Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Health: 9ኙ ቦርጭን ማጥፊያ የምግብ ዓይነቶች

$
0
0

(ይህ ጽሁፍ በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 58 የታተመ ነው።)
ሆድ አካባቢ የሚገኝን የስብ መጠን(ቦርጭን) ለመቀነስ ሙከራ ሲያደርጉ የፕሮቲን ይዘታቸው ከፍ ያለ፣ ሰውነት ውስጥ ተቋጥሮ የሚገኝን አላስፈላጊ ውሃ ማስወገድ የሚችሉ እና የምግብ መፈጨት ሂደትን የሚያቀላጥፉ ምግቦችን መርጦ አዘውትሮ መመገብ ይመከራል፡፡ እነዚህ ምግቦች የምግብ መፈጨት ሂደትን ቀልጣፋ ከማድረግ ባሻገር ሆድ አካባቢ የሚገኝን አይነተኛ ሚና ይጫወታሉ፡፡
ቦርጭን (ሆድ አካባቢ የሚገኝን የስብ መጠን) ሊቀንሱ የሚችሉ የምግብ አይነቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
color-133-Tomato-2
ቲማቲም

ቲማቲም ስብን ለማቃጠል ከሚረዱ ምግቦች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ ቲማቲም የማይነጥፍ ‹‹Anti oxidants›› በአጭሩ ኦክሲጅን ከሌሎች ‹ፍሪ ራዲካልስ› ከሚባሉ ንጥረ ነገሮች ጋር ውህደት በመፈፀም ሰውነት ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳይ ይከላከላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ቲማቲም ‹ሌፕቲን› የተሰኘ ፕሮቲን ሰውነታችን ውስጥ በብዛት እንዲመረት ስለሚያግዝ የምግብ ፍላጎትን ይጨምራል፡፡ እንዲሁም የምግብ መፈጨት ሂደትን ቀልጣፋ ያደርጋል፡፡
ሀባብ

ሀባብ የውሃ ሀብታም ነው፡፡ 94% የሚደርሰው ይዘቱ ውሃ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ተመራጭ አነስተኛ ካሎሪ ያለው ፍራፍሬ ነው፡፡ ሆድ አካባቢ የሚገኝን አላስፈላጊ ፈሳሽ በማስወገድ የሆድ መጠን እንዲስተካከል ያደርጋል፡፡ ሆድ አካባቢብቻ ሳይሆን ሌሎች የሰውነት ክፍሎ ውስጥ ውሃ አለአግባብ እንዳይጠራቀም ያደርጋል፡፡
እንጉዳይ

እንጉዳይ የ‹ፋይበር› ይዘቱ ከፍተኛ ስለሆነ ረዘም ላለ ጊዜ ጥጋብ እንዲሰማችሁ በማድረግ የምግብ ፍላጎታችሁን እና አወሳሰዳችሁን ይቀንሳል፡፡ የምግብ መንሸራሸር ሂደትንም ያቀላጥፋል፡፡
papaya
ፓፓያ
ፓፓያ ሆድ አካባቢ የሚገኝን ስብ ለማቃጠል በእጅጉ ይረዳል፡፡ ‹ፓፔይን› የሚባል ኢንዛይም ውስጡ ስለሚይዝ ይህ ኢንዛይም ደግሞ ምግብ በፍጥነት እንዲሰባበር እና ሆድ ልሙጥ እንዲሆን ያግዛል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ፓፓያ አላስፈላጊ እብጠት እና መነፋትን ያስተካክላል፤ የምግብ መፈጨት ሂደትንም ቀልጣፋ ያደርጋል፡፡
ኦሊቭ ኦይል
ብዙዎቻችን ክብደት ለመቀነስ ሙከራ ስናደርግ ከስብ ነክ ነገሮች እንድንርቅ ተመክረናል፡፡ ነገር ግን ኦሊቭ ኦይል ውስጥ የሚገኘው ኦሌይክ አሲድ ደማችን ውስጥ የሚገኝን የስኳር መጠን በመቆጣጠር ለክብደት መቀነስ ቀላል የማይባል አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡
አልሞንድስ
አልሞንድስ የካሎሪ ይዘታቸው ከፍተኛ ቢሆንም ሆድ አካባቢ ውፍረት በመፍጠር ግን አይታሙም፡፡ ይልቁንም ለቆዳ ጤንነት መጠበቅ እገዛ ሊያደርግ የሚችል ቫይታሚን ሲ ውስጣቸው ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የፋይበር ይዘታቸው ከፍተኛ በመሆኑ የምግብ ፍላጎትን ያስተካክላሉ፤ የምግብ መፈጨት ሂደትን ያፋጥናሉ፡፡ ይህ በበኩሉ ሰውነታችን ውስጥ የሚገኝን አላስፈላጊ ስብ በማቃጠልና በማቅለጥ ክብደት እንድንቀንስ ያግዛል፡፡
banana
ሙዝ
ክብደት ለመቀነስ ሙከራ ስናደርግ ብዙዎቻችን ሙዝ መመገብ እናቆማለን፡፡ ይሁን እንጂ ሙዝ የፖታሺየም ይዘቱ ጥሩ በመሆኑ ሰውነት ያለአግባብ የሚቋጥረውን የውሃ መጠን ይቀንሳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሙዝ በፋይበር የበለፀገ ስለሆነ የምግብ ፍላጎታችሁ ያለአግባብ ሳይጨምር ጤናማ ሆኖ እንዲቆይ እገዛ ያደርጋል፡፡
አፕል
አፕል መርዛማ ነገሮችን የማስወገድ ባህሪ አለው፡፡ በዚህ ምክንያት የምግብ መፈጨት ሂደትን ቀልጣፋ ያደርጋል፤ ሰውነታችን ውስጥ የሚገኝ አላስፈላጊ ውሃም እንዲወገድ ያደርጋል፡፡
ኦትስ
ኦት የካሎሪ ይዘቱ አነስተኛ ቢሆንም ለሰውነት የሚሰጠው ኃይል ግን ከፍተኛ ነው፡፡ ክብደት መቀነስ ስትፈልጉ ታዲያ ጠዋት ከቤታችሁ ኦትስ ቀማምሳችሁ ብትወጡ በቂ ኃይል ስለሚሰጣችሁ የምግብ ፍላጎታችሁን ጋብ አድርጎ በማዋል ክብደት እንድትቀንሱ ያደርጋል፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>