Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በተለያዩ ከተሞች የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ ዓላማዎችን የያዘ ፓምፕሌ መበተኑ ተገለፀ

$
0
0

Zehabesha News

ደህሚት እንደዘገበው በቅርቡ የድርጅቱን ወቅታዊ መልእክትና የትህዴንን አላማ የያዘ ፓምሌት በአዲስ አበባ አውራ ጎደናዎች፤ ሚያዝያ ሰባት ላይ በዓድዋ መናሃሪያ፤ ፊሾ ተብሎ በሚጠራ አካባቢና ሰልፍ ሜዳ በተንቤን አብይ ዓዲ ከተማ፤ ሽሬ እንዳስላሴ ውስጥ በሚገኙ የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችና፤ ሚያዝያ 6 ላይም በአክሱም መናሃርያ፤ እንዳማርያም፤ ወጋገን ባንክ አካባቢ በሚኘው መናፈሻና ሌሎችን ህዝብ በብዛት በሚንቀሳቀሱባቸው ቦታዎች መበተኑና በርካታ የህብረተሰቡ አካላት ለማንበብ እድል እንዳገኙ ለማወቅ ተችሏል።

ይህ ከተማው ውስጥ በሚገኙ የተደራጁ አባላት የተበተነው የፓምፕሌት ይዘትና መልእክት የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ጭቁን ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጋር ሆኖ ለ 17 ዓመት ያህል ያካሄደውን አስቸጋሪ የትጥቅ ትግል ለግል ጥቅማቸው በሚያስቡ የህወሃት/ኢህአዴግ መሪዎች ተክዶ የመስዋእትነቱ ፍሬ ተጠቃሚ ባለመሆኑ ትህዴን ይህን የተካደ የሰማእታትን አደራ ዳሩ ላይ ለማድረስ መፍትሄው የትጥቅ ትግል ነው ብሎ በማመን እንደገና መስዋእትነት እየከፈለ ባለበት ባሁኑ ግዜ ህዝቡ ስርዓቱ ግንቦት ወር ሊያካሂደው ባሰበው አስመሳይ ምርጫ ላይ ጀሮ ሳይሰጥ የትጥቅ ትግሉን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው የሚጠራ ፅሁፍ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

ባለፉት ቀናቶች በዓዲ ግራትና መቐለ ከተማ ውስጥ ከሦስት ግዜ በላይ የትህዴን ፓምፕሌት ተበትኖ በነዋሪው ህዝብ በደረሰበት ግዜ ህዝቡ እንደ አንድ ትልቅ ተስፋ በመቁጠር ሲቀበለው በአንጻሩ የስርአቱ ካድሬዎች ግን እንቅልፍ እንዳሳጣቸው በተገኘው መረጃ ለመረዳት ተችሏል።

The post በተለያዩ ከተሞች የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ ዓላማዎችን የያዘ ፓምፕሌ መበተኑ ተገለፀ appeared first on Zehabesha Amharic.


በአፍሪካና በአረብ አገሮች በስደት ላይ የሚገኙ ወገኖቻችን ላይ እየተፈጸሙ ስላሉት ፋሽስታዊ  ድርጊቶችን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

$
0
0

ENTCሀገር በቀሉ የወያኔ አፓርታይድ ሰርአት በሃገር ውስጥ በህዝባችን ላይ የፈጠረውን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ስነልቡናዊ ቀውስ በመሸሽ በአፍሪካና በአረብ አገሮች በስደት ላይ የሚገኙ ወገኖቻችን፤ የዜጎቹን መብት የሚያስጠብቅ ኢትዮጵያዊ መንግስት ባለመኖሩ እጅግ አሳዛኝና ዘግናኝ ለሆኑ ስቃይና ግድያዎች ተጋልጠዋል።

ባሳለፍንው የአንድ ሳምንት ጊዜ ብቻ፤ የመን ውስጥ በተፈጠረው ጦርነት፤ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ወገኞቻችን የድረሱልን ጥሪ ቢያቀርቡም ስርአቱ ዜጎችን ለመታደግ ምንም ዐይነት ፍላጎት እንደሌለው በድጋሚ አሳይቷል። ወገኖቻችን መውጫ አጥተው በየእለቱ ህይወታቸውን ለማትረፍ በሚጮሁበት በዚህ የስቃይ ወቅት፤  የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ እጅግ አሳፋሪ በሆነ መንገድ በፌስ ቡክ ላይ የስልክ ቁጥር በማስቀመጥና የሳውዲ መንግስት የሚያካሂደውን የአየር ድብደባ ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፍ በመግለጽ በህዝብ ደምና እንባ ላይ በማላገጥ፤ ዛሬም እንደወትሮው ከባእዳን ጋር ያላቸውን አጋርነት አረጋግጠዋል።

በደቡብ አፍሪካ በተለያዩ ስደተኞች ላይ በጅምላ እየተደረገ ያለውን አሰቃቂ ግድያ ተከትሎ የተለያዩ አገሮች፤ የደቡብ አፍሪከን ኤምባሲ እስከመዝጋት ሲያስጠነቅቁ፤ የወያኔ ስርአት ግን ኢትዮጲያዊያኖች ከነህይወታቸው ሲቃጠሉና ሲገደሉ እያየ፤ አንድ ኢትዮጲያዊ ብቻ መገደሉን ከመናገር በስተቀር ምንም አይነት እርምጃ አልወሰደም፡፡

በሊብያ፤ አይሲስ የተባለው አሸባሪ ቡድን ኢትዮጵያውያንን፤ ክርስቲየናች በመሆናቸው ምክንያት ብቻ በጠራራ ፀሃይ ባሰቃቂ ሁኔታ አንገታቸውን በመቅላትና በጥይት በመደብደብ ገሏቸዋል። አሸባሪ ቡድኑም ክርስትያን በሆኑ ኢትዮጵያውያን ላይ ይህን ፋሽስታዊ ድርጊት መፈጸሙን በይፋ ማረጋጡን የተለያዩ አለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃኖች ቢዘግቡትም፤ የወያኔው ፋሽስታዊ ስርአት ግን በግብፅ ካይሮ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ፤ ስደተኞቹ ኢትዮጵያውያን ስለመሆናቸው ማረጋገጫ እንዳልሰጠ በመግለጽ የተለመደውን ከፍተኛ ክህደት ፈድሟል፡፡

የኢትዮጲያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ከላይ የተዘረዘሩትን ፋሽስታዊ ድርጊቶችና ሀገር በቀሉን የወያኔ አፓርታይድ ሰርአት በጅምላ እያወገዘ በዚህ አጋጣሚ ለሟችና ተጎጂ ቤተሰብ፤ ዘመድና ወዳጆች በሙሉ የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እንገልጻለን።

ከላይ ባጭሩ የተዘረዘሩት በንጹሃን ወገኖቻችን ላይ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ እይተፈጸሙ ላሉት ፋሽስታዊ ድርጊቶች፤ ቀደም ሲል ለተፈጸሙት ተደጋጋሚ ብሄራዊ ቅሌቶችና ላለፉት 24 አመታት የኢትዮጵያ ህዝብ እያሳለፈ ላለው የመከራ ዘመን ዋናው ምንጭ ሀገር በቀሉ የወያኔ አፓርታይድ ስርአት ነው። ይህን መሰሪ ስርአት ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከስሩ ነቅሎ ለመጣል ብቸኛ መፍትሄው፤  የኢትዮጲያ ዲሞክራሲ ሃይሎችን በማስተባበር የነጻነት ትግሉን  በአንድ ማእከል እንዲመራ ሊያደርግ የሚችል፤ ለኢትዮጲያ ህዝብና ለአለም አቀፍ ህብረተሰቡ አማራጭ የሚሆን ሁሉን አቀፍ ያማራጭ ሃይል ወይም የስደት መንግስት ማቋቋም ሲቻል ነው በለን እናምናለን።

የሽግግር ምክር ቤቱ ከመግለጫና ይፋዊ ጥሪ ከማድረግ ባሻገር ከላይ የተቀመጠውን ጭብጥ ተግባራዊ ለማድረግ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ሲያደርግ ቆይቷል። ባሳለፈንው ወር የካቲት 2007፤ ሽግግር ምክር ቤቱ ከሸንጎ ጋር ስምምነት በማድረግ ለዚህ አማራጭ ሀይል መመስረት የመሰረት ድንጋይ መጣሉ አንድ ምሳሌ ነው። በተመሳሳይም ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት በማድረግ ላይ ሲሆን እነኚህን የሁለትዮሽ ውይይቶች ወደወል ውይይቶች ባስቸኳይ እንዲሸጋገር ለማድረግና ያማራጭ ሃይል እንዲቋቋም ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። የሂደቱን ውጤትና፤ ከእያንዳንዱ ድርጅት ጋር የምናደረገውን ሰምምነት ለህዝባችን ይፋ እንደምናደርግ እየገለጽን፤ በዚህ አጋጣሚ ዛሬም እንደወትሮው ነጻነት ናፋቂ ለሆነው ኢትዮጵያዊ፤ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ ሲቪክ ማህበራት፤ ለእምነት ተቋሟት፤ ለመገናኛ ብዙሃን (የፓልቶከ ክፍሎች)፤ ታወቂ ምሁራንና አክቲቪስቶች ይህን ወቅታዊ አጀንዳ የግል ጉዳይ በማድረግ አስተዋጽኦና ግፊት ታደርጉ ዘንድ ሃገራዊ ጥሪያችንን ባክብሮት እናስተላልፋለን።

ትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት (ENTC)

The post በአፍሪካና በአረብ አገሮች በስደት ላይ የሚገኙ ወገኖቻችን ላይ እየተፈጸሙ ስላሉት ፋሽስታዊ  ድርጊቶችን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄና ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ሁሉን አቀፍ አማራጭ ሀይል የማቋቋም ሂደትና ወቅታዊነቱን አስመልክቶ የተሰጠ የጋራ መግለጫ

$
0
0

ሚያዝያ 17፣ 2007  (April 25, 2015)

entc-logo-5Ethiopian_Youth_Movement_Logoሀገር በቀሉ የወያኔ አፓርታይድ ሰርአት በሃገር ውስጥ በህዝባችን ላይ የሚያደርገው  የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ አፈና፤ እስር፤ ግድያ፤ በዘር ከፋፍሎ ማጋጨት፤ ዘረፋና ሀገራዊ ጥቅምን ለባእዳን አሳልፎ መሸጥ የዘወትር ተግባራቶች ከሆኑ አመታት ተቆጥረዋል። ይህንን ግፍ በመሸሽ በአፍሪካና በአረብ አገሮች በስደት ላይ የሚገኙ ወገኖቻችን የዜጎቹን መብት የሚያስጠብቅ ኣትዮጵያዊ መንግስት ባለመኖሩ እጅግ አሳዛኝና ዘግናኝ ለሆኑ ስቃይና ግድያወች ተጋልጠዋል። ይህን ፋሽስታዊ ድርጊትና ተደጋጋሚ ብሄራዊ ቅሌት ለማስቆም የወያኔን መሰሪ ስርአት ከስሩ ነቅሎ ለመጣል በቆራጥነት በጋራ መታገል ብቸኛው መፍትሄ ነው።

