Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ሆቴል ውስጥ የተደባደቡት የብሔራዊ ቡድናችን ተጫዋቾች ሲሳይ ባንጫንና አበባው ቡታቆ ተቀጡ

$
0
0

Abebaw-Butakoየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን ጥፋት ፈፅመዋል ባላቸው ተጫዋቾች ሲሳይ ባንጫ እና አበባው ቡታቆ ላይ የገንዘብ ቅጣት መንግስታዊው ሚዲያ ራድዮ ፋና ዘገበ። ሲሳይ ባንጫ የአስር ሺህ አበባው ቡታቆ ደግሞ የአምስት ሺህ ብር ቅጣት ነው በፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተወሰነባቸው።
እንደ ፋና ዘገባ ተጫዋቾቹ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ካላባር ላይ ከናይጄሪያ አቻው ጋር ከተጫወተ በኋላ ቡድኑ ባረፈበት ሆቴል ውስጥ በመጣላታቸው ነው ቅጣቱ የተወሰነባቸው። ፌዴሬሽኑ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው ግብ ጠባቂ ሲሳይ ባንጫ ከቡድን አጋሩ ጋር መጣላቱን በማመን ይቅርታ ጠይቋል።
ራድዮው ጨምሮም በተመሳሳይም ተከላካዩ አበባው ቡታቆ የፀቡ መነሻ እንዳልሆነ በመግለፅ ነገር ግን ከቡድን አጋሩ ጋር መጣላቱ ስህተት መሆኑን አምኖ ይቅርታ ጠይቋል።
የፌዴሬሽኑ አመራሮችም በወቅቱ በተጨዋቾቹ የተፈፀመውን የስነ ምግባር ግድፈት በተመለከተ የምስክርነት ቃላቸውን መስጠታቸውንም ነው መግለጫው ያመለከተው። ከዚህም በመነሳት በፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የገንዘብ ቅጣቱ የተወሰነባቸው ሲሆን ወደፊትም እንዲህ ዓይነት
ከባድ ጥፋት እንዳይፈፅሙ ከባድ ማስጠንቀቂያም እንዲደርሳቸው መወሰኑን ነው ፌዴሬሽኑ መግለጹን ራድዮው ዘግቧል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>