Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ትንሽ ሰለ ጀማል ወይም በትክክለኛው ስለ ኤፍሬም የማነ

$
0
0

Muslim Wedaje

11188495_847159402031809_4959704176181540321_nበሊቢያ ከተገደሉት ንፁሃን ዜጎች መካከል በሚዲያ በተለቀቀው መሰረት 28 ኢትዬጲያውያን እንደተገደሉ ተገልፆ ነበር፡፡ ሆኖም ከቀናት ቡሃላ ኢትዬጲያውያን ብቻ ሳይሆኑ ኤርትራውያንም አብረው እንዳሉ ተገልፆል፡፡

የሟቿቹ ማንነት እየተለየ በመጣ ወቅት አንዳንዱ ወድያው ማንነታቸው ታውቆ ቤተሰቦቻቸው ሃዘን ሲቀመጡ ሌሎች ደግሞ ፎቶዋቸው የተመሳሰለባቸውን እከሌም ሞተ በማለት በፌስቡክ ሲሰራጭ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ያልሞቱት ሰዎች እረ እኔ በሂወት አለው በማለት ስህተቱን እያረምን በጋራ ስንጓዝ ነበር፡፡

በተመሳሳይም ከተገደሉት መካከል ጀማል ራህማ የተባለ ሙስሊም ኢትዬጲያዊ አብሮ መገደሉን ሶማሌላንድ ፕሬስ የተሰኘ ድህረ ገፅ መረጃውን ለቆ ነበር፡፡ ይህም መረጃ በተለያዩ ቦታዎች ተሰራጭተው ነበር፡፡ ይህንንም መረጃ በሚያጠናክር ሁኔታ የቪኦኤ የኦሮምኛው ክፍል በሊቢያ ካሉ ኢትዬጲያውያን ጋር ባደረገው ቃለመጠይቅ አንድ በሊቢያ የሚገኝ ኢትዬጲያዊ የተገደሉትን በሙሉ እንሚያውቃቸውን ቃሉን በመስጠት ከሞቱት ውስጥ አንድ ሙስሊም መኖሩን ለቪኦኤ ተናግሮ ነበር፡፡ በወቅቱ ስሙን ግን አልጠቀሰም ነበር፡፡ በዚህ መረጃ የተነሳ ጀማል ራህማ ከወገኖቹ ጋር መሰዋቱ በሰፊው ሲነገር ቆይቷል፡፡ ይህ መረጃ ሁሉም ሲቀባበለው ግን አንዳንድ እሳት ለመጫር ሌት ቀን የሚለፊት የክብሪት ልጆች እንደሚያናፍሱት ታሪክ ለመጋራት አልያ ደግሞ በውሸት ሰዎችን ለመሸንገል በሚል አልነበረም፡፡

ለመጀመርያ ጊዜ ጀማል የተባለ ሰው መሰዋቱን የዘገበው ይህ ድህረገፅ ይህ ነበር፡፡

http://www.somalilandpress.com/ethiopia-muslim-martyr-amon…/

በመቀጠልም የቪኦኤ የኦሮምኛው ክፍል በሊቢያ በስደት የሚገኝ የኦሮምኛ ተናጋሪው የሆነ ኢትዬጲያዊን ያነጋገረበትን እና ከተገደሉት ውስጥ 1 ሙስሊም መኖሩን የተናገረበትን ከቪኦኤ የኦሮሚኛ ድህረገፅ ውስጥ ገብታቹ አልያ የሚከተለውን ሊንክ በመክፈት ማድመጥ ትችላላችሁ፡፡

http://www.voaafaanoromoo.com/audio/2714864.html

ሁለቱም መረጃዎች ከላይ የተቀመጡ በመሆናቸው የመረጃ ምንጮቹን መጠየቅ እና ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

እንደ ዳንኤል ክብሪትአይነቱ ጭራሽም ሙስሊም እና ክርቲያኑን ለማዋደድ የተፈጠረ ድራማ እንደሆነ አስመስለው ሲያቀርቡ ነበር፡፡ የሙስሊም እና የክርስቲያን ተከባብሮ በሰላም የመኖር ታሪክ አሁን የተጀመረ እስኪመስል ድረስ ሙስሊሞች ድራማ እንደሰሩ አስመስሎ ማቅረብ ለምን አስፈለገው ??ስለመስዋትነትስ በኢትዬጲያ ሙስሊሞች ላይ ለመንጠባረር ስለምን አስፈለገው??? መስዋትነትን፣ መታረድን ለኢትዬጲያ ሙሰሊምስ ይነገረዋል እንዴ???. እስቲ ቦሩ ሜዳ ትመስክር!!

የኢትዬጲያ ሙስሊም ከጥንት ታሪኩ ጀምሮ በኢትዬጲያ ውስጥ ባሉ መሪዎች አንገቱ ሲቀላ፣ሲታረድ እና ሲጨፈጭ እመቢኝ ብሎ ለእምነቱ ሲሰዋ እና ሲንገላታ መቆየቱን ሊዘነጋ አይገባውም፡፡ ሙስሊሙ የተጨፈጨፈው በውጪ ጠላት ሳይሆን በሃገሬው መሪ መሆኑም ይሰመርበት፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ ግን ሙስሊሙ በክርስቲያን ወገኖቹ ላይ አልተዘባበትም፣በፍቅር እና በሰላም ተዋዶ ተከባብሮ እየኖረ ይገኛል፡፡

የኢትዬጲያ ሙስሊም ድርጊቱን ያወገዘውስ ሃይማኖቱ ስለሚያዘው፣ሰብአዊነት ስለሚሰማው እና የሞቱት ወገኖቹ በመሆኑ እንጂ የክብሪት ልጆች እንዳይከፋቸው በሚል አልነበረም፡፡

ግድያን እና ግፍን የምናወግዘው እምነት እየለየን ቢሆን ኖሮ የሊቢያ የተገደሉት ክርስቲያኖች ስለሆኑ ምን አገባን ባልን ነበር፡፡ እስካሁን አይኤስ ከገደላቸው ሙስሊሞች ቁጥር አንፃር ሲታይ እምነታቸው ክርስቲያን በመሆናቸው የተገደሉት ሰዎች ቁጥራቸው ለንፅፅር እንኳን የማይቀርብ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ምክንያቱም ISIS በአስርሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞችን በኢራቅ እና በሶሪያ አርዷል ጨፍጭፏል፡፡ ሌላው ቢቀር ሰሞኑን ብቻ የመን ገብቶ የገደላቸውን ሰዎችን ስናይ ክርስቲያኖች አልነበሩም፡፡ ይህ ስል ግን ግድያን ከቁጥር ጋር እያወዳደርኩኝ እያቃለልኩኝ አይደለም፡፡ የአንዲት ነፍስ ዋጋ በኢስላም ከሰው ልጆች ነፍስ እኩል ዋጋ እንዳላት ስላስተማረን ማንም በግፍ ቢገደል እናዝናለን እንጂ እምነቱ ሌላ ስለሆነ አንደሰትም፡፡ ሙስሊሞች እየተጨፈጨፉ በመሆኑ የሌላ እምነት ተከታዬችም ይገደሉ አንልም፡፡

በወገኖቻችን ላይ በሊቢያ የደረሰው ግድያ የሽብር ቡድኑ ISIS በለቀቀው የ 28 ደቂቃ ቪዲዬ ላይ እምነታቸውን እንዲቀይሩ ብቻ ተጠይቀው መገደላቸውን ሳይሆን የተገለጸው እምነታቸውን የማይቀይሩ ከሆነ መክፈል ያለባቸውን ግብር እንዲከፍሉ እና እንዲለቀቁ ተጠይቀው እንደነበር ነው፡፡ ሽብር ቡድኑ ሁለቱንም የማታደርጉ ከሆነ በሚል እንደገደላቸው በቪዲዬ ላይ ተገልፆል፡፡ አንድ መዘንጋት የሌለበት ጉዳይ ግን ሶርያ እና ኢራቅ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች እምነታቸውን ሳይቀይሩ ግዴታ የሚደረግባቸውን አመታዊ ግብር እየከፈሉ በሰላም እምነታቸውን እያራመዱ እየኖሩ መሆኑን ማስታወስ እወዳለው፡፡ ይህን ለማንሳት የፈለኩት ዳንኤል ክብሪት የኢትዬጲያ ሙስሊሞች ወንጀሉን የፈፀሙት ያህል ሙስሊሙን በመጠየፍ በተደጋጋሚ በጀማል ሽፋን ሙስሊሞች የክስርስቲያኖችን ክብር ለማጉድፍ እንደተንቀሳቀሱ አስመስሎ ሲያቀርብ ስለነበር ነው፡፡ –

መታወቅ ያለበት ሌላው ነጥብ የኢትዬጲያ ሙስሊም ማንንም ፈርቶ ለማጭበርበር የሚሞክበት ነገር የለም፡፡ ጀማል ሙስሊም ሆነ ክርስቲያን አልያ ድንጋይ አምላኪ ለኛ ለሙስሊሞች ሰው በመሆኑ ብቻ የተፈጸመበትን ድርገት እናወግዛለን፡፡ ጀማል ሙስሊም በመሆኑም አንዳችም ለኢትዬጲያ ሙስሊም የሚጨምርለትም ሆነ የሚቀንስበት ነገር የለም፡፡ ከተገደሉት መካከልም ሙስሊም አለ ብሎ መናገሩ ሆን ተብሎ ሰዎችን ለማጭበርበር ሳይሆን የአይን እማኞች አይተናል ብለው የተናገሩትን መረጃ በመመርኮዝ ነው፡፡

ጀማል የተባለው ሰው ትክክለኛ ማንነቱ ኤፍሬም የማነ መሆኑ ቢታወቅ ቀድሞ የተለቀቀው መረጃ ስህተት ነበር ብሎ እንደሌሎቹ ከማለፍ ይልቅ ሙስሊሙ ሆን ብሎ ክርስቲያኑን ለመሸንገል የፈጠረው አድርጎ ለማቅረብ መሞከሩ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ያለውን ንቀት እና በሙስሊም እና በክርስቲያኑ ወገኖች መካከል እሳት ለማቀጣጠል ያለውን ትጉህ ፍላጎት ያሳየ ነው::

ጀማል የተባለው ሰው ኤፍሬም ሆኖ በመገኘቱ ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች የሚያጡት አንዳችም ነበር የለም፡፡ ድርጊቱን ያወገዙት ጀማል ስለሆነ አልያ ገብረማርያም ስለሆኑ ሳይሆን ሰው በመሆናቸው ብቻ ነው፡፡ በእምነታቸው መገደላቸው የእምነቱ ተከታዬች የበለጠ ቢያስቆጫቸውም በአለም አቀፍ ደረጃ የሽብር ቡድኑ እየጨፈጨፈ የሚገኘውን ሙስሊም ብዛት አይናቸው ተከፍቶ ቢያዩ ግን ተመስገን ብዙም እኛን አልነኩንም ብለው ያመሰግኑ ነበር፡፡

በተረፈ የሙስሊሞችን ስብእና ለማጉላት ጀማል የተባለ ገጸ ባህሪ ፈጥሮ የምናወራበት ምክንያት አለመኖሩ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ለ 1400 አመታት ሙስሊሙ ከክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቹ ጋር ችሎ በመኖር አስመስክሯል፡፡ አሁንም በሊቢያ ባሉ ስቃይ እየደረሰባቸው በሚገኙ ክርስቲያን ወገኖች ላይ ሂወታቸውን በከፍተኛ አደጋ ውስጥ በመክተት ድጋፍ እና ትብብር እያደረጉላቸው የሚገኙት የዳንኤል ክብሪት ቲፎዞዎች ሳይሆኑ ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች መሆናቸው ሊዘነጋ አይገባም፡፡ ይህን ደሞ በድህረገጽ መረጃ የተገኘ ሳይሆነ በሊቢያ የሚገኙት ክርስቲያን ወገኖቻችን በአንደበታቸው የመሰከሩት ነው፡፡ ሙስሊሙ ግን ይህን መልካም ነገር በመደረጉ በክርስቲያን ወገኖቹ ላይ እንደዳንኤል ክብሪት አልተመፃደቀም፡፡ ሙስሊሞቹ ሃይማኖታዊም ሆነ ሰብአዊ ግዴታቸውን በመወጣታቸው እናመሰግናቸዋለን እንጂ ሙስሊሞቹ በሰሩት ስራ እዚህ ያለነው ሙስሊሞች አንመፃደቅም፡፡

በመጨረሻም፡,- ጀማል በሚል ተሰራጭቶ የነበረው መረጃ ትክክለኛ መረጃው ሲጣራ እነክብሪት ሲፎክሩ እንደነበረውኢትዬጲያዊ ሳይሆን ኤርትራዊ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ ትክክለኛ ስሙም ኤፍሬም የማነ የሚል ነው፡፡ የራሱ የፌስቡክ ገፅ ላይ እንደተመለከትኩት የሙስሊሞችን ነጭ ጀለብያ ለብሶ የተነሳውንም ፎቶ ተመልክቻለው፡፡ እንደዛም ሁሉ ክር አንገቱ ላይ የሚያሳይ ፎቶም አድርጎ ተመልክቻለው፡፡ በመሆኑም ጀማል ተብሎ የነበረው ኤፍሬም የማነ በሚል መረጃውን እናስተካክላለን ማለት ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከራሱ የፌስቡክ ገፅ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

https://www.facebook.com/efremg.yemane/

ኤፍሬም ሙስሊም ነው ክርስቲያን ነው ብለን ሂሳብ አናወራርድም፡፡ ሙስሊም መሆኑን የሚገልፅ የፅሁፍ እና አይን እማኞች መረጃ ሰማን፡፡ እሱን ተቀበልን፡፡ መረጃው ሲጣራ ጀማል ሳይሆን ኤፍሬም መሆኑ ታወቀ፡፡ ስለዚህ ኤፍሬም የሚለውን ተቀብለን አንሄዳለን፡፡ በድህረገፅ የተለቀቀው መረጃ ስህተት መሆኑን ስንቀበል በቪኦኤ በኦሮምኛው ክፍል የቀረበውን መረጃ ደግሞ ልክ እንደዚሁ ሁሉ እስኪረጋገጥ እንጠብቃለን ማለት ነው፡፡ ለኛ ለሙስሊሞች ግን ኤፍሬም መሆኑ ወይም ጀማል መሆኑ ወይም ኢትዬጲያዊ ወይም ኤርትራዊ መሆኑ ሳይሆን ሰው በመሆኑ ብቻ የደረሰበትን ግድያ አውግዘናል፡፡ወደፊትም እናወግዛለን ኢንሻአላህ

ከዚህ በዘለለ ጉዳዩ ሆን ተብሎ የተደረገ በማስመሰል የፖለቲካ ቁማር ለማድረግ ለሚኳትኑ ክብሪቶች ልክ እንደስሟ ክብሪት ከራሷጋር ተጋጭታ እሳት ፈጥራ እንደምትቃጠለው ሁሉ የሰው ክብሪቶችም ከራሳቸው ጋር ተጋጭተው ሲነዱ ይከርማሉ እንጁ ሙስሊሙ እና ክርስቲያኑ ወደ እርስ በእርስ እልቂት አይጋበዝም፡፡

ለሙስሊም ወንድም እና እህቴቼ ደግሞ ሚያዚያ 30 መላው ሙስሊም ማህበረሰብ ላይ የፍርድ ውሳኔ የሚተላለፍበት ቀን በመሆኑ በዚህ ጉዳይ ቢዚ በመሆን እንዳንዘናጋ አደራ እላለው፡፡

ለሃገራች አላህ ሰላምን ያስፍንልን

ለኤፍሬም ቤተሰቡ መፅናናትን አላህ ይስጣቸው

The post ትንሽ ሰለ ጀማል ወይም በትክክለኛው ስለ ኤፍሬም የማነ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

↧

ጠ/ሚኒስትር ናታኒያሁ የተቃውሞው መነሻ የሆነውን ወታደር ደማስ ፈቃደማስ ፈቃደን አነጋገሩ

$
0
0

natanyahu 2

netanyahu
ኢሳት ዜና :-በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተእስራኤላውያን ዘረኝነትን በመቃወም ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ የጀመሩት የተቃውሞ ሰልፍ እሁድ ተጠናክሮ ከቀጠለ በሁዋላ፣ የአገሪቱ ጠ/ሚኒስትር ቤንጃሚን ናታኒያሁ ፣ የተቃውሞው መነሻ የሆነውን ወታደር ደማስ ፈቃደን አነጋግረውታል።

ወታደር ደማስ በእስራኤል ፖሊሶች መደብደቡ በአገሪቱ የሚኖሩትን በተእስረኤላውያንን በእጅጉ አበሳጭቶ ለተቃውሞ አደባባይ አስወጥቶአቸዋል። ቤተእስረኤላውያኑ በአገሪቱ ውስጥ ያለውን ዘረኝነት እጥብቀው የተቃወሙ ሲሆን፣ ቁጣቸውንም የተለያዩ ጠርሙሶችና ፕላስቲኮችን በፖሊሶች ላይ በመወርወር ገልጸዋል። በፖሊሶችም በቤተእስረኤላውያን ላይ ጉዳት መደርሱን መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።

እሁድ የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በቅርብ የእስራኤል ታሪክ ያልታየ ነው ተብሎአል። ተቃውሞውን ተከትሎ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያውያኑ በአግባቡ አለመያዛቸውን፣ ቁጣውም ለአመታት የተጠራቀመ መሆኑን በመግልጽ ይቀርታ ጠይቀዋል።

ጠ/ሚኒስትሩም ችግሩን እንደሚፈቱ ቃል በመግባት ሁኔታውን ለማረጋጋት እየሞከሩ ነው።
ኢሳት ያነጋገራቸው ቤተእስራኤላውያን እንደሚሉት የአሁኑ ተቃውሞ የ30 አመታት የዘር መድሎ የወለደው ነው። ቤተእስረኤላውያኑ ተቃውሟቸውን የሚቀጥሉ ከሆነ፣ ሁኔታው ሊቀየር እንደሚችል ተስፋቸውን እየገለጹ ነው።
የአለም የመገናኛ ብዙሃን ቤተእስረኤላውያኑ ያደረጉትን ተቃውሞ ሰፊ የዜና ሽፋን ሰጥተውታል።

The post ጠ/ሚኒስትር ናታኒያሁ የተቃውሞው መነሻ የሆነውን ወታደር ደማስ ፈቃደማስ ፈቃደን አነጋገሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የትውልደ-ኢትዮጵያ ቤተ-እሥራኤል ቁጣ – VOA

$
0
0

60167F0B-2C9A-46FD-A63D-B03C1534AF37_w640_r1_sትውልደ-ኢትዮጵያ ቤተ-እሥራኤል ይደርስብናል የሚሉትን የዘረኝነት መድልዎህ የፖሊስ ጭካኔ የሚያጣራ የመንግሥት ኮሚቴ በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ተቋቁሟል፡፡

ትውልደ-ኢትዮጵያ ቤተ-እሥራኤል ይደርስብናል የሚሉትን የዘረኝነት መድልዎህ የፖሊስ ጭካኔ የሚያጣራ የመንግሥት ኮሚቴ በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ተቋቁሟል፡፡

የቤተ-እሥራኤላዊያኑ ችግር መድኃኒት ሊፈለግለት የሚገባ “ክፍት ቁስል” ነው ሲሉ የእሥራኤል ፕሬዚዳንት ሩቨን ሪቭሊን ዛሬ አስታውቀዋል፡፡

ትናንት በሺሆች የሚቆጠሩ እሥራኤላዊያኑ የኢትዮጵያ አይሁድ በማዕከላዊ ቴል አቪብ ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተው ዋናውን አውራ ጎዳና ለረዥም ሰዓት ዘግተዋል፡፡

የእሥራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ከትውልደ-ኢትዮጵያ ቤተ-እሥራኤል ማኅበረሰብ አባላት ጋር ዛሬ ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡

እሥራኤላዊያኑ የኢትዮጵያ አይሁድ በማዕከላዊ ቴል አቪብ ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተው ዋናውን አውራ ጎዳና ለረዥም ሰዓት ዘግተዋልእሥራኤላዊያኑ የኢትዮጵያ አይሁድ በማዕከላዊ ቴል አቪብ ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተው ዋናውን አውራ ጎዳና ለረዥም ሰዓት ዘግተዋል

ፕሬዚዳንት ሪቭሊን በዛሬው መግለጫቸው “አላስተዋልንም፤ በቅጡ አላዳመጥንም፡፡ እኛ’ኮ እርስ በራሣችን ባይተዋር አይደለንም፤ ወንድማማች ነን፡፡ በኋላ ሁላችንም ወደሚያሳዝነን ወይም ሊቆጨን ወደሚችል ደረጃ ልንዘቅጥ አይገባንም” ብለዋል፡፡

ችግሮቹና በደሎቹ እንዳይደገሙ ሊወሰዱ የሚገባቸውን እርምጃዎችም ዛሬ የተቋቋመው ኮሚቴ ይተልማል ተብሏል፡፡

የተቃውሞ ሰልፎቹ የተጀመሩት ባለፈው ሣምንት የእሥራኤል ፖሊሶች አንድ የደንብ ልብስ የለበሰ የኢትዮጵያ ዝርያ ያለውን የራሣቸውን ወታደር ክፉኛ ሲደበድቡ የሚያሣይ ቪዲዮ ከወጣና ከተሠራጨ በኋላ ነው፡፡

እሥራኤል ውስጥ ከ135 ሺህ በላይ ትውልደ-ኢትዮጵያ ቤተ-እሥራኤል ይኖራሉ፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

The post የትውልደ-ኢትዮጵያ ቤተ-እሥራኤል ቁጣ – VOA appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እየታደኑ እየታሰሩ ነው:: ‪

