Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

‹‹አሸባሪዎቻችን›› ሲኖ ትራኮች ብቻ አይደሉም!! –ለ85 በመቶ የትራፊክ አደጋዎች መንስኤ ሆኖ እርምጃ ያልተወሰደበት አንድ ብቻ ምስጢር!!

$
0
0

ለሥራ ጉዳይ ወደ ጎጃም ስጓዝ ያየሁት ነገር ትኩረቴን በጣም ሳበው፡፡ ሁሉም እግረኞች ግራቸው ይዘው ነው የሚጓዙት፡፡ ቆም ብዬ አካባቢዬን ስቃኝ ቀኜን ይዤ የምጓዘው እኔ ብቻ ነኝ፤ ሁሉም እግረኛ ግራውን ይዞ ነው የሚጓዘው፡፡ ከቀናት በኋላ በአንድ የገበያ ቀን የወንበርማ ወረዳ ዋና ከተማ በሆነችው ሸንዲ ከተማ ቢጫ ቲሸርት የለበሱና ፊሽካ የያዙ ወጣቶች ገበያተኞችን ግራቸውን እንዲይዙ ሲያደርጉ ተመለከትኩ፡፡ እኔም አንዱን ወጣት ጠጋ ብዬ ስለሁኔታው ጠየኩት፡፡ በጎ ፍቃደኞች እንደሆኑና ሁሌም ቅዳሜ ሰውን እንደሚያስተምሩ ነገረኝ፡፡

sinotruck accident addis abab

ይህ ከሆነ ከወራት በኋላ ፌስቡክ ላይ የሚገርም ምስል አየሁ፡፡ ከላይ ጽሑፍ አለ ከታች ፎቶ፡፡ ናይጄሪያ ብሎ ቦኮሃራም ይላል፡፡ ሱማሊያ ብሎ አልሸባብ ይላል፡፡ ሶሪያ ብሎ አይሲስ ይላል፡፡ ኢትዮጵያ ብሎ ፎቶ ተለጥፏል፡፡ ፎቶውም ቀደም ሲል ‹‹ቀይ ሽብር›› አሁን ደግሞ ‹‹ድሮኖቹ›› (The Drones) ማለትም ‹‹ሹፌር አልባዎቹ›› እየተባለ የሚሽሟጠጠው የሲኖትራክ መኪና ፎቶ ነው፡፡ የእኛ ሀገር አሸባሪ ይኸው ሲኖ ትራክ መሆኑ ነው፡፡ ሌሎቹ መኪናዎቹስ እያሸበሩን አይደለምን? እስኪ ዛሬ ስለ ትራፊክ አደጋ ልፃፍ፤ እናንተም አንብቡ፡፡ መልካም የንባብ ጊዜ!

የመኪና አደጋ ሁኔታ ቅኝት

ለእንደ ኢትዮጵያ ላሉ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት መኪና ዋነኛው የመጓጓዣ መንገድ ነው፡፡ የተለያዩ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት በአፍሪካ 80 ከመቶ የሚሆነው ሰው እና ዕቃ የሚጓጓዘው በመኪና ነው፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ሁኔታ ስንመጣ ደግሞ በከተሞች መሀከል ከሚደረጉ የሰዎችም ሆነ የዕቃዎች መጓጓዝ ውስጥ 90 ከመቶ የሚሆነው የሚካሄደው በመኪና ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በመኪና መጓጓዝ ውስጥ አደጋ የመፈጠር ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ በዓለም የጤና ድርጅት ግምት መሰረት በዓለም ላይ በመንገድ ላይ በሚደርሱ የመኪና አደጋዎች በየዓመቱ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች የሚሞቱ ሲሆን 50 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳቶች ይዳረጋሉ፡፡ በዓለም ላይ ያለውን የአደጋ ቁጥር የመጨመር ሁኔታን ያጤኑት ደግሞ ሁኔታው ከጊዜ ወደ ጊዜ በአደገኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው ይላሉ፡፡ ናድ፣ ቺሾልም እና ባከር የተባሉ ተመራማሪዎች እንደሚሉት እ.ኤ.አ በ2020 የትራፊክ አደጋ ከኤች.አይ.ቪ እና ከቲቪ ቀጥሎ 3ኛው ገዳይ ይሆናል፡፡

ይህን ሁኔታ በአንክሮ ስንቃኘው ደግሞ የትራፊክ አደጋ የሚበዛው በሰለጠኑትና ብዙ መኪና ባላቸው ሀገራት ሳይሆን ጥቂት የመኪና ቁጥር ባላቸው ታዳጊ ሀገራት ነው፡፡ ከዓለም ህዝብ ውስጥ 81 ከመቶ የሚሆኑ የሚኖሩት ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ሲሆን በእነዚህ ሀገራት የሚገኙ መኪናዎች በዓለም ከሚገኙ መኪናዎች ውስጥ 20 ከመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው፡፡ ሆኖም ግን በትራፊክ አደጋ ምክንያት የሚሞቱት ሰዎች በብዛት የሚገኙት በእነዚህ ሀገራት ነው፡፡ እንደ ሙራይ እና ሎፔስ ስሌታዊ አገላለፅ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት በትራፊክ አደጋ ምክንያት በቀን ውስጥ 3 ሺ ሰዎች ይሞታሉ፣ ሌሎች 30 ሺ ሰዎች ደግሞ ለአካል ጉዳት ይዳረጋሉ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ እንደ የዓለም ጤና ድርጅት ግምት ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት 227,835 እግረኞች፣ መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት 165,501 እግረኛ እና ከፍተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት 22,500 እግረኞች በየዓመቱ በመኪና አደጋ ምክንያት ይሞታሉ፡፡

እንደ አንድ ዝቅተኛ ገቢ ያላት ሀገር ኢትዮጵያ በትራፊክ አደጋ የሚደርሱ ገፈቶች ቀማሽ ነች፡፡ ከቤቱ ሳይወጣ ሬዲዮ የከፈተ ሰው እንኳ ቢያንስ አንዴ ስለ አንድ የትራፊክ አደጋ ይሰማል፡፡ ጥናታዊ መረጃ ለማቅረብ ያህል እንኳ ዳንኤል አድማሴ፣ ታከለ ይርጋ እና ብሩክ ዋሚሽ የተባሉ ተመራማሪዎች እ.ኤ.አ በ2010 ባሳተሙት የምርምር ወረቀት እ.ኤ.አ በየካቲት እስከ ነሐሴ 2007 ወደ ጥቁር አንበሳ በአጥንት ስብራት ምክንያት ከገቡት 422 ታካሚዎች ውስጥ 49.7 ከመቶ (202 ታካሚዎች)የመኪና አደጋ የደረሰባቸው ናቸው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ከ15-25 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ወጣቶች ናቸው፡፡ በሬዲዮና በቴሌቪዝን የሚነገረን በግርድፉ ሲሆን ጥናቶቹ የሚነግሩን ደግሞ ወጣቶች እና እግረኞች ከፍተኛው ጉዳት እየደረሰባቸው እንደሆነ ነው፡፡ ለምሳሌ ተወልደ መኮንን የተባለ ተመራማሪ እ.ኤ.አ በ2007 በሰራው ጥናት በመኪና አደጋ ከሞቱ ሰዎች ውስጥ 51 ከመቶ የሚሆኑት እግረኞች ናቸው፡፡ ወደ አዲስ አበባ ስንመጣ ደግሞ በሀገሪቱ ከሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች ውስጥ 60 ከመቶ የሚሆኑት አደጋዎች የሚደርሱባት ከተማ ነች ብሎም ከሟቾች ውስጥ 90 ከመቶ የሚሆኑት ሟቾች እግረኞች ናቸው፡፡

ምክንያቶቹ አልተለዩም ወይ?

ሀገራችን ውስጥ የሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች ብዙ ናቸው፡፡ ጥያቄው ምክንያቶቹ አልተለዩም ወይ የሚለው ነው፡፡ እዚህም እዚያውም የተሰሩ ጥናቶች መንስኤ የሚሏቸውን አስቀምጠዋል፡፡ ለአብነት ያህል የተወሰኑትን እንመልከት፡፡

በቅርቡ ከተሰራ ጥናት ለመጀመር ያህል እ.ኤ.አ በ2014 ኃይሌ መኮንን እና ደመቀ ላቀው የተባሉ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህራን በባህርዳር ከተማ የሚከሰቱ የትራፊክ አደጋዎችን አጥንተዋል፡፡ ጠቅለል አድርገን ስንመለከት ለእግረኞች ቅድሚያ አለመስጠት፣ እግረኞች መንገድ ሲያቋርጡ የሚያሳዩት ባህሪ እና የሹፌሮች የወንበር ቀበቶ አለማሰር በትራፊክ አደጋዎች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳይተዋል፡፡ ዝርዝር ውጤቶችን ስንመለከት ደግሞ፡-

