Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

Health: የመገጣጠሚያ ሕመም – Arthritis

$
0
0

arthritis
(በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም)

መገጣጠሚያዎ ላይ ሕመም ይሰማዎታል? ምን እንደሆነስ ያውቃሉ?

ይህ የመገጣጠሚያ ሕመም በአገራችን የብዙ ሰዎች ችግር እየሆነ መጥቷል፡፡
የመገጣጠሚያ ሕመም በሕክምናው ቋንቋ አርተራይተስ (Arthritis) የምንለው ሲሆን የሚከሰትባቸው ምክንያቶች ደግሞ የተለያዩ ናቸው፡፡

የተለመደው የሕመም ዓይነት በዕድሜ ወይንም በኢንፌክሽን ምክንያት የሚከሰተው የመገጣጠሚያ ሕመም ሲሆን ሌሎች የመገጣጠሚያ ሕመም ዓይነቶችም በሰውነታችን በሚከሰቱ አለርጂ (Autoimmune Related) ምክንያት ያመጣሉ፡፡
እነዚህም፡-

• ሮማተቶይድ አርተራይተስ (Rheumatoid Arthritis )
• ሶሪያቲክ አርተራይተስ (Psoritic arthritis) በመባል ይታወቃሉ፡፡
የመገጣጠሚያ ሕመም ያላቸው ሰዎች በተጠቃው መገጣጠሚያ ላይ ከፍተኛ የሕመም ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ ይህም የሚሆነው በመገጣጠሚያው አካባቢ ባሉ ጡንቻዎች መቆጣት ምክንያት ነው፡፡
የመገጣጠሚያ ሕመም ምልክቶች
በኢንፌክሽን ምክንያት የሚከሰትን የመገጣጠሚያ ሕመም ምልክቶች
• ትኩሳት
• ብርድ ብርድ ማለት
• የመገጣጠሚያ ላይ ሕመም (ውጋት)
በአለርጂ ምክንያት የሚከሰት የመገጣጠሚያ ሕመም
• የመገጣጠሚያ ላይ ሕመም ከእብጠት ጋር
• በጣት፤በእጅ እና በእግር መገጣጠሚያዎች ላይ
• ሕመሙ በድንገት የሚከሰትና ምክንያቱ ያልታወቀ ከሆነ
• ሕመሙ ከትኩሳት ጋር የተያያዘ ከሆነ
• ከፍተኛ ሕመምና መገጣጠሚያ አካባቢ ላይ መውላት ካለ በአፋጣኝ ወደ ሕክምና
ማዕከል መሄድ አስፈላጊ ነው፡፡
ሕመምዎን ለማስታገስ
– አቀማመጥዎን መቀያየር
– በአንድ መገጣጠሚያ ላይ ብቻ ጫና አለማብዛት
– በየግማሽ ሰዓት ተነስቶ መራመድ
ከዚህ በተጨማሪ
– ክብደትዎን ማስተካከል
– ሲጋራ የሚያጤሱ ከሆነ ማቆም
– ቀላል እንቅስቃሴን ማድረግ የመገጣጠሚያ ሕመም እንዲቀንስ ያደርጋል
የመገጣጠሚያ ሕመም ካለብዎ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ነገሮች ባያደርጉ ይመከራል
– መሮጥ
– መዝለል
– ከፍተኛ ጉልበት የሚጠይቅ አካል ብቃት እንቅስቃሴ
የመገጣጠሚያ ሕምዎን በተመለከተ ከሐኪምዎ ጋር መመካከር እና ያለብዎትን የመገጣጠሚያ ሕመም ዓይነት ማወቅ አስፈላጊ መሆኑን መዘንጋት የለቦትም፡፡
ጤና ይስጥልኝ

Arthritis is a common condition that causes pain and inflammation in a joint.

Types of arthritis
The two most common types of arthritis are osteoarthritis and rheumatoid arthritis.

Osteoarthritis

Osteoarthritis initially affects the smooth cartilage lining of the joint. This makes movement more difficult than usual, leading to pain and stiffness.

The cartilage lining of the joint can then thin and tissues within the joint can become more active. This can then lead to swelling and the formation of bony spurs, called osteophytes. In osteoarthritis, the cartilage (connective tissue) between the bones gradually erodes, causing bone in the joints to rub together. The joints that are most commonly affected are those in the hands, spine, knees and hips.

Symptoms of arthritis

The symptoms of arthritis you experience will vary depending on the type you have.
This is why it’s important to have an accurate diagnosis if you have:

joint pain, tenderness and stiffness
inflammation in and around the joints
restricted movement of the joints
warm, red skin over the affected joint
weakness and muscle wasting
When to seek medical advice
You should see your GP if you have persistent symptoms of osteoarthritis so they can try to identify the cause.
To help determine whether you have osteoarthritis, your GP will ask you about your symptoms and examine your joints.

via NHS

The post Health: የመገጣጠሚያ ሕመም – Arthritis appeared first on Zehabesha Amharic.


የ23ኛ ክፍለጦር፤ 1ኛ ሬጅመንት የፋይናንስ ሰራተኞች ገንዘብ እየያዙ በመጥፋት ላይ ናቸው

$
0
0

የደህሚት ድምጽ እንደዘገበው በኢህአዴግ ስርዓት የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ እምነት ያጡ የ23ኛ ክፍለጦር፤ 1ኛ ሬጅመንት የፋይናንስ ሰራተኞች ገንዘብ እየያዙ በመጥፋት ላይ እንደሚገኙ ተገለፀ።
defense minster ethiopia
በማዕከላዊ እዝ የ23ኛ ክፍለ ጦር አባላት ለበዓል ማክበሪያ እየተባለ ከነፍስ ወከፍ ወታደር 87 ብር ያለፍላጎታቸው እንደተቆረጠባቸው የገለጸው መረጃው ሃምሳ አለቃ ብርሃኑ የተባለ የአንደኛ ሬጅመንት የፋይናንስ ሓላፊ ሃላፊነቱን ተጠቅሞ የፋይናንስ ካዝና በመክፈት የሬጅመንቱን አምሳ ሁለት ሽህ አምስት መቶ (52,500) ብር ገንዘብ ይዞ ከዝባን ገደና ተነስቶ ከሽራሮ ከተማ በመኪና ተሳፍሮ ለማምለጥ ሲሞክር እንደተያዘ ለማወቅ ተችሏል።

በእዙ ውስጥ የሚገኙ የሰራዊት አመራሮች በየወቅቱ ምክንያቶችን እየፈጠሩ የሰራዊቱን ደመወዝ በመቁረጥ ለግል ፍላጎታቸው ማሟያ እያዋሉት ስለሚገኙ እያንዳንዱ ወታደር ተቆራርጣ በእጁ ከምትደርሰው አነስተኛ ደመወዝ ቤተሰቡን ሊያግዝ ይቅርና ለራሱም መሆን እንዳልቻለ የደርሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል ሲል ደህሚት ድምጽ ዘግቧል::

The post የ23ኛ ክፍለጦር፤ 1ኛ ሬጅመንት የፋይናንስ ሰራተኞች ገንዘብ እየያዙ በመጥፋት ላይ ናቸው appeared first on Zehabesha Amharic.

ግብፅ፤ በምስራቅ ሊቢያ የሚገኘውን የአይ.ኤስ.አይ.ኤስ መቀመጫ ለመደምሰስ ዝግጅቷን አጠናቀቀች

$
0
0

ethiopians isis
የግብፅ መንግስት በምስራቃዊ ሊቢያ ዴርና ከተማ የከተመውን አይ.ኤስ.አይ.ኤስ አሸባሪ ኃይል ለመደምሰስ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የወታደራዊና የደህንነት መረጃዎችን በማጠናከር የሚዘግበው ዴብካ ፋይል ድረ ገጽ ይፋ አደረገ።

ግብፅ ከፍተኛ መጠን ያለው የምድር ጦር እና አየር ሃይሏን በማቀናጀት በምስራቅ ሊቢያ የሚገኘውን የአይ.ኤስ.አይ.ኤስ አሸባሪ ኃይል ለመደምሰስ እና ምስራቅ ሊቢያን ለመቆጣጠር የግብፅ ወታደራዊ ሃይል በተጠንቅ መሆኑ ታውቋል።

ግብፅ ይህን ወታደራዊ ዘመቻ የምታከናውነው ፕሬዚዳት አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ በደረሳቸው የሀገር ውስጥ ደህንነት መረጃ ሲሆን የደህንነት መረጃዎቹ እንደሚያሳዩት በምስራቅ ሊቢያ የከተመው የአይ.ኤስ.አይ.ኤስ አሸባሪ ቡድን በግብጽ ብሔራዊ ደህንንት ላይ አደጋ መጋረጡን ነው። ይህም ሲባል፣ የእስልምና መንግስትን ለመመሥረት ያቀዱት እነዚሁ አሸባሪዎች በአንዳንድ የግብፅ ከተሞች ሰርገው መግባታቸው ተረጋግጧል። እንዲሁም በግብጽ ጦር ሰራዊት ውስጥም መስረጋቸው የደህንነት መረጃዎች አሳይተዋል።
የአይ.ኤስ.አይ.ኤስ አሸባሪ ቡድን በበኩሉ የግብፅ እንቅስቃሴ ስላሰጋው ከኢራቅ እና ከሶሪያ አሸባሪ ሃይሎችን እያመጣ ወታደራዊ እቅሙን እያጠናከረ እንደሚገኝ ለማወቅ መቻሉን ዘገባው ያሳያል። ከሶሪያ የሚንቀሳቀሰው ሃይል በአየርና በሜዲትሪያን ባሕር ወደሊቢያ የሚገባ ሲሆን፣ ከኢራቅ የሚንቀሳቀሰው አሸባሪ ሃይል በሲናይ ፔኒንሱላ በኩል እንዲሁም በነዳጅና በሃሺሽ አዟሪዎች እገዛ በሲውዝ ካናል ግብፅ አድርገው ምስራቅ ሊቢያ እየገቡ ነው።
Ethiopian killed by ISIL
ዴብካ ፋይል እንደሚለው ግብፅ በሊቢያ ላይ ወረራ ለመፈጸም መዘጋጀቷ በአሜሪካ መንግስት የአጀንዳ ቅደም ተከተል ቁጥር አንድ ቦታ መያዙን አስነብቧል። ይህም በመሆኑ የአሜሪካው የሲ.አይ.ኤ. ዳሬክተር ጆን በርናንስ ያለረተጠበቀ ጉብኝት በካይሮ አድርገዋል። ከግብፅ ፕሬዝደንትም ጋር ውይይት መቀመጣቸው ታውቋል። ግብፅ በሊቢያ ላይ ልትከፍተው ላሰበችው ወረራ ማምራሪያ የጠየቁት የሲ.አይ.ኤ.ው ዳይሬክተር ከግብፅ መንግስት ዋስትና ያለው መግለጫ ቀርቦላቸዋል። ይሄውም፣ ፕሬዝደንት ኤል ሲሲ በሰጡት የዋስትና ማረጋገጫ ላይ እንዳሉት የግብፅ ጦር ሰራዊት ሊቢያ ውስጥ ገብቶ የመቆየት ፍላጎት የለውም። ጂሃዲስቱን ካሸነፉና ጦር መሳሪያውንም ካስፈቱት በኋላ በምስራቅ ሊቢያ በሚገኘው ቱብሩክ ከተማ ላለው የሊቢያ ጦር አሳልፈው እንደሚሰጡት አስታውቀዋል። የቱብሩክ ከተማ አስተዳደር የተመሰረተው በሊቢያ የፓርላማ አባሎች ሲሆን፣ ቲሪፖሊ በፅንፈኛ ሃይሎች እጅ በመውደቋ ምክንያት ነበር ወደዚህ ከተማ ሸሽተው የመጡት፡

አሜሪካ ሙሉ ለሙሉ ግብፅ ሊቢያን ለመውረር ያደረገችውን ዝግጀት ባትደግፈውም፣ ፕሬዝደንት ኤል ሲሲ ግን በሀገራቸው ላይ የተደቀነውን የአሸባሪዎች አደጋን ለመዋጋት ቁርጠኛ አቋም መውሰዳቸው ተዘግቧል።

ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ

The post ግብፅ፤ በምስራቅ ሊቢያ የሚገኘውን የአይ.ኤስ.አይ.ኤስ መቀመጫ ለመደምሰስ ዝግጅቷን አጠናቀቀች appeared first on Zehabesha Amharic.

