Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

“የህወሓት 40ኛ ዓመት በዓል የጨረሻው በዓል እንዲሆን ተባብረን ሕወሓትን እንቅበር”–የአርበኞች ግንቦት 7

$
0
0

የአርበኞች ግንቦት 7 ወቅታዊ ጽሑፍ:

ድግሶችን፣ ወታደራዊ ሰልፎችንና ሀውልቶችን ማብዛት የአባገነኖች ሁሉ የጋራ ባህርይ ነው። ዘረኛውና ፋሽስቱ የህወሓት አገዛዝም በሕዝብ እየተጠላ፣ እያረጀና እየወላለቀ በሄደ መጠን በየተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ደግሶ መብላት፤ ወታደራዊ ሰልፍና የመሣሪያ ጋጋታ ማሳየት እና በየመንደሩ ሀውልት መመረቅ ሙያው አድርጎት ቆይቷል።
arbegnoch ginbot 7
የህወሓት ድግሶችና ፌሽታዎች የአገራችን ሀብት ከማሟጠጣቸውም በላይ የመንግሥት ሠራተኞችን፣ የአርሶ አደሮችንና የአነስተኛ ነጋዴዎችን ኪስ እያራቆቱ ናቸው። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች በእስር ቤቶች እየማቀቁ በሚገኙበት ሁኔታ፤ በመቶ ሺዎች የሚገመቱ የአማራ አርሶአደሮች ተፈናቅለው እያለ፤ በጋምቤላና በኦጋዴን ወገኖቻችን ላይ ዘግናኝ የጅምላ ጭፍጨፋዎች እየተደረጉ፤ በአፋር፣ በሲዳማ፣ በቦረና፣ በወልቃይት እና በመላው ኢትዮጵያ ግጭቶች በበዙበት፤ ሕዝብ እያለቀሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት “የብሔር፣ ብሔረሰቦች መብት ተከበረ” እያሉ እነዚህኑ በደል እየደረሰባቸው ያሉ ዜጎችን ማስጨፈር እና ለእነዚህ ጭፈራዎች በርካታ ሚሊዮኖች ብር ማውጣት በእጅጉ ያስቆጫል። እነዚህ ጭፈራዎች ለህወሓት ሰዎች የገቢ ምንጮች መሆናቸው ጥርጥር የለውም፤ ለድሀው ኢትዮጵያዊ ግን መራቆቻዎች ናቸው። ከዚህም አልፎ በዘረኝነት እየተበደለ ያለ ሕዝብ ስለእኩልነት ዝፈን ማለት ክብረ ነክ ተግባር ነው። ዘንድሮ በአሶሳ የተደረገው አገር አቀፍ ድግስ ካለቀ ጥቂት ወራት በኋላ አገራችን በሌላ ዙር የህወሓቶች ድግስ ተወጥራለች።

ሰሞኑን በባህር ዳር በተደረገው የጦር ሠራዊት ሰልፍ እና ሰልፉን ተከትሎ በነበረው የድግሶች ግርግር ከሁሉም በላይ የተሰደበውና የተዋረደው የሠራዊቱ አባል ነው። አዛዦቹ መቶ በመቶ የህወሓት አባላት የሆኑበትን ሠራዊት “የኢትዮጵያ መከላከያ” ተብሎ መጠራቱ ራሱ የሚያሳፍረው ኢትዮጵያዊ ወኔ በልባቸው ውስጥ እየተንቀለቀለና እልህ እየተናነቃቸው ያሉ የሠራዊቱን አባላት ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እንዴት የኢትዮጵያ ጠላቶች በሆኑ የህወሓት ካድሬዎች ይመራል? እንዴት የአስር አለቃ እንኳን ሊሆን የማይገባው የህወሓት ካድሬ “ጄኔራል” ተብሎ ኢትዮጵያዊያን ወታደሮችን እንደ ሎሌው ያዛል? እንዴት አንድ የህወሓት ሎሌ ሹመት ተሰጥቶት እየፏለለ በልምድ፣ በትምህርትና በእውቀት የሚበልጠውን ኢትዮጵያዊ ተንቆ ይዋረዳል? ይህ ቁጭትና እልህ ሠራዊቱ የዘረኛውን ህወሓት ሰልፍ አድማቂ መሆኑ የሚያከትምበት ጊዜ ይበልጥ እንዲናፍቅ የሚደረገው ነው። አልያማ ሰልፍ ያሳመረ ሠራዊት ሁሉ አሸናፊ እንዳልሆነ የታወቀ ነው። በሰልፍ ብዛትና በመሣሪያ ትዕይንት ማሸነፍ ቢቻል ኖሮ የትም አገር አምባገነኖች ባልወደቁም፤ ህወሓት ራሱን ስልጣን ላይ ባልወጣም ነበር።

የህወሓት ምሥረታ 40ኛ ዓመት ድግስም ሌላው የታሪክና የሀብት ውድመት የሚያስከትል ክስተት ነው። የካቲት 11 ቀን 1967፣ ጥቂት ኢትዮጵያዊያን እናታቸውን ኢትዮጵያን ለመግደል ያሴሩበት እና ልጆች በእናታቸው ላይ ቢላዋ የሳሉበት ዕለት በመሆኑ በሀዘንና በሱባኤ እንጂ በድግስና በጭፈራ የሚታሰብ ዕለት አይደለም። ሲነሳ ምንም ይሁን ምን ዛሬ በደረስንበት ሁኔታ ሲገመገም፣ ኢትዮጵያ በታሪኳ ውስጥ ህወሓትን የመሰለ መሠሪና አድርባይ ድርጅት ገጥሟት አያውቅም። እነሆ ዘንድሮም ይኸው አድርባይ ድርጅት የመሪዎቹን የሀብትና ዝና ረሀብ ለማስታገስ ሲል ያልነበረ ታሪክ እየፈጠረ በድግስ ስም ከድሀው ገንዘብ እየሰበሰበ ለሀብታም የህወሓት አባላትና ደጋፊዎች ያሸጋግራል። የድግሶቹ ሁሉ አዘጋጆች፣ እቃ አቅራቢዎችና ተጠቃሚዎች ራሳቸው የህወሓት መሪዎችና አሽቃባጮቻቸው ሲሆኑ ከፋዩ ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። በህወሓት ድግስ የሚባክነው የሕዝብ ሀብት ስንት ሆስፒታል ይገነባ እንደነበር ስናስብ እና ይህ ሀብት በተገቢው ቦታ ውሎ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ስም ብቻ የያዙ ዩንቨርስቲዎቻችንን ትምህርት መቅሰሚያ ማድረግ እንችል እንደነበር ስናሰላ ሀዘናችን ጥልቅ ነው። ህወሓት ለልጅ ልጆቻችን የሚተርፍ ዕዳ እየቆለለ ዳንኪራ ሲረግጥና ሲያስረግጥ ማየትና መስማት ህሊና ሊሸከመው ከሚችል በላይ ነው።

አርበኞች ግንቦት 7፡ የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በህወሓት ወታደራዊ ሰልፍ እና የመሣሪያዎች ትዕይንት የሚረበሽ ድርጅት አይደለም። ይልቁንም በሰልፉ ጨኸት የታፈነው የኢትዮጵያዊ ወታደር ጩኸት ይሰማዋል። ኢትዮጵያዊ ወታደር በአዛዦቹ ላይ ጥርሱን ነክሶ፣ ቂም አርግዞ ሰልፋቸውን እንደሚሰለፍ አርበኞች ግንቦት 7 ያውቃል። አርበኞች ግንቦት 7፣ የሠራዊቱ አባላት ውስጥ ውስጡን እየተሰቃዩ የታዘዙትን መፈፀማቸው መብቃት አለበት ይላል፤ ወይ ተቀላቀሉን፣ አሊያም እውስጡ ሆናችሁ ሥርዓቱን የማዳከም ሥራዎችን ሥሩ። በእናንተ ውርደት የዘራፊዎች፣ ሙሰኖች፣ ጎጠኞችና ዘረኞች ደረት አብጦ መታየት የለበትም።

አርበኞች ግንቦት 7፣ የዘንድሮው የህወሓት 40ኛ ዓመት በዓል የጨረሻው በዓል እንዲሆን፤ ከርሞም ተመሳሳይ አዋራጅ በዓል እንዳናከብር፤ ሠራዊቱ በዘራፊዎች ታዞ የሚሰለፍበት ውርደት እንዲያበቃ ተባብረን ህወሓትን እንቅበር ይላል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

The post “የህወሓት 40ኛ ዓመት በዓል የጨረሻው በዓል እንዲሆን ተባብረን ሕወሓትን እንቅበር” – የአርበኞች ግንቦት 7 appeared first on Zehabesha Amharic.


ብርሃኑ ተዘራ ከጃኪ ጎሲ ጋር የሠራው አነጋጋሪ ዘፈን የ1 ደቂቃ ማስታወቂያ ተለቀቀ (ይዘነዋል)

$
0
0

ባለፈው ሳምንት ዘ-ሐበሻ የላፎንቴኑ ብርሃኑ ተዘራ ከጃኪ ጎሲ ጋር በመሆን ሃገራዊ ስሜት ያለው ዘፈን መስራታቸውንና በቅርብ ቀን እንደሚለቀቅ መዘገቧ ይታወሳል:: በዚህም መሠረት ዛሬ የዚህ አነጋጋሪ ዘፈን የአንድ ደቂቃ ተቆርጦ በሶሻል ሚድያዎች ተለቋል::

ሙሉው ዘፈንን በሚቀጥለው ሳምንት በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ይጠብቁ:-

Birhanu Tezera and Jacky Gosee

The post ብርሃኑ ተዘራ ከጃኪ ጎሲ ጋር የሠራው አነጋጋሪ ዘፈን የ1 ደቂቃ ማስታወቂያ ተለቀቀ (ይዘነዋል) appeared first on Zehabesha Amharic.

ሀይለማርያም ደሳለኝ የወልቃይትን ህዝብ ለማነጋገር ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ

$
0
0

ኢሳት ዜና :-የህወሀትን 40ኛ ዓመት አክብረው ሲመለሱ እግረ መንገዳቸውን በ አማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎችን እየጎበኙ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ፤የካቲተ 16 ቀን በወልቃይት ሊያደርጉት የነበረውን ጉብኝት የህዝቡን ተቃውሞ በመፍራት መሰረዛቸው ነዋሪውን ክፉኛ አስቆጥቷል።
H Desalegn
የወልቃይት ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የካቲት 16 ቀን ወልቃይትን እንዲጎበኙ በአካባቢው ሹመኞች መነገሩን ተከትሎ በየገጠር የሚኖረው ህዝብ ሳይቀር በመሰባሰብ እና ምሳ በማሰናዳት ሲጠባበቃቸው ቢውልም የውሀ ሽታ ሆነው ቀርተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩን በአካል አግኝቶ የአስተዳደራዊ በደል ጥያቄውን ለማቅረብ ከ8 ሺህ በላይ ህዝብ ተሰባስቦ እንደነበር የገለጹት የነዋሪዎቹ አስተባባሪዎች፤ ህዝቡ ተቃውሞውን ለመግለጽና ጥያቄ ለማቅረብ እንደተዘጋጀ የተረዱት የአካባቢው ሹመኞች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ወልቃይት እንዳይገቡ አድርገው ቅጠታ ወደ ደጀና እንደወሰዷቸው ተናግረዋል።

ይህ በመሆኑም ተሰባስቦ ሲጠባበቅ የነበረው ህዝብ በቁጣና በብስጭት ወደ ቤቱ መመለሱን የገለጹት አስተባባሪዎቹ፤ ንዴታቸውን መቆጣጠር የተሳናቸው የአካባቢው ወጣቶችም በአደባባይ የህወሀትን ባንዲራ በማቃጠል የዚያኑ እለት ለትግል ወደ በረሀ መውጣታቸውን ተናግረዋል።
ቀርቦ በማናገር እንጂ ከህዝብ በመደበቅ ወይም በመሸሽ ከችግር መሸሽ እንደማይቻል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሊረዱት ይገባል ያሉት ነዋሪዎቹ፤ አንድ የሀገር መሪ- ከህዝብ ጋር የዚህ ዓይነት ድብብቆሽ ጨዋታ ውስጥ መግባቱ እጅግ እንዳሳፈራቸውም ገልጸዋል።

> የሚሉት ወልቃይቶች፤ ፡>በማለት አስጠንቅቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የወልቃይት ህዝብ ላለማየት ተራምደውት ያለፉት አቶ ሀይለማርያም ትናንት ምሽት ከ አቶ አርከበ እቁባይና ከአማራ ክልል ርእሰ-መስተዳድር ከ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር በመሆን ኮምቦልቻ ከተማ መግባታቸው ታውቋል።

ዛሬ ጧት የኮምቦልቻ ከተማ ተማሪዎች – ለአቶ ሀይለማርያም አቀባበል ለማድረግ በሚል ከትምህርት ገበታቸው በግዳጅ መወሰዳቸውን የገለጹት ምንጮችን የከተማውም ነዋሪ በተመሳሳይ መንገድ ለ አቀባበል ተብሎ በግዳጅ እንዲወጣ መደረጉን ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማለዳ ላይ የዛሬ ዓመት የተመረቀውን የ ኮምቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ እንደ አዲስ እንዲመርቁ ከተደረገ በሁዋላ ለአዋሽ-ኮምቦልቻ የባቡር ሀዲድ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጣቸውን የገለጹት ምንጮቹ፤ የመሰረት ድንጋይ የማኖር ፕሮግራሙ የተካሄደውም የሽህ መሀመድ ሁሴን አል አሙዲ የቆርቆሮ ፋብሪካ አጠገብ በተጣለ ዳስ ውስጥ እንደነበር አመልክተዋል።

ወደ ዳሱ እንዲገቡ የታደሙት > የሚል መግቢያ ባጅ የተሰጣቸው የኢህአዴግ ካድሬዎች ብቻ መሆናቸውን የጠቀሱት ምንጮቹ፤ ይሁንና ከነበረው እጅግ ጥብቅ ፍተሻ አኳያ፤ ተጋባዦቹ የኢህአዴግ አባላት ሳይሆን አደገኛ ጠላት ነበር የሚመስሉት ብለዋል።

አቶ ሀይለማርያም የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጣቸውን ተከትሎ “ኢህአዴግን ምረጡ” የሚል ቅስቀሳ መደረጉን የጠቀሱት ምንጮች፤ የመሰረት ድንጋይ ሊጥሉ መጡ የተባለውም ሆነ ከአመት በፊት የተመረቀን አውሮፕላን ማረፊያ እንደ አዲስ እንዲመርቁ የተደረገውም ለምርጫው ህዝቡን ለማታለል እንደሆነ በደንብ ገብቶናል”ብለዋል።

የምንልሰውና የምንቀምሰው ባጣንበት ወቅት በባቡር ፕሮፓጋንዳ ሊያታልሉን አይችሉም ያሉት ነዋሪዎቹ፤ በትራንስፖርትም ረገድ ቀደም ሲል 1 ብር የነበረው የታክሲ ታሪፍ እስከ 3 ብር፣ 2 ብር የነበረው እስከ 6 ብር ደርሶ ህዝቡ እየተማረረ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

The post ሀይለማርያም ደሳለኝ የወልቃይትን ህዝብ ለማነጋገር ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከአንድነት ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበርና ከሰማያዊ ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበር የተሰጠ የጋራ መግለጫ

$
0
0

ANAASO Blueእንደሚታወቀው የኢህአዴግ አገዛዝ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጸረ ዲሞክራሲ አካሄዱ እየባሰበት የመጣና መሠረታዊ መብቶችን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ማፈኑን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡ በቅርቡ በአንድነትና በመኢአድ ፓርቲ ላይ አገዛዙ በሚያዝዛቸው የተቋማት ኃላፊዎች ቀጭን ትዕዛዝ የፓርቲዎቹ ሕልውና ለጥቂት ግለሰቦች ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡ ይህ ዓይነቱ ህገ-ወጥ ድርጊት መቼዉም ቢሆን ተቀባይነት አይኖረውም! ለአገራችን የሠላማዊ የስልጣን ሽግግር ከባድ መሠናክል ሊሆን እንደሚችል ሁሉም ይገነዘባል ብለን እናምናለን፡፡ የኢህአዴግ የምርጫ ቦርድ እንዲህ ዓይነቱን ክፉ ስራ ሲወስን የአገራችንን የረጅም ሠላም አይተው ሣይሆን በአገዛዙ ቁንጮ ሰዎች በመታዘዝ በተቋም ስም የሚሠሩት የማደናገር የድንቁርና ተግባራቸዉ አንድ አካል ነው ብለን እናምናለን፡፡ ማህበራችን ይህን ድርጊት እጅጉን ያወግዛል። በመሆኑም ድርጊቱን በጋራ እንቃወማለን።

በምርጫ ቦርድ ስም የተወሰነው ህገ-ወጥ ውሣኔ ምክንያት መላ የአንድነትና የመኢአድ አባላት የፖለቲካ እንቅስቃሴአቸው ተገድቧል፡፡ ይሁን እንጂ ለአገራቸው ካላቸው ፅኑ ፍቅር አኳያ ትግሉን ለማስቀጠል ከሠማያዊ ፓርቲ ጋር አብሮ ለመሥራት የአባልነት ፎርም በመሙላት ትግሉን ቀጥለዋል፡፡ ይህ ዓይነቱ የአባላት ቆራጥ ውሣኔ ሊበረታታና ሞራል ሊሰጠው የሚገባ ነው ብለን እናምናለን! እኛም በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የሁለቱ የድጋፍ ማህበራት ሙሉ በሙሉ ድጋፋችንን እንደምንሰጥ እናረጋግጣለን፡፡

ስለሆነም በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የአንድነትና የሠማያዊ የድጋፍ ማህበራት በጋራ በኮሜቴ ደረጃ ተዋቅረን በዋና ዋና ጉዳዬች ላይ ማለትም በፋይናንስ፤ በእስረኞች ጉዳይ እና በዲኘሎማሲው ዙሪያ ሙሉ በሙሉ በትብብር አብረን እየሠራን የሰማያዊ ፓርቲንና ሌሎች በሃገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን በጋራ ድጋፍ ለመስጠት ውሣኔ አሣልፈናል፡፡ በቀጣይም በጋራ የኮሚቴ ውይይቶችን እያደረግን ለሰማያዊ ፓርቲ የሚያስፈልጉ የሞራልና የማቴሪያል ርዳታ እንደምንሰጥ እናረጋግጣለን፡፡
የሰማያዊና የአንድነት ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበራት
የካቲት 19 2007 ዓ/ም

The post ከአንድነት ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበርና ከሰማያዊ ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበር የተሰጠ የጋራ መግለጫ appeared first on Zehabesha Amharic.

ለአንድ ቀን የሚቆይ የቦይኮት ዘመቻ በድምፃችን ይሰማ ጥሪ ቀረበ

$
0
0
10920943_352316331618819_5078649879608517565_n‹‹እስር ከትግላችን አያስቆመንም!›› – ለአንድ ቀን የሚቆይ የቦይኮት ዘመቻ
ነገ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከምሽቱ 12 ሰዓት ስልካችንን እናጠፋለን!
መንግስት ሙስሊሞችን ከያሉበት በማሰር ህገ ወጥ ዘመቻ ላይ መሰማራቱን እና በህዝበ ሙስሊሙ ላይ ግፍ መፈጸሙን በመቃወም ነገ ጁሙዓ ታላቅ አገር አቀፍ ተቃውሞ እንደሚኖረን እና በዛሬው እለትም የተቃውሞው መርሃ ግብር ይፋ እንደሚሆን መገለጹ ይታወሳል፡፡በዚሁ መሰረት እነሆ የነገው አገር አቀፍ ተቃውሟችን በመጠነኛ የቦይኮት ዘመቻ (የራስን መብት በራስ ላይ የመንፈግ ተቃውሞ) የሚጀመር ይሆናል፡፡ኢትዮ ቴሌኮም ለመንግስት ከፍተኛ ትርፍ ከሚያስገኙ ካምፓኒዎች አንዱ ሲሆን
በቀን ከተጠቃሚዎች በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ገቢ ያገኛል፡፡ ሙስሊሙ
ማህበረሰብ ደግሞ የአገሪቱ ግማሽ እንደመሆኑ መጠን በአንድ ቀን ለቴሌ
የሚያስገኘው ገቢ እንዲሁ በሚሊዮን የሚቆጠር ነው፡፡ በመሆኑም የማይናቅ
ቁጥር ካለው ማህበረሰብ የሚያጣው የአንድ ቀን ገቢ ለኢትዮ ቴሌኮም
በሚሊዮን የሚቆጠር ብር አክሳሪ መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ የነገው
ቦይኮት በኢቲዮ ቴሌኮም ካምፓኒ ላይ የሚያተኩረውም ለዚህ ነው፡፡
ነገ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ ሁላችንም ስልካችንን
በመዝጋት ተቃውሟችንን እናሰማለን፡፡ አስቸኳይ ጉዳይ ካላጋጠመን በስተቀርም
ስልካችንን አንከፍትም፤ አንጠቀምምም፡፡

አስቸኳይ ጉዳይ ሲያጋጥመን ለአፍታ ስልካችንን በመክፈት ቶሎ ጉዳያችንን ፈጽመን ወዲያው እንዘጋለን፡፡
ይህንን አገር አቀፍ እና መላ አገሪቱን ያካለለ ዘመቻ ላልሰሙት ሁሉ በማሰማት ለስኬቱ የቻልነውን ሁሉ መጣር ታላቅ ተግባር ሲሆን ለዲናችን ስንል ለምንከፍለው
መስዋእትነትም ከጌታችን አላህ ዘንድ ምንዳችንን እንተሳሰባለን፡፡ አላህ ፈተናውን
እንዲያነሳልንም አጥብቀን ዱዓ እናደርጋለን፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ
አይደለምና!!!

አዎን! አንድነት ያለው ህዝብ ያሸንፋል!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!

ድምጻችን ይሰማ!

The post ለአንድ ቀን የሚቆይ የቦይኮት ዘመቻ በድምፃችን ይሰማ ጥሪ ቀረበ appeared first on Zehabesha Amharic.

