Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ርዕዮት ዓለሙ ምስጋና አቀረበች

$
0
0

በእስር ቆይታዬ ወቅት ከጎኔ ለነበራችሁ ሁሉ
ርዕዮት አለሙ

የፕሬስ ነፃነትን በማፈንና የሰብአዊ መብትን በመርገጥ የሚታወቀው የኢህአዴግ መንግስት የፈፀመብኝን እስር በመቃወምና በማውገዝእንዲሁም ያለቅድመ ሁኔታ እፈታ ዘንድ በመጠየቅ ከጎኔ ለነበራችሁ በሙሉ ምስጋናዬን የማቀርበው በታላቅ ትህትናና አድናቆት ነው፡፡

ርዕዮት ዓለሙ ከእህቷ እስከዳር ዓለሙ ጋር ከ እስር ከተፈታች በኋላ

ርዕዮት ዓለሙ ከእህቷ እስከዳር ዓለሙ ጋር ከ እስር ከተፈታች በኋላ

በነዚያ የጨለማ ቀናት አብሮነታችሁ ያልተለየኝ አለምአቀፍና ሀገር አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡
ዩኔስኮ፣ አለምአቀፍ የሴቶች ሚዲያ ፋውንዴሽን፣ ሚዲያ ሌጋል ዲፈንስ ኢንሼቲቭ፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሂዩማን ራይትስዎች፣ ሲፒጄ፣ ፔን ኢንተርናሽናል፣ ዶሀ ፍሪደም ሴንተር፣ አርቲክል 19ንና ሌሎች ያልጠቀስኳችሁ በርካታ አለምአቀፍ ድርጅቶች ለጉዳዬ የሰጣችሁት ትኩረት በኢትዮጵያ ያለውን አምባገነን ስርዓት በማጋለጥ በኩል ትልቁን ድርሻ ተጫውቷልና ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርብላችኋለሁ፡፡

መፈታቴን እንደራሳቸው ጉዳይ ቆጥረው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እንደ ማርቲን ሽቢዬ፣ፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም፣ አና ጎሜዝ፣ ናኒ ጃንሰን፣ ክርስቲያን አማንፑርና ሌሎች ዘርዝሬ መጨረስ የማልችላቸው በርካታ ግለሰቦች ለጉዳዩ የነበራቸውን ጠንካራ መሰጠት አብዝቼ አደንቃለሁ፡፡

ምንም እንኳን በአስከፋ ሁኔታ ተገልዬ የቆየሁባቸውና ጤናዬ ተቃውሶ የነበረባቸው መጥፎ ጊዜያትን ያሳለፍኩ ቢሆንም ከእስር የወጣሁት ግን ሁኔታዎቹ ሞራሌን ሳይሰብሩትና ይልቁንም ለዲሞክራሲ በተለይ ደግሞ ለፕሬስ ነፃነት መከበር የምችለውን ሁሉ ለማድረግ የበለጠ ቁርጠኝነት ኖሮኝ ነው፡፡

በመሆኑም ለዲሞክራሲ ስለታገሉና ሀሳባቸውን ስለገለፁ ብቻ በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ካለምንም ጥፋታቸው ታስረው የሚሰቃዩ በጣም ብዙ አርበኞችና ጓዶች ከሀሳቤ አይለዩም ፡፡ ኢፍትሀዊነትን አምርራችሁ የምትጠሉ ኢትዮጵያዊያንም ሆናችሁ የሌላ ሀገራት ዜጎች ለነዚህ ሰዎች መፈታት ያላሳለሰ ጥረት ታደርጉ ዘንድ እጠይቃለሁ፡፡
በድጋሚ አመሰግናለሁ
ርዕዮት አለሙ

To all those who stood by me when I was in prison.
Reeyot Alemu

It is with great humility and appreciation that I convey my gratitude to all who protested and condemned my incarceration by the EPRDF Government which is known worldwide for trampling on freedom of the press and human rights, and demanded my unconditional release.

I would like to thank those international and local Medias for being with me in my darkest days.
Special thanks goes to UNSECO , IWMF, Media Legal Defense Initiative, Amnesty International, Human Rights Watch, CPJ, Pen International , Doha freedom center, Article 19 and countless organization whose championship of my incarceration helped expose the cross dictatorship prevailing in Ethiopia.

I am also very appreciative of the steadfast commitment shown by those individuals who made my release their case like Martin shibbye, Prof. Alemayehu G.mariam, Ana Gomez, Nani Jansen, Christian Amanpour and so many others.
Though the harsh conditions under which I was kept some times incommunicado, precipitated in the deterioration of my health, I came out morally unscathed and even more resolved to do everything within my power in the cause of democracy, particularly freedom of the press in my country.

My thoughts go out to my so many compatriots and compatriots and comrades who are suffering in Ethiopian jails for no reason other than expressing their views and advocating democracy. I urge all Ethiopians and all people who abhor injustice to work tirelessly for their release.
I thank you all again
Reeyot Alemu


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>