የህወሃት ደባ በምስጢራዊዉ ስብሰባ – (ክፍል ሁለት) –የህወሃትን እብሪት፣ ጸብ አጫሪትና አደጋ የሚያሳይ የሳዲቅ አህመድ ፕሮግራም

አሜሪካ አይሲስን ለምን ፈጠረችው? –ክንፉ አሰፋ

$
0
0

ግብጽ የሃያ አንድ ክርስቲያን ዜጎችዋን በአይሲስ መታረድ ዜና እንደሰማች ዝም ብላ አልተቀመጠችም ነበር። ብሄራዊ የሃዘን ቀንም አላወጀችም። እንዲህ ነበር የሆነው። ከመቅጽበት ተዋጊ አውሮፕላኖችዋን አስነስታ ወደ ሊቢያ ላከቻቸው። የአይሲስ አራጆች የተከማቹበትን ደርና የተሰኘ ስፍራ እያከታተለች በቦምብ ቀጠቀጠችው። ብዙ አራጆች በድብደባው አለቁ። እንደ ግብጽ አጀማመር ቢሆን የሊብያው አይሲስ ክንፍ ድሮ-ድሮ ከምድረ-ገጽ ይጠፋ ነበር። ግና አልሆነም። አሜሪካ ጣልቃ ገባች። ግብጽ የአሜሪካን “ጸረ-ሽብር” ዘመቻ በማገዝዋ ምስጋና ማግኘት ሲገባት በተቃራኒው ተወገዘች።   ከጥቂት ድብደባ በኋላ ፔንታጎን ግብጽን አስጠነቀቀ[0]።  የኦባማ አተዳደርም ደብደባው በአፋጣኝ እንዲቆም ቀጭን መልእክት ላከ። ይህ ድርጊት ከዚህ ቀደም ስለ አይሲስ አፈጣጠር ኤድዋርድ ስኖደን[1] የለቀቀው ምስጢራዊ መረጃ ጋር ተዳምሮ በአሜሪካ ላይ የነበረውን ጥርጣሬው አጠናከረው።
Ethiopian killed by ISIL

ነገሩን ለማመን ያዳግት ይሆናል። በግልጽ የሚታዩ መረጃ እና ማስረጃዎች ግን ተአማኒነታቸው ጥርጥር ውስጥ የሚገባ አይደለም። “በአይሲስ እየታረዱ ያሉት ዜጎች የፊልም ቅንበር እንጂ እውነት አይደለም![2]” የሚሉ ባለሞያዎችም የትንተናቸው መነሻ ከዚህ ጉዳይ ጋር ይያያዛል።

ይህ አሸባሪ ድርጅት ስራውን ከጀመረ አንድ አመት ባልሞላ ግዜ ውስጥ ከመቶ ሺ በላይ ዜጎችን በአሰቃቂ ሁኔታ እንደገደለ ይናገራል። ቦምብ እንደዝናብ የሚወርድባቸው ሃገሮች፤ ሶማልያ፣ የመን፣ ኢራቅ፣ ሶርያ፣ አፍጋኒስታን፣ፓኪስታን… ተደምረው አይሲስ ከሚነግረን ግድያ ሩብ ያህሉንም አላደረጉም።  የሃያላን ሃገሮች ምላሽ ግን በአፍ ከማውገዝ ያለፈ አለመሆኑ በአይሲስ አሰራር ላይ ተጨማሪ ጥርጣሬ ይፈጥራል።

አይሲስ የእስራኤል፣ የኢንግሊዝ እና አሜሪካ የጋራ ፕሮጀክት መሆንን ያጋለጠውን፤ የኤድዋርድ ስኖደን መረጃ እንደገና እንድንመረምረው ይገፋናል። በአይሲስ ዙርያ የሚተነትኑ አንዳንድ ጸሃፊዎች እጃቸውን በአሜሪካ ላይ መቀሰር ከጀመሩ ሰነበትበት ብለዋል። አሸባሪ ሃይልን መፍጠር ለአሜሪካ የመጀመርያ አይደለም። አላማው ይለያይ እንጂ ኦሳማ ቢን ላደንም የአሜሪካ ስሪት መሆኑ በይፋ ተገልጿል። የአሜሪካ ቁጥር አንድ ጠላት የነበረው ኦሳማ ቢን ላደን በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት በአሜሪካው የስለላ ተቋም፤ በሲ.አይ.ኤ እንደተፈጠረ በግልጽ ተቀምጧል። እ.ኤ.አ. በ1979 ሶቭየት ህብረት አፍጋኒስታንን በወረረች ግዜ ኦሳማ ቢን ላደን አማጺውን የሙጃህዲን  ሃይል በመቀላቀል ወደ አፍጋኒስታን አመራ። በወቅቱ አሜሪካ ሙጃህዲንን ለማሰልጠን እና ለማስታጠቅ ሶስት ቢሊየን ዶላር እንዳፈሰሰች የብሪታንያው ዜና አገልግሎት ቢ.ቢ.ሲ. ዘግቧል። እንደ ቢ.ቢ.ሲ. ዘገባ ሲ.አይ.ኤ. ለኦሳማ ቢን ላደን በግል ደረጃውን የጠበቀ የኢንተልጀንስ ስልጠናም አድርጎለታል። ቀዝቃዛው ጦርነት ሲያበቃ እና ሶቭየት ህብረት አፍጋኒስታንን ለቅቃ ስትወጣ ነው ቢን ላደን አሜሪካ ላይ የዞረው።

የዘመናችን ዘግናኝ የሽብር ድርጅት የሆነው አይሲስንም የፈጠረችው አሜሪካ ናት የሚሉ ጸሃፍት ጥቂት አይደሉም። የእነዚህ ተንታኞች መረጃ በከፊል የሚንተራሰው ከአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት ኤጀንሲ ሰነድ የጠለፈው ኤድዋርድ ስኖደንን ነው። የአሜሪካ ስለላ ድርጅት NSA ውስጥ ይሰራ የነበረው ይህ ሰው የአሜሪካን ብሄራዊ ምስጢሮች ካጋለጠ በኋላ ሩስያ ውስጥ ተደብቋል።  እርግጥ ነው። ኤድዋርድ ስኖደን የለቀቀው ሰነድ የአይሲስን አፈጣጠር ምስጢር በጥቁርና – ነጭ አስቀምጦታል። ሾልኮ የወጣው ይህ ሰነድ የአይሲሱ መሪ አቡባክር አል ባግዳዲ የአሜሪካ ደህንነት ግብአት እንደሆነ ይገልጻል። እንደ  ምስጢራዊው የኬብል መረጃ ከሆነ ለአይሲስ መመስረት ሃላፊነቱን የሚወስዱት እስራኤል፣ ታላቋ ብሪታንያ እና አሜሪካ ናቸው። “ምክንያቱም” ይላሉ ዶክመንቱን የሚተነትኑ አምደኞች፣”ምክንያቱም እስላማዊ ጦረኞች የሚሏቸው ሃይሎች ሁሉ ከአለም ዙርያ እየሄዱ ሶርያ ላይ እንዲሰባሰቡ ነው።” ይህ ስትራቴጂ እውን ሲሆን፤ በአንድ በኩል በእነሱ የሚመራ ህይል ለማስቀመጥ እና በሌላ በኩል ደግሞ እስራኤል በቅርብ አደጋ ላይ መውደቋን ለማስመሰል የተወጠነ ታክቲክ ነው። መካከለኛው ምስራቅ ሽብር ያለ ማስመሰሉ አካባቢውን ዘልቆ ለመቆጣጠር ይረዳቸዋል።  ይህን ለማድረግ አይሲስን እንደ ምክንያት ይጠቀሙበታል።”

የኤድዋርድ ስኖደን ምስጢራዊ መረጃ በጥሬው ተቀብለን፣ ስነዱን እንደማስረጃ ወስደን ለድምዳሜ መቸኮል የለብንም።  ጉዳዩ ትንሽ ከበድ ያለ ነውና ሌሎች ተጓዳኝ ነገሮችን መመርመርም ተገቢ ይሆናል።

የእስላማዊ ዲሞክራቲክ ጂሃድ ፓርቲ መስራች እና ቀደም ሲል ከፍተኛ የአልቃይዳ ኮማንደር የነበረው ናቢል ናኢም ለሜዲያ የተናገረው መረጃ የኤድዋርድ ስኖደንን ማስረጃ ያጠናክረዋል። ናቢል ናኢም ለቤይርቱ ፓን አረብ ቴሌቭዥን በሰጠው ቃል፤ “አይሲስን ጨምሮ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያላቸው ደርጅቶች ሁሉ፤ በአሁን ሰዓት እየሰሩ ያሉት ለአሜሪካው የስለላ ተቋም ለሲ.አይ.ኤ. ነው።” ሲል በዚህ ወር መግቢያ ላይ ተናግሯል[3]።

ናቢል ናኢም በቴሌቭዥን የሰጠው አስደንጋጭ ምስጢር በዚህ አላበቃም፤ ሌላም ለማመን የሚከብድ ነገር አክሎበታል። አይሲስ በደንብ የሰለጠነ እና በደንብ የታጠቀ የሽብር ድርጅት ነው። መጠነ ስፊ የሆኑ የኢራቅን እና የሶርያን ክልሎች ተቆጣጥሯል።

የባህሬኑ “ዘ ገልፍ ዴይሊ ኒውስ” ጋዜጣም ባለፈው አመት አጋማሽ ላይ በዋና ገጹ  የአይ.ሲስ መሪ አቡ ባክር አል ባግዳዲን የእስራኤሉ የስለላ ድርጅት ሞሳድ በጦር፣ በመንፈሳዊ ትምህርት እና በንግግር ክህሎት እንዳሰለጠነው ጽፏል[4]።

የዮርዳኖስ ባለስልጣናትን ጠቅሶ “ወርልድ ኔት ዴይሊ” የተሰኘው ጋዜጣ የአሜሪካ ወታደሮች በዮርዳኖስ ግዛት ውስጥ የአይሲስ አባላትን እንዳሰለጠኑ ዘግቧል[5]።

እነዚህን መረጃዎች በአንድ ወገን እንያዛቸው እና ወደ ሌሎች ምልከታዎች ደግሞ እንሂድ። ታላላቅ የአሜሪካ ጋዜጠኞችም የአይሲስ መጠናከር እና የአለም ዝምታ እንቆቅልሽ ነው የሆነባቸው።  የፎክስ ኒውስ አምደኛ የሆነችው ግሬታ ቫን ሱስተረን እንግዳ የሆነባትን አስደንጋጭ የአይሲስ ግድያ እና የምእራባውያን ዝምታ እጅግ በመደነቅ ታነሳለች። አይሲስ በሺዎች የሚጠጉ ክርስቲያኖችን እያረደ፤  የተባበሩት መንግስታት፣ አሜሪካም ሆነ የአውሮፓ ህብረት ጉዳዩን ከምንም አልቆጠረውም ብላለች። ጋዜጠኛ ግሬታ ንግግርዋን ቀጠለች። “ያለነው በሂትለር ዘመን አይደለም። ዘመኑ የመረጃ ነው። እልቂቱን የሚያሳዩ መረጃዎች በግልጽ ይታያሉ። አሰቃቂ መረጃዎችን እየተመለከተ አለም ግን ዝም ነው ያለው። ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ሊጋባን በማይችል ምክንያት ጉዳዩን ችላ ብሎታል። …” ትላለች።

ሌላው ሉ ዶብስ የተባለ በአሜሪካ ታዋቂ የቴሌቭዥን አቅራቢና ጸሃፊ፤ ህዝብ እየታረደ አለም ግን በአይሲስ ላይ ችላ ማለቱ እንዳስገረመው ይናገራል።  ጋዜጠኛ ሉ ዶብስ ሜሪካዊውን ደራሲ ጆኒ ሞር በጉዳዩ ማብራርያ እንዲሰጥም አድሮታል።  ጆኒ ሞር “Defying ISIS”  “ውጉዝ መአሪዮስ አይሲስ” የሚል መጽሃፉ አይሲስን ከናዚዎች ጋር እያመሳሰለ ነው ያስቀመጠው።  ጆኒ ሞር በፎክስ ኒውስ ላይ ቀርቦ የተናገረው ያስደምማል። “የ አይሲስ አራጆችን የጫኑ አርባ መኪናዎች በአንዲት የሶሪያ መንደር በነጻነት እየተዘዋወሩ 3000 ክርስቲያኖችን አፍሰው ወሰዱ። … ቦስንያ ላይ በቀን 140 ቦምብ ሲጥሉ የነበሩ የኔቶ ተዋጊ አውሮፕላኖች፣ በኢራቅ እና ሶርያ ላይ በቀን ከ 7 – 12 ቦምብ ሲጣል አይሲስ ግን ችላ ነው የተባለው።”

ጆን ዊልገር የተሰኘ የፖለቲካ ተንታኝ ደግሞ በአንድ ጥናታዊ ጽሁፉ፤ “አይሲስ የአሜሪካ ፍጡር ነው” ከማለት አልፎ፣  አይሲስን ከካምቦዲያው ካመሩዥ ጋር ያመሳስለዋል። በ 1969 እ.ኤ.አ. ፕሬዝዳንት ኒክሰን ካምቦዲያን በቦንብ አስደብድበው ሲያበቁ አንባገነኑ ፖል ፖትን አበቀሉ። የፖልፖት ካመሩዥ ከአይሲስ ጋር የሚያመሳስላቸው ነገር አለ። “ሁለቱም የአሜሪካ ውጤቶች፣ ሁለቱም የጨለማው ዘመን ጨካኞች ናቸው” ሲል ጽፏል።

ይህን ክስተት ስከታተል “ሲ. አይ. ኤ – ዘ ከልት ኦፍ ኢንተሊጀንስ” የተሰኘው መጽሃፍ ታወሰኝ።  ቪክቶር ማርቼቲ የተባለ የቀድሞ ሲ.አይ.ኤ አባል የጻፈው “ዘ ከልት ኦፍ ኢንተሊጀንስ” መጽሃፍ አሚሪካኖች ብሄራዊ ጥቅማቸውን ለማስከበር የማያደርጉት ነገር እንደሌለ ይነግረናል። ሲ. አይ.ኤ. የአሜሪካን ብሄራዊ ጥቅም ሲያስከብር ለሞራል እሴቶች፣ ለሰዎች ስብዕና እና ለፍትህ ቦታ እንደማይሰጥ ደራሲው ቪክቶር ማርቼቲ ይነግረናል። መጽሃፉ በከፊል በአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሳንሱር ተደርጎ የወጣ ነው።  እንደዚህም ሆኖ ሲ.አይ.ኤ.  ከረቀቀ ቴክኖሎጂ እስከ ረቀቀ ወንጀል እንደሚሰራ ይተነትናል።  አሜሪካኖች ጉዳያቸውን ለማስፈጸም ዝናብ ማዘነብ ካለባቸው እንኳን፤ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ያንን ሊያደርጉ እንደሚችሉ መጽሃፉ ያሳየናል።

የአይሲስ አራጆች የሚናገሩት እንግሊዝኛ በአሜሪካ ቅላጼ (አክሰንት) ነው።  አሜሪካ ተወልደው ያደጉ ሽብርተኞች ሊሆኑ ይችላሉ ብለን እንውሰድ። አይሲስ የሚለቅቃቸውን የቪድዮ ምስሎች የሚጠራጠሩ ባለሙያዎች፤ ጉዳዩን ከፖለቲካ ብቻ ሳይሆን ከሙያ አንጻርም ይመለከቱታል።  የጃፓን ዜጎች ሲታረዱ የሚያሳየውን ቪድዮ ፍሬም፣ በፍሬም እያሳዩ  የአይሲስ ግድያ ውሸት መሆኑን ለመግለጽ የሚሞክሩ የፊልም ባለሞያዎች የሚናገሩት ሙሉ በሙሉ ባያሳምንም  ተመልካቹን ማደናገሩ አልቀረም[6]። እየወጡ ያሉት የግድያ ፊልሞች በአረንጓዴ ጨርቅ green screen  በስቱዲዮ ውስጥ የሚሰሩ የትራይካስተር ቴክኒኮች ናቸው ብለው ነው እርግጠኝነት የሚናገሩት።  ግሎባል ሪሰርች የተባለ አንድ የካናዳ የምርምር ተቋም፤ ISIS Video ‘Execution’ of Ethiopians in Libya Appears Fake [2] ሲል በሊቢያ የተሰዉት የኢትዮጵያ ሰማእታት ጉዳይ፤ የቪድዮ ቅንብር እንጂ እውነት አይደለም ሲል የምስሉን ፍሬም እየከፋፈለ በስሎው ሞሽን አቅርቦታል። ትንተናው አሳማኝ ላይሆን ይችላል። አይቶ መፍረዱ ግን ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም። ምኞታቸውም ከሆነ ይህ  እውነት ይሆን ዘንድ ጸሎታችን ነው።

ያልተፈታ እንቆቅልሽ!

ለመሆኑ እስራኤል፣ የኢንግሊዝ እና አሜሪካ በጋራ ሆነው የአይሲስን ፕሮጀክት ለምን ፈጠሩ? የሚለው ጥያቄ ምላሽ ካገነ እንቆቅልሹን ይፈታው ይሆናል።  ተንታኞች እና ተቺዎች ለዚህ በርካታ ምክንያቶችን ይደረድራሉ። አንደኛው ምክንያት እስራኤል በመሃከለኛው ምስራቅ ውስጥ ሁከት በመፍጠር የሁከቱ ተጠቃሚ ለመሆን እንድትችል ነው ይላሉ። ይህ ከሆነ እስራኤል በክልሉ ሃያልነቷን ሙሉ ለሙሉ ለማስከበር ይረዳታል ይላሉ። አይሁዶች ክርስትና እና እስልምና ጠላት ባይሆኑም በሁለቱም እምነቶች ላይ ችግር አለባቸው።  ይሁንና አላማቸው የአይሁድን እምነት ለማስፋፋት ሳይሆን የእስራኤልን በሄራዊ ጥቅም ማስጠበቁ  ላይ ነው። የእስራኤል አላማ የሁለቱ ሃይማኖት ተከታዮችን እርስ-በእርስ ማፋጀትና ማዳከም ነው ብለው የሚጽፉም አሉ። በእርግጥ አረቦች በሙሉ ጸረ-አይሁድ ናቸው። አረቦች በሙሉ ደግሞ ሙስሊሞች አይደሉም። እንደፍልስጤም፣ ኢራቅ፣ ዮርዳኖስ፤ ሊባኖስ እና ሶርያ ባሉ አረብ አገሮች ክርስቲያኖችም አሉ።

አሜሪካ እና እንግሊዝም ከዚህ ሽብር ጀርባ የሃገራቸውን ብሄራዊ ጥቅም ያስከብራሉ። አለምን በአሜሪካ አምሳል መፍጠር ከሚለው የአሜሪካ የውጭ ፖሊሲን በሌላው ከመጫን  ባሻገር ከመካከለኛው ምስራቅ በኢኮኖሚ ዘርፍ የሚያገኙት ጥቅምም ቀላል የሚባል አይደለም። አንደኛው “ሽብርን መዋጋት” በሚል ምክንያት የጦር መሳሪያ ሽያጭ ነው። ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በመሳርያ ሽያች በአመት ከአራት ትሪልዮን ዶላር በላይ ገቢ ያገኙበታል። መካከለኛው ምስራቅ ሃገር ያሉ ዋና ዋና የነዳጅ ክምችቶችን ለመቆጣጠርም የእነሱ የሆነን ሃይል በሽብር ሰበብ በስፍራው ማስቀመጥ ግድ ነው።

አሜሪካ ለሃገሯ ብሄራዊ ጥቅም ስትል በሌሎች ላይ ቁማር መጫወት አይገዳትም። በዚያን በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት አሜሪካኖች ከምስራቁ ጎራ ጋር የቃላት ጦርነት ነበር ያካሂዱ የነበረው። ያ ወቅት ለእኛ ግን ቀዝቃዛ አልነበረም። ለሁለቱ ሃያላን ሃገሮች የጦር ቀጠና ነበርን። አይሲስ የአሜሪካ ፍጡር ይሁንም አይሁን ገፈቱን የምንቀምሰው እኛው ሆነናል። በሰማዕታቱ እልቂት ምክንያት ከገባንበት ብሄራዊ ሃዘን ገና አልተላቀቅንም። ሁኔታው ሰቅጣጭ፣ ድርጊቱ ቅስም ሰባሪ ነውና የሃዘኑ ሸክም በቀላሉ የሚወርድ አይመስልም። ከዚህ ሁሉ ሃዘን በኋላም በአልጃዚራ ቴሌቭዥን ላይ የቀረቡ ወጣቶች ከአገር ቤቱ ኑሮ ወደውጭ መውጣቱን እንደሚመርጡ ተናግረዋል።  አሁን ያለውን መረጃ ብቻ ይዞ አይሲስን የፈጠረችው አሜሪካ ናት ብሎ መደምደም ባይቻልም፤ ጥቅሟን ካስጠበቀላት ይህንን ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማትል ያለፉ ተመክሮዎች ይጠቁሙናል።  የሌላው ማለቅ፣ መረበሽና መተራመስ ለአሜሪካ ደንታ አይሰጣትም።

[0]http://www.americanthinker.com/blog/2015/02/obama_administration_egypt_bad_iran_good_israel.html

[1]http://www.hangthebankers.com/?s=snowden

[2]http://www.globalresearch.ca/stagecraft-isis-video-execution-of-ethiopians-in-libya-appears-fake/5444466

[3]http://www.infowars.com/former-al-qaeda-commander-isis-works-for-the-cia

[4]http://www.gulf-daily-news.com/NewsDetails.aspx?storyid=381153

[5]http://www.infowars.com/blowback-u-s-trained-isis-at-secret-jordan-base/

[6]https://www.youtube.com/watch?v=QrdDavSw_Fg

The post አሜሪካ አይሲስን ለምን ፈጠረችው? – ክንፉ አሰፋ appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: መጥፎ የአፍ ጠረን ሕይወትን እስከማሳጣት ሊደርስ ይችላል

$
0
0

በአፋችን ውስጥ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ባክቴሪያዎች አሉ። እነዚህ ባክቴሪያዎች ንፅህናው በተጠበቀ አፍ ውስጥ ከሆነ የሚገኙት ምንም አይነት ጉዳት ሳያደርሱ ተስማምተው የሚኖሩ ሲሆን፤ ንፅህናው ካልተጠበቀ ግን አፋችን ውስጥ በሚገኙ አካሎቻችን ላይ ችግር ከመፍጠርም አልፈው ለመጥፎ የአፍ ጠረን ያጋልጡናል። መጥፎ የአፍ ጠረን ደግሞ በማኅበራዊ እና ስነልቦናዊ መንገድ ህይወታችንን ከማስተጓጐልም አልፎ ህይወትን ለሚነጥቅ ችግር ሊዳርገን ይችላል። በዚህ መጥፎ የአፍ ጠረን እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ትምህርት ቤት መምህር ከሆኑት ዶክተር ሔኖክ ገዛኸኝ ጋር ቆይታ ሰንደቅ አድርገል።
smelly
ሰንደቅ፡- ለመጥፎ የአፍ ጠረን የተለያዩ ምክንያቶች ይጠቀሳሉ። በሕክምናው ረገድ በትክክል እነዚሁ ናቸው ተብለው የሚቀመጡት መንስኤዎች ምንድን ናቸው?

ዶ/ር ሔኖክ፡- ለዚህ መጥፎ የአፍ ጠረን ወይም በህክምናው ሀሊቶሲስ (Halitosis) ለሚባለው ችግር በርካታ ምክንያቶች አሉ። እነዚህን ምክንያቶች በሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን። አንደኛው በአፍ ውስጥ የሚፈጠር ምክንያት ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ የውስጥ ህመሞች ሊሆን ይችላል። በአብዛኛው ግን ለዚህ ችግር ምክንያት የሚሆነው በአፍ ውስጥ ያለው ችግር ነው። ጥርሳችን ላይ ወይም ምላሳችን ላይ የሚኖር ቆሻሻ ወይም ፈንገስ፣ የጥርስ መቦርቦር እና ቆሻሻ መያዝ በአፍ ውስጥ የሚፈጠሩ የመጥፎ የአፍ ጠረን መንስኤዎች ናቸው። በተጨማሪም በጥርሳችን እና በድዳችን መካከል የሚኖረው ክፍተት የሰፋ ከሆነ በርካታ ባክቴሪያዎች በዚያ ቦታ ላይ በመፈጠር ለዚህ ለመጥፎ የአፍ ጠረን ያጋልጡናል።

የውስጥ ህመም ወይም ሲስተሚክ ዲዝስ የምንላቸው ደግሞ አንዱ ከጭንቀት ጋር ተያይዞ የሚመጣው ሊሆን ይችላል። እንዲሁም የመድማት ችግር ያለባቸው (Hemophilic) የሆኑ ሰዎች መጥፎ የአፍ ጠረን ይኖራቸዋል። በተጨማሪም የስኳር ህመም፣ የጨጓራ ህመም ወይም የአንጀት ችግር እና የማስመለስ ችግር ያለባቸው ሰዎች ለዚህ ችግር የተጋለጡ ናቸው። በሌላ በኩል ደግሞ በምራቅ አመንጪ ዕጢዎች ላይ የሚከሰት በሽታ ለዚሁ ችግር መንስኤ ሊሆን ይችላል። እነዚህ በምራቅ አመንጪ ዕጢ ላይ የሚከሰቱ በሽታዎች በአፍ ውስጥ የምራቅ መመንጨት አቅምን በመቀነስ አፍ እንዲደርቅ ያደርጉታል። በዚህም ሳቢያ መጥፎ የአፍ ጠረን ሊከሰት ይችላል።

ሰንደቅ፡-በአብዛኛው መጥፎ የአፍ ጠረን በሰዎች ላይ የሚስተዋለው ጠዋት ላይ ነው። ምናልባት መጥፎ የአፍ ጠረን የተለያዩ አይነቶች ይኖሩት ይሆን?

ዶ/ር ሔኖክ፡- የአፍ ጠረን በሁለት የሚከፈል ነው። አንደኛው ጠዋት ላይ የሚሸት የአፍ ጠረን (Morning Bad Breath) እንዲሁም ከላይ በጠቀስናቸው ምክንያቶች የሚፈጠር መጥፎ የአፍ ጠረን ናቸው። ጠዋት ላይ የሚፈጠር መጥፎ የአፍ ጠረን በማንኛውም ሰው ላይ የሚከሰት ነው። በአፋችን ውስጥ የሚገኙት ምራቅ አመንጪ ዕጢዎች በሽታ እንኳን ባይኖርባቸው ምሽት ላይ እንደ ቀኑ ብዙ ምራቅ ማመንጨት አይችሉም። በዚሁም ሳቢያ የአፍ መድረቅ ስለሚከሰት ጠዋት ላይ መጥፎ የአፍ ጠረን ይፈጠራል። ሁለተኛው ግን ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች የሚከሰት ነው።

ሰንደቅ፡- የምንመገባቸው የተለያዩ የምግብ አይነቶች ለምሳሌ ነጭ ሽንኩርትን የመሳሰሉት ለመጥፎ የአፍ ጠረን መንስኤ ይሆናሉ የሚል አመለካከት አለ። ይኔ ነገር ምን ያህል የተረጋገጠ ነው?

ዶ/ር ሔኖክ፡- ልክ ነው። ነጭ ሽንኩርት ብቻም ሳይሆን የተለያዩ ከፍተኛ የቅመም መጠን ያለባቸው ምግቦችን የምናዘወትር ከሆነ መጥፎ የአፍ ጠረን ሊያመጡ ይችላሉ። እነዚህን ምግቦች በከፍተኛ መጠን የምንመገብ ከሆነ ወደ ደም ዝውውር ስርዓት ውስጥ ስለሚገባ የአፋችንን ጠረን ወደ መጥፎነት የመቀየር አቅም አለው። እነዚህ ነገሮች ከተዘወተሩ ከጊዜያዊ ሽታ አልፈው ቋሚ መጥፎ የአፍ ጠረን ያመጣሉ። በዚህ በኩል በእስያ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ከፍተኛ ቅመም ያለባቸው ምግቦችን ስለሚጠቀሙ ተጠቃሾች ናቸው።

ሰንደቅ፡- ብዙዎች ዘመናዊ የጥርስ ሳሙናዎች ተጠቅመን ስናቋርጥ ለመጥፎ የአፍ ጠረን ተጋለጥን ሲሉ ይሰማሉና ምን ያህል እውነት ነው?

ዶ/ር ሔኖክ፡- እንደዚህ አይነት ነገሮች ብዙ ጊዜ ይነገራሉ። ተጠቅሜ የማቋርጥ ከሆነ የአፍ ጠረኔን ሊለውጥብኝ ስለሚችል አልጠቀምም የሚሉ አሉ። በመሠረቱ እነዚህን የጥርስ ሳሙናዎች መጠቀም ግዴታ ነው። ጀምሮ ማቋረጥም አያስፈልግም። እነዚህ የጥርስ ሳሙናዎች አገልግሎታቸው ማፅዳት ብቻ አይደለም። የጥርስ ሳሙናም ሆነ የእንጨት መፋቂያ ጥርስን ያፀዳሉ። በእንጨት ሲፋቅ የጥርስን የውጪውን ክፍል ሊጐዳው ይችላል። የጥርስ ሳሙና ግን ከማፅዳትም በላይ በርካታ ንጥረ ነገሮች አሉት። እነዚህ ንጥረ ነገሮች የጥርስን ጥንካሬ የሚጠብቁ እና ቀለሙን እንደጠበቀ እንዲቆይ የሚያደርጉ ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ ፍሎራይድ የሚባል ንጥረ ነገር ስላለው ጥርሳችን የፍሎራይድ እጥረት ተፈጥሮበት እንዳይበልዝ ያደርገዋል። ስለዚህ ጥርስን በተከታታይ ማፅዳት ግዴታ ነው።

ባይቋረጥ የሚባለው ነገር መታሰብ የለበትም። ልብሳችንን የምናጥብ ከሆነ ማጠቡን ስናቋርጥ ልብሱ ይቆሽሻል። ልክ እንደዚያው ጥርስን ማፅዳት ማቆሙ ችግሩን ሊያመጣው ይችላል እንጂ ችግሩ የሳሙናው አይደለም። ከጥቅሙም አንፃር በሳሙናው የማፅዳት ተግባሩ መቋረጥ የለበትም።

ሰንደቅ፡- ብዙ ጊዜ መጥፎ የአፍ ጠረንን በአዋቂነት እድሜ ክልል ውስጥ ካሉ ሰዎች ጋር ነው የምናያይዘው። በህፃናት ላይስ የመታየት እድሉ ምን ያህል ነው?

ዶ/ር ሔኖክ፡- ህፃናት ከእድሜ ጋር ተያይዘው ለሚመጡ የአፍ ችግሮች ገና ናቸው። ህፃናት አፋቸውን ለረጅም ጊዜ ስላልተጠቀሙበት ከጥርስ መቦርቦር ጋር ተያይዞ ለሚመጣው የአፍ ጠረን አይጋለጡም። እነዚህ ነገሮች ሊረዷቸው ይችላሉ። ነገር ግን ከውስጥ ህመም ጋር የተያያዘ እና ከምራቅ አመንጪ ዕጢዎች ህመም ምክንያት የሚመጣው ችግር በእነርሱ ላይም ይከሰታል። ለምሳሌ የስኳር ህመም ከህፃንነት እድሜ ጀምሮ ስለሚከሰት ህፃናትም የችግሩ ተጠቂዎች ናቸው። ህፃናት በንፅህና ካልተያዙ ዞሮ ዞሮ ለችግሩ የመጋለጥ እድል አላቸው።

ሰንደቅ፡- መጥፎ የሆነ የአፍ ጠረን ከሰዎች ጋር የሚኖረን ግንኙነት ላይ በተለያዩ መንገዶች አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል። ይሄ ችግር በወቅቱ መፍትሄ ካልተገኘለት የሚያመጣው የመጨረሻ ውጤት ምንድን ነው?

ዶ/ር ሔኖክ፡- መጥፎ የአፍ ጠረን በዋናነት በሰዎች ላይ ስነ-ልቦናዊ እና ማኅበራዊ ተፅእኖዎችን ያስከትላል። አንዳንድ ጊዜ ሰዎች መጥፎ የአፍ ጠረን ይኑራቸው አይኑራቸው ላይገነዘቡት ይችላሉ። አፍ-ለአፍንጫ ቅርብ በመሆኑ ይሄ ነገር ሁልጊዜ ካለ የመለመድ ነገር ሊመጣ ይችላል። ነገር ግን ሌላ ሰው ሲያሳውቃቸው ከሰው ጋር ለማውራት መፍራት እና መራቅ ይመጣል። ይሄ ነገር ግንኙነትን ይጐዳዋል። ፍቅረኛሞች ወይም ባልና ሚስት ይሄንን ችግር መነጋገር በመተፋፈር እስከመለያየት የደረሱበት ጊዜ እንዳለ አውቃለሁ። ስለዚህ ግንኙነት ላይም ሆነ ስራ ላይ ከፍተኛ ችግር ያመጣል።

በአፍ ውስጥ በሚከሰት ችግር ምክንያት የሚመጣው መጥፎ የአፍ ጠረን ካንዲዲያሲስ የሚባለው ፈንገስ ነው። ይሄ ፈንገስ በአብዛኛው ምላስን እና የአፍን ወለል የሚያጠቃ ነው። በመሆኑም በወቅቱ ካልታከመ በምላስ እና በአፍ ላይ ጉዳት ያመጣል። በጥርስ ላይ የሚከማች ቆሻሻ በጊዜ የማይፀዳ ከሆነ ድድን የመብላት እና የጥርስን ስር የማጋለጥ ችግር ይፈጥራሉ። ከድድ ስር ከገባም ጥርስ እንዲበላ እና ኢንፌክሽን እንዲፈጠር ያደርገዋል። ይሄ ኢንፌክሽን ወደ አጥንት ከዘለቀ ደግሞ የላይኛውን እና የታችኛውን የጥርስ ደጋፊ አጥንት ያጠቃል። የላይኛው ጥርስ ቆሻሻ ተጠራቅሞበት የማይታከም ከሆነ የሳይነስ ህመም፣ የአጥንት ኢንፌክሽን እና የመሳሰሉትን ሊያመጣብን ይችላል። በዚህ መልኩ የሚመጡት ችግሮች ደግሞ ህይወትን እስከማጣት የሚያደርሱ ሊሆኑ ይችላሉ።

ሰንደቅ፡- ሰዎች መጥፎ የአፍ ጠረንን ለመከላከል የሚጠቀሙባቸው እንደማስቲካ ያሉ ዘዴዎች ይኖራሉ። በህክምናው ዘርፍ ያሉት መከላከያዎች ምንድን ናቸው?

ዶ/ር ሔኖክ፡- በቅድሚያ ይሄ መጥፎ የአፍ ጠረን መንስኤው በአፍ ውስጥ በተፈጠረ ችግር ወይም በውስጥ ህመም ምክንያት መሆኑ መለየት አለበት። ጥሩ ነገሩ መጥፎ የአፍ ጠረን ወይም የአፍ ውስጥ ችግሮች ሲያጋጥሙ የአፍ ውስጥ ችግርን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ተያያዥ ችግሮችንም ለመታየት ያግዛል። ችግሩ የኤች አይ ቪ ወይም የኩላሊት አሊያም ደግሞ የልብ ችግር መሆኑን በአፍ ውስጥ ምልክቶቻቸውን ማየት ይቻላል። በዚህ ህክምና ከአፍ ችግር አልፎ ሌሎች ችግሮችንም ለመለየት ጠቃሚ ነው። ዋናው ነገር ችግሩ እንደተከሰተ ወደ ህክምና መሄዱ አስፈላጊ ነው።

በአብዛኛው ይሄ መጥፎ የአፍ ጠረን የሚከሰተው በአፍ ውስጥ በሚከሰት ችግር ነው። ይሄ ችግር ደግሞ መንስኤው ብዙ ጊዜ የንፅህና ጉድለት ነው። ስለዚህ ጥርሳችንን እና ምላሳችንን ምግብ ከተመገብን በኋላ በመቦረሽ ማፅዳት ያስፈልጋል። ይሄ መሆን ካልቻለም ቢያንስ ጠዋትና ማታ ድድን እና ምላስን በማይጐዳ መልኩ መቦረሽ ያስፈልጋል። አፋችን ከፍተኛ የሆኑ ባክቴሪያዎች የሚገኙበት የሰውነት ክፍል ነው። ጥርስ ከተቦረሸ ከሁለት ደቂቃ በኋላ በአፋችን ውስጥ የሚኖረው ባክቴሪያ ቢጠና በአንዱ ጥርስ ላይ ብቻ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ባክቴሪያዎች ይገኛሉ።

በአፋችን ውስጥ ቢያንስ ከ500 ዓይነት በላይ ባክቴሪያዎች እያንዳንዳቸው ደግሞ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ባክቴሪያዎች አሉ። እነዚህ ባክቴያዎች አፋችንን በንፅህና ካልያዝን ወይም ለሌላ በሽታ ተጋልጠን የመከላከል አቅም የሚያንሰን ከሆነ ጉዳት ያደርሳሉ። ነገር ግን ጤናማ ከሆንን ተቻችለው ይኖራሉ እንጂ ወደ ማጥቃት አይገቡም። እነዚህ ባክቴሪያዎች አፋችንን በንፅህና ካልያዝን በአፋችን ውስጥ ያለውን ቆሻሻ እንደ ድንጋይ እንዲጋገር ያደርጉትና የድድ መቁሰልን ጭምር ሊያመጡብን ይችላሉ። የውስጥ ደዌ ችግር ከሌለ የአፍ ንፅህናን በመጠበቅ እነዚህን ችግሮች መከላከል ይቻላል።

ጊዜያዊ መከላከያዎችን በተመለከተ ማስቲካ በህክምናውም የሚበረታታ ነው። እንደ ማስቲካ ያሉ ነገሮችን በአፋችን ውስጥ የምናመላልስ ወይም የምናኝክ ከሆነ በአፋችን ውስጥ ምራቅ እንዲመነጭ ስለሚያደርግ ከአፍ መድረቅ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን መጥፎ የአፍ ጠረን መከላከል ይቻላል።

ህክምናውን ስንመለከት ችግሩ ከአፍ ውስጥ በሚፈጠር ምክንያት ከሆነ የሚከሰተው አፍን የማፅዳት እና ለፈንገሱም መድሐኒት የመስጠት ስራ ይሰራል። አፍ ከተፀዳ በኋላም ድድ እንዲጠነክር የማድረግ ስራ ይሰራል። በድድ እና በጥርስ መካከል ያለውን ክፍተት መሙላት በክፍተቱ ውስጥ የሚከማቹትን ባከቴሪያዎች መከላከል ይቻላል።

The post Health: መጥፎ የአፍ ጠረን ሕይወትን እስከማሳጣት ሊደርስ ይችላል appeared first on Zehabesha Amharic.

በአፍሪካና በመካከለኛው ምሥራቅ በወገኖቻችን ላይ በደረሰው የግፍ ግድያ ተናደናል፣ አዝነናል፣ተቆጥተናልም!

$
0
0

 

ethiopiaእስላሚክ ስቴት የሱኒ ካሊፌት ግዛት ለመፍጠርና ለማስፋፋት በሚል ብዥታ በክርሲቲያኖችና ሱኒ ባልሆኑ የእስልምና ተከታዮች ላይ በፈጸመው አስቃቂ ግድያና ከኑሮአቸው የማፈናቀልና እንዲሰደዱ የማድረግ አረመናዊ ተግባሩ በጣም ከፍተኛ ሀዘን ተሰምቶናል። ኮፕቲክ ክርስቲያኖችን እያሳደደ በሚገድልበት ሰሞን፤ 30 የሚሆኑ ወገኖቻችን ወደ አውሮፓ ሥራ ፍለጋ ለመሸጋገር ሊቢያ እንዳሉ “የጠላታችን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አባሎች” በማለት ገሚሱን አንገታችውን በጎራዴ በማረድ ሌሎቹን በጥይት በመምታት በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሎአቸዋል። ለሥራ ፍለጋ ሲሉ ከአደገኛ የባህርና የምድረ-በዳ ጉዞ ተርፈው በየመን ባህር ዳርና፤ በረሃ፤በተባበሩት መንግሥታት ጣቢያዎች የተጠለሉ ወገኖቻችን በሀገሪቱ ወሮበሎችና ዘራፊዎች፤በሕገ ወጥ መንገድ ስዎችን ከአንዱ ሀገር ወደ ሌላ ሀገር በከፍተኛ ገንዝብ በማስተላሰፍ የሚነግዱ እንደዚሁም በሳውዲ አውሮፕላኖች ቦምብ እየተደበደቡ የሚያልቁት ኢትዮጵያኖች ሕይወት በከንቱ ማለፉ የማይጠፋ እሳት በልባችን ጭሮብናል።

በደቡብ አፍሪካ ዘርፎ-በሎች አማካኝነት በወገኖቻችን ላይ ስለሚደርስው ግፍ በተከታታይ በዜና ማስራጫዎች እንደምንሰማው ፤ በእሳት አቃጥሎ የመግደልና አይን ያወጣ ዘረፋ አስቆጥቶናል፤ አሳዝኖናል። የሀገራቸውን አምባገነን መንግሥት ሲሸሹ የተሳፈሩበት ጀልባ በመስመጡ በየጊዜው ህይወታቸው የሚያልፈው ኢትዮጵያውያኖች፤ ሌሎች አፍሪካውያንና በየመን በረሃ የስውነታቸውን አካል  ለሕክምና ጥቅም ለማዋል ሲባል በየጊዜው የሚገደሉት ወገኖች ሰቆቃ እጅግ በጣም አስቆጥቶናል። በእነኝህ  አረመኔአዊ ወንጀሎች እኚስ በወጣት ወገኖቻችን ላይ ከሚደርሱት በይፋ ከሚታወቁት ወንጀሎች በጣም ጥቂቶቹ ናቸው። ከነዚህም ውስጥ በሳውዲ አረቢያ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን የተባረሩበት፤ሴቶች በጉልበት የተደፈሩበት፤ ንብረታቸው የተዘረፈበት፤ በቤይሩትና በሌሎች የመካከለኛው ምስራቅ አረብ ሀገሮች በሚደርስባቸው አሰቃቂ ግፍ የተነሳ ወገኖቻችን ሀይወታቸውን ለማጥፋት የተገደዱበት ይገኙበታል።

