Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Sport: የባርሴሎና ተጨዋቾች የእግር ኳስ ተንታኞች ሚዛን

$
0
0

በአዲስ አሰልጣኝ የ2013/14 የውድድር ዘመንን የጀመረው ባርሴሎና እንደቀድሞው አስፈሪ አለመሆኑ እየተነገረ ቢተችም ውጤት ከሚለውጡ ተጨዋቾች ጋር ውድድር ዘመኑን አጋምሷል፡፡ የተጨዋቾቹን ብቃት የታዘቡ የእግር ኳስ ተንታኞችም የባርሳን ከዋክብት
‹‹ልዩ ብቃት ያሳዩ››፣
‹‹ጥሩ አቋም ላይ የሚገኙ››፣
‹‹ሊሻሻሉ የሚገባቸው›› እና
‹‹የተቸገሩ›› በሚል እንደሚከተለው ለይተዋቸዋል፡፡


ልዩ ብቃት ያሳዩ

Barcelona v Real Madrid - La Liga
ቪክቶር ቫልዴዝ
ዘንድሮ በረኛው ጉዳት እስከሚገጥመው ድረስ በዓለም የጊዜው ምርጥ ግብ ጠባቂ ያስባለውን ብቃት አሳይቷል፡፡ አምና በረኛው ሲበዛ ብቃቱ ስለመውረዱ እና የሚሞክሩበትን ኳሶች ለማዳን ብዙም ጥረት እንደማያሳይ እየተነገረ ተተችቷል፡፡ እንዲያውም ቀደም ባሉት ዓመታት ለክለቡ የሰጠው ጥቅም ከግምት ገብቶለት እንጂ ቫልዴዝ ይፋ ወቀሳ ይገባው ነበር የሚሉት ጥቂት አይደሉም፡፡ ዘንድሮ ግን በባርሴሎና የግብ ቋሚዎች መካከል ቆሞ ሊያድናቸው የነበሩት ኳሶች በመጪው ክረምት በዓለም ዋንጫው የስፔን ቋሚ በረኛ እንደሚያስደርገው እስከ መነገር ደርሷል፡፡ ከአምናው አንጻር ዘንድሮ ያሳየው መሻሻል ብዙዎችን አስደንቋል፡፡
ዣቪ ሄርናንዴዝ
ባለፉት ሁለት ዓመታት የዣቪ ብቃት መጠነኛ መቀነስ ታይቶበታል፡፡ በተለይ ኳስ ሲነጠቅ ተመልሶ ቦታውን ለመያዝ እጅግ ሲቸገርም ተስተውሏል፡፡ ባርሴሎና በመልሶ ማጥቃት አደጋ ውስጥ ሲገባ የሚደርሱለት ፈጣን አማካዮች ያስፈልጉታል፡፡ ባርሴሎና በፔፕ ጋርዲዮላ ጊዜ ‹‹ከፈውስ አስቀድሞ መጠንቀቅ ይሻላል›› የሚል ፍልስፍና ነበረው፡፡ ቡድኑ የተወለደበትን ኳስ ለማስመለስ ከመሯሯጥ ይልቅ አስቀድሞ አለማስነጠቅ እንደሚሻል ያምናል፡፡ ሆኖም ይህንን ለማረጋገጥ ተከላካዮቹ ወደ ኋላ አፈግፍገው ሲጫወቱ በኋላ መስመር እና በአጥቂዎቹ መካከል ያለው ክፍተት ይሰፋል፡፡ ስለዚህ አማካዮቹ ክፍተቱን ለመሙላት ብዙ ይሮጣሉ፡፡
በእርግጥ ዣቪ የተዳከመ አይመስልም፡፡ ተጨዋቹ የሚነጠቃቸው እና ለተጋጣሚ ቡድን ተጨዋቾች የሚሰጣቸው ኳሶች ይኖራሉ፡፡ ሆኖም እንደ አማካይ ቦታ ተጨዋችነቱ የኳስ ንክኪው፣ የፓሲንግ ስኬቱ፣ ያለ ኳስ የሚያደርገው ሩጫ፣ ጉልበቱ፣ መረጋጋቱ እና የመሪነት አቅሙ አሁንም ድንቅ ነው፡፡ ዣቪ አሁንም መቼ ከመሀል ሜዳ ተነስቶ ወደ ፊት መሮጥ፣ ተጋጣሚውን ማስጨነቅ፣ የጨዋታውን ፍጥነት መጨመር እንዳለበት በሚገባ ይገነዘባል፡፡ ዘንድሮም ተጨዋቹ በልዩ ልእና የጥራት ደረጃውን በሚያሳይ መልኩ ቡድኑን መጥቀሙን ገፍቶበታል፡፡
Neymar-Barcelonaኔይማር
ከሀገር ወደ ሀገር ቀርቶ ከሀገር ሀገረ ተዛውሮ መጫወት በራሱ ፈተና ነው፡፡ በዚህ ላይ የኔይማር ዕድሜ እና የወጣበት ገንዘብ ብቻውን ከባድ ውጥረት ይፈጥራል፡፡ ሆኖም ወደ ባርሴሎና ከመጣበት ቀን ጀምሮ ዓለም አይኑን የጣለበት ብራዚላዊ በካታሎኒያው ክለብ ድንቅ ብቃቱን ማሳየት ጀምሯል፡፡ ተጨዋቾ ወደ ስፔን የመጣው ከብራዚል ጋር የኮንፌዴሬሽን ዋንጫን አንስቶ እና በራስ መተማመኑ ላቅ ያለ ደረጃ ላይ ደርሶ ቢሆንም ጅማሮው ቀላል አልሆነለትም፡፡ ሆኖም አሰልጣኙ ማርቲኖ የሰጡትን ምክር ተቀብሎ ሜዳ ላይ እየተገበረ አቅሙን ማሳየት ችሏል፡፡ በተለይ ኃላፊነት በጥሩ ሁኔታ እየከፈለ በትልቅ ደረጃ መጫወት እንደሚችል አስመስክሯል፡፡ ተጨዋቹ በመጀመሪያዎቹ ወራት ያሳየው ድንቅ ብቃት በቀሪዎቹ የውድድር ዘመኑ ወራት ብዙ እንዲጠበቅበት ያደርጉታል፡፡ ሆኖም ልጄ ይበልጥ ባይሻሻል እንኳን እስካሁን ያሳየውን ብቃት መድገም ብቻ ያስመሰግነዋል፡፡
ሰርጂዮ ቡስኬትስ
ይህ አማካይ በሚናው ላይ የሚያሳየው አስገራሚ ብቃት በቦታው የዓለም ምርጥ ያሰኘዋል፡፡ ኳስ ሲይዝ ፖሲንግ ችሎታው ያልተዛነፈ ነው፡፡ ኳስን በቁጥጥሩ ስር ለማቆየት ሲል አዟዟሩ እና አቅጣጫ የሚቀይርበት መንገድ የሚታመን አይደለም፡፡ ያለ ኳስም ቡስኬትስ ድንቅ ነው፡፡ በተለይ በአዲሱ አሰልጣኝ ስር ተጨዋቹ ይበልጥ መሻሻሉን እና የተከላካይ መስመሩን በመጠበቅም በኩል ሆነ መሀል ሜዳውን በበላይነት በመምራት የላቀ ብቃት ይስተዋልበት ጀምሯል፡፡ ሰርጂዮ አሁንም ሸርተቴ የመውረድ ድካም ቢታይበትም የእይታው እና የፓሲንግ ብቃቱ የተለየ ተጨዋች ሆኖ እንዲቀጥል አድርጎታል፡፡

