Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በሚኒያፖሊስ 9 የኢትዮጵያውያን ንግድ ቤቶች በቃጠሎ ወደሙ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በሚኒያፖሊስ ሚኒሶታ 9 የኢትዮጵያውያን የንግድ ቤቶችን ጨምሮ የሌሎች ንግድ ቤቶችን የያዘ ሕንጻ በቃጠሎ ወደመ። ጁላይ 31 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 11:40 ላይ በተነሳው በዚህ ቃጠሎ የኢትዮጵያውያን ጋራዦች፣ የግሮሰሪ ሱቅ እንዲሁም የሕፃናት ደይ ኬር (ሕፃናት መዋያ) ሙሉ በሙሉ በቃጠሎ መውደማቸው ታውቋል።

በቃጠሎው የወደመው ሳብሪና ግሮሰሪ (ፎቶ ዘ-ሐበሻ)

በቃጠሎው የወደመው ሳብሪና ግሮሰሪ
(ፎቶ ዘ-ሐበሻ)


በተለይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሕፃናትን ማስተናገድ የሚችለው ‘ሃምዲ የህፃናት መዋያ’ በቃጠሎው ወቅት ምንም ዓይነት ሰው በውስጡ ባለመኖሩ አንዳችም ጉዳት በሰው ሕይወት ላይ አለመድረሱ መልካም ቢሆንም ንግድ ቤቶቹ በጠቅላላ መውደማቸው፣ እንዲሁም በኢትዮጵያውያን መካኒኮች ለሥራ የተቀመጡ መኪናዎች መቃጠላቸው ብዙዎቹን አሳዝኗል። በአጠቃላይ በጋራዦቹ ውስጥ የነበሩ በግምት ከ30 በላይ የኢትዮጵያውያን መኪኖች በቃጠሎው መውደማቸውን ከጋራዦቹ ባለቤቶች መካከል አንዳንዶቹ ለዘ-ሐበሻ አስረድተዋል።
የ70 ዓመት ዕድሜ እንዳለው የሚነገርለት ይኸው ኢትዮጵያውያኑ በብዛት የንግድ ቤት ከፍተው የሚሰሩበት ይኸው ህንፃ የቃጠሎው መነሻ ምን እንደሆነ ባይታወቅም የህንፃው አስተዳዳሪ ጄፍ ባርኔት ለጋዜጠኞች “ቃጠሎው በደረሰበት ወቅት ምንም ዓይነት ሰው አልነበረም፤ በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ አደጋ የለም። የእሳቱን መነሻም ምን እንደሆነ አላወቅኩም” ሲል ተናግሯል።
በቃጠሎው መኪኖቻቸው ከወደመባቸው የኢትዮጵያውያን የንግድ ቤቶች ውስጥ የገመቺስ ጋራዥ ባለቤት አቶ ገመቺስ ጋራዡ ሙሉ በሙሉ መውደሙን እና 7 መኪኖቹም አብረው መቃጠላቸውን ለዘ-ሐበሻ ተናግሯል።
ይህ የእሳት ቃጠሎ ከኢትዮጵያውያኑ የንግድ ቤቶች በተጨማሪ 200 ጫማ ርቀት ላይ የሚገኘውን የሬድዮ ምሰሶ አውድሟል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዘ-ሐበሻ በሚኒሶታ ለሚገኙ ነዋሪዎች በእሳት አደጋው ንብረታቸውን ላጡ ወገኖቻቸን ጎን በመቆም እርዳታ በማድረግ እንዲተባበር ጥሪዋን ታቀርባለች።
ቃጠሎው የንግድ ቤቶቹን እንዲህ አውድሟል (ፎቶ ዘ-ሐበሻ)

ቃጠሎው የንግድ ቤቶቹን እንዲህ አውድሟል
(ፎቶ ዘ-ሐበሻ)

(በቃጠሎው የወደሙ መኪኖች) ፎቶ ዘ-ሐበ4ሻ

(በቃጠሎው የወደሙ መኪኖች) ፎቶ ዘ-ሐበ4ሻ

ከቃጠሎው በኋላ የሚኒያፖሊስ እሳት አደጋ አካባቢውን እንዲህ አድርጎ አጥሮ ጉዳዩን እያጣራ ነው።

ከቃጠሎው በኋላ የሚኒያፖሊስ እሳት አደጋ አካባቢውን እንዲህ አድርጎ አጥሮ ጉዳዩን እያጣራ ነው።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>