ከ ጻድቅ አህመድ
በሺዎች የሚቆጥሩ ተሳትፈዉበታል
የህወሃትን ማስፈራራትና ማፈራራት ችላ በማለት በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ዛሬ ገና ጎሕ ሳይቀድ ወደ ቂሊንጦ ወህኒ ቤት ተመሙ። የታሰሩትን የሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎችንና ሌሎችን የሕሊና እስረኞችን በመጠየቅ ህዝባዊ እንቢተኝነትንም አሳዩ።
ህወሃት መራሹ የ ኢትዮጵያ መንግስት በሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ላይ በካንጋሮ ፍርድ ቤቱ ሊፈርድባቸዉ እያቅማማ ቢሆንም ዛሬ በነቂስ የወጣዊ ህዝብ “ዋ!.. በነርሱ ላይ መፍረድ በኛ ላይ መፍረድ ማለት ነዉ” በማለት ሰላማዊ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶታል።
ህወሃት በነዚህ የሰላም አንባሳደሮች ላይ የረከሰ ፖለቲካዊ ፍርዱን በይኖ ለተለመደዉ የይቅርታ ፍጆታዉ ከዲያስፖራ ሰዎችን በመመልመል ቢኳትንም እራሱ በድሎ በስዉር ሽምግልና ይቅርታ ለማስጠይቅ የሚያደርገዉ ሙከራ በገሃድ ሲከሽፍበት ተስተዉሏል በሺዎች የሚቆጠሩ ዛሬ የድምጻችን ይሰማን ትእዛዝ ተከትለዉ “ዋ” ብለዉታልና!
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን ምን ይላሉ?
“ጽናት ከደማችን የተቀላቀለ የማንነታችን ምስክር ነው!…ጽናት እኮ የማነነታችን ነጸብራቅ እንደሆነ ላለፉት ሁለት አመታት አሳይተናል።ለበደል ለጭቆናዉ ናዳ ናዳ በህብረ ድምጽ በቃልኪዳናዊ ቅላፄ በአንድ አምላካዊ ጎዳና ወደ ነፃነት እየተጓዝን “አሃዱን አሃድ” እንላለን ።ስቃይንም መከራንም ልክ እንደ ዉዱ የሐበሻ ልጅ ቢላል እንችላለን! ከስቃይንና መከራም በሗላም በስኬት ተምሳሊትነት እንደተዘከሩት የብርቅ ስብእና ባለቤቶች እንዘከራለን። እናንት ከንቱ አንባገነናዉያን ሆይ!…ግድ የለም…አንባገነናዊ ክንዳቹ እስኪዝለፈለፍ ድረስ አሰቃዩን…መግረፍ፣መደብደብ፣ማሰርና መግደል ሲያቅታቹ እዉር ድንብራዊ መፈርጠጥን ትፈረጥጣላቹ። ዛሬ በቂልንጦ የጽናት ድምጽን አስተዉላችሗልን?ጽናታዊ ጉዞአችን ይቀጥላል…ልክ እንደቢላል ሁሉ “አሃዱን አሃድ!” የሚል ድምጽ ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ እያስተጋባ ነዉ እኮ!..ዋ!” ይላሉ ሚሊዮኖች ይህ የናንተዉ የኛዉ ድምጽ የሆነዉ ቢቢኤን ነዉ ሊንኩን በመጫን ፕሮግራሙን ያዳምጡ ለሌሎችም ያስተላልፉ።ልብ ያለዉ ልብ ይበል!