የዚህ ሁሉ ችግር መንሣኤና ምንጩ ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑ መታወቅ አለበት። የቀይ ሽብር ከተካሄደበት እ ኤ አቆጣጠር እስከ 1970ው አጋማሽ ድረስ ኢትዮጵያ በስደተኞች ቁጥር አንጻር ዝቅተኛ ደረጃውን የያዘችና ወደ ሀገራቸው በሚመለሱት ከፍተኛ ደረጃውን የያዘች ነበረች። ከ 1970 ዓ ም ጀምሮ በሀገሪቱ የሰብዓዊ መብቶች አለመከበርና የግፍ አገዛዝ እንደዚሁም በከፍተኛ የሥራ እጦት ምክንያት ወጣቱ ህይወቱን ለአደጋ እያጋለጠ በገፍ ሀገር ለቆ ለመኮብለል ተገዶአል። የቤተስብ ችግር ያስጨነቃቸው ወጣቶችና  በስደተኞች በሚላክ የሚተዳደሩት ሁለቱ ፓራሳይት፤ ግዴለሽና አምባገነን መንግሥታት ምክንያት የኢትዮጵያና የኤርትራ ወጣቶች የሚገጥማቸውን አደጋ ቢያውቁም እንኽዋን አደገኛውን የቀይ ባህር አቋርጠው መሰደዱን እንደሚመርጡ በግብር አሳይተዋል።

ይበልጥ የሚያሳዝነው የኢሐደግ መንግሥትና ኢምባሲዎቹ ከዜጎቹ ጋር ከመወገን ይልቅ የተፈጸመውን ግፍ አጣጥሎ “ስደተኞቹ ሕገ ወጦች ናቸው” በማለት ከአንድ መንግሥት የማይጠበቅ ተግባር መፈጸሙ ነው። በሊቢያ የተስውቱን ወገኖች አስመልክቶ የዓለም ህዝብ በተለያዩ የሜድያ አውታሮች ኢትዮጵያዊነታቸውን እየገለጹና የሞዋች ቤተስቦች እያሉ የኢሐደግ መንግሥት “ሞአቾቹ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን እያጣራሁ ነው” በማለት በሕዝባችን ላይ ሲያላግጥ መክረሙ ነበር።

ማናቸውም በራሱ የሚተማመን መንግሥት ዜጎቹ በአሰቃቂና በግፍ ሲገደሉ በይፋ የሚታየውን ሁኔታ እያጣራሁ ነው በማለት በሕዝብ መራራ ሀዘን ላይ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻና ማላገጥ አያደርግም ነበር፤በሀገሪቱ በይፋ ተስፋፍቶ የሚገኘውን ሥራ አጥነት ችግር ፈጽሞ እንደሌለ ለማስመል አይሞክርም ነበር። ከስሞኑ የወገኖቻንን የግፍ ግድያ አስመልክቶ በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች የሚደረጉ ስላማዊ ስልፎችን ተክትሎ የተሳተፉትን ወገኖች በአገዛዙ ላይ ተቃውሞ ተናገራችሁ በማለት ክፉኛ በመደብደብና በማቁሰል ሕዝባችንን በማስቃየት ላይ ይገኛል። ረብሻ ያስነሳሉ በሚል ክስም በአሁኑ ወቅት ከ 500 በላይ የሆኑ ወጣቶች በሰማያዊ ፓርቲ ስም ታፍሰው ገሚሱም ከየቤታቸው ተለቅመው ታሥረዎል።

 

ስለሆነም “ኢትዮጵያዊነት፤ የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባኤ” ጥሪውን ለወገኖቹና ለዓለም ሕብረተሰብ እንደሚከተለው  ያቀርባል:-

  • የኢትዮጵያ መንግሥት በአልባሌ ምክንያት ከሀላፊነቱ ለመሽሽ መሞከሩ እንደማይጠቅመው ተገንዝቦ፤ ወገን ሳይለይ የዜጎችን መብት በማክበር የሚጠብቅበትን ግዴታና ሀላፊነት እንዲወጣ፤ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አሁንም ለሚደርስባቸው ግፍና በደል አስፈላጊውን የመከላከያ እርምጃ እንዲወስድ እናሳስባለን። ለአደጋ ተጋልጠው ለሚገኙ ወገኖችም ተፈላጊውንና ተገቢውን አስቸክዋያ እርዳታ እንዲሰጥ እንጠይቃለን።
  • ድምጻቸውን በአደባባይ በማሰማታቸውና በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ አለአግባብ ያሰራቸውን በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የፓለቲካና የሕሊና እሥረኞች በአስቸኽዋይ እንዲፈታ እንጠይቃለን። በሕገ መንግሥቱ የተፈቀዱ የሰብዓዊ መብቶችን ማፈኑንና መርገጡን በአስቸክዋይ እንዲያቆም እንጠይቃለን።
  • የሳውዲ አረብያ፤የሊቢያ፤የየመንና የደቡብ አፍሪካ መንግሥታት ዓለም አቀፍ ስደቶኞች መብትና ሕግጋት ዉሎች መሰረት ሀላፊነታቸውን በሚገባ መወጣት ይጠበቅባቸዋል። ስለሆነም በሀገራቸው ውስጥ በወገኖቻችን ላይ ለተፈጸመው ወንጀል በሙሉ ለጠፋው ሕይወትና ንብረት ለቤተስቦቻቸው ካሣ ለመክፈል ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ እንጠይቃለን።
  • የአውሮፓ ህብረትና የአሜሪካ መንግሥት በእነዚህ ሀገሮች (አፍጋንስታን፤ሊቢያ፤ ሶማሊያ፤ሲሪያና የመን) ላይ በሚከተሉት የሞናጋት ፖሊሲና በሚወስዱት እርምጃ ሳቢይ የስደተኞች ቁጥር እየናረ መሄዱን የሚያውቁት ሲሆን ለተፈጠረው ችግር መፍትሄውን መጋራት ይኖርባቸዋለን እንላለን። የጥቅም-መር ፓሊሲያቸውን ለማራመድ ሲሉም በተለይም ሕዝብ ካልመረጣቸውና ካልተቀበላችው አምባገነን መንግሥታት ጋር በማበር የሚፈጽሙት ተግባር ችግሩን የበለጠ አስከፊ እንዳደረገው ተገንዝበው ኅላፊነቱን መጋራት ይኖርባቸዋል። ኅያላን መንግሥታት የውች ጉዳይ ፓሊሲዎቻቸው ስለባ የሆኑትን በስብዓዊ ርኅራሄ እንዲታደጉና ችግሩን ከማፈን እንዲቆጠቡ እንጠይቃለን። እንዲሁም፣
  • የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን የስደተኞች መብት በማስከበርና ከአደጋ በመከላከል የጦርነት ቀጠና ከሆኑት ከሊቢያና ከየመን ወደ ሰላማዊ ቦታ በአስቸክዋይ በማዛወር ዓለም አቀፋዊ ግዴታውን በብቃት እንዲወጣ አጥብቀን እንጠይቃለን።

 

በመጨረሻም ሀላፊነቱ በመላው ዓለም በምንኖር ኢትዮጵያኖችና የኢትዮጵያ ወዳጆች ላይ የተጣለ ስልሆነ፡ ይኅውም የስብዓዊ መብት ረገጣውን በመቅዋቃም የተጀመረውን እንቅስቃሴ አጠናክረን በመቀጥል፤ እንደዚሁም አስፈላጊ ድጋፍና እርዳታ ለተጎጅዎቹ በአስቸክዋይ በማድረስ፤ በዚህ አክዋያ በየጊዜው ለሚፈጠሩ ሁኔታውችን ተከታትሎ ለዓለም ህብረተሰቡ በማሳወቅና በማጋለጥ የወገኖቻችንና የውድ ሀገራችንን ችግር መታደግ ግዴታችንና ሀላፊነታችን እንደሆነ ለማስገንዘብ እንወዳለን።

 

ኢትዮጵያ ለዘላለም በልጽጋና ተከብራ ትኖራለች!

 

ኢትዮጵያዊነት፤ የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባኤ

www.ethiopiawin.com

 

The post በአፍሪካና በመካከለኛው ምሥራቅ በወገኖቻችን ላይ በደረሰው የግፍ ግድያ ተናደናል፣ አዝነናል፣ተቆጥተናልም! appeared first on Zehabesha Amharic.

በኦሮሚያ ሰበታ አንድ የመድረክ አባል ተገደለ

$
0
0

Zehabesha News
በኦሮሚያ ክልል ሰበታ በተባለው ቦታ አንድ የመድረክ አባል ግለሰብ በጉጅሌው የኢህአዴግ ፀጥታ አካላት እንደተገደለ ተገለጸ።

የደህሚት ድምጽ ያገኘው መረጃ እንዳመለከተው በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የተቃዋሚ ድርጅት አባላት በስርአቱ የታጠቁ ሃይሎች እየደረሰባቸው ያለው የማስፈራራት ዛቻ አልበቃ ብሏቸው ከተማ ፋፎ የተባለውን የመድረክ አባል ሚያዚያ 12/ 2007 ዓ/ም 2:00 ሰአት አመሻሽ ወደ ስራው እየሄደ በነበረበት ጊዜ በኢህአዴግ የፀጥታ አካላት እንደተገደለ ለማወቅ ተችሏል።

የግለሰቡ መገደል ሁኔታ ገዢው የኢህአዴግ ስርአት እየተከተለው ያለውን የግብር አከፋፈል ሂደት በፅናት እየተቃወመው የነበረ በመሆኑ ብቻ እንደሆነና በጉጅሌው አይን እይታ በመውደቁ ሊገደል እንደቻለ የገለፀው ምረጃው እንደዚ አይነት በሰላማዊያን ድርጅት አባላቶች ላይ እየተወሰደ ያለው አሰቃቂ የግድያ ተግባርም ስርአቱ እየቀጠለበት መሆኑን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።

The post በኦሮሚያ ሰበታ አንድ የመድረክ አባል ተገደለ appeared first on Zehabesha Amharic.


በኦስትርያ ቬየና ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

$
0
0

austria

austria 2

austria 4
(የአብስራ ዳኛቸው)

ISIS፣ ደቡብ አፍሪካ፣ የመን እና አልሻባብ ወገኖቻችን ላይ እያደረሱ ያለውን በደል በመቃወም ኢትዮጵያዊያን፣ ኤርትራዊያን እና ሌሎች የአፍሪካ አገሮች አንድ ላይ በመሆን ነበር በ 29.04.2015 በቬየና ይህን ሰላማዊ ሰልፍ ያደረግነው። ይህ ሰልፍ ከሾቶንቶር ዩንቨርስቲ አንስቶ መዳረሻውን ስቴፈን ፕላትዝ ነበር። በዚህ ሰልፍ ላይ የተለያዩ መፈክሮች የተሰሙ ሲሆን ከነዚህም መካከል STOP GEWALT GEGEN IMMIGRANTEN, GEGEN MENSCHEN LÖTEN MENSCHEN, ISIS & TPLF ARE TERRORIST THEY KILLED INNOCENT ETHIOPIAN, EU STOP SUPPORTING TPLF, STOP ALSHABAB የሚሉት ይገኙበታል።

ማንኛውም ህዝብ ከሀገሩ ተሰዶ በባዕድ ሀገር ኑሮውን ለመግፍት የሚገደደው፣ በባህር ላይ ህይወቱን እንዲያጣ የሚደረገው እንዲሁም በአሸባሪዎች አንገት ለመቀላት ምክንያት የሚሆነው በሀገሩ ላይ ያለው የፖለቲካ አለመረጋጋት እና በሀገሩ ላይ በነፃነት መኖር ባለመቻሉ ነው።

ለምሳሌ የሀገራችንን የኢትዮጵያን ብንመለከት ህዝቡ ለስደት የሚዳረገው አምባገነን የሆነ አንድ ቡድን ሀገራችንን በእጅ አዙር ቀኝ ግዛት ስለገዛት የመናገር፣ የመፃፍ፣ የመደራጀት፣ የፈለገውን ፖርቲ የመደገፍ መብቱ ተረግጦ እኔ ብቻ ያልኩት በማለት ወጣቱን በከፍተኛ ሁኔታ በማኮላሸት እና ተስፍ መቁረጥ ውስጥ እንዲገባ በማድረግ የስራ ማጣት፣ ተምሮ እንዳልተማረ በማድረግ፣ የወያኔ አባል ካልሆኑ ምንም አይነት ተስፍ እንዳይኖራቸው በማድረግ ሀገራቸውን ለቀው ወደ አልፈለጉት ሀገር ህገወጥ በሆነ እና ህይወታቸውን ለከፍ አደጋ ለሚጥል ስደት እንዲዳረጉ አድርጓቸዋል። ለዚህም ነው ወገኖቻችን በደቡብ አፍሪካ በጎማ የተቃጠሉት፣ በየመን የተገደሉት፣ በሜድትራኒያ ባህር ውስጥ የሰመጡት እና በሊቢያ የተሰውት። ይህም አጉልቶ የሚያሳየው በሀገራችን ላይ ያለውን የፖለቲካ እና የአስተዳደር ችግር ነው። ምክንያቱም ሰው ቢደላው ከሀገሩ ባልተሰደደ ፣ ባልተዋረደ፣ በቢለዋ ባልታረደ፣ ከፎቅ ባልተወረወረ፣ በእሳት ባልተቃጠል ነበር። ለዚህም ነው ለአውሮፓ ህብረት እና ለኦስትርያ መንግስት ድምፃችንን ያሰማንነው።
በሚያሳዝን ሁኔታ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን እግዚአብሄር አምላክ ነፍሳቸውን ይማርልን መንግስተሰማያት ያዋርስልን ለቤተሰቦቻቸው እና ለኢትዮጵያ ህዝብ መፅናናትን እመኛለሁ።

The post በኦስትርያ ቬየና ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ appeared first on Zehabesha Amharic.