ጥሩ ብቃት ላይ የሚገኙ

ጄራርድ ፒኬ
ተከላካዩ ዘንድሮ በገዛ ደጋፊዎቹ ሳይቀር ሲበዛ ተተችቷል፡፡ ሆኖም ተጨዋቹ ባርሳ በሊጉ አናት እንዲቀመጥ እና በቻምፒዮንስ ሊግም ምድቡን በመሪነት እንዲያጠናቅቅ ልዩ ብቃት አሳይቷል፡፡ በተለይ ከቡድኑ የፍፁም ቅጣት ምት ክልል በቴስታ እያገኘ ያራቃቸው የማዕዘን ምቶች እና ክሮሶች እጅግ ይበዛሉ፡፡ ሆኖም ማርቲኖ በግቡ ቋሚዎች ላይ የሚቆሙ ተጨዋቾችን በማዕዘን ምቶች ጊዜ አለመጠቀማቸው እና ዳኒ አልቬስ አብዝቶ ወደ ፊት መሄዱ በመከላከሉ ጨዋታ ላይ ለሚፈጥረው ችግር ፒኬ ተጠያቂ ይደረጋል፡፡ እንዲያውም ላለፉት ሁለት ዓመታት ያለ እረፍት የተጫወተ ተከላካይ ከጨዋታ መደራረብ ችግሩ ጎን ለጎን አሁን በሚያሳየው ብቃት መጫወቱ ሳያስመሰግነው አይቀርም፡፡ ፒኬ የሚሸፍነው ርቀት፣ አስደናቂ ረጃጅም ፓሶቹ፣ የማጥቃት ባህሪዩ እና የጎል ሪከርዱ በዓለም ላይ ከሌሎች የመሀል ተከላካዮች ሁሉ የላቀ ያደርገዋል፡፡ ከዚህ ውጪ የመከላከል ጨዋታ በቡድን የሚሰራ ነው፡፡ ጎሎች በቀላሉ ከተስተናገዱ ችግሩ ከግለሰብ ይልቅ የቡድን ነው፡፡ ለምሳሌ ቫልዴዝ ዘንድሮ ልዩ ብቃት አሳይቷል፡፡ የተከላካይ መስመሩ ቀሽም ቢሆን በረኛው ተመሳሳይ ውዳሴ ሊያገኝ አይችልም፡፡ ፒኬ ምፍትሃዊ ሚዛን ከታየ መጥፎ ብቃት ላይ አይደለም፡፡
ፍራንሴስክ ፋብሪጋዝ
ሴስክ ለባርሴሎና የሚሰጠውን ጥቅም በታክቲካዊ መለኪያ መመልከት እንችላለን፡፡ ስፔናዊው የማጥቃት ባህሪዩ የጎላ አማካይ ነው፡፡ ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ክልል ሲቃረብ መቼ አደገኛ ኳሶችን ለጓደኞቹ መስጠት እንዳለበት ያውቃል፡፡ በአዕምሮው በኩል ፋብሪጋዝ አሰልጣኙ በሚሰጡት በየትኛውም ሚና ለመጫወት ዝግጁ ነው፡፡ በአካላዊ መመዘኛ ቀርፋፋ የሚባል ቢሆንም በመጨረሻ አቅሙ ሳይቆጥብ ለመሮጥ ግን ዝግጁ ነው፡፡ ሜሲ በጉዳት ከሜዳ ከራቀ ወዲህ ተጨዋቹ በሀሰተኛ ዘጠኝ ቁጥር ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ሚናው ፍጥነት የሚጠይቅ መሆኑ ለፋብሪጋዝ ፈታኝ ያደርገዋል፡፡
አለመታደል ሆኖ የባርሴሎና ተጋጣሚዎች ወደኋላ አፈግፍተው እና ተጠቅጥቀው የሚከላከሉ መሆናቸው ፋብሪጋዝ ተከላካይ ለንጣቂ ኳሶችን በተደጋጋሚ እንዳይሰጥ ይገድበዋል፡፡ አስፈላጊውን ክፍተት ሲያገኝም ቢሆን የክንፍ ተጨዋቾቹ ወይም አጥቂዎቹ ሰዓቱን የጠበቀ ሩጫ ካላደረጉ ዋጋ አይኖረውም፡፡ እንዲህም ሆኖ ፋብሪጋዝ ጎል በማስቆጠር ጥሩ ሲሆን ለጎል የተመቻቹ ኳሶችን በማቀበል በኩልም የላሊጋው የበላይ ነው፡፡