የመለስ ትሩፋቶች ደራሲ ኤርሚያስ ለገሰ ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት የጻፈው ግልጽ ደብዳቤ

$
0
0

ከአንድ ሰአት በላይ የፈጀውን ጥናታዊ ጵሁፍህን ሰማሁት። ሰምቼ ስጨርስ ደነገጥኩ። ከራሴም ጋር ለሰአታት ሙግት ገጠምኩ ። ኢህአዴግን ለቅቄ የወጣሁት ልቤ የፈቀደውን በነጳነት ለመናገር ነውና የማውቀውን እና የሚሰማኝን መናገር እንዳለብኝ ተሰማኝ ። ርግጥ በሐይማኖት ጉዳዬች ላይ መናገር ከባድ እንደሆነና ዋጋ እንደሚያስከፍል ጠንቅቄ አውቃለሁ ። በሌላ በኩል የሚያውቁትን አለመግለጵም የፀፀት ዋጋ አለው። በመሆኑም ባለመናገሬ ከሚሰማኝ ሙግት መናገሩን ስለመረጥኩ የሚከተለውን አጭር አስተያየት ለመስጠት ተገደድኩ።
1• ያቀረብከውን መረጃዎች እንዴት እንዳሰባሰብካቸው የተገለፀ ነገር የለም። በተለይም በድህረና ቅድመ ምርጫ 97 ባሉት ሶስት አመታት( ከኃላም ከፊትም) ያቀረብካቸውን መረጃዎች ምንጭ ማወቅ እፈልጋለሁ ። ይህን ጥያቄ የማነሳበት መሰረታዊ ምክንያቶች ስላሉኝ ነው።
daniel kibret
1•1• በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2001 አ• ም• ኢሕአዴግ ለሕዝቡ ይዞለት የመጣው እቅድ ” በአክራሪነት ” ስም ሀይማኖቶችን ማዳከም ነበር። ይህንንም ለማቀጣጠል እንዲረዳው በኢህአዴግ ቢሮ፣ በኮሙዩኒኬሽን ጵ/ ቤት፣ ፌደራል ጉዳዬች እና ፌደራል ፓሊስ መረጃ እንዲሰባሰቡ ተደረገ። የእስልምና ጉዳዬች ላይ ዝርዝር ጥናቱን እንዲሰራ የቤትስራ የተሰጠው ሽመልስ ከማል ነበር። ዛሬ አንተ ካቀረብክልን ውስጥ ግማሹ የቃላት ለውጥ እንኳን ሳይደረግለት በሽመልስ ከማል ጥናታዊ ፅሁፍ የቀረበ ነበር። በወቅቱ እጅግ ከመደንገጤ የተነሳ ሽመልስ እንዴት እንዲህ አይነት ጥናት እንደሰራ ለማወቅ ከጀርባው መጓዝ ነበረብኝ ። መጓዜ ያልጠበኩትን ውጤት አመጣ። ሽመልስ በእስልምና ላይ ከፍተኛ ጥላቻ የያዘው በቤተሰቡ ውስጥ በተፈጠረው ምስቅልቅል እድገት መሆኑን ተገነዘብኩ። አባቱ በአንድ ወቅት የመስኪድ አስተዳደር ነበሩ። በኃላ የሳውዲ ጉዞ አድርገው ሲመለሱ አስተዳደሩን በመነጠቃቸው ከሀይማኖቱ በተቃራኒ ተሰለፋ ። ” ከመካ መዲና ደርሶ መልስ” የሚል መጵሀፍ አሳትመው ክርስትና ተነሱ። ስማቸውም ወደ ሀይለየሱስ ተቀየረ። ባስታወቀው እርምጃ ቤታቸው ተመሰቃቀለ።ወንድማማች እና እህታማቾች የሚጠሩበት የአባት ስም እስከ መለያየት ደረሰ። ባጭሩ የሽመልስ ፀረ -እስላም የመሆን ምንጩ ይሄ ነው። በመሆኑም በሽመልስ ሲቀርቡ የነበሩ ዳታዎችና ትንታኔዎች እንደወረዱ ከአንተ ሲቀርቡ ስሰማ የመረጃ ምንጭህን ተጠራጠርኩ። በተለይ ቴኳንዶ ፣አክሱም፣ መያዶች …ወዘተ ብለህ የገለጵከው የካርቦን ግልባጭ ሆኖ አግኝቸዋለሁ።

1•2• ሌላኛው ዳታ የሰበሰበው የፌደራል ጉዳዬች ሚኒስተር የነበረው ዶክተር ሽፈራው ከፓሊስ ጋር በመሆን ነበር። ዶክተሩ ያጠናቀረው መረጃ ተመሳሳይ ሲሆን በማጠቃለያው ” የኦርቶዶክስ አክራሪነት አለ” የሚል ነበር። የአክራሪነቱ አስኳል ማህበረ ቅዱሳን እንደሆነ አፅንኦት ሰጥቶበት ነበር። ይህ የዶክተሩ መረጃ በአንተ ጥናታዊ ፅሁፍ ላይ አልቀረበም ።
( ግምቴን አስቀምጬ ለማለፍ ይህን የዶክተር ሽፈራው ዳታና ትንታኔ ለሌላ የእስልምና መምህር እንዲደርሰው ይደረግና እንደአንተ እንዲያቀርብ ይደረጋል ። ርዕሱንም ” የኦርቶዶክስ አክራሪነት ” ብሎ እንዲጠራው ይደረጋል ።)

2• የመረጃዎቹ ምንጭ እንደተጠበቀ ሆኖ ኩነቶቹ ሲፈጠሩ ሀገሪቷ የነበረችበትን ፓለቲካዊ ሁኔታ ከግምት አላስገባህም። ለምሳሌ ከምርጫ 97 በኃላ በኦሮሚያ የተከሰቱት የሐይማኖት ግጭቶች የተጠነሰሱት በአቶ መለስና ደህንነት ጵ/ ቤት ሲሆን ዋነኛ አሰፈጳሚዎቹ እነ አባዱላና የኦህዴድ ካድሬዎች ነበሩ። ” ቅንጅት የክርስቲያን ጠበቃ ነው” የሚለው መልእክት የተቀረፀው አንተ በጥናታዊ ጵሁፍህ ላይ ” ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል” የሚለው መርሆ አቀንቃኝ የሆነው አቶ በረከት ነው። በየጉራንጉሩ መልእክቱን ያሰራጩት ደግሞ ” እኔ ከሞትኩ… ” በሚለው ብሂል እነ አባዱላና ጁነዲን ናቸው። በተለይ በድሬደዋ የጠነሰሱት ሴራ ባይከሽፍ ኖሮ ዘግናኝ እልቂት ይከሰት ነበር። በመሆኑም ከምርጫ 97 በኃላ የተከሰቱት ግጭቶች ( በተለይ በኦሮሚያ) ጠንሳሾቹ አሁን እየመሩን ያሉት ፓለቲከኞች ሲሆኑ መንስኤውም ፓለቲካው የፈጠረው ነበር። አንተ ግን በየትኛው ቦታ ላይ የፓለቲከኞቹን ሚና ማንሳት አልፈለክም ። ይልቁንስ መንግስት አበረደው፣ መከላከያ አረገበው ማለትን መርጠሀል። ጥናትህን ሰፋ ብታደርገው ኢትየጵያ ውስጥ አክራሪነት በዋነኛነት እየሰፋ የሄደው በፓለቲካው መበላሸት ምክንያት የተፈጠረ መሆኑን ትደርስበት ነበር። አሁንማ በድጋሚ ለማየት ጊዜው አልረፈደም።
ermias copy
3• በጥናታዊ ጵሁፍህ ላይ በአሁን ሰአት ያለውን የኢትየጵያ ሙስሊሞች ” ኢትዬጲያዊነት የተላበሰ፣ ሰላማዊና ፍትሐዊ ጥያቄ” ማንሳት አልፈለክም ። እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተቃወሙት የመንግስት ጣልቃ ገብነት ነው።ኢህአዴግ ከሀይማኖቱ ላይ እጁን እንዲያነሳ ነው በሰላማዊ መንገድ እየጠየቁ ያሉት። አመራራችን በእኛ ይመረጡ፣ ተቋማችንን ራሳችን እናስተዳድር የሚል ነው። ለዚህ ደግሞ እኔ በየትኛውም ቦታና ሰአት ምስክር መሆን እችላለሁ። ታዲያ አክራሪን፣ አክራሪ ካልሆነው ለይቶ የማስረዳት አላማ ካነገብክ ለምን ፍትሐዊ የሆነውን ይህን ጥያቄ ሳታነሳ ቀረህ? እንደ ገዥዎቻችን ” የሙስሊሙ ጥያቄ አክራሪነት የወለደው ነው” የምትለን ከሆነም ወደ መድረክ አውጣውና እንነጋገርበት ።

4• አጀንዳህ ስለ ” ሙስሊም አክራሪነት ” ሆኖ ወደ ማጠቃለያህ ላይ በውጭ ሀገር ያለውን ሲኖዶስ ወደ መዝለፍ ለምን ተሸጋገርክ። ከአንደበትህ የወጣው ቃል ” የሐሰት ሲኖዶስ ተቋቁሞ መንጋ የማይጠብቅ ጳጳሳት ይሾማል ” የሚል ነው። ይህ ንግግር በራሱ አንድነት የሚያመጣ ነው? ውጭ ያለው ሲኖዶስ የሐሰት ነው / አይደለም ከሚለው ትርክት በፊት ይህ እንዲፈጠር ያደረገው ምክንያት ምንድነው የሚለውን ብታነሳ የተሻለ መልስ ታገኝ እንደነበር እገምታለሁ። ሐገር ቤት ያለውን ሲኖዶስ ማን ከጀርባ ሆኖ እንደሚያሽከረክረው ካላወክ በኢትዮጵያ ምህዳር ላይ መኖርህን እንድጠራጠር ያደርገኛል።

4• ሌላኛው ” ለምን አሁን?፣ ምን አዲስ ነገር አለ?” የሚል ጥያቄ እንዳነሳ አድርጐኛል ። የሙስሊሞች ሰላማዊ ትግል በተጠናከረበት፣ መንግስት በጅምላ ማሰር በጀመረበት ፣ ማህበረ ቅዱሳን ላይ በተዛተበት ወቅት ለምን የሚከፋፍል አጀንዳ ይዞ ብቅ ማለት ተፈለገ? የማን አጀንዳ ነው እየተራመደ ያለው የሚለውን ማየት ተገቢ ይሆናል
Ermias Legess / የ መለስ ትሩፋቶች/

The post የመለስ ትሩፋቶች ደራሲ ኤርሚያስ ለገሰ ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት የጻፈው ግልጽ ደብዳቤ appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: የማይግሬን ራስምታትን ለማስታገስ የሚጠቅሙ 6 ሁኔታዎች

$
0
0

Migrin
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር )

የማይግሬን ራስምታት በሚነሳበት ጊዜ ህመሙን ለማስታገስ የሚጠቅሙ ሁኔታዎችን እገልጽላችኋለሁ፡፡
1. የተረጋጋ እና ፀጥ ያለ ቦታ ይምረጡ
✔ በአካባቢዎ የሚገኝ መብራት ማጥፋት እና ከተቻለ እንቅልፍ መተኛት፣
✔ የሞቀ ወይንም የቀዘቀዘ ውኃን በላስቲክ በማድረግ በእራስዎ እና በአንገትዎ ላይ ማስቀመጥ፣ ይህ ማለት ደግሞ
• ቅዝቃዜው በማደንዘዝ ሕመም እንዳይሰማዎ ሲያደርግ ሙቀቱ ደግሞ የራስና የአንገት ጡንቻዎችን እንዲፈታቱ ያደርጋል
• ሕመም የሚሰማዎ ቦታ ላይ በቀላሉ ማሸት አንገትዎን እና ትከሻዎን ማሸት
✔ ገላዎን በሙቅ ውሀ መታጠብ
2. በቂ እረፍት ማድረግ
✔ መደበኛ የእንቅልፍ ሰዓት ይኑርዎ
✔ ሁሌም በተመሳሳይ ሰዓት የመተኛት ልምድ ያዳብሩ
✔ በቀን እንቅልፍ መተኛት ያስለመዱ ከሆነ ከ20-30 ደቂቃ ብቻ ቢሆን ይመከራል። ከዛ በላይ እንቅልፍ ከወሰዱ የለሊት እንቅልፍዎን ሊያዛባ ይችላል
✔ እንቅልፍዎ ያልመጣ ከሆነ እራስዎን አያስገድዱ መጽሐፍ በማንበብ ራስዎን ያድክሙ
3. አመጋገብዎን ያስተካክሉ
✔ መደበኛ የሆነ የምግብ ሰዓት ይኑርዎ
✔ ቁርስዎን መመገብ አይዘንጉ
✔ ማይግሬን ቀስቃሽ የሆኑ ምግቦችን ያስወግዱ (እንደ ቼኮሌት፣አይብ፣ቡና እና የአልኮል መጠጦች)
4. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የማይግሬን ራስ ምታትን ይቀሰቅሳል ነገር ግን ሐኪምዎን በማማከር ቀለል ያሉ እንቅስቃሴዎችን ያድርጉ
(ለምሳሌ እንደ ውሃ ዋና፤የእግር ጉዞ የመሳሰሉትን ማድረግ ይችላሉ)
5.ጭንቀትዎን ይቆጣጠሩ
ጭንቀት የማይግሬን ራስ ምታትን ይቀሰቅሳል፡፡ በዕለት ተዕለት የኑሮ ሁኔታዎች የሚያጋጥሙንን አስጨናቂ ነገሮች መከላከል ባይቻልም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በመፈፀም መቀነስ ይችላሉ።
✔ ቀለል ያለ የኑሮ ዘይቤ ይኑርዎ
✔ ጊዜዎን በአግባቡ ይጠቀሙ
✔ የዕረፍት ጊዜ ይኑርዎ
✔ ለነገሮች በጎ አመለካከት ይኑርዎ
✔ ራስዎን ዘና ያድርጉ
6. የራስ ምታትዎን በተመለከተ የግል ማኅደር ይኑርዎ
✔ በግል ማኅደር መመዝገብ ራስምታትዎን የሚያስነሳውን ሁኔታ ለማወቅ እና ምን እንደሚያስታግስልዎም ለማጤን ይረዳል፡፡
ጤና ይስጥልኝ

The post Health: የማይግሬን ራስምታትን ለማስታገስ የሚጠቅሙ 6 ሁኔታዎች appeared first on Zehabesha Amharic.

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ISIS በአራት ኪሎ ቤተ መንግስት የተቀመጠው ህወሃት/ኢህአዴግ ነው

$
0
0

Muslim in ethiopia
ከዳዊት ሰለሞን (ጋዜጠኛ)

ኢትዮጵያዊያኑ የእስልምና እምነት ተከታዬች ፍጹም ጨዋዎች መሆናቸውን ለመመልከት ላለፉት ሶስት ዓመታት በአገሪቱ ያደረጓቸውን ሰላማዊ ተቃውሞዎች መታዘብ ይበቃል፡፡ሺህዎች በታደሙባቸው ተቃውሞዎች አማንያኑ የሚጤስ ጧፍን ሳያጠፉ ቅጥቅጥ ሸንበቆ ሳይሰብሩ ወደየቤታቸው ተመልሰዋል፡፡

እነዚሁ ሙስሊሞች ፓርቲዎች በጠሯቸው ሰላማዊ ሰልፎች (አንድነትና ሰማያዊ) በመገኘት አቡበከር እንዲፈታ የጠየቁትን ያህል እስክንድር ነጋ፣ርዕዮት ዓለሙ፣አንዷለም አራጌና ሌሎችም ነጻነታቸውን እንዲያገኙ ጠይቀዋል፡፡
በአንጻሩ ስርዓቱ ISISዊ ተግባሩን በወታደሮቹ በኩል በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡እነ ጋዜጠኛ የሱፍና ሰለሞን በማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ የተፈጸመባቸው ማሰቃየት ፣በኮፈሌ፣ደሴ፣በአዲስ አበባና በሌሎች ስፍራዎች አይ ኤስ አይ ኤስ (ፌደራል ፖሊስ) በወሰደው ጭፍን እርምጃ ብዙዎች ደማቸው ፈሶ ይህችን ዓለም ተለይተዋል፡፡ይህ ድርጊት መንግስታዊው ISIS የፈጸመው ከማለት ውጪ ምን ሊሰኝ ይችላል ?

ሽብርተኛው ቡድን ያርዳል፣ያሰቃያል፣ሰብዓዊ ክብርን ያዋርዳል ፡፡ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ይሀንን አጥብቀው ይቃወማሉ፡፡ነገር ግን በመንግስታዊው ሽብርተኛ ቡድን ይታሰራሉ፣ባልዋሉበት በኢትዮጵያ እስላማዊ መንግስት ለመመሰረት አሲረናል በሉ ተብለው እንዲፈርሙ ይደረጋሉ፣ውሃ የተሞሉ ላስቲኮች ብልታቸው ላይ ተንጠልጥሎ፣እግራቸው ተገልብጦ ይገረፋሉ፣በአፍጋኒስታን፣በኢራቅ ፣በሶማሊያ ስልጠና ወስደናል እንዲሉ ይገደዳሉ፣መንግስት የለም ወይ በማለታቸው ብቻ በአደባባይ ይረገጣሉ፣በጥይት ይመታሉ፣መንግስት በሚቆጣጠረው ሚዲያ ሹማምንት ቀርበው ‹‹ሽብርተኞች ፣ክርስቲያኖችን ለማጥፋት የተላኩ የጥፋት መልእክተኞች ይባላሉ፣ጥናት አቀረብን የሚሉ የሌላ ሐይማኖት መምህራን ኢትዮጵያዊያኑ ሙስሊሞች እየደረሰባቸው የሚገኘውን የመብት ጥሰት ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ‹‹አክራሪዎች ››ይሏቸዋል፡፡

እውነት ብትቀጥንም ፈጽማ የማትጠፋ መሆኗ ግን የትግል ተስፋ ነው የሚለው ማን ነበር?

The post የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ISIS በአራት ኪሎ ቤተ መንግስት የተቀመጠው ህወሃት/ኢህአዴግ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.


ወያኔ ታሪክ ሰሪ ነው ወይስ ታሪክ አጥፊ? –ከ-ሳሙኤል አሊ

$
0
0

samuelኢትዮጵያ ላይ መጭው ትውልድ ይቅር የማይለው  የታሪክ ሰህተት  እየስራ ያለው የትግራይ ነጻ አውጭ ነኝ ብሎ በኢትዮጵያ  ምድር  ስልጣን ላይ ያለው የወነበዴ ግሩፕ  እንደሆነ  የታወቀ ነው።እዚህ ጋር በትንሹ  እንደ  ጠቋሚነት መጥቀስ የምፈልገው እና አንባበውም ሊያሳድገው  የምፈልገው ነጥብን  ነው።

ኢትዮጵያ  ረጅም እድሜ  ያላት የታሪክ አገር፣ የፍቅር አገር፣ አብሮ ተቻችሎ የሚኖርባት  አገር፣ናት።  ወያኔ ግን ይህቺን ባለብዙ ታሪካዊ አገርን ሙሉ በሙሉ አፍርሶታል። ያለውን እውነት ትንሽ ወደሃላ ሄደን እንመልከት

ኢትዮጵያ ታረክ ያላት አገር ናት። ይንን ስንል የሰው መገኛ እንደሆነች ታሪክ የሚነግርላት የነድንቅነ ሽ(ሉሲ) መገኛ፣ የጥንት  አብያተ ክርስትያናትና ጥንታዊ መስጊዶች ያሉባት አገር፣ ክርስትና እና እስልምናው ተፋቅረው ተጋብተው ተዋልደው የሚኖሩባት ታሪካዊ ፊቅራዊም  አገር ነች። ለአለም በሙሉ ምሳሌ መሆን የምትችል የፍቅር ተምሳሌት የውቦች አገር እንደሆነች ታሪክን ወደሃላ አገላብጦ ማየት እና የስውን አኗኗር መቃኝት በቂ ነው። ለዚህም ታሪክነን ስንቃኝ  ኢትዮጵያዊ ንጉስ አርማህ በአረቦች አገላለጽ ንጉስ ነጃሺ የሚባሉት በዛ ዘመን ንጉስ አርማህ ሙስሊም ስደተኞችን ተቀብሎ አገራቸው ሰላም እስኪሆን ድረስ ያለምንም ችግር እንዲኖሩ አድርጎ  መጠለያ  የሰጠ የአለማችን ቀዳሚ መንግስት እንደሆነ  ታሪክ ይነግረናል። ንጉስ አርማህ   የክርስትና እምነት ተከታይ ቢሆንም  ከሳውዲ የመጡትን የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑትን ያለምንም ችግር በእምነታቸው ሳያገላቸው  በዚህም በንኖርባት  አለማችን ላይ ስደተኞችን በመቀበል  የመጀመርያ አገር ያደርጋታል። ይህ የሆነው በ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ ነው። ሌላው ደሞ አብሮ ተቻችሎ እና ተዋደው የሚኖሩባት አገር ነች።82 የተለያዩ ብሔር ያለባት አገር ብትሆንም  የዘር ልዩነት ሳይኖር በኢትዮጵያዊነቱ ብቻ ዘር ሳይጠይቅ ተጋብተው በፍቅር የሚኖሩባት አገር የነበረች ነች ሌላው ቀርቶ ሃይማኖትም ሳይለያችው ተዋልደው ተፋቅረው የሚኖሩባት አገር ኢትዮጵያ መሆኗን ታሪክ የዘገበው አሁንም ያለ እውነታ ነው። ለዚህም እረጅም ግዜዎችን በፍቅር አሳልፋለች ኢትዮጵያን የመቻቻልና የፍቅር ተምሳሌት የምትደረገው ያለ ምክንይት አይደለም። ዛሬ ዛሬ የምናየው ግን በጣም የሚገርምና የሚደንቅ  የሚያሳዝንም ነው።  የምን ጉድም እንደመጣብን አናውቅም የኢትዮጵያ ታሪክ ጀማሪ ወያኔ እስክመስለው ድረስ ኢትዮጵያዊነትን እንዲረሳ የሚያደርጉት  እንቅስቃሴ በጣም የሚደንቅ ነው።

ቅዱስ ያሬድ የበቀለባት ምድር ፈላስፋው ዘረያቆብ የተገኘባት ምድር ዛሬ እነዚህን ወያኔ የሚባል ጉዶችን ታውጣ።  በለስ ኩርንችትን  ሲያፈራ አላየንም ነበር… አሁን ግን በለስ ኩርንችትን አፍርቶ አየነው። እነዚህን ኩርንችቶች ደግሞ የራሳቸውን ባንዲራ እየለበሱ በተለያየ መድረኩ ላይ ለብሰውት ሲጨፍሩ ይታያሉ። የኢትዮጵያ  ባንዲራ ጥለው ቢጫና  ቀይን ባለኮኮቧን መልበስና ማውለብለብ  እየፈለጉ እንደመጡ የሚያሳዩ ነገሮች እየታዪ  ነው።  ቢጫውም  ፍጥነትህን ቀንስ ቀዩ ደሞ ቁም የሚል መልዕክት እንዳለው አልተገነዘቡ ይሆን? ዝም ብለው  ቀይና ቢጫ ባለኮኮቧን የወያኔ ባንዲራ ለብስው የሚዘሉብን። ሰው ልቦናው ካልመለስው  እና ካላስቆመው በሌላ ሃይል መቆም እንደሚቻል አልተረዱ ከሆነ የግድ ቀን ሲመጣ የኢትዮጵያ ህዝብ በሃይል ሲያስቆማቸው ያኔ ትረዱታላቹሁ።

ወያኔወች ለኢትዮጵያን ነጻነት እንዳመጡልን በተደጋጋሚ እየነገሩን ነው። ኢትዮጵያኑ ደግሞ በወያኔ በሚባል አገር በቀል ቅኝ ገዥ ስር  ወደቀች እንጂ ነጻነታን አላገኘችም እያሉ ነው። በዚህ ዙርያ ግን ትግሬዎች በዚህ ተሳትፎ ውስጥ እንዳሉ እሙን ነው ምክንያቱም ቋንቋው ማስፈራሪያ  እስከመሆ ን የደረሰበት ግዜ ላይ ደርስናል።ትግሪኛ ተናጋሪ ከሆነ የፈለገውን  ነገር ማደረግ  የሚችል ከመሰላቸው ሁሉ ነገር ከፊታቸው ያዩታል። ግዜው ደርሷል።

ድልና ዘላለማዊ ክብር ለኢትዮጵያ!!!

ከ-ሳሙኤል አሊ                                                                                                                              26.02.2015                                                                                                                              Email-samilost89@yahoo.com

The post ወያኔ ታሪክ ሰሪ ነው ወይስ ታሪክ አጥፊ? – ከ-ሳሙኤል አሊ appeared first on Zehabesha Amharic.

የአድዋ ድልና ትሩፋት ፈተናዎቹ –ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

$
0
0

amsalugkidan@gmail.com

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው


በእርግጠኝነት ኢትዮጵያዊ ልብ ላለው ሰው ሁሉ ስለ አድዋ ድል ሲሰማና ሲያወራ ልቡ በኩራት ይሞላል መንፈሱ ይነቃቃል፡፡ ኢትዮጵያዊ ብቻም አይደለም በየትኛውም ዓለም ያለ በቅኝ ግዛት ቀንበር ፍዳ ያየ የትኛውም የሰው ዘር ጭምርም እንጅ፡፡ ይህን አንጸባራቂ ድል መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት ተሰልፎ ካስመዘገበ እነሆ ነገ የካቲት 23 ቀን 2006ዓ.ም 118 ዓመቱን ይይዛል፡፡ ይህንን ድል ለመቀዳጀት ፈተና የነበሩት ነገሮች ምን ምን ናቸው? ለመሆኑ ይህ ድል እንዴት ተገኘ ?  የዚህ ታላቅ ድል ትሩፋቶችስ ምን ምን ናቸው? የዚህ ድል ጠላቶች እነማን ናቸው? ይህ ድል እንዴት ይጠበቃል? ብዙ ቢባልለት ከማይበቃው ከአድዋ ድል እነዚህን ነጥቦች ብቻ ነጥለን ለማየት እንሞክራለን፡፡

ዐፄ ምኒልክ ምታ ነጋሪት ክተት ሠራዊት ብለው ፋሽስት ጣሊያን በዘመነ ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ከነበረበት አልፎ የትግሬ ገዥ የነበሩትን ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ከእሳቸው ቀጥለው እንዲነግሡ በማሰብ ሊሞቱ በሚያቃትቱበት ወቅት ወራሸ ነው ለእኔ ያደረጋችሁትን ሁሉ ለእሱም አድርጉ በማለት ተናዘውላቸው የነበሩትን ራስ መንገሻን ድል አድርጎ ሠራዊታቸውን ከበተነ በኋላ አልፎ መላዋን ሀገራችንን ቅኝ ለመግዛት ወደ መሸገባቸው ቦታዎች ወደ አንባ አላጌ፣ መቀሌ እንዳኢየሱስና አድዋ ከመዝመታቸው እነዚያን አኩሪ ድሎች ከማስመዝገባቸውና ታሪክ ከመሥራታቸው በፊት እነኝህን ድሎች እንዳንቀዳጃቸው የሚያደርጉ እጅግ ከባባድ ፈተናዎች ተጋርጠውብን ነበር፡፡ የአድዋን ድል በሌሎች ሀገራት ከተገኙት ድሎች ልዩ የሚያደርገውም ይሔው ነው፡፡ እነዚህ ፈጽሞ ሊታለፉ የማይቻሉ መሰናክሎችን ታልፎ የተገኘ ድል በመሆኑ፡፡

የአድዋን ድል ለመቀዳጀት አያስችሉ የነበሩት ፈተናዎች ምን ምን ናቸው፡- 

  1. የከብት እልቂት፡- ፋሺስት ጣሊያኖች ኢትዮጵያን ቅኝ ለመያዝ ሲያስቡ ቅኝ ገዥዎች በአፍሪካና እስያ በቀላል ግጭት ቅኝ ሀገር መያዝ እንደቻሉ ሁሉ በኢትዮጵያ ይህ መልካም እድል እንደማያጋጥማቸው ጠንቅቀው ዐውቀውት ነበር፡፡ በመሆኑም ጦርነት መግጠማቸው የማይቀር ከሆነ የኢትዮጵያንና የመንግሥቷን አቅም ለማዳከም የሚያስችል ስልት ነደፈ ከስልቶቹ አንዱም የሀገሪቱ ሀብት መሠረት የሆነውን ግብርናዋን ማሽመድመድ መጉዳት ነበር፡፡ ይህንን ሲያስቡ ግብርናዋን ለመጉዳት ማድረግ የሚችሉት ነገር ሆኖ ያገኙት የከብት ሀብቷን መጨረስ ነበር፡፡ ይህንን ለመፈጸም ሲባል ከህንድ ሀገር ሶስት የታመሙ ከብቶችን በምጽዋ በኩል አስገብተው ከደማቸው እየወጉ የኞቹን ደኅናዎቹን ከብቶች በመውጋት አጋቡባቸው በሽታውም በአጭር ጊዜ ተዛምቶ ከኢትዮጵያም አልፎ አጠቃላይ የቀጠናውን ከብት ፈጀው፡፡ ውጤቱም ፋሽስቶቹ ከጠበቁት እጅግ የበዛ ሆኖ በሀገራችን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ‹‹ክፉ ቀን›› በመባል የሚታወቀውን ረሀብና ችጋር አመጣ፡፡ የሚበላ ነገር ጠፍቶ ዋልካ አፈርና ሳር ቅጠሉ ሁሉ የተበላበት ዘመን ነበር፡፡ ሕዝቡ ደቀቀ አለቀ ሀገሪቱ ተሽመደመደች፡፡
  2. የስንቅና ትጥቅ (logistics) ዝግጅት እጅግ ውስንነት፡- ፋሽስት ጣሊያን በወቅቱ ኃያላን ከሚባሉ የአውሮፓ ሀገራት አንዱ ነበረ፡፡ እንደ ኃያልነቱም ከ20 ሺ በላይ ለሆነው ላሰለፈው ጦሩ ዘመናዊ መሣሪያ በነፍስ ወከፍ ከማስታጠቁም ባሻገር ሠራዊቱ በወጉ የተደራጀ ዘመናዊ የውትድርና ሥልጠና የወሰደ ባጠቃላይ ከበቂ በላይ የስንቅና ትጥቅ ዝግጅት የነበረው ነበር፡፡ በእኛ በኩል የነበረው ደግሞ ባጋጠመው የረሀብና አስከፊ ችጋር የደከመ ሠራዊት ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ የሆነ የስንቅና ትጥቅ አቅርቦች ችግር ነበረበት፡፡ በወቅቱም ሠራዊቱ ነፍሱን ለማቆየት በቀን እጅግ መጥኖ ከሚቀምሳት በየ አገልግሉ ቋጥሮ ከያዛት ጥቂት ዳቦቆሎ፣ የደረቀና የሻገተ ቂጣ፣ ቆሎና በሶ የመድኃኒት ያህል ጥቂት ጥቂት የሚቀምስ ሠራዊት ነበረ እንጅ የስንቅ አቅርቦቱን አስቦ በየ ዕለቱ አብስሎ የሚያቀርብለት አካል አልነበረም፡፡ ሰራዊትም ሲባል ሐበሻ እንዲያው በተፈጥሮው ተዋጊ በመሆኑ እንጅ ሊገጥመው እንደተዘጋጀው ጠላቱ ሠራዊት በወጉ የወሰደው የውትድርና ትምህርት ጨርሶ አልነበረም፡፡ የታጠቀው መሣሪያም ቆመህ ጠብቀኝ በሚባል የሚታወቁ ኋላ ቀር መሣሪያ ሆኖ ይሄንንም ቢሆን የያዙት ከሠራዊቱ እጅግ ጥቂቶቹ ነበሩ የተቀረው ግን የያዘው ጦርና ጋሻ ጎራዴ ነበር፡፡ ይሔም አይጠቅምም ማለት ሳይሆን በጦር በጎራዴና በጋሻ ውጊያ የሚደረግበት ዘመን አልፎ ከሩቁ ጠላትን መልቀም ማስቀረት የሚቻልባቸው ከመድፍ እስከ መትረየስ ያሉ ዘመናዊ መሣሪያዎች የወጡበት ዘመን በመሆኑ ለሚደረገው ጦርነት የጦር የጎራዴ እና የጋሻ ጥቅምና አገልግሎት እጅግ በጣም ውስን ሆኖ ነበር፡፡ ጦርነት በጦር በጎራዴ ይደረግ የነበረበት ዘመን ለእኛ እጅግ የቀና የበጀና የሰለጠም ነበር፡፡
  3. የባንዶች ሚናና የጠላት የመከፋፈል ስልት፡- ፋሽስት ጣሊያን የኢትዮጵያን ሠራዊት ለማዳከም ከተጠቀመበት ስልት ሌላኛው ባላባቶችንና መሳፍንቱን እስከ ራሶች ድረስ እንዲከዱ በማድረግ ከጎኑ ማሰለፍ ነበር፡፡ ጥቂት የማይባሉትንም ማስካድ ችሎ ነበር ነገር ግን እነዚህ የከዱና ከነሠራዊታቸው በባንድነት የተሰለፉ መኳንንት የጠበቁትንና የፈለጉትን አቀባበልና መስተንግዶ እንዳላገኙና እንደማያገኙም ሲገባቸው የዐፄ ምኒልክ ይቅር ባይነት ዋስትና ሆኗቸው ብዙዎቹ ተመልሰዋል፡፡ ይሁን እንጂ እነኝህ ከድተው የነበሩ ሹማምንት መመለሳቸው የእውነት ከልብ ነው ወይስ ለተልዕኮ? የሚለው ጉዳይ ለወገን ሠራዊት በወቅቱ እጅግ አንገብጋቢ ጥያቄና እውነቱን ለመረዳት ከመቸውም አጋጣሚ በበለጠ አምላክነትን የሚያስመኝ፤ ሥጋት ጥርጣሬውም እረፍትና እንቅልፍ የሚነሳ አምኖ ለማሰለፍም ለመተውም ያስቸገረበት ጉዳይ ሆኖ ነበር፡፡
  4. የፋሽስት ጣሊያን ጦር መሽጎ ያለ መሆኑ፡- ጦርነት በሚደረግበት ወቅት ጦርነት ከሚያደርጉት ባላንጣ አካላት አንደኛው ምሽግ ይዞ የሚጠብቅ ከሆነ ጦርነቱ ለአጥቂው ወይም ምሽግ ላልያዘው ክፍል እጅግ ከባድና አስቸጋሪ የሚያስከፍለው ዋጋም ከመሽገው አካል ጋር ሲነጻጸር በጣም የሚበዛ መሆኑ የማይቀር ነው፡፡ እኛንም ያጋጠመን ይሄው ነበር በሶስቱም ቦታዎች የጠላት ጦር ምሽጉን በሚገባ ገንብቶ ከምሽግ ማዶም በባዶ እግሩ የሚጓዘውን አርበኛ ሠራዊት እንዲቆራርጥ በጠርሙስ ስብርባሪና በጦር ችካሎች ከዚያም በፈንጂ የታጠረ ምሽግ ውስጥ ሆኖ አድፍጦና መሽጎ ይጠብቅ የነበረ ጦር ከመሆኑ የተነሣ የጠላትን ጦር ከዚህ ምሽጉ ለማስወጣት ምን ያህል መሥዋዕትነት ሊጠይቅና ሊያስከፍል እንደሚችል መገመት ይቻላል፡፡ እንኳንና ተመጣጣኝ ትጥቅ ሳይያዝ ቢያዝም እንኳ ሁኔታው እጅግ ከባድ ነው በዚህ ላይ የእኛ ጦር ዘመናዊ የውጊያ ስልት ካለመማሩ ጋር ተያይዞ ተኝቶ መሬት ላይ በመሳብ መተኮስን እንደ ነውርና ፈሪነት አድርጎ የሚቆትር በመሆኑ ደረቱን ሰጥቶ በከፍተኛ ድፍረትና ወኔ ይዋጋ የነበረ ጦር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ መሥዋዕትነቱን እጅግ የከበደ አድርጎት ነበር፡፡ የሚገርመው ነገር ግን ከነዚህ ነባራዊ ሁኔታዎች አኳያ ከጦርነቱ በኋላ የደረሰብን የሟችና ቁስለኛ መጠን በጠላት ሠራዊት ከደረሰው እምብዛም የሚበልጥ አልነበረም፡፡
  5. የህክምና አገልግሎት ችግር፡- እንዲህ ዓይነት የሕዝብ እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት ወረርሽኝ ይከሰታል፡፡ ወረርሽኝ ሲከሰትም ለዚህ ጉዳይ ቀድሞ የተዘጋጀ ህክምና ከሌለ ከባድ ጥፋት አስከትሎ ያልፋል፡፡ የወገን ጦር ይሔንን አደጋ መከላከል የሚችልበት አቅምና ዝግጅት አልነበረም ሌላው ቀርቶ ቁስለኛን እንኳን ማከም የምንችልበት መድኃኒትና ባለሙያ አልነበረንም ሁሉም ለየራሱ ሐኪም ነበረ፡፡ አስተናግር ቅጠሉን ጨምቆ አዘጋጅቶ ይዞት የመጣውን ቁስሉ ላይ እያፈሰሰ እርስ በራሱ ለመተካከም ይሞክራል እንጅ ይሔንን ጉዳይ የሚከውን የህክምና ቡድን አልነበረም፡፡

እንግዲህ እነዚህና ሌሎች ሊታለፉ የማይችሉ እንደተራራ የገዛዘፉ ከባባድ ደንቀራዎችን ፈተናዎችን በእግዚአብሔር ቸርነት በሐበሻነት ጽናት እናት አባቶቻችን አልፈው ነው የአንባላጌውን፣ የመቀሌውን፣ በመጨረሻም የአድዋን ድል ለመቀዳጀት የቻሉት፡፡ የአድዋ ድል በሌሎች ዜጎች ዘንድም በከፍተኛ አድናቆት የሚደነቀው የሚከበረውም ከዚህ የተነሣ ነው፡፡

ለመሆኑ ይህ ድል እንዴት ሊገኝ ቻለ?፡- ለድሉ መገኘት ትልቁ ድርሻ የእግዚአብሔር ረድኤት ቢሆንም እግዚአብሔር ሲሠራ በምክንያት ወይም መሣሪያ የሚያደርገው ነገር መኖሩ አይቀርምና ለእናት አባቶቻችን ቁርጠኝነትን፣ ጽናትን፣ መጨከንን ሰጥቶ ከቶውንም የማይታለፉትን ፈተናና መከራን አስተናግዶም በእነሱም ደክሞ ደቆ የነበረ ሕዝብ ተሰባብሮ ተነሥቶ እንዲህ ዓይነት አስደናቂ ድል ለማስመዝገብ በቃ፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ድል ለማስመዝገብ ሐበሻ ሆኖ መገኘትን የግድ ይጠይቅ ነበር አደረግነውም፡፡ በመሆኑም “ነፃነት ወይም ሞት” “ባሪያ ሆኖ ከመኖር ነፃ ሆኖ መሞት” የሚለው የጨከነ መርሑ ከፊቱ የተደቀኑ ግዛዙፍ ፈተናዎችን መሰናክሎችን ከነ አካቴው ከግምት ውስጥ እንዳያስገባ አድርጎት በከፍተኛ ቁርጠኝነትና ጽናት በመዋጋቱ ድሉን ሊያገኝ ቻለ፡፡

የዚህ ታላቅና አንጸባራቂ ድል ትሩፋቶች ምን ምን ናቸው? ይህ ታላቅ ድል ከእኛም አልፎ ለመላው ዓለም ጭቁኖች በርካታ ትሩፋቶችን አበርክቷል ከእነዚህ በርካታ ትሩፋቶቹ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል፡-

  1. የቀለም ልዩነትን መሠረት ያደረገው የብቃት ደረጃ ልዩነት አስተሳሰብን ፉርሽ መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል፡፡ ከዚህ ድል አስቀድሞ ጥቁር ሲባል ሰብአዊ እሴት አልባ፣ ለባርነት የተፈጠረ፣ ሥልጣኔ የማይገባው አድርገው ያስቡት ነበር፡፡ ከዚህም አልፈው ተናጋሪ እንስሳ እያሉ ይገልጹት ነበር፡፡ ጥቁሮቹ እናት አባቶቻችን ግን ፈጽሞ ሊታለፉ የማይቻሉ ፈተናዎችን አልፈው ለክብራቸው ለነፃነታቸው፣ ለሉዓላዊነታቸው የማይችሉት ነገርም እንኳን ቢሆን አንችለውምና ምን እናድርግ ብለው ክብራቸውን፣ ነፃነታቸውን፣ ሉዓላዊነታቸውን ለድርድር ሳያቀርቡ ለሰብአዊ ክብራቸውና ለማንነታቸው ታይቶ በማይታወቅ ቀናኢነት በየትኛውም የዓለም ክፍል ያለ ማንኛውም ዓይነት የሰው ዘር አደርገዋለሁ ብሎ ሊሞክረው ቀርቶ ሊያስበው በማይችለው ሁኔታ በግሩም ችሎታና የአጨራረስ ብቃት ከውኖ በማሳየቱ ጥቁር እንዲህ እንዲህ ነው እየተባለ ዝቅ ተደርጎ ይቆጠርና ይታይ የነበረው አስተሳሰብ የተሳሳተ መሆኑን የግዳቸውን እንዲያምኑ አድርጓል፡፡
  2. የነፃነት ትግልን አነቃቅቷል ቀስቅሷል፡- ጥቁር አፍሪካዊያን ለአምስት ምእተ ዓመታት ያህል በግፈኛ ነጮች ሲሰበክላቸው የኖረውን የጥቁርን ተገዥነት ወይም ለአገልጋይነት መፈጠር አምኖ ተቀብሎ ሰጥ ለበጥ ብሎ የመገዛትን አስተሳሰብ አዳብሮ ወደ አውሮፓና አሜሪካ እየተጋዘ እየተሸጠ እየተለወጠ ይገዛ ያገለግል ነበር፡፡ ሐበሾቹ ጥቁሮች አድዋ ላይ ያበሩላቸው ፀሐይ ግን ይሄንን የጨለመ አስተሳሰብ ጠራርጎ በማጥፋቱ የነጻነት ትግልንና የነፃነት ታጋዮችን በየስፍራው በየአቅጣጫው እንዲቀጣጠል አድርጎ እነሆ ዛሬ ላይ ያን ሁሉ ግፍ በጥቁርነቱ ብቻ ይጋት የነበረው የሰው ዘር ነጻነቱን አረጋግጦ ቢያንስ በገዛ ሀገሩ እንኳን እንደ ሰው መኖር የሚችልበትን ሁኔታ መፍጠር እንዲችል አብቅቷል፡፡
  3. የተረሳውን ታሪካችንን አስታውሷል፡- ሐበሻ እንደሕዝብና እንደ ሀገር ከማንም የቀደመ የሥልጣኔና የመንግሥት ታሪክ ያለውና የነበረው ሕዝብ ነው ይህ ግን በወቅቱ በነበረው አስገዳጅ ችግር ሳቢያ ከዐፄ ፋሲል ጀምሮ ለረጅም ጊዜ ቆይቶ በነበረው ዝግ መመሪያ (closed policy) ምክንያት ዓለም እኛን እኛም ዓለምን ረስተን ተረሳስተን ስለነበረ ዓለም በየጊዜው መረጃውን እያደሰ እንዳወቀን እዲቀጥል ማድረግ ሳንችል ቀርተን ነበር፡፡ የአድዋ ድል ግን ዓለም ስለኛ ያለውን መረጃ ካጎረበት እያወጣ እንዲያወራ እንዲህ እኮናቸው እንዲህእኮ ነበሩ እያለ እንዲያወራ አድርጎታል፡፡ ያወሩልን ይፅፉልን ከነበረው ታሪኮቻችን የሚበዛው እኛም እንኳን እራሳችን የማናውቃቸው ናቸው፡፡
  4. የሕዝባችንን አንድነት አጽንቷል፡- የጠላት ወረራ ለመኳንንቶቻችንና ለመሳፍንቶቻችን ትልቅ ትምህርትን ሰጥቷል፡፡ በአንድነት የመቆምን አስፈላጊነት የአንድነትን ጥቅም በሚገባ አስገንዝቧቸዋል፡፡ ከዚያ አስቀድሞ ከዘመነ መሳፍንት ጀምሮ በመሳፍንቱና በባላባቶች ዘንድ የየራሳቸውን ጎጥ እንደ ሀገር በመቁጠር የየራሳቸውን ‹‹ሀገር›› የመመሥረት የማይጠቅምና ኋላ ቀር አስተሳሰብ ያስቡ ነበር፡፡ ይህን የትም የማያደርስ አስተሳሰብ ለማጥፋት ዐፄ ቴዎድሮስን እጅግ አድክሟል፡፡ በዐፄ ቴዎድሮስ እጅ ያደጉት ዐፄ ምኒልክ 2ኛም የዐፄ ቴዎድሮስ 2ኛ ሕልም ገብቷቸው ስለነበር ጥረታቸውና ሁኔታዎች ፈቅደውላቸው የዐፄ ቴዎድሮስን ሕልም ለማሳካት ችለዋል፡፡ የአድዋ ድልም ለመሳፍንቱ የማይረሳ ትምህርትን ስለጣለላቸው ከዚያ በኋላ አስቀድሞ የነበረው ዓይነት የመሳፍንት አስተሳሰብ እንዳይኖር አድርጓል፡፡
  5. ለቀጣይ ትውልድ ታሪክ እንዴት እንደሚሠራና እንደሚጠበቅ ምሳሌነቱን ትቶ አልፏል፡- ሀገራችን ከ4500ዓመታት በላይ የመንግሥት ታሪክ አላት እንደ ሀገር ከቆመችበት ጊዜ ጀምሮ ነጻነቷን ለመንጠቅ ተደጋጋሚና አደገኛ ፈተናዎችን አሳልፋለች፡፡ እነዚሁ ጣሊያኖች በቀደመው ስማቸው ሮማዊያን ከቄሳሮች ዘመን ከሁለት ሽህ ዓመታት በፊት ጀምረው ሲፈታተኑን ኖረዋል፡፡ የአድዋ ድል እናት አባቶቻችን የዚህችን ሀገር ነጻነት እንደምን ባለ መሥዋዕትነት አስጠብቀው እንደቆዩና ይህ ረጅም ታሪኳ እንዴት እንደተሠራ የቅርብ ጊዜ ምሳሌነት የተወ ድል ነው፡፡ በደካማ ጎን መግባት የሚችሉበት ጠላቶቻችን ግን የትግል ስልታቸውን በቀጥታ ከሚተኮሰው አፈሙዝ ወደ ተለየ ዓይነት በመለወጥና ባንዶችን በማሠማራት የአድዋ ድል ከተወልን ምሳሌነት ልንማርና እኛም የድርሻችንን ታሪክ ልንሠራ የምንችልበትን ዕድል አጥበውት ሀገርን፣ አንድነትን፣ታሪክን፣ ነጻነትን፣ ሉዓላዊነትን፣ ክብርን መሠረቱ ያላደረገ የየግል ዓላማና አስተሳሰብ አራጋቢዎች አድርገውን አንድነታችንን አደጋ ላይ ጥለውታል፡፡በዚህ ረገድ እየተሳካላቸው ይገኛል፡፡ ፈጣሪ ይቅደምልን እንጂ የዚህ ውጤት ደስ የሚያሰኝ አይሆንም፡፡
  6. የታሪክ ሀብትን ትቶልናል፡- አንዲት ሀገር ዜጎቿ ጠንካሮች ከሆኑ ሁለቱም ሀብቶች ይኖሯታል ቁሳዊና መንፈሳዊ ሀብቶች ታሪክ መንፈሳዊ ሀብት ነው፡፡ ታሪክ መነቃቃትን የሚፈጥር ታላቅ ኃይል ነው፡፡ ቁሳዊ ሀብትም የመፍጠር ዐቅም አለው፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሁለቱም ሀብቶች ነበሯት፡፡ ነበሯት ማለቱ ግድ ሆኗል አሁን ላይ ቁሳዊው እንደሌለ ግልጽ ቢሆንም መንፈሳዊው ሀብታችንም ራሱ ድራሹ እንዲጠፋ በከፍተኛ ትጋት እየተሠራበት ነውና ነበረን ማለቱ ይቀላል፡፡ ሊገባኝ ያልቻለው ነገር ግን ከዚህ ማን ምን ዓይነት ትርፍ አንዴት ሆኖ እንደሚያገኝ፤ ጥቅሙ ምን እንደሆነ ነው፡፡ ለሕዝቡ ልጠይቅ የምሻው አንድ ጥያቄ አለኝ  የእናት አባቶቻችን ሀገር ኢትዮጵያ በዓለም  ውስጥ ከነበሩት አራት  ኃያላን መንግሥታት አንደኛዋ  ነበረች፡፡  ይህች ሀገር ዛሬ የዓለም  ጭራ ደሀዋ ሀገር ሆናለች ለምን? ይህ እንዴት ሲሆን ቻለ? እነሱ ጋር የነበረው ጠንካራ ጎን ይህችን ደሀና ደካማዋን ኢትዮጵያ ከፈጠርነው ከእኛ ጋር ያለው ደካማ ጎን ምንድን ነው?
  7. ዕውቅናና መከበርን አትርፎልናል፡- ይህ ድል የማያውቁን አንዲያውቁንና ሀገር ለሀገር ለሚደረግ ግንኙነት ተመራጭ እንድንሆን አድርጓል፡፡ የሚያውቁንም እንዲያከብሩን አድርጓል፡፡ ባጠቃላይ ወዳጅ ብቻ ሳይሆን ጠላትም እንዲሁ በተመሳሳይ ሳይወድ በግድ ዕውቅናና ክብር እንዲሰጥ አድርጎታል፡፡ የዛሬን አያርገውና ከዚያ በኋላ ለመጣችው ኢትዮጵያም ሞገስን አጎናጽፎ በዲንሎማሲው (በአቅንዖተ ግንኙነቱ) ተደማጭ ተከባሪ እንድንሆን አድርጓል፡፡
  8. ለመሪነት ሚና ተመራጭ እንድንሆን አድርጓል፡- ይህ ድል በሰጠን ዕውቅና ሳቢያ በተለያየ አቅጣጫ የፈጠራቸው በቅጭ ግዛት ይማቅቁ የነበሩ ሀገራት የፀረ ቅኝ ግዛት እንቅስቃሴ በሚያደርጉበት ወቅት ይህንን እንቅስቃሴያቸውንና ትግላቸውን እንድንደግፍ እንድናስተባብር ለመጠየቅ አስገድዷቸዋል፡፡ ሀገራችንም ይህንን ትግል የመምራቱን ታሪካዊ ኃላፊነት ሙሉ ለሙሉ በማመን ሀገራቱ ነጻ እስኪወጡ ድረስ የራሷን የጦር መሪዎችንና ተዋጊዎችን በማሰለፍ ጭምር ትግሉን ስታግዝ ስታስተባብር የተጣለባትንም አደራ በሚገባ ተወጥታለች፡፡ ለቀድሞው የአ.አ.ድ ለአሁኑ አ.ህ እና ለሌሎች አህጉራዊና ዓለም ዓቀፋዊ ድርጅቶች መቀመጫነት እንድትመረጥ ያበቃትም የዚሁ ድል ትሩፋት ነው፡፡
  9. ሰንደቅ ዓላማችንን እንድንወስን አብቅቷል፡- በእርግጥ ከአድዋ ድል አስቀድሞም የሀገራችን ነገሥታት ቀይ ቢጫ አረንጓዴ ወይም አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ሰንደቅ ይጠቀሙ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ነገር ግን በአዋጅና በይፍ ዕውቅና ተሰጥቶት ሀገራችንንና ሕዝባችንን እንድትወክል የተደረገው ዐፄ ሚኒልክ አድዋ ላይ ይህንን አንጸባራቂ ድል ከገኙ በኋላ እዚያው አድዋ ላይ አዋጅ አስነግረው ከእንግዲህ ወዲህ ይህ ቀይ ቢጫ አረንጓዴ  ሰንደቅ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ  ሆኗልና ከክብር በላይ ክብርን፣ ከፍቅር በላይ ፍቅርን፣ ከአለኝታነት በላይ አለኝታነትን ስጧት ብለው በማስነገራቸው ይፋዊ ሰንደቃችን ሆና ለመቀጠል ቻለች፡፡

እንግዲህ በአጭር እንቋጨው እንጅ የአድዋን ትሩፋት እንዲህ በቀላሉ ዘርዝሮ የሚጨረስ   ጉዳይ አይደለም፡፡ በመቀጠል የአድዋ ድል ጠላቶች እነማን ናቸው? የሚለውንና ይህንን ቅርስ እንዴት ልንጠብቀው እንችላለን? የሚለውን በአጭር በአጭሩ ዐይተን እንቋጭ ፡፡

የአድዋ ድል ጠላቶች እነማን ናቸው?

የእድለቢስነት ጉዳይ ሆኖ ሀገራችን ኢትዮጵያ ለጠላት የታደለች ሀገር ነች፡፡ በዚህች ሀገር በየትኛውም ሀገር ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ለቁጥር የሚያታክቱ ጦርነቶች ከውጭና  ከውስጥ በሚፈጠር ቀውስ ሰበብ አስተናግዳለች፡፡ ይህች ሀገር ካስተናገደችው የጦርነቶች ብዛት አንጻር በታሪኳ በአማካኝ ከ10 ዓመታት ያለፈ የሰላምና የእፎይታ ቆይታ ዓይታ አታውቅም፡፡ ተአምር የሚሆንብኝ ነገር ቢኖር ይህንን ያህል የአውዳሚ ጦርነት ዓይነት ያስተናገደች ሀገር ደብዛዋ አለመጥፋቱ የሥልጣኔና የታሪክ አሻራዎቿም ጥቂቱንም ያህል ቢሆን መቆየት   መቻላቸው ነው፡፡ አሁን ላይ አስቀድሞ የነበሩን ጠላቶቻችንም ሆኑ ሌሎች አዳዲስ ቢኖሩ ጥቃታቸውን እየፈጸሙብን ያለው እንደቀድሞው በወረራ ሳይሆን በመሀከላችን ልዩነቶች እንዲፈጠሩ በማድረግና እርስ በእርስ በማናቆር በማፋጀት ሆኗል፡፡ ይሄም ይዞላቸዋል፡፡ አርቀውና አስፍተው ማሰብ የማይችሉ ወገኖቻችን የሀገራችን የሕዝብ  ለሕዝብ ግንኙነት  ምንም እንኳን እንከን የለሽ ነበር ማለት ባይቻልም በየትኛውም የዓለም ክፍል ከነበረው እጅግ የተሻለው እንጅ ተመሳሳይ እንኳን እነዳልነበረ፤ በበቂ ምክንያትና አማራጭም በመታጣቱ ለሀገር አንድነትና ህልውና ሲባል አንዳንድ የማያስደስቱን ነገሮች መደረጋቸውን መገንዘብ ማስተዋል የተሳናቸው ደናቁርት ለእነኝህ ጠላቶቻችን መሣሪያ በመሆን የሀገራችንንና የሕዝባችንን ህልውና ገደል አፋፍ ላይ አድርሰውታል፡፡ ዛሬ ላይ በየትኛውም የዓለም ክፍል ላይ ያሉ የባርነትና ጭቆና ቀማሽ የነጻነት ደጋፊና አቀንቃኞች የሚኮሩበትን የሚያከብሩትን የሚያደንቁትን  የአድዋን ድልና ያንን ድል ያስገኙልንን አርበኞች እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነው በጥላቻ የሚመለከቱ መጥፋት መረሳቱን የሚፈልጉ ለዚህም የሚሠሩ ዜጐች ለማየትና ለመስማት ደርሰናል፡፡ መፍትሔው ምንድን ነው ትላላቹ?

