“እኔ በአዋጅ ሳይሆን በትዕዛዝ ነው የምመራው፤ እሰር የሚል ትዕዛ ደርሶኝ አስሬያቸዋለሁ”
- የፖሊስ አዛዥ
(ዘ-ሐበሻ) የፊታችን እሁድ ነሐሴ 19 ቀን 2005 ዓ.ም (ኦገስት 25 ቀን 2013) በአዲስ አበባ በሚገኘው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት/መ.ኢ.አ.ድ/ ዋና ጽ/ቤት 33ቱ ፓርቲዎች ለጠሩት ህዝባዊ ውይይት የመኪና ላይ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ የፓርቲዎቹ አባላት በህገወጥ መንገድ መታሰራቸውን የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት አስታወቀ።
እንደ ዘገባው ከሆነ በቅስቀሳው ላይ ከነበሩት ወገኖች መካከል
1ኛ አቶ ደመላሽ፣
2ኛ. አቶ አብርሃም ፣
3ኛ. አቶ አታላይ በለው፣
4ኛ. አቶ እዮብዘር
5ኛ. አቶ መላኩ መሰለ
የተባሉት አባላት የቅስቀሳ መከናውን ከያዘው ሹፌርና ረዳት ጋር ታስረዋል፡፡
የፓርቲዎቹ አመራሮች አባሎቻቸው ወደታሰሩበት 1ኛ ፖሊስ ጣቢያ አቅንተው እስሩ ህጋዊ አለመሆኑን አዋጅ በመጥቀስ ቢያስረዱም በስፍራው የነበሩት የፖሊስ አዘዥም “እኔ በአዋጅ ሳይሆን በትዕዛዝ ነው የምመራው፤ እሰር የሚል ትዕዛ ደርሶኝ አስሬያቸዋለሁ” የሚል ምላሽ እንደሰጣቸው የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘገቧልል።