Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Hiber Radio: “በሳውዲ አሁንም ከሰማኒያ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን በየቤቱ ተደብቀው የሳውዲዎቹን ቅጣት እየጠበቁ ነው”ነብዩ ሲራክ (ቃለምልልስ)

$
0
0

የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ህዳር 29 ቀን 2006 ፕሮግራም

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

<<... ኢትዮጵያውያን ከማንዴላ ብዙ ሊማሩ ይገባል ከጎሳ ይልቅ ሰብዓዊነት ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል። የገዢው ፓርቲ ሰዎች የትግራይ ተወላጅ የስርዓቱ ደጋፊዎች ይህን የምንዴላን ሞት ጥሩ አጋጣሚ አድርገው መውሰድ አለባቸው ።የብሔራዊ እርቅ በአገሪቱ ያስፈልጋል አሁን ያለው የአፓርታይድ ስርዓት ...>>

አቶ ኦባንግ ሜቶ ማንዴላን ስናከብር ኢትዮጵያውያን መርሳት የሌለብን ባሉዋቸው ጉዳዮች ላይ ከህብር ጋር ካደረጉት ቃለ ምልልስ የተወሰደ

<<...በሳውዲ አሁንም ከሰማኒያ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን በየቤቱ ተደብቀው የሳውዲዎቹን ቅጣት እየጠበቁ ነው። ይህ አሳሳቢ ነው። አገር ቤት አስቀድሞ በገቡት ላይ ንብረታቸው ቦሌ ላይ መቀማቱን ገልጸዋል ። ይህ መስተካከልና በስደት ያፈሩትን እንዲቋቋሙበት ከቀረጥ ነጻ እንዲያስገቡ መፈቀድ አለበት ይህ ካልሆነ ምን አገር አለን እዚሁ የሚመጣውን እንቀበላለን ብለው ብዙዎች አሉ አፋጣኝ ምላሽ ይጠብቃሉ...>>

ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ከሳውዲ አሳሳ ስለሆነው በሳውዲ ስለቀሩ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ለህብር ከሰጠው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ

ማንዴላ ልዩ ዝግጅት

የዓለም መሪዎች ስለ ማንዴላ ምን አሉ? (ልዩ ጥንቅር)

<<...በአሜሪካ በፕ/ት ሬገን ማንዴላ የትጥቅ ትግል ማወጃቸውን በመቃወም አሸባሪ ተብለው መመዝገባቸውን በመቃወም በኮሎራዶ ዩኒቨርስቲ ተማሪ እያለሁ ሰልፍ ወጥተን ነበር...እንደ ማንዴላ ለነጻነት መቆም ተስፋ ሳይቆርጡ ጸንቶ መቆምና አሸናፊነትን መቀዳጀት መማር አለበት... >>

ዶ/ር ሙሉጌታ ካሳሁን የማንዴላ ሞት ተከትሎ ካደረግነው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ

<<... የዘሐበሻ አንባቢዎች ሁሉም ጊዜና ገንዘባችንን መስዋዕት አድርገን እንደምንሰራ ይረዳሉ ብዬ አላስብም...ዘሐበሻ ከዜሮ ተነስተን ዛሬ ሚሊዮን አንባቢያንን በመላው ዓለም አፍርታለች ድህረ ገብዙዎች ጹን ይጎበኙታል...>> ጋዜጠኛ ሔኖክ አለማየሁ የዘሐበሻን አምስተኛ ዓመት አስመልክቶ ለህብር ከሰጠው ቃለ መጠይቅ

ማንዴላ!(ወቅታዊ ግጥም በጸሐፊው አንደበት)

ሌሎችም ዝግጅቶች

ዜናዎቻችን

- በሳውዲ የቀሩ ቁጥራቸው ከ80 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን አደጋ አንዣቦባቸዋል

- አገር ቤት የገቡት ንብረታቸው ቦሌ ላይ እየተዘረፈ መሆኑን ገለጹ

- በደቡብ አፍሪካ ለማንዴላ ዛሬ በአገሪቱ ብሔራዊ የጸሎት ስርዓት ተደረገ

- ዓለም ዕውቁን የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ በልዩ ልዩ ዝግጅት እያከበረ ነው

– የሱዳን ፕ/ት አልበሽር በምስጢር የኢትዮጵአና የኤርትራ መሪዎችን ለማደራደር ሽር ጉድ ማለታቸው ተገለጸ

- የኢትዮጵያ ጦር ትላንት ከአልሸባብ ጋር ሊፋለም ባኮል ግዛት መግባቱ ተዘገበ

- የሱዳን ብሔራዊ ቡድን የኢትዮጵያን ቡድን 2 ለ 0 አሸነፈ

ሌሎችም ዜናዎች አሉን


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>