Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የጅንካ ሕዝብ በአድማ በታኝ ፖሊሶች ታጅቦ ሰልፉን በሰላም አጠናቀቀ፣ አርባ ምንጭና ወላይታ ላይም ሕዝቡ ድምጹን አሰማ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) “የሚሊዮኖች ነፃነት በኢትዮጵያ” በሚል አንድነት ፓርቲ በተለያዩ ከተሞች ከጠራው ህዝባዊ ስብሰባ እና የተቃውሞ ሰልፍ አካል አንዱ የሆነውና በጅንካ ከተማ የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በሺዎች የሚቆጠሩ የጂንካ ነዋሪዎች ሲወጡ በአድማ በታኝ ፖሊሶች የቅርብ ክትትል እንደነበር ከስፍራው ያገኘነው መረጃ አመለከተ።
ምንም እንኳ ህዝቡ ላይ ሽብር ለመንዛትና እንዳይወጣ ለማስፈራራትም ጭምር ነው የአድማ በታኙ ብዛት የታየው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች ቢኖሩም የጅንካ ህዝብ ግን በተቃውሞ ሰልፉ ላይ በመውጣት የተገፈፈው መብቱ እንዲከበር ጠይቆ በሰላም አጠናቋል ተብሏል።
አንድነት ፓርቲ በጅንካ ከተማ የዛሬው ተቃውሞ ከመደረጉ በፊት እንዳይቀሰቅስና ሰልፉም እንዳይካሄድ በመንግስት ከፍተኛ ጫና እየተደረገበት መሆኑን ሲግልጽ የነበረ ሲሆን ይህ ጫና ሰልፉ በሰላም እሰከሚጠናቀቅ ድረስ መቆየቱ ተዘግቧል።
ከጅንካ በተጨማሪም በአርባ ምንጭ አንድነት የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ እንዲሁ ዛሬ ሲካሄድ ውሏል። በአርባምንጭም እንዲሁ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ይህን ሰልፍ ታድመውታል።
በሌላ በኩልም በወላይታ አንድንት የጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ በሰላም ተጠናቋል። አንድነት እንደገለጸው “ስብሰባውን የከፈቱት የአንድነት አመራር ይህን ሁሉ አፈና እና ማስፈራራት ተቋቁሞ በአዳራሹ የተገኘውን ህዝብ “ጀግኖች ናችሁ” ሲሉ አወድሰዋል። ወ/ሮ ሀድያ የሚባሉ የአንድነት አመራር አባል በቅስቀሳ ወቅት ተይዘው እንደታሰሩና አሁንም በእስር ላይ እንደሚገኙ ስብሰባውን የሚመሩት የአንድነት አመራሮች ለህዝቡ ይፋ አድርገዋል።”

በጅንካ፣ በአርባምንጭና በወላይታ ስለተደረጉት ሕዝባዊ እንስቃሴዎች ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱን እንመለሳለን። እስከዚያው በጅንካ እና በአርባ ምንጭ የተሰሙት መፈክሮችን በከፊል እነሆ፦

• የታሰሩ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች ይፈቱ
• መንግስት ህገ-መንግስቱን ያክብር
• መንግስት በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን ያቁም!
• መንግስት ለብሄራዊ መግባባት ባስቸኳይ መልስ ይስጥ!
• ውሸት ሰልችቶናል! ይቁም!!!
• የጸረ – ሽብር ህጉ ባስቸኳይ ይሰረዝ!
• ዘርን መሰረት ያደረገ ማፈናቀል ባስቸኳይ ይቁም!!
• ሙወስና የስርአቱ መገለጫ ነው!!
• የአባይ ጉዳይ የኢትጵያ ሕዝብ ነው!
• ለተከሰተው የኑሮ ውድነት ተጠያቂው መንግስት ነው!!
• የዜጎች ሰብአዊ መብታቸውን የማግኘት መብታቸው ይከበር!!
• ዜጎች በሀገራቸው ስራ የማግኘት መብታቸው ይከበር!!
• በአባይ ጉዳይ ወሳኙ የኢትጵያ ሕዝብ እንጂ ግብጾች ይደሉም!!
• የፓርቲ አባልነት በፍላጎት መሆን አለበት!!
• ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>