት ይዘርፉብናል ምንስ ያልደረሰብን በደል አለ?» ይላሉ የአካባቢው ነዋሪዎች።

በተለይ ትናንት በአካባቢው ቁጥራቸው 5 የሚሆኑ ሴቶች በተለያየ ርቀት ፍየሎቻቸውን እየጠበቁ በነበረ ሰአት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከዚህ በፊት አስጠንቅቋቸው እንደነበረ በመናገር ባደረሱባቸው ከፍተኛ ደብደባ እና የተወሰኑ ሰዓታት እስራት ሴቶች ላይ ከደረሰው የአካል ጉዳት ባለፈ ፍየሎቻቸው ጠፍቶባቸዋል። በእርግጥ በዔሊ ዳዓር በቡሬ አካባቢ ይሄ ነገር የተለመደ ቢሆንም የሰሞኑን ነገር ለየት የሚያድረገው የመከላከያ ሰራዊቱ በአዳዲስ ቦታዎች ህዝብን ማሸበር መጀመራቸው ነው።
ምናልባት ሰሞኑን የአርበኞች ግንቦት 7 በወያኔ ስርዓት ላይ ያወጀው ጦርነት ከህዝብ ለመደበቅ ሲባል የሚወስዱት እርምጃ ይሆን?

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live