ህዝብንና አገራችንን ወደከፍተኛ አደጋ እየገፋ የሚገኘውን ይህን ፋሽስታዊ ስርአት ማስወገድ ያለመቻላችን ምክንያትና የጋራ ችግራችን፤  የኢትዮጲያ ዲሞክራሲ ሃይሎች በማስተባበርና በአንድ ማእከል በመንቀሳቀስ የነጻነት ትግሉን ማካሄድ የሚችል፤ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለአለም አቀፍ ህብረተሰቡ አማራጭ የሚሆን ሁሉን አቀፍ ያማራጭ ሃይል ማቋቋም ያለመቻላችን ነው።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሽግግር ምክር ቤት (ENTC) እና የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄና (EYNM)  ቀደም ሲል ጀምሮ በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ አብሮ ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወቃል። በጁላይ 2013፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤቱ  በዋሽንግተን ዲሲ ባዘጋጀው ታሪካዊ የምክክር ጉባኤ ላይ፤ በርካታ ድርጅቶችና ታዋቂ ግለሰቦች በመገኘት በተሳተፉበት ወቅት ሁለቱ ድርጅቶች ትግሉን በመደጋገፍ ለማካሄድ በተለያዩ ነጥቦች ላይ የመግባቢያ ሰነድ (Memorandum of Understanding) በመፈራረም ለህዝብ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። ይህንን መሰረት በማድረግ፤ በሃገራችን ኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሂደት የተሳካ እንዲሆንና በተለያዩ ጐራዎች በተናጥል የሚደረጉ ትግሎች የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመኘውን ነፃነት እውን ለማድረግ በቂ አለመሆናቸውን በመረዳት፤ ሁሉን አቀፍ የአማራጭ ሃይል መኖር እጅግ አስፈላጊ፣ ወሳኝና፣ ወቅታዊ መሆኑን በመገንዘብ፤ የአማራጭ ሃይል የማውጣት ሂደቱን በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ተግባራዊ ለማድረግ፤ የሁለትዮሽ ውይይቶችንና ግንኙነቶችን ወደወል ባስቸኳይ በማሸጋገር በጋራ ለመስራት ሙሉ ስምምነት ላይ ደርሰናል።

በዚህ አጋጣሚ ዛሬም እንደወትሮው ነጻነት ናፋቂ ኢትዮጵያዊ  ይህን ወቅታዊ አጀንዳ የግል ጉዳይ በማድረግ አስተዋጽኦና ግፊት ያደርግ ዘንድ አገራዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት (ENTC) እና

የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ (EYNM)

The post ከኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄና ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ሁሉን አቀፍ አማራጭ ሀይል የማቋቋም ሂደትና ወቅታዊነቱን አስመልክቶ የተሰጠ የጋራ መግለጫ appeared first on Zehabesha Amharic.

በባሌ ጎባ ሰማያዊን ለማውገዝ የተጠራው ሰልፍ ተበተነ

$
0
0

(ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ) በባሌ ጎባ አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በሚል ሰማያዊን ለማውገዝ የተጠራ ሰልፍ ህዝቡ ፈቃደኛ ባለመሆኑ መበተኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ዛሬ ሚያዝያ 20/2007 ዓ.ም በባሌ ጎባ በተጠራው ሰልፍ የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ደም ከማፋሰስ ተግባሩ ይቆጠብ›› የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን ይዘው እንዲወጡ ከማድረግ ባሻገር ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ አሸባሪ ነው›› በሚል ህዝቡን ቀስቅሰው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡
Zehabesha News
ሆኖም ሰልፉ በሚደረግበት ጎባ ከተማ በተመሳሳይ ሰዓት ሰማያዊ ፓርቲ በመኪና ቅስቀሳ እያደረገ ስለነበር ሰልፉ ላይ ሰማያዊን እንዲያወግዝ ተጠርቶ የነበረው ህዝብ ‹‹አሸባሪ የምትሏቸው ሰዎች ሰላማዊ ቅስቀሳ እያደረጉ ነው፡፡ አሸባሪ ከሆኑ ለምን የምርጫ ቅስቀሳ ያደርጋሉ? አሸባሪ ያልሆኑትን ሰዎች ለምን አሸባሪዎች ናቸው ትሉናላችሁ?›› በሚል ሰልፉን ጥለው በመሄዳቸው ሰልፉ እንደተበተ ተሰምቷል፡፡ ህዝቡ ሰልፉን ጥሎ በመሄዱ የቀሩት ካድሬዎችም ወደ ቀበሌ የስብሰባ አዳራሽ በመሄዳቸው ሰልፉ ወደ ስብሰባ ተቀይሯል ተብሏል፡፡

The post በባሌ ጎባ ሰማያዊን ለማውገዝ የተጠራው ሰልፍ ተበተነ appeared first on Zehabesha Amharic.

ኣባ ይፍቱኝ(በዉቀቱ ስዩም)

$
0
0

Bewketu Seyoum – Hagere Mariam (Maryland) USA [Must Listen)
ኣባ ይፍቱኝ !
ሲኦል ኣለ ሲሉኝ፤ የለም ብየ ክጀ
የባልቴት ተረት ነው፤ በማለት ቀልጀ
ኣውቄ በድፍረት፤ በድያለሁና
ያንጹኝ በንስሃ፤ ያንሱኝ በቀኖና
ሲኦል ከነጭፍራው፤ በጉም ተሸፍኖ
እንዴት ሳላየው ኖርኩ፤ ካጠገቤ ሆኖ?
ኣባ ይፍቱኝ
ሰይጣን ብሎ ነገር፤ የተጭበረበረ
ዋዛ ነው ቧልት ነው፤ ብየ ኣስብ ነበረ
ይሄው እውነት ሆኖ፤ ዋዛና ተረቱ
ባይኔ በብረቱ
ዲያብሎስን ኣየሁት፤ በሸሚዝ ዘንጦ
እልፍ ግዳይ ጥሎ፤ ቸብቸቦ ጨብጦ፡፡
ኣባ
ልክ እንደ ብርሌ ፤ኣጥንት ሲከሰከስ
ኣባይን ኣዋሽን፤ የሚያስንቅ ደም ሲፈስ
ለምለም ፍጥረት ሁላ፤ ወደ ኣመድ ሲመለስ
ልክ እንደ ጧፍ ሃውልት፤ ምስኪኖች ሲጋዩ
ምድጃው ዳር ሆነው፤ ይሄንን እያዩ
ገሃነም ከላይ ነው፤ ብለው መሳትዎ
እስዎ እንደፈቱኝ ፤ እግዚሃር ይፍታዎ

The post ኣባ ይፍቱኝ(በዉቀቱ ስዩም) appeared first on Zehabesha Amharic.

የማዕከላዊ ዕዝ አባላት በከተማ ውስጥ የሠራዊቱ እርስ በራሳቸው እየተገዳደሉ ነው

$
0
0

Zehabesha News
የደህሚት ድምጽ እንደዘገበው በገዢው የኢህአዴግ ስርአት ውስጥ የሚገኙ የማእከላዊ እዝ ሰራዊት አባላት ወደ ከተሞች በመሄድ ህውከት እየፈጠሩ እርስ በራሳቸው እየተገዳደሉ መሆናቸውን ምንጮቻችን ገለፁ።

እንደምንጮቻችን መረጃ መሰረት ሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ላይ በሚገኝ “ብሄራዊ ሆቴል” ውስጥ ሚያዚያ 4/2007 ዓ/ም የኢህአዴግ መከላከያ ሰራዊት አባላት የሆኑት ወታደሮች መጠጥ በመጠጣት እርሰ በራሳቸው ተጣልተው ከፍተኛ ግርግር እንደተነሳ የገለፀው መረጃው ህውከት ፈጣሪ ከሆኑት የሰራዊቱ አባላትም መቶ አለቃ ደሳለኝና ምክትል መቶ አለቃ አየለ ናሳ የተባሉት መሆናቸውና በጠርሙስና ሌሎች የሆቴሉን ንብረት በማንሳት እየተወራወሩ መደባደባቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በተከሰተው ብጥብጥ ሁለቱም መኮንኖች በከባድ መጎዳታቸውና በተለይ ምክትል መ/አለቃ አየለ ናሳ ላይ በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት ምክንያት ከሁለት ቀን በኋላ እንደሞተ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።

The post የማዕከላዊ ዕዝ አባላት በከተማ ውስጥ የሠራዊቱ እርስ በራሳቸው እየተገዳደሉ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

ኤዶምንና ማህሌትን ብቻ ሳይሆን የ45 ሚሊዮን ሴቶች ክብርን ነው ያቀለሉት –ግርማ ካሳ

$
0
0

edom Jpurnalist
ኤዶም ካሳዬ ጋዜጠኛ ናት። ማህሌት ፈንታሁን ደግሞ «ሰለሚያገባን እንጦምራለን» በሚል የአለም አቀፍም ሆነ የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት በሚፈቅድላቸው መሰረት፣ ብሎግ ከሚያደርጉ ዞን ዘጠኞች አንዷ ናት። ኤዴሞም ሆነ ማህሌት የጻፉት፣ የተናገሩት የተደበቀም ሆነ የተሸፈነ ነገር የለም። ለፍትህ ከመቆማቸው በቀር ያጠፉት ጥፋት የለም። ወንጀላቸው አገራቸውን መዉደዳቸው ነው። ሆኖም ሕወሃት «ሽብርተኞች» ብሎ ካሰራቸው ይኸው አንድ አመት ሆናቸው። ቢያንስ ከ27 ጊዜ በላይ ፍርድ ቤት ተመላልሰዋል። አስቡት በአንድ አመት ዉስጥ ቢያንስ 27 ጊዜ !!!!!

የአገሪቷ ሕገ መንግስት በማረሚያ ቤት ያሉ እስረኞች በምን መልኩ መያዝ እንዳለባቸው በግልጽ አስቀምጧል። በአንቀጽ 19 ንኡስ አንቀጽ አንድ ላይ፣ እያንዳንዱ ዜጋ ፣ እስረኞችን ጨምሮ፣ ኢሰብአዊ ፣ ጭካኔ የተሞላባቸዉና ክብርን የሚነኩ ቅጣቶች ሊቀበል እንደማይገባ ያስቀምጣል። ሆኖም ረእቡ ሚያዚያ 14 ቀን፣ የአዲስ አበባ ሰልፈኞች እንዳሉት፣ ለሕወሃት ሕገ መንግስቱ ወረቀት ብቻ ነው። እህቶቻችን ሞራላዊ፣ መንፈሳዊና የሴትነት ክብራቸውን በመድፈር ፣ ራቁታቸውን ሆነው በአረመኔ የሕወሃት ወንድ ምናምንቴዎች ፊት ስፖርት እንዲሰሩ መገደዳቸው ምን ያህል እንደ አገር መዝቀጣችንን የሚያሳይ ነው። በርግጥ ኤዶምና ማህሌትን ብቻ ሳይሆን ሕወሃቶች ከ40 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑትን የአገራችንን እናቶችና እህቶች ነው የደፈሩት።

ለሰብአዊ መብት ጉባኤ ኮሚሽን፣ ኤዶም ላሳዬና ማህሌት ፋንታሁን ከተናገሩት የተወሰነውን እንሆ፡

«ሙሉ ልብሴን እንዳወልቅ ተገድጄ ራቄቴን በወንድ መርማሪዎች ፊት ስፓርት አንድሰራ እገደድ ነበር ፡፡ “ሴትነትሽ አንዲህ ከሚዋረድ አመጽ እንዳነሳሳሽ እመኚ ተብያሁ”»

ማህሌት ፋንታሁን
«በተለምዶው ከምመረመርበት ቢሮ ውጩ አንደኛ ፎቅ አዳራሽ ውስጥ ለምርመራ ተወስጄ ልብሴን እንዳወልቅ እና የተለያዬ ለመናገር የሚከብዱ ስፓርታዊ አንቅስቃሴዎችን እንድሰራ ተገድጃለሁ፡፡ እንዲህ ከምትዋረጂ አመጽ ልናስነሳ ነበር ብለሽ ለምን አታምኚም እያለ ይመታኝ ነበር »
ኤዶም ካሳዬ

እንግዲህ የዛሬይቱ የሕወሃት ኢትዮጵያ ይች ናት። ይህ አይነቱን ኢሰብዊነት ማስቆም ካልቻልን እንደ አገር ሆነ እንደ ሕዝብ መቀጥል አንችልም። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ፣ ይህ አይነቱ ብሄራዊ ዉርድት እንዲቆም መነሳት አለበት። ፈረንጆችን እንደሚሉት “We have to claim back our country from these monsters” ። በተለይም እናቶችና እህቶች ፣ አዉቃለሁ ብዙ ግርግር አትወዱም። ግን አሁን እናንተም ከወንዱ ባልተናነሰ የምትነሱበት ጊዜ ነው።

The post ኤዶምንና ማህሌትን ብቻ ሳይሆን የ45 ሚሊዮን ሴቶች ክብርን ነው ያቀለሉት – ግርማ ካሳ appeared first on Zehabesha Amharic.

የብአዴን አባላት በአማራው ሕዝብ ምላሽ የተነሳ ጭንቅ ውስጥ መውደቃቸው ተዘገበ

$
0
0

በአማራ ክልል የሚገኙ የብ.አ.ዴ.ን/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ባለስልጣናት ሲያካሂዱ የቆዩትን የምረጡን ቅስቀሳ ህዝቡ ስላልተቀበለው በከባድ ስጋት ላይ መውደቃቸው ታወቀ ሲል የደህሚት ድምጽ ዘገበ::
bereket alamudi demeke

በአማራ ክልል የሚገኙ ባልስልጣኖች በመጪው ግንቦት ወር በሚካሄደው የይስሙላ ምርጫ ህዝቡ እንዲመርጣቸው ያካሄዱት ቅስቀሳ በህዝብ ተቀባይነት በማጣቱና በስርዓቱ ላይ እየተካሄደ ያለው ተቃውሞ ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ ተቃዋሚ ድርጅቶችን ሊመርጡ ይችላሉ በሚል የጠረጠሯቸውን ንፁሃን ዜጎች ንብን የያዘ ፖስተር ቀድዳችኋል በማለት እያሰሯቸው መሆናቸው ሊታወቅ ተችሏል።
ንብ ያለበትን በራሪ ወረቀት ቀደዳችሁ በሚል ከታሰሩት ወገኖች መካከል የተወሰኑትን ለመግለፅ ያህል ሙስጠፋ አሊ ነዋሪነቱ ደቡብ ወሎ ዞን ቦረና፥ መኩየ ሃይሉ ከባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 03፥ ታደሰ ጌቱ ከላሊበላና ሌሎችም መሆናቸውና ህዝቡ በላዩ ላይ እየወረደ ያለውን ግፍ ተቋቁሞ በኢ.ህ.አ.ዲ.ግ አንገዛም በማለት ተቃውሞው እየቀጠለ መሆኑን ከተለያዩ አካባቢዎች የደረሰን መረጃ አስረድቷል።

The post የብአዴን አባላት በአማራው ሕዝብ ምላሽ የተነሳ ጭንቅ ውስጥ መውደቃቸው ተዘገበ appeared first on Zehabesha Amharic.


በሊቢያ ሚስቱንና የሶስት ወር ልጁን ትቶ የደረሰበት ያልታወቀው ሰው ከእስር ቤት አምልጦ ከቤተሰቡ ጋር ተቀላቀለ

$
0
0

Zehabesha News

ኢሳት ዜና :-በሊቢያ ቤንጋዚ የሚኖር አንድ ሙስሊም ኢትዮጵያዊ በጦርነት መሃል አልፎ ከ3 ወር ልጇ ጋር ለሶስት ቀናት ቤት ዘግታ የተቀመጠቸውን ኢትዮጵያዊት ማዳኑን ኢሳት በልዩ ዘገባ ካቀረበ በሁዋላ፣ ባልየው ከ4 ቀን በሁዋላ ከእስር ቤት አምልጦ ከቤተሰቡ ጋር ተቀላቅሏል።

በቀሌ አስፋው የተባለው ኢትዮጵያ ወደ ሊቢያ የሄደው በቅርብ ሲሆን፣ የሊቢያ ፖሊሶች መንገድ ላይ በድንገት እንደያዙት ገልጿል። ከተያዘ በሁዋላ ስሙን ወደማያውቀው እስር ቤት መወሰዱን ገልጿል። ወደ ሊቢያ ለምን መጣህ ተብሎ መጠየቁንና መደብደቡን የገለጸው በቀለ፣ ከአራት ቀን በሁዋላ የልጁን ናፍቆት መቋቋም ባለመቻሉ ከገደሉኝም ይግደሉኝ ብሎ ከእስር ቤት ዘሎ ማምለጡንና በሰላም ከቤተሰቡ መገናኘቱን ገልጿል። ከ15 እስከ 20 የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን በእስር ቤት ውስጥ እንደሚገኙ ተናግሯል።

ከኦሮምያ ክልል መምጣቱን የሚናገረው ኢትዮጵያዊ ፣ ቤተሰቡንና ልጆቹን ላተረፈለት ኢትዮጵያዊው ስደተኛ ምስጋናውን ገልጿል።

The post በሊቢያ ሚስቱንና የሶስት ወር ልጁን ትቶ የደረሰበት ያልታወቀው ሰው ከእስር ቤት አምልጦ ከቤተሰቡ ጋር ተቀላቀለ appeared first on Zehabesha Amharic.

የሰማዕታቱ ሰማዕትነት ለቤተ መንግስቱ እና ቤተ ክህነቱ የመጨረሻው የማስጠንቀቅያ ደወል ነው

$
0
0

cherkos addis ababa
ከጌታቸው በቀለ
(የጉዳያችን ልዩ ማስታወሻ)

ለሰማዕታቱ ለቅሶ አዲስ አበባ

ያለፈው ሳምንት እሁድ ለኢትዮጵያውያን እና ለመላው ዓለም አእምሮ የሚነሳ ግፍ ተፈፀመ። በአክራሪው አይ ኤስ ኤስ ስል ቢላዋ እና የጥይት አረር ሰላሳ ኢትዮያውያን ክርስቲያኖች ሊብያ ውስጥ ሰማዕትነት ተቀበሉ።ይህ መላው ዓለምን ያስደነገጠ ኢትዮጵያውያንን በሙሉ ቀልብ አስቶ ያስለቀሰ ጉዳይ ሌላ ሃዘን ተጨመረበት።ይሄውም ድርጊቱ ለመላው ዓለም የዜና አውታሮች በተለቀቀበት ሚያዝያ የሰንበት እለት ምሽት የኢትዮጵያ ሕዝብ በሀገር ውስጡ ኢቲቪ ዜና ላይ ስለ ስማዕታቱ ለማየት እና የመንግስት የጉዳዩን አተያይ፣ቀጥሎም ስለሚወሰዱ እርምጃዎች ይናገራል ተብሎ ሲጠበቅ የዕለቱ የመጀመርያ ዜና ሳይሆን ቀረ።ኢቲቪ የቱርክን ውለታ በቀዳሚ ዜናነት በጨርቃ ጨርቅ ምርት እያደረገች ያለችውን፣ቀጥሎ ኮርያ እያለ በሶስተኛ ደረጃ ድርጊቱን ”አይ ኤስ ኤስ የለቀቀው ዜና” የሚል ስም ከሰጠው በኃላ ”የተገደሉት ኢትዮጵያውያን ለመሆናቸው ካይሮ የሚገኘው ኤምባሲያችን እያጣራ ነው” በሚል ሰማዕታቱ ገና ለሞታቸውም እውቅና እንዳልሰጣቸው ተናገረ።የሚገርመው ይህንኑ ”ኢትዮጵያውያን መሆናቸው እየተጣራ ነው” የሚለውን አባባል ቤተ ክህነቱም ዘግየት ብሎ ደገመው።ይህ የሆነው የዓለም ታላላቅ የዜና አውታሮች ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን ባረጋገጡበት፣ገዳዩ ቡድንም በቪድዮ መልካቸውን እያሳየ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን በገለፀበት እና የሰማዕታቱ ቪድዮ በትትክክል ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን አይደለም እኛ ኢትዮጵያውያን የውጭ ዜጎች በቀላሉ ሊለይ በሚችልበት መንገድ ነበር።

