የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን ዳይሬክተር የነበሩት አቶ እውነቱ ብላታ ደበላ ከያዙት ኃላፊነት ተነስተው ከፍ ወዳለው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው መሾማቸውን ሰንደቅ ጋዜጣ ከአዲስ አበባ ዘገበ። እንደጋዜጣው ዘገባ አቶ እውነቱ የተሾሙት ቦታ አቶ በከር ሻሌ በአሁኑ ወቅት የገቢዎችና ጉምሩክ ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት የያዙት ቦታ ሲሆን አቶ በከር ከዚህ ኃላፊነታቸው ተነስተው የአዳማ ከንቲባ ሆነው ከተሾሙ በኋላም ከዘጠኝ ወራት በላይ ቦታው ክፍት ሆኖ መቆየቱ ታውቋል።
ጋዜጣው ዘገባውን ቀጥሎ አቶ እውነቱ ብላታ ቀደም ሲል በኦሮሚያ ክልል የፍትህና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው የሰሩ ሲሆን በኋላም በፌዴራል ጉዳዮች ጽ/ቤት በከፍተኛ የኃላፊነት ደረጃ ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ተሹመው ለአንድ ዓመት ሲሰሩ ቆይተዋል ብሏል።
↧
አቶ እውነቱ ብላታ የሥልጣን ዕድገት አገኙ
↧