ከአዲስ አበባ ፖሊስ ምንጮች አሁን በደረሰኝ መረጃ የአገር ውስጥ ደህንነት ሃላፊ የነበረው አረመኔው ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል በማእከላዊ ወንጀል ምርመራ መገረፉን አስታውቀዋል። የአዜብና መለስ ቀኝ እጅ የነበረው ይህ ጨካኝ የደህንነት ሹም በስልጣን በነበረበት ወቅት እነ ጄኔራል አሳምነውን በመደብደብ፣ አይናቸውን በቦክስ በመምታት ከፍተኛ የጭካኔ ተግባር ይፈፅም እንደነበረ ምንጮች አስታውሰዋል። በ1997-98 ዓ.ም በሺህ የሚቆጠሩ ሰላማዊ ወገኖች እንዲገደሉ፣ እንዲታሰሩና አሰቃቂ ግፍ እንዲፈፀምባቸው ያደረገው ወ/ስላሴ መሆኑን አያይዘው ገልፀዋል። በርካታ ሰዎች ከመግረፍና ከማሰቃየት ባለፈ በጥይት ደብድቦ ይገድል እነደነበረ አመልክተዋል። የቤተመንግስት የጥበቃ ሃላፊ አቶ ዘርኡ መለስ አንገታቸውን በስለት በማረድ እንዲሁም የመንገድ ት/ሚኒስትሩን አቶ አየነው ቢተውልኝን በገመድ አንቆ የገደለው ወ/ስላሴ መሆኑን ከዚህ ቀደም መገለፁ ይታወሳል። ወ/ስላሴ በትላንትናው እና በዛሬው እለት ሁለት ጊዜ መገረፉን ምንጮች አረጋግጠዋል።
↧