ይሄንን ቅርስ እንዴት ልንጠብቀው  እንችላለን?

ይሄንንና  ሌሎች ቅርሶቻችንን ሀብቶቻችንን ታሪኮቻችንን ልንጠብቃቸው  የምንችለው ለነዚህ  ሀብቶቻችን አንድ ዓይነት መግባባት ሲኖረን ሀብቶቹ በሚገባ የመጠበቅ እድል ይኖራቸዋል፡፡ አእምሮ ካለን እዚህ አንድ ዓይነት መግባባት ላይ ላንደርስ የምንችልበት እንድም ምክንያት አይኖርም፡፡ ወደራሳችን ወደ ውስጣችን እንመልከት፡፡ እያደረግነው ያለውን ነገር ከመፈጸሙ በፊት የሚገኘውን ትርፍና ኪሳራ እንመዝን፡፡ እንዲህ እንድናደርግ  እንድንናቆር እንድንባላ የሚመክሩን የሚገፋፉን የሚደግፍን ሀገራት በታሪካቸው ከእኛ የከፋ  የእርስ በእርስ ሰብአዊ መብት ገፈፋ ዝጋብ (record)  ያለባቸው ሀገራት ናቸው፡፡ ነገሥታቶቻቸው ሲያርፉ ጠባቂ እያሉ ሰዎችን ከነነፍሳቸው ግራና ቀኝ ይቀብሩ የነበሩ ናቸው፡፡ የሰው ልጆችን ከአራዊት ጋራ እያታገሉና እያስበሉ ለመዝናኛነት ይጠቀሙ የነበሩ ሀገራት ናቸው፡፡ ይህ ተሞክሮ በሀራችን ፈጽሞ ኖሮ አያውቅም፡፡ ዛሬ ላይ እነሱ እንኳን አንድ ዓይነት መግባባት ደርሰው በአንድነት   ቆመው ለሀገራችው ጥቅሞች በአንድ የተሰለፉ ሆነዋል፡፡ እነሱ ለዚህ የበቁ እንደነዚህ ያሉ ዘግናኝና ኢሰብአዊ ድርጊቶችንና አስተሳሰቦችን ዓይተን የማናውቀው እኛ ኢትዮጵያዊያን እንዴት አንድ ዓይነት መግባባት ላይ ለመድረስ ያቅተናል? ለሀገርና ለሕዝብ እስካሰብን ጊዜ ድረስ ፈጽሞ አያቅተንም፡፡ ሀገርንና ሕዝብን ጠልተንና ንቀን ባንዳነትን ከመረጥን ግን መቸም ጊዜ ቢሆን ልንግባባና የሰላም አየር ልንተነፍስ አንችልም፡፡

ዘለዓለማዊ ክብር ለአርበኞቻችን!!

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!

 

The post የአድዋ ድልና ትሩፋት ፈተናዎቹ – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው appeared first on Zehabesha Amharic.

ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው! –ከኣባ ሚካኤል

$
0
0

የካቲት ፳፫ ቀን ፪ሺህ፯ ዓም

ተፃፈ ከኣባ ሚካኤል።

loveቸሩ መድኃኔ ዓለም ይመስገንና እርሱ በመጀመሪያ የሰውን ዘር ከዘለዓለማዊ ሞት ሊታደግ ሲመጣ ዓለሙ በሙሉ እርሱን ደስ የማያሰኝ የጌታ ጠላት ነበር። ጌታ መድኃኔ ዓለም ግን ለሰው ልጅ ያለው ፍቅር እርሱን ከዙፋኑ ስለሳበው ዕውነተኛ የፍቅር መሥዋትን ይህቺውም ሕይወቱን ኣሳልፎ እስኪሰጥ ድረስ ወድዶናል፥ በደሙም ነፃ ኣውጥቶናል።  ሕግ ሁሉ በፍቅር ስለሚፈጸም ጌታ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ ካለን በኋላ ጌታችን ያለው፦ እኔንስ ብትወዱ ትዕዛዜን ጠብቁ ነው፥ በዕውን ትዕዛዙን ጠብቃችኋል?

ዛሬ በኢትዮጵያ ሃገራችሁ ውስጥ ፖለቲካው ባመጣባችሁ በደል ምክንያት በተከበራችሁበት ሃገራችሁ ላይ ለመኖር ስላልቻላችሁ በዐራቱም ማዕዘናት ተሰድዳችሁ ባላችሁበት ክፍለ ዓለማቶች ሁሉ ኃይማኖታችሁን ጠብቃችሁ ቤተ ክርስቲያኖችንና መስጊዶችን ከፍታችሁ እየተገለገላችሁ ትገኛላችሁ። ይህንንም በማድረጋችሁ እራሳችሁን ታድጋችኋል፤ ይህም ለጊዜው መልካም ነው፥ ምንም ቢሆን እንደ ዕራስ ሃገር ኣይሆንምና።

ባላችሁበት ሥፍራ ሁናችሁ ደግሞ የሃገራችሁን ውሎና ኣዳር በትጋት ትከታተላላችሁ። ሁላችሁም “በዚያች ሃገር” ላይ ሳይሆን በኢትዮጵያ ሃገራችሁ ላይ ሠላም ወርዶና እርቅ ተደርጎ መቻቻልን የተዋሃደ ሕዝባዊና ፍህታዊ የሆነ መንግሥት ፈጥራችሁ እንዲሁም የመከላከያ ኃይሏ ለሕዝቧ እንዲያገለግል እንጂ ሥልጣን ላይ የሚወጣውን ጥቅም ኣስከባሪ እንዳይሆን ቀርጻችሁ ወደ ሃገራችሁ ተመልሳችሁ ተከብራችሁና ኣክብራችሁ መኖርን ትሻላችሁ።

በውድ ሃገራችን ላይ እንጂ በባዕድ ሃገር ላይ ኣንኖርም ያሉና በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩትን የእህቶቻችሁንና የወንድሞቻችሁን ሕይወት ስናይ ደግሞ ነፃነታችውን ለማግኘትና እናንተም በየሃገሩ ተበትናችሁ የምትገኙትን ወደ ሃገራችሁ እንድትመለሱ በሚያደርጉት ትግል ላይ እናንተ የፈራችሁትንና ከሃገር ያሳደዳችሁን ህዋሓት፦ እነርሱ በጠራራ ፀሐይ እየተጋፈጡት ድብደባ፣ እስራት፣ መሸማቀቅ፣ ረሃብ ወዘተ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛውን የፍቅርን ዋጋ ሞትን እየሞቱላችሁ ይገኛሉ።

የሚገርመኝ ቢኖር ክርስቲያኖች ወይም ሙስሊም ሆናችሁ ሳለ ጠላትህ ቢራብ ኣብላው፣ ቢጠማም ኣጠጣው፣ ቢራዝ ኣልብስው /ሮሜ ፲፪ ቁ ፳/ የሚለው የኣምላክ ቃል በየጊዜው እየተሰበከላችሁ ጠላቶቻችሁ ሳይሆኑ የገዛ ወንድሞቻችሁ እንኳን ቢራቡም፣ ቢጠሙም፣ ቢራቆቱም፣ በግፍ ቢገደሉም ወዘተ ፓትርያርኩም፣ ጳጳሱም፣ ቄሱም፣ ፓስተሩም፣ ሼሁም፣ ኢማሙም እንዲሁም ምዕመኑ ዝም። እግዚዖታን እንኳን ነፈጋችሗችው።  በሃገር ቤቱስ ላሉት ውስጡን ለቄስ ነው፥ ህዋሓት ናት የሓይማኖቱን ሥራ የምትሠራው። ከሃገራችሁ ዕርቃችሁ በነፃነት የምትኖሩ ክርስቲያኖች እስቲ ቆም በሉ። በእውን የሞተላችሁን ክርስቶስን ትወዱታላችሁ? ትዕዛዙንስ ትፈጽማላችሁ? ኣምላካችሁ ክርስቶስ ለሞተላት ክብርት ቤተ ክርስቲያን ፍቅር ኣላችሁ? ወይስ ከኢትዮጵያ ጠላት ጋር ኣብሮ የወገኑ ሞት ለእርሱ ሕይወት እንደ ሆነለት ሆድኣደር ሆናችሁ? ሙስሊሞችስ?

ህዋሓት ዛሬ ሳይሆን ከ፳፬ ዓመት በፊት ጀምራ የኦርቶዶክስ ክርስቲያንና የእስልምናን ዕምነት ለማጥፋት በሚገባ የቤት ሥራዋን ሠርታ ዛሬ በተግባር እየተረጎመችው ነው። ንዋየ ቅዱሳኖችን ኣውጥታ ሽጣለች፣ ቤተ ክርስቲያንን ኣቃጥላለች፣ መነኮሳትን ከገዳም ድረስ በመሄድ ደብድባለች፣ በቅርቡም ኢትዮጵያ ካለው ሲኖዶስ ይልቅ ለኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በሃገር ቤት ግልጋሎት የሚሰጠውን ማኅበረ ቅዱስንን ልትመታ ቃጥቷታል፥ ምንም እንኳን ማኅበረ ቅዱሳን ከሃገር ቤት ውጪ የተከፈቱትን ኣብያተ ክርስቲያናት ህዋሓት በሚቆጣጠረው በሃገር ቤቱ ሲናዶስ ሥር እንዲተዳድሩ በማድረግ ከፍ ያለ ሚና ቢጫወትም ለህዋሓት ማኅበረ ቅዱሳን ከኣብዮታዊ ዲሞክራሲው ኣይበልጥበትምና ከ፪ሺህ፯ ምርጫ በውኋላ ተመልሳ የቃጣችውን በተግባር ልታውል ትችላለች ብዬ እገምታለሁ፤ እስልምና ኃይማኖትን የሚመሩትን ትመርጣለች፤ ፕሮቴስታንቶቹን ደግሞ ኣንድ ቀን መንካቷ ኣይቀርም።

እስቲ እዩ፥ በኣካባቢያችሁ ስለ ኢትዮጵያ የሚያስቡትንና ኢትዮጵያን ነፃ በማድረግ ኃይማኖት እና ፖለቲካ ተከባብረው በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲኖሩ ደማቸውን ከሚያፈሱት ጋር ኣጋር በመሆን ጊዜያቸውንና ገንዘባችውን ለትግሉ መሳካት የሚሰጡትን፣ ስለ ወገናቸው ግድ የሚላቸው፣ ስለ ኃይማኖታችውም ስለ ሃገራቸው ፖለቲካም ቢናገሩ ዕውነተኞችና ታሪክ ሠሪዎችን፣ ህዋሓት እስካለች ሃገሬን ባላይስ መጀመሪያ ነፃነቴን ያሉትን። በኣንፃሩ ደግሞ እናንተ ዛሬ ገንዘብ ኣግኝታችሁ ቤት በሃገር ቤት ስትሠሩና ንብረት ስትመሠርቱ ወደ ሃገር ቤት የምትልኩት የውጪ ምንዛሪ የህዋሓትን የጭቆና ሥርዓት እንደሚረዳ እያወቃችሁ ስለራሳችሁ ብቻ ትጨነቃላችሁ። ገንዘባችሁ ባለበት ምናችሁ ኣብሮ ይኖራል ኣለ? ህዋሓት እንዲህ እያረገች ነው የምትቆጣጠራችሁ።

ከሃገራችን ተከትሏችሁ የመጣው የፖለቲካ ችግር ደግሞ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናችሁን በሦስት ቦታ ከፍሏታል። ኣሁን ባላችሁበት ሃገር የኣቡነ ማቲያስ ሥም የሚጠራባቸውን ቤተ ክርስቲያኖችን ብትመለክቱ፥ ወይ በበላይነት ወይም በኃላፊነት ላይ ያሉት ካህናቶችና ግለሰቦች የህዋሓት ደጋፊዎች ናችው። በመሆናቸውም፥ ምዕመኑን በተቻላቸው መጠን ኢትዮጵያን ከህዋሓት እንዳያላቅቅና ወደ ተቃዋሚ የትግሉ ጎራ እንዳይሄድ ኣድርገውታል። ኣይ ሃገራችን መልካም ኣስተዳደር ኣላት ትግሉ ኣያስፈልግም የምትሉ ካላችሁ ግን ለምን በሃገራችሁ እንደማትኖሩ ይገርመኛል፥ ሌላ ተልዕኮ ከሌላችሁ በስተቀር።

በምን ሰሌት እያሰላችሁ ነው ህዋሓት ከምትመራው ሲኖዶስ ጋር ተሰልፋችሁ ቤተ ከርሰቲያኒቷን  እያጠፋችኋት ያላችሁት። ባለፈው ሣምንት ውስጥ ከእንጦጦ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ዕድሜ ጠገብ ወርቆች ወዘተ ለኣባይ ግድብ መዋጮ ተወሰዱ የሚል ዜና ሰማሁ ግን ኣቡነ ማቲያስ  ከጽህፈት ቤታቸው ስለዚህ ጉዳይ ያወጡት መግለጫ የለም። እናንተ የእርሳቸውን ሥም በማንሳት የምትተባበሩትስ ምን ኣላችሁ? ምንም። ቤተ ክርስቲያኗስ ኣትጠፋም፥ ኣንዴ በክርስቶስ ደም ላይ ተመሥርታለችና፥ ውዮ ግን ለእናንተ የኣምልኮ መልክን ብቻ ለያዛችሁ፥ ለወገናችሁ ስቃይ ሳይሆን ስለራሳችሁ ብቻ ለምትጨነቁ።

በውጭ ሃገር ሲኖዶስ መቋቋሙን  ባንደግፈውም የኣቡነ መርቆርዮስን ፓትርያርክነት የሚክዱት ህዋሓት የሰለበቻችው የዋሆች ካልሆኑ በስተቀር ኣሁንም ቢሆን ሕጋዊው ፓትርያርክ እንደሆኑ ሌሎቻችን እንረዳዋለን። ይህንንም የውጪውን “ሲኖዶስ” ደግሞ ጠጋ ብሎ ላየው ሰው፥ የጎንደር ሃገር ስብክት እንጂ የኢትዮጵያ ሲኖዶስ ለመባል የሚችል ስብስብ ኣይደለም፤ እንዲሁም ለወደፊቱ ፓትርያርክ ለመተካት እንኳን ሥልጣን የለውም።  እዛ ጊዜ ላይ ቢደረስ፥ የገለልተኛው ቁጥር ከሌሎቹ እንደሚበልጥ እገምታልሁ።

ለዚህ ሁሉ ችግር መንስኤ የሆነችውን ህዋሓትን በማስወገድ ነፃነታችሁን ማወጅ ኣማራጭ የሌለው መንገድ ነው። ኣቋማችሁን ኣስተካክላችሁ ስለ ኢትዮጵያ ጉዳይ ስብሰባ ስትጠሩ በስበሰባው ላይ ተገኙና ስለ ኃይማኖታችሁና ስለ ሃገራችሁ ያገባናል በሉ። በፀሎትና በሃሳብ እንዲሁም በገንዘባችሁ ወገኖቻችሁን ታደጉ። ካህናቶቻችሁ በሃገር ቤት የሚደረገውን ግፍ ኃይማኖትን በጠበቀ መልኩ እንዲያወግዙ ግዴታ ኣለባቸውና ይህንን እንዲያደርጉ ጫና መፍጠር ኣለባችሁ። ካህናቶቹ ይህንን ባያደርጉ ግን፥ ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ ግድ ከሚላቸው ካህናቶች ከሚያገለግሉበት በመሄድ የሕብረት ጸሎት በማድረግና በተግባር ደግሞ ሰለ ኢትዮጵያ ነፃነት ከሚታገሉት ጎን በመቆም ዕውነተኛ ፍቅርን በማሳይት ትዕዛዝ ማክብራችሁን ኣረጋግጡ።

ተፃፈ ከኣባ ሚካኤል።

 

 

The post ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው! – ከኣባ ሚካኤል appeared first on Zehabesha Amharic.

ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች የተሳተፉበት የስልክ ጥሪ ማቆም አድማ ተካሄደ

$
0
0

10920943_352316331618819_5078649879608517565_nየካቲት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን እንዳዲስ ተጠናክሮ በቀጠለው ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን የማሰር ዘመቻውን በመቃወም ድምጻችን ይሰማ የጠራው ስልክን ለ12 ሰአታት የማጥፋት ዘመቻ በተሳካ ሁኔታ መካሄዱን ዘጋቢያችን ገልጿል፡፡

በርካታ ሙስሊሞች ስልኮቻቸውን አጥፍተው የዋሉ ሲሆን፣ በማህበራዊ የመገናኛ ብዙሃን የሚያደርጉትን እንቅስቃሴም አቁመው ውለዋል። በርካታ ክርስቲያኖችም ጥሪውን ደግፈው ስልካቸውን ዘግተው ውለዋል።

እርምጃ የመንግስት ዋነኛ የገቢ ምንጭ በሆነው ቴሌ ላይ የኢኮኖሚ ጉዳት ለማድረስ ታቅዶ የተተገበረ ነው።

Source:: Ethsat

The post ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች የተሳተፉበት የስልክ ጥሪ ማቆም አድማ ተካሄደ appeared first on Zehabesha Amharic.

በአማራ ክልል ነዋሪዎች በአገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች መማረራቸውን ተናገሩ

$
0
0

Amharamapየካቲት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በክልሉ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ እና የተለያዩ ቢሮዎች በየእለቱ ጉዳያቸውን ለማስፈጸም የሚመላለሱ ባለጉዳዮች በተለያየ ሰበብ ፈጻሚ በማጣት መቸገራቸውን ድርጅቱ ባዘጋጀው የአስተያየት መስጫ መዝገብ ላይ ማስፈራቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያሳያል።

ከተለያዩ አካባቢዎች ጉዳይ ለማስፈጸም እንደመጡ የገለጹት ቅሬታ አቅራቢዎች በተለይ በስብሰባ ሰበብ ለረዢም ጊዜ መጉላላታቸውን ባሰፈሩት የሃሳብ መስጫ ደብተር ላይ ለማንበብ ይቻላል። አስተያየት ሰጪዎች በዋነኝነት ያነሱት ችግር ባለስልጣኖች በስብሰባ ሰበብ ባለጉዳይ ለማስተናገድ አለመቻላቸውን ሲሆን፣ የብቃት ማነስም ችግርም ተጠቅሷል።

“ለማን ብሶታችንን እንናገር ፣ ጠዋት ስንመጣ ከሰአት ከሰዓት ስንመጣ ጠዋት፣ ቢሮ ኃላፊው የለም፣ ሂደት አስተባባሪው የለም፣ የድርጅቱና የመንግስት ሚዲያ በየመድረኮች ሚናገሩት ሌላ ፣

…የከተማው ህዝብ በመሬት እጦት፣ የመንግስት ሰራተኛው በደመዎዝ ማነስና ፣ተመርቆ ከቤተሰቡ ጋር ቁጭ ብሎ በመቅረቱ የገጠሩ ህብረተሰብ በማዳበሪያ ውድነት ተወጥሮ ፣ በሌትና በቀን የቁም ቅዠት አያሰቃየው አሁን ለማን ነግሮ መፍትሄ ያገኛል? ለመንግስት ቢነግሩ ከወረቀት የዘለለ የተግባር ፍሬ የለውም ኧረ ለማን እንንገረው?አምላክ አይፈጥን እንደሰው!እባክህ ጌታዬ የኢትዮጵያ አምላክ በ2007 ምርጫ ገላግለን ፣ በቸርነትህ መንግስት በዘር በዘመድ አዝማድ በገንዘብ እየተሸበበ በቁማችን እየተጓዝን ተቀበርን፡፡

…..ለአመራሮች በጣም ከፍተኛ የሆነ ስልጠና ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ባለስልጣኖቹ ድሃውን ህዝብ በማንገላታት የታወቁ መሆናቸው በአለም ታውቋል የነሱን ምቾት ካገኙ ለሌላው ምንም ደንታ የላቸውም……

…..ባሁኑ ሰዓት አቤት ባይ ሲበዛ ፍትህ ሰጪ ግን የለም፡፡ለምን ይሆን ህብረተሰቡን የተጣላው?እግዛብሄር ይሆን መንግስት ነው አልገባኝም…….

የሚሉት አስተያቶችን የያዙ ማስታሻዎች ለስሙ በተቀመጡ ያአስተያየት መቀበያ ደብተሮች ላይ ሰፍረው ይነበባሉ፡፡

የገዢው መንግስት ባለስልጣናት ከህዝቡ አስተያየት በመሰብሰብ አገልግሎት አሰጣጣችንን እናስተካክላለን እያሉ ቢናገሩም የአስተያየት ደብተሮችን እንደማይመለከቱ አስተያየት ሰጪዎች ገልጸዋል፡፡

Source:: Ethsat

The post በአማራ ክልል ነዋሪዎች በአገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች መማረራቸውን ተናገሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሰቆጣ አርሶደአሮች በረሃብ ምክንያት ተሰደዱ

$
0
0

esat

esat 2

ESAT 3
የኢሳት ወኪል እንደዘገበው በሰቆጣ አካባቢ የተከሰተውን ከፍተኛ ድርቅ ተከትሎ አርሶደአሮቹ ወደ ምእራብ ጎጃምና ሌሎች የአማራ ክልል አካባቢዎች በመሰደድ ላይ ናቸው።

ተፈናቃዮቹ ከክልሉ ባለስልጣናትም ይሁን ከፌደራል መንግስቱ ምንም አይነት እርዳታ አለማግኘታቸውን ገልጸዋል።

ብዙዎቹ ተፋናቃዮች ወጣት ወንዶችና ሴቶች ሲሆኑ፣ በሰፈሩባቸው አካባቢዎች ስራ ሰርተው ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ እየጠየቁ ነው።

ተፈናቃዮቹ በዝናብ እጥረት ምክንያት ሰብላቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙን ገልጸዋል።
መንግስት በአካባቢው ስለተከሰተው ድርቅ እስካሁን የሰጠው ምንም አይነት መልስ የለም።

The post ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሰቆጣ አርሶደአሮች በረሃብ ምክንያት ተሰደዱ appeared first on Zehabesha Amharic.

የጉራጌ ካድሬዎች አንገታቸውን ያስደፋ ክስተት

$
0
0

‹‹ያለ ኢኮኖሚ የበላይነት የፖለቲካ የበላይነት አይመጣም››

የሚለው የህውሃት ኢህአዲግ ፖለቲካ ኢኮኖሚውን ከመቆጣጠር ባለፈ ደጋፊዎቹን በኢኮኖሚ በማብቃትና በተጠቃሚነታቸውም ፖለቲካውን በመጠበቅ የበረኛነት ሚና እንዲጫወቱ በ97 ምርጫ ማግስት ከተወሰዱትርካሽ እርምጃዎች አንዱ በግምታዊ አቀማመጥ መሃከለኛ ገቢ ያላቸውን የመርካቶ ጉራጌዎች በማዳከም የህውሃትን ተጠቃሚዎች ማጠናከር ነበር::
Ethiopia
የወቅቱ የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዲኤታ ኤርሚያስ ለገሰ ይህንን ይላል በምርጫ 97 ማግስት አቶ መለስና በረከትን ጨምሮ ከፍተኛ የኢህአዴግ ካድሬዎች ‹‹ጉራጌ አብዮት አካሄደብን›› በማለት ይናገሩ ነበር፡፡ በኢህአዴግ ማእከል በተዘጋጀው ሰነድ ላይ የጉራጌ ብሄረሰብ ከትምክህት ጎራ ጋር በተቀላቀሉ ልጆቹ ምክንያት የሀይል አሰላለፍ ቀውስ ውስጥ በመግባት ከጥገኛ ኃሎች ጋር ተሰልፎ ወደ ዝቅጠት ገብቶ እንደነበር ይገልጻል፡፡ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የብሄረሰቡ ተወላጆች(በጉራጌ ዞን ያለውን መዋቅራችንን ጨምሮ) የዜጎችን በነጻነት የማሰብና የመምረጥ መብት በመጋፋት እስከ ጎጣቸው በመሄድ ‹‹ኢህአዴግን የመረጠ ውሻ ይውለድ!›› የሚሉ ቃል ኪዳኖችን እስከ ማጥለቅና መማማል ዘልቀው ነበር በማለት ይከሳቸዋል፡፡ የጉራጌ ብሄረሰብ እንደ ሌሎች የሀገራች ጭቁን ብሄረሰቦች ህገ-መንግስታዊ መብቱ በተከበረበት፣ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብት በተጎናጸፈበት ሁኔታ ወደ ትምክህት ሀይል ሽግሽግ ማድረጉ ያልተጠበቀ እንደነበር ሰነዱ አመላከተ፡፡( ቅንፍ የራሴ በምርጫ ኢህአዴግን አለመምረጥ መብት ሳይሆን ትምክህተኝነት የሚባል ሃጥያት ነበር ዛሬም ነው)

በቀረበው ዶክመንት ላይ በመመስረት በየወረዳው የተካሄዱት መድረኮች አስደንጋጮች ነበሩ፡፡ የምርጫ 97 ውጤት የኢትዮጵያ ህዝቦች የትግ ውጤት መሆኑን በመካድ ‹‹ጉራጌ መራሽ አብዮት›› የሚል ስያሜ እስከ መስጠት ተደረሰ፡፡ ጣቶች በሙ ወደ ጉራጌ ብሄረሰብ በተለይም የብሄሩ ተወላጅ የኢህአዴግ ካድሬዎች ላይ ተቀሰሩ፡፡ ነጋዴው ጸረ-ኢህአዴግ እንዲሆን ከአመታት በፊት የተጠነሰሰ ሴራ እደሆነ በሰፊው ተነገረ፡፡ የጉራጌ ካድሬዎች አንገታቸውን ደፉ፡፡

ኢኮኖሚውን የሚቆጣጠር ኃይል በሂደት ፖለቲካ ኢኮኖሚው ላይ የበላይነት ማሳረፉ ስለማይቀር ጉራጌን ከንግዱ ዓለም ማስወጣት ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም፡፡ ሮማን (የህወሃት ባለሃብቶችን መፍጠር አላማ አስቀጣይ የሆነች) የጉራጌ ነጋዴዎችን እንዳያሰራሩ የምትቀጣበት ምክንያት ይህ ነበር፡፡
እነ ሮማ በፈጠሩት ልዩነት ጉራማሌዋ መርካቶ ይበልጥ ተዘበራረቀች፡፡ ተመሳሳይ እቃዎች በነባሮቹና አዲሶቹ ነጋዴዎች መካከል የዋጋ ልዩነት አሳየ፡፡ የግብርና የሊዝ እፎይታ ያገኙት አዲሶቹ ነጋዴዎች ዋጋቸውን አወረዱ ሸማቹሚስጥሩ ሳይገባው ቅናሽ ወዳገኘበት አዲሶቹ ነጋዴዎች ፊቱን አዞረ፡፡ ቀስ በቀስ ነጋዴው ከገበያ ወጣ፡፡
የማፊያ ባህሪ ያላቸው አዲሶቹ ነጋዴዎች ሰው ሰራሽ እጥረት በመስከሰትም ተወዳዳሪ አልነበራቸውም፡፡ በሰአታት ውስጥ አንድ ኪሎ ጨው ዋጋ ከአንድ ብር 50 ብር የተሸጠበት አጋጣሚ ልብ ይሏል፡፡

ነባሩ ነጋዴ ከገበያ መውጣቱ እልህ የተጋቡት የጉራጌ ካድሬዎቹ እነ ሺሰማ ክትትል ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ ከብዙ ጥረት በኋላ ሸፍጥ የሚሰራበትን ቦታ ይደርሱበታል፡፡ ሮማንና ወዳጆቿ ፋይል የሚሰርዙና የሚደልዙት፣ ግብር የሚጨምሩትና የሚቀንሱት፣ ሱቅ የሚሰጡትና የሚቀሙት አምባሳደር ፊልም ቤት የሚገኘው ካፍቴሪያ የሕገወጥነቱ ማዕከል ነበር፡፡….

ከምርጫ 97 በኋላ የጉራጌ አብዮትን ለመቀልበስ በስብሰባ ማዕከል በተጠራ የመጀመሪያው ዙር ማጠቃለያ ኮንፍረንስ ላይ ተገኝቼ ነበር፡፡ በጉባኤው የተሳተፉት ከአንድ ሺህ በላይ የጉራጌ ነጋዴዎችና ባለሃብቶች ነበሩ፡፡ ይህን ለአንድ ሳምንት የዘለቀ ጉባዔ የመራው ዶ/ር ካሱ ኢላላና ሚኒስትር መኩሪ ነበሩ፡፡ ነጋዴዎች በሲቃ ስለ ሮማንና ሉሌ የሚነሱት ወንጀል ጨጓራ የሚልጥ ነበር፡፡ በተለይ የክፍለ ከተማው የገቢዎች ኤጀንሲ ሙያተኛ የሆነ የጉራጌ ተወላጅ ስራየን ለመልቀቅ ብዙ ተሟግቻለሁ በማለት የገለጸው ታሪክ ዶ/ር ካሱ አንገቱን አቀርቅሮ አንዲቀር አድርጎታል፡፡ ከመቀመጫው ተነስቶ የኮንፈረንሱን ተሳታፊ አንባ እየተናነቀው ይቅርታ ጠይቋል፡፡

እንዲህ ነበር ያደረጉት፣
ሎሌና ሮማን ከቢሮአቸው ሳይወጡ ከአስር እጥፍ በላይ ግብር እንዲጥሉ ሙያተኞችን አስገደዱ፡፡ ከስረው ለመዘጋት አፋፍ ላይ ያሉ ነጋዴዎችን ከግብር ሕጉ በተቃራኒ ታክስ አስከፈሉ፡፡ በድርጊቱ የተበሳጨ አንድ ነጋዴ ራሱን በገመድ አንጠለጠለ፡፡ ተመሳሳይ ሱቅና የንግድ ዓይነት ያላቸውን ጎረቤት ነጋዴዎች አንዱን በዜሮ ፣ሌላውን በአስር ሺዎች ታክስ እንዲከፍል አድርገዋል፡፡ ይህ በዘር ላይ የተመሰረተ እርምጃ ቀድሞ በነጋዴዎች ዘንድ የነበረን በደጋገፍ እንዲቀር በማድረግ እርስ በራስ በጥላቻ እንዲተያዩ አድርጓል፡፡ በዚህ ምክንያት መሳሪያ የተማዘዙ፣ በገጀራ ተፈነካክተው ወህኒ የወረዱ ነጋዴዎች ይገኙበታል፡፡

(ለግምገማ ቀርባ የነበረችው ሮማን እንዳትጠየቅ አርከበ ተከላክሎ አትርፏታል)

The post የጉራጌ ካድሬዎች አንገታቸውን ያስደፋ ክስተት appeared first on Zehabesha Amharic.


ከሃረር እስከ ጎዴ እንዲሁም ሃርጌሳ አፈሳው እና አፈናው ተጥውጡፏል

$
0
0

(ምንሊክ ሳልሳዊ) ባለፉት ቀናቶች ውስጥ ወያኔ እና የኦጋዴን አማጺ ሃይሎች ያደረጉትን ጦርነት ተከትሎ ከግድያው በተጨማሪ ከሃረር እስከ ጎዴ ያካልለ የመንገድ ላይ አፈሳ እና የቤት ለቤት አፈና እየተካሄደ እንደሆነ ከሰራዊቱ እስጥ የሚገኙት ወታደራዊ ደህንነቶች ተናግረዋል::
news
በልዩ ሃይል መሪነት እና በሕወሓት ጦር ተባባሪነት እየተፈጸመ ያለው አፈሳ እና አፈና የወያኔ ጦር ባልውፉት ቀናት የደረሰበትን ሽንፈት እና ኪሳራ ለማካካስ የጀመረው ሲሆን እስካሁን የቤት እመቤቶችን ጨምሮ ከ400 ሰዎች በላይ ተይዘው መታሰራቸው ሲነገር ዋና ዋና ናቸው የተባሉ የኦጋዴን አማጺ ሃይሎች አባላት ወደ መሃል አገር መላካቸው ታውቋል::በዚህም መሰረት የስለላ ስራ ያካሂዳሉ የተባሉት አጋስ መሃመድ አብደላ እና አብዱላዚዝ አብዶ ቀሽር የተባሉ የአማጺ አባላት ይገኙበታል::አፈሳው እና አፈናው በሃረር በጎዴ በቀብሪበያህ በቀብሪ ደሃር በጅጅጋ በሃርሸክ እና በሰሜን ሱማሊያ ሃርጌሳ እየተካሄደ እንደሆነ ምንጮቹ ገልጸዋል::

በአንድ በኩል እንደራደር እያለ በአንድ በኩል በውጊያ የሚጠዛጠዘው ሰው በላው ወያኔ ምን ያህል የፖለቲካ ኪሳራ እና መበስበስ እንደሚጠቁም እና የኦጋዴንን ነዋሪዎች እያፈነ እና እያሰቃየ በየትኛው የሞላር ሚዛን ድርድር ላይ እንደሚቀመጥ እና ከነማንስ ነው የሚደራደረው የሚለው ጉዳይ ጥያቄ አስነስቷል::

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በኦጋዴን አማጺ ሃይሎች እና በወየኔ ጦር መካከል በኦጋዴን ደገሃቡር አከባቢ ከፍተኛ ውጊያ መካሄዱ ሲታወቅ በሰጋጋ አከባቢ የኦጋዴን አማጺ ሃይሎች ኮማንደር ተገለዋል:: የአማጺ ሃይሎች ተዋጊዎች በአከባቢው ከሚገኘው ልዩ ሃይል ተብሎ ከሚጠራው እና በወያኔ ጦር ጋር የአከባቢው ነዋሪዎች መታፈናቸውን ተከትሎ ከሃረር ከተማ 160 ኪሎሜትር ደቡብ ምስራቅ በምትገኝ በአኪርሚሽ ላስጋሎል በተባለ ቦታ መዋጋታቸውም ይታወሳል::

The post ከሃረር እስከ ጎዴ እንዲሁም ሃርጌሳ አፈሳው እና አፈናው ተጥውጡፏል appeared first on Zehabesha Amharic.

ሰበር ዜና: የወያኔ ሰላይ ከሆላንድ ተባረረ!

$
0
0

ሂሩት መለሰ – ከሮተርዳም

ሮተርዳም፣ ጥቅምት 28 ቀን 2015 – በስደት ስሙ አለማየሁ ስንታየው በመባል የሚታወቀው የህወሃት ሰላይ ከኔዘርላንድስ ተባረረ። አለማየሁ ስንታየሁ ቋሚ ነዋሪ ከነበረበት ከኔዘርላንድስ እንዲባረር የተደረገው በዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በከፈቱበት የስለላ ክስ መሆኑም ታውቋል።

የሮተርዳም ከተማ ፍርድ ቤት በአለማየሁ ላይ የተመሰረተውን የስለላ ክስና ማስራጃ ለረጅም ጊዜ ሲመረምር ከቆየ በኋላ የግለሰቡ የመኖርያ ፈቃድ እና ቤት እንዲነጠቅ፣ የሆላንድን ምድርም በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣ ውሳኔ አስተላልፏል። ከሆላንድ የምመራ ቡድን እንደተረዳነው ከሆነ – የግለሰቡ ቤት ሲፈተሽ ወያኔ የሰጠው እውነተኛ መታወቂያ እና በርካታ የስለላ ሰነዶች ተገኝተውበታል። በእርዳታ ስም የተቋቋመለት ድርጅትም ተፈትሾ ማስረጃዎች እንደተገኙ ለማወቅ ተችሏል።
alemayehu-sentayehu

ይህ ሰው ትክክለኛ ስሙ ዘለቀ ፎላ ይባላል። በደርግ ጊዜ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባል ሆኖ ለረጅም አመታት አገልግሏል። ወያኔ ስልጣን ሲቆጣጠር ለፖለቲካ ተሃድሶ አዋሳ ደቡብ ጦር ቅጥር ግቢ ተላከ። በተሃድሶ በነበረበት ጊዜ ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ የሰራዊቱ አባላትን ለወያኔ በማጋለጥ ታማኝነቱን ሲያሳይ እንደነበር የዚህ ዜና ዘጋቢ እማኝ ነው። የበርካታ ኢትዮጵያውያን ደም በእጁ ያለው አለማየሁ ከተሃድሶው ከወጣ በኋላ እስራኤል ገደቡ (የፓልቶክ ስሙ ኢዛና) ከተባለ ወታደር ጋር በመሆን የሰላም ተጓዥ ነኝ ብሎ በመገናኛ ብዙሃን ሲታይ ነበር። አለማየሁ እና ኢዛና በየሃገሩ እየዞሩ ስለ አዲሱ ስርዓት መልካምነት ሲሰብኩ ከረሙ። ከዚያም አስመራ ድረስ ተልከው የሻእቢያውን መሪ ኢሳያስ አፈወርቂን በወታደሩ ስም ይቅርታ ጠይቀዋል።

አለማየሁ እና ኢዛና ለወያኔ በሰሩት ውለታ ሆላንድ ገብተው እንዲቀሩ ተደረገ። ይህም የተደረገበት ምክንያት በአውሮፓ የሚኖሩ ኢዮጵያውያንን ተቃዋሚ በመምሰልና በረቀቀ መንገድ እንዲያበጣብጡና እንዲሰልሉ ነው።
በሆላንድ ሃገር የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቆ ለወያኔ ቡድን የስለላ ስራ መስራት ወንጀል ነው። አለማየሁ የሆላንድ ዜግነት ቢኖረው ኖሮ ቅጣቱ የከፋ ይሆን እንደነበር ጉዳዩን እየተከታተሉ ያሉ የህግ ባለሙያዎች ተናግረዋል።
የአለማየሁ መባረር በተሰማ ግዜ በሮተርዳም ያሉ የህወሃት ደጋፊዎች የአቤቱታ ደብዳቤ በመጻፍ ፊርማ ማሰባሰብ ቢጀምሩም ሊሳካላቸው አልቻለም። የአቤቱታ ደብዳቤው ግለሰቡ እዚህ የተወለዱ ሁለት ለጆቹን እየመጣ እንዲጎበኝ ይፈቀድለት የሚል ነበር።
አለማየሁ ስንታየሁ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከሆላንድ ተባረረ። ኢዛና ግን አሁን የተቃዋሚ ጭንብሉን አውልቆ በግልጽ ወያኔ መሆኑን መናገር ጀምሯል። ኢዛና የሆላንድ ዜግነት ቢኖረውም በሆላንድ ሃገር ስራ ሰርቶ አያውቅም። የቀንና ማታ ስራው በፓልቶክ ላይ ነው። ባለፈው ወር ኢትዮጵያ የተጓዙ ዲያስፖራ ኢንቨስተሮችን እየመራ በቴሌቭዥን መግለጫ ሲሰጥ አይተነዋል። ይህ ትርኢት የወያኔ ኢንቨስተሮች በጨበጣ እንደሚንቀሳቀሱም ያሳየናል።

The post ሰበር ዜና: የወያኔ ሰላይ ከሆላንድ ተባረረ! appeared first on Zehabesha Amharic.

በሥራ ሂደት ባለቤቶች የተጥለቀለቀች ብቸኛዋ ሀገር! –ነፃነት ዘለቀ

$
0
0

ነፃነት  ዘለቀ (ከአዲስ አበባና ከፊንፊኔ)

ሰሞኑን አንድ ጉዳይ ገጥሞኝ የወያኔውን የዱርዬ መንግሥት በርካታ ቢሮዎች ማንኳኳት ነበረብኝ፡፡ ጉድ አየሁላችሁ፡፡ የጉድ ጉድ! ስንቱን ነግሬያችሁ እንደምዘልቀው ግን አላውቅም፡፡ በሀገራችን ተዝቆ የማያልቅ  ብዙ ጉድ እየፈላና እየተንተከተከ ነው፡፡ በአንዲት ሀገርና በአንዲት መናገሻ ከተማ ስንት መንግሥት እንዳለም ለማወቅ ሞክሬ አልተቻለኝም፡፡ አንዱ ጋ ስትሄድ አዲስ አበባ ይልሃል፤ ሌላው ጋ ስትሄድ ፊንፊኔ ይልሃል፤ ወደ አንዱ ኤፍ ኤም ብትሄድ ደግሞ ሸገር ይልሃል፡፡ አንዱ “ወደናዝሬት ልሄድ ነው” ሲልህ ሌላው “ወደአዳማ ልሄድ ነው” ይልሃል፡፡ ስሞችም ፖለቲካዊ ይዘት እየተላበሱ በአጠራር ልየነት መቀያየምና በነገር መጓነፍ ይታያል፡፡ “እህሉ አንድ ዓይነት ሴቱ አሥራ ሁለት” የሆነበት ዘመን ሆኗል፡፡ ዘመነ ግርምቲ! ቧይ!! አዲስ አበባ – ፊንፊኔ፣ ናዝሬት – አዳማ፣ ደብረ ዘይት – ቢሾቱ፣ አዋሳ – ሀዋሳ፣ ጅጅጋ -ጅግጅጋ፣ አለማያ- ሀሮማያ፣ ውጥንቅጡ የወጣባት ሀገር – ሰው በስያሜም ይለያያል? በስያሜና በተሰያሚ መካከል እኮ የባሕርይ ግንኙነት የለም፡፡ ስለዚህ ሰዎች ለምን በዚህ ቀላል ነገር ይሻኮታሉ? በተለመደው ቢጠራ ችግሩ ምን ይሆን? ባቢሎን በሣሎን፤ ባቢሎን በኢትዮጵያ፡፡

ወደ አንዱ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ሂድ – ወግ ነውና ሲዳሩ ማልቀስ የወያኔ “መንግሥት”ም ያው መንግሥት መባሉ ነው እንግዲህ፡፡ እናም ስትሄድ ምን እንደሚገጥምህ ያየሁትን ልነግርህ ነው – ተዘጋጅ፡፡

በብዙ መሥሪያ ቤቶች ከዘበኛ ጀምሮ እስከላይኛው ሥራ አስኪያጅ ወይም ሥራ አስፈጣሚ ድረስ የምታገኘው ከትግሬው ብሔር የተገኙ ጥቂት የተማሩ ወይም ሞፈር ቀምበር ሰቅለው የመጡ – ግን እንደከተመኛ የለበሱ – ማይም ሰዎችን ነው – ከመደነቋቆር በስተቀር የማትግባባቸው ፍጹም ማይማን፡፡ አልፎ አልፎም የመሥሪያ ቤቶች የመግባቢያ ቋንቋ የሀገሪቱ ኦፊሴላዊ ቋንቋ አማርኛ መሆኑ ቀርቶ ትግርኛ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ – ይሄ ምንም ማለት አይደለም፡፡ ይህን ያነሳሁት ለወቀሣ ሣይሆን የትግሬው ጠባብ ቡድን ወደ ዘጠና ሚሊዮን የሚገመተውን መላዋን የሀገሪቱን ሕዝብ በምን ያህል ብልጫ ገለባብጦ አንድን የመንግሥት መሥሪያ ቤት በቁጥጥሩ ሥር እንዳደረገው ለማሳየት ነው፡፡ እንጂ ማንም ዜጋ በፈለገው ቋንቋ የመግባባት መብቱ ተፈጥሯዊ እንጂ ሰብኣዊ ስጦታ እንዳይደለ እረዳለሁ፡፡ በትግርኛችን የብሔራዊ አገልግሎት ድርሻን መውሰድ ቀንቼበት ወይም ተመቅኝቼ አይደለም፡፡ ሁሉም የኔው ነው፡፡

መሄድ የነበረብኝ መሥሪያ ቤቶች በውነቱ ጥቂቶች ነበሩ፡፡ ነገር ግን በነዚያ መሥሪያ ቤቶች በታዘብኩት የተወላገደ ሀገራዊ ምስል ምክንያት ሌሎች ብዙዎችንም ጨመርኩ – ለግንዛቤየ ስል ብቻ (just for curiosity purpose)፡፡ እናም መከላከያና ውጭ ጉዳይም አልቀሩኝም – ከሃይማኖቱም ፓትርያርክ ጽ/ቤትና ምግባረ ብልሹ ማለትም “ምግባረ ሠናይ” የሚባለውን የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስታን ሆስፒታልን ጭምር በሰበቡ ጎበኘሁ፡፡

አንድ ነገር ማስቀደም ፈለግሁ፡፡ በደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ ሥርዓት ከነጮቹ ውስጥ ያን ወንድምና እህቶቻቸው በጥቁሮችና በቅይጦች ላይ የዘረጉትን የአፓርታይድ አገዛዝ አጥብቀው የሚቃወሙና የሚታገሉም ነበሩ፡፡ እነዚያን ዓይነት ጤናማ አእምሮ የነበራቸውና ያላቸው ምርጥ የዓለማችን ዜጎች ከየቆሻሻ ክምሮች ውስጥ እያፈነገጡ የሚወጡበት ሁኔታ ብዙውን ጊዜ ይታያል፡፡ የእናት ሆድ ዥንጉርጉር መሆኑ አዲስ አይደለምና ከወያኔም አንጀተ ብቡ እንደማይጠፋ ሁሉ ከለዬለት ሰይጣንም ተስቶትም ቢሆን ምሕረትን የሚያደርግ አይጠፋም፡፡ የነዚህ የፀረ አፓርታይድ ነጭ ታጋዮች ጉዳይ ግን ለየት ይላል፡፡ እነሱን የመሰሉ ፀረ ጽዮናውያንም እንዳሉ ስንሰማ ለሰዎች አእምሯዊ ዕድገት ያለን አድናቆት ይጨምራል፡፡ የሚገርማችሁ ነገር የሚጓዙበትን ብርሃን መሰል ጨለማ የመጨረሻ ዕጣ ፋንታ ሲረዱ ከ32 እና ከ33 ዲግሪ የኢሉሚናቲ የዕድገት ደረጃ ሣይቀር እየወጡ የጓደኞቻቸውን የቀን ቅዠት የሚያጋልጡና መልካም ሕይወትን መኖር የሚጀምሩ ደጋግ የቀድሞ የሉሲፈር እምነት አራማጆች አሉ፡፡ በበኩሌ ምንም እንኳን ትልቅ አደጋ የሚጋረጥባቸው መሆናቸውን ብረዳም በነዚህ ወደኅሊናቸው የሚመለሱ ሰዎች በጣም እደሰታለሁ፡፡ በዚህ መልክ የዘርም ይሁን የእምነት ጓዶቻቸውን የዕውር ድንብር የጨለማ ጉዞ እየከዱ ወደ እውነት ጎዳና የሚገቡና በስህተታቸው የሚጸጸቱ አሉ፡፡ በሀገራችንም የነዚህን ዓይነት ከጠማማ መንገድ ተመለሾችን ቁጥር እንዲያበዛልንና የነፃነታችንን ቀን እንዲያቀርብልን ፈጣሪን በጸሎት ተግተን እንወትውተው፡፡

የሩዋንዳን ነገር ሣልጠቅስ ማለፍ አልወድም፡፡ አክራሪ ሁቱዎች ቱሲዎችን በሚጨፈጭፉበት ጊዜ ለዘብተኛ ሁቱዎች  ቱሲዎችን የመታደግ ብዙ ታሪካዊ ሥራ ሠርተዋል፡፡ በቤታቸው ሸሽገው አደጋውን እንዲያልፉ ያደረጉ የጤናማ አእምሮ ባለቤት ሁቱዎች ነበሩ፡፡ እንደጓደኞቻቸው ሣያብዱና ሣይወፍፉ በጭፍጨፋውም ሣይሣተፉ ለቱሲዎች መልካም ነገርን በማድረግ አሁን ላለው አንጻራዊ ሰላም የበቁ፣ በዚያም ምክንያት ኅሊናቸውን በደም ታሪክ ያላጨቀዩ ሁቱዎች አሉ፤ ለደግ አሳቢ አእምሮ ምሥጋና ይድረሰው፡፡ ሁሉም ያልፋል፤ የማያልፍ ነገር ቢኖር ኖሮ ቁጭት ንዴታችን ወሰን ባልተገኘለት፡፡

ከፍ ሲል ያልሁትን ያልሁት አለምክንያት አይደለም፡፡ ደጋግ ትግሬዎች አለን፡፡ ከነፈሰው ጋር የማንነፍስና በወገኖቻችን መገፋትና መሳደድ/መሰደድ የምንከፋ፣ የምንበሳጭና የምንቆጭ ጥሩ ጥሩ ትግሬዎች አለን፡፡ አላህ ጨርሶ አይበድልም፡፡ ከንፍሮም ጥሬ ይወጣል፡፡ እናም ጥቂቶችም ቢሆኑ በአሁኑ ሸውራራ የትግሬ አገዛዝ አንጀታቸው የሚያርር በዚህም ምክንያት የዘር ሐረጋቸው ያመጣውን ሀገራዊ መቅሰፍት ለመንቀል ከጭቁኖች ጋር ለመታገል የቆረጡ አሉ፡፡ ትግላቸው እስከሞት የሚያደርስ መሆኑን እያወቁ ለኅሊናቸው ሲሉ ከመከረኛው ሕዝብ ጎን ተሠልፈው የሚዋደቁ እነአብርሃ ደስታና አሥራት አብርሃም፣ አብርሃም በላይ – እንዴት ነገሩ ይሄ አብርሃ የሚሉት ስም … ብቻ ጥቂት የማይባሉ ትግሬዎች አሉን፡፡ ጌታ ጥሎ አይጥልም፡፡ ጥቂትም ቢሆኑ የመከራ ገፈታችንን የሚጋሩ ትግሬዎች መኖራቸው ሸክማችንን የሚጋራን ከመኖሩ አኳያ መጠነኛ እፎይታ ይሰማናል፡፡ በተረፈ ተከድኖ ይብሰል፡፡ ለዛሬ ግን ለምን ይከደናል? ያየሁትን እዘከዝከዋለሁ፡፡