ካርሎስ ፑዮል
ፑዩል ዘንድሮ ብዙ ጨዋታ ላይ ያልተሳተፈ እንደመሆኑ በእርሱ ዙሪያ የሰላ ግምገማ ማድረግ ያስቸግራል፡፡ ጤንነቱ ሲሻሻል እና ወደ ሜዳ ሲገባ ግን ተከላካዩ ምርጥ ብቃቱን ለማሳየት ተቸግሮ አያውቅም፡፡ ነገር ግን ተደጋጋሚ የጉልበት ጉዳቱ አንጋፋውን አምበል ወደ ጫማ መስቀሉ እየገፋው ይገኛል፡፡ ባለፈው ክረምት እግርኳስን ለመሰናበት ከጫፍ ከደረሰ በኋላ ሀሳቡን አስለውጠው የአንድ ዓመት ኮንትራት ያቀረቡለት የክለቡ ፕሬዝዳንት ላንድሮ ሮሴል ናቸው፡፡ አሁን ግን በውድድር ዘመኑ ቀሪ ጊዜ ፑዩል በትልቅ ደረጃ ቡድኑን መጥቀም መቻሉ አጠራጣሪ ሆኗል፡፡ በዚህም የተከላካዮ እጥረት የሚገጥመው ባርሳ ምናልባት ለማርክ ባርትራ የተሻለ የመሰለፍ ዕድል ሊሰጥ ይገደዳል፡፡ እንደ አምናው የአደጋ ጊዜ መሸፈኛ በመሆን አድሪያኖም ሊጫወት ይችላል፡፡ ሆኖም ባርሴሎና በዋናነት አዲስ ተከላካይ ፍለጋ ወደ ገበያ እንደሚወጣ ይጠበቃል፡፡
አንድሬስ ኢኒዬሽታ
አማካዩ የጎል እድል በመፍጠር እና ጎሎች በማስቆጠር የተመሰገነ ይሁን እንጂ ዘንድሮ ወደ ኋላ እየተመለሰ ኳስ ለማስጣል ከባላጋራዎቹ ጋር የሚገጥመው ትግል ያስገርማል፡፡ በየጨዋታው በሙሉ ቁርጠኝነት ወደ ሜዳ የሚወጣው ስፔናዊ በተለመደ የጎል ምንጭነቱ ረገድ መቀዛቀዝ ታይቶበታል፡፡ በሌሎች መለኪያዎች ግን አሁንም ኢኒዬሽታ ምርጥ ነው፡፡ እንደ ጄራርድ ባለፉት ሁለት ዓመታት ብዙ ጨዋታዎች ያደረገው ኮከብ ምናልባት በእያንዳንዱ ግጥሚያ 90 ደቂቃ እንዳጨርስ እና ይበልጥ እንዳይደክም አሰልጣኙ ሊያግዙት ይገባል፡፡
ማርክ ባርትራ
በአሰልጣኙ ብዙም የመሰለፍ ዕድል የማይሰጠው ተጨዋች አጋጣሚው ሲፈጠርለት ምርጥ ብቃቱን ማሳየት ይኖርበታል፡፡ ይህ ልጅ አሁን ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሉን እያሳየ መጥቷል፡፡ ከታዳጊ ማዕከሉ እንደ መምጣቱ ለዝውውር የተከፈለበት ገንዘብ ወይም ሌላ አይነት ወጪ ጫና አይሰማውም፡፡ ብዙ ከታዳጊ ማዕከል የሚመጡ ተጨዋቾች ችግር ውስጥ የሚገቡ ቢሆኑም ባርትራ በዋናው ቡድን በጊዜ ሂደት የሚሳካለት ይመስላል፡፡ ከዕድሜው አንጻር ወደ ሜዳ ሲገባ ያሳያቸው መሻሻሎች ጥሩ ተስፋ እንዲጣልበት ያደርገዋል፡፡
ዮርዲ አልባ
ፋልባኩ ለረጅም ሳምንታት በጉዳት ከሜዳ መራቁ ቢያሳዝንም በሌላ በኩል ሲሳይ ሳይሆንለት አልቀረም፡፡ ተከላካዩ በአጭር ጊዜ ውስጥ በብሔራዊ ቡድን እና በክለብ ብዙ ጨዋታ ካደረጉ ተጨዋቾች መካከል ይመደባል፡፡ በአውሮፓ ዋንጫ ፍጻሜ ጣልያን ላይ ጎል ያስቆጠረው ተጨዋች ራሱን እና ቡድኑን ከአደጋ ማዳን የሚችልበት የሩጫ ፍጥነት ባለቤት ነው፡፡ በቀጣዮቹ ወራት ባርሴሎና እንደ ቡድን ከበረታ አልባ ይበልጥ የመሻሻል ዕድል ይኖረዋል፡፡
አድሪያኖ
ይህ ተጨዋች ሁለገብ ባህሪይ መያዙ ለባርሴሎና ብዙ ጠቅሟል፡፡ ዘንድሮ ብዙ ጊዜውን በግራ ፉላብክ ቦታ ቢያሳልፍም በውድድር ዘመኑ መጀመሪያ ማላጋ ላይ የማሸነፊያውን ጎል እስከማግባት ደርሷል፡፡ አድሪያኖ በተደጋጋሚ ጉዳት ቢሰቃይም የክለቡ ሰዎች ተስፋ አልቆረጡበትም፡፡ በእያንዳንዱ ወደ ሜዳ በገባበት ጨዋታ በቁርጠንነት የሚሰጠውን ኃላፊነት ሲወጣ ተስተውሏል፡፡ አሁን የዋናው ቡድን ጠቃሚ አባል መሆኑንም አረጋግጧል፡፡
ዳኒ አልቬስ
ዘንድሮ በፉልባክ ሚና ባርሴሎናን በጥሩ ሁኔታ እየጠቀመ ያለ ሌላኛው ብራዚላዊ ነው፡፡ አልቬስ ሲጫወት ብቻ ሳይሆን ያልተሰለፈ ቀንም የሚናፈቅ አይነት ተጨዋች ነው፡፡ በቅርቡ ቡድኑ ከሄታፌ ጋር ሲጫወት ፉልባኩ ለግጥሚያው ዝግጁ ያልነበረ መሆኑ ቢታይም በቀጣዮቹ ጨዋታዎች ወደ ብቃቱ እንደሚመለስ ይጠበቃል፡፡
አልቬስ ባለፉት ዓመታት በክለቡ እና በብሔራዊ ቡድኑ የቀኝ ክንፍ ያለማቋረጥ እየተመላለሰ በመሮጥ ተጫውቷል፡፡ እንዲህም ሆኖ ብዙ ጉዳት አለማስተናገዱ ያስደንቃል፡፡ በቅርቡ በኢንተርናሽናል ጨዋታ ወቅት የገጠመው ጉዳት እግረ መንገዱን ተጨዋቹ እረፍት እንዲወስድ እና ለቀሪው የውድድር ዘመን በብቃት እንዲመለስ ሊያግዘው ይችላል፡፡
በታክቲክ በኩል የአልቬስ ወደ ፊት አብዝቶ መሮጥ የባርሴሎናን የተከላካይ መስር በተጋነነ መልኩ ወደ ጎን እንዲለጠጥ ሲያደርገው የመልሶ ማጥቃት አደጋዎችን ለመመከት ብዙ እንዲለፉ ያስገድዳቸዋል፡፡ ሆኖም ከትልልቅ ቡድኖች ጋር በሚደረጉት ጨዋታዎች ተከላካይ ክፍሉ ይበልጥ ወደ ኋላ አፈግፍጎ እንዲከላከል ይታዘዛል፡፡ በዚህ መሰል አጋጣሚዎች አልቬስ በሚገባ መከላከል እንደሚችል ታይቷል፡፡ ሆኖም በቀሪዎቹ የውድድር ዘመኑ ቀጣይ ወራት ብራዚላዊው ይበልጥ ተሻሽሎ ልዩ ብቃት ሊያሳይ ይችላል፡፡
barcelona
ሊሻሻሉ የሚገባቸው

