በአርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ “ሦሥት መዓዘን” ፊልም እና በደራሲ አትንኩት ሙሉጌታ “ፍቅር ሲበቀል” የተሠኘ ረጅም ልብወለድ መፅሐፍ መካከል የነበረው የ10 ሚሊዮን ብር የፍትሐብሔር ክስ ክርክር ለፍርድ ማስፈፀሚያ የሚሆን ብር ማስያዣ ማቅረብ ይችላል የሚል ሀሣብ አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ ባቀረበው ተቃውሞ መሠረት ከጥቅምት 22/2007 ዓ.ም ጀምሮ ሲከራከሩ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ሰኔ 24/2007 ዓ.ም የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 13ኛ ምድብ በዋለው ችሎት የደራሲ አትንኩት ሙሉጌታ ጠበቃ አቶ አንዱዓለም በእውቀቱ እና የአርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ ጠበቃ አቶ ኤልያስ ተ/መድህን ያቀረቡትን አቤቱታ ዳኛው ግራ ቀኙን ካዩ በኋላ ብይን የሠጡ ሲሆን አርቲስት ቴዎድሮስ ለሐምሌ 23/2007 ዓ.ም ለተከሰበት ክስ መልስ ይዞ እንዲቀርብ ዉሳኔ ሲሰጡ ከዚህም ጋር አያይዘውም የመፅሀፉን አንድ ኮፒ አብረዉ ሠጥተዋል፡፡
ከሳሽ ደራሲ አትንኩት አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ ለእይታ ያበቃው “ሦስት ማዕዘን” የተሰኘ ፊልም ታሪክ በ2000 ዓ.ም ካሳተሙት “ፍቅር ሲበቀል” የተሰኘ የረዥም ልቦለድ መፅሃፍ የተወሰደ ነው የሚል አቤቱታ ማሰማታቸውን ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም መዘገቧ አይዘነጋም::