በሚቀጥሉት ቀናት የአዲስ አበባ ሕዝብ ማንም ሳይጠራው በእራሱ ያደረገው ሰልፍ እና ግፈኛውን ፅንፈኛ ቡድን አይ ኤስ ኤስ እና ኢህአዲግ/ወያኔን ያወገዘበት ሰልፍ የገዢዎቻችንን ልብ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ሕዝብ ደም መክበራቸውን የዘነጉ የዘመናችን ቅምጥሎች የጥቅም ተጋሪዎችንም ሰውነት አራደ።የሚይዙት የሚጨብጡትን አጡ።የአዲስ አበባ ሕዝብ ”ሉዓላዊነት ማለት በየትኛውም ቦታ የሚገኙ ዜጎችን መብት ማስከበር ማለት ነው!” የሚል እና ሌሎች መፈክሮችን ይዞ ወደ ቤተ መንግስት ተመመ።ስርዓቱ ሰራዊቱን አሰልፎ ለመግታት ሞከረ።ነገሩ ልመናም ነበረበት።ለተማፅኖ ከቀረበው መባ ውስጥ አንዱ እና ዋናው ”እባካችሁ ነገ ሮብ ሰልፍ ስለምንፈቅድ ያኔ በደንብ መሰልፍ ትችላላችሁ” የሚል ነበር።ህዝቡ ቤተ መንግስቱን ትቶ ወደ መስቀል አደባባይ እና ዋና ዋና መንገዶች ተመመ።በቀጣዩ ቀን ሮብ ሚያዝያ 14/2007 ዓም አዲስ አበባ ከአስር ዓመት በፊት ሚያዝያ 30፣1997 ዓም ወደነበረችበት የተቃውሞ መልክ ተቀየረች።ያለፈው ሳምንት ግን ከቀድሞው እጅግ በላቀ መልኩ ቁጣ፣ለቅሶ እና እልህ የተቀላቀለበት ነበር።

ቤተ ክህነቱ

ሰማዕታቱ የህዝብን አይን ይበልጥ ገለጡ፣የመሪዎቻችንን የስብዕና ደረጃ አየንባቸው

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታይ የሆኑት በሊብያ ሰማዕትነት የተቀበሉ 30 ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ጉዳይ በመንፈሳዊ ሚዛን ሲመዘን የቤተ ክርስቲያኒቱ የ21ኛው ክ/ዘመን መንፈሳዊ ተጋድሎ ውስጥ በወርቅ ቀለም የሚፃፍ ታላቅ የሰማዕትነት ተግባር የፈፀሙ ናቸው።ለኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ሰማዕትነት አዲስ ክስተት አይደለም።በዮዲት ጉዲት፣በግራኝ መሐመድ፣በፋሺሽት ጣልያን የአምስት ዓመት ወረራ፣ባለፉት 24 አመታት በ ደቡባዊ፣ምዕራባዊ እና ምስራቃዊ ኢትዮጵያ በልዩ ልዩ ስፍራዎች እና በጅማ በርካታ ክርስቲያኖች ሰማዕትነት ተቀብለዋል።

ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሰማዕትነት ክብር እንጂ ውርደት አይደለም።ጌጥ እንጂ ጉድፍ አይደለም። የፅናት ምልክት እንጂ የድክመት መገለጫ አይደለም።ይልቁንም በእዚህ ዘመን ያውም በወጣት አማኞቿ በእዚያ በበረሃ ከሳሽ እና ወቃሽ በሌለበት ለእምነታቸው የታመኑ ምዕመናን ዛሬም በፅናት መቆማቸውን የሚያሳይ ልዩ የተስፋ ችቦ ነው።የቅዱስ ጊዮርጊስን፣የቅዱስ ቂርቆስን እና የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስን እና የሌሎች አያሌ ሰማዕታትን የምትዘክር ቤተ ክርስቲያን ሰማዕታቱ አሁንም የክብር ፈርጦቿ ናቸው።በመሆኑም ቤተ ክርስቲያን በሰማእታቷ ይበልጥ ትነጥራለች እንጂ ፈፅሞ የኃልዮሽ ጉዞ ምልክት አታሳይም።

ሰማዕታት ዓለምን የሚንጡበት ልዩ መንፈሳዊ ኃይል አላቸው።በ1929 ዓም በፋሽሽት ጣልያን በጥይት የተደበደቡት የአቡነ ጴጥሮስ ሰማዕትነት መላ ኢትዮጵያን በአዲስ መንፈስ አስተሳሰረ።ከከተማ እስከ ገጠር ኢትዮጵያውያንን አነጋገረ። ፍርሃት ገፈፈ።ለኢትዮጵያ ነፃነት ኢትዮጵያውያንን አንድ ልብ አደረገ።በውጭ ያሉ የኢትዮጵያ ወዳጆችን አስነሳ።የኢትዮጵያ የታሪክ ተመራማሪ የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስ እናት እንግሊዛዊቷ ሲልቭያ ፓንክረስ ኢትዮጵያን ብላ ከሀገር ሀገር ተንከራተተች።በበረሃ ያሉ የኢትዮጵያ አርበኞች እና የከተማ የውስጥ አርበኞች በአዲስ መልክ ተነሱ።ስማዕታት መላው አለምን የመናጥ ኃይላቸው ልዩ ነው። የቅዱስ እስጢፋኖስ መወገር ከስምንት ሺህ በላይ የሚሆኑ የጉባዔው ታዳሚዎች ይብሱን በየስፍራው ተበትነው ክርስትናን አፀኑ።የቅዱስ እስጢፋኖስ ስማዕትነት ይብሱን አፅናቸው።የቅዱስ ጳውሎስ እና ቅዱስ ጴጥሮስ ሰማዕትነትም እንዲሁ መላዋ ሮምን ብሎም አውሮፓን በሃይማኖት አፀና ከእዚህ ሁሉ አልፎ ክርስትና የሮም ቤተ መንግስትን አንዘፍዝፎ ወደ ክርስትና ቀይሯል።

ዛሬም የዘመን ልዩነት ካልሆነ በቀር የሰማዕታት ክብርም ሆነ የህዝብን አይን የመግለጥ ፀጋቸውን አይተንበታል።የመሪዎቻችንን የግፍ ዳር አየንባቸው፣ኢትዮጵያ ቤተ መንግስቷ ክፍት መሆኑን፣ውሳኔ የመስጠት ብቻ ሳይሆን ብሔራዊም ሆነ ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን የማይድረዱ ሰዎች ስብስብ መሆኑን ከመቸውም ጊዜ በላይ ወደ አጥንታችን እስኪዘልቅ ድረስ ገባን።ከወጣት እስከ ሕፃን፣ ከህፃን እስከ ሽማግሌ በልበ ሙሉነት ኢትዮጵያን በጎሳ የከፋፈላትን ስርዓት በግልፅ በአደባባይ ”ሌባ ነህ” አሉት።የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ከእረጅም ዓመታት መተኛት በኃላ የዩንቨርስቲውን ኩሩ ታሪክ ከተጣለበት አቧራውን አራግፈው የቤተ መንግስቱን አጥር ”የሀገር አንበሳ የውጭ ሬሳ” እያሉ እየዘመሩ አለፉ። እርግጥ ነው።በእዚህ ሁሉ መሃል የስርዓቱ ቅልቦች ካለ አንዳች ርኅራኄ በወጣቶቹ ላይ የዱላ ውርጅብኝ አወረዱባቸው።ቂርቆስ የሚገኘው ሃዘንተኞቹ የተሰበሰቡበት ስፍራ በፖሊሶች ተበተነ።የኢትዮጵያ ልጆች በታሪካቸው ከተፈፀሙት አበይት ግፎች ውስጥ የሚዘከሩ ተግባራት በአዲስ አበባ ተደረገ።እናቶች አለቀሱ።ወጣቶች እግራቸው ተሰበረ፣እጃቸው በፖሊስ ዱላ ተቆለመመ።ሰማዕት በሆኑት ያለቀሰው ሕዝብ ዳግም በእራሱ ሀገር ፖሊስ ተደበደበ።በሺህ የሚቆጠሩ ታሰሩ።ወዳልታወቀ ቦታ ተውሰዱ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቤተ ክህነት በብዙ የአሰራር ጉድለቶች ሲወቀስ የነበረ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው። የአስተዳደር መዋቅር ወጥነት አለመኖር፣ግልፅ የገንዘብ አያያዝ አለመኖር፣ካለ ችሎታችው አገልጋዮችን በማይመጥናቸው ቦታ መመደብ፣የቅዱስ ሲኖዶስ አሰራር እና ደንብ በፓትራሪኩ ጣልቃ ገብነት መበላሸት፣ቤተ ክርስቲያኒቱ ተገቢው ቦታዋን በሁለንተናዊው የሀገሪቱ እንቅስቃሴ አለማግኘት እና ቤተ ክርስቲያን ለተበደሉት፣ፍትህ ላጡት ፣ለታሰሩት እና ለተሰደዱት ድምፅ አልባ መሆኗ ሁሉ የቤተ ክህነቱ ትልቅ የቤት ሥራ ነው።የኢትዮጵያ ሕዝብ ባለፈው ሳምንት ያሰማው ድምፅ የመጨረሻ ደወል አይደለም ብሎ የሚከራከር ያለ አይመስለኝም።ቤተ ክህነቱ ከቤተ መንግስቱ ጋር የሚኖረው አግባብነት የሌለው መሞዳሞድ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ለብዙ ትችቶች ብቻ ሳይሆን ምመናኗንም ከፍ ወዳለ ቅሬታ መርቶታል።ለችግሩ መፍትሄ ካልተሰጠው ሕዝብ አንድ ቀን በእራሱ ኃይል መፍትሄ እንደሚሰጠው መታወቅ አለበት።የሰማዕታቱ ደም በልቦናው የተቀበረ ምዕመን የኢህአዴግ/ወያኔ ቅልብ ወታደር ይፈራል ማለት ዘበት ነው። አሁንም ግን ቤተ ክህነቱ ይህንን ደውል በውቅቱ ተረድቶ ለማስተካከል መነሳት ካለበት አሁን ነበር።ግን አይመስልም።

ቤተ መንግስቱ

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ባለፉት አርባ ዓመታት ውስጥ በሕዝብ የታወቁ እና ያልታወቁ ሰማዕትነት የተቀበሉ ኢትዮጵያውያን ቢኖሩም ሕዝብ ክፉኛ ያስደነገጠው የዛሬ አርባ ዓመት በደርግ የተገደሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የወቅቱ ፓትሪያርክ አቡነ ቴዎፍሎስ ነበሩ።ከእዛ ወዲህ የጅማው የፅንፈኞች በቤተ ክርስቲያኒቱ ምእመናን ላይ የፈፀሙት ግድያ እና አሁን በሊብያ የተፈፀመው ዋነኞቹ ናቸው።እዚህ ላይ ኢህአዴግ/ወያኔ ለሊብያው ጉዳይ የሰጠው ቸልተኝነት ብቻ ሳይሆን አሁን በፅንፈኛው አይ ኤስ ኤስ የተከበቡትን ኢትዮጵያውያውን ክርስቲያኖች ለመርዳትም ምንም አይነት እንቅስቃሴ አለማሳየቱ አሁንም ሕዝብ በመንግስቱ ተስፋ ከቆረጠበት አያሌ ጥፋቶች ጋር ተዳምሮ ዛሬም ትኩስ የሆነ ጉዳይ እንደሆነ አለ።