$
0
0

ሰማያዊ ፓርቲ የአፍሪካ ህብረት ምርጫውን እንዳይታዘብ እንደሚፈልግ ገለጸ

•የህብረቱ ታዛቢ ቡድን ፓርቲዎችን አነጋግሯል
• በየ ክፍለ ሀገሩ የሚገኙ አባላት ላይ የሚፈፀመው ድብደባ ቀጥሏል
• ‹‹የተጀመረውን የሀሰት ክስ እውነት ለማስመሰል የታቀደ ነው››

ethiopia-blue-party-300x164የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም አይ ኤስ አይ ኤስን ለማውገዝ በጠራው ሰልፍ ሰበብ እየታደኑ እየታሰሩ መሆኑን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ ሀሙስ ሚያዝያ 22/2007 ዓ.ም ብሌን መስፍንና ተዋቸው ዳምጤ ከመስሪያ ቤት ተይዘው የታሰሩ ሲሆን ሚያዝያ 24/2007 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበው ‹‹ሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተደረገውን አመጽ መርታችኋል፡፡›› በሚል ፖሊስ ክስ እንዳቀረበባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡
በተመሳሳይ ዛሬ ሚያዝያ 26/2007 ዓ.ም ማቲያስ መኩሪያ ቤቱ ውስጥ እያለ በፖሊስ ተይዞ ታስሯል፡፡ ማቲያስ፣ ብሌንና ተዋቸው ወረዳ 10 (ላዛሪስት ፖሊስ ጣቢያ) ታስረው ይገኛሉ፡፡ ይህንን የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ የሚደረገው እስርም ‹‹መንግስት በሰማያዊ ፓርቲ ላይ የጀመረውን የሀሰት ክስ እውነት ለማስመሰል የታቀደ ነው፡፡ ፖሊስ ምርመራ ሳይጨርስ በሀሰት 20 አባላትንና 6 አመራሮችን አስረናል ብለው ነበር፡፡ እነሱ የፈለጉት ይህን ሚዲያ ላይ ወጥተው በሀሰት የፈፀሙትን ውንጀላ ማሰመሰል ነው፡፡›› ሲል አቶ ዮናታን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

በሌላ ዜና በየ ክፍለ ሀገሩ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ ደህንነትና ፖሊስ የሚፈፅመው ድብደባ አሁንም መቀጠሉ ተገልጾአል፡፡ በዛሬው ቀን የደብረማርቆስ ከተማ ነዋሪና የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነችው የሀሳብ ጌታቸው ‹‹ለሰማያዊ ፓርቲ ወረቀት በትነሻል›› በሚል ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀሙባት ተገልጾአል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ የአፍሪካ ህብረት 5ኛውን ሀገራዊ ምርጫ እንዳይታዘብ እንደሚፈልግ ለህብረቱ ታዛቢ ቡድን ገለጸ፡፡ የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ዛሬ ሚያዝያ 26/2007 ዓ.ም በምርጫ የሚወዳደሩ ፓርቲዎችን በተናጠል በምርጫው ዙሪያ ያነጋገረ ሲሆን፣ ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ቡድኑን ያነጋገሩት አቶ ወረታው ዋሴ እና አቶ እምዕላሉ ፍስሃ ህብረቱ ምርጫውን እንዳይታዘብ እንደሚፈልጉ አስረድተዋል፡፡

የህብረቱ ታዛቢ ቡድን ከአሁን ቀደም በተካሄዱት ሀገራዊ ምርጫዎች መታዘቡን ያወሱት የሰማያዊ ተወካዮች፣ ህብረቱ በሪፖርቱ ለአምባገነኖች እውቅና ከመስጠት ያለፈ አንዳች እውነታውን የሚያሳይ ትዝብቱን አላስቀመጠም ሲሉ ለታዛቢ ቡድኑ መግለጻቸውን ተናግረዋል፡፡

‹‹ህብረቱ የአምባገነኖች ስብስብ ነው›› ያሉት የፓርቲው ተወካዮች፣ የአውሮፓ ህብረትና አሜሪካ በኢትዮጵያ ምርጫ ላይ ተስፋ በማጣት በታዛቢነት እንደማይሳተፉ ማሳወቃቸውን በመግለጽ፣ የአፍሪካ ህብረት ግን ለአምባገነኖች እውቅና ለመስጠት መምጣቱ በሰማያዊ ፓርቲ ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋል፡፡

‹‹ቀደምት ፓን አፍሪካኒስቶች አፍሪካን ከቅኝ ግዛት ነጻ ለማውጣት ታግለዋል፤ የአሁኖቹ እውነተኛ ፓን አፍሪካኒስቶች ደግሞ አፍሪካን ከአምባገነኖች ነጻ በማውጣት ወደ ዴሞክራሲ ማሸጋገር ይጠበቅባቸዋል›› በማለት ለህብረቱ ታዛቢዎች የገለጹት የፓርቲው ተወካዮች፣ በዚህ ረገድ ህብረቱ ተገቢውን ስራ እያከናወነ ነው ለማለት እንደማይቻል አስረድተዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ መንግስት ጋባዥነት 5ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለመታዘብ በቅርቡ አዲስ አበባ መግባቱ ይታወቃል፡፡ ህብረቱ በዛሬው ዕለት ያነጋገራቸው ፓርቲዎች ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ በውል አልታወቀም፡፡

The post የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እየታደኑ እየታሰሩ ነው:: ‪ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የዜጎች ከፍተኛ ጭፍጨፋ በመተማ

$
0
0

– የሚሊዮኖች ድምጽ
በሰሜን ጎንደር ዞን በመተማ ከተማ፣ በሕግ ወጥ መንገድ የተሰሩ ቤቶች ናቸው ያሏቸውን ቤቶች ለማፍረስ በሚሞክሩበት ጊዜ፣ ከነዋሪው በተነሳዉ ተቃዉሞ ምክንያት በተፈጠረው ግጭት፣ የሕወሃት ታጣቂዎች ሁለት ነዋሪዎችን ሲገድሉ፣ ሶስት ለሞት የሚያደርስ ከፈተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከአምሳ በላይ የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል።
metema 3

metema 2

metema
በአምቦ፣ በባህር ዳር በመሳሰሉት ቦታዎች እንደታየው ዜጎች በሕወሃት ታጣቂዎች ጥይት እንደ ቅጠል እየረገፉ ነው። ህወሃት ከሕዝብ የሚነሱትን መሰረታዊ የፍትህ፣ የዴሞክራሲና የለዉጥ ጥያቄዎች፣ በሃያ አንደኛ ክፍል ዘመን እንዳሉ ድርጅቶ ዘመናዊና ስልጣኔ በተሞላበት መልኩ ማስተናገድ ሲገባው፣ በስድሳዎች ጊዜ እንደነበረው መግደል፣ ማረድና ፣ ዜጎችን እንደ እንስሳ መደብደቡን በመምረጥ የጫካን ኋላ ቀር ፖለቲካ እያራመደ መሆኑ በድጋሚ ዛሬ ደግሞ በመተማ ተመስክሯል።

ለኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት ከደርቡሽ ጋር በተደረገ ትንቅንቅ አጼ ዮሐንስን ጨመሮ በርካቶች ደማቸውን ያፈሰሱባት መተማ፣ ዛሬ ከዉጭ ወራሪዎች ሳይሆን፣ ከሕወሃቶች በተተኮሰ ጥይት የልጆቿ ደም እየተረጨባት ይገኛል።
መተማ ዛሬ ይሄንን ትመስል ነበር።

The post የዜጎች ከፍተኛ ጭፍጨፋ በመተማ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

የሽራሮ ከተማ አስተዳዳሪዎች የስር ተላላኪዎቻቸውን ሕዝቡ ኢሕአዴግን እንዲመርጥ አልቀሰቀሳችሁም በሚል ከሃላፊነታቸው ማውረዳቸው ተዘገበ

$
0
0

የሽራሮ ከተማ አስተዳዳሪዎች በነሱ ስር ሆነው ሲያገለገሏቸው የቆዩትን ሰዎች; ህዝቡን ኢህአዴግን እንዲመርጥ በሚያስችል መንገድ አልቀሰቀሳችሁትም በማለት ከሃላፊነታቸው እያወረዷቸው እንደሆኑ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ገለፀ ሲል የደህሚት ድምጽ ዘገበ::
election
በሸራሮ ከተማ የሚገኙት አስተዳዳሪዎች በነሱ ስር የሚገኙትን በሃላፊነት የተቀመጡ አባላት ላይ እምነት ስላጡባቸው ነዋሪው ህዝብ ህ.ወ.ሃ.ት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግን እንዲመርጥ የሚያስችል አስፈላጊውን ቅስቀሳ አላደረጋችሁለትም በሚል ምክንያት ከሃላፊነታቸው እያወረዷቸው መሆኑን የገለጸው መረጃው ከስልጣናቸው ከተወገዱት መካከልም የወረዳው ፕሮፖጋንዳ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሃፍቲና የወረዳው የሴቶች ሃላፊ ወ/ሮ ደስታ ማሙ እንደሚገኙባቸው ለማወቅ ተችሏል።

እነዚህ በሃላፊነት ደረጃ ሲሰሩ ቆይተው ባሁኑ ሰአት ከስልጣናቸው የታገዱት የህወሃት ኢህአዴግ አመራሮች ስርአቱ በህዝቡ ላይ ያለው ተቀባይነት ስላጣ የስርዓቱ ሃላፊዎች በነሱ ስር ለሚገኙ አመራሮች ከሃላፊነታቸው እያወረዷቸውና እየሾሟቸው አንደሆኑና; ይህ ድርጊትም በሸራሮ ከተማ ብቻ ሳይሆን; በመላው ያገራችን አካባቢዎች እየተሰራበት እንደሆነ መረጃው አክሎ አስረድቷል።

The post የሽራሮ ከተማ አስተዳዳሪዎች የስር ተላላኪዎቻቸውን ሕዝቡ ኢሕአዴግን እንዲመርጥ አልቀሰቀሳችሁም በሚል ከሃላፊነታቸው ማውረዳቸው ተዘገበ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

[በዚህ ሳምንት የተማርናቸው ሦስት ነገሮች] 1ኛ) ቶርቸርን እስከ መቼ “ጆሮ ዳባ ልበስ” እንለዋለን? – 2ኛ) የጦስ ዶሮ ለእርድ እየቀረበ ስለ ላባው መሟገት – 3ኛ) ወጣትነትን የሚበላውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ በብርቱካን ልደት እናስብ

$
0
0

1ኛ) ቶርቸርን እስከ መቼ “ጆሮ ዳባ ልበስ” እንለዋለን?

እ.ኤ.አ. በ2008 ዓ.ም የጆርጅ ታውን ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር የኾኑት ጀምስ ራይመንድ ቭሪላንድ በቶርቸር ጉዳይ የተለመደ አስተሳሰባችንን የሚፈታተን አንድ ጥናታዊ ጽሑፍ አሳትመው ነበር። በርካቶች ለፖለቲካ ፓርቲዎች እና ለገልለተኛ ፕሬስ ምንም ቦታ የሌላቸው አምባገነኖች ለይስሙላም ቢኾን የፓርቲ ፉክክር እና ምርጫን ከሚፈቅዱ አምባገነኖች በተለየ የከፉ ቶርቸር ፈጻሚዎች ናቸው ብለው ያስባሉ። የፕሮፌሰሩ ጽሑፍ ይህን አስተሳሰብ የሚመታ ነው። በጽሑፋቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዲኖሩ የሚፈቅዱ እና የይስሙላ ምርጫ የሚያካሂዱ አምባገነን መንግሥታት (electoral dictatorships) ከሌሎች አምባገነን መንግሥታት የበለጠ ቶርቸር እንደሚፈጽሙ በጠንካራ ዴታ ላይ ተመሥርተው ያሳያሉ። ሁሉም አምባገነኖች ቶርቸር ይፈጽማሉ፤ የምርጫ አምባገነኖች ግን የበለጠ ይፈጽማሉ። ይህ ለምን ይኾን?
edom Jpurnalist
ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ባሉባቸው አምባገነኖች የኩብለላ አደጋ (threat of defection) ተቃዋሚ ከሌለባቸው አምባገነኖች የላቀ ነው። ይህን አደጋ ለመቀነስ የምርጫ አምባገነኖች የተለያዩ ስልቶችን እና መሣርያዎችን ይጠቀማሉ። ከስልቶቹ መካከል አንዱ የኩብለላን ዋጋ እጅግ ከፍተኛ ማድረግ ነው። ለዚህ ደግሞ ቶርቸር ከዋነኛ መሣርያዎች አንዱ ነው። ይኹንና የምርጫ አምባገነኖች ቶርቸርን የመደበቅ እና የማዳፈን አቅማቸው የፓርቲ ውድድር ከሌለባቸው አምባገነኖች የተሻለ ነው። ለዚህ የተለያዩ ምክንያቶች አሉ። የምርጫ አምባገነኖች ዓለምአቀፍ ጸረ-ቶርቸር ሕጎችን ለመፈረም አያቅማሙም። በዚህ ምክንያት ብዙዎች እነዚህ አምባገነኖች ቶርቸር ላለማድረግ የቆረጡ መስለው ይታይዋቸዋል። እነዚህ አገሮች የሚፈጥሯቸው የይስሙላ ዴሞክራሲያዊ ተቋማት የሚሰጧቸው የዴሞክራሲያዊነት ድባብ ለአምባገነኖቹ አዎንታዊ አመለካከት (positive perception) ያላብሷቸዋል። ይህ አመለካከት እንደ ቶርቸር ያለ ክፉኛ ጥቃት አይፈጽሙም ተብሎ እንዲታመን ያደርጋል። መንግሥታቱ ይህን መሰሉን የማሰቃየት ተግባር ፈጽመዋል ተብለው ሲከሰሱ የመጀመርያ መስመር መከላከያቸው የይስሙላ ተቋማት መኖራቸውን መጥቀስ ነው። ይህ የሙግቱን መድረክ ያጨቀየዋል። አንዳንድ ጊዜ ራሳቸው የቶርቸር አጣሪ ኮሚሽኖችን በመፍጠር ተጠያቂነት ያለባቸው ለማስመሰል ይሞክራሉ። “የተሻሉ አምባገነኖች” የሚለው ስማቸው ቶርቸር አልፈጸምንም ብለው ሲከራከሩ ሙግታቸው እንዲደመጥ ዕድል ይፈጥርላቸዋል። ከግብጽ አብዮት በኋላ እንደተመለከትነው በእነዚህ ዐይነት አገራት የሚፈጸመው የቶርቸር መጠን እና ስፋት በደንብ የሚታወቀው ሥርዐቶቹ ከፈራረሱ በኋላ በሚደረጉ ምርመራዎች እና ጥናቶች ነው።

ባለፈው ሳምንት የዞን ዘጠኝ ታሳሪዎች ላይ የደረሰው ቶርቸር በታሳሪዎቹ በራሳቸው ተጋልጧል። ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በታሳሪዎቹ ከገባው አቤቱታ መካከል በተለይ በሁለቱ ሴት ታሳሪዎች ላይ የደረሰው ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እና ግፍ ሲያስቡት ያጥወለውላል። ማሕሌት እና ኤዶም ራቁታቸውን በመርማሪዎቻቸው ፊት እንዲቆሙ ተደርገዋል፤ ክብራቸው እና ሰብእናቸውም ተደፍሯል፤ እንደዚህ ዐይነት ቶርቸር እ.ኤ.አ በ1930ዎቹ በጀርመን “verschärfte vernehmung” በሚል ስም የተፈጠረ ነው። ዓላማው በሰውነት የአካል ክፍል ላይ ምንም ዐይነት ጠባሳ ሳይታይ እስረኛን ማሰቃየት ነው። እስረኞች ቶርቸር ተደርገናል ብለው ጠባሳቸውን እንደ ማስረጃ እንዳያሳዩ ያደርጋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህ በፊት ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳን፣ ርዕዮት ዓለሙን እና እስክንድር ነጋን ጨምሮ በበርካታ የፖለቲካ ተቀናቃኞቹ ላይ እንዲህ ዐይነት ዝምተኛ ቶርቸር ፈጽሟል። እነዚህ ሰለባዎች ከእስር ቤት የሰቆቃ ድምጻቸውን ሊያሰሙላቸው የሚችሉ ደጋፊዎች እና ወዳጆች ያሏቸው ባለ ከፍተኛ ስም (high profile) ታሳሪዎች ናቸው። ባለፉት ዐሥር ዓመታት በተለያዩ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የወጡ ዳጎስ ያሉ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት በሺሕዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን (በኦጋዴን፣ በኦሮምያ፣ በአማራ ክልል፣ በአዲስ አበባ ወረዳ ስምንት ቶርቸር ቻምበር) ጠባሳ ለመደበቅ ሙከራ ያልተደረገባቸው ስቃዮች ተፈጽሞባቸዋል። እነዚህ እንግዲህ በአጥኚዎች ምርመራ የታወቁ ናቸው፤ ያልታወቁትን ቤት ይቁጠራቸው።

ይህ ሁሉ ኾኖ ግን የኢትዮጵያ መንግሥት ልክ እንደ ሙባረክ መንግሥት ሁሉ የቶርቸር ዲፕሎማሲን ያሸነፈ ይመስላል። የመንግሥቱ ስም ከቶርቸር ጋር የሚነሳበት አጋጣሚ እጅግ ውሱን ነው። አገር ውስጥም ቢኾን የኢትዮጵያ መንግሥት ስለሚጨፈልቃቸው የተለያዩ ሕገ መንግሥታዊ መብቶች የፖለቲካ ውዝግብ ቢኖርም በአገሪቱ እየተደረገ ያለው መጠነ ሰፊ የማሰቃየት ተግባር ግን በሚገባው መጠን ሲወሳ እና የክርክር እና የሙግት ማዕከል ሲኾን አይታይም። የቶርቸር የፖለቲካ ጉልህነት (political salience) አለማግኘት ለኢትዮጵያ መንግሥት ጠቅሞታል፤ ምክንያቱም መንግሥት ጥሷቸዋል ተብለው በተደጋጋሚ ከሚጠቀሱት መብቶች በላይ ቶርቸር የፖለቲካ ጎራውን እና ጨዋን ኅብረተሰብ በሙሉ የሚያስቆጣ እና የሚያጥወለውል በመኾኑ ቅንጅት ያለበት ተቃውሞን የማፋፋም ዕድሉ ከፍ ያለ ነው። ከዞን ዘጠኝ፣ ከእነ እስክንድር ነጋ እና ከአጠቃላዩ የፖለቲካ እስረኛ የሚመጡትን የሰቆቃ ድምጾች ጆሯችንን ከፍተን እናድምጥ።
Yilikal
2ኛ) የጦስ ዶሮ ለእርድ እየቀረበ ስለ ላባው መሟገት

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት ኢንተርቪው ሲሰጡ እና ንግግር ሲያደርጉ ብዙ ጊዜ ሶሻል ሚዲያ ይታመሳል። በተለይ በተቺዎቻቸው ዘንድ ጥልቅ አሉታዊ ስሜትን ይቀሰቅሳሉ። “የአዲሲቲቱን ኢትዮጵያ ኹኔታ ያልተረዱ አክራሪ ኢትዮጵያዊ ብሔርተኛ፣ የአሮጌው ሥርዓት ናፋቂ፣ የፖለቲካ እና የፖሊሲ እውቀት የሌላቸው፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን አይዲዮሎጂ እና የፖለቲካ ስልት ወደ 1980ዎቹ የሚመልሱ” ወዘተ የሚባሉ ክሶች ይሰነዘሩባቸዋል። በዚህ ሳምንት ሊቀመንበሩ በአሜሪካ የኢትዮጵያውን ስብሰባ ላይ ያደረጉት ንግግር ከተሠራጨ በኋላ እርሳቸው እና ፓርቲው እነዚህን ትችቶች እንደ አዲስ አስተናግደዋል። በተመሳሳይ ወቅት የኢትዮጵያ መንግሥት ፓርቲው ላይ ከፍተኛ ጥቃት ሊፈጽም እንደተዘጋጀ የሚጠቁም መጠነ ሰፊ ፕሮፖጋንዳ የመንግሥት ሚዲያን በመጠቀም እያፋፋመ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ፓርቲው ባለፈው ሳምንት በመስቀል አደባባይ በአይሲስ የተገደሉ ኢትዮጵያውያንን ለማሰብ በተጠራው የሕዝብ ስበሰባ ላይ “የተቃውሞ ጩኸት አቀነባብሯል፣ ኹከት ለመፍጠር ሞክሯል” ሲል ይወነጅለዋል። በቅርብ ጊዜ በርካታ የፓርቲው አባላት የመንግሥት ዱላ አርፎባቸዋል። የእነዚህ ሁለት ክስተቶች ግንኙነት መረዳት ስለ ሰማያዊ ፓርቲ ብቻ ሳይኾን በአምባገነን አገሮች ስለሚደረጉ በፓርቲ ዙርያ ስለተደራጁ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ጥሩ ግንዛቤ ይሰጠናል።

አምባገነን መንግሥታትን የሚያጠኑ የፖለቲካ ሳይንቲስቶች የተቃውሞ ፓርቲ ፖለቲካን በተመለከተ የሚያነሱት አንድ እንቆቅልሽ አለ፤ ምርጫን በሚያደርጉ አንዳንድ አምባገነን መንግሥታት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምርጫን የማሸነፍ መጠነኛ የኾነ ዕድል አላቸው። እነዚህ የፉክክር አምባገነናዊ ሥርዐቶች (competitive authoritarianism) ይባላሉ። ከእነዚህ ሥርዐቶች ውጪ ግን በሌሎች የምርጫ አምባገነን መንግሥታት ተቃዋሚዎች ምርጫን የማሸነፍ ዕድላቸው ወደ ዜሮ ይጠጋል። ይህን ፓርቲዎቹም ያውቁታል፤ ደጋፊዎቻቸውም ይገነዘቡታል፤ ሌላውም ሕዝብ ይረዳዋል። ነገር ግን እነዚህ ፓርቲዎች በየጊዜው ለምርጫ ይሳተፋሉ፤ ከዚያ ጋር ተያይዞ አባሎቻቸው ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ይቀበላሉ። እንቆቅልሹ ይህ ነው፡- የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖለቲካው መድረክ አመክኗዊ ተዋናይ (rational actor) ከኾኑ እንዲህ ዐይነት ኹኔታ ሲያጋጥማቸው እንደ ከሰረ ቢዝነስ ለምን ራሳቸውን አይዘጉም? ወይም መጀመርያውኑ ለምን ይፈጠራሉ?

