Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የኢትዬጵያ ቡና የተጫዋቾች ሰርቪስ የመጋጨት አደጋ ገጠመው

$
0
0

buna sport
የኢትዬጵያ ቡና የተጫዋቾች ሰርቪስ የመጋጨት አደጋ ገጠመው ፡፡

የኢትዬጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ከ17 አመት በታች ቡድን ለጥሎ ማለፍ ዋንጫ ለዋንጫ ለማለፍ ሰኔ 28/2007 ዓ.ም ከደደቢት ጋር ወሳኝ ግጥሚያ ነበረባቸው ፡፡ ይህን ተከትሎ ዛሬ ልምምዳቸውን በሱሉልታ ሜዳ አድርገው በሰርቪሱ ሲመለሱ ከቀኑ 4፡30 ሰዓት አካባቢ ወደ 18 ማዞሪያ የመኪና አደጋ አጋጥሟቸዋል ፡፡ በአደጋው ሶስት ተጫዋቾች ላይ ቀላል ጉዳት የደረሰ ሲሆን ህክምናቸውን በጌታ ከፍተኛ ክሊኒክ ዕየተከታተሉ ይገኛሉ ፡፡

በተጨማሪም አሰልጣኙ እና የክለቡ ሰዎች እዛው እንዳሉና ከድንጋጤ እና ቀላል መፈንከት ውጪ በአጠቃላይ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳሉ ከስፍራው ገልፀውልናል ፡፡

አሰግድ ታመነ

The post የኢትዬጵያ ቡና የተጫዋቾች ሰርቪስ የመጋጨት አደጋ ገጠመው appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>