Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ መስቀል ከሰማይ ወረደ መባሉ አነጋጋሪ ሆኗል

$
0
0

(....ከሰማይ ወረደ የተባለውን መስቀል ይዘው)

(….ከሰማይ ወረደ የተባለውን መስቀል ይዘው)

(ዘ-ሐበሻ) “ገላን ጉራ ፈለገ ግዮን ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ብርሃን የተሞላ መስቀል ከሰማይ ወረደ” በሚል እየተወራ ያለው ዜና በኢትዮጵያ ዋነኛ መነጋገሪያ መሆኑ ታወቀ።

ከአዲስ አበባ የመጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በገላን ጉራ ፈለገ ግዮን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተከሰተ በተባለ ተአምር መስቀሉ ወረደ የተባለው ሐሙስ ለአርብ አጥቢያ ከለሊቱ 9፡00 ሰዓት አከባቢ ነሐሴ 23 ቀን 2013 ሲሆን ካህናት አባቶች እና ምእመናን የክርስቶስ ሳምራን የበአል ዋዜማ ማህሌት ቆመው እንዳለ መስቀሉ ወርዷል ተብሏል።

ከስፍራው የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ማህሌት ቆመው የነበሩት አባታኦች ከሰማይ የወረደውን መስቀል ድምጽ ድምፅ ሲሰሙ ካህናትና የቤተክርስቲያን አስተዳደሩ ከቤተመቅደስ ወጥተው ሁኔታውን ሲመለከቱት ብርሀን ከሰማይ እንደወረደና አከባቢውን በብርሀን እንደሞላው ተመልክተዋል ተብሏል። መስቀሉ የጌታ ስቅለት ያለበት ነውም ተብሏል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ሕዝቡ ጉዳዩን በጥርጣሬ በማየት እየተነጋገረበት ሲሆን ለማመን የተቸገሩ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ የመስቀሉን መውረድ የሚያምኑ ሰዎችም ቁጥራቸው አናሳ አይደለም።

በቅርብ ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ አንዲት ሴት ድንግል ማርያም ነኝ በሚል ብዙ ሰዎችን አጭበርብራለች ተብላ መታሰሯ ይታወሳል። ከዚያ ቀደምም ባህታዊ ገብረ መስቀል የተባሉ ሰው ራሳቸው ታቦት አስቀብረው ሕዝቡን ‘ራዕይ ታይቶኛልና እዚህ ቦታ ብትቆፍሩ ታቦት ታገኛላችሁ” በሚል በማጭበርበር መጋለጣቸው ይታወሳል።

አንባቢዎች የእናንተ አስተያየት በዚህ ጉዳይ ምን ይመስላል?


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles