Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በሳዑዲ አረቢያ አልቃሲም ከተማ አፈሳ ተጀመረ

$
0
0

Saudicry
(ዘ-ሐበሻ) ከሳዑዲ አረቢያ 13 ግዛቶች ውስጥ በሰው ብዛት 7ኛ እንደሆነች በሚነገርላት አል ቃሲም ከተማ ስደተኞችን ማፈስ ተጀመረ። ከትናንት ጀምሮ ፖሊስ በየቤቱ እየሰበረ በመግባት ስደተኞችን እያፈሰ መሆኑን ከአካባቢው የዓይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ በላኩት መረጃ ዘገበዋል።

ከዚህ ቀደም በሪያድና በመካ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሞት፣ ለድብደባ፣ ለዝርፊያና ለአስገድዶ መደፈር ያበቃው ስደተኞችን የማባረሩ ተግባር ወደ አልቃሲም ከተማ ተሸጋግሮ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካታ ኢትዮጵያውን ታስረዋል። ፖሊሶች ካለምንም ማስጠንቀቂያ ቤታቸውን ሰብረው በመግባት በተለይ በሴቶቻችን ላይ ጉዳት እያደረሱ እንደሚገኝ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በሳዑዲ አረቢያ ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን ለማስወጣት በሚል የተጀመረው ይኸው የአፈሳ ተግባር ከኢትዮጵያውያን ውጭ ሌሎችንም ሃገራት የሚመለከት ቢሆንም በኢትዮጵያኑ ላይ የሚደርሰው ጥቃት ግን ለየት ያለ ነው። ሰርተው ያፈሩትን ንብረት እየተዘረፉ የሚገኙት እነዚሁ ኢትዮጵያውያን እቃቸውን ሸጠው እንዳይጨርሱ በፖሊስ ስለማይጠበቁ ወደ እስር ቤት የሚጓዙት ካለምንም ንብረት ነው።

በአልቃሲም ከተማ በተጀመረው አፈሳ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እየተፈጸሙ ነው ያሉት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ይህ ስደተኞችን የማሳደድ ተግባር በ13ቱም የሳዑዲ ግዛቶች ይቀጥላል ተብሏል። እንደደረሰን መረጃ ከሆነ በአል ቃሲም ከተማ የመኖሪያ ወረቀት ለሌላቸው ወገኖች ቤት ያከራዩ ሰዎች ይቀጣሉ።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>