Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ጉደኛው አርከበ እቁባይ “ወደብ ልማት ያመጣል ብለው የሚያስቡ ሰዎች ስለ ኢኮኖሚ ልማት ምንም የማይገባቸው ሰዎች ናቸው”አሉ

$
0
0

የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ አማካሪ አቶ አርከበ እቁባይ ግንቦት 20ን አስመልክቶ ከዘመን መጽሔት ጋር ቆይታ አድርገዋል። ከቀረበላቸው ጥያቄ መካከል ድርጅትና መንግሥታቸው ኤርትራንም ሆነ ወደቡንም አሳጥቶናል የሚሉ ወገኖች አሉና ለእነዚህ ወገኖች ምላሽዎ ምንድን ነው? የሚለው አንደኛው ነበር። እንዲህ ብለው መለሱ-
Arkebe Equbay
“ስለ ሕዝብ የማያነሳና የማያስብ ግለሰብ ወይም ቡድን ብቻ ነው ስለ መሬትና ወደብ የሚያነሳው። አገር ማለት ሕዝብ ነው። ስለሆነም ስለ ሕዝቦች በምናስብበት ጊዜ የኤርትራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ነው መወሰድ ያለበት።” በማለት የጀመሩት አርከበ ስለ ኤርትራ ህዝብ ፍላጎትና ስለድርጅታቸው አቋም እንዲህ ብለዋል “ የኤርትራ ሕዝብ ምን ይፈልጋል? ለብዙ ዓመት በጦርነት ውስጥ የቆየ ሕዝብ ነው፤ ከ30 ዓመታት በላይ። ከኢትዮጵያ መገንጠል እንፈልጋለን አሉ። 99 በመቶ የሚሆነው የኤርትራ ሕዝብ ነፃ ኤርትራን እንፈልጋለን አለ። ሕዝቡ ፍላጐቱን በድምፅ አረጋገጠ ማለት ነው። የሕዝቡ ፍላጐት ደግሞ መሟላት አለበት። ዴሞክራሲ ማለት ለሕዝብ መቆም ማለት ነው። ማነው የመጀመሪያ
አገር ኤርትራን እንደ አገር የተቀበለው? የኢትዮጵያ መንግሥት ነበር። ያ ሆኖ ሰላም ማረጋገጥ ተችሏል። ስለዚህ ያንን ያደረግነው ከሰላም፣ ከዴሞክራሲ፣ ከሕዝቦች መብት ማረጋገጥ አንፃር ነውና ይሔ መሆኑ ተገቢ ነው።”

ወደብን አስመልክቶ ግን አቶ አርከበ የሰጡት ማብራሪያ “የአሰብን ወደብ (ባለመጠቀም) የግመል መጠጫ ሆኖ ይቀራል (እናደርገዋለን?) በማለት ዝተው ከነበሩት ከአቶ መለስ ዜናዊ ንግግር ጋር የሚመሳሰል ይመስላል። “እኛ ወደብ መች ቸገረን?” ያሉት አቶ አርከበ ወደብ ብቻውን ልማትን የማያስገኝ መሆኑን በመግለጽ ጥያቄውንም ሆነ ባለወደቢቷን ኤርትራን ከሶማልያ ጋር በመደመር ያናናቁ መስለዋል። እንዲህ ብለዋል-
“ግን ዋናው ነጥብ ምንድንነው ወደብ ልማት ያመጣል ብለው የሚያስቡ ሰዎች ስለ ኢኮኖሚ ልማት ምንም የማይገባቸው ሰዎች ናቸው። በአካባቢያችን ሠፋፊ ወደብና የባህር ዳርቻ ያላቸው አገሮች እነማን ናቸው? አንዷ ሶማሊያ ናት። ሁለተኛዋ ማናት? ኤርትራ
ናት። ሁለቱንም እንያቸው በጥፋት ሂደት ያሉ አገሮች ናቸው። ሶማሊያ ግን አሁን በተሻለ እንቅስቃሴና
መረጋጋት ውስጥ ናት። ኢኮኖሚ ልማት በእነዚህ አገራት የለም። ስለዚህ ልማትና ዕድገትን የሚያመጣው ወደብና የባህር ዳርቻ ነው የሚለው አስተሳሰብ ሕዝብን እንደ ሕዝብ ያለ ማየት አስተሳሰብ ምንጭ ነው። እኛ ወደብ መች ቸገረን? በጂቡቲና በበርበራ መጠቀም እንችላለን። የኤርትራም ሁኔታ መቀየሩ አይቀርም፡፡ አሁን ያለው ሁኔታ ለዘለዓለም ይኖራል ብለን አንገምትም። በእኔ ግምት በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ውስጥ ለውጥ ይመጣል ባይ ነኝ። የኤርትራን ወደብ እንጠቀማለን። የኬንያን ወደብ መጠቀም እንችላለን። ከዚያ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ መስመር ለመገንባት ታቅዷል። የሱዳንንም እንጠቀማለን። ቢቻል ወደብ ቢኖረን ጥሩ ነበር ግን የሁሉም መቋጫና መፍትሔ እርሱ ነው ማለት አይደለም። የሚያመጣው መሠረታዊ ለውጥም የለም በእኔ እምነት።”


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>