ጊብሰን ዩዝ አካዳሚ የሚባለው ትምህርት ቤት የከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትንና የጄኔራሎችን ልጆች በስኮላርሺፕ ስም በነፃ የሚያስተምር መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ ይህ ት/ቤት በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ክፍያ የሚያስከፍል ሲሆን በአመት ወደ400 ሚሊዮን ብር ከወላጆች ያገኛል፡፡ ይህ አልበቃ ብሎት በየአመቱ ከፍተኛ ጭማሪ እያደረገና በተለያዩ መንገዶች ህገ ወጥ ስራዎች ላይ እየተሰማራ በመገኘቱ የማስተማር ፍቃዱ ተሰርዟል፡፡ የት/ቤቱን የማስተማር ፈቃድ መሰረዝ የሚገልፀውን ደብዳቤ እነሆ አቅርበናል፡፡
ይሁን እንጂ ይህ ደብዳቤ በአገሪቱ ውስጥ የተንሰራፋው የመልካም አስተዳደር ችግርን ጥያቄ ምልከት ውስጥ የሚከት ነው፡፡ አንዱ የሰረዘውን ደብዳቤ የሚሰርዝ ሌላ አካል ካለ የምናየው ይሆናል፡፡ መንግስት ራሱ ያወጣውን ህግ ራሱ የማስፈጸም ችግር እንዳለበት የዚህ ትምሀርት ቤት ጉዳይ ትልቅ ማሳያ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም የከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና የጄኔራሎች ልጆች በነፃ እያስተማረ ይህ ደብዳቤ ተግባራዊ ይሆናል ማለት ዘበት ነው፡፡ በዚያ ላይ ይህ የ400 ሚሊዮን ብር ቢዝነስ ጉዳይ ስለሆነ ለሙስና ቅርብ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ደብዳቤ በስፋት በተገለፀው ህገወጥ ተግባር የተነሳ ጊብሰን ዩዝ አካዳሚ በሚቀጥለው አመት ማስተማር ቢከለከልም ማስተማሩን እንደሚቀጥል ከወዲሁ መገመት እንችላለን፡፡
The post የጊብሰን ዩዝ አካዳሚ ጉዳይ | መልካም አስተዳደርን ጥያቄ ምልክት ውስጥ የከተተው ደብዳቤ appeared first on Zehabesha Amharic.