ይህን ለመመለስ ብዙ ቲዎሪዎች ተነድፈዋል፤ ብዙ ኢምፔሪካል ምርመራዎች ተደርገዋል። ከእነዚህ ጥናቶች ውስጥ የወርቅ ደረጃ ካገኙት አንዱ ኬኔት ግሪን በላቲን አሜሪካ አምባገነን መንግሥታት ላይ ያደረጓቸው ጥናቶች ናቸው። እንደ ግሪን በእንደዚህ ዐይነት አምባገነን መንግሥታት የሚፈጠሩ ፓርቲዎች ዋነኛ ባሕርያቸው ሐሳብ ገላጭነት (expressive) ነው። ሐሳብ ገላጭ ፓርቲዎች በምርጫ የማሸነፍ ዕድል ባይኖራቸው እንኳ የፓርቲውን አባላት ጥልቅ ተቃውሞ በፖለቲካ መድረኮች ለማሳየት ይኖራሉ። ሐሳብ ገላጭ ፓርቲዎች በአምባገነን አገራት ብቻ ሳይኾን በዴሞክራሲያዊ አገራትም ይመሠረታሉ። ለምሳሌ በአሜሪካ ሊበሪቴርያን እና ግሪን ፓርቲዎች ምርጫን እንደማያሸንፉ ቢያውቁም ምርጫን ጨምሮ በተለያዩ የፖለቲካ መድረኮች ሲሳተፉ ረዥም ጊዜ አስቆጥረዋል። በአምባገነን መንግሥታት ወደ ተቃውሞ የፓርቲ ፖለቲካ መምጣት ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍላል። ግሪን እንደሚሉን እና በሌሎች ጥናቶች እንደተረጋገጠው የአይዲዮሎጂ ጽናት እና ታማኝነት ያላቸው ሰዎች ከሌሎች በበለጠ ይህን ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ ናቸው። ወደ ፖለቲካው መድረክ መጥተው የሚገነቧቸው ፓርቲዎች የአይዲዮሎጂ ፍጹማዊነት (ideological purism) ይታይባቸዋል። በተጨማሪም እንደዚህ ዐይነት የአይዲዮሎጂ ጽናት እና ፍጹምነት ከመንግሥት የሚመጣ ጥቃትን ለመከላከል ይጠቅማል። መሀል ሰፋሪዎች ጫናን አለመቋቋም ብቻ ሳይኾን ለመንግሥት ማባበያዎች የመንበርከክ ዕድላቸው ከፍ ያለ ነው። ስለዚህ በአምባገነን ሥርዐት የምናገኛቸው ፓርቲዎች በአብዛኛው የአይዲዮሎጂ ፍጹማዊነት የሚታይባቸው ናቸው። ይህን አንዳንድ ጊዜ በተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ስትራቴጂካዊ መተባበር እንዳይኖር ያደርጋል። ይኹንና ለእነዚህ ፓርቲዎች መኖር ከፍተኛ አስተዋጽዖ አለው። አቶ ይልቃልም ይኹኑ ፓርቲያቸው ለመሀል ሰፋሪ (median voter) የሚመች አይዲኦሎጂ እና ፖሊሲ ባያመጡ ሊገርመን አይገባም። የአምባገነንነት ተጨባጭ ኹኔታዎች ውጤት ነው። ግሪን እንደሚያሳዩን በተለያዩ ምክንያቶች አምባገነን መንግሥታት እየተዳከሙ መጥተው ወደተፎካካሪ አምባገነናዊነት ወይም ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት ከተቀየሩ የእነዚህ ፓርቲዎች ባሕርይም ይለወጣል። አይዲዮሎጂያዊ ፍጹማዊነታቸውም ይቀንሳል። የፖለቲካ ተሳትፎ ዋጋ (cost of participation) ሲቀንስ ብዙ የመሀል ሰፋሪዎች እነዚህን ፓርቲዎች ስለሚቀላለቀሉ የፓርቲዎቹ አቋም ይለዝባል። በተጨማሪም ፓርቲዎቹ በምርጫ ለማሸነፍ ሲሉ ፍጹማዊ ፖሊሲዎቻቸውን እና አይዲዮሎጂያቸውን ያረግባሉ፤ ያለሰልሳሉ፤ ከሐሳብ ገላጭነት ወደ ምርጫ ፓርቲነት (electoral party) ይሸጋገራሉ።

ይህ ከኾነ ከእነ ሰማያዊ ፓርቲ ዐይነት ቡድኖች ጋር “ጽንፈኝትህን ቀንስ አትቀንስ፣ ፖሊሲህ አይረባም ይረባል” ብሎ መነታረክ ነጥብ ዐልባ እና ጉንጭ አልፋ ይኾናል። መጀመርያውኑ እንደ ፓርቲ እንዲፈጠሩ ያደረጋቸው፤ በኋላም የመቆየት ዕድላቸውን ያሰፋው እና ዕድሜያቸውን የሚያራዝመው የአይዲዮሎጂ ጽናታቸው ነው። በሥርዐቱ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን እንደ ሐሳብ ገላጭ ፓርቲ ከተመለከትናቸው የሚያስጨንቀን ለመሀል ሰፋሪ የሚማርክ ፖሊሲ እና አይዲዮሎጂ ይዘው መምጣታቸው ሳይኾን የሚደርስባቸው የመብት ጥሰት እና እንግልት ይኾናል። ከአቶ ይልቃል ጌትነት ንግግር ይልቅ አሳሳቢው የኢትዮጵያ መንግሥት ለእርሳቸው እና ለፓርቲ ባልደረቦቻቸው የሳለው ቢላዋ ነው።
birtukan-mideksa
3ኛ) ወጣትነትን የሚበላውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ በብርቱካን ልደት እናስብ

በኢትዮጵያ ተቃውሞ ፖለቲካ ኅየንተ ክብር ያገኙት ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በዚህ ሳምንት 41ኛ የልደት በዐላቸውን አክብረዋል። በብርቱካን የፖለቲካ ሕይወት መነጽር ኢትዮጵያ ለስለስ ካለ አምባገነንነት ወደ ሙሉ አምባገነንት ያደረገችውን ሽግግር ልንቃኘው እንችላልን። እርሳቸው በ26ዓመታቸው ለጸረ ሙስና አጀንዳ የፓርላማ ተወዳዳሪ ኾነው ወደ ፖለቲካ ብቅ ሲሉ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት እየተጠናቀቀ ነበር። በጦርነት ወቅት የታየው ትብብር ለወደፊቱ የዴሞክራሲያዊ እና የባልንጀሬነት መሠረት ይኾናል ብለው የገመቱ በርካቶች ነበሩ። በዚያ ምርጫ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) “አዲስ አበባን ነጻ እናውጣ!” በሚል መፈክር ስር ተንቀሳቅሶ ማሸነፍ ባይሳካለትም በየወረዳው ገዢውን ፓርቲ ተገዳድሮ ነበር። ከብዙዎቹ የሽንፈት ምክንያቶች መካከል ዋነኛው በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል የተፈጠረው የድምጽ መከፋፈል ነበር።

ወይዘሪት ብርቱካን 27ኛ ዓመት የልደት በዐላቸውን ሲያከብሩ በኢሕአዴግ ውስጥ ክፍፍል ተነስቶ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አሸናፊነት ተጠናቀቀ። አቶ መለስ ተሸናፊን ቡድን ወደ ኋላ የሚያይ እና ራሳቸውን ደግሞ ወደፊት የሚመለከቱ፤ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲን እና ካፒታሊዝምን የሚያጸኑ አድርገው አቀረቡ። በክፍፍሉ ተሸንፈው ለእስር የተዳረጉት አቶ ስዬ አብርሃን በመፍታት ወይዘሪት ብርቱካን ብሔራዊ ትኩረት አገኙ። በተለይ በአዲስ አበባ በወቅቱ የተቀሰቀሰው ኹከት ለበርካታ ወጣቶች መታሰር እና መሞት ምክንያት ቢኾንም የአቶ መለስ ቃል ኪዳን ላይ ተመሥርተው መጪውን ጊዜ በተስፋ የሚጠብቁ ብዙ ነበሩ። በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት እየተሻሻሉ የመጡት የፕሬስ፣ የመደራጀት፣ የመሰብሰብ እና የመናገር ጥበቃ ይህን ተስፋ አጠናከረው። አቶ መለስ በምዕራብ አገር ከተሞች እየዞሩ “ዲሞክራሲን አሰፍናለሁ፣ ኢኮኖሚን አሳድጋለሁ፣ ሲቪል ሶሳይቲ እንዲሰራፋ አደርጋለሁ፤ የሚሰጠኝ ብድር እና ርዳታ እጥፍ ይደረግልኝ” እያሉ ሲወተዉቱ ነበር። በመሬት ላይ መሻሻሎች እየታዩ ስለነበረ ጥያቄ እና ጥርጣሬ አልተነሳባቸውም። ይህ አድቮኬሲ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት አጥተውት የነበረው ክብር መልሶ አስገኘላቸው፤ የብሌየር ኮሚሽን ዋነኛ አባል እንዲኾኑም አደረጋቸው። እነዚህ ለውጦች እያደጉ ሄደው ምርጫ 97ን ወለዱ።

ብርቱካን ሚደቅሳ በ32 ዓመታቸው የአገሪቱ ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲ ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት ሲኾኑ ከመጪዎቹ ዘጠኝ ዓመታት መካከል አራቱን በእስር ቤት፤ ሦስቱን ደግሞ በስደት ያሳልፋሉ ብሎ የጠበቀ አልነበረም። በምርጫው ምክንያት የተነሳው ውዝግብ ጦዞ ብርቱካን እና ሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ዘብጥያ የወረዱት፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር በፍጥነት እየጠበበ የመጣው እና ጥበቃቸው የተሻሻለ ይመስል የነበረው መብቶች የተቀለበሱት፣ እርሳቸው የልደት በዐላቸውን ባከበሩ በስድስተኛ ወሩ ነበር። በዚህ ሳምንት ወይዘሪት ብርቱካን ልደታቸውን ያከበሩት በስደት ነው፣ ከእስር ፋታ ሲያገኙ የፈጠሩት ፓርቲ ከመንግሥት በደረሰበት ጥቃት እና በውስጥ ችግር ምክንያት ተዳክሟል። እርሳቸው ወደ ፖለቲካ ሲመጡ የነበረው የዴሞክራሲ ተስፋ ጨልሟል።

በዲሞክራሲያዊ አገሮች እንደ ብርቱካን ያሉ በወጣትነታቸው ብዙ የተጓዙ እና ብሔራዊ ትኩረትን ያገኙ ፖለቲከኞች 41 ዓመት ሲኾናቸው ከተሞክሯቸው ተምረው፣ የአመራር ብቃታቸውን አሻሽለው፣ የአይዲዮሎጂ እና የፖሊሲ ግንዛቤያቸውን አዳብረው የሞያቸው ጫፍ ላይ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። አምባገነን ሥርዐት ግን በራሱ ቡድን ውስጥ ለሌሉ ወጣቶች እንዲህ ያለውን ዕድል አይሰጥም። ወይዘሪት ብርቱካን 41ኛ ዓመት የልደት በዐላቸውን ሲያከብሩ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ብዙ አስተዋጽዖ ማድረግ እየቻሉ በጡንቻ ከመድረኩ እንዲገለሉ የተደረጉ ወጣቶችን እናስባለን፤ ለወይዘሪት ብርቱካን ደግሞ ረዥም ዕድሜ እንመኛለን።

Source: 7-killo Magazine

The post [በዚህ ሳምንት የተማርናቸው ሦስት ነገሮች] 1ኛ) ቶርቸርን እስከ መቼ “ጆሮ ዳባ ልበስ” እንለዋለን? – 2ኛ) የጦስ ዶሮ ለእርድ እየቀረበ ስለ ላባው መሟገት – 3ኛ) ወጣትነትን የሚበላውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ በብርቱካን ልደት እናስብ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

Health: ሞባይል ስልክን በኋላ ኪስ ማስቀመጥ ለጤና ያለው ጉዳትን እነሆ

$
0
0

phone in back pocket
የተተረጎመው በሄኖክ ሰለሞን

ይህም ምንም አይነት ጉዳት ሊያስከል እንደማይችል ነው እንጂ እንዴት ሞባይልን ከኪስ ማስቀመጥ ከጤና ጋር ሊያያዝ ይችላል ብለን ልንጠይቅ እንችላለን።

ሊግ ኦፍ ኔሽን ሄልዝ የተባለው የጤና ተቋም ያካሄደው ጥናት ግን ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ይስጣል።

ኒኮላይ ኮኖቭ የሊግ ኦፍ ኔሽን ሀልዝ ምክትል ፕሬዚዳንት ሲሆኑ ስለ ጥናቱ እንዲህ ይላሉ፤ “የስማርት ስልክን አብዝቶ ጆሮ ላይ በማድረግ መጠቀም እንዲሁም ኪስ ውስጥ አድርጎ መንቀሳቀስ የነርቭ ሲስተማችን ላይ የረጅም ጊዜ ጉዳት ያስከትላል”::

የማእከላዊ የነርቭ ሲስተማችን ደግም የሰውነታችንን እያንዳንዷን እንቅስቃሴ የሚቆጣጠር አካል በመሆኑ ይህ መጥፎ ዜና ነው ሲሉ ያክላሉ።

በስልካችን ውስጥ የሚገኘው የኤሌክትሮ ማግኔቲክ ሲስተም የመራቢያ አካላትም ላይ ተፅእኖ እንደሚኖረው የሚናገሩት አጥኚዎቹ ሆኖም ስልክን ብዙ በመጠቀም የሚመጣውን አደጋ እንዲህ በቀላሉ ለማግኘት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል ነው የሚሉት።

ተጠቃሚዎችም ከሳይንሳዊ ጥናቶች ስልካቸውን ያምናሉ፤ ይህ ደግም በረጅም ጊዜ ለሚመጣው ጉዳት ቀዳሚ ተጠቂ ሊያደርጋቸው ይችላል ባይ ናቸው አጥኝዎቹ።

ኤሌክትሮ ማግኔቲክ ፊልድ ለጤናችን ጎጂ የሆነ ንጥር ነገር እና እንደነ ሉኪሚያ፣ የሆርሞን መዛባት፣ የአእምሮ ካንሰር እንዲሁም የነርቭ እና የመራቢያ ሲስተማችንን ሊያጠቃ ስለሚችል የስልክ አጠቃቀማችን እና አያያዛችን ላይ ጥንቃቄ እንድንወስድ ሲል ጥናቱ ጠቁሟል።

ምንጭ፦ሄልዝ ዳይጄስት

The post Health: ሞባይል ስልክን በኋላ ኪስ ማስቀመጥ ለጤና ያለው ጉዳትን እነሆ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ከአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

$
0
0

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ትናንት ሚያዝያ 27/2007 ዓ.ም ከአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ኃላፊዎች ጋር መወያየታቸውን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
Yilikal
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት የዴሞክራሲ፣ ሰብአዊ መብትና ሰራተኞች ምክትል ዋና ፀኃፊ የሆኑት ሚስተር ስቲቭ ፌልድስቴይን ጨምሮ ሌሎችንም ኃላፊዎች አግኝተው ስለ ኢትዮጵያና ስለ ቀጠናው ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል፡፡

ኢ/ር ይልቃል ከስቴት ዲፓርትመንት ኃላፊዎቹ ጋር በነበራቸው ቆይታ ስለ መጭው ምርጫ፣ ሰብአዊ መብት አያያዝ፣ የእምነት እና ሀሳብን በነፃነት መግለጽ መብት፣ ሲቪክ ማህበረሰብ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በፀረ ሽብር ህጉና በደህንነት ስም እየተፈፀሙ ያሉ ችግሮች ላይ ተነጋግረዋል፡፡

ሚስተር ፌልድስቴይን ስለ ሰማያዊ ፓርቲ እንቅስቃሴዎች ዝርዝር ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን ኢ/ር ይልቃልም በዝርዝር ማስረዳታቸው ታውቋል፡፡ በቅርቡ ምክትል የውጭ ጉዳይ ኃላፊዋ ውይንዲ ሸርማን ንግግር ላይም መወያየታቸው ታውቋል፡፡

The post የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ከአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

የሰሜን ጎንደር ሕዝብ አመጽ በርትቷል * በድንበር ከተሞች አሁንም ችግሩ እየሰፋ ነው

$
0
0

metema 2
ምንሊክ ሳልሳዊ

የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች እና ካድሬዎቻቸው በሕወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ተወካዮች መሪነት በባህር ዳር ስብሰባ መቀመጣቸው በታወቀበት በዚህ ሳምንት በአማራ ክልል ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ሕዝባዊ እምቢተኝነት መከሰቱን እና የፌዴራል ፖሊሶች ከሕዝቡ ጋር እየተጋጩ መሆኑ ሲጠቆም በጎጃም ገበሬው በብጡ ደጃፍ እና በቤቱ ውስጥ የእያኔን የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት እንዲለጥፍ እየትገደደ እና እምቢ ያለ በመታሰር ላይ መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል::

ሕወሓቶች በሚመሩት እና በባህር ዳር እየተካሄደ ያለው የብአዴን ስብሰባ ላይ ከምርጫው ጋር ተያይዞ የሚመጥውን ችግር እና ሕዝቡ ሊመርጠን ስለማይችል በድምጽ መስጫ ካርዶች ዙሪያ መወሰድ ስላለባቸው እርምጃዎች እንዲሁም ትጥቅ ያልፈቱ መሳሪያ የቀበሩ ሰዎች ካሉ አስቸኳይ ክትትል ተደርጎ እርምጃ እንዲወሰድ የሚሸፍቱ ሰዎች የሚተረጠሩ ካሉ እንዲታሰሩ የሚሉ ተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን ከትግራይ ክልል አማራ አዋሳኝ በሆኑ ቦታዎች ያሉ የሕወሓት ሚሊሻዎች እና ካድሬዎች ወደ አማራ ክልል በማምጣት ድምጽ ሰጥተው እደ አከባቢያቸው እንዲመለሱ እንዲሁም በተለያየ ወረዳ የተለያያ የመራጭ ካርድ ዬሰዱ ሰዎች አስቸኳይ የትራንስፖርት አቅርቦት እየተደረገላቸው በየወረዳው እየሄዱ እንዲመርጡ ሲባል ከምርጫው በኋላ ሊነሱ የሚችሉ የአመጽ ስጋቶችን ለመቆጣጠር የመከላከያ ሰራዊት አባላይ የፌዴራል ፖሊስ ልብሶችን በመልበስ ተክተው እንደሚሰሩ እና ካድሬዎች እና የጸጥታ ሰራተኞች አስፈላጊዉን ትብብር በማድረግ የሚፈጠረው ችግር በቁጥጥር ስር እንዲውል እንዲያደርጉ ከሕወሓት ሹሞች መመሪያ ተሰቷቸዋል::

በሰሜን ጎንደር የላይ እና የታች አርማጮ ጨምሮ በአብድራፊ በሁመራ በመተማ በሸዲ በጭልጋ አክባቢዎች በከፍተኛ ደረጃ ሕዝቡ እና የወያኔ ፖሊሶች ውጊያ የገጠሙ ሲሆን በርካቶች ሲቆስሉ በአከባቢው የተነሳው የህዝብ እምቢተኝነት እየሰፋ መምጣቱን እና ጥያቄዎች ምላሽ አለማግኘታቸው ሲከፋ የመኖሪያ ቤታችውን በማፍረስ ሕዝቡን ለጎዳና ተዳዳሪነት መዳረጉ በመተማ እና አከባቢው የሚኖሩ ሕዝቦችን ቁጣ ቀስቅሶ እስከ ዛሬ ድረስ ሊበርድ ያልቻለ ከፍተኛ ግጭት በአከባቢው እየተደረገ እንደሆነ የአከባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ::በአጠገባችን መጥቶ የሚያግዘን ማጣታችን ነው እንጂ ወያኔን ከጎንደር ክፍለሃገር ጠራርገን እናወጣው ነበር ያሉ ወጣቶች ባለው ስርአት መማረራቸውን በቁጣ ይናገራሉ::ይህ በእንዲህ እንዳለ በጎጃም ክፍለሃገር የሚኖሩ ገበሬዎች የወያኔን የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት በቤታቸው እስጥ እና በቤታቸው ደጃፍ ላይ በግዳጅ እንዲለጥፉ የተደረገ ሲሆን ለመለጠፍ ፍቃደኛ ያልሆኑ ገበሬዎች በመታሰር ላይ እንደሚገኙ አንድ የደብረማርቆስ ወጣት በላከው መረጃ ገልጿል:: ሕዝቡ አስተባባሪ እና አደራጅ ነው ያጣው ቢባልም በራሱ መሪነት ብሶቱን እየገነፈለ እየወታ የሚገኘው ሕዝብ ለነጻነቱ በጋራ ሆኖ መታገሉን እንደቀጠለ ነው::

The post የሰሜን ጎንደር ሕዝብ አመጽ በርትቷል * በድንበር ከተሞች አሁንም ችግሩ እየሰፋ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

“የጀግኖች እናቶቻችንን እና አባቶቻችንን ፈለግ እንከተል!”–ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

$
0
0

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ማክሰኞ ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፪ሺህ፯ ዓ.ም. ቅፅ ፫ ፣ ቁጥር ፲፭

ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ አድርገዋት የኖሩት ደረታቸውን ለጦር፣ እግራቸውን ለጠጠር፣ ሕይዎታቸውን ለሀገር ሉዓላዊነት እና ክብር እንዲሁም ለወገኖቻቸው ነፃነት ሲሉ ሲገብሩ የኖሩ ጀግኖች እናቶች እና አባቶች ስለነበሩን ነው። ከ፸፬(ሰባ አራት) ዓመታት በፊት ፋሽስት ጣሊያንን ያንበረከኩት የዛሬው ትውልድ ወላጆች እና አያቶች፣ ከሁሉም የሚበልጠው የጽናታቸው ምንጭ፣ ለአገራቸው ነፃነት የነበራቸው ቀናዒነት ነበር። ነገር ግን «የእሣት ልጅ ዐመድ» ሆኖ፣ በእኛ ትውልድ ዘመን እነርሱ በብዙ ልፋት እና ትግል የገነቧት ኢትዮጵያ በመፈራረስ ሂደት ላይ ናት።
moresh
በአምሥቱ ዓመት የአርበኝነት ዘመን፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን «ዱሩ ቤቴ» ብለው የፋሽስት ጣሊያኖችን እና የእነርሱ ባንዳዎች የነበሩትን ከሃዲዎች ጥምር ጦር ተፋልመዋል። በኅዳር ወር ፲፱፻፳፯ ዓ.ም. ኦጋዴን ውስጥ ወልወል ወደተባለው የኢትዮጵያ ግዛት የፋሽስት ጣሊያን ወታደሮች ዘልቀው በፈጠሩት ትንኮሣ የተጀመረው ጦርነት፣ ከአምሥት ዓመታት በላይ ወስዶ ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፲፱፻፴፫ ዓ.ም. ቀዳማዊ ኃይለሥላሤ በድል አድራጊነት አዲስ አበባ ሲገቡ ወረራው ተቀልብሷል። በእኒያ አምሥት የአርበኝነት ዓመታት፣ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን፣ በተለይ ዐማሮች፣ በግፍ ተጨፍጭፈዋል። በአሁኑ የገንዘብ ስሌት ሲተመን በቢሊዮን ብሮች የሚገመት ንብረት ወድሟል። ውድ እና መተኪያ የሌላቸው ቅርሶች ተዘርፈዋል፣ ወይም እንዲወድሙ ተደርጓል። ይህ ሁሉ መስዋዕትነት የተከፈለው ክቡር የሆነውን የአገርን ነፃነት ለማስመለስ ነበር፣ ጀግኖቹ የዚያን ዘመን ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነቱን ከፍለው አድርገውታል!

ከተለያዩ የታሪክ ድርሣናት እና መጻሕፍት ለማመሣከር እንደሚቻለው (ደጃዝማች ከበደ ተሰማ በ፲፱፻፷፪ ዓ.ም. «የታሪክ ማስታወሻ»፣ ዶ/ር ተወልደ ትኩዕ በ፲፱፻፺ ዓ.ም. «የኢትዮጵያ አንድነት እና ኢጣሊያ»፣ ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ በ፲፱፻፺፱ ዓ.ም. «የኢትዮጵያ ታሪክ ከ1847 እስከ 1983»፣ ገብረወልድ እንግዳወርቅ በ፪ሺህ ዓ.ም. «ማይጨው፣ የማይጨው ዘመቻና የጉዞ ታሪክ»፣ አምባሳደር ዘውዴ ረታ በ፪ሺህ፬ ዓ.ም. «የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መንግሥት»፣ ፕሮፌሰር መሥፍን ወልደማርያም በ፪ሺህ፭ ዓ.ም. «መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ») ለማመሣከር እንደሚቻለው፣ በአምሥቱ ዓመት የፋሽስት ጣሊያን የወረራ ዘመን ከፍተኛውን መስዋዕትነት የከፈሉት አርበኞች በስፋት ይንቀሳቀሱ የነበሩት በተለይ፦ በሸዋ፣ በጎጃም፣ በጎንደር እና በወሎ ክፍለሀገሮች ነበር። ከእነዚያ ስመጥር የአርበኞች መሪዎች መካከል ለአብነት ያህል የሚከተሉት ይገኙበታል።

· በሸዋ፦ አቡነ ጴጥሮስ፣ መላከፀሐይ ኢያሱ (የልጅ ኢያሱ ልጅ እና የሸዋ አርበኞች መሪ፣ አበበ አረጋይን ራስ ብለው የሾሙ)፣ ራስ ደስታ ዳምጠው (በሲዳሞ ግንባር ያዋጉ እና በጉራጌ አውራጃ በፋሽስቶች ተማርከው የተገደሉ)፣ ራስ አበበ አረጋይ (መንዝ፣ ተጉለትና ቡልጋ፣ ምንጃር)፣ ራስ መስፍን ስለሺ፣ ደጃዝማች አበራ ካሣ (ሰላሌ)፣ ደጃዝማች አስፋው ወሰን ካሣ (ሰላሌ)፣ ደጃዝማች ወንደወሰን ካሣ (ሰላሌ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሣፎ (በጉራጌ)፤ ደጃዝማች ፍቅረማርያም አባተጫን፣ ደጃዝማች አውራሪስ (መሐል ሸዋ)፣ ደጃዝማች መንገሻ ወሰኔ (መሐል ሸዋ)፣ ደጃዝማች ፀሐዩ እንቆሥላሤ (መርሃቤቴ እና ሰላሌ)፣ ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ (ጅባትና ሜጫ)፣ ደጃዝማች ከበደ ብዙነሽ (ጅባትና ሜጫ)፤ ደጃዝማች በቀለ ወያ (በጉራጌ)፤ ጄኔራል ጃጋማ ኬሎ፣ ልጅ ኃይለማርያም ማሞ፣ ወይዘሮ ሸዋረገድ ገድሌ፣

· በጎጃም፦ ራስ እምሩ ኃይለሥላሴ (የጎጃምን እና የጎንደርን ጦር መርተው በሽሬ ግንባር ያዋጉ)፣ ራስ ኃይሉ በለው (ሞጣ)፣ ቢትወደድ አያሌው መኮንን (ባህርዳር-አቸፈር)፣ ቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ (አቸፈር እና አገው ምድር)፣ ደጃዝማች አበረ ይማም (ባህርዳር፣ አቸፈር እና ሜጫ)፣ ደጃዝማች ነጋሽ በዛብህ (ቡሬ ዳሞት)፣ ደጃዝማች ደስታ እሸቴ (ደጋ ዳሞት)፣ ደጃዝማች ኃይለኢየሱስ ፍላቴ (ደጋ ዳሞት)፣ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ (ብቸና)፣ ደጃዝማች መንገሻ አቦዬ (ሞጣ፣ ትውልዳቸው አልቡኮ (ወሎ))፣ ቀኝጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ፣ አአቶ ጌታሁን ተሰማ (በኋላ ሚኒስትር እና አምባሣደር)፤

· በጎንደር፦ ደጃዝማች ዮሐንስ እያሱ (የልጅ እያሱ ልጅ፣ እና የቤገምድር አርበኞች አስተባባሪ)፣ ቢትወደድ አዳነ መኮንን፣ ቢትወደድ ገሠሠ ረታ፣ ራስ ውብነህ (አሞራው) ተሰማ፣ ደጃዝማች ዳኘው ተሰማ (ጎንደር፣ ቤገምድር)፣ ደጃዝማች ብሬ ዘገዬ፣ ደጃዝማች ታደሰ ይማም፣ ደጃዝማች ጀምበሩ፣ ደጃዝማች ገብሬ ካሣ፣ ፊታውራሪ ሥዩም ነጋሽ፣ ፊታውራሪ ሽፈራው ጌታሁን(አባ ከንትር)፣ ፊታውራሪ አለማየሁ ቢተዋ (ጭልጋ)፤

· በወሎ፦ ደጃዝማች ኃይሉ ከበደ (በላስታ)፣

· በባሌ፦ ደጃዝማች በየነ መርዕድ፤

· በሐረርጌ (ኦጋዴን)፦ ግራዝማች (በኋላ ደጃዝማች) አፈወርቅ ወልደሰማዕት፤

· በኢሉባቦር፦ አቡነ ሚካኤል፤

በዚህ ዝርዝር ውስጥ ስማቸው ያልተካተቱ አያሌ አርበኞች አሉ። ለወደፊት እያጣራን በስፋት እንዘግብበታለን።

ከፋሽስት ጣሊያን ጦር ጋር ሲፋለሙ የነበሩት አብዛኞቹ ጀግኖች እናቶች እና አባቶች ዛሬ በሕይዎት የሉም። ከመቃብር በላይ የሚውል ሥራቸው ግን ለዘለዓለም በትውልድ ሲዘከር የሚኖር ነው። ለመሆኑ እኒያ ጀግኖች ዛሬ ከመቃብር ተነስተው የትግሬ-ወያኔ የሚያመሰቃቅላት አገራቸው ኢትዮጵያ ያለችበትን እጅግ አሣፋሪ የታሪክ ምዕራፍ ቢመለከቱ ምን ይሰማቸው ይሆን? መቼም በምንም ተዓምር የባንዶች ልጆች እና የልጅ-ልጆች የሆኑት እነ መለስ ዜናዊ፣ ስብሐት ነጋ፣ ወዘተርፈ የሚያፈራርሷት የኢትዮጵያ ሁኔታ ሐሴትን ሊያቀዳጃቸው በፍጹም እንደማትችል ማንም ጤነኛ አዕምሮ ያለው ሰው የሚገነዘበው ነው። ስለዚህ በእኛ ስንፍና እና ቸልተኝነት አገራችንን ለዚህ የታሪክ ውርደት ያበቃነው የአሁኑ ትውልድ፣ ለተተኪው ትውልድ የባሰ ችግር ከምናወርሰው፣ ቆም ብለን ያለፍንበትን የስህተት ጎዳና እንመርምር፣ ጊዜው ሣይጨልምብንም እናርመው!

ኢትዮጵያ በታማኝ እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ለዘለዓለም ፀንታ ትኖራለች!

The post “የጀግኖች እናቶቻችንን እና አባቶቻችንን ፈለግ እንከተል!” – ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የአዲስ አበባ አስተዳደር ሰማያዊ ፓርቲ በመስቀል አደባባይ ሕዝባዊ ስብሰባ እንዳያደርግ ከለከለ (ደብዳቤውን ይዘናል)

$
0
0

semayawi
• ‹‹ተቀባይነት የሌለው ተልካሻ ምክንያት ነው›› አቶ ዮናታን ተስፋዬ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 9/2007 ዓ.ም መስቀል አደባባይ ላይ ለማድረግ ያቀደውን ህዝባዊ ስብሰባ እውቅና እንደማይሰጠው ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ ገልጾአል፡፡ አስተዳደሩ በላከው ደብዳቤ ‹‹መስቀል አደባባይ ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ መጨናነቅ ያለበት ከመሆኑም በላይ በርካታ የተከማዋ ነዋሪ የሚተላለፍበት እና የከተማው ነዋሪ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥር›› ነው ሲል ለህዝባዊ ስብሰባው እውቅና እንደማይሰጥና ሰማያዊ ፓርቲ ስብሰባውን መስቀል አደባባይ ማድረግ እንደማይችል ገልጾአል፡፡

በሌላ በኩል የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት አቶ ዮናታን ተስፋዬ አስተዳደሩ የሰጠው መልስ ‹‹ተቀባይነት የሌለው ተልካሻ ምክንያት ነው›› ሲል ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ ኃላፊው አክሎም ‹‹አደባባዩ የተሰራው እንደዚህ አይነት ተግባራት ሊከናወኑበት ነው፡፡ ኢህአዴግ ሲጠራ ትራፊክ ተጨናነቀ ተብሎ አያውቅም፡፡ ሰማያዊ ሰልፍና ስብሰባ ሲጠራ ግን እንዲህ አይነት ተልካሻ ምክንያት ያቀርባሉ፡፡ በመሆኑም ይህን ተልካሻ ምክንያት ሰማያዊ ፓርቲ አይቀበለውም›› ብሏል፡፡

ከትራፊክ መጨናነቅ ባሻገር አስተዳደሩ ሰማያዊ ለሚያደርገው ህዝባዊ ስብሰባ የፀጥታ ኃይል ለመመደብ እንደሚቸገርም የገለጸ ሲሆን አቶ ዮናታን ተስፋዬ በበኩሉ ‹‹ለጥበቃ የለንም ያሉትን የፀጥታ ኃይል ንፁሃንን ለመደብደብ ሲያሰማሩ በተደጋጋሚ አይተናል፡፡ አሁንም የጥበቃ ኃይል የለንም የሚሉት ስብሰባውን ለማስተጓጎል ነው፡፡ ያኔ ግን ሰላማዊ ዜጎችን ለመደብደብ ይልኩታል፡፡ በመሆኑም የአስተዳደሩ ውሳኔ በምክንያት ያልተደገፈና ተቀባይነት የሌለው ነው›› ብሏል፡፡

ምንጭ ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ

The post የአዲስ አበባ አስተዳደር ሰማያዊ ፓርቲ በመስቀል አደባባይ ሕዝባዊ ስብሰባ እንዳያደርግ ከለከለ (ደብዳቤውን ይዘናል) appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ሰመጉ ጥቃት እየደረሰበት መሆኑን አስታወቀ

$
0
0

Semguኢሳት ዜና :-የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ( ኢሰመጉ) የአሁኑ ሰመጉ ሚያዚያ 26 ቀን 2007 ዓም ባወጣው መግለጫ በአዋሳና አዲስ አበባ በሚገኙ የድርጅቱ ፅህፈት ቤቶች ላይ ጉዳት እንደደረሰበት

አስታውቋል።

መንግስት በተለያዩ ወቅቶች ላይ በድርጅቱ ላይ አፍራሽ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን የጠቀሰው ሰመጉ፣ ሚያዚያ 24 ቀን 2004ዓም የሰመጉ የሃዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቢሮ በስራ ቀን ከጠዋቱ 4 ሰአት ላይ ተደፍሯል። ሰመጉ የጽ/ቤቱን የጠረጴዛ መሳቢያዎች ገንጥሎ

ሰነዶችን ሲበረብር እጅ ከፍንጅ የተያዘ ግለሰብ ለፖሊስ ተላልፎ ቢሰጥም፣ የክስ ሂደቱ በመታየት ላይ እያለ ግለሰቡ በዋስ ተለቋል በሚል ከአካባቢው እንዲሰወር ተደርጓል ብሎአል።

መጋቢት 21 ቀን 2007 ዓም የሃዋሳ ሰመጉ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቢሮ ግልጽ ባልሆነ መንገድ በሩ ተከፍቶ ተገኝቷል የሚለው መግለጫው፣ በውስጡ የሚገኙት የመዛግብትና የልዩ ልዩ እቃዎች መስቀመጫ ቁምሳጥኖችና የቢሮው ጠረጴዛ መሳቢያዎች ተሰብረዋል።

ብዛት ያላቸው የድርጅቱ መዝገቦችና የሂሳብ ሰነዶችም በስርአት ተቀምጠው ከነበሩበት ስፍራ ተነስተው በጠረጴዛውና በወለሉ ላይ ተበታትነው ተገኝተዋል። የድርጅቱ ማህተም ከተቀመጠበት ቦታ ተንስቶ ሌላ ስፍራ በመገኘቱ፣ ማህተሙ ለህገወጥ ተግባር ውሎ ይሆናል

የሚል ከፍተኛ ጥርጣሬና ስጋት ማሳደሩን የሰብአዊ መብት ተማጓቹ ድርጅት ጠቅሷል። ጉዳዩን የያዘው ፖሊስ ውጤቱን እስካሁን ለሰመጉ አላመለከተም።

መጋቢት 24 ደግሞ ከቀኑ 11 ሰአት አካባቢ አዲስ አበባ በሚገኘው የሰመጉ ዋና ጽ/ቤት የመኪና ማቆሚያ ስፍራ ላይ በነበረ የሰመጉ መኪና ላይ ከፎቅ ላይ ወደቀ የተባለ እቃ ጉዳት እንዳደረሰበት ገልጿል። ጉዳዩን ለፖሊስ ቢያመለክትም ምንም መልስ ሊያገኝ

አለመቻሉንም ገልጿል።

መንግስት በሃገሪቱ ውስጥ የሚካሄዱ ሰብአዊ መብቶችን የማስከበር እንቅስቃሴዎችን በአሉታዊ መንገድ መመልከቱ፣ እንቅስቃሴዎችንም በተለያዩ መንገድ ማዳከሙ እና ጭራሹ አፋኝ ህጎችን በማውታት የማጥፋት ሙከራ ማድረጉ ህጋዊና ጠቃሚ አሰራር አለመሆኑን

በተለያዬ ጊዜያት መግለጹን ድርጅቱ ጠቅሷል።

መንግስት የሰብአዊ መብት ተሟጋች አባሎቻቸውንና ሰራተኞቻቸውን ደህንነት የመጠበቅና የማስጠበቅ ግዴታውን እንዲወጣ ሰመጉ ጠይቋል።

ብቸኛው የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት፣ በመላው አገሪቱ የነበረውን ጥንካሬ በገዥው ፓርቲ ተጽእኖዎች እንዲያጣ ተደርጓል። ድርጅቱ ላለፉት 24 አመታት የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ሲያጋለጥ መቆየቱ ከገዢው ፓርቲ ጋር እንዲላተም አድርጎታል። በአሁኑ ጊዜ

አብዛኞቹን የክልል ጽ/ቤቶች በገንዘብ እጥረት ምክንያት እንዲዘጋ በመደረጉ ፣ በፊት እንደሚያከናውነው ተከታታይ መግለጫውን ሲያወጣ አይታይም። ይሁን እንጅ በተወሰኑ ወራት የሚያወጣቸው መግለጫዎች አሁንም ገዢውን ፓርቲ እያስቆጡት መሆኑን ዘጋቢያችን

ገልጿል።

Source:: Ethsat

The post ሰመጉ ጥቃት እየደረሰበት መሆኑን አስታወቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

ከተማረ የተጋደለ (ሽሙጣዊ ግጥም) (ፍቅሬ ቶሎሳ፥ ፒ ኤች ዲ – የሁማኒቲስ ፕሮፌሰር)

$
0
0
↧

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የተያዙበት ሁኔታ ለህይወታቸው አስጊ ነው ተባለ

$
0
0

የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በከፍተኛ ህመም በመሰቃየት ላይ ሲሆኑ እስካሁን በዶክተሮች ለመጎብኘት አልቻሉም።
andargachew new picture
አያያያዛቸው የከፋ መሆኑን በማስመልከት የእንግሊዝ መንግስት አስቸኳይ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መጻፉንም ምንጮቻችን ገልጸዋል።

አቶ አንዳርጋቸው ያለፉትን ተከታታይ ወራት ጸሃይ የሚባል ነገር ሳያዩ ጨለማ ቤት ተዘግቶባቸው አሳልፈዋል; ከህመማቸው ጋር በተያያዘም ምግብ መመገብ በእጅጉ ቀንሰዋል።

በከፍተኛ የስነ ልቦና ጫና ውስጥ የሚገኙት አቶ አንዳርጋቸው፣ አያያዛቸው አስከፊ እንደሆነ በቅርቡ ለጎበኙዋቸው የእንግሊዝ አምባሳደር መናገራቸውን ምንጮች ገልጸዋል። ይህንን ተከትሎም የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ለኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
ጠንከር ያለ ደብዳቤ መጻፉን የአዲስ አበባ ምንጮች ገልጸዋል። የአቶ አንዳርጋቸው አያያዝ በአፋጣኝ የማይለወጥ ከሆነ፣ በህይወታቸው ላይ ያልተጠበቀ አደጋ ሊፈጠር እንደሚችል ያስጠነቀቁት የእንግሊዝ ባለስልጣናት፣ አቶ አንዳርጋቸው የኮንሱላር ድጋፍ እንዲያገኙ፣
በመደበኛ እስር ቤት ውስጥ እንዲታሰሩና በጠያቂዎች እንዲጎበኙ ፣ ሃኪሞች እንዲያዩዋቸውና ሰብአዊ መብታቸው እንዲከበር ደብዳቤ መጻፋቸውን ምንጮች ገልጸዋል።

ገዢው ፓርቲ ከአቶ አንዳርጋቸው የረባ መረጃ ለማግኘት ባለመቻሉ_የስነ ልቦና ጫና በማሳረፍና ህክምና በመከልከል ለመጉዳት ማሳቡን ምንጮች ገልጸዋል።

የእንግሊዝ ባለስልጣናት በሂደት ስለሚወስዱት እርምጃ ግልጽ ባያደርጉም፣ ጉዳዩን በቀላሉ እንደማያዩት ለኢህአዴግ ሹሞች እንደገለጹላቸው ታውቋል።

አቶ አንዳርጋቸው በየመን የጸጥታ ሃይሎች ተይዘው ለኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች ተላልፈው ከተሰጡ በሁዋላ፣ ገዢው ፓርቲ ሁለት ጊዜ በቴሌቪዥን አቅርቧቸዋል። ተቆራርጦ የተላለፈውን ቪዲዮ ተከትሎ ገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ትችት ሲቀርብብት ቆይቷል።

ኢህአዴግ አቶ አንዳርጋቸውን ህዝብ ሊጎበኛቸው በሚችል እስር ቤት አለማሰሩና ሰብአዊ መብታቸውን ሁሉ መግፈፉ የገዢውን ፓርቲ የፍርሃትና የበቀል ደረጃ፣ እንዲሁም ራሱ ላወጣው ህግ እንኳን የማይገዛ መሆኑን የሚያሳይ ነው ተብሏል።

The post አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የተያዙበት ሁኔታ ለህይወታቸው አስጊ ነው ተባለ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

አሁን ገና ‹‹ፕሮፌሰሮቹ›› ሞቱ

$
0
0

ከዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ

ባለፈው ወርኃ መጋቢት 19፣ ቅዳሜ ቀትር ላይ ከወዳጆቼ አንዱ ይደውልልኛል፡፡ ለጥሪው ምላሽ ስሰጥ፣ በዚያው ሰዓት ከሸገር ኤፍ. ኤም 102.1 እየተላለፈ የነበረውን የቀትር ወሬዎች እንዳዳምጥ ይጠቁመኛል፡፡ የስርጭት መሥመሩን አስተካክዬ ሳዳምጥ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አድማሱ ጸጋዬ ከምክትል ፕሬዝዳንቶቹ ጋር ስለ ሰጡት መግለጫ የሚተላለፍ ዘገባ ነበር፡፡ ከመግለጫ አርእስተ ጉዳዮች ውስጥ ዩኒቨርስቲው እኔን እና ዶ/ር መረራ ጉዲናን ስለማባረሩ የተመለከተ ማብራሪያ ይገኝበታል፡፡
Dr Dagnachew
ዘገባውን በማዳመጥ ላይ እንዳለኹ በአእምሮዬ የመጣችው ዕውቋ ድምፃዊት አስቴር ዐወቀ ነበረች፡፡ የፕሬዝዳንቱን እና በተለይም የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ዶ/ር ጄይሉ ዑመርን ከእውነት የማፍግፈግ እና ሐቅን የመሸፋፈን ድርጊት በተመለከተ ‹‹እስኪ ይሰማለት ምን አለችኝ ይላል›› እና ‹‹ራሱ በድሎ ራሱ አለቀሰ፤ በአሉባልታ ፈረስ አገር አዳረሰ›› የሚሉት የድምፃዊቷ ዜማዎች እና የዜማ ስንኞች በአዕምሮዬ ላይ ተመላለሱ፡፡

ለአንባቢያን ግልጽ ይኾን ዘንድ ኹለቱ የዩኒቨርስቲው ሹማምንት፣ ከሪፖርተሩ ጋዜጠኛ ነአምን አሸናፊ ሲቀርብላቸው የሰማኹት ጥያቄ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል፡-

“ከሠራተኛ ምደባ ጋራ በተያያዘ ከመድረኩ የተብራራ ነገር ነበር፡፡ ምደባው የተከናወነው በሕጉ መሠረት አድርጎ ግልጽነት በተሞላበት አኳኋን ነው ተብሏል፡፡ በሚዲያዎች እንደምንሰማው ደግሞ ከኹለት ወይም ከሦስት መምህራን የቅጥር ውል እድሳት ጋራ በተያያዘ የተለያዩ ዘገባዎችን እያዳመጥን ነው፡፡ በተለይም ዶ/ር ዳኛቸውን እና ዶ/ር መረራን ይመለከታል፡፡ ከዶ/ር መረራ ጉዳይ ጋራ በተገናኘ የፖሊቲካ ሳይንስ ትምህርት ክፍል ሊቀ መንበር ዶ/ር ካሳሁን ብርሃኑ ከሓላፊነታቸው መልቀቃቸውን ሰምተናል፡፡ በነዚኽ ጉዳዮች ላይ የዩኒቨርስቲው አያያዝ እና ምላሽ ምንድን ነው? የሰዎቹ የኮንትራት ውልስ ያልታደሰው ለምንድን ነው? ”

ለዚኽ ጥያቄ ፕሬዝዳንቱ እና ምክትላቸው የሰጧቸው መልሶች፣ የመጀመሪያው የአሠራር ሒደትን የሚመለከት ሲኾን፣ ኹለተኛው ደግሞ የአካዳሚክ ስታፍን የሥራ አፈጻጸም የሚጠቅስ ነው፡፡ ሹማምንቱ በእኒኽ ኹለት ነጥቦች ላይ በማተኮር ከሰጧቸው ምላሾች የሚከተሉት ተጠቃሾች ናቸው፤
አንደኛ ዶ/ር አድማሱ ጸጋዬ ከተናገሩት፡-

“የኹለቱ መምህራን ጥያቄ ከጡረታ ጋራ የተያያዘ ነው፡፡ ይኼ እንግዲኽ መንግሥት ያወጣው መመሪያ አለ፤ ደንብ አለ፤ አንድ የአካዳሚክ ሠራተኛ የጡረታ ዕድሜው ከደረሰና የሚተካው ሰው ከሌለና ከጠፋ፣ የጡረታ ዕድሜው ሊራዘምለት ይችላል፤ ይኼም ፕሮሰስ አለው፤ ከሦስት እና ከአራት ወራት በፊት ቀደም ብሎ መጀመር አለበት፤ በትምህርት ክፍሉ ይታያል፤ ማስታወቂያ ይወጣል፤ በዚያ ሞያ በገበያ ላይ ሰው ማግኘት የማይቻል መኾኑ ማስታወቂያ ይወጣና ትምህርት ክፍሉ ካየው በኋላ ለኮሌጁ ይላካል፤ ኮሌጁ ለአካዳሚክ ይልከዋል፤ ከዚያ ሒደቱን ተከትሎ ወደ ፕሬዝዳንቱ ይመጣና ለሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ይላካል፤ ጡረታ የማራዘሙ ኹኔታ፤ በዚኽ መሠረት የመጣ ጡረታን የማራዘም ጥያቄ የታገደበት ኹኔታ የለም፥ እውነቱን ለመናገር፡፡

… ለማራዘም ደግሞ ወቅቱን ጠብቆ በትክክለኛው መንገድ ማስታወቂያ ወጥቶ ገበያ ላይ ሰው ሳይኖር ሲቀር ያ በደንብ ተጠናቅሮ ለዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ይላካል፤ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ደግሞ ወደ ሲቪል ሰርቪስ የሚጠይቅበት ኹኔታ አለ፤ በነገራችን ላይ የአንድን ሠራተኛ የጡረታ ዕድሜ ለማራዘም መሥሪያ ቤቱ ፍላጎት ማሳየት አለበት፤ ሠራተኛው ይጠቅመኛል፤ የሚሠራው ሥራ አለ፤ ብሎ በደንብ አድርጎ ማስታወቂያ ማውጣት አለበት፡፡ ይህ ሒደት አለው፤ ይኼ ሕጋዊ ፕሮሰስ አለው፤ ይኼ ሕጋዊ ፕሮሰስ ተግባራዊ ባልኾነበት ኹኔታ የአንድን መምህር የጡረታ ጊዜ ማራዘም አንችልም፡፡”
ኹለተኛ ዶ/ር ጄይሉ ዑመር በበኩላቸው፡-

“ምናልባት በጡረታው ላይ አንድ ነጥብ ብጨምር ደስ ይለኛል፡፡ በመሠረቱ እንደ ሌላው ሲቪል ሰርቫንት አይደለም ሃየር ለርኒንግ አካዳሚክ ኢንስቲቱሽንስ አካዳሚክ ስታፉን የሚያስተዳድሩበት፡፡ እያንዳንዱ አካዳሚክ ስታፍ በየኹለት ዓመቱ ኮንትራት ይታደስለታል፡፡ ኮንትራት ነው የሚፈርመው፡፡ ስለዚኽ በየኹለት ዓመቱ ውስጥ የአካዳሚክ ስታፉ ፐርፎርማንስ በሚፈለገው ደረጃ ካልኾነ ተቋሙ የፈረመውን ኮንትራት ያለማደስ መብት አለው፡፡ ከጡረታ በኋላ ደግሞ የሚነሡ ጥያቄዎች፣ የሥራው ተፈላጊነት እና በቦታው የሚተካ ብቁ ሰው ያለማግኘት ኹኔታ ነው ከጡረታ በኋላ ‘further extension’ የሚጠየቅበት፡፡ በተቋሙ ጡረታን ማስረዘም እንደ ግዴታ ወይም እንደ መብት ሊነሣም አይችልም፤ በዩኒቨርስቲው የሴኔት ሕግ መሠረት፡፡”

ሹማምንቱ የዩኒቨርስቲውን የአሠራር ሒደት እና የአፈጻጸም ምዘና ሕግ ጠቅሰው የሰጡት መግለጫ የተዛባ እና ዕብለት የተመላበት ነው፤ ለዚኽም ሩቅ ሳንሔድ አልያም የእኔን ማብራሪያ ሳይሻ ወሳኝ ምላሽ አድርጌ የማቅርበው በመጀመሪያ ላለፉት አራት ዓመታት የፍልስፍና ትምህርት ክፍልን በሊቀ መንበርነት የመሩት ዶ/ር ጠና ዳዎ የእኔን የጡረታ ጊዜ ስለማራዘም እና ሳባቲካል ፈቃድ በተመለከተ በወቅቱ የሶሻል ሳይንስ ዲን ለነበሩት ለዶ/ር ገብሬ ይንቲሶ የጻፉትን ደብዳቤ ሲሆን በተጨማሪ ዶ/ር ጠናን ተክተለው እስከ አለፈው ወር መጨረሻ ድረስ የትምህርት ክፍሉ ዋና ሓላፊ የነበሩት ዶ/ር ዐቢይ ጸጋዬ፣ ለማኅበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ዲኑ ፕሮፌሰር ወልደ አምላክ በዕውቀት፣ በቅርቡ በፍልስፍና ትምህርት መስክ ለሚከፈተው የሦስተኛ ዲግሪ (ዶክትሬት) መርሐ ግብር የሥራ ጊዜዬን፣ የሞያ አስተዋፅኦዬን እና ደረጃዬን አስመልክቶ የሰጡትን የማያሻማ ምስክርነት ነው፡፡

የቀድሞው የፍልስፍና ትምህርት ክፍል ሊቀ መንበሩ ዶ/ር ጠና ዳዎ ባለፈው ዓመት ግንቦት 2 ቀን 2006 ዓ.ም. በጻፉት ሦስት ገጽ ደብዳቤአቸው፣ የጡረታዬ ጊዜዬ እንዲራዘም እና የሳባቲካል ፈቃድ እንዲሰጠኝ ትምህርት ክፍሉ መክሮ በወሰነው መሠረት የሚከተለውን ምስክርነት በመስጠት ጥያቄ አቅርበው ነበር፤

“…ትምህርት ክፍሉ አገልግሎታቸውን አጥብቆ የሚፈልግ በመኾኑ ደብዳቤአቸውን መነሻ በማድረግ የጡረታ ጊዜ እንዲራዘምላቸው መጠየቅ ወይም እርሳቸውን የሚተካ ባለሞያ ማዘጋጀት ነበረበት፡፡ በዚኽ መሠረት በዕድገትም ኾነ በድልድል እርሳቸውን ሊተካ የሚችል ከክፍሉ መምህራን መካከል ማግኘት አልተቻለም፡፡ ስለዚኽ በእርሳቸው ቦታ መቀጠር የሚችል መምህር ለመፈለግ በእርሳቸው ጠያቂነት ዩኒቨርስቲው በጋዜጣ ማስታወቂያ እንዲያወጣ ተደረገ፡፡ ይኹን እንጂ በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ያመለከተ ሰው ባለመኖሩ ትምህርት ክፍሉ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ በአመለከቱት መሠረት የአገልግሎት ጊዜአቸው እንዲራዘም ጠየቀ፡፡

…. የትምህርት ክፍሉ ባለበት የመምህራን እጥረት ምክንያት የእርሳቸውን አገልግሎት በእጅጉ ይፈልጋል፡፡ በመኾኑም የተጠቀሰው የጡረታ ጊዜ እንዲራዘምላቸውና የሳባቲካል ፈቃዳቸው የሚራዘምበት ኹኔታ እንዲመቻችላቸው የትምህርት ክፍሉ ይጠይቃል፡፡”
ዶ/ር ዐቢይ ጸጋዬ በበኩላቸው የኮንትራት ዉሌ እንዲራዘም ካቀረቡት ምክንያቶቸ ውስጥ በዋናነት የሚከተለውን እናገኛል፡-
‘Launching of the PhD program:
The department is ready to launch the PhD program during the second semester of the current academic year. The program contains two streams of the studies: Africans and Western philosophy. Even though we have excellent instructors in our department in African and Asian philosophy, Dr. Dagnachew is the only Ethiopian staff who has done his PhD in Western philosophy, as a result his services are indispensable in covering the Western stream.
In view of his diligence as a teacher and strong commitment to the world of academia, and also in lieu of his much needed services by the department, the Department is strongly looking forward for your good office to extend his services by three years.’
ይህም የእንግሊዘኛ ጽሑፍ ወደ አማርኛ ሲተረጎም፡-

“የዶክትሬት ዲግሪ መርሐ ግብር ስለ መጀመር፤
የፍልስፍና ዲፓርትመንት በተያዘው የትምህርት ዘመን ኹለተኛ አጋማሽ ላይ የዶክትሬት ዲግሪ መርሐ ግብር ይጀምራል፡፡ መርሐ ግብሩ የአፍሪቃ ፍልስፍና እና የምዕራብ ፍልስፍና የተሰኙ ኹለት የጥናት ዘርፎችን የያዘ ነው፡፡ የትምህርት ክፍላችን በአፍሪቃ እና ኤዥያ ፍልስፍና ጥናት ላቂያ ያላቸው መምህራን ቢኖሩትም በምዕራብ ፍልስፍና አስተምህሮ የዶክትሬት ጥናታቸውን የሠሩ የዲፓርትመንቱ ብቸኛ ኢትዮጵያዊ ባልደረባ፣ ዶ/ር ዳኛቸው በመኾናቸው በዘርፉ ያላቸው አስተዋፅኦ በእጅጉ አስፈላጊ እና ወሳኝ ነው፡፡

ዶ/ር ዳኛቸው ለመምህርነት ሞያ ያላቸው አቅም እና ተነሣሽነት እንዲኹም በአካዳሚው መድረክ (በዩኒቨርስቲው) የሚያሳዩት ትጋት ለትምህርት ክፍላችን ከሚኖረው ጠቀሜታ በመነሣት የአገልግሎት ዘመናቸው መራዘም አስፈላጊ መኾኑ ታምኖበታል፡፡ ስለዚኽም የትምህርት ክፍሉ የዶ/ር ዳኛቸው የሥራ ጊዜ በሦስት ተጨማሪ ዓመታት እንዲራዘም ይደረግ ዘንድ የቢሮውን መልካም ትብብር ይጠይቃል፡፡”

ፕሬዝዳንቱ እና ምክትላቸው ከተናገሩት በተፃራሪ ከዚኽ በላይ በአስረጅነት የቀረቡት ሰነዶች ለአንባቢያን እውነታውን በሚገባ ያሳያሉ ብዬ አምናለኹ፡፡ በፍልስፍና የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች የቀረበው ገለፃ፣ የሁለቱን ሹማምንት እበላ እና ሃሰተኛ አቀራረብ ፍንትው አድርጎ እንደሚያሳይ ብዙም ክርክር አያስፈልገውም፡፡

ምናልባት እነኚህ በትልቅ ተቋም ውስጥ በኃላፊነት የተቀመጡ ግለሰቦች፣ እንዴት ከእውነት ጋር የተጣላ ግንኙነት ሊኖራቸው ቻለ ብሎ የሚጠይቅ ሰው ይኖራል፡፡ እኔ እስከምረዳው ድረስ ሁለቱ ግለሰቦች የሚከተሉት ፈለግ ከእምሯዊ ግድፈት የመነጨ ችግር ብቻ ሳይሆን፣ የተደላደለ ኑሮን ለመጎናጸፍ እውነት መሽቀንጠር ካለባት ያለ ምንም ማቅማማት ገፍትረው ለመጣል ምን ግዜም ዝግጁ በመሆናቸው ነው፡፡

የድሎትንና የውሸትን ግንኙነት እና መስተጋብር ለመረዳት፣ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ‹‹ውይይት›› (Dailogue) በሚል ርዕስ በዩኒቨርስቲ መምህራን ማህበር የሚታተም መጽሔት ላይ የዛሬ አርባ አምስት ዓመት የደጃዝማች ከበደ ተሰማን ‹‹የታሪክ ማስታወሻ›› የሚባለውን አስደናቂ መጽሐፍ ሲገመግሙ፣ በአንድ ጉዳይ ላይ የሚከተለውን ብለዋል፡-

‹‹… ለምን እንዲህ እንደሚሆኑ መጠይቅ አይሻም፤ በአንድ በኩል እንጀራቸው ውሸት መሆኑን፣ በአንድ በኩል ደግሞ የእውነትን ግርማና ሥቃይ ያውቁታል፡፡›› ፕ/ሩ በዚህ ጥቅስ ውስጥ ሁለት አበይት የሆኑ ጉዳዮችን አቅርበዋል፡፡ አንደኛ፣ አንዳንድ ሰዎች ውሸትን የሚኖሩት ብቻ ሳይሆን፣ እንጀራቸው ውሸት ላይ የተመሰረተ መሆኑን፣ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ፣ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ ‹‹እውነት ማለት የኔ ልጅ›› ብሎ እውነትን መጨበጥና አብሮ መራመድ አልፎ-አልፎ አደጋ እና ችግር እንደሚያስከትል በተዋበ ስንኝ የነገረንን፣ ከላይ እንዳየነው ቀደም ሲል ፕ/ር መስፍን የእውነትን “ግርማና” ችግር መሸከም አስቸጋሪ ስለሚሆንባቸው አንዳንድ ሰዎች ወደ ውሸት ማዘንበሉን ይመርጣሉ ሲሉ በሚያምር ገለፃ አቅርበውታል፡፡

በሌላ በኩል ኹለቱ ሹማምንት ስለ ጡረታ ጊዜ ማራዘም ከሰጧቸው ማብራሪያዎች እርስ በርሳቸው የሚጣረሱ ነገሮችን መመልከቱ አስቸጋሪ አይኾንም፡፡ ከኹሉ በፊት፣ ፕሬዝዳንቱ የጡረታ ጊዜን ለማራዘም ዩኒቨርስቲው ጥያቄ ያቀርባል እንጂ፣ ሥልጣኑ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ነው ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል፣ ደግሞ የጡረታ ጊዜውን ለማራዘም ወሳኝ የኾነው ሒደት በዩኒቨርስቲው ተቋማዊ ሥርዐት እና ደንብ ውስጥ እንደሚከናወን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ይኸው በራሳቸው ቃል በወሳኝነት የተገለጸውና ዲፓርትመንቱ እንዲኹም ኮሌጁ ሕጋዊ አካሔዱን ተከትለው ያቀረቡትን የማራዘም ጥያቄ ተቀብለው ተገቢውን ምላሽ መስጠት ተስኗቸዋል፡፡ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴርም ቢኾን በዩኒቨርስቲው የተጠየቀውን የጡረታ ማራዘም ጥያቄ ያለአንዳች ማንገራገር ተቀብሎ ያስተናግዳል እንጂ፣ ፕሬዝዳንቱ ከተጠያቂነት ለመሸሽ እንዳደረጉት፣ ‹‹ሞያዊ አስተዋፅኦው ተፈላጊ ነው›› የተባለን መምህር የማባረሪያ ምክንያት ሊኾን አይችልም፡
፡
ሳባቲካል ፈቃድን በተመለከተ፣ አሠራሩ አንድ መምህር ለስድስት ተከታታይ ዓመት ካስተማረ፣ አንድ ዓመት የጥናት እና ምርምር ፈቃድ ዕረፍት እንደሚያገኝ በሴኔት ሕጉም ኾነ በሥራ ውሉ ላይ በግልጽ የተቀመጠ ነው፡፡ ኾኖም ፕሬዝዳንቱ አንድ መምህር በማመልከቻ ቅጹ መሠረት ፈቃዱን ሲጠይቅ ጠቅሶ እና አካትቶ የሚያቀርባቸውን የተለመዱ ነጥቦች የማይታወቁ ያኽል፣ ከሳባቲካል ፈቃድ መልስ ‹‹ብቁ አስተማሪ ይኾናል፤ ምርምር እየሠራ አስተዋፅኦ ያደርጋል›› በማለት መናገራቸው ነገሮችን ለማወሳሰብ ካልኾነ በቀር፣ ለተያዘው ጉዳይ ምንም ፋይዳ አይኖረውም፡፡ በእኔ ሳባቲካል ፈቃድ ጉዳይ ወደሚመለከተው ፍርድ ቤት የሚያመራ ቢኾንም ፕሬዝዳንቱ እና ምክትላቸው ከተናገሩት በተቃራኒ ከጡረታ ዘመኔ በፊት ማቅረቤን የሚያሳይ ማስረጃ በእጄ ይገኛል፡፡

ነፃነትና ዩኒቨርስቲ

ከግል ጉዳዬ ትንሽ ፎቀቅ ብዬ ስለሰው ልጅ የነፃነት ሕሊና እና ስለ ዩኒቨርስቲ ባህርያት የተወሰኑ ነጥቦችን ማንሳት እፈልጋለሁ፡፡
Beings who have received the gift of freedom are not content with enjoyment of
comfort granted by others.
[ Immanuel Kant, The Quarrel Between the Faculties (1798) ]
ትርጉም፡- የነፃነትን ጸጋ የተሰጡ ህልዋን (ሰዎች) ከሌሎች በሚናኝ ተድላ እና ምቾት፣ ደስታ እና እርካታ
አያገኙም፡፡ (ኢማኑኤል ካንት)
ነፃነት ለሰው ልጅ ተፈጥሮ ባሕርያዊ ቢኾንም፣ አልፎ አልፎ ሰው ለቁሳዊ እና ጊዜያዊ ፍላጎቱ ሲል፣ ባሕርያዊ ነፃነቱን አሳልፎ ይሰጣል፤ መጽሐፉም፣ ብኵርናውን በምስር ወጥ ስለለወጠው ዔሳው ያስተምረናል፡፡ በዩኒቨርስቲው ላዕላዊ አመራር ውስጥ ያለው ሰብአዊ እና አእምሯዊ ነፃነትን ከሚፈታተኑ ቁልፍ ችግሮች አንዱ ይኼ ነው፡፡

በሌላ በኩል፣ ከመልካም አስተዳደር የተጣላ ሥርዐት እንዲያብብ ያደረገው በዩኒቨርስቲው አሠራር ውስጥ የሰረገው ጥቅምን መሠረት ያደረገ ሽርክናዊነት (Patrimonialism) ነው፡፡ እንደ ዕውቁ የኻኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሥነ ማኅበረሰብ ተመራማሪ ማክስ ቬበር (Max Weber)፣ ጥቅምን መሠረት ያደረገ ዝምድና በመደበኛ እና በግላዊ የሥራ ድባብ መካከል ልዩነት አያደርግም፡፡ አንድን ተቋም የሚመለከት ጉዳይ በሙሉ ከተቋሙ ዋነኞች የግል ስንክሳር ጋራ በማቆራኘት ነው የሚወስደው፤ ሲከፋም ተቋሙን ሳይቀር እንደ ግል ንብረት ይቆጥራል፡፡

ለዚኽም ነው፣ ዶ/ር አድማሱ በድርጊቶቻቸው እና በመግለጫዎቻቸው ደጋግመው እንዳረጋገጡት፣ ዩኒቨርስቲው ሲተች እርሳቸው በግል እንደተተቹ፣ የእርሳቸውም የአመራር አቅም ሲጠየቅ፣ የዩኒቨርስቲው ስም እንደ ጎደፈ እና እንደጠፋ የሚመስላቸው፡፡

በዚኽ ጽሑፌ ዋናው መልእክቴ፣ የፕሬዝዳንቱ እና የምክትላቸው ማብራሪያዎች እኔን በትክክል እና በአግባቡ ከሚገልጹ የዩኒቨርስቲው ሰነዶች ጋራ የቱን ያኽል እንደሚራራቁ ማስረዳት ነው፡፡ስለ ዶ/ር አድማሱ ጸጋዬ፣ ‹‹የካውንት ሊዮ ቶልስቶይ ጀነራል እና የኢሕአዴጉ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት›› በሚል ርእስ ሰፋ ያለ ሐተታ በቅርብ አቀርባለኹ፡፡ የጥቅቅም ሽርክናው (Patrimonialism) በተመለከተ ግን ለጊዜው፣ ምክትላቸው ዶ/ር ጄይሉ ዑመር ያሉበትን ኹኔታ በአብነት አቀርቤ ጽሑፌን እቋጫለኹ፡፡

ከላይ እንዳወሳነው፣ ሰብአዊ እና አእምሯዊ ነፃነትን በሚፈታተነው የዩኒቨርስቲው የጥቅቅም ሽርክና የተመላበት የሥራ ዝምድና፣ ለሓላፊነት እና ለሹመት ለመታጨት ቀዳሚ መለኪያው አካዳሚያዊ እና አስተዳደራዊ ብቃት ሳይኾን፣ በአገሪቱ የፖሊቲካ ክፍል በጠንካራ ዐቃቤ (Patron) መደገፍ ወሳኝ ነው፡፡ በዩኒቨርስቲው ላዕላዊ አመራር ጠገግ ጠንካራ ዐቃቤ እና የፓርቲ ድጋፍ የሌለው ከፍተኛ ሹም ማግኘት አዳጋች ነው፡፡ ይህን የተደገፉበትን ጠንካራ አጋር ሲያጡ በራስ መተማመናቸው ከድቷቸው በሌሎች መገፍተሩ እና መናቁ የሚጠበቅ ነው፡፡ ጥቂት በማይባሉ የዩኒቨርስቲ መምህራን ዘንድ እንደሚነገረውም፣ የዶ/ር ጄይሉ ዑመር ችግር ከዚኽ ያልተለየ ነው፡፡

አንድ አረጋዊ ከዐፄ ቴዎድሮስ ጋራ በተያያዘ ያጫወቱኝ ነገር ዶ/ር ጂይሉ ዑመር ያሉበትን ኹኔታ በትክክል ሊያስረዳልኝ ይችላል፡፡ ዐፄ ቴዎድሮስ የሚወዱት ‘ቀንዲል’ የሚባል በሬ ነበራቸው፡፡ በሬው ባሻው ማሳ እየገባ ይበላል፤ በመሸበት ያድራል፤ ገበሬው ይቅርና ሹመኞቹ እንዲሁም ጅብ እንኳን ሳይቀር ዐፄውን ስለሚፈሩ ‹‹ማንም አይነካውም›› ይባል ነበር፡፡

የንጉሠ ነገሥቱ ዘመን ፍጻሜ ሲቃረብ ግን፣ በሬው ይጠፋል፡፡ ብዙ ቢታሰስም መገኛው ባለመታወቁ በጅብ ሳይኾን በገበሬዎች ታርዶ እንደተበላ ለንጉሡ ጭምጭምታ ይደርሳቸዋል፡፡ ከበሬው መጥፋት በኋላ በአጀብ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላው ሲሔዱ በአንዳንድ ቦታ ባላገሩ ፍርድ እንዲያገኝ፣ ‹‹ንጉሥ ሆይ፣ ጃንሆይ›› እያለ አቤት ሲል፣ በፈረሳቸው እንዳሉ ወደ አጃቢዎቻቸው ዘወር እያሉ ‹‹አኹን እኮ የእውነት ‹ንጉሥ› እየመሰልኋቸው ነው›› ሲሉ አጃቢዎቻቸው ‹‹በሚገባ እንጂ፣ ንጉሥ ነዎት እኮ›› ሲሏቸው፤ እሳቸውም ‹‹የእውነት ንጉሥ ብኾን ኖሮ ‘ቀንዲልን’ አርደው ይበሉት ነበር ወይ?›› ብለው በመደመም ሳይፈርዱ አልፈው ይሔዱ ነበር፡፡

ዶ/ር ጄይሉ ዑመርም በሥልጣናቸው ክልል ሊታይና ሊወሰንበት የሚችልን ጉዳይ እና አቤቱታ ሲቀርብላቸው፣ በአንድ በኩል መልስ ባለመስጠት (በእኔ ላይ እንዳደረጉት) በሌላ በኩል ወደ ፕሬዝዳንቱ በመግፋት ድርሻቸውን አይወጡም፤ ከሓላፊነትም ይሸሻሉ፡፡ እኔ እንደሚመስለኝ ፍጻሜ መንግሥታቸው የተዳረሰባቸው ንጉሠ ነገሥቱ ‹‹አኹን እኮ ንጉሥ መስዬአቸው ነው›› እንዳሉት ዐቃቤአቸውን ማጣታቸውን ተከትሎ ‹‹አኹን እኮ የእውነት ምክትል አካዳሚክ ፕሬዝዳንት እየመሰልኋቸው ነው›› ሳይሉ ቀርተው ነው ብላችኹ ነው!?

እዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባው፣ ዶ/ር ጄሉ ዑመር ያለ አጋር እና ድጋፍ (Patron) መሆናቸውን ቀድመው የተረዱት የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አድማሱ ጸጋዬ ናቸው፡፡ ምክትላቸው የበላይ ጠባቂያቸው እንደሌለ ሲያውቁ፣ በመጀመሪያ ያደረጉት ነገር በዩኒቨርስቲው ታሪክ የመምህራኑን የውል ዘመን የማራዘም ሥልጣን የምክትል ፕሬዝዳንቱ ሆኖ ሳለ፣ ፕሬዝዳንቱ የሆነ የሲቭል ሰርቪስ አንቀጽ ጠቅሰው ይሄንን ሥልጣናቸውን ወደ ራሳቸው ጠቅልለዋል፡፡ የም/ል ፕሬዝዳንቱን ሥልጣን የመጠቅለል ድርጊት በተለያየ ኹኔታ ስለተከሰተ ማስረጃ ማቅረቡ አስቸጋሪ አይሆንም፡፡ ለዚህም ነው ዶ/ር ጄሉ ዑመር የውሳኔ ጉዳይ ሲቀርብላቸው አንገታቸውን ደፍተው ወደ ፕሬዝዳንቱ ቢሮ የሚያስተላልፉት፡፡
ጉዳያችንን ከመቋጨታችን በፊት፣ ስለ ዩኒቨርስቲ ምንነት ጥቂት ነጥቦች ማንሳቱ ተገቢ ነው፡፡ ይሄም የሚሆንበት ምክንያት፣ ዩኒቨርስቲ መሆን የሚገባውን አጠቃላይ ገጽታ በጥቂቱም ቢሆን እያቀረብን፣ በአንፃሩ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አሁን ያለበትን ሁኔታ በተወሰነ መልኩ ለመቃኘት ይረዳናልና፡፡
ይሄንንም ለመተግበር በቅርቡ በፕሮፌሰር አለን ብሉም (Allan Bloom) The Closing of the American Mind በሚል ርዕስ ስለ ዩኒቨርስቲ በፃፉት ሃሳብ ላይ በመመርኮዝ ይሆናል፡፡ እንደ እርሳቸው አቀራረብ ዩኒቨርስቲ ቢያንስ- ቢያንስ የሚከተሉትን አራት ባህሪያትን ይይዛል፡፡
አንደኛ- ዩኒቨርስቲ ‹‹ከብርሃነ-ህሊና›› ጋር የተያያዘ ገጽታ አለው፡፡ ይሄም ማለት፣ ዩኒቨርስቲ ከጨለማ ወደ ብርሃን የሚደረግ አዕምሯዊ ወይንም የአመለካከት ሽግግር የሚካሄድበት መድረክ ነው፡፡ ከጨለማ ወደ ብርሃን ጉዞ ማለት ደግሞ ከአስተያየት፣ ከመላምት፣ ከዘልማድ፣ ከደመነፍስ ወዘተርፈ የምንቀበላቸውን ኹነቶች በአግባቡ ፈትሸን ከአለማወቅ ወደ ማወቅ የምንሸጋገርበት ሂደት ነው፡፡ ጥንታዊ ግሪካዊያን እንደሚሉት ሽግግሩ በአጠቃላይ ከአስተያየት (Doxa) ወደ ሳይንስ (Episteme) ይሆናል ማለት ነው፡፡

ኹለተኛ- ዩኒቨርስቲ የሚል ስያሜ የተሰጠው ማንኛውም ተቋም በሙሉ፣ ሁለት ቁም ነገሮችን አቅፎ የያዘ ነው፡፡ 1. ዩኒቨርስቲ ማለት የአዕምሮ ህይወት ተዘርቶ የሚኮተኮትበት መስክ ነው፡፡
2. ዩኒቨርስቲ በማያጠራጥር መልኩ ‹ምክንያታዊነትን› በበላይነት አንግቦ የሚንቀሳቀስ ተቋም ነው፡፡
ሦስተኛ- ዩኒቨርስቲ ከዚህ ቀደም በሰው ልጅ ታሪክ የተነሱትን ጥያቄዎች እንዳይረሱና እንደገና እንዲፈተሹ የሚያደርግ ሲሆን፣ አሁን ባለንበት ጊዜም ቢሆን አዳዲስ ጥያቄዎችን አንስቶ የሚወያዩበት እና ከግለሰብ ሆነም ከአገር አስተዳዳሪዎች የሚመጣን ሃሳብ በወል የሚመረመርበት ሥፍራ ነው፡፡ ዩኒቨርስቲ በአንድ በኩል ‹‹ጥቅም አቅራቢ›› በሌላ በኩል ደግሞ ‹‹ችግር ፈቺ›› መሆን አለበት በሚል ፈሊጥ የተነሳበትን ዓበይት ርዕይ እና ዓላማ መሳት የለበትም፡፡

አራተኛ- ብዙ ጊዜ ሀገር የሚያስተዳድሩ ባለሥልጣናት አንድ ፖሊሲ ወይንም መመሪያ ከቀረጹ በኋላ፣ ለህዝቡ ይህ ከመሆን በቀር ‹‹ሌላ አማራጭ የለም›› በማለት ሃሳባቸውን ያለ ምንም ተገዳዳሪ ሃሳብ ለመተግበር ይፈልጋሉ፤ በአንፃሩ ዩኒቨርስቲ ይበጃል ተብሎ በብቸኝነት የቀረበን ሃሳብ አሻሽሎ ወይንም ሽሮ አሊያም በርካታ የሆኑ አማራጭ ሃሳቦችን ማቅረብ የሚችል ተቋም ነው፡፡

ስለዩኒቨርስቲ ባህሪያት ይሄንን ካልን ዘንዳ፣ ስለ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጥቂት ነገሮችን ብለን ብዬ ጽሑፌን አጠናቅቃለሁ፡፡ የዩኒቨርስቲ ልዕልና ወይም የአካዳሚክ ነፃነት፣ ከሀገሪቱ የፖለቲካ ሥርዓት ጋራ በእጅጉ የተሳሰረ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ሊብራል ዴሞክራሲ በሰፈነበት ቦታ የአንድ ዩኒቨርስቲ ልዕልና የተከበረ ይሆናል፡፡
ወደ እኛ ሀገር በምንመጣበት ጊዜ ሀገሪቱን የሚያስተዳድረው ፓርቲ የምከተለው ሥርዓት ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ነው ብሎ ያምናል፤ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት እንደተመለከትነው ደግሞ ሥርዓቱ ለማንም ተቋም ልዕልና እና በራስ የመወሰንን መብት የማይሰጥ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ገዢው ፓርቲ አንድን ነፃ ተቋም መቆጣጠር ሲፈልግ አስቀድሞ የእርሱን ፍልስፍና እና ፈለግ የማይከተሉትን አስተዳዳሪዎች ይሽርና የራሱን ሰዎችና ካድሬዎች በቦታው ላይ ይሾማል፡፡ በቅርብ ጊዜ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም ውስጥ የተካሄደው ይሄው ነው፡፡
ወደ ፕሮፌሰር ብሉም መጽሐፍ ልመለስና አንድ ያስደመመኝን ነገር ላቅርብ፤ በጀርመን አገር ‹‹ናሽናል ሶሻሊስት ፓርቲ›› (የሂትለር ፓርቲ) ሥልጣን ሲይዝ በአገር ውስጥ ያሉትን ዩኒቨርስቲዎች በሙሉ በቁጥጥር ሥር ያውልና የፓርቲውን ተቀዳሚ ካድሬዎች በአስተዳዳሪነት ይሾማል፡፡ ይሄንን የታዘበ አንድ የሕገ-መንግሥት ኅልዮት ባለሟል፣ ምንም እንኳን እርሱ ራሱ የፋሽስት ፓርቲ አቀንቃኝ ቢሆንም ነገሩ አንገሽግሾት ‹‹አሁን ገና ሄግል በጀርመን ሞተ›› ብሎ ትዝብቱን ተናገረ፡፡ይህንንም በዋነኛነት ያለበት ምክንያት ሄግል ለብዙ ዓመታት በዩኒቨርስቲ ውስጥ ያገለገለ ስለሆነ ነው፡፡
እኔም አሁን በከፍተኛ አመራር ላይ ያለውን የዩኒቨርስቲ የካድሬ ስብስብ በምመለከትበት ጊዜ የተሰማኝ ልክ ‹‹ሄግል አሁን ገና በጀርመን ሞተ›› እንደተባለው፣ በኢትዮጵያም እነ ታደሰ ታምራት፣ ሠርገወ ሀብለሥላሴ፣ መርዕድ ወልደ አረጋይ፣ ካሳ ወልደማርያም፣ ዮናስ አድማሱ፣ ዳኛቸው ወርቁ፣ ደበበ ሠይፉ እና ሌሎችም በህይወት የሌሉ በዩኒቨርስቲ ያስተማሩ አሁን ገና እንደሞቱ ተሰማኝ፡፡

The post አሁን ገና ‹‹ፕሮፌሰሮቹ›› ሞቱ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ገዥው ፓርቲ ኦሮሚያ ውስጥ ምርጫውን ጀምሮታል ተባለ

$
0
0

(ነገረ ኢትዮጵያ) ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ገዥው ፓርቲ ምርጫውን ከአሁኑ እንደጀመረው ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች ካድሬዎች መራጮችን በጋንታ፣ በሴልና በኔትወርክ እያደራጁ ‹‹ኦህዴድ/ኢህአዴግን መርጫለሁ›› በሚል እያስፈረሙና ፎርም እያስሞሉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በጋንታ፣ በሴልና በኔትወርክ ተደራጅተው ‹‹ኦህዴድን መርጠናል›› ብለው እንዲፈርሙ የተደረጉ ዜጎች ፎርሙን ከሞሉበት ቀን ጀምሮ የምርጫ ካርዳቸውን ለጋንታ፣ ሴልና ኔትወርክ መሪዎቻቸው እንደሚሰጡ ታውቋል፡፡ የጋንታ፣ የሴልና የኔትወርክ መሪዎችም ኢህአዴግን ከአሁኑ መርጠዋል ተብለው የተደራጁ ዜጎችን ስምና የምርጫ ካርድም ለኦህዴድ/ኢህአዴግ ከፍተኛ ካድሬዎች እንደሚሰጡ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡
Oromia
ካድሬዎች ግንቦት 16 ቀን በፊት የምርጫ ካርዳቸውን ለጋንታ፣ ለሴልና ለኔትወርክ መሪዎች የሚሰጡትን ዜጎች ቤት ለቤት እየዞሩ እያስፈረሙ እንደሚገኙ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ በጋንታ፣ ሴልና ኔትወርክ ተደራጅተው ኦህዴድ/ኢህአዴግን ከአሁኑ እንደመረጡ በፊርማቸው አረጋግጠዋል የተባሉት ዜጎች ግንቦት 16/2007 ዓ.ም በሚደረገው ምርጫ እንደማይሳተፉ የታወቀ ሲሆን አብዛኛዎቹ በግዳጅና በማስፈራሪያ እየሞሉ እንደሚገኙ ተገልጾአል፡፡

የጋንታ፣ የሴልና የኔትወርክ እንዲሁም የመራጮች ስምና ፊርማቸው እየሰፈረበት ከግንቦት 16 በፊት እንደመረጡ ተደርጎ ዜጎች እንዲሞሉት የሚደረገውና ከስር የሚታየው ቅጽ ካድሬዎች በአርሲ ዞን በቆጅ ወረዳ ቤት ለቤት ሲያስሞሉ የተገኘ ነው፡፡

The post ገዥው ፓርቲ ኦሮሚያ ውስጥ ምርጫውን ጀምሮታል ተባለ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

አነጋጋሪው በጥላሁን ገሠሠ ዙርያ የወጣው መጽሐፍ –‹መፅሐፉ የተዛቡ የጥላሁን ገሠሠን ታሪኮች ያጠራል› –ጋዜጠኛ ዘከርያ መሐመድ

$
0
0

tilahun gesese

ቁም ነገር ቅጽ 13 ቁጥር 201 ሚያዝያ 2007

ዘከርያ መሐመድ ይባላል፡፡ ጋዜጠኛ ነው ለረጅም ዓመታት በጋዜጦችና በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ላይ ሰርቷል፡፡ በ1984 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቲያትር ጥበባት የተመረቀው ዘከርያ ቢላል መፅሔት፣ ህፃናትና ወጣቶች ትያትር ቤት፣ ልዩ አቃቢ ህግ መስሪያ ቤት፣ ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና ኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን በመሳሰሉ ተቋማት በጋዜጠኝነት እና በተለያዩ የሙያ ዘርፎች አገልግሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት በግሉ የዶክመንተሪ ፊልሞችን በመስራትና በኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ላይ በማማከር ተግባር ተሰማርቶ ይገኛል፡፡
በጋዜጠኝነት ህይወት ውስጥ ረጅም ጊዜ ያሳለፈው ዘከርያ ከቀናት በፊት ጥላሁን ገሠሠ የህይወቱ ታሪክና ሚስጢር በሚለው ርዕስ አዲስ መፅሐፍ ለንባብ አብቅቷል፡፡ መፅሐፉ በጥላሁን ገሠሠ ህይወት ዙሪያ እስከ ዛሬ የምናውቃቸውንና በመገናኛ ብዙሀን ሲነገሩ የነበሩትን ሀቆች የተዛቡ እንደነበሩ ያስረዳናል፡፡ ከአዳዲስ ሀቆች ጋር ያስተዋውቀናል፡፡ እነዚህን አዳዲስ ሀቆች ጥላሁን ገሠሠ በህይወት በነበረበት ወቅት ለአንዴም ቢሆን በይፋ ተንፍሷቸው አያውቅም፡፡
ጋዜጠኛው ዘከርያ እድለኛ በሚያስብለው ሁኔታ በጥላሁን አጎት በአቶ ፈይሳ ሀሰና ሐይሌ የተፃፈውን የቤተሰብ ማስታወሻ አግኝቷል፡፡ መፅሐፉ የያዛቸው ጥሬ ሀቆች ከዚህ ማስታወሻ ላይ የተቀዱ ናቸው፡፡ ‹‹በጥላሁን ገሠሠ ዙሪያ ለዓመታት ሲተላለፉ የነበሩ የተዛቡ እውነታዎች በማያዳግም ሁኔታ መልስ ያገኛሉ›› የሚለው ዘከርያ መሐመድ ከፍስሃ ጌትነት ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡

ቁም ነገር፡- የጥላሁንን ታሪክ ለመጻፍ ምን አነሳሳህ?
ዘከርያ፡- በአጋጣሚ ነው ወደዚህ ስራ የገባሁት፡፡ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሙዚቃ አፍቃሪ ጥላሁንን እወደዋለሁ፤ በቤተሰባችን የእሱን ሙዚቃዎች እየሰማን ስላደግን ለጥላሁን ልዩ ስሜት አለኝ፡፡ ጥላሁን ህይወቱ ካለፈ ከሁለት ወር በኋላ ከአንድ ጓደኛዬ ጋር ሬዲዮ እየሠማን ነበር፡፡ ስለ ጥላሁን ይወራል፡፡ ጥላሁን ገሠሠ ያልዘፈነበት ርዕስ የለም እየተባለ ነው፡፡ ትክክል ነው በብዙ ርዕሶ ላይ ጥላሁን ዘፍኗል፡፡ ነገር ግን ስለጥላሁን ያ ብቻ ነው ወይ የሚወራው የሚል ጥያቄ ፈጠረብኝ፡፡ 68 ዓመት ረዥም እድሜ ነው፡፡ የጥላሁን ህይወት በብዙ ክስተቶች የተሞላን ነው፤ ጥላሁን ከህዝብ ጋር የኖረ ሰው ነው፡፡ ስለዚህ ጥላሁን በብዙ ጎን ሊዘገብ የሚገባው ሠው ነው፡፡ መባል የሚገባውን ያህል አልተባለም፡፡ ሊጻፍ የሚባውን ያህልም አልተጻፈለትም፡፡ በዚህ መነሻነት ከጓደኛዬ ሲሳይ ገብረጻድቅ ጋር አንድ ነገር ለመስራት ተነጋገርን፡፡ መጽሐፍ ልጽፍ፤ እሱ ደግሞ ዶክመንተሪ ፊልም ሊሠራ በዚያ ቀን ወሰንን፡፡ መሳይ ምትኩ የተባለ ሌላ ጓደኛችን ደግሞ ዌብሳይት አዘጋጃለሁ አለ፡፡ ከዚያ ይሄንን ካነሳን በኋላ 3 ቀን ቆይቶ አንድ ነገር ተከሠተ፡፡ አንድ ሠው ሲሳይ ጋ ደውሎ አባታቸው ስለጥላሁንና ስለቤተሰቡ የጻፈው ማስታወሻ እጁ ላይ እንዳለ ነገረው፡፡
ቁም ነገር፡- የአቶ ፈይሣ ልጅ ማለት ነው?
ዘከርያ፡- አዎ የአቶ ፈይሣ ልጅ ነው የደወለው፡፡ ሳምሶን ይባላል፡፡ አቶ ፈይሣ ሃይሉ ከ1934 ዓ.ም ጀምሮ ጥላሁን ከተወሰደበት ጊዜ አንስቶ የቤተሰቡን ታሪክ በማስታወሻቸው ጽፈው አስቀምጠው ነበር፡፡ ከሳምሶን ጋር ተገናኝተን ለመጀመርያ ጊዜ እነዚህን አስገራሚ የሆኑ የቤተሰብ ታሪክ የያዙ ማስታወሻዎች አየኋቸው፡፡ እነዚህን ማስታወሻዎችና ራሳቸው አቶ ፈይሣ ያነሷቸው ፎቶ ግራፎችን በእምነት ሰጠኝ፡፡ ማታውኑ ሳነበው አደርኩ፡፡ ከዚያ በኋላ ነው ወደኋላ ተመልሼ ማጥናት የጀመርኩት፡፡ የጥላሁን ታሪክ ላለፉት ዓመታት ተዛብቶ ሲቀርብ የነበረበትን ምክንያት ለመመርመር የተለያዩ ጽሑፎችን ተመለከትኩ፡፡ አቶ ፈይሣ በጻፉት የቤተሰቡ ማስታወሻና በመገናኛ ብዙሐን ሲነገረን የነበረው መረጃ መካከል ከፍተኛ ልዩነት አለ፡፡ የልዩነቱ ምንጭ ሌላ ሰው ሳይሆን ጥላሁን ነው፡፡
ቁም ነገር፡- ጥላሁን የራሱን ታሪክ አዛብቶ ሲነግረን ነበር ማለትህ ነው?
ዘከርያ፡- ለምሳሌ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ያሳተመው መጽሐፍ ላይ የተጻፉ ታሪኮች ተመልከት፡፡ በቀጥታ ከሱ የተገኘውን ነገር ነው ያሰፈሩት፡፡ ስለ መጀመሪያ ሚስቱ ሲናገር ወ/ሮ አስራት እንደሆነች ይገልጻል፡፡ እውነታው ግን እሱ አይደለም፤ የመጀመሪያ ሚስቱ ወ/ሮ ፈለቀች እንደሆነች የሚያስሳየውን እውነት ታገኛለህ፡፡
ቁምነገር፡-ስለዚህ አሁን አንተ ያወጣከው ጥላሁን በሕይወት በነበረበት ዘመን የደበቀን ታሪኮች ናቸው ማለት ነው?
ዘከሪያ፡- ይህ መፅሐፍ የተፃፈው እንደነገርኩህ ነው፡፡ እንዲሁ ዝም ብለን ጥላሁን ቡቡ ነበር፣ ያለቅስ ነበር እያልን ማውራት ብቻ ልክ አይሆንም፤ ለምን ብለን መጠየቅ አለብን፤ የጀርባ ታሪኩን ማጥናት አለብን፡፡ ልንረዳው ይገባል፡፡ ያላወቅንለት ነገር ነበረ ማለት ነው፡፡
ቁም ነገር፡- ያላወቅንለት ነው ወይስ የደበቀን?
ዘከሪያ፡- እኛም አላወቅንለትም፤ እሱም ልክ ነህ ደብቆናል፡፡ ሁለቱም ነው የሚባለው፤ እሱ ስለደበቀን ነው እኮ እኛም ያላወቅነው፡፡ ነገር ግን ስለደበቀንና ሌላ ታሪክ ስለነገረን ውሸታም ነው ልንለው አንችልም፡፡ በርግጥ ውሸት ነው፡፡ ግን ለህልውናው ሲል እራሱን ለማቆየት ሲል ስሜቱን ለማጠገግ ሲል በሰቀቀን ላለመሞት ሲል አንድ ሰው ይዋሻል፡፡ ይሄ የሁላችንም ጉዳይ ነው፡፡ ይሄ መፅሐፍ እኮ የጥላሁንን ታሪክ ለመናገር የወጣም አይደለም፡፡ ብዙ ሰዎችን ያክማል ብዬ አስባለሁ እኔ፡፡ ጥላሁን ያደረገውን ማድረግ ጉዳትም ጥቅምም ይኖረዋል፡፡ ወደኋላ ያሉ መጥፎ ትውስታዎችን እንሸሻቸዋለን፡፡ ማስታወስ አንፈልግም ስለዚህ ከዚያ ጋር የተያያዘ ጉዳይ ማውራት ካለብን ከዚያ ሸሽተን ሌላ ታሪክ ጨምረንበት እንናገራለን፡፡ ጥላሁን ዝነኛ ባይሆን ኖሮ እኮ ሁሉም ሰላም ይሆን ነበር፡፡ ዝነኛ የሆነውም ያንን ታሪክ በመሸሹ ነው፡፡ ጥቅምም ጉዳትም ነበረው፡
፡ ጥላሁን ደስተኛ ሰው አልነበረም፤ ለራሱ ተርፎ አይደለም የኖረው፡ ፡ እነዚያ የሚጎዱት
ነገሮች ደግሞ በቀላሉ የሚታረቁት አይደሉም፡፡ እና ለምን ለህዝብ ያንን ታሪኩን አልተናገረም ልል አልችልም፡ ፡ ግን ስነልቦናውን ጎድቶታል፡፡ የተረጋጋ የትዳር ሕይወት እ ን ዳ ይ ኖ ረ ው አድርጎታል፡፡ የሆነ አቅሙን ነስቶታል፡ ፡ የሚፈጠሩ አደጋዎችን የመጋፈጥ አቅሙን ሸርሽሮታል፡፡ በዚህ ምክንያት ቤተሰቡ ይፈርሳል፡፡ ምክንያት አለው ሰዎች እንዲረዱት እፈልጋለሁ፡፡ አሁን ለምሳሌ ጥላሁን ብዙ ስለማግባቱ
አንስተው በመጥፎ ሁኔታ የሚተረጉሙት አሉ፡፡ ለምንድነው ብለው ግን አይጠይቁም፡፡ ዝም ብለው ‹አለሌነት › አድርገው ይወስዱታል፡፡ አይደለም / ላይሆን ይችላል፡፡ መጀመሪያ ለምንድ ነው ብለን ጠይቀን ትክክለኛውን ነገር መረዳት አለብን፡፡
ቁም ነገር፡- በመፅሐፍህ ውስጥ የልጅነት ሕይወቱ ለዚህ እንደዳረገው ነው የምትነግረን?
ዘከሪያ፡- አዎ ቤተሰባዊ ዳራው ነው ዋናው ምክንያቱ፤ በመፅሐፉ ውስጥ በደንብ ተቀምጧል፤ በሽሽት ውስጥ ስትኖር እውነተኛውን ነገር ስትሸሸው ጠንካራ ስብዕና ታጣለህ፡፡ ደካማ ኢጎ ይቆጣጠርሀል፡፡ እንደዚህ ስትሆን ደግሞ መደረግ ያለበትን ትተህ መደረግ የሌለበትን ታደርጋለህ፡ ፡ ችግሩ የሚከሰት መሆኑን እያወክ እንኳ የለም
ይቅርብኝ ብለህ ፊትህን አታዞርም ፡፡ ዝም ብለህ ትገባበታለህ፡፡ ስለጥላሁን ያናገርኳቸው አንድ ሦስት ሰዎች ‹‹ ጥላሁን የቦይ ውሃ ነው›› ብለውኛል ቃል በቃል፡፡ ካንተ ጋር ተቀጣጥሮ ሌላ ሰው መንገድ ላይ ካገኘው ከሱ ጋር ሊሄድ ይችላል፡፡ ጥላሁን ያንን አቅም ነው ያጣው፡፡ በዚህ ምክንያትና ሌሎች ከሱ ውጪ የሆኑ ተፅእኖዎች ተደምረው የኖረውን
አይነት ህይወት ውስጥ ከትተውታል፡፡ ይሄንን ልንረዳለት ይገባል፡፡
ቁም ነገር፡- ከዚህ አንፃር የመፅሐፉ መፃፍ አላማ ምንድ ነው ማለት ነው?
ዘከርያ፡- የተዛቡ ታሪኮችን ማስተካከል፤ የተዛቡ እይታዎችንና ግንዛቤዎችን ማስተካከል፣
ሰውዬውን መረዳት ፣ ከሱ ህይወት መማር እንድንችል ነው፡፡ለኛም እኮ ይጠቅመናልየ የሱ
ህይወት ምን አይነት ምስቅልቅል ውስጥ እንደነበር እናያለን፡፡ ዝም ብሎ ከሆነ ታሪክ መሸሽ አያዋጣም፤ ምን አይነት ጥፋት እንደሰራ ላታውቅ ትችላለህ፡ ፡ ስነ አእምሮአዊ ጉዳይ ስለሆነ በምን መልኩ እየተጎዳህ እንደሆነ አታውቀውም ፡፡ ሌላኛው ነገር ግን እኔ ጥላሁን ገሰሰ ዝም ብሎ ተረት እንዲሆን አልፈልግም፡፡ ማንም የሚፈልግ አይመስለኝም፡ ፡ ጥላሁን የተለያየ ሰው በሚያነሳው ብጥስጣሽ አሉባልታ መካከል እንዲቆም አልፈልግም፡፡ ይሄ
ለማንም አይጠቅምም፡፡ በተናጠል ስናውቀው ነው፡፡ ምን አይነት ስብዕና ነበረው፤ ከህዝቡ ጋር ምን አይነት መቀራረብ ነበረው፤ የልጅነት ህይወቱ ምንድነው የሚሉትን ነገሮች መለስ ብለን ብናውቅ እንማ ርበታለን፤ እንጠቀምበታለን፤ እሱንም ደግሞ ከተዛቡ ግንዛቤዎች እናጠራዋለን፡፡
ቁም ነገር፡- ስለጥላሁን ከወጡት የተዛቡ ታሪኮች ውስጥ በምሳሌነት ማንሳት የምንችላቸውን ንገረኝ?
ዘከሪያ፡- ለምሳሌ ህይወቱ ካለፈ በኋላ ካ የ ኋ ቸ ው ፅሑፎች መካከል የጥላሁን ስም
ደንዳና አያና ጉደቱ እንደሆነ ይገልፃል፡፡ ሌላ ቦታ ደግሞ ጥላሁን ገሠሠ የንጉሴ ልጅ
መሆኑን ይፅፋል፡ ፡ የአባቱ ስም ኩምሳ አንጋሱ ነው የሚልም አለ፡፡ እናቱ ድሀ
ነች የሚልም አ ን ብ ቤ ያ ለ ሁ ፤ ዝም ብሎ አ ፈ ታ ሪ ክ ይወራል፡፡ አቶ
ፈይሳ ሀሰን ሀይሌ የፃፉት የቤተሰብ ማስታወሻ ግን ይሄን ሁሉ ነገር ያጠራልናል፡፡
ቁም ነገር፡- በጥላሁን ገሠሠ ታሪክ ውስጥ ስንሰማቸው ከነበሩት እውነታዎች መካከል አሁን ባንተ መፅሐፍ ውስጥ ፍፁም ተቃራኒ ሆነው የመጡ አሉ፤ የውልደት ቦታው፣ የመጀመሪያው የትዳር ህይወቱ እና የ1985ቱ የግድያ ሙከራን በምሳሌነት ማንሳት ይቻላል?
ዘከሪያ፡- እነዚህ ነገሮች ላይ በመፅሐፉ ጥሩ መልስ ተሰጥቷል ብሎ ማለፍ ይሻላል፡፡ በእውነትና በጥንቃቄ ተተንትኖ በምክንያታዊነት የተሰራ መፅሐፍ ነው፡፡ አሁን ባልካቸው ነገሮች ላይ ይሄ መፅሐፍ ክፍተት የለበትም፡፡ አሻሚ የነበሩ ታሪኮች በጠቅላላ
መልስ ተሰጥቷቸዋል ብዬ አምናለሁ፡፡ ከትውልድ ቦታው ጋር የተገናኘውና ከቤተሰቡ ጋር እና ከናትና አባቱ ትዳርና ማንነት ጋር፣ ከራሱ ትዳር ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ከዚያም ደግሞ ከ1985ቱ የግድያ ሙከራ ጋር ያሉት ነገሮች በሙሉ በበቂ ሁኔታ ተተንትነው፣
ተብራርተው ቀርበዋል፡፡ የማያዳግም ምላሽ ተሰጥቷል ብዬ አስባለሁ፡፡
ቁም ነገር፡- የጥላሁን ቤተሰቦች ስለ መፅሐፉ ያውቃሉ?
ዘከሪያ፡- የግል ታሪክ መፅሐፍ እራሱ ነው የሚመራህ፤ የሰውየውን የህይወት ምዕራፍ ነው
የምትከተለው፡፡ የአቶ ፈይሳ ሐሰና ሀይሌ የቤተሰብ ማስታወሻ ከተመለከትኩ በኋላ ሌሎች ተጨማሪ ታሪኮችን ለማሰባሰብና ለመተንተን የጥላሁንን ቤተሰቦችና የሱን የቅርብ ወዳጆች አነጋግሪያለሁ፡፡ ከወዳጆቹና የስራ ባልደረቦቹ መካከል እነ መሐሙድ አህመድ፣ ደበበ እሸቱ፣ አቶ ከበደ ወጋየሁ፣ ወ/ሮ ቆንጅት፣ ወ/ሮ አድባሪቱ የመሳሰሉትን አነጋግሪያለሁ፡

ቁም ነገር፡- ከቤተሰቦቹስ? ዘከሪያ፡- ወ/ሮ ማርታ፣ ወ/ሮ ሒሩትን
እንዲሁም ልጆቹንም አግኝቻቸዋለሁ፤ ይህን ስራ እየሰራሁ እንደሆነ የማያውቁ አሉ ብዬ አላስብም፡፡ ልጆቹንና የትዳር አጋሮቹን አግኝቻቸዋለሁ፡፡
ቁም ነገር፡- የመፅሐፉን የህትመት ወጪ ማነው የሸፈነልህ?
ዘከሪያ፡- ከቤተሰቦቼ ተበድሬ ነው፡፡
ቁም ነገር ፡- አመሠግናለሁ፡፡

The post አነጋጋሪው በጥላሁን ገሠሠ ዙርያ የወጣው መጽሐፍ – ‹መፅሐፉ የተዛቡ የጥላሁን ገሠሠን ታሪኮች ያጠራል› – ጋዜጠኛ ዘከርያ መሐመድ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

እኔ እንዲህ አስባለሁ – [ለወንድሜ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት] –ዶክተር በድሉ ዋቅጂራ

$
0
0

እኔ እንዲህ አስባለሁ፡፡

ለወንድሜ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

የአንተን ጽሁፍ ሀሳብ መነሻ አድርጌ፣ ‹‹ጀማል ማንስ ቢሆን?›› በሚል ርእስ ስር ያነሳሁትን ሀሳብ ተመርኩዘህ፣ የጻፍክልኝን ሶስት አብይ ጥያቄዎች የያዘ አጭር ጽሁፍ አነበብከት፡፡ የዚህ ጽሁፌም አነሳስ እነዚያን ጥያቄዎች ለመመለስ መሞከር ነው፡፡
bedilu wakjira
የአንድን ሰው ማንነት ከባለቤቱ ውጭ ያለ ሰው ለእርሱ በሚመስለውና በሚፈልገው መንገድ ለመቀየር መብት አለውን?
በአጭሩ መብት የለውም፡፡ እኔም በቀደመው ጽሁፌ ያልኩት፣ ‹‹ዳንኤል ልብ እንድትልልኝ የምፈልገው፣ አንተ የጻፍከው እውነት አይደለም ማለቴ እንዳልሆነ ነው፤ እኔ የምለው፣ ‹እኔ እውነት ብዬ የተቀበልኩት (አንተ ሀሰት ነው ያልከው) ሀሰት ቢሆን እንኳን፣ አሁን ባለንበት ሁኔታ ከእውነቱ የበለጠ ዋጋ አለው›› ነው፡፡ ስለዚህ የእኔ ሀሳብ የተሰነዘረው ጉዳይ (ታሪኩ) ማህበረሰቡ ውስጥ ከሚያሳድረው ስለምንና ባለንበት ስሱ ሁኔታ ከሚያሳርፈው ተጽእኖ አንጻር እንጂ፣ የሰማእቱን ማንነት (ዜግነቱን፣ ጎሳውን፣ አስተዳደጉን፣ ሀይማኖቱን) በማስረጃ አስደግፌ፣ እውነት ውሸት ብዬ ለመከራከር አይደለም፤ በዚህ ጉዳይ ላይ እንኳን ለአደባባይ ሙግት፣ ለማኪያቶ ወግ የሚበቃ እውቀትም ሆነ መረጃ የለኝም፡፡

በዚህ ረገድ የእኔ ነጥብ፣ በዚህ ሀይማኖትን ተመርኩዞ በደረሰብን ጉዳት፣ ምንም እንኳን አይ.ኤስ ሙስሊሞችን ባይወክልም፣ የገዳዮቹ ሙስሊምነትና እራሳቸውን ትክክለኛ የእስልምና ተከታይ አድርጎ ማየት፣ ሙስሊም ገዳይ ክርስቲያን ተገዳይ የሚል ስሜት መፍጠሩ አይቀርም፡፡ አብዛኛው ህዝብ ደግሞ (የከተማውም ቢሆን) እንደእኔና እንዳንተ ባለቻናል ቲቪ የለውም፤ የኢንተርኔቱንም ተደራሽነት የምናየው ነው፡፡ እና የመጀመሪያው የጀማል ታሪክ ይህንን ሀሳብ የሚያፈርስ በመሆኑ ብዙዎችን አጽናንቷል፤ ቢያንስ በእኔና በዙሪያዬ ስላሉት ሰዎች ስሜት እማኝ ነኝ፡፡ ታሪኩ ፈጣራም ቢሆን እንኳ የፈጠረው በጎ መንፈስ ነው፡፡ እስቲ የጀማልን ኤፍሬምነት ከገለጥክበት ጽሁፍ ስር ያለውን አስተያየት አስተውል፤ በአብዛኛው ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች ወገን ለይተው የሚነታረኩበት ነው፡፡ እኔንም ጣልቃ ገብቼ ሀሳቤን እንድገልጥ ያደረገኝ የኸው ነው፡፡ የአንተም ሆነ የብዙዎች የሀሳብህ ተጋሪዎች ነጥብ፣ ‹‹እውነትና ታሪክ ለምን ይደበቅ?›› የሚል አስተያየት ነው፡፡ እኔ ይህ ድርጊት ከመቸው ታሪክ እንደሆነ፣ ከመቼው ተደብቆ የመቅረቱ አደጋ ሰዎችን እንዳሳሰበ ይገርመኛል፤ ጎበዝ ገና እኮ የሀዘን ድንኳን አልፈረሰም፡፡ ታሪክን የመዘገብ፣ ትላንታችንን ቆፍሮ እውነትን መግለጥ ለሚሻ፣ የሰው ዘር መገኛ፣ የጥንታዊ ስልጣኔ ባለቤት የሆነች ሀገራችን ያሏት የታሪክ መዛግብት ቢቆጠሩ፣ በክፍለ ዘመን አንድ ወይም ሁለት ቢደርሱ ነው፡፡ ወንድሜ ዳንኤል በዚህ የተነሳ ነው ህሊናዬ፤ ‹‹ታሪክ እንዳይቀበር . . .›› የሚለውን ምክንያት አልቀበል ያለኝ፡፡

ደግሞ እንዲህ በሀዘን ስሜት ውስጥ ተሁኖ የተጻፈ ታሪክ በስሜት የመበረዝ እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ ይቅርታ አድርግልኝና ወንድሜ ዳንኤል፣ ከዚህኛው ጽሁፍህ ቀደም ብሎ፣ ‹‹ጎበዝ እየተስተዋለ እንጂ. . ›› በሚል፣ የጻፍከውን ጽሁፍ ከዚህኛው ሳስተያየው፣ ህሊናዬ ስሜታዊነትህን አግዝፎ፣ መረጃህን እንድጠራጠር ነግሮኛል፡፡ እስቲ ከቀደመው ጽሁፍህ ልጥቀስ፣

‹‹ . . . ከኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ጋር ጀማል የተባለ ሶማልያዊ ሙስሊም ክርሲቲያኖችን እረዳለሁ ብሎ፣ አብሮ ተሰውቷል የሚለውን መረጃ ለመቀበል ያስቸግራል፡፡ በመጀመሪያ ሶማልያውያንን ለጥያቄ አይቀርቧቸውም፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ጓደኞቼን ትቼ አልሄድም ስላለ፣ ና አብረሀቸው ሂድ ብሎ አስተያየት የሚያደርግ ቡድን አይደለም፡፡ በሊላ በኩል ተጓዦቹ ሲያዙ የሊቢያ ወታደሮች እንደያዝዋቸው እንጂ፣ አይኤስኤስ መሆናቸውን የሚያውቁበት እድል የለም፡፡ የለበሱትም የወታደር ልብስ ነው፡፡ . . . .በዚህ ሁሉ ነገር ጀማል ኢትዮጵያዊ ክርስትያኖችን ለመርዳት እድል የሚያገኝበት መንገድ የለም፡፡ ቢፈልግ እንኳን፡፡ . . . . እንኳን ለመታረድ አብሮ ለመቆየት እድል የለውም፡፡…››

እንግዲህ ወንድሜ ዳንኤል አንተ፣ ስለአሸባሪው ቡድን ባህሪ፣ ስለአካባቢው ሁኔታ አገናዝበህ፣ ንባብና እውቀትክ ተጠቅመህ፣ የጀማልን እውነትነት መቀበል ያስቸግራል ያልከው አስቀድመህ፣ የኤፍሬምን መረጃ ከማምጣትህ በፊት ነው፡፡ በሁለቱ ፅሁፎች መካከል ያለው ልዩነት፣ የመጀመሪያውን ጥርጣሬህና ግምትህን ሁለተኛው ላይ ኤፍሬምን መረጃ አድርገህ ለማስረገጥ መሞከርህ ነው፡፡ በነገራችን ላይ አንድ ኤፍሬም የሚባል ሰማእት መኖሩ ከጀማል ጋር እንዴት እንደሚገናኝ አልገባኝም (ዝርዝሩን የሚቀጥለውን ጥያቅ ስመልስ እመለስበታለሁ)፡፡ እና ወንድሜ ዳንኤል እውነትን ለመግለጥ የሚለውን ሀሳብህን ያልተቀበልኩት በቀደመው የግል ትንታኔህና፣ እውነት ባልከው መካከል ምንም ልዩነት ባለመኖሩም ጭምር ነው፡፡

