(ዘ-ሐበሻ) በሳዑዲ አረቢያ ከ35 ሺህ የማያንሱ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ እየተጠባበቁ ባለበት ወቅት የኢትዮጵያ ኢምባሲም ችግር ያለባችሁን እንረዳለን እያለ ስልኮቹን ሲለጣጥፍ ቆይቶ በዛሬው እለት በጅዳ የቆንስላ ጽህፈት ቤቱ ደጃፍ ላይ “ከህዳር 8 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ ቆንስላ ጽ/ቤቱ ላልተወሰነ ጊዜ አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑን እንገልጻለን” የሚል ደብዳቤ ለጥፏል። ዘ-ሐበሻ ይህ ፖስተር እንደደረሳት ወደ ኢምባሲው በመደወል ጉዳዩን ለመጠይቅ ብትሞክርም ስልክ የሚያነሳ የለም። በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያውያን ስቃይ አሁንም እንዳየለ ነው። አሁንም ማብራሪያውን ለማግኘት እንሞክራለን።
↧
በጅዳ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ደጃፍ “ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎት አቁመናል”የሚል ፖስተር ተለጠፈ
↧