Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የወያኔ ልዩ ፖሊስ በምስራቅ ሃረርጌ ዞን ንጹሃንን በጥይት ፈጀ

$
0
0

(ከምኒልክ ሳልሳዊ) በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልላዊ መንግስት ሚሊሻዎች የሆኑ እና “ልዩ ፖሊስ” በመባል የሚታወቁት የወያኔ የጸጥታ ሃይሎች በምስራቅ ሃረርጌ ዞን አራት ንጹሃን ዜጎችን ገለው ሁለት ማቁሰላቸው ታውቋል::እንዲሁም እስካሁን ቁጥራቸው ያልታወቁ ነዋሪዎች ከአከባቢው መፈናቀላቸው ታውቋል::

ባለፉት ወራቶች ጀምሮ የልዩ ፖሊስ ሃይሎች አከባቢውን በመውረር በዚሁ ምስራቅ ሃረርጌ በማዩ ሙሉጋ አከባቢ የሚኖሩ ንጹሃንን በማንገላታት በማሰር በመግደል የአከባቢውን ነዋሪዎች ከአከባቢው በማፈናቀል ላይ ሲሆኑ ይኸው ወረራ እና ማፈናቀል መግደል ጡምቢጎሃ ; ሴላጃጆ እና አናሚኖ;በስፋት እየተካሄደ ሲሆን አብዛኛው የአከባቢው ነዋሪዎች ቦታቸውን በመልቀቅ ይህንን የወያኔ ወረራ በመሸሽ ከአከባብያቸው ተፈናቅለው ወደ ቡርቃ ቲልጢላ እና የአከባቢ ወረዳዎች በመሸሽ ቦታቸውን የአከባቢው የወያኔ ሚሊሻዎች ወይንም ልዩ ፖሊስ ተቆጣጥሮት ይገኛል::


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>