Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Sport: ‹‹ሚላን የሕይወቴ አንድ አካል ነው›› ፓውሎ ማልዲኒ

$
0
0

ጥያቄ፡- በቻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ በተቃራኒ ተሰልፈን ከተጫወትን 10 ዓመት ሆነው፡፡ አሁን ሁኔታዎች ከ2005 ፍፁም የተለዩ ናቸው፡፡ በዚህ የውድድር ዘመን የሁለታችንም ቡድኖች ጥሩ ጊዜን አሳለፉም፡፡ ሊቨርፑል ሲሸነፍ ስመለከት ያመኛል፡፡ አንተስ ሚላን ሲሸነፍ ተመሳሳይ ስሜት ይሰማሃል?

መልስ፡- በትክክል፡፡ ክለቡን የተቀላቀልኩት በ10 ዓመቴ ነው፡፡ እስከ 41 ዓቴ ድረስ በዚያ ተጫውቻለሁ፡፡ አባቴ የቡድኑ አምበል ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት ልጆቼ በአካዳሚው ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ሚላን ለእኔ ቡድን ብቻ አይደለም፡፡ የህይወቴ አንድ አካል ነው፡፡ ቤተሰቦቼ ለማልያው ፍቅር አላቸው፡፡ ግን ምን ታደርገዋለህ? እንደዚህ ሆኖ ስመለከተው አዝናለሁ፡፡ ከሌሎች ትላልቅ ተጨዋቾች ጋር በመሆን የተለየ ነገር ገንብተን ነበር፡፡ ነገር ግን የእነዚህን ሰዎች አስፈላጊነት አይገነዘቡም፡፡ በአሁኑ ወቅት በዚያ የሚሰራው ፍራንኮ ባሬዚ ብቻ ነው፡፡ ሌላ የቀድሞ ተጨዋች በክለቡ አታገኝም፡፡ ያሳዝናል፡፡ ሚላን ትልቅ ባህል ነበረው፡፡ ሆኖም ሙሉ በሙሉ እየተጠፋ ነው፡፡ አዲሱ ትውልድ ይህንን በቅጡ አይገነዘብም፡፡ ክለቡ የዳበረ ታሪክ ነበረው፡፡ አሁን ግን ተለዋውጧል፡፡

Paolo-Maldini

ጥያቄ፡- ያንን ስትመለከት ልትረዳቸው ታስባለህ?

መልስ፡- ያንን ባደርግ ደስ ይለኛል፡፡ ከክለቤ ብዙ ነገር ተቀብያለሁ፡፡ ስሜቴን እና ሰውነቴን ለጥቄያቸዋለሁ፡፡ አሁን በቅጡ እንኳን መራመድ የማልችለው ለዚያ ነው (ሳቅ)፡፡ ሆኖም ተጨማሪ ነገር መልሼ መስጠት ብችል ደስ ይለኛል፡፡ ተሞክሮዬን ባካፍላቸው እወድዳለሁ፡፡ ታዳጊዎቹ ደካሞች አይደሉም፡፡ ነገር ግን ትክክለኛውን አቅጣጫ የሚያሳያቸው ይፈልጋሉ፡፡ ያ የሚሆን ግን አይመስለኝም፡፡

 

ጥያቄ፡- ያደግኩት ሚላንን እየተመለከትኩ ነው፡፡ የአሪጎ ሳኪ እና የፋቢዮ ካፔሎን ቡድኖች ሁልጊዜ እመለከት ነበር፡፡ ባለፈው ሳምንት ማድሪድ ውስጥ ሳኪን አይቼዋለሁ፡፡ ስለ አንተ እና ስለዚህ ቡድን እያወራ ነበር፡፡ በተጨዋችነት ዘመንህ የእርሱ ተፅዕኖ ምን ነበር?

መልስ፡- በጣም ጥብቅ ነበር፡፡ የልምምድ መርሃ ግብሮች አስቸጋሪዎች ነበሩ፡፡ እንድትታትር ያደርግሃል፡፡ አዕምሮህንም ያዘጋጃል፡፡ አንድን ነገር ደግመህ ደጋግመህ እንድትሰራ ያደርጋል፡፡ በተለይ ተከላካዮችን፡፡ በየዕለቱ ተመሳሳይ ነገር እንሰራ ነበር፡፡ እኔ፣ ባሬዚ፣ አሌሳንድሮ ኮስታኩርታ እና ማውሮ ታሶቲ አሁን ብንገናኝ በ1990ዎቹ እናደርግ እንደነበረው በጥሩ ሁኔታ መጫወት እንችላለን፡፡ በአዕምሮህ ውስጥ ተቀርፆ ይቀራል፡፡ የስኬታማነታችን አንዱ ምስጢር ያ ነበር፡፡ የሚላን ታሪክ እንዲቀጥል ረድቷል፡፡ ያ ቡድን በዚያ ደረጃ ለረዥም ጊዜ (እጆቹን ወደ ላይ እያነሳ) ተጫውቷል፡፡ እንደ ቻምፒዮንስ ሊግ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሸነፍኩት በ1989 ነው፡፡ የመጨረሻውን የቻምፒዮንስ ሊግ ድሌን ያጣጣምኩት ደግሞ ከ18 ዓመት በኋላ ነው፡፡ አሁን ግን የሚታየው ነገር አሳዛኝ ነው፡፡

 

ጥያቄ፡- ታዲያ ፓውሎ ስለ ኢስታምቡሉ ጨዋታ ማውራት እንችላለን?

መልስ፡- አዎን! አልፎ አልፎ ይነሳል፡፡ የመጀመሪያውን አጋማሽ የተመለከተ ይሸነፋል ብሎ አይገምትም፡፡ ነገር ግን ሰዎች ጥሩ እንቅስቃሴ ያደረግነው በመጀመሪያው አጋማሽ ብቻ እንደሆነ ይዘነጋሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ጨዋታችንን ፈጠርን፡፡ ስቲቨን ዤራርድ የተከላካይ ሚና ሲወጣባቸው የነበሩ ደቂቃዎችን አስታውሳለሁ፡፡ በአንተ ቡድን ውስጥ የነበሩ ተጨዋቾች በአካል ብቃት ረገድ ተዳክመው ነበር፡፡

 

ጥያቄ፡- በ1989 ባርሴሎና ላይ ስቲሞ ቡካሬስትን 4-0 ያሸነፋችሁበትን የዩሮፒያን ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ ተመልክቼዋለሁ፡፡ ምናልባትም ግን የኢስታንቡሉ ብቃትህ የተሻለ ሳይሆን አይቀርም?

መልስ፡- ከዚያ በላይ ልናደርግ የምንችለው ነገር አልነበረም፡፡ የሚያስገርመው ነገር ሚላን ስንደርስ ደጋፊዎች እየጠበቁን ነበር፡፡ ‹‹ምን ነካችሁን?!›› እያሉ ይጮሁ ነበር፡፡ የአቅማችንን ሁሉ ፈጽመናል፡፡ በ1994 ባርሴሎናን 4-0 ካሸነፍንበት ጨዋታ ቀጥሎ ምርጡን የፍፃሜ ጨዋታ አድርገን ነበር፡፡ ውድድሩን የማሸንፍበት የመጨረሻ ዕድሌ እንደሆነ አስቤ ነበር፡፡ ሆኖም አመለጠን፡፡ ጨዋታው አስገራሚ ነበር፡፡ ጎል አስቆጠርኩ፡፡ ያውም በፍፃሜ ከተቆጠሩ ጎሎች ሁሉ ፈጣን የሆነችውን፡፡ ግን ጨዋታው ባሰብነው መንገድ ሳይጠናቀቅ ቀረ፡፡

 

ጥያቄ፡- እስከ እረፍት 3-0 እየመራችሁ ነበር፡፡ ያን ያህል ቀላል ይሆናል ብለህ አስበህ ነበር?

መልስ፡- በእረፍት ሰዓት እየጨፈርን እንደነበር የሚያትቱ ታሪኮችን ሰምቼያለሁ፡፡ የፈፀምነው የማይቻል ነገር ነበር፡፡ ወደ መልበሻ ክፍል ስንገባ ቀውጢ ሆነ፡፡ ሰዎች የሚጣሉ እስኪመስል ድረስ ይጯጯሁ ነበር፡፡ ይህን ጊዜ አንቼሎቲ ተቆጣ፡፡ ‹‹ለአምስት ደቂቃ አፋችሁን ዝጉ፡፡ ማንም ሲናገር መስማት አልፈልግም፡፡ አንዲት ቃል መስማት አልሻም›› አለ፡፡ ያን ጊዜ ሁላችንም ፀጥ አልን፡፡ ተረጋጋን፡፡ ከዚያም በደካማ እና ጠንካራ ጎናችን ላይ ተነጋገርን፡፡ ስለ ሁለተኛው አጋማሽ ማሰብ ጀመርን፡፡ እውነታው ይህ ነው፡፡ እኔ በልቤ ‹‹ትልቅ ዕድል አለን›› ብዬ አስቤያለሁ፡፡ ነገር ግን ምንም አልተናገርንም፡፡ ማንም የተናገረ የለም፡፡

 

ጥያቄ፡- 3-0 እየተመራህ ያለኸው እንደምትበልጠው በምታስበው ቡድን ቢሆን ዕድል ይኖርሃል፡፡ ነገር ግን የምንመራው በኤሲሚላን ነው፡፡ በወቅቱ አስብ የነበረው ባርሴሎና እና ስቴዋ ቡካሬስትን 4-0 አሸንፈዋል፡፡ እኛን በምን ያህል ጎል ያሸነፉን ይሆን? በአምስት ወይስ በስድስት? ለውጡ ምን ነበር?

መልስ፡- በሁለተኛው አጋማሽ የተከሰተ ነገር ነበር፡፡ ደጋፊዎቻችሁ የማይታመኑ ነበሩ፡፡ ያለማቋረጥ ይዘምሩ ነበር፡፡ ብዙውን ጊዜ በስታዲየም እኩል ቁጥር ያላቸው በሁለት ቡድን ደጋፊዎች እንዲገቡ ይደረጋል፡፡ ያን ዕለት ግን የሊቨርፑል ደጋፊዎች 75 በመቶ ይሆኑ ነበር፡፡ ለሊቨርፑል ደጋፊዎች ትኬቶቻቸውን የሸጡ የሚላን ደጋፊዎች ትኬቶቻቸውን የሸጡ የሚላን ደጋፊዎች በርካታ ነበሩ፡፡ የመጀመሪያዋን ጎል አስታውሳታለሁ፡፡ ዤራርድ እና ያፕስታም ይታዩኝ ነበር፡፡ ‹‹ተጠንቀቅ እየመጣ ነው! ለምን የሆነ ነገር አላልኩም ነበር?›› ብዬ ከራሴ ጋር አወራሁ፡፡

 

ጥያቄ፡- ጨዋታውን የቀየረችው ቭላድሚር ስሚሰር ያስቆጠራት ሁለተኛ ጎል እንደሆነች ታስባለህ?

መልስ፡- አዎን! ጎሏ ብዙ ነገር ለውጣለች፡፡ በድንገት አቻ ለመሆን የሚያስፈልጋችሁ አንድ ጎል ብቻ መሆኑን አወቃችሁ፡፡ ነገር ግን 3-3 እኛ ጨዋታውን እንደ አዲስ ጀመርን፡፡ ዕድሎችንም ፈጠርን፡፡ 3-3 ስንሆን የጨዋታው ስነ ልቦና ተቀየረ፡፡ እናንተ የምታጡት ነገር እንዳለ ማሰብ ጀመራችሁ፡፡

 

ጥያቄ፡- በዕለቱ የዤራርድ አቋም እንዴት ነበር? በሶስት የተለያዩ ቦታዎች ላይ ተጫውቷል፡፡ አሁም ድረስ ሰዎች በጣልያን ስለ እርሱ ያወራሉ?

መልስ፡- አሁንም ድረስ ፊቱን አስታውሰዋለሁ፡፡ በተደጋጋሚ በመገጨቱ ምክያት የፈጠረበትን ህመም ገፁ ላይ በግልፅ ይታይ ነበር፡፡ እንደዚያም ሆኖ ሜዳውን እያካለለ መጫወቱን እና ሸርተቴ መውረዱን አላቆመም፡፡ ሁሉንም ነገሩን ሰጥቷል፡፡ ለሌሎቻችሁ ጥሩ ምሳሌ ነበር፡፡

 

ጥያቄ፡- ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ እኛ ደስታችንን ስንገልፅ መመልከት ለእናንተ ፈታኝ ስሜት መፍጠሩ አይካድም፡፡ እኔ እና አንተ ስንጨባበጥ የሚያሳይ ፎቶ አለኝ፡፡ ከዚያ ሁሉ ስኬትህ በኋላ በዚያ ጨዋታ ላይ በመሸነፍህ የተፈጠረብህን የህመም ስሜት ተመልክቼዋለሁ፡፡ ነገር ግን በሰጠኸው ምላሽ ደረጃህ ምን ያህል ከፍ ያለ እንደሆነ አሳይተሃል?

መልስ፡- የቱንም ያህል አሳዛኝ ቢሆን ውጤቱን በፀጋ መቀበል ይኖርብሃል፡፡ ነገር ግን ዕድለኞች ነበርን፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላ የምንበቀልበትን አጋጣሚ አገኘን፡፡ በአቴንስ ያደረግነው ጨዋታ የኢሰታምቡሉን ያህል ጥሩ አልነበረም፡፡ ነገር ግን አሸነፍን፡፡

 

ጥያቄ፡- በ2007 ዳግም ሊቨርፑልን ስትገጥሙ ምን ተሰማህ?

መልስ፡- በፍፃሜው ጨዋታ ጥሩ አልተጫወትንም፡፡ በእርግጥ በሙሉው የውድድር ዘመን ጥሩዎች አልነበርንም፡፡ ሩብ ፍፃሜውን ከተቀላቀልን በኋላ ግን መሻሻሎች  አሳየን፡፡ በዚያ የፍፃሜ ጨዋታ ልንሸነፍ የምንችልበት ዕድል ነበር፡፡ በሊቨርፑል ሌላ ሽንፈት ብናስተናግድ የበለጠ አሳዛኝ ይሆን ነበር፡፡ ነገር ግን ተጋጣሚያችንን የመምረጥ መብት አልነበረንም፡፡ ከፍፃሜው ጨዋታ በፊት ለሶስት ወራት ወደ ሜዳ አልገባሁም፡፡ በፍፃሜው ጨዋታ ጉልበቱ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ ሆነ፡፡ ያንን ጨዋታ መጫወት እንደማልችል አንቼሎቲም ያውቀው ነበር፡፡ ነገር ግን ሞከርኩ፡፡ በእነዚያ ሶስት ወራት በርካታ የህመም ማስታገሻ መርፌዎችን ተወግቼያለሁ፡፡ አስገራሚው ነገር ስለ ጨዋታው ብዙም የማስታውሰው ነገር የሌለኝ መሆኑ ነው፡፡

 

ጥያቄ፡- እኔም እንደዚያው፡፡ ጨዋታውንም ዳግም አልተመለከትኩትም፡፡ እንደዚያ አይነት ትልቅ ጨዋታዎችን ስትሸነፍ…?

መልስ፡- የማስታውሰው ብቸኛ ነገር ዋንጫውን ማንሳቴን ነው፡፡ ለ36 ሰዓታት ደስታችንን ገለፅን፡፡ ፌሽታው እንደተጠናቀቀ በቤልጅየም ወደ ሚገኝ የቀዶ ጥገና ሐኪም አመራሁ፡፡ ጉልበቴ ከጥቅም ውጪ ሆኖ ነበር፡፡ በደንብ የማስታውሰው ከተጨማሪ 24 ሰዓታት በኋላ በወለድኩት ማደንዘዣ ምክንያት ከገባሁበት ሰመመን ስነቃ የሆነውን ነው፡፡ ‹‹አሸንፌያለሁ ወይ?… አሸንፌያለሁ ወይ?›› እያልኩ አሰብኩ፡፡ ከአስር ሰከንዶች በኋላ አዕምሮ ‹‹››…አዎ አሸንፈናል!›› የሚል ምላሽ ሰጠኝ፡፡

 

ጥያቄ፡- ያ የፍፃሜ ጨዋታ ለስምንተኛ ጊዜ የተሰለፍክበት እና ለአምስተኛ ጊዜ ያሸነፍክበት ነበር፡፡ ቅድሚያ የምትሰጠው ድል የትኛው ነው?

መልስ፡- ፍራንሲስክ ጄንቶም ከሪያል ማድሪድ ጋር በስምንት የቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜዎች ላይ ተጫውቷል፡፡ በስድስቱ ደግሞ አሸንፏል፡፡ እንደዚያም ሆኖ የእኔ ሪከርድ መጥፎ የሚባል አይደለም፡፡ እያንዳንዱ ድል የተለየ ስሜት ነበረው፡፡ የመጀመሪያው ቀዳሚ በመሆኑ ብቻ የተለየ ነው፡፡ ወደ ስታዲየሙ ስገባ የተሰማኝ ስሜት በህይወት ዘመኔ ካጣጣምኩት ሁሉ ቀዳሚው ነው፡፡ እናንተ በኢስታምቡል ከተሰማችሁ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ታላቅ ስሜት ነበር፡፡ ከእርሱ ቀጥሎ በአቴንስ ባርሴሎናን ያሸነፍንበት ሊጠቀስ ይችላል፡፡

 

ጥያቄ፡- ከተጫወትክባቸው የሚላን ቡድኖ ምርጡ የትኛው ነበር? ማርኮ ቫንባስተን እና ሩድ ጉሊትን የያዘው የ1989 ቡድን ወይስ ከአምስት ዓመት በኋላ የገነባችሁት?

መልስ፡- የሁሉም ነገር መጀመሪያ ሳኪ ነው፡፡ ሶስት ሆላንዳውያን ተቀላቀሉን፡፡ ካፔሎ ቡድኑን ሲረከብ ደግሞ በርካታ ታላላቅ ተጨዋቾች ነበሩን፡፡ ምናልባትምምርጡ ቡድን ከ1991 – 94 የነበረው እንደሆነ አስባለሁ፡፡ በየዓመቱ ትልቅ ተጫዋች እንገዛ ነበር፡፡ በቀኝ መስመር ጉሊት አለ፡፡ ከኋላው ታሶቲ ነበር፡፡ ቫን ባስተን፣ ዳኒኤሌ ማሳሮ፣ ዦን ፒዬ ፓፒን፣ ዝቮንሚር ቦባን እና ዴያን ላቪቾቪች ነበሩ፡፡ ዋው… የተለየ ስብስብ ነበር፡፡

 

ጥያቄ፡- አብረሃቸው ከተጫወትካቸው አልያም በተቃራኒ ከገጠምካቸው ሁሉ ምርጡ ቫን ባስተን ነው?

መልስ፡- በትክክል፡፡ በቀኝ እና በግራ እግሩ ይጠቀማል፡፡ በግንባሩ ይገጫል፡፡ ጠንካራ እና ፈጣን ነው፡፡ አመቻችቶ ያቀብላል፡፡ ምርጥ ነበር፡፡ አጨዋወቱ ጊዜ የማይሽረው ነበር፡፡ ነገር ግን በ28 ዓመቱ ከጨዋታ ለመገለል ተገደደ፡፡ በቁርጭምጭሚቱ ላይ ያልተሳካ ቀዶ ጥገና ማድረጉ ለዚያ አበቃው፡፡ ያሳዝናል፡፡

 

ጥያቄ፡- ምርጡ ተከላካይስ? ባንተ ላይ የባሬዚ ተፅዕኖ ምን ያህል ነው? የተከላካይ መስመር መሪ ነበር? ልዩ የሚያደርገውስ ምንድን ነው?

መልስ፡- በትክክል፡፡ በቀኝ እና በግራ እግሩ ይጠቀማል፡፡ በግንባሩ ይገጫል፡፡ ጠንካራ እና ፈጣን ነው፡፡ አመቻችቶ ያቀብላል፡፡ምርጥ ነበር፡፡ አጨዋወቱ ጊዜ የማይሽረው ነበር፡፡ ነገር ግን በ28 ዓመቱ ከጨዋታ ለመገለል ተገደደ፡፡ በቁርጭምጭሚቱ ላይ ያልተሳካ ቀዶ ጥገና ማድረጉ ለዚያ አበቃው፡፡ ያሳዝናል፡፡

 

ጥያቄ፡- ምርጡ ተከላካይስ? ባንተ ላይ የባሬዚ ተፅዕኖ ምን ያህል ነው? የተካላካይ መስመር መሪ ነበር? ልዩ የሚያደርገውስ ምንድን ነው?

መልስ፡- በትክክል እንደዚያ ነው፡፡ ልዩ ነበር፡፡ በጣም ከፍ ብሎ መዝለል ይችላል፡፡ አጨዋወቱ ለሁሉም ሰው ምሳሌ ነበር፡፡ ተናጋሪ አይደለም፡፡ ብዙ አያወራም፡፡ ነገር ግን አጨዋወቱ እና የሚለማመድበት መንገድ ምሳሌ የሚሆን ነበር፡፡ እንደ ስታም አይነት ጠንካራ እና ፈጣን የሆነ ግዙፍ ተከላካይ አልነበረም፡፡ ፈጣን ቢሆንም 70 ኪሎ ግራም ብቻ ይመዝን ነበር፡፡ ሸርተቴ ሲወርድ ጠንካራ ነበር፡፡ አርአያዬ ነበር፡፡ ማነፃፀሪያዬ ነበር፡፡ ከኳስ ጋርም ጥሩ ነበር፡፡ በጣም ጥሩ ነበር፡፡ ጠንካራ የሆነ እና ጥሩ የኳስ ክህሎት ያለው ተከላካይ ማግኘት ከባድ ነው፡፡

 

ጥያቄ፡- እኔ ታዳጊ በነበርኩበት ወቅት እንግሊዝ ውስጥ የነበሩ ተከላካይ መሆን የሚፈልጉ ልጆች የአንተን እና የባሬዚን ስም ይጠሩ ነበር፡፡ እንደ ሊሊያን ቱራም፣ ማርሴል ዴሳይ እና ፋቢዮ ካናቫሮን የመሳሰሉ ታላላቅ ተከላካዮችም ነበሩ፡፡ አሁን ላይ ስላለው የተከላካዮ ደረጃ ምን ትላለህ?

መልስ፡- ተከላካዮች እየጠፉ ነው፡፡ ታላላቅ ተከላካዮች ከአጥቂዎች ባልተናነሰ በገበያው ላይ ይፈለጋሉ፡፡ ምን እንደተፈጠረ ታውቃለህ? የግራ መስመር ተከላካይ ሆኜ ተጫውቼ አውቃለሁ፡፡ ዛሬ ላይ የግራ መስመር ተከላካይ የሚመዘነው ከኳስ ጋር በሚሰራው ነገር ብቻ ነው፡፡ በመከላከሉ ረገድ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ከግምት አይገባም፡፡ ትኩረት የሚሰጠው በማጥቃት እንቅስቃሴው ላይ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ነው፡፡ አስቸጋሪው ክፍል መከላከል መሆኑን አውቃለሁ፡፡ አሳምሬ አውቀዋለሁ፡፡ ምክንያቱም በሳኪ ዘመን ከአጥቂዎቹ ጀምሮ እስከ ግብ ጠባቂው ድረስ ሁሉም የመከላከል ግዴታ ነበረን፡፡ ዛሬ ላይ ያንን እያጣነው ነው፡፡ ለምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ በአሁኑ ወቅት የዓለማችን ምርጡ ተከላካይ ቲያጎ ሲልቫ እንደሆነ አምናለሁ፡፡

 

ጥያቄ፡- ወደ እንግሊዝ የምትሄድበት ዕድል ተፈጥሮልህ ያውቅ ነበር፡፡ ወደዚያ ባለመሄድህስ ትፀፀታለህ? ሁሉም ሰው በፕሪሚየር ሊግ ቢመለከትህ ደስ ይለው ነበር፡፡

መልስ፡- ማንቸስተር ዩናይትድ ጥያቄ አቅርቦልኝ ነበር፡፡ ነገር ግን በቀጥታ አላነጋገርኳቸውም፡፡ ሉካ ቪያሊ የቼልሲ አሰልጣኝ በነበረበት ወቅት ደውሎልኛል፡፡ ይህ የሆነው በ1996 ነው፡፡ ያሳለፍነው መጥፎ የውድድር ዘመን ነበር፡፡ አርሰናልም እንደዚሁ ፍላጎት አሳይቷል፡፡ ነገር ግን በቀጥታ አነጋግሬያቸው አላውቅም፡፡ ያም ቢሆን እሺ አልላቸውም ነበር፡፡ ቪያሊ ጓደኛዬ ነበር፡፡ ጉዳዩን እንዳስብበት ያደረገኝ እርሱ ብቻ ነው፡፡ በቡድኑ ውስጥ የተወሰነ አለመግባባት ነበር፡፡ ከደጋፊዎች ጋርም ጥሩ ጊዜ አልነበረኝም፡፡ ለአንድ ቀን ‹‹ባደርገውስ?›› ብዬ አሰብኩና በፍፁም የሚል ውሳኔ ላይ ደረስኩ፡፡

 

ጥያቄ፡- ቼልሲን የምታሰለጥንበት አጋጣሚም ተፈጥሮልህ ነበር?

መልስ፡- ጥያቄው የቀረበልኝ ለሚላን የመጨረሻ ጨዋታዬን ባደረግኩ ሳምንት ነው፡፡ ዝግጁ አልነበርኩም፡፡ ቤተሰቤን ወደ ለንደን መውሰድ አልፈለግኩም፡፡ ወደዚያ ሄጄ ከሚስተር አብራሞቪች ጋር ተነጋገርኩ፡፡ በሚላን አብሬው ከተጫወትኩት ሬይ ዊልኪንስ ጋር አወራሁ፡፡ አላውቅም በመጨረሻ ኃላፊነቱን ላለመቀበል ወሰንኩ፡፡

 

ጥያቄ፡- ስለ እንግሊዝ እግርኳስ ምን ታስባለህ? በ1990ወቹ እንዳደረጉት የጣሊያን ክለቦች በአውሮፓ የበላይነት ይጨብጣሉ የሚል ግምትስ አለህ?

መልስ፡- የእንግሊዝን እግርኳስ እከታተላለሁ፡፡ ጠንካራ የአካል ብቃት ይጠይቃል፡፡ ማንቸስተር ሲቲ እና ሊቨርፑልን የመሳሰሉ ጥሩ እግርኳስ የሚጫወቱ ቡድኖችም አሉ፡፡ ነገር ግን ከየትኛውም ሀገር የተለየ ሊግ ነው፡፡ ሊጉ ጠንካራ የአካል ብቃት ስለሚጠይቅ እና አካላዊ ንክኪዎች ስለሚበዙበት ብቻ ወደዚያ ሄደው መጫወት የማይችሉ ታላላቅ ተጨዋቾች አሉ፡፡ የጣሊያን ክለቦች ወደ ቀድሞ ስፍራቸው ለመመለስ ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው አስባለሁ፡፡ የገንዘብ እጥረት አለ፡፡ ስታዲየሞቹ አመቺ አይደሉም፡፡ ከነውጠኛ ደጋፊዎች ጋር የተያያዙ ችግሮች ሊቀረፉ ይገባል፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን ይዘው ወደ ስታዲየም መግባት የማይችሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ሚላን አዲስ ስታዲየም ለመገንባት እየሞከረ መሆኑ ይነገራል፡፡ መሳካቱን ግን እጠራጠራለሁ፡፡ ሚላን ከ45 ሺ መቀመጫዎች በላይ ያለው ስታዲየም እንደሚገባው አምናለሁ፡፡ ቢያንስ 60 ሺ ሰዎችን የመያዝ አቅም ያለው ስታዲየም ያስፈልገዋል፡፡ ሳን ሴሮ አሁንም ውብ ነው፡፡ ነገር ግን አርጅቷል፡፡

 

ጥያቄ፡- ነገር ግን እነ ሚላን ወደ ቀድሞ ክብሩ ተመልሶ መመልከት እፈልጋለሁ፡፡ ስሙ፣ ማልያው እና ታሪኩ ታላቅ ነው፡፡ ለሊቨርፑልም የሚሰማኝ እንደዚህ ያለው ስሜት ነው፡፡

መልስ፡- እኔም ያንን መመልከት እሻለሁ፡፡ ሚላንን እንደ ሪያል ማድሪድ፣ ባርሴሎና እና ሊቨርፑልን ከመሳሰሉ ታሪካዊ ተቀናቃኞቻችን ተርታ ተሰልፎ ላየው እወድዳለሁ፡፡ ቁልቁል ሲጓዝ መመልከት ያሳዝናል፡፡

 

ጥያቄ፡- ወደፊት በሚላን ስለሚሆነው ነገር እርግጠኛ ባትሆን እንኳን ስለራስህ የምታውቀው ይኖራል? በቅርቡ በሚያሚ አዲስ ፕሮጀክት ጀምረሃል፡፡ ነገር ግን አሰልጣኝ የመሆን ህልም አለህ?

መልስ፡- በፍፁም፡፡ ሥራውን አልወድደውም፡፡ አሁንም ድረስ ከጓደኞቼ ጋር የሚላንን ጨዋታዎች ለመመልከት እሄዳለሁ፡፡ ነገር ግን ከሚላን ጋር አብሬ የምሰራ አይመስለኝም፡፡ ለጊዜው የሙሉ ጊዜ አባለት ነኝ፡፡ ነገር ግን ከሚላን ጋር ዳግም የምሰራበት አጋጣሚ ቢፈጠርልኝ ደስታውን አልችለውም፡፡ ከሰጠኝ ነገር ትንሹን መልሼ የምከፍልበት ዕድል አገኛለሁና፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>