(ዘ-ሐበሻ) ባለፈው ሳምንት ዘ-ሐበሻ በሰበር ዜና እወጃዋ “እነ ሌንጮ ለታ ኢትዮጵያ ሊገቡ ነው” ስትል መዘገቧ ይታወሳል። የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግምባር ሊቀመበር የሆኑት አቶ ሌንጮ ለታ ጀርመን ድምጽ ራድዮ ላይ ቀርበው “አዎ እውነት ነው ሃገር ቤት ገብተን ልንታገል” ነው ሲሉ አረጋግጠዋል። “ባለፉት 20 ዓመታት ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ ይህ ወሬ ይወራ ነበር ያሉት አቶ ሌንጮ በቃለምልልሳቸው “ኖርዌይ ተቀምጬ ምን አደርጋለሁ፤ እዚህ የሚደረግ ትግል የለም ስለዚህ ሃገር ቤት ገብተን ነው የምንታገለው” ብለዋል።
“ለኢትዮጵያ ህዝቦች አዲስ ራዕይ አለኝ” በሚል የተመሰረተው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ህጋዊ መሰረት ያለው አገራዊ አንድነትን ለመመስረትና ለሁሉም የምትሆን ኢትዮጵያን ለማቅናት ሃገር ቤት በመግባት እንደሚታገል ይፋ አድርጓል።
አቶ ሌንጮ ለታ ከጀርመን ድምጽ ራድዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “ከመንግስትም ሆነ ከተቃዋሚዎች ጋር ድርድር እንፈልጋለን” ያሉበትን ቃለ ምልልስ ያድምጡት፦