Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

”አላሙዲን ሆይ…??”–ከኤርሚያስ ለገሰ

$
0
0

በዚህ አመት በሀገረ አሜሪካን በሚገኙ ታላላቅ ሚዲያዎች አነጋጋሪ የሆነውን የፒተር ሽዊዘር ” CLINTON CASH” የሚለውን መጵሀፍ እንደነበረ የሚታወቅ ነው። መጵሀፋን ከወዳጆቼ ተውሼ እያነበብኩ ገጵ 134 ስደርስ ከዛ በላይ መቀጠል አልቻልኩም። እንዲህ በማለት ራሴን ጠየኩ፣
” አላሙዲን ሆይ ከኢትዬጲያውያን የነጳነት ጫንቃ መቼ ነው የምትወርደው?፣
” አላሙዲን ሆይ እንደ ሰው ተቆጥረን የመኖር መብታችን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀህ የምትኖረው እስከመቼ ነው?”

እነዚህን ጥያቄዎች ለማንሳት ያስገደደኝ በፒተር መጵሀፍ ከገጵ 128 -134 የሰፈረውን ቁምነገር በማንበቤ ነው። ርግጥ አላሙዲን እና ከስሩ የኮለኮላቸው ኮልኮሌዎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የፈጰሟቸውን ወንጀሎች ጠንቅቄ ስለማውቅ ፒተር በምርመራ አግኝቶ ከጳፈው በላይ መናገር እንደሚቻል አውቃለሁ። ጊዜውና ሰአቱ ሲደርስ። በነገራችን ላይ ከእኔ በላይ ስለ አላሙዲን እና ግብረአበሮቹ ብዙ የሚያውቁ ኢትዬጲያውያን በየቦታው አጋጥመውኛል። አንዳንዶቹም ለሼሁ እንደነገሩት እና ” ጆሮ ዳባ ልበስ!” እንዳለ አጫውተውኛል። እሁድ እለት ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ላሊበላ ሆቴል ያገኘሁት የሆቴሉ ቋሚ ደንበኛ የሼሁ የቅርብ ጓደኛ እንደነበረ ብዙዎች ስለመሰከሩ፣ ጆሮዬን ከፍቼ አዳምጠው ነበር።
Shek AlAMUDI
ባለፋት 24 አመታት ሼህ መሀመድ አላሙዲን በኢትዬጲያውያን የእለት ተእለት ህይወት ውስጥ ተጵእኖ የሚያሳድር ሰው እንደሆነ ማንም አይክደውም። በዚህ ምክንያት የሼሁ ሁኔታ በኢትዬጲያውያን ዘንድ በበርካታ ወለፈንዲዎች የተሞላ ነው። ከኮልኮሌዎቹ አንጳር ሰውየው በተቃርኖ ውስጥ ባለ ቀጭን ገመድ ላይ ተዝናንቶ የቆመ ነው። በዝህች በተወጠረች ገመድ ስር በርካታ ሹል ምስማሮች ተሰክተው ይጠብቁታል። ቀን ሲጥለው እነዛን ሹል ምስማሮች ከማንም ቀድመው እየተስፈነጠሩ ይሰኩበታል። ምስማሮቹ ኮልኮሌዎቹ ናቸው። ከሌላው ኢትዬጲያዊ አንጳር የተቃርኖው ምንጭ ከሰው ሰው ይለያያል። በአንድ በኩል ሰውየው በሀገሪቱ ታይተው የማይታወቁ ኢንቨስትመንቶች አሉት፣ እጁን ፈታ አድርጐ ሊረዱ የሚገባቸው ታዋቂ ግለሰቦችን ይረዳል የሚል ነው። በሌላ በኩል የሀብት ምንጩ የሀገራችን ወርቅ፣ የተሰጡት የትየለሌ መሬቶች፣ በሞተ ዋጋ የገዛቸው መንግስታዊ ተቋማት ናቸው። የሚረዳውም በአካፋ ከወሰደው ውስጥ በቡና ማንኪያ ነው። አረዳዱም እንደ አለቆቹ በከፋፍለህ ግዛው መርሆ በመመራት ነው የሚሉ በርካታ ናቸው። እኔም የምስማማው በመጨረሻው ዘርፍ ካሉት ሰዎች ቢሆንም በዝች አጭር ማስታወሻ ከዚህ በላይ መሻገር አልፈልግም።

ለዛሬው ” አላሙዲን ሆይ… ?” የሚለውን ጥያቄ ከፒተር መጵሀፍ አንጳር ላንሳ። ፒተር በምእራፍ ስምንት ” WARLORD ECONOMICS” ብሎ በጠራው ክፍል ውስጥ በሼህ አላሙዲን፣ በመለስ ዜናዊ ( ነብሱን ይማረው!”) እና በክሊንተን መካከል የነበረውን ግንኙነት በዝርዝር ያብራራል። ሼህ መሀመድ እና ክሊንተን በእንግሊዝ ለንደን ተገናኝተው እንደነበረና እንደተወያዩ ይነግረናል። አፍታም ሳይቆይ እ• ኤ•አ ግንቦት 14 ቀን 2007 በተካሄደ አጭር ድግስ ሼሁ ለክሊንተን ፋውንዴሽን ሀያ ሚሊዬን ዶላር ለመስጠት ቃል ይገባል። የዛኑ እለት ሁለት ሚሊዬን ዶላር በቼክ ይከፍላል።

ፒተር ባደረገው ጥናት አላሙዲን የአማላይ ( lobbing firm) እንዳለው ያረጋግጣል። በዚህ አማላይ ተቋም ውስጥ በአባልነት ሶስት ትላልቅ ሰዎች በተከፋይ አማካሪነት እንደሚሰሩም ይናገራል። እንዲህ በማለት፣

“… His lobbying firm in washington included Senators George Mitchell, Lioyd Bentsen( who had been treasury secretary when Bill was president), and Bob Dole as paid advisers.”

ፒተር ከዚህ በኃላ የሚያመጣው መረጃ ለኢትዬጲያውያን በጣም አስደንጋጭ ነው። አላሙዲን ይህንን ቃል የገባው ኮንግረስ ማን ዶናልድ ፔይን የኢትዬጲያ ባለስልጣናትን የሚቀጣው H•R• 2003 ተብሎ የሚጠራው ህግ ባስተዋወቁ ወቅት እንደሆነ ይገልጳል። የህጉ ተኮላሽቶ መቅረት በዚህ ምክንያት እንደሆነ ያሳውቃል። በወቅቱ እነ አቶ በረከት ደረታቸውን ነፍተው ህጉ አይፀድቅም ያሉበት ዝርዝር ምክንያት በጣም ግልጵ ሆኖልኛል። ፒተር የጳፈው ከፊሉ እንደሚከተለው ይነበባል፣

” In may 2007, when he made his commitement to the clinton Foundation, the Ethiopian Democracy and Accountablity Act ( H•R• 2003) had just been introduced by congressman Donald Payen.”

ፒተር በዚህ ክፍል ሌላው የገለፀው በአላሙዲን እና በአቶ መለስ መካከል ስላለው ግንኙነት ነበር። አቶ መለስ በሞተ ሰአት አላሙዲን ቀኝ እጄ ተቆረጠ ብሎ እንደተናገረ አስታውሷል ( When Zenawi died with in 2012 of a mysterious stomach ailment, Amoudi would say, ” I lost my right hand”).

እንግዲህ በአጭሩ አላሙዲን የኢትዬጲያ ሰብአዊ መብት ጥሰትን የሚያበረታታው በዚህ መልኩ ነው። በኢትዬጲያ መንግስት ስም ገንዘብ እየለገሰ፣ ሴናተሮችን በአማላይነት እየቀጠረ እና በወሳኝ ወቅቶች ተጵእኖ እየፈጠረ። ያውም በራሳችን ገንዘብ!! … በነገራችን ላይ በህውሀት መራሹ መንግስት ላይ እንደዛ ውርጅብኝ እየወረደ የኦባማ ወደ ኢትዬጲያ መጓዝ ከላይ ከተጠቀሰው የሼሁ ተልእኮ አንጳር አይተነው ይሆን?…ታሪክ ያወጣዋል!… እስከዛው ግን ለራሴ ” ያልጠረጠረ ተመነጠረ!” የሚለውን የሀገሬ ብሂል ብል ምን ይለኛል?


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>