የኢህአዴግ/ወያኔ መንግስት ዘግይቶ የሶስት ቀን ሃዘን ማወጁን ይግለፅ እንጂ ይህንን ያደረገው በሕዝብ ተገዶ መሆኑ የድርግቶቹ ሂደት በእራሳቸው በሚገባ አጋልጠውታል።የኢትዮጵያ ሁኔታ በተለይ ለማንኛውም አደጋ ከመቼውም ጊዜ በላይ መጋለጧ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ግልፅ ሆኗል።በመንግስትነት የተቀመጠው አካል በሁለት መልክ ይገለጣል።የመጀመርያው መገለጫ ለዜጎቹ ምንም የማያደርግ ባጭሩ ሽባነት (Non-functionality) ሲሆን ሁለተኛው መገለጫው ደግሞ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሳይሆን የጎሳ ዜጋ የሚያውቅ መሆኑ ነው። አሁን ጥያቄው ቤተ ክህነቱም ቤተ መንግሥቱም ቤተ ክህነቱም ያለፈው ሳምንት የህዝብ እንቅስቃሴ የሚያስተምሩት እና ሹክ የሚሉት ጉዳይ አድርገው ወሰዱት። የመጨረሻ ደውል! ከእዚህ በኃላ ”ቀሚሰ አወላከፈኝ” የለም።ሕዝብ ከተነሳ የሚመልሰው የለምና።
yilikal
ሽባነት (Non-functionality)

ኢህአዴግ/ወያኔ የመንግስት መዋቅሩም ሆነ አጠቃላይ እንቅስቃሴው ወደ ሽባነት (Non-functionality) መቀየሩ በግልፅ ታይቷል።አንድ መንግስት ወደ ሽባነት ሲቀየር የሀገር ውስጥ የፖለቲካ፣የምጣኔ ሀብት እና የማህበራዊ ችግሮችን ሁሉ በጉልበት ብቻ እና ብቻ ለመፍታት ይነሳል።እርግጥ ኢህአዴግ/ወያኔ ይህ በሽታ ከጀመረው መቆየቱ ይታወቃል።በእጅጉ የባሰበት ግን በ1997 ዓም ምርጫ ክፉኛ ከተመታ በኃላ መሆኑ ይታወቃል።ላለፉት አስር አመታት ምንም የማይሰራ የሽባነት በሽታው አድጎ አሁን በመላው ዓለም ኢትዮጵያውያን በባዕዳን መከራ ሲቀበሉ ምንም ማድረግ የማይችል ተመልካች ወደመሆን መቀየሩ በግልፅ ታይቷል።በሳውዲ አረብያ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩኢትዮጵያውያኖች በግፍ ሲባረሩ ጠንከር ያለ መግለጫ ማውጣት አልቻለም።በተመሳሳይ መንገድ ሊብያ ለተፈፀመው የግፍ ተግባርም ሆነ በደቡብ አፍሪካ በወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን ሁሉ ከዝምታ ባልተሻለ መልክ ማለፉ ሌላው የሽባ መንግስት መገለጫ ሆነው ቆትይተዋል።

ለጎሳ ዜጋ ቅድምያ የመስጠት አባዜ

በሊብያ ሰማዕታት ጉዳይ የኢህአዲግ/ወያኔ መንግስት ”ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ላጣራ” ያለበት ምክንያት እጅግ ታሪካዊ ስህተት የሰራበት ብቻ ሳይሆን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚገዛውን ድርጅት ማንነት ለማወቅ የቻለበት ነበር።ምን ያህል ሰብዓዊ አስተሳሰብ የራቃቸው፣ከዓለም አቀፍ መረጃ የራቁ፣እንደመንግስት አይደለም እንደ አንድ የቤተሰብ አስተዳዳሪ በፍጥነት ውሳኔ የመስጠት የአቅም ድህነት ላይ ያሉ እና የሚመሩትን ሕዝብ በጥላቻ እና በቂም የሚመለከቱ መሪዎች ኢትዮጵያ እንደተሸከመች ፍንትው ብሎ ታየ።የሚገርመው መንግስት ”ላጣራ” እያለ ሲያላግጥ አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ እና ዋይት ሃውስ ድርጊቱን ኮንነው ማዘናቸውን የሚገልፅ መግለጫ አወጡ።ሰማያዊ ፓርቲ ድርጊቱን ኮንኖ የመንግስትን ቸል ባይነት አስምሮ አወገዘ።ምን ይሄ ብቻ የሁለቱ የሟች ቤተሰቦች ከቤተ መንግስቱ ዝቅ ብሎ ቂርቆስ ሰፈር እያነቡ፣ሕዝቡም ለቅሶ እየደረሰ ነበር።

ይህ ጉዳይ በጣም አስደንጋጭ ነው።መላው ዓለም ስለእኛ ያለቅሳል፣ሃገራት የሃዘን መግለጫ ይልካሉ፣ሃዘንተኞች ለቅሶ ላይ ናቸው፣መንግስት ግን ”ኢትዮጵያዊነታቸውን ገና እያጣራሁ ነው” አለ።ይህንን ያለው ቪድዮው ለዓለም ዓቀፍ መገናኛ ብዙሃን ከተለቀቀ ከ 16 ሰዓታት በኃላ መሆኑን ልብ በሉ።ይህ ድርጊት ለመጪው ትውልድ አይደለም አሁን ላለነውስ ማን በትክክል ሊያስረዳን ይቻላል።ለምን አንድ መንግስት ነኝ ያለ አካል ዜጎቹን እና ሀገሪቱን በእንዲህ ያህል ደረጃ ስልጣጣኑን ወዶ ህዝብን ጠልቶ ይገኛል።ለምን? መልሱን ታሪክ በሚገባ ይመረምረዋል።ለጊዜው ግን አንድ ነገር ማለት ይቻላል።ለኢሕአዴግ/ወያኔ ”ኢትዮጵያዊ ዜጋ” የሚባለው ማን ነው? የሚለውን ጥያቄ ማንሳቱ ብዙውን ምላሽ ያሰጣል። እንደ ኢትዮጵያዊነት ሳይሆን በጎሳ ካልተጠራን እንደማያውቁን አልጠፋንም።ችግሩ በመንግሥትነት የተቀመጠው አካልም በእራሱ በፈጠረው ዓለም ውስጥም ከጎሳውም ”ዜጋ” የሚለው ስም የተሰጣቸው ትናንሽ ”ልዑላን” ሃገሩን እንደሞሉት ያስረዳል።ለህወሓት የኪነት ቡድን ለደረሰበት የመኪና አደጋ ከሰበር ዜና ባላነሰ መደናገጥ ዜናውን ያነበበው ኢቲቪ፣”አንድ የቀድሞ ታጋይ አረፉ” ለሚል ዜና ቀዳሚ ዜናው የሚያደርገው ኢቲቪ፣ለሰላሳ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደል ቀዳሚ ዜና ማድረግ አቃተው።ለዚያውም ኢትዮጵያዊነታቸው አልተረጋገጠም አለን።
ethiopian killed by isil 1
ባጠቃላይ

በሊብያ ሰማዕትነት የተቀበሉ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች በሶስት ቀናት ውስጥ ብዙ ነገሮችን ቀይረዋል።
የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር አስጠብቀዋል፣
ከሊቅ እስከደቂቅ ልቡ እየነደደ የቤተ ክህነቱ እና የቤተ መንግስቱን ጥፋት ካለ አንዳች ፍራቻ ከማውገዙም በላይ ለማስተካከል ቃል የገባበት ታሪካዊ ኩነት ሆኗል፣
ሕዝብ እርስ በርሱ እንዳይፈራራ ፈር ቀዷል፣
የችግሩ ምንጭ ውጫዊ ሳይሆን ውስጣዊ ማለትም የገዢው ኢህአዴግ/ወያኔ የተሳሳተ ፖሊሲ እና ስልጣን እንደ ከረሜላ የጣማቸው የስርዓቱ መዘውሮች መሆኑን ከእዚህ በፊት የደመደመውን ለመጨረሻ ጊዜ አረጋግጧል፣
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለህሊና በሚከብድ ደረጃ ለኢትዮጵያውያን ስቃይ እና መከራ ልባቸው የማይደነግጥ በባዕዳን ዘንድም የሌለ የጥላቻ እና የጭካኔ መንፈስ በመሪዎቹ ላይ ተመልክቷል።

በባዕድ ሀገር ስደት እና መገፋት ሊገታ የሚችለው ኢትዮጵያ በጎሳ ከፋፍሎ ከሚገዛት የኢህአዲግ/ወያኔ አገዛዝ ነፃ መውጣት ስትችል ብቻ መሆኑን ቀደም ብሎ በለዘብተኛነት የሀገሩን ጉዳይ ስመለከት የነበረው ኢትዮጵያዊ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የተረዳበት እና የወሰነበት ጊዜ ነው።ያወቀ እና የወሰነ ሕዝብ ለማታለል መሞከር ደግሞ ብዙ ዋጋ ማስከፈል ብቻ ሳይሆን እንዳይሆኑ ሆኖ መውደቅን ያስከትላላ።

እነኝህ ሁሉ ክስተቶች ሕዝብ የመጨረሻ ጠርዝ ላይ እንደደረሰ በግልፅ አመላክተዋል።ጉዳዩን ኢህአዴግ/ወያኔም ምን ያህል በሕዝብ ታንቅሮ እንደተተፋ በአይኑ አይቷል።በጆሮው ሰምቷል።ይልቁንም በእዚህ ወቅት ብዙዎች ከጎኑ የነበሩ የስርዓቱ አካላት ትተው የሚኮበልሉበት ትክክለኛ ጊዜ መሆኑን ያለፈው ሳምንት ክስተቶች ሁሉ እንዳስተማሯቸው ከግምት በዘለለ መረዳት ይቻላል።አንድ ቀን የቦሌ መንገድም በሕዝብ ይዘጋል።አንድ ቀን ከቤት ሳሉ በሕዝብ ኃይል የመታሰር ዕጣ እንደሚገጥም ደጋፊዎቹ ከግምት የዘለለ እውነታ እየሸተታቸው ነው።ችግሩ ለመፍትሄው እራሳቸውን አንድ አካል ማድረግ እና ወደፊት ከመሄድ ይልቅ በትናንሽ አስተሳሰቦች እየተጠለፉ እራሳቸውን እየደለሉ መገኘታቸው ነው።የኢትዮጵያ ሕዝብ ተስፋ እና ጭላንጭል ማየት የጀመረው አሁን ነው። ያለው አማራጭ አንድ እና አንድ ብቻ መሆኑ በሰማእታቱ ደም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከመቼውም በበለጠ ተከስቷ።ይሄውም ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊ መንግስት አሁን በስልጣን ያለውን ስርዓት መቀየር ብቻ ነው።ይህ እንዴት ይሆናል? እያንዳንዱ ሰው ኃላፊነት

ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

The post የሰማዕታቱ ሰማዕትነት ለቤተ መንግስቱ እና ቤተ ክህነቱ የመጨረሻው የማስጠንቀቅያ ደወል ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

ብሔራዊ ባንክን በማጭበርበር 25 ዓመታት የተፈረደበት ግለሰብ ቅጣቱ ተሰርዞ ክሱ እንደገና እንዲጀመር ተወሰነ

$
0
0

national bank of ethiopiaቁርጥራጭ ብረቶችን ወርቅ በማስመሰል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን ከ95.5 ሚሊዮን ብር በላይ አጭበርብሮ ተሰውሯል ተብሎ በሌለበት 25 ዓመታት ጽኑ እስራትና 180 ሺሕ ብር የተፈረደበት አቶ አስማረ አያሌው፣ የቅጣት ውሳኔው ተሰርዞ ክሱ እንደ አዲስ እንዲጀምር ተወሰነ፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 18ኛ ወንጀል ችሎት ሚያዝያ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. ውሳኔውን ያሳለፈው፣ ግለሰቡ ‹‹በሌለሁበትና ባልተከራከርኩበት ይኼንን ያህል የእስራት ቅጣት ሊወስንብኝ አይችልም፤›› ብሎ በመከራከሩ ነው፡፡

ፍርድ ቤቱም ግለሰቡ ያቀረበው የመከራከሪያ ሐሳብ ትክክል መሆኑን በማመን፣ እንደገና በማረሚያ ቤት ሆኖ እንዲከራከር አዟል፡፡

አቶ አስማረ አያሌው ከታህሳስ 1998 ዓ.ም. እስከ መጋቢት 1999 ዓ.ም. ባሉት ጊዜያት ከንግድና ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሐሰተኛ የሆነ የላኪና የአስመጪ ፈቃድ በማዘጋጀት፣ ከማዕድንና ከኢነርጂ ሚኒስቴር ሐሰተኛ የሆነ የወርቅ ጥራት ማረጋገጫ በመያዝ፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በውስጣቸው ቁርጥራጭ ብረታ ብረት የያዙ 29 የታሸጉ ሳጥኖች በማቅረብ፣ ብሔራዊ ባንክን ከ95.5 ሚሊዮን ብር በላይ በማጭበርበሩ ተከሶ ነበር፡፡

አቶ አስማረ ድርጊቱን መፈጸሙ ሲታወቅባት በኬንያ በኩል ከአገር እንደወጣና ለሰባት ዓመታትም መኖሪያውን በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ አድርጎ እንደቆየ ታውቋል፡፡ አቶ አስማረ ፈጽሞታል በተባለው በማጭበርበር ድርጊት ክስ ተመሥርቶበት ባለመቅረቡ እርሱ በሌለበት ክሱ እንደተሰማና ፍርድ ቤቱም ጥፋተኛ ብሎት የ25 ዓመት ጽኑ እስራት እና የ180 ሺሕ ብር ቅጣት አስተላልፎበት እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ግለሰቡ እ.ኤ.አ. መስከረም 30 ቀን 2014 በቁጥጥር ሥር ውሎ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ፖሊስ ኮሚሽን በብሔራዊ ኢንተርፖል ተቋማቶቻቸው አማካይነት በተደረገ ትብብር ተላልፎ መስጠቱን መዘገባችን አይዘነጋም፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

The post ብሔራዊ ባንክን በማጭበርበር 25 ዓመታት የተፈረደበት ግለሰብ ቅጣቱ ተሰርዞ ክሱ እንደገና እንዲጀመር ተወሰነ appeared first on Zehabesha Amharic.

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የፕላስቲክ ፋብሪካ በከፊል በእሳት ቃጠሎ ወደመ

$
0
0

-የወደመው ንብረት ግምት ተጣርቶ አላለቀም ተብሏል

098b70d8c90cd383f97007e41b77cd5a_Lበግዙፉ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ ኮርፖሬሽን ሥር በሚተዳደረው ኢትዮ ፕላስቲክ ፋብሪካ ላይ፣ ሚያዝያ 17 ቀን 2007 ዓ.ም በማምረቻ ክፍሉ ውስጥ የተቀሰቀሰ እሳት በከፊል ውድመት አደረሰ፡፡

በፋብሪካው ውስጥ ኬሚካሎችና ሌሎች የተቀጣጣይነት ባህሪ ያላቸው ጥሬ ዕቃዎች ተከማችተው የነበሩ ቢሆንም፣ የተነሳው እሳት በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት አለመድረሱ ተገልጿል፡፡

ሚያዝያ 17 ቀን 2007 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ 8፡30 ሰዓት ገደማ የአንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ዋና መሥሪያ ቤት አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ፋብሪካ ላይ የተነሳው ቃጠሎ በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፣ ኬሚካል ነክ የሆኑ ጥሬ ዕቃዎች የተከመሩበት መጋዘን ሙሉ በሙሉ ወድሟል። እሳቱ የተነሳው በፋብሪካው የጥሬ ዕቃዎች ማከማቻ መጋዘን ላይ ቢሆንም፣ ከሁለት ሰዓታት በላይ በተደረገ ርብርብ በቁጥጥር ሥር ውሏል፡፡

የአዲስ አበባ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና ቁጥጥር ኤጀንሲ ከተደወለለት በኋላ ቃጠሎው ቦታ ለመድረስ ከአንድ ሰዓት በላይ መዘግየቱን የፋብሪካው ሠራተኞችና በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ የእሳት አደጋ መከላከል ሠራተኞች በበኩላቸው፣ በዕለቱ የነበረው የትራፊክ መጨናነቅ በሚፈለገው ፍጥነት መድረስ እንዳይችሉ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል፡፡

የእሳት አደጋ መከላከል ሠራተኞች ዘግይተው ከደረሱ በኋላም ቃጠሎውን ገብተው ለማጥፋት እንዳይችሉ፣ የፋብሪካው የውስጠኛ ክፍል ለተሽከርካሪዎች አስቸጋሪ በመሆኑ በግምት ተጨማሪ 20 የሚሆኑ ደቂቃዎች ሲባክኑ ታይቷል፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎችን ጨምሮ ፖሊስና የእሳት አደጋ መከላከል ሠራተኞች እሳቱን ለመቆጣጠር በሚሞክሩበት ወቅት፣ ከሚቃጠለው ኬሚካል ይወጣ የነበረው ጭስ የሚያቃጥል በመሆኑና በመተንፈሻ አካላት ላይ በደረሰባቸው ተፅዕኖ ሲፈተኑ ተስተውሏል፡፡ የአደጋ ሠራተኞቹ ከኬሚካሉ ጭስ ሊከላከላቸው የሚችል የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ አልነበራቸውም፡፡

በዚያው ቅጽበትም አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል በጭሱ ምክንያት ራሱን ስቶ ወድቆ የአደጋ ሠራተኞች በፍጥነት ወደ ሆስፒታል ወስደውታል፡፡ ነገር ግን ከቆይታ በኋላ ከሆስፒታል ተሽሎት እንደወጣ ከቀጣና ሦስት ፖሊስ ማዘዣ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡

የፖሊስ ማዘዣ ጽሕፈት ቤት ኃላፊው ሳጂን ኪሮስ ፍቃዱ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ከአንድ አባላቸው ጊዜያዊ ጉዳት ውጪ በሰው ሕይወት ላይ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰና መንስዔው ገና በምርመራ ተጣርቶ አለማለቁን ገልጸዋል፡፡ እሳቱን ለማጥፋትም ሰባት የአደጋ መከላከያ ተሽከርካሪዎች ሲሰማሩ፣ በአደጋው የጠፋው የንብረት መጠን ግን ለጊዜው አለመታወቁ ተገልጿል።

በተመሳሳይ ሚያዝያ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ምሽት አንድ ሰዓት አካባቢ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ስሙ 7ኛ ሸንኮራ በረንዳ በተባለው ሥፍራ በተነሳ የእሳት አደጋ፣ 800,000 ብር የተገመቱ ሁለት ካፍቴሪያዎችና አንድ የመኖርያ ቤት ተቃጠሉ። በተለይ ዓለም ካፌ በሚል መሠርያ ተመርቆ ሥራ ለመጀመር አንድ ቀን ሲቀረው መቃጠሉ ታውቋል፡፡

በአንድ የእሳት አደጋ አጥፊ ባለሙያ ላይም መጠነኛ ጉዳት መድረሱ ተረጋግጧል። ሦስት ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ንብረትን ግን እሳቱን በማጥፋት ርብርብ ማትረፍ መቻሉን፣ የሁለቱም አደጋዎች መንስዔ በመጣራት ላይ መሆኑን ሪፖርተር ከእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና ቁጥጥር ኤጀንሲ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

Source:: Ethiopian Reporter

The post የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የፕላስቲክ ፋብሪካ በከፊል በእሳት ቃጠሎ ወደመ appeared first on Zehabesha Amharic.