ፔድሮ ሮድሪጌዝ
ወጣቱ አጥቂ በቅርቡ ለባርሴሎና ሀትትሪክ ቢሰራም ብቃቱ ይዋዥቃል፡፡ በዘንድሮ ብቃቱ ጥሩ ተጫወቱ የማያስብል አቋም ያሳዩ ከነበረ ሶስት ወይም አራት ተጨዋቾች በአንዱ ነው፡፡ በእርግጥ በሊጉ 10 ጎሎች ማስቆጠሩ (የሳምንቱ መጨረሻ ጨዋታን ሳይጨምር) እውነት ቢሆንም ራዮ ቫዬካኖ እና ሄታፌ ላይ ሁለት ጊዜ ሁት ትሪክ መስራቱ እንደጠቀመው መዘንጋት አይገባም፡፡ ስለዚህ ልጁ በተቀሩት ጨዋታዎች ሁሉ ያስመዘገበው አራት ጎሎች ብቻ ነው፡፡
በእርግጥ ፔድሮ በቡድኑ ከኔይማር እና ከተሸሻለው አሌክሲስ ሳንቼዝ ፉክክር አለበት፡፡ ሆኖም ብዙ መሻሻል እንደሚገባው መናገር ይቻላል፡፡ ምክንያቱም አሁን እያሳየ ከሚገኘው ብቃት የተሻለ የማሳየት አቅሙ አለው፡፡ ፔድሮ ሴፕቴምበር አጋማሽ አካባቢ ባርሴሎናን በሙሉ ኃይሉ እያጠቃ የኋላ ክፍሉ በሳሳው ቫዬካኖ ላይ ሶስት ጎሎች ካገባ በኋላ ቀጣይ ጎሉን በቤቲስ ላይ ለማስቆጠር እስከ ኖቬምበር ጊዜ ፈልጓል፡፡ ለጎል የተመቻቸ ኳስ በማቀበልም ቢሆን በጉዳት ብዙ ጨዋታዎች ያለፉት ማሊ ከፔድሮ መሻሉ ያስደንቃል፡፡
ሆኖም ፔድሮ ብዙ የመሻሻል አቅም አለው፡፡ አሁንም ቢሆን ያለኳስ የሚያደርገው እንቅስቃሴ እና የሩጫ ፍጥነቱ ድንቅ ነው፡፡ ፍጥነቱ ሲስክን ከመሳሰሉ ተጨዋቾች ተከላካይ ሰንጣቂ ኳሶችን ለመጠቀም የተሻለ ዕድል ይሰጡታል፡፡ ነገር ግን አፈግፍገው የሚከላከሉ ቡድኖች ሲገጥሙት ብዙ መቸገሩን በልምምድ መቀየር አለበት፡፡

