Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ተመስገን ደሳለኝ በጀግና ትዉልድ የተንበሸበሸ ጀግና ትዉልድ

$
0
0

ከሰንቁጥ አየለ

ይህ ትዉልድ ምን ያህል ጀግኖች በመሃከሉ እንዳሉ እንዳስተዋለ አላቅም:: በጀግና ትዉልድ የተንበሸበሸ ጀግና ትዉልድ መሆኑን ግን ማንም ቆም ብሎ ያስተዋለ ባለ አዕምሮ መመስከር ይችላል:: ማሙሸት አማረ : ተመስገን ደሳለኝ: እስክንደር ነጋ: አንዱአለም አራጌ :ዘመነ ምህረት: መለሰ መንገሻ : ጌትነት ደርሶ: አብርሃ ደስታ: የዞን ዘጠን ጦማሪያን ጀግኖች: እና በርካታ ለቁጥር የሚያታክቱ ጀግኖች በትዉልዱ መሃከል ይመላለሳሉ:: በርካታ ጀግኖች በእስር ቤት በደስታ ስለሀገራቸዉ እየዘመሩ አንባገነኖችን አንገታቸዉን ያስደፋሉ::

ተመስገን ደሳለኝ)

ተመስገን ደሳለኝ)

ይባስ ብሎም እንደ ወጣት ሳሙኤል አወቀ አይነት የጀግናም ጀግና የሆኑ ልጆችም ከመታሰር በላይም ሊገደሉ እንደሆነ እያወቁ አንድ ነብሳቸዉን ለታላቁ ሀገራቸዉ መስዋዕት አድርገዉ ያቀርባሉ:: ሞታቸዉ ስለ ታላቅ ሀገርና ስለ ታላቅ ህዝብ በማሰብ ነዉና የትዉልድ አደራቸዉን ከመወጣትም በላይ ይራመዳል:: በሚገርም መልኩ “እኔ ብሞትም ትግሉን ቀጥሉ:: ትግሉን እንዳታቆሙ” ሲሉ አስደማሚ ቃል ኪዳን የትግል አጋሮቻቸዉን እያስገቡ ይሞታሉ:: እንዲህ አይነት ጀግና ትዉልድ ካልተወደሰ ማን ይወደስ?
ዛሬ የማነሳሳቸዉ ጀግኖች የዕድሜአቸዉ ለጋነትና ወጣትነት ሲታይ ደግሞ ሀበሻ ጀግና ማዉጣት የሚያዉቅ ታላቅና ጀግና ህዝብ መሆኑን ማንም አይስተዉም:: እነዚህን ጀግኖች ባሰብኩ ቁጥር የጣሊያኖች ጥናት ልቤ ዉስጥ ይመላለሳል:: “የሀበሻ ሰዉ ጀግና ከሆነ ፍጹም ጀግና ነዉ:: ወደኋላና ወደፊት አያዉቅም::” የሚለዉ ድምዳሜ::
ከጥቂቶቹ ጀግኖች ጋር አንድ ቀን አብሮ የዋለ ሰዉ የነዚህ ጀግኖች አስተሳሰብና አይበገሬነት ሳይያስደምመዉ አያልፍም:: ያንዳንዶቹ አስተሳሰብ ደግሞ ከጀግናም በላይ የገዘፈ መሆኑን ላስተዋለ ደግሞ በልጆቹ ከመኩራት በዘለለ በርካታ አድናቆት በዉስጡ መመላለሱ አይቀርም::
ለዛሬ ተመስገን ደሳለኝን ማሰብ አሰኘኝ:: ጀግኖቻችንን መቼም አንረሳቸዉምና:: አንባገነኖች ወንጀለኛ እያሉ ቢያስሯቸዉም እነዚህ ጀግኖች ዲሞክራሲያዊ: ሰበአዊ : ፍጹም ኢትዮጵያዊ መሆናቸዉን የምናዉቅ ሰዎች ደጋግመን ልናስባቸዉ ይገባል::ልንናገርላቸዉም ግድ ይለናል:: ልንዘምርላቸዉ ግዴታም አለንን::የጀግና ጀግንነቱ የሚጎላዉ ሲነገርለት ነዉና::

ተመስገን ደሳለኝ ምን አይነት ጀግና እንደሆነ አሁን መተንተን አልፈልግም:: ከዚያ ይልቅ የተመስገን ደሳለኝን ጀግንነት ከጀግና በላይ የሚያደርገዉን አንድ ነገር ብቻ ማካፈል ፈልጌ እንጅ::

እንደሚታወቀዉ ተመስገን ደሳለኝ አካፋን አካፋ ዶማን ዶማ ብሎ የሚጽፍ ሰዉ ነዉ:: እናም በዚህ አጻጻፉ አንድ ቀን ችግር እንዳይደርስበት ስጋት ገብቶኝ “ተሜ ጽሁፎችህን ለዘብ አድርጋቸዉ:: ጭብጡን ሳትለቅ ጥቂት የቃላት ማለዘቢያ ብታደርግስ ? ” የሚል ሀሳብ አቀረብኩለት::

“ለእኔ አታስቡ:: ቢያስሩኝም: ቢገሉኝም : ቢደብድቡኝም ግድ አይሰጠኝም:: ለሀገሬ መስዋዕት ልሆንላት ወስኛለሁ:: ይልቅ ስለ እናንተ አስባለሁ:: እናንተ የቤተሰብ ሀላፊ ናችሁ:: ልጆች አላችሁ:: ስለዚህ እናንተ ከዚህ ነብስ በላ ቡድን እራሳችሁን ጠብቁ:: ሁላችን ባንድ ጊዜ መስዋዕት መሆን የለብንም:: እኛ መስዋዕት ከሆንን ይበቃል:: እናተ ደግሞ ለሀገሪቱ የምታስፈልጉበት ጊዜ ይመጣል::አሁን ግን የእኛ መስዋዕትነ መሆን ይበቃል:: ” ሲል ያልጠበቅሁትን መልስ ሰጠኝ::

ቀና ብዬ አዬሁት:: ቁመቱ እረዥም አይደለም:: እደሜዉ ትንሽ ነዉ:: የልቡ ግዝፈትና የሀሳቡ ጥልቀት ግን አስደምሞኛል:: ይህ ልጅ ገና በዚህ እድሜዉ ለሀገር አስቦ: ለግለሰብ አስቦ እንዴት ይዘልቀዋል ብዬ እየተደመምኩ ሳለ ተሜ ሀሳቡን ቀጠለ:: እንዲህ ሲል ” አሁን የሚያሳስበዉ የኢትዮጵያ ጉዳይ ነዉ:: ድህነት: ኢዲሞክራሲያዊነት: ሙስና እና ብሄራዊ ማነት ማጣት ሰፍነዋል:: ከሁሉም በላይ ህዝቦቿን በጎሳና በብሄር እየከፋፈለ ኢትዮጵያዉያን አንድ ህዝብ እንዳልሆኑ የሚያተራምሰዉ ገዥዉ ቡድን ጎሰኝነትን አጥብቆ ያዞታል:: ይሄን የጎሰኝነት አስተሳሰቡን ወደ መሬት እንዳያወርደዉ የሚያስረዳ አንድ ጽሁፍ ማስነበብ እፈልጋለሁ:: አንተ ብዙ ጊዜ በኢትዮጵያዊነት ላይ ስለምትጽፍ የሆነ ጽሁፍ ካለህ በጋዜጣዬ ላይ ላወጣዉ እፈልጋለሁ::” ሲል ሌላ ያስገረመኝ ነገር ጨመረልኝ::

ኢትዮጵያዉያኖች በብሄር እንዳይከፋፈሉ ተሜን ያሳስበዋል:: እናም ስለ ብሄር የሚሰበከዉ አስተሳሰብ በኢትዮጵያዊነት አስተሳሰብ እንዲሸነፍ ይተጋል:: ዲሞክራሲ : ሰበአዊነት እና ብልጽግና የኢትዮጵያዊነት መገለጫ ይሆን ዘንድ ተሜ ወስኗል:: ለዚህም እራሱን መስዋዕት አድርጎ አቅርቧል::
ይበልጥ ተገረመሁ:: ተሜ አዲስ አበባ ካሳንችስ ተወልዶ አድጎ እንዲህ ስለ መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነት ምን ያብከነክነዋል? ኢትዮጵያዉያኖች በጎሳ ልዩነት እንዳይከፋፈሉበት ምን ያስጨንቀዋል? ጀግና ከራሱ በላይ ስለወገኑ ይብከነከናል:: ጀግና ስለ አጠቃላይ ትዉልዱ ይጨነቃል:: እንዲያዉም ስለ እያንዳንዱ ዜጋ:: ጀግና በሚኖርበት ዘመን ያሰበዉ አላማ ግብ ሊደርስለትም ወይም ላይደርስለትም ይችላል:: ዲሞክራሲያዊነት : እኩልነት : እና ሰበአዊነትና ብልጽግና በጀግናዉ ዘመን ላይሰፍን ይችላል::

ይሄ ሁሉ ነገር ሰፍኖ ለማዬት ግን የሚተጉ እራሳቸዉን መስዋዕት አድርገዉ ያቀረቡ ሚሊዮን ጀግና ኢትዮጵያዉያን እንዳሉ : እስር ቤት አልበቃ እንዳላቸዉ እሙን ነዉ:: ይሄ ትዉልድ ጀግና ነዉ:: ኢትዮጵያዊም ጀግናና ታላቅ ህዝብ ነዉ:: በማስተዋል ልብ ላለ ባለ አዕምሮ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እነዚህ ጀግኖች መስዋዕት እየከፈሉ ያለዉ ለመላዉ ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ይበልጥ እንድናከብራቸዉ ያደርገናል ::

ይሄ ትዉልድ ተመስገን ዳሳለኝን የመሳሰሉ ሚሊዮን ጀግኖች በመሃከሉ እንደሚመላለሱ ጠንቅቆ ማስተዋልም የቤት ስራዉ ነዉ:: በጀግና ትዉልድ የተንበሸበሸዉ ይሄ ጀግና ትዉልድ እራሱን በደንብ ሊያዉቅ ይገባዋል::

The post ተመስገን ደሳለኝ በጀግና ትዉልድ የተንበሸበሸ ጀግና ትዉልድ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>