ኮሚቴዎቻችን ላይ የሚተላለፈው ውሳኔ ቀጣይ የትግል አቅጣጫችንን የሚቀርፅ ጉዳይ ቢሆንም በራሱ ግን የትግላችን መዳረሻ አይደለም፡፡ ትግላችን ከመነሻው የተገነባው፣ በሂደትም የውድ ኮሚቴዎቻችንን እስርና እንግልት ጨምሮ በርካታ መስዋእትነት የተከፈለበት የተሸራረፉ መብቶቻችንን በማስከበርና የእምነት ነፃነታችንን በህገ መንግስቱ መሰረት በማረጋገጥ ዓላማ ላይ ተመስርቶ ነው፤ ይህ ዛሬ አንስተነው ነገ የምንቀይረው መፈክር፣ አልያም በሌሎች አጀንዳዎች የሚዋጥና የምንዘነጋው ጉዳይ ሳይሆን ለተፈፃሚነቱ አስፈላጊውን ሁሉ መስዋእትነት የምንከፍልበት ትግላችን የተጠረገበት ጎዳና ነውና! ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል! ድምጻችን ይሰማ! አላሁ አክበር!
The post ወኪሎቻችንን በነጻ ከማሰናበት ያነሰ አንዳችም ብይን አንቀበልም! – ድምጻችን ይሰማ የተሰጠ ማሳሰቢያ! appeared first on Zehabesha Amharic.