Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ጀግኖቹ የነፃነት አርበኞች ፍልሚያቸውን የሚያቆሙት የነፃነት አደባባይን ሲረግጡ ብቻ ነው

$
0
0

ከደግነቱ አንዳርጋቸው

ሁለገብ የትግል ስልት የሚከተለው አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ በሁለት ድርጅቶች /በኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባርና በግንቦት 7 ንቅናቄ/ ውህደት ጥር 2 ቀን 2007 ዓ.ም እንደ አዲስ ከተመሰረተ በኋላ ተቀዳሚ ስትራቴጅው የሆነውን የህወሓትን አምባገነናዊ አገዛዝ በጠብመንጃ ትግል የማንበርከኩን እንቅስቃሴ ሰኔ 25 2007 ዓ.ም በትግራይ ክልል አሀዱ ብሎ ጀምሯል፡፡

ginbot 7

በመሆኑም በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙ ልዩ ልዩ ቦታዎች /ገሚሶቹ የአማራ ክልል አጎራባች መንደሮች ናቸው/ ህወሓት ከሚቆጣጠረው የመከላከያ፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የልዩ ኃይልና የሚሊሻ ሰራዊት ጋር ያለምንም ፋታ ለሰዓታት የዘለቁ ከባድ ውግያዎችን አድርጓል፡፡ አሁንም ቢሆን ለህዝብ ነፃነት የሚያደርገውን ፍልሚያ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ለዘመናት በአምባገነኖች የጭቆና ቀንበር አንገቱ ተፈጥርቆ ተይዞ ሲማቅቅ ለኖረው የኢትዮጵያ ህዝብ ሉኣላዊ የስልጣን ባለቤትነት መተኪያ የሌላት አንዲት ህይወታቸውን ዋጋ ለመክፈል የቆረጡ ጀግና የህዝብ ልጆች የሆኑ ወጣት አርበኛ ታጋዮች ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቀው በመዋደቅ ላይ ናቸው፡፡ በትጥቅና ስንቅ እንዲሁም በሰው ኃይል ቁጥር ከእነሱ በእጅጉ የሚልቀውን ህወሓት ያሰለፈውን ጦር ሰራዊት ልክ እንደ ቅጠል እያረገፉ በሬሳ ላይ በመረማመድ ወደ ፊት በመገስገስ ላይ ናቸው፡፡

ጀግኖቹ አርበኛ ታጋዮች የህወሓት ዋነኛ ወታደራዊ ቤዝ በሆኑት ቃፍታ መሲን እና ኮርጃሙስ ሰኔ 25 2007 ዓ.ም እኩለ ቀን ላይ የነፃነት ፍልሚያ ትንቅንቁን የጀመሩት ሲሆን የ24ኛ ክፍለ ጦር፣ የፌደራል ፖሊስ እና ልዩ ኃይል ቅይጥ የሆነውን እንደ ጉንዳን የሚርመሰመስ ከመጠን በላይ የታጠቀ ሰራዊት በእሳት አለንጋ በመግረፍ ገድለውና አቁስለው የተረፈውን ደግሞ ዳግመኛ እንዳያንሰራራ አድርገው በትነውታል፡፡

እነዚህ የነፃነት ቀንዲል ሞት አይፈሬና አይበገሬ ወጣት የአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች በአየር በራሪ በምድር ተሽከርካሪ ለመንቀሳቀስ የሚሞክረውን የጠላት ጦር የላስቲክ ጫማ ባጠለቁ የብሆር እግሮቻቸው ተራራውን፣ ሸለቆ፣ ወንዝ፣ በርሃና ጫካውን እያቆራረጡ ለረሃብና ጥም እጅ ሳይሰጡ በገጠጠ ረመጥ ላይ በመረማመድ የእሳት አቀበት ወጥተው የእሳት ቁልቁለት ወርደው በደም ጅረት እየዋኙ ተሻግረው ከቃፍታ መሲን ኮርጃሙስ፣ ከኮርጃሙስ ማይ ሰገን እየተወረወሩ ህወሓት መራሹን ጦር ሰራዊት መግቢያ አሳጥተው የጨበጠውን ጠብመንጃና ጥይት ሳይቀር እየነጠቁ በአረር አነደዱት፡፡

ቃፍታ መሲን፣ ኮርጃሙስና ማይ ሰገን ላይ ህወሓት መራሹን ሰራዊት የባሩድ ጭስ በማጠን እርሳስ እያስቆረጠሙ ከራሱ አካል መንጭቶ እንደ ጎርፍ በሚፈስ ደም እንዲያወራርድ በማድረግ ህወሓትን መራራ ሽንፈት ግተው የድልን ካባ ደራርበው የደረቡት ጀግኖቹ የአርበኞች ግንቦት 7 የነፃነት ፋኖዎች ማይ ሰገን ደርሰው አልቆሙም፡፡ እንደ አቦ ሸማኔ ሽምጥ በመጋለብ ከፊታቸው ያገኙትን የታጠቀ ኃይል ሁሉ እየደመሰሱ ወደ በዋል ተወነጨፉ፡፡

ጀግኖቹ አርበኛ ታጋዮች በዋል ላይ አድፍጦ የጠበቃቸውን የመከላከያ እና የሚኒሻ ኃይል መሪዎቹንም ጭምር ደረታቸውን ሰንጥቀው አፈር ላይ በማጋደም ህወሓትን ድባቅ መቱት፡፡ በርካታ የሚሊሻ ታጣቂ ጦር እየመራ ከባህከር የመጣው ኮማንደር ካህሳይ ነጋሽ እና በስሩ የነበሩት ታጣቂዎች ሬሳ በዋል የእርሻ ማሳ ላይ ተዘራ፡፡ የመከላከያ ሰራዊት እየመራ የገባው አንድ መቶ አለቃ ወታደራዊ አዛዥም ከነሚመራቸው ወታደሮች የጥይት በረዶ ዘንቦባቸው ሬሳቸው በየስርቻው ተልከስክሶ የሸሪፍ ሙሐመድን የእርሻ ማሳ በደማቸው አርሰውታል፡፡

ጀግኖቹ የህዝብ ልጆች በዚህ አልተመለሱም፡፡ የድልን እሸት ቀጥፈው እያጣጣሙ በከፍተኛ ሞራልና ወኔ ወደ ጓንጋ አሳግላ ገሰገሱ፡፡ ቃፍታ መሲን፣ ኮርጃሙስ እና ማይ ሰገን ላይ የረገጠው አንድ እግሩ የተቆረጠው 24ኛ ክፍለ ጦር ጓንጋ አሳግላ ላይ አሳርፎ ጠበቃቸው፡፡ ጀግኖቹ ግን ሁለተኛውንም እግር ቆርጠው ጥለው ጉዟቸውን ወደፊት ለመቀጠል ምንም ጊዜ አልወሰደባቸውም፡፡ እኩለ ቀን ላይ ከቀኑ ስድስት ሰዓት እስከ ሰባት ሰዓት ለ60 ደቂቃዎች ተፋልመው የህወሓትን ገረገራ የእሳት አጥር ደረማምሰው ወደ ማይ እምቧ አለፉ፡፡

ህወሓት 44ኛ ክፍለ ጦርን ከዳንሻ በፍጥነት አንስቶ በማሻገር እና ዲቪዥን እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ሰፋፊ መሬቶችን ሰጥቷቸው በእርሻ ልማት ላይ የተሰማሩ የቀድሞ ታጋዮቹን ጭምር ማይ አምቧ ላይ አሰልፎ ቆያቸው፡፡

ማይ እምቧ ላይ ህወሓት አሁንም ሌላ ተጨማሪ ውርደት ተከናነበ፡፡ ጀግኖቹ የአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች እንደ በዋሉ ሁሉ ከዳንሻ የመጡትን የ44ኛ ክፍለ ጦር አባላትንና የቀድሞ የህወሓት ታጋዮችን ከነመሪዎቻቸው አደባይተው ማይ እምቧ ላይ ቀበሯቸው፡፡

የዲቪዥኖቹ የሰፋፊ እርሻዎች ባለቤትና የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች ጠርናፊ ኮማንደር ካህሳይ እንደሻው እና የ44ኛ ክፍለ ጦር ወታደራዊ አዛዦች ሻለቃ ሐለቃ እና መቶ አለቃ በቀለ ተስፉ ከነሚመሩት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት ጀግኖቹ የነፃነት ፋኖዎች የተፉት እሳት ፈጅቷቸው ለህወሓት ስልጣን ሲባል ብቻ ህይወታቸው በከንቱ አለፈች፡፡
በማይ እምቧ የተደረገው ጦርነት ምድርን በማናወጥ ያራደ እና ከአካባቢው አልፎ ሌሎች በዙሪያው እስከሚገኙ በርካታ ጎረቤት የሆኑ መንደሮች ድረስ የተሰማ ነበር፡፡ በመሆኑም ህዝቡ አርበኛ ታጋዮችን “መጣችሁልን! ደረሳችሁልን…” እያለ በደስታ ተቀብሏቸዋል፡፡ ከእነሱ ጎንም ተሰልፏል፡፡

እስካሁን ድረስ ባለው መረጃ ቃፍታ መሲን፣ ኮርጃሙስ፣ ማይ ሰገን፣ ጓንጋ አሳግላ እና ማይ እምቧ ላይ አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ባደረጋቸው ውጊያዎች በትንሹ ከ300 በላይ የሚሆኑ ህወሓት በደማቸው ስልጣኑን ሊያራዝም በፀረ-ህዝብነት ለጦርነት ባሰለፋቸው የመከላከያ፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የልዩ ኃይል፣ የሚኒሻ አባላትና የቀድሞ ታጋዮቹ ሲገደሉ ከ260 በላይ ደግሞ በፅኑ ቆስለዋል፡፡

ከህዝብ አብራክ ተከፍለው ለስልጣኑ የሚዋጋውን ህወሓት በመፋለም ለሀዝብ ህይወታቸውን ለመስጠት ታጥቀው የተነሱት ጀግኖቹ የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ አርበኛ ታጋዮች አሁንም ወደ ፊት በመገስገስ ላይ ናቸው አልፋ እና ኦሜጋ የሆነ ታሪክ በደማቸው ሊፅፉ…

ዘላለማዊ ክብር ለጀግኖች ሰማዕታት!
ድል ለአርበኞች ግንቦት 7 ጀግኖች!
ሞት ለዘረኛውና ፋሽስቱ ወያኔ!

The post ጀግኖቹ የነፃነት አርበኞች ፍልሚያቸውን የሚያቆሙት የነፃነት አደባባይን ሲረግጡ ብቻ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>