የሳንቲም የመሰብሰቡ ተቃውሞ ስኬታማ በሆነ መልኩ እንደቀጠለ ነው

$
0
0

ረቡእ ሚያዝያ 21/2007
ህዝበ ሙስሊሙ ሀይማኖታዊና ህገ መንግስታዊ መብቶቹ እንዲከበሩለት ቢጠይቅም አሁንም ድረስ ከመንግስት ጠብ ያለ መልካም ምላሽ አላገኘም፡፡ እንዲያውም ከወትሮው በለየለት መልኩ መንግስት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ እየፈፀመ ያለው ጭቆና ፍጥጥ ባለ ሁኔታ ተባብሶ የቀጠለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጋር የሚያገናኛቸው ሥውር መስመር እንኳ የሌላቸውን ዓለም አቅፍ ክስተቶች ሁሉ እየጎተተ ለዚሁ የጭቆናው ጉዞው ተጨማሪ መንደርደሪያ ማድረግን መርጧል፡፡ ይህም ሆነ በዚህ የበደል ደመና ባጠለለበት ድባብ ውስጥም ግን የመንግስትን መጠነ ሰፊ ጭቆና በመቋቋም ህዝባዊ ተሳትፎን በሚያረጋግጡ፣የመነቃቃትን ስሜት በሚፈጥሩ፣ ከአደጋ ነፃ በሆነ ክልል ውስጥ በተቀመሩና ለቀጣይ መጠነ ሰፊ ትግሎች መስፈንጠሪያ በሚሆኑ የትግል ስልቶች በአዲስ የትግል ምህዋር ላይ ትግላችንን አጠናክረን ቀጥለናል፤ አልሐምዱሊላህ!
santim
አሁን ላይ እየተገበርነው ያለነው የሳንቲም ማሰባሰብ መርሃ ግብርም የዚህ ተቃውሟችን አዲስ ምእራፍ አካል ነው፡፡ በአገር አቀፍ ደረጃ እንዲተገበር የታዘዘው የሳንቲም ማሰባሰብ መርሃ ግብር ይፋ ከሆነ ጀምሮ ህዝበ ሙስሊሙ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም የሀገራችን ከተሞች የሚገኙ ሙስሊሞች አኩሪ እና ስኬታማ በሆነ መልኩ ሳንቲሞችን በመሰብሰብ የዘመቻውን ውጤታማነት ወጋገን እያሳዩ ነው፡፡ ለአብነት ያህልም በሀገራችን የሚገኙ በርካታ የመንግስት እና የግል ተቋማት፣ እንዲሁም መሰል ድርጅቶች የሳንቲም እጥረት እየተከሰተ በመሆኑ መንግስት መፍትሄ እንዲሰጣቸው እየወተወቱ እንደሆነ ታውቋል፡፡ ሳንቲም የመሰብሰቡ መርሃ ግብር የተጀመረው ቅርብ ሊባል በሚችል ጊዜ ቢሆንም ህዝቡ መብቱን ለማስከበር ካለው ቁርጠኝነት በተወለደ ተነሳሽነት ሳንቲሞችን ከያሉበት በማደን እና በመቆጠብ ላይ ትጉህ ሆኖ በመገኘቱ ከላይ ለተገለፀው አመርቂ ውጤት መገኘት ምክንያት ሆኗል፡፡ በሳንቲም ትብብር መንፈጉ እንቅስቃሴ ከምናገኛቸው ጥቅሞች አንዱ ህዝቡ የትብብር መንፈግ ትግል ልምድ እንዲኖረው ማድረግ እንደመሆኑ መጠንም ርብርቦሹ በዚሁ ከቀጠለ ካቀድነው ጊዜ ቀድመን የዚህን ዘመቻ ውጤታማነት በማረጋገጥ ወደ ቀጣዩ የትግል ስልት እንንደረደራለን ተብሎ ይጠበቃል፡፡

አሁንም ቢሆን ግን ከከተማ እስከ ገጠር የምንገኝ ሙስሊሞች ሁሉ በእስከዛሬው ሳንቲም የመሰብሰብ ስኬታማ እንቅስቃሴያችን ሳንዘናጋ በአዲስ ወኔና ጉልበት በሳንቲም አሰባሰቡ ላይ ልንበረታ ይገባል፡፡ መቼም ቢሆን ህዝብ የተረባረበበት ስራ ከውጤታማነት የሚርቀው በጊዜ ብቻ ነውና የጀመርነውን መርሃ ግብር በአዲስ መንፈስ በማስቀጠል የድል ግስጋሴያችንን እናፍጥን፡፡ ትግሉ የሁላችንም እንደመሆኑ መጠን ቀልጣፋና የተሻለ የአሰባሰብ ጥበቦች ሲኖሩን ልምዱ ወደ ሌሎቻችንም እንዲደርስ በማድረግ ለተሻለ ውጤት እንትጋ፡፡ እናቶች፣ አባቶች፣ ወጣቶች፣ ተማሪዎች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ ነጋዴዎችና ሌሎችም የሚመለከታቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ሁሉ ተሳትፏቸው ይጨምር ዘንድ በየቤታችን በመመካከርና ግንዛቤ በመስጠት ጥረታችንን እንድናጠናክር፣ እንዲሁም መርሃ ግብሩ ወሳኝ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ መንገዳችን ላይ ሊገጥሙን ከሚችሉ አዘናጊ ጉዳዮች በመጠንቀቅ ይህን የተቃውሞ መርሃ ግብር ባማረ ውጤት እንድናሳካ አደራ እንለላን!

ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

The post የሳንቲም የመሰብሰቡ ተቃውሞ ስኬታማ በሆነ መልኩ እንደቀጠለ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: የብሄራዊ ቡድናችን አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ማን ናቸው?

