Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ተግባር አሸናፊ ነው! (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 14.07.2015 (ሲዊዘርላንድ ዙሪክ)

ግን ዓይኔ የኔ ነበርክን? መንፈሴስ? በእርግጥም ከእኔ ጋር ነበራችሁን? „ የአንቺ – ነበርን“ – መልሱ።

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

አይደለም ዛሬ ቀድሞም ቢሆን ትግራይ – የበላይ ነው። ወያኔ ሃርነት ትግራይን ለድል ያበቃው ጥንካሬው – አልነበረም። ጦርነትን ለማሸነፍ ሚስጢር በመዳፍ መሆንን – ይጠይቃል። አቅም ያለው፤ ቀልፉን የያዘ ሥጋና ደም ነበረው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ነበር ማለት – ይቻላል። ተገለን ተጨቁነን ነበር የሚለውን ቅጥፈት አመድ የሚያአደርገውም ይህ ቆሞ የሚሄድ – የታሪክ ሃቅ ነው። እነዛ የዘር ልክፍተኞች እንደ የተሰጣቸውን ሃላፊነት፤ የገቡትን ቃል ተላልፈው ታማኝነታቸውን አፈር አስግጠው ሚስጥርን እንደ ቄጠማ ባይነሰንሱት ኖሮ፤ በሁለት ቢላዋ ባይበሉ ኖሮ .. ኖሮ ኖሮ ወያኔና ኑሮው በጫካው የዕድሜ ልክ በሆነ ነበር። ክህደቱ ሀገርን እንዲህ አፈረሰ – ትውልድንም ቀጣ። ያን የመሰለ በ200 ዓመት ሊገነባ የማይችል ተቋማት፤ የመንፈስ ሃብታት ሁሉ – ፈራረሰ። በውስጥ አርበኛ – ባንዶች። ዛሬም የነፃነት ትግሉን ካባ ደርበው ውስጣችን እያረዱ የእኛ የሚመስሉ ግን የእኛ ያልሆኑ አሉ። ስለዚህ ቅኖች በቅንነት የሚያስተላልፉትን መልዕክት እንዳሻቸው በማደረግ፤ በመደለዝ ምኞታችን ህልማችን እንዲጎዳ ጥፈረ መጥምጦች አሉና ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል፤ ጋርድ ተቁሞ ተውሎ የሚታደረውም – ለዚኽው ነው። የሳይበሩ ጦርነት ቅራኔው እዬከረረ በመጣ ቁጥር እጅግ የከፋ በመሆኑ ብዕሮች ትጥቃቸውን ጠበቅ አድርገው ሊጠብቁት ይገባል ነው – ዕድምታው። ህልም እንደፈቺው እንዳይሆንም፤ ብልህነት መልካም ስለሆነ ነበር የጻፍኩት። እንጂ ትራሴን ከፍ አድርጌ መተኛት – ይቻለኛል።

ጤና ይስጥልኝ የተከበሩ አቶ ይገረም አለሙ እንዴት ሰነበቱልኝ – በአያሌው። እጅግ አድርጌ – አመሰግነወታለሁ። ከሁሉም በላይ እንዲህ ቅርብ ያደረጉኝ መሆኑን በአሁኑ ጹሑፉዎት – ተገነዘብኩ። እንኳንም – ፃፍኩት። በውስጠዎት ሥርጉተ ያላትን የእህትነት ልዩ ቦታ መረዳት – ቻለች። እናም ሐሤትን አፈሰች – ቸረፈሰች። ከልቤ ነው ተረብ – እንዳይመስለዎት። እሺ!

ውድ ወንድሜ – ዛሬ የኔው ይባሉ፤ ወያኔ መጥላቱ ብቻ በቂ – አይደለም። ይህን ተግባር ላይ ስላሉ የሚውቁት – ይመስለኛል። ወያኔን ሃርነት ትግራይን የጠላንበትን መሠረታዊ ምክንያት ሥሙንም  ግብሩን ተንተርሶ ያወጣው ማንፌስቶውን ነው። ማንፌስቶ የተመሰረተበት ዓላማና ተልዕኮ – አለው። ተልዕኮውና ዓላማውን በመፈጸመና በማስፈጸም እረገድ ግዳጁን የተወጣ የጎጥ ድርጀት ነው። የቀረውም ቦታም ካለ እስከ ተኛን ድረስ – ይቀጥላል። ስለዚህ ዘንበል ወይንም ዘመም ብለው የሚቀርቡ ሃሳቦች ወደ ዬትኛው መንገድ ወይንም አቅጣጫ ወይንም ተፋሰስ እንደሚነጉዱ ወይንም ለዬትኛው ፍላጎት አቅም ሊሆኑ እንደሚችሉ ቆም ብለን በማስተዋል ሊቃኝ ይገባዋል ነበር የጹሑፌ – ዕድምታ። ያነበብኩት ከልብ ነበር ውስጤን ሰጥቼ –  ቢያቅለሸልሸኝም – ስለማከብረዎት። ፁሑፎዎት ዘሃበሻ ብቻም አይደለም ፖስት ያደረገው፤ ሌላ ቦታ ላይ – ተገናኝተናል። በጎሪጥ ሳላዬው ተዚኽም አለህ ለካ? ብዬ ከአቦል አስከ በራካው ቤት ያፈራውን የቡና ቁርሳችን እዬከሰከን – በቤተ – ኢትዮጵያ – ተንበሽብሸንበታል።

ወንድሜ – እኔ አይጋ ፎረም ገብቼ – አላውቅም። ምን እንደሚመስል መልኩንም ገፁንም – አላውቀውም። ወይንም በስልትና በጥበብ፣ በሚያምር የድምጽ ቅላጼ የመርዝ ሰለባ ለመሆን – አልፈቅድም። „ሲወዱም ሲጠሉም እስከ ንፍጥ ልጋጉ“ ይላሉ ጎንደሬዎች። ማለት የሸገር ራዲዮ ታዳሚ – አይደለሁም። ከሰማዬ ሰማይት በላይ ቅዝፈት በሚያሰኘው ጹዑም ድምጽ ዲዲት እሰኪበቃው ድረስ – ይረጫል፤ ዬኢትዮጵያዊነት ተቋማት ሁሉ – ያለርህራሄ ይደረመሳል – ዝግጅቱ። የተረሱ የቂም ኩትኩቶችን እዬቀራረፈ – ግመጡት ይላል – መሰናዶው፤ በፍቅር እብድ የሚሉ የተሰለቡ አሉ ማር ወላላ በሃሞት ጠቅልሎ  – ስለሚያዘንብላቸው፤ እኔ እህተዎ የተመሠረተበትን መሰረታዊ ፍላጎት ጠረኑን ከሩቁ – አውቀዋለሁ። „አማራጭ ራድዮ¡“ እንዴት ተቀለደ?!  ህም – ምን ልልዎት ነበር ለማለተርፍበት ጊዜ – አልከስርም። እምታደምባቸው ድህረ ገፆችም ቢሆኑ እጅግ ውስን – ናቸው። እኔን የሚመስሉኝን  – ብቻ። ውስጤን የሚፈውሱትን – ብቻ። ወይንም ዕንባን ሳይረገጡ ግን የተለዬ ሃሳብን የሚያስተናግዱትን – ብቻ፤ ወይንም ማጣቀሻ – ሲያስፈልገኝ፤ ወይንም ትንተናቸው ት/ቤቴ የሆኑትን ብቻ። ነገረ ጥፋትን ወያኔዊ ተፋሰሱንማ –  አድገን አረጀንበት እኮ፤ ጥዋት ማታ የሚፈሰው ዕንባ ይበቃል …. ዜናው እሱ ነው መሽቶ እስኪ ሲነጋ …. እሱም ይሰንብትልንም እዬተባለ ነው¡ – እያደመጥን፤ አይገርመዎትም መከራ ይቀጥል … ህም!

ሌላው ሃሳበዎትን በሃሳብ ሙግት እንዳልተመቸኝ የጻፍኩትም – ስላከበርኩዎት ነው። እርስዎ ሳላነብ እንደጻፍኩት አድርገው ነው – የገለጹት። አልከፋኝም። ሁሉንም ለማስመቸት ነው አደባባይ – የወጣሁት። ከዚህ በበለጠም ፈጨትም – ደቆስም ቢያደርጉኝም በመከራ የሰለጠነ ሰብዕና ስላለኝ አቀባበል ይደረግለታል –  ደስ ብሎኝ። ተደብቄ – አላውቅም።

አማርኛ ቋንቋ የፍልፍስና – ቋንቋ ነው። አማርኛ ቋንቋ የምርምር – ቋንቋ ነው። አንዱ ቃል፣ አንዱ ስንኝ፣ አንዱ ፊደል በዬሥርአቱ ሚስጢርን – ይቃኛል። ድምጽ ምቱ እራሱ ነጮች የቀረብን – ይሉታል። ቲያትርም – እጫወታለሁ። የቲያትር ቲሙ እኔን ከሚፈልግበት ዋንኛው አማርኛ ትረካዎቼንና ግጥሞቼን እጅግ ስለሚያፈቅሩት – ነው። ሙዚቃዊ ቃናው በነፋሻማ ምት እያዝናና፣ እዬጠገነ በልስሉስ መዳፉ – ይፈውሳል – ድህነትም ነው። አማርኛ ቋንቋ የአፍ መፍቻ ቋንቋዬ ነው። የጻፉት አሳምሮ – ገብቶኛል። እርግጥ – እርእሱ አልሰረሰረኝም። ወይንም እኔን ለመዝረፍ አቅም – አልነበረውም።

የማከብረዎት ጸሐፊ አቶ ይገርም እኔ የፖለቲካ መሪ – አይደለሁም። ወይም የፓርቲ አባል – አይደለሁም። ስለዚህ ውስጤን ግልጥልጥ አድርጌ ለማሳይበት የታሰርኩበት ፕሮግራምና የፓርቲ ደንብ – ገመድ የለም። ገፊ ኃይል የለኝም – ከዕንባ በስተቀር። ፖለቲካ መሪዎች ሆዳቸው የሚውቀውን ሃቅ ለበስ አድርገው በቅኔ – ይቃኙታል። ፖለቲካ ሥነ ጥበብ ነውና። ሥርጉቴ ግን ክንብንቡን ገለጥ አድርጋ ተክለ ቁመናውን ከውስጧ ጋር በሃዲድ – ታገናኘዋለች። የሆነ ሆኖ ህዝብ መስታውት ነው ዳኝነቱን ለብዙኃኑ ህሊና – አስጠዋለሁ። አንድ መስመርም ላይ ካለንም ደስታውን አልችለውም – ችርስ! በዚህ ባንመቻች በሌላው ይደምር ነው አይደል? በነገራችን ላይ የጹሑፎዎት ሊንክ በሙሉ – እይዛቸዋለሁ ዝምድና ስላላቸው – ከስሜቴ ጋር። ሳይመቸኝ ደግሞ እንዲህ ቅርቤ ስለሆኑ ወጥቼ አልተመቹኝም – እላለሁ። ሸጋ ነው አይደል?! እንደወደዱት መግቢያወት ፏ ብሎ አቀባበል – አድርጎልኛል። ለማንኛውም የወያኔ ሃርነት ትግራይን ማጣጣል ከፈለጉ ሥርዓተና ህግን በተሟላ ሁኔታ ያለው እጬጌው – ቅኔኛው አማርኛ ቋንቋ ህገ = ነጥብ አለው ስላቅ የሚባል ¡ እርስዎም ያውቁታል በዚህ ቢጠቀሙ ኖሮ በተወሰነ ደረጃ መግባባት እንችል – ነበር። ሌላው ስድስት ገፅ እንደሆነም – ነገርውኛል። የተሸከመው ዬዘሃበሻ ብራና ነው። ዘሃበሻ ስብሰባውን የሚመራበት ህገ ደንብ ሲኖረው በፍትሃብሄሩ ህግና ሥርዓት ክሱ – ይቀጣኛል ወይንም በወንጀለኛ መቅጫውና ሥርዓት። የተዳፈነ ወይንም የተከረቸመ ሙግት የለም። ያ ሙግት አይደለም። ተጠዬቅ ለማለት አቃቢ ህጉን፣ ዳኛውን፣ ጠበቃውን፣ ችሎቱን ሊይ የታደመውን ግራቀኙን መርታት መሠረት ያደረገውን መነሻውን ሳያስታምሙ ወይንም ሳያቆላምጡ መፋለም የተገባ ነበር።ከአያያዝ ይቀዳል ከአነጋገር ይፈረዳል“ እንዲሉ።  አማርኛ ቋንቋ እንደ ወድአራባ – ወዳከር ወይንም ደበር እንጀራ ሊጥ ሊሸበልል – አይችልምቦንዳም ወይንም ጣቃም – አይደለም። እራሱን መግለጽ እንዲችል ሆኖ የተፈጠረ ፀዲቅ ነው። እንደ ተፈለገ በክትና በዘወትር ቃናዎች ማዘናጠፍ – ይቻላል። ስለዚህ ሙግቴ ብትን ብሎ መብራራት – ስለነበረበት በፈቀድኩት መልክ – ተከውኗል። አንድ ተናጋሪ ለንግግር ከመሳናዳቱ በፊት ንግግሩን ሊያግዘው ፤ ለንግግሩ አጥንትና ሥጋ ሆኖ እንዲያቆመው መረጃዎችን በእውነት ላይ ተንተርሶ በአግባቡ እንደ ዕርዕሱ ፍላጎትና ዝንባሌ አቀናብሮ በዘርፍ ዘርፎ አደራጅቶ ማቅረብ – አለበት። በሚገባ ተሰናድቶ። ጸሐፊም እንደ ተናጋሪ ማለት ነው። ልዩነትም አንድነትም እንዳላቸው ለማጠዬቅ ነው „እንደን“ የተጠቀምኩት።

ሌላው አጫጭር ጹሑፎች ለራዲዮ፤ ለዜና፣ ለማስታወቂያ፤ ለባራሪ ጹሑፍና ለርዕሰ አንቀጽ የሚያገልግሉ ናቸው። ይህን በሚመለከት ከ5 ዓመት በፊት ድህረ ገጼ ላይ ያልሰረዝነው አለ። እንዲያውም የዛን ጊዜው እና የዛሬውን አቋሜንም ያሳዬወታል። በድምጽ ነው የተሠራ …. ለናሙና እንጂ ከጹሑፉ ጎል ጋር አደራጅቶ መምራቱም ቢሆን – ተኑሮበታል።

http://www.tsegaye.ethio.info/kana.html (www.tsegaye.ethio.info)

  • እስከ መቼ?
  • ክብር ከሚሸጥ …
  • ምን ምን ይሸትሃል?
  • ሞትና ሞት ሲፋጠጡ …
  • የራህቡ ነጋሪት ከአምስት ደቂቃ በላይ አልሄዱም ከሙዚቃ ጋር —-

ወንድሜ ሆይ! እርቅና ሰላም የሚወርደው በጥት ፍልስፍና – አይደለም፤ ነገን ለማሳደር ሃቅ ዓይነ እርግብ ተዘጋጅቶለትም – የማይሆን ነው። ቀጥ ባለ ግልጽነትና – ቀጥተኝነት እንጂ። ምንም እንኳን እርስዎን ባይመለከትም ጦር የተመዘዘበት የጋራ ሃብታችን አማርኛ ቋንቋ ከመሰረቱ ጠፍቶ በትግረኛ ቋንቋ እንዲተካ ተግቶ በታታሪነት እዬማሰነ ያለው የትግራይ ወያኔ ሃርነት ትግራይ እንዴት ድቅቅ እንዳለ አንድ ጨዋታ – ላወጋዎት – ፈልግኩኝ። ያው ቋንቋውም የጥቃቱ ሰለባ – ስለሆነ። ዝምድናችንም – እንዲጠብቅልን በማሰብ፤ ቀኑን አላስታውስውም ሚዚያ ላይ በያዝነው ዓመት „አርተ“ የሚባል የኦስትሪያ የጀርመንና የሲዊዝ የጋራ የቴቪዥን ፕሮግራም አለ። „የትምህርት ሂደትና የትውልዱ እንክብካቤ“ የሚል በታላቋ ብርታንያ እና ኢትዮጵያ ያሉ ሁለት የ13 ዓመት ታዳጊዎችን በንጽጽር አቅርቦ ነበር። በዛ ፕሮግራም አፋር ነበር – የተመረጠው። የ13 ዓመት ታዳጊ ወጣቱ ሃመድ ት/ቤቱ ለመድረስ የሦስት ሰዓት የእግር ጉዞ – ያደርጋል። ደርሶ መልስ ስድስት ሰዓት፤ ቃጠሎ ነው ቋያ ነው። መንገዱ አሽዋ ነው። ውሃ ጥሙ ይህ ነው አይባልም ለዛ ለጋ – ቀንበጥ። ወደ ቤቱ ሲመለስ መንገድ ላይ ካለው ምንጭ መቅጃ ሳያስፈልገው አንገቱን ከጉድጓዱ ውስጥ እንዳለ አስገብቶ ተጎንብሶ – ይጠጣል። አይጠቅመውም – ተቃጥሏላ! ሃመድ ጎበዝ የሦስተኛ ክፍል ተማሪ ነው። በሂሳብ አጅግ ጎበዝ ነው። ጋዜጠኛው „የትኛውን ትምህርት ትወዳለህ ብሎ ሲጠይቀው“ „አማርኛ ቋንቋን“ አለው። „ለምን?“ ሲለው „ስለምወደውና ከወገኖቼ ጋር መግባባት እንድችል“ አለው። በቃ የ40 ዓመት የተጋዳላይ ተልዕኮ አሽዋ ውስጥ ሲቀበር ቁጭ ብዬ – ተመለከትኩት። ተነስቼም ሻማ – አበራሁኝ። እንዲህ ነው ፈጣሪ ካሳ – የሚያዘጋጀው፤  ስለዚህ አማርኛ ለእኔ – ፀሐዬ ነው። በስስት ነው – እምወደው። አይቼም – አልጠግበውም። ማለት የፃፉት በመደዴ አልተሄደበትም – ገብቶኛል ለማለት ነው። ስለሆነም ለጻፍኩት መልስ ይቅርታ – አልጠይቅበትም። ትውልዱ አበጥሮና አንተርትሮ እንዲያውቅ በምፈልገው መልክ ተዛማጅ በደሎችን አክዬ – ኮልሜዋለሁ። ግቡን እንደሚመታም ተስፋዬ ዝልቅ ነው። „በቃኝን – እንዲያነጥር“ ሆኖ ተላከ። እርግጥ ነው ዕራእሱ ብቻውን ወንዳታ የሚሉለት  – ይኖራሉ። የእርስዎ ትንተና የሚመቻቸውም – ይኖራሉ። ክር ላይ የተንጠለጠሉ ዕሳቤዎች ጥገታቸው ስለሆነ። ኤንም ቢንም ሲንም ዲንም እንዳይከፋው መንደር ፍለጋ ሲማስኑ ውለው ለሚያድሩት ሊመች ይችል – ይሆናል። ለእኔ ግን ከእርእሱ ጀምሮ  – አልተመቸኝም ነበር። የአንድ ጹሑፍ እርእስ አኮ ጎል – ነው። ውስጥ ሳይገባ እርእሱ ራሱ በቂ  – ነበር።

ይህ ያነሱት ነጥብ በ90ዎቹ አጋማሽ እንደ ኢሮፓ አቆጣጠር አሽኮኮ የተበላለት ሃሳብ – ነበር። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ከራሱ በበቀሉ ይጠፋል የሚል ዕድምታ የነበራቸው ወንድሞቼና እህቶቼ ብዙ – ደክመውበታል። እነዛ አድራጊ ፈጣሪ ሆነው የተከበከቡት ወገኖቻችን ግን ለቀለም ትምህርት ቅድሚያ በመስጠት ያን ተስፋ ጣል ጣል አድርገው እንጀራቸው ላይ በማተኮር ዛሬ እናቴ ቢጠሯቸውም – አይሰሙም። በቀለሙ ከመጨረሻው ደረጃ – ደርሰዋል። ያን ጊዜም ቢሆን „ትግራይ የሞተለትን ያህል አልተጠቀመም“ ነበር – ሙግታቸው፤ ወይ መዳህኒተአለም አባቴ እል ነበር ያን ጊዜ? ይገረም አሉ ሥመዎትን ይገረም ነው ነገርዬው፤ ዛሬም ቢሆን ወያኔ ሃርነት ትግራይ ከሥሩ ይነቀል ቢባሉ የሚስማሙ – አይመስለኝም። ክርና መርፌ የሚያደርጋቸው ማጣበቂያ መስመር አለና። የተከደነች ኪዳን አለች። ስለዚህ በዚህ ሃሳብ ዙሪያ ተደክሞበታል እነ አጅሬ ግን ወይ – ንቅንቅ!  እርግጥ ለዬት አድርገን ልናያቸው የሚገቡ ምርጥ ወገኖቼ እንዳሉ – አውቃለሁ። ዘውድ – የተከበሩ አቶ ገ/መድህን አርያ አይነት፤ በፐርሰንት ሲታይ ግን እጅግ ዝቅተኛ – ነው ዳታው።

ሌላው የተጎዳው አይደለም ቀልብ – የሚሰጠው። የአያያዝ ጥበቡም ቢሆን ተጠቃሚው ሲቆላመጥ ተዘውትሮ – ይታያል። ኑልን ተብሎ ሲለመን። ለእኔ ይህ የተንጋለለ – ነው። የተጎዳው ደግሞ እኩልነት ቀርቶበት ለሥነ – ልቦናው ራፊ ሲደረብለት – አይታይም። ብልጫው ቀርቶበት ማለቴ ነው። ማስታመሙ ይበቃ ነው – ጹሑፌ ያለው። ጊዜ ከመብላት አቅምን እንደ ዘር ከመበትን በስተቀር ትርፉ – ምንም ነው። አልጨመርነም። በ24 ዓመት ስንት አሉን?! ስንቶቹ ናቸው የእኛ – የሆኑት። እንዲያውም ከእኛ የተዘረፍነው የሚያል ይመስለኛል። አሁን እራሱ  ዬአርበኛውን እንቅስቃሴ በነቂስ እንደ ጦር ይፈሩታል ብዬ አስባለሁ። በነቂስ እንደ ጦር ይፈሩታል ብዬ አስባለሁ። ለዚህም ነው „ኤርትራ“  እነማን? ከእነሱ በላይ ላሳር – ያልንላቸው። ለዚህም ነው „ኤርትራ“ አጀንዳ የሆነችው። እናም ሁል ጊዜ ፍላጎታችን ቁልቅል ….

እንዲሁም – በፖለቲካ አስተሳሰብ ወተት ያደገውን እና ህሊናው ሊለማ የሚገባው ዕንቡጥ መንፈስ እኩል አይተረጉሙትምት – ጹሑፉዎትን። ለዚህ ነው በፈቃደኝነት በዘበኝነት የነፃነት ትግሉን እያገለገልኩ – ያለሁት። በትርጉም የሚቃናውን – በትርጉም፤ በሥርዓት መታረቅ ያለበትንም – በህግና በጭብጥ – እምፋለመው፤ የእኔ መርኽ ተከስክሰው ወይንም ተልከስክሰው ሊቀሩ የማይገባቸው የሃቅ ወርቆች በአታቸው መንበራቸው ላይ መሆን ይገባቸዋል ባይ – ነኝ። በመርህ ደራጃ በችግራችን አመንጪ ላይ መስማማት ካልተቻለ መፍትሄ አምንጭነቱም የጫጫ ነው የሚሆነው። ፍላጎታችን – ንፋስ በነፈሰ ቁጥር ሲፍረከረክ እንቦጭ ብሎ ሲወድቅ የሚታዬውም ለዚህ ነው።

የትም ቦታ ተሰክስከው ቀን አብረው ይተክላሉ፤ ሌት ሲነቅሉ – ያድራሉ። አቅም የማያድግበትም፤ አቅም የሚሳደድበትም ምክንያት ይሄው ነው። ቆዳ ለእኛ፤ ሥጋ – ለሥጋ። ይህን – አይተናል። ትናንት ኢትዮ ኤርትራዊውን የአጥፊው ማንፌስቱ መሥራች አዛውነቱን አቶ ሰዬ አብርሃምን ካልተቀበላችሁ፣ ዘውድ ካላደፋችሁ ይምራን ይግዛን ይንዳን ብለው ተራማጅነትን – አወጁ። ወይንም እስከ መገንጠል ብለው፤ አሻም ያልነውን ደግሞ በአጥር ጣሾች በተራማጅ ሃሳብ ሥር ይሾጎጡና እዬተገላበጡ እያደኑ አቅምን እንዴት እንዳወደሙት – ታዝበናል። ይገርመወታል ለጎሰኝነት ጥብቅና ቆመው አውራ የነበሩት ዛሬ ደግሞ በአንድ አፍ ሁለት ምላስ ሆነው – እያዬን ነው። ጃንጥላውን ሸንቁረውም ሸንጉረውም – ፈረሰ። ያ ጃንጥላ ግርዶሽ – ነበር። እንዲህ ዓይነት ሃሳቦች ድሎታቸው ነው።  አብዝተው ያደባሉ አቅም ብቅ ሲል ከተቀበሩበት ይወጡና ጦርነት – ያውጃሉ። ግን ምንግዜም አዝማቹ – ተግባር ነው። ተግባር – ያሸንፋል። አሸናፊው ተግባር ያስቀደመው ሃሳብ ደግሞ የብዙኃን ነው። አሁን አውላላ ሜዳ ላይ ያሉ – ይመስሉኛል። ትግሉ ዓላማን ማሳካት ሆኖ ሳለ ህዝበ ጠቀም በሆነ ፍላጎት ላይ ስንጥር ማባዛት። በቃ! ለነገሩ በሚመጥን ተግባር የሚመጥን ፍቅር ይዛቅበታል። በስተቀረ አይደለም መጠለያ – መቆናጠጫም አይኖርም። ስለዚህ ቀዳዳ የሚከፍቱ ነገሮች ሁሉ ጥንቃቄ ሊሰጣቸው ይገባል። አብሶ እርእስ በሚገባ በተደሞ ሊታይ ይገባዋል።

አዩ ወንድምአለም — ይህን የማነሳለዎት በምክንያት ነው። ተጠቃሚው በሥነ ልቦናው ላይ የደረሰበት ጉዳት – የለውም። ሥነ ልቦናው የበላይ ነው። በግራ በቀኝ ነው የሚደገፈው። የተጎዳው ግን ሥነ ልቦናው በግፍ – ተደርምሷል። መንፈሱ በልዟል – ወይቧል። ማዲያታማ ሆኗል። በተቀጠቀጠ ሥነ ልቦና አቅም መገንባት ፈፅሞ –  አይቻልም። ከምንግዜውም በላይ አቅምን ለማምጣት የተጎዳውን ሥነ ልቦና በጥሩ አቀራረብና አያዬአዝ የኃይል ምንጭ ማደረግን – አሁን ይጠይቃል። እሱዎ ያሉት ሃሳብ ቀደም ብዬ እንደገለጽኩለዎት በ90ዎቹ አጋማሽ ብዙ – ተደክሞበታል፤ ግን – አልሠራም። እንዲህ በቀላሉ ለቅለቅ ተደርጎ ማጥራት – አይቻልም። የተጎዳና ያልተጎዳን፤ ተጠቃሚና – ተገፊን በእኩል አያያዝ በአንድ ማስኬድ በፍፁም – አይቻልም። እውነቱ ይሄ ነው። ከንፍሮ ጥሬ ካወጣቸው እጅግ እጅግ ጥቂቶች በስተቀር ጥቅሙን የሚጻረር ተጠቃሚ – የለም። ኑሮም – አያውቅም። በዬፌርማታው ነው – የሚንጠባጠበው። ንክኪ ያለው ሁሉ። ጥርት ላለ ድል ጥርት ያለ አቋም ወሳኝ ነው። በጥገና  – አይሆነም። በውሽልሽል ዕሳቢም ቀዳዳ በቀዳዳ ነው – የሚሆነው። የማይጠገነው – አይጠገነም። ሁለት ውሃ ዬያዘን ብርጭቆ አንድ ብርጭቆ አድርጎ ማዋህድ – አይቻልም። ቢሞከር ብርጭቆው ይሠበራል ውሃውም – ይፈሳል። ሃቁ ያለው ከበይ ተመልካቹ ሳይሆን – ከተጠቃሚው ነው። ተጠቃሚው አልተጠቀመም እዬተባለ አቅም መፍጠር – ፈጽሞ አይቻልም። በእኛ ውስጥ ለመኖር ጥቅምን በርግጫ ማለት – ያስፈልጋል። ስለማያውል – ስላማያሳድር። ስለማያሰነብትም። በመርኽ ድርድር – የለም። no አልተግባብቶም – yes ተግባብቶ። ይሄው ነው። ጨረስኩኝ። በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ይህ የመጨረሻዬ ነው። ሌላ ከኮለሙ ደግሞ ካልተመቸኝ መስመር ላይ እንገናኛለን .. ወይ ፌርማታው ላይ እንጠባበቃለን … ደህና ይሰንብቱልኝ። የእኔ ድንግልም – ትጠብቅልኝ።

የኔዎቹ እኔ ሰንበትን ተንተርሼ – አሰብኩኝ። ለዛውም አሁን ጥብብ ያለ ጊዜ ላይ – ነበርኩኝ። ታዲይንላችሁ በድንገት አቶ ይገርም ወደ ቤተ ሥርጉተ ጎራ አሉና ቡናና ሻይ፤ ሽሮዋንም ተከተክ አድርጌ በዘንጣፌ ቤት ለእንግዳ ስልላችሁ እግረ መንገዴን ናፍቆቴቼን ግኝት። መሸቢያ ሰሞናት! ዘሃበሻ ኑሩልኝ – ለምልሙልኝ።

„እንቅልፍ ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም!

አርበኞቻችን መርሆቻችን መንገዶቻችን ናቸው!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>