በዬመሥሪያ ቤቱ ኃላፊውም ዘበኛውም ጽዳቱም ትግሬ ነው፡፡ ለይስሙላ ቢሮ ተቀምጦ የሚገኘውን ኃይለ ማርያም ደሳለኝን የመሰለ መናጆና “ሲጠሩት አቤት፣ ሲልኩት ወዴት” ባዩን ዜጋ ታዲያ ከቁም ነገር እንዳትቆጥሩት – አንድም ሥልጣን የሌለው በዓይን ጥቅሻና በቀጭኒቱ ሽቦ ከትግሬዎች መንደር የሚታዘዝ መጋጃ ነው፡፡ ይህ በጣም ግልጽ ነው፡፡  ወ/ሮ ትብለፅ ጎይታይ – የሰው ኃይል አስተዳደር የሥራ ሂደት ባለቤት፣ አቶ መሓሪ ሽኑን – የወጪና ገቢ ቁጥጥር የሥራ ሂደት ባለቤት፤ ዶክተር ሐጎስ ዕንቋይ – የአማራ ክልላዊ መንግሥት ዕንባ ጠባቂ የሥራ ሂደት ባለቤት፣ አቶ ዘርዑ መዓሾ – የደቡብ ሕዝቦች ክልል የመሬት ድልድል የሥራ ሂደት ባለቤት፤ ወ/ሮ ሐረጓ ግደይ – የአዲስ አበባ ሴቶች ሊግ ሰብሳቢ፤ ወጣት አረጋዊ አስገዶም – የአዲስ አበባ ወጣቶች ሊግ የዘርፍ ሰብሳቢ፤ እማሆይ አብረኸት ፍትዊ የኪዳነ ምሕረት ገዳም እመምኔት፤ አባ ናትናኤል ኪሮስ የአ.አ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ፤ አቡነ ናትናኤል የኦርቶደክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክና… አቶ ማለትም ዶክተር ኃይለሚካኤል ጎይቶም የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ የዕድሜ ልክ ፕሬዝደንትና በወያኔ ማዕከላዊ ጽ/ቤት የሙስና ማቀላጠፊያ ዘርፍ  የሥራ ሂደት ባለቤት … አይ! ያሣፍራል፡፡ አንዳርጋቸው ያቺን ስድ ሴት በተመለከተ ሲናገር የአማርኛውን “ያሸማቅቀኛል” የሚለውን ቃል በስሜታዊነት ዘንግቶት በእንግሊዝኛው “cringe” አደርጋለሁ ብሎ ነበር፡፡ እኔም በዚህ የትግሬው ገዢ መደብ ክሪንጅ አደረግሁ – ተሳቀቅሁለት – ተሸማቀቅሁላቸው፡፡ አንጎል ምን ያህል ቢጠፋ የዚህችን ቀመር የኋላ ጦስ እንዴት ያጧታል? እንዴ! ከታች እስከ ላይ በትግሬ አስይዘህ ስታበቃ፣ ሌላውን ዜጋ እንደባይተዋር ወርውረህ ስታበቃ፣ ሌላውን ዜጋ በተለይም አማርኛ ተናጋሪውን ጨፍጭፈህና አስጨፍጭፈህ ንቀህና አዋርደህ ከሀገሩ ጉዳይም አግልለህ የትሚናውን ጥለህ ስታበቃ፣ … በዚህ በተደናበረ አገዛዝ ስንት ዓመት ትኖራለህ? የአንዲን ቃል ልድገመው – ተሸማቀቅሁላቸው፡፡ እኔ ያፈርሁት በነሱ ነው፡፡ ማይምነት ለካንስ እስከዚህን ያጋልጣል? ሱቅ ውስጥ እንደገባ ሕጻን ሁሉ ነገር ዐይን ዐዋጅ ሆነባቸውና ተጨነቁ፡፡

ትግሬዎቹ የተማሩ ቢሆኑና ለቦታው ቢመጥኑ ለኔ ጉዳየ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ለቦታው የሚመጥን ሰው ከሆነ ትክክለኛ አገልግሎት ይሰጣልና የሚበሳጭና የሚናደድ ተስተናጋጅ አይኖርም፡፡ እነሱ ግን ምኑንም ስለማያውቁት በዘር ብቻ እየተጠራሩ ሀገሪቱን የጨረባ ተዝካር አድርገዋታል፡፡ የአምስተኛ ክፍል ጄኔራልና የአሥረኛ ክፍል ዶክተር ባለሥልጣን ባለባት ሀገር – የመካከለኛና ዝቅተኛ ቢሮዎች ባለሥልጣናት እስከምን ድረስ ሊማሩ እንደሚችሉ ይታያችሁ፡፡ ሀገሪቱን ከዳር እዳር እየተጫወቱባት እኮ ነው፡፡ ኧረ ጓዶች ፍጠኑና ይህችን ሀገር ከዚህ አረንቋ በቶሎ እናውጣት ማለትም አውጧት፡፡

በየቀበሌዎችና ወረዳዎችም ሄጃለሁ፡፡ ሁሉም ቦታ አዛዥ ናዛዡ ትግሬ ነው፤ ልብ አድርጉ – የሌላ ዘውግ ተሹዋሚ የለም እያልኩ አይደለም – ሞልቷል፡፡ ግን ራሱን ችሎ አይሠራም – ከጥቃቅን ነገሮች በስተቀር፡፡ ኦነግ ወይም ከወሮች አንድኛው እንዳይለጠፍበት በመስጋት ሁሉም የሌላ ብሔር “ሹም” ክፉኛ እየተሳቀቀ ነው ሥራ ውሎ የሚገባው፡፡ በተረፈ የትግሬው ባለሥልጠን ደረቱን ነፍቶ ሲነፈርርና በሥነ ልቦናዊ የበላይነት እርካታ ሲንጎማለል ታያዩታላችሁ፡፡

ባይገርማችሁ የዛሬ ሁለት ዓመት አሥረኛ ክፍልን ማለፍ ያቃተው አንድ ወጣት ትግሬ አሁን የአንድ ወረዳ ሥራ አስፈጻሚ ነው፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉም ተሹዋሚ ትግሬ በችሎታውና በትምህርቱ ሣይሆን በዘውጋዊ ቀረቤታው ነው፡፡ የቀረቤታው ልክ ደግሞ ከትግሬም ትግሬ እየተማረጠ ነው፡፡ ቅድሚያ አድዋ፣ ቀጥሎ ሽሬ፣ ቀጥሎ አክሱም … ዓይነት እጅግ የወረደ ጎጠኝነትና መንደርተኝነት፡፡ በትምህርትና በችሎታ መመደብማ ለይቶለት ገደል ከገባ ሃያ አራት ዓመታትን ሊያስቆጥር ጥቂት ወራት ብቻ ቀርተዋል፡፡ መለስ – ባለበት ሲያስመልሰው ውሎ ይደርና –  በሕይወት እያለ ለፖለቲካው እስከታመነ ድረስ ዘበኛንም ሚኒስትር ማድረግ እንደሚቻል በኩራት ተናግሮ ነበር፡፡ ለንግግርም ለከት የሌላቸው እንዴት ያሉ ባለጌዎች ናቸው እኮ! ፈጣሪን ምን ቢበድሉት ይሆን እንዲህ አበለሻሽቶ የፈጠራቸው? እኛስ ብንሆን ኃጢኣታችን ምን ያህል ከተራራ ቢገዝፍ ይሆን ካልጠፋ አምባገነን እነዚህን የመሰሉ የሲዖል ትሎች የሰጠን? እስኪ ቁጭ ብላችሁ አስቡት፡፡ ሀሁንና ኤቢሲዲን ባልቆጠሩ ማይማን እንዴት ሀገር ትተዳደር? ምን ዓይነት ውርጅብኝ ነው? በስማም!

ጭንቀቴን ልናገር፡፡ አሁን በትግሬ ወያኔ ከላይ እስከታች የተጥለቀለቀውን የሀገሪቱን ቢሮክራሲ ነገ ነፃ ስንወጣ እንዴት አድርገን ነው የምናስተካክለው? ማን ነው ወንዱ ይህን ሁሉ በትግሬ የተጨናነቀ መሥሪያ ቤት ሁሉ አስተካክሎ እውነተኛ የሁሉም ብሄሮች የተማሩ አባላት በውድድር አልፈው ሀገሪቷን እንዲመሩ የሚያደርግ? በጣም ከባድ የቤት ሥራ ተጎልቶላችኋል፡፡ መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት ካልታከለበት ከሆድና ከዘረኝነት የቤት ጣጣ በስተቀር አንድም ዕውቀት የሌለውን ይህን የወያኔ መንጋ በሠለጠነና በተማረ ኃይል ለመተካት ትልቅ ችግር ይገጥማችኋል – እናንት ኢትዮጵያውያን፡፡ እኔ ኢትዮጵያ ነፃ በወጣች ማግሥት ይህን ጉድ ላለማየት እግሬ ባወጣኝ  ከሀገሬ የምሰደድ ይመስለኛል፡፡ እፈራለሁ፡፡ አሁን ያለው ሁኔታ በጣም ያስፈራል፡፡ ሁሉም በአንድ ብሔር ይያዝ? አደገኛ መቅሰፍት ነው! የሚገርምህ ሌላ ነገር – ወያኔ ከሆንክ የፈለገውን ዓይነት የአካል ጉድለት ቢኖርብህ ከሥራህ የሚያነቃንቅህ የለም፡፡ ጣቶች የሌሉት ፖሊስ፣ እጅግ እግር የሌለው (በአርትፊሻል የሚንቀሳቀስ) የጥበቃ አባል ታገኛለህ፡፡ የትግሬነት ማንነት ብዙ ምናልባትም ሁሉንም ህጎች ይደፈጥጥልሃል፤ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ዘረኝነት በምንም ዓይነት ምድራዊ ህግ የሚገዛ አይመስለኝም፡፡ ህግ የሚሠራው ለሌሎች እንጂ ለወያኔ አይደለም፡፡ ይህም በጣም አሣፋሪ ነው፡፡ ከህግ ውጪ ይነግዳሉ፤ ከህግ ውጭ ያመርታሉ፤ ከህግ ውጪ ያከፋፍላሉ፤ ከህግ ውጪ የሀገርን ሀብት ይቀራመታሉ፤ ከህግ ውጪ ያስገባሉ፤ ከህግ ውጪ ያስወጣሉ፤ ከህግ ውጪ ይጠቃቀማሉ፤ ከህግ ውጪ ሌሎችን ያፈናቅላሉ፤ ከህግ ውጪ የፈለጉትን ቦታ አጥረው ይይዛሉ – ይሸጣሉ- ይለውጣሉ፤ ከህግ ውጪ – ከፈለጉ ላይመልሱ ጭምር –  ከባንክ ይበደራሉ፤ከህግ ውጪ ያሻቸውን ሁሉ አላንዳች ማመንታት ይፈጽማሉ፡፡ እነሱ ህግና እግዜር ሆነዋል – ኧረ ከማያውቁት እግዜሩም በላይ፡፡ እኛን ምሥኪኖቹን ምን ይዋጠን?

ሌሎች ዜጎችን ስታዩዋቸው አንጀታችሁን ይበሉታል፡፡ ሀገሪቱ በአንድ ብሄር ቁጥጥር ሥር እንደመዋሏ ሌሎች የቀላዋጭነት ጠባይ ይታይባቸዋል – ሀገሪቱ የነሱም እንዳልሆነችና ባይተዋር የመሆናቸውን ጉዳይ ሳይወዱ በግዳቸው እንዳመኑ ያህል ትረዳላችሁ – ከሁኔታቸው፡፡ ለበርካታ ዓመታት በቅልውጥናና በማጎብደድ መኖር የበታችነት ስብዕናን ሣያዳብር የሚቀር አይመስለኝም – ስለሆነም ኢትዮጵያውያንን ከዚህ አገዛዝ ነፃ አውጥቶ የራሳቸውን ሰብኣዊና ብሔራዊ ማንነት እንደገና ለማላበስ ከፍተኛ ትግል ሣያስፈልግ አይቀርም፡፡ በየመሥሪያ ቤቱ እንደልቡ ሲደነፋና ሌሎችን እያንጓጠጠና እያላገጠባቸው ሲያዝ የምታዩት ትግሬ ነው – ባለጌው የሕወሓት ጀሌ ማለቴ ነው፡፡ ሌላውማ እንደኔው አክስትና አጎት በልመና አዲስ አበባን እያጥለቀለቀ ነው፡፡ ግራ የተጋባ ነገር ነው የገጠመን፡፡ ማጣፊያው ያጠረን ግራ መጋባት፡፡ ቁጭ ብለን የሰቀልነውን ቆመን ማውረድ ያቃተን ትልቅ አደጋ፡፡

ትግሬ ያልሆነ የይስሙላው ባሥልጣን ለምሳሌ ጽዳቷ ቢሮውን ለማጽዳት ብትገባ ልታዘው የመጣች መስሎት የሚያሸረግድላት አይጠፋም – ትግሬ በመሆኗ ብቻ፤ በራስ የመተማመን ነገር ከብዙዎች ዜጎች ሙልጭ ብሎ ጠፍቷል፤ ፍርሀት ነግሦአል፡፡ በየቦታው የሚታየው የሌሎች ወገኖች መሳቀቅ በአንዲት ሀገር የተለያዬ ዜግነት መኖርን ያመላክታችኋል፡፡ “ለካንስ አእምሯዊ የዕድገት ደረጃውን ባልጨረሰ ሰው መገዛት እጅግ ከባድና አዋራጅም ነው” ብላችሁ ትተክዛላችሁ – ልክ እንደኔ፡፡ በየሄድኩበት ቦታ ሁሉ በሀፍረት እየተሸማቀቅሁ እመለሳለሁ፡፡ ደግሞም የሚከረፋኝ ነገር አለ፡፡ በቃ – ቢሮውም፣ ሕንፃውም፣ ምኑም ምናምኑም እንዳንዳች ነገር ይሸተኛል – እጅግ የሚቀረናና የሚከረፋ ሽታ፡፡ የሽታው መንስኤ እንደሚመስለኝ ማይምነቱ፣ ዘረኝነቱ፣ መድሎው፣ በየሥፍራው የሚታየው የማስመሰል፣ የመዋሸትና በግልጽ የማጭበርበር ወያኔዊ ባሕርይ በድምሩ የፈጠሩት ግማት ነው፡፡ የመሥሪያ ቤቱ ጋጋታ፣ የሥራ ሂደቶቹና ንዑስ የሥራ ሂደቶቹ ብዛት፣ የሥራ ፈት “ሠራተኛ”ው መርመስመስ፣ የቴሌቪዥኑና የጋዜጣው ዐይን ያወጣ ቅጥፈትና ዕብለት፣ የውሸቱ ምርጫ የማታለልና ሕዝብን የማነሁለል ሂደት፣ ዘገምተኛ ዜጎችን ሣይቀር ያጡ የነጡ ድሆችን በካድሬነት መልምሎ በማሠማራት በሕዝብ ላይ የሚደረገው ወከባ … ሲታይ ሀገር በነሲብ እየተነዳች እንደሆነ ግልጽ ይሆንላችኋል፡፡ ከምርጫ ውጪ ሌላ ዜማ የለም፤ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የሚያካሂዱ ይመስል በም..ር..ጫ(በትግርኛ ሥልት አንብቧት) ወሬ ናውዘዋል – የማያውቁትን ምርጫ፡፡ በየሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ ትርምስ ነው፡፡ እዚህም እዚያም ውክቢያ ነው፡፡ መርመስመስ ነው፡፡ ለቀልድ በተቋቋመ የሚንስትር መሥሪያ ቤት ውስጥ አንድ ሚኒስትር ሦስትና አራት ሚኒስትር ዴታ፣ ሃያና ሠላሣ ዋና የሥራ ሂደት ባለቤቶች … ቅብጥርስ ቅብጥርስ፡፡ ግን ሁሉም ከንቱ፡፡ ጠብ የሚል ነገር የለም፡፡ ሁሌ ቁልቁል፡፡ የመፈክሩ ዓይነት አበዛዙ… ሙስና የዕደገት ፀር ነው … እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን … ራዕይህን ከግብ እናደርሳለን … አንተ ብትለየንም ራዕይህና ውድ ባለቤትህ አዜቢና ከኛ ጋር ናቸው(ከራሴው ምርቃት ጋር)፤ ከሦስት ዓመታት በላይ የወሰደ በየትም ሀገር ያልታዬ ሀዘን – በዚህስ ሰሜን ኮሪያም ሳትበልጠን አትቀርም – ወዲያው ነው የረሱት የነኪምን ሞት፡፡ የባልና ሚስት ወይም የልጅ፣ የወንድምና የእህት ሞት እንኳን በስድስት ወርና በዓመት ይረሳል፡፡ ሕይወት በየፈርጁ ነው፤ የሞተ ይረሳል -ያልሞተ ኑሮውን ይቀጥላል፡፡ በሞተ ሰው ምክንያት ሕይወት ቀጥ አትልም – እንደኢትዮጵያ፤ እኛ ከመለስ ሞት በፊት እንደነበርነው ቀጥ ብለን አለን – እንዲያውም ብሶብን፡፡ በሞተ ማላዘን የጤናማነት ምልክት አይደለም፡፡ ደግሞም ብዙዎቹ መለስን ከልባው ወደውት አይመስለኝም – ለማስመሰል ነው፡፡ እንደታዘብኩት በርሱ ስም ልጁን የሚጠራ እንኳን አልገጠመኝም፡፡ ይህ በራሱ የሚያሳየው እርሱን የወደዱት ለጥቅማቸው እንጂ ማፈሪያቱን እንደማይክዱት ነው፡፡

ደግሞም… የዓላማና ግቡ ዝርዝር … የዚህ ሚኒስትር መ/ቤት ራዕይ …. ዓላማዎች …. ግብ …. የሥነ ምግባር መርሆዎች … ታማኝነት፣ ግልጽነት፣ ሃቀኝነት፣ ተጠያቂነት፣ ቅንነት፣ ለሕዝብ ታዛዥነት፣ … አቤት አቤት የሚነበበው ጉድ! በተግባር ግን ሁሉም ከዜሮ በታች፡፡ መጥኔ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን! ሶማሌና ጂቡቲ በስንት ጣማቸው! ምነው ጂቡቲያዊ ወይም ፊጂያዊ ወይንም ዶሞ ሃይቲያዊ ሆኜ በተፈጠርኩ ኖሮ፡፡

ለማንኛውም የቤቴን የሰሞኑን አዲስ ሹመት ልግለጽላችሁና ልሰናበት፡፡ መቼም ጊዜው የቀልድ ሆኗል፡፡ የቤተሰቤ አባላት ለጊዜውና ለአሁኑ ስድስት እንደሆኑ ይታወስልኝ – ቡችዬንና ውርየን ጨምሮ፡፡

 

በህገ መንግሥታችን አንቀጽ 39 መሠረት የነፃነት ዘለቀ ቤት አዲሱ የሥልጣን መዋቅር

 

ዶክተር ነፃነት ዘለቀ

የቤቱ የውጭ ጉዳዮች የሥራ ሂደት ባለቤት

ረዳት ፕሮፌሰር ሸዋርካብሽ እርገጤ

የቤቱ የቤት እመቤትነት ጉዳዮች የሥራ ሂደት ባለቤት

 

ወጣት ዘገየ ነፃነት (ወንድ ነው)

የቤቱ ፀረ-ኢሣት አባላትን የማብዛትና ፎክስሙቪስን የማዘውተር ንዑስ የሥራ ሂደት ባለቤት

 

ሕጻን ደምመላሽ ነፃነት

የቤቱ የሞሰብና ድስት ጉዳዮች ንዑስ የሥራ ሂደት ባለቤት

 

ችሎማደር (ቡቺ)

የግቢው ፀጥታና ደኅንነት ጉዳዮች የሥራ ሂደት ባለቤት

በድምጽሽ ይራዱ (ውርዬ)

የቤቱ ሞሰብ ገልብጥ ዐይጦችን አባራሪ ግብረ ኃይል የሥራ ሂደት ባለቤት

 

ማሳሰቢያ፡- ይሄ አበበ ገላው የተባለ ልጅ ነገር መፈልፈል ይዟልና ለርሱ ሸር ላለመመቸት ስል              የኔን የዶክትሬት ማዕረግ ያገኘሁት እንደወያኔዎቹ ከሴንቸሪ ዩንቨርስቲና ከመሳሰሉት           ዲግሪ ቸብቻቢዎች በዶላር ገዝቼ ሣይሆን በላቤና በጥረቴ በቤተሰብ ጉባኤ የተሰጠኝ            መሆኑን እንዲሁም ክብርት ባለቤቴ በሆም ኢኮኖሚክስ የረ/ፕሮፌሰርነትን ማዕረግ ከዚሁ       ቤተሰባችን ያገኘች መሆኗን ልገልጽ እፈልጋለሁ(አይ የምትጠምቀው ጠላ – የዶሮ ዐይን              ይመስላል፡፡)

ዘግይቶ የደረሰኝ አዝናኝ ወሬ!

የወያኔ የምርጫ ቡችሎች እንዲህ አደረጉ አሉ፡፡ በዚያን ሰሞን ደብረ ዘይት አካባቢ የምግብ ዘይትን ከየሱቁ ያጠፋሉ፡፡ ከዚያም ሕዝቡ ሲንጫጫ በየቀበሌው ያመጡና ሕዝቡ ወደነዚያ ቀበሌዎች በመሄድ ዘይት እንዲገዛ ያስነግራሉ፡፡ ነዋሪው ወደየቀበሌው ሲሄድ ግን “የምርጫ ካርድ የማይወስድ ዘይት አይሰሸጥለትም” ይሉና በግድ ካርድ ያስወስዳሉ፡፡ ይቺ ናት ምርጫ፡፡ ሕዝብን እያስራብክና በመሠረታዊ ፍላጎቱ እየመጣህ ምርጫ ካርድ እንዲወስድ ማስገደድ፡፡ ከዚያም በኮሮጆ ገልባጭ ልዩ ኃይል የሕዝብን ካርድ ለወያኔ ማዛወር፡፡ ከዚያም የግፍ አገዛዝህን መቀጠል፡፡ ቀልደኞቹ የወያኔ የምርጫ አስፈጻሚ ካድሬዎች ልክ ይሕዋ ምሥክሮች     ይቺን ጽሑፍ አይተዋታል?” እያሉ ሃይማታውን ለማስፋፋት እንደሚሞክሩት የወያኔ ጭፍሮችም በየመንገዱና በየጥጋጥጉ በየመውጫና መግቢያ በሮቸ እየጠበቁ “የምርጫ ካርድ ወስደሃል?” እያሉ ሲያሰለቹ ብታዩ ደግሞ አዲስ ሃይማኖት ተመሠረተ ወይ ትላላችሁ፡፡ የጉድ ሀገር፡፡ አፉን ከፍ በሚውል የምርጫ ካርድ መውሰጃ ጣቢያ ስንትና ስንት ሚሊዮን ሕዝብ መመዝገቡን ስንሰማ የወያኔውን ውሸት ለከት የለሽነት እንረዳለን፡፡ በ97 ያ ሁሉ ሕዝብ ተመዝግቦ 26 ሚሊዮን ነበር የተባለው – እርግጥ ነው ያ ቁጥር እውነትም ሊሆን ይችላል፡፡ በቀጣዩ የ2002 “ምርጫ” ግን ጥቂት መቶ ሺዎችን መዝግበው ሲያበቁ በሀገሪቱ 32 ሚሊዮን መራጭ እንደተመዘገበ ቅንጣት ሣያፍሩ በሚዲያቸው ለፈፉ፡፡ ቁጥር የሚያውቁ አይመስሉኝም እነዚህ ደነዝ ወያኔዎች፡፡ ከሁሉም የበደላቸው እርጉሞች፡፡

comment_stage_5

 

 

 

The post በሥራ ሂደት ባለቤቶች የተጥለቀለቀች ብቸኛዋ ሀገር! – ነፃነት ዘለቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

የ 119ኛው ዝክረ አድዋ ፤ 1888   –ከበደ አገኘሁ ቦጋለ

$
0
0

Battle of Adwaየተከበራችሁ አባቶች ፥ እናቶች፥ ወንድሞች፥ እህቶችና ልጆች ! ዛሬ በዚህ የተሰባሰብነው ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን የዛሬ 119 ዓመት እንደዛሬው በነገድ ወይምብ ብሔር እንዲሁም በሃይማኖት ሳይከፋፈሉ ፥ ለአንድ ብቸኛ ዓላማ በአንድነት ተሰልፈው ባህላቸውን ፤ ሃይማኖታቸውን፤ ታሪካቸውን፤ ሰብአዊና ብሔራዊ ነፃነታቸውን፤ ባጠቃላይ ኢትዮጵያዊ ማንነታቸውን አጥፍቶ የቅኝ ተገዥ ባርያ አድርጎ ለመግዛት ከአህጉረ አውሮፓ ተንቀሳቅሶ፥ ባህረ ኢያሪኮንና ቀይ ባሕርን ተሻግሮ፥ የእናት አገራችንን ክብረ ወሰን ጥሶ የገባውን የጣልያን ወራሪ የጠላት ጦር አይቀጡ ቅጣት ቀጥተው ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ጥቁር ሕዝቦች በአውሮፓውያን ቅኝ ገዥዎች ላይ ድል ተቀዳጅተው በዓለም ታሪክ ውስጥ ታላቅ ምዕራፍ ያስመዘገቡትን ታሪካዊ ዕለት እኛ የልጅ ልጆቻቸው በኩራት ለማስታወስ ነው ። ይህ ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን ደማቸውን ቀለም አጥንታቸውን ብዕር አድርገው ያስመዘገቡት ታላቁ የታሪክ መዝገብ የተመዘገበበት ዕለት፥ እሑድ ዕለተ ሰንበት ፥ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም ነበር።

ለመሆኑ የጦርነቱ መንስኤ ምን ነበር ?