$
0
0

Yohanes sahele
ኢትዮ ኪክ እንደዘገበው

* የተወለዱት አዲስ አበባ ጉለሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲሆን
* ያደጉት ደግሞ አዋሬ / 4 ኪሎ አካባቢ ነው
* በርካቶችን ባፈራው ቤልየር ሜዳ ኳስ ተጫውተው አደጉ
* ወቅቱ የሚጫወቱበት ቦታ አማካኝ ስፍራ
*በዛ የልጅነት ጊዜም አንበሳ እፃናት ተጫወተው ያደጉበት ቡድን ሲሆን
*ቀጠሉና ቀድሞ ከፍተኛ 13 ቀበሌ 15 ጨምሮ
* ለከፍተኛ ውድድሮች ተመርጥው 4ኪሎ/ ፖርላማ በነበረ ሜዳ በተዘጋጀ ውድድር ላይ ተጫወተዋል
*ራስ ሆቴል ለተባለ ቡድን 4 ቁጥር ማሊያ ለብሶው ሲጫወቱ በወቅቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ በሆኑት መንግስቱ ወርቁ እይታ ውስጥ ገብተው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ተመረጡ
* ለመጀመሪያ ጊዜም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማሊያ ከየመን ብሔራዊ ቡድን በነበረ ጨዋታ ላይ ተሰልፎ ተጫወቱ
* በክለብ ራስ ሆቴል ቡድን ለቀው ሌላ ከለብ መጫወት መፈለጋቸውን የተገነዘቡት የጊዜው የመንግስት ኃላፊ ሌላ ክለብ የምተቀይ ከሆነ መቻል ክለብ ተጫወት አለበለዚያ ለሌላ ክለብ መጫወት አትችልም ሲባሉ
* ለ1 አመት ለማንም ክለብ ሳይጫወቱ የቅጣቱን ጊዜ አዲስ ከነማ የተባለ ክለብ በማሰልጠን አሳለፉ
• ቀጠሉ እና ለቅድስ ጊዮርጊስ ክለብ ለመጫወት ተስማሙ፧ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቆይታቸው ጊዮርጊስ ከኬንያ ክለብ ጋር የአፍሪካ የክለቦች ሻምፒዮን ሊግ ለመልስ ጨዋታ ኬንያ ሲያመራ ከጨዋታው በኃላ ሳይመለሱ ቀሩ ፧ ከኬንያ በዛው ወደ አሜሪካ አቀኑ።
* የ49 አመቱ አሰልጣኝ ከ25 አመት በላይ አሜሪካ ኑሯቸውን አድርገው የአሜሪካ ዜግነት ይዘዋል።
— –በአሜሪካ ቆይታቸው—-
~~~~~~~~~~~~~~~~
፥ ለተማሩበት ኮሌጆች በስፖርት ቀጥተኛ ተሳታፊ ነበሩ
፥ በእዛው አሜሪካ በማስሜዲያ ኮሚንኬሽን ዲግሪ ተመርቀዋል
፥ ስፖርት ሊደርሺፕ እና ኮቺነግ ማስተር ይዘዋል
፥የአሰልጣኝነት B እና C ላይሰንስ አላቸው
፥ በአሜሪካ በአልባማ ዮኒቨርስቲ እና ኮሌጆች ላይ የማሰልጠን አጋጣሚ ነበራቸው
፥ በኢትዮጵያ ቴክኒካል ዳሬክተርነት ከ8 አመት በላይ ሰርተዋል
፥የደች ዲፕሎማ
፥ የCAF ኢንስትራክተር
፥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ17 አመት በታች አሰልጣኝ
፥ የደደቢት ስፖርት ክለብ የቴክኒካል ዳሬክተር በኃላም የክለቡ ዋና አሰልጣኝ
፥ አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ

The post Sport: የብሄራዊ ቡድናችን አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ማን ናቸው? appeared first on Zehabesha Amharic.

የህወሃት ደባ በሚስጥራዊዉ ስብሰባ * የህወሃትን ደባ የሚያጋልጥ የሳዲቅ አህመድ ልዩ ፕሮግራም (ሊደመጥ የሚገባ)


“ሞት የዘመኑ ዕለት እንጅ የመነኑ ዕለት አይደለም”–ከበልጂግ አሊ

$
0
0

ethiopians isis
“ከመሸ ተነሳሁ ከተፈታ በሬ፣
እደርስ አይመስለኝም ከእንግዲህ ሃገሬ።“
አገኘሁ እንግዳ

ጀርመን ፍራንክፈርት በሚገኘው የመድኃኒዓለም ቤተክርስትያን ውስጥ በሊቢያ ለተሰው ዜጎቻችን ጸሎተ-ፍትሃትና ከዛም ሰላማዊ ሰልፍ ሲደረግ ተገኝቼ ነበር። በደቡብ አፍሪካም ይሁን በሊቢያ በደረሰው ችግር ሁላችንም ሃዘን ገብቶናል። በዚህ ግፍ እንባ ያነባንም አለን። ከልባችንም ያዘንን ብዙ ነን። ቄሱ ትምህርት ሲሰጡ እነዚህ ለሃይማኖታቸው ሲሉ በወጣትነት የሞትን ጽዋ የተቀበሉ ሰማዕታት ትልቅ በረከት አግኝተውበታል ነው ያሉት። አዎ ለእምነት መሞት ትልቅ በረከት ነው። ጥንትም ለአመኑበት መሞት ታሪክ መስራት ነው፤ ሕይወትን በሌላ ፈርጅ መቀጠል ነው፤ ዳግም ትንሳዔ፣ ዳግም ልደት ነው። አሁንም ቢሆን የተቀየረ ነገር የለም።

Read full story in PDF

The post “ሞት የዘመኑ ዕለት እንጅ የመነኑ ዕለት አይደለም” – ከበልጂግ አሊ appeared first on Zehabesha Amharic.

(ሰበር ዜና) ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ በሊቢያ ኢትዮጵያውያን ሞተው የኔ 25ኛ ዓመት የሢመት በዓል እንዲከበር አልፈልግም አሉ * በስደት ያለው ሲኖዶስ በሊቢያ ያለቁት ወገኖች “ሰማዕታተ ኢትዮጵያ በምድረ ሊቢያ”ተብለው እንዲታሰቡ ወሰነ

$
0
0

holy sinod ethiopia
(ዘ-ሐበሻ) በስደት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕጋዊ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ የ25ኛ ዓመት የሢመት በዓል ሰሞኑን እንደሚከበር ተገልጾ የነበረ ቢሆንም ፓትሪያርኩ “ወገኖቼ በሊቢያ በደቡብ አፍሪካ እና በአረብ ሃገራት እያለቁ የኔ በዓል እንዲከበር አልፈልግም” አሉ:: የበዓሉ መርሃ ግብር ተቀይሮም መታሰቢያነቱ በሊቢያ ለሞቱት መታሰቢያ እንዲሆን ጠይቀዋል::

ሲኖዶሱ ዓመታዊ ጉባኤውን በባልቲሞር መካነ ሰላም ኢየሱስ ቤ/ክ ዛሬ ያካሄደ ሲሆን በሊቢያ በአይሲኤል የተገደሉት 28 ኢትዮጵያውያን ልክ ሰማዕታተ ናግራን ተብሎ እንደሚዘከሩት “ሰማዕታተ ኢትዮጵያ በምድረ ሊቢያ” ተብለው እንዲዘከሩ መወሰኑን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል::

ፓትሪያሪክ አባ መርቆርዮስ በዓሉ አይገባኝም ያሉበትን ደብዳቤ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ:: ሲኖዶሱ በቀጣይ ቀናት ሰፊ መግለጫ ይሰጣል::
HH letter

The post (ሰበር ዜና) ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ በሊቢያ ኢትዮጵያውያን ሞተው የኔ 25ኛ ዓመት የሢመት በዓል እንዲከበር አልፈልግም አሉ * በስደት ያለው ሲኖዶስ በሊቢያ ያለቁት ወገኖች “ሰማዕታተ ኢትዮጵያ በምድረ ሊቢያ” ተብለው እንዲታሰቡ ወሰነ appeared first on Zehabesha Amharic.

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ 25ኛ በዓለ ሢመታቸው መታሰቢያነቱ በሊቢያ ለተሰውት እንዲሆን አሳሰቡ

$
0
0
አባ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ

አባ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ

“…ይሁን እንጅ ይህ ጊዜ ልጆቻችን በስደት ሀገር በሃይማኖታቸው ምክንያት በሰይፍ እየታረዱ ያሉበት ጊዜ በመሆኑ የተዘጋጀው የ25ኛ ዓመት በዓለ ሲመት መታሰቢያ፣ የመርሐ ግብር ማሻሻያ ተደርጎበት፣ በሊቢያ ሚያዝያ ፲፩ ቀን ፪ሺ፯ ዓ.ም ለተሰየፉትና በጥይት ተደብድበው ለሞቱት ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች የመታሰቢያ በዓል እንዲሆን ይደረግ ዘንድ በአክብሮት አሳስባለው። [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

 

The post ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ 25ኛ በዓለ ሢመታቸው መታሰቢያነቱ በሊቢያ ለተሰውት እንዲሆን አሳሰቡ appeared first on Zehabesha Amharic.

በሴቶች ፕሪምየርሊግ የአዳማ ከተማ ተጫዋቿ ሕይወት በመርዝ ማለፉ ተዘገበ

$
0
0

በሴቶች ፕሪምየር ሊግ የደቡብ ምስራቅ ዞን የ12ተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ማክሰኞ ቀን ሚያዚያ 20/2007 ተከናውነዋል ከነዚህም መካከል አሰላ ላይ ሙገር ሲሚንቶ ከአዳማ ከተማ ጋር 1ለ1 የተለያዩበት ጨዋታ ይገኝበታል:: በዚህ ቀን ለክለቧ አዳማ ግቧን ያስቆጠረችው የኔነሽ ጌቱ ወይም በጓደኞቿ አጠራር የኑ ነበረች በማግስቱ ረቡዕ ከረፋድ 3 ሲል ከቡድኑ አባላት ጋር ናዝሬት ማረፊያ ካምፓቸው ውስጥ ነበረች ሀኪም ቤት የተኛች አያቴን ልጠይቅ ብላ ፈቃድ ወስዳ ሄዳለች በኋላ ላይ ወደ ክለቡ የደረሰው ወሬ መልካም አልነበረም ተጫዋቿ መርዝ በመጠጣት ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች ቀደም ብሎ ሂወቷን ለማዳን ወደሆስፒታል የወሰዳት ወንድሟ ነበር ነገር ግን ሳይሳካለት ቀርቷል።
merz
ድሬቲዩብ የቡድኑን ቡድን መሪዋን ወ/ሮ ጀሚላ ኡስማንን አነጋግሯል > ብለዋል::

ከ2005 ጀምሮ የቡድኑ አባል የነበረችው የኔነሽ ጌቱ የቀብር ስነስርአቷ ሀሙስ ሚያዚያ 22 በናዝሬት መድሀኔአለም ቤተክርስቲያን ይፈፀማል።

ምንጭ – ድሬ ቲዩብ

The post በሴቶች ፕሪምየርሊግ የአዳማ ከተማ ተጫዋቿ ሕይወት በመርዝ ማለፉ ተዘገበ appeared first on Zehabesha Amharic.

ፖሊስ በ‹‹በሁከትና ብጥብጥ›› ተጠርጣሪዎች ላይ ሦስት መዝገብ አደራጅቻለሁ አለ •እነ ወይንሸት ለሁለተኛ ጊዜ 6 ቀን ተቀጥሮባቸዋል

$
0
0

•እነ ወይንሸት ለሁለተኛ ጊዜ 6 ቀን ተቀጥሮባቸዋል
•‹‹ወይንሸት ከአሁን በፊትም ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ጋር ስታሸብር ነበር›› ፖሊስ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም መንግስት አይ.ኤስ.አይ.ኤስ ሊቢያ በሚገኙ ንጹሃን ኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸመውን አሰቃቂ የሽብር ድርጊት ለማውገዝ ጠርቶት በነበረው ሰልፍ ላይ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ አስነስታችኋል፤ ተካፍላችኋልም›› በሚል ፖሊስ ባሰራቸው ሰዎች ላይ ሦስት የተለያዩ መዝገቦች ማደራጀቱን አስታውቋል፡፡
addia ababa
ዛሬ ሚያዝያ 22 ቀን 2007 ዓ.ም በቄራ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀረቡ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ሌሎች በዕለቱ የተያዙ ሰዎችን በተመለከተ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ሲያስረዳ እንደገለጸው፣ ፖሊስ የራሱን ቡድን በማዋቀር ተጠርጣሪዎችን በሦስት መዝገቦች ስር እንደየተሳትፏቸው አደራጅቻለሁ ብሏል፡፡ በዚህ መሰረት በሶስተኛው መዝገብ ላይ ያካተታቸውን በርካታ ታሳሪዎች አጣርቶ መልቀቁን የገለጸው ፖሊስ፣ በሁለተኛውና በአንደኛው መዝገብ ላይ ባሉት ተጠርጣሪዎች ግን ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ገልጹዋል፡፡

አንደኛው መዝገብ ላይ በእነ ወይንሸት ሞላ መዝገብ 5 ሰዎች የተካተቱ ሲሆን አራቱ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ናቸው፤ አንደኛዋ ተጠርጣሪ ደግሞ ፖሊስ የፓርቲው አባል እንደሆነች የሚገልጸው፣ እሷ ግን አባል አለመሆኗን የገለጸች መሆኗን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ስለሆነም በዚህ መዝገብ የተካተቱት ወይንሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ጸጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬ፣ ማስተዋል እና የፓርቲው አባል ያልሆነችው ቤተልሄም ይገኙበታል፡፡ ማስተዋል በዛሬው ዕለት ቀደም ብሎ የተሰጠው የቀጠሮ ቀን ስላልደረሰ ፍርድ ቤት አልቀረበም፡፡ ቤተልሄም ‹‹የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሳልሆን አባል ነሽ እየተባልኩ ምርመራ ይደረግብኛል፤ ሌሊት እየተጠራሁ እመኝ እየተባልኩ ነው›› ስትል ለፍርድ ቤቱ ገልጻለች፡፡
weyeneshet molla
በሁለተኛው መዝገብ ላይ ደግሞ 15 ተጠርጣሪዎች ተካትተዋል፡፡ ፖሊስ በዚህ መዝገብ በተካተቱ ተጠርጣሪዎች ላይ ክሱን ሲያሰማ እንዲህ ብሏል፤ ‹‹ተጠርጣሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ሲያደርጉ ‹ጠንካራ መሪ እንጂ ጠንጋራ መሪ አንፈልግም›፣ ‹ወያኔ አሳረደን›፣ ‹ፍትህ የለም!››› በማለት ሁከት እንዲነሳ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡››

የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በምርመራ ወቅት የገጠማቸውን አቤቱታ ለፍርድ ቤቱ ያሰሙ ሲሆን፣ በተለይ የሚደረግባቸው ምርመራ ከፓርቲው ጋር የተያያዘ እንጂ ከተጠረጠርንበት ጉዳይ ጋር የተያያዘ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ ‹‹ምርመራው ከጉዳዩ ጋር የሚገናኝ አይደለም፤ ሌሊት ሌሊት እየተጠራሁ ምርመራ ይደረግብኛል፡፡ የፓርቲ አባል መሆን ወንጀል እስኪመስለኝ በፓርቲ አባልነቴ ጫና ይደረግብኛል፡፡ በዚያ ላይ የጤና እከል ገጥሞኛል፤ ህክምና ያስፈልገኛል›› ስትል ለፍርድ ቤቱ ያስረዳችው ወይንሸት ሞላ፣ ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብት እንዲሰጣት ጠይቃለች፡፡

በሁለቱም መዝገብ የተካተቱት ሁሉም ተጠርጣሪዎች የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጠይቀዋል፡፡ ፖሊስ በበኩሉ በመጀመሪያው መዝገብ ላይ ያሉት እነ ወይንሸት ላይ የምርመራ ስራውን እንዳልጨረሰ በመግለጽ 14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡ በተለይ ወይንሸት ሞላ ላይ ፖሊስ፣ ‹‹ከአሁን በፊትም ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ጋር ተመሳስላ በመልበስ ስታሸብር ነበር›› በማለት ዋስትና እንዳይሰጥና የጠየቀው የምርመራ ጊዜ እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡ በሁለተኛው መዝገብ ላሉት ደግሞ 7 ቀን ፖሊስ ጠይቋል፡፡ ፍርድ ቤቱ በበኩሉ በሁለቱም መዝገብ ላይ በተመሳሳይ የ6 ቀን ጊዜ በመስጠት ለሚያዝያ 28 ቀን 2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
መንግስት በጠራው ሰልፍ ላይ የተሳተፉ ወጣቶች እስር አሁንም እንደቀጠለ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ይጠቁማሉ፡፡ በትናንትናው ዕለትም ሦስት የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አባላት (አንደኛው አሁን ላይ የሰማያዊ አባል) መታሰራቸው ይታወሳል፡፡

The post ፖሊስ በ‹‹በሁከትና ብጥብጥ›› ተጠርጣሪዎች ላይ ሦስት መዝገብ አደራጅቻለሁ አለ •እነ ወይንሸት ለሁለተኛ ጊዜ 6 ቀን ተቀጥሮባቸዋል appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live