ሥርጉተ ሥላሴ 22.12.2013
ዕለቱ ሰንበት የተቀደሰ የተወደደ በፈጣሪው የተመረጠ ነበር። በዲኔግዲ አማክኝነት ሸገር የዘገበው የታልቅ ሚስጢር ዕውነተኛ ቀን ነበር 08.12.2013። በዚህ ሰዓት ነበር አባ መላ /አቶ ብርኃኑ ዳምጤ/ የሩሙ ባላቤት እጅግ በተመሰጠና ተቆርቆሪነቱ በአዬለ ሁኔታ በዕለቱ ስልኩን ፈልጎ ቃላቸውን በጀሯችን ያደረሰን። ስደት ደስታን የሚገፍ ሲሆን ያን ቀን ግን እውነተኛ ደስታ ነበር የተሰማኝ ከደስታም በላይ ሐሴት። በወቅቱ „ኢትዮጵያዊነት የታላቁን የሰላም አባት የኔልሰን ማንዴላ ህይወት የታደገ ታላቅ ሚስጢር …. አነጠረ።“ በሚል አንድ መታጥፍ ቢጤ ጽፌ ዘኃበሻም ታድጎኝ ለንባብ በቅቶ ነበር አመስግናለሁም።
አባ መላ ጥሩ ተናጋሪ ነው። ንግግር ሥነ – ጥበብ ነው። ጸጋም ነው። ተሰጥዖ። ሥጦታውም የማዳህኒዓለም ቢሆንም በክህሎት፤ በስልጠና ሥነ ደንቦችን በማጥናት ማሳደግ የሚቻል ጉልበታም ፊኖሚና ነው። ንግግር አድማጭን ወደ ተፈለገው አቅጣጫ የሚመራ የተዋጣለት መሪ ነው። ጥሩ ንግግር … በእጅ ያለ ወርቅ ነው። ጥሩ ንግግር ገዢ መሬት ላይ አለ አጥቂ ሰራዊት ነው። ይህን ለመልካም ተግባር ካዋሉት ውስጥ ዕውቅ የዓለማችን ሰዎች ውስጥ ኪንግ ማርቲን ሉተር፤ ፕሬዚዳንት አብርኃም ሊንከን፤ ማህተመ ጋንዲን ትናት፤ ዛሬ ደግሞ ፓኪስታናዊዋ የ16 ዓመቷ ታዳጊ ወጣት የታለቢና ጥቃት ሰለባ ሆና ከሞት የተረፈቸው ማላለ ለምሳሌነት ብናነሳ … ለጥፋት ደግሞ ጀርማናዊ አዶልፍ ሂትለር – ለናኒዝም፤ ሞሶሎኒ – ለፋሺዝም ተግባራዊነት ህዝብን በምዕላት ያንቀሳቀሱበት ታላቅ መሳሪያ ነው።
እኔ የአባ መላን የንግግር ጸጋ የማዬው ከዚህ አንጻር ነው። አባ መላ የተዋጣለት ተናጋሪነቱ ብቻ ሳይሆን የድምጹ ቃና ሳቢነት፤ እንዲሁም ሳቁ እራሱ ውበት አለው። ጥሩ ተናጋሪ ልብን ገዝቶ፤ ግርቶ ወደ ተፈለገው አቅጣጫ የመምራት ሞገዱ ሆነ አቅሙ መጠነ ሰፊ ነው። የአባ መላ የመታገስ አቅም፤ ኦዲዬንስ እንደ ባህሪው ለማስተናገድ ያለው ስልት፤ ከተረብ ጋር ይመቻል። የነፃነት ጉዞም ምልክት ነው – ለእኔ። የተመቸንና ያልተመቸን ኃሳብ አንዱ ለሌላው ቢጎረብጠውም አለስልሶ እውነትን አሸናፊ የማደረግ ኃይሉ ዓምድ ነው። አንድ ጊዜ እንደ ዋዛ „ከአባይ በፊት ሽሮ ይገደብ“ ሲል አዳምጥኩት። ይህ ቅኔ ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ ላይ ወፈር ያለ ሽሮ ሰርቶ ለመብላት እንኳን ያልተቻለበት የተፋቀ ዘመን ስለመሆኑ እዬሳቀ ግን መንፈስን ሰርስሮ የገባ ሥነ – ቃላዊ አገላላጽ ነበር። ይህ አገላለጽ ህሊናን በአግባቡ የማዘጋጀት ስበቱ እጅግ ጠንካራና ረቂቅ ነው።
የታላቁ ሚስጢር ባላቤትና ባለውለታ የሆኑትን ትክሊላችን ካፒቴን ሻንበል ጉታ ዲንቃን ህይወት ከኢትዮጵያዊነት ሚስጢራዊ ተፈጥሮ ጋራ ከፍ ብሎ ዕውቅና እንዲያገኝ የነበረው ፍላጎትና ጉጉት ውስጡን ገልጦ ያሳይ ነበር ንግግሩ። ያን ቀን አባ መላ ዓዋጅም ዓወጆ ነበር ከእንግዲህ አለ … “ልጅ የምትወልዱ ቤተሰቦች ልጆቻችሁን ጉታ ዲንቃ እያላችሁ ጥሩ“ አለ። የዛሬ ሳምንት ደግሞ „ ኢትዮጵያዊነት መሪ አገኘ ጉታ ዲንቃን“ አለን።
የካፒቴን ጉታ ዲንቃ ህልም ደቡብ አፍሪካ ሄዶ የምህረት፤ የትግል፤ የጽናት፤ የይበቃኛል አባት ከሆኑት ከኔልሰን ማንዴላ ቀብር ላይ መገኘት ስለነበር። የማይቻለውን ቻለ። በአራት ቀን ውስጥ ከኢትዮጵውያን የሚሰበሰበወን ገንዘብ ሳይጠብቅ የራሱን ገንዘብ የትኬት ምግዣ ልኮ። የኢሳትን ቲም፤ አርቲስት ታማኝ በዬነን፤ አቶ ነዓምን ዘለቀን በመያዝ በንዑድ ቅንነት ተግባሩን ጀመረ። በሩሙ ታዳሚዎች በመተማመን። ያው በፍቅር ስለሚያስተናግድ ለፍቅሩ የሚቻለውን ዋጋ ለመክፈል የቻሉ፣ በወቅቱ መልዕክቱን ያደመጡ፣ እንደ አቅማቸው ተባበሩት። ሀገር ውስጥም ደቡብ አፍሪካም የነበረውን ትብትቡን ቢሮክራሲ በታታሪንት ተቋቁሞ የዛሬ ሳምንት ዕለተ ቅዳሜ 14.12.2013 ዘውዳችን ሻንበል ጉታ ዲንቃ አውሮፕላን ውስጥ እንዳሉ ሲነገረን ፈነጠዝን። ዛሬ እኛነታችን፤ ማንነታችን ፈተና ላይ ወድቆ፤ ባለቤት አጥቶ ወገኖቻችን በዬተሰደደበት እያታነቁ በሚገደሉበት ወቅት አጋጣሚው የሰማይ ገድል ነበር። ሊያመልጠን አይገባም ነበር። በተባረኩ ወገኖችም አጋጣሚው እነሆ አፈራ። ቀሪው የሎቢ ተግባር ተጠናክሮ ከተሰራበት የበለጠ ትርፋማ መሆን ይቻላል። ኢትዮጵያዊነት የተከበረ ሰንደቅ ስለመሆኑ የዓለም ሚዲያ እንደመሰክር ማደረግ ይቻላል።
የተከበሩ ሻንበል ጉታ ዲንቃ ደቡብ አፍሪካ ከደረሱበት እስከ ተመለሱበት ድረስም የደቡብ አፍሪካ ጥቁር አንባሶች የኢትዮጵያዊነት ዓርማ ናቸውና አደራቸውን በተግባር አቅልመው ኢትዮጵያዊነትን ከፍ አደረጉልን። እግዚአብሄር ይስጣችሁ። በ2013 የአፍሪካ የእግር ኳስ ዋንጫ ወቅት ኢሮ ስፖርት ደቡብ አፍሪካ ላይ ስለሚገኙት ኢትዮጵውያን ልክ እንደ ሀገሩ ዜጋ ነበር በክብር ሲገልጻቸው የነበረው። ያኮራሉና! ኢሮ ስፖርት ስለ ኢትዮጵውያን የዘገበው እጅግ ነፍስን የሚገዛ ነበረ። ዛሬም ታሪካዊ ኃላፊነተቸውን በብቃት ተወጡ ሁነኛዎቻችን መካታና መመኪያዎቻችን ናቸው። ጠቅላላ ቃለ ምልልሱ፤ ምን እንደ ተሳማቸው ምስጋናው ሁሉም አለ …. ያልነባራችሁ ሲቢሊቲ ሩም እንሆ …. የ22.12.2013 የካፒቴን ሻንበል ጉታ ዲንቃ ቃለ ምልልስ በሲብሊቲ ሩም … „ፓን አፍሪካኒሰት የዘመኑ“ ይላቸዋል አባ መላ። በ አስር እጣታችን እንፈርማለን …. ጧፋችን ….
ማጠቃለያ …. አረሙ ወያኔ የምታሴሩትን የልዩነት ትብትብ ኢትዮጵውያን ፈተን አንድ ቀን ኢትዮጵያ ወደ ነበረችበት ክብር ትመለሳላች። በዚህ መልክ በትግባር፣ በመደማመጥ፣ ከተጋን አትጠራጠሩ የቀን ጉዳይ ነው። ከዚህ በተጨማሪ አሁንም የታሪካችን ሚስጢር አካል የሆኑት የጄ/ታደሰ ብሩ ልጆች ቤተሰቦች ይኖራሉ። እነሱን አፈለልጎ የተገባውን ክብር መስጠት የተገባ ነው። ከዚህ በተጨማሪም የማዲባ የቅርብ ጓደኛቸውና መምህራቸው የነበሩት ዛሬ ህመም ላይ ያሉት የኮ/ ፈቃደንም ጉዳይ የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ራዲዮ ያደረገው ቃለ ምልልስ በተጠናከረ ሁኔታ ቀጥሎ ትውልዱ ታሪኩን በአግባቡ ይዘግበው ዘንድ ዝቅ ብዬ አሳስባለሁ። አክብሮታችን ፍለጋችን እኩል በተግባር ደምቆ መከናወን አለበት። ኢትዮጵያዊነትም ወደ ዘውዱ።
ዛሬ ደግሞ አባ መላ አዲስ ሃሳብ ይዞ መጥቷል ከትንሹ እንጀምር እያለን ነው። ወያኔ ለእርቅ ጠርቶ እስርና ለበሸታ የዳረጋቸውን ጽኑ አቶ አበራ የማናአብ ከቤተሰባቸው ጋር አሜሪካን ሀገር የማቀላቀሉ የሎቢ ተግባር አብረን እንታደም ዘንድ አሳስቦናል። ወያኔ የሚጠላውን ስንፈጽም ወያኔን በቁሙ መግደል እንችላለን። ለነጻነት የአንድ ወጣት ዕድሜን ያሳለፉ፤ በሳንባ በሽታ የተጠቁ አካላችነን በአክብሮት ማገዝ በመርዳት ከጎን ተሰልፎ የድርሻን መወጣት ይገባል – ከትህትና ጋር። ቃለ ምልልሱ፤ ምን እንደ ተሳማቸው ምስጋናው ሁሉም አለ …. ያልነባራችሁ ሲቢሊቲ ሩም እንሆ …. የ22.12.2013 የካፒቴን ሻንበል ጉታ ዲንቃ ቃለ ምልልስ በሲብሊቲ ሩም … „ፓን አፍሪካኒሰት የዘመኑ“ ይላቸዋል አባ መላ። በ አስር እጣታችን እንፈርማለን …. ጧፋችን …. ልብል እኔ ደግሞ
ኢትዮጵያ ለዘለ ዓለም ትኑር!
እግዚአብሄር ይስጥልኝ