“የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ጥሪ የሁሉም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ጥሪ ነው!” ሲል የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ ባወጣው መግለጫው አስታወቀ።
ንቅናቄው ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ “የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ጥሪ ወሳኝና ህዝባዊ ጥሪ እንደሆነ ታሪካዊ ምስክርናውን በመስጠት፤ በዚህ ዘረኛ የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት ከልክ ያለፈ ጭቆና ፣ ረገጣና ፣ እንግልት ደርሶብኛል የምትሉ ንፁሃን ኢትዮጵያውያን ዜጎችና ፣ በምንወዳት ሃገራችን ለህዝብ የሚበጅ ቀና ለውጥ ለዘለቄታው ይሰፍን ዘንድ የምትመኙ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ፤ እንዲሁም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ፣ የሃይማኖት ተቋማትና ፣ የሲቪክ ማህበራት ታላቅ ሃገራዊ ሃላፊነትና የህዝብ አደራ በጫንቃችሁ እንደተሸከማችሁ በመገንዘብ ፤ የሚጠበቅባችሁን ህዝባዊ ተልኮ መፈፀም ታሪካዊ ግዴታችሁ መሆኑን በመረዳት ፤ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ጎን እንድትቆሙ ሲል በጥብቅ እያሳሰበ ፤ ሃገራዊ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል:: የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ጥሪ የሁሉም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ጥሪ ነው!” ብሏል።
↧
የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ “የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ጥሪ የሁሉም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ጥሪ ነው”አለ
↧