(ዘ-ሐበሻ) በ እስር ላይ ቆይተው ባለፈው ማርች 30, 2015 የተፈቱት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር ኦቦ በቀለ ገርባ ዛሬ ጠዋት ዋሽንተን ዲሲ መግባታቸውን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አስታወቁ::
አቶ በቀለ ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ ዱልስ ኤርፖርት ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን በቀጣይም በሰሜን አሜሪካ የተለያዩ ከተሞች በመዘዋወር ሕዝባዊ ስብሰባ እንደሚያደርጉ ተገልጿል:: በቅድሚያ ዋሽንግተን ዲሲ በሚደረገው በኦሳ (Oromo Studies Association/Waldaa Qorannoo Oromoo) ኮንፍረንስ ላይ የሚሳተፉት ኦቦ በቀለ በዚሁ ኦገስት 1 እና 2, 2015 በሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ ለ29ኛ ጊዜ በሚደረገው ኮንፍረንስ የክብር እንግዳና ተናጋሪ እንደሆኑ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመልክቷል::
ኦቦ በቀለ በሚኒሶታ ኦገስት 8 ሕዝባዊ ስብሰባ እንደሚያደርጉ ሲጠበቅ – ቦታውን እና ሰዓቱን እንደምናሳውቅ ከወዲሁ እንገልጻለን::