9 የጦር መኮንኖች ስርዓቱን ጥለው ጠፉ * ሃምሳ አለቃ ዓሊ እንዴሬና ምክትል አስር አለቃ ከበደ አበጀ ይገኙበታል

$
0
0

Zehabesha News
በማእከላዊ እዝ የ23ኛና 33ኛ ክፍለጦር የኢህአዴግ ስርአት ሰራዊት አባላት እየደረሰባቸው ባለው የአስተዳደር ግድፈትና የኑሮ ችግር ምክንያት ተማርረው በመጥፋት ላይ እንደሚገኙ ታወቀ::

የደሀሚት ድምጽ እንደዘገበው የማዕከላዊ እዝ 23ኛና 33ኛ ክፍለጦር የሰራዊት አባላት የሆኑት ወታደሮች ሃምሳ አለቃ ዓሊ እንዴሬ፤ ምክትል አስር አለቃ ከበደ አበጀና ወታደር መሳይ፤ የሚገኙባቸው በሃላፊዎቻቸው እየወረደባቸው ያለውን የአስተዳደር አድልዎና የኑሮ ውድነትን ሊቋቋሙት ባለመቻላቸው ምክንያት ሰራዊታቸውን በመተው ጠፍተዋል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ የ24ና የ48 ሰአት ፋቃድ እንዲሰጣቸው በመጠየቅ በሽራሮ ከተማ እንዲገናኙ ተቀጣጥረው አንድ ላይ ሁነው የጠፉት. 2 ምክትል የአስራ አለቃ፤ 3 የአስራ አለቃ፤ 3 ተራ ወታደሮችና አንድ የአምሳ አለቃ በጠቅላላ 9 የኢህአዴግ መከላከያ ሰራዊት አባላት ሚያዚያ 14 /2007ዓ/ም ብቻ፣ ክፍላቸውን ትተው እግራቸው ወዳመራቸው እንደጠፉ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።

The post 9 የጦር መኮንኖች ስርዓቱን ጥለው ጠፉ * ሃምሳ አለቃ ዓሊ እንዴሬና ምክትል አስር አለቃ ከበደ አበጀ ይገኙበታል appeared first on Zehabesha Amharic.

በሊቢያ የተገደሉት ኢትዮጵያውያን እስካሁን የ14ቱ ማንነት ተለይቷል * አያልቅበት ስንታየሁና ብርሃኑ ጌታነህ ማንነታቸው ተለይቷል

$
0
0

birhanu getaneh

Ayalkibet sintayehu
(ዘ-ሐበሻ) በሊቢያ በአይሲኤል አንገታቸውን በመታረድ እና በጥይት በመመታት ሕይወታቸውን ያጡት 28 ኢትዮጵያውያንን ማንነት ለማወቅ የሚደረገው ጥረት እንደቀጠለ ነው:: እስካሁን የ12ቱ ማንነትን በዘ-ሐበሻ ላይ አቅርበንላችሁ ነበር:: ዛሬ ደግሞ የ2ቱ ማንነት ታውቋል በሚል በመንግስት ሚድያዎች ተዘግቧል::

እንደ መንግስት ሚድያዎች ዘገባ አሁን ደግሞ አቧሬ እና ገርጂ አካበቢ ነዋሪ የነበሩ ሌሎች ወጣቶች በአይ ኤስ መገደላቸው ታውቋል። ወጣቶቹ አያልቅበት ስንታየሁ እና ብርሃኑ ጌታነህ ይባላሉ።

አያልቅበት የ30 አመት ወጣትና ከሶስት አመት በፊት ወደ ሱዳን ያቀና ሲሆን፥ ከእናቱ ጋር ሲኖር የነበረ መሆኑን ከቤተሰቦቹ የተገኘው መረጃ ያመለክታል::
አያልቅበት ስንታየሁ ብቸኛ ልጃቸው እንደነበርም እናቱ ተናግረዋል ።

ብርሃኑ ጌታነህ ደግሞ ባለትዳር እና በፎቶግራፉ ላይ እንደምንመለከተው የስምንት እና የአራት አመት ልጆች ያሉት ወጣት ነበር ። በአዲስ አበባ አቧሬ አካባቢ ይኖር የነበር ሲሆን፥ ከአገር ከወጣ አራት ወር አልፎታል። ባለቤቱ ብርቱካን ጌቱ ስትባል በአሁኑ ወቅት ባለቤቷን ማጣቷ ተደራራቢ ችግር ላይ እንደጣላት ገልፃለች።

እስካሁን ያወቅናቸው፦
1. ኢያሱ ይኵኖአምላክ
2. ባልቻ በለጠ
3. ዳንኤል ሐዱሽ
4. ቡሩክ ካሳሁን
5. ኤልያስ ተጫኔ
6. በቀለ ታጠቅ
7. በቀለ አርሰማ
8. ዳዊት ሐድጉ
9. መንግሥቱ ጋሼ
10. ጀማል ራህማን
11. አወቀ ገመቹ
12. እንዳልክ ሐጎስ አየለ
13. ብርሃኑ ጌታነህ
14. አያልቅበት ስንታየሁ

The post በሊቢያ የተገደሉት ኢትዮጵያውያን እስካሁን የ14ቱ ማንነት ተለይቷል * አያልቅበት ስንታየሁና ብርሃኑ ጌታነህ ማንነታቸው ተለይቷል appeared first on Zehabesha Amharic.

ሶፊያን አህመድ በዋሽንግተን ዲሲ ተዋረደ * የወያኔ ተላላኪዎች በዲያስፖራው ውሻ መሆናቸውን ቀጥለዋል (Video)

$
0
0

ሶፊያን አህመድ በዋሽንግተን ዲሲ ተዋረደ * የወያኔ ተላላኪዎች በዲያስፖራው ውሻ መሆናቸውን ቀጥለዋል
በውጭ ያለው ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የወያኔ ተላላኪ ባለስልጣናትን እና የወያኔ ባለስልጣናትን እንደውሻ አሳፍሮ ወደ መጡበት መመለሱን ቀጥሎበታል:: መለስ ዜናዊ.. አቦይ ስብሃት.. ሬድዋን ሁሴን… ህላዊ ዮሴፍ.. ቴዎድሮስ አድሃኖም… አባዱላ ገመዳ… እስካሁን ከተዋረዱት መካከል ሲጠቀሱ አሁን ደግሞ የገንዘብ ሚኒስትሩ የሕወሓት ተላላኪ ሶፊያን አህመድ ቀልቡን በዋሽንግተን ዲሲ ተገፎ ወደ መጣበት ተመልሷል:: ቭዲዮ::

sofian_ahmed

The post ሶፊያን አህመድ በዋሽንግተን ዲሲ ተዋረደ * የወያኔ ተላላኪዎች በዲያስፖራው ውሻ መሆናቸውን ቀጥለዋል (Video) appeared first on Zehabesha Amharic.

በአይሲስ ላይ ኢትዮጵያ የሃይል እርምጃ መውሰድ አለባት ያሉ የሠራዊቱ አዛዦች ታሰሩ

$
0
0

ethiopians isis
ሊቢያ ውስጥ አይ ኤስ በተባለው አሸባሪ ቡድን በዜጎች ላይ የተፈፀመውን ግፍ የተሞላበት ግድያ መንግስት ፈጣን ግብረ መልስ መስጠት አለበት በማለት የጠየቁ የሰራዊት አዛዦች እየታሰሩ መሆናቸውን ምንጮች ሲል የደህሚት ድምጽ ዘገበ::

ለደህሚት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው የምዕራብ እዝ 7ኛ ሜካናይዝድ የሬጅመንት ምክትል አዛዥ ሻለቃ ሙሉአለም የተባለ መኮነን የኢህአዴግ ገዥው መንግስት በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ እንዲሁም በየመን በኢትዮጵያውያን ዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ላለው አስቃቂ ግፍ መንግስት ፈጣን ግብረ መልስ መስጠት አለበት ብሎ ስለጠየቀ ብቻ ፀረ ሰላም ነህ ተብሎ ባህር ዳር መኮድ በተባለ ቦታ እንደታሰረ ምንጮቻችን አስታወቁ።

ስርዓቱ በአይ ኤስ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ፍላጎት ስለሌለው የዜጎቻችንን ደም መመለስ አለብን የሚል ጥያቄ ለሚያነሱ ሰዎች እንደ ጠላት እያዬ ወደ እስር ቤት እያስገባቸው እንደሚገኝ የገለፀው ይህ መረጃ የመከላከያ ሰራዊትም በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ላለው የሚያሳዝን ተግባር ዋነኛ ተጠያቂው በስልጣን ላይ ያለው የኢህአዴግ ስርዓት መሆኑን በተደጋጋሚ እየገለፁ እንደሚገኙ ምንጮቻችን ያደረሱን መረጃ ገልጿል።

The post በአይሲስ ላይ ኢትዮጵያ የሃይል እርምጃ መውሰድ አለባት ያሉ የሠራዊቱ አዛዦች ታሰሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

በሶማሊያ የባህር ዘራፊዎች ታፍኜ ነበር –“ሁላችንም በፍርሐት ውስጥ እንድንገባ አደረጉን; ግርፋቱንና ስቃዩን በአይኔ ባላየውም ጩኸቱን ግን እሰማው ነበር”

$
0
0

ባለፈው አመት ሚያዝያ ላይ ነበር ሙምባይ ውስጥ በሚገኝ የኬሚካል ኩባንያ አማካኝነት የባህር ሐይል ኦፊሰር ለመሆን ስልጠና የወሰድኩት። ስራችንን ለመጀመር ወደ መርከቧ የተሳፈርነው ሰዎች እኔን ጨምሮ 22 ነበርን፡፡ ከህንድ የተውጣጡ ፕሮፌሽናል መርከበኞች እና ኢንጂነሮች ይገኙበታል። መርከቧ ላይ ከተሳፈርነው ሰዎች መካከል በእድሜ ትንሹ እኔ ነበርኩ፡፡ 21 ዓመቴ ነው፡፡
alshebab
መርከባችን የተነሳችው ከህንድ ሲሆን አቅጣጫዋ ደግሞ ወደ ኖርዌይ ነበር፡፡ ጉዞው 25 ቀናቶችን ይወስዳል፡፡ ጉዞ በጀመርን በአራተኛው ቀን ላይ አንድ ባልደረባችን ከፊት ለፊታችን የምትመጣውን ጀልባ ተመልክቶ ጩኸቱን አቀለጠው፡፡ ከኦማን 120 ማይል በሚርቅ ባህር ላይ ነበርን፡፡ ይህ ክልል ደግሞ አደገኛና አስፈሪ ነው፡፡ የጀልባዋን አመጣጥና መጠን ተመልክተን ዘራፊዎች መሆናቸውን አወቅን፡፡

ወዲያውኑ ህንድ ውስጥ ላለው የባህር ሐይል ጣቢያ የሬዲዮ ግንኙነት አደረግሁኝ፡፡ ነገር ግን ዘግይቼ ነበር፡፡ በደቂቃዎች ውስጥ ስድስት የባህር ዘራፊዎች መርከባችን ላይ በመንጠላጠል የጥይት እሩምታ ከፈቱብን፡፡ በጣም አስፈሪና አስደንጋጭ ነበር፡፡ እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አልነበረንም።
ወዲያውኑ በቀማኞቹ እየተገፈተርን ወደ ሞተር መቆጣጠሪያው ክፍል ውስጥ ገባን፡፡ ወለሉ ላይ በደረታችን እንድንተኛ ታዘዝን፡፡ ዘራፊዎቹ ለምንሰራለት ኩባንያ የ15 ሚሊዮን ዶላር ጥያቄ እንደሚያቀርቡና ገንዘቡን ካላገኙ እንደሚገድሉን በተሰባበረ እንግሊዝኛ ደነፉብን፡፡ ከፍተኛ ፍርሐት ዋጠን፡፡ እስከ ቀጣዩ ጧት ድረስ ሁላችንም ከተኛንበት ወለል ላይ ሳንንቀሳቀስ በዝምታ አሳለፍን፡፡ ሌሎች 6 ዘራፊዎች መርከባችንን ከተቀላቀሉ በኋላ ወደ ሶማሊያ ሊወስዱን እንደሆነ ነገሩን፡፡

በመርከብ ላይ ታፍነን ያሳለፍነው አስቸጋሪ ህይወት እንዲህ በቀላሉ የሚነገር አልነበረም፡፡ በመቆጣጠሪያው ክፍል ውስጥ በየጥጉ ኩርምት ብለን ተቀምጠናል፡፡ መስኮት የሌለው ክፍል በመሆኑ የታፈነ አየር ለመሳብ ተገደናል፡፡ መፀዳጃ ቤት እንድንጠቀም ቢፈቀድልንም ተበላሽቶ በመጥፎ ጠረን ታውዷል፡፡ በዚህ ምክንያት ሁላችንም ታመምን፡፡ ምግብ የሚሰጠን በሳምንት ሁለት ጊዜ ብቻ ነው፡፡ እሱም ህይወታችንን ለማቆየት እንዲረዳን ያህል ከድንች እና ሽንኩርት የተሰራ ነበር። በኋላ ላይ እግራችንን እንድንዘረጋ ስለፈቀዱልን ትንሽ ተንፈስ አልን፡፡

ዘራፊዎቹ የደቀኑብን ጠብመንጃ የማምለጥ ተስፋችንን ገድሎታል፡፡ ከነሱ ጋር ወዳጅነት እንዳንፈጥር ደግሞ ዘወትር ያስፈራሩናል፣ ይደበድቡናል፡፡ በኔ ላይ መጥፎ ድብደባ እንዳይደርስብኝ የተቻለኝን ባደርግም ባልደረቦቼ ግን ክፉኛ ሲቀጠቀጡና ሲሰቃዩ ተመልክቼያለሁ። አንደኛውን ባልደረባዬን በኤሌክትሪክ አሰቃይተውታል፤ ሌላኛውን ደግሞ ከብረት ጋር ጠፍረው በማሰር ለረዥም ሰዓት ደብድበውታል። በሌላኛው ክፍል ውስጥ የነበሩ ወዳጆቼ እንደሚሰቃዩ በድምፃቸው አረጋግጫለሁ፡፡ አሁን ድረስ የስቃይ ድምፃቸው ያቃጭልብኛል፡፡ እኔን ልክ እንደ ሌሎቹ ባልደረቦቼ ለምን ብዙ እንዳላሰቃዩኝ አላውቅም፡፡ ምን አልባት ገና ለጋ አልያም የማልጠቅም መሆኔን ተረድተው ይሆናል።

አንዳንድ ባልደረቦቼ ከዘራፊዎቹ ጋር ይፋጠጡ የነበረ ቢሆንም እኔ ግን ከእንዲህ መሰሉ ነገር እጠነቀቅ ነበር፡፡ በእያንዳንዱ ቀን ጧት፤ ከተኛሁበት የብረት ወለል ላይ ስነቃ በዚያው ቀን እንድሞት እመኝ ነበር። ወዲያው ደግሞ ራሴን በማረጋጋት የወደፊቱን ለማየት እቅበጠበጣለሁ፡፡ ማድረግ የቻልኩት ግን ዝም ብዬ መጠበቅ ነበር፡፡ አልፎ አልፎ ከመካከላችን ውስጥ አንደኛችንን መርጠው ህንድ ለሚገኘው ኩባንያችን እንድንደውል ያደርጉ ነበር፡፡ እኛም በተሰጠን የስልክ እድል ተጠቅመን ህይወታችንን እንዲታደጉልን የኩባንያ ሰዎቻችንን እንማፀናለን፡፡ እነሱ ግን የገንዘቡ መጠን እስካልተቀነሰላቸው ድረስ ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ይነግሩናል፡፡

በመጀመሪያዎቹ አራት ወራቶች ውስጥ፤ በወር አንድ ጊዜ ከቤተሰቦቻችን ጋር በስልክ እንድንገናኝ ተፈቀደልን፡፡ ዘራፊዎቹ ይህን ያደረጉት ቤተሰቦቻችን ኩባንያ ላይ ግፊት እንዲያደርጉ ነበር። ነገር ግን ከቤተሰቦቻችን ጋር ገና ጥቂት ቃላቶችን ብቻ እንደተለዋወጥን ስልኩን ይነጥቁናል፡፡ ከስልኩ መቋረጥ ጋር የኛም አንጀት አብሮ ይቆረጣል፡፡

ገንዘቡ ሳይከፈል ብዙ ወራቶች ካለፉ በኋላ ዘራፊዎቹ ካፒቴናችንን ወስደው በሌላ ጀልባ ለብቻው አስቀመጡት፡፡ ይገድሉታል በሚል ሁላችንም ጭንቀት ውስጥ ገባን፡፡ እነሱ ግን ኩባንያው የተጠየቀውን ገንዘብ እንዲከፍል አሁንም የበለጠ እንድንለምን ነገሩን፡፡ ከ238 ቀናቶች በኋላ፣ እንድናለን ብለን ባልገመትንበት ሰዓት ኩባንያችን አምስት ሚሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ፡፡ የጀርመን መርከብ ሊወስደን እንደሚመጣም ተነገረን፡፡ ዘራፊዎቹ ገንዘባቸውን ካገኙ በኋላ ሌላ ጀልባ ላይ ተሳፍረው ከአካባቢው ጠፉ፡፡ የተባለችው የጀርመን መርከብ መጥታ ስትወስደን ደስታዬ ወደር አልነበረውም፡፡ ከ238 ቀናት በኋላ አይኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ብርሐን አየ፡፡ ደንዝዤ ስለነበረ አላለቀስኩም፡፡ ሌሎቹ ግን እየነፈረቁ ነበር፡፡ ለቅሷቸውን መቆጣጠር አልቻሉም፡፡ እኔ እንደገና የተወለድኩ ያህል ነበር የተሰማኝ። ለመጀመሪያ ጊዜ የበላሁት ምግብ፣ የወሰድኩት ሻወር፣ የቀየርኩት ልብስ ሁሉ ለኔ የማይታመን እንግዳ ነገር ነበር፡፡ ከስድስት ቀናት በኋላ ቤተሰቦቼ ጋር ተቀላቀልኩ። ሰውነቴ ከመክሳቱ በተጨማሪ ሁለመናዬ አስቀያሚ ሆኗል፡፡ ይህን ጉስቁልናዬን የተመለከቱት ቤተሰቦቼ በጣም አለቀሱ፡፡ ወደተከራየሁት መኖሪያ እንደተመለስኩ መርከብ ላይ በተፈጠረብኝ አጠቃላይ ሁኔታ ንዴቴን መቆጣጠር አቅቶኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ምንም አይነት ህክምና ለመውሰድ አልፈለግሁም፡፡ በህይወቴ ውስጥ የተፈጠረው ይህ አስቀያሚ አጋጣሚ ስራዬን እንድተው አላደረገኝም፡፡ እንዲያውም ተጨማሪ የመርከበኝነት ስልጠና ከወሰድኩ በኋላ እንደገና ወደ ባህር ስራዬ ተመለስኩ፡፡ ዘራፊዎቹ የህይወቴን አቅጣጫ እንዲቀይሩት አላደረግሁም፡፡ ጉዳቱን እንደሆነ አንዴ ቀምሼዋለሁ፤ ከዚህ በላይ ምኔን ይጉዱት?
(ዲፔንድራ ይሀንን ታሪኩን በራሱ ድምፅ ቀርፆ በኢንተርኔት ለቆታል፡፡)

Source: Addis Admass Newspaper

The post በሶማሊያ የባህር ዘራፊዎች ታፍኜ ነበር – “ሁላችንም በፍርሐት ውስጥ እንድንገባ አደረጉን; ግርፋቱንና ስቃዩን በአይኔ ባላየውም ጩኸቱን ግን እሰማው ነበር” appeared first on Zehabesha Amharic.

ያሬድ ጥበቡ ስለ ህላዌ ዮሴፍ፣ ታምራት ላይኔ፣ ዳዊትና ሙሉአለም አበበ የትናትና የዛሬ ማንነት ይናገራል (ሊያነቡት የሚገባ)

$
0
0

ያሬድ ጥበቡ በትግል ስማቸው ጌታቸው ጀቤሳ ይህን ጽሁፍ ያሰፈሩት በፌስቡክ ገጻቸው ነበር:: ለግንዛቤ ይረዳል ብለን በማሰብ አካፍለናችኋል::
Getachew Jebesa
ይህ ፎቶ ከተነሳ 30 አመት ሆነው ። የካርቱምን የአራዊት መናኸሪያ (ዙ)፣ ስንጎበኝ የተነሳነው ነው ። ከግራ ወደቀኝ ህላዌ ዮሴፍ፣ ታምራት ላይኔ፣ ዳዊት፣ ሙሉአለም አበበና እኔ ነን ። ህላዌ በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ሲሆን፣ እኔ ታምራትና ዳዊት በአሜሪካ ስደተኞች ነን ። ሙሉአለም የኢህአዴግ የአዲስ አበበሰ ከንቲባ ሆኖ ካገለገለ በሁዋላ፣ አጨቃጫቂ ነበረ ከተባለ የብአዴን ስብሰባ መልስ፣ ባህርዳር ቤተመንግስት አልጋው ላይ ተንጋሎ ሳለ፣ መስኮቱ ክፍት ስለነበር ከውጪ በተወረወረ የእጅ ቦምብ መገደሉን ሰምቻለሁ ።

ዳዊት የወያኔ ባታሊየን ኮማንደር የነበረ ሲሆን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተሰዶ መጥቶ 22ኛ ና ፒ ስትሪት መገናኛ ላይ የቤንዚን ማደያ ተቀጣሪ ሆኖ ሲሰራ አየሁት ። እናም አዘንኩ ። በስንት ጦር ሜዳ ጀግንነቱን ያስመሰከረ የጦር መሪ ዝቅ ብሎ ለእለት ጉርሱ ሲማስን ማየት ልብ ደሰብራል ። ዝም ብሎ የወያኔ ጄኔራል በመሆን የፎቆች ባለቤት እንደማይኮንና፣ የፖለቲካ ሰልፍን ካላሰመሩ ትግሬነትም ሆነ ጀግንነት ብቻውን ፋይዳ እንደሌለው ዳዊት ጥሩ ምስክር ይመስለኛል ።

ታምራት ከእስር እንደተለቀቀ በስልክ የተገናኘን ቢሆንም፣ አልፎ አልፎ የጴንጤዎች ስብሰባ ላይ ሲያለቃቅስ በዩቱብ ከማየት ውጪ ሰምቼውም አግኝቼውም አላውቅም ። ወደ ሃይማኖት ፊቱን ማዞሩን አልጠላሁትም ነበር ። እኔ ራሴም ፊቴን ወደመንፈሳዊ ጥናቶች መልሼ እነ ኤካርት ቶሌን ማጥናት ጀምሬ ስለነበር፣ ታምራት “ከእንግዲህ ስለ ፍቅር አስተምራለሁ” ማለቱን ወድጄው ነበር ። በብቸኛው የስልክ ወሬያችንም ያንን የገለፅኩለት ይመስለኛል ። ሆኖም አሜሪካ ሲመጣ መገናኘት አልፈለገም ። የመጨረሻዎቹ የበረሃ አመታት ላይ አርሱ ከነመለስ ወግኖ የቆመ ቢሆንም፣ አግኝቼ ላወራው ግን ይናፍቀኛል ። የሆነው ሁሉ እንዴት እንደሆነ የርሱን ግንዛቤና አስተያየት ለማወቅ ሁሌም እፈልጋለሁ።

ከኢህአፓና ኢህዴን የበረሃ ህይወታችን በኋላ ከህላዌ ጋር የተገናኘነው ሁለት ጊዜ ነው ። አንዱ ከምርጫ 97 ሁለት ወራትበፊት አዲስ አበባ በሄድኩበት ወቅት፣ ምክትል ከንቲባ ሳለ አርከበ ቢሮ ውስጥ ያደረግነው አጭር ውይይት ነው ። ሌላ ጊዜ የተገናኘነው ከበረከት ጋር ዋሽንግተን መጥተው፣ አምባሳደር ብርሀኔ በቤቱ የራት ግብዣ አድርጎላቸው ሳለ ነው ። አመሻሽ ላይ ውጪ እናውራ ተባበለን በረንዳው ላይ ቁጭ ብለን ሳለ፣ ቃል አቀባይ ሶሎሜ ታደሰ መጣችና “ደህነታችሁን ለማረጋገጥ ነው” ብላ ቀለደች ። ህላዌም ሲመልስ “ነገ አንቺ ከሰልፈኛው ጎን ቆመሽ ይሰቀሉ እያልሽ ስትፈክሪ ሰለ ንፅህናችን የሚመሰክርልን ጀቤሳ ነው” ብሎ መለሰና ተሳሳቅን ። በቅርቡ ሶሎሜ ነፃ እጩ የፓርላማ ተወዳዳሪ ሆና ስትቀርብ በሎተሪ መጣሏን ስሰማ ይህችን ምሽት አስታወስኩ ።

የዚህ ፎቶና መጣጥፍም መልእክት ይሄው ይመስለኛል ። ትናንት የት ነበርን፣ ዛሬ የት ነን? የሚል ። ፖለቲካ ውስጥ መፋታትና መለያየት ተፈጥሯዊ መሆኑን ። ሆኖም መቃቃርና ጠላትነት ቦታ ሊኖረው እንደማይገባ። መለያየትም እስከመጨረሻው መሆን እንደሌለበተ ። እኔና ታምራት ከድርጅታችን ከተለየን ያካበትነውን የእውቀት፣ የመንፈሳዊነት ሀይል ይዘን ብንመለስ ኢህአዴግን እንዴት አድርገን ከገባበት አረንቋ ልናወጣው እንደምንችል ሳስበው “ወይ አለመታደል” እላለሁ ። እኔ እንደዚህ በአግራሞት ብዋጥም፣ ዛሬ ጠዋት ባህርዳር የሚገኘው የሰማእታት ሃውልት አስጎብኚ፣ ግድግዳው ላይ ከተሰቀለው ፎቶዬ ሥር ቆማ “ይህ ደግሞ ጌታቸው ጀቤሳ ይባል የነበረው የአመራር አባላችን ነው ። በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ የግንቦት ሰበት መሥራች ሆኖ፣ ዴሞክራሲያችንን በመፈታተን ላይ ይገኛል” እንዳለች ጉብኝት ላይ ከሚገኝ የሥራ ባልደረባዬ የቫይበር መልእክት ደረሰኝ ። አይገርምም የሰው ነገር? የአስቴር አወቀን “ለሰው ሞት አነሰው ትላለች ቀበሮ” ን እያዳመጣችሁ እስቲ አላምጡት ይህን ነገር ።

The post ያሬድ ጥበቡ ስለ ህላዌ ዮሴፍ፣ ታምራት ላይኔ፣ ዳዊትና ሙሉአለም አበበ የትናትና የዛሬ ማንነት ይናገራል (ሊያነቡት የሚገባ) appeared first on Zehabesha Amharic.


ሐዲስ ሐዋርያ አባ ወልደ ትንሳኤ “ከኤማሁስ መንደር ሊብያ ትበደር”በደብረ ፅዮን ድንግል ማርያም ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ካቴድራል

Next: Hiber Radio: በእስራኤል የዘረኝነት ጥቃት ሰለባ የሆኑ ኢትዮጵያውያን የጠነከረ ተቃውሞ ተከትሎ ባለስልጣናት ዘረኛ እርምጃ የወሰደውን ፖሊስ እናባርራለን ማለታቸው፣ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ያላትን አቋም እንድትመረምር መጠየቁ፣በየመን ያሉ ኢትዮጵያውያን ሞተን ሻማ ከማብራታችሁ በፊት በሕይወት ታደጉን ሲሉ ጥሪ አስተላለፉ፣ዶ/ር መረራ በአገር ቤት ያለው የወጣቱ ሁኔታ ምርጫ 97ን ያስታውሳል ማለታቸው፣ የመኢአድ አባላት እየታፈኑ መወሰድ መቀጠሉ፣ የጦማሪ ሶሊያና ሺመልስ ቃለ መጠይቅ እና ሌሎችም
$
0
0

ሐዲስ ሐዋርያ አባ ወልደ ትንሳኤ “ከኤማሁስ መንደር ሊብያ ትበደር” በደብረ ፅዮን ድንግል ማርያም ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ካቴድራል

 

debre

The post ሐዲስ ሐዋርያ አባ ወልደ ትንሳኤ “ከኤማሁስ መንደር ሊብያ ትበደር” በደብረ ፅዮን ድንግል ማርያም ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ካቴድራል appeared first on Zehabesha Amharic.

Hiber Radio: በእስራኤል የዘረኝነት ጥቃት ሰለባ የሆኑ ኢትዮጵያውያን የጠነከረ ተቃውሞ ተከትሎ ባለስልጣናት ዘረኛ እርምጃ የወሰደውን ፖሊስ እናባርራለን ማለታቸው፣ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ያላትን አቋም እንድትመረምር መጠየቁ፣በየመን ያሉ ኢትዮጵያውያን ሞተን ሻማ ከማብራታችሁ በፊት በሕይወት ታደጉን ሲሉ ጥሪ አስተላለፉ፣ዶ/ር መረራ በአገር ቤት ያለው የወጣቱ ሁኔታ ምርጫ 97ን ያስታውሳል ማለታቸው፣ የመኢአድ አባላት እየታፈኑ መወሰድ መቀጠሉ፣ የጦማሪ ሶሊያና ሺመልስ ቃለ መጠይቅ እና ሌሎችም

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ ሚያዚያ 25 ቀን 2007 ፕሮግራም

ጦማሪ ሶሊያና ሽመልስ በማዕከላዊ ምርመራ ሳሉ ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬና ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁን በመርማሪዎች የተፈጸመባቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ ያቀረቡትን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ለጠየቅናት ከሰጠችን ማብራሪያ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሀይማኖት ከየመን ሰንዓ ለህብር ከሰጠው ወቅታዊ ማብራሪያና የድረሱልን ጥሪ መልዕክቱ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

በእስራኤል የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በወገናቸው ላይ ለተወሰደው ዘረኛ እርምጃ ያሳዩት ቁጣ የተቀላቀለበት ተቃውሞና የባለስልጣናቱ ምላሽ (ልዩ ጥንቅር)

ውይይት በኦቲዝም ላይ

ኦቲዝም ምንድነው? የኦቲዝም ያለባቸውን ልጆች እንዴት ለይተን በጊዜ ተገቢውን የህክምና እርዳታ ማግኘት ይችላሉ? ኦቲዝም ያለባቸው ልጆችና ወላጆቻቸው በማህበረሰባችን የሚገጥማቸው ፈተና እና መፍትሄው

ከዶ/ር ኤፍሬም መኮንን ከአትላንታ፣ ሰናይት አድማሱ የስነ ልቦና ባለሙያ ከሎስ አንጀለስ እና ከዚያው ከተማ የሁለት ልጆች ወላጅ የሆነችው ወ/ሮ ፌቨን ፋንቱ ጋር ተወያይተናል(ሙሉውን ያዳምጡት)

ዶ/ር መረራ ጉዲና ስለ ወቅታዊው የፓርቲያቸው የምርጫ ቅስቀሳ እና በስርዓቱ ስለሚደረግባቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ ከሰጡን ማብራሪያ(ሙሉውን ያዳምጡ)

የክፍለ ዘመኑ የቡጢ ውድድር በቬጋስ እና የአሸናፊው ቡጢኛ ማይዌይዘርና የፓኩዋያ የቅዳሜ ምሽት ግብ ግብ(ውይይት)

አቶ ጸጋዬ አላምረው በስርዓቱ የፈረሰው የእውነተኛው አንድነት የም/ቤቱ ም/አፈ ጉባዔና የፓርቲው የፋይናንስ ሀላፊ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስደተኛው ሲኖዶስ የሊቢያ ሰማዕታትን በየዓመቱ ለመዘከር ወሰነ

ሕዝቡ አሸባሪዎቹን በወገኖቹ ላይ የወሰደውን የግፍ ግድያ ኢንዳያይና እንዳያሰራጭ ተጠይቋል

በየመን የሚገኘው አይሲስ የሱኒ አማጽያንን በጭካኔ ገደለ

የኢትዮጵያኑ እጣ ፋንታ አልታወቀም

የአሜሪካ መንግስት የአገር ቤቱን አገዛዝ ከማሞካሸት እንዲቆጠብና ስለ ኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት አያያዝ ትክክለኛ ምልከታ እንዲኖረው ተጠየቀ

ኤርትራ የኬኒያ ፕሬዝዳንት ሁሩ ኬኒያታ በአየር ክልሌ እንዳያመሩና ወደ አሜሪካ የሚያደርጉትን ጉዞ አላስተጓጎልኩም ስትል አስተባበለች

በየመን ያሉ ኢትዮጵያውያን የአሸባሪዎች ጥቃት ሰለባ ከመሆናችን በፊት በቁማችን ድረሱልን አሉ

ዶ/ር መራራ ጉዲና በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የወጣቱ ስሜት ምርጫ 97 የሚያስታውስ መሆኑን ገለፁ

የመኢአድ አባላት ታድነው እየታሰሩ ነው

የእስራኤል ባለስልጣናት በኢትዮጵያ ቤተ እስራኤላዊ ላይ የዘረኝነት ጥቃት የፈፀመው ፓሊስ ከስራ እንደሚባረር አስታወቁ

ጠ/ሚ/ር ኔታኒያሁ የኢትዮጵያውያኑን ተወካይ ሊያነጋግሩ ነው

የሚሉና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

The post Hiber Radio: በእስራኤል የዘረኝነት ጥቃት ሰለባ የሆኑ ኢትዮጵያውያን የጠነከረ ተቃውሞ ተከትሎ ባለስልጣናት ዘረኛ እርምጃ የወሰደውን ፖሊስ እናባርራለን ማለታቸው፣ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ያላትን አቋም እንድትመረምር መጠየቁ፣በየመን ያሉ ኢትዮጵያውያን ሞተን ሻማ ከማብራታችሁ በፊት በሕይወት ታደጉን ሲሉ ጥሪ አስተላለፉ፣ዶ/ር መረራ በአገር ቤት ያለው የወጣቱ ሁኔታ ምርጫ 97ን ያስታውሳል ማለታቸው፣ የመኢአድ አባላት እየታፈኑ መወሰድ መቀጠሉ፣ የጦማሪ ሶሊያና ሺመልስ ቃለ መጠይቅ እና ሌሎችም appeared first on Zehabesha Amharic.

የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እየታደኑ እየታሰሩ ነው

Previous: Hiber Radio: በእስራኤል የዘረኝነት ጥቃት ሰለባ የሆኑ ኢትዮጵያውያን የጠነከረ ተቃውሞ ተከትሎ ባለስልጣናት ዘረኛ እርምጃ የወሰደውን ፖሊስ እናባርራለን ማለታቸው፣ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ያላትን አቋም እንድትመረምር መጠየቁ፣በየመን ያሉ ኢትዮጵያውያን ሞተን ሻማ ከማብራታችሁ በፊት በሕይወት ታደጉን ሲሉ ጥሪ አስተላለፉ፣ዶ/ር መረራ በአገር ቤት ያለው የወጣቱ ሁኔታ ምርጫ 97ን ያስታውሳል ማለታቸው፣ የመኢአድ አባላት እየታፈኑ መወሰድ መቀጠሉ፣ የጦማሪ ሶሊያና ሺመልስ ቃለ መጠይቅ እና ሌሎችም
$
0
0

ነገረ ኢትዮጵያ
• በየ ክፍለ ሀገሩ የሚገኙ አባላት ላይ የሚፈፀመው ድብደባ ቀጥሏል
• ‹‹የተጀመረውን የሀሰት ክስ እውነት ለማስመሰል የታቀደ ነው››
ethiopia-blue-party-300x164የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም አይ ኤስ አይ ኤስን ለማውገዝ በጠራው ሰልፍ ሰበብ እየታደኑ እየታሰሩ መሆኑን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ ሀሙስ ሚያዝያ 22/2007 ዓ.ም ብሌን መስፍንና ተዋቸው ዳምጤ ከመስሪያ ቤት ተይዘው የታሰሩ ሲሆን ሚያዝያ 24/2007 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበው ‹‹ሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተደረገውን አመጽ መርታችኋል፡፡›› በሚል ፖሊስ ክስ እንዳቀረበባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡
በተመሳሳይ ዛሬ ሚያዝያ 26/2007 ዓ.ም ማቲያስ መኩሪያ ቤቱ ውስጥ እያለ በፖሊስ ተይዞ ታስሯል፡፡ ማቲያስ፣ ብሌንና ተዋቸው ወረዳ 10 (ላዛሪስት ፖሊስ ጣቢያ) ታስረው ይገኛሉ፡፡ ይህንን የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ የሚደረገው እስርም ‹‹መንግስት በሰማያዊ ፓርቲ ላይ የጀመረውን የሀሰት ክስ እውነት ለማስመሰል የታቀደ ነው፡፡ ፖሊስ ምርመራ ሳይጨርስ በሀሰት 20 አባላትንና 6 አመራሮችን አስረናል ብለው ነበር፡፡ እነሱ የፈለጉት ይህን ሚዲያ ላይ ወጥተው በሀሰት የፈፀሙትን ውንጀላ ማሰመሰል ነው፡፡›› ሲል አቶ ዮናታን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
በሌላ ዜና በየ ክፍለ ሀገሩ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ ደህንነትና ፖሊስ የሚፈፅመው ድብደባ አሁንም መቀጠሉ ተገልጾአል፡፡ በዛሬው ቀን የደብረማርቆስ ከተማ ነዋሪና የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነችው የሀሳብ ጌታቸው ‹‹ለሰማያዊ ፓርቲ ወረቀት በትነሻል›› በሚል ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀሙባት ተገልጾአል፡፡

The post የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እየታደኑ እየታሰሩ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

ወላይታ ላይ ሰማያዊ ፓርቲ ቅስቀሳ እንዳያደርግ ተከለከለ

$
0
0

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

• ‹‹ወላይታ ውስጥ መንግስት የለም›› አቶ ስለሽ ፈይሳ

blue partyበወላይታ ዞን ሰማያዊ ፓርቲ ቅስቀሳ እንዳያደርግ እንደተከለከለ የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊው አቶ ስለሽ ፈይሳ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ በመኪና ላይ ቅስቀሳ እያደረጉ እንደነበር የገለጹት አቶ ስለሽ ሆኖም የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች በሞተር ብስክሌት በመከታተል የመኪናውን ጎማ በሚስማር በማስተንፈስ እንዲሁም የምርጫ ዘመቻ አባላቱን በመደብደብ ቅስቀሳውን ማስተጓጎላቸውን ገልጸዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ ወረቀት የሚቀበለውን ህዝብ እየተከታተሉ እንደሚያስፈራሩና እንደሚደባደቡ አቶ ስለሽ ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ ጌትነት በሱፍቃድ የተባሉ ዕጩና ሌላ የሰማያዊ ፓርቲ አባልን ሞባይሎች በመቀማት ከፍተኛ ድብደባ እንደፈፀሙባቸው ተገልጾአል፡፡

የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች ስም፣ የሚጠቀሙበትን መኪና ታርጋና ሌሎችም የፈፀሙትን ድርጊት በዝርዝር በማቅረብ ለፖሊስ ቢያቀርቡም ፖሊስ ‹‹ይህ ማስረጃ ሊሆን አይችልም›› በሚል ለተፈፀመባቸው በደል ምንም አይነት ትኩረት እንዳልሰጠው አቶ ስለሽ ገልጸዋል፡፡ ፖሊስ ለጉዳዩ ትኩረት ባለመስጠቱ ለዞኑ የምርጫ ኃላፊ ቢያመለክቱም፣ የምርጫ ኃላፊው ‹‹ይህንማ ሊያደርጉ አይችሉም፡፡ ከዞኑ የኢህአዴግ የድርጅት ጉዳይ ጋር እንነጋገርበታለን›› እንዳሉ ገልጸው ምርጫ ቦርድም ከኢህአዴግ የድርጅት ጉዳይ ጋር ተነጋግሮ ነው ውሳኔ የሚሰጠው ብለዋል፡፡ ለሚፈፀምባቸው በደል መፍትሄ የሚሰጥ አካል እንደሌለ የገለጹት አቶ ስለሽ ‹‹ወላይታ ውስጥ መንግስት የለም›› ሲሉም በፓርቲው ላይ ስለሚደርሰው በደል ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

The post ወላይታ ላይ ሰማያዊ ፓርቲ ቅስቀሳ እንዳያደርግ ተከለከለ appeared first on Zehabesha Amharic.

ኢትዮጵያ ብትመች – (ፍቅሬ ቶሎሳ፥ ፒ ኤች ዲ –የሁማኒቲስ ፕሮፌሰር)

$
0
0
ዶ/ር ፍቅሬ ቶለሳ

ዶ/ር ፍቅሬ ቶለሳ

አንተ የደላህ ሰው ሁሉን ለራስ ይዘህ፥ ተው ግፍ

አትናገር፥ “ወጣቱን ከሃገር ማን ውጣ አለው?” ብለህ፥

ሕሊናህ ደንዞ በምቾትህ ብዛት፥ የወጣቱን ስቃይ

ተስኖህ መረዳት፤ኧረ ተው አትቅጠፍ አውነቱን አብለህ!!!

ጊዜ ያነሳውን እሽቅብ ተኩሶ፥

ግፍ አዳላጭ ሆኖ ቁልቁል ሲከሰክስ፥

ፍርድ ይስተካከላል፤ ፍትህ ይበቀላል፥

የድሃ እምባን ሊያብስ፥ ተበዳይን ሊክስ ።

—ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ —-

 

 

 

 

The post ኢትዮጵያ ብትመች – (ፍቅሬ ቶሎሳ፥ ፒ ኤች ዲ – የሁማኒቲስ ፕሮፌሰር) appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live