ቢቢኤን ሰበር ዜና
ልዩ ፕሮግራም
ሁሉም ኢትዪጲያዊ ሙስሊም ሊሰማው የሚገባው የችሎት ውሎ
የኮሚቴዎቻችንን ጠበቆች ተማም አባቡልጉንና ጠበቃ አዲስን አነጋገራናል፡፡ትግሉ በተጠናከረ መልኩ ለመቀጠል ህዝቡ የአሚሩን ትዛዝ በመጠበቅ ላይ ነው
መንግስት ከሰረየሰላም አምባሳደር በሆኑት የብርቅ ሰብእና ባሌበቶች ላይ መንግስት ፖለቲካዊ ፍረጃዉን ጭኖባቸዋል፤ ይህ ደግሞ መንግስት መክሰሩን ፍንትዉ አርጎ የሚያሳይ ነዉ።በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ዉድ ዜጎች የተወከሉትን ኢትዮጵያዉያንን ፍትህ-አልባ በሆነዉ ፍርድ-ቤት ለማሸማቀቅ መሞከሩ፤ አለም-አቀፋዊ የሆኑ የህግ መስመሮችን አልፎ ሰርዓት-አልበኝነትን ለማንገስ የሚደረግ አይን-አዉጣነት በመሆኑ በዛሬዉ ችሎት መንግስት ከስሯልና እናንተ የተስፋ ባለቤት የሆናችሁ ኢትዮጵያዉያን ድል አይቀርምና ተጽናኑ።መንግስት የኛዎቹን ማንዴላዎች መፍታት ሲገባዉ ወደ እስር ቤት ልኳቸዋል። የትላንቶቹ አፓርታይዶች ኩምሽሽ-ሽምቅቅ-ስዉር እንዳሉት የዛሬዎቹም የኢትዮጵያ አፓርታይዶች ኩምሽሽ-ሽምቅቅ-ስዉር ማለታቸዉ አይቀሬ ነዉ። ልክ እንደማንዴላ ሁሉ ኮሚቴዎቻችን ከተጎናጸፉት የሰብዓዊነት ማእረግ በላይ እፁብ-ድንቅ ምድራዊ ብሎም ሰማያዊ የሆነን የብርቅ ሰብእናን እርከንን ይሻገሩ ዘንድ የፍትህ ቀበኞች ወደ እስር ቤት መልሰዋቸዋል። ድል አይቀርምና ወደ ድል በሚያሽግረዉ ሰላማዊ ታንኳ “ድምጻችን ይሰማ!” እያልን በቃልኪዳናዊ ጥምረት እንጓዝ። ልብ ያለዉ ልብ ይበል!
BBN Your Voice