ከደርግ የ17 አመታት የአገዛዝ ውደቀት በኋላ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች በስፋት ሲንጸባረቁ ከነበሩ ጥያቄዎች መካከል የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄ ዋነኛው ነው::
በዚህ ወቅት ውስጥ ለብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄ በፖለቲካ ኃይሎች የቀረቡት የመፍትሔ ሃሳቦች የተለያዩ ቢሆንም የመፍትሔ ሃሳቦቹ የሚመነጩት ግን በዋናነት ከሁለት ተገዳዳሪ አስተሳሰቦች ነው:: አንደኛው አስተሳሰብ የሚያጠነጥነው የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄው የሚካትተው ከኢትዮጵያ ዘመናዊ የሃገር ግንባታ ጋር ተያይዞ የተፈፀሙ ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነትንና በደሎችን እንዲሁም በያ ትውልድ ውስጥ የተፈፀሙ መጠፋፋትን አካቶ ሁሉን-አካታች መድረክ በማዘጋጀት ያለፈውን በደሎች ዕውቅና በመስጠት በፖለቲካ ሊህቃን መካከል መግባባትን ማስፈንን ነው:: ሁለተኛው አስተሳሰብ የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄን የሚመለከተው ኢትዮጵያን እንደ ሀገር በአዲስ መሰረት ላይ የመገንባት ሂደት አድርጎ ነው:: ይህም ማለት የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄ የሚያቅፈው ሁሉንም አይነት ማለትም ብሔር፣ ሃይማኖት እንዲሁም መደብ ላይ መሰረት ያደረገ ኢ-ፍትሃዊነትና መገለልን ከኢትዮጵያ ዘመናዊ የሃገር ግንባታ ጀምሮ የኢህአዴግን የአገዛዝንም የሚያካትት ነው:: ...የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄና ፈተናዎቹ በኢትዮጵያ….