የሕወሓት አስተዳደርን በማገልገል የንግድ ሚኒስትር ደኤታ በመሆን ሲሰሩ የቆዩት አቶ አሊ ሲራጅ ዛሬ በድንገት ማረፋቸው ተዘገበ:: እኚህ የኦህዴድ ከፍተኛ ባለስልጣን በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ባለው የጨፌ ኦሮሚያ ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ላይ በነበሩበት ወቅት ድንገት በመታመማቸው ወደ ሆስፒታል በመወሰድ ላይ እንዳሉ በ46 ዓመታቸው ህይወታቸው ማለፉን መንግስታዊ ሚዲያዎች ዘግበዋል::
አቶ አሊ የንግድ ሚኒስትር ደኤታ ሆነው ከመሾማቸው በፊት የኢፌዴሪ የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመሆን ማገልገላቸውን የሚዘግቡት አፍቃሬ ሕወሓት ድረገጾች በቅርቡ በተካሄው የውሸት ምርጫም ኢህአዴግን ወክለው በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተወዳድረው በማጭበርበር ማሸነፋቸው ይታወሳል።