ያልነጠረና ውሸት የሆነ ታሪክን ለምን እናቆየዋለን? በዘመናችን ለምን አናጠራውም?
እውነት ነው ውሸትን ታሪክ ብሎ ማቆየት ይቅርና እውነት ብሎ መቀበል በጎ አይደለም፡፡ ግን በዚህ ጉዳይ ላይ እውነቱ ምንድነው? የቱ ነው?እሲቲ ጉዳዩን በተጠየቅ እንፈትሸው፡፡

መነሻው፣ ‹‹ጀማል የሚባል ሙስሊም የክርሲቲያኖችን መገደል ተቃውሞ አብሮ ሞተ›› የሚለው ነው፡፡ ማፍረሻ ተደርጎ የቀረበው ሀሳብ ጀማል የሚባል ሰው የለም፤ ጀማል የተባለው ኤፍሬም ነው የሚል ነው፡፡

ተጠየቅ 1፡ ኤፍሬም የሚባለው ኤርትራዊ ሰማእት እንደምን ከጀማል ጋር ሊያያዝ ቻለ? ይህ ሊሆን የሚችልበት መንገድ ሁለት ነው፡፡ አንድ፣ የኤፍሬም ፎቶ ጀማል ነው ተብሎ ተቀምጦ ከሆነ፡፡ ሁለት፡ ለጀማል የተሰጠው ታሪክ የኤፍሬም መሆኑ ከተረጋገጠ፡፡ ኤፍሬም ክርስቲያን ነው፤ ሰማእት የሆነው እንደሁሉም ሰዎች ክርስቲያን ስለሆነ እንጂ የሌሎቹን መገደል ተቃውሞ አይደለም፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ታሪካቸው ስለማይመሳሰል ሁለተኛው ምክንያት ውድቅ ነው፡፡ ችግሩ የመጀመሪያው (የፎቶ መሳከር) ከሆነ ደግሞ፣ ይህ የሚያረጋግጠው ጀማል የተባለው ኤፍሬም መሆኑን፣ የሰማእታቱን ማንነት መለየት ላይ ችግር መፈጠሩን እንጂ፣ ጀማል የሚባል ሰው አለመኖሩን አያረጋግጥም፡፡ ስለዚህ በምንም መንገድ የኤፍሬም ማንነት መረጋገጥ የጀማልን አለመኖር አያረጋግጥም፡፡ በጀማል አለመኖር እርግጠኛ መሆን የሚቻለው የሰላሳውም ሰማእታት ማንነት ተለይቶ፣ ከመካከላቸው ጀማል የሚባል ሰው ከሌለ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ዲያቆን ዳንኤል ከጻፍከው ውስጥ እውነቱ የኤፋሬም መኖር ብቻ ነው፡፡ ገና ማንነታቸው ያልተረጋገጠ በርካታ ሰማእታት እያሉ ‹‹ጀማል የሚባል ሰው መኖሩ ውሸት ነው ብሎ መደምደም አይቻልም፡፡ ካልንም ከግምት ውጭ እውነት ሊሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ ወንድሜ ዳንኤል፣‹‹ ያልነጠረ ውሸት የሆነ ታሪክ ለምን እናቆያለን?›› ብለህ ለጠየቅከኝ መልሴ፣ የጀማል ታሪክ መቶ በመቶ ውሸት መሆኑ የሚረጋገጠው ሁሉም ሰማእታት ተለይተው ሲታወቁ ብቻ ሆኖ ሳለ ለምን አሁን እርግጠኛ ሆነህ ትናገራለህ? ችኮላው ምንድነው? የኤፍሬም ማንነት ጊዜውን ጠብቆ እንደተገለጠው፣ ሁሉም እስኪረጋገጥ መጠበቅ አይሻልም? ይህ ግን የኤፍሬምን ማንነት ስለአበሰርከን ያለኝን አድናቆት አይቀንሰውም፡፡

3 .የኢትዮጵያውያን የሙስሊሞችና ክርሲቲያኖች የፍቅርና የመግባባት ታሪክ በውሸት ላይ ለምን ይመሰረታል? ሰብአዊነትን በእውነት ላይ እንጂ በውሸት ላይ ለምን እንመሰርተዋለን?

ለዚህ የምሰጠው መልስ አጭር ነው፤ ወንድሜ ዳንኤል የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችና ክርሲቲያኖች የፍቅርና የመግባባት ታሪክ ለምን በውሸት ላይ ይመሰረታል ያልከው፣ የሁለቱን ህዝቦች የአብሮነት ታሪክ ዛሬ ‹‹ሀ›› ብለም መሰረት ልንጥልለት የተዘጋጀን ያስመስለዋል፡፡ የሁለቱ ህዝቦች ታሪክ መሰረቱን ከጣለ አይደለም፣ ጣራውን አልብሶ ካጠናቀቀ ክፍለ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ አሁን የእኛ ትውልድ በዚያ የፍቅርና መተሳሰብ ቤት ውስጥ እየኖረ ነው፡፡ እና የጀማልን ትርክት ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችና ክርሲቲያኖች የፍቅርና የመግባባት ታሪክ መሰረት አድርጎ ማሰብ፣ ከልቤ ነው የምልህ፣ እንዳንተ ከፍተኛ የሀይማኖትና ታሪክ እውቀት ካለው ሰው የመጣ መሆኑ አስገርሞኛል፡፡

ሰብአዊነትን በእውነት ላይ እንጂ በውሸት ላይ ለምን እንመሰርተዋለን? ላልከው፣ የሰብአዊነት መሰረቱ እውነት ወይም ውሸት አይደለም፡፡ የሰብአዊነት መሰረቱ ሰው ሆኖ መፈጠር ብቻ ነው፡፡

እንደ ማስገንዘቢያ፤

የሰው ልጅ ነጻነት የመጨረሻው መገለጫ ኅሊና ነው፡፡

ወንድሜ ዳንኤል፣ እንዳነበብከው በአንባቢዎቻችን ከተሰጡት አስተያየቶች እጅግ የሚበዙት ወገናዊነትን መሰረት ያደረጉ፣ ስሜታዊነት የተንጸባረቀባቸው ናቸው፡፡ ይህንን አንተም ልብ ያልከው ይመስኛል፡፡ ለካ በጎሳ፣ በፓርቲ፣ በወንዝ ብቻ ሳይሆን፣ በሀሳብም እየተቧደንን ነው፡፡ ይህንን ዝም ብዬ ማለፍ አቃተኝና ነው እዚህ ላነሳው የወደድኩት፡፡

የሰው ልጅ ነጻነት የመጨረሻው መገለጫ ኅሊና ነው፡፡ የአንድ ሀገር ዜጎች፣ የአንድ ዘር ውላጆች፣ የአንድ እናትና አባት ልጆች ልንሆን እንችላለን፡፡ በመሆኑም የሀገሩ ህግ፣ የጎሳው ልማድና ደንብ፣ የምንከተለው ሀይማኖትና የቤተሰባችን የአስተዳደግ ሁኔታ በየደረጃው ሊጫነን ይችላል፤ በዚህ ሁሉ ተጽእኖ መሀል የተለየን ነጻ ሰብአዊ ፍጡር መሆናችንን የሚያረጋግጥልን ህሊናችን ነው፡፡ ህሊናችን ነገሮችን በራሳችን መንገድ እንድንመረምር ሙሉ ነጻነት ይሰጠናል፡፡ የአንድ ሰው ሀሳብ ከሀሳባችን ጋር ሲሰምር እንደግፈዋለን፤ ሲቃረን ደግሞ ሀሳቡን በሀሳብ እንሞግታለን፡፡ አለመታደል ሆኖ እኛ በዚህ በኩል ብዙ ይቀረናል፡፡ ብዙዎቻችን የጎሳችንንና የሀይማኖታችንን ተጽእኖ አልፈን ከህሊናችን የማሰብ ነጻነት ጋር አልተገናኘንም፡፡ አሁን እኔና አንተ ውይይት ላይ እንኳን ብትመለከት፣ እኔ ያንተን ሀሳብ ስላልተቀበልኩ፣ ሙስሊምና ፕሮቴስታንት መሆኔን እርግጠኛ ሆነው ሀሳባቸውን ሳይሆን ስድባቸውን የገለጹ አሉ፡፡ የአንተንም ሃሳብ ከእስልምና ጥላቻ ጋር አያይዘው ዘለፋ የጻፉ ብዙዎች ናቸው፡፡ ለምን እንዲህ አደረጉ ማለት አይቻልም፤ ይህ በሁለት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ አንደኛው፣ ሀሳቡ ካንተ ወይም ከእኔ ሀሳብ የሰመረለት ሰው፣ ለሚቃረኑት ሀሳቦች የሚያቀርበው ስድብና ማንቋሸሽ ነው፡፡ ይህ ሰው የማያውቀው የሌላን ሰው ሀሳብን ማክበርንና ሀሳብ ላይ መሟገትን ነው፡፡ ገዢዎቹ በአንባገነንነት፣ ማህበረሰቡና ቤተሰቡ በ‹‹ተው! ይህን አታድርግ›› ሲሰድቡትና ሲያበሻቅጡት አሳድገውታልና እሱም ከሀሳብህ ተሻግሮ አንተን ይሰድብና ያበሻቅጥሀል፡፡ ይሁን እንጂ እንዲህ አይነቱ ሰው የራሱ ሀሳብ አለው፤ የቸገረው ተግባቦቱ ነው፡፡ ሁለተኛው አይነት ሰው የራሱ ሀሳብ የለውም፤ የሚያስበው እንደአንድ ነጻ ሰብአዊ ፍጡር ሳይሆን፣ በቡድን ነው፡፡ እንደ እንድ ሀገር ዜጋ፣ እንደእንድ ጎሳ አባል፣ እንደአንድ ፓርቲ አባል፣ እንደአንድ ሀይማኖት ተከታይ . . ወዘተ. ያስባል፡፡ እና በምንም መንገድ ከነዚህ ቡድኖች ፍላጎት ጋር የተቃረኑ ሀሳበችን አይቀበልም፤ እንዲያውም መደፍጠጥና ማጥፋትን ያስቀድማል፡፡ በዚህ የተነሳ ይህ ቀድሜ ከጠቀስኩት የበለጠ ለለውጥና መሻሻል እንቅፋት ይሆናል፡፡

የአንድ ማህበረሰብ ጥንካሬና እድገት ከግለሰባዊ ሰብአዊ ነጻነቱ ጋር እጅጉን የተቆራኘ ነው፡፡ የማሰብ ነጻነት ሁለንተናችንን የመመርመር ነጻነት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ብዙ የሚበጁና የማይበጁ ሀሳቦች ወደ አደባባይ ወጥተው ውይይት እንዲደረግባቸው እድል ይሰጣል፡፡ ያን ጊዜ በሰለጠነ መንገድ በሀሳብ ላይ የመወያየት ባህል ያዳበረ ማህበረሰብ፣ የሚበጀውን ሀሳብ እያዳበረ ያድጋል፤ በበጎ ይለወጣል፡፡ እንደእኛ ያለው የማሰብ ነጻነቱን ያላስከበረ፣ የመወያየት ባህሉን ያላዳበረው ደግሞ፣ አዲስ ሀሳብ ብቅ ባለ ቁጥር አሳቢውን ጭምር እየኮረኮመ ባለበት ይረግጣል፤ አንዳንዴም ይዘቅጣል፡፡ እኔ እዚህ ላይ የምለው ነገር ‹‹ሰው የለስላሳ ጠርሙስ ወይም፣ በአንድ ፋብሪካ የተመረተ የሸራ ጫማ አይደለም!›› ነው፡፡ ሰው ተመሳሳይ ሊሆን አይችልም፡፡ 80 (?) ሚሊየን ህዝብ በአንድ ወይም በሁለት ሀሳብ ላይ ይስማማ ማለት እንዴት ይቻላል? ማንም ማንንም ‹‹እንዲህ አስብ›› ሊለው አይችልም፡፡ ፈጣሪም እኮ አላደረገውም! አዳምና ሄዋንን ሲፈጥርና ‹‹አትብሉ›› ሲላቸው እንኳ ትእዛዙን እስከመጣስ የሚያደርስ ህሊናዊ ነጻነት ነበራቸው፡፡ አይገርምም! እና እባካችን ሀሳብ ላይ የመወያየት ባህላችንን እናዳብር፡፡

ቸር እንሰንብት!

The post እኔ እንዲህ አስባለሁ – [ለወንድሜ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት] – ዶክተር በድሉ ዋቅጂራ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ከአገራችን  ያሰደደንን  ወያኔን አሳደን አገር ነፃ ሆና የምንኖርበትን ዘመን እናምጣ!!!

$
0
0

samuelወያኔ ምን ሰራ ብትሉኝ ምንም ነው መልሴ ምክንያቱም እንደ መንግስት ለአንድ አገር መስራት ካለበት ደረጃ  10%  እንኳን መስራት ያልቻለ መንግስት ሰለሆነ።  በወንጀል የተዘፈቁ ባለስልጣናት፤ በሙስና  የተጨማለቁ ካድሬወችን ፈልፍሎ  በየክፈለሃገሩ በትኖ  ወንጀልኝነታቸው እንዳይታወቅ  ሙስናቸው እንዳይጋለጥ የወያኔ መንግስት የልማት የዲሞክራሲ የእድገት በማለት አሰልቺ መፍጨርጨር ውስጥ የገባው ዱኩማኑ ወያኔ  ዛሬ  ኢትዮጵያ ላለችበት ችግር ተጠያቂው በዋንነት  እርሱ መሆኑን አስረግጠን መናገር ያለብን ጌዜ ላይ ነን ኢትዮጵያ ዛሬ ትጣራለች የሰላም ያለህ እያለች ህዝቦቿ በወያኔ መፈናፈኛ በማጣቱ ሰላሙን ረግጦ  በመያዝ ነጻነቱን በመንፈግ ሰለ ነጻነት የሚናገሩትን  እና  የሚታገሉትን በሙሉ ከአገር እንዲጠፋ  በማድረግ በአገሪቱ ላይ ታላቅ ወንጀልን እየሰራ ያለ መንግስት ነው ።

በሌላ ጎኑ  ደግሞ ሰላምን እኩልነትን አምጥቻለው ሁሉም የቤሔር ቤሔረሰብ መብት የተከበረው በኛ አገዛዝ ነው ይሉናል ውሃ ቢወቅጡት እንቦጭ የሆነ ወሬ እንጂ እውነቱ ይህ አይደለም እውነቱ ምንድነው ከተባለ፦

በኢትዮጵያ ውስጥ የኢትዮጵያንን ንብረት በሙሉ የሚያንቀሳቅሱት TPLF የሚባል  ከአንድ መንደር የተሰባሰቡ  አገር በቀል አሸባሪ ቡድኖች ናቸው።  ለምን አሸባሪ እንዳልኩት ወደ ታች  እዘረዝረዋለው እነዚህ ከአንድ መንደር ከትግራይ የተሰባሰቡ ቡድኖች 90 በመቶ የአገሪቱን ንብረት እየዘረፉ እራሳቸውን እያሳደጉ ሕዝቡን እያደህዩ   መኖር የሚፈልጉ የቀን ጅቦች ናቸው።  ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ አንድም ጊዜ ሰለንብረቱ መጠን ለህዝብ ተነግሮ  የማያውቀው ኤፈረት ተብሎ በሚጠራው  የማች ጠቅላይ ሚኒስቴር ሚስት የሙስና እናት  በሆነችው አዜብ መስፍን የበላይ ሃላፊነት የሚተዳደረው  ይሄ የማፊያወች ድርጅት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በህገወጥ መንገድ ተቆጣጥሮት ይገኛል።

መሰቦ ሲሚንቶ፣ መስፍን ኢንዱስትሪያል፣ ባባ ዳይሜንሽናል ስቶን፣ ሱር ኮንስትራክሽን፣ ኤክስፕረስ ትራንዚት፣ ትራንስ ኢትዮጵያ፣ አዲስ ፋርማሲዩቲካል፣ ጉና ትሬዲንግ፣ ሂወት አግሪካልቸር፣ ሼባ ታነሪ፣ ኤክስፔሪየንስ ኢትዮጵያ፣ አልመዳ ጨርቃ ጨርቅ በቴሌ በመራት ሃይል በስኳር ፋብሪካ ወዘት.. ብቻ አጠቃላዩን የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ  ተቆጣጥረው እየዘረፉ ያሉት እነዚህ የወያኔ ጉዶች ናቸው። ይሄንን ሁሉም ኢትዮጵያዊ  ጠንቅቆ  ያወቀዋል።   እነሱ ግን  የዘረፉንን ዝርፊያ  ልማት ነው እያለማን ነው ኢትዮጵያ  እያደገች ነው ይሉናል ለምሳሌ ያህል በአዲስ አበባ ከተሰሩት ፎቆች ሙሉ ለሙሉ ሊያስብል  በሚያስችል መልኩ የአንድ ብሔረሰብ ሰወች  የገነቡት የቤተሰብ ፎቅ ነው ይሄ ነው ለነሱ ልማት።

ወያኔወች ከጫካ ይዘውት የመጡት አስተሳሰባቸው በ24 አመት ውስጥ መለወጥ ስላልቻሉ መረዳትም ሆነ ማስረዳትም አይችሉም ሰለ እውነትም አይሰሩም  አገሩን ወዳዱ የኢትዮጵያ ህዝብ   በአገሩ መኖር የሚፈልግ በስደት ላይ ሆኖ  እንኳን አገሬን የሚል ሆኖ ሳለ በግድ ከሚወዳት አገሩ ግፈኞች ነግሰውበት አሰደዱት በደለኞች እያስተዳደሩት ከፍተኛ በደል አደረሱበት በደሉንም መሸከም ሲከብደው አገሩን ጥሎ  መሰደድ ጀመረ እንግዲህ እውነት ያለው እዚህ ጋር ነው  የተገፋ ህዝብ የተበደል ህዝብ ከአገሩ ሲወጣ  በስደት መልካም ነገር ካልገጠመው ሁለተኛ  ሞት ነው። የውርደት ሞት ነው። ስለዚህ ውርደትን ማስቆም አለብን ፦

ውርደት እንዴት ይቆማል ካልን ከላይ ወያኔ አሸባሪ ነው እንዳልኩኝ  አሸባሪውን  በማስወገድ ነው። ወያኔ ኢትዮጲያውያንን የሚያሸበርበትን  ስራውን በዚህ መልኩ ያከናውናል….

1፦ዘርን ከዘር በማጋጨት የእከሌ ዘር በዳይ የእከሌ ዘር ተበዳይ አንዱ አጥፊ አንዱ ተጠፊ በማስመሰል የዘረኝነት መርዝን በኢትዮጵያ ሕዝብ መሃል በመርጨት በጥላቻ   እንዲተያዩ  በማድረግ እርስ በእርስ እንዲጫረሱ ሌት ተቀን የሚሰራ አሸባሪ ቡድን ነው።

2፦ እውነትን የሚጠላው ወያኔ የሽብር ቡድን ከምስረታው ጀምሮ  በደም የተጨማለቁ የወንጀለኞች ስብስብ ስለሆኑ እውነትን ይጠላሉ  ለኢትዮጵያን መፃኢ ተስፋ ቅን የሚያስቡትን የነፃነት አርበኞችን    እውነትኞችንና  እውነትን  ተናጋሪወችን    እያደኑ ያጠፋሉ።

3፦ የተማረን ይጠላሉ የወያኔ ባለስልጣኖች 98%  ከትምርት ነጻ ናቸው ባላቸው እውቀት የበታችነት  ሰለሚሰማቸው የተማሩ ኢትዮጵያዊያንን በማሰር፤ በመግደል፤ በማሳደድ እንደተጠመዱ ነው፡፡  ዛሬ መንግስት ማለት ከተወሰነ አካባቢ  የተውጣጣ የደንቆሮ ስብስብ የሆነ ይመስላል።

ብዙ ሰለወያኔ  ክፋት እና  ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚሰራውን ስራ ብንዘረዝረው አያልቅም  ወደ ስራ የምንገባበት ወደ ተግባር የምንለውጥበት ጊዜው አሁን ነው ።ገዳያችንን መግደል አለብን፡ አሳዳጃችንን ማሳደድ አለብን ፡በዘረኛው የወያኔ አምባገነናዊና ግፈኛ አገዛዝ እየተማረሩ ሃገራቸውን ጥለው የሚኮበልሉት ኢትዮጵያዊያን ቁጥር እጂግ በርካታ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በወገኖቻችን ላይ በሳውዲ፤ በየመን ፤በደቡብ አፍሪካን ፤በሊብያ፦ የደረሰባቸው ግድያ   ወያኔ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ  መቀጠሉ ስለማይቀር የኢትዮጵያ  ህዝብ ሆይ አንተ ኦሮሞ፤ አማራ፤ ሱማሌ ፤ ጉራጌ ፤ ሃድያ፤ ሐረሪ፤ ከንባታ ፤አፋር ፤ትግሬ፤ አንባባል ጠላት ከፊታችን ነግሶ  አሸባሪ በላያችን ተሹሞ።ወገኖቻችንን በአገራቸው ላይ  እየተገደሉ  በስደትም እየሞቱ ሰለሆነ  ሞትንን ማሸነፍ ያለብን ገዳዩን ስንገድል ነውና በአገር ተደስቶ  ለመኖር ሰርቶ ለማደግ ፍቅር አንድነት ለማምጣት ቆርጠን  ከዳር እስከዳር ሁሉም በአንድነት በመነሳት ወደየትም እንዳይፈናፈኑ አድርገን አሸባሪውን  ወያኔን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ግዜ እናጥፋ።

እምዬ  ኢትዮጵያ  የሚያስለቅሰሽ ያልቅስ ደምሽንም የሚያፈሱት ደማቸው ይፍሰስ የሚያስጨነቁሽም ይጨነቁ የሚረብሹሽም ይረበሹ ደስታሽን የሚናፍቁ ሁሉ ደስታሽን በአንድነት ይዩ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!!!!

ሳሙኤል አሊ (ከኖርዌይ) 08.05.2015

Email samilost89@yahoo.com

 

The post ከአገራችን  ያሰደደንን  ወያኔን አሳደን አገር ነፃ ሆና የምንኖርበትን ዘመን እናምጣ!!! appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live