(ዘ-ሐበሻ) ባለፈው አርብ በሳዑዲ አረቢያ በወገኖቻቸው ላይ እየደረሰ ያለው ስቃይ ያመማቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ቢገኙም የመንግስት ፌደራል ፖሊሶች በሳዑዲ አረቢያ ላይ ተቃውሞ ሊያሰሙ የወጡትን ኢትዮጵያውያን በቆመጥ በመምታት ሰልፉን በመበተን በርካታ ሰዎችን ማሰራቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያውያን “እየመራን ያለው የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ነው ወይ?” እስኪሉ ድረስ በቅርቡ ከሳዑዲ የተመለሰች ወጣት ሳትቀር ሁለተኛውን ዱላ ከራሷ መንግስት ቀምሳለች። ይህ የመንግስት ለሳዑዲ ጥብቅና መቆም ቀጥሎ በዛሬው እለት መድረክ በሳዑዲ አረቢያ ኢምባሲ ፊት ለፊት የጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ በደብዳቤ መከልከሉን ድርጅቱ ለዘ-ሐበሻ በላከው መረጃ አስታውቋል።
መንግስት በሳዑዲ አረቢያ ኢምባሲ ፊት ለፊት የተጠራውን ሰልፍ የከለከልኩት በቂ ጥበቃ ስለሌለኝ ነው በሚል ነው። ደብዳቤው ይኸው”-
ከሳዑዲ አረቢያ መንግስት እየበደለን ያለው የኢትዮጵያ መንግስት ነው – የሚለውን የነብዩ ሲራክን ትንታኔ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