አውሮፓንን ያጥለቀለቀው የ19ኛው ምእት ዓመት ዘመናዊ የእንዱስትሪ ለወጥ ወይም እንዳስትርያል ሪቮሉሺን ለእንዳስትሪያቸው ጥሬ ዕቃ፥ ማለት እንደማዕድን የመሳሰሉትን ሀብተ ከርሠ ምድሮች እንዲፈልጉ አውሮፓውያኑን አስገደዳቸው። ስለዚህ ዘመናዊ እንዳስትሪ ባስገኘላቸው ዘመናዊ የጦር መሳርያ አውሮፓዊ ያልሆነ ዘር የማይኖርባቸውን የአፍሪካንና የ እስያን ፤ ቀደም ብለውም የሰሜንና የደቡብ አሜሪካን ነባር ሕዝቦች እየጨፈጨፉ በቁጥጥራቸው ስር አደረጉ።የፈለጉትን ጥሬ እቃም በነፃ ማጋዝ ፤ ያመረቱትን ሸቀጥም በቅኝ በሚገዟቸው አገር ሕዝቦች ላይ በማጋረፍ ካፒታሊዝምን ገነቡ። በቅኝ የሚገዟቸውን ሕዝቦች ነባር ኃይማኖታቸውን፣ ቋንቋዋቸውንና ታሪካቸውን ለወጡት። የስነ መንግሥት፥ የምጣኔ ሀብት፥ የማኅበራዊ ኑሮ ነፃነታቸውንና ሰብአዊ ክብራቸውን ገፈፉት። ስነ ልቦናቸውን በመቀየር በራሳቸው እንደሰው  የመተማመን ባህርያቸውን እንዲያጡ በማድረግ የበታችነት ስሜት እንዲያድርባቸው አደረጉ። ባጠቃልይ በቃላት ለመግለጽ የሚያስቸግር ኢሰብአዊ ድርጊት የሚፈጽሙበት ዘመን ነበር። ይህን በመሰለው የዓለም ተጨባጭ ሁኔታ ፥ አውሮፓዊ ያልሆነ ሕዝብ ፥ በተለይም ጥቁር አፍሪካዊ ሕዝብ ሁኖ ለአውሮፓውያን ነጮች አልገዛም ፣ ክብረወሰኔንና ሰብአዊ ክብሬን አላስደፍርም ብሎ ለውጊያ መሰለፍ የማይሞከር እርምጃ ነበር። ዘመኑ ነጮች ነጭ ያልሆነውን ሕዝብ ነፃነት መግፈፍ ከላይ ከአዶናይ (ከአምላክ) የተሠጣቸው ሥልጣን አድርገው ይቆጥሩት ነበር።ለዚህ አላማቸውም ‘የሞራል የበላይነት አለን ‘ ይሉ የነበሩት ምስዮኖቻቸው በክርስትና ስም  “የቄሣርን ለቄሣር ፥ የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር አድርግ ” የተባለውን መለኮታዊ ትእዛዝ ጥሰው የቄሣራውያን መሳርያ ሁነው ከክርስትና እምነት ጋር የተቃረነ የግፍ ተልእኮ ይፈጽሙና ያስፈጽሙ ነበር። በክርስትና ስም የተፈጸመውን ባርባራ ኪንግሶልበር የተባሉ አሜሪካዊት “ ዘ ፖይዝን ውድ ባይብል” በተባለው ታሪካዊ ልብ ወለድ መጽሐፋቸው በሰፊው ገልጸውታል። ፖፕ ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛም ይህን በሚመለከት የዛሬ 18 ዓመት አካባቢ በዘመኑ በክርስትና ስም ግፍ ለተፈጸመባቸው ሕዝቦች ይቅርታ ጠይቀውበታል።

አውሮፓውያን በዚህ መልክ በተለይም በአፍሪካ ሕዝቦች ላይ ይህን ግፍ ሲፈጽሙበት በነበረበት ዘመን አገራችን ኢትዮጵያ ለዚህ አይነት የነጮች ግፍ ሰለባ ባትሆንም በራሷ ልጆች በመሳፍንት አገዛዝ ተከፋፍላና በእርስ በርስ ጦርነት ተዳክማ ነበር። በዚህም ምክንያት ማዕከላዊ መንግሥቷ መኖሩና አለመኖሩ ለውጭ ኃይሎች አጠራታሪ ነበር። በዚህ ሁኔታ እንግሊዞች በ1797 ዓ.ም. ምጽዋ ላይ ሰፈሩ። ነገር ግን አካባቢው ያኔ በራስ ሚካኤል ስዑልና ማዕከላዊ መንግሥቱን ወክለው በነበሩት በጎንደር ነገሥታት ቁጥጥር ሥር እንደነብር በሚገባ የሚያረጋግጡ የታሪክ መረጃዎች ኣሉን። ይህ በዚህ እንዳለ ፥ በ1846 ዓ.ም ጀምረው ቆላማውን የባህረ ነጋሺ አካባቢ ግብጾች ሰፍረውበት ነበር። ከዚያም አንድ የግል ንብረት የነበረ የኢጣልያ የባህር ጭነት ማጓጓዥያ ኩባንያ አሰብን ከአካባቢው መስፍን (ሡልጣን) በ1874 ዓ.ም ገዛው። በመቀጠልም ከ3 ዓመት በኋላ በእንግሊዞች አበረታችነት በ1877 ዓ.ም የኢጣልያ ሠራዊት ምጽዋ ላይ ሠፈረ። በዚህም ወቅት ግብጽም በበኩሏ በዚህ አካባቢና በሃረር በኩል ክብረ ወሰናችን ደፍራብን ነበር።

ይህን በመሰለ ሁኔታ አገራችን ኢትዮጵያ ከአድዋ ጦርነት በፊት ለ20 ዓመታት ያለ እረፍት ከውጭ ጠላቶች ጋር ክብረ ወሰኗንና ብሔራዊ ነፃነቷን ለመጠበቅ ስትታገል መቆየቷ ይታወሳል። ለዚህ ታላቅ ብሔራዊ ነፃነትና ማንነት ጥበቃ ጀግኖች መሪዎቿም መስዋዕት ሁነዋል። ከተሰውት መሪዎች መካከል ሁለቱን እንጥቀስ። ዘመነ መሳፍንትን አጥፍተው ዘመናዊትና አሐዳዊት ኢትዮጵያን የመሠረቱት ጀግናው አፄ ቴዎድሮስ በጀኔራል ናፔር የተመራውን የእንግሊዝ ጦር በለስ ቀንቷቸው ድል ባያደርጉትም መቅደላ ላይ በ1860 ዓ.እ ‘’እምተቀንዮ በነገደ ያፊት ፥ ይሄሰኒ መዊት” ብለው ራሳቸውን ሰውተዋል። አዎ ‘የአቢሲንያው አምበሳ በአሮፓ ድመት ተዋርጀ እጅ ሰጥቸ ከምገዛስ የማይቀረውን ሞት ብመርጥ ይሻለኛል’ ብለው ፥ በፈረንጆች አቆጣጠር April 13, 1868 (በእኛ በ1860 ዓ.ም)፣ ሊረዳቸው የሚገባው የወገን ኃይልም ለጠላት አሳልፎ ስለሠጣቸው፣ የራሳቸውን ሺጉጥ ጥይት ጠጥተው፥ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ ከ13 ዓመት የውስጥ ውጣ ውረድ በኋላ ይህን በሚመስል አሳዛኝ ሁኔታ ተሰውተዋል።

ከአፄ ቴዎድሮስ አሳዛኝ እረፍት በኋል ለሁለት ዓመት ያህል ንጉሥ ተክለ ጊዮርጊስ በሚል የዘውድ ስም የነገሡት ዋግሹም ጎበዜን ድል አድርገው የነገሡት አፄ ዮሐንስ 4ኛ እና የጦር መሪያቸው የነብሩት ጀግናው ራስ አሉላ አባ ነጋ የመሩት የኢትዮጵያ ጦር ፥ በ1867 ዓ.እ ጉንደት ላይ እና በ1868 ዓ.እ ጉራ ላይ የግብጽን ጦር ፣ በ1879 ዓ.እ  ዶጋሌ ላይ የኢጣልያንን ጦር ተዋግቶ ድል ተቃዳጅቶ ነበር። ከዚያም በመቀጠል አፄ ዮሐንስ ጎንደርን ወሮ የነበረውን የድርቡሽ/ሱዳን ጦር ለመዋጋት የሰሜኑን ግንባር ትተው ወደ ጎንደር ተመለሱ። ጎንደርን ነፃ ካወጡ በኋላ መተማ ከሀገራቸው ድንበር ላይ መጋቢት 1 ቀን 1881 ዓ.ም ፥ በፈረንጆች March 10, 1889 ለሀገራቸው ተሰውተዋል።

ስለዚህ እነዚህ ያለምንም ፋታ ከውጭ ወራሪ ኃይል ጋር ለ20 ዓመታት የተደረጉ ጦርነቶች ይህን ዛሬ የምናስበውን የአድዋን ድል በአፄ ምንይልክ ለተመራው ኅብረ-ብሔራዊ ጦር ትልቅ ልምድና ወታደራዊ ተመክሮ ሠጥተውት ነበር። በአንፃሩ ደግሞ ለ20 ዓመታት የተደረገው የማጥቃትና የመከላከል ጦርነት ብዙ ብሔራዊ የሀብት ምንጭ አስጨርሶ ነበር። የዘመነ መሳፍንት ስሜትም በአንድ አንድ አካባቢ ጨርሶ አልጠፋም ነበር። ከዚህም በተጨማሪ ከፍተኛ ድርቅ ሀገሪቷን ጎድቷት ስለነበር  ከአድዋ ድል በኋላ ጣልያንን ከኤርትራም ጭምር ጨርሶ ለማስወጣት የነበረውን ወታደራዊ እቅድ እንዲደናቀፍ አድርጎታል። ስለዚህ ሰው ሠራሽና የተፈጥሮ ችግሮች ተባብረው የኢትዮጵያን ሕዝብ አጎሳቁለውት ስለነበር ነበራዊ ሁኔታው ለኢጣልያ ወራሪ ጦር ምቹ ሁኒታን የፈጠረ መስሎ ይታይ ነበር። ሆኖም ግን ይህን የተፈጥሮና ሰው ሠራሺ ችግር አፄ ምንይልክ በጣም አዋቂና አስተዋይ መሪ ስለነበሩ ሁሉንም በብልሀትና በትግስት ይዘውት ነበር። ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ብጡል ኃይለ ማርያምም ‘’መልካም ሚስት ለባልዋ ዘውድ ናት” እንደተባሉት ፥ እውነትም ዘውዳቸው ስለነበሩ የሚሠጧቸውን ምክር ሁሉ ንጉሠ ነገሥቱ በጥሞና ያዳምጡ ነበር። እቴጌ ጣይቱ በሀገራችን ሥርዓተ ትምህት መሠረት ከውዳሴ ማርያም ጥሬ ንባብም አልፈው ዜማውን ፤ እንዲሁም ጾመ ድጓና ቁም ጽፈት ጭምር ደበረ ታቦር ኢየሱስ እየተማሩ ያደጉ ሴት ነበሩ። ከዚህም ሌላ የስሜኑ መስፍን የደጃዝማች ዉቤ ኃይለ ማርያም ወንድም የደጃዝማች ብጡል ኃይለ ማርያም ልጅ ስለነበሩ የቤገምድርንና ስሜንን ፥ ከዚያም አልፈው ጠቅላላ የሰሜን ኢትዮጵያን ሕዝብ ስነልቦና በሚገባ ጠንቅቀው ያውቁ ስለነበር አፄ ምንይልክ “እቴጌ ጣይቱ ብርሃን ዘኢትዮጵያ “ የሚል ማኅተመ ስም ሠጥተዋቸው ነበር። እቴጌ ጣይቱ ጎንደሬ ብቻም ሳይሆኑ ከወሎ ኦረሞወችና ሺሬ ከትግራይዮችም ተወላጅ ስለነብሩ ፥ ያኔ የጣልያን ጠቅላይ ምንስቴር የነበረው ፍራንሲስኮና መረብ ምላሺን “ኤርትራ” በሚል ስም በጣልያን ፓርላማ አሰይሞ ፥ ከአፄ ዮሐንስ ዘመነ ዕረፍት ጀምሮ ሲገዛ የነበረው ጀኔራል ባርትየሪ ውስጥ ውስቱን የሰሜን ኢትዮጵያን መሳፍንቶች በምንይልክ ላይ እንዲያምፁ ሲያደርጉት የነበረውን ማባበል እቴጌቱ በነበራቸው የሥጋ ዝምድና ትስስር አክሽፈውታል። ማለት የሰሜን ኢትዮጵያ መሳፍንቶች የጠላትን የማባበልና የመከፋፈል  ሴራ ሳይቀበሉት ቀርተዋል።

ጣልያን ኢትዮጵያን ጠቅልሎ የመግዛት ዓላማው የማይሳከለት መሆኑን ከተረዳ በኋላ የኤርትራ ግዛቱ ብቻ በኢትዮጵያ በኩል እውቅና እንዲያገኝለት ወሰነ። አፄ ምንይልክም ዙርያውን በአውሮፓ ቅኝ ገዥ ኃይሎች ተከበው ስለነብሩ ሁሉን ከማጣት ብለው፥ ከነበረው ተጨባጭ ሁኔታ ተነስተን ስናየው ሃሳቡን መቀበል ግድ እንደሆነባቸው መገመት አያዳግትም። ስለዚህ በሁኔታው አስገዳጅነት ሚያዝያ 25 ቀን 1881 ዓ.ም ኢጣልያ የኤርትራ ቅኝ ገዥ መሆኗን የሚያረጋግጥ 19 አንቀጽ ያለው ስምምነት ወሎ ውስጥ ልዩ ስሙ ውጫሌ ከተባለ ቀበሌ ላይ ተደረገ። በተለይ አንቀጽ 17 በጣልያንኛ የተጻፈው ከዐማርኛው ጋር የተቃረነና አሻሚ ትርጉም ይዞ ነበር ለአውሮፓ መንግሥታትና ሕዝቦች የተበተነው። ኢትዮጵያ የኢጣልያ ጥገኛ (protectorate)እንደሆነችና ከውጭ መንግሥታት ጋር የሚኖራት የዲፕሎማቲክ ግንኙነት በኢጣልያ በኩል ካልሆነ እንደ ነፃ ሀገር በራሷ ብቻ ማድረግ እንደማትችል ተደርጎ ነው ለአውሮፓ መንግሥታት የተበተነው ።

ይህ ውል የተጭበረበረ እንደነበር በኢትዮጵያ በኩል ሊታወቅ የቻለውም አለቃ አጽመ ጊዮርጊስ የተባሉ ኢትዮጵያዊ የቋንቋ ሊቅ በጣልያንኛ የተጻፈውን እንዲመረምሩት ተሠጥቷቸው ስለነብር ፣ አለቃ ይህን ነገር በሚገባ ለንጉሡ አደገኛነቱን አስረዷቸው። ይህን እንደተረዱ አፄ ምንይልክ ወደቤተ መንግሥታቸው እየተመላለሰ ፤ ‘’ጌታየና ግርማዊ’’ እያለ በለሰለሰ አንደበቱ በውዳሴ ከንቱ ሲደልላቸው የነበረውን ስኞር ኮንቲ አንቶሊኒ የተባለውን፥ ማለት ጣልያንን ወክሎ ውሉን የፈረመውን ዲፕሎማት አስጠርተው ፥ አንቀጽ 17 የተጭበረበረና ከዐማርኛው ቅጅ/ኮፒ በፍፁም የማይገናኝ መሆኑን እንደደረሱበት ነገሩት። እሱ ግን በተለመደው ለስላሳ አንደብቱ ‘’ይህን ያለወት ሰው በመንግሥትዎ ላይ ቅን አስተሳሰብ የሌለውና በጠላትነት ሊነሳብዎ ያሰበ ሰው መሆን አለበት አንጅ ነገሩ ምንም የተጭበረበረ ትርጉም የለውም” ብሎ ለጊዜው አሳመናቸው። ንጉሡም በአለቃ ላይ ተበሳጭተው አለቃን እንዲታሰሩ አደረጓቸው። ‘እውነትና ብርሃን እያደር ይጠራል ‘ ነውና ፥ ሳይውል ሳያድር ሙሴ ማሪ ዴሎሜኩል የተባለ ፈረንሳዊ ዲፕሎማት በጅቡቲ በኩል ወደ አንኮበር መጥቶ ልክ አለቃ አጽመ ጊዮርጊስ የተናገሩትን ነገር ሳይጨምርና ሳይቀንስ በማስረዳት አገራቸው ኢትዮጵያ የጣልያን ጥገኛ አገር እንደሆነች የአንቀጽ 17ቱ ውል እንደሚያስረዳ በአውሮፓ መንግሥታት ዘንድ ግንዛቤ እንደተጨበጠ ነገራቸው። ንጉሡም አለቃን ይቅርታ ጠይቀው ፈቷቸው።

አፄ ምንይልክ ይህን ከተረዱ በኋላ ለአውሮፓ መንግሥታት ማስተባበያቸውን ላኩ። ኢትዮጵያ ያቀረበችውን ማስተባበያ ያኔ ሦስተኛውን ዓለም በአብዛኛው በቅኝ ስትገዛ የነበረችው ታላቋ ብርታንያ  አልቀበለውም አለች። አፄ ምንይልክም እናንተ ባትቀበሉት ‘ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔርና ልጆቿ ትዘረጋለች’ ብለው በአምላካቸውና በሕዝባቸው ተማምነው አሻፈረኝ አሉ። አንቀጽ 17ን ብቻም ሳይሆን ጠቅላላ የውጫሌን ውል ኢትዮጵያ ማፍረሷን ወይም መሰረዟን ንጉሠ ነገሥቱ ጥር 4 ቀን 1885 ዓ.ም. ለዓለም አሳወቁ። ፈረንሣይና ሩሲያ የኢትዮጵያን ተቃውሞ በመቀበል የኢጣልያንን የኢትዮጵያ የበላይ ጠባቂነት እንደማይቀበሉት ተስማሙ። በተለይ የሩሲያው ንጉሥ ወይም ዛር ኒኮላስ ወታደራዊ እርዳታ ለማድረግ ወሰኑ። የጦር መሣርያም በመላክ ውሳንያቸውን በድርጊት ፈጸሙ።

በዚህ ምክንያት ከሁለት ዓመት ውዝግብ በኋላ የጣልያን ወራሪ ጦር መረብን ተሻግሮ ደብረ ሃይላ ላይ አደጋ ጥሎ አካባቢውን እንዲጠብቁ ተሹመው የነበሩትን የትግራይ ባላባቶች፣ ፊታውራሪ ንጉሤን፥ ቀኛዝማች ኃይለ ማርያምን፥ ቀኛዝማች አንድአርጋቸውንና ባላምባራስ በየነን ወግቶ በመስከረም 29 ቀን 1888 ወረራ መጀመሩን አፄ ምንይልክ ሰሙ። ከዚህ በኋላ አፄ ምንይልክ ጥቅምት 2 ቀን 1888 ዓ.ም የሚከተለውን የጦርነት አዋጅ አውጀው ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን ጦር ግምባር ከእቴጌ ጣይቱ ጋር ኅብረ ብሔር ሠራዊታቸውን መርተው ለመንቀሳቀስ ተዘጋጁ። የጦርነቱ አዋጅ በዛን ጊዜው ዐማርኛ ይህን ይመስል ነበር።

ቃለ አዋጅ !

“እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላት አጥፍቶ፣ አገሬን ጠብቆ አኖረኝ። እኔም እስካሁን በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ። እንግዲህ ብሞትም ሞት የሁሉም ነውና ስለኔ ሞት ኣላዝንም። ደግሞም እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም። እንግዲህም ያሳፍረኛል ብየ አልጠራጠርም።

አሁንም አገር የሚያጠፋ፥ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት እግዚአብሔር የወሰነልንን ባህር አልፎ መጥቷል። እኔም ያገሬን ከብት ማለቅ የሰውንም መድከም አይቸ እስካሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደ ፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር።

አሁን ግን በእግዚአብሔር ረዳትነት አገሬን አሳልፌ አልሰጠውም። ያገሬ ሰው ! ካሁን ቀደም የበደልኩህ አይመስለኝም። በድየህም ከሆነ ለሀገርህ ስትል ይቅር በለኝ። አንተም እስካሁን አላስቀየምከኝም። ስለዚህ ጉልበት ያለህ በጉልበትህ እርዳኝ። ጉልበት የሌለህ ለሚስትህ፥ ለሃይማኖትህ፥ ለሀገርህና ለታሪክህ ስትል በጸሎትህ እርዳኝ። ወስልተህ የቀረህ ግን ኋላ ትጠላኝ አለህ ፣ አልተውህም ! ማርያምን ! ለዚህ አማላጅ የለኝም ! “ የሚል ነበር የአዋጁ ቃል ።

አዋጁን አውጀው ወደ ሰሜን ጦር ግምባር ከመሄዳቸው በፊት የተቀረውንም የሀገሪቱን ክፍል ዙሪያውን አውሮፓውያን ከበውት ስለነበር ወሰን ጠባቂ ጦር መመደብ ነበረባቸው። በዚህ መሠረት የጅማው ሹም ጅማ አባ ጅፋር ፥ የሊቃው ሹም ደጃዝማች ገ/እግዚአብሔርና ደጃዝማች ጆቴ፥ የወላይታው ሹም ንጉሥ ጦና ካዎና ሌሎች፥ የምዕራቡንና ደቡቡን ድንበር እንዲጠብቁ። በምሥራቅና በሰሜን ምሥራቅ ደግሞ ከአፋር አርበኞች ጋር ተባብረው በአሰብ በኩል ጠላት እንዳይመጣ እንዲጠብቁ ራስ ወልደ ጊዮርጊስ፥ ደጃዝማች ተሰማ ናደውና የወሂን አዛዥ ወልደ ጻድቃን 15,000 ጦር ይዘው እንዲሰለፉ ሁኖ ነበር።የመናገሻ ከተማዋንና አካባቢውንም ራስ ዳርጌ ሣህለ ሥላሴ፥ ራስ ልዑል ሰገድና ደጃዝማች ኃይለ ማርያም 8000 ጦር ይዘው እንዲጠብቁ ተመድበው ነበር።

ይህን ካጠናቀቁ በኋላ የሰሜኑ ዘመቻ ቀጠለ። የመጀመሪያውን የጠላት ጦር አምባ ላጌ ላይ በፊታውራሪ ገበየሁና ፊታውራሪ ተክሌ የተመራው የግንባር አብሪ ጦር በሻለቃ ቶዘሊን ይመራ የነበረውን የጠላት ጦር  ኅዳር 28 ቀን 1888 ዓ.ም ደምስሰው ጠላት ሲጠቀምባቸው የነበሩትን መድፎችና ሌላ መሳርያ ከነብዙ ጥይቱ ማርከው፥ የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ ከአምባይቱ ላይ ሰቅለው እያውለበለቡ ቆዩ። (የአምባላጌ ከፍታ 11,279 ፊት ነው።) ቀጥለውም ግፋ ወደፊት በማለት ታህሣስ 29 የክርስቶስ የሥጋዌ ልደት መታሰቢያ ቀን መቀሌ ደርሰው መሺጎ ከነበረው ከጠላት ጦር ጋር ፍልሚያ ጀመሩ። ነገር ግን ምሺጉን ሰብሮ መግባት ከወገን በኩል ከፍተኛ መስዋዕትነት የሚጠይቅ መሆኑ ስለተረጋገጠ ፥ እቴጌ ጣይቱ ሲመሯቸው ከነበሩት መካከል 300 አርበኞችን ጠላት ባልጠበቀው መንገድ ልከው ፥ ጠላት ሲጠቀምበት የነበረውን የውሀ ምንጭ ኣስደፈኑት። ከ15 ቀን ቆይታ በኋላ የጠላትን ጦር በተለመደው ኢትዮጵያዊ ሰብአዊ ርህራሄ ምሺጉን ለቆ እንዲሸሺ ምህረት አደረጉለት። የዚህ ታሪክ ምንጭ አንዱ ከሆኑት ከአቶ ዮሐንስ መሸሻ ጽሑፍ ላይ የመቀሌውን ድል አስመልክቶ የገጠሙት ግጥም እንዲህ ይላል።

መቀሌ እንዳ ኢየሱስ ጦር ያሰፈረው ፥

አንድ ሺህ አንድ መቶው እውሀ እንዲጠማው፥

ምንጩን አዘግታ ጣይቱ አቃጥላው፥

ማጆር ጋሊያኖ ጉሮሮው ደርቆበት እንባ ሲወርደው፥

መኮነን አማልዶት እምየ ምንይልክ በምህረት ላከው ።

የኢትዮጵያ ጦር በዚህ ሁኔታ ጠላትን ከመቀሌ ካስለቀቀ በኋላ በቀጥታ ጠላት ሠፍሮበት ወደነበረው ሕዳጋ ሐሙስና አዲግራት መሄዱን ትቶ በምዕራብ በኩል ወደ አድዋ ሄደ። ምክንያቱም ሕዳጋ ሐሙስና አዲግራት ላይ የጠላትን ምሺግ በቀላሉ መስበር እንደማይቻል የወገን ጦር መረጃ ነበረው። የጠላት ጦርም የወገን ጦር ወደ አዲግራትና ሕዳጋ ሐሙስ እንደማይመጣ ከተረዳ በኋላ ፥ ወደ ምዕራብ ተንቀሳቅሶ ከአድዋ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ከምትገኘው ሳውርያ ላይ ምሺግ ቆፍሮ 20,170 የታጠቀ ጦር ይዞ የኢትዮጵያ ጦር ጥቃቱን እንዲጀምር ይጠባበቅ ነበር። ነገር ግን ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ወታደራዊ እቅድ እንጅ በጠላት ፕላን መሄድን ስላልፈለጉ ጥቃቱ ከጠላት በኩል የሚጀመርበትን ዘዴ ማቀነባበር ጀመሩ። ማን እንደሚጀምር ሲጠባብቁ ግን በሁሉም በኩል ስንቅ እያለቀ ነው። የባሰው ግን በጣላት በኩል ነበር። በዚህም ምክንያት ጠላት ጥቃቱን እንዲጀምር ሁኒታዎቹ እያስገደዱት መጡና የአድዋው ትያትር /ትርኢት እንደሚከተለው ሆነ።