ሊዮኔል ሜሲ

አርጀንቲናዊው ጉዳት ባይረብሸው ኖሮ በ11 የሊግ ጨዋታዎች ስምንት ጎሎች እና በሶስት የቻምፒዮንስ ሊግ ግጥሚያዎች ስድስት ጎሎች ማግባቱ ሊያስመሰግነው በቂ ነበር፡፡ ሆኖም ጉዳት የዓለማችንን ድንቅ ተጨዋች ሜዳ ላይ ሆኖም በከፍተኛ አቅሙ እንዳይጫወት አድርጎት ነበር፡፡ የኑካምፕ ታዳሚዎች ምርጡ ልጃቸውን ከቀጣዩ ኤልክላሲኮ እና ከቻምፒዮንስ ሊጉ የማንችስተር ሲቲ ፍጥጫ በፊት በጤንነት ሊያገኙት ይፈልጋሉ፡፡ የባርሴሎና ደጋፊዎች አምና በባየርን የደረሰባቸው ሰቀቀን እንዳይደገም ቢያንስ ሜሲ ያስፈልጋቸዋል፡፡ እርሱ ጤነኛ ከሆነ የብቃቱ መመለስ ብዙም አያጠራጥርም፡፡ የዚህ ኮከብ ስም ‹‹መሻሻል በሚገባቸው›› ተጨዋቾች ዝርዝር ውስጥ መገኘቱ እንግዳ ቢሆንም በክረምት በርካታ የወዳጅነት ጨዋታዎችን ማድረጉ እንዲሁም እንደጎዳው መናገር ይቻላል፡፡ ሆኖም ወደ ሜዳ ሲመለስ ይበልጥ ተሻሽሎ እንደሚቀርብ ይጠበቃል፡፡
ሀቪየሮ ማሼራኖ

ማሼራኖ ዘንድሮ እያሳየ ያለው ብቃት መጥፎ አይደለም፡፡ ሆኖም የአርጀንቲናዊውን ድንቅ ችሎታ ለሚያውቁ ሁሉ የዘንድሮ አቋሙ ይበልጥ መስተካከል ይኖርበታል፡፡ ባርሴሎና ሁነኛ የመሀል ተከላካይ ማስፈረም ነበረበት የሚለው ቅሬታ ትኩረት ሳይደረግበት ቀረ እንጂ ማሼራኖ ይሰራቸው የነበሩት ስህተቶች ከወቀሳ የሚያድኑት አልነበሩም፡፡ የስፔን ጋዜጦችም ማሼራኖ የፔኬ እና ፑዮልን ቦታ መረከብ እንዳለበት ከመናገር ይልቅ ከውጪ በዝውውር ሊመጣ ስለሚችለው ጥሩ ተከላካይ መናገር ቀጠሉ እንጂ አርጀንቲናዊው በሁለተኛው የውድድር ዘመኑ አጋማሽ ተሻሽሎ ቦታውን መሸፈን እንደሚጠበቅበት አልጠቆሙም፡፡ ዘንድሮ ባርሴሎና ከሜዳው ውጪ ተጉዞ በሚላን እና አምሰተርዳም ሲጫወት ማሼራኖ የፈጸማቸው ስህተቶች ወደ ጎልነት ተለውጠዋል፡፡ ተጨዋቹ ጥሩ እርምጃ ወስዶ ያስጣላቸው ኳሶች ብዙ ቢሆኑም በስንፍና ወይም በፍጥነት ማጣት ያበላሻቸው ኳሶች ሊሻሻል እንደሚገባው ያሳያሉ፡፡

