$ 0 0 ሰሞኑን ወደ አዲስ አበባ የሚመጡት ያሜሪካው ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ተቃዋሚዎችን የማነጋገር ፕሮግራም እንደሌላቸው ግልጽ እየሆነ መጥቷል፤ ሲሉ ጥያቄ ያቀረቡ ፓርቲዎች መሪዎች ተናገሩ። ፕሬዘዳንቱ ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ አይቀር እኛንም ያነጋግሩን በሚል ያቀረቡት ጥያቄም ይፋ ምላሽ እንዳላገኘ እነዚሁ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች አስረድተዋል።