ዳዊት ሰለሞን
መስከረም 3/2004 የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ የሆነውን አንዷለም አራጌ፣የብሄራዊ ምክር ቤት አባሉን ናትናኤል መኮንንና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በቁጥጥር ስር መዋላቸው አይዘነጋም፡፡መንግስት ተጠርጣሪዎቹን ካሰረ በኋላ አሁን በህይወት የሌሉት መለስ ዜናዊ በፓርላማ‹‹ማስረጃም መረጃም አለን››በማለት እነአንዷለም ሽብርተኞች ስለመሆናቸው በድፍረት መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ኢቴቪም ከጸረ ሽብር ግብረ ሀይል ጋር በመተባበር መለስ የፎከሩበትን መረጃና ማስረጃ ‹‹አኬልዳማ››በሚል ርዕስ ለማሳየት መዘጋጀቱን አታሞ መጎሰም ጀመረ፡፡አኬልዳማ ተጠርጣሪዎቹን ከፍርድ ቤት በፊት በሽብርተኝነት የወነጀለ፣ፓርቲውን ከሽብርተኛ ተቋማት ጋር ጋብቻ እንደፈጸመ አድርጎ በተራ ውንጀላ የፈረጀና የአንድነት አባላት ያልሆኑ ሰዎችን አባላት በማድረግ ያቀረበ የተለመደው ማጥላላት፣ሴራና ውሸት በመሆኑ ፓርቲው ለኢቴቪ አቤቱታ በማቅረብ እርምት እንዲወሰድ ይጠይቃል፡፡የኢቴቪ ቦርድ አመራሮች ግን ለዚህ ጆሮ አልነበራቸውምና፡፡በጥር 2004 ፓርቲው ክሱን አቀረበ፡፡
የፓርቲው ጠበቆች በቢፒአር መታየት ይገባዋል በማለት በፍጥነት እንዲታይላቸው ያቀረቡት ክስ እነሆ እስካሁን ድረስ ውሳኔ ሳያገኝ በድጋሜ ለጥር ወር ቀጠሮ ተሰጥቶታል፡፡ለ20ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረበው ክሱ በጥር ወር ሁለተኛ አመቱን ይደፍናል፡፡
↧
ፍርድ ቤቱ አንድነት በኢቴቪ ላቀረበው ክስ ውሳኔ መስጠት ተስኖታል
↧