የካቲት 20 ቀን 1888 ወደማታ አካባቢ የግፈኛውን የጣልያ ወራሪ ጦር ሲመሩ የነበሩት 5ቱ ጀኔራሎች እንትጮ ተራራ ላይ ድንኳናቸው ወስጥ ተሰብስበው የጥፋት ተልዕኳቸውን ማሳካት የሚችል ወታደራዊ ፕላናቸውን መቀየስ ጀመሩ። የጀኔራሎቹም ስም የሚከተለው ነበር። የኤርትራ ገዥ የነበረው ጀኔራል አረስቲ ባራትየሪና አራቱ የብርጌድ ኣዝዦች ፥ ጀኔራል አልበርቶን፥ ጀኔራል አርሞንዲ፥ ጀኔራል ዳቦርሚዳ፥ እና ጀኔራል ኢለና ነበሩ። በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ጣልያናዊና ጥቁር እራስ አስካሪ በዚያ ዘመን ደረጃ እጅግ ዘመናዊ ሥልጠና በተሠጣቸው የበታች የጦር መኮንንኖች ስር ተሰልፎ ትእዛዝ ከበላይ አዛዦቹ በመጠባበቅ በተጠንቀቅ ላይ ነበር። ያን የመሰለ ሠራዊት በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ለውጊያ ሲሰለፍ በታሪክ የመጀመሪያው እንደነበር ብዙ የታሪክ ጠበብቶች ይስማማሉ።

20 ኪሎ ሜትር ራቅ ብሎ አድዋ ላይ ደግሞ ፣ ቀደም ብሎ ጣልያኖችን በድንበር ሲከላከላቸው የነበረው የራስ መንገሻ ዮሐንስ ጦር ብቻ ሳይሆን ባጠቃላይ ከላይ ተደጋግሞ እንደተገለጠው የመላው ኢትዮጵያ ኅብረ ብሔር ጦር በታላቁ ንጉሠ ነግሥት ምንይልክ ኃይለ መለኮትና በጀግናዋ እቴጌ ጣይቱ ብጡል ኃይለ ማርያም የበላይ አዛዥነት፣ በእግዚአብሔር የበላይ ጠባቂነትና በርሱም ፍፁም ታማኝነት፣ ሠራዊቱ ከዚህ እንደሚከተለው በሀገር ወዳድ አዛዦች ስር እየጣለ ለመውደቅ በቆራጥነት ተሰለፈ።

በሰሜን በኩል የትግራይ ጦር በራስ መንገሻ ዮሐንስ አዛዥነት፣ በስተደቡብ በሽሎዳ ተራራ በኩል ያኔ የማህል ሰፋሪ እየተባለ የሚታወቀውን ሠራዊት በመምራት ፊታውራሪ ገበየሁ፣ የሐረርን ጦር በመምራት የአፄ ኃይለ ሥላሴ አባት ራስ መኮነን ወ/ሚካኤል፣ የታች ወሎን ጦር በመምራት ንጉሥ ሚካኤል አሊ ፣ ዋግሹም ጓንጉል ፥ ደጃዝማች ኃይሉና (የራስ ካሣ አባት) ጃንጥራር አስፋው (የእቴጌ መነን አባት)የዋግን ፥ የላስታንና የአምባሰልን ጦር በመምራት በአድዋ ከተማ ደቡብ በኩል ፣ ራስ መንገሻ አትከም የኤፍራታን ፣ ራስ ወሌ ብጡል (የቴጌ ጣይቱ ወንድም) የቤገምድርንና ስሜንን ጦር በመምራት ፣ ደጃዝማች ባሻህና ሊቀ መኳስ አባተ የሽዋን ጦር በመምራት ፣ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት የጎጃምን ጦር በመምራት ፣ ደጃዝማች ባልቻ አባ ነብሶ ጀግናውን የኦሮሞና የጉራጌን ፈረሰኛ ጦር በማሰለፍ ‘’ኢትዮጵያ ወይም ሞት !” እያሉ ለእናት አገራቸው ነፃነት እየጣሉ ለመውደቅ ተሰለፉ።

የግብጹ ተወላጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፥ ታቦተ ጽዮንን በማስያዝ ፣ የአኩስሙ ንቡረ ዕድና የደብረ ሊባኖሱ እጬጌ አፍሮ አይገባውን መስቀል ተሸክመው፣ከአኩስም ቆይታቸው አድዋ ላይ ለውጊያ ወደተሰለፈው ብሔራዊ ጦር ሲጓዙ በተመለከታቸው ጊዜ ሠራዊቱ “የሙሴ ጽላት/ የአማላክ እናት መጣችልን” በማለት የበለጠ መንፈሳዊ ሞራልና ኢትዮጵያዊ ወኔ ተሰማው። በአምላኩ ኃይል ግፈኛውን ወራሪ የጣልያን ሠራዊት እንደሚያቸንፍ ያለምንም ጥርጥር እምነቱን በማረጋገጥ ‘ግፋ ወደፊት ማለት ጀመረ። ሊቀ ጳጳሱም “ ልጆቸ ሆይ ! በዛሬዋ ዕለት ፥ የካቲት 23 ፥ 1888፥ እግዚአብሔር አምላክ ከእኛ ከደካማዎቹ ጎን ተሰልፎ በግፈኛ ወራሪዎች ላይ እውነተኛ ፍርዱን የምናይበት ቀን ይሆናል። የቅዱሳን አባቶቻችሁ ፥ የነቅዱስ ያሬድ፥ የነቅዱስ ላሊበላ፥ የነቅዱስ ተክለ ሃይማኖት፥ የነአባ ኤዎስጣቴዎስ ከፋሌ ባህር፥ የነአባ ፊልጶስ ዘደብረ ቢዘን፥ የነአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ አምላክ ከእናንተ ከግፉአኑ ጋር ነው ! ሂዱ ወደፊት! ኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖታችሁን፥ መካነ ቅዱሳንና ሀገረ እግዚአብሔር የሆነችውን ቅድስት ኢትዮጵያንና ንጉሣችሁን ተከላከሉ ! ኃጢአታችሁ ይሰረይላችሁ።” በማለት ጸሎተ ንስሐ ለንጉሡና ለሠራዊቱ ሠጡ። ካህናቱም ከዚህ ድርጊት ጋር የሚዛመደውን፥ ንጉሠ እስራኤል ዳዊት ከ1,000 ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት የተነበየውን ትንቢት በዚህ ታሪካዊ አካባቢ የተወለደው ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ በ520 ዓ.ም አካባቢ በደረሰው የዜማ ስልት

  • ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ ፥ ከመ ያምስጡ እምገጸ ቀስት፥ ወይድኀኑ ፍቁራኒከ።
  • ጸርሁ ጻዳቃን ወእግዚአብሔር ሰምዖሙ ፥ ወእምኩሉ ምንዳቤሆሙ ያድኅኖሙ፥ ቅሩብ እግዚአብሔር ለየዋሃነ ልብ ።
  • ይገንዩ ቅድሜሁ ኢትዮጵያ ፥ ወጸላእቱሂ ሀመደ ይቀምሁ።
  • አንተ ቀጥቀጥኮ አርስቲሁ ለከይሲ ፥ ወወሐብኮሙ ሲሳዮሙ ለሕዝበ ኢትዮጵያ።
  • ኢትዮጵያ ታበጽህ እደዊሃ ሃበ እግዚአብሔር ፥ ነገሥተ ምድር ሰብህዎ ለአምላክነ ፥ ወዘምሩ ለስሙ እያሉ ይጸልዩ ነበር።

የእስልምና እምነት ተከታይ የነበሩ ኢትዮጵያውያንም ከክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ተሰልፈው እኩል መስዋእትነት ከፍለዋል። እንደ ካህናቱም ሁሉ መንፈሳውያን ሸኽወቹም ድዋ በመያዝ ወይም በመጸለይ አገራቸው ኢትዮጵያን ባህር አቋርጦ ከመጣው ግፈኛ ጠላት ከተቃጣባት ጥፋት እንዲታደጋት አምላካቸው አላህን በመማጸን ላይ ነበሩ። ክርስቲያኑም ሆነ ሞስሊሙ የክተት አዋጁ ከታወጀበት ከጥቅምት 2 ቀን 1888 ዓ.ም ጀምሮ ቀንና ሌሊት የጋራ አምላኩን ከመማጸን አላቋረጠም ነበር።

የጦርነቱ ዝግጅት ሰው ሰራሺ በሆነው ዘዴም ፥ ማለት በመረጃ አሰባሰብም በኩል የተጫወተው ወሳኝ ሚና ነበረው። ታሪኩ እንደዚህ ነበር። አውአሎም ሐረጎት የተባለ የአካባቢው ተወላጅ ወጣት ለኢጣልያ መንግሥት በመረጃ አቅራቢነት እንዲያገለግል ተቀጥሮ ይሠራ ነበር። ታድያ አውአሎም ምንም ቢሆን አፉ እንጅ ልቡ ወደወገኖቹ ያደላ ነበርና ፣ ጠላት በእናት አገሩና በወገኖቹ ላይ ሊፈጽመው ለተዘጋጀው ጥፋት ተባባሪ መሆንን አልመረጠም። ይህም ኢትዮጵያዊ ንቃተ ህሊናው ከጠላት የተማረውን የመረጃ አሰባሰብ ዘዴ አገሩንና ወገኑን እንዲጠቅምበት አስገደደው። ይህን የተቀደሰ ዓላማ ለጓደኛው ለብላታ ገ/እግዚአብሔር ያለምንም ፍርሀት ገለጸለት። ሁለቱ ጓደኞች ይህን ሲያሰላስሉ በነበረበት ወቅት ውዝግቡ በሰላም እንዲፈታ ድርድር ቀጥሎ ነበር። የነዚህ ሁለት ኢትዮጵያውያን አለቃ የነበረው ጣልያናዊው የመረጃ መኮንን ስለድርድሩ  “ ኃያሉ የጣልያን መንግሥት ሠራዊት ይህን የኢትዮጵያን የዝንብ መንጋ ባንድ ቀን አራግፎ ግዛቷን መቆጣጠር ያቅተዋል ተብሎ ነው ድርድር እየተባለ ጊዜያችን የምናጠፋው ?” እያለ ሲደነፋ ለሀገራቸው ሕዝብ ያለውን ንቀት ሲገልጽ፥ አውአሎም እየሰማ ውስጡ ይቃጠላል። ከዚያ ብላታ ገ/እግዚአብሔር አውአሎምን ከራስ መንገሻ ዮሐንስ ጋር የሚተዋወቅበትን መንገድ ይፈልግና ከራስ ጋር አገናኘው። ራስ መንገሻም የአውአሎምን ታማኝነት ካረጋገጡ በኋላ የሚከተለውን ዘዴ ይቀይሳሉ።

ዘዴውም ይህ ነበር። የካቲት 21 ቀን ማርያም ስለሆነች አብዛኛው መሳፍንት ከሚመራው ጦር ጋር ቤተ ክርስቲያን ለመሳለምና ለመጸለይ ወደ አኩስም ጽዮን እንደሚሄድ፣ የንግሥቲቱ ወንድም ራስ ወሌም ስለሞቱ ንጉሡና ንግሥቲቱ በኀዘን ላይ እንደሆኑ፣ አንዳንድ መሳፍንቶችም የሚመሩትን ጦር ይዘው ጣልያንን ድል ማድረግ እንደማይቻል ተስፋ ቆርጠው እየከዱ ወደየመጡበት እየተመለሱ እንደሆነ ፣ የተቀረው ሠራዊትም ስንቅ ጨርሶ ምግብ ፍለጋ ተከዜን ተሻግሮ ጠለምትና ወልቃይት ድረስ እንደሄደና ንጉሡና ንግሥቲቱ ከጥቂት የክብር ዘበኞቻቸው ጋር ድንኳናቸው ውስጥ ስለሚገኙ፥ ስንቅ ፍለጋ ወደ ጠለምትና ወልቃይት የሄደውና፥ ወደ ኣኩስም ጽዮን የሄደው ሠራዊት ከመመለሱ በፊት እሑድ የካቲት 23 ቀን አደጋ ቢጣል በቀላሉ ድል አድርጎ ንጉሡንና ንግሥቲቱን መማረክ እንድሚቻል አድርጎ፥ አዘናጊና የተሳሳተ መረጃ አውአሎም ለጀኔራል ባራትየሪ እንዲሠጠው ይሆናል። እቴጌ ጣይቱ እጅግ በጣም አርቆ አሳቢና ጥበበኛ ስለነበሩ ፥ የጠበቀ እምነት እግዚአብሔርም ስለነበራቸው፥  ከአውአሎም ጋር የተቀየሰውን ዘዴ በቃል ኪዳን ለማጠንከር አውአሎምን እንደልጃቸው እጁን ጨብጠው እየሳቡ ወደ ድንኳናቸው ይዘውት ገቡ። “ ይህን የማቀርብልህን ምግብ እንደ ክርስቶስ ሥጋ ወደሙ ቆጥረህ እናት አገርህንና ወገንህን ላትከዳ በመሃላ ቃል ገብተህ ይህን ያቀርበኩልህን ምግብ ተመገብልኝ “ አሉት። እርሱም “ አገሬንና ወገኔን ለጠላት አሳልፌ ብሠጥ ፥ ሰማይና ምድርን የፈጠር አምላክ ይፍረድብኝ” በማለት ይህን ጠንከር ያለ የተለመደውን አስተማማኝ ኢትዮጵያዊ ቃል ኪዳን ከገባ በኋላ ምግቡን ተመግቦ ፥ ኢትዮጵያ በድል አድራጊነት የተወጣችበትን ወሳኝ ብሔራዊ ግዳጁን ለመወጣት ወደጠላት ጦር ሠፈር ጉዞውን ቀጠለ።

ከጠላት ካምፕ እንደ ደረሰ ከላይ የተዘረዘረውን የተሳሳተ፥ ግን ለጠላት እጅግ አስደሳች የሚመስለውን መረጃ ለጀኔራል ባራትየሪ አቀረበ። ባራትየሪም በቀረበለት መረጃ ረክቶና ተደስቶ ከምሺጉ ወጥቶ ምንይልክን ለመማረክና አገሪቱንም በቅኝ ለመግዛት እየተዝናና መጣ። የተናቀው የኢትዮጵያ ጀግና ሠራዊት ግን ቀደም እንደተገለጸው በየምሺጉ ሁኖ ማህል እስከሚገባ ድረስ አድፍጦ ጠበቀው። ከዚያማ ያን ነጭ የሮማ ስንዴ በጋለ ጥቁር ምጣድ ይቆላው ጀመር !! (እልልልልል!!)። በዚሁ ዕለት ፥ እሑድ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. ወደ 11 ሰዓት አካባቢ እንደ አንድ አገር ሕዝብ በአንድ አመራር ሥር የተሰለፈው የኢትዮጵያ ጀግና ሕዝብ፥ በአምላኩ በእግዚአብሔር ረዳትነት ፥ በጀግና መሪዎቹ አርቆ አሳቢነትና አገር ወዳድነት ጠላቱን ደምስሶ ብሔራዊና ሰብአዊ ማንነቱን ጠብቆ አስጠበቀ። በዚህም ታሪካዊ ድል ከጠላት እብሪተኛ ጀኔራሎች መካከል ጀኔራል አርሞንዲና ጀኔራል ዳቦርሚዳ ሲገደሉ ፣ ጀኔራል ኢለና ወደኤርትራ እንደአጋጣሚ ከተወሰነ ጦር ጋር አመለጠ። 262 የኢጣልያን ተወላጅ መኮንኖችና 4,000 ተራ ወታደሮች ሲገደሉ ፥ 954 የደረሱበት ሳይታወቅ ቀርቷል (Missing in action)። 470 ነጭና 958 ጥቁር ራስ ባንዳዎች ቆስለዋል። ጀኔራል አልቨርቶን ጨምሮ 1,900 ነጭና ከ1,000 በላይ ወደውም ሆነ ተገደው ከጠላት ጋር ተሰልፈው ወገኖቻቸውን የወጉ የመረብ ምላሺ አበሾች ተማርከዋል። 56 መድፎችና 11,000 በዘመኑ የነበሩት ቀላልና ከባድ መሳሪያዎች ሊገመት ካልተቻለ ጥይት ጋር ተማርኳል። ክ100,000 በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሠራዊት ይዟቸው የተሰለፈው 40 መድፎችና 80,000 የሚሆኑ ቀላል የጦር መሣሪያዎች እንደነበሩ ሪቻርድ ፓንክረስትና ሌሎች የታሪክ ጸሓፊዎች ዘግበዋል። ከወገን በኩልም ለሀገራቸው ክብርና ነፃነት መስዋዕት የሆኑት ጥቂቶች አልነበሩም። ከ5,000 በላይ ተሰውተዋል። 8,000 ቆስለዋል። ከተሰውት ውስጥ የአፄ ምንይልክ የአከስት ልጅ፥ የወ/ሮ አያህሉሽ ሣኅለ ሥላሴ ልጅ ደጃዝማች ባሻህና ፊታውራሪ ገበየሁ ይገኙበታል።

ይህን በመሰለ ሁኔታ ለመጀመሪያ ጊዜ አውሮፓዊ የሆነ የነጭ ኃይል በጥቁር አፍሪካዊ ኃይል በመደምሰሱ ድሉ የኢትዮጵያውያን ብቻም ሳይሆን በዚያ ዘመን ተንቆና ተዋርዶ በቅኝ ግዛትና በባርነት ቀምበር ሥር ሲማቅቅ ለነበረው የመላው ጥቁር ዘር ሁሉ ነበር ተደርጎ የታየው። አዎ በአፍሪካ ፥ በካረብያንና በሰሜን አሜሪካ በዘረኛ ነጮች መንግሥትና ሕዝብ ሰብአዊነታቸው ተርሰቶ የነበሩት ጥቁሮች የደስታ ጭላንጭል የሰሙበት ዕለት ነበር። ከዚህም ዕለት ጀመሮ ነበር እነዚህ ህዝቦች ለነፃነታቸው ቆርጠው ለመታገል የበለጠ የተበራቱት። ወርሐ የካቲትንም ልዩ ትኩረት ሠጥተው ‘’Black History Month/ ታሪካዊ የጥቁሮች ወር “ እያሉ እስከዛሬ ድረስ በየዓመቱ እንዲያስቡት ካደረጋቸው አንደኛው ምክንያት ይህ የአድዋ ድል ነው።

እንግዲህ ከተለያዩ የታሪክ ምንጮች የቀዳዋቸው ፥ አባቶቻችንና እናቶቻችን የሠሩት እውነተኛው ትውልድ አኩሪ ታሪክ ከረጅሙ በአጭሩ ይህን ይመስላል። ጥያቄው ግን ዛሬስ ያች የታሪክና የብሔረሰቦች ቤተ መዘክር የሆነችው አገራችን ኢትዮጵያ የ 1888ቱ አይነት ጠንካራ የውጭ ወራሪ ክብረ ወሰኗን ጥሶ ቢገባ ለድል የሚያበቃት አስተዋይ መሪ አላት ወይ ? የጋራ ማንነቱ መገለጫ ከሆነው ከኢትዮጵያዊነቱ ይልቅ ለየግል ማንነቱ፥ ማለት ለዐምሐራነቱ፥ ለኦሮሞነቱ፥ ለትግሬነቱ፥ ለጉራጌነቱ፥ ለአፋርነቱ፥ ለወላይታነቱ፥ ለአገውነቱ ወዘተርፈ..ቅድሚያ እንዲሠጥ ተደርጎ እየተተካ ያለው አዲሱ ትውልድ ፣ ነገ ከነገ ወዲያ አንድነቱን ጠብቆ፥  የሚመጣበትን የውጭ ጥቃት ሊመክት  ይችላል ማለት እንዴት ይቻላል? ይህ የአሁኑ ትውልድ ለብሔር ማንነቱ ነው እንጅ ቅድመ ሁኔታ መሥጠት እንደማይችል እየተነገረው ያለው ኢትዮጵያዊነቱን እኮ በሕገ መንግሥቱ ኣንቀጽ 39 ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው እስከፈለገው ድረስ ነው። ማለት የብሔር ማንነት ግዴታ ሲሆን ኢትዮጵያዊ ማንነት ግን በአማራጭ ደረጃ ነው ትውልዱ እንዲቀበለው ተደርጎ እየተተካ ያለው። ለዚህ እኮ ነው ብሔራዊ ማንነት ከብሔር ማንነት ይቅደም የሚል አጀንዳ ያላቸው በግልም ሆነ በድርጅት ደረጃ እንዲዳከሙ ሁነው በግል ማንነት ላይ ያተኮረ አጀንዳ ያላቸው እየተጠናከሩ የመጡት።

ታድያ የዛሬ 119 ዓመት ‘’ አባት ያበጀው ለልጅ ይበጀው ‘’ ብለው ከአራቱም ማዕዘናት በአንድ ኢትዮጵያዊ ማንነት፥ በአንድ ሠንደቅ ዓላማ አርማ፥ በአንድ መንግሥታዊ አመራር ሥር፥ አንድ አገር አንድ ሕዝብ ብለው ተሰልፈው ደማቸውን ቀለም አጥንታቸውን ብዕር አድርገው ያስመዘገቡትን አኩሪ ታሪክ ጠብቀን ለተተኪው ትውልድ ማስተላለፍ አይጠበቅብንም? ለጥያቄው መልሱ አወንታዊ ነው መሆን ያለበት። አዎ እኛም ዛሬ ለነገው ትውልድ የሚያኮራና የነገው ትውልድ ዛሬ እኛ አባቶቻን የሠሩትን አኩሪ ታሪክ እያሰብነው እንዳለነው ሁሉ  ነገም እኛን እንድንታወስ የሚያደርግ ጥሩ ታሪክ እየሠራን እንለፍ። ይህ ነው የሰውን ልጅ ከእንስሳት ልዩ የሚያደርገው። እናም እንሰባሰብ እንጅ አንበታተን። አንድነት ኃይል መሆኑን ይህ አድዋ ላይ ከ 119 ዓመት በፊት የተሠራው ታሪክ ዘለዓለማዊ የሆነ ታላቅና ቋሚ ምሥክር ነውና በእኩልነት ላይ የተገነባ አንድነት እንገንባ እያልኩ ዝግጅቴን ከዚህ ላይ አጠናቃለሁ። በጥሞና ስላዳመጣችሁኝ አመሰግናለሁ፤ እግዚአብሔር ይሥጥልኝ።

 

ከበደ አገኘሁ ቦጋለ፣ የካቲት 23 ቀን 2007 ።

 

መወድስ ቅኔ ዘአለቃ ዘወልዴ ዘአንኮበር ለአፄ ምንይልክ የተሠጠ።

ትውልድ የኀልፍ ወሰነ አበው ወትውልድ ይተርፍ እምነ አቡሁ በግብር ፤

ምሳሌ ዝኒ ላዕሌከ ሣህለ ማርያም (ምንይልክ)ደብር፤

ሐሰውከሂ ኢትበለኒ እሙነ ዜናሁ ለሰሎሞን በኩር፤

ጠይቅ ወተዘከር ፥ እመ ነባቢሁ ተቀብረ አምጣነ ንባቡ ኢይትቀበር፤

በይነ ጽድቅሂ ወበይነ ርትዕ ወበይነ የዋሃት መንክር ፤

እስከነ ትግሬ ይመርሐከ ስብሐተ የማንከ ፍዳ ጸር፤

አርቲዐከሂ ፍኖተ ማዕከለ ወሎ ሀገር ፤

ተሠራሕ ለኮንኖ ወንገሥ በጎንደር።

The post የ 119ኛው ዝክረ አድዋ ፤ 1888   – ከበደ አገኘሁ ቦጋለ appeared first on Zehabesha Amharic.

የአድዋ ድል በዓል በሚኒሶታ ተከበረ

$
0
0

ESM 2

ecm minnesota

(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ማህበረሰብ (ኮምዩኒቲ) በሚኒሶታ ያዘጋጀው 119ኛው የአድዋ ድል በዓል በሚኒሶታ ተከብሮ ዋለ::

በሚኒሶታ ከኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ ከወጣትም ሆነ ከአዛውንቶች የተውጣጡ የተለያዩ የማህበረሰቡ ክፍሎች በተገኙበት በዚሁ በዓል ላይ የአድዋ ድል በዓል በተለይ ለኢትዮጵያውያን እና ለጥቁር ሕዝቦች ያለው ትልቅ ም ዕራፍ ተዘክሯል::

ዛሬ በተከበረው በዓል ላይ በክብር እንግድነት የተገኙትና ስለአድዋ ድል ገለጻ የሰጡት ዶ/ር ዳንኤል ሲሆን የአድዋ ድል ከጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ጋር ያለውን ተያያዥነት አውስተው የተለያዩ ገለጻዎችን ሰጥጠዋል::

በዚሁ ዕለት በስፍራው የተገኙ የማህበረሰቡ አባላት እንዲሁ በበዓሉ ዙሪያ ትምህርታዊ አስተያየቶችን እንደሰጡም በስፍራው የተገኘው የዘሐበሻ ዘጋቢ አስታውቋል::

The post የአድዋ ድል በዓል በሚኒሶታ ተከበረ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live