አሌክስ ሶንግ
ካሜሮናዊውን ለመመዘን ተጨዋቹን ከኳስ ጋር እና ያለ ኳስ ብሎ መለያየት ያስፈልጋል፡፡ ዘንድሮ ሶንግ በባርሴሎና ይበልጥ ተደላድሏል፡፤ ወደ ፊት ተጠግቶ እንዲጫወት ከተደፈቀደለት በኋላ የኳስ አያያዙ እና ውሳኔው ጥሩ ሆኗል፡፡ በመከላከሉ ረገድ ግን አፍሪካዊው አሁንም እንከኖች አልጠፉበትም፡፡ ሶንግ ምርጥ ሽርተቴዎችን ቢወርድም ቀጣዩን እርምጃ ለመውሰድ የሚያሳየው መንቀራፈፍ ለተጋጣሚ ሌላ አደጋ የመፍጠር ዕድል ይሰጣል፡፡ ቡስኬትስ ጨዋታን በማንበብ በኩል የተሻለ በመሆኑ አንዳንድ ጊዜ ኳሷን እግሩ ላይ ሊያገኛት ሌላ ጊዜ ደግሞ ሸርተቴ ሳይወርድ እንዲቀማ ያስችለዋል፡፡ ሶንግ ይህ ብቃት የለውም፡፡ ቡድኑ በሊጉ አነስተኛ ግምት ከሚሰጣቸው ቡድኖች ጋር ሲጫወት የሶንግ ፓሲንግ ስኬት እጅግ ከፍ ይላል፡፡ ሆኖም በትልልቆቹ ጨዋታዎች ይህንን ማድረግ አይችልም፡፡ ቡስኬትስ በማንቸስተር ሲቲው ጨዋታ ጉዳት ቢገጥመው ሶንግ ምን ያህል ቦታውን እንደሚሸፍን መገመት ይከብዳል፡፡ የቀድሞው የአርሰናል አማካይ በጥቃቱ ረገድ ዘንድሮ ብዙ የተሻሻለ ቢሆንም በመካከሉ በኩል ብዙ መስራት ይኖርበታል፡፡

ክርስቲያን ሬዮ
የባርሴሎና የቡድን አባላትን በቅርበት የሚገመገትሙ ተንታኞች ቴዮ ባለፈው የውድድር ዘመን እና በተጠናቀቀው ግማሽ የውድድር ዘመን በውሰት ሊሰጥ ይገባ እንደነበር ይናገራሉ፡፡ ፈጣኑ ወጣት ብዙ የመሻሻል ዕድል ቢኖረውም በኑካምፕ የመጫወት ዕድል ማግኘት አይችልም፡፡ በቀጣዮቹ ሳምንታት ሜሲ ወደ ሜዳ ሲመለስ የቴዮ የመጫወት ዕድል ይበልጥ ያበቃለታል፡፡ ምናልባትም አሰልጣኙ ከኮፓ ዴል ሬይ እና አልፎ አልፎ በሊጉ ጨዋታዎች ይጠቀመብት እንደሆነ ለመመልከት ጊዜ መጠበቅ ያሻል፡፡ አሁን ባለበት ሁኔታ ግን ተጫዋቹ እምቅ ችሎታውን አውጥቶ ማሳየት የሚችልበት እድል የለም፡፡

አይዛክ ኩኤንካ
ኩኤንካ ዘንድሮ ለባርሴሎና የመጫወት ዕድል አላገኙም፡፡ ሆኖም ከጉዳቱ ሲመለስ ለቡድኑ መጫወት እና ዕድገቱን የመቀጠል አጋጣሚው ይፈጠርለታል፡፡ እንደበርካታ የክለቡ ደጋፊዎች እምነት ኩኤንካ በኑካምፕ ከኢብራሂም አፌ ላይ ወይም ጆናታን ዶስ ሳንቶ በተሻለ ስኬታማ ጉዞ ሊኖረው ይችላል፡፡ ሆኖም ተጨዋቹ ከጉዳቱ በሚገባ ማገገም እና ዕድገቱን መቀጠል ይኖርበታል፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>