Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ሰበር ዜና- የአቶ ገብሩ አስራት መኪና በእሳት ነደደች (በአስራት አብርሃም)

$
0
0

(በአስራት አብርሃም)

Seber Zenaየቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት እና የዓረና ሊቀመንበር አቶ ገብሩ አስራት ከባለቤታቸው ከወ/ሮ የውብማር አስፋው ጋር በመሆን በመኪና እየሄዱ እያለ ድንገት መኪናቸው በእሳት መያያዟን የተመለከቱ ሰዎች ባደረጉላቸው ጥቆማና ርብርብ ከእሳቱ ቃጠሎ ለጥቂት መትረፋቸውን ማወቅ ተችሏል። በመኪናዋን ግን እዚያ የነበረው ሰው ሁሉ ብዙ ርብርብ ቢያደርግም ከቃጠለው ማተረፍ አልተቻለም። በእውነቱ ይህን መረጃ እንደደረሰኝ አላመንኩም ነበር፤ በመሆኑም ወዲያው ወደ አቶ ገብሩ አስራት ስልክ ደውዬ እውነት መሆኑን ማረጋገጥ ችያለሁ። ነገር ግን ይሄ አደጋ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ የግዲያ ሙከራ ይሁን አሊያም በአጋጣሚ የተፈጠረ የእሳት ቃጠሎ ይሁን ማወቅ አልተቻለም። የአቶ ገብሩ ባለቤት ወ/ሮ የውብማር አስፋው ህወሃት ባካሄደው የትጥቅ ትግል ግንባር ቀደም ሚና ከነበራቸው ጥቂት ሴት ታጋዮች ውስጥ የሚመደቡ እና “ፊኒክስዋ ሞታም ተነሳለች፥ ያልተቋጨው የትግራይ ሴቶች ትግል” የሚለውን መፅሐፍ የፃፉ ናቸው።
ለማነኛውም ለአቶ ገብሩ አስራት እና ለባለቤታቸው ወ/ሮ የውብማር አስፋው እንኳን በህይወት አተረፋችሁ ለማለት እፈልጋለሁ።

https://www.facebook.com/abraha.desta1


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>