Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

እነ ወይንሸት ሞላ እያንዳንዳቸው 5000 ብር ዋስ ተጠየቀባቸው •ነገ ደግሞ ይግባኝ በተባለባቸው ጉዳይ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

$
0
0

9271_728586630600331_5995106938468341166_n
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

መንግስት አይ.ኤስ.አይ.ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ የታሰሩት ወንይሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤተልሄም አካለ ወርቅ ፖሊስ ምስክሮችን አስፈራርተውብኛል ካለው ጉዳይ ጋር በተያያዘ ዛሬ ሰኔ 23/2007 ዓ.ም በቄራ ፍርድ ቤት ቀርበው እያንዳንዳቸው የ5000 ብር ዋስ ተጠይቆባቸዋል፡፡

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እነ ወይንሸት ቀደም ብሎ ጉባኤንና ስብሰባን በማወክ በተከሰሱበት ወቅት ምስክሮቼን አስፈራርተውብኛል ያለው ፖሊስ ለምስክርነት የማረሚያ ቤት ፖሊስን ቢያስመዘግብም በዛሬው ዕለት ምስክሮቹን ይዞ መቅረብ ሳይችል ቀርቷል፡፡ በዚህም ተጨማሪ ቀጠሮ ጠይቆ የነበር ቢሆንም፣ እነ ወይንሸት የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጠይቀው እያንዳንዳቸው 5000 ብር ዋስ እንዲያስይዙ ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡

እነ ወይንሸት ሞላ ቀደም ሲል የቄራ ፍርድ ቤት ከእስር እንዲወጡ ውሳኔ በሰጠበት ጉዳይ ላይ የስድስተኛ ፖሊስ ይግባኝ ስለጠየቀባቸው በሚል ነገ ሰኔ 24/2007 ዓ.ም ቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኘው ማስተዋል ፍቃዱን ጨምሮ ልደታ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ እነ ወይንሸት በፍርድ ቤት ከእስር እንዲፈቱ ቢወሰንላቸውም ፖሊስ ውሳኔውን ባለማክበር አስሯቸው እንደሚገኝ ተመልክቷል፡፡

መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም ከጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ጋር በተያያዘ ብዙ ዜጎችን አስሮ እንደሚገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

The post እነ ወይንሸት ሞላ እያንዳንዳቸው 5000 ብር ዋስ ተጠየቀባቸው •ነገ ደግሞ ይግባኝ በተባለባቸው ጉዳይ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>