– 55.5 ከመቶ የሚሆኑት አደጋዎች የተከሰቱት ከ30 ዓመት በታች ዕድሜ ባላቸው ሹፌሮች ነው፤

– 42.2 ከመቶ የሚሆኑት አደጋ ያደረሱ መኪናዎች ለረዥም ዓመት አገልግሎት የሰጡ ናቸው፤

– 69.8 ከመቶ የሚሆኑት አደጋዎች የደረሱት ለእግረኞች ቅድሚያ ባለመስጠት ነው፤

– 55.6 በመቶ የሚሆኑ ሹፌሮች የወንበር ቀበቶ የሚጠቀሙት አልፎ አልፎ ነው፤

– 57.8 በመቶ የሚሆኑ አደጋዎች የደረሱት ሹፌሮች ሞባይል እያነጋገሩ ነው፤

– 66 ከመቶ የሚሆኑት ሹፌሮች እግረኞች የተሳሳተ የመንገድ ማቋረጫ ይጠቀማሉ ብለው ያምናሉ፤

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ የሚከሰትባት ሀገር፣ አዲስ አበባ ደግሞ 60 ከመቶ የሀገሪቱ አደጋ የሚከሰትባት ከተማ በሚል መነሻ በአዲስ አበባ ጥናት ያደረገው ተወልደ መኮንን የሚከተሉትን ውጤቶች አግኝቷል፤

– አብዛኛዎቹ አደጋዎች የደረሱት በመኖሪያ አካባቢዎች ነው፡፡

ኢብራሂም ሃሰን እና ጓደኞቹ እ.ኤ.አ በ2011 350 ሾፌሮችን በማካተት ስለመቀሌ ከተማ የትራፊክ አደጋ ጥናት ሰርተው የሚከተሉትን ውጤቶች አግኝተዋል፡፡

– 233 ሹፌሮች አደገኛ የአነዳድ ባህሪ አላቸው

– 100 ሹፌሮች ስለመሰረታዊ የትራፊክ ምልክቶች ያላቸው እውቀት አናሳ ነው

– 148 ሹፌሮች እያሽከረከሩ ሞባይል የመጠቀም ልምድ አላቸው

– 28 ሹፌሮች ከጠጡ በኋላ የመንዳት ልምድ አላቸው

– 77 ሹፌሮች ከዚህ በፊት አደጋ አጋጥሟቸው ያውቃል

– ሁሉም የባጃጅ ሹፌሮች፣ 62.6 ከመቶ የሚሆኑት የቤት መኪና የሚይዙ እና 37.4 ከመቶ የሚሆኑት የታክሲ ሾፌሮች በሚያሽከረክሩበት ሰዓት የወንበር ቀበቶ አይጠቀሙም፡፡

ኢትዮጵያን ኢኮኖሚክስ አሶስየሽን በ2012 ባወጣው የምርምር ማብራሪያ (research brief) የሚከተሉትን ጉዳዮች በመንገድ ላይ ለሚከሰቱ የትራፊክ አደጋ ምክንያቶች ናቸው ብሎ ከተለያዩ ምርምር ውጤቶች እንደተገኙ የገለፃቸው የሚከተሉት ናቸው፡፡

– ደካማ የመንዳት ክህሎት

– ‹‹ለእግረኛ ቅድሚያ ስጥ›› የሚለውን ህግ አለማክበር

– ከተፈቀደው የፍጥነት ገደብ በላይ ማሽከርከር

– በዕቃ መጓጓዣ የተሰሩ መኪናዎችን ለሰዎች ማጓጓዣነት መጠቀም

– የትራፊክ ህጎችን አለማክበር

– ደካማ ቴክኒካዊ ብቃት ያላቸውን መኪናዎችን ማሽከርከርና ለመኪናዎች በቂ ጥንቃቄ አለማድረግ

– የመኪና መንገዶች በእንስሳትና በእግረኞች መያዝ/መጨናነቅ

– እግረኞች ስለትራፊክ ህጎችና ምልክቶች ያላቸው እውቀት አናሳ መሆን

– የትራፊክ ህጉን በተግባር ያለማዋል

– ከመንገዶች ጥራትና ዲዛይን ጋር የተያያዙ ችግሮች

– የመኪኖች መናኸሪያ አለመኖር

– በቂ የፓርኪንግ ቦታ ያለመኖር ችግር

ምክንያቶቹ ተለይተዋል ካልን ምን የእርምት እርምጃ ተወሰደ?

የሚመለከታቸው መንግሥታዊም ሆኑ መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላት የትራፊክ አደጋን ለመከላከል የተለያዩ እርምጃዎችን ወስደዋል፡፡ በሀገር ደረጃ በመንገዶች ምክንያት የሚመጡ ችግሮችን ለመቅረፍ እ.ኤ.አ ከ1997 ጀምሮ የመንገድ ዘርፍ እድገት ፕሮግራም መንግሥት ቀርፆ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ዋና ትኩረቱም 3 ጉዳዮች ሲሆኑ እነሱም ሀ/ ዋና ዋና መንገዶችን ማሻሻልና ማሳደግ ለ/አዳዲስ መገንባት እና ሐ/ መንገዶችን በተከታታይ ጥገና መስጠት ናቸው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም መንግሥት የተለያዩ አዋጆችን፣ ደንቦችን፣ ፖሊሲዎችን በማውጣት የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ በጀ የሚያሰኙ ጥረቶችን አድርጓል፡፡ ለዚህ ጥሩ አብነት የሚሆነን ደግሞ እ.ኤ.አ በ2011 የወጣው የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ፖሊሲ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም የተሞከሩ ሂደቶችን፣ በሂደቱ ውስጥ የታዩ ችግሮችን እና የተሻለ ውጤት ለማምጣት መከወን ስላለባቸው ተግባራት በዝርዝር አስቀምጧል፡፡ ሞባይል እያወሩ ማሽርከርና ቀበቶ የማሰር አስገዳጅ ደንቦች ተጠቃሽና ቀበቶ የማሰር ጉዳዮች ናቸው፡፡ እርግጥ ነው የዜብራ መንገድ አጠቃቀም ህጉም ከባድ እንዲሆን የተደረገ ሲሆን እግረኞችም በዜብራ መንገድ ሲያቋርጡ በተገኙ ጊዜ የሚጠቀሙበት አሰራርም ተጀምሮ ነበር፡፡

የሚዲያ ተቋማትም ሁኔታውን ከመዘገብ አንስቶ ህብረተሰቡን በተለያዩ ዘዴዎች እስከማስተማር ያሉ ወሳኝ ተግባራትን እየወከኑ ነበር፤ ናቸውም፡፡ በተለያዩ የሙያዘርፍ የተሰማሩ ግለሰቦችም የበኩላቸውን እየተወጡ ይገኛሉ፡፡ ‹‹አሽከርክር ትደርሳለህ፤ ረጋ ብለህ›› በማለት ያቀነቀነው ሞገስ ተካ ለዚህ ምርጥ አብነት ነው፡፡ መፅሐፍ በመፃፍና የተለያዩ የሚዲያ ተቋማትን በመጠቀም ያለመታከት አደጋዎችን ከዘገብ እስከ ትምህርታዊ መልዕክቶችን በማስተላለፍ ኢንስፔክተር አሰፋ መዝገቡ እየሰራ ያለው ሥራ ከፍተኛ ምስጋና የሚቸረው ግለሰብ ነው፡፡

የመንገድና ትራንስፖርት ባለስልጣን በበኩሉ የመንጃ ፈቃድ አሰጣጡን እስከመቀየር የደረሰ መሰረታዊ የእርምት እርምጃ ወስዷል፡፡ በቅርቡ ደግሞ በሲኖትራክ መኪና የሚደርሱ አደጋዎች ላይ ጥናት እንደሚደረግ የተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ዘግበውት እሰይ ብለናል፡፡

የእርምት እርምጃዎቹ ውጤታማ ለምን አልሆኑም?

እላይ የጠቀስኳቸውና ያልጠቀስኳቸው የተለያዩ የእርምት እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡ ይህ በራሱ መልካም ነገር ነው፡፡ ያም ሆኖ ግን እየደረሱ ያሉ አደጋዎች ከመቀነስ ይልቅ እየጨመሩ እንደሆነ ነው እያየንና እየሰማን ያለነው፡፡ ማስረጃ ለመስጠት ያህል እንደ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሲየሽን ማብራሪያ እ.ኤ.አ ከ2003/2004 እስከ 2010/11 በትራሪክ አደጋ የደረሰው የሟቾ ቁጥር በ6 በመቶ፣ ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር በ4.5 በመቶ እና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር በ3.6 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

እርምጃዎች እየተወሰዱ የአደጋው ሁኔታ አሁንም እየጨመረ የሚመጣ ከሆነ ለምን ብሎ መጠየቅ እጅጉን ወሳኝ ነው፡፡ ውጤታማ የሆኑ እርምጃዎች ደግሞ ከውጤታማነታቸው ጀርባ ያለውን ምስጢር ማጤኑ አስፈላጊ ነው፡፡ በእነዚህ መነፅሮች ውጤታማ እና ውጤታማ ያልሆኑትን ተግባራት በማነፃፀር ትምህርት መውሰዱ እና የተሻለውን መተግበሩ ለነገ የሚባል አይደለም- ሰው እያለቀና ንብረት እየወደመ ነውና!

ቀደም ብየየ የጠቀስኳቸውንም ሆነ ያልጠቀስኳቸውን የጥናት ውጤቶችን በጥሞና ያጤነ ሰው የሚገነዘበው አንድ አብይ ጉዳይ አለ፡፡ አብዛኛዎቹ የአደጋ መንስኤዎች ከሰዎች ባህሪያት ጋር የተያያዙ መሆናቸውን ከሹፌሮች፣ ከእግረኞች፣ ከሕግ አስከባሪዎች፣ ከባለንብረቶች፣ ወዘተ፡፡ ጥቂቶቹ ደግሞ ከመኪናዎች እና ከመንገዶች ሁኔታ/ችግር ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ ቀደም ብዬ የጠቀስኳቸው ናድ፣ ቺሾልም እና በከር የተባሉ ተመራማሪዎች እ.ኤ.አ በ2009 በሰሩት ዓለም አቀፍ ጥናት እንዳገኙት ደግሞ 85 ከመቶ ለሚሆኑት አደጋዎች መንስኤ ከሰዎች ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ ከመንገድ ጋር እና ከመኪናዎች ጋር የተያያዙ ሁኔታዎች ለቀሪ 15 ከመቶ አደጋዎች መንስኤ ሆነዋል፡፡

እናም የሚወስዱት የእርምት እርምጃዎች ውጤታማ ይሆኑ ዘንዳ መሰረታዊ መርሃቸው ከሰዎች ጋር የተያያዙ መንስኤዎችን መቅረፍ ላይ ማድረግ አለባቸው፡፡ ይህ ማለት ግን ከመንገድና ከመኪናዎች ጋር የተያያዙ መንስኤዎችን መተው አለባቸው ማለት አለመሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ይልቁንም ሁሉንም ችግሮች ለመቅረፍ እየተንቀሳቀሱ አብላጫውን ትኩረት ሰዎች ጋር ከተያያዙት ላይ ማድረግ አዋጭ ነው፡፡ ውጤታማ የሆኑት እርምጃዎችም ይህንን ነው የሚያሳዩን፡፡ የጎጃሙ ሁናቴ ለዚህ ዓብይ ምሳሌ ነው፡፡ እግረኞች ላይ አተኩረው ሰሩ የትራፊክ አደጋዎችን ቁጥርም በእጅጉ ቀነሱ፡፡ ያ ማለት ግን የመኪኖችን ዓመታዊ ፍተሻ እና መንገዶችን ምቹ ማድረጉን አቆሙ ማለት ሳይሆን ትኩረታቸውን በእግረኞች ላይ በማድረግ ሁሉንም እርምጃዎች ጎን ለጎን ከወኗቸው ማለት እንጂ!

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰዎች ላይ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች አነስተኛ ወይም ከሚጠበቀው በታች ናቸው፡፡ ይህም ዋጋ እያስከፈለን ይገኛል፡፡ በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ፖሊሲ ውስጥ የሚመለከታቸው አካላት ስለ ትራፊክ ያላቸው ዕውቀትና አመለካከት ወሳኝ እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡ በመቀጠልም በዚህ ረገድ ከበፊቱ የተሻለ ሥራ እየተሰራ ቢሆንም የማያረካ፣ ቀጣይነት የሌለው እና በተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የተገደበ እንደሆነ ያስረዳል፡፡ ፖሊሲው የተለያዩ ምክንያቶችን ከጠቆመ በኋላ ደግሞ እግረኞችም ሆኑ ሹፌሮች የትራፊክ ሕጉን አያከብሩም የሚል ድምዳሜ ያስቀምጣል፡፡ ሕግ አስከባሪ አካላትም ሕጉን አይተገብሩም ይላል፡፡ እነዚህ የተጠቀሱት ነገራት ሁላ የሚያሳዩት ከሰዎች ጋር የተያያዙ ችግሮች መሆናቸውን ልብ ይሏል፡፡

በቅርቡ ይወሰዳል በተባለው አስደሳች እርምጃ ውስጥም የዚህ አይነት የትኩረት ስህተት ይታያል፡፡ በሲኖትራክ መኪና የተከሰቱ አደጋዎች ላይ ጥናት ይደረጋል የሚለው ሃሳብ ሲብራራ የጥናቱ ትኩረት በዋናነት በመኪናዎቹ ቴክኒካዊ ምርመራ ላይ እንደሚሆን ነው የተነገረው፡፡ ይህ መደረጉ በራሱ ጥሩ ሆኖ እያለ አሁንም የተዘገና ነገር ይታያል፡፡ ስንቶቻችሁ አጋጥሟችሁ እንደሆነ ባላውቅም አንዳንድ የሲኖትራክ ሹፌሮች ከፊታቸው የሆነ መኪና መንገድ ሲዘጋባቸው በመስኮት በኩል አንገታቸውን አውጥተው ‹‹ወዮልህ፣ መጣሁብህ፣ እላይህ ላይ እንዳልወጣ›› ሲሉ እንሰማለን፡፡

ታዲያማ የመኪናው ሁናቴ ተፈትሾ፣ ችግር ከተገኘበትም ተስተካክሎ፣ የሹፌሮቹ ባህሪ ካልተቀየረ ችግሩ ይቀንስ ይሆን እንጂ መቸ ይቀረፍና? የእግረኛ ማቋረጫውን በቅርብ ርቀት እያዩ በመሀል የሚያቋርጡ እግረኞች ባህሪ ካልተለወጠ የተስተካከለ መንገድና ጥሩ ብቃት ላይ ያሉ መኪናዎች ቢኖሩንም አደጋውን የመቀነስ ሁኔታችን ምን ያህል ውጤታማ ይሆናል? ለእግረኞች ቅድሚያ የሚሰጥ ሹፌር መንገደኞችን ሲያሳልፍ ሌላ ግድ የሌለውና ያልተረጋጋ ሹፌር እየተሻገሩ ያሉትን መንገደኞች ገጭቶ እንደገደለ የሰማነው በቅርቡ አይደለምን? ለጥ ባለ የአስፋልት መንገድ የሚሄድ ከባድ መኪና ለቁጥር የበዙ ግመሎችን የረጋገጠው ግመሎቹን ባለቤታቸው ወደ መንገድ ስላስገባቸው አይደለምን?

ትራፊክ የሚገጩ ሹፌሮች፣ ጋቢና ውስጥ ትራፊክ ተቀምጦ ከመጠን በላይ በሆነ ፍጥነት የሚያሽከረክር ሹፌር፣ የተሳፈሩበት መኪና እየተንቋቋና የመበላሸት ድምፅ እየሰሙ የማይናገሩ ተሳፋሪዎች፣ በዕቃ  መጫኛ መኪና ሰዎችን የጫነ መኪና ሰላምታ ሰጥተው የሚያሳልፉ ትራፊኮች፣ ከተገዛ ሁለት ቀን የሖነው አዲስ መኪና ደረጃ አንድ በሆነ መንገድ ጠጥቶ ሲያሽከረክር የተገለበጠ ግለሰብ፣ መንገድ ለማሳጠር በእግረኞች መንገድ የሚነዱ ሹፌሮች፣ መፍጠን ልምድ አድርገውት ምንም የሚያስቸኩል ሥራም ሆነ ቀጠሮ ሳይኖራቸው የሚካለቡ ባለመኪኖች፣ ሕግ መጣስ ልምድ ሆኖባቸው የትራፊክ መብራት እየበራ የሚጥሱ፣ በህይወታቸው የራስ ወዳድነት ባህሪያቸው በመጉላቱ ቅድሚያ ለራሳቸው እንጂ ለሌሎች መስጠትን የሚጠሉ እልኸኛ ሾፌሮች፣ መቅደምን እንጂ መቀደምን የማይወዱ፣ ወዘተ… በምናይበት ሁናቴ የሰዎችን ባህሪ መለወጥ ላይ ትኩረት ያላደረገ እርምጃ ምን ተጨባጭ ለውጥ ያመጣል?

በአጠቃላይም እስካሁን የተወሰዱ እርምጃዎችን እያደነቅን፣ እንዲቀጥሉም እየጠየቅን በቀጣይ ግን ትኩረታችንን በዋነኞቹ የችግሮቹ መንስኤዎች ማለትም በሰዎች ባህሪ ለውጥ ያመጣልና የሚመለከታቸው አካላት ያስቡበት ባዮች ነን፡፡ ያለበለዚያ ግን ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ እንደሚሉት ብሂል ሆኖብን ታጥቦ ጭቃ እንዳንሆን ያሰጋል፡፡ ለዛሬ አበቃሁ፡፡ የሳምንት ሰው ይበለን፡፡ ቻው!

‹‹አሸባሪዎቻችን›› ሲኖ ትራኮች ብቻ አይደሉም!!

ለ85 በመቶ የትራፊክ አደጋዎች መንስኤ ሆኖ እርምጃ ያልተወሰደበት አንድ ብቻ ምስጢር!!

ለሥራ ጉዳይ ወደ ጎጃም ስጓዝ ያየሁት ነገር ትኩረቴን በጣም ሳበው፡፡ ሁሉም እግረኞች ግራቸው ይዘው ነው የሚጓዙት፡፡ ቆም ብዬ አካባቢዬን ስቃኝ ቀኜን ይዤ የምጓዘው እኔ ብቻ ነኝ፤ ሁሉም እግረኛ ግራውን ይዞ ነው የሚጓዘው፡፡ ከቀናት በኋላ በአንድ የገበያ ቀን የወንበርማ ወረዳ ዋና ከተማ በሆነችው ሸንዲ ከተማ ቢጫ ቲሸርት የለበሱና ፊሽካ የያዙ ወጣቶች ገበያተኞችን ግራቸውን እንዲይዙ ሲያደርጉ ተመለከትኩ፡፡ እኔም አንዱን ወጣት ጠጋ ብዬ ስለሁኔታው ጠየኩት፡፡ በጎ ፍቃደኞች እንደሆኑና ሁሌም ቅዳሜ ሰውን እንደሚያስተምሩ ነገረኝ፡፡

ይህ ከሆነ ከወራት በኋላ ፌስቡክ ላይ የሚገርም ምስል አየሁ፡፡ ከላይ ጽሑፍ አለ ከታች ፎቶ፡፡ ናይጄሪያ ብሎ ቦኮሃራም ይላል፡፡ ሱማሊያ ብሎ አልሸባብ ይላል፡፡ ሶሪያ ብሎ አይሲስ ይላል፡፡ ኢትዮጵያ ብሎ ፎቶ ተለጥፏል፡፡ ፎቶውም ቀደም ሲል ‹‹ቀይ ሽብር›› አሁን ደግሞ ‹‹ድሮኖቹ›› (The Drones) ማለትም ‹‹ሹፌር አልባዎቹ›› እየተባለ የሚሽሟጠጠው የሲኖትራክ መኪና ፎቶ ነው፡፡ የእኛ ሀገር አሸባሪ ይኸው ሲኖ ትራክ መሆኑ ነው፡፡ ሌሎቹ መኪናዎቹስ እያሸበሩን አይደለምን? እስኪ ዛሬ ስለ ትራፊክ አደጋ ልፃፍ፤ እናንተም አንብቡ፡፡ መልካም የንባብ ጊዜ!

የመኪና አደጋ ሁኔታ ቅኝት

ለእንደ ኢትዮጵያ ላሉ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት መኪና ዋነኛው የመጓጓዣ መንገድ ነው፡፡ የተለያዩ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት በአፍሪካ 80 ከመቶ የሚሆነው ሰው እና ዕቃ የሚጓጓዘው በመኪና ነው፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ሁኔታ ስንመጣ ደግሞ በከተሞች መሀከል ከሚደረጉ የሰዎችም ሆነ የዕቃዎች መጓጓዝ ውስጥ 90 ከመቶ የሚሆነው የሚካሄደው በመኪና ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በመኪና መጓጓዝ ውስጥ አደጋ የመፈጠር ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ በዓለም የጤና ድርጅት ግምት መሰረት በዓለም ላይ በመንገድ ላይ በሚደርሱ የመኪና አደጋዎች በየዓመቱ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች የሚሞቱ ሲሆን 50 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳቶች ይዳረጋሉ፡፡ በዓለም ላይ ያለውን የአደጋ ቁጥር የመጨመር ሁኔታን ያጤኑት ደግሞ ሁኔታው ከጊዜ ወደ ጊዜ በአደገኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው ይላሉ፡፡ ናድ፣ ቺሾልም እና ባከር የተባሉ ተመራማሪዎች እንደሚሉት እ.ኤ.አ በ2020 የትራፊክ አደጋ ከኤች.አይ.ቪ እና ከቲቪ ቀጥሎ 3ኛው ገዳይ ይሆናል፡፡

ይህን ሁኔታ በአንክሮ ስንቃኘው ደግሞ የትራፊክ አደጋ የሚበዛው በሰለጠኑትና ብዙ መኪና ባላቸው ሀገራት ሳይሆን ጥቂት የመኪና ቁጥር ባላቸው ታዳጊ ሀገራት ነው፡፡ ከዓለም ህዝብ ውስጥ 81 ከመቶ የሚሆኑ የሚኖሩት ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ሲሆን በእነዚህ ሀገራት የሚገኙ መኪናዎች በዓለም ከሚገኙ መኪናዎች ውስጥ 20 ከመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው፡፡ ሆኖም ግን በትራፊክ አደጋ ምክንያት የሚሞቱት ሰዎች በብዛት የሚገኙት በእነዚህ ሀገራት ነው፡፡ እንደ ሙራይ እና ሎፔስ ስሌታዊ አገላለፅ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት በትራፊክ አደጋ ምክንያት በቀን ውስጥ 3 ሺ ሰዎች ይሞታሉ፣ ሌሎች 30 ሺ ሰዎች ደግሞ ለአካል ጉዳት ይዳረጋሉ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ እንደ የዓለም ጤና ድርጅት ግምት ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት 227,835 እግረኞች፣ መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት 165,501 እግረኛ እና ከፍተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት 22,500 እግረኞች በየዓመቱ በመኪና አደጋ ምክንያት ይሞታሉ፡፡

እንደ አንድ ዝቅተኛ ገቢ ያላት ሀገር ኢትዮጵያ በትራፊክ አደጋ የሚደርሱ ገፈቶች ቀማሽ ነች፡፡ ከቤቱ ሳይወጣ ሬዲዮ የከፈተ ሰው እንኳ ቢያንስ አንዴ ስለ አንድ የትራፊክ አደጋ ይሰማል፡፡ ጥናታዊ መረጃ ለማቅረብ ያህል እንኳ ዳንኤል አድማሴ፣ ታከለ ይርጋ እና ብሩክ ዋሚሽ የተባሉ ተመራማሪዎች እ.ኤ.አ በ2010 ባሳተሙት የምርምር ወረቀት እ.ኤ.አ በየካቲት እስከ ነሐሴ 2007 ወደ ጥቁር አንበሳ በአጥንት ስብራት ምክንያት ከገቡት 422 ታካሚዎች ውስጥ 49.7 ከመቶ (202 ታካሚዎች)የመኪና አደጋ የደረሰባቸው ናቸው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ከ15-25 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ወጣቶች ናቸው፡፡ በሬዲዮና በቴሌቪዝን የሚነገረን በግርድፉ ሲሆን ጥናቶቹ የሚነግሩን ደግሞ ወጣቶች እና እግረኞች ከፍተኛው ጉዳት እየደረሰባቸው እንደሆነ ነው፡፡ ለምሳሌ ተወልደ መኮንን የተባለ ተመራማሪ እ.ኤ.አ በ2007 በሰራው ጥናት በመኪና አደጋ ከሞቱ ሰዎች ውስጥ 51 ከመቶ የሚሆኑት እግረኞች ናቸው፡፡ ወደ አዲስ አበባ ስንመጣ ደግሞ በሀገሪቱ ከሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች ውስጥ 60 ከመቶ የሚሆኑት አደጋዎች የሚደርሱባት ከተማ ነች ብሎም ከሟቾች ውስጥ 90 ከመቶ የሚሆኑት ሟቾች እግረኞች ናቸው፡፡

ምክንያቶቹ አልተለዩም ወይ?

ሀገራችን ውስጥ የሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች ብዙ ናቸው፡፡ ጥያቄው ምክንያቶቹ አልተለዩም ወይ የሚለው ነው፡፡ እዚህም እዚያውም የተሰሩ ጥናቶች መንስኤ የሚሏቸውን አስቀምጠዋል፡፡ ለአብነት ያህል የተወሰኑትን እንመልከት፡፡

በቅርቡ ከተሰራ ጥናት ለመጀመር ያህል እ.ኤ.አ በ2014 ኃይሌ መኮንን እና ደመቀ ላቀው የተባሉ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህራን በባህርዳር ከተማ የሚከሰቱ የትራፊክ አደጋዎችን አጥንተዋል፡፡ ጠቅለል አድርገን ስንመለከት ለእግረኞች ቅድሚያ አለመስጠት፣ እግረኞች መንገድ ሲያቋርጡ የሚያሳዩት ባህሪ እና የሹፌሮች የወንበር ቀበቶ አለማሰር በትራፊክ አደጋዎች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳይተዋል፡፡ ዝርዝር ውጤቶችን ስንመለከት ደግሞ፡-

– 55.5 ከመቶ የሚሆኑት አደጋዎች የተከሰቱት ከ30 ዓመት በታች ዕድሜ ባላቸው ሹፌሮች ነው፤

– 42.2 ከመቶ የሚሆኑት አደጋ ያደረሱ መኪናዎች ለረዥም ዓመት አገልግሎት የሰጡ ናቸው፤

– 69.8 ከመቶ የሚሆኑት አደጋዎች የደረሱት ለእግረኞች ቅድሚያ ባለመስጠት ነው፤

– 55.6 በመቶ የሚሆኑ ሹፌሮች የወንበር ቀበቶ የሚጠቀሙት አልፎ አልፎ ነው፤

– 57.8 በመቶ የሚሆኑ አደጋዎች የደረሱት ሹፌሮች ሞባይል እያነጋገሩ ነው፤

– 66 ከመቶ የሚሆኑት ሹፌሮች እግረኞች የተሳሳተ የመንገድ ማቋረጫ ይጠቀማሉ ብለው ያምናሉ፤

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ የሚከሰትባት ሀገር፣ አዲስ አበባ ደግሞ 60 ከመቶ የሀገሪቱ አደጋ የሚከሰትባት ከተማ በሚል መነሻ በአዲስ አበባ ጥናት ያደረገው ተወልደ መኮንን የሚከተሉትን ውጤቶች አግኝቷል፤

– አብዛኛዎቹ አደጋዎች የደረሱት በመኖሪያ አካባቢዎች ነው፡፡

ኢብራሂም ሃሰን እና ጓደኞቹ እ.ኤ.አ በ2011 350 ሾፌሮችን በማካተት ስለመቀሌ ከተማ የትራፊክ አደጋ ጥናት ሰርተው የሚከተሉትን ውጤቶች አግኝተዋል፡፡

– 233 ሹፌሮች አደገኛ የአነዳድ ባህሪ አላቸው

– 100 ሹፌሮች ስለመሰረታዊ የትራፊክ ምልክቶች ያላቸው እውቀት አናሳ ነው

– 148 ሹፌሮች እያሽከረከሩ ሞባይል የመጠቀም ልምድ አላቸው

– 28 ሹፌሮች ከጠጡ በኋላ የመንዳት ልምድ አላቸው

– 77 ሹፌሮች ከዚህ በፊት አደጋ አጋጥሟቸው